ለሕይወት ጥያቄዎች መልስ እየፈለግህ ይሆን?
የ
እውነተኛ
ሕይወት
መድረሻ ግብህን በተመለከተ እርግጥኛ ነህ?
የ
እውነተኛ
ሕይወት በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ
ምስጢር
እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
እውነተኛ ሰላም የማገኘው እንዴት ነው?
ምስጢር
ፊልጵስዮስ 4:6-7
ከባድ ሸክም ተጭኖህ ይሆን?
ለሕይወት ጥያቄዎች መልስ እየፈለግህ ይሆን?
የ
እውነተኛ
ሕይወት
መድረሻ ግብህን በተመለከተ እርግጥኛ ነህ?
እውነተኛ ሰላም የማገኘው እንዴት ነው?
ምስጢር ከባድ ሸክም ተጭኖህ ይሆን?
ሕ ወትህን
ፈጣሪ ባቀደው ሁኔታ መኖር የምትችልበትን መንገድ ዕወቅ የተፈጠርኸው ደስተኛና የተሳካ ሕይወት እንድትኖር ነበር። ይህ ትንሽ መጽሐፍ ሕይወትን ፈጣሪ ባቀደው ሁኔታ መኖር እንድትችል ይረዳሃል። በዓለም ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሽያጭ ካለው መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል። ለሕይወት ጥልቅ ጥያቄዎችና ችግሮች አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ሲሉ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሚሊዮኖች ወደዚህ መጽሐፍ ዘወር ብለዋል። ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ይህ ትንሽ መጽሐፍ፣ ስለ እግዚአብሔር - ዓለምን ስለ ፈጠረው እና ለተለየ ዓላማው ሰውን በአምሳሉ ስለ ፈጠረው እግዚአብሔር ይናገራል። ታዲያ፣ ችግሩ ምንድነው? ይህ ትንሽ መጽሐፍ ከሉዓላዊው እግዚአብሔር ጋር እንዴት ሕይወት ለዋጭ ግንኙነት ሊኖ ርህ እንደሚችል ይገልጻል፤ ደግሞም ያሳያል። 2
በ « በ
እ ፍ ከ ፍ እ ታ ሆ
እ በ በ በ በ
እ ፈ
እ ባ
ዘ
ት
ሉዓላዊ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። እግዚአብሔር፣ «ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጡራን ይሞሉ፤ ወፎችም ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ» አለ። እግዚአብሔር፣ «ምድር ሕያዋን ፍጡራንን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ» አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
እግዚአብሔር የፈጠረው ዓለም
እግዚአብሔር፣ «ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር በሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው» አለ። እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው። እግዚአብሔም፣ «ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም» ብሎ ባረካቸው። ዘፍጥረት 1፥1፣ 20፣ 24፣ 26-28 3
ሉዓላዊው እግዚአብሔር
እ የ
አፍቃሪ አባት ነው
«እኔ አባት እሆናችኃለሁ፤ እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ» ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ 2 ቆሮንቶስ 6፥18
ይ ስ መ
ማ
ለ አ የ ክ
1 4
እናንተ ወላጆች - ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጥ አባት አለ? ወይንም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ
ጋይ ድን
ይኖራል? ታዲያ፣ እናንተ ክፉዎች ሳላችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፣ የሰማዩ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም? ማቴዎስ 7፥9-11
ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከእርሱ የሆነ፣ እኛም ከእርሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር በእርሱ አማካይነት የሆነ፣ እኛም በእርሱ አማካይነት የሆን፣ አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን። 1ቆሮንቶስ 8፥6 5
አሳዛኙ ነገር
ሰው ከእግዚአብሔር ዘወር አለ እኛ ሁላችን እንደ በጐች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን። ኢሳይያስ 53፥6
ቂ ተ
በ እ ዘ
መ
6
የእኔ የእግዚአብሔር መንገድ መንገድ ሴ በራንገድ መ ድሁ ነጐ
ቂል በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጐ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም! በማስተዋል የሚመላለስ፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት እግዚአብሔር ከሰማይ፣ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ። ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ አንድ እንኳ በጐ የሚያደርግ የለም! መዝሙር 53፥1-3
7
በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል
ሉዓላዊውን አምላክ ማወቅ ትችላላችሁ እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮች ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ቈላስይስ 1፥15-16
አ አ ራ ተ
1
እ በ በ
ዕ
ወ አ
1 8
ሰው
ና
እግዚአብሔር
አንድ እግዚአብሔር አለ፤ ደግሞም አንድ አስታራቂ አለ አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጐ ሰጠ፣ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 1 ጢሞቴዎስ 2፥5-6
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኃያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኃጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ። ዕብራውያን 1፥3
ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው። 1 ዮሐንስ 2፥23 9
ጌታ ኢየሱስ
መልካም ዜና ይዞ ለ...
ለድኾች፣ ለታሰሩት፣ ለተጨቈኑት እና ለታመሙት መጣ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኃይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ ሐዋርያት ሥራ 10፥38 10
ከ እ ተ በ
« ለ ለ ነ የ ል
ኢ በ ይ የ
ሉ
ከዚህም በኃላ ኢየሱስ ወደ አደገበት አገር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሣ፤ የነቢዩ የኢሳይያስ መጽሐፍ ተሰጠው፤ መጽሐፉንም በገለጠ ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ።
«የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤ እንዲሁም ጌታ ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል።» ኢየሱስ መጽሐፉን አጥፎ ለአስተናባሪው ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ የነበሩትም ሁሉ ትኩር ብለው ወደ እርሱ ይመለከቱ ጀመር፤ እርሱም፣ «እነሆ! ይህ አሁን ሲነበብ የሰማችሁት የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ» አላቸው። ሉቃስ 4፥16-20
11
ጌታ ኢየሱስ
የ መፈወስ ኃይል አለው ፀሐይ ጠልቃ በመሸ ጊዜ ሰዎች በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ። የከተማው ሰዎች ሁሉ በደጅ ተሰብስበው ነበር። ኢየሱስ በልዩ ልዩ በሽታ የሚሠቃዩትን ብዙ ሰዎች ፈውሰ፤ ብዙ አጋንንትንም አስወጣ፤ አጋንንቱም እርሱ ማን እንደ ሆነ ያውቁ ነበር፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም። ማርቆስ 1፥32-34
ዐ ከ ነ የ መ እ ከ
ኢ ዘ
ደ የ
እ ሴ በ አ
ማ
12
ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች። ከሐኪም ወደ ሐኪም በመሄድ ብዙ ተሠቃይታና ገንዘብዋንም ሁሉ ጨርሳ ነበር። ነገር ግን እየባሰባት ሄደ እንጂ ምንም አልተሻላትም። እርስዋም የኢየሱስን ዝና ሰምታ ስለ ነበር በሚጋፋው ሕዝብ መካከል ከበስተ ኃላው መጥታ ልብሱን ነካች። ይህንንም ያደረገችው፣ «ልብሱን እንኳ ብነካ እድናለሁ» በሚል እምነት ነበር። የሚፈሰው ደምዋም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሕመምዋም እንደ ዳነች በሰውነትዋ ታወቃት። ኢየሱስም ወዲያውኑ ኃይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ፤ ወደ ሕዝቡም ዘወር ብሎ፣ «ልብሴን የነካ ማን ነው?» ብሎ ጠየቀ። ደቀ መዛሙርቱም፣ «ሕዝቡ እየተጋፋ ሲከተልህ እያየህ፣ ‹ማን ነው የነካኝ› ትላለህን?» አሉት። እርሱም ይህን ያደረገው ማን እንደ ሆነ ለማየት ዘወር ብሎ ተመለከተ። ሴትዮዋ ግን በእርስዋ የሆነውን በማወቅዋ በፍርሃት እየተንቀጠቀጠች በፊቱ ወድቃ እውነቱን ሁሉ ነገረችው። እርሱም፣ «ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈውሺ» አላት። ማርቆስ 5፥25-34
13
ጌታ ኢየሱስ
በርኩሳን መናፍስት ላይ ሥልጣን አለው ያስፈራል
14
አልፈውም ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ደረሱ፤ ወዲያው በሚቀጥለውም ሰንበት ኢየሱስ ወደ ምኩራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ። ኢየሱስ የሕግ መምህራን እንደሚያስተምሩት ዐይነት ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ስለ ነበር የሰሙት ሁሉ በትምህርቱ ተደነቁ። ርኩስ መንፈስ ያደረበት በምኩራባቸው የነበረ አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጮኸ፤ «የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!» ኢየሱስም ርኩሱን መንፈስ፣ «ጸጥ ብለህ ከእርሱ ውጣ!» ብሎ ገሠጸው። ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኃላ በታላቅ ድምፅ እየጮኸ ከእርሱ ወጣ። «ይህ ምንድን ነው? ምን ዐይነት አዲስ ትምህርት ነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳ በሥልጣኑ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል!» እያሉ ሁሉም በመገረም እርሱ በርሳቸው ይጠያየቁ ጀመር። ማርቆስ 1፥21-27
ይገርማል?!
15
ጌታ ኢየሱስ
በተፈጥሮ ላይ ሥልጣን አለው
16
ው
አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፈረና፣ «ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር» አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ። በባሕሩ ላይ እየቀዘፉ ሲሄዱ ሳሉ፤ ኢየሱስ አንቀላፋ፤ በዚያን ጊዜ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ተነሣ፤ ውሃውም በጀልባው ውስጥ መሙላት ስለ ጀመረ አደጋው አስግቶአቸው ነበር። ደቀ መዛሙርቱ፣ «መምህር ሆይ፤ መምህር ሆይ! ልናልቅ ነው!» ሲሉ ኢየሱስን ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚያናውጠውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ነፋሱና የሚያናውጠው ማዕበል ወዲያውኑ ቆመ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ከዚያም በኃላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ «እምነታችሁ የት አለ?» አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፤ «ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታ፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?» ተባባሉ። ሉቃስ 8፥22-25
17
ጌታ ኢየሱስ
ኃጢአትን የማስተረይ ሥልጣን አለው
ያን ያደረገው እንዴት ነው?
እ ኢ ነ አ በ ኢ ተ
የ የ
ኢ ይ ‹ በ አ ወ
ሽ ተ ሁ እ
ሉ
18
እነሆ አንድ ሽባ ሰው በአልጋ የተሸከሙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቤትም አግብተው በፊቱ ሊያኖሩት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ቤት ማግባት አቃታቸው፤ ስለዚህ ወደ ጣራ ይዘውት ወጡ፤ ጣራውንም ከፍተው በመካከሉ አውርደው ሽባውን ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አኖሩት። ኢየሱስም እምነታቸውን ባየ ጊዜ ሽባውን፣ «አንተ ሰው! ኃጢአትህ ተደምስሶልሃል» አለው። የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን «በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማነው?» እያሉ ያስቡ ነበር። ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ «በልባችሁ ስለምን ይህን ታስባላችሁ? ለመሆኑ፣ ‹ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል› ከማለትና ‹ተነሥተህ ሂድ!› ከማለት የትኛው ይቀላል? ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለመደምሰስ ሥልጣን እንዳለው ማወቅ አለባችሁ!» ብሎ ሽባውን፣ «አንተ ሰው ተነሥ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ!» አለው። ሽባውም በሰዎቹ ፊት ወዲያው ተነሣና ተኝቶበት የነበረውን አልጋ ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ተገርመው በመፍራት፣ «ዛሬ ድንቅ ነገር አየን» እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ሉቃስ 5፥18-26
19
እኔን ኃጢአተኛውን ማን ይወዳል… ማንስ ስለ ኃጢአቴ ይሞታል?
20
ጌታ ኢየሱስ
ለኃጢአታችን ለመሞት መጣ
ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል። ሮሜ 5፥8
እንዲሁም ሁለት ወንጀለኞችን ከኢየሱስ ጋር ሊገድሉአቸው ይዘው ሄዱ። ቀራንዮ ወይም የራስ ቅል ወደ ተባለ ስፍራም በደረሱ ጊዜ በዚያ ኢየሱስን ሰቀሉት፤ እንዲሁም ሁለቱን ወንጀለኞች በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉአቸው። ሉቃስ 23፥32-33
ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እናንተ ተፈውሳችኃል። 1 ጴጥሮስ 2፥24
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ፣ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። 1 ጴጥሮስ 3፥18 21
ጌታ ኢየሱስ
ሞትን አሸነፈ ዛሬም ሕያው ነው
ሴቶቹ ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ጠዋት በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ መቃብሩ የተዘጋበትን ድንጋይ ከመቃብሩ ወዲያ ተንከባሎ አገኙት። ወደ ውስጥ በገቡ ጊዜ ግን የጌታ ኢየሱስን አስከሬን አላገኙም። ስለዚህም ነገር በመገረም ላይ ሳሉ እነሆ የሚያንጸባርቅ ብሩህ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች መጥተው በአጠገባቸው ቆሙ።
22
ሴቶቹም እጅግ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ፣ «ስለ ምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ? እርሱ እዚህ የለም፤ ተነሥቶአል፤ በገሊላ በነበረበት ጊዜ የነገራችሁን አስታውሱ፤ ‹የሰው ልጅ ለኃጢአተኞ ተላልፎ መሰጠት፣ መሰቀልና በሦስተኛውም ቀን ከሞት መነሣት ይገባዋል› ብሎአቸሁ ነበር» አሉአቸው ሉቃስ 24፥1-7
እኔ የተቀበልኩትን በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ነገር ለእናንተ አስተላለፍኩላችሁ፤ ያስተላለፍኩላችም ነገር በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ከዚያም ለጴጥሮስ ታየ፤ ኃላም ለዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ታየ፤ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ተከታዮቹም በአንድ ጊዜ ታያቸው። 1 ቆሮንቶስ 15፥3-6
23
ጌታ ኢየሱስ
የኃጢአታችንን ቅጣት ተቀበለ
የእግዚአብሔር መለኪያ
ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል። ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጐ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ሥርየት እንዲያገኙ ነው። ሮሜ 3፥23-25
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላት «መንገድና እውነት፣ ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።» ዮሐንስ 14፥6
የሰው መለኪያ
የእግዚአብሔርን መለኪያ ማሟላትና በራሳችሁ ጥረት እርሱን ደስ ማሰኘት አትችሉም፤ እንዲታደጋችሁ ጌታ ኢየሱስ ያስፈልጋችኃል። ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ መንገድ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው።
24
የእግ
የእግዚአብሔርን መለኪያ ማሟላት የምንችለው በክርስቶስ ብቻ ነው የእግዚአብሔር መለኪያ
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይላል፤ «ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ! የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ሁሉ የባስሁ ኃጢአተኛ እኔ ነኝ። ነገር ግን ምሕረት ተደረገልኝ፤ ምሕረት የተደረገልኝም ኢየሱስ ወሰን የሌለውን ትዕግሥቱን ከሁሉ የባስሁ ኃጢአተኛ በሆንኩት በእኔ ላይ በማሳየቱ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን ነው።» 1 ጢሞቴዎስ 1፥15-16
መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም። የሐዋርያት ሥራ 4፥12
25
በጌታ ኢየሱስ በኩል
የዘላለም ሕይወት ማግኘት ትችላላችሁ
የኃጢአት ይቅርታ
ኢ ሕይወት
ኢ እ ይ
ሮ
የ
ለ ል
ዮ
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘላለም ሕይወት ነው። ሮሜ 6፥23
ነጻ የእግዚአብሔር ስጦታን ከእግዚአብሔር ተቀበሉ
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደው አንድያ ልጁን ሰጠ። እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለም። ዮሐንስ 3፥16-17 26
አ
ከ
ኢ አ የ ጌ አ ስ አ አ
ጌታ ኢየሱስ ወደ ሕይወታችሁ ይግባ
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ «እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።» ራእይ 3፥20
ኢየሱስ ለኃጢአታችሁ መሞቱን እመኑ
ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በአፍህ ብትመሰክርና እግዚአብሔር ከሞት እዳስነሣውም በልብህ ብታምን ትድናለህ። ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል። ሮሜ 10፥9-10
የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን ዕወቅ!
ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። ዮሐንስ 1፥12
አሁኑኑ ኢየሱስ ክርስቶስን መቀበል ትችላላችሁ ከልባችሁ ይህን ጸልዩ
ኢየሱስ ሆይ ለኃጢአቴ መስቀል ላይ ስለ ሞትህ አመሰግንሃለሁ። የአንተን መለኪያ ማሟላትና ራሴን ማዳን እንደማልችል ዐውቃለሁ። ጌታ ኢየሱስ አንተ ታስፈልገኛለህ። ኃጢአቴን ይቅር በል። አድነኝ! አሁኑኑ ራሴን ለአንተ እሰጣለሁ። ስለ ወደድኸኝና የራስህ አድርገህ ስለ ተቀበልኸኝ አመሰግንሃለሁ። አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ስለ ሆንሁ አመሰግንሃለሁ! አሜን 27
ጌታ ኢየሱስ
ስለ ችግሮቻችሁ ያስባል። እንድታሸንፉ ይረዳችኃል
ገጽ 27 ላይ ያለውን ጸሎት ከጸለያችሁ፣ ኃጢአታችሁ ይቅር ተብሏል። አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ! የእግዚአብሔር መንፈስ - መንፈስ ቅዱስ እናንተ ውስጥ ይኖራል። የጌታ ኢየሱስ ተከታዮች እንድትሆኑ ይረዳችኃል - በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ያበረታታችኃል፤ ይመራችኃል። ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ «የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኃል።» ዮሐንስ 16፥13
ስ
በ በ እ ስ በ ተ
መንፈስ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁና እንደሚያስብላችሁ ያሳስባችኃል።ችግር ሲመጣ ብቻችሁን አትሆኑም፣ መጽናናትን፣ ማስተዋልንና ብርታትን ለእናንተ ለመስጠት ድንቅ የተስፋ ቃሎቹ ሁሉ ከእናንተ ጋር ናቸው። ጥቂቶቹ ቀጥሎ ያሉት ናቸው -
ፍርሀት ሲሰማችሁ
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝና ተስፋ አትቁረጥ እኔ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ ኢሳይያስ 41፥10
ችግር ውስጥ ስትሆኑ
ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል። 28
መዝሙር 34፥17-18
ወ
ወ ሰ እ እ ጋ
1
ኢ በ አ
ዮ
ስትታመሙ
በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቆሰለ አድርገን ቈጠርነው። እርሱ ግን ተወግቶ የቆሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው! እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን። ኢሳይያስ 53፥4-5
ድካም ሲሰማችሁ
ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ «እናንተ በጉልበት ሥራ የደከማችሁ! ሸክምም የከበደባችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ! እኔም ዕረፍት እሰጣችኃለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህና ትሑት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ። ቀንበሬ ልዝብ፤ ሸክሜም ቀላል ነው።» ማቴዎስ 11፥28-30
ወደ ሞት እንደ ቀረባችሁ ሲሰማችሁ
ወንድሞች ሆይ! ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ስለ ሞቱት ሰዎች እውነቱን እንድታውቁ እንወዳለን። ኢየሱስ እንደ ሞተና ከሞትም እንደ ተነሣ እናምናለን፤ ስለዚህ በኢየሱስ አምነው የሞቱትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል። 1 ተሰሎንቄ 4፥13-14
ኢየሱስም፣ «ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በሕይወትም የሚኖርና በእኔ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?» አላት። ዮሐንስ 11፥25-26 29
ዋስትና ማጣት ሲሰማችሁ
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል? እግዚአብሔር ለአንድ ልጁ ሳይራራ ስለ እኛ አሳልፎ ከሰጠው እንዴት ከልጁ ጋር ሁሉን ነገር በነጻ አይሰጠንም? ሮሜ 8፥31-32
ጭንቀት ሲሰማችሁ
እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ። እርሱ ለእናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሐሳብ ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1 ጴጥሮስ 5፥6-7
ገንዘብን በተመለከተ ሐሳብ ሲገባችሁ
ስለዚህም አምላኬ ከክብሩ ብልጽግና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኃል። ፊልጵስዮስ 4፥19
ስትቆጡ
ተቈጡ፤ በቁጣችሁ ግን ኃጢአት አትሥሩ፤ ቁጣችሁም ሳይወገድ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ።
ስ
ስ የ ሲ ይ ሆ
ማ
መ ነ ብ
ነ
ጌ ት
ኢ
ኤፌሶን 4፥26
ብቸኝነት ሲሰማችሁ
ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ «ያዘዝኃችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው። እነሆ፣ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።» ማቴዎስ 28፥20 30
በደለኝ
ስትሰደቡ
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለሆነች የተባረኩ ናቸው። በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ፣ በውሸት ስማችሁን ሲያጠፉት ደስ ይበላችሁ፤ በመንግሥተ ሰማይ የምታገኙት ዋጋ ትልቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ
ማቴዎስ 5፥10-12
የፍትሕ መጓደል ሲኖር
በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ። መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የፍትህ መጓደል የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ እናንተ ክፉ ነገርን በማድረግ መከራ ከምትቀበሉ መልካም ነገርን በማድረግ መከራ ብትቀበሉ ይሻላል። 1 ጴጥሮስ 3፥15-17
ነገር አልሳካ ሲላችሁ
ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ። ለዘላለም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ። ኢሳይያስ 26፥3-4
የበደለኝነት ስሜት ሲሰማችሁ
በደለኝነት
ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ብንናዘዝ እርሱ ታማኝና ጻድቅ ስለ ሆነ ኃጢአታችንን ይቅር ይልልናል፤ ከበደላችንም ሁሉ ያነጻናል። 1 ዮሐንስ 1፥9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ «እስቲ ኑና እንወያይ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ፣ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን፣ እንደ ባዘቶ ይነጣል።» ኢሳይያስ 1፥18 31
ትዕግሥት ስታጡ
በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ። መዝሙር 37:7
Copyright © 2015 FL Media
መብቱ የተጠበቀ ነው።
Printed in India for MediaServe, 2015 www.mediaserve.org
Amharic
አብዛኞቹ በዚህ መጽሐፍ ያሉ ጥቅሶች የተወሰዱት ቀለል ባለ አማርኛ ከተተረጐመው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ጥቂት ጥቅሶች ከአዲሱ መደበኛ ትርጉም ተወስደዋል።
ካርቱን በአልፍሬድ ሉተር
የምስጋና ጸሎት የተወደድህ እግዚአብሔር ሆይ፣ አባቴ ብዬ ልጠራህ ስለ ቻልኩ ተመስገን። ለእኔ እንዲሞት፣ እኔን ከኃጢአትና ከበደል ለመዋጀት እንዲሞት ኢየሱስን በመላክህ ለዘላለም ተመስገን። ስለምትወደኝና ስለምታስብልኝ አመሰግንሃለሁ። አንተ የማታየው ትንሽ ችግር፣ አንተ የማትፈታው ከባድ ችግር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉት ድንቅ የተስፋ ቃሎች ተመስገን። መንፈስ ቅዱስ ሁሌም ከእኔ ጋር እንዲሆንና በየዕለቱ ኑሮዬ እንዲመራኝና እንዲያጽናናኝ እጸልያለሁ። እምነቴን አንተ ላይ በማድረግ ስለማገኘው ደስታና ሰላም ተመስገን። አሜን
የ
እውነተኛ
ሕይወት
ምስጢር
ስለ መጽሐፍ ቅዱስና ስለ እግዚአብሔር፣ ለእናንተ ስላለውም ዕቅድ፣ ይበልጥ ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ከታች ያለውን ፎርም ሙሉና፣ ለ ላኩ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስና እግዚአብሔር ለእኔ ስላለው ዕቅድ የበለጠ ማወቅ እፈልጋለሁ።
4 ከታች ካሉት ምርጫዬ ላይ ምልክት አደርጋለሁ፣ የመጻጻፍ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መማር እፈልጋለሁ። ሕይወቴን ለኢየሱስ ሰጥቻለሁ፤ አንድ ሰው እንዲጐብኘኝና ስለ እርሱ (ኢየሱስ) የበለጠ እንዲነግረኝ እፈልጋለሁ። በዚህ ትንሽ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች የተወሰዱበትን አዲስ ኪዳን ነጻ ኮፒ ማግኘት እፈልጋለሁ። ስም አድራሻ የሚከተለው ነው፣ ስም:
!
አድራሻ:
ለሕይወት ጥያቄዎች መልስ እየፈለግህ ይሆን?
የ
እውነተኛ
ሕይወት
መድረሻ ግብህን በተመለከተ እርግጥኛ ነህ?
የ
እውነተኛ
ሕይወት በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ
ምስጢር
እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
እውነተኛ ሰላም የማገኘው እንዴት ነው?
ምስጢር
ፊልጵስዮስ 4:6-7
ከባድ ሸክም ተጭኖህ ይሆን?