Coca-Cola: Keeps Refreshing

Page 44

ማን ልበል አላወኩህም እሙን በጣም ነው የምወዳት ፣ ሙሉ ህይወቴ ለሷ የተመሰረተ እስኪ መስለኝ ። የዕሙም መውደድ ግን ከናፍሯ ላይ ከኔ በተሻለ ነው ። ሆዴ … ዛሬ ሙሉ ቀን የት ነው ጠፍተህ የዋልከው ? እንዴት እንደናፈከኝ ፣ ስትጠፋ እኮ ይጨንቀኛል ። ያነጋገር ለዛዋ ከዜማ ጋር የታጀበ ስለሆነ እንዴት ደስ እንደሚል ። ከእሙ ጋር የተገናኘ ነው ተቀጥራ በምተሰራበት ሆቴል ውስጥ ለመዝናናት በሔድኩበት ሰዓት ነው ። የመጀመሪያ ቀን ያየኋት በዩኒፎርም ሲሆን ፣ ሆኖም ግን የለበሰችው አጭር ቀሚስ ልዩ ውበት ሰጥቷታል በደንብ እንዲታይ የሰውነት ቅርጿ እድሉን አመቻችቷል። እሙ ብዙም ቆንጆ ባትባልም ሆኖም ያላት የሰውነት ቅርፅ አቤት ፣ ወዴት ? እንድትል በሩን ክፍት ነው የሚያደርግው። ዓይኖችህ ማረፍ እስኪያቅታቸው ድረስ ነው ሰላማቸውን የምትነሳቸው። የአፍንጫዋ አቀማመጥ ብዙም ባይባልም እኔ ስለወደድኩት ለኔ ተውልኝ ። ብቻ የውስጤን ምን እንደነካችው ባላውቅም ነገረ ስራዬ ሁሉ የሚያስበው እሙን ነው ። የኔ እንደዛ መሆን ለእሙ…ሌላው ቢቀር ስለመፈጠሬም የምታቀው ቦታው ላይ ስገኝብቻ ነው ። የትኛው ዘመን ነው፣ እንደዚህ ነገሩ ሁሉ የህሊና ቀርቶ የዳቦ የሆነበት?። ከየትም አቅጣጫ ይምጣ በየትኛውም የድምጽ ቃና ብቻ የሷ ስም ይሁን እንጂ ሁሌም መልሷ ወዬ ነው። ታድያ ወዬ ያመጣብኝ ጣጣ

42 Abyssinia Business Nework መጋቢት

ወር 2012 March 2020

?

። የካሮት እድገት ሆኖብኝ ይሄው ዓመት አስቆጥሬያለሁ ከወዬ ጋር፣ በመሃከል በተዋወኳት ሶስተኛ ወሬ ይመስለኛል በሳምንቱ የመጨረሻ አንዱ ቀን ልጋብዛት ፈለኩና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ። እንዴት ግን ትወደኛለች ? ስል የመጀመርያ ጥያቄ ለራሴ ጠየኩ ። ለምን አልጋብዛትም ብዬ እራሴን ደፋር አደርኩት። አድራሻዋን አንድ ትሰጠኝ ጠየኳት ከቢል ጋር አብሮ መጣልኝ ። እስከምደውል እንዴት ሰዓቱ ይሂድልኝ የአመት ያህል ነው የራቀብኝ ። መድረሱ አይቀርም ረፋዱ ላይ ደወልኩላት። ከእንቅልፏ እየተንሳች ነበረና ድምጿ ትንሽ ወፈር አለ ቢሆንም ግን ለኔ የትኛውም ይሁን ማናገሬን ብቻ ነው ያሰብኩት ሆኖም ግን ስወጣ ልደውልልህ ብላ ብዙ ሳታዋራኝ ስልኩን ዘጋችው ። ስልኬ በጮኽ ቁጥር የሷ እየመሰለኝ እደነግጣለሁ ። የሷ ስልክ ግን የውሃ ሽታሆነ ! አላስችል አለኝና ደውልኩ እዛ እንገናኝ አለችኝ የስራ ቦታዋ መሆኑ ነው ። ሰዓቴን ጠብቄ ሄድኩ ። ሰላም ነው አባት ብላ ሞቅ ባለ ሰላምታ ከሰጠችኝ በኋላ ምን ላምጣልህ ስትል ጠየቀችኝ ቡና አልኩ አፌ ላይ የመጣው እሱ ስለነበር ። የፈለኩት ግን ቡና አልነበረም ። እሙን ነበር ውስጤ የፈልገው ። እሙ ፈጥና ቡናውን ይዛልኝ ስትመጣ ያለኝን አቅም አስባስቤ ውጭ ምሳ ልጋብዝሽ ፈልጌ ነበር


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.