Total Ethiopia Keeps Energizing

Page 44

ጌጡ ተመስገን ( የጉዞ ማስታወሻ )

ምንጭ (በቅርቡ ለህትመት ከሚበቃ የተወዳጁ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን የጉዞ ማስታወሻ መጽሐፍ የተወሰደ)

የአበቅየለሽን ጠጅ፤ በቡርቧክሶች ዜማ አይቆረጠምም ደረቁ ባቄላ፣ ጎንደር ከተማ ከመድረሳችን በፊት በማክሰኚትና በጠዳ መካከል እናገኛታለን፡፡ በመሰንቆ ጨዋታ የገነነችዋን መንደር፤ ቡርቧክስ እግር ጥሏችሁ ከመንደሯ ቤቶች ወደ አንደኛው ድንገት ጐራ ብትሉ ከሁለት እስከ አምስት የሚደርሱ መሰንቆዎችን የቤቱ ምሰሶ ላይ በክብር ተሰቅለው ታገኛላችሁ፡፡ የእማሆይ አበቅየለሽ ጥንታዊ ጠጅ ቤት የሚገኘው ጎንደር፤ ከፋሲል ግንብ ዋና መግቢያ በር ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ፣ ከዣን ተከል ዋርካ ወረድ ብሎ ነው፡፡ መኳንንቱና መሣፍንቱ - በአንገተ ረዥሙ የመጀን ብርሌ ‹አስናቀ› የሚባል ጠጅ (ዘመናዊውን ውስኪ ያስንቃል ለማለት ነው) ያንደቀደቁበት፤ የቡርቧክስ የመሰንቆ ጨዋታ የኮመኮሙበት ታሪካዊ ጠጅ ቤት ነው - እማሆይ አበቅየለሽ ጠጅ ቤት፡፡ አበቅየለሽ ይመር፤ በ1912 ዓ.ም. በጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሙ ባርደምባ በሚባል ቀበሌ ከደብረ ምህረት እያሆ ቅድስት ማርያም ገዳም ተወለዱ፡፡ በ1934 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ገቡ ፡፡ የጀመሩት የጥሩ ማር ጠጅ ጣይነት የንግድ ሥራ ከፍተኛ እውቅና አስገኝቶላቸዋል ፡፡ ከጎንደር ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ አልፈው በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ስማቸውና ዝናቸው ናኘ፡፡ በኢትዮጵያ የኪነት ባለሙያዎችም ዘንድ ‹‹ጎንደር አበቅየለሽ›› እየተባለ ሲገጠምላቸውና ሲነገርላቸው ኖረዋል::

42 Abyssinia Business Nework የካቲት ወር 2012 February 2020

አበቅየለሽ ጐንደር ፋርጣ የኔ ገላ፤ *** እመቴ አበቅየለሽ፣ (ከጠጁ፣ ከጮማው) አታመጪው የለሽ!

*** አንድ ዕለት በለስ ቀንቶት እማሆይ አበቅየለሽ ጠጅ ቤት ተገኘሁ፡፡ እሳቸው የሉም፡፡ በ78 ዓመታቸው ነው ይህቺን ዓለም የተሰናበቷት፡፡ ትዝታቸውን ግን ጥለው አልፈዋል፡፡ ወደ ጠጅ ቤቱ ስትዘልቁ እርሳቸው በህይወት ሳሉ የሚቀመጡባት ቀይ ሶፋ፣ ከወንበሩ አጠገብ መቋሚያቸው፣ ከመቋሚያው አናት ላይ የእማሆይ አበቅየለሽ ይመር ባለ ጥቁርና ነጭ ፎቶግራፍ በክብር ተሰቅሎ ይጠብቃችኋል፡፡ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ወደ ጠጅ ቤቱ ሲዘልቁ ለአፍታ ቆመው፣ ባርኔጣቸውን አውልቀው ለቀይ ወንበሯ እጅ ይነሳሉ፡፡ ወንበሯ ላይ ማንም ሰው አይቀመጥም፡ ፡ አግራሞት ያጫረብኝ ደግሞ ጠጅ ጠግበው የሚወጡ እንግዶች ሁሉ የእማሆይ አበቅየለሽ ይመርን ‹ወንበር› በክብር ተሰናብተው መውጣትን ፈጽሞ አለመዘንጋታቸው ነበር፡፡


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.