መምህር ኃይለ-ሚካኤል አስፋው (Memher Haile-Michael Asfaw)

Page 1

መምህር ኃይሇ ሚካኤሌ መምህር ኃይሇ ሚካኤሌ ከኣባታቸው ከአቶ አስፋው ማሩ ( በስመ ክርስትናቸው ሣህሇ ማርያም) እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ተዋበች ካሣ ( በስመ ክርስትናቸው ወሇተ ኢየሱስ) በዴሮው ወል ጠቅሊይ ግዛት በአሁኑ ዯቡብ ወል ሀገረ ስብከት አማራ ሳይንት ውስጥ ምስካበ ቅደሳን ገዲም ሕዲር 12 ቀን 1923 ዓ.ም. ተወሇደ፡፡ በተወሇደ በዏራት ዏመታቸው ጀምረው በገዲሟ ከነበሩት መምህር ፋንታ ከፊዯሇ ሏዋርያ አንሥተው ዲዊት ዯግመው ግብረ ዱቁናውን አጠናቅቀው በሰባት ዏመታቸው ከብጹዕ አቡነ ይስሏቅ ዱቁና ተቀበለ፡፡ ከዚያ ጊዜ አንስተው ገዲሟን በዱቁና እያገሇገለ የቅስናውን ጓዝ ካጠኑ በኋሊ በገዲሙ ከነበሩት መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ቅኔ ተቀኙ፡፡ ከዚሁ በማስከተሌም በዚሁ ገዲም ጾመ ዴጓ፣ ምዕራፍ እና የብለያት ትርጓሜን ተምረዋሌ፡፡ ከዚያም በ18 ዏመታቸው በዚያው በምስካበ ቅደሳን ገዲም መንኩሰው አሁንም ቅስና ከአቡነ ይስሏቅ ተቀበለ፡፡ በገዲሚቱም በረዴእነት( እንጨት በመፍሇጥ፤ ውኃ በመቅዲት፤ እርሻ በማረስና በመሳሰሇው) በኋሊም ዯግሞ በገበዝነት ሇሁሇት ዓመታት ያህሌ አገሌግሇዋሌ፡፡ ከዚህ አገሌግልት በኋሊ ግን እዚያው ሳይንት ውስጥ ወዲሚገኘው መሇክዯፈር ኢየሱስ በመሔዴ ከመምህር ገብረ ጻዴቅ ሦስት ዓመት ቅዲሴውን ከነሙለ ጓዙ አጥንተው አስመስክረዋሌ፡፡በ1944 ዓ.ም ዯግሞ ዯሴ ወጥተው ቁምስናውን ከብጹዕ አቡነ ገብርኤሌ ተቀብሇዋሌ፡፡ መምህር ኃይሇ ሚካኤሌ ከዚህ ቆይታቸው በኋሊ በ1947 ዓ.ም. ዯቡብ ጎንዯር እስቴ ወረዲ ውስጥ ወዯሚገኘውና ወሊዳ ሉቃውንት መካነ ጉባዔያት ወዯ ሆነው ጥንታዊው ዯብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ተሻግረው ከስመ ጥሩ የቅኔና የመጻሕፍት ሉቅ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ጉባኤ ገቡ፡፡ ይህን ታሊቅ ጉባኤ ከተቀሊቀለ በኋሊ ቅኔውን አስፋፍተው መጻሕፍቱን ማሔዴ ጀመሩ፡፡ በአምስት ዏመት ቆይታቸውም ሏዱሳትን በሙለ ፤ውዲሴ ማርያምና ቅዲሴ ማርያም ትርጓሜ፣ ፍትሏ ነገሥት፣ባሕረ ሏሳብ፣ ኪዲንና ትምህርተ ኅቡአት ትርጓሜን አጠናቅቀው ተምረዋሌ፡፡ በወቅቱ ንግሥተ ንግሥታት ዘውዱቱ በአንዴ ግሪካዊ መሏንዱስ ያሠሩት የዯብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በጣሌያን ከተቃጠሇ በኋሊ ዲግመኛ በንጉሠ ነገሥቱ ቀዲማዊ ዏጼ ኃይሇ ሥሊሴ ትዕዛዝ በታሊቁ አቡነ ሚካኤሌ አስተባባሪነት ተሠርቶ ተጠናቅቆ ስሇነበርና እቦታው ሊይ ተቀምጠው ያሠሩት የነበሩት በዚሁ ቦታ ተምረው ከጣሌያን ወረራ በኋሊ ግብጽ ወርዯው ከተሾሙት አምስቱ ሉቃነ ጳጳሳት አንደ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ሚካኤሌ ሉቀ ጳጳስ ዘጎንዯር ሁሌ ጊዜ እንዯሚያዯርጉት መስከረም 21 ቀን ወዯተወሇደባትና ወዯ አዯጉባት ግሸን ማርያም ሉሳሇሙ ሔዯው በዚያው አርፈው ስሇተቀበሩ ሇምርቃቱ የመጡት የኋሊው ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍልስና የትግራዩ ታሊቁ አቡነ ዮሏንስ ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የጉባኤውን ታሊቅነትና የመምህሩን ሉቅነት የተመሇከቱት አቡነ ዮሏንስ መምህር ገብረ ጊዮርጊስን አግባብተው ወዯ ትውሌዴ አካባቢያቸው አክሱም እንዱሔደ ሲያዯርጉ መምህር ኃይሇ ሚካኤሌ በዚያው ዓመት በ1952 ዓ.ም. ጉባኤውን ተረክበው ማስተማር ጀመሩ፡፡ እንዯ የኔታ ትውስታ ጉባዔውን ከመረከባቸው አንዴ ዓመት ቀዯም ብል ንጉሠ ነገሥቱ እቦታው ዴረስ በሄሉኮፕተር መጥተው ቤተ ክርስቲያኑንና አብያተ ጉባኤያቱን ጎብኝተዋሌ፡፡ በጊዜው ቅኔና የመጻሕፍት የሚማር ብቻ 400 የሚዯርስ ተማሪ ስሇነበር ተማሪዎቹ ሇንጉሡ ዯበሎቸውን እያነጠፉ ተቀብሇዋቸው ነበር፡፡ ንጉሡ ግን እያስነሱ እያሸከሙ ሳይረገጡት ከመግባታቸውም በሊይ ሲመሇሱ ሇሁለም የሚዲረስ አንሶሊና አቡጀዱ ሌከውሊቸው ነበር፡፡ መምህር ኃይሇ ሚካኤሌ ጉባኤውን ከተረከቡ በኋሊ ሊሇፉት ሃምሳ ዓመታት በዯብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ወንበራቸውን ሳያጥፉ በማስተማር እጂግ ብዙ ሉቃውንትን ሇኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበርክተዋሌ፡፡ ከ90 በሊይ በስም የሚታወቁ ሉቃውንትንም አፍርተዋሌ፡፡ የቀሇም ቀንዴ ይባለ ከነበሩት ከቀዴሞው ሉቀ ጉባኤ አስበ (በኋሊ አቡነ ኤሌያስ ይባለ ከነበሩትና ከአቡነ ዮሴፍ ጋር በመኪና አዯጋ ያረፉት) ጀምሮ አሁንም በሉቃውንት ጉባኤ የሚያገሇግለ በአዱስአበባና ከትግራይ እስከ ሸዋ ዴረስ ባለት ብዙ ጥንታውያን ቦታዎች የሚያገሇግለ ታሊሊቅ ሉቃውንትን አፍርተው አሌፈዋሌ፡፡


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.