እይታ www.amisom-au.org
እትም 23 | ጥር - መጋቢት 2018 ዓ.ም
የአመራር
ለውጥ
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
1
ከኤስ.አር.ሲሲ የተላከ
መልዕክት
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለሶማሊያ ልዩ ወኪል፣ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማድሪያ
በቦታው ያስቀመጥነው የመሸጋገሪያ እቅድ በአግባቡ ከተተረጎመ የርክክቡ ሂደት ያለ እክል ለመወጣት ያስተማምነናል። የወሳኝ አጋሮቻችንን አስተማማኝ ድጋፍ ሽግግሩን ሰኬታማ ለማድረግ እንጠብቅባቸዋለን። አሚሶም በሶማሊያ ያለውን ተልእኮውን በሀላፊነት ለማስፈጸም በቆራጥነንት መወጣቱን ቀጥሏል ፣ በዚሁም አላማውም ሀገሪቷ ለመኖር አስተማማኝ እና የተሻለ ሰላምና ጸጥታ የሰነፈባት ለማድረግ ነው” አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴራ
2
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
በ
ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት ተልእኮ ለመመርመር ስብሰባ ተቀምጧል፡፡ ሀሳባችን የተባበሩት መንግስታት (ዩኤን) ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰጡትን አስተያየቶችን በተለይም በአብዛኛዎቹ የማዘዣ ጣቢያዎች የአሚሶምን ተግባር ወደ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለማስተላለፍ የታቀደውን የሽግግር እቅድ በተመለከተ የቀረቡ ሀሳቦችን በጥልቀት እንዲመረምር ነው፡፡ ሆኖም አዲሱን ተልእኮ እየጠበቅን እንደመሆኑ አሚሶም በሀገሪቱ ብሄራዊ የጸጥታ መዋቅር መሰረት የሽግግር እቅድ አዘጋጅቷል፡፡ ሁሉም ነገር በእቅዱ መሰረት የሚከናወን ከሆነ አሚሶም እንደ ሽግግር እቅዱ አንድ ክፍል በዚህ አመት ቢያንስ 10 ቀጣይ የማዘዣ ጣቢያዎችን በአግባቡ ለተጠናከረ የሱማሊያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት ለማስረከብ አቅዷል፡፡ ያለፈው አመት ትኩረታችን በዙር በተከፋፈለና በሁኔታዎች ላይ በተመሰረተ ሽግግር ወታደሮችን በዩን ሴኪዩሪቲ ካውንስል ውሳኔ ቁጥር 2372 ኦገስት 30, 2018 የመቀነስ እቅድ ማዘጋጀትና መተግበር ላይ ነበር፡፡ በዚህ አመት ትኩረት ያደረግነው በተለቀቁ ቦታዎች ንግድና የልማት ስራዎች የሚካሄዱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ዋና ዋና የአቅርቦት መስመሮችን ለመክፈትና ነጻ የሰዎች ዝውውር እንዲኖር የሚያስችሉ ወታደራዊ ስምሪቶችን ማካሄድ ነው፡፡ በተጨማሪም የሱማሊያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊትን እና የሱማሌ ፖሊስ ሀይልን በአሚሶም የሚለቀቁ ኃላፊነቶችን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆኑ ለማስቻል ለሱማሊያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት እና ለሱማሌ ፖሊስ ሀይል የሚሰጠው ትምህርትና ስልጠና ይቀጥላል፡፡ በቅርቡ የ160 የሴራሊዮን የፖሊስ ኦፊሰሮች በጁባላንድ ለሚገኙት የሱማሊያ ፖሊስ ኦፊሰሮች የሚሰጠውን ስልጠና ለማቀላጠፍ በሱማሊያ መሰማራት የሱማሊያ ፖሊስ ሀይሎችን እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ እንዲችሉ የሚደረገው የአቅም ግንባታ አንድ ክፍል ነው፡፡ ቀደም ብለን እንደገለጽነው የሽግግር ሂደቱ የተገኙ ስኬቶች እንዳይሸረሸሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ መካሄድ አለበት፡፡ የአሚሶም ተልእኮ ቀጣዩ ግምገማ የአፍሪካ ህብረትን፤ወታደሮች ያዋጡ ሀገራትን፤ የሶማሊያ መንግስትን እንሂሁም የአሚሶምን ትኩረት ያገናዘበ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የሽግግር እቅድ ያዘጋጀን ሲሆን እቅዱ በአግባቡ ከተተገበረ የተሳለጠ ሽግግር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሽግግሩን ስኬታማ ለማድረግ የዋና ዋና አጋሮቻችንን ያልተቋረጠ ድጋፍ እንፈልጋለን፡፡ አሚሶም ዋነኛ አላማውን ሀገሪቱን ሰላማዊና ለመኖሪያ ምቹ በሆነ ደረጃ ላይ ማድረስ አድርጎ የሱማሊያ ተልእኮውን በትጋት እየተወጣ ይገኛል፡፡
መልካም ንባብ
ማውጫ 2
የኤስአርሲሲ መልእክት
4
በዜና ገጾች
8
የጥበቃ ለውጥ
9
የሽግግር እቅድ ዝግጅት
12
የአሚሶም የገንዘብ ማስገኛ ምክክሮች
13
በአይኢዲዎች ላይ የሚደረግ ጦርነት
የሽፋን ምስል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ ሊቀመንበር ልዩ ተወካይ (አስአርሲሲ) በሞቃዲሾ ሶማሊያ ውስጥ የዕዙ ርክክብ በቀን 31 ጃንዋሪ 2018 በተፈጸመበት ወቅት የአፍሪካ ህብረትን ባንዲራ የአሚሶም አዲስ ሃይል ኮማንደር ለሆኑት ለሌውተናንት ጀነራል ጂም ቤስጊዬ ኦዉዬሲጊሬ ያስረክባሉ፡፡ እየተመለከቱ የነበሩት የቀድሞው የጦር ኃይል አዛዥ ሌፍተናንት ጀነራል ኦስማን ኑር ሶባጋሌህ ናቸው፡፡ (የአሚሶም ፎቶግራፍ/ኦማር አብዲሳላን)
15
በሽብርተኝነት ጊዜ የደህንነትና መረጃ ልውውጥ ማካሄድ
16
አሚሶም የአየር ላይ የቅኝት መሳሪያ አገኘ
17
ዩኬ አሚሶም የሽብርተኝነት ስጋትን በመቀነሱ አመሰገነች
18
የፒኤስኦዲ የዳሰሳ ጥናት የሱማሊያ ተልእኮ
19
በአሚሶም ዙሪያ
20
በግጭት ቀጠናዎች የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር
21
የስማይል ትሬይን ወደ ደቡብ ምእራብ መሄድ
22
የሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሴቶች ቀንን ማክበር
23
የስነ ጾታ ጉዳዮች በሶማሊያ ፓርላማ
24
ከሚዲያ ጋር መገናኘትና መጋበዝ
25
በሰላም አስከባሪ ወታደሮቻችን ላይ ማተኮር
30
ሴራሊዮን በሶማሊያ ከፍተኛ ተጠባባቂ ፖሲስ አሰማራች
31
የዳርዊሽ ታጣቂዎችን ማዋሀድ
32
አሚሶም ለሰብአዊ እርዳታ አጋሮች ስልጠና ሰጠ
33
የሂርሸበሌ ኤምፒዎች የፓርላማ ሥነ ሥርአቶች ክህሎቶች ማደግ
34
ወርቃማው የልጃገረዶች እግር ኳስ
ዲዛንይና ሌይአውት፡- ኤዩ-ዩኤን አይሲስቲ ፎቶግራፍ፡- ኤዩ-ዩኤን አይሲስቲ ኒውስሩም ¦ thenewsroom@auunist.org ኢ-ሜይል፡ amisommediacentre@gmail.com ፖ.ሣ.ቁ. 20182-00200፣ ናሮቢ፣ ኬንያ፣ ስልክ ቁጥር +254 202 713 755 /56 /58 ፋክስ፡- +254 202 713 766 አሳረታሚ፡ የአሚሶም ፐብሊክ ኢንፎርሜሽን ዩኒት
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
3
ከዜና
ማህደር 2018
2018 ጥር
10
በ
ጥር 10 በደቡባዊ ምዕራብ ግዛት ለሱማሊያ የፖሊስ ሀይል የፎረንሲክ የጣት አሻራ ምርመራ ስልጠና መስጠት የጀመረ ሲሆን ለ14 ቀናት የሚሰጠው መሰረታዊ ኮርስ ኦፊሰሮቹ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችን ተጠቅመው የወንጀል ጉዳዮችን የሚመረምሩበት ክህሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
ጥር
15
የ
ዩኤን የመስክ ድጋፍ ዲፓርትመንት (ዲኤፍኤስ) ለአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በከባድ የምህንድስና ተግባሮች ላይ ያተኮረ አዲስ ዙር ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡ ፡ ሰልጣኞቹ ከኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዛምቢያና ኢትዮጵያ የተውጣጡ አስራ ሁለት ወታደሮች ሲሆኑ ናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የሰብአዊ ሰላም ድጋፍ ትምህርት ቤት (ኤችፒኤስኤስ) በሰላም ማስከበር የከባድ ምህንድስና ተግባሮች ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሶስት ወራት ጥልቅ የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት ይወስዳሉ፡፡
2018 ጥር
27
የ
ተለያየ ዜግነት ያላቸው ከጋና፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ኡጋንዳ እና ዛምቢያ የተውጣጡ የፖሊስ ኦፊሰሮች ቡድን ከተልእኮው ጋር የተዋወቀ ሲሆን አርባዎቹ ኦፊሰሮችና ሌሎች የስራ ባልደረቦች ሀገሪቱ የጸጥታ ተቋማቷን መልሳ እየገነባች እንደመሆኗ ለአካባቢው ፖሊስ ህግና ደንብን የመቆጣጠር ስልጠናና ትምህርት ይሰጣሉ፡፡
2018 ጥር
31
ሌ
ተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ በ31/01/2018 ሌተናል ጀነራል ኦስማን ኑር ሱባግሌን ተክተው የአሚሶም ሀይል አዛኝነት ኃላፊነትን ተረክበዋል፡፡ ሌተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ ኃላፊነቱን በተረከቡበት ወቅት ‹‹በሙያዬ ባለፉት 39 አመታት ውስጥ ከጦርነት ሜዳ ተለይቼ የማላውቅ ሲሆን ስልጠና እወዳለሁ፤ ከሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ጋርም የማደርገው ይህን ነው፣ አብሬያችሁ የምሰራ ሲሆን ስልጣን የማስረከቢያው የሽግግር ጊዜ በሚደርስበት ወቅትም ይህን አደርጋለሁ፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡
4
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
2018
የካቲት
የ
አፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ድጋፍ ኦፕሬሽኖች የስራ ክፍል ልዑካን (ፒኤስኦዲ) ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች የማስተላለፍ ሂደቱ ቅርጽ እየያዘ የመጣ እንደመሆኑ የሰላም ማስከበሩን የስራ እንቅስቃሴዎች ለማጥናት ወደ ሱማሊያ መጥቷል፡፡ 10 አባላትን የያዘው የልዑካን ቡድን ከከፍተኛ የአሚሶም ኃላፊዎች፣ ዩኤንኤስኦኤስ፣ የሱማሊያ ፌደራል መንግስት እና ወታደሮች ካዋጡ ሀገራት አምባሳደሮች (ቲሲሲኤስ) ጋር ውይይቶች አካሂዷል፡፡
13
2018
የካቲት
23
በ
ሱማሊያ መዲና መቋዲሾ በአሚሶም የስራ ሂደት መሻሻል ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የሱማሊያ ፖለቲከኞችን፣ የሲቪል ማህበረሰቡ አባላትን እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን፣ የሀይማኖት መሪዎችን፣ የትምህርት ባለሙያዎችን እና የጸጥታ ኤክስፐርቶችን ያጠቃልላሉ፡፡ ውይይቱ በ11 አመታቱ የአፍሪካ ህብረት (ኤዩ) ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
2018
2018
መጋቢት
የካቲት
3
27
የ
ሱማሊያ ፌደራል መንግስት፣ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች፣ ለአሚሶም ወታደር ያዋጡ ሀገራት የመንግስት ኃላፊዎች እና አለም አቀፍ አጋሮች አሚሶም ከሱማሊያ ለመውጣት በሚያደርገው ሽግግር ላይ በካምፓላ፣ ኡጋንዳ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የቲሲሲ መሪዎች በታህሳስ 2017 የተጀመረው ወታደሮችን የማስወጣት ሂደት እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል፡፡
አ
ሚሶም የሱማሊያ የፓርላማ አባል ለሆኑ ሴቶች የፓርላማ አባል የሆኑ ሴቶች በፍትህ ላይ ስለሚጫወቷቸው ሚናዎች ያተኮረ የሶስት ቀናት አውደ ጥናት ያዘጋጀ ሲሆን አውደ ጥናቱ በሴቶችና ህጻናት መብቶች ፍትህ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
2018
መጋቢት
8
2018
በ
አሚሶም ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሴት ሰላም አስከባሪዎች የአለም የሴቶች ቀንን ባከበሩበት ወቅት መንግስታት በሰላም ማስከበር ተልእኮዎች ላይ የሴቶችን ቁጥር ለማብዛት ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪ አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ወታደሮችና ፖሊስ ካዋጡ ሀገራት እና የሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ተቋማት የተውጣጡት ሴቶች በሱማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ለማሳየት ሞቃዲሾ ውጥ ተሰባስበዋል፡፡
መጋቢት
13
የ
አፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካታኖ ማዴይራ ከሂርሸበሌ ግዛት ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዲ ዋሬ ጋር በግዛቷ የጸጥታ ሽግግር እቅዶች እና በአሸባሪው ቡድን አልሸባብ ላይ የሚካሄደው ጤርነት እንዴት መጠናከር እንደሚችል አስመልክተው ተወያይተዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
5
2018
መጋቢት
19
አ
ላማውን በሱማሊያ የሚገኙ የተለያዩ የደህንነት ተዋናዮች ተቀራርበው የሚሰሩበትን ሁኔታ መፍጠር ያደረገው ሶስተኛው የደህንነትና መረጃ መለዋወጫ ኮንፍረንስ በሱማሊያ መዲና መቋዲሾ ተካሂዷል፡፡ ‹‹የደህንነት/መረጃ መለዋወጫ መድረኩ አንደኛው ዋነኛ ትኩረት አዲስ የሚፈጠሩ ከሽብርተኝነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥቃቶችና ስጋቶች በተቀናጀ ስርአት መለየት፣ መከላከልና ምላሽ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሆኖ ይህ በተጨማሪም ለቲያትርና አካባቢያዊ የህዝብ ተቋማት የደህንነትና ጥቃት ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያደርጉት ጥረት ላይ ድጋፍ በመስጠት ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡ የደህንነት መረጃና የደህንነት አሰራር ሂደት የሽብርተኞች በተለይም በአልሸባብ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ ወሳኝ ሚና እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል›› ያሉት ሜጀ. ጀነራል ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ፣ የአሚሶም ምክትል ሀይል አዛዥ፣ ኦፕሬሽኖችና እቅዶች ናቸው፡፡
2018
መጋቢት
ከ
20
2018
መጋቢት
26
በ
መላው ሱማሊያ የተውጣጡ በጠቅላላው ሰላሳ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ሰራተኞች በሞቃዲሾ በተካሄደ የሶስት ቀናት አውደ ጥናት በህጻናት ጥበቃ ላይ ስልጠና ወስደዋል፡፡ በአሚሶምና በሱማሊያ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ትብብር በተካሄደው በዚህ አውደ ጥናት ህጻናትን በሱማሊያ የትጥቅ ግጭት ላይ መጠቀምን በመከላከያ እርምጃዎች ላይ አተኩሮ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የአሚሶም ምክትል ኃላፊ ሚ/ር ሲሞን ሙሎንጎ ‹‹ይህ ስልጠና በሱማሊያ ሪፑብሊክ ውስጥ ህጻናትን በመጠበ ረገድ እጅግ አስፈላጊ ተግባር ማካሄድ የምትችሉበት ክህሎት የሚሰጣችሁ በመሆኑ ምክንያት እጅግ አስፈላጊ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡
2018
መጋቢት
30
ሱማሊያ ከአፍሪካ ህብረት ተልእኮ (አሚሶም) የተውጣጡ 39 የሰራዊቱ የህክምና ሙያተኞችን የያዘ ቡድን እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች በሚካሄዱ ድንገተኛ ክትባቶች፣ የተጎጂዎችና አስጊ ሁኔታዎች ላይ የሚገኙ ታማሚዎች ቁጥጥር ላይ የሶስት ቀናት ማብራሪያ ለመቀበል በመቋዲሾ ተሰብስበዋል፡፡
አ
ሚሶም በጁባላንድ ግዛት የዳርዊሽ ታጣቂዎች በግዛቱ የጸጥታ ሀይሎች ውስጥ ከመመዝገባቸው በፊት የባዮሜትሪክስ ምዝገባ አድርጎባቸዋል፡፡ የምዝገባው አላማ በጌዶ፣ የታችኛው ጁባ እና የመካከለኛው ጁባ ክልሎች የሚገኙ ከአምስት መቶ በላይ የታጣቂ ቡድኑን አባላት መመዝገብ ነው፡፡ የባዮሜትሪክ ምዝገባው የእያንዳንዱን የቡድኑን አባል ፎቶግራፎችና የጣት አሻራዎች ጨምሮ ዋና ዋና የግል ዳታ ይሰበስባል፡፡
6
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
2018
ሚያዚያ
1
የ
አፍሪካ ህብረት - ዩኤን የአሚሶም የገንዘብ ማሰባሰብ አማካሪ ልዩ ልኡክ በሀገሪቱ ለሰላም ማስከበር ስራዎች አስተማማኝ ገንዘብ በሚሰበሰብበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት በሚያዚያ 1 በሱማሊያ የ1 ቀን ጉብኝት አድርጓል፡፡ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዑካን የሆኑት ራምታኔል ላማምራ እና ሜሪ ጉሄኖ የሀገሪቱን ጸጥታ በማስጠበቅ ላይ እየታዩ የመጡት መሻሻሎችን ወደ ኋላ በማይመልስ መልኩ የጸጥታ ኃላፊነቶች ቀስ በቀስ ከአሚሶም ወደ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች በሚተላለፉበት ሁኔታ ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የዩኤን ልዑክ ዣንሜሪ ጉሄኖ ‹‹እስከ አሁን ድረስ የተደረጉትን ጥረቶች መና በማያስቀር አኳኋን የጸጥታ ኃላፊነቶችን ቀስ በቀስ ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ ባለስልጣናት ማስተላለፍ አስፈላጊ ነው›› በማለት ተናግረዋል
2018
ሚያዚያ
10
የ
ዩኬ የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ሚኒስትር አርቲ. የተከበሩ ማርክ ላንካስተር ሱማሊያን የጎበኙ ሲሆን ለአፍሪካ ህብረት ወታደሮች የሀገሪቱን ጸጥታ በማስከበርና የሽብርተኝነት ስጋትን በመቀነስ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሱማሊያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ መዳይራ እና የአሚሶም ሀይል አዛዥ ሌተ. ጀነራል ጂም ቢሲጌኦወዬሲግሬ ጋር የተገናኙ ሲሆን የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ማሸጋገር እና ዩኬ ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በምትሰጠው ድጋፍ አይነትና ይዘት ላይ ተወያይተዋል፡፡ ሚ/ር ላምካስተር ‹‹ንግግሬን አሚሶም ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ ላደረጋቸው አስተዋጽኦዎችና የከፈላቸው መስዋእትነቶች ምስጋናዬን በመግለጽ እጀምራለሁ፤ ምክንያቱም ያለ ምንም ጥርጥር አሚሶም ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ የሰራቸው መልካም ስራዎች ባይሰሩ ኖሮ ሱማሊያ አሁን
2018
ሚያዚያ
16
በምትገኝበት የመሻሻል ሂደት ላይ መገኘት ስለማትችል ነው›› በማለት ተናግረዋል
2018
ሚያዚያ
18
የ
ማጥቃት አቅምን እንደ ማጠናከር አንድ ክፍል 145 የሴራሊዮን ተጠባባቂ የፖሊስ ኦፊሰሮች በደቡብ ማእከላዊ ክልል የፖሊስ አገልግሎት ፕሮግራሞችን ለመተግበር እገዛ ለማድረግ ወደ ሱማሊያ መጥተዋል፡፡ 145 የፖሊስ ዩኒት (ኤፍፒዩ) ኦፊሰሮችን የያዘው ቡድን በኪስማዩ፣ ጁባላንድ የሰፈሩ ሲሆን ቀደም ብሎ ወደ ቦታው ከደረሰው 15 ኦፊሰሮችን ከያዘው ቡድን ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ‹‹ሞቃዲሾን ለቀን እንዴዳለን፡፡ ወደ ክልላዊ አስተዳደሮችና ወረዳዎች ዘልቀን የምንገባ ሲሆን እነዚህን የፈለግንበት ምክንያት በእንቅስቃሴያችንና ሌሎች ኦፕሬሽኖች ላይ ስለሚረዱን ነው›› ሲሉ ክሪስቲን አላሎ ተናግረዋል፡፡
አ
ራተኛው የግማሽ አመት የአይኢዲ ጉባኤ በመቋዲሾ ተካሂዷል፡፡ በሱማሊያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሰብሳቢ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ ሱማሊያ ውስጥ በቤት ውስጥ በሚሰሩ ፈንጂ መሳሪያዎች (አይኢዲዎች) የተነሳ በጸጥታ ሀይሎችና ሲቪል ማህበረሰቡ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል፡ ፡ አምባሳደር ማዴይራ ይህን ጥሪ ያደረጉት አራተኛውን የግማሽ አመት የአይኢዲ ጉባኤ፣ ሞቋዲሾ ውስጥ በይፋ በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
7
የጥበቃ ለውጥ ሌተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ በ31/01/2018 ሌተናል ጀነራል ኦስማን ኑር ሱባግሌን ተክተው የአሚሶም ሀይል አዛኝነት ኃላፊነትን ተረክበዋል፡፡ አዲሱ የሀይል አዛዥ የተጀመረውን ስራ ለማስቀጠል በተለይም የሱማሊያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊትን አቅም ግንባታ እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ የ39 አመታት የውትድርና ልምድ ያላቸው ሌተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ ለጸጥታ ሀይሉ በኡጋንዳ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የአየር ሀይልና የእዝ አዛዥ - የምድር ጦር ምድብና ሌሎችም ኃላፊነቶች ላይ እንደመስራታቸው መጠን ለጸጥታ ሀይሉ በምድር ጦርና የአየር መከላከያ መስኮች ላይ ጥልቅ እውቀት ይሰጣሉ፡፡ አዛዡ ቅድሚያ ሰጥተው የሚያከናውኗቸው ተግባሮች ያለ ችግር፣ ቀስ በቀስና በሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የሚካሄደውን ሽግግር እና
የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ኃይሎች ማስተላለፍን እንዲሁም ቀሪ በአልቃኢዳ የሚደረገፉ የአልሸባብ ታጣቂዎችን የመደምሰስ ስራዎችን መቆጣጠርን ያጠቃልላሉ፡፡ ሌተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ ኃላፊነቱን ከሌተ. ጀነራል ሱባግሌ በተረከቡበት ወቅት ‹‹ሁላችንም እዚህ ያለነው አንድ ችግር ያለብን ሲሆን ይህም ችግር አልሸባብ ነው፡፡ ከአልሸባብ ጋር መሰብሰብ የለብንም፡፡ ከዚያ ይልቅ ቡድኑን ተዋግተንና የጀርባ አጥንቱን ሰብረን በመጨረሻም ማጥፋት አለብን፡፡ ይህ የኔ ግብ ሲሆን ይህንንም አሳካዋለሁ፡፡ ›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ሌተናል ጀነራል ጂም ቢሲግዬኦዎዬሲግሬ በሙያ ረገድ በመከላከያና ስትራቴጂክ ጥናቶች እና በሀይማኖት፣ ሰላም ማስከበርና የግጭት አፈታት ሁለት የማስተርስ ዲግሪዎች አሏቸው፡፡
ከኬንያ የመጡት ሜጀ. ጀነራል ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ በየካቲት 2018 የኦፕሬሽንና እቅዶች ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮን በምክትል የሀይል አዛዥነት ተቀላቅለዋል፡፡ ከአዛዡ ጋር በተካሄደ ጥያቄና መልስ አሚሶም የሱማሊያን ብሄራዊ የጸጥታ ቁጥጥር ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ስለሚያስረክብበት የሽግግር እቅድ ትግበራ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጥያቄ፡- የኦፕሬሽኖችና እቅድ ዝግጅት
ኃላፊነት የተሰጥዎ ምክትል የሀይል አዛዥ እንደመሆንዎ ስላልዎት ሚናና ይህ በአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ተልእኮ ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖዎች ያብራሩልን? መልስ፡- በዚህ ደረጃ ላይ ቅድሚያ የምንሰጠው በሱማሌ መንግስት አነሳሽነት ለሚደረገው የሽግግር እቅድ ነው፡፡ ይህ ከሆነ አሁን ማድረግ ያለብን ነገር በሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የሚካሄደውን የአሚሶም ወታደሮችን ቁጥር የምንቀንስበትን ስትራቴጂያዊ እቅድ ማዘጋጀት ነው፡፡ በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ማለት ይህ የወታደሮችን ቁጥር መቀነስ መካሄድ ያለበት አጠቃላይ የጸጥታ አቀራረብ (ሲኤኤስ) በምንለው አካሄድ ሲሆን በዚህ አካሄድ የወታደሮቹን ብዛት እየቀነስን ስንሄድ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይል በእኛ የተለቀቁ ቦታዎችን መያዝ ይችላል፡፡ በተጨማሪም
ሚጀር ጀነራል ሲ ታይ ጉቱዋይ የአሚሶም ምክትል የጦር ሃይል አዛዝ፣ የዘመቻ እና እቅድ.
8
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ሌፍተናንት ጀነራል ጂም ቤስጊዬ ኦዉዬሲጊሬ ቀጣዩ ያአሚሶም የጦር ኃይል አዛዥ በዕዝ ርክክቡ ወቅት ንግግር ያደርጋሉ፡፡
ማየት ያለብን ነገር እኛ በምንለቃቸው ቦታዎችና እንደ ፖለቲካ ባሉ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉ የጸጥታው መስክ ማሻሻያዎችን ሲሆን እነዚህ አስተዳደርን እና የመንግስት መዋቅሮችን ማቋቋምን ያጠቃልላሉ፡፡ በተጨማሪም በፖሊስ አገልግሎት ህግና ደንብን ማስከበር ቅርጽ መያዝ አለበት፡፡ ትምህርት ቤቶችን መልሶ መገንባትና ለህዝቡ ንጹህ የመጠጥ ውሀ ማቅረብም በተመሳሳይ የሚካሄድ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ህዝቡን ነጻ ወጥቻለሁ ብሎ እንዲያስብ በራስ መተማመን ስሜት መፍጠርና በነጻነት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቹን እንዲያከናውን ማስቻል አለብን፡፡ ስለዚህ እንደመውጫ እቅዳችን አንድ ክፍል የምንሰራቸው ስራዎች እነዚህ ናቸው፡፡ ጥያቄ፡- አሚሶም ይህን ሽግግር ለመቆጣጠር
ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች ለማካሄድና የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ብዛት ለመጨመር እያሰበ ነው፡፡ በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ምን አይነት ኦፕሬሽኖችን መጠበቅ እንችላለን? መልስ፡- በሽግግር እቅዱ ማሳካት የምንፈልጋቸው ልዩ አላማዎች አሉን፡፡ አንዳንድ ዋና ዋና የአቅርቦት መስመሮችን (ኤምኤስአርኤስ) ማጥራት መቻል ያለብን ሲሆን ይህን ስራ ለመስራት በቂ ሀይል መኖር አለበት፡፡ እንደምታውቁት ላለፉት 11 አመታት አሚሶም ሱማሊያ ውስጥ የቆየ ሲሆን ተልእኮው በጥቅሉ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፤ ሁሉም ወታደር ያዋጡ ሀገራት በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ሆኖም የአልሸባብ ታጣቂዎች የውጊያ ስልታቸውን እየቀያየሩ በደቡብ ማእከላዊ ሱመሊያ አነስተኛ የደፈጣ ጥቃት ቡድኖችን የፈጠሩ ከመሆኑም በተጨማሪ በዛ የፈንጂ ማምረቻ አቋቁመዋል፡፡ ስለዚህ መስመሮቹን የሚያጸዳ እና ቦታዎቹን የያዙትን ታጣቂዎች የሚያጠፋ በቂ ሀይል ያስፈልገናል፡፡ አጠቃላይ አቀራረብ የተከተልነው ለዚህ ነው፡፡ ይህ ማለት አሁን ነጻ የወጡ ከተሞችን ደህንነት መጠበቅ የሚችል በቂ ሀይል ያስፈልገናል፡፡ የምናወራው ይህንን ነው - የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎችን እነዚህን ቦታዎች ለመያዝ፣ ለልማት ምቹ ሁኔታ
መፍጠር፣ መሰረተ ልማት እንዲዘረጋ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና እንደ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ያሉ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎችን ለማቋቋም ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ አለብን፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ እምነት የሚጣልበት ሀይል ካልኖረ፣ የተወሰነ የአስተዳደር ደረጃ ካልኖረ በስተቀር በተለይም አረጋውያንን የተወሰነ የማረጋጋት አቅም ካልተፈጠረላቸው በስተቀር ይህን ማድረግ አይቻልም፡፡ የተወሰኑ ስልጣኖችና ተግዳሮቶች ያሉበት አስተዳደር ሊፈጠር ይችላል፡፡ አሁን የምንነጋገርባቸው ጉዳዮች እነዚህ ናቸው፡፡ ዘልቆ መግባት በተለይም ስትራቴጂ በሆኑ ቦታዎች ላይ መካሄድ ያለበት ሲሆን ለዚህ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልገን እናምናለን፡ ጥያቄ፡- ከእነዚህ ቦታዎች ውስጥ ጥቂቶቹን ሊነግሩን ይችላሉ? መልስ፡- ለምሳሌ የጁባ ሸለቆ መተላለፊያን መውሰድ እንችላለን፣ ቦታው አልሸባብ በብዛት ተሰማርቶ የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡ ምክንያቱም ቦታው በጣም ለምና ምግብ በቀላል ማግኘት የሚቻልበት ስለሆነ እዛ በመቆየት እድሜያቸውን ማርዘም ይችላሉ፡፡ የሀይል ማጠናከሪያዎች ለምሳሌ አውሮፕላኖችና በትጥቅ የተደገፈ ሀይል መጠቀም ከቻለን ታጣቂዎቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ እንችላለን እንዲሁም የሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት (ኤስኤንኤን) እነዚህን ቦታዎች እንዲይዝ ማድረግ እንችላለን፡፡ ጥያቄ፡- እነዚህ ሁሉ እቅዶች እንዳሉ ሆነው ማነቆዎችም አሉ፡፡ አሚሶም ማነቆዎቹን መፍታት የሚችለው እንዴት ነው? መልስ፡- በየትኛውም እንደዚህ አይነት ሁኔታ ተግዳሮቶች የግድ ያጋጥማሉ፡፡ ሆኖም አላማችንን ለማሳካት ግን ያለንን ነገር ሁሉ ተጠቅመን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ጥያቄው እንዴት ስኬታ በሆነ መልኩ ማሰማራት እንችላለን ከሆነ ሰራዊታችንን በድጋሚ በማሰማራትና ተንቀሳቃሽ ሀይሎችን በመፍጠር ወደፊት የሚኖሩ ቀጣይ ቤዞችን እንቀንሳለን፤ ወታደሮቻችንን ስትራቴጂያዊ ቦታዎች ላይ በማሰማራት የሚያጋጥሙ ስጋቶችን እንከላከላለን፡፡
ስለ ሽግግሩ ማቀድ
ለ
አሚሶም ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ያዋጡ ሀገራት የመንግስት ኃላፊዎች (ቲሲሲዎች)፣ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች፣ የሱማሊያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት እና አለም አቀፍ አጋሮች በመጋቢት መጀመሪያ ላይ አሚሶም በሱማሊያ በሚያደርገው ሽግግር ላይ እና በተለይም ከአፍሪካ ቀንዷ ሀገር ባለፈው ታህሳስ ወር የተጀመረው የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቁጥር መቀነስ ላይ ለመወያየት በካምፓላ ኡጋንዳ ተሰብስበዋል፡፡ የኡጋንዳው ፐርሲዳንት የተከበሩ ዮሪ ሙሶቪኒ፣ የሱማሊያ አቻቸው የተከበሩ መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ ‹‹ፋርማጆ››፣ የቡሩንዲው ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት፣ ጋስቶም ሲንድምዎ፣ የኬንያው የመከላከያ ካቢኒ ጸሀፊ ሚስ. ሬይቼሎኦማሞ፣ የጅቡቲው የመከላከያ ሚኒስቴር አሊ ሀሰን ባህዶን፣ የኢትዮጵያው አምባሳደር በኡጋንዳ፣ ቶሌሳሻጊ ሞቲ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የተከበሩ ሙሳ ፋቂ መሀመት እና የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሀፊ ሙህቡማሊም የአፍሪካ ህብረት ሰሎም አስከባሪ ወታደሮችን ከሱማሊያ ማስወጣት በአስቸኳይ እንዲቆም መግባቢያ ተፈራርመዋል፡፡ መግባቢያው በኡጋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳም ኩቴሳ የተነበበ ሲሆን ለዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቁጥር መቀነስ ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው፣ የወታደሮቹ ቁጥር ቀድሞ ወደነበረበት እንዲመለስ እና ግዛቱን ከአልሸባብና ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ለማስለቀቅ የትኛውም ተጨማሪ የወታደሮችን መቀነስ ቁጥር እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጉባኤው ለፕሬዝዳንት ዮሪ ሞሱቪኒ ውሳኔውን ለአፍሪካ ህብረትና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሊቀመንበር ለሆኑበት ለአፍሪካ ህብረት እንዲያሳውቁ ስልጣን ሰጥቷል፡፡ መሪዎቹ በዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ላይ የተቀመጠው የወታደሮችን ቁጥር መቀነሻ ጊዜ ተጨባጭ ሁኔታውን ያላገናዘበ እና በአሚሶም ላለፉት አመታት አልሸባብን ድል በመምታት ያገኛቸውን ድሎች በተቃራኒው የሚገለብጥ እንደሆነ ተስማምተዋል፡፡ መግለጫው አሚሶም የወታደሮችን ቁጥር ለመቀነስ በራሱ ለመወሰን ያለውን ስልጣን ያላከበረ እና የሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊትን አቅም የመገንባት ጥረቶችንና የሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ሀይሎች ማቋቋም ሂደቱን የሚያጓትት እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ መግለጫው በአሚሶም ቲሲሲዎች፣ ሶማሊያና አጋሮች መካከል በሚስጥር የተካሄደ ውይይት የጋራ ውጤት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ‹‹አፍሪካውያን ያልሆኑ ሆኖም ግን ለአፍሪካ ለረጅም
ክቡር ሙሳ ፋኮ ማሃማት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር (በቀኝ) እና ጋስቶን ሲዲመዎ የቡሩንዲ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዚዳንት የጦር ሰራዊት ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ያበረከቱ ሃገራትን መሪዎች በኡጋንዳ ካምፓላ፡፡
በኡጋንዳ በተኪያሄደው ስብሰባ ላይ ለአሚሶም ወታደሮች ያበረከቱ ሀገራት መሪዎችና የብሰባው ልኡጋነ ታደመዋል፡፡
ተካሄደውን ስብሰባ እየተከታተሉ)፡፡ የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሶማሊያ የተመድ ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ከሚካኤል ኪቲንግ፣ በጋር እያወሩ የጦር ሰራዊት ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ያበረከቱ ሃገራትን መሪዎች በኡጋንዳ ካምፓላ የተካሄደውን ስብሰባ በሚካሄድበት ወቅት እርስ በእርስ እየተወያዪ፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
9
ጊዜ ድጋፍ ሲሰጡ የቆዩ ብዙ የአፍሪካ ወዳጆች አሉ፡፡ እነዚህ ወዳጆች (የልማት አጋሮች ተወካይ ኃላፊዎች) አሜሪካውያን፣ አውሮፓውያንና እሲያውያን ናቸው፡፡ እነዚህ አጋሮች የሱማሊያ ኦፕሬሽንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ገንዘብ ሲያዋጡና ለወታደሮቻችን ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል›› በማለት ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ቀጣይነት ባላቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሒ ሞሐመድ በቡድን ፎቶግራፍ ላይ የጦር ሰራዊት ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ካበረከቱ ሃገራትን መሪዎች በኡጋንዳ ካምፓላ የተካሄደውን ስብሰባ ስብሰባ ተሳተፊ የሃገራት ተወካዮች ጋር ይታያሉ፡፡
እና በመላው ሀገሪቱ በሚካሄዱ የማረጋጋት ፕሮግራሞች አማካኝነት የሱማሊያን ጸጥታ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማሻሻል ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ከጊዜው አስቀድሞ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ማስወጣት ባለፈው አስር አመት ውስጥ ከፍተኛ ሰብአዊና የገንዘብ ወጪ ተከፍሎ የተገኙትን ድሎች የሚያበላሽ ነው፡
፡ ከዛ ይልቅ ትኩረት መሰጠት ያለበት ለአሚሶም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች የማስተላለፍ ሂደቱን ማመቻቸት ነው›› በማለት ማህመት ተናግረዋል መሪዎቹ የአሚሶምን ተልእኮና የሽግግር እቅዱን ውጤታማ ትግበራ በጋራ ለማቀድ፣ ሂደቱን ለመመርመርና ቀጣይ እርምጃዎችን
የጉባኤው ድምጽ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት የተከበሩ መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ ‹‹ፋርማጆ›› ‹‹ገና ረጅም ርቀት መሄድ እንዳለብን አምናለሁ፡፡ አልሸባብን ስኬታማ በሆነ መልኩ ተዋግቶ ድል ለመንሳት ውጤታማ የሆነ ስትራቴጂ ስራ ላይ ማዋል አለብን፡፡ እነሱ የዛን ያህል ጠንካራ እንዳልሆኑ አምናለሁ፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡
የኡጋንዳው የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ዴቪድ ሙሁዚ በበኩላቸው ‹‹አሚሶም በተልእኮው ተግባሮችና በሚያስፈልጉት ግብአቶች መካከል ያለውን አለመጣጣም ተቋቁሞ የሚፈለገውን ውጤት በአስፈላጊው ጊዜ ለማምጣት እርምጃዎች መውሰድ ጀምሯል፡፡ ይህ የሀይል ማጠናከሪያዎችን መሬት ላይ ማውረድን፣ ውጤታማ የተልእኮ ድጋፍ መፍጠርን እና የሱማሊያ መከላከያ ሰራዊትን መገንባትን ያጠቃልላል፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡
10
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የአሚሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴይራ ‹‹የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ማስወጣትና ቁጥራቸውን መቀነስን ማካሄድ በበቂ የሀይል ማጠናከሪያና ሀይል ማብዣ ካልተደገፈ በስተቀር በራሱ ችግር አለው፡፡ አልሸባብን በቂ ሁኔታ መደምሰስ ያስፈልገናል፡፡ ይህን ለማድረግ አስፈላጊው ሀይል፣ የሀይል ማጠናከሪያና የሀይል ማብዣ ያስፈልገናል፡፡›› ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር ስማኤል ቼሩጊ በበኩላቸው ‹‹በቀጣዩ ጊዜ የአፍሪካ ህብረት ዋነኛ ትኩረት አሁን የተጀመረውን ጅምር ለማፋጠን፣ የሱማሊያ ፌደራል አባል ግዛቶችን ያሳተፈ የፌደራል መንግስ ለመመስረት እና ለሱማሊያ የሽግግር እቅድ ሙሉ ትግበራ ድጋፍ ማድረግ መሆን አለበት፡፡›› ብለዋል፡፡
ለመወሰን በየአመቱ እና በሚኒስቴሮችና በመከላከያ ኃላፊዎች ደረጃ በአመት ሁለት ተገናኝተው ለመወያየት ተስማምተዋል፡፡ ጉባኤው አጠቃላይ የጸጥታና ሰላም አቀራረብን የያዘ ተጨባጭ የአሚሶምሱማሊያ መር የሽግግር እቅድ እንዲዘጋጅ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ ጉባኤው በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ የአሚሶም መሪዎችና የሱማሊያ መንግስት በቀጣዩ ጉባኤ ላይ የሚቀርብ እቅድ ለማዘጋጀት
ተቀራርበው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ስለ ቅድመ ጉባኤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ሲናገሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላምና ጸጥታ አምባሳደር እስማኤል ቼሩጊ ሱማሊያ በአዎንታዊ መንገድ ላይ እንደምትገኝና በጸጥታና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ጉልህ መሻሻል እያመጣች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኃላፊ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎችን መልሶ ለመገንባት፣
አሳታፊ ፖለቲካ ለመፍጠር መንገድ የሚጠርግ፣ የህገ መንግስት ምርመራ ሂደትን የሚያመቻች እና በ2020 አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚሰጥበት የምርጫ አሰራር እውን ማድረግ የሚቻልበት ብሄራዊ የጸጥታ መዋቅር መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው በሱማሊያ የፖለቲካ መረጋጋት መፈጠር ዋናው ቡድን ረቂቅ የሽግግር ሰነድ ያዘጋጀበት የሱማሊያ የሽግግር እቅድ እንዲጀመር ለማድረግ እንዳስቻለ ጠቅሰዋል፡፡ እቅዱ የኦፕሬሽኖች ንድፈ ሀሳቦችን መከለስን እና ውጤታማነቱን ማሻሻልን ጨምሮ ለአሚሶም የሽግግር እቅድ ወሳኝ ግብአት ሆኖ እንደሚያገለግል አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ነሀሴ የጸደቀው የዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2372(2017) ከሱማሊያ ቀስ በቀስ፣ በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የወታደሮች ከሱማሊያ ማስወጣትን እና ብሄራዊ የጸጥታ ኃላፊነቶችን በዙር በዙር ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ሃይሎች ማስተላለፍን ይፈቅዳል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ማስወጣት ባለፈው ታህሳስ 1 ሺ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን በዚህም የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ቁጥር ከ22,126 ወደ 21,626 ቀንሷል፡፡ ሆኖም ይህ በቀሪ ወታደሮች ላይ የተግባርና ኃላፊነቶች ጫና እንዲጨምር አድርጓል፡፡
የሽግግር ጓድ ቡድን
የ
ሱማሊያ ፌደራል መንግስት፣ አሚሶም፣ ዩኤን፣ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮችን እና ሌሎች ዋና ዋና አለም አቀፍ አጋሮችን የሚይዘው የሽግግር ጓድ ቡድን ለሱማሊያ የሽግግር እቅድ እያዘጋጀና ብሄራዊ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ኃይሎች ማስተላለፍ ሂደትን እያስተባበረ ነው፡፡ ቡድኑ በሱማሊያው ፕሬዝዳንት ብሄራዊ የጸጥታ አማካሪ እየተመራ ለፕሬዝዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሽግግር ሂደቱን እንዲመሩና ለሽግግር አቀራረቡ እገዛ ያደርጋል፡፡ የቡድኑ ዋነኛ አላማ ‹‹ብሔራዊ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለማስተላለፍ የሚያስችል ተጨባጭ፣ በዙርና ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ እና ወቅቱን የጠበቀ ሽግግር የሚደረግበትን እቅድ ማቅረብ ነው፡፡ እንደ የሽግግር ሂደቱ ቅድመ ሁኔታ አሚሶም የሀይል ግብአት ደረጃዎችን እና የሀይል ማጠናከሪያዎችን
አምባሳደር ፍራንጬስኮ ማዲዬራ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሶማሊያ ተልዕኮ (ኤስአርሲሲ) ልዩ ተወካይ እና የተመድ ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ከሚካኤል ኪቲንግ የተባበሩት ምንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በጥምረት በሞቃዲሾ በተደረገው ጉብኝት ላይ አጅበው ይታያሉ፡፡
መገምገምን ጨምሮ ሽግግሩ የሚፈጸምባቸውን መርሆዎች ለመወሰን የሽግግር እቅድ ዝግጅት ስብሰባ እንዲካሄድ የጠየቀ ሲሆን የፌደራል መንግስቱና የፌደራል መንግስቱ አባል ግዛቶች አመራሮች
ለአሚሶም ‹‹ያልተከፋፈለ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት›› እንዲኖራቸው ጥሪ አድርጓል፡፡›› የአሚሶም ምክትል የተልእኮ ኃላፊ ሲሞን ሙሉንጎ በመዲናዋ መቋዲሾ በመጋቢት ወር በሽግግር እቅድ ዝግጅቱ ላይ
ለመወያየት በተጠራው ስብሰባ ላይ ‹‹ይህ በተደራጀ መልኩ፣ ቀስ በቀስና በዘዴ ኃላፊነትን ከአሚሶም ወደ ኤፍጂኤስ የማስተላለፍ ሂደት ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
11
የአሚሶም የገንዘብ ማሰባሰብ ምክክሮች
ለ
አሚሶምና የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ገንዘብና ድጋፍ ማሰባሰብ ለለፉት ወራት የሱማሊያ የሽግግር እቅድ ዋነኛ የመወያያ ርእስ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በመጋቢት ወር በካምፓላ በተካሄደው የቲሲሲ ሀገራት መሪዎች ጉባዔ በቲሲሲ ሀገራት፣ በሱማሊያ መንግስት፣ የአፍሪካ ህብረትና አለም አቀፍ አጋሮች መካከል የሽግግር እቅዱን ለማስጀመር የሚያስፈልገው ገንዘብ እንዲለቀቅ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የአሚሶም ገንዘብ ማሰባሰብ አማካሪ ልዩ ልዑክ በሚያዚያ 1 ለአፍሪካ ቀንዷ ሀገር የሰላም ማስፈን ስራዎች ቀጣይነት ያለው የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት መቋዲሾ መጥተው ነበር፡፡ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዑካን የሆኑት ራምታኔ ላማምራ እና ዣን ሜሪ ጉሄኖ የሀገሪቱን ጸጥታ ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ የተሰሩትን ስራዎች ወደ ኋላ በማይመልስ መልኩ ቀስ በቀስ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ኃይሎች የማስተላለፍ አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ ሁለቱ ልዑካን ከፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ ፋርማጆ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀሰን አሊ ካሪ፣ የአፍሪካ ህብረትና የዩኤን የሱማሊያ ልዩ ተወካዮች አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴራና ማይክል ኪቲንግ፣ ለሱማሊያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ካዋጡ ሀገራት አምባሳደሮች እና ከአውሮፓ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሒ ሞሐመድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልዕኮ ልዑክ ራማታኔ ላማምራ እን የተባበሩት ምንግስታት ደርጅት ልዑክ ጁን ማሬሮ ጉሄየኖ ቪላ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ውስጥ ስብሰባ አድርገዋል፡፡ የአፍሪካን ህብረት የሶሞሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) የጥምረት የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ጉብኝት ልዑካን ናቸው፡፡
በእነዚህ ቡድኖች መካከል የተካሄደው ውይይት የጸጥታ ኃላፊነቶች በተሳለጠ ውጤታማ መልኩ ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለማስተላለፍ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ የዩኤኑ ልዑክ ‹‹ቀስ በቀስ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ ባለስልጣናት የማስተላለፍ ሂደቱ አስከ አሁን ድረስ የተደረጉትን ሁሉንም ጥረቶች መና በማያስቀር መልኩ መካሄድ አለበት›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ጉጌኖ በተጨማሪም በሱማሊያ የጸጥታና የሰላም
ዣን ሜሪ (ከበስተግራ ሁለተኛ) በሱማልያ መቋዲሾ ውስጥ የተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ተልእኮ እና የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ ዩኤን ለአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) በዩኤን የገንዘብ ድጋፍ ምክክር ላይ ሲናገሩ፡፡
12
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ኤስአርሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ እና የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ የሱማሊያ ልዩ ተወካይ ማይክል ኪቲንግ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ የጋራ ተልእኮ በሱማሊያ መቋዲሾ ለጋራ ምክክር የተገናኙትን የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ህብረት ልዑካን ሲያገኙ፡፡
ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ በርካታ የተለያዩ ድጋፍ ሰጪዎች መሳተፍ እንዳለባቸው እና ዘላቂነት ያለው ሰላም መስፈንን ማሳካት አስፈላጊ እንደሆነ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ‹‹በቀጣዩ ዙር የሁሉም አካላት ትብብር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነና ይህን በጣም አስቸጋሪ ጉዳይ አይደለም›› በማለት ተናግረዋል፡፡ የልዑካኑ የሱማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ የማጥናት ጉዞ በቀጣይ በአፍሪካ ህብረትና ዩኤን ለአሚሶም በሚደረጉ የሰላም ማስከበር ድጋፍ ተግባሮች ላይ የሚደረጉ ምክክሮች አካል ነው፡፡ በመጋቢቱ የካምፓላ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የተከበሩ ፋቂ ማሃማት ‹‹ልዩ ልዑኩ አጋር ሀገራትን፣ ለአሚሶም ሰላም አስከባሪ ወታደሮች
የላኩ ሀገራትን እና ሌሎች ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የአመለካከት ልዩነታቸውን የሚያስታርቁበትና ፕሮግራም ተኮርና ፖለቲካዊ ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ይዘው የሚመጡበት የጋራ ምክክሮች ማካሄድ ጀምሯል፡ ፡ የምክክሮቹ ውጤት ለሚመለከታቸው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት አካሎች ይቀርባል›› በማለት ተናግረዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ከአልጄሪያ፣ ጋና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ቃታር፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ስዊድን፣ ቱርክ፣ የተባበሩት ረብ ኢሜሬትስ፣ የናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ህብረት የተውጣጡ አለም አቀፍ አጋሮች ተሳትፈዋል፡፡
የአይኢዲዎች ጦርነት
ሱ
ማሊያ ጾታ ሳይለዩ ጥቅም ላይ እየዋሉ ለሚገኙት በቤት ውስጥ የሚሰሩ ፈንጂ መሳሪያዎች ዘላቂ መፍትሄ ለመሻት የታቀደውን አራተኛውን የግማሽ አመት የምላሽ መስጫ የአይኢዲ ኮንፍረስን በሚያዚያ 16 በመዲናዋ ሞቃዲሾ አካሄደች፡፡ ኮንፍረንሱ የተካሄደው በአሚሶምና በዩናይትድ ኪንግደም ድጋፍ ሲሆን ከሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን፣ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ተወካዮችን፣ የተባበሩት መንግስታትን እና አለም አቀፍ አጋሮችን ባገናኘው በዚህ ጉባኤ በአሸባሪ ቡድኑ አልቃኢዳ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ውጤታማ
በሆነ መልኩ ለመመከት የአሚሶምን እና የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎችን አቅም መገንባት የሚቻልባቸውን አዋጭ ዘዴዎች በመፈለግ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ በሱማሊያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሰብሳቢ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ ሱማሊያ ውስጥ በቤት ውስጥ በሚሰሩ ፈንጂ መሳሪያዎች (አይኢዲዎች) የተነሳ በጸጥታ ሀይሎችና ሲቪል ማህበረሰቡ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል፡፡ አምባሳደሩ የሱማሊያ መከላከያ ሰራዊት፣ ፖሊስና
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሊቀመንበር የሶማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ምክትል የሃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሀሩሺማና ሳልቫቶር፣ እና የእንግሊዝ ጦር ሀይል የሶማሊያ አዛዥ ኮሎኔል ሪቻርድ ሙንድሬ መቋዲሾ ሶማሊያ በቀን አይኢዲዎችን መከላከል ላይ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በተከፈተው ኤግዚቢሽን በቤት ውስጥ የሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎች ናሙና ሲመለከቱ፡፡
ኮሎኔል ሪቻርድ ሙንድሬል በሚያዚያ 16/2018 በሶማሊያ መቋዲሾ በቤት ውሰጥ የሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎችን (አይኢዲዎችን) መከላከልን አስመልክቶ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
የፌደራል መንግስቱ የአይኢዲዎች ያልተገደበ ጥቅም ላይ መዋልን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመከላከል መተባበር እንዳለባቸው እና ይህን በአይኢዲዎች ላይ የሚካሄድ ጦርነት ለማሸነፍ ውጤታማ የሆነ የደህንነት ስራ መስራትና ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር መረጃ መለዋወጥና በአጋርነት መንቀሳቀስ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ የእንግሊዝ የሱማሊያ ሀይል አዛዥ ኮሎኔል ሪቻርድ ማውንድሬል የአይኢዲ ምንጮችን ለማጥፋት በባለድርሻ አካላትና የጸጥታ ድርጅቶች መካከል የበለጠ ትብብር መካሄድ አለበት የሚለውን የማዴይራን ሀሳቦች አስተጋብተዋል፡፡ ‹‹ይህን ለማሳካት በእነዚህ ደረጃዎችና ድርጅቶች መካከል መረጃ መለዋወጥና ትብብር ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ሀይል ማዘጋጀትና
መሳሪያዎቹን መግታት አስፈላጊ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ለአይኢዲ ጦርነት ምላሽ ለመስጠት ብቸኛው ዘዴ ለአይኢዲ ሲስተሞች ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ዘመቻዎች መክፈት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአይኢዲ አዘጋጆች ላይ የሚያተኩር ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ኮንፈረንሱ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል ምንጮቹን ለመዋጋት የፎረንሲክ ጥቅም ላይ መዋል መበረታታት እንዳለበት እና አይኢዲዎችን በመመርመርና በማክሸፍ ረገድ ለሙያተኞች ጥልቅ ስልጠና መሰጠት እንዳለበት ወስኗል፡፡ አሚሶም፣ የሱማሊያ ፌደራል መንግስትና የልማት አጋሮች በአሁኑ ወቅት ለአይኢዲ ጥቃቶች ምላሽ መስጫ ስትራቴጂዎችን ለመንደፍና እስካሁን የተገኙ ድሎች እንዳይሸረሸሩ ለመጠበቅ በመስራት ላይ ናቸው፡፡ አሚሶ ም መ ጽሔ ት
13
ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለአይኢዲዎች ምላሽ መስጫ ስልጠና መስጠት
ከ
ውትድርና ባሻገር ላለፉት በርካታ ወራት ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለአይኢዲዎች ምላሽ መስጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ለሱማሊያ አጋሮቹ የአይኢዲ ጥቃቶችን በመከላከል፣ በማስቀረትና ምላሽ መስጠት ዋና ዋና ክህሎቶች ላይ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እያደረገ ነው፡፡ የአሚሶም ፖሊስ የሽብርተኝነት ምላሽ አሰልጣኝ የሆኑት አይፒ ሀሰን ጉሀድ አብዱላሂ በአዲሱ አመት
መጀመሪያ ላይ በአንድ ስልጠና ላይ ሲናገሩ አልሸባብ በሱማሊያ እያደረገ ያለውን ያልተገደበ አይኢዲዎች መጠቀም ፈንጂዎቹ በሲቪሉ ማህበረሰብ እና በጸጥታ ሀይሎች ላይ እያደረሱ ያሉትን ተጽእኖ ኮንነዋል፡፡ በሞቃዲሾ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ለኦፊሰሮች ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርገው ለመግባትና የአይኢዲዎች ጥቃቶችን ለመፈጸም በሚጠቀሙባቸው ቴክኒኮችና ዘዴዎች ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
የሶማሊያ ፖሊስ ኦፊሰሩ ቨበቤት ውስጥ በሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎች (አይኢዲ) ስልጠና ገለጻ ላይ አንድ ኦፊሰር ሲቀበሉ፡፡
የአሚሶም ፖሊስ በደቡባዊ ምዕራብና በጂባ ላንድ ክልሎች ለሚገኙ የፖሊስ ኦፊሰሮች ተመሳሳይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በደቡብ ምእራብ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ባይድዋ ስልጠናው ላይ የአሚሶም ፖሊስ አስተባባሪ ትሬስፎርድ ካሳል ታድመዋል፡፡ ‹‹በአይኢዲና ኢኦዲ (የፈንጂ መሳሪያዎች አወጋገድ) ላይ በተሰጠው ስልጠና ከሱማሊያ ፖሊስ ሀይል የተውጣጡ 15 ሰልጣኞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የዚህ ስልጠና አላማ ለኦፊሰሮቹ አይኢዲዎችን ለይተው ለማወቅ፣ እነዚህን ለማክሸፍ ኤክስፐርቶችን መጥራትና በጥንቃቄ ማክሸፍ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው›› በማለት ካሳል አብራርተዋል፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ኢንስፔክተር ሻር ኢማኑኤል ኮባይ-አሩና ስልጠናው ደቡብ ምእራብ ፖሊስ ሀይል አቅም ለማሳደግ የታለመ እንደሆነና ለኦፊሰሮቹ በበርካታ የደህንነትና ጸጥታ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርት እንደተሰጠ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ይህ ከአሚሶም የሱማሊያ ፖሊስ ሀይልን አቅም ከማጎልበት ተልእኮ ውስጥ አንዱ ሲሆን ስለ ተወሰኑ የአይኢዲ/ኢኦዲ ክፍሎች፤ የአይኢዲ/ኢኦዲ አይነቶችና ሌሎች የቁጥጥር ኮርስ ሞጁሎች አስተምረናቸዋል፡ ፡ በተጨማሪም የወንጀል ድርጊት ስለሚፈጸምባቸው ቦታዎች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታና የጉዳት ግንዛቤ ጥናት አስተምረናቸዋል›› በማለት ሚ/ር ኩባይ አሩና ተናግረዋል፡፡ ከሰልጣኞቹ አንዱ የሆኑት ሚስ. ፋሪያ አህመድ መሀመድ ትምህርቱ ወቅቱን የጠበቀና ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲፈጽሙ የሚያግዛቸው እንደሆነ
14
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የጸረ ሽብርተኝነት የፖሊስ አሰልጣኝ በታህሳስ 31/2017 መቋዲሾ ውስጥ በበቤት ውስጥ በሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎች (አይኢዲ) ስልጠና ላይ ለፖሊስ ኦፊሰሮች ገለጻ ሲያደርጉ፡፡
‹‹ኦፊሰሮቹ ከተማሯቸው ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ ጥቃት አድራሾቹን ጉዳት እንዳያደርሱ እንዴት መከላከል እንደሚቻል እና በሚሰበሰብ የደህንነት መረጃ ላይ ተመስርቶ ጥቃት የመፈጸም አቅማቸውን ማዳከም እንዴት እንደሚቻል የተመለከተ ነው›› በማለት አይፒ ሀሰን አብራርተዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽ/ ቤት (ዩኤንኦፒኤስ) በኩል በጃፓን መንግስት ድጋፍ የሚሰጠው የአይኢዲ ስልጠና
እንዴት ከአይኢዲ ጥቃቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ለተለያዩ ክስተቶች ምላሽ መስጠት እንደሚቻል የተመለከቱ የተግባር ሙከራ ክፍለ ጊዜዎችን ይዟል፡፡ በታህሳስ/ጥር ከተሰጠው የአስር ቀናት ስልጠና ተጠቃሚ የሆነው የፖሊስ ኦፊሰር አብዲ አደን ጋል ‹‹ለእኔምና የስራ ባልደረቦቼም ሆነ ለሱማሊያ ፖሊስ ሀይል የሚረዱ በርካታ የተለያዩ ጠቃሚ ነገሮችን ተምሬያለሁ፡፡ ስልጠናው ለሚያዬ እጅግ ጠቃሚ ነው›› በማለት ተናግሯል፡፡
ከደቡብ ምእራብ ግዛት የተውጣጡ የፖሊስ ኦፊሰሮች በቤት ውስጥ የሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎች እና በቀላል የሚሰሩ ተቀጣጣይ መሳርያዎች ላይ የተሰጠውን ስልጠና ሲከታተሉ፡፡
አስረድተዋል፡፡ ‹‹ዛሬ በአሚሶም የተዘጋጀውን የአይኢዲ/ኢኦዲ ትምህር ያጠናቀቅን ሲሆን የምስክር ወረቀትም ተሰጥቶናል፡፡ ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ነገሮችን ተምረናል፣ ለምሳሌ መሬት ውስጥ የሚቀበሩ ፈንጂዎች የት እንደሚቀበሩ ስለመመርመር ተምረናል፡ ፡ በተጨማሪም ለተጎጂዎች እንዴት የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንደምንሰጥና ተጊጂዎችን እንዲት ህክምና እንዲያገኙ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል መውሰድ እንዳለብን ተምረናል›› በማለት ከሰልጣኞቹ አንዷ የሆኑት ሚስ ፋሪያ አህመድ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ አሚሶም የደቡብ ምእራብ ፖሊስ ሀይልን በማቋቋም ላይ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በግዛቷ ለ600 የፖሊስ ኦፊሰሮች ስልጠና የሰጠ ሲሆን ኦፊሰሮቹ በአሁኑ ወቅት በግዛቱ የተለያዩ የጸጥታ ተግባሮች ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ በተጨማሪም በጁባ ላንድ
አሰልጣኝ ኢቬሊን ለደቡብ ምእራብ ፖሊስ ኦፊሰሮች ለተወሰነ ቀን በቤት ውስጥ በሚሰሩ ፈንጂ መሳርያዎች እና በቀላል የሚሰሩ ተቀጣጣይ መሳርያዎች ላይ በተሰጠው ስልጠና ላይ ከሰልጣኞቹ ላንዱ የምስክር ወረቀት ሲሰጡ፡፡
ለሌሎች 600 ኦፊሰሮች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በትምህርት አመቱ ውስጥ በሂርሸበሌ ግዛት ተጨማሪ ኦፊሰሮችን መልምሎ ስልጠና ለመስጠት ታቅዷል፡፡
በተባበሩት የአንግሊዝ ተልኮን በሚደግፈው ቡድን አጋርነት በተደረገው የአሚሶም የመረጃ ማካፈል ጉባኤ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ በአሚሶም ስር የሚያገለግሉ ወታደሮችና ሌሎች አጋሮች የተካፈሉበት ሂደት
የሽብር ድርጊት ጊዜያት የደህንነትና መረጃ ልውውጥ
አ
ላማውን በተለያዩ የደህንነት ተዋናዮች መካከል በቅርበት በትስስር መስራት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር እና በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ አሰራሮችና ትብብርን ማሻሻልን ያደረገው ሶስተኛው የደህንነትና መረጃ ልውውጥ ኮንፍረንስ በአሚሶም ምክትል ሀይል አዛዥ የኦፕሬሽኖችና እቅድ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ መሪነት በመጋቢት በሞቃዲሾ የተካሄደ ሲሆን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ የደህንነት መረጃ መለዋዋጥን ማስረጽ ላይ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ ‹‹ደህንነት የተልእኮውን የሰላም ማስከበር ስራ ውጤታማ በሆነ መልኩ የማከናወን ህጋዊነትና ወገንተኛ አለመሆን በማይፈታተን መልኩ ውጤታማ ተግባር ማከናወን በሚያስችል ሁኔታ መሰብሰብና ጥቅም ላይ መዋል አለበት›› የተናገሩት ሜጀር ጀነራል ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ የደህንነት መረጃ ለመሰብሰብ ባህላዊ የመረጃ ምንጮችን እና የተሻሻሉ የደህንነት መረጃ ልውውጦችን መጠቀም ባለፉት ጊዜያት
የሽብርተኝነት ጥቃቶችን ለመከላከል ወሳኝ እንደሆነ መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡ ጉባኤው በተጨማሪም የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን ከፌደራል መንግስቱ፣ የአፍሪካ ህብረትና አጋር ሀይሎች ከፍተኛ ጥቃት ስለደረሰበት አቅም መዳከሙን ተከትሎ ሊጠቀምባቸው በሚችሉ አዲስ የጥቃት መሰንዘሪያ ዘዴዎች ላይ ተወያይቷል፡፡ ሜጀር ጀነራል ጊቱዋይ ከአሚሶም ዘርፎች የተውጣጡ የደህንነት ኦፊሰሮችን፣ የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ተወካዮችን እና ዋና ዋና አለም አቀፍ የጸጥታ አጋሮችን ለያዙት ተሳታፊዎች ‹‹ደህንነት ለሰላም ማስከበር ተልእኮ በተለይም ለውሳኔ ሰጪዎች በተልእኮው የተለያዩ ክፍሎች በሚካሄድ የተቀናጀ የመረጃ ትንተና አማካኝነት ስለ አንድ ሁኔታ በተለያየ አቅጣጫ የማየት ግንዛቤ ለመፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ሜጀር ጀነራል ጊቱዋይ የሚሰበሰበው መረጃ ለሁሉም ባለድርሻ አካለት ጠቃሚ በሆነ መልኩ እንዲገለጽና በሚስጥር እንዲያዝ ለማድረግ የሚያስችል ‹‹ውጤታማ
የአሚሶም ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ቻርለስ ታይ ጊቱዋየ ከዩናይትድ ኪንግደም ተልእኮ ድጋፍ ሰጪ ቡድን (ዩኬኤምኤስቲ) ጋር በተካሄደው የመረጃ ልውውጥ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (አሚሶም) ውስጥ በሶማሊያ በማገልገል ላይ የሚገኙ ወታደሮች፣ እና የሶማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ኦፊሰሮች (ኤስኤንኤ)፣ የተባበሩት መንግስታትና የዩናይትድ ኪንግደም የጦር ሰራዊት አባላት ከዩናይትድ ኪንግደም ተልእኮ ድጋፍ ሰጪ ቡድን (ዩኬኤምኤስቲ) ጋር የተካሄደውን የመረጃ ልውውጥ ስብሰባ ሲከታተሉ፡፡
የአሰራር ሂደትና መዋቅር›› አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የአሚሶም ዋና የወታደራዊ ደህንነት ኦፊሰር ኮሎኔል ናቦዝ ምዌሲግዋ በበኩላቸው ኮንፈረንሱ ‹‹የደህንነት መረጃ ስብሰባን ከማጠናከር›› ጎን ለጎን በአጋሮችና በሱማሊያ ፌደራል መንግስት መካከል መተማመንንና ትስስርን በመፍጠር የመከላከያና ሌሎች የማጥቂያ ችሎታዎችን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ ኮንፍረንሱ የተዘጋጀው ከዩናይትድ ኪንግደም የተልእኮ ድጋፍ ሰጪ ቡድን (ዩኬኤምኤስቲ) ጋር በመተባበር ነው፡፡ አሚሶ ም መ ጽሔ ት
15
አሚሶም የአካባቢ ቅኝት መሳሪያ አገኘ
አ
ዲሱ በዩኤስ የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው የአካባቢ ቅኝት ሲስተም የደህንነት መረጃ አሰባሰብን ለማሳደግ በሱማሊያ የታችኛው ሸበሌ ክልል በባሌዶግል ወታደራዊ አየር ማረፊያ ተተከለ፡፡ የአሚሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴይራ ዩናይትድ ስቴትስን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ለአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ተልእኮ እያደረገች ስለምትገኘው ተከታታይ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ማዴይራ ባለፈው የካቲት የቅኝት መሳሪያውን በተረከቡበት ወቅት ‹‹መሳሪያው ለአሚሶም ሀይል ካሉበት የአቅም ችግሮች ውስጥ አንደኛውን በመቅረፍ ረገድ እጅግ ወሳኝ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ መሳሪያው በአልሸባብ ላይ ለሚካሄዱ ወታደራዊ ዘመቻዎች አስፈላጊ ወታደራዊ አቅሞች ክፍተቶችን ይሞላል፡፡ ተልእኮው የአልሸባብ ታጣቂዎች በስፋት በሚገኙበት የደቡብ ማእከላዊ ሱማሊያ ክልል ጠንካራ የጥቃት ዘመቻዎችን ለመሰንዘር አቅዷል፡፡ የዩኤስ የሱማሊያ ተልእኮ ተወካይ ማርቲን ዴል የዩኤስ መንግስት በሱማሊያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹እዚህ የተገኘነው የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮቻችሁን ደህንነት የሚጠበቅበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ብቻ ሳይሆን የሱማሊያ ህዝብ የተሻለ ህይወት መምራት እንዲችል በአሸባሪዎች ላይ የሚደረገውን ጫና ከፍ ለማድረግ እርዳታ ለመስጠት ነው፡፡ አሁን ሁሉም ሰው በአንድነት አብሮ መስራት ያለበት ጊዜ ነው፡፡ ግፊቱን ለመጨመር ሁላችንም በአንድ ላይ መስራት አለብን›› በማለት ዴል ተናግረዋል፡፡ ሚ/ር ዴል በተጨማሪም ‹‹ይህ ወሳኙ ክፍል ነው›› ካሉ በኋላ ‹‹ሱማሊያውያን በጸጥታቸውና ብልጽግናቸው
16
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ላይ መዋእለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉ ሲሆን እኛ እዚህ የተገኘነው ይህን ሁኔታ
የአሚሶም ሀይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጂም ቢኦውዬሲግሬ እና ሌሎች የአሚሶም ሀላፊዎች ባሌ ዶግሌ፣ሶማሊያ ውስጥ በዩኤስ ሃላፊዎች ያለትጥቅ አካባቢያዊ ቅኝት ስለሚያካሄድ ተሸከርካሪ ገለጻ ሲደረግላቸው፡፡
ለማመቻቸት ነው›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ሆዜማዴራ በ26/02/2018 ባሌ ዶግሌ፣ሶማሊያ ውስጥ በዩኤስ ሃላፊዎች ያለትጥቅ አካባቢያዊ ቅኝት ስለሚያካሄድ ተሸከርካሪ ገለጻ ሲደረግላቸው፡፡
የዩኬ ለአሚሶም ሽብርተኝነትን በመቀነሱ ምስጋናውን ገለጸች
የ
ዩኬ የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ሚኒስትር አርቲ. የተከበሩ ማርክ ላንካስተር ሱማሊያን የጎበኙ ሲሆን ለአፍሪካ ህብረት ወታደሮች የሀገሪቱን ጸጥታ በማስከበርና የሽብርተኝነት ስጋትን በመቀነስ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሱማሊያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ መዳይራ እና የአሚሶም ሀይል አዛዥ ሌተ. ጀነራል ጂም ቢሲጌኦወዬሲግሬ ጋር የተገናኙ ሲሆን የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ማሸጋገር እና ዩኬ ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በምትሰጠው ድጋፍ አይነትና ይዘት ላይ ተወያይተዋል፡፡ ሚ/ር ላምካስተር ‹‹ንግግሬን አሚሶም ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ ላደረጋቸው አስተዋጽኦዎችና የከፈላቸው መስዋእትነቶች ምስጋናዬን በመግለጽ እጀምራለሁ፤ ምክንያቱም ያለ ምንም ጥርጥር አሚሶም ባለፉት ሰባት አመታት ውስጥ የሰራቸው መልካም ስራዎች ባይሰሩ ኖሮ ሱማሊያ አሁን በምትገኝበት የመሻሻል ሂደት ላይ መገኘት ስለማትችል ነው›› በማለት ተናግረዋል የዩናይትድ ኪንግደም ተልእኮ ድጋፍ ሰጪ ቡድን (ዩኬኤምኤስቲ) በዩኬ-70 ኢኒሺየቲቭ ስር በሞቃዲሾና
የዩኬ መከላከያ ሃይል ሚኒስቴር ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) እንዲያገለግል በወታደሮች የተተከለው መጠበቂያ ማማ ላይ ፍተሻ ሲያደርጉ፡፡
ሌሎች ክልሎች ለአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮችና የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች የስልጠና ድጋፍ ይሰጣል፡፡ የዩኬ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ‹‹ተልእኮውን የበለጠ ለመደገፍ ማድረግ በምንችላቸው ነገሮች ላይ የተወያየን ቢሆንም በተመሳሳይ ሁኔታ በመጪዎቹ ወራትና አመታት በሱማሊያ ያለውን ሁኔታ እንዴት እንደምናሻሽልም ተነጋግረናል›› ብለዋል፡፡
የዩኬ የአሚሶም ምክርና ስልጠና ድጋፍ በሎጅስቲክስ፣ ህክምናና ከባድ ምህንድስና ችሎታዎች ላይ ይሰጣል፡፡ አምባሳደር ማዴይራ ከሚ/ር ላንካስተር ጋር ከተገናኙ በኋላ ‹‹እኛ እዚህ እያደረግን ላለው ስራ ዩኬ ፍላጎቷን ለማሳየት የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ሚኒስትሯን በመላኳ እጅግ ተደስተናል፡፡ ጉብኝቱ በራሱ የዩኬ መንግስት ከፍተኛ አባል እዚህ በጦርነት ሜዳ ከእኛ ጋር አብረው
ናቸው የሚለውን ስሜት የሚፈጥርልን በመሆኑ እጅግ ጠቃሚ ነው›› ብለዋል፡፡ ሚ/ር ማዴይራ አሚሶም ሱማሊያ ከሚገኘው የዩኬ ተልእኮ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳለው ገልጸው ቡድኑ ለአሚሶም ተልእኮ እስከ አሁን ድረስ እየሰጠ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ሚኒስትሩ የመከላከያ ሀይሉን የስራ እንቅስቃሴዎች የዘ፡፡
የዩኬ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለአሚሶም ድጋፍ አደረጉ
የ
ዩኬ መከላከያ ሰራዊት አባላት ቡድን በዩኬ-70 ኢኒሺዬቲቭ አማካኝነት ሱማሊያ ለሚገኙት የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ስልጠና የሰጡ ሲሆን ስልጠናው ዩኤን ለአሚሶም የሚሰጠው ድጋፍ አካል ነው፡፡ የዩኬ መከላከያ ሚኒስቴር እንደሰጡት መግለጫ እንደ ዩኬ ጠቅላላ ቃል ኪዳን አንድ ክፍል የዩኬ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለአሚሶም የህክምና፣ ሎጅስቲክስና የምህንድስና ድጋፍ እየሰጡ ነው፡፡
በኢኒሺዬቲቩ ስር ቡድኑ በሱማሊያ መዲና መቋዲሾና ሌሎች የፌደራል አባል ግዛቶች ለሚገኙት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች እንደ ዩኬ ሱማሊያን የማረጋጋት አስተዋጽኦ ቃል ኪዳን አንድ ክፍል ለሰላም ማስከበር ጥረቶችና በሱማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው፡፡ የአሚሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ በቅርቡ የዩኬ የመከላከያ ሚኒስቴር ምክትል
በዩኬ-70 ስር በሶማሊያ ዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ህክምና ስልጠና ቡድን አባል በአሚሶም የህክምና ሙያተኞች በጥይት ቁስለት የሚከሰት የደም መፍሰስ እንዴት ማቆም እንደሚቻል ገለጻ ሲያደርጉ፡፡
ሚኒስትር አርቲ. የተከበሩ ማርክ ላንካስተር ሱማሊያን በጎበኙበት ወቅት ‹‹ዩኬ70 ብዙ ነገሮችን ከእኛ ጋር ከመስራት በተጨማሪ በስራችን ላይ የበለጠ ውጤታማ እንድንሆን እያስቻለን ነው፡፡ አሁን ጠቅላላ የአይኤስአር (ደህንነት፣ ቅኝትና ቁጥጥር) ሲስተም ያለን ሲሆን ይህን በቦታው ላይ ለመትከልና ስራ ላይ ለማዋል ረድተውናል›› ብለዋል፡፡ በሱማሊያ የሚገኙት 70ው የመከላከያ ሰራዊት አባላት
የዩኬ-70 ኃላፊዎች በባይድዋ የኤስኤስቲ የስልጠና ካምፕ የኤስኤንኤ ወታደሮች የካምፑን ስራ በሽቦ አጥር ሲያጥሩ ሲመለከቱ፡፡ ይህ በዩኬ ለአሚሶም እና የሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሚሰጠው የስልጠና ድጋፍ አንድ ክፍል ነው፡፡
በውጊያ እንቅስቃሴዎች ላይ አይሳተፉም፡፡ የተልእኮ ድጋፉ ዳይሬክተር፣ ዩኒሶምና ዳይሬክተር፣ ዩኤንኤስኦስ አማዱ ካማራ በበኩላቸው ‹‹ይህን ኢኒሺየቲቭና የሚደረግልንን ድጋፍ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል፤ ምክንያቱም ለአዳዲስ የዩኤንኤስኦኤስ ፕሮጀክቶች ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ሙያዊ ክህሎቶች በሚጠይቁ ቦታዎች ላይ ሌሎች በቁጥር አነስተኛ ሰዎችን የያዙ ቡድኖችን ለማሰማራት አስችሎናል›› ብለዋል፡፡
የዩኬ ኃላፊ ኤስጂቲ አዳም አንደርሰን ኪስማዮ በሚገኘው የዩኤን ቅጥር ግቢ ውስጥ ለአሚሶም ወታደሮች በወታደራዊ ዘመቻዎች ወቅት እንዴት የተሽከርካሪ ሞተር እንደሚጠገን ሲያሳዩዋቸው፡፡ ይህ በዩኬ ለአሚሶም እና የሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሚሰጠው የስልጠና ድጋፍ አንድ ክፍል ነው፡፡ አሚሶ ም መ ጽሔ ት
17
የአፍሪካ ህብረት ፒኤስኦዲ የሱማሊያ ዳሰሳ ጥናት ተልእኮ
የ
አፍሪካ ህብረት የሰላም ድጋፍ ኦፕሬሽኖች ምድብ (ፒኤስኦዲ) ልኡካን የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች የማስተላለፍ እቅዱን ከማፋጠን ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ የሰላም ማስከበር የስራ እንቅስቃሴዎችን ለመመለክት በየካቲት ሱማሊያን ጎብኝተዋል፡፡ በአራት ቀናቱ የሱማሊያ ጉብኝት 10 አባላትን የያዘው የልኡካን ቡድን ከአሚሶም ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የተባበሩት መንግስታት የሱማሊያ ድጋፍ ሰጪ ጽ/ቤት (ዩኤንኤስኦኤስ እና በሱማሊያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ካዋጡ ሀገራት አምባሳደሮች) ጋር ተወያይቷል፡፡ በፒኤስኦዲ የኦፕሬሽኖችና እቅድ ዋና ኃላፊ በሜጀር ጀነራል ፍራንሲስ ኦኬሎ የተመራው ልዑካን ቡድን በተጨማሪም በሱማሊያ ፕሬዝዳንት የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ በአብዲ ሰኢድ አሊ ከተመራው የሱማሊያ ፌደራል መንግስት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል፡፡ ውይይቶቹ በሰላም ማስከበሩ የስራ እንቅስቃሴዎች፣ የሱማሊያን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ስለተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም ወደ ሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ሀይሎች ማስተላለፍ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ የልኡካን ቡድኑን የተቀበሉት የአሚሶም ምክትል ሀላፊ ሲሞን ሙሎንጎ ‹‹የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ይህን የልኡካን ቡድን ወክሎ ወደዚህ የላከው ከእቅዱና ከተከናወኑ የስራ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ የተደረጉ ዝግጁነቶችን እንዲሁም
የአፍሪካ ህረብረት የሰላም ድጋፍ ሰጪ ኦፕሬሽኖች ምድብ (ፒኤስኦዲ) ልዑካን ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ፍራንሲስ ኦኬሎ በመቋዲሾ ከሰፈሩት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ካዋጡ ሀገሮች (ቲሲሲዎች) ተወካዮችና ሌሎች ከፍተኛ የአሚሶም ኃላፊዎች ጋር በተካሄደ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
እንደ ሱማሊያ ፌደራል መንግስት፣ የፌደራል መንግስቱ አባል ግዛቶች እና እንደ ዩኤንና በተለይም ዩኤንኤስኦኤስ ካሉት ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር
ያለንን ግንኙነቶች እንዲያጠና ነው›› በማለት አብራርተዋል፡፡ የሰላም ድጋፍ ሰጪ ኦፕሬሽኖች ምድብ (ፒኤስኦዲ) በአፍሪካ ህብረት ሁሉንም
የሰላም ማስከበር ድጋፍ የስራ እንቅስቃሴዎች እንዲያቅድ፣ እንዲተገብር፣ እንዲቆጣጠርና እንዲያዋህድ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡
በሜጀር ጀነራል ፍራንሲስ ኦኬሎ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ እና በሌሎች የአሚሶም ኃላፊዎች የተመራው የአፍሪካ ህረብረት የሰላም ድጋፍ ሰጪ ኦፕሬሽኖች ምድብ (ፒኤስኦዲ) ልዑካን ቡድን ከሱማሊያ ፕሬዝዳንት ብሄራዊ የጸጥታ አማካሪ አብዲሰኢድ ሙሳ አሊ ጋር ስብሰባ ሲያካሂዱ፡፡
ወቀስ
ፕሬዝድንት ፋርማጆ (ከግራ መሀከል) ጥቁር መነጽር ያደረጉትና የወታደር ልብስ የለበሱት እና ኤስአርሲሲ ማደይራ (ከቀኝ መሀከል) ቡኒ ሱፍ የለበሱት በአሁኑ ወቅት በቡሩንዲ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በተያዘው ጃሌ ሲያድ ወታደራዊ አካዳሚ (ሰኢድ ባሬ) ላይ ድንገተኛ ጉብኝት ሲያደርጉ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ጋር የተወያዩ ሲሆን ለወታደሮቹ አሚሶም ሱማሊያ ውስጥ እየሰራ ላለው መልካም ስራ ምስጋናቸውን ገልጸው በጥሩ ስራቸው እንዲገፉበት አበረታተዋቸዋል፡፡
18
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ ‹‹ፋርማጆ›› የኤስኤንኤ 58ኛ የመታሰቢያ ክብረ በአል ላይ (ፎቶ አባሪ ተደርጓል) ከአሚሶም ጋር በተደረገው የክብ ጠረጴዛ ውይይት (ገጽ 19) ላይ ‹‹መቋዲሾን ነጻ ማውጣት ቀላል የሚባል ስራ አይደለም፡፡ ስራው ከባድ ነበር፤ ለዚህ ትልቅ ስራ ከተማዋን ከአልሸባብ ታጣቂዎች ለማስለቀቅ የደምና የህይወት መስዋእትነት ለከፈሉት ወንድሞቻችን አሚሶም፣ የኡጋንዳና ቡሩንዲ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ያለኝን አክብሮት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ እዚህ በቆምንበት የመከላከያ ዋና ለመስሪያ ቤት ለመቆማችን በተከፈለው መስዋእትነት ከፍተኛ ደም ፈሷል፡፡ ሁልጊዜም ለአሚሶም መስዋእትነት የከፈሉ ወንድሞቻችን ታላቅ አክብሮት አለን፡፡ ወንድሞቻችን የሱማሊያን ሉአላዊነት ለመጠበቅ በየቀኑ ደማቸውን እያፈሰሰዉ መሆኑን በፍጹም መዘንጋት የለብንም፡፡ ሁልጊዜም አሚሶም የከፈለልንን መስዋእትነት ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ አሁንም ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊታችንን እንድናቋቁም እየረዱን ነው፡፡ እነዚህ ወንድሞቻችንን እያመሰገንን እግዚአብሄር ሱማሊያ በአንድ እግሯ ቆማ በተመሳሳይ የሰላም ማስከበር ተልእኮዎች አፍሪካን ነጻ ለማውጣት ተሳታፊ ሆነን እንዲያሳየን ያለኝን ምኞት እገልጻለሁ›› በማለት ተናግረዋል፡፡
በአሚሶም ዙሪያ
ባ
ለፈው የካቲት ወር ከሱማሊያ የቅርስ ጥበቃ ተቋም ጋር በመተባበር ባካሄደው የክብ ጠረጴዛ ውይይት በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ ተግባር ላይ የተሻለ መግባባት መፍጠርን አላማ አድርጎ ተልእኮው እስከ አሁን ድረስ በሱማሊያ በሰራቸው ስራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በአሚሶም ከፍተኛ አመራር የተልእኮ ስኬቶች፣ ጉድለቶች፣ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮች፣ የመውጫ ስትራቴጂዎችና ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች በሚሰጡ የስልጠና ፕሮግራሞች እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ በተደረገው ውይይት ላይ ፖለቲከኞች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ የትምህርት ባለሙያዎችና የጸጥታ ኤክስፐርቶች ተሳትፈዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ልዩ ተወካይና የአሚሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴራ እና ሌሎች የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች በህብረቱ ምንም አልተሰራም በሚል ለሚቀርቡ ክሶች አፍሪካ ህብረት በ2007 ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ቀንዷ ሀገር ከተሰማራበት ጀምሮ የስራቸውን ስኬታማ ስራዎች በዝርዝር መዝግበው አቅርበዋል፡፡ ማዴይራ ሱማሊያ የፖለቲካና የጸጥታ መረጋጋት ጊዜ ላይ እንደምትገኝ አብራርተዋል፡፡ ‹‹አሁን እየጨመረ የመጣ የሰዎች እንቅስቃሴና የንግድ እንቅስቃሴ፣ የግልም ይሁን የመንግስት እየጨመረ የመጣ የአለም አቀፍ አየር መንገዶች እንቅስቃሴ አለ፡ ፡ በሀገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማትን ቁጥር ሳንረሳ የሪል ስቴትና ግንባታው ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል፡፡ እነዚህ ተነጻጻሪ ስኬቶች የመጡት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል በመኖሩ ምክንያት ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የአሚሶም ዋና ኃላፊ በፖለቲካው መስክ ከተገኙ ዋና ዋና ስኬቶች ውስጥ የ2016/2017 የምርጫ ሂደትና አሳታፊ ፓርላማ መቋቋምን በመጥቀስ ይህ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሊቀመንበር የሱማሊያ ልዩ ተወካይ እና የአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ ሱማሊያ ውስጥ በአሚሶም የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ሲያደርጉ፡፡
ሊመጣ የቻለው አሚሶምና የሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ሀይሎች የቅርብ ትብብር በማድረጋቸው ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በማፋጠን ላይ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ አሁን ሱማሊያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ምቹ ሁኔታና የተሻለ መተማመኛ ተፈጥሯል›› ብለዋል፡፡
በአሚሶም የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ላይ አንድ ተሳታፊ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሊቀመንበር የሱማሊያ ልዩ ተወካይ እና የአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ ጥያቄ ሲያቀርብ፡፡
ማዴራ በተጨማሪም በተገኘው አንጻራዊ ሰላም የተነሳ የብድር ተቋማት በተለየም አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ ከ25 አመታት በኋላ ወደ ሀገሪቱ ተመልሰው መምጣታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ‹‹የአለም ባንክ በአሁኑ ወቅት ለሱማሊያ መንግስት ተቋማት መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ የኢኮኖሚ ማገገምና የስራ እድሎች ፈጠራን
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (ኤስአርሲሲ) ሊቀመንበር የሱማሊያ ልዩ ተወካይ እና የአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ እና ሌሎች ከፍተኛ ሀላፊዎች በተመራውና በ22/02/2018 በሱማሊያ በተካሄደው የአሚሶም የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ላይ የተካፈሉ ተሳታፊዎች ምስል፡፡
ባለፈው አመት አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሱማሊያ ኢኮኖሚዋን መልሳ ለማደራጀትና አስተዳደሯን ለማሻሻል ተጨባጭ እርምጃዎችን የምትወስድ ከሆነ አበዳሪዎች $5.3 ቢሊዮን ዶላር እዳዋን ሊቀንሱላት እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር፡፡ አምባሳደር ማዴራ አሚሶም የሱማሊያ የፌደራል መንግስት ለህዝቡ የተሻሉ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንዲችል ለማድረግ ከመንግስት ጋር ያለው ትብብር እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ‹‹እነዚህ ሁሉም ነገሮች እየተከሰቱ ያሉት አሚሶም ለመንግስት በፍትህ፣ ሥነ ጾታ፣ የእርቅ፣ የግጭት አስተዳደርና አፈታት ለመንግስት ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ማዴራ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በጸጥታው ግንባር ረገድ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት አረጋግጠው የወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ እየተከፋፈለ መምጣት ለሱማሊያ መረጋጋት ትልቁ ፈተና እየሆነ መምጣቱን እንዲሁም ለአመጽ ድርጊት የመመልመል፣ ማሰልጠንና በሀሳብ የመጋት ተግባሮችን ኮንነዋል፡፡ የባህልና ቅርስ ጥበቃ ተቋም ኃላፊው አብዱራሺድ ሀሺ ውይይቶቹ አሚሶም ሱማሊያ ውስጥ እየተጫወተ ያለውን ሚና በበለጠ ለማስገንዘብ ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
19
በግጭት ቀጠናዎች የሚደርሱ ጉዳቶችን መቆጣጠር
የ
አሚሶም 39 ወታደራዊ የህክምና ሙያተኞችን የያዘ ቡድን በድንገተኛ ጊዜ ክትባቶች፣ ከፍተኛ ውጥረት ባለባቸው ቦታዎች የጉዳቶችንና በጭንቀት ውስጥ ያሉ ታማሚዎች አስተዳደርን በተመለከተ ማብራሪያ በተሰጠበት አውደ ጥናት ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በእያንዳንዱ መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ የሚሰጠው ማብራሪያ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ሁሉም የህክምና ሰራተኞቹ የጦርነት ሜዳ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ፣ የተጎጂዎች ክትባትና እንክብካቤ፣ የመድሀኒት አያያዝና የህክምና ተረፈ ግብአቶች ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚያካሂደው የህክምና ድጋፍ እቅድ አንዱ ክፍል ነው፡፡ የሶስቱ ቀናት ማብራሪያ አመቻቾች የዩኬ ወታደራዊ ስለጠና ቡድን ኃላፊዎችን ይጨምራሉ፡፡ ‹‹ይህ ተልእኮ ለጉዳቶች በተለይም ለአይኢዲ አይነት ጉዳቶች ሊያጋልጣችሁ እና እነዚህ ለእናንተ ያልተለመዱ ሊሆኑ ይችላሉ›› ሲሉ በጡረታ ላይ የሚገኙት የቀድሞው የአሚሶም የተልእኮ ድጋፍ ኃላፊው ጀነራል ፊድዛድ ዲድሉ በህክምና አውደ ጥናቱ የመጨረሻው ቀን ላይ ለተሳታፊዎቹ ነግረዋቸዋል፡፡ የሀይሉ የክምና ኦፊሰር ሌተናል ኮሎኔል ዶክተር ቦኒፌስ ማንዲሾና በውጊያ ቀጠናዎች የሚደርሱት አብዛኞቹ ጉዳቶች በአልሸባብ አሸባሪዎች ጥቅም ላይ በሚውሉት በቤት ውስጥ የሚሰሩ ፈንጂ መሳሪያዎች ምክንያት መሀጎኑን እና
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ውስጥ በማገልገል ላይ ያሉ የወታደራዊ ህክምና ሙያተኞች እንዴት መድማትን ማቆም እንደሚቻል ልምምድ ሲያደርጉ፡፡ ይህ መቋዲሾ ሱማሊያ ውስጥ በተካሄደው ኮንፍረንስ ላይ ነው፡፡
አይኢዲዎች ሱማሊያ ውስጥ ለሲቪሉ ማህበረሰብና የጸጥታ ኃይሎች ትልቅ ስጋት ሆነው መቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ማንዲሾና ‹‹እኛ አስቀያሚ ጉዳቶች ያጋጠሙን ሲሆን አንዳንድ ሰራተኞቻችን
እኛን ያጋጠሙንን ጉዳቶች አይነት አላጋጠመማቸውም፡ ፡ ይህ ስልጠና ለእነዚህ ሰራተኞች ከስልጠና ቡድኑ ጋር የሚወያዩበት እድል የሚፈጥርላቸው በዚህም የዚህ አይነት ባህሪ ያላቸውን
ሁኔታዎች የሚቆጣጠሩበት እውቀት ማግኘት ይችላሉ›› በማለት ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ከሁሉም ዘርፎች የተውጣጡ የህክምና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በኦፊሰሮች በውጊያ ቀጠናዎች የሚፈጠሩ ድንገተኛ ጭንቀቶችን እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸው ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ማብራሪያው የተጎዱ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በሰላም ወደ ሆስፒታል ለማድረስ የሚያስችሉ ከመጠን በላይ የደም መፍሰስን ማስቆሚያ ዘዴዎችንና ተገቢ አያያዝን የተመለከቱ ትምህርቶችን ያጠቃልላል፡፡ የአሚሶም ምክትል የሀይል አዛዥ የድጋፍና ሎጅስቲክስ ኃላፊው ሜጀር ጀነራል ሳልቫቶሬ ሀሩሺማና ተሳታፊዎች በግጭት ቀጠናዎች ድንገተኛ ሁኔታዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር የተማሯቸውን ክህሎቶች እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ውስጥ በማገልገል ላይ ያሉ የወታደራዊ ህክምና ሙያተኞች እንዴት መድማትን ማቆም እንደሚቻል ልምምድ ሲያደርጉ፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የድጋፍ ተልእኮ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ፊድዛ ድሉድሉ በአሚሶም ውስጥ በማገልገል ላይ ካሉ የህክምና ኦፊሰሮች ጋር፡፡
20
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
በ
‹የስማይል ትሬይን› ወደ ደቡባዊ ምእራብ ሄደ
መጋቢት ወር የአሚሶም ዶክተሮችን፣ የአለም አቀፉ በጎ አድራጎት ‹ስማይል ትሬይን› እና የባንክሮፍት አለም አቀፍ ልማት የተውጣጡ አባላትን የያዘ ቡድን የደቡብ ምስራቅ ግዛት አስተዳደራዊ ዋና ከተማ በሆነችው በባይድዋ ካምፕ ነጻ የከንፈርና መንጋጋ ህክምና በመስጠት በነዚህ ሁኔታዎች ተጠቂ ለሆኑ 10 ታማሚዎች እርዳታ አድርጓል፡፡ የህክምና ዘመቻው የተዘጋጀው በባይድዋ ክልል ሆስፒታል አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆም ለ49 ታማሚዎች ስኬታማ የቀዶ ህምክምና አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ብሄራዊ የሱማሊያ ድጋፍ ሰጪ ጽ/ቤት (ዩኤንኤስኦኤስ)፣ አሚሶምና የሱማሊያ የህክምና ሙያተኞች እንዲሁም የስማይል ትሬይን ቡድን ለአሚሶም ዶክተሮችና ለሶማሊያ ፋርማሲስቶች ወደፊት ተመሳሳይ ቀዶ ህክምናዎችን እንዲያካሂዱ የስራ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ የከንፈር መሰንጠቅ በሱማሊያ የተለመደ የአካል ጉዳት ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላለፉት አስርት አመታት በአካባቢው ሆስፒታሎች ህክምናውን ለመስጠት የቴክኒክ አቅም ማጣት የተነሳ የከንፈር መሰንጠቅና የድድ በሽታ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ የዘመቻው ዋና ቀዶ ሀኪም ኡጋንዳዊው ኮሎኔል ዶ/ር ጀምስ ኪዬንጎ ‹‹የከንፈር መሰንጠቅ ወይም ፋሩር (በሱማሊኛ አጠራር) በሱማሊያ ተለመደ ሁኔታ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ኪዬንጎ የከንፈር መሰንጠቅ ታማሚዎች ህክምናው ሱማሊያ ውስጥ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ከመሆኑ ባለፈ ማህበራዊ መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹የከምፈር መሰንጠቅ ታማሚዎች አንዳንድ ጊዜ በሌሎች ህጻናት ስለሚሾፍባቸው ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም፣ በአግባቡ ማውራት አይችሉም፣ በሚያወሩበት ጊዜ እንደ ‹ፒ›
የቀዶ ጥገና ሀኪሞች፥የማደንዘዣ ባለሙያዎች፥ የህክምና ባለሙያ ረዳቶች በተፈጥሮ የከንፈር ክፍተት ኖሯቸው ለሚወለዱ ህፃናት የከንፈር መልሶ መግጠም ህክምና ሲያደርጉ። በቤይ ክልል በቦይዳ ሆስፒታል ሶማሊያ
ያሉ ቃላትን በትክክል ማንበብ አይችሉም፣ በትክክል መናገር እንዳይችሉ መንጋጋቸው ያቆማቸዋል›› ሲሉ ዶ/ር ኪዬምጎ አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ታማሚዎቹ እንክብካቤ አናገኝም የሚል ስሜት ቢፈጠርባቸውም እንኳ በሽታው እንደ ፊት ቅርጽ መበላሸትና የጆሮ ኢንፌክሽኖች ላሉ በረጅም ጊዜ ውስጥ ችግር ሊፈጥሩ ለሚችሉ ሌሎች የጤና ችግሮች ስለሚያጋልጣቸው አስቀድመው ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የባይድዋ ክልል ሆስፒታል አስተዳዳሪ በደቡብ ምእራብ የጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ቀዶ ህክምና የሚደረግላቸው ታማሚዎች ወደ ህክምና እንዲመጡ አድርገዋል፡፡
የከንፈር መሰንጠቅና የመንጋጋ ታማሚዎች በባይድዋ፣ ሱማሊያ የቤይ ክልላዊ ሆስፒታል ህክምና ለማግኘት ተራ ሲጠባበቁ፡፡
በሆስፒታሉ ኮሪደር የነበረው ረጅም ሰልፍ በርካታ ህክምናው የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ለመኖራቸው ማረጋገጫ ነው፡፡ የባይድዋ ክልል ሆስፒታል ዳይሬክተር አብዲፋታህ ኢብራሂም ሀሺ ‹‹ማህበረሰቡ ወደ ቀዶ ህክምናው እንዲመጣ የማመቻቸት ሚና እየተጫወትን ነው፡፡ አንዳንድ ታካሚዎች ወደ ህክምና ቦታው የሚመጡት ከሌሎች ክልሎች ስለሆነ ቀድመው ወደ ህክምና ቦታው መምጣት አለባቸው፡፡ እስከ አሁን ከባይድዋ ከተማና በአቅራቢያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች በተለይም ከቤይና ባኮል ክልሎች የመጡ ሰዎችን መዝግበናል›› በማለት ተናግረዋል፡፡ የህክምናው ተጠቃሚዎች አንድ ዘመድ ለታናሽ ወንድሙ የተካሄደለት ህክምና ህይወቱን የሚቀይር እንደሆነ ገልጿል ‹‹የመጣነው ከሞድሞደን ወደብ ዳርቻ ነው፡፡ የወንድሜ ፊት የአካሉ እጅግ ወሳኝ ክፍል በመሆኑ ምክንያት አንዳንድ የፊቱ ገጽታዎች ተመልሰውለታል እንዲሁም አሁን በነጻነት ከማህበረሰቡ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላል›› ሲል ማዲኩሶው ወንድሙ ስኬታማ ቀዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ተናግሯል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ህክምናውን ሳያገኙ ስለተመለሱ ሁሉም ታካሚዎች ቀዶ ህክምና አልተደረገላቸውም፡ ፡ የባንኮችት አለም አቀፍ ልማትና አጋሮች ቀዶ ህክምናውን በቀርቡ በድጋሚ መስጠት የሚችሉበትን እድል እየፈለጉ ነው፡፡ በ2016 እና 2017 ሞቃዲሾ በሚገኘው የአሚሶም ደረጃ 2 ሆስፒታል በተደረገው ተመሳሳይ የቀዶ ህክምና ከ700 በላይ ታካሚዎች የተሳካ ቀዶ ህክምና ተካሂዶላቸዋል፡፡ የከንፈር መሰንጠቅ ከንፈር ወይም አፍ በአግባቡ ሳይገጥም ሲቀር፣ ጽንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ የሚፈጠር በሽታ ነው፡፡ አሚሶ ም መ ጽሔ ት
21
ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአል አከበሩ
በ
የአመቱ መጋቢት 8 የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሴቶች አለምን የተመቸች መኖሪያ ለማድረግ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አስችሏቸዋል፡፡ በአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የአለም የሴቶች ቀንን ባከበሩበት ወቅት መንግስታት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሴቶችን በሰላም የማስከበር ተልእኮዎች ላይ ለማሰማራት ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከሁሉም የሰላም አስከባሪ ወታደሮችና ፖሊስ ያዋጡ ሀገራት (ቲሲሲዎች) የተውጣጡት ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቀኑን ለማክበር
የአፍሪካ ህብረት የመከላከያ አማካሪ ብርጋዴር ጀነራል ጌርትሩድ ቢሊ ምዋሌ መቋዲሾ ውስጥ የአለም የሴቶችን ቀን ባከበሩበት ወቅት በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር በማገልገል ላይ የነበሩ ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ንግግር ሲያደርጉ፡፡
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር በማገልገል ላይ የነበሩ ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች መጋቢት 08/2018 መቋዲሾ ውስጥ የአለም የሴቶች ቀንን ሲያከብሩ፡፡
22
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ከሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች አጋሮቻቸው ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ለአለም የሰላም ሻምፒዮን የእግር ጉዞ በማድረግ ሲሆን የበአል ዝግጅታቸው በአመራር ላይ በተካሄደ ጉባኤ ተፈጽሟል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአሚሶም ውስጥ በጠቅላላው 850 ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሚገኙ መሆኑ ተልእኮውን በመላው አለም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በመያዝ ቀዳሚ አድርጎታል፡፡ የ2020/2021 የአንድ ሰው ለአንድ ሰው ምርጫ ከመካሄዱ አስቀድሞ ሀገሪቱን የማረጋጋት ሂደቱን ለማፋጠን እንዲያግዙ የሴት ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ቁጥር ለመጨመር እቅድ ተይዟል፡፡
በሶማሊያ ፓርላማ ውስጥ ያለው የስነ ጾታ ሁኔታ
አ
ሚሶም በየካቲት ወር ለሱማሊያ ሴት የፓርላማ አባላት በሱማሊያ ፍትህ ውስጥ ስለሚጫወቱት ሚና፣ እና ሴቶችና ህጻናትን ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ መንገዶች መፈለግን
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ዲኤስአርሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ ሲሞን ሙሎንጎ በየካቲት 26/2018 መቋዲሾ ውስጥ በተካሄደው የሱማሊያ ሴት ህግ አውጪ አባላት አቅም ግንባታ አውደ ጥናት ላይ ንግግር ሲያደርጉ፡፡ የአውደ ጥናቱ አላማ ሴት ህግ አውጪዎች የሴቶች፣ ህጻናትንና ሌሎች ተጠቂ የሆኑ ቡድኖችን መብቶች ማስጠበቅ እንዲችሉ አቅማቸውን ማጎልበት ነው፡፡
በተመለከተ ለመወያየት የሶስት ቀናት አውደ ጥናት አዘጋጅቶ ነበር፡፡
በሞቃዲሾ ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው አውደ ጥናት ተሳታፊዎች ከፌደራል ፓርላማ ከላይኛውና የታችኛው ምክር ቤት የተውጣጡ ሴት የፓርላማ አባላትን ያሳተፈ ነበር፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሱማሊያ ልዩ ተወካይ ሲሞን ሙሎንጎ ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ንግግር ላይ ‹‹የእናንተ አሁን እዚህ መገኘት የመልካም አስተዳደርን፣ የጾታ እኩልነትን፣ የሰብአዊ መብቶችና የህጻናት ጥበቃን ለማስፈን ለምታደርጉት አስተዋጽኦ መሰረታዊ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሞሎንጎ ለሴት ኤምፒዎቹ አንድ ላይ ሆነው በማህበረሰቡ ውስጥ እጅግ ተጋላጭ የሆኑት ሴቶችና ህጻናትን መብት የሱማሊያ ሴት ህግ አውጪ አባላት በየካቲት 26/2018 መቋዲሾ ውስጥ የተሰጠውን የአቅም ግንባታ አውደ ጥናት ሲከታተሉ፡፡ ለማስጠበቅ እንዲታገሉ የአውደ ጥናቱ አላማ ሴት ህግ አውጪዎች የሴቶች፣ ህጻናትንና ሌሎች ተጠቂ የሆኑ ቡድኖችን መብቶች ማስጠበቅ እንዲችሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡ አቅማቸውን ማጎልበት ነው፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
23
ከሚዲያ ጋር መገናኘትና መጋበዝ
ጋዜጠኞች በ21/12/2017 ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ኤስአትሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ የተሰጠውን የሚዲያ ገለጻ ሲከታተሉ፡ ፡ ኤስአርሲሲው ሱማሊያ ውስጥ በቅርቡ ስለታዩ የጸጥታ መሻሻሎች እና ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተደረገ ስላለው ብሄራዊ የጸጥታ ኃላፊነትን ከአሚሶም ወደ ሶማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ኃይሎች የማስተላለፍ ሂደት ገልጸዋል፡፡
የ
አሚሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማዴይራ ባለፈው መጋቢት ወር በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ብዙ ሚያዲያዎች -ክፍለ አህጉራዊና አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የተገኙበት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 2017 አልሸባብን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ ስኬት የተገኘበት አመት እንደሆ ባብራሩበት ወቅት የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ልዩ ተወካዩ የሱማሊያን ከአፍሪካ ህብረት የተለያዩ ሀገራት ሀይሎች ወደ ሱማሊያውያን ማሸጋገሩ ላይ ያጋጠሙ ማነቆዎችን አብራርተዋል፡፡ ማዴይራ ለክፍለ አህጉራዊና አለም አቀፍ ጋዜጠኞቹ በ2017 የተገኙ ስኬቶችን ባብራሩበት
አንድ ጋዜጠኛ በናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ኤስአትሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ የተሰጠውን የሚዲያ ገለጻ ሲቀዳ፡፡
አንድ ጋዜጠኛ በናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በተሰጠው የሚዲያ ገለጻ ላይ ጎን ለጎን ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ኤስአትሲሲ) የሱማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ፡፡
24
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ወቅት ከተገኙ ስኬቶች ውስጥ አሚሶም በሱማሊያ በመገኘቱ ምክንያት አዲስ ፕሬዝዳንት፣ የፓርላማና ሴት አባላትን ለመምረጥ የተካሄደው የምርጫ ሂደት በስኬት መጠናቀቅን በአጽንኦት ገልጸዋል፡ ፡ ማዴይራ ቀሪ በአልሸባብ የተያዙ ግዛቶችን ነጻ ለማውጣት የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎችን የጸጥታ ኃላፊነቶችን ከአሚሶም መቀበል እንዲችሉ አቅማቸውን ለማጠናከር በ2018 ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ አሚሶም ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሎጅስቲክ ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ ወታደራዊ ሀይሉ በዋናነት አሁንም በአልሸባብ ታጣቂዎች ተወረው በሚገኙት በጁባ ሸለቆ፣ የጌዶ ክልልና መካከለኛው የጁባ ክልሎች ጠንካራ ጥቃቶች ለመሰንዘር አቅዷል፡፡›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ማዴራ በተጨማሪም በተለያዩ ቡድኖች ባልተቀናጀ መልኩ የሚሰጠው ስልጠና መቆም አለበት በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡ ‹‹የውትድርና ስልጠናው መቀናጀትና በጋራ አመለካከትና ርእዮት የተማከለ መሆን አለበት፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦፕሬሽን ዝግጁነት የዳሰሳ ጥናት ላይ እንደተመለከተው ያለምንም የተቀናጀ እቅድ በርካታ ባለድርሻ አካላት ለጸጥታ ሀይሎቹ ስልጠና በመስጠት ላይ እየተሳተፉ ነው›› በማለት አስገንዝበዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎችን ሁሉንም ነጻ የወጡ ግዛቶች መቆጣጠር እንዲችሉ አቅማቸውን የመገንባት ቁርጠኝነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ አሁን አስር አመት ያስቆጠረው ተልእኮው በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2372(2017) መሰረት የወታደራዊ ኦፕሬሽኖቹን ቁጥር ‹‹ወታደሮች መቀነስን›› ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሲሄድ የሱማሊያ ፌደራል መንግስት ቀስ በቀስ የአሚሶምን ኃላፊነቶች ይረከባል፡፡
ትኩረት በወታደሮቻችን ላይ ኬንያ
ዩኤን ዲኤፍስ ለአፍሪካ የሰላም አስጠባቂ ሰራዊት አዲስ የስልጠና ዙር ከፈተ
የ
ዩኤን የመስክ ድጋፍ ዲፓርትመንት (ዲኤፍኤስ) በጥር ወር ለአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በከባድ የምህንድስና ተግባሮች ላይ ያተኮረ አዲስ ዙር ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡ ሰልጣኞቹ ከኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዛምቢያና ኢትዮጵያ የተውጣጡ አስራ ሁለት ወታደሮች ሲሆኑ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የሰብአዊ ሰላም ድጋፍ ትምህርት ቤት (ኤችፒኤስኤስ) በሰላም ማስከበር የከባድ ምህንድስና ተግባሮች ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሶስት ወራት ጥልቅ የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት መውሰድ ጀምረዋል፡ ፡ የትሬአንጉላር ፓርትነርሺፕ ፕሮጀክት (ቲፒፒ) ምክትል የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ጁሊያን ኦቲንኮራንግ ኢኒሺዬቲቩ አላማው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በምህንድስና መስክ ያለባቸውን ክፍተት
በመቅረፍ የሰላም ማስከበር ስምሪቶችን ማመቻቸት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በ2015 በዩኤን የሚደገፈው ስልጠና ከተጀመረ አንስቶ
የተባበሩት መንግስታት ትሬአንጉላር ፓርትነርሺፕ ፕሮጀክት (ቲፒፒ) ምክትል የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ጁሊያን ኦቲንጎራንግ በናይሮቢ ኬንያ በሰብአዊ የሰላም ድጋፍ ትምህርት ቤት የተሰጠው የዩኤን-ዲኤፍኤስ ትሬአንጉላር ፓርትነርሺፕ ፕሮጀክት የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት ላይ ለተሳታፊዎች ገለጻ ሲያደርጉ፡፡
ከ
ኬንያ መከላከያ ሰራዊት የተውጣጡ የአሚሶም ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሚያዚያ ወር በሱማሊያ ለቡሳር ከተማ ነዋሪዎች ነጻ የህክምና ዘመቻ አካሄዱ፡፡
የኬንያ ዘርፍ 2 ተጠባባቂ ሀይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ጆአኪም ምዋቡሪ፡፡
ወታደሮቹ ለህጻናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና አረጋውያን ክትትል ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ለማህበረሰቡ መድረሳ (የእስልምና ትምህርት ኮሌጅ) አቋቁመዋል፡፡ የህክምና ዘመቻው ተጠቃሚዎች ማህበረሰቡን ከሰላም አስከባሪ ወታደሮችና አለም አቀፍ ቡድኖች ህክምና ማግኘትን በሚከለክለው የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን ማእቀብ ተጎጂዎች ናቸው፡፡ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ህክምና መስጫ ቦታው የመጡ ሲሆን ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ በመላው ደቡብ ሱማሊያ ተመሳሳይ ዘመቻዎችን ያካሂዳሉ (ፎቶ ተያይዟል)
ተሳታፊዎች በናይሮቢ ኬንያ በሰብአዊ የሰላም ድጋፍ ትምህርት ቤት የተሰጠው የዩኤን-ዲኤፍኤስ ትሬአንጉላር ፓርትነርሺፕ ፕሮጀክት የአሰልጣኞች ስልጠና ትምህርት መክፈቻን ሲከታተሉ፡፡
በወካይ ሀገራት የተመረጡ 170 ወታደሮች በምህንድስና ማሽኖች ማንቀሳቀስና ጥገና ላይ ስልጠና ወስደዋል፡፡ ቀደም ሲል የተሰጠው ለሰላም ማስከበር ተልእኮ ወሳኝ የሆኑ ከባድ ማሽኖች ማንቀሳቀስ ላይ ትምህርት የተሰጠበት ስልጠና ተጠቃሚዎች 11 የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን፣ 60 የኬንያ ወታደሮችን፣ 10 የሩዋንዳ ወታደሮችን፣ 9 የኡጋንዳና 7 የጋና ወታደሮችን ያካተተ ነው፡፡ በዚህ አመት ስልጠና ላይ ኢትዮጵያ አዲስ ተሳታፊ ሆናለች፡፡ ኬንያ በዩኤን፣ የስዊዘርላንድ፣ ጃፓን እና ሌሎች የሰላም
አስከባሪ ወታደሮች ያዋጡ ሀገራት መንግስታት ትብብር ለሚሰጠው የቲፒፒ ስልጠና የስልጠና አገልግሎት መስጫዎችን አቅርባለች፡፡ በአለም አቀፉ የሰላም ማስከበር ድጋፍ ስልጠና ማእከል (አይፒኤስቲሲ) አማካኝነት ኤችፒኤስኤስ በምርምር፣ ስልጠናና የወታደሮች አቅም ግንባታ ላይ ከዩኤንና የስዊዘርላንድ መንግስት ጋር ትብብር ፈጥሯል፡፡ በስልጠናው አማካኝነት ወታደሮች የአየር መቃወሚያዎችን ማቆምና ማሰራትን፣ መስኮችን ማጽዳትን፣ የካምፕ ዝግጅት፣ የማለፊያ መንገዶችን መጠገንን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ ክህሎቶችን ቀስመዋል፡፡
የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮች እና የመንደሩ ነዋሪዎች በቡሳር ከተማ የተገነባውን አዲሱን መድረሳ ከውጭ ቆመው ሲጎበኙ፡፡ በተጨማሪም የኬንያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ነዋሪዎቹን ለመርዳት ነጻ የህክምና ዘመቻ አካሂደዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
25
ትኩረት በወታደሮቻችን ላይ ቡሩንዲ
የሰላም አስከባሪ ወታደሮች የመቋዲሾጁሃርኤምኤስአርን ከፈቱ፡፡
I
የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲካሄድ ለማስቻል በ5 ዘርፍ መንገዱን ነጻ ካደረጉ በኋላ የመቋዲሾጁሃርኤምኤስአር ዋና የአቅርቦት መስመር መከፈቱ ለተጠቃሚዎች ትልቅ እፎይታ ፈጥሯል፡፡ የቡሩንዲ ሰላ አስከባሪ ወታደሮች አልሸባብ አደጋ ለመጣል ይጠቀምበት የነበረውን በባልካድና ጋልሳር መካከል የሚገኘውን የጎሮሌ አካባቢ ተቆጣጥረዋል፡፡ ቦታውን ለማስለቀቅ የተካሄደው ዘመቻ ከሚያዚያ 5 እስከ 9/2018 ተካሂዷል፡፡
ሜጀር ኒጋባ ቴዎዶር እንደተናገሩት የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ የሰዎች ነጻ እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ እና የአቅርቦት ኮንቮዮችን ጨምሮ የሁሉንም የመንገድ ተጠቃሚዎች ደህንነት ለማረጋገጥ በኤምኤስአር ላይ በቅርበት ቁጥጥር ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የ43ኛው ባታሊዮን አዛዥ ሜጀር ቻቲየር ኒያንድዊ የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ጎሮሌይን ለመያዝ ያጋጠማቸው አነስተኛ የመከላከል ጥቃት እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ለመካከለኛው ሸበሌ አስተዳደርና ለህዝቡ
የአሚሶም የዘርፍ 5 የቡሩንዲ ተጠባባቂ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሞቋዲሾ - ጆውሀር ዋና የአቅርቦት መስመርን በስኬት ካጸዱ፣ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴና ለአቅራቢዎች ምቹ ካደረጉ በኋላ በመንገዱ ላይ ቅኝት ሲያደርጉ፡፡
የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ በመንገዱ ላይ የደፈጣ ጥቃት የሚፈጽሙ አሸባሪዎችን ለመዋጋት ከእነርሱ ጋር እጅ ለእጅ ሆነው እንደሚሰሩ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
የመካከለኛው ሸበሌ አስተዳደር ለሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ለሰሩት መልካም ተግባር መደሰቱን ለመግለጽ ሁለት ላሞች አበርክቶላቸዋል (ፎቶ ተያይዟል)፡፡
ሁለት የቡሩንዲ ባታሊዮኖች የተልእኮ የቅኝት ጉዞ አጠናቀቁ
የ
ቡሩንዲ 40ኛና 41ኛ ባታሊዮኖች በፊት መስመር አስደናቂ ድል ካስመዘገቡ በኋላ የተልእኮ ቅኝት ጉዟቸውን አጠናቀዋል፡፡ የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ባካሄዷቸው ዘመቻዎች፣ የሲቪል ውትድርና ትብብርና የሱማሊያ አጋሮችን አቅም በመገንባት ረገድ ጉልህ ውጤቶችን አሳክተዋል፡፡ የ40ኛው ባታሊዮን የስምሪት አዛዥ ኦፊሰር
የሆኑት ሜጀር ላዲስታስ ሲንጊራንካቦ ‹‹ጠላት ከቀጣይ የዘመቻ ቤዛችን መወገዱን ለማረጋገጥ የግንኙነት ቅኝቶችን አካሂደናል፡ ፡ ኮንቮዮቻችንና ማህበረሰቡ በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል በየእለቱ የአቅርቦት ዋና መስመሮች ላይ ጥበቃ አድርገናል›› ሲሉ በመጋቢት ወር የተግባር ስምሪታቸውን ባጠናቀቁበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
የዘርፍ 5 የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ዋና ዋና ተግባሮች በ2017 የተካሄደውን የሂርሸበሌ ግዛት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫና የፕሬዝዳንቱን ሹበት ክብረ በአል ጸጥታ ማስጠበቅን ያጠቃልላል፡፡ የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ በባዮካድል እና ሚር ቲቅዎ የተሰነዘሩባቸውን በርካታ ጥቃቶች በብቃት ከመመከታቸውም በተጨማሪ በበርካታ አጋጣሚዎች ጣልቃ በመግባት የአካባቢውን
ማህበረሰብ ከአልሸባብ ሰርጎ ገቦች ጥቃት ስጋት ታድገዋል፡፡ ባታሊዮኖቹ በተጨማሪም ከኤስኤንኤ ጋር በመተባበር በጎሎሊ በተካሄደው ‹‹ወደፊት መግፋት›› ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ዘመቻው የአካባቢውን ጸጥታ ማስከበርና ነጻ ማውጥትን እና ጠላት በድንገት የደፈጣ ጥቃት ሊፈጽምበት የሚችለው ወደ ጆውሀር አየር ማረፊያ የሚወስደውን መንገድ መያዝን ያካተተ ነበር፡፡
በሂርሸበሌ ግዛት የአካባቢ የጸጥታ ሀይሎችን ክህሎቶች ማጎልበት
በ
አስከባሪ ወታደሮቻችን መጋቢት ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ወር አሚሶም አስቡት፤ አይኢዲዎችን ከዩኤምኤኤስ (የዩኤን ለማስወገድ የሰላም አስከባሪ ማይን አክሽን ሰርቪስ) ወታደሮቹና የሱማሊያ ጋር በመተባበር ለሂርሸበሌ የጸጥታ ሀይሎች ተባብረው ግዛት የፖሊስ ኦፊሰሮች መስራት አለባቸው›› በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ካሉ በኋላ ‹‹ስልጠናው ፈንጂ መሳሪያዎችን ለሱማሊያ የጸጥታ (አይኢዲዎችን) መጠቀምን ሀይሎች የአፍሪካ ህብረትና እንዴት መከላከል የተባበሩት መንግስታትን እንደሚቻል የተመለከተ ዘመቻዎችና ሥነ ሥርአቶች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የሚገነዘቡበት አቅም በጆህዋር አየር ማረፊያ ይፈጥርላቸዋል›› በማለት የተሰጠው ስልጠና ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው የተዘጋጀው በዩኤምኤኤስና በጆውሀር በአይኢዲ ላይ የተሰጠው አውደ ጥናት ተሳታፊዎች ቡድን ፎቶ፡፡ አውደ ጥናቱ የተዘጋጀው አራት ሚኒስቴሮችና የዘርፍ 5 ሰላም አስከባሪ በሂርሸበሌ ግዛት ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ነው፡፡ ምክትሎቻቸውን እና ወታደሮች ትብብር ነው፡፡ የመካከለኛው ሸበሌ ግዛት የዘርፉ አዛዥ የስልጠና በማሰብ በኤምኤስአሮች ላይ የዘርፍ 5 አዛዥ ገዢን የያዘ አራት የልኡካን ፕሮግራሙን በከፈቱበት ወቅት በቤት ውስጥ የሚሰሩ ፈንጂ ብርጋዴር ጀነራል ቪክቶር ቡድን ወደ ስልጠናው መክፈቻ ለስልጠናው ተሳታፊዎችና መሳሪያዎችን ለመጥመድ ንዱዉሙኪዛ ‹‹አልሸባብ ይዘው የመጡትን የሂር ተጋባዥ እንግዶች ‹‹የአይኢዲ በርካታ ስትራቴጂያዊ ከተሞችና የሚያስችሉትን የሰርጎ ሸበሌ ግዛት የጸጥታና መልሶ መሳሪያዎች መጠበቅ መግባት ታክቲኮችና ዘዴዎች መንደሮችን ከተነጠቀ በኋላ ማቋቋሚያ ሚኒስቴርን ያሳተፈ ባለብን የሶማሊያ ህዝብ፣ እየተጠቀመ ነው›› በማለት አቅሙ ስለተዳከመ በንጹሀኑ ነበር (ፎቶ ተያይዟል)፡፡ መሳሪያዎቻችንና ሰላም ተናግረዋል፡፡ ህዝብ ላይ ሽብር ለመንዛት
26
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ትኩረት በወታደሮቻችን ላይ ዑጋንዳ፡
ዑጋንዳ፡ የውጊያ ቡድን 21
በ
አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ለልዩ አገልግሎት ተሰማርተው የነበሩ የኡጋንዳ ተጠባባቂ ወታደሮች በሱማሊያ መዲና መቋዲሾ የሜዳሊያ ሽልማት ሥነ ስርአት ተካሂዶላቸው ተሸኙ፡፡ ወታደሮቹ በሱማሊያ የሰላም ማስከበር ግዴታውን ያጠናቀቀው የኡጋንዳ ህዝቦች መከላከያ ሀይል የውጊያ ቡድን 21 አባላት ናቸው፡፡ የአሚሶም ምክትል አዛዥና የድጋፍና ሎጅስቲክስ ኃላፊው ሜጀር ጀነራል ሳልቫቶር ሀሩሺማና በኮሎኔል ክሪስ ኦግዋል እዝ ስር የነበሩት ተሰነባቾቹን ወታደሮች ባሰናበቱበት ወቅት የአፍሪካ ህብረት በሱማሊያ ጸጥታና መረጋጋትን ለማስፈን ለሚያደርገው ቃል ኪዳን ስላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነው፡፡ ስራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ መፈጸም ስለመቻላቸው አመስግነዋል፡፡ ምክትል የሀይል አዛዡ ዋና የውጊያ ቡድኑ የአቅርቦት መስመሮችን ከአልሸባብ እጅ ለማስለቀቅ የታካሄዱ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ጨምሮ መደበኛ ቅኝቶችን በማካሄድና የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን በማጀብ
በሱማሊያ የኡጋንዳ ምክትል አምባሳደር ሜጀር ጀነራል ናታን ሙጊሻ ለኡጋንዳ የመከላከያ ኦፊሰሮች የሜዳሊያ ሽልማት በተሰጠበት ወቅት ንግግር ሲያደርጉ፡፡
በበርካታ ወታደራዊ ዘማቻዎች ላይ እንደተሳተፈ ተናግረዋል፡፡ የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርአቱ ተጋባዥ እንግዳ የነበሩት በሱማሊያ የኡጋንዳ ምክትል አምባሳደር ሜጀር ጀነራል ናታን ሙጊሻ ለሱማሊያ ህዝብ ወሳኝ የሆኑ የበለጡ ማህበራዊ ኢንቨስትመንቶች እንዲደረጉ፣ ሀገሪቱን ለማረጋጋት ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሱማሊያ የኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ተጠባባቂ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ፖል ሎኬች የሰላም አስከባሪ
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር እያገለገለ ያለው የኡጋንዳ ተጠባባቂ ሀይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ፖል ሎክ የአንድ አመት ተልእኳቸውን ላጠናቀቁት የኡጋንዳ የመከላከያ ኦፊሰሮች የሜዳሊያ ሽልማት በተሰጠበት ወቅት ንግግር ሲያደርጉ፡፡ (ኢኤንኤስኢቲ) በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር እያገለገለ ያለው የኡጋንዳ ተጠባባቂ ሀይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ፖል ሎክ ለአሚሶም ኦፊሰሮች የሜዳሊያ ሽልማት ሰጥተዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ምክትል የሀይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሳልቫቶሬ ሀሩሺማና መቋዲሾ፣ ሱማሊያ ውስጥ የሜዳሊያ ሽልማት ስነ ስርአት በተካሄደበት ወቅት ለአሚሶም የመከላከያ ኦፊሰር የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡
ወታደሮቹ የአፍሪካ ቀንዷን ሀገር ጸጥታ ለመጠበቅ እራሳቸውን አሳልፈው ለሰጡት አገልግሎት አመስግነው ‹‹ለመላው አለም አፍሪካ ምን ማድረግ እንደምትችል አሳይታችኋል፡፡ በ2007 እዚህ በመጣንበት ጊዜ ይህ ተልእኮ ከመነሻው እንደማይሳካ ነግረውን ነበር፤ ነገር ግን ዛሬ ከ10 አመታት በኋላ የአፍሪካ ተልእኮንና የኡጋንዳን ሰንደቅ አላማ ይዘን ወደፊት እየተጓዝን ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ጀነራሉ በተጨማሪም የሱማሊያን ሰላም በማስከበር ተግባር ህይወታቸው ያለፈ ወታደሮችን ሁልጊዜም በጀግንነታቸው ይታወሳሉ በማለት የመታሰቢያ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
27
ትኩረት በወታደሮቻችን ላይ ኢትዮጵያ
የዘርፍ 3 ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለአካባቢ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ለገሱ
የ
አሚሶም የዘርፍ 3 ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በመጋቢት 19 ለባይድዋ የአሊ ሳላሚ ማእከል የአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ራሽቸውን አካፈሉ፡፡ በባይድዋና አካባቢው እየተባባሰ በመጣው ድርቅ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሰራዊት (ኢኤንዲኤፍ) የሰላም አስከባሪ ወታደሮች አቅመ
ደካማ የሆኑ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ አንገብጋቢ የምግብ ፍላጎት ላለባቸው ሰዎች ምግብ በመለገስ የእርደታ እጃቸውን ዘርግተዋል፡፡ በምግብ እርዳታው አካል ጉዳተኞችና እናቶችን ጨምሮ 110 አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በባይድዋ የሚገኙ የአፍሪካ ሰላም
የባይድዋ፣ ሱማሊያ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተሰጠውን የምግብ እርዳታ ሲቀበሉ፡፡
28
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር በማገልገል ላይ በሚገኙት የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተሰጠውን የምግብ እርዳታ ለባይድዋ፣ ሱማሊያ ነዋሪዎች ሲያከፋፍሉ፡፡
አስከባሪ ወታደሮች ቀደም ሲል ከካምፓቸው አቅራቢያ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ለመታደግ ተመሳሳይ እርዳታዎችን አድርገዋል፡፡ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ በደቡብ ምእራብ ግዛት ለማህበረሰቡ ፍላጎት ምላሽ በመስጠታቸው በክልሉ
ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዲሻሻል አድርጓል፡፡ በአከባቢው የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶችተጨማሪ እርዳታዎችን የሰጡ ሲሆን ማህበረሰቡ የሰላም አስከባሪ ወታደሮቹ ላደረጉት ልገሳ ልባዊ ምስጋናውን ገልጿል፡፡
የባይድዋ፣ ሱማሊያ ነዋሪዎች በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር በማገልገል ላይ በሚገኙት የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተሰጠውን የምግብ እርዳታ ሲቀበሉ፡፡
ትኩረት በወታደሮቻችን ላይ ጅቡቲ
የ
አሚሶም ዘርፍ 4 የስራ እንቅስቃሴዎች አጭር ማብራሪያ - የጅቡቲ ተጠባባቂ ሀይሎች የሰፈሩበትና አሁንም በዩኤንኤምኤኤስ ስለጣና እየተሰጠ ያለበት አካባ ከቢዬት ዌይን አየር መንገድ ምእራብ አቅጣጫ 5 ኪሜ ራዲየስ ውስጥ የእግር ቅኝት አካሂደዋል፡፡ የጅቡቲ የመጠባበቂያ ሀይል በቅርቡ
ከኦራሳን ደቡብ ምእራብ በሚገኘው አደን ጋራብ 17 ሞርታሮችና 12.7ሚሜ ፈንጂዎችን አክሽፈው አውድመዋል፡፡ የመጠባበቂያ ሀይሉ በተጨማሪም ከቤሌትወይን ሰሜን ምስራቅ 15 ኪሜ አቅጣጫ በሚገኘው ካላቤይር አካባቢ እና በቤሌትዌይን በስተሰሜን አቅጣጫ በሞተር የተደገፉ
ቅኝቶችን አካሂዷል፡፡ ሚያዚያ 2/2018 - የታጠቁ የሱማሊያ ሀይሎች የሂራር ክልል በርካታ መንደሮችን ተቆጣጠሩ፡፡ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሂራር ክልል በርካታ ከተሞችን የሚያገናኙ መንገዶችን በድጋሚ ከፍተዋል፡፡ የሂራር ገዢ አሊ ጄዬት ኦስማን የመንገዶቹን መከፈት አረጋግጠዋል፡፡
ሚያዚያ 3/2018ወታደራዊ ሀይሎች ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ከቡድኑ የጦር መሳሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የህክምና አቅርቦቶችን አስመልሰዋል፡፡ አሚሶም በሂራን ገዢ አሊ ጄዬት በተመራ ወታደራዊ ዘመቻ በሂራን የሂስና አሊ ፋና መንደሮችን መልሶ ተቆጣጥሯል፡፡
((ፎቶ))፡ የአሚሶም የጅቡቲ ተጠባባቂ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከሱማሊያ አጋሮቻቸው ጋር ሆነው በሂራን ክልል ቅኝት ሲያደርጉ፡፡ በቅኝቱ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተማርከዋል እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች ተመልሰዋል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
29
ሴራሊዮን በርካታ ቁጥር ያለው የፖሊስ ተጠባባቂ ሀይል በሶማሊያ አሰማራች
ሴ
ራሊዮን በሚያዚያ ወር 160 የፖሊስ ኦፊሰሮችን በሱማሊያ ያሰማራች ሲሆን ሀገሪቱ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የሚሰማሩ የፖሊስ ኦፊሰሮች ቁጥርን ቢበዛ እስከ 1,040 መጨመር ለሚፈቅደው የ2017ቱ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ምላሽ በመስጠት በምስራቅ አፍሪካ ቀንዷ ሀገር በርካታ ቁጥር ያለው ተጠባባቂ ፖሊስ ያሰፈረች ሀገር ሆናለች፡፡ ተጨማሪ የፖሊስ ኦፊሰሮቹ በጁባላንድ አስተዳደር ህግና ደንብን በማስከበር ላይ ለሶማሊያ አጋሮቻቸው ድጋፍ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ቡድኑ የሱማሊያ የጽጥታ ሀይሎችን በተለቀቁ ቦታዎች ህግና ደንብን ማስከበር የመሳሰሉ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆን ለሱማሊያ የፖሊስ ኦፊሰሮች ስልጠናና ትምህርት እየሰጡ የሚገኙትን የአፍሪካ ህብረት የፖሊስ ኦፊሰሮች ቁጥር በመጨመር አቅማቸውን ለማጠናከር የተያዘው እቅድ አንድ ክፍል ነው፡፡ የአሚሶም ተጠባባቂ የፖሊስ ኮሚሽነር ሚስ. ክርስቲን አላሎ ‹‹የፖሊስ ኦፊሰሮቹ ወደዚህ መምጣት የጁባ ላንድ ፖሊስ ሀይልን ያጠናክራል፡፡ በ2016 በጁባ ላንድ 600 የፖሊስ ኦፊሰሮችን ያሰለጠንን ሲሆን የሴራሊዮን ኤፍፒዩ እነዚህን ሰልጣኞች በፖሊስ አገልግሎት ስዎቻቸው ላይ አቅማቸውን በመገንባት ያግዛል›› ብለዋል፡፡ ሚስ ክርስቲን የሴራሊዮን መንግስት የሀገሪቱን ማረጋጋት ጥረቶች ለመደገፍ ተጨማሪ ኦፊሰሮች ስላሰማራ አመስግነው የኤፍፒዩ ኦፊሰሮች ነጻ በወጡ አካባቢዎች የተሻሻለ የጸጥታ ሁኔታን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል፡፡ የፖሊስ ኦፊሰሮቹ ዋና ዋና ተግባሮች የህዝብ ደንብ መከበርን ማረጋገጥ፣ የአገልግሎት ተቋማትን መጠበቅን እና የተቀናጀ ጥረት ለሚፈልጉ የፖሊስ ተግባሮች ድጋፍ ማድረግን ያጠቃልላሉ፡፡ የተጠባባቂ ኦፊሰሮቹ መምጣት ለአሚሶም የሱማሊያ ፖሊስ ሀይልን
30
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
የሱማሊያ ጁባላንድ ግዛት የአሚሶም ፖሊስ አስተባባሪ ኦፊሰር አቢሉ ማርቲን አርነስት አዲስ የተሰማሩትን የሴራሊዮን ጥምር የፖሊስ ዩኒት (ኤፍፒዩ) ኦፊሰሮች በኪስማዮ አየር መንገድ ሲቀበሉ፡፡
አቅም ለማጠናከር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ወደ ፌደራሉ አባል ግዛቶች እንዲያስፋፋ በማስቻል ረገድ መልካም ዜና ነው፡፡ አሚሶም የጸጥታ ኃላፊነቶችን በዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ላይ በተገለጸው መሰረት ለሱማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ለማስረከብ ተጨማሪ የሱማሊያ
የፖሊስ ኦፊሰሮችን ለማሰልጠን እና ለመቅጠር ጥረት እያደረገ የሚገኝበት የሽግግር ጊዜ ላይ ይገኛል፡፡ ሚስ አላሎ ‹‹ከመቋዲሾ ለቀን እየወጣን ነው፡፡ ወደ ክልላዊ ግዛቶችና ወረዳዎች ዘልቀን የምንገባ ሲሆን ኦፊሰሮቹ ለእንቅስቃሴና ሌሎች ተልእኮዎች እገዛ ለማድረግ ያስፈልጉናል›› ብለዋል፡፡
አ
የዳርዊሽ ሚሊሺያ መዋሀድ
ሚሶም በመጋቢት ወር በጁባላንድ የዳርዊሽ ታጣቂዎች ከግዛቱ የጸጥታ ሀይሎች ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት የባዮሜትሪክ ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በዚህ የምዝገባ እንቅስቃሴ በጌዶ፣ ታችኛው ጁባና የመካከለኛው ጁባ ክልሎች ከአምስት ሺ በላይ የታጣቂ ቡድኑን አባላት ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡ የባዮሜትሪክ ምዝገባው የእያንዳንዱን የቡድኑ አባል ፎቶግራፎችና የጣት አሻራዎች ጨምሮ ዋና ዋና የግል መረጃዎችን ለመሰብሰብ ያስችላል፡፡
‹‹ይህ በጁባ ላንድ ህግና ደንብን የማስከበርና የግዛቷን ጸጥታ የመጠበቅ ተግባር ያለው የፖሊስ ሀይል ማዘጋጀትን አላማ ባደረገው የአሚሶምና የዩኤን ፕሮግራም መሰረት የሚካሄድ ነው፡፡›› ሲሉ የኪስማዮ የአሚሶም ፖሊስ አስተባባሪ ማርቲን አቢሊ ተናግረዋል፡፡ አቢሊ ታጣቂዎቹ ከጁባ ላንድ ፖሊስ ሀይል ጋር ወይም ከፓርላማ ወይም ከሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ጋር እንደሚዋሀዱ አብራርተዋል፡፡ የሱማሊያ ብሄራዊ የጸጥታ ተቋማትን ለማዘጋጀትና ለማጠናከር ድጋፍ የሚሰጠው ይህ እንቅስቃሴ የጸጥታው ዘርፍ ማሻሻያ አካል ሲሆን
ማሻሻያው በሱማሊያ መሪዎች መካከል በሚያዚያ 2017 በብሄራዊ የጸጥታ መዋቅር ላይ በተደረሰው ፈር ቀዳጅ ስምምነት ላይ በተገለጸው መሰረት የሱማሊያ ፌደራል መንግስትን እና አጋሮቹን ለማቀናጀትና በ17/05/2017 የለንደኑ የሱማሊያ ኮንፍረንስ የጸጥታ መርሀ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ የጁባ ላንድ የጸጥታ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር ሚ/ር አዳን ዩሱፍ ሳላ በአሚሶምና የጁባ ላንድ ግዛት መካከል የሚካሄደው ትብብር ይህን አላማ ለማሳካት ወሳኝነት እንዳለው አስተጋብተዋል፡፡
የጁባላንድ የሀይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል አዳን መሀመድ ኢብራሂም እንቅስቃሴው ለክልሉ ‹‹ወሳኝ›› እንደሆነ ገልጸው ‹‹በሁሉም ቦታ የሚገኙትን ታጣቂዎች ለምዝገባ ለማቅረብ ዝግጁ ነን›› ብለዋል፡፡ ጀነራል አዳን ለአሚሶም፣ የተባበሩት መንግስታትና ሌሎች አጋሮች የሱማሊያ ብሄራዊ መከላከያ (ኤስኤንኤ) እና የሱማሊያ ፖሊስ ሀይል ‹ትክክለኛ መጠን› እና ማሻሻያ ወሳኝ ክፍል የሆነውን የተግባር ዝግጁነት የዳሰሳ ጥናት ለማጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉላቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የፖሊስ ምድብ ሰራተኞች የዳርዊሽ ታጣቂዎችን በጁባላንድ ግዛት የጸጥታ ሀይል ውስጥ ለመቀላቀል በኪስማዮ፣ ሱማሊያ ሲመዘግቡ፡፡
አሚሶም ለሱማሊያ ፖሊስ ኦፊሰሮች የሚሰጠውን ስልጠና ማጠናከር
አ
ሚሶም የሶማሊያ የፖሊስ ኦፊሰሮችን ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በዙርና በሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የጸጥታ ኃላፊነቶችን ለሶማሊያ የጸጥታ ሀይሎች ማስተላለፍ እንዲጀምር ከሚያዘው በነሀሴ ከተላለፈው የዩኤን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ጋር በተጣጣመ መልኩ ተጨማሪ የጸጥታ ኃላፊነቶችን እንዲቀበሉ ለማስቻል ለፖሊስ ኦፊሰሮቹ የሚሰጠውን ስልጠናና ትምህርት አጠናክሯል፡፡ የአሚሶም ምክትል ኃላፊ ሲሞን ሙሎንጎ የሱማሊያ ፖሊስ አቅም አለም አቀፍ ተቀባይነት ወዳላቸው ደረጃዎች ማደግ እንዳለበት ተናግረዋል፡ ፡ ሚ/ር ሲሞን በጥር ወር የሱማሊያ ተልእኳቸውን ላጠናቀቁት የናይጄሪያ ፖሊስ ቡድን በተካሄደው የሜዳሊያ ሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ
የአሚሶም ዲኤስአርሲሲ ሲሞን ሙሎንጎ በ06/01/2018 በመቋዲሾ ሶማሊያ ለተሰናባች የናይጄሪያ ተጠባባቂ የፖሊስ ኦፊሰሮች በተዘጋጀው የሜዳሊያ ሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ የምስክር ወረቀት ሲሸልሙ፡፡
‹‹በዚህ አመት ለሱማሊያ ፖሊስ ኦፊሰሮች የበለጠ የተጠናከረ ስልጠናና የተጠናከረ ትምህርት የምንሰጥ ሲሆን ይህ ማለት አሁን ያለው ፖሊስ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር የዋና ዋና ቡድን ምልመላ፣ ስልጠናና
ምስረታ ይካሄዳል ማለት ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ለዚህ እድሜን፣ ምን ያህል ስልጠና እንደሚያስፈልግና የአካል ብቃትን እንመለከታለን፡፡ ያላቸውን መሳሪያ፣ ሎጅስቲክስ፣ ማዘዣና መቆጣጠሪያ እንዲሁም
ያሉ አገልግሎት መስጫዎችን እናያለን›› ሲሉ ሙሉንጎ አብራርተዋል፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ዋና ኃላፊ ሬክስ ዱንዱን እና የአሚሶም ፖሊስ የኦፕሬሽኖች አስተባባሪ በበኩላቸው ለኦፊሰሮቹ ለሳዩት ከፍተኛ የሙያዊነት ደረጃና ጥንቃቄ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡ ናይጄሪያ ለአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከተደራጀው የፖሊስ ሀይል (ኤፍፒዩ) ግለሰብ የፖሊስ ኦፊሰሮችን (አይፒኦዎችን) አዋጥታለች፡ ፡ ኤፍፒዩ ለሶማሊያ የፖሊስ ሀይል የተግባር ድጋፍ የሚያቀርብ ሲሆን አይፒኦዎች ለኦፊሰሮች ስልጠና፣ ትምህርትና ምክር የሚሰጡ ናቸው፡፡ የሁለቱም የሱማሊያ ተልእኮ ህግና የመንግስት ትእዛዝን መቆጣጠርን፣ የሱማሊያ ፖሊስ ኦፊሰሮችን ማስተማርን፣ ድጋፍና የቅርብ ጥበቃ መስጠትን ያጠቃልላል፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
31
አሚሶም ሰብአዊ አጋሮችን አሰለጠነ
የ
አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) በጆውሀር፣ ቤሌትዌይን ሂርሸበሌ ግዛት ለሲቪል አጋሮችና ያልታጠቁ ሰራተኞች የሰብአዊ አገልግሎቶች ማመቻቸት ስልጠና ሰጠ፡፡ የስልጠናው አላማ ሰልጣኞቹ ስለ ሱማሊያ ሀገር ተኮር ልዩ የሰብአዊ ሲቪል የውትድርና መመሪያዎች እንዲያውቁ ማስቻል ሲሆን ይህ ከአጋሮችና ተልእኮው ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች ላይ በመመሪያነት ያገለግላቸዋል፡፡ በስልጠናው ክፍለ ጊዜያት ላይ የአሚሶም ከፍተኛ የሰብአዊ ግንኙነት ኦፊሰር ሰኢድ አብዱል ዲያባጋቴ ‹‹ሰብአዊ ተግዳሮቶች በአሚሶምና ነጻ በወጡ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ አጋሮች መካከል የበለጠ ትብብርና ውይይት ማድረግ አስፈላጊ እንዲሆን አስገድደዋል›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ዲያባጋቴ ከባድ ቀውስ ውስጥ ባሉና የተፈጥሮ አደጋዎች በደረሱባቸው ቦታዎች የሰብአዊ አገልግሎት የማመቻቸት ስራዎችና ከማህበረሰቡ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች የበለጠ መጨመር ያለባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የስልጠናው አላማ በአሚሶም የሲቪል ግንኙነት ኦፊሰሮችና አጋሮች መካከል የሚካሄደውን ትብብር የበለጠ ከማሳደግ በተጨማሪ ለተሳታፊዎቹ አለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ህግን፣ የሰብአዊ እርዳታ መርሆዎችንና አለም አቀፍ የስደተኞች ህግን ማስገንዘብ ነው፡፡
የአሚሶም ከፍተኛ የሰብአዊ ግንኙነት ኦፊሰር አብዱል ዲያጋባቴ በጆውሀር በተሰጠው የሰብአዊ እርዳታ ማመቻቻ ስልጠና ላይ ለሲቪል አጋሮች ንግግር ሲያደርጉ፡፡
ዲያባጋቴ ተልእኮው፣ የመንግስት ባለስልጣናትና አጋሮች በሰብአዊ እርዳታ ማመቻቸት ላይ የበለጠ ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት አሚሶም የ2017 የሱማሊያ የሲቪል ውትድርና ስራ ቡድን ሪፖርትን የገለጸ ሲሆን የቡድኑ ስራ የተጀመረው ባለፈው መስከረም ወር
ሲቪል አጋሮች ጆውሀር ውስጥ በአሚሶም በተዘጋጀው የሰብአዊ እርዳታ ማመቻቻ ስልጠና ላይ ሲሳተፉ፡፡
32
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ነው፡፡ ሪፖርቱ የስራ ቡድኑን ስኬቶች፣ የተሻሉ ተሞክሮዎች እና በድርቅ የሚቁና የሚፈናቀሉ ሰብአዊ ዜጎችን ስቃይ ለማስቀረት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ስትራቴጂያዊ አጋርነቶች ያብራራል፡፡ ላልታጠቁ ሰራተኞች የሚሰጠው ቀጣዩ ስልጠና በቤሌትዌይን፣ ሂርሸበሌ በቀጣዩ ሳምንት ይሰጣል
የሂርሸበሌ ኤምፒዎች በፓርላማ ሥነ ስርአቶች ላይ ክህሎታቸውን እያሳደጉ ነው
የ
ሂርሸበሌ ክልላዊ ጉባኤ አርባ ሁለት አባላት በመጋቢት ወር በፓርላማ ተግባሮች፣ የምክር ቤት ስነ ስርአቶች፣ ረቂቅ ህግና የፓርላማ ተቆጣጣሪ ኮሚቴዎች ሚና ላይ የአቅም ግንባታ አውደ ጥናት ለማካሄድ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተሰብስበዋል፡ እንደ ትምህርት ልምድ ማግኛ አንድ ክፍል ኤምፒዎቹ በናይሮቢና አጎራባች ማካኮስ ካውንቲ የሚገኙ ጉባኤዎችን ከኬንያውያን አጋሮቻቸው ጋር ለመገናኘት እና ስለ ፓርላማ ክርክር ክህሎት ለመቅሰም በማሰብ ጎብኝተዋል፡፡ ስልጠናውና የኬንያን የካውንቲ ጉባኤዎች መጎብኘቱ ኤምፒዎቹን የፓርላማ የተሻሉ ተሞክሮዎችን እንዲያዩ ከማስቻሉም ባሻር የህግና ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ለሆኑት ለ42 ህግ አውጪዎች የፓርላማ ስራዎችን በማስተዳደር ረገድ የመጀመሪያ ደረጃ ልምድ እውቀት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡ የአቅም ግንባታ አውደ ጥናቱ የተዘጋጀው አሚሶም የፌደራል አባል ግዛት የሆኑ ክልሎች አቅም ለማሳደግ እንደጀመረው የተልእኮ ጥረት አንድ ክፍል በአሚሶም ነው፡፡ የአሚሶም የማረጋጋትና ቅድመ ማገገም ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ኦፒዮ ኦዳ ‹‹እንደ አሚሶም የሱማሊያ ተቋማት እንዲጎለብቱ፣ አቅም እንዲኖራቸውና ስራቸውን በአግባቡ መስራት እንዲችሉ የማረጋገጥ ኃላፊነት አለብን፡፡ የሂርሻየር ይህ የፓርላማ አባላት ጉብኝት ይህን መስፈርት የሚያሟላ አፈ ጉባኤ እንዲኖርና ቡድኑ ከናይሮቢ ካውንቲ ጋር በጋራ እንዲሰራ አስችሏል፡፡ በተጨማሪም የማኮስ ካውንቲን የምንጎበኝ ሲሆን በዚያ የሂርሸበሌ ጉባኤ አባላት በፍትህ፣ የኮሚቴ ስራ ላይ እንዲለማመዱና በሁለቱም ካውንቲዎች እንዴት ሙያዊ ጉባኤዎች እንደሚካሄዱ እንዲያዩ እናደርጋለን›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ሂርሸበሌ ከሱማሊያ አምስቱ የፌደራል አባል ግዛቶች አንዷና ባለፈው አመት መጋቢት በጁባላንድ ጉባኤ አባላት ተመሳሳይ ጉብኝት ከተደረገ በኋላ በኬንያ ጉብኝት ለማድረግ ሁለተኛዋ ትልቋ ግዛት ነች፡፡ አፈጉባኤው ሼክ ኡስማን ባሬ መሀመድ የተጨማሪ ኤምፒዎችን አቅም ለማጎልበት ወደፊት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሱማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ (አሚሶም) ተጨማሪ አውደ ጥናቶችን እንዲያዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አፈ ጉባኤው አሚሶም ከእኛ ጋር እየሰራ ያለው አልሸባብን ማስወገድ
እንድንችል እኛን ጠንካራ ሀይል ለማድረግና በሰላም መገንባት ጥረቶች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሚሶም በማረጋጋት ፕሮግራሙ አማካኝነት ባለፉት ጊዜያት ለሌሎች የፌደራል አባል ግዛቶች ህግ አውጪዎች እንደ ተልእኮው አንድ ክፍል ከሀገሪቱ ጸትጻና ጎን ለጎን መልሶ ግንባታና የመንግስት ግንባታው እንዲቀጥል ለማስቻል በህግና የፓርላማ ተግባሮች አስተዳደር ላይ ለተሰጡ ስልጠናዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህም ስልጠና ያለፉት ስልጠናዎች ቀጣይ ክፍል ሲሆን አላማው የተገኙ የጸጥታና ፖለቲካዊ ድሎችን ማጎልበት እና የኤምፒዎችን ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውሳኔዎችን የማሳለፍ አቅምን ለማጠናከር ነው፡፡ ዶ/ር ኦፒዮ በተጨማሪም በለጋ እድሜ ላይ በምትገኘው ሱማሊያ ውስጥ የሚያስፈልገው ፈጣን ፍትህ የአካባቢ ጥበቃና የድርቅ ተጽእኖዎችን የሚቀርፉ ህጎችን ማውጣት እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ዶ/ሩ በተጨማሪም ኤምፒዎቹን የመረጣቸውን ህዝብ እየተፈታተኑ ላሉ ተግዳሮቶች ፈጣን መፍትሄዎች ማምጣት እንዳለባቸው አሳስበው ‹‹በዚህ ጉዞ ላይ አሚሶም አብሯችሁ ይጓዛል›› ሲሉ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ የአሚሶም ምክትል ኃላፊ ሲሞን ሙሎንጎ የስድስት ቀናቱ ጉዞ ሲያበቃ ‹‹ተመልሳችሁ ስትሄዱ ይህን የስልጠና እድል ጥሩ ፓርላማ ለመፍጠር ተጠቀሙበት›› በማለት አሳስበዋል፡፡ የኬንያ ብሄራዊ ጉባኤ አብላጫ መሪ የተከበሩ አደን ዱሌ በበኩላቸው በአውደ ጥናቱ የመጨረሻ ቀን ለኤምፒዎቹ ለሀገር ግንባታ አስተዋጽኦ ያደርጉ ዘንድ ‹‹ለሴቶች እድል መስጠት›› እንዳለባቸው አሳስበው ከአውደ ጥናቱ የተማሯቸውን ትምህርቶች በግዛታቸውም ሆነ በመላው ሱማሊያ አቅምንና ዲሞክራሲን የሚያጠናክሩ ሀሳቦችን ለማፍለቅ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አድርገዋል፡፡ ዱዋሌ የኬንያ ፓርላማ የሱማሊያን የፍትህ ተቋማት አቅም ለመገንባትና ተምሳሌት ለመሆን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ቃል በገቡበት ወቅት ‹‹የሱማሊያ ፌደራል መንግስትን የክልል መንግስታት አቅም ማሳደግ አስፈላጊ ነው፤ ይህ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ግጭቶች በኋላ በሀገሪቱ የተገኙ ድሎችን ለማፋጠን እጅግ ወሳኝ ነው፡፡›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከሱማሊያ ሂርሸበሌ ግዛት የተውጣጡ ኤምፒዎች በኬንያ የማቻኮስ ካውንቲ ጉባኤ ላይ የሚካሄዱትን የፓርላማ ክርክሮች ሲከታተሉ፡፡
ከሱማሊያ ሂርሸበሌ ግዛት የተውጣጡ ኤምፒዎች ከማቻኮስ ካውንቲ ጉባኤ ውጭ ዳንሰኞችን እየተመለከቱ ሲዝናኑ፡፡
የኬንያ ፓርላማ አብላጫ አባላት መሪ አዳን ዱዋሌ (በስተግራ) ለሂርሸበሌ ግዛት ጉባኤ በናይሮቢ ኬንያ ሳሮቫ ሆቴል የተሰጠው የአቅም ግንባታ አውደ ጥናት መዝጊያ ላይ ለሂርሸበሌ ግዛት ጉባኤ አፈ ጉባኤ ሼክ ኦስማን ባሬ መሀመድ (ከግራ ሁለተኛው) የምስክር ወረቀት ሲሰጡ፡፡ በምስሉ ላይ የሚታዩት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር (ዲኤስአርሲሲ) የሱማሊያ ምክትል ልዩ ተወካይ ሲሞን ሙሎንጎ፣ የአሚሶም የማረጋጋትና ቅድመ ማቋቋሚያ ፕሮግራም ዋና ኃላፊ ዶ/ር ኦፒዮ ኦዶዳ እና የአሚሶም ሲቪል ጉዳዮች ኦፊሰር ፋድሂል ካራር (በስተ ግራ) ናቸው፡፡
የሂርሸበሌ ግዛት ጉባኤ አፈ ጉባኤ ሼክ ኦስማን ባሬ መሀመድ በ29 መጋቢት 2018 በናይሮቢ ኬንያ በአሚሶም ለኤምፒዎች በተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና መዝጊያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
አሚሶ ም መ ጽሔ ት
33
የወርቃማ
በ
ሻይማ ሻላል ሞሀመድ የጎልደን ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ዋና ሀላፊ ከተጫዋቾቹ ጋር በልምምዳቸው ወቅት እየተወያየች:: ሶማሊያ ሞቃዲሾ
ሱማሊያ የወጣት ልጃገረዶች እግር ኳስ ቡድን በሁሉም ሴቶች የእግር ኳስ አካዳሚ አማካኝነት በሀገሪቱ ሰፍኖ የቆየውን የባህል ማነቆ ሰበረ፡፡ የአካዳሚው መስራች የ24 አመቷ ሻይማ ሳላ ስትሆን እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፊሰርነቷ ‹‹የወርቃማ ልጃገረዶች የስፖርት ማእክልን›› እጥፍ አድርጋለች፡፡ ሻይማ ቡድን ማዋቀርና አካዳሚ ማቋቋም ከባድ ተግባር ሆኖባት እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሻይማ ‹‹በ2015 የራሴን ቡድን መመስረት ፈልጌ የነበረ ቢሆንም አገሪቱ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ስላልነበረች ይህን ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ባለፈው አመት 2017 ህልሜና ግቦቼን ለማሳካት ወሰንኩኝ፡፡ በዚህም እንዴት የእግር ኳስ ቡድን ማቋቋም እንዳለብኝ ስትራቴጂያዊ እቅድ አዘጋጀሁ፡፡ ልጃገረዶችን በስፖርት ላይ ለማሳተፍ አቅም የሚፈጥርልኝ ኤንጂኦ ለማቋቋም መንቀሳቀስ ጀመርኩኝ›› ስትል ገልጻለች፡፡ ምንም እንኳን ተግዳሮቶች ቢያጋጥሟትም ባለፈው አመት አራት ልጃገረዶች ወደ አካዳሚዋ እንዲቀላቀሉ ማድረግ የቻለች ሲሆን በ2018 የቡድኑ አባላት ቁጥር በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሮ አሁን 30 ደርሰዋል፡፡ የአልሸባብ የእስልምና አክራሪ ቡድን የሴቶች ስፖርቶችን ባገደባት ሀገር ሻይማና የቡድኗ ልጃገረዶች የአልሸባብ ደጋፊ አካላት ጥቃት እንዳያደርሱባቸው እየተጠነቀቁ ‹‹የወርቃማ ልጃገረዶች የስፖርት ቡድንን›› አቋቁመው መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ሻይማና የቡድኗን አባላት ይህን ለማድረግ የገፋፋቸው ሻይማ ለስፖርት ያላት ፍቅር ነው፡፡ ሻይማ ‹‹እግር ኳስ ህይወቴ፣ ህልሜ፣ ተስፋዬ ሁሉም ነገሬ ነው፡፡ እግር ኳስ መጫወት የጀመርኩት ገና ልጅ እያለሁ ነው፡፡ ሴት ፕሮፌስናል የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ልጃገረዶቹን ክህሎት እንዲያገኙና እንዲሰለጥኑ ለማድረግ ወሰንኩ›› ትላለች፡፡
የወርቃማ ልጃገረዶች የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በመቋዲሾ ሱማሊያ ልምምድ ጋደረጉ በኋላ በቡድን የተነሱት ፎቶ፡፡
34
አ ሚሶ ም መ ጽ ሔ ት
ልጃገረዶች እግር ኳስ የወርቃማ ልጃገረዶች እግር ኳስ ክለብ መስራቿ ሻይማ ያደገችው በኬንያ መዲና ናይሮቢ ሲሆን የእግር ኳስ ፍቅሯ የተጀመረው እዛ ነው፡፡ ሻይማ ከወንዶች ጋር እግር ኳስ ጨዋታ ስትጫወት አፍጥጠው ይመለከቷት እንደነበር ትናገራለች፡፡ ትልቅ ድጋፍ ታገኝ የነበረው አብረዋት ካደጉ ወጣት ወንዶች ብቻ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ‹‹አብሬያቸው ያደግኳቸው በእጅጉ ያበረታቱኝ ነበር፡፡ ኳስ መጫወት ስጀምር የጀመርኩት ከወንዶች ጋር ነው፡፡ ከሴቶች ጋር አይደለም›› ትላለች፡፡ ከሻይማ የእግር ኳስ አካዳሚ ጋር በቅርበት የሚሰሩት የሱማሊያ ሆፕ ሪስቶሬሽን ድርጅት (ኤስኦኤችአርኦ) መስራች የሆኑት መሀመድ ሸሪፍ ከሻይማ ታላላቅ ደጋፊዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ‹‹የሱማሊያ ልጃገረዶች ለመጀመሪያ ጊዜ እግር ኳስ ለመጫወት ሲወጡ ማየት ልብ የሚነካ ነገር ነው፡፡ ይህ ከእነርሱ ጋር መስራቴን እና ህልማቸውን እንዲያሳኩ ለማበረታታት አነሳስቶኛል›› በማለት ይናገራሉ ሱማሊያ ውስጥ እግር ኳስ ብዙ ተከታይ አለው፡፡ የሀገሪቱ የወንዶች እግር ኳስ ሊግ የተጀመረ ሲሆን በርካታ ሱማሊያውያን ወንድ እግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ፊታቸውን በማዞር የተሸሉ እድሎችን ፍለጋ ሀገሪቱን ጥለው ይሄዳሉ፡፡ ሻይማ ሱማሊያ ውስጥ የሴቶች እግር ኳስን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የሚቻልበት ጥሩ እድል አለ ብላ ታምናለች፡፡ በጥቂት ግፊት ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በሀገሪቱ ታዋቂነትን ሊያገኙ እና ምናልባትም የሴት የእግር ኳስ ቡድኖች በቂ ድጋፍ ከተደረገላቸው ከወንዶች እኩል ታዋቂና ተወዳጅ ይሆናል ብላ ተስፋ ታደርጋለች፡፡ አሚሶም እንደ ሻይማ፣ የቡድን ጓደኞቿ እና ሌሎችም ወጣቶች የሚዝናኑባቸው እግር ኳስና ሌሎችም የስፖርት አይነቶች እንዳይስተጓጎሉ አሁን የተፈጠረውን መረጋጋት ዘላቂ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
የወርቃማ ልጃገረዶች የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በመቋዲሾ ሱማሊያ ልምምድ ሲያደርጉ፡፡ አሚሶ ም መ ጽሔ ት
35
መስመር ላይ እኛን ያግኙ: