zethiopia issue 80 www.zethiopia.com
የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ፌስቲቫል ከጁላይ 27-29 ይካሄዳል
“ሲልቨር
ስፕሪንግ ወደፊት የኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ትሆናለች!” አቶ ጥበቡ አሰፋ የጁላይ 22ቱ የሲልቨርስ ስፕሪንግ ሁለተኛው የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል አዘጋጅ
Page B2
P.O.Box 2049 Fairfax, VA 22031
202-518-0245
July 2012
መለስ ያልተገኙበት የመሪዎች ጉባኤ በአ.አ ተካሄደ መለስ እንደታመሙ ነው ስጋት አለ አቶ መለስ ዜናዊ ሰሞኑን በአኢ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በጠናባቸው ህመም ምክንያት አልተገኙም። የዓለም መነጋገሪያ የሆኑት አዲሱን የግብጽ ፕሬዚዳንት ጨምሮ ብዙዎቹ አዲስ አበባ ቢገቡም እሳቸው የሉም። የጤንነታቸው ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡእ እለት ብራሰልስ በሚገኘው ሴት ሉክ ሆስፒታል ተመልሰው መተኛታቸውን የግንቦት7 ራዲዮን ጠቅሶ ኢሳት ዘግቧል። አቶ መለስ በህይወት የሚቆዩበት ጊዜ ቀናት ወይም ወራት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ዘገባው፣ አቶ መለስ በካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ መሆኑንም ጠቁሟል ። አቶ መለስ ትናንት የተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በንግግር ከሚከፍቱት መካከል አንዱ ቢሆን አላደረጉትም። ከጋዜጠኛ አበበ ገላው የተቃውሞ አጋጣሚ ጋር የሚያያዙት አሉ።
“ከአንተ ጋር የተያያዘ ይመስልሃል?” በሚል ከዘኢትዮጵያ ልቀረበለት ጥያቄ እኔ ይህን በእርግጠኝነት መናገር አልችልም። መናገር የምችለው ነገር ቢኖር እኚህ ሰው ከዚያ በፊት ሲያስጠነሱ እንኳ አይተን አናውቅም። አልፎ አልፎ ለህክምና መሄዳቸውን ብንሰማም፣ በግልጽ መታመማቸውን የሰማነው አሁን ነው። ከቻይናው መሪ ጋር ሲታዩ እንደዚያ አልቀው ያየናቸው በቴሌቪዥን በጣር እንደተያዘ ሰው እያቃሰቱ የሰማናቸው ከዚያ አጋጣሚ በኋላ ነው።” ብሏል፡ ፡ ቅዳሜ በተደረገው የኔፓዱ ስብሰባ አቶ መለስ በህመም ምክንያት አለመገኘታቸው ተገልጿል። ጸጥታው ከወዲሁ ስጋት እየፈጠረ ሲሆን በፖሊስና በሙስሊሞች መካከል በተፈጠረ ግጭትም አምስት ሰዎች መገደላቸውን በርካቶች መቁሰላቸውን የደረሰን ዜና ያስረዳል።
እንደምንም ስቀዋል
$1.00
መለስን የሚተኩ መለሶች
አንዷለምና እስክንድር ተፈረደባቸው
እንደተጠበቀው የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ አመራርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አራጌ በዕድሜ ልክ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ደግሞ 18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም የወሰነባቸው መሆኑ ተነገረ።
በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ከተላለፈባቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል። ውሳኔውን የአሜሪካ መንግሥትን መንግሥት ጨምሮ አለማቀፍ የሚዲያና የሰብ ዓዊ መብት ተሟጓች አውግዘውታል።
ለማንኛውም የአዜብና እጃቸው የገባው የኤፈርት ገንዘብ እጣ ምን ይሆናል?
ደስታ የፈነቀላቸው የዳላስ ታዳሚዎች
የዳላስና ዲሲው ዝግጅት አለቀ- ከዚያስ? 30ኛው የስፖርት በዓል በዋሽንግተን!? ለ29 ዓመታት በአንድነት የኖረው የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽንንና፣ ከሱ ተነጥለው በመውጣት “የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ማህበር - አንድ!” በሚል የራሳቸውን የስፖርት ማህበር ባቋቁሙት ወገኖች ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው ውዝግብና ዝግጅት አብቅቷል። በተመሳሳይ ቀናት ከጁላይ 1 እስከ 7/2012
በቆዩትና በቴክሳስ ዳላስና ዋሽንግተን ዲሲ የተደረጉት የፌዴሬሽኑና የማህበሩ ዝግጅቶች የየራሳቸውን የተለየ መልክ አሳይተው ማለፋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። በዳላስ የተካሄደው የስፖርት በዓል የዋሽንግተኑን ዝግጅት ግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር እልህና ቁጣ የተቀላቀለበት በመሆኑ
የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ማህበር - አንድ!” በጁላይ 4ቱ ዝግጅት ከ85 ከመቶ በላይ የሚገመቱት የአፍሪካ አሜሪካን እንግዶች ነበሩ። ከሜዳው ዝግጅቶች በሙሉ ስቴዲዮሙ ሰው በርከት ብሎ የታየበት እለት አድርገውታል። እንግዶቹ ሊያይዋቸው የመጡት ሙዚቀኞችም እንደነሱው አፍሪካን አሜሪካን ዘፋኞች ነበሩ። አልፎ አልፎ የሚታዩ እዚህ አገር ያደጉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም ነበሩ። በዝግጅቱ የኢትዮጵያ ስም ከመጠራቱና የተወሰነ ቦታ ላይ ባንዲራ ይዘው መታያታቸው ካልሆነ በስተቀር እንግዶቹም ስለኢትዮጵያ ምን እንዳወቁ አዘጋጆቹም ምን እንዳገኙበት ወጣቶቹም ምን እንደተማሩበት ግልጽ አይደለም። መረጃውን በቪዲዮ ምስል ያገኘነው ቢሆንም እዚያም ላይ ያስተዋልነው ነገር የለም።
ዳላስ ተጀምሮ እስኪያልቅ ከየሥፍራ ነቅሎ በወጣው ህዝብ ተሞልቶ ከርሟል። እልህ የፈነቀለው ህዝብ በቦታው መገኘት ብቻ ሳይሆን ከፊሉም በድል ስሜት እየጨፈረ የዋሽንግተኑን እያወገዘ፣ ለከርሞው ደግሞ በዲሲ ለመገናኘት ሲዝት ታይቷል። ዓመታዊ ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ናቸው። የክብር እንግዶቹ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔም እንደነበሩ ተገልጿል። ከድምጻውያን አንጋፋው መሀሙድ አህመድ፣ ፀሐዬ ዮሐንስ፣ ማሪቱ ለገሠ፣ መዝጊያውም ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ ተገኝተዋል። የፌዴሬሽኑ ውስጥ አዋቂዎች ለዘኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ከወጣቶቹ ድምጻውያን ብዙ የተለመነው ጎሣዬ ተስፋዬ ለራሱ የኮንሰርት ሥራ እዚያው ዳላስ ነበር። ለፌዴሬሽኑ እንዲጫወት ብዙ ተለምኖ ፈራ ተባ እያለ ሲያንገራግር ቆየ። የህዝቡን ብዛት ሲመለከት ግን በመነሸጡ የመዝጊያው ምሽት ላይ ተጫውቷል። ቴዲ አፍሮ ዳላስ ይመጣል ተብሎ በመወራቱ ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ራሱ ዜናውን አውጥቶት ነበር። ይሁን እንጂ ከአንድ የፌዴሬሽኑ ኃላፊ እንደተረዳነው ከቴዲ አፍሮ ፕሮሞተር ከአዲካ
ኢንተርቴይመንት ጋር ሲደረግ የነበረው ድርድር በመካከል እንዲቆም ተደርጓል። የታሰበው ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ቀን መጥቶ አንድ ሁለት ዘፈን ይጫወታል። ከዚያ “በሉ እንግዲህ ዛሬ ማታ እዚህ ቦታ እንገናኝ” ብሎ ቴዲ ይሄዳል። የተባለበት ቦታ ህዝቡ ይሄድና ቴዲ ገንዘብ ይሠራል። በመዝጊያው ቀን ደግሞ መጥቶ ከህዝቡ ጋር ያመሻል። ጥሩ ውለታ ነበር። ቴዲ 100ሺ ብር ጠይቋል ተብሎ የተወራው ግን ፍጹም ውሸት ነበር። የቅርብ ምንጮች እንደጠረጠሩት በዋሽንግተንም በኩል ቴዲ ሳይጎተጎት አልቀረም። ጊዜው ደግሞ ቴዲ ጥቁሩ ሰው የሚለውን የሚኒሊክን ዜማ አልበም ያወጣበት ጊዜ ነበር። “እኔ ዳላስም ሆነ ዲሲ አልሄድም እዚሁ አርፌ እቀመጣለሁ” አለ። ፕሮሞተሩ አዲካ ይህንኑ ለፌዴሬሽኑ አስረዳ። ፌዴሬሽኑም ግድ የለም ቴዲ አትምጣ ችግርህን እንረዳለን ዘፈንህንም እናጫውትልሃለን አለ ። የዳላሱ ስቴዲዮም ከህዝቡ ጋር “ጥቁሩ ሰው” ሲል ዋለ። በዘንድሮው የዳላስ ዝግጅትም ብዙ ሰው የገባው ኢትዮጵያ ቀን ሲሆን 10ሺ ሰዎች ያህል ተግኝተዋል። ሰው ቆጠራ ላይ ግን ፌዴሬሽኑ ይጠነቀቃል። አንድ የፌዴሬሽን ኃላፊ
3
ገጽ A
አቶ መለስ ታመዋል። ሄዱም ዳኑም የአቶ መለስ መሞት ከእንግዲህ ሰበር ዜና አይሆንም! ድንገተኝነቱን አጥቷል። ፍጹም ተሽሏቸው ብቅ ቢሉም እንኳ የተፈራው ጥያቄ መጠየቅ ተጀምሯል። ከሳቸው በኋላ ምን ታስቧል? ቢወርዱ ቢሞቱም የአቶ መለስ መጨረሻ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል ወይም እስከዛሬ የተሰጡ መልሶችን ወደ ጥያቄነት ይቀይራል ተብሎ ይገመታል። ከሰሞኑ የህመም ወሬ ጋር የቅርብ ተከታይ ባለሥልጣኖቻቸው ለአንድ አፍታም ቢሆን መጪው ይታያቸዋል። እውሮች አይደሉም። በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌላቸው ፣እንደተነጠሉ ይገባቸው ይሆናል። አቶ መለስ ከእንግዲህ ብዙ እንደማይቆዩም ያውቃሉ። ስለዚህ ተደብቀውም ቢሆን አንድ ነገር ያስባሉ። እነሱን ሳይጎዳ ሪፎርም/ጥገናዊ ለውጥ ካለም አይጠሉም። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ መለስም እንኳን ታመው በደህናውም ጊዜ ቢሆን የሩቁን አስበው ከሆነ ሁኔታዎችን ሳያመቻቹ እንደማይቀሩ ይታመናል። ከዚያም የተሻሉ ሰው ሆነው ደግሞ የወደፊቱን ነገር ከድርጅታቸው ጋር ተማክረው ወስነውና ኑዛዜያችን ጽፈው ተቀምጠው ከሆነ ሁሉም ነገር በርግታ መጓዙን ይቀጥላል። የአቶ መለስ መካሪዎች ወይም እንዲህ አይነቱን ነገር ለይስሙላም ቢሆን ከሳቸው ጋር በክብ ጠረጴዛ ተቀምጠው መምከር የሚችሉት እነማን ናቸው? አቶ መለስ አገልጋይ እንጂ መሪ አላፈሩም። በምክትሎቻቸው እንኳ የማይከበሩ ሚኒስትሮችን ሲሾሙ ነው የኖሩት። የራሳቸው
ደጋፊ የነበሩትን ቀርቶ የድርጅታቸውን ነባር ታጋዮች ሳይቀር እያዋረዱ ክብራቸውን አራግፈው አርቀዋቸዋል። ቀና ብሎ ሊያያቸው የሚችል ሰው መኖሩን መገመት ቀላል አይደለም። ይሁን እንጂ ግን ሥርዓትና የአስተዳደር መዋቅር ያለ በመሆኑ መለስ በሌለቡት ስለሳቸው እንኳ ተወያይቶ ውሳኔ ሊሰጥ የሚለችለውና አግባብ ያለው ይህ አካል ማነው? አገሪቱን በጎሳ የከፋፈለው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ድርጅት ራሱም በመንደር ጎጥ የተከፋፈለ በመሆኑ ከአመለካከት ይልቅ የአካባቢ ልጅነት ወሳኝነት እንዳለው ይታወቃል። ያንን ተከትሎ ውልደትና መንደር ቆጠራው የራሱን ችግር እየተጫወተ መሆኑ ይሰማል። ክዚያ ባልተናነሰ የጥቅም አሰላለፍም ሌላው ትርጉም የሚሰጠው ይመስላል። በዚህም መሠረት አዜብ ጀነራል ሳሞራና ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አርከበ ደግሞ በደህንነቱ ጌታቸው ተደግፈው ቀና ቀና ማለት ጀምረዋል። አቶ በረከት ሰምዖን ደግሞ ብአዴንንና ደቡብን ይዘው የመሻኮት ሀሳብ አላቸው እየተባለ ነው። አቶ መለስ በመተካካት ሰበብ የጀመሯቸው ውጥኖች መኖራቸው ተነግሯል። አገግመው ሲነሱ ሊያስተካክሉት የሚችሉት ካልሆነ ግን ሽኩቻው የማይቀር ነው። ተነጥለው የወጡትን እነ አቶ ስዬን ወደ ድርጅቱ የመመለስ ፍላጎትም ሊኖር ይችላል እየተባለ ነው። ሁሉም ግምትና መላምት ሆኗል። ቢያንስ መላምትና ግምት ያልሆኑ ቁልፍ የአቶ መለስ ሰዎች እነማን እንደሆኑ የተዘጋጀው ዘገባ ግን ቀጥሎ ያለው ነው። ገጽ A
3
2ኛው የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ዝግጅት ይካሄዳል የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ በሰሜና አሜሪካ ከዓርብ ጁላይ 27 እስከ እሁድ ጁላይ 29/2012 በዋሽንግተን ዲሲ የሚያካሂደውን ዝግጅት የተለያዩ የታሪክ፣ የቅርስ፣ የስነጥበብና ባህላዊ የስፖርት Next time I travel to Ethiopia, I may be arrested as a terrorist. Why? Because I have published articles about Ethiopian politics. By TOBIAS HAGMANN- NewYork Times Page B4
ጨዋታዎችን በማካተት ሊያከብር መዘጋጀቱን አስታውቋል። ለሁለተኛ ዓመት የሚከበረው ይህ በዓል በተለይም ህጻናትና ታዳጊ ወጣቾችን በማነጽና ከባህልና
ታሪካቸው ጋር ለማስተዋወቅ አልሞ መነሳቱን ገልጿል። የኢትዮጵዊነት ውርስና ቅርስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ኃይሉ ለዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደገለጹት ዝግጅቱ ከዓርብ ጁላይ 27 ቀን ከሰዓቱ 3፡30 ፒ ኤም ጀምሮ፣ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ በተሰናዳው የአርት ኤግዚብሽን በይፋ ይጀመራል። በዝግጅቱ ምርትና ለሽያጭ የሚያቀርቧቸውን (ድራይ ጉድስ) ያዘጋጁ እንዲሁም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን
የሚያከናውኑ ድርጅቶችም ቦታቸውን ይዘው ተሳታፊ ይሆናሉ። በእለቱ የ3 ሕጻናት አርቲስቶች ሥራ እንደሚቀርብ ሲገለጽ አንዷ ተስታፊ የምትመጣው ከአትላንታ መሆኑን አቶ አበበ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ፊልሞች እና በዲጂታል የሚንቀሳቀሱ ልዩ የሆኑ የአርት ሥራዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ የግጥም መጻሕፍትም ይነበባሉ። በተለይም የኢትዮጵያ የሙዚቃና ኪነጥበብ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ያላቸው አቶ ተስፋዬ ለማ የኢትዮጵያ ስነጥበብና ሙዚቃ አነሳስ ታሪክና ሂደት አሁን ከደረሰበት አኳያ ገለጻ ያደረጋሉ። በመጨረሻም የኮክቴል ዝግጅት ይኖራል።
Page A6
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ክርስቲያኖች የጋራ ስፖርት በዓል አደረጉ Page A8
0312-57DC2_Ad_11x21_AM_OL.pdf
C
M
Y
CM
MY
CY
CMY
K
1
6/25/12
11:22 AM
A-3
ሰዎቻቸው
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው የመጨረሻው የሥልጣን መዋቅር የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የሥራ አስፈጻሚ አካላትን የያዘው የፖሊት ቢሮ ነው። የዚህ ቢሮ አባላት ከአቶ መለስ ጋር እየተነጋገሩ ወሳኝ የሆኑ የፖሊሲና አስፈላጊም ከሆነ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን የሚሰጡ ናቸው። ይኸው ዝርዝራቸው! ኣባላት ፈጻሚ ስራሕ ሕወሓት ኮይኖም ዘለዉ፡ ኣቶ መለስ ዜናዊ ኣቶ ጸጋይ በርኸ (የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ) ኣቶ ኣባይ ወልዱ(የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና የህወሃት ም/ ሊቀመንበር) ኣቶ ኣባዲ ዘሞ (ከአዜብ ተጣልተው በቅርቡ ከኤፈርት ተነስተው ወደ ሱዳን አምባሰደርነት የተላኩ) ኣቶ ቴዎድሮስ ሓጎስ (የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ኃላፊ) ዶ/ር ቴዎድሮስ ኣድሓኖም (የጤና ጥበቃ ሚኒስትርና የአዜብ ወዳጅ) ኣቶ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአል (የቴሌኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅና የደህነንት ሰው) ኣቶ በየነ ምክሩ የትግራይ ም/ርዕሰ መስተዳደር ወ/ሮ ኣዜብ መስፍን የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት
መለስን የሚተኩ መለሶች
ከዚህ በተጨማሪ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ባስፈለገ ጊዜ ብሔራዊ የፀጥታና የደህነንት ወይም በተለመዶ ወታደራዊ ኮሚቴ የሚባለው ውስጥ ደግሞ እነዚህ የሥራ አስፈጻሚዎችን ጨምሮ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ እና የደህነነት ሚኒስትሩን አቶ ጌታቸው አሰፋን ያካትታል። አቶ መለስ በሌሉ ጊዜ በአግባቡ መሠረት ለምክክር የሚቀመጡት እነዚሁ ግለሰቦች ናቸው። ሥልጣንም ሊያዝ የሚችል ኃይል የሚወጣው ከዚሁ ስብስብ መካከል ነው። ግን ማነው? እስኪ አንዳንዶቹን በጨረፍታ እንያቸው፦
ቴዎድሮስ ሓጎስ ባንድ በኩል የተቃዋሚ መሪዎችን ወደ ሁለተኛ ዙር ነውጥ እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ አግኝተን ህዝቡን ለማረጋጋት በማሰብ ተቃዋሚዎችን ለውይይት ጋበዝናቸው(...136)...ሰኔ 3/1997 ከተቃዋሚዎች ጋር በቲም ክላርክ ቢሮ ተገናኘን። በስብሰባው ላይ ከኢህአዴግ ቴዎድሮስ ሓጎስና እኔ ከቅንጅት ዶ/ር ብርሃኑና ዶ/ር ያእቆብ፣ ከህብረት ደግሞ ዶ/ር በየነና መረራ ተገናኘን። (ገጽ 139)... ይላል የአቶ በረከት መጽሐፍ። አቶ መለስ በዚያ ቀውጢ ወቅት ካላቸው ሰው ሁሉ ከበረከት ሌላ አምነው የላኩት ሰው ቴዎድሮስ ሓጎስን ነው። በእንደዚያ ያለ ቀውጢ ወቅት የሚታመኑ እኚህ ሰው ማን ናቸው?
ቅንጅት ከሕወሃት እየታገለ ከ“ኤርትራውያን እየተደራደረ” ነበረ እንዴ? የሚል ቲዮሪ ለማውጣት ግን መቸኮል አይገባም። ያለ ጊዜው ቀድሞ የሚቀነጠስ ቲዮሪ ሊሆን ይችላል። መንግሥትም ተቃዋሚም አይወዱትም። የኤርትራውያን እጅ እንደ አቶ ኢሳያስ ቁመት ረጅም መሆኑን ማስተዋል ግን አይቸግርም። ስለ ኤርትራ ፍቅር ጭምር ሲሉ ከአቶ ኢሳያስ ፀብ የገቡ እነዚህ መለስ- በረከት- ቴዎድሮስ የሚባሉ...ነገራነገሮች ታሪክ እንዴት
አድርጎ እንደሚጽፋቸው ወይም እነሱ እንዴት እንደሚጽፉት ወደፊት የምናየው ይሆናል። ከአቶ መለስ ተገንጠለው የወጡት የህወሃት ባለሥልጣናትና እኛን ደስ እንዳይለን ብለው የሸሸጉን ሚስጥር ሲወጣ ብዙ እናውቅ ይሆናል። ዝኾነ ኾይኑ አቶ ቴዎድሮስ ሓጎስ በህወሃት ክፍፍል ጌዜም የአቶ መለሰን ቡድን ተሟምተው ካዳኑ ጥቂት ባለውለታዎች አንደኛው ናቸው ። ቀላልኮ ነው። የአንድን “አብዮታዊ” የገዢ ፓርቲ ፖለቲካ
የሚዘውረው ወይም የተዘወረውን እየተቀበለ የሚያስፈጽመው የፖለቲካውና የፕሮፓጋንዳው ዘርፍ ኃላፊ ነው። ኢትዮጵያን የሚገዛው ፓርቲ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲ ከሆነ ደግሞ የህወሓት የፕሮፖጋንዳ ኃላፊፍ ማነው የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ጥሩ ያጫውታል። የህወሃት የፖሊት ቢሮ አባልና የፖለቲካውና የፕሮፖጋንዳው ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ ስማቸው ብዙ አይሰማም። ምክንያቱም እኚህ
ሰው ብዙ ጊዜ መግለጫ የሚሰጡት በአማርኛ ሳይሆን በትግርኛ ነው። በትግርኛ የሚሰጥ ማንኛውንም መግለጫም ቢሆን እኚህ ሰው ማወቅ አለባቸው። ትግርኛን ደግም ከዚያው ከምንጩ መቆጣጣር ስለሚያስፈልግ ቴዎድሮስ ተቀማጭነታቸው አዲስ አባባ ሳይሆን ትግራይ እንዲሆን ተደርጓል። ትግራይን ልክ እያገቧት አጋድመው ተቀምጠውባታል። ሥራ አስፈጻሚውን አባዲ ዘሙን እንኳ ከትግራይና ከኤፈርት ፈንቅለው ሱዳን ያሽቀነጠሯቸው እኚሁ ቴዎድሮስ ሐጎስ ናቸው ይባላል። ለመለስ ነግረው! እንጂ አምባሳደሩን አቶ አሊ አብዶን ከእንቅልፍ ቀስቅሶ በአባዲ ዘሙ መተካት ትክክለኛ “ልዋጭ ልዋጭ” አይመስልም። (የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ባንድ ወቅት ያዘጋጀው ከነበረው ኋላም ሟቹ ጋዜጠኛ አብርሃም ረታ ከተረከበው ከሩሕ ጋዜጣ መጋቢት 21 ቀን 1993 እትም የተገኘ ጽሑፍ እንዲህ ይላል) “ከበረከት ሌላ ከመለስ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሴራውን በማክሸፍ የተባበረው ቴዎድሮስ ሐጎስ የሚባለው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነው። እነዚህ ኤርትራውያን ናቸው በመባል የሚታወቁት በረከት ስምዖንና ቴዎድሮስ በይፋ ከመለስ ጎን መቆም በተለይም በመቀሌ ወጣቶች ዘንድ ግልጽ አቋም እንዲንጸባረቅአድርጓል። የመቀሌ ወጣቶች እነ መለስ “በኤርትራዊነት” ቫይረስ የተለከፉ ህመምተኞች ናቸው ለማለት ERወደ ገጽ A4 ዞሯል
የዳላስና ዲሲው
ከ ገጽ A1 ዞሯል
ለዘኢትዮጵያ እንደገለጹት የሰው ቁጥር አስቸጋሪ ነገር ነው። ምክንያቱም አንዳንዱ ብዙ ሰው ተገኝቶልኛል በማለት ይህን ያህል ሺ ሰው ገባ ብሎ ያወራል። ኋላ ግን ያን ያህል ሰው ገብቷል ተብሏል ብሩ የታለ ሲባል ጣጣ ይመጣል። በዚያ ላይ የቁጥር ችግር አለብን። ሰው መሬት ላይ ያለውን ሳይሆን ስሜቱን ነው የሚቆጥረው። ለምሳሌ የመዝጊያው ምሽት ላይ የገባው ሰው ብዛት እስከ 6ሺ ይደርሳል ብለው የተናገሩ አሉ። የሸጥከው ቲኬት ግን የሚናገረው ከፍሎ የገባው ወደ 2ሺ ሰው መሆኑን ነው። በነጻ የሚገቡ ተጫዋቾችን ጨምረውህ ከ3ሺ500 እስከ 4ሺ ሰው ቢደርስ ነው።
ዘንድሮ በዋሽግንተን ዝግጅትስ እንዴት ነበር?
የተካሄደው
በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውና በሼህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ ስፖንሰር አድራጊነት የተደገፈው “የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት ማህበር - አንድ!” በብዙ ተቃውሞና ጩኸት መካከል የራሱን ዝግጅት አከናውኗል። አጀማመሩ ላይ በዋሽንግተን አካባቢ ከሚኖረው ህዝብ አንጻር የተገኘ ሰው አልነበረም ማለት ብቻ ሳይሆን ባዶነቱ አስደንጋጭ ነበር። የስቴዲዮሙ ቦርቃቃነት እንደተጠበቀ ሆኖ 45ሺ ሰው ይይዛል፣ በተባለ ሜዳ ውስጥ 1ሺ ሰው እንኳ ማየት አለመቻሉ አሳሳቢ ሆኖባቸው እንደነበር ተሰምቷል። ዋሽንግተን ፖስት 100 ያህል ሰው ማለቱ የተዛባ ዘገባ ነው በማለት የተቃወሙ ነበሩ።ቢያንስ ወደ 600 የሚደርሱ ተጫዋቾች ማሰባሰብ መቻሉን ምናልባት ከግምት አልገባላቸው ሊሆን ይችላል። በተለይም ከ90 ከመቶ በላይ የአፍሪካን አሜሪካን ታዳሚዎች በዝተው ታይተውበታል ከተባለው የጁላይ 4 ዝግጅት በስተቀር የተቀሩት የሜዳ ዝግጅቶች በሙሉ የተጠበቀው ሰው ያህል እንዳልተገኘበት ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። ከስቴዲዮሙ ዝግጅት ይልቅ በመዝጊያው የጭፈራ ፕሮግራም ላይ በዋሽንግተን ኮንቬንሽ ሴንተር የተገኘው ሰው ከተጠበቀው በላይና በሺ የሚቆጠር መሆኑ ታውቋል። በተለይም እድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ ወጣቶች እጅግ በዝተው የሚታዩበት መሆኑንን ዝግጅቱን አስመልክቶ ከተሰራጩ ቪዲዮችና ዘጋቢዎች መረዳት ተችሏል።
ቤተሰብ በዳላስ አስተያየት የሚቀጥለው ዓመት ፌዴሬሽኑ 30ኛ ዓመቱን ያከብራል። ገና ከወዲሁ ፌዴሬሽኑ በቦርዱ አማካይነት ተሰብስቦ በዓሉ በዲሲ እንደሚደረግ ከስምምነት ሳያደርስ ሌሎች ዲሲ መሆኑን እየተናገሩ ነው። ቦርዱም ዲሲ ከማድረግ ውጭ ሌላ ምርጫ ያለው አይመስልም። በአብዛኞቹ ስምምነት (ኮንሰንሰስ) የተወሰነ ይመስላል። ፌዴሬሽኑ ዳላስ ላይ ያወጣው ወጪ 50ሺ እንኳ የማይሞላ ቢሆንም ዲሲ ላይ ያን በሚያክል ዋጋ ትልቅ በዓል ለማክበር የሚያስችለው
ቦታ ማግኘቱ ከወዲሁ የጓዳ ጭንቀት መሆኑን ተረድተናል። አሁን በዋሽንግተን ያደረጉትም እዚሁ ዲሲ ለማድረግ ለሁለትና ሶስት ዓመታት ስቴዲዩሙን ደግመው ለመኮናተር ስምምነት መያዛቸው ተሰምቷል። እንግዲህ ሁለቱ ዝግጅቶች ዲሲ ላይ ሲሆኑ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰቡ ይቸግራል። ታላቅ ውጊያ ይሆናል። ያኔ ብዙ ስሞች ብዙ ብሮች ይወድቃሉ። ግን ለምን? መቸም በእልህ ከተሞሉት ወገኖች ደፍሮ ቀኑን የሚለውጥ የለም። 30ኛውንም ሁለተኛውንም የሚያከበሩት ወገኖች አንድ ቀን አድርገው ይፎካከራሉ። ይህም ሕዝቡን ያም ገንዘቡን ይመዛል። ኢትዮጵያን ዞር ብለው ቢያይዋት
ወይም ኢትዮጵያ ዞር ብላ ያየቻቸው ቀን ለውጥ ይኖር ይሆናል። እስከዚያው ግን እርቅ እንዲፈጠር ውስጥ ውስጡን የሚተጉ አሉ እየተባለ ነው። የማይታረቅ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ወገኖች ቢኖሩም በተለይ ተጫዋቾቹ ያንን አቻችሎ ያኖራቸው የስፖርት ቤተሰብነት አብሯቸው ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመለስ እርቅ መፍትሔ መሆኑን ውስጥ ውስጡን የሚሰብኩ አሉ። እልህ የተጋቡ ወገኖች ግን አሁንም ከምክንያታቸው ይልቅ አቅማቸውን የተማመኑ መስለዋል። ዘንድሮ የቻሉትን ያህል ማድረግ በመቻላቸውም ለከርሞው የተበረታቱ መስለዋል። የቻሉትን ሁሉ ለማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ መናገራቸውም ተሰምቷል። የቻሉትን ስለቻሉ ብቻ ማድረግ አቅምን እንጂ ትክክለኛውን ጎዳና የማያመላክት ወደ ገጽ A5 ዞሯል
202-717-8212
cono TRAVEL
SUPER SPECIAL FARES TO AFRICA
Fall Travel*
Summer Travel*
$10 OFF**
Addis Abuja Accra Libreville Nairobi Ndjamena
(August)
MENTION CODE: SUMMER2012
$1,371 $998 $1,048 $1,072 $975 $1,395
Abidjan Dakar Douala Harare Lusaka
(Jun-Jul) $1,335 $1,345 $1,276 $1,255 $1,245
Accra Entebbe Karthoum Libreville Nairobi
* Advertised price shown includes fuel surcharge and taxes, and based on weekday departure and return. Fares, fare rules and applicable surcharges are subject to change without advance notice. Seats are subject to availability and price is not guaranteed until ticketed.
$1,785 $1,725 $1,735 $1,795 $1,698
**Expire Jun 30, 2012 coupon has no cash value and can not be combine with other promotion.
Econo Travel: www.econotraveltours.com Phone: 202-717-8212
www.econotraveltours.com
A-4 መለስን የሚተኩ positive የሚል የስላቅ መጠሪያ ሰጥተዋቸዋል። ህወሃትን ቀርጥፎ በልቷል የሚባለው ይሄ የደም ቆጠራ ኤርትራዊና የትግራይ ልጅ ብቻ ብሎ አላቆመም። ወይም ቀድሞውኑም ቢሆን መነሻው እሱ አልነበረውም። ያው ሲባል የኖረው አድዋ ሽሬ አክሱም አሽአ እና ሌላው የትግራይ ክፍል መካከል ያለው ነው በተለይ የአድዋ ልጆች ያላቸው መንደርተኝነት የሚሉ አሉ። ህወሓትን ለክፍፍል ያበቃውም ይህ ሳይሆን አይቀርም ብለው የሚከራከሩ አሉ። ከአቶ መለስ ጋር የቀሩትንና አውግዘዋቸው የወጡትን የህወሃት አባላት ዝርዝር ሲታይ ግን ይህንን አያረጋግጥም። ለምሳሌ ከወጡት መካከል የሕወሓት የፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት ዓለምሰገድ ገብረአምላክ የአድዋ ልጅ ናቸው። በእዚያኛው ወገን ደግሞ መለስ ዜናዊ፣ ስብሐት ነጋ ግማሽ አድዋዎች ናቸው። በመለስ ወገን ደግሞ ስዩም መስፍን አዲግራት ነው። ተወልደ ወልደማርያምና አባይ ፀሐዬ የአክሱም ልጆች ናቸው። ስዬ አብርሃ የተምቤን ልጅ ሲሆን ገብሩ አሥራት ከመቀሌ የተገኘ የድሀ ልጅ ነው። ከእዚህ በመነሳት ልዩነቱ የጎጥ ሳይሆን የአመለካከትና የጥቅም ጉዳይ መሆኑ ያዘነብላል። እንደተባለውም የያንጊዜው ክፍፍል በተወላጅነት ሳይሆን በጥቅምና በአመለካከት ይመስላል። አመለካከት ሲባልም በኤርትራ ጉዳይ ላይ ሳይሆን በሻዕቢያ ጉዳይ ላይ ባላቸው አቋም መሆኑ ግልጽ ነው።ኢሳያስን በቴስታ እንግጨው ወይስ አንግጨው ዓይነት የእልህ ነገር ይመስላል። ሌላውንማ አብረው ነው ሲወስኑ የኖሩት! ተነጥለው ከወጡት የህወሃት መሪዎችም መካከል በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያላቸውን መሠረታዊ አቋም ቀይረው የታዩት ጥቂት መሆናቸውም ለዚህ ነው። ከእነ አቶ ገብሩ አስራት በስተቀር እንደ አቶ ተወልደ ያሉት አሁንም በኤርትራ ጉዳይ ከአቶ መለስ የተለየ አቋም የላቸውም። ፖለቲካ ነውና እያደረ የተሠራው ፖለቲካ ግን አቶ መለስና ጎዶቻቸውን እዚያ የተወላጅነት ጉድጓዳቸው ውስጥ ሳይከታቸው አልቀረም። አንድም ከተባልኩ፣ ስሜም መጥፋቱ ካልቀረ፣ ወይም ከተነቃብኝማ ምን አስደበቀኝ ይመስላል መለስ ከነገር አዛውንቱ ከስብሐት ነጋ ጋር ሆነው ብዙዎቹን እየቀነሉ በአምቼዎችና በአድዋዎች ሞሉት። ጭራሹንም ስብሐት ነጋ አደባባይ ወጥተው የአክሱም ሥልጣኔ ከአድዋ በታች ያሉትን ትግራዮች አይመለከትም ብለው ታሪክን እንደብርድ ልብስ መግፈፍ ያዙ። ከአክሱም ስልጣኔ ታሪክ ባለቤትነት ብቁ ሆኖ ያልተገኘው ከፊሉ የትግራይ ልጅም ንቀቱን ውጦ
ተወላጆችን ያስቀምጣሉ። አስቂኙ ነገር ከኤርትራውያን ጋር ግንኙነት አላችሁ አሸባሪዎች ናችሁ እያሉ የትግራይን ልጆችን ጭምር ሳይቀር የሚያስጨንቁት እኚሁ በ እናታቸውም በአባታቸውም ከኤርትራ የሚወለዱት አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ ናቸው። ትግርኛ ተናጋሪዎቹን ተቃዋሚዎች በተለይም እንደ አረና ትግራይ ያሉትን መሪዎች እነ አቶ ገብሩ አስራትን “ ትግርኛ ተናጋሪዎቹ ቅንጅት!” የሚል ስያሜ ያሰጡት እኚሁ ቴዎድሮስ ሐጎስ ናቸው። ስለዚህ አቶ መለስ ላይ ከውስጥ ሊነሱ የሚችሉ ተቃውሞዎችን ሁሉ ካውንተር በማድረግ ሥራ ተጠምደዋል። በረከት ስምዖን ትግርኛ ተናጋሪ ባልሆነው ህዝብ ላይ እንደሚሰሩት ማለት ነው።
አቶ በየነ መክሩ ቤተ እስራ ኤልያውያን ፈላሾች በጥቂቱም በትግራይ ክክል ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል። ከዚያ መካከል አቶ
ዝም አለ። አንዱ ወርቅ አንዱ አርቲፊሻል ህዝብ ሆኖ ተገኘ። ለካ “የቀን እንጂ የሰው ጀግና የለውም” የሚለውን የሌላውንብሄረሰብ ብሂልና ብሶት ሳይረዳው አይቀርም። ለማንኛውም ከአድዋ በላይ ወዲ አስመራ የሆኑት እነ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ መቀሌ ወርደው የልማትና የዲሞክራሲ እንዲሁም የሥልጣኔ መርሃ ግብርን ማስተማር የያዙት ለዚህ ይመስላል። ቴዎድሮስ ትግራይን አንቀው ይዘውታል። ለምሳሌ ብዙ ጊዜ በቪኦኤ የትግርኛው ፕሮግራም ቀርበው ስለ ትግራይ የሚናገሩት ቴዎድሮስ ናቸው። ለክልሉ ፕሬዚዳንት አይታዘዙም። ምክንያቱም “ንቀዋቸው ሳይሆን” ከአስተዳደሩ ይልቅ ዋናው ተጠሪነታቸው ለፖለቲካው ዘርፍ ለአቶ መለስ ስለሆነ ነው። የትግራይ ህዝብ ግን ቴዎድሮስን አይወዳቸውም የሚሉም አሉ። “ለምሳሌ ባለፈው የምርጫ ወቅት የትግራይ ህዝብ ቴዎድሮስን መልሳችሁ አታምጡብን ቢልም ህወሓት ግን መልሶ አቀርቧቸዋል። “ቴዎድሮስ ትግራይ ውስጥ ከራሱ ጋር እንኳ ተወዳደሮ ያሸነፈው ለጥቂት ነው።” ብለውናል አንድ የህወሃት የቀድሞ ታጋይ። እንኳን እሳቸውን አዛውንቱ አባታቸውን አቶ ሐጎስንም ቢሆን አካባቢው አይፈልጋቸውም ነበር ሲሉም ገልጠውልናል። አቶ ሐጎስ በአካባቢው ነዋሪ ስለነበሩ የባድመን አካባቢ በማመላከት ስለነበረው ሁኔታ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ በማግስቱ ታመዋል ተብለው አዲስ አበባ በመግባታቸው የአካባቢው ሰው ቂም ይዞባቸው እንደነበር ተነግሯል። በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ኤርትራዊያን አዛውንቶች ምስክርነታቸውን ሲሰጡ እሳቸው አልሰጡም። የቴዎድሮስ አባት አቶ ሓጎስን የጠሉበት ምክንያት በኤርትራዊ ተወላጅነታቸው ሳይሆን ግልጽ ተቆርቋሪነት በመኖሩ ነው እያሉ መረጃ እያጣቀሱ የሚከራከሩ አሉ። ለምሳሌ ጦርነቱ በተነሳበት ወቅት ላይ ሽሬ አካባቢ የሚገኝ ቢችላማ በሚባል ቦታ የሚቆፈር ወርቅ ነበር። ለመቆፈሪያ የተገዙ በጣም ዘመናዊና ውድ መሣሪያዎች ነበሩ። የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲያስገምግም አንዳንድ ማሽኖችን ማግለል አንዱ አጣዳፊ ሥራ ነበር። እነዚህ መሥሪያዎቹ ግን ሳይነሱ ቀርተው ሻእቢያ እጅ እንዲገቡ ተደርገዋል። በዚህ የተነሳ ሆን ብለው እንዲዘረፍ አድርገዋል በሚል ግምገማ ቴዎድሮስ እንዲነሱ ተደርጎ ነበር። እሳቸው ግን ከፍ አሉ እንጂ አልተነሱም። ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሥራ አስፈጻሚነት ተሾሙ። ሶስተኛ በተለያዩ ጊዜያት ከኤርትራ ተሰደው ወደ ትግራይ የሚገቡ በርካታ ስደተኞች አሉ። በተለይ በአንድ ወቅት ቁጥራቸው እጅግ ከፍተኛ ስለነበር ቴሌቪዥን ካሜራ ተዘጋጅቶ የአካባቢው የትግራይ ህዝብ ወጥቶ እልል ብሎ እንዲቀበላቸው ተደርጓል። ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ የተለመደና የቆየ ቢሆንም እንደዚህ በእልልታና በሆታ የሚደረግ አቀባበል አስፈላጊነቱ ምድነው የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ማን ይመልሳል? አቶ መለስ አቶ ቴዎድሮስን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርገው መሾም ይችሉ ነበር። ግን ስም ሳይኖር ሥልጣን መስጠቱን ስለሚችሉበት ብዙም አላስፈልጋቸውም። የክልል ፕሬዚዳንትነቱን ለአባይ ወልዱ ሰይመው ቴዎድሮስን ሾሙባቸው። አቶ አባይ ወልዱ በቅጽል ስማቸው “እትሮ” ተብለው ይታወቃሉ። እንሰራ እንደማለት ነው። ባዶ እንሰራ ስለሆኑ ይሆናል ብለው ይቀልዱባቸዋል የሚያውቋቸው። አቶ መለስ የትግራይ ባልሆኑ ባለሥልጣናት ሥር ም/ል እያደረጉ የትግራይ ልጆችን ያስቀምጣሉ። የትግራይ ልጆች ሥር ደግሞ የኤርትራ ወይም የአድዋ ካልሆኑ የአድዋ
ኃ/ማርያም ደሳለኝ
ያለፉት አቶ አርከበ በአቶ መለስ ብዙም አይታመኑም። አርከበ ጠቅላይ ምኒስትር ለመሆን ካሉት በተሻለ ደረጃ ላይ ቢገኙም አቶ መለስ በህይወት እስካሉ የሚሆን አይመስልም። ቤተሰቦቻቸው አድዋ ሊሆኑ ቢችሉም ውልደትና እድገታቸው አዲግራት ስለሆነ አጋሜ ናቸው። በዚያ ላይ በአድዋዎቹ እነ ስብሐት ነጋ ትንታኔ አርከበ ከአክሱም ሥልጣኔ ከሚመደቡት ሥልጡን ወገኖች አይደሉም። አርከበ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የወሰደው የኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ ኃላፊ (የከንቲባዎች ከንቲባ) ሆነው በኮንስትራክሽን ላይ ሥራ ላይ ተጠምደው መዋላቸው ነው። ከሥልጣን እንዲርቁ በመፈለጉ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ከወረዳና ዞን ማዘጋጃ ቤት ሹሞች ደረጃ በመሆኑ ላይ ላዩን ስለሚደረገው ነገር ምንም እውቀት የላቸውም። የወ/ሮ አዜብን ያህል እንኳ እውቀት አንሷቸው የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ተሿሚ ለመሆን አልበቁም። እሳቸው መለስ በህይወት እያሉ እሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ የሚችሉት ኩዴታ ከተደረገ ብቻ ነው ማለት ይቻላል።
ሳሞራ አቶ ሳሞራ የኑስ (ሙሉ ጄኔራል) አክሱም ውቅሮ ማይ የተባለች ቦታ ሱዳናዊና ኤርትራዊ ከሆኑ ወላጆቻቸው የተወለዱ ሲሆን ትምህርታቸውንም እስከ 11ኛ ክፍል የተከታተሉት እዚያው ነው። ከዚያ በኋላ ኃይስኩል እንኳ ሳይጨርሱ አቋርጠው በረሃ ገቡ። ዛሬ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሙሉ ጄኔራልነት የበቁ ባለ አራት ኮከብ መኮንን ሆነዋል። አቶ መለስ ማእረጉን ሲሳጧቸው እባካህ አትቀልድብኝ ሳይሉ የምር አድርገውት ኮከቡን ተሸክመው ይዞራሉ።
በየነ ምክረ እንደሆኑ ይነገራል። ለነገሩ አባትና እናታቸው እንጂ እሳቸው አይደሉም። እሳቸው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥራ አስፈጻሚና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር/ፕሬዚዳንት፣ የህዳሴ ግድብ የሕዝብ ንቅናቄ አስተባባሪ ምክር ቤት ፀሐፊ ናቸው። አቶ በየነ እናትና አባታቸውን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው በሙሉ ቤተ እስራኤላያውያን ስለሆኑ የሚኖሩት እስራኤል ነው። ስለዚህ ለጥየቃ እስራኤል አገር ይመላለሳሉ። መቀሌ ለሥራ ይሄዳሉ። አዲስ አበባ ለስብሰባ ይመጣሉ። መንገድ ሳይበዛባቸው አይቀርም። በተለይ እስራኤል ሲሄዱ ስለ ህዳሴ ግድቡ አልፎ አልፎ ግብጽን ከተጎራበቷት አይሁዶቹ ጋር መጨዋወታቸው አይቀርም። አቶ መለስ ዜናዊ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎቻቸውን መልሰው ሲያዋቅሩ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አድርገው ከሾሟቸው መካከል አቶ በየነ አንዱ ናቸው። ከአዜብ ጋር አንድነት ነው የተሾሙት። አዜብ ደግሞ ከቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር። ሁለቱ መቸም አይለያዩም።
ደብረ ጽዮን እና ጌታቸው አሰፋ ቴዎድሮስ ሓጎስ
መለስ አንድ ነገር ቢሆኑ አዜብ ምን ይሆኑ ይመስልዎታል ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አንድ ሰው “ደግሞ ለሷ እንጨነቅ እንዴ?” የሚል መልስ ሰጥተዋል። አስተያየት ሰጪው ሲናገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃዋሚውንም ደጋፊውንም የህወሓት ካድሬዎችንም በአንድነት የሚያስማማ ነገር ቢኖር የአዜብ ጉዳይ ነው። አንድም ሰው በደህና አያነሳቸውም። የሳቸው እጣ ሊሆን የሚችለው የያዙትን ያህል ገንዘብ ይዘው ከአገር መውጣት ነው። አዜብ ጓደኛ ያላፈሩ ከገዛ ሴት ልጃቸው ጋር እንኳ ሲጣሉ የሚወሉ፣ ከብዙ ሰው የተጣሉ ሴት ናቸው። በድርጅታቸውም ውስጥ ለኃላፊነት ያበቋቸው በርካታ ሰዎች ቢኖሯቸውም ያንን ከውለታ ቆጥሮ ሊከተላቸው የሚፈልግ ሰው ይኖራል ብሎ ማሰብ የሚችግራቸው አጋጥመውናል። የአቶ መለስ ከቦታው አለመኖር የወ/ሮ አዜብን መነሳት በእርግጠኝነት ወዲያው (አውቶማቲክ) እንዲፈጸም የሚያደርግ መሆኑ ይገመታል።
የደህንነት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋን ሳይተኩ አይቀርም ሲባል ቆይቷል። የደብረ ፅዮንን ቦታ ደግሞ ኻደራ የሚባሉት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይ ቲ) ሰው ከደህንነት ተዛውረው ቦታውን ሊሸፍኑ ይችላሉ። አቶ ኻደራ የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲኖራቸው ብዙ የተደከመባቸው ሰው ስለሆኑ አቶ ደብረ ፅዮን የዘረጉትን ወሬውንም ኔትዎርኩንም የመጠላለፉን ሥራ ሊረከቡት ይችላሉ ተብሎ እየተወራላቸው ነው። የአድዋ ተዋላጅ የሆኑት ኻደራ ከኤርትራዊት እናታቸው ተወልደዋል የተባሉትን የአቶ ደብረፅዮንን ቦታ ሲወስዱ የሳቸውን ቦታ ለማን እንደሚሰጥ አልታወቀም። በደህነንቱ ውስጥ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸውም ሆኑ ምክትላቸው አቶ
ኃይለማርያም የተማሩ አዋቂና የበሰሉ ሰው ሊሆኑ ይችላሉ። ሥልጣኑ የ እውነት ሆኖ ይሰጣቸው እንኳ ቢባል የሚያምናቸው አይኖርም። የሚያምናቸው ቢገኝም የአቶ መለስ ቦታ ላይ ለመቀመጥ ግን የሚጎድላቸው ክፋት አለ። መለስ ገና ከጧቱ ጀምሮ እየተሽለኮሎኩ የሚያስወግዱትን ሁሉ እያስወገዱ እዚህ የደረሱ ሰው ናቸው። እንደ መለስ ጨካኝ ልሁን ቢሉ እንኳ መሆን አይችሉም። በታሪክ ውስጥ አንድ መለስ ነው ሊኖር የሚችለው ሁለተኛ መለስ አይኖርም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ትፈለጋለህ ተብሎ የመጣ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን አይችልም። ዝም ብሎ “ደሳለኝ” ማለት ብቻ ይችል ይሆናል። በአቶ ኃይለማርያም ወደ ሥልጣን መምጣት በጣም ከተበሳጩት ውስጥ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን መሆናቸው ይሰማል። አቶ ስዩም የተበሳጩት በአቶ ኃይለማርያም ሳይሆን የስዩም ሥራ እንዲሰሩ በተሾሙት በአቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ነው። ውጭ ጉዳይ ውስጥም ሆነ ከቅርብ ባለሥልጣናት ውስጥ ያንን ቦታ ሊመጥን የሚችል ሰው የጠፋ ይመስል ኃ/ ማርያምን ማምጣት እንደ ስድብ መቆጠሩ ተሰምቷል። የሥልጣን ዘመናቸውን ሁሉ አቶ መለስን ሲያስተካክሉ የቆዩት አቶ ስዩም መስፍን ወዲህ በአቶ ደሳለኝ በፓርቲያቸው ደግሞ የም/ሊቀመንበርነቱን ቦታ ለአቶ አባይ ወልዱ መስጠታቸውን አልወደዱትም። የሆኖ ሆኖ አቶ መለስን እስከመጨረሻ ድረስ ከማይክዱት መካከል የሆኑት አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የመለስ የግል ህይወት ምስጢረኛ ስለገንዘብም እውቀት ያላቸው ሰው መሆኑ ይነገራል። የገንዘብ ነገር ከተነሰ አቶ መለስ የኤፈርትን ነገር ለባለቤታቸው ሰጥተዋል።ብዙ ሰው የማያስተውለው ሌላ የገዘብ ካዝና ደግሞ አለ። ማረት - ገንዘብ ተክለወይኒ አሰፋ የኤርትራ ተወላጅ ሲሆኑ የማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት) ኃላፊ ናቸው። ማረት ከኤፈርት ጋር የሚስተካከል ሌላኛው ዶላር መዛቂያ ተቋም ነው። ያኛው በንግድ ሲሆን ይሕኛው የእርዳታ ገንዘብ ነው። በክፍፍሉ ጊዜ መቀሌ የሄዱትን የአቶ መለስ ተቃዋሚዎች በሙሉ ቢሯቸውን ዘጋግቶ እንዳይንቀሳቀሱ ያደረጉትና እንቅስቃሴውን ካከሸፉት ሰዎች አንዱ እኚህ አቶ ተክለወይኒ አሰፋ መሆናቸው ይነገር ነበር። ብዙ ሰዎች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ከበረሃ ጀምሮ ከተቀመጡበት የማረት አላፊነት ያልተነሱ ሰዎች ናቸው።
እስከ ዛሬ የተደረገ ዝግጅት ባይኖርና መለስ በድንገት አንድ ነገር ቢሆኑ ሊከሰቱ ከሚችሉ ነገሮች አንዱ በሌሎችም አገሮች ሆኖ የሚታየው የሠራዊቱ ጣልቃ ገብነት ነው። “የአገሪቱን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት” አለብን። የሚነታረኩ ባለሥልጣናትን ሥርዓት እናስይዛለን የመሳሰሉ ቃላትና፣ “ያለምንም ደም” የመሳሰሉ መዝሙሮች በነውጥና ቀውጥ ወቅት ወታደሮችን ወደ ቤተመንግሥት የሚስቡ ማግኔቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ይህ ይፈጸም ይሆን? ይህ ስለመሆኑ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጦሩን ሁኔታ ማየት ይጠይቃል። ጦሩ ላይ ሙሉ ስልጣን ያላቸው ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ናቸው። እንደ ውስጥ አዋቂዎች አባባል ሳሞራ ቦታውን የሚመጥን እውቀትና ችሎታ ባይኖራቸውም ያልተገደበ ሥልጣን አላቸው ። ይህ ከተወዳጅነትና ከእውቀት የመጣ ሳይሆን መለስ ከሳሞራ ሌላ የራሳቸው የሆነ ሌላ ሰው ስለሌላቸው ነው። ሳሞራም ከመለስ ሌላ የሚሆናቸው ሰው እንደሌለ ያውቁታል። ሳሞራን ከምንም አንስተው ባለ አራት ኮከብ ጄነራል ያደረጓቸው አቶ መለስ ናቸው። ከስራቸው አንዳንድ ወሬ አቀባዮችን ከማሰቀመጥ በቀር ብዙም የተጫኗቸው አለመሆኑ ይነገራል። በዚያ ላይ ሳሞራ በብርቱ የህክምና ክትትል ስር ስለሚገኙ ብዙም የሚያጓጓ ቀሪ ህይወት እንደሌላለቸው ይታወቃል። ሳሞራ የሚሞቱ ወይም የደከሙ ቢሆን እሳቸውን የሚተኩትና እንደምክትላቸው የሚታዩት ሰዓረ መኮንን ናቸው። ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የሽሬ ልጅ ሲሆኑ በጦሩ አወቃቀር ከሳሞራ ቀጥለው እንዳሉ ይታመናል። የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሲሆኑ እሳቸውም በትምህርት ብዙ እንዳልገፉ ይነገራል። የባድመው የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦርነት አካባቢ ገና ኃይስኩል ሲማሩ እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ በኃላፊነት አካባቢ ያሉትን በዚህ መንገድ ያስቀመጧቸው ጄኔራሎች ከሳቸው በኋላ ስለሚጠብቃቸው ህይወት ስለሚያስቡ ብዙ አያስቸግሯቸውም። አቶ መለስ የተማሩ ጄኔራሎችን ብዙ አያበረታቱም ብቻ ሳይሆን ሙከራ የሚያሳዩትንም አያቆይዋቸውም ይባላል። ለምሳሌ ከተባረሩት ጄኔራሎች መካከል ወዲ አሸብር የሚባሉት የአድዋ ልጅ አንዱ ናቸው።ሜ/ጄኔራል ሲሆኑ የኮር አዛዥ ነበሩ። ከአንድም ሁለት ማስተርስ እንዳላቸው ይነገራል። ትምህርታቸውን የተከታተሉት ባለቻቸው የትርፍ ጊዜ በግላቸው እያጠኑ መሆኑ ተነግሯል። ይሁን እንጂ በግምገማ “ጦሩን የማስተባበር ሥራ ትቶ አብዛኛው ጊዜውን በትምህርት ላይ ያጠፈል” ተብለው እንዲባረሩ ተደረገ። እንደጓደኞቻቸው እየዞሩ መጠጣት ነበረባቸው? ብለው የጠየቁ ነበሩ። እስካሁን ያየነው በሙሉ በነሱ ዓለም ነው። ነገሮች ሁሉ የሚወሩት ልክ ሌሎቻችን ምኑም ውስጥ እንደሌለንበት ተቆጠረን ነው። አንዳንዴ ሲራኮቱ ሌሎቻችን ይዘነጋሉ። ህዝቡም ቁጣ ላይ መሆኑን አልተገነዘቡም። ሁኔታው በሙሉ ጥይት ተቀባብሎ እንደተቀመጠ ጠመንጃ ይመስላል። ባለሥልጣኖች ሳይቀሩ ከህዝቡ ጋር ሆነው
አለቃ ፀጋይ መለስ አንድ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ባለፉ ደጋፊዎቻቸው ስለ አቶ ስዬ ተጠይቀው ነበር። ስዬን ለምን አይፈታቸውም? ፍርድ ቤት ነው የሚፈታቸው እኔ አይደለሁም።
ደብረፅዮን ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቢሆኑም እንደ አቶ ደብረፅዮን የአቶ መለስን አመኔታ አግኝተው ለፖሊት ቢሮ አባልነት አልበቁም። አቶ ደብረፅዮን አቶ ክንፈ ገ/መድህን የደህነንት ሹም በነበሩ ጊዜ ከሳቸውና ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ዝቅ ብለው ሶስተኛ ሰው ቢሆኑም አሁን ሁለቱንም አልፈው የፖሊት ቢሮ አባል መሆናቸው ጌታቸውንና ኢሳያስን ሳይስከፋቸው አይቀርም የሚሉ አሉ። በተለይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቁጡና በቀላሉ የሚገነፍሉ ቢሆኑም በሥራ ኃላፊነታቸው ግን የማንንም ጣልቃ ገብነት ማስገባት የማይወዱ ለአቶ መለስም ቢሆን አልፎ አልፎ የማይመለሱ በኃይለኛነታቸው የታወቁና የሚፈሩ ሰው መሆናቸውን ሰዎቻቸው ያወራሉ። ውሎ አድሮ ግን የትም አይደርሱም እየተባለ ነው። በዚያ ላይ አቶ ክንፈ የአክሱም ልጆ እንደሆኑት እሳቸውም የመቀሌ ልጅ ናቸው። ውልደታቸው አድዋ አይደለም። አንዳንድ የተበሳጩ ታጋዮች ትግራይ እኮ ስም ነው የቀራት እንጂ ጎጥና አውራጃነት እሷንም አኝኮ እየፈጃት ነው። መለስና ሌት ተቀን የሚንቋትን ስብሀት ነጋን ተሸክማ መኖሯም ለዚህ ይመስላል። ስብሀት ከሰላምታ ቀጥሎ የሚያቀርቡት ጥያቄ የት ነው የተማርከው ብለው ነው የሚጀምሩት ወረዳ ኻበይ ተሚርካ
ከመለስ በኋላ አዜብ ምን ይሆናሉ? ባንድ የቅርብ ወቅት ወደ ኤርትራ በሚተላለፍ የኤርትራ ተቃዋሚ ሬድዮ ላይ ቀርበው የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ከማንም በላይ ባለቤታቸውን እንደሚያምኑ መናገራቸው ተሰምቷል። አዜብ ለሳቸው የጥንካሬ ምንጭ የሆኑ ጎበዝ ሴትና ከማንም ያላነሰ ችሎታ ያላቸውም መሆናቸውን ገልጸዋል። መለስ ከሌለ ግን ማን ያምናቸዋል?
ፍርድ ቤት ቢፈታቸው ግን ደስተኛ ነዎት? አይደለሁም። ይኸው ተመሳሳይ ጥያቄ ለአለቃ ፀጋይ ቀርቦላቸው ነበር አሉ። እንደ አቶ መለስ ፍርድ ቤት ምናምን የሚለውን አወሩና በግል ግን እንዲፈቱ ይፈልጋሉ ሲባሉ “አዎ እፈልጋለሁ!” ብለዋል። ይህ አመላለሳቸው አንድ ሰሞን ከአቶ መለስ ጋር ግጭት ውስጥ ከቷቸው እንደነበር ተነግሯል። አልፎ አልፎም ቢሆን አቶ መለስን ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን በመጠየቅና በመከራከር ይታወቃሉ የሚሉላቸውም ተሰምተዋል። አቶ መለስም ብዙም ክብደት ሳይሰጧቸው አንዳንዴም ደንቆሮ እያሏቸው ያልፏቸው እንደነበር ተሰምቷል። ምንጮች እንደሚሉት ፀጋይ ምንም አይመስላቸውም። የሆኖ ሆኖ በመለሰ ሰርክል ውስጥ ብዙ የቆዩ ናቸው። እሳቸውን ከትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትነታቸው ወደ አዲስ አበባ ስቦ የደህንነት አማካሪ አድርጎ ማስቀመጥ ያስገረማቸው አሉ። ምክንያቱም አለቃ ፀጋይ ሽሬ ዓዲ አገራይ የተወለዱ መቀሌ የተማሩ ሰው እንጂ አድዋ የተወለዱ አይደሉም። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ተብሎ መሾማቸው ስለደህንነትም ሆነ በዚያ ዙሪያ ስላለ ነገር የሚያውቁት ነገር ኖሮ አይመስልም። ፀጋዬ በርኼ የስብሐት ነጋን እህት ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ነው ያገቡት። መቀሌ ሆነው ለስብሐት ነጋ ነገር እንዳይጎነጉኑ መለስ አምጥተው አዲስ አበባ አስቀምጠዋቸዋል። እንዳይከፋቸው ደግሞ የሥራ አስፈጻሚነታቸውን አልነሷቸውም። ሥራ አስፈጻሚ ከመባል የዘለለ ነገር የላቸውም። መለስን ስለመተካት አይታሰቡም።
አርከበ ህወሃትን የመጨመረሻውን ጉባኤ አድርጎ አመራሩን ሲመርጥ ከአቶ መለስ ጋር እኩል ድምጽ አግኝተው
ሳሞራ መንግሥትን እያሙ ነው። አቶ መለስም የመንግሥት ሌባ አስቸገረ እያሉ ነው። ታዲያ መንግሥት ማነው? ሰሞኑን ደብረዘይት ላይ ሰብስበው ከተዋቸዋል የተባሉትን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ተቃዋሚ ወጣቶችን አሠልጥነውስ ምን ሊያደርጓቸው ይሆን? መንግሥት የለም ከተባለ ይህን የሚያደርገው መንግሥት ማነው?
A-5
ዘኢትዮጵያ
ለአዲስ አበባ 72 ከመቶ የታክስ ገቢ የሚገኘው ከመንግሥት ሠራተኞች ብቻ ነው!
ነጋዴውስ?
ርዕሰ አንቀጽ
ትንሿ ጥንቸል ወግ ደርሷት መጠጥ ቤት ገባች አሉ። ጠጥታ ጠጥታ ስትሰክር መንገድ ጀመረች። ስካር አዙሮ ጣላትና ጫካ ውስጥ ወደቀች። አንድ የራበው ጅብ አይቶ ሊበላት ገና አፉን ከመክፈቱ ሌላኛው ጅብ ደረሰና ተጣሉ። እኔ ልብላት እኔ ልብላት በሚል አምባጓሮ ሲደባደቡ ክፉኛ ተቆሳስለው ኖሮ ሁለቱም አጠገቧ ወድቀው ሞቱ። ጉረኝቷ ጥንችል ጧት ከስካር እንቅልፏ ስትነቃ ሁለት ጅቦች ግራና ቀኝ ወድቀዋል። ግርም ብሏት፦ “ወይ ጉድ ደግሞ ምን አድርጌያቸው ይሆን? እኔኮ ስጠጣ የማደርገውን አላውቅም” አለች አሉ -ደብድባ ገድላቸው ይሆናል!
የአዲስ አበባ ከተማን የ2003 በጀት ዓመትን የገቢ አሰባሰብ መሠረት ያደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፣ 72 ከመቶ የሚሆነውን ታክስ/ግብር የሚከፍሉት የመንግሥት ሠራተኞች ብቻ ናቸው። በ2003 የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን አማካይነት፣ ከቀጥታ ታክስ ከተሰበሰበ 2 .4 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1.76 ቢሊዮን ወይም 72 .7 ከመቶው ከደመወዝተኞች ገቢ ተቆርጦ የተሰበሰበ ነው፡፡ ከንግድ ትርፍ ግብር 525. 6 ሚሊዮን ወይም 21.7 ከመቶ ብቻ እንደተሰበሰበም ተገልጿል። “ኅብረተሰብ በአግባቡ የሚጠበቅበትን ግብር እየከፈለ አለመሆኑንን” በመጥቀስ ያማረረው መንግሥታዊ መግለጫ ግብር ከፋዮች አለመክፈል ብቻ ሳይሆን ከሚከፍሉትም ውስጥ በርካቶች እንደሚያጭበረብሩ ገልጿል። ለምሳሌ በዚሁ በጀት ዓመት በከተማው በ98ሺ የንግድ ቤቶች በተደረገው የቤት ለቤት አሰሳ 41 ሺ የሚደርሱት አጭበርብረው ተገኝተዋል። አንዳንዶቹ 33 ከመቶ የሚሆኑት ገቢያቸውን ቀንሰው ሌሎቹም 10 ከመቶ የሚሆኑትም ጭርሱኑ የማይከፍሉበት ሁኔታ መኖሩም ተመልክቷል። 8ሺ900 የሚደርሱት ትላልቅ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ቢሆንም የንግድ ፈቃድ ያላወጡና ለግብር ከፋይነትም ያልተመዘገቡ መሆናቸው ተደርሶበታል። ፈቃድ አውጥተው ገቢያቸውንም አሳውቀው ታክስ ግን የማይከፍሉ በሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውንም መንግሥት ገልጿል። የግብር ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ናቸው ከሚባሉት የግብር ከፋዮችም መካክል ብዙዎቹ የሚከፍሉት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በየወሩ ከደመወዙ ከሚከፍለው በታች መሆኑን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ በቅርቡ ለመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ከሰጡት ገለጻ መረዳት ተችሏል። መንግሥትም ማስከፈል ህዝብም መክፈል የተደካከሙ ይመስላል። የመንግሥት ዋነኛ ገቢ ታክስ ከሆነ ታዲያ መንግሥት ብሩን የሚያመጣው ከዬት ነው ማሰኘቱ አልቀረም።
ነዳጅ አለኝ በሰማይ?! በአገሪቱ ዘጠኝ ኩባንያዎች በነዳጅ ፍለጋ ተሰማርተዋልበኢትዮጵያ በነዳጅ ፍለጋ ዘርፍ ዘጠኝ ኩባንያዎች ተሰማርተው እንደሚገኙ የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ከ2 .4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ አድርገው ነዳጅ ፍለጋ “ጉድጓድ እየማሱ” ነው። ከቀደሙት መንግሥታት ዘመን አንስቶ እስካሁን ድረስ የነዳጅ ፍለጋ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች አሁንም እየተቆፈሩ ቢሆንም ነዳጅ አልሰጡም። መንግሥት ግን ከነዳጁ ይልቅ እናወጣለን ከሚሉት ኩባንያዎች የሚያገኘው ገቢ እየጣመው ይመስላል። ባለፉት አስር ወራት ብቻ ከነዳጅ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከ16 ነጥብ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገልጿል፡፡ ገቢው የተገኘው ከነዳጅ ስራ ጋር በተገናኘ ከመሬት ኪራይ፣ ከስልጠና፣ ከፊርማ ቦነስ እና ከነዳጅ ስራዎች ነው። ኩባንያዎቹ በጋምቤላ፣ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሶማሌ ኦጋዴን፣ በአፋር፣ በመካከለኛው አባይ ሸለቆና በሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ላይ ተሰማርተዋል። በተለይ በኦጋዴንና በቤዚን ካሉብ ሂላል አካባቢም እንዲሁ ሲቆፈር የኖረው አሁንም በአዲስ ጉልበት እየተቆፈረ ነው። ፍለጋውና ጥናቱም ቀጥሏል። እንደ መማሪያ መጻሕፍ (ቴክስት ቡክ) ያጠናው ተማሪ ሲሄድ ያላጣነው የሚማርበት መስሏል የኢትዮጵያ መሬት። ነዳጁ ግን ምድር ሳይሆን ከሰማይ ይመስላል!
የመንግሥት ሠራተኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ደረሰ - 300ሺው ካድሬ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ከጥቂት ዓመታት በፊት የመንግሥት ሠራተኞች ቁጥር 700ሺ አካባቢ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ መንግሥት ተቋማት በሠራተኝነት የተጨመሩት ካድሬዎች ቁጥሩን ወደ አንድ ሚሊዮን ከፍ ማድረጋቸው እየተነገረ ነው። ሰሞኑን የመንግሥት ሠራተኞቹን የውሎ አበል ለማስተካከል ከወጣው መግለጫ ጋር ተያይዞ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ምንጮቻችን የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው መንግሥት በየቦታው ለሚያንቀሳቅሳቸው ካድሬዎቹ ሲል የሠራተኞችን የቀን ውሎ አበል አከፋፈል ለማሻሻል አቅዷል። ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ሳይሻሻል የቆየው የቀን አበል ዝቅተኛው 35 ሲሆን ከፍተኛው 70 ብር መሆኑ ተመልክቷል። በአዲሱ የአበል ማሻሻያ መሰረትም ለሠራተኞች እንደየአካባቢያቸውና ደመወዛቸው መጠን ከ182 እስከ 218 ብር ክፍያ መታቀዱ ተዘግቧል። ታሳቢው አበል ደመወዝ ጭማሪ ሳይሆን ለሥራ ጉዳይ ከቦታ ቦታ ለሚዘዋወሩ ሠራተኞች ብቻ መሆኑ ታውቆ ነጋዴዎች ዋጋ እንዳይጨምሩ መንግሥት መማጸኑም ተነግሯል።
መቀሌ ዩኒቨርስቲ ጃፓንኛ ሊያስተምር ነው ከጃፓን ከ106 ሺህ ዶላር በላይ አግኝቷል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የጃፓንኛ ቋንቋ ለማስተማር ከጃፓን መንግስት ከ106 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ማግኘቱ ታውቃል። በቅርቡ በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ መኖሪያ ቤት በተከናወነው የድጋፍ ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ገንዘቡ ዩኒቨርሲቲው ጃፓንኛን ለማስተማር እንዲሁም የቋንቋ ማስተማሪያ ቤተ ሙከራውንና ሌሎች ተያያዥ ቁሶችን ለማሟላት እንደሚውል ተገልጿል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ቋንቋውን ለማጥናት 60 ተማሪዎች ሲሆን የተሰጠው የገንዘብ ድጋፍም ቋንቋውንና ባህሉን ለማጥናት ፍላጎት ያላቸውን ተጨማሪ ተማሪዎች ለመቀበል እንሚያግዝ ተነግሯል፡፡
እኛም ሳናውቅ ለደበደብናቸው እግዜር ይቅር ይበለን። ትግል እንዲህ የሆነብን፣ ጡንቻችን እንዲህ የፈረጠመብን ሁሉ ከስካር በነቃን ቁጥር ከምናሰማው ፉከራና ፀፀት እግዜር ይጠብቀን ከማለት ሌላ ምን እንላለን። ተኝተን ተኝተን መንቃት ሲጀማምረን አቶ መለስ አፈወርቂ እና አይተ ኢሳያስ ዜናዊ “ሊሞቱ ነው” እያልን እንደ ጥንችሊቷ ከመፎከሪያው ዘመን ጫፍ የቆምን እየመሰልን ነው። በሞቱና በፎከርን አይባል ነገር እኛ በከንቱ ሰከርን እንጂ እነሱስ ገና ሳይሆኑ አልቀረም። ገና ብዙ ሥራ ይጠብቀናል። ቢኖሩም ቢሞቱም ጣጣው ከአናታችን አይወርድም። ስለዚህ ገና ብዙ እንሰክራለን! የስካር ያልሆነው የተረጋጋው ጎዳና፣ የተስፋውና መሀሉ ወርቃማ መንገድ የትኛው ነው። በቃ ያንን የማሰብ ችሎታው የለንም ማለት ነው? ከተቆጡት ጋር ካልተቆጣን፣ ከአበዱት ጋር ካላበድን፣ ስልት አልባ ጩኸት ከሚጮኹት ጋር ካልጮኽን፣ ካደሩት ጋር ካላደርን፣ ካበሩት ጋር ካላበርን፣ ከሳይለንት ማጆሪቲው ጋር አርፈን ካልተገዛን፣ የገዛ ፖለቲካችንን ካላጥላላን፣ ህዝብ ሆነነ ህዝቡን በሐሜት ካልበላን፣ ጎሰኞችን ጎሰኞች ሆነን ካልጠላን፣ ክርስቲያን ከክርስቲያን ሙስሊም ከሙስሊም ካልተጣላን፣ ስፖርተኞች ከስፖርተርኞች ካልተባላን አይሆንልንም ማለት ነው? •
ተነሱ እነመለስን እንታገል- እነዚህ ተቃዋሚዎች በባዶ ሜዳ ይጮኻሉ!
•
ኑ እነ መለስን እንደግፍ- እነዚህ ሆዳሞች ይጮኻሉ
•
ኑ እስኪ መጯጯሁን ትተን እንነጋገር- ይሄ ፈሪ አቋም የለውም!
•
በቃ ሁላችንም ዝም እንበል- ይሄ ህዝብ ምን አባቱ ሆኗል ዝም ብሏል?
እግዚኦ! ይህ ሁሉ የሚሆነው ያም ፈራጅ ያም አዳኝ ያም አራጅ ስለሆነ ይሆን? አዳሜ ተቆጪ፣ ዜግነት ነሺና ሰጪ ስለሆነ ይሆን? እንግዲህ ሁሉም እንዲያ ከሆነ፣ እኛስ ከሁሉ ስለምን እንለያለን? ትንሽ ትንሽ እንቆጣ! ህዝብን መቆጣት ግን ተገቢ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ቀላልም ነገር አይደለም። ራሳቸውን የህዝብ ጠበቃ ያደረጉ የቁርጥ ቀን ልጆች ቀድመው ይጮኻሉ። ስለሆነም ህዝብን ንቆ፣ ያለ እውቀቱ እየገባ በድፍረት ልምራህ ያለ ባለጌ ሁሉ እየተነሳ ህዝቡን አትናገሩት፣ ህዝቡ ታላቅ ነው ይላል- ሲሸነግለው። ህዝብ የሚከበረው ብዙ ስለሆነ ነው ወይስ ሁሉን ነገር ስለሚያውቅ ነው? ወይስ ለናቁት ስላጨበጨበ ነው? ወይስ ለገዙት ስለተገዛ ነው? ወይስ ወይስ ወይስ ወይስ.... የታል እውቀቱ? ራሱን መለወጥ የሚያስችል፣ ራሱን ከአምባገነኖች ማጽዳት የሚያስችል፣ አንድነትና ታሪኩን ግዛትና መሬቱን ማስጠበቅ የሚያስችል እውቀት ከሌለው የህዝብ አዋቂነትና እወቀቱ ምን ይረባዋል? “ህዝብን አንድ ጊዜ ማታላል ይቻላል ሁል ጊዜ ማታላል ግን አይቻልም” አንድ ጊዜ ማለት ስንት ነው? 20 ዓመት? አርባ አምሳ....? በወደቀ ግንድ እንደበዛ ምሳር (መጥረቢያ) ሰዓት እየጠበቀ ሲነቃ የጥንችሏን ፉከራ የሚፎክር ህዝብ አቅምና ወኔ አለህ እያሉ ቢሸነግሉት አብሮና አድሮ መኖር እንጂ ሐቅ አይሆንም። በየመስኩ ልቀው የወጡት የሚያደርጉትን እያየን ነው። አገር አበልጻጊ ነው የተባለ ቢሊየነር እንዲህ እንደ መንደር ወጠምሻ ወርዶ የይዋጣልን እልህ መጋባት ካሰየ፣ ገንዘቡን እንዳልተደከመበት ገንዘብ የትም እየረጨ ጠላት ካበዛ፣ ማንም እየተነሳ ሌባው፣ ቀማኛው፣ ደሙ፣ አጽሙ... እያለ ስድብ መለማመጃ ካደረገው... ሀብት ለምኔ ያሰኛል። በባዶ ሜዳ፣ መናናቅና መተናነቅ የያዙት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ በጀሌዎቻቸው እየተበለጡ፣ በንቀት ከተደፈጠጡ፣ ይህ ሁሉ ዶክተርና ምሁር የሚርመሰመስበት የፖለቲካ ድርጅት፣ ግልብ አፈጮሌዎችና የደናቁርት አምታቾችን ያህል የሚያስጨበጭብ ሀሳብ ማመንጨት ከተሳነው ትምህርት ለምኔ ያሰኛል። ምርቱን ከገለባ መለየት እየተሳነው፣ የነገር ሥሩን ሳያገኘው፣ ላይ ላዩን እየዘለለ፣ በከንቱ ተስፋ እየተደለለ፣ ያንኑ አምና የሰማውን መልሶና መላልሶ እየሰማ፣ “መለስ አምባገነንና ጎሰኛ መሪ ናቸው” የሚል ከ20 ዓመት በኋላ የመጣ “ብሬኪንግ ኒውስ” እየተጋተ፣ በየአዳራሹ የሚያጨበጭብ ግልብ ሰው ከበዛ፣ የኛዎቹን ሳራ ፔለኖችና ተከታዮቿን እያሰቡ ከመዝናናት በቀር ምን ተስፋ ይሰጣል? ሳራ ፔለንን ፕሬዚዳንት መሆን እችላለሁ ማለቷ ብቻ ሳይሆን እሷ ፕሬዚዳንት መሆን ትችላለች የሚል ህዝብ ብዛት ራሱ የሚያስፈራ ነበር። በሰለጠነው አገር ያ ከታየ- ነግ በኔ ነው! የሚሆነውን ጉድ ሁሉ በየቤቱና ስርቻው ሥር ተወትፎ የሚታዘብ፣ የኛ “ሳይለንት ማጆሪቲ” መኖሩ የሰከሩ ቀን “ሳይለንሰር” ይመኙለት ካልሆነ፣ ስለምን “ለሰፊው ህዝብ ጥቅም” እያሉ በስሙ ይመጻደቁለታል። ምን ስላደረገ ነው? ዝም ስላለ? ወገኖቹ ሲረገጡና ሲጋዙ፣ ልጆች እየተሰደዱ ባህር እየሰመጡ፣ እህቶች ለግርድና ባርነት እየተሸጡ፣ የወጣቶች አስክሬን በየአፍሪካው ጫካ ከመኪና እየተጣለ፣ በየባህሩ ከጀልባ እየተሽቀነጠረ፣ የኑሮ ውድነት ህጻናትንና ደካሞችን ሲያጎሳቁል እያየ.. ዝም ስላለ፣ (ሳይለንት ስለሆነ) ነው “ሳይለንት ማጆሪቲ” የሚባለው? ጅሉን ሁሉ ጅል ነህ ማለት የሚችል አርበኛ ካልመጣ ፖለቲካውን ዝምብለው ቢተነትኑት ያው ይተናል እንጂ ምንም አያስገኝም። ወንድነት መለስ ላይ ብቻ መጮህ አይደለም። እሱ ላይ በሽታ እየጮኸበት ነው። ይልቁንስ መለስን መለስ አድርጎ እድሜ የሰጠው፣ አሁንም ሌላ መለስ የሚያስተክል ችግር በወዲህ በኩል አለ። በተለይ ይህን ፖለቲካ አልወድም እያለ ራሱ ሳይረባ፣ የረባ ተቃዋሚ የሚጠብቅ “ሳይለንት ማጆሪቲ” ልብ ለመግዛት እሹሩሩ የማለት ጥቅሙን የሚያስረዳ ጎበዝ ቢገኝ ያስመኛል። ምርጫ ቢኖር ለምርጫ ሲባል ማባባል ያስፈልግ ይሆናል። ከሌለ ግን ባሉት ከመጫወት ሌላ ምን አማራጭ ይገኛል? ተተኪ ሰው መቸም ከሰማይ አይወርድም። ዝም ብሎ እየደጋገመ ሌት ተቀን “ቆይ እስኪ እሺ አሁን ማን አለ?” የሚል ሽባ ትውልድ ሌላውን ሽባ ከማድረግ ውጭ ነገን አያመለክትም። መለስ አልቆለታል ወያኔ አክትሞለታል በቃ በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ተነሱ ከሚሉትም የሚለይ አይደለም። ምሬት በዝቶ አማራጭ ሲጠፋ ግን፣እንዲህ ቁጣ ቁጣ ማለቱ፣ ጩኸት መበርከቱ የሚጠበቅ ነው። ቢሆንም ቢሆንም... “አንተም ጩኸትህ ይገባኛል፣ አንተም የዝምታህ ምክንያት ይሰማኛል፣ ግን እስኪ ደግሞ ረጋ ብላችሁ ተደማምጣችሁ ተመካከሩ” የሚል ብልህስ እንዴት ይጠፋል? “አንተም ተው አንተም ተው!” የሚል ገላጋይ ሽማግሌ አባት ጠፍቶ፣ አገር በያለበት እየተከፈለ፣ እንደ እንቧይ ካብ እዚህም እዚያም ሲናድ ማየት ከበዛ መብሰል ለምኔ፣ ልምድና አስተዋይነት፣ ዋሽቶ አስታራቂነት ባፍንጫዬ ይውጣ ያሰኛል። እንደው እንደ እንጨት ግትር ብሎ የአህያውን ፈርቶ ዳውላውን ቀረርቶ በምስኪን ዜጎች ላይ መልቀቅ እንደኔ ካላሳብክ የት አባትክ ብሎ በስድብ ውርጅብኝ ማሸማቀቅ ብቻውንም መፍትሔ አይደለም። ይህን አስተዋይ ወገን (መቸም ተገኝቶ አላየነውምና) ማፍራት የማይችል ህዝብ ምን ዓይነት ነው? ይህ ዝምተኛውና ገለልተኛው መንጋ የአምባገነኑ ያህል ያቺን አገር እየገደላት ነው። ገለልተኛነትና ዝምታ አስፈላጊ ነው። አስፈላጊነቱ ግን ለሚቀጥል ድርጊት እንጂ በዚያው ጭልጥ ብሎ 20 ዓመት ለመተኛት አይደለም። ገለልተኝነት ስንፍናና ባርነትን ድንቁርናና ሽባነትን መሸፈኛ ሰበብ አይደለም። “እኔ ግራ ገብቶኛል አላውቅም” ማለት አንድ ነገር ነው፤ “እኔ ፖለቲካችሁን መስማት አልፈግልም!” ማለት ግን ኩርፊያ ነው። መቸም ሰው ስለማንነቱ ከራሱም ጋር ማውራቱ መንደድ መቃጠሉ አይቀርም። በየትኛውም መመዘኛ ቢሆን ግን ፖለቲካውን የሚያቦኩት ደናቁርት መድረኩ ላይ መብዛት፣ ፖለቲካውን ላኮረፉት ምሁራን ማምለጫ ምክንያት አይሆንም። ምክንያቱም ብዙ ፍትፈታ የመጣው በነሱ ኩርፊያም ጭምር ነው። እርግጥ ነው ገለልተኞች ዝም በማለታቸው ሊወቀሱ አይገባም። እርግጥ ነው ዝምታ መብታቸውም ስለሆነ ወቃሽና ከሳሽም አያስፈልጋቸውም። ግን ችግሩ ዝም ያሉ ይምሰሉ እንጂ ዝም አላሉም። አፋቸው ለመፍትሔ እንጂ ለሰላቢ ሽሙጥ አልተዘጋም። “አሁን መለስን የሚተካ ምን የረባ ተቃዋሚ አለ?!” የሚል አድካሚና ሰርሳሪ የፖለቲካ መርዝ ይረጫሉ። የመለስን ችሎታ አይተውና ፈትነው ለሥልጣን ያበቁት ይመስል፣ ያለፈቃዳቸው አናታቸው ላይ ጉብ ስላለው ሰው ሲያወሩ በከንቱ ይመጻደቃሉ። የቱን ያህል ዝቅ አድርጎ እንዳያቸው አይገባቸውም። እኔ ከሌለሁ አገር ትፈርሳለች ብሎ የሚያስፈራራን መሪ ቃል ያመነ አገር ቀድሞ ፈርሷልና ባይፈራ ይሻለዋል። ስለዚህ እነሱ ራሳቸውን ንቀው ቤታቸው ከተቀመጡ፣ መለስን የሚተካው ያ መድረክ ላይ ያለውና እነሱ የሚንቁት ተቃዋሚ ኃይል ወይም የአቶ መለስ ወራሽ ወንድም ሊሆን ይችላል። ከዚህ ሌላማ መቸም ከደቡብ ሱዳን ወይም ከቻይና ሰው አይመጣላቸውም። “እሱን ማን ይተካዋል?” ማለት ግን አሁንም “ሰው ናፋቂ” እንጂ “ሥርዓት ናፋቂ” ትውልድ መኖሩን አያመለክትም። ተናፋቂው ለውጥ የሥርዓት እንጂ የሰው አለመሆኑ መታሰብ የተጀመረ ቀን የለውጥ ብርሃን መታየት ይጀምራል። ያለ ሥርዓት ለውጥ አቶ መለስ ቢተኩም የአቶ መለስ ሥርዓት ሊሰጠን የሚችለው ያው ሌላ አቶ መለስን ነው። ተቃዋሚውም አካል ሌላው መለስ እንዳይሆንብን መስጋቱ ሳይዘነጋ ማለት ነው። እንደ ጥንቸሊቷ ከእንቅልፋችን ስንነቃ የተቃዋሚዎቹና የአቶ መለስ ወገኖች ፍልሚያ አብቅቶ ብናየው ግን ጥሩ ነበር። እግዜር ሰካራሟን ጥንችል እንደጠበቃት እኛንም ይጠብቀን! መቸም ከሁለቱ ጅቦች አንዳቸው ቢያሸነፉ ኖሮ ምን ይውጣት ነበር?!
የዳላስና ዲሲው አለመሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው። ሌሎችም ንግግር መብት ስለሆነ ብቻም ያገኙትን ጸያፍ ቃል እየመዘዙ አብሮ በአንድነት የቆየውን የስፖርት ቤተሰብና ኮሙዪኒቲ ባያውኩት የተሻለ ይሆናል። ዋሽንግተኖቹ በዳላስ የተደረገው ሁኔታና በዋሽንግተን ገና አንጀቱን ቅቤ ያላጠጣ ወገን በበዛበት ሁኔታ፣ ዝግጅቱን ለከርሞ ያለ ሁከት ማካሄድ ሳያስቸግራቸው አይቀርም። መጪው ዝግጅት ስም የሚታደስበት ሳይሆን ይበልጥ የሚጠፋበት እንዳይሆንም ያሰጋል። ስም የሚታደሰው ስሙን አጥፍተዋል በተባሉ ወገኖች እንጂ ሌሎችማ ቀድሞም ቢሆን ሲያከብሩት የኖሩት ስም ነው። ስም በመልካም ሥራ እንጂ በአሸነፍኩህ እልህ አይቃናም። ለዚህ ደግሞ መቻቻልና ከዚያ ልዩነት እነማን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አርቆ ማየትን ይጠይቃል። ነገ በዋሽግንተን አደባባዮች ይዋጣልን እያልን ለመቧቀስ እንደሚሰልፍ ሰልፈኛ ጦር ለመሰባበቅ ዝግጅት ማድረግ ከጨዋ ህዝብ አይጠበቅም። ግራና ቀኝ ባሉ ጥቂት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ተከታከቱ ጎራ ለይተው ተፈነካከቱ የሚል ዜና ልጆቻችን ባይሰሙ ደስ ይለናል። ፖቶማክን የማያሻግር ድል ለማግኘት እነዚህ ጽፍነኛ ዳያስፖራዎች ናቸው ወይም እነዚህ ሆዳሞች ናቸው እያሉ ዳር ተመልካች
ሰዎችን ማሸማቀቅ አይገባም። ማንም ስለጮኸ ሳይሆን የሆነውን ራሱ መዝኖ ግራና ቀኝ ሰምቶ አቋሙን ባለመተባበር የገለጸ ህዝብ አለ። ህዝቡ ባዶ ስቴዲየም የሚያስታቅፈው አድማ ስልተጠራ፣ ዘለፋውን ስለፈራ ሳይሆን፣ ምክንያቱን ስላላመነበት የእብሪት ጥሪ ስለሆነበት ይሆናል። የዲሲውን ዝግጅት ያደረጉትና ተባባሪ ሆነው የተገኙትም ወገኖች ሌላው ይተባበራቸው ዘንድ ምክንያታቸውን በበቂ ሁኔታ አላብራሩም። ብድግ ብለው አቅም አለንና ያሻንን ነገር ማድረግ እንችላለን አሉን። ከሀሳባቸው ቀድሞ የተሰማው ገንዘባቸው ነው። ያ ትልቁ ስህተታቸው ነው። አዎ እውነት ነው እነሱም ተበድለው ይሆናል። አብረው የኖሩ ስንት ዘመን የደከሙ ጓደኞቻቸውን እንደ ውሾች አዋርደው እየዘለፉ አሸክርና ሆዳሞች እያሉ በሚዘልፏቸው ሰዎች ስሜታቸው ተነክቶ ሊሆን ይችላል። ዘለፋ ለአብሮ አደግ ባልንጀሮች የተገባ ነገር አይደለም። በጣም የሚያሳዝነው ግን ምንኑም ሳያውቁት ለቁምነገር ሳይሆን ለጭፈራ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ክው ክው እያሉ የሚሄዱ ታዳጊ ወጣቶቻችንን በዘለፋ ማስበርገጋችን ነው። ልጆቻችን ተቃውሞና ተቃዋሚ ሁሉ ባገኘው ነገር ላይ
የሚጮኽ ጭራቅ እንዳይመስላቸው ልንጠነቀቅ ይገባል። አይደለንማ! ተቃዋሚዎች ጨዋዎች ነን። ትህትህና አለን። ክብራችንን እንወዳለን። አንደበታችን የተቆጠበ ነው። በዚህ በዚህ ምክንያት ግን እንለያለን ብለን የማስረዳት ልበ ሙሉነት አለን። ደግሞ ያም ባይሆን የት ያሳደግነውን ልጅ ነው የምቆጣው? ምኑንም የማያውቁትን ታዳጊ ወጣቶች ከአዋቂዎች ጋር ደማምሮ በዘለፋ ከማሸበር መጀመሪያ ማስተማር ይገባል። ክብርን ጨዋነት እውነትን የአገር ፍቅርን ያላስተማሩት ሰው ስቶ ቢገኝ፣ ይውገር ይሰቀል ማለት ፍርድ አይደለም። የሚሆነውን ሁሉ አውቀው የሚሄዱ እንኳ ቢሆን ነጻነታቸውን እናክብርላቸው። ለጠላናቸው ሰዎች የከለከልነውን ነጻነት ለወደድናቸው ሰዎች አንሰጥም! እዚህ በአንደበቱ መግደል የለመደ ኢትዮጵያ ላይ በጥይት ያደርገዋል! በዚያም በኩል “እንዲህ የመሳሰሉ ዘልዛላ ዘፋኞች መጥተውልሃልና ናና ከነሱ ጋር ሆነህ ባህልህን አክብር!” ማለት የህዝብ ብዛት ለማግኘት ሲባል ልጆች ላይ የተፈጸመ ነውር ነው። ባህል የሚበልጽግበት ስፖርተኛ የሚፈጠርበት ኮሙዪኒቲ የሚያድግበት ዝግጅት መሆኑ ቀርቶ ገንዘብና ህዝብ ወዲያና ወዲህ ሆነው እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በሚል ጩኸትና ኹከት መታማሰቸው ያሳዝናል።
ዘኢትዮጵያ- በየወሩ የሚታተም አሳታሚና አዘጋጅ ደረጀ ደስታ ተባባሪ አዘጋጅ ተስፋዬ ተሰማ
የፈጠሩትንና አንገዳግደው ያቆዩትን የስፖርት ፌዴሬሽን ጥለው በመቃብሩ ላይ ራፐሮች እንዲጨፍሩበት መጓጓት ድል አይደለም። ወጣቶቻችንን ታሪካቸው የአገራቸውን ፖለቲካ ሳናስተምራቸው በየፖለቲካውና በየቤተክርስቲያኑ አሁን ደግሞ በየስፖርቱ እየተባላን በመካከል ወዲያና ወዲህ የምናንገላታቸው ታዳጊ ወጣቶቻችን ሊያሳስቡን ይገባል። “ዛሬ ለጠላቶቻችን ያወጣነው ህግ ነገ በወዳጆቻችን ላይ ተግባራዊ ይሆናል” የሚለውን ባህል አንርሳ። ቅጣ ያጣ ስድብ፣ ትልቅ ትንሹን መዘርጠጥ አልፎ ተርፎም ካልተማታሁ የማለት ባህል እየበዛ ነው። እነዚህ ሁሉ የትናንሽ ሰዎች እንጂ የኢትዮጵያውያውን ባህርይ አይደሉም። በጡንቻቸው በፈረጠመ ገንዘባቸው በንቀታቸው የሚገዙንን ወገኖች ለመዋጋት መንገዱ ይህ ያው የነሱን መንገድ መከተል ብቻ አይደለም። “ፖሊስ ጫፌን ነካ” በሚባልበት አገር፣ ጉልበት እያበበ ሲመጣ፣ ለጋዜጠኞችም ቢሆን አደጋ መሆኑ አይቀርም። “እኛ የተናገርነውን ብቻ ጻፍ” የሚለውን ሸሽተን የመጣነው በዚያ ዓይነት ፍርሃት ውስጥ ተመልሰን መግባት አንፈልግም። ለጌታ ለጌታማ ኢትዮጵያም መች አነሰን!
Publisher and Editor Dereje Desta dereje@zethiopia.com
(202) 518- 0245 P.o.box 2049 Fairfax VA 22033
A6
አንዳንድ ነገሮች ስለ ሕግ ዶ/ር ፍጹም አቻምለህ ዓለሙ ከሀገንጋሪ ቡዳፔስት በህግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው እ ኤ አ. በ1988 ነበር። ከኢትዮጵያ ለትምህርት ከሄደበት ሃንጋሪ ትምህርቱን እንደጨረስ ለተጨማሪ ትምህርት በቡዳፔስት ከሚሠራበት የሰብዓዊ መብት ድርጅት ስኮላርሺፕ አግኝቶ ወደ አሜሪካ መጥቷል። እንደገና ወደ አውሮፓ ቡዳፔስት በመመለስ በሃንጋሪ ታዋቂ ለሆነ አንድ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጠበቃና የፕሮጀክት ማኔጀር ሆኖ ሠርቷል። ከ1996 ጀምሮ ወደ አሜሪካ በምመጣት በተለያዩ ቦታዎች ሲሠራ ከቆየ በኋላ ከዲሴምበር 2003 ጀምሮ የራሱን የፍጹም አቻምየለህ የጥብቅና ድርጅት አቋቁሞ እየሠራ ነው።
ዶ/ር ፍጹም አቻምለህ
በዚህ ዓምድ ላይ የሚወጡ ጽሑፎች ለህብረተሰቡ ጠቅላላ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እንጂ በእያንዳንዱ ሰው የግል ግዳዩ ላይ ምክር ለመስጠት አይደለም። ስለሆነም እዚህ አምድ ላይ ብቻ በተጻፈው መመርኮዝ የማይገባ ሲሆን የህግ ችግር ያለበት ግለሰብ ሁሉ ጠበቃውን ማመከር ይኖርበታል።
አዳዲስ ሕጎች በቨርጂኒያ እንደተመለደው ሁሉ በቨርጂኒያው ጠቅላይ ሸንጎ (General assembly) የሚወጡ አዳዲስ ሕጎች በብዛት ፍጻሜ ላይ የሚውሉት በየዓመቱ ከሐምሌ አንድ ጀምሮ ነው። በዚህ መሠረት በዚህ ዓመት ከሐምሌ አንድ ጀምሮ ሥራ ላይ ከሚውሉት ወደ 900 ያህል ህጎች መካከል ለህብረተሰባችን ይጠቅማሉ ብለን የምናስባቸውን እንደሚቀጥሉት እናቀርባለን። የፍርድ ቤት ቅጣት ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ በወሰነ በ15 ቀን ውስጥ መከፈል የነበረበት የፍ/ቤት ቅጣት አሁን በ30 ቀን ሆኗል። ጠጥቶ መንዳት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑንና ጠጥተው ሲነዱ የተያዙ ወጣቶች፣ ለአንድ ዓመት ያህል የመንጃ ፈቃድ እንዲቀሙና ከ500 ብር ያላነሰ ቅጣት እንዲከፍሉ፣ ብሎም 50 ሰዓት ማህበረሰባዊ አገልግሎት (Community Services) እንዲሰጡ ተወስኗል። ከዚህ ውጭ ጠጥቶ በመንዳት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ከሐምሌ አንድ ጀምሮ የመኪና ሞተር መቆለፊያ መሣሪያ (ignition interlock device) ማስገጠም ይኖርበታል። ይህ መሣሪያ የመኪናውን ሞተር ማስነሻ፣ ከትንፋሽ መርማሪ መሳሪያ ጋር የሚያገናኝና አሸክርካሪው መጠጣት አለመጠጣቱን የሚያረጋግጥ ነው። ይህም ማለት ሹፌሩ መኪናውን ከማስነሳቱ በፊት መሣሪያው ላይ መተፈንስ ይኖርበታል። ከጠጣ ሞተሩ አይነሳም። ካልጠጣ ይነሳል። ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት መሣሪያ መግጠም ይገደድ የነበረው ጠጥቶ በመንዳት ሁለት ጊዜ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወይንም ደግሞ በደሙ ውስጥ ያለው የአልኮል መጠጥ ከዜሮ ነጥብ 15 በላይ የሆነ ሰው ብቻ እንደነበር ይታወሳል። ይህን መሳሪያ የሚገጥሙት በቨርጅኒያ መንግሥት የተፈቀደላቸው ሁለት ኩባንያዎች ብቻ ሲሆኑ መሣሪያውን ለማስገጠም ከ450 እስከ 600 ዶላር ወጪ ማውጣት ይኖራል። መንጃ ፈቃድ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የቃል ፈተናውን ያለፈ ሰው፣ የመንዳቱን ፈተና መፈተን የሚችለው፣ የቃሉን ፈተና ባለፈ በ30 ቀን መሆኑ ቀርቶ ከሐምሌ አንድ ጀምሮ በ60 ቀን ይሆናል። የመንዳት ፈተናውን ከመውሰዱ ወይም ከመወስዷ በፊት ደግሞ በቨርጂኒያ መንግሥት እውቅና በተሰጠው የመማሪያ ትምህርት ቤት መማሩን የሚያሳይ ወረቀት ማምጣት ወይም የመንዳት ልምምድ ማድረጉን በፊርማ ማረጋገጥ ይኖበታል። የመጀመሪያውን የመንጃ ፈቃድ ፈተና የወደቀ ሰው በድጋሚ መውሰድ የሚችለው ከሁለት ቀን በኋላ ነው። አዲስም ሆነ የቆየ መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ ከሐምሌ 1 ጀምሮ 20 ዶላር ያስከፍላል። ቦሎና የመኪና ባለቤትነት ከሐምሌ አንድ ጀምሮ የተቃጠለ ቦሎ ለማሳደስ የ10 ዶላር ቅጣት ይኖራል። ከዚህ በፊት ለማሳደስ ቅጣት አልነበረም። ስለዚህ የመኪና ቦሎዎ ከመቃጠሉ በፊት አስቀድሞ ያሳድሱ። የትምህርት ቤት አውቶብስን አልፎ መሄድ ተማሪዎችን የሚያወርድም ሆነ የሚጭን አውቶብስን አልፎ መሄድ (passing school bus) ከሐምሌ አንድ ጀምሮ በቸልተኝነት እንደመንዳት ይቆጠራል። (reckless driving) ምርጫ ከሐምሌ 1 ጀምሮ መራጮች ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ መታወቂያ መያዝ አለባቸው። ከምርጫው ቀን በፊት ድምጽ የሰጠ ሰው (absentee ballot) ከምርጫው ቀን በፊት ህይወቱ ቢያልፍ ድምጹ ይቆጥርለታል። ቤት አከራዮችና ሻጮችን በተመለከተ፣ የቤት አከራዮችና የቤት አሻሻጭና አከራይ ደላላዎች፣ የተበላሸ የችቡድ ግድግዳ (defective drywall) ቤት ውስጥ እንደተገጠመ ካወቁ ለተከራይ ወይም ለገዢ ማሳወቅ አለባቸው። የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የነፍስ ወከፍ (concealed handgun) ጦር መሳሪያ ፈቃድ ያለው ሰው፣ ፈቃዱን እንዲያሳይ በፖሊሲ በሚጠየቅበት ጊዜ፣ ፈቃዱንና መታወቂያውን ካላሳየ 25 ዶላር ይቀጣል። ስለዚህ እንደዚህ ያለ ፈቃድ ያለው ሰው፣ መሣሪያውን ይዞ በሚወጣበት ጊዜ ፈቃዱንና መታወቂያውን ይዞ መውጣት ይኖርበታል። ፍቺ በአዲሱ የቤተሰብ ሕግ መሠረት የስምምነት ፍቺ የሚያደርጉ ባለጉዳዮች፣ ሁለቱም ባለጉዳዮች በፍቺው ከተስማሙና ማመልከቻው ወደ ፍርድ ቤት ከገባ በኋላ የግድ ፍርድ ቤት ሄደው ቃል መስጠት አያስፈልጋቸውም። ይሁን እንጂ ከፍርድ ቤት ውጭ ቃለ መሃላ ፈጽመው፣ የምስክርነት ቃል በጽሑፍ ከሰጡና የምስክርነት ቃል ተጽፎ ፍ/ቤት ከገባ፣ ፍ/ቤቱ የፍቺ ውሳኔ ሊሰጣቸው ይችላል።ይህ ማለት ከሐምሌ አንድ ጀምሮ የስምምነት ፍቺዎችን ከፍጻሜ ለማድረስ የግድ ፍ/ቤት ሄዶ ቃል መስጠት አያስፈልግም። ሌላው የፍቺ የክስ ወረቀት በእጁ ተስጥቶት መልስ ያልሰጠ ተከሳሽ ከፍ/ቤቱ ሁለተኛ ደብዳቤም ሆነ መጥሪያ የማግኘት መብት አይኖረውም። ፍ/ቤቱም ከሳሽ ባስገባው ማመልከቻ መሠረት ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ምግብ ቤቶችና የወይን ጠጅ የአልኮል መጠጥ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ምግብ ቤቶች፣ ተመጋቢዎቻቸው ወይም ደንበቻቸው ከውጭ ይዘውት የሚመጡትን ወይን እንዲጠጡ መፍቀድ ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጂ ለቡሹ ክፍያ ማስከፈል ይችላሉ።
ባሻ አምባሻ! እንዲህ ጻፈ ብላችሁ ደግሞ ትሰድቡኝ ዘንድ አትድከሙ። ራሴን ከዘልፍኩት በላይ አትሰድቡኝም። በራሴ ላይ ያለኝ ሀዘን ከናንተ የበረታ ነውና አዝናችሁብኝ ላትጨርሱ አትድከሙ። ብትንቁኝማ እስቃለሁ። ንቀታችሁ የሚያስቀኝ ቀድሜ ስለምንቃችሁ ብቻ አይደለም፤ እኔ ላይ የምታጠፉት ጊዜ ስለሚያስቀኝ ነው። አንዳችሁ አንዳችሁን በመስደብ የምታጠፉትን ጊዜ እስኪ አስቡት። ክልላችሁን፣ ክፍለሀገራችሁን፣ ፓርቲያችሁን፣ ኃይማኖታችሁን የለየላችሁም ኤርትራዊነታችሁን እየጠራችሁ በጅል እብጠት ስትናገሩ እስኪ አስቡት! እበልጥሃለሁ ባይ ቁጫጭ ሁሉ እርስ በርሱ ሲንጫጫ አምባገነኖች ባንዲት ስኒ ሙቀጫ ልክ ያገቡታል። “ሎሚና ትርንጎ ሞልቶ ባገልግልህ እንቧይ ታሸታለህ የደሀ ነገርህ!” ይባላል። ኢትዮጵያን የሚያክል ታሪካዊና ትልቅ አገር ይዞ ብሄረሰብና ጎሳ ምድጃ ስር መርመጥመጥ እምቧይ እንደማሽተት ነው። ሳይንስ የቀደመች አገር ናት አለ። ጸሐፊዎች ታሪካዊ ናት አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ 40 ነው 60 ጊዜ ጠራት። ኢትዮጵያ ቅኝ አልተገዛችም። ለነገሩ እንኳን ለሌላ ለራሷም መች ተገዛች? ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊም አትገዛም። ገዢዎቿ ሁሌም የውጭ አገር ሰዎች እንደሆኑ ሁሉ ታማርራለች። የሚገዟትም የውጭ አገር ህዝብ የሚገዙ ይመስላቸዋል። ግራ ናት። ጉደኛ፣ መአተኛ፣ ጥጋብም፣ ችጋርም፣ የማትችል አገር ናት። ችጋር እንኳ ትችላለች። ችጋር አትቸገርም። ረሀብ ጌጧ ጥጋብ ምጧ ነው። የጠገበች ቀን ትእቢት ትወልዳለች። እህል ከምራ ክምሩን በጥይት እየበሳች ትጫወታለች። እህሉ የጠፋለት ደግሞ ኢላማዋ ሰው ይሆንና ቀይና ነጭ ሽብር ትላለች። እሱ ሲያልፍ ደግሞ መሬቷን ቆርሳ ኤርትራ ምናምን ብላ እንደ ዒላማ ዛፍ ላይ ሰቅላ እሱን በጥይት ትደበድብላች። መተኮስ ትወዳለች። የተኮሱት አሸንፈው ሥልጣን ይይዛሉ። የተሸነፉት በተራቸው ለመውጣት አድፍጠው ጥይት ያቀባብላሉ - ጠመንጃቸውን ወልውለው ቀን ይጠባበቃሉ። ኢትዮጵያ እንዲህ ነበረች አሁንም እንዲሁ ናት! ትንሽ እህል ስትቀምስ አትቻልም። ይኸው አሁን እንኳ ግብጽ ምናምን እያለች ነው። በወዳደቀችው አገር ሶማሌ እንኳ ላይ ጥይት ስታጮህ ትውላለች። ደቡብ ሱዳን ጠመንጃዋን እየወለወለች ሰሜኑን ነገር እየፈለገች ነው። ትንሽ ፑሽ አፕ ሠርቶ ደረቱ እንዳበጠ ጎረምሳ ያደርጋታል። ጉልቤው የሠፈር ሰው ሲያሸንፍ ሌላ ሠፈር ሄዶ ነገር መፈለጉ ያለ ነው። መሪም ተቃዋሚም የሚፎክሩባት አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት። ምክንያቱ እብሪት ስላወራቸው አያዩማ! መንግስቶቹ አንድ ቀን አይነስወሩን ዘፋኝ አንተ ሰው እማታርፍ ከሆነ ወይ ዝዋይ ወይ ቃሊቲ እንወስድሃለን ብለው አስፈራሩት አሉ። አይነስውሩም ተሳለቀባቸው። “እኔ አሁንስ ዝዋይ ልሁን አዲስ አበባ የት አውቀዋለሁ?” ብሏቸው አረፈው። ኢትዮጵያውያን አስመራ ይሁኑ አዲስ አበባ ጎንደር ይሁኑ አፋር ሲዳሞ ይሁን ትግራይ ምኑን ያውቁታል? ሁሉም ያው ነው ባሻ፣ ሆደባሻ፣ አምባሻ፣ ቆሎ፣ ደበሎ፣ አክምባሎ፣ ባፋንኩሎ ነው! ማሰብ ቶሎ የሚሰልችባት ችኩል አገር ናት። ነገር ሁሉ ቶሎ ቶሎ ወዲያው ወዲያው እጅ በእጅ አገር እንዲደረጅ ነው።ኢትዮጵያ ቸኩላ ያፈሰሰችውን ቸኩላ ካላስለቀመች ስትሮጥ ያሰረችውን ስትሮጥ ካላስፈታች አይሆንላትም። ትችኩላለች። ሥጋ እንኳ ጠብሳና አብስላ ለመብላት ጊዜ የላትም ጥሬውን ትለዋለች። የኢትዮጵያ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ነው። ጥብስና ጥሬ- ክትፎና ጥብስ ነው። አቤቱ! ነጋ ጠባ ነገር ይተነተናል። አንድ ነገር ሳይታሰብ የሚተነተንበት አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት። መለስ አምባገነን ነው ለማለት የሰው ልጅ ስድስት ሰዓት ያወራል። ሌላው ተጨማሪ ይልና ሌላ 12 ሰዓት ያወራል።ከዚያ 12ቱ 24ቱ 48ቱ ሳምንታቱ ወራቱ ዓመታቱ ....ይወራል። እንደጉድ ይወራል። ሌላው ደግሞ 20 ዓመት ያዳምጣል። የአገሬ ሰው ጆሮ እንደ ሆድ ሆኗል። ሆድ ጧት ጠብስቆ በልቶ ምሳ ላይ አምጡ ይላል። ራትም ላይ ባዶ ይቀራል። የአገሬም ሰው ጧት የሰማውን ማታ ላይ ይረሳል። የመለስ አምባገነንነት 6ሺ ጊዜ ይተነተንለታል። ጋዜጠኛው ለቁርስ አክቲቪስቱ ለምሳ ፖለቲከኛው ለራት...ይተነትናሉ። ህዝብም ጋዜጣውን ሬዲዮኑን ቴሌቪዥኑን ኢንተርኔቱን በቀን ሶስት ጊዜ ይመገባል። አይነሳም። የሰማው ጦቢያ ሲሄድ ያልሰማው ምኒልክና ኢትኦጵ ይመጣል እሱ ሲሄድ አዲስ ነገር የተፈጠረ ይመስላል። አዲስ ነገር ሲጠፋ ሰው ላውራ ብሎ አውራ አምባ ይወጣል። አውራምባ ሲወጣ ነጻነትና ፍትህ አገር ላይ ይወጣሉ። እነሱ ሲያልፉ ሌላ ይመጣል። አዳሜ የቀደመውን እየረሳ አዲሱን ያዳንቃል። ወዳጄ ሆይ አሉ ከበደ ሚካኤል ለወንዙ የሚዘፍነውን አዝማሪ ለምን በከንቱ ትደክማለህ የሰማው ሲሄድ ያልሰማው ይመጣል። ይህ መከረኛ ትውልድ ዲሞክራሲን ለመጣው መንግሥት ሁሉ ይዘምራል። የሰሙት ንጉሡ ሲሄዱ ያልሰማው መንጌ መጡ መንጌ ሲያልፉ መሌ መጡ። እሳቸው ሲሄዱ ማን ይመጣል? ማን ግድ አለው? ይሄ ቅንድባም ወደ ፈለገበት ይሂድ እንጂ ሌላ የፈለገ ለምን አይመጣም። እስከዚያው ፍሪ አስራት፣ ፍሪ ታዬ፣ ፍሪ መሪዎቻችንን፣ ፍሪ ብርቱካን፣ ፍሪ እስክንድር፣ ነገር ደግሞ ፍሪ ተመስገን፣ ከዚያ ፍሪ...
ደ.ደ
2ኛው የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ዝግጅት..ከገጽ 1 ቅዳሜ ጠዋት ከ10 ሰዓት ጀምሮ የፓናል ውይይቶች ያሉ ሲሆን በዚህም በተለይም ዶ/ር አህመድ እስልምና በኢትዮጵያ ከየት ወዴት በሚል የእምነቱን ጉዞና ታሪክ አስመልክቶ ትምህርታዊ ገለጻ ያደርጋሉ። በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኩልም ተመሳሳይ ገለጻ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፣ ዶ/ር አብርሃም በቀለ ስለ ጎንደር ነገሥታት አጭር ታሪካዊ ቅኝት እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያን ጥናታዊ የቅርስና ውርስ አስመልክቶም ዶ/ር ሞገስ ገ/ማርያም ማብራሪያ ይሰጣሉ። በኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ላይ እየደረሰ ስላለው ውድመትም አቶ አብርሃም ዓለም ገለጻ ያደርጋሉ። የወጣት አርቲስቶች ፎረምም አርቲስቶቹ ተገናኝተው ስነጥበባዊ ውይይት እንደሚያደርጉበት ተነግሯል። መስክ ላይም የተለያዩ ርቀት ያላቸው የህጻናትና የአዋቂዎች ሩጫ ይደረጋል። የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃዎች የህጻናት የባህል ልብስና የፋሽን ትርኢቶች ይቀርባሉ። በማግስቱ እሁድም በአብዛኛው ቅዳሜ እለት የተደረጉት ዝግጅቶች እንደሚደገሙ ተብራርቷል። የዝግጅቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተመረጡት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባደረጉት የረጅም ጊዜ መንፈሳዊ አገልግሎት፣ እግረ መንገዳቸውን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች እንዲጠበቁ አድርገዋል። ከ40 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን በስደት እንዲቋቋሙ በመርዳትና ኢትዮጵያውያን
ከመንፈሳዊ እሴቶቻቸው እንዳይርቁ አስተዋጾ አድርገዋል። በተለያዩ የኢትዮጵያ የእምነት ተካታዮችም ዘንድ አገራዊ አንድነት እንዲኖር ጥረዋል። ለቤተከርስቲያን ነጻነትም ግንባር ቀደም ተቆርቋሪና ተሟጋች በመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ብጹእ
አቡነ መልከ ፀዲቅ የንጉሡ መንፈሳዊ አማካሪ በነበሩበትም ወቅት ንጉሠ ነገሥቱን በማሳመን የሴት እህቶቻችን ዘማሪያን ለመጀመሪያ ጊዜ በዝማሬ አምላክና ቤተክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ማስደረጋቸው ለክብር እንግድነቱ እንዲታጩ ካሳቻሏቸው ምክንያቶች ውስጥ
ጥቂቶቹ መሆናቸው ታውቋል። በሌላም በኩል የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር ህዝባቸውን በማገልገል ከፍተኛ መሰዋእትነት በመክፈል ላይ የሚገኙትን ለማሰብ ፕሮግራም ማዘጋጀቱንም አስታውቋል። በተለይም በኢትዮጵያ ለሀሳብ ነጻነት ሲባል ዋጋ በመክፈል ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች እነ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙን ለማሰብና በስደትም ያሉትን ጋዜጠኞች ምስጋና ለማቅረብ በጋዜጠኛ አበበ ገላው በኩል
ድጋፉን ለጋዜጠኞቹ ለመግለጽ ማሰቡን፣ በሳንፍራንሲስኮ ነዋሪ የሆኑት፣ የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ በሰሜና አሜሪካ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አበበ ኃይሉ ገልጸዋል። (ዘኢትዮጵያ)
ሬዲዮ አቢሲኒያ ዘወትር ቅዳሜ ከ 5pm-7pm እሁድ 5pm-7pm AM730 WTNT
Radio Abisinia Saturday 5pm-7pm and Sunday 5pm-7pm ON AM730 WTNT TO LISTEN BY PHONE CALL 712 432 0075 ACCESS CODE 850575# LIVE ON AM730 WTNT
202-644-9991
Does your visa petition need family relationship testing?
ባለፉት 9 ወራት 13 ሺ ወጣቶች ድንበር ላይ ተያዙ?
Laboratories DNA-based testing to establish family relationships. AABB accredited, as required the Department of Homeland Security. Experienced in service to embassies worldwide. Pricing includes: - Collection of petitioner’s sample - Collection materials to the foreign embassy for the beneficiary - Clear, easily understood reports of conclusions sent directly to the embassy - Rapid return to meet interview deadlines Fairfax Identity Laboratories is a full service relationship testing laboratory with over twenty years experience in providing services to government agencies for establishment of biological relationships. Services include determination of paternity (father-child), maternity (mother-child), full sibling relationships (brothers or sisters with the same two parents), half sibling relationships (brothers or sisters with one parent in common between them). Other types of relationship testing are available; call to inquire.
To inquire or to set up your test, call 800-234-2528
ባለፉት 9 ወራት በህገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ የተደረሰባቸዉ 13 ሺህ 600 ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን መንግሥት አስታውቋል ። አብዛኞቹ በመተማ በኩል ወደ ጎረቤት አገር ሱዳንና በኦሮሚያ ክልል በኩል ደግሞ ወደ ጅቡቲና ሳውዲ አረብያና ወደ አፍሪካ አገሮች በህገ ወጥ መንገድ ሊወጡ ሲሞክሩ ነው ተብሏል ። ሰሞኑን የወጣው የአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መግለጫ እንደገለጸው ወጣቶቹን ከአገር እንዲሰደዱ አድርገዋል ያላቸውን 130 የሚደርሱ ህገወጥ ደላሎች በቁጥጥር ሥር አውሏል። የተሻለ ሕይወት ፍለጋ አገር ጥለው ሲወጡ ተይዘው እንዲመለሱ ከተደረጉት መካከል 9 ሺህ 800 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ተመልክቷል።
ኩላሊት በኢት. ለዳያለሲስ በወር እስከ 12ሺ ብር ያስፈልጋል ዳያለሲስ፣እጅግ የተጎዳ የኩላሊት ክፍል ኖሯቸው፣ እክል የገጠማቸው ህሙማን፣ በህይወት እስካሉ ድረስ፣ የግዴታ መውሰድ ያለባቸው ህክምና በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ይህን ህክምና ለማግኘት፣ በወር እስከ 12ሺ ብር እንደሚያስፈልግ ተነግሯል። በኢትዮጵያ ቢያንስ 1 .9 ሚሊዮን የኩላሊት ሕሙማን ሲኖሩ አገሪቱ በዓለም በ14ኛ ደረጃ እንደምትገኝ ተገልጿል። የዋጋው ብዛት ለምን ያህሉ በሽተኛ እንደሚቻል ማሰቡ አስቸጋሪ መሆኑም ተነግሯል። ጤነኛ ኩላሊትን ከሌላ ሰው ወስዶ ለታመመው ሰው የመተካቱ የህክምና ጥበብ፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ ቢኖርም፣ በኢትዮጵያ ግን ይህን ለማድረግ የሚያስችል ደረጃ ላይ ገና ያልተደረሰ መሆኑ ተሰምቷል።
ማር በዝቶ መረረ!? አንዳንዱ ነገር ፕሮፕጋንዳና ጉራ ሳይሆን ለካ እውነት ነው። ለምሳሌ ከአፍሪካ በማር ምርት አንደኛ ነን። ልክ በቀንድ ከብት አንደኛ ሆነን ወተት እንደሞላን ማለት ነው። ማርና ወተት የሞላባት አገር! ላሚቷ እንኳ ከራባት ወተት አትሰጥም። ማርም ከበዛ “ንቢቷም” የምርጫ ሰሞን ከተናደፈች የማር ነገር አይሆነነም። ለማንኛውም በአገሪቱ የማር ምርት አቅም አቅርቦትና ገበያ ሲጠና ኢትዮጵያ በዓመት 500 ሺሕ ቶን ማር የማምረት አቅም አላት፡፡ ይህ ከአፍሪካ አንደኛ ያደርጋታል። ኢትዮጵያ ግን እያመረተች ያለችው 43ሺ 000 ቶን ብቻ ነው፡፡ ከዚህም ምርት ውስጥ ቢሆን ከ90 በመቶ ያላነሰው ማር ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ነው። ለውጭ ገበያ ማቅረብ የቻለችው ከ112 ቶን የበለጠ አይደለም። 500ሺ ቶን ማር ማምረት የምትችል አገር ባላመረተችው ማር የመረራት ይመስላል።
LAW Office of Thomas Hailu የቶማስ ኃይሉ የጥብቅና ድርጅት
• Personal Injury • Criminal Defense • Immigration Licensed Virginia, Maryland and DC Also licensed at Supreme Court and US, US Court of Appeals for 4th and 9th circuits LAW Office of Thomas Hailu
www.Hailulaw.com
4609 H Pinecrest Office Park Drive Alexandria, VA 22312
703- 807- 0780
• • • •
የወንጀል ጉዳይ ኢምግሬሽን በአካል ላይ የሚደርስ ጉዳት በፌደራል ወይም በስቴት የወንጀል ጉዳዮች እርዳታ ቢያስፈልግዎ
•
ወይም በቸልተኝነት የአካል ጉዳት ቢደርስብዎ
ለብዙ ዓመታት የህግ ልምድ ያላቸውን አቶ ቶማስን ደውለው ያነጋግሩ
ይፎ Ethiopian ዜ ሕ a ጃ F d
ሚ i u ኢ to connect, to be educated
heritage & culture camp
QRSÂ ÆHL µMP
We are Ethiopian,
We are American, We are Parents,
4th
Annual
We are Siblings, we are sharing, we are loving,
Q
(ተስፋዬ ተሰማ- ዘኢትዮጵያ፟) የኢትዮጵያና የኤርትራ ክርስቲያኖች በጋራ ያዘጋጁት የስፖርት በዓል እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በዌስት ፊልድ ስታዲየም ተደረገ። ከጁላይ 4 እስከ ጁላይ 7 ለአራት ቀናት በተደረገው በዚህ የስፖርት ውድድር ከሲያትልና ከቺካጎ የመጡትን ቡድኖች ጨምሮ ስድስት የ እግር ኳስና አራት የሴቶች መረብ ኳስ ቡድኖች ቤተክርስቲያኖቻቸውን ወክለው በውድድሩ ተካፍለዋል። በዚህ ውድድር የፌስቲቫሉ ዋና አዘጋጅ የሆነው የአቤዜኔዘር ኤርትራዊያን ቤተከርስቲያን ቡድን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያንን ቡድን በጎል ብልጫ አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቅቷል። ወጣቱ...ከኢትዮጵያ ወንጌላዊ ቤተከርስቲያን ኮከብ ተጫዋችና 10 ግብ በማግባቱ ደግሞ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ተሸልሟል።
co
we are learning, we are growing… Join us Aug 9 - 12, 2012 Harrisonburg, VA
design | www.yolkworks.com
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ክርስቲያኖች የጋራ ስፖርት በዓል አደረጉ
www.heritageandculturecamp.org
1.800.775.1797
የአራት ቀን ዝግጅት! 4 DAYS/3 NIGHTS GETAWAY
የስፖርቱ አዘጋጆች “ ስፖርት በአሉ መሰረት ያደረገው የእግዚአብሔርን ቃል ነው” ብለዋል። “የ እግዚአብሄር ቃል ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው እንዲሁም ያማረ ነው” ስለሚል የዚህ ስፖርት በዓል ዋና ዓላማም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያንን ወክሎ ይህን ኮሚቴ ማስተባበር የሚሰራው ነበዩ እንደተናገረው ይህ የመጀመሪያችን ነው ሙቀቱም ትንሽ አስቸጋሪ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት የተሻለ ዝግጅት አድርገን ብዙ ቡድኖችን እንዲሳተፉ በማድረግ በአሜሪካን ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ክርስቲያኖች የበለጠ እንዲቀራረቡ ለማድረግ እንሞክራለን።” ብሏል። በዚህ ዝግጅት የተሳተፉ ክርስቲያኖች እንደነገሩ ብዙዎቹ በዚህ ፌስቲቫል በጣም ተደስተዋል። እርስ በርስ በመተዋወቅና ለመቀራረብ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል ብለውኛል። በሌላም በኩል፣ በኤርትራና በኢትዮጵያውያን መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር “ክርስቶስ እኛን ከዘርና ከወገን ዋጅቶ አንድ አድርጎናል።” በማለት በአውሮፓና በአሜሪካ በመዘዋወር፣ የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ቤተከርስቲያናት በአንድ ኮንፈረንስ እንዲያዘጋጁ በማድረግ በኩል ፓስተር ቶለሳ ለብዙ ዓመታት ብዙ ታላላቅ ስራዎችን ሠርተዋል ይባላል። በክርስቲያኖች መካከል ያለን ወንድማማችነትን ለማጠናክር፣ እርስ በርስ ለመተዋወቅ፣ በሁሉም በላይ እግዜአብሔርን ለማምለክ ነው ብለዋል። የአቤኔዘር የኤርትራውያንን ቸርች ወክሎ በአስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ እያገለገለ የሚገኘው ተስፋ ባራኪ እንደተናገረው ደግሞ ይህ የስፖርት በአል በቤተክርስቲያን መካከል መቀራረብን ይፈጥራል። በኢትዮጵያውያንና በኤርትራውያን ክርስቲያኖች መካከል በዚህ በምንኖርበት አሜሪካን ሀገር ያለንን እውቀትና ልምድ በመለዋወጥ እርስ በርስ ለመረዳዳትም ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል ብሎአል። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እስካሁን ያልተፈቱ ብዙ የፖለቲካ ችግሮች አሉ። ፅንፈኛ የሆነ አመለካከት ያላቸው ሰዎችም በሁለቱም ወገኖች ይኖራሉ። እና ይሄ የፖለቲካ አለመግባባት በዝግጅታሁ ላይ ችግር አልፈጠረም የሚል ጥያቄ አንስቼባቸው ነበር። ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ ወገን በአዘጋጅ ኮሚቴው ውስጥ የነገሩኝ ነገር ተመሳሳይ ነው እንደነሱ አባባል እኛ ክርስቲያኖች ነን ፖለቲከኛ አይደለንም። ክርስቲያን ደግሞ የሰላም መል እክተኛ ነው። የእግዚአብሄርም ቃል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ብሎ ነው የሚያስተምረን። ስለዚህ ምንም ዓይነት አለመግባባት ጥል፣ ቅሬታ በሰላምና በፍቅር ቢፈታ ይችላል ብለን እናምናለን። ለዚያም ደግሞ እንሰራለን ብለዋል።
የወሩ የመጨረሻ
ዓርብ
ሲሆን በጣይቱ ግጥም ይነበባል ወይም ይሳቃል
የግጥም ምሽት
Tayitu Cultural Center at 7:00pm Unification Church 1610 Columbia Rd NW Washington, DC 20009
ና
አ፵፶፷፸፹፺፻፼፤፥፦፧ዥዖዟጇዷዻኧፘፗዧጯጓዃኞሀ
B
section
፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲ zethiopia issue #80
www.zethiopia.com
የኢትዮጵያ አሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ ለንደን ላይ በሚካሄደው 30ኛው ኦሎምፒክ ውድድር የሚሳተፉትን እነዚህን 33 አትሌቶች መርጧል
P.O.Box 2049 Fairfax, VA 22031
ከ30 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ?
202-518-0245
አስተያየት «ድልድሉ የዕጣ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን ጋር መደልደሉ ቀላል፣ ከኮትዲቯር ጋር መደልደሉ ደግሞ ከባድ ነው ሊባል አይችልም» ብለዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ መሥራች
July 2012
ዛምቢያን ሁለት ለዜሮ አሸንፋለች። «ውጤቱ ሱዳን ጠንካራ እንደሆነች የሚያሳይ ቢሆንም አሸንፈን በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ እንጫወታለን» በማለት አሠልጣኝ ሰውነት ተናግረዋል።
ሲልቨር ስፕሪንግ ወደፊት
400 ሜትር ወንዶች በረከት ደስታ 800 ሴቶች ሜትር ፍንቱ ሚጌሶ ወንዶች መሐመድ አማን 1 ሺ 500 ሴቶች አበባ አረጋዊ ገንዘቤ ዲቢባ መስከረም አሰፋ ወንዶች መኮንን ገብረመድህን፣ ዳዊት ወልዴ፣ ተሾመ ደሪሳ አማን ወጤ በተጠባበቂነት 3ሺ000 መሰናክል ሴቶች ሶፍያ አሰፋ፣ ህይወት አያሌው፣ እቴነሽ ዲሮ ዘመዘም አህመድ በተጠባባቂነት ወንዶች ሮባ ጋሪ ፣ ብርሀኑ ጌታሁን ናሆም መስፈን 5ሺ000 ሴቶች መሰረት ደፋር፣ ገለቴ ቡርቃና ገነት ያለው ጥሩ ነሽ ዲባባ በተጠባበቂነት በወንዶች ደጀነ ገብረመስቀል ፣ ሐጎስ ገብረ ህይወት፣ የኔው አላምረው ኢማና መርጋ
10ሺ000 ሴቶች
ጥሩነሽ ዲባባ በላይነሽ አልጅራ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ አበሩ ከበደ በተጠባባቂነት
የኢትዮጵያውያን
ዋና ከተማ ትሆናለች!
በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ታሪኩ በቀለና ገብረእግዚሀቤር ገብረማርያም ሌሊሳ ዲሳሳ በተጠባባቂነት ተመርጠዋል ። በማራቶን ሴቶች ቲከ ገላና፣ አሰለፈቸ መርጊያ ፣ ማሬ ዲባባ እና ብዙነሽ በቀለ በወንዶች አየለ አብሽሮ፣ ዲኖ ስፍር ፣ ጌቱ ፈለቀ ታደሰ ቶላ ብቸኛው የውሃ ዋናተኛ ያኔት ስዩም ለለንደኑ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክላ ትወዳደራለች ።
ወንድማማቾቹ ቀነኒሳና ታሪኩ በቀለ በሚያደርጉት የርስ በርስ ውድድር የዘንድሮውን የለንደን ኦሎምፒክ አጓጊ ሳያደርጉት አይቀሩም
Champion of Change ለውጥ አምጪው ጥበበ አሰፋ!
ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ትጫወታለች። በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ጨዋታታቸውን የሚያደርጉ ሀገሮች ድልድል ይፋ ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሩ ብቃት ያሳየችውን የሱዳን ብሔራዊ ጋር ይገጥማል። በርካቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን ጋር መደልደሉ ከሠላሳ ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ የሚያስችለው መልካም አጋጣሚ እንደተፈጠረ ቆጥረውታል። «አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው በበኩላቸው ሱዳንን አክብደንም አቅለንም አናይም» ማለታቸውን አዲስ ዘመን ዘግቧል። አሠልጣኝ ሰውነት በስልክ በሰጡት
የሴቶቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሩ መሻሻልና ለውጥ እያመጣ ያለ ይመስላል። የሴቶች ቡድን በዓለም አቀፍ መድረኮች ብቅ ብቅ እያለ ጥንካሬ ልዩ የአጨዋወት ጥበብና ወኔያቸው ከፍ ያለ እህቶቻችንን እያሳየን ነው። ተፈላጊውን ውጤት የሚያስገኙበት ጊዜ ሩቅ አለመሆኑን የሚያሳይ ይመስላል።
ዘኢትዮጵያ
$1.00
10ኛ ዓመት በቅርብ ቀን
ከሆኑ ሀገሮች መካከል ሱዳንና ኢትዮጵያ ግንባር ቀድሞቹ እንደሆኑ በማስታወስ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በርካታ ጊዜ የተጫወቱ ሲሆን የተሸናነፉበት አቻ የወጡበት ጊዜ መኖሩንና አንዱ ከሌለው በላይ እንዳልሆነም አሰልጣኝ ሰውነት ተናግረዋል። በ1998 ዓ.ም በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆነው ሱዳንን ሦስት ለአንድ በሆነ ውጤት ከውድድር ውጭ እንዳደረጉት ያስታውሱት አሠልጣኝ ሰውነት የሱዳን ብሔራዊ ቡድን «ጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ቡድን ቢሆንም የተለየ ግምት አንሰጠውም» ማለታቸውን የሪፖተር ቦጋለ አበበ ዘገባ ያስረዳል። ሱዳን በተደጋጋሚ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈችና የጠንካራ ክለቦች ባለቤት እንደመሆኗ መጠን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀድሞ የነበረውን ደካማ አቋም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ መልካም የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ተጫዋቾችም በአፍሪካ እግር ኳስ ጥሩ ደረጃ ላይ ከሚገኙት የደቡብና የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች ቡድኖች ጋር ተጫውተው አመርቂ ውጤት በማስመዝገባቸው በራስ የመተማመን ስሜታቸው ከፍ እንዳለና ጠንካራ የአሸናፊነት መንፈስ እንደተጐናፀፉ አሠልጣኝ ሰወነት ገልጸዋል። ዋሊያዎቹ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገሮችን ገጥመው ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸው ከፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ጋር የመጫወት ልምድ ስላዳበረላቸው የሱዳንን ብሔራዊ ቡድን አግዘፈውም ይሁን አሳንሰው እንደማይመለከቱት አሠልጣኝ ሰውነት ተናግረዋል። «ከሱዳን አይደለም ከሶማሊያም ብንጫወት ልንደሰት አይገባም» ያሉት አሠልጣኝ ሰውነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ባለፉት ወደ ገጽ B2
ገጽ B2
የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ደንበኛ ይሁኑ በዓመት $38 ቤትዎ ድረስ 202 518 0245
B-2 ትላልቅ ተቋማት ሳይቀር የተያዘ ጥናት ነው። እዚህ ውስጥ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ተ ማ ሪ ዎ ች ል ጆ ቻ ች ን እንዴት ናቸው? ብዙዎቹ ኬጂ ና ሚድል ስኩል ላይ ደህና ቢሆኑም ሃይስኩል ላይ እየደከሙ ወይም እየጠሉት ያቋርጣሉ ። ምክንያቱም ልጆቹ ላይ ዝቅተኝነትን፣ የበታችነትን፣ በራስ አለመተማመንን የሚፈጥር ሲስተም አለ። ያ ከማንነት ጋር የተያያዘም ጭምር ነው። ስለዚህ ልጆቻችን ልበሙሉ እንዲሆኑ ማነጽ አለብን። ከትልቅ አገር እንደመጡ፣ ትልቅ ታሪክ፣ ትልቅ ማህበረሰብ እንዳላቸው፣ በሥራ ጭምር ልናሳያቸው ልናኮራቸው ያስፈልገናል። “ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት!” ማለት ብቻ አይበቃም። ኢትዮጵያዊነትን ካላሳደግን ኢትዮጵያዊነታችን ዋጋ አይኖረውም። ኢትዮጵያውያን የተሰደድነው ለልጆቻችንም ጭምር ነው። ወላጆች የተከበረ ሥራና ኑሯቸውን ለልጆቻቸው ሲሉ ትተው ይመጣሉ። ልጆቻቸው የተሟላ ኑሮ እንዲኖራቸው ይመኛሉ። ልጆቻችንን አሜሪካን አገር እንዲመጡ ስናደርግ የሰጠናቸው ማቴሪያል ነገር ብቻ ከሆነ ግን ችግር ነው። ባህላዊ ማንነት ያስፈልጋቸዋል። አቺቭመንት ጋፑን ክፍተቱን መዋጋት የምንችለው በዚህ ነው። ካለበለዚያ ማቴሪያል ነገር ብቻ እንዲያሟሉ የምንጥር ከሆነ እንቸገራለን። እንዲያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ጥሩ ዜጋ ሆነው ማደግ የሚችሉ ልጆችን አውጥተን ልናሰናክላቸው እንችላለን። ሁለትና ሶስት ሥራ እየሠራን፣ እነሱን ቤት ትተን ምንድነው የፈጠርነው? ቆም ብለን ማሰብ አለብን። በአጠቃላይ አሁን ፀሎትቻን ይህ ነው ማለት ነው። መቸም በረጅም ጊዜ አደርጋለሁ እያልኩ አሁን የማወራህ ፀሎቴን ነው ማለት ትችላለህ። አቶ ጥበበ ዓይናቸውን ጨፍነው ብቻ የሚጸልዩ ሰው ግን አይደሉም ገልጠው የሚሠሯቸው ነገሮች አሉ። ከዚያ ውስጥ በሜሪላንድ ዳውን ታወን ሲልቨር ስፕሪንግ ማዘጋጀት የጀመሩት ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል በሳቸው አጠራር “ክበረ በዓል” እና የተባረከ ቡና Blessed Coffee የሚሉት ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሳራ ጋር ቀደም ብለው የጀመሩት የቡና ፕሮጀክት አላቸው። ፕሮጀክቱ ለዋይት ሐዉሱ እውቅና ያበቃቸውና “የለውጥ ሰው” ሻሚዮን ኦፍ ቼንጅ ያሰኛቸው ነው። አምራችና ተጠቃሚውን በቀጥታ የማገናኘት፣ በመካከል ያለውን ረጅም ሰንሰለት በማሰወገድ ተገቢና ጤናማ የገበያ ግንኙነት ለመፍጠር የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እየሠሩ ነው።
“ሲልቨር ስፕሪንግ ወደፊት የኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ትሆናለች!”
Champion of Change
ለውጥ አምጪው ጥበበ አሰፋ! ኢትዮጵያዊው አቶ ጥበቡ አሰፋ፣ ባለፈው ጃንዋሪ 30/2012 ዋይት ሐውስ ፣ ለውጥ አምጪዎች (Champion of Change) ብሎ ከሰየማቸው 15 የምስራቅ አፍሪካ ተወላጅ ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው። ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሳራ ሙሴ ጋር በሜሪላንድ “የተባረከ ቡና” በሚል ያቋቁምትን ድርጅት እየመሩ ነው። በሜሪላንድ የገቨርነሩ የአፍሪካ ኮሙዪኒቲ አማካሪ ናቸው። በቶኮማ ፓርክ ኮሙዪኒቲ አክሽን ግሩፕ ውስጥም በኮሙኒኬሽን ዳይሬክተርነት (Takoma park community action group communications director) እያገለገሉ ነው። ባለፈው ዓመት ወደ 12ሺ ሰው ተገኝቶበታል በተባለለት የሜሪላንዱ የዳወን ታወን ሲልቨር ስፕሪንግ የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል ከአቶ ሸዋ ኢታናና ከሌሎች 26 ከሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ አሜሪካውያን ጋር አዘጋጅተዋል። አሁን ጁላይ 22 በሲልቨር ስፕሪንግ እዚያው ቦታው ላይ ለሚካሄደው ሁለተኛው ዓመታዊ ፌስቲቫልም እየተዘጋጁ ነው። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አንዱ መገለጫ ስለሆነው ቡና እና አምራቹ ገበሬም በሥራ የተደገፈ ልዩ ራእይ አላቸው። ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ አነጋግሯቸዋል። ራዕይ አቶ ጥበበ ሥራና እንቅስቃሴዎቻቸው ሁለት የቅርብና የሩቅ ግቦች እንዳሏቸው ከዘኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የቅርቡን እንዲህ ገልጸውታል። በአሜሪካውን ዘንድ እኛ የተቀረጽነው ቀድሞን በቆየው ገጽታ ነው። ስለኛ ያላቸው አመለካካት ቀደም ሲል በሚዲያው ተቀርጿል። እኛ መጥተን አንዳንድ ነገሮችን ከመሞከራችን በፊት ገጽታችን የጦርነት የረሀብ ሆኖ ቆይቷል። በሳቸው አገላለጽ እኛ ስለራሳችን ያለን፣ እውነቱና ሌሎች/አሜሪካውያን ስለኛ ባላቸው አመለካከት መካከል ልዩነት አለ። ያ ልዩነት ክፍተት/ ጉድለት ያሳያል። ያ ጉድለት መለወጥ አለበት። አንድን ጉስቁል አካባቢ (ghetto)
ብቻ ወስዶ አሜሪካንን በዚያ ዓይን ብቻ ተመልክቶ ይህንን ትመስላለች እንደማለት ነው። የኢትዮጵያም ሆነ የኢትዮጵያውያ መልካችን እንደዚህ አይደለም። ትክክለኛና የተሟላ መልካችንን ማሳየት ያስፈልጋል። በዚያ ላይ እዚህ ያለነው ስደተኞች እንደ ግለሰብ ነው የምንታወቀው። እንደ ህብረተሰብ ገና በሚገባ አንታወቅም። ምክንያቱም እስካሁን የምናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ በራሳችን ለራሳችን ብቻ ታጥሮ የቀረ ይመስለኛል። የራሳችን ኮሙዩኒቲ ሴንተር፣ የራሳችን የሆነ ምግብ ቤት፣ የራሳችን ...እያልን በራሳችን ክልልና አኗናር ታጥረናል። ከዚያ ወጥተን ከሌላው ጋር መቀላቀል ገጽታችንን ማስተካከል፣ መታወቅ ራሳችንን ማስተዋወቅ ይኖርብናል። በግል ብቻ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ መታወቅ አለብን። በዓለም ገበያዎች በዓለም መድረኮች ብቅ አላልንም የዓለም መድረክ ላይ አልወጣንም። ይህን ለማድረግ በተደራጀ መልኩ “የኢሜጅ ግንባታ” ያስፈልገናል። በግልባጩ ስላለው ሌላኛው የቅርብ ጊዜ ዓላማቸውም ጥበበ ሲገልጹ ኢትዮጵውያን ወሳጅና ተጠቃሚ ብቻ ሳንሆን ሰጪና ባለ አስተዋጽኦ መሆናችንን ማሳየት ነው። እዚህ መጥተን በግለሰብም በማህበረሰብም ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን። የደከመ ሰፈር እናነሳለን፣ የቆሸሸ ሠፈር እናጸዳለን፣ የተዘነጋ ሠፈር እናድሳለን፣ በሬስቶራንቱ፣ በህግ፣ በሳተላይት ሬድዮ ሳይቀር በመሥራት በዓለም የቴክኖሎጂ አደባባይ ሳይቀር ተሳታፊ ሆነናል። የሳተላይት ሬዲዮን ያስተዋወቀው (አቶ
ኖህ ሰማራ) ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ ከቡና እስከ ሳተላይት ተዋናይ ነን። ። ያንን እኛም ህዝቡም አናውቀውም። እዚህ አገር ስንኖር ዋጋችንን ማሳወቅ ይኖርብናል። ለምሳሌ አንድ ቻይናዊና አንድ ኢትዮጵያዊ መንገድ ላይ ቢታዩና ዋጋ ይሰጣቸው ቢባል የተለያዩ ዋጋ ነው ያላቸው። ያንን መቀየር አለብን። እኛ ከወሰደነው በላይ የምንሰጥ መሆናችንን ማወቅ ይኖርባቸዋል። የዜግነት ዋጋችንን ማወቅ አለባቸው። ደራሲያን፣ የህግ ባለሙያዎች፣ መንግሥታዊ ተቋማትም፣ ሚዲያውም፣ ህዝብም እንዲያውቁን ስለኛ እንዲናገሩ ማድረግ አለብን። 2ኛው ዓላማችን ባህላችንን አስከብሮ በዓለም መድረክ እንድንከበር ማድረግ ነው። አሜሪካውያን እኛ የነሱን ጂንስ እንደለበስን እነሱም የኛን ሸማ መልበስ አለባቸው። አሁን እንጀራ ይበላሉ። ነገ ደግሞ አዋዜያችንን በጠርሙስ ቤታቸው እንዲያስገቡት በር መክፈት ይኖርብናል። የአቶ ጥበቡ የሩቅ ጊዜው ትልማቸው ደግሞ የዜግነት ግንባታ ነው። በግል የሁለት ልጆች አባት ነኝ። ታኮማ ፓርክ ውስጥ በኮሙዪኒቲው ዙሪያ እሳተፋለሁ። በልጆች ዙሪያም የትምህርት ጉዳዮች ላይ ውይይት አለ። እሱን እከታተላለሁ። ለምሳሌ በልጆች መካከል የስኬት (ብቃት) መበላለጥ (Achievement Gap)የሚባል ነገር አለ። ያንድ ኮሪያዊ፣ የአንድ ነጭ፣ የአንድ ጥቁር ተማሪ ማርክ እንበለው ውጤት... (Achievement Gap) አንድ አይደለም። ለምን ተበላለጡ? ለዚያ መሠረታዊ ምክንያቱ ምንድነው? መፍትሔውስ? ይህ በሐርቫርድ ዩኒቨርስቲና በመሳሰሉት
የተባረከ ቡና ከኢትዮጵያ በ1976 ነው የወጣሁት። አውሮፓ ኖሬያለሁ። እዚህም ኖሬያለሁ።
የኢትዮጵያ ገበሬ፣ የአውሮፓን ገበሬ፣ የአሜሪካን ገበሬ አይቻለሁ። በጣም የሚደክመው የኢትዮጵያ ገበሬ ነው። እኔ ኢትዮጵያ እመላለሳለሁ። ስሄድ ገጠር ነው የምወርደው። እዚያ የማየው ነገር ያሰቅቀኛል። ለምሳሌ አንድ ቀን አንዱን አርሷ አደር የሥራ ጠባዩን ጠየቅኩት። በስንት ሰዓት ትወጣለህ? ስለው “ፀሐይ ስትወጣ!” አለኝ። ፀሐይ እስክትጠልቅ ይሠራል። የአሜሪካው ገበሬ ትንሽ ነው የሚሠራው። ምክንያቱም በዓለም ላይ መብታቸውን የሚያስጠብቅ ነገር አለ። ለኛ አርሶ አደር ግን የለም። ድካማቸው ከምንም ነገር በላይ ነው። እነሱ እዚያ እንደዚያ ያለ ችግር ላይ እያሉ እኔ እዚህ አሜሪካ መጥቼ ውስጤ ባዶነው... አሜሪካ የሚሰጥህ አንድ ቤትና ሁለት ቆርቆሮ መኪና ነው። ይህ ነገር ለወገኔ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ሁሌም ያሳስበኛል። ቡና የገበሬውን ህይወት መለወጥ የሚችል ቢሆንም በኢትዮጵያ ጉዳይ ግን አልሆነም። ለብዙ ዓመት ቡና እናመርታለን፤ የምናመርትበትም፣ ለገበያ የምናቀርብበትም መንገድ ግን ብዙም አልተለወጠም። እስካሁ ያልተቆላ ቡና ነው ለአለም የምንሸጠው፣ ቆልተን መሸጥ እንኳ አልቻልንም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ገበሬው የልፋቱን እያገኘ አይደለም። ለምሳሌ እንደ ስታር ባክስ ዓይነቱ የቡና ሻጭ ድርጅት አንድ ፓውንድ የተቆላ ቡና በ14 ዶላር ሲሸጥ ያንን ቡና ከገበሬው የሚገዛው በሶስት ወይም አራት ዶላር ነው። የኛ ገበሬ ያን ሁሉ ደክሞ በዓለም ገባያ ላይ የሚያገኘው ከሁለት ዶላር ያነሰ ነው። ያ ቡና ግን ተቆልቶና ታሽጎ ሲሸጥ ከ13 እስከ አስራ አምስት ዶላር ያወጣል። በስኒ ወይም በትንሽ መጠጫ ደግሞ ተፈልቶ ሲሰጥ ወደ ሁለት ሶስት መቶ ዶላር ይሆናል። ይህ ትክክለኛ የገበያ ሥርዓት አለመኖሩን ያሳያል። አሁን በዓለም ላይ ያለው ግብይት ሶስት ዓይነት ነው። በእነዚህ የግብይት ዓይነት ውስጥ በቡና አምራቹንና ተጠቃሚው መካከል ያለው የጥቅም ሰንሰለት ሚዛናዊነት መመልከት ይቻላል። ለምሳሌ የመጀመሪያው የገበያ ዓይነት ኮሞዲቲ ማርኬት -ይባላል። በዚህ ሥርዓት-- በገበሬውና በተጠቃሚው መካከል ከ6-8 ሰዎች አሉ። ሁለተኛው ፌር ትሬድ የሚባለው በመካል ያሉ ነጋዴዎች ትንሽ የተቀነሱበት ነው። በኢትዮጵያ በኩል ያለውን ትንሽ ቀንሰው ስጥተውታል። ሶስተኛው እኛ ቨርቹዋል ኤክስቼንጅ (virtual exchange) በማለት በአዲስ መልክ ፈጥረን የምናስተዋውቀው የገበያ ሥርዓት፣ ገበሬውን ኢንቨስተርም ነጋዴም ጭምር በማድረግ ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት ነው። ይህ ቡና አምራቹ ከተጠቃሚው ጋር በቀጥታና ቅርበት የሚገናኝበት መንገድን የሚያመቻች ብቻ ሳይሆን ራሱን ባለቤት የሚያደርግበት የግብይት ሥርዓት ነው። ስለሆነም ለዚህ ሥርዓት መሳካት እየሠራን ነው። ለምሳሌ የኦሮምያ ኮፊ ፋርመርስ ኮርፖሬሽን ዩኒየን የሚባል አለ። በኢንተርናሽናል ኮርፖሬት ህግ ወደ ገጽ B7
የአፍሪካ ዋንጫ...ከገጽ አንድ የዞረ የአፍሪካና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያዎች ላይ የነበራቸው መልካም የሥነ-ልቦና ዝግጅት በአሁኑ ጨዋታም ይጠቅመናል» ብለዋል። ወደ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመቶ ሰማኒያ ደቂቃ ጨዋታ ብቻ የቀረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በፈረንጆቹ ከመስከረም ሰባት እስከ ዘጠኝ ባሉት ቀናት ውስጥ ከሜዳው ውጪ ካርቱም ላይ ይጫወታል። የመልስ ጨዋታውንም ከጥቅምት አስራ ሁለት እስከ አስራ አራት ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ላይ ያካሂዳል። የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩንም አስረድተዋል። «እግር ኳስ የሕዝብ ነው» ያሉት አሠልጣኝ ሰውነት «ብሔራዊ ቡድኑ አሁን ለደረሰበት የተሻለ ደረጃ የሕዝቡ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል» በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የማጣሪያ ጨዋታው የምድብ ድልድል የምዕራብ አፍሪካዎቹን ጠንካራ ቡድኖች ኮትዲቯርና ሴኔጋልን አፋጥጧል። በዚህም ከደርሶ መልስ ጨዋታው በኋላ በአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ስም ካላቸው ኮትዲቯር ወይም ሴኔጋል አንድ ቡድን ወዳቂ ይሆናል። ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ያልተሳተፈችው ካሜሮን በእግር ኳስ ብዙም ከማትታወቀው ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላለች። ካሜሮን ማጣሪያውን አልፋ የደቡብ አፍሪካው ዋንጫ ላይ ተፎካካሪ ትሆናለች ተብሎም ግምት ተሰጥቷታል። የዘንድሮ ሻምፒዮና ዛምቢያም በማጣሪያ ጨዋታው ከኡጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ይጠበቅባታል። ፊፋ ከትናንት በስቲያ ባወጣው የደረጃ ሠንጠረዥ ከአፍሪካ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አልጄሪያና አራተኛ ላይ የተቀመጠችው ሊቢያ ተገናኝተዋል። ሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገሮች በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ለመሆን ቀላል የማይባል ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ተገምቷል። ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ጋና ሃያ አራተኛ ደረጃ ላይ ያለችውን ማላዊን ትገጥማለች አምስተኛ ደረጃ ላይ ያለችው ማሊ ደግሞ ከቦትስዋና ጋር ትገጥማለች። በአፍሪካ ዋንጫ መልካም ስም የነበራት ናይጄሪያም በማጣሪያው ላይቤሪያን አሸንፋ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ትመለሳለች ተብሎ ይጠበቃል። በአፍሪካ ዋንጫ ማራኪ ጨዋታ የሚያሳዩት የሰሜን አፍሪካዎቹ ሞሮኮና ቱኒዚያ ከሞዛምቢክና ሴራ ሊዮን ጋር ተደልድለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጥምር አዘጋጇ ጋቦን ከቶጐ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከዲሞክራቲከ ሪፐብሊክ ኮንጐ ጋር ይጫወታሉ። በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በኢትዮጰያ ሁለት ለዜሮ የተሸነፈችው መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ከኒጀር የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ለማድረግ ተደልድለዋል። (ምንጭ አዲስ ዘመን)
ሰላዲን ሰይድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፉት ግጥሚያዎቹ ካስቆጠራቸው 7 ግቦች 5ቱን ያስቆጠረው ሰላዲን ሰኢድ ነው። ሰላዲን የሚጫወተው ለአንድ የግብጽ ቡድን ሲሆን የቤንሻንጉል ተወላጅ ነው። እስካሁን ባሳየው ጫወታም የሊሎች አገሮች ክለቦች እየረፈበት መጥቶ ለበግዢ ዝውውር እስከመጠየቅ መድረሱም ተነግሯል። ፕሮፌሽናል ተጫዋች በመሆኑም ኢትዮጶያን በዓለም አቀፍ ውድድሮችና ውስጥ የማጣሪያ ግጥሚያዎችን እያለፈች ትንሽ እንድትሰነብት ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
B-3
English section
Will Smith, Jada Pinkett Smith Visit Ethiopia for Charity
Modern psychiatric hospital under construction The Ministry of Health said the construction of a modern mental hospital and research institute is well underway in Addis Ababa at a cost of 190 million birr.
Jada Pinkett and Will Smith receive gifts of gratitude from a village that will receive clean water from a charity: water project Courtesy of Charity: Water Talk about giving back for your birthday! Will Smith and Jada Pinkett Smith, who in 2010 used their birthdays to raise $109,000 for charity: water, a nonprofit organization which brings clean water to developing nations, have taken it one step further. The couple just visited Ethiopia with charity: water and inaugurated a clean well for a village of 400. Spotted smiling at
each other while receiving gifts from grateful villagers, the two witnessed the construction of a brand-new well in the Maego village, Tigray, and even manned the organizations new drilling rig, Yellow Thunder. The celebration for the new water supply was made complete when the Smiths danced and sang along with the community. Jada Pinkett Smith checks out charity: water’s brand new drilling rig, Yellow Thunder, before it drills it’s 31st well in Ethiopia. “Our trip to Ethiopia with charity: water
was an incredibly eyeopening and authentic experience,” said Smith in a statement. “It was extraordinary to meet and spend time with the people of Tigray and to see first-hand how clean water changes everything for these communities.” The Smiths raised more than $789,000 for charity: water by promising to take the top donors with them to Ethiopia. Ethiopia, the most populated landlocked country in the world, still has 50 million people who live without clean water. (charitywater.org. – Evan Lambert)
Public Relations Officer with Amanuel Specialized Mental Hospital, Aschalew Abayneh, said that the hospital will have 292 beds and will also provide outpatient service. Aschalew said the 110 million birr budget has been allocated for the construction of a psychiatric department, offices and the mental health institute which will be launched next year. Mekbib Abera, Project manager of Santa Maria Construction Company, which is constructing the hospital, said so far 53 percent of the hospital has been constructed and will become operational in 2006 E.C. (The Ethiopian Herald)
B4
Egypt’s new President Morsy to visit Ethiopia to discuss Nile wate Agreements
delegation at the African Summit on 15 and 16 July. Ambassador Mona Omar, assistant foreign minister for African affairs, stressed the importance of Morsy’s participation in the next African Summit. President Morsy’s participation at the summit is a message to Africa and the world, stating that Egypt, in the era of the [second] presidency, intends to play an influential and active role in all African issues,” the ambassador told Al-Masry Al-Youm.
President Mohamed Morsy will visit Addis Ababa, the capital of Ethiopia, following his visit to Saudi Arabia on Wednesday, according to Al-Masry AlYoum. It will be his second visit to a foreign country as president. Morsy will visit as the head of Egypt’s
It will be the first time an Egyptian president has participated in an African summit in Addis Ababa since a failed assassination attempt on former President Hosni Mubarak in 1995, and the first since the African Union was replaced by the Organization of African Unity. According to Omar, the president is expected to
B4
B-4 Assegid Habtewold [Dr.] is the author of Redefining Leadership: Navigating the Path from Birthright to Fulfillment in Life. He is also the Lead Consultant, Coach, and Facilitator at Success Pathways, LLC.
Assegid Habtewold [Dr.]
Living each day with a sense of urgency When it comes to time management, there are three kinds of people: a) Those who abuse time as if they live forever, b) Those that live with a sense of urgency, and c) Those in between. I have been in these categories at some points in my life. What about you? In which category do you find yourself in this season of your life? Time is one of the scarce resources in this world and how we spend it determines our status in life now, and most importantly in the future. Paradoxically, whether we are rich or poor, educated or illiterate, known or obscure, we all have equal amount of time per day. If we lose the time we have today, we lose it forever. No rich, title, money or recognition can buy us back a fraction of second we have already spent. On the other hand, if we lose our money, friendship, or health, we may get it back. That is not the case when it comes to time. Time is nonrenewable. That is why we need to enter into a sense of urgency to use our time on a daily basis wisely, effectively, consciously, and by pursuing those important things in our life, for which we care deeply. We should also know that there is a direct correlation between using time efficiently and success. Successful people live with a sense of urgency and as if each day is their last. Accordingly, they allocate the chunk of their best time towards the accomplishment of those things they care the most. They don’t just make the time available though; they maximize it by investing their scarce resources. Not only that, they remain continuously aligned with those main things closer to their heart and exploit the time they have now and today regardless of so many distractions they may face every now and then, especially in this information age. Unfortunately, we don’t find many people living each day with a sense of time. The majority of us fail to adopt this lifestyle and remain there for a very long period of time. There are, at least, three compounding factors that may disallow us from living each day with a sense of emergency and at the end of the day deny many of us success, significance, and most importantly fulfillment in life. These triads include but not limited to 1) Preoccupying ourselves with the past in the expense of the moment at hand; talking, celebrating, or complaining about the past takes the majority of our time, focus, and energy. 2) Procrastination. By waiting too long until pursuing those crucial things in our life becomes too late or impossible. We pause or slow down today for better days ahead. 3) Skepticism about the future. Some people have a very gloomy picture about the future that they forsake making each day count. Martin Luther disagrees when he said: “Even if I knew that tomorrow the world would go to pieces, I would still plant my apple tree.” In conclusion, you might have made quality decisions and equipped with the necessary skills to turn things around. You may still need a sense of urgency to experience a breakthrough. The journey from where you are now to where you want to arrive will be fueled and ultimately shortened when you enter into a sense of urgency. Yet, you should be cautious not to enter into a state of pseudo sense of urgency. For instance, sense of urgency doesn’t mean, we do things with a fast pace and all the time, without rest, and by ignoring some important tasks such as learning and growing on a daily basis. It doesn’t mean also that we avoid our obligations in serving our communities, churches, nations, and undermine other important aspects of our life such as our relationships, health, spirituality, and social life.
Ethiopian Airlines Targets August for Dreamliner Delivery Ethiopian Airlines (Ethiopian), which has been the flag carrier for Ethiopia for the past 65 years, has announced that it could take delivery of its first Dreamliner aircraft in August. The airline said that the craft would enhance its business in the region. The Dreamliner has been configured to carry 246 economy-class customers and 24 business-class customers. It is expected that the new aircraft will cement the airline’s position as one of the leading aircraft carriers in Ethiopia. Even though the initial launch of the Dreamliner craft was expected in June, its delivery had been delayed until August. The aircraft could be used to connect Johannesburg and Dubai, as previously announced.
The 787 Dreamliner is claimed to offer customers a better flying experience. For the company, acquiring the craft will mean greater efficiency to serve its point-to-point routes. It will also be able to increase its frequency of preferred and popular routes. The 787 Dreamliner claims to use 20 percent less fuel than most modern airplanes of comparable size. It also offers 45 percent more cargo revenue capacity. Other customer-centric features include a better interior environment, larger windows, better lighting, more storage space and other conveniences. The company has so far ordered ten B787 Dreamliners. (travel news)
Egypt’s...
(From Page B1)
hold bilateral meetings with many African leaders at the summit, including Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi. She pointed out that after the of the 25 January revolution, Zenawi announced the signing of the Entebbe Agreement, which
would govern the division of Nile water, would be postponed until a new president is elected in Egypt. The agreement was signed by six Nile Basin countries, but rejected by Egypt and Sudan.
Zenawi is a sign of Cairo’s genuine desire to reach out to Addis Ababa for closer cooperation in all fields. She said Cairo is seeking a compromise with all Nile Basin countries for the benefit of everyone.
Omar said the meeting between Morsy and
Supporting Stability, Abetting Repression By TOBIAS HAGMANN BERKELEY, CALIFORNIA NEY YORK TIMES
I wrote a policy report on Ethiopia’s difficulties with federalism. I gave a talk in which I questioned Ethiopia’s May 2010 elections, in which the ruling EPRDF party (Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front) won 545 out of 547 seats in the Parliament. As part of my ongoing research on mass violence in the Somali territories, I interviewed members of the Ogaden National Liberation Front, a separatist rebel group in eastern Ethiopia that the government has designated as a terrorist organization. In the eyes of the government of Prime Minister Meles Zenawi, my work is tantamount to subversion. Not only do his officials have zero tolerance for criticism, they consider people who either talk to or write about the opposition as abetting terrorists. In recent years the government has effectively silenced opposition parties, human rights organizations, journalists and researchers. On June 27 a federal court convicted the journalist Eskinder Nega and 23 opposition politicians for “participation in a terrorist organization.” More than 10 other journalists have been charged under an antiterrorism law introduced in 2009. Among them are two
Swedes, Martin Schibbye and Johan Persson, who are serving an 11-year prison sentence in Ethiopia. Hundreds of opposition supporters languish in prisons for exercising the very democratic rights that the Ethiopian Constitution nominally protects. Most people outside Ethiopia associate the country with famine and poverty. They know little about the country’s history and politics — for example that Ethiopia was never colonized, or that it has Africa’s second biggest population. Nor are they aware that Ethiopia is a darling of the donor community, receiving more aid than any other African country. Over the past year alone, the U.S. Agency for International Development has given Ethiopia $675 million in aid. The United States closely collaborates with Ethiopia in covert missions against radical Islamists in neighboring Somalia. Much of this support comes from the portrayal of Ethiopia as a strong and stable government in a region riddled with political upheaval. The problem, however, is that
Ethiopia is plagued by too much state control. When EPRDF came to power in 1991, it promised to democratize the country. Two decades later the party has a tight grip on all public institutions, from the capital to remote villages. Formally a federal democracy, Ethiopia is a highly centralized one-party state. No independent media, judiciary, opposition parties or civil society to speak of exist in today’s Ethiopia. Many of the country’s businesses are affiliated with the ruling party. Most Ethiopians do not dare to discuss politics for fear of harassment by local officials. As I found out in dozens of interviews with Ethiopian Somalis, security forces indiscriminately kill, imprison and torture civilians whom they suspect of aiding Ogaden rebels. How have donors who fund about one third of Ethiopia’s budget and many humanitarian programs reacted to this? They haven’t. They not only continue to support the Ethiopian government but in recent years have increased their aid. The West, most
prominently the United States and the European Union, have concluded a strange pact with Meles Zenawi: So long as his government produces statistics that evince economic growth, they are willing to fund his regime — whatever its human rights abuses. This policy is wrong, shortsighted and counterproductive. It is wrong because billions in Western tax money are spent to support an authoritarian regime. It is shortsighted because it ignores the fact that the absence of basic rights and freedoms is one of the reasons Ethiopians are so poor. It is counterproductive because many Ethiopians resent the unconditional aid and recognition given to their rulers. In Ethiopia — and also in Rwanda and Uganda — the West is once again making the mistake of rewarding stability and growth while closing its eyes to repression. Tobias Hagmann specializes in East African politics. He is a visiting scholar at the Department of Political Science at the University of California at Berkeley
Zethiopia Newspaper 202-518-0245
B-5
Opinion The People Always Support A Dictator In every age and in every country, the people of every nation have always supported a dictator. Ludwig Von Mises
By Henock Y. Tessemma
But Ethiopia: A Curse of Disunity? Why?
Arguably one of the only two institutions that nearly all Ethiopians seem to agree on—Ethiopian Soccer Federation North America (ESFNA)—is faced with an existential threat from within. (The other institution, by the way, in my opinion, is Ethiopian Airlines.) While it appears that the 29-yearold federation has weathered the storm, the danger it had faced—and continues to face—is not something to be taken lightly. Far from it! A splinter group bankrolled by a worldrenowned billionaire who spent more than $2 million on just advertisement of a week’s event; promoters that were “persuasive” enough to make many prominent Ethiopian entertainers to join the breakaway despite the devastating stigma attached to it; organizers (former insiders) that were hell-bent on making their patron, Sheik Al-Amoudi, happy—if this is not an existential threat to the popular federation, I don’t know what is.
Yes, the Al-Amoudi-sponsored one-week event held last week simultaneously with the original federation (it was able to retain its label by a court order) was a simply a financial and public-relations disaster. True, the splinter festival held at RFK stadium is probably the first soccer tournament to have players the participating teams as almost the only spectators. But that does not make it any less formidable. A matter of Principle? The major reason for the division among the executive members of the soccer federation was reported to have been a disagreement over “rules and principles” of the federation. The runaway group ferociously objected to the idea that prominent opposition figure Birtukan Mideksa would be a guest of honor on the last year’s annual festival in the honorable belief that the federation should not get involved in politics. I could have taken my hat of a million times to these guys for their integrity if I had not come to be convinced lately that they have been on Al-Amoudi’s payroll all along. Why would any self-respecting person who takes a firm stand on the grounds of principle end up doing something that brazenly and outrageously negates that very principle? Well, this is exactly the Al-Amoudi faction did: they started with protesting against the “politicization” of the federation, and, guess what; they ended up trying not just to politicize the federation, but also actively engaging in a fifth-column activity by trying to divide the entire Ethiopian community in North America and Europe in the name of unity. What Next? There is no doubt on my mind that the runaway group will leave no stone unturned to destroy the federation. And they have all the necessary resources available to them, thanks to Al-Amoudi. But, fortunately, money or other resources usually backfire when they are used to disrespect and patronize Ethiopians. The Ethio-Saudi billionaire is a living testimony in that regard. Meles Zenawi and his henchmen are obviously doing everything in their power to control every Ethiopian living everywhere. Let’s hope that they won’t succeed outside of Ethiopia. Let’s hope that the spirit that kept the federation going for the past three decades will continue to prevail.
RETAIL SPACE FOR LEASE BUILDAMERICASKYLINE SHOPPING CENTER RETAIL SPACE FOR LEASE 3825- J South George Mason Drive, Falls Church, VA
1200 SQ.FT. $3,500/MO. Require Good Financial Statement
George Chaplin, Broker GCHAPLIN2@gmail.com
703-938-1566
But why? Why is it that people have always given up everything they have to bow to the king and kiss his ring? Why do people love supporting dictators and giving away their power? This is a very big topic and I it can be answered many ways. Here is one take on it: When nations are founded they are usually founded by just a small group of people of high integrity and intelligence - just a small clique who is interested in the pursuit of truth and development. This group inevitably helps others by creating a prosperous body that others may be able to benefit from, although these others may not necessarily coincide with or agree with the views of the founders. They were never part of the group of hard working and dedicated individuals that created this opportunity for them. Look at the American Revolutionary War, only 3% of Americans actually got up and
fought for America - the rest simply stayed home and watched basketball, so to speak. It has been this way for a long time and will most likely continue to be this way for a long time. And because of this we are going to always experience the tearing of a lesser energy sucking from that of a greater energy. With all great civilizations you have a small nucleus of energy at the heart of the formation, a few people that represent the pinnacle of human development, and this group creates a huge stir in the world as it creates the new development. Unfortunately, there are but few great men in the world and as a result nobody is able to sustain this high level of moral, integrity and wisdom. Slowly but surely we experience the sucking of the lesser taking from the greater. And such is the cycle of life. Majority of people can’t and don’t want to take care of themselves. Self-responsibility is foreign to their character. They don’t want to develop their spiritual, emotional or even physical wellbeing. They want to engage their senses in whatever impulse strikes them.
Couple this with a small group of extremely intelligent people who want nothing more than power and you have all the ingredients needed for a dictatorship: Many stupid, lawless, apathetic people ready to support the every whim of the king and his aristocratic pupils. The king is able to afford all his luxuries and maintain his control by the expenditure of the people working to support their dictator. They are too consumed by daily life that they can never emerge or figure out how to grow past their paradigm of complete servitude. And dictators will do well to support the debauchery and vice practiced by his serfs as they dig their grave deeper each day, never for a minute suspecting that they’ve been had. I say these things in light of the United States of America and the decline that we have seen. We are just about reaching our end and as I look back and study history I can see how it happened, why it happened and who was involved in making it happen. I find it interesting that it is normal for people to make decisions that are almost completely
the opposite of what the American Constitution says. We love Independence Day, but don’t understand the premise of the Declaration of Independence declaring independence from the King. People have totally accepted the complete reversal of almost everything as a result of ignorance and apathy. They have accepted their own demise and are eagerly supporting it more and more on a daily basis - with high praise. It’s like a sucking spiral spinning to the depths of hell and the people are loving every minute of the ride. They can’t get enough of giving their money to criminals, destroying families, killing people, educating people on fallacies and denying God. So why do people support a dictator? Because they have weaknesses that they are on this earth to help mend. But the king knows this and will do well to exploit such weaknesses and use these against the people for his own gain. And so this is the cycle of dictators ruling the world and the people loving it. (This article was originally published
Husband charged with running over wife and daughter pleads guilty, gets 20 years HOUSTON – A man who ran over his wife and daughter following a domestic dispute last year was sentenced to 20 years in prison Tuesday after pleading guilty to the crime. It happened June 9, 2011 at the Westward Square Apartments on Gulfton, across the street from Benevidas Elementary School. Witnesses said the couple was arguing around 2:30 p.m. when Tamiru Etana Gillede left the complex, but came back and drove up on a Dama Ethiopian Restaurant & Bakery 1505 Columbia Pike Arlington, VA 22204 Tel (703) 920-5620 Phone (703) 920-3559
sidewalk, striking the woman and child. The 10-year-old daughter, identified as Dibora Kasaye, was rushed to Memorial Hermann Hospital with severe head injuries. The wife, 29-year-old Alemestayhey Kasaye, was taken to Memorial Hermann Southwest Hospital with a broken jaw and other injuries. Gillede had been charged with aggravated assault and injury to a child.
202- 518- 0245
ሸገር ገበያ (New Hampshire Ave. እና East-West Hwy መጋጠሚያ ላይ ይገኛል መደብራችን ከጠዋቱ 8:00 AM ጀምሮ ክፍት መሆኑን በትህትና እንገልጻለን
የምግብ ራሽን Food Stamp መቀበል ጀምረናል በመንስተንግዷችን ይረካሉ እናመሰግናለን - ሸገር ገበያ 912 East-West Hwy, Takoma Park MD 20912
301-270-0200
B-6 not both sides, all sides!
Subscription Form
Subscribe today & get your copy of Zethiopia delivered to your doorsteps Yes I would like to subscribe, a year subscription for only $38 Name:
Date: City/State/Zip:
Phone:
10 Years of Excellence
Address: Email:
Amount paid/enclosed $___________ Mail to P.O.Box 2049 Fairfax, VA 22031. Tel: (202) 518-0245 email: dereje@zethiopia.com Please, do not mail cash. Make checks payable to Zethiopia. Zethiopia is a free newspaper & your payment is only needed for shipping & handling. Thank you for your interest in Zethiopia. for office use only
Start issue :
www.zethiopia.com
not both sides, all sides!
Harambe Travel
Subscription Form
for the best rate opitons
Subscribe today & get your copy of Zethiopia delivered to your doorsteps Yes I would like to subscribe, a year subscription for only $38
Ethiopian’s Date: new 787 Dremliner is coming this summer
Name: Address:
fly
City/State/Zip:
Phone:
Email:
Non Stop flight from Wahsington to ADDIS
Amount paid/enclosed $___________ Mail to P.O.Box 2049 Fairfax, VA 22031. Tel: (202) 518-0245 email: dereje@zethiopia.com Please, do not mail cash. Make checks payable to Zethiopia. Zethiopia is a free newspaper & your payment is only needed for shipping & handling. Thank you for your interest in Zethiopia. for office use only
Start issue :
3919 D S.George Mason Dr.
www.zethiopia.com
Falls Church, VA 22041 Next to Skyline Restaurant Tel 703 931 2700 Fax 703-931-3248
Addis Ababa,Ethiopia Olympia Road Tel 00114-668515 00114-668393
B-7 አሜሪካ ውስጥ የራሳችንን ኢትዮጵያ ፈጥረን ነው የምንኖረው። የራሳችን የሲቪክ፣ የራሳችን የሶሻል ኤንድ ካልቸራል ስፔስ የራሳችን ቢዝነስና ኢክኖሚክ ስፔስ አለን ወደ አሜሪካ አልገባንም። አሜሪካ ትልቅ፣ ሜዳው ሰፊ ነው። አቶ ጥበቡ አሰፋ
ሲልቨር ስፕሪንግ ወደፊት የኢትዮጵያውያን... የተደራጀ አካል ነው። በዓለም ይታወቃል። ከነሱ ጋር በመሠረተ ሀሳብ ደረጃ ስምምነት ተፈራርመን በጋራ የምንሠራበትን መንገድ እያመቻቸንና ሁኔታዎችን እየተጠባበቅን ነው። ሀሳቡ እነሱ ኢንቨስት አድርገው የ50 ከመቶው ባለቤት እንዲሆኑ ነው። በዩኒየኑ የታቀፈ አንድ ገበሬ፣ በዓመት የሶስት ዶላር ቡና እያዋጣ፣ ለሶስት ዓመት ኢንቨስት ቢያደርግ፣ የ200 ሺው ገበሬ 1.8 ሚሊዮን ዶላር ይሆናል። ይህን አስረድተን ግብዣውን አቅርበንላቸዋል። ስለዚህ ገበሬውን ኢንቨስተር አድርጎ ተሳታፊ የማድረግ ራዕይ ይዘን እየሰራን ነው። አሁን የነሱን ቡና በፌር ትሬድ ዋጋ እየገዛን እያስተዋወቅን ነው። ምክንያቱም የነሱም ሆነ የኛ የመሸጥ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የተጠቃሚውም ቡናውን ወዶ መግዛት ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ቡናው የተለየ መሆኑን፣ ደረጃውን ጣዕሙን የጠበቀ ቡና መሆኑን፣ ከዚያም በላይ ገበሬውን የመደገፍ ዓላማው ያላው መሆኑን ሁሉ እየገለጹ ፣ ሰፊ የማስተዋወቅ ሥራ መሥራትን ይጠይቃል። አሁን በተለይ በሲልቨር ስፕሪንግና በታኮማ ፓርክ አካባቢ ያሉት አሜሪካውያን በሚገባ ያውቁታል። ቡናውን ቆልተን፣ ፈጭተን፣ ጣዕምና መዓዛውን አስለምደናቸዋል። ወደፊትም ማድረግ የምንፈልገው ይህንኑ ሥራ ለማገዝ አሜሪካ ውስጥ፣ የገበሬውን አኗኗር በትክክል በሚያሳይ መልኩ ፣ የአብነት (ሞዴል የሚሆኑ) ጎጆ ቤቶችን በያንዳንዱ ከተማ እየሠራን እንደ ስታር ባክስ ቡናችንን ፍራንቻይዝ ለማድረግ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ገበሬዎችና ተጠቃሚዎች በቅርበት ይገናኛሉ። መሃል ላይ ያሉት የጥቅም ሰንሰለቶች ከመሃል ይወጣሉ። ቢዝነስንና በጎ አድራጎትን ባጣመርንበትና ለጥምረቱ ከሜሪላንድ መንግሥት ልዩ የኮርፖሬት ፈቃድ (Benefit Corporation a public corporation chartered and produce public benefit as well as profit) ባገኝንበት በዚህ አዲስ የለውጥ ሞዴላችን የገበሬዎቻችን ህይወት ይለወጣል ብለን ተስፋ አድርገናል። የተባረከ ቡና ማለታችንም ለዚህ ነው።
ከገጽ 2 የዞረ
“ክብረ በዓል!” እኔ አሜሪካም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ኖሪያለሁ። የሁለቱ ልዩነት ይገባኛል። እዚህ ባለሁበት ሜሪላንድ የታኮማ ኮሙዪኒቲው ውስጥ ትንሽ ስለምንቀሳቀስ እውቅና አለኝ። በኛ ኮሙዪኒቲ ውስጥ ግን ብዙም አልታወቅም። ስለኮሙዪኒቲያችንም ያለኝ እውቀት ትንሽ ነው። ባለሁበት የአሜሪካ ኮሙዪኒቲ ግን ትንሽ ቦታና ተሳትፎ አለኝ ብዬ አስባለሁ። እዚያ ያገኘሁትን ልምድና እውቀት ወደ ኮሙዩኒቲዬ ለማምጣት ነው ጥረቴ። ልምድም ብቻ ሳይሆን የአሜሪካኖቹን ተመሳሳይ ድርጅቶች ሪሶርስ አምጥተናል። ስለዚህ ያገሬን ችግር ባውቅም ፖለቲካውን ብዙ አላውቀውም። ከሩቅ ነው ብዙውን ነገር የማየው። እኔን የሚገባኝ የዚህ አገሩ ዓይነት ፖለቲካ ነው። መሬት የያዘ!
ካለብን (image deficit) ትልቅ ሥራ መሥራት አለብን። ያኔ እንከበራለን! የሲልቨር ስፕሪንጉን ዓመታዊ ፌስቲቫል የምናደርገውም ለዚህ ነው። “ክበረ በዓል” ብለነዋል። ኢትዮጵያውያን የሚከበሩበት ልጆቻችን የሚኮሩበት እንዲሆን መጀመሪያ ኢትዮጵያ መከበር አለባት። ለዚያ ክብር አዲስ ኢትዮጵያ መወለድ አለባት። የኢትዮጵያን ልደት ለማክበር ደግሞ እኛ ወላጆች መሆን አለብን። ስለሆነም የዚህ በዓል ዓላማ ሁለት ነው። 1ኛ የኢትዮጵያን ባህልና ገጽታ በዓለም መድረክ ላይ አክብሮ ማስከበር፣ 2ኛ የልጆቻችን አሜሪካዊነት በጠንካራ ኢትዮጵያዊነት ላይ እንዲገነባ ለማድረግ ነው። ይህን ለማድረግ ባለፈው ዓመት በሲልቨር ስፕሪንግ ያደረግነውን በዓል ጨምሮ በርካታ ሙከራዎችን አድርገናል። በዚያም ውጤት
የህዝቡ ትብብር ያም ሆኖ ግን ውጤቱና የህዝቡ ትብብር አስደሳችና አበረታች ነበር። ባለፈው ዓመት 28 በጎ ፈቃደኞች (ቮለንቲሮች) ነጭና ጥቁር አሜሪካውን፣ ኤሽያኖችና የመሳሰሉት የተለያዩ አገር ዜጎች “ፍሬንድስ ኦፍ ኢትዮጵያ” (friends of Ethiopia) የሚል ቲሸርት ለብሰው ተባብረውናል። ህዝባችን ያሳየው ሰላማዊነትና ጨዋነት የሚገርም ነበር። የማንትገመሪ ፖሊሲ ስለበዓሉ ትብብር ስንጠይቅ፣ 5ሺ ኢትዮጵያዊ ይመጣል ስንለው ደግንጦ ነበር። እንደዚያ ከሆነማ ረብሻ ይኖራል ብለው በመስጋት ተጨማሪ ፖሊስና ጭማሪ ክፍያ ያስፈልጋል ብሎ ነበር። ኢትዮጵያውያን እንደዚያ አለመሆናቸውን በልበ ሙሉነት ገለጥኩላቸው። እንደተባለውም 10ሺ ኢትዮጵያዊ በዚያች በጠበበች ቦታ ምንም
የገበሬዎቹ ህብረት! የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኘው ቡና፣ ለቡና አምራች ገበሬዎች ተገቢውን ጥቅም እንዲያስገኝ ጥረት ከሚያደርጉት መካከል በ1991 ግንቦት ወር የተመሠረተው የኦሮሚያ ቡና አምራች ገበሬዎች ኅብረት ሥራ “ዩኒየን” አንዱ ነው። ዩኒየኑ በ34 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲመሠረት ወደ 22ሺ 503 የሚሆኑ አባላት 825 ሺ ብር የመነሻ ካፒታል እንደነበሩት ዘገባዎች ያመለክታሉ። በ1993 ለመጀመሪያ ጊዜ ቡናን መላክ በመጀመሩ፣ ዛሬ እያንዳንዳቸው ከ1ሺ ያላነሰ አባልና በድምሩ ደግሞ ከ190ሺ አባላት በላይ ያላቸው 197 ማኅበራትን ይዟል። ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከዩኒየኑ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ ከ95 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አለው። እስከ 10 ሺ ቶን የሚይዙ የቡና መጋዘኖችን ከ71 ሚሊዮን በላይ የወጣባቸው የቡና መፈልፈያ አለው። ለአባላቱና የአካባቢው ህዝብ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ማእከላትን በመገንባት፣ የመጠጥ ውሃ የመሳሰሉ ከ150 በላይ ፕሮጀክቶችን አስፋፍቷል። ገበሬው የድካሙ ተጠቃሚ ሆኖ በቂ ገቢ እንዲያገኝ፤ በዓለም ገበያ ራሱን ችሎ እንዲገባ ዓላማ ይዞ መነሳቱን የዚህ ዩንየን መስራቾች መካከል ግንባር ቀደሙ የሆኑት ሥራአስኪያጁ አቶ ታደሰ መሰቀሌ “Black Gold” በተባለው ዝነኛው ፊልማቸው ገልጸዋል። እንደ አቶ ጥበበ ገለጻ ያ ፊልምም ሆነ የአቶ ታደሰ ጥረት ግለሰቦች ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ያሳየ ነው። ዛሬ የለውጥ ጽንሰ ሀሳብ ሌላ መልክ መያዙን ጥበበ ተናግረዋል። “ ብዙ ነገሮች ላይ እንደ ዓለም ባንክና አይ ኤምፍ ከመሳሰሉት ትላልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት እስከ መንግሥታችን የሚደረጉት ጥረቶች አልተሳኩም (ፌል አድርገዋል)። ተቋማት ብዙም አልተሳካላቸውም። ድሮ ሰዎች ለልማትና ማህበራዊ ለውጥ የሚነሳሱት (Inspireድ የሚሆኑት) በድርጅትና በመሪ ወይም በአይዶሎጂና ፍልስፍና እየተገፋፉ ነበር። አሁን ተለውጧል። ምክንያቱም ምንም ለውጥ የለም። ሰዎች ዛሬ እነሱን ትተው ለትንናሽ ችግር ራሳቸውን አነሳስተው ትላልቅ ሥራ ይሠራሉ። መለወጥ የሚችሉትን ይለውጣሉ። ግራስ ሩት (grassroots) ማለት እሱ ነው። በአገራችንም ይህ ይታያል። ለምሳሌ ለዘመናት ስንሸጠው በኖርነው ቡና የታየው ይኸው ነው። እኛ የምንደግፋቸው እነ ታደሰ መስቀሌ የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። እነሱ በቡና ካደረጉት ሌላውም በሌላው ሊያደርገው ይችላል። በማር በበርበሬ በሽሮና በሌሎች በርካታ ነገሮች ለውጥ ማምጣት ይቻላል።ሰዎች በግል የራሳቸውን ህይወት ቀይረው አገራቸው ላይ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። እዚህ ኮሙዪኒቲያችን ላይ እዚያም አገራችን ላይ ማድረግ ያለብን ይህንን ነው። እንደ አቶ ጥበበ እምነት የቡናም ሆነ ሌሎች የንግድ መስኮቻችን ላይ የተሳካ ውጤት መምጣት የሚችለው የአገሪቱም ሆነ የማህበረሰባችን ገጽታ በዓለም አቀፍ መድረክ ሲሻሻል ነው። የዚህ የሲልቨር ስፕሪንግ “ክብረ በዓል” አንዱ መሠረታዊ ዓላማም እሱ ነው።
ሲልቨር ስፕሪንግ በተደረገው ያለፈው ዓመት ዝግጅት በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል። ለውጥ ከፈለግክ እሱን መከተል ይኖርብሃል። እዚህ አገር ሦስት ዓይነት የፖለቲካ መስክ ነው ያለው። ሲቪክ ስፔስ- የሚባለው የሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉት ነው። መብትህን የምታሰከብርበት፣ ዜግነትህን የምታረጋግጥበት፣ ሙያህን እውቀትና ልምድህን የምታበልጽገበት፣ ትውልድህን የምታንጽበት ነው። የመምረጥ መመረጥ መብታችንን አስከብረን የኛን መብት የሚያስጠብቁትን መምረጥ እንድችል የሚያስችለን ነው። ይህን ለማድረግ የተደራጀ ጥረትና ኮሙዪኒቲ ያስፈልጋል። “ሶሻል ኤንድ ካልቸራል ስፔስ” የሚሉት ሁለተኛው ነው። ይህ ባህልን ራስህን ማንነትህን በማስተዋወቅ የምታደርገው ጥረት ነው። ገጽታህን በማስተካከል በጎና አኩሪ መልክህን ታሳይበታለህ። አሜሪካን ዓለምን የገዛችን በሆሊውድ ነው። ስለዚህ እኛም በዓለም አደባባይ የሚያሳውቀንን መልካም ነገር ሁሉ ይዘን መቅረብ አለብን። ባህላችን፣ ታሪካችን፣ ስነጥበባችን፣ ትልቁ መሣሪያችን ነው። ያንን በታላቅ ኩራት ማሳየት ይኖርብናል። “ኢኮኖሚክ ስፔስ” የሚባለውም ሌላው የመጫወቻ መልክ ነው። በቢዝነስና በኢኮኖሚ ረገድ አቅምህን መገንባት ተደማጭነትህን ይጨምራል። የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም ገበያ ላይ በተወዳዳሪነት እንዲቀርቡና ራሳችንን ሐብታም አድርገን፣ አምራቹ ወገናችን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ መፍጠር ያስፈልገናል። የተባረከ ቡናንም ሆነን ቨርቹዋል ኤክስቼንጅን በማስተዋወቅ የምንንቀሳቀሰውም ይሄ እንደሚቻል በአርአያነት ለማሳየት ነው። ስለዚህ የኔ ፖለቲካ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ መጫወት ነው። የምሰራቸው የማምንባቸው ነገሮች በሙሉ በእነዚህ ሶስት ነገሮች ዙሪያ ያጠነጠኑ ናቸው። ሶስቱ የተጣመሩበት ወይም ከሶስት አንዱ እንኳ ጠንክረው የተሠሩበት ከሆነ ለውጥ ይኖራል። እንደኛ እዚህ አገር የሚኖረው ስደተኛ ማህበረሰብ እነዚህ ነገሮች ላይ ይጫወታል። እኛ ግን እንዳልኩህ አሜሪካ ውስጥ የራሳችንን ኢትዮጵያ ፈጥረን ነው የምንኖረው። የራሳችን የሲቪክ፣ የራሳችን የሶሻል ኤንድ ካልቸራል ስፔስ የራሳችን ቢዝነስና ኢክኖሚክ ስፔስ አለን ወደ አሜሪካ አልገባንም። አሜሪካ ትልቅ ሜዳው ሰፊ ነው በአሜሪካ አይሁዶቹ (ጁዎች) ጥቂት ሆነው 1 ሺ ሎቢስት ነው ያሰለፉት። እኛ 100ሺ ሆነን ብንሄድ የሚሰማን የለም። ምክንያቱም በቋሚነት የሚሰማ ጠንካራ የኮሚዪኒቲ መሠረት የለንም። ስለዚህ አንደመጥም። በየቀኑ ከግለሰብ ጀምሮ
አግኝተንበታል።አሜሪካውያን ስለ ኢትዮጵያውያን ባህልና በአሜሪካም ውስጥ ያላቸውን ሁለገብ አስተዋጽኦ ተረድተዋል። ይህ ፌስቲቫል እኛ እርስ በርስ እንድገናኝ ብቻ ሳይሆን እኛ ከአሜሪካዊውና ከዓለም ማህበረሰብ ጋር እንድገናኝ የተዘረጋ ድልድይ ነው።
ድጋፍ ይህ ሁሉ ሲደረግና ወደፊትም እንዲሁ ለማድረግ ችግሮችና ፈተናዎች መኖራቸውንም ጥበበ እንደሚከተለው ገልጸዋል። “ ዘንድሮ ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ የፈንድ ሬይዚንግ ችግር አለብን። ለምሳሌ ለጠቅላላ ወጪያችን ዘንድሮ ልናሰባስበው የቻልነው ከመቶ 20 የወረደ ነው። ምክንያቱም ይህ ሥራ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። እኛ ደግሞ በዚያ ረገድ 6 ወር ያህል ብቻ ነው የሠራነው። ይህንንም ስናደርግ የራሳችንን አቅም እንዲሁም በሥራና ወዳጅነት አጋጣሚዎች የተፈጠሩትን ግንኙነቶች በመጠቀም ነው። ህዝቡ ሊያግዘን፣ አርቲስቶች ሊደግፉን ፣የቢዝነስ ሰዎች ማስታወቂያ በመግዛት ሊተባበሩን ይገባል። የቢዝነስ ኮሙዪኒቲውም ሆነ ህብረተሰቡ እኛንም ብቻ ሳይሆን በህብረተሰባችን ውስጥ ያሉትን ባህል አበልጻጊ ተቋማት፣ ማለትም እንደ አርት፣ የባህልና ሚዲያዎችን የመርዳት ባህሉን ማሳደግ አለበት። ሌላው የአሜሪካ ማህበረሰብ የሚያድገው ለዚህ ነው ባህሉን ስለሚንከባከብ ነው። አምና ያ ሁሉ ሰው መጥቶ ሲታይ ብዙ ነገር የተገኘ ይመስላል። ግን ምንም የተሸጠ ነገር አልነበረም፣ ምክንያቱም ለሽያጭ የቀረበ ነገር ብዙ የለም። የነበሩትም 21 ቬንደሮችም የተገኘው ከ3ሺ ዶላር ያላላፈና በጣም አነስተኛ የሆነ ነው። እንደነገሩ ከቀረበው 4 የእጣ ጨዋታ ቲኬት (ራፍል) ላይ የተገኘው ወደ 800 ዶላር አካባቢ ቢሆን ነው። ወጪውን ግን ወደ 70ሺ ዶላር ያህል ነበር። አሁን በዘንድሮው ዝግጅትም ወጪያችንን እንሸፍናለን ብለን ተስፋ ያደርግነው ራፍልና ቲሸርቶችን በመሸጥ ነው። ትላልቁን ወጪዎች የተጋሩልን የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ የገባቸው የአካባቢው ተቋማት ናቸው። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት በዓል ላይ ተሳታፊ ለነበሩት የባህላዊ ጭፈራ ተወዛዋዦች 3ሺ ዶላር የከፈሉት የሲልቨር ስፕሪንግ ዳውን ታወን ቢዝነስ አሶሴይሽን ናቸው። ለሳውንድ ሲስተም ለስቴጅ ለባነር ወደ 20 ሺብር ከፍለውልናል። አሁን ያንን ድሮፕ አድርገዋል፡፡ የተወሰነውን የማንትገመሪ ካውንቲ የኮሙዪኒቲው ዲፓርትመንት ነው ዘንድሮ የሚከፍለው።
ሳይረብሽ በሚገርም መልኩ መውጣቱ ገርሟቸዋል። ስለዚህ ህዝቡ ዘንድሮም ኢትዮጵያዊ የባህል ልብሱንና ባህርዩን ለብሶ እንዲመጣ ነው የምንፈልገው።
ዋና ከተማ
“ሲልቨር ስፕሪንግ ወደፊት የኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ትሆናለች!” አቶ ጥበበ አሰፋ “በሜሪላንድ በተለይም በሲልቨር ስፕሪንግ ከአፍሪካውያን ስደተኞች መካክል በቁጥር አንድ እያደገ ያለው ኢትዮጵያዊው ማህበረሰብ ነው” ባይ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ቢዝነስ መስራት ብቻ ሳይሆን የቢዝነስ ምንጭ ሆነው የአሜሪካን ኢኮኖሚ የሚደጉሙ መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይ በቢዝነሱ በኩል “እንደ ሬስቶራንቶች፣ፀጉር ቤቶች፣ የታክስ፣ የኮምፒውተር የህግ፣ የቴክኖሎጂ፣ ሚዲያና የተለያዩ መልክ ያላቸው ፣ በዚህ ሲልቨር ስፕሪንግ ብሎክ ውስጥ ብቻ የሚገኙ፣ ወደ 75 ቢዝነስ ድርጅቶች ቆጥሬያለሁ። ወደፊትም እንደዚሁ ኢትዮጵያውያን ወደ መሃል ከተማ እየገባን ራሳችንን ማስፋፋት ይኖርብናል። እዚህ የሚታየው ይህ ነው። ሲልቨር ስፕሪንግ ወደፊት የኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ትሆናለች። ባለፈው ዓመት በዚያች የፌስቲቫል ቀን ብቻ የአካባቢው የቢዝነስ ድርጅቶች ወደ 500ሺ ዶላር ገንዘብ ሠርተዋል። ለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ የካውንቲውን ባለሥልጣናት ሳናግራቸው “እኛኮ የናንተን ሥራ ነው የምንሠራው” እላቸዋለሁ።
የፌስቲቫሉ ዝግጅት
የአምናው ፕሮግራም 5 ሰዓት የፈጀ ሲሆን የተካሄደው ከሰዓት በኋላ ከ2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 9 ሰዓት ነበር። ዝግጅቱ የልዩ ልዩ ብሄረሰቦችን ባህል ያካተተ የባህላዊና የዘመናዊ ሙዚቃና የባህላዊ ጭፈራን ያካተተ ነበር። የኢትዮጵያ ባህላዊ አልባሳት የታዩበት የፋሽን ትርኢትም ነበረው። በአካባቢውም በኢትዮጵያውያን ማህረሰብም ውስጥ የሶሻል ካፒታል ሊያንፀባርቁ የሚችሉትን ያካተተ ነበር ። የዘንድሮውም ከዚህ በተሻለ ሁኔታ፣ እንደ ጣይቱ የባህል ማዕከልን ጨምሮ ዛፍ ተካይና ተፈጥሮን የሚንከባከቡ፣ ልጆችን የሚያንጹ፣ የስነጥበብና አርት ኤግዚብሽኖች እንዲሁም የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ለማድረግ እየሞከርን ነው። በሌሎች የኮሙዪኒቲ በተለይም በቡናው ዙሪያ ከአቶ ጥበበ አስፋ ጋር የምናደርጋቸውን ጥልቅ ውይይቶች ይዘን እንቀርባለን። ዘኢትዮጵያ!
B-8
ላኮመልዛ Downtown Silver Spring 7912 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20910
301-326-2435
የኢትዮጵያዊነት ድምጽ ሬዲዮ አገልግሎት
ዘወትር ቅዳሜ ከምሽቱ 10 እስከ 12PM እሁድ ከ 1 እስከ 3PM በ730 AM ራዲዮ እንደዚሁም በዌብ ሳይት www.ethiopiawinet.net ይከታተሉ ለመረጃ
202-431-2022
ኢትዮጵያዊነት ቀጣይ ነው!