2016 naespasa Magazine

Page 1

1 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማኅበር የተዘጋጀ

2016


2 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማኅበር የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ

አብዲ ሰይድ ፕሬዚዳት

ታደሰ ገብረስ ፀሐፊ

መንግቱ ሁሴን ምክትል ፕሬዚዳንት

ማሕደር ገብረሥላሴ ሕዝብ ግንኙነት

ክፍሉ መብራቱ ኦዲተር

ካሳዬ አራጌ ገንዘብ ያዥ

ፀጋዬ ዘነበ ሂሣብ ሹም


3 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ብርሃኑ ወልደማርያም የቦርድ ሰብሳቢ

አበበ ሽፈራው ፀሐፊ

ሰለሞን መገርሣ ዓባል

አስናቀ ደምሴ አ.አ. ከተማ ተጠሪ ዳይሬክተር

ንጉሤ ገብሬ ፕሬዚዳንት

ጌቱ መልካ ገንዘብ ያዥ

ፍታነገስት በርሔ ሕዝብ ግንኙት

ሰለሞን መኩሪያ ሂሣብ ሹም

ምትኩ ከበደ ዓባል

በሐብቱ ገብረማርያም ምክትል ፕሬዚዳንት

ተስፋዬ ወልደሰንበት ኦዲተር

ሽመክት በቀለ ዓባል


4 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሰይፈ ውብሸት ፕሬዚዳንት

አዲስ ብሥራት አማካሪ

ናይጄሪያ አብዱራዛቅ ምክትል ፕሬዚዳንት

ገነነ መክብብ ፀሐፊ

ጌታቸው በለጠ ኦዲተር

አንድነት በቀለ ሕዝብ ግንኙነት

ባዩ ሙሉ ገንዘብ ያዥ


5 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቡልቻ ጃርጎ

አዲስ አለማየሁ

አማረ ዘውዴ

አስራት ገብሬ

እልፏ ነጋሽ

ፍስኃ ተስፋጽዮን

ፍስኃ ወልደአማኑኤል

ለማ ክብረት

ዳዊት አስመላሽ

ሲሳይ ተሰማ

ሰለሞን ደራ

ታዬ ወግደረስ

ተስፋዬ ውርጌቾ

ፀጋዬ ባቲ

ወርቅዬ አለማየሁ

ዮሴፍ ነጋሽ

ቢኒያም ተሻለ

ሰለሞን አየለ

ብርሃኑ ወልደማርያም

ቅዱስ ረዳ


6 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አፈወርቅ ጂሞ

ኤርሚያስ አበራ

ታምራት ፀጋዬ

አሸናፊ አትራጋ

መሰለ ገዳ

ትእዛዙ ነጋሽ

ፍቅሩ ኪዳኔ

አቡዱል ከሪም ኡመር

አቦነህ ማሞ

አብርሃም ብሥራት

ኃይሉ ሃብቴ

ኤርሚያስ ኪዳኑ

መርእድ

ተቀባ ሁሪሳ

የምስራች ማሞ

አበበ ገላጋይ

አፈወርቅ ከበደ

ዮሐንስ

አበራ መንግሥቴ

አፈወርቅ ኪሮስ


7 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አፈወርቅ ጠናጋሻው

አረጋኸኝ ወራሽ

ብርሃኑ ወልደሥላሴ

ብሩክ እስጢፋኖስ

ዳንኤል ክፍሌ

አፍሪካ ተፈራ

አሸናፊ ሲሳይ

ቢኒያም ገብሩ

ቸርነት ተክሉ

ዳዊት ጌታቸው

አሌክስ አበራ

አንዱአለም አርአያ

አየለ መንጀታ

በኃይሉ አሰፋ

ቢኒያም ኃይለ ሥላሴ

ቦጋለ ወ/ማርያም

ዳግም መንበሩ

ዳኛቸው ጥቅሻ

ኤልያስ ነጋሽ

ተሾመ በየነ


8 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

እሱባለው ኦሜጋ

ፋሲል ስዮም

ጌቱ ከበደ ገብሩ ወልደ አማኑኤል

ግርማ ታፈሰ

ግሪቲ ገብረመሥቀል

መስፍን ገብረጊዮርጊስ

ሙሉጌታ ወልደየስ

ሚኪያስ ጉርሙ

ጎላ ብርሃኑ

ጆርጅ እሸቱ

ኃይሉ ገብረኪዳን

ኪነ ጥበቡ

መሰለ ክፍሌ

ሚኪኤሌ ሽፈራው

ናርዶስ ስለሺ

መስፍን ተሰማ

ግርማ ታፈሰ

ሳዲቅ ኑሩ

ወንድወሰን አስራት


9 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሰናይ ወልደጊዮርጊስ

ሲራክ ዮሐንስ

ታዲዎስ ጌታቸው

ታምሬ ተፈራ

ተፈሪ ሚካኤል

ተካልኝ ኀብተሥላሴ

ተስፋዬ ታደሰ

ቴድሮስ አባይ

ወልዴ ወልደአማኑኤል

ይማም መሐመድ

የሱፍ አብደላ

ዘላለም ተሾመ

ዘነበ በየነ

ዘሪሁን ከበደ

ሰለሞን ገብሩ

ሰይፈ ብርሃኔ

ቁምላቸው በቀለ

ሐሰን ብርሃን

ሰለሞን መንገሻ

ታደሰ ላቀው


10 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ናደው አምባዬ

መኰንን ጉርሙ

ፀጋዬ ፋንታሁን

ኤርሚያስ ብርሃኔ

አያያ አረጋ

ተድላ ፍስሃዬ

ሙሉጌታ ብርሃኔ

ቢተው አብሬ ኤፍሬም ተሾመ

ወንድወሰን ከበደ

ጠንክር አስናቀ

ዳዊት አጎናፍር

ሰለሞን ኃይሌ

ሞሐባ ላሎ

ሰብስቤ አሰፋ

በቅርቡ በድንገተኛ ሞት ያጣናቸው የማህበራችን አባሎች

ዳዊት በርሄ (ጂንጆ)

መሐመድ አሊ (ሸዳድ)

ዮሐንስ ታምራት


11 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚዳንት መልዕክት፤ በመጀመሪያ የዚህ ማህበር (NASPASA) አባላት እስከ ዛሬ አብዲ ሄርሺ ፕሬዚዳንት

ላደረጋችሁት እና ወደፊትም ለምታደርጉት ትብብር ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡ በመቀጠልም ይህንን ማህበር በተለያየ መልኩ የረዳችሁንና ለማህበራችን መጠናከርና እዚህ መድረስ ከፍተኛ እገዛ ያደረጋችሁትን በሙሉ በእኔና በማህበሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፡፡ ምንም

እንኳን ማህበራችንን (NASPASA) እኛ ያሰብንበት እና የፈለግንበት ደረጃ ባይደርስም ባለችን ዝቅተኛ አቅም የተሰሩትን በጎ ስራዎችና እርዳታዎች ምን እንደሚመስሉ በዚሁ መጽሄት ላይ ማህበሩ የሰራቸውን ስራዎች ተጽፎ ያገኙታል፡፡ ከሁሉም የበለጠ የሚያስጨንቀውና ውስጣችንን የሚረብሸው በሀገር ቤት ለመረዳት በተስፋ የሚጠብቀው ስፖርተኛ ብዛት እና ለመዳን ያላቸውን ጉጉት ሀገር ቤት

በመሄድ በግንባር አግኝተን አውርተናቸዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ በአንድ ወቅት የሀገራቸውን ባንዲራ በአደባባይ ያውለበለቡ ህዝቡን ሲያስጨፍሩና ሲያስደስቱ የነበሩ ዛሬ በተያዩ ምክኒያቶች ተስፈኞች ሆነዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ ተስፈኞች ወንድሞቻችንን ብዙ ልናደርግ ባንችል እንኳን አለሁ ብለን ጥቂት ነገር በማድረግ ተስፋቸውን ልናበራ ይገባናል፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ ማንኛውም የኢትዮጵያ የስፖርት አፍቃሪዎች የሆናች ለዚህ ለተቀደሰ አላማ ይረዳን ዘንድ የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉልን ጥርዬን አቀርባለሁ፡፡

በመጨረሻም በውጭ የምትገኙ እግር ኳስ ተጫዋቾች አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንደሚባለው ሁሉ ለስፖርተኛው ከስፖርተኛ ቀድሞ ሊደረስለት የሚችል የለምና ይህንን መልዕክት እያየንና እየሰማን የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብለን ልንል አይገባንም፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የስታዲየምን በር የረገጠ በሙሉ ይህንን ከዘር፤ ከሀይማኖት፤ ከፖለቲካ፤ እና ከጾታ ነጻ የሆነ የእርዳታ ማህበር አባል በመሆን ወገናዊ ድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡ ከምስጋና ጋር


12 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የአውሮፓ የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር መልዕክት በአውሮፓ የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ከተቋቋመ እነሆነ ሰባት ዓመቱን የያዘ ሲሆን ለዚህ ማህበር መቋቋም ትልቁን ሚና ለተጫወተው እና ዛሬ ማህበሩ እዚህ እንዲደርስ ላደረገው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ታላቅ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

የማህበሩ ዓላማ 1. በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ካለባቸው የጤናም ሆነ የኑሮ ችግር ለማላቀቅ የተቻለውን ሁሉ እርዳታ ማድረግ፤ 2. በአውሮፓ በተለያዩ አላማት የሚገኙትን የቀድሞ ስፖርተኞችን በተቻለ መጠን በዓመት ሁለት ጊዜ ግንኙነት መፍጠር ማገናኘት፤ 3. በአውሮፓ የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በየዓመቱ በሚያደርገው ውድድር ላይ ከሁለት ያላገቡ የቀድሞ ተጫዋቾችወይም አሰልጣኞችን በመጋበዝ ለዝግጅቱ የክብር እንግዳ ማድረግ፤ 4. በአገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ የስፖርት አካዳሚ በመክፈት ለልጆቻችን የስፖርት እድገት እንዲያገኙ ማዘጋጀት፤ 5. ከሰሜን አሜሪካ ካለው የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የተለያየ ዝግጅቶችን በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ታላቅ በዓል ማዘጋጀትና የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ገቢውን ለምናስበው ዓላማ ማለትም አንድ ትልቅ የስፖርት አካዳሚ ለመክፈት በአሰብነው መሰረት ለዚሁ አካዳሚ ማዋል፤ 6. ወደፊት በዓመት አንድ ግዜ በሰሜን አሜሪካ ካለው የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስና ደጋፊዎች ማህበር ጋር በሰሜን አሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ውድድሮችን በማዘጋጀት ገቢ ማሰባሰብ፤


13 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር አመሰራረትና የተከናወኑ ተግባራት፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር በምጻረ ቃል የኢ/እ/ኳ/ታ/ደ/መ/ማ በእንግሊዝኛው ደግሞ NAESPASA ተብሎ የሚታወቀው ለበጎ ስራ ዓላማና ተግባር የተሰባሰበና የተቋቋመ ሲሆን በግሪጎሪያንስ ቀን አቆጣጠር በሐምሌ ወር በ2007 ዓ.ም. ነበር የተመሰረተው፡፡ ይህ የበጎ አድራጎት መረዳጃ ማህበር ከተመሰረተበትና በሁለት እግር ከቆመበት ከዳላስ ቴክሳስ የምስረታ ቀን ጀምሮ እጅግ በርካታ የሆኑ የተነሳላቸውንና ያቀዳቸውን ተግባሮች እንዲሁም መልካም ቁምነገሮች ሲያከናውን

ቆይቷል፡፡ እያከናወነም ነው፡፡ ለዚህ ማህበር መመስረት ዋነኛ በር ከፋች የESFNA በየዓመቱ በሚያደርገው የስፖርት ውድድር ላይ አብዛኛው የቀድሞ ተጫዋቾች ቀኑን ጠብቀው እየመጡ የሚገናኙበት የሚደሰቱበት የድሮ ትዝታቸውን የሚቀሰቅሱበት ግዜ በመሆኑ ሁሉም ያንን ግዜ በጉጉት ይጠብቃል፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ ስንገናኝ የተለያዩ ሀሳቦች ይነሳሉ ሁሉም በየጎራው ሆኖ እንዲህ ቢሆን እንዲህ ብናደርግ እየተባባልን እንከርምና ሳምንቱ አልቆብን ሁሉም ወደ ሀገሩ ይመለሳል፡፡ ታዲያ ESFNA ባይኖር ኖሮ እንዴት መገናኘት ይቻል ነበር የሚለውን ስናስበው በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ለዚህ ነው የ ESFNA መኖር ለኛ ማህበር መወለድ ዋንኛ ምክንያት ነው የምንለው፡፡ ሌላው ይህንን በጎ አመለካከትና ለሌሎች የመድረስን የመርዳትና የማቋቋምን ራዕይ ከራሱ ጋር ብዙ ጊዜያትን ሙግት ገጥሞ ከየት እንደሚጀመር ለራሱና በራሱ ተማምሎ ማድረግ ከሚቻለው ጀመረ የቀድሞው የኤሌክትሪክ፤ የመድንና የኢትዮጵያ

ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አብዲ ሰይድ፤ ሁሌም እየተገናኙ መለያየት በቂ አለመሆኑን አጥብቆ ያምናል፤ ከብዙዎቹ ጋር በተገናኘበት አጋጣሚ ይህንኑ እያነሳ ይወያያል፡፡ ታዲያ አጋጣሚን በመጠቀም በ ESFNA ባዘጋጀው በ2007 ዓ.ም. በዳላስ ውድድር ላይ የተወሰኑ በአንድ ዘመን አብረው የተጫወቱትን ተጫዋቾች ስልክ በመደወል አንድ ላይ ራት ለመብላት ቀጠሮ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ በዚህም የራት ምሽት ላይ ከተደወለላቸው ተጫዋቾች አብዛኞቹ ይገኛሉ እንደተባለው እራት ተበላ ተጠጣ በዚህ ወቅት አንድ ራዕይ ሰንቆ የመጣው አብዲ አስቲ ልጆች አንድ ሀሳብ አለኝ የሚል ድምጽ አሰማ፡፡ የነበረው ተጫዋች በጸጥታ ማዳመጥ ጀመረ በአሁኑ ሰዓት እኛ እዚህ ጠግበን ጠጥተን አንጨፍራለን ከኛ ጋር አንድ ማሊያ ለብሰው ለአንድ ሀገር ለአንድ ባንዲራ አብረውን የተጫወቱ ጓደኞቻችን በሀገር ቤት በህመም ስራ በማጣት እየተሰቃዩ ነው ሌላው በሰው ሀገርም በስደት ላይ ሆነው ስለሚንገላቱ ወንድሞቻችንና ጓደኞቻችን ምን ማድረግ

አለብን፤ የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድ ተጫዋች ተነስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረ በኬንያ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል፤ ለምን አሁን አንድ ነገር አናደርግም የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡ ሁሉም ሰው ወዲያውኑ በእጁ ላይ የያዘውን አዋጥቶ እንዲላክለት ተባለ ሆኖም ሁሉንም ነገር የምናደርገው በስሜትና በፍላጎት እንጂ እንዴት መደረግ እንዳለበት እንኳን ውይይት የለም፡፡ ለአብዲ ገንዘቡ ተሰጥቶ ይላክለት በማለት ተስማማን፡፡ ከቤቱ ደግሞ አንድ ሌላ ተጨዋች ሀሳብ አቀረበ ይሄ ነገር በዚህ እንዳይቆም በየወሩ እናዋጣ የሚል በዚህም ሀሳብ ሁሉም ሰው ተስማማ እውነቱን ለመናገር ሁሉም ተጫዋች ተደስቶ ምሽቱ አለፈ፡፡


14 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የNAESPASA ረጅም ጉዞ በአብዲ ሰይድ ጠንሳሽነትና በ22 የቀድሞ የብሔራዊ ቡድንና የክለብ ተጫዋቾች ተጀመረ፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ግብዣ በኋላ ብዙ የተሟላ ነገር የለም መጀመሩ እንጂ አቅጣጫው ምን እንደሆነ እንኳን አናውቅም ነበር፡፡ ብቻ ስፖርተኛው ለስፖርተኛው መድረሱ ውስጣችንን ደስታ ሰጥቶናል፡፡ በተለይም ሀገር ቤት ስላሉት ስናስብ እያንዳንዱ ውስጡን የሚሰማው ስሜት አለ፡፡ እኔም ባልወጣ ኖሮ ይኸው ነበር የሚጠብቀኝ የሚል ጥያቄ እራሱን ይጠይቃል፡፡ ለዚህም ይመስለናል ማህበሩ ገና ከጅምሩ ፍቅር እምነት ተስፋ በእያንዳንዱ ሰው ፊት ላይ ይነበብ የነበረው፡፡ ምንም አይነት ነገር ቢመጣ የሚያቆመን ነገር እንደሌለ ብዙዎቻችን ለራሳችን ቃል ገብተናል፡፡ ለዚህ ነው ማህበሩ ተቋቁሞ ለሁለት ዓመታት ያህል ሀላፊነቱን ለአብዲ ሰይድና ለታደሰ ተክለጻድቅ ላይ ትቶ የአባላት ክፍያችንን ለነሱ በመላክ በመተማመንና በፍቅር በተቻለን አቅም የተጎዱትን ስንረዳ ቆይተናል፡፡

ከነዚህ ሁለት ዓመታት በኋላ ግን ነገሮች እየሰፉ ማህበራችን እየታወቀ እርዳታ ጠያቂው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በዚህ አይነት መልኩ መቀጠል አስቸጋሪ ስለሚሆንና ህጋዊ መሆን ስላለበት እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. በችካጎ ከተማ ላይ በተደረገው አጠቃላይ ስብሰባ ሰባት አባላት ያሉት የተሟላ የስራ አመራር ኮሚቴ እንዲመረጥ ተደረገ፡፡ ይህንን ምርጫ ስናካሂድ ብዙ ህግና ደንብ ወጥቶለት ሳይሆን አብዛኞቹ መስራች የነበሩ በማህበሩ መቋቋም በተለያየ መልኩ እገዛ ያደረጉ በተጫዋችነት ዘመናቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለክለቦች ረጅም ጊዜ ያላገለገሉ በተጨማሪም ከስፖርተኛ ጋር ይግባባሉ የሚሏቸውን ስድስት አባላት ተጠቁመው በሙሉ ድምጽ ተመረጡ፡፡ አንድ አባል ደግሞ ከደጋፊዎች ተብሎ ሁሌም ከኳስ ሜዳ የማትጠፋ እህታችንን በማካተት ምርጫው ተጠናቀቀ፡፡

በምርጫውም መሰረት አብዲ ሰይድ

ፕሬዚዳንት

መንግስቱ ሁሴን

ም/ፕሬዚዳንት

ታደሰ ተክለጻዲቅ

ጸሐፊ

ካሳዬ አራጌ

ገንዘብ ያዥ

ክፍሉ መብራቱ

ኦዲተር

ጸጋዬ ዘነበ

ሂሳብ ሹም

ማህደር ገ/ስላሴ

ህዝብ ግንኙነት

መስፍን ገ/ጊዮርጊስ

አባል

አቦነህ ማሞ

አባል

ዳዊት ጌታቸው

አባል

ናርዶስ ስለሺ

አባል

ዳዊት አጎናፍር

አባል በመሆን ተመረጡ፡፡


15 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ይህ የስራ አመራር ኮሚቴ ከዚህ ቀደም በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ገብተው ያገለገሉ ባይሆኑም እንኳን አላማውን የሚያምኑበት በመሆኑ ስራቸውን በቅልጥፍና ጀምረው በሀገር ህግና ደንብ መሰረት የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ሌሎች አባላቶችና ሙያተኞችን በማነጋገር ማህበራችንን ሊመጥን በሚችል መልኩ ማህበራችንን ከዘር፤ ከሀይማኖት፤ ከጾታ፤ ከፓለቲካ ነጻ የሆነ መተዳደሪያ ደንብ አዘጋጅቶ በማቅረብ በመላው ጉባኤ ፊት አጸደቀ፡፡ የማህበራችን ስም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር (NAESPASA) በሚል ተሰየመ፡፡ በመቀጠልም በ2010 ዓ.ም. ከታክስ ነጻ የሚያደርገንን ህጋዊ ላይሰንስ በእጃችን አስገባን፡፡ እንግዲህ የ(NAESPASA) አመሰራረት ከጥንስሱ እስከ ህጋዊነቱ ይህንን ይመስላል፡፡ ይህ በሐምሌ ወር በ2007 ዓ.ም. የተቋቋመው ማህበር አላማም ብሎ የተያዘው ለሌሎች የመድረስ የእርዳታ ሰጪነት በጎ ፈቃደኝነት ላይ በመንተራስ ለብዙዎቹ በሚችለው አቅምና ጉልበት ሀሳብና ገንዘብ በተጠየቀውና በተፈለገው ግዜና ስፍራ ላይ ሁሉ ተገኝቶ ድርሻውን በተገቢው መልክ አድርጓል፡፡ በጠቅላላው ማህበሩ ከተቋቋመ በኋላ እጅግ በጣም ብዙ የተረጂዎች ጥያቄዎች ስለሚመጡ እኛ ያለን አቅምና መረዳት የምንችለው ምንያህሉን ነው በሚልከተወያየን በኋላ ተረጂዎች ሟሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች አዘጋጀን፡፡ ይህንን ጉዳይ እንዲህ ሲያዩት ቀላል ቢመስልም ስራው ላይ ግን እጅግ በጣም አስጨናቂና ህሊናህን እረፍት የሚነሳ ነው፡ ምክንያቱም እነዚህ ተረጂዎች በአንድ ወቅት የሀገር ባንዲራን ያውለበለቡ የኢትዮጵያ ስም ያስጠሩ ብርቅ ተጫዋቾች የነበሩ

ክብርና ዝና የነበራቸው ስለሆኑ ከእነዚህ ተረጂዎች የምትሰማው ችግር ያስጨንቅሃል በዛ ላይ እያንዳንዱ ተረጂ የራሱን ችግር ከሁሉም የበለጠ አድርጎ ነው የሚያስበው ደግሞም አይፈረድባቸውም ግማሹ ታሞ አልጋ ላይ ነው ሌለው ደግሞ የሚላስ የሚቀመስ የለውም የቀረው ደግሞ ውጭ ሄጄ ካልታከምኩ እግሬ ሊቆረጥ ነው ይልሃል፡፡ የቱን ይዘህ የቱን ትተዋለህ የሚበላውና የሚጠጣው አጥቶ የሰው እጅ ላለማየት በችግር የሞቱ ስፖርተኞች እንደነበሩ እናውቃለን ወይስ የሚረዳው አጥቶ የአልጋ ቁራኛ የሆነ አልያም መድሀኒት መግዣ አጥቶ አይኑ ሊታወር የደረሰ ስንቱን ሰምቶ ይቻላል፡፡ አቅም ኖሮን ለሁሉም ብናደርግላቸው እንዴት በተደሰትን ነበር፡፡ ነገር ግን አቅማችን ስለማይፈቅድ ቀደም ብለን እንደገለጽነው ትንሽዬ መመዘኛ አድርገን ተራ በማስያዝ ይህ ማህበር የሚችለውን ያህል አድርጓል፡፡

NAESPASA በተለያየ መልኩ ብዙ ጥያቄዎች ቢቀርቡልንም ትክክለኛ መስመሩን ተከትለው ለ48 ስፖርተኞች ጥያቄያቸውን ያስተናገድን ሲሆን በቁጥር ከ35 በላይ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን የህክምና ወጪአቸውን ሸፍነን አሳክመናል ለተቸገሩትም ከችግራቸው እንዲያገግሙ የእርዳታ እጃችንን ዘርግተናል፡፡ ከእነዚህ እርዳታችንን ከፈለጉትና ምላሽ ከሰጠናቸው ውስጥም ከ6 በላይ የሚሆኑ ወደ መልካ ጤንነታቸው ተመልሰው ከነበረባቸው ድካምና ህመም አገግመው እራሳቸውን ቤተሰቦቻቸውን ችለውና አሻሽለው ለሌሎች ልክ እንደነሱ እርዳታን ለፈለጉ መድረስ ችለዋል፡፡ (ይህንን የምስክርነት ቃል ከራሳቸው እንደበት በዚሁ መጽሄት ገጽ ላይ ያገኙታል፡፡)


16 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ይህ በምጻረ ቃል NAESPASA ተብሎ በእግር ኳስ ተጫዋቾች የተቋቋመው ማህበር ከምስረታው እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የተለመደውን እርዳታውን በተለያየ ዓለምና ሀገራት ያሉትን ወንድሞቻችንን ተደራሽነቱን በደንብ አረጋግጧል፡፡ በዚህ መሰረት ይህ በገንዘብ ሲተመን 1,213,160 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሶት ሺ አንድ መቶ ስድሳ) የኢትዮጰያ ብር የሚሆን ወጭ በማድረግ ከደረሰባቸው ችግርና ህመም እንዲያገግሙ እንደሁም ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በሰሜን አሜሪካ እጅግ ብዙ የሚባሉ በተለያየ ዘመን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋችነት ህይወት ውስጥ ያለፉ ተጫዋች እንዳሉ የታወቀ ነው ሆኖም ግን ይህ የቀድሞ ተጫዋቾች ማህበር ከተቋቋመ ጊዜያት አንስቶ በዚህ ማህበር ውስጥ አለመሰባሰባቸው በመጠኑም ቢሆን ያሳዝናል፡፡ ይህ ማህበር ሲቋቋም የኛን እድል ያላገኙትን በችግራቸውም ማንም ሊደርስላቸው ያልተቻላቸውን

የዛን ዘመን ብርቅዬዎች ለመታደግ ባጠቃላይ ባልቻሉበት መንገድ ልንደርስላቸው ስላሰብን ነውና የተሰባሰብነው ይህ መልዕክት የሚደርሳቸው ሁሉ ሙሉ ሀሳባቸውን ወደዚህ ማህበር እንዲያደርጉ በተጎዱትና እርዳታችንን በሚፈልጉ ወንድሞቻችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ማህበራችን ከተቋቋመ ግዜ አንስቶ ብዙና ወጥ የሆኑ ስራዎችን መከናወናቸው በዓላማና በእቅድም ውስጥ የተያዙ እጅግ ብዙም የሆኑ ውጥኖች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ግማሾቹ አላማዎች በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተቀመጡ ሲሆኑ የተግባራዊነት (የመተርጎም አቅማቸው ጊዜያትንና አቅማችንን እየጠበቀ መሆኑ በይፋ ይታወቃል፡፡ የወደፊት የማህበሩ ዓላማን ጎል በሚለው አንቀጽ ስር በሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ግልጋሎት ሰጥተው ዕድሜና ጤና ማጣት

ችግራቸው ሆኖ በተለያየ ችግር አረንቋ ውስጥ የወደቁ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች በቀረችው ዘመናቸውና ህይወታቸው ስራ ሰርተው እራሳቸውን መቻል ደረጃ እንዲደርሱ ለቀረውም ቤተሰቦቻቸው በማሰብ ጭምር አንድ ትልቅ የሆነ ፕሮጀክት ለመክፈት ከፍተኛ የሆነ እቅድ ተነድፏል፡፡በተግባራዊነቱና ተፈጻሚነቱ የኛ የዚህ የስራ ባለድርሻዎችና ለዓላማው ውጥን ከግብ መድረስ ከፍተኛ ጥረት አድራጊዎች ትልቁ የቤት ስራችን ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለወደፊትዋ ሀገራችን ኢትዮጵያ የእግር ኳስ እድገትና መሰረት ሊሆን ይቻላልብለን በእቅድና በዓላማችን ውስጥ ያስቀመጥነው ለወደፊቱም መጪው ትውልድ ይጠቅማል ብለን ያሰብንለት አንድ ዘመናዊ ሁለገብ ሁሉን አቀፍ የእግር ኳስ አካዳሚ ለመክፈትና በተተኪነትና በጥራት እንዲሁም በእውቀት ደረጃ እየወረደ የሄደውን ይህን ተወዳጅ የሀገራችን አንዱን የስፖርት መስክ (እግር ኳስ) ችግሮች ለመቅረፍ በማሰብ እንዲሁም ለመታደግ ጭምር ነው፡፡ ይህም ስለሆነ የማህበሩ የስራ

አመራር ኮሚቴ ከሚያወጣቸው ከሚነጋገርባቸው የስራ ውጥኖች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ዓላማ አድርጎት የተነሳው ይህ መነሳሳትና የዓላማ ጽናታችን ከልብ እንዲደርስ ደግሞ ግለሰቦች ድርጅቶች አባላቶች እንዲሁም የዚሁ የማህበራችን ደጋፊዎች ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን አሁንም እናሰማለን፡፡ NAESPASA ሲመሰረትም ሆነ ተቋቁሞ እንደ አንድ የእርዳታ ድርጅት የራሱ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲጀምር ከማንኛውም የፖለቲካ የሃይማኖት የዘርና ከቀለም ልዩነት ውጪ መሆኑን በነጻነት የሚንቀሳቀስ እራሱን ለመቻል በራሱ ህግና ደንብ የሚመራ ስለመሆኑ የእስከ ዛሬው ታሪኪና እንቅስቃሴው በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡


17 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

እኛ የNAESPASA የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ወደ እውነተኛ መንገድ የሚያስኬደውን የሽምግልና ሂደት ለማድረግ ስንነሳ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ምን ይላል የማህበሩ ስራ አመራር ህግና ደንቡን ተከትለን ሽምግልና ውስጥ የገባን ብንሆንም እንደ ግል ስሜታችን ሳይሆን እንደ ማህበር መሪነታችን ለማሰብ በመቻላችን የማህበሩን ህግና ደንብ በመጠበቅ በውስጡ ብዙ አወዛጋቢና አከራካሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም የማህበራችን አንድነትን ቅድሚያ በመስጠት የመጨረሻ ውሳኔ ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ ጠቅላላ ጉባኤው የወሰነውን ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ይህ የአሰራር ሂደት ነው የማህበሩን አመራር ጥንካሬ ያስመሰከረው እንግዲህ በእነዚህ ሁለት ጠንካራ ነጥቦች ላይ ተመርኩዘን በመስራታችን ማህበራችን ከመናጋት ድኗል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ጠንካራ የስራ አመራር ኮሚቴ መኖሩ ነው ብለን እናምናለን፡፡

ይህንን ለማለት የቻልነው በወቅቱ በሁለቱም ፌዴሬሽኖች ደጋፊዎች አማካኝነት በማህበራችን ላይ በተለያየ መልኩ ጫና ያሳደረብን ቢሆንም በተለይ የስራ አመራር ኮሚቴውን ሁለት ቦታ ለመክፈል ያልተደረገ ጥረት የለም በሌላ በኩል ደግሞ የማህበሩ አባላቶች በአመራር ላይ እምነት እንዲያጡ በማድረግ አባላቶቻችን ለማነሳሳት ተሞክሯል፡፡ ከዚኅም በተጨማሪ በወቅቱ በብዛት አዳዲስ አባላት ተመዝግቦ በመግባት ይህንን ጉዳይ ለማባባስና ችግር ለመፍጠር ታስቦ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴ በሚያምንበት ጉዳይ በአንድ ላይ ቆሟል የስራ አመራር ኮሚቴው አንድ ላይ ሊቆም የቻለበት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ለችግሮች መልስ የሚሰጡ ይሆናሉ፡፡ የማህበሩ ዋና ዓላማ ምንድን ነው፡፡ የተነሳንበት ዋናው ዓላማ ከኛ የባሱና የተጎዱትን ወንድሞቻችንን ለመረዳት እስከሆነ ድረስ እርዳታው ሊቀጥል የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ማለትም ቢቻል ሁላችንንም ሊያያዘን የሚችል ድልድይ በመፍጠር በአንድነት

መጓዝ እንድንችል ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሁሉንም በእኩል አይን የምናይበትን ሁኔታ መፍጠር ነበረብን ለዚህ ነው ከዚህ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ውስጥ አንዳችንም ብንሆን በማህበሩ ስም ምንም ዓይነት ጋዜጣዊ መግለጫ ወይም ቃለ ምልልስ በወቅቱ ያላደረግነው ምክንያቱም በዚህ ዓይነት ውስጥ እያለን የሚሰጠው የግል አስተያየት እንኳን የማህበሩ አመለካከት ወይም አቋም ተደርጎ ሊወሰድ ስለሚችል ከተለየ አቅጣጫ የተነሱትን ችግሮች አርግበናል፡፡ በወቅቱ ተፈጥሮ በነበረው የማያስማማ ልዩነት ይህ የመረዳጃ ማህበር ሁለቱንም ወገኖች ወደ አንድ ጠረጴዛ ላይ ለማምጣት ለማነጋገር የተፈጠረው ችግር እንዲቀረፍ በውይይት እንዲፈታ የነበረ አብሮነት ወደፊትም እንዲራመድ አንድነታችን እንዲጠነክር የሚበጅና የተሻለ ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ እንዲካሄድ አበክረን መክረንበት ተወያይተንበትና መፍትሄ እንዲኖረው ተመኝተን ብዙ ጥረቶች አድርገን ነበር፡፡ ሆኖም ግን በወቅቱ በነበሩት የሁለቱ ወገኖች አመራርና ሰብሳቢዎች ምን ዓይነት አዋንታዊ ምላሽ ሳናገኝ ለኛም የሰጡት ግምት

አነስተኛ መሆኑን ተረድተንበት በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ የሽምግልና ሂደታችን ከተወሰነ መንገድ በኋላ ለማቆም ተገደናል፡፡ በወቅቱ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የማህበራችን ህልውና ይነካል አባላቶቻችን በአመለካከት መለያየት ወደ ተለያየው ሁለት ወገን ሊሄዱብን ይችላሉ ትንንሽም ቢሆን ማህበራችንን ሊያዳክም ይችላል ከሚል በጎ አመለካከትና ሆደ ሰፊነትም ጭምር ነበር እንደምነታችንና አመለካከታችንም ጭምር አዲስ ወደ ተመሰረተው የስፖርት ፌዴሬሽን ስለሄዱት የዚህ ማህበር አባላቶች አመለካከት ይቀየራል ብለን አንዲትም ሰኮንድ አስበን እንዳልነበር ይህም የመረዳጃ ማህበራችንም ከማንኛውም ፌዴሬሽን ያልወገኑ መሆኑን ልብ ብለን ተረድተው እስከ መጨረሻው ከኛው ጋር ይቀጥላሉ ብለን አስበን ነበር፡፡ ነገር ግን የሆነው ሁሉ ከዚህ የተለየ ነበርና እንደስሜታቸውና እንደአመለካከታቸው ሆኗል፡፡ እንደ አለመታደል ሆነና ነው እንጂ ሰከን ብለው ቢመለከቱት ያለውን ልዩነቶች ልብ ቢሉ ምላሹ በእጃቸው ነበር፡፡


18 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የሚገርመውና የሚያስደንቀው የሰው ተብዬም አስተሳሰብ አመለካከት ስር የሰደደ በዚህን ያህል ደረጃ የተለያየ መሆኑን ያሳምን ያስመስከሩን ማንነታቸው በገሀድያመለከቱን ሁሌ አክብሮታችን እንደማይለያቸው ያለው በጎአዊ ስሜትና ወገናዊነት በቃላትና በአረፍተ ነገሮች ድርደራ ብቻ ልንገልጸው የምንችለው አይደለም፡፡ እስከዛሬም የማህበራችንን እንቅስቃሴና እመርታ ከጎናችን ሳይለዩ በኛም ውስጥ ያለው የመልካም ነገር መስራትና ለሌሎች የመድረስ ዓላማቸው አንድ ሆኖ በየወሩ የአባላትን ክፍያ ሳያቋርጡ የሚከፍሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ይህ ማህበራችንም በእነዚህ የማህበራችን አርቆ አሳቢ ልጆች ላይ ያለው አመለካከት ፍቅር እስከወዲያኛው ነውና ልንሰጣቸው

የሚገባው ፍቅርና አክብሮት ወደር የለውም በመፈጠራችን እንኮራለን በመኖራችን እንጠነክራለን በመሰባሰባችን በመጠናከራችን ደግሞ ለሌሎች እንተርፋለን ለሌሎች ተስፋና ስንቅ ብርታትና ጉልበት እንሆናለን፡፡ ይህ ማህበር ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ተስፋ ሰጪና አሉታዊ እንዲሁም አመርቂ የሆኑ ሰራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ከነዚህም ሰራዎች ውስጥ የማህበሩን አድማስ በማስፋት በሌሎች ክፍላተ ዓለማት ጋር በመገናኘት በመወያየትና በመመካከር ተመሳሳይ አላማ ያላቸው እህት ማህበራትን በያሉበት እንዲቋቃሙና ዘርፈ ሰፊ የሆኑ ስራም ለወደፊቱ ለመሰራት በአያሌው እጅግ አመርቂና አስደሳች እመርታዎችን አሳይቷል፡፡ በተለይም በአውሮፓ በኢትዮጰያ፤ በአውስትራሊያን መልካም ጅምሮች ተሰርተዋል ታይቷልም፡፡ አብዛኛው እህት ማህበራት ዓላማውና ግቡ አንድ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሲተገብሩም ተስተውሏል፡፡ ለዚህም ባለፈው ጃዋሪ 2013 ከሰሜን አሜሪካ፤ ከአውሮፓ የተውጣጡ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በመሰባሰብ በአዲስ አበባ

ስታዲየም አንድ የእግር ኳስ ውድድር በማድረግ ከዛም በተረፈ ከ150 በላይ የሚደርሱ ለድሮ ጫዋች የራት ግብዣ በማድረግ የተጎዱ የተቸገሩ የታመሙ ተጫዋቾችን በአካል በማግኘት ምንግዜም እነዚህ ማህበሮች ከጎናቸው እንደሆኑ አረጋግጠንላቸዋል፡፡ በተረፈም የሁለቱን ማህበር ዓላማ ለኢትዮጵያ ስፖርት አፍቃሪና ህዝብ አስተዋውቀን ተመልሰናል ይህ ደግሞ ለተነሳንለት ዓላማና በጎ ተግባር የሚያበረታታና እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንደሚባለው በተለይም የአውሮፓ እኛን መሰል ማህበር እየሰሩና እየበረቱበት ያለው መልካም ጥረታቸው ይሁንታን ያገኘ አስደሳችና ከምንም በላይ አመርቂ ስራ ነው ብለን ስላመንን በአክብሮት ሳናመሰግናቸው አናልፍም፡፡ ይህንን መልካም ስራቸውንና ጥረታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በ2013 ከላይ እንደገለጽነው በኢትዮጵያ ላይ በተደረገው መልካም መገናኘት አጋጣሚን ተጠቅመን የወደፊት ትብብርና አብሮ መስራትን እቅዶችን የስራ ተግባራትን መረዳዳትንና ተቻችሎ

በመቆም የተነሳንለትን ዓላማ ከታሰበው የመጨረሻ ታርጌታችን ለማድረግ በአሜሪካካ በአውሮፓ፤ በኢትዮጵያ ባሉት እህት ማህበራት መካከል ህጋዊነት የተላበሰ ውል ከመፈራረማችን በተጨማሪ ለማንኛውም የስራ እንቅስቃ ለወደፊቱም አብሮ ለመስራት በመተማመንና በመግባባት አመርቂና አስደሳች ስምምነቶች ላይ መደረሱ እሙን ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ በዚህ በሰሜን አሜሪካም ሆነ በቀሪው አለም ከዚህ በበለጠ ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎች እንዳሉበት ስለሚያምን ከዚህም በላይ ለመራመድ የአባላቶችንም ሆነ የደጋፊዎችን የማያቋርጥ ድጋፍና ብርታት ይጠይቃልና በNAESPASA አባላትና በስራ አመራር ኮሚቴው ስም ሁሉም ድጋፋችሁን እንድትሰጡን እንጠይቃለን፡፡ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር 2016


19 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የኢትዮጵያው ማህበር ሊቀመንበር የአቶ ንጉሴ ገብሬ መልዕክት፤ በሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የቀድሞ ተጫዋቾችን በችግራቸው ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ማህበር ከመሆኑም በላይ ከዚህ ቀደም ተቸግረውና ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ከ30 ሰዎች የማያንሱ ወንድምና እህቶቻችንን በመርዳት በሃገር ውስጥ በመልካም ስነ ምግባር እንዲጠሩ አድርጓቸዋል፡፡ በመሆኑም በአዲስ አበባ ውስጥ ሊያግዛቸው የሚችል አጋር ማህበር በመስራትና ረዥም የሆነ እቅድ በመንደፍ ለመስራት እንዲያመች ከ60 በላይ የቀድሞ ተጫዋቾች የተካተቱበት በአባላቱን በመያዝ ወደ ሃገር ቤት በመምጣት የእግር ኳስ ውድድር በማድረግ በህይወት የሌሉትን በማሰብ በህይወት ኖረው ምንም ገቢ የሌላቸውን ለመርዳት ያደረጉት ዝግጅት መላውን የኢትዮጵያን ስፖርት ወዳድ ያስደስት ነበር፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ዕውቅና በማግኘት የተሻለ ስራ ለመስራት ጥረቱ የቀጠለ በመሆኑ ምንም እንኳን በሰው ሀገር ለፍታችሁ ደከማችሁ ይህንን የመሰለ በጎ ተግባር በመፈጸም ወገኖቻችሁን ለማገዝ ያደረጋችሁትን ጥረት ብናደንቅም በጋራ የምንሰራው የሚቀረን ብዙ ስራ ስለሚኖር ምን ግዜም አብረናችሁ እንደሆንን በኔና በተቀሩት የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ስም እየገለጽኩ ፈጣሪ ያሰባችሁትን ሁሉ እንዲያሳካ ከልብ እየተመኘሁ መልክቴን አጠቃልላለሁ፡፡

የወ/ት ብዙአየሁ ጀምቡሩ ምስክርነት

ህይወት ሁሌ እኛ እንዳሰብናት አትሆንም በብዙ ነገር ልንፈተን እንችላለን እንደ እኔ ግን የተፈተነ ያለ አይመስለኝም፡፡ በጤና፤ በቤተሰብ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ ሆኜ እንኳን ተስፋን እጠብቅ ነበር፡፡ እግር ኳስ ለእኔ እስትንፋሴ ነበር ሁሉ ነገሬ እያንዳንዱን ችግሬን ርሀቤን ደስታዬን የማጣጥመው በመጫወት ነው፡፡ ቁርስ በልቼ ምሳ ሳልበላ ከበሉት በላይ ኳስን እጫወታለሁ ህልሜ እሩቅ ነበር፡፡ በልጅነቴ ገና 17 ዓመት እንኳን በቅጡ ሳይሞላኝ ለብሔራዊ ቡድን የተመረጥኩት እግር ኳስን

በመዝናናት የምጫወት የት ትደርሳለች ተብዬ የምጠበቅ ተጨዋች ነበርኩ ግን ምን ያደርጋል ጉዳት ለዚህ ነው መግቢያዬ ላይ ሰው እንዳሰበው አይሆንም ያልኩት፡፡ በህይወቴ በጣም ያዘንኩት እናቴን በለጋ እድሜ ያውም 11 ዓመቴ ያጣኃት ቀንና የተጎዳሁበትን ቀን አምርሬ እጠላዋለሁ ለሰባት ዓመት የሚያሳክመኝ አጥቼ በጉዳት እሰቃይ ነበር፡፡ እንደዚህም ሆኜ ተስፋ አልቆረጥኩም እምነቴ ትልቅ ነውና አንድ ቀን እግዚአብሔር ሁሉን ያስተካክለዋል እያልኩ እጠብቅ ነበር በየሰው እቤት እየተንከራተትኩ የሰው ፊት እየገረፈኝ ትምህርቴን እማራለሁ ከነጉዳቴ ከአቅሜ በላይ እየሰራ ሀዘኔን የሚጋራኝ እህት ወንድም ሳይኖረኝ በተስፋ እምነት ብቻ መጠበቅ፤


20 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ይህ ሁሉ መስዋትነት የከፈልኩበት ህይወቴ በፋርማሲ ትምህርት በዲፕሎማ ተመረኩ በቃ እራሴን ቻልኩ ስል እግሬን አቃተኝ የቤት እስረኛ ሆንሉ በየመንገዱ ይጥለኛል ሰው እየከበበኝ እያለቀስኩ ከንፈሩን ሲመጥልኝ አቤት ሞራሌ እንክት እንደሚል በዚህ የተነሳ ለብዙ ጊዜ ከእቤት አልወጣም እስቲ አስቡት እያንዳንዳችሁ በኔ ቦታ ለአንድ ደቂቃ እኔ ውስጥ ሁኑ ምን ያህል ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንዳለሁ ግን ይህን ሁሉ የሚመለከትልኝ አምላክ አለኝ፡፡ በቃሽ የሚለኝ የሚያጽናናኝ ጽናትን የሚያጎናጽፈኝ እስካሁንም ያኖረኝ እሱ ተስፋ ማድረጌ ነው አለበለዚያማ እናንተም ዛሬ አታገኙኝም ነበር፡፡ ተስፋ ቆርጬ በሱስ ተዘፍቄ ወይም ከማንም ልጅ ወልጄ ከንቱ ነበር የምባለው፡፡ እውነታው የኢትዮ አሜሪካ እግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ግን በአምላኬ የጠበኳችሁ ተስፋዎቼ እናንተ ሆናችሁኝ አንድ ቀን እግዚአብሔር ሁሉን ያስተካክልልኛል ብዬ በእምነት ተስፋ የሰነቁኩት እናንተ ነው በጋዜጣ ላይ ወጥቼ ዳዊት ጌታቸው ለኔ አባቴም ጭምር ነው አንብቦ ትራንስፖርት ልኮልኝ ከእናንተ ያገናኘን ባለውለታዬ ነው በጣምም አመሰግናሁ፡፡

እውነት እላችኋለሁ እስከዛሬ ካሳከማችኋቸው ውስጥ በስኬት እንደ እኔ የደረሳችሁለት ሰው የለም እኔን ያዳናችሁት እግሬን ብቻ አይደለም ምንነቴን ጭምር ነው፡፡ እራእዬን ከንቱ እንዳይሆን የታደጋችሁኝ እኔ ውስጥ ብዙ ታሪኮች አሉ አንድ ቀን ስኬታማ ስሆን የምተነፍሰው ለዚህም ነው ዛሬ ድኜ ታዳጊ ሴቶችን ሰብስቤ የማሰለጥነው እየሰራሁ የማሰራው እኔ ለእነሱ አሰልጣኛቸው ብቻ ሳልሆን ትምህርት ቤታቸውም ጭምር ነኝ እንዳይሰናከሉ አላማ እንዲኖራቸው እራሳቸውን እንዴት እንደሚጠብቁ የኔን ተሞክሮ አስተምራለሁ፡፡ ስለዚህ የማሰለጥነው ኳስን ብቻ አይደለም፡፡

ከእኔ ጀርባ የዚህ ሁሉ ውጤት እናንተ ናችሁ በኔ ስኬት ሁሉ የምትጠሩ ለዚህም ነው በየሄድኩበት ሁሉ የማመሰግናችሁ ለቀጣይ ስረችሁ ጥንካሬ የምሆናችሁ በመልካምነታችሁ ውስጥ ስንቅ የሆንኳችሁ እኔ ነኝ የእናንተ ምስክር ለሌላው የበለጠ እንድትደርሱ ሀይል የምሆናችሁ በሚያጋጥማችሁ ችግር ሁሉ በአንድነታችሁ እንድታሸንፉ የማደርጋችሁ፡፡ ምክንያቱም በመስጠት ጽድቅና ሳይኖር ይችላል ነገር ግን በፊት በሀዘን የተከራመተው ፊቴ ዛሬ በደስታ ከራሴም አልፌ ለሌሎች መድረሴ ያ ነው ለእናንተ የመንፈስ እርካታ በሰዎች ደስታ መደሰት በህይወቴ ያጋጠመኝ አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ ትምህርቴን የተማርኩት ክረምት ላይ በሚዘጋጅ ውድድር ላይ ኮከብ ተጨዋች ተብዬ በማገኘው ሁለት ደርዘን ደብተር ሽልማት ነበር ያውም ከወንድ ጋር እየተጫወትኩ አንዱን አመት ተጎዳሁና ሰባተኛ ክፍል ነበርኩ አምርሬ አለቀስኩ ማንም አይገዛልኝም ትምህርቴን ላቋርጥ ነው ብዬ አንድ ስጫወት የሚያደንቀኝ ተመልካች ነበር ተመልከቱ የእግዚአብሔር ስራ ሲያጣኝ ጊዜ ይጠይቅና መጎዳቴን ነገሩት ደብተርና ዩኒፎርም ይዞልኝ መጣ በጣም አለቀስኩ ካደረገልኝ ይልቅ የተናገረው እስካሁን አይምሮዬ ውስጥ አለ እኔ ላንቺ ባደረኩት ገንዘብ ምናልባት ያማረኝን ልብስም ይሁን ሌላም ነገር ላደርግበት እችል ይሆናል ነገር ግን የምደሰተው ለአንዴ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ላንቺ ሳደርግ ሁለቴ ተደሰትኩ አንዱ አንቺ ፊት ላይ በማየው ደስታ አንዱ ደግሞ ይህን በማድረጌ፡፡ ስለዚህ ደስታን ለማግኘት ለአብላጫው ማደላት ነው ብሎ አስተማረኝ፡፡ ዛሬ ደስተኛ ነኝ በምወደው ሙያ ባይከፈለኝ እንኳን 30 ልጆች አሰለጥናለሁ ደስ ብሎኝ እሰራለሁ ወደፊት ትልቅ ቦታ መድረስ የሚችሉ ናቸውና፡፡ ስለዚህ ዛሬ እናንተን የማመሰግንበት ቃላቶች አይገልጹልኝም ባይሆን ጠንክሬ ሰርቼ ትልቅ ቦታ ደርሼ በስኬቴ ያደረጋችሁልኝን ነገር ከንቱ እንዳልነበር ከእመቤቴ ድጋፍ ጋር አሳካዋለሁ ሁላችሁም ባላችሁበት ከነቤተሰባችሁ እግዚአብሔር ፍቅር፤ ጤና፤ ሰላምን አብዝቶ ይስጣችሁ በጣም እጅግ በጣም በእግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ!!! ብዙአየሁ ጀምቡሩ


21 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የፋሲል አድማሱ ምስክርነት

ፋሲል አድማሱ ከእናቱ ወ/ሮ ዘገኑወርቅ ፈይሳ ከአባቱ ከአድማሱ ደገፋ በ1972 ተወለደ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮከበ ጽባህ ሁለተኛ ደረጃን በምስራቅ አጠቃላይ ት/ቤቱ ተከታትሏል፡፡

የእግር ኳስ ፍቅሩ እየጠነከረ በመምጣቱ በቀበሌ ቡድን ውስጥ ጀምሮ በከፍተኛ ምርጥ ከዛም ለአውራጃ

ተጫውቷል፡፡ አቶ ጥላሁን የሚባሉ በቀበሌያችን የሚኖሩ የኳስ ችሎታዬን በማየት ለሚሰሩበት መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ውስጥ ወስደው ለሲ ቡድን አስገቡት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአንድ ዓመት ከተጫወተ በኋላ ወደ ፔፕሲ ኮላ ክብ አመራ በእዚህን ክለብ ውስጥ ለአንድ ዓመት ተጫውቶ ወደ አንጋፋው ክለብ መብራት ሃይል (ኤሌክትሪክ) ክለብ ገባ፡፡ ለመብራት ሀይል ክለብ ለሰባት ዓመት ተጫውቷል፡፡ በዚህም ክለብ ውስጥ አያለ ለአዲስ አበባ ምርጥ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እየተጫወተ ሳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ቡድን ጋር ሞሮኮ ላይ ለማድረግ በተጓዙበት ግዜ ጣሊያን ሀገር ላይ ትራንዚት ሲያደርጉ ፋሲል ከቡድኑ በመለየት ጣሊያን አገር ቀረ፡፡

ለረጅም ዓመት ያለ መኖሪያ ፍቃድ በጣሊያን ሀገር ሲኖር ከቆየ በኋላ በጣሊያን ሀገር መኖሪያ ፍቃድ ማግኘት

አልቻለም ስራም መስራት ስለማይችል በችግር ላይ ለብዙ ጊዜ በመቆየቱ NASPASA የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ይህንን ልጅ ከችግር የሚወጣበትን መንገድ ከአውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋች ማህበር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ በማድረግ ወደ ኖርዌይ እንዲገባ አድርጓል፡፡ ፋሲል በአሁኑ ጊዜ በኖርዌይ ሰላማዊ ህይወት እየኖረ ይገኛል፡፡


22 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የጥንቱ ትዝ አለኝ - ከፍቅሩ ኪዳኔ የስምንት ዓመት ልጅ ሆኜ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ጃንሜዳ ሄጄ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን

ሲጫወት ያየሁት፡፡ አሁን እንኳ ስምንቱ ላይ ዜሮ መጨመር ትችላላች አበቴ ኪዳኔ ገብሬ ጣሊያን አገራችንን ለቆ ከወጣ በኋላ በኢትዮጵያ ሻምፒዮን የሚካፈሉት አምስት ቡድኖች ብቻ ነበሩ፡፡ እነርሱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ማለትም ሳንጆርጅ (ኢትዮጵያ) ጁቬንቱስ (ጣሊያን) ኦሊምፒያኮስ( ግሪክ) አራራት(አርመን) እና (እንግሊዝ) የሳንጆርጅ ተጨዋቾች አብዛኞቹ ተማሪዎች ስለነበሩ መኪና ያላቸው ደጋፊዎች ከየተማሪ ቤቱ ወደ ኳስ ሜዳ አምጥተው ይመልሱ ነበር፡፡ የኔም አባት አንዱ አመላላሽ ስለነበረ አብሬው በመሄድ ስፖርት ዓለም ውስጥ ጥልቅ አልኩ፡፡ እኔ ያደኩት ጉለሌ ዘመናዊ ስልጣኔ ያረፈበት ሰፈር ውስጥ ነው፡፡ ዋና ሞልክቱ ጣሊያኖች የሰሩት የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ሐኪም ቦራ ይባል የነበረው ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ሊፍት ያለበት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በሊፍት የተጠቀምን የጉለሌ ልጆች ነን፡፡ ዓጼ ምኒሊክ መናገሻ ከተማቸውን ወደ አዲስ ዓለም ያዛውራሉ ተብሎ ስለታቀደ በመጀመሪያ አስፋልት መንገድ የተሰራው ከፒያሳ አንስቶ ጉለሌን የሚያቋርጠው ነው፡፡ ጣሊያኖች ሊሰሩት ጀምረው የነበረው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልጆች የሆነንን ኳስ መጫዎቻችን ነበር፡፡ የጨርቅ ኳስ ማለቴ ነው፡፡ ከፊት ለፊቱ የግሪክ ኦሎምፒያ ኮስ ክለብ ነበር፡፡ ጠባቂው የዝነኛው አርቲስት የመሃመድ አህመድ አባት ነበሩ፡፡ ሌላው መጫወቻ ሜዳችን የሳንጆርጅ ተጨዋች የነበረው የዶክተር ያየህራድ ቅጣው አባት ቤት ደጀፍ ላይ ነበር ጉለሌ ተማሪ ያቀፈች ሰፈር ነበረች፡፡ የስዊድሽ ሚሽን ቄስ ትምህርት ቤት ያለ ዲፕሎም ተመርቄ ዳዊት ደግሜ ናኩተከ የእናትህ ሽሮ ተንከተከተ በማለት ቀልጄ በመጀመሪያ የተመዘገብኩበት ሲሆን የአርበኞች መምህራችን ማሰልጠኛ የአባዲና ፖሊስ አካዴሚ የኢንስቲቱት ፖስተር ላቦራቶሪ የመድሃኔዓለም (የጀኔራል ዊንጌት) ላዛሪት ሚሲዎን ትምህርት ቤቶች የነበሩበት ሰፈር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በታሪካችን ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በክረምት ወራት የህዝብ ቆጠራ ሲያካሂድ በወር አምስት ብር ተቀጥሬ ሰርቻለሁ፡፡ መሃለቅዋም ያለቀችው በሻይና በፓስቲ ነው፡፡ ዝነኛው የሸሪፍ ፓስቲ ቤት እና የግሪኩ ከረላምቦ ዳቦ ሱቅ እንዲሁም የእማረጠጅ ቤት እኛው ሰፈር ነበር፡፡ ስምም እስካሁን ደስ የሚለኝ አትለፋ ጎብኙን የምትባለው ሰባራ ዛፍ አጠገብ የነበረችው ቡና ቤት ነች፤ የእንጨት ፋብሪካ ባለቤት አቶ ተክለማቲያስ ካሳሁን የሽቶ ፋብሪካ ባለቤት አቶ ሁነኛው መራ የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤት አቶ ማሞ ካቻ የሰፈራችን ነዋሪዎች ነበሩ፡፡ የጠላት ንብረት የነበረ አንድ ሰሞን አባቴ ያስረዳደረው የወተትና የበረዶ ፋብሪካዎችም ጉለሌ ነበረ፡፡ ይልቁንም ዓለማየሁ እሸቴ እና መሐመድ አሕሙድ ጠለላ ከበደ ስመ ገናና ዘፋኞች ይሆናሉ ብሎ ስፈራችን ውስጥ የጠረጠረ የለም፡፡ ልጆች ሆነን የምንጫወታቸው ጨዋታዎች በየአይነቱ ነበረ፡፡ ጢብ ጢብ ማለትም ቅጠል በውሃ አርሶ ባንድ እግር ቆሞ በመምታት ቅጠልዋ ሳትወድቅ ብዙ ማስቆጠ ከኛ ተምረው ይሆናል፡፡ የዘመኑ ኳስ ተጨዋቾች በኳስዋ ጢብ ጢብ የሚፎካከሩት፤


23 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በኛ ዘመን የጣሊያን ሊሬ ወይም ቦልደ እና የምስራቅ አፍሪካ ቀዳዳ ቫሊን በብዛት ይገኝ ስለነበር ትንሽ ጉድጓድ ቆፍሮ በየተራ እየወረወሩ በማስገባት ወይም ባለጋራ የመረጠውን አነጣጥሮ በመምታት የሚከናወን የቁማር ጨዋታ ነበላስ ቬጋስ እንኳን አልገባም፡፡ ፍሉስ የሌለው ደግሞ ቆርኪ ሰብስቦ በመጠፍጠፍ ይጫወታል፡፡ በክረምት ጭቃ አቡክቶ ኮሮኮንች መንገድ ላይ ማፈንዳት የተለመደ ነው፡፡ ክሪኬት ወይም የአሜሪካ ቤዝቦል የሚመስለው ጨዋታ ደግሞ የጨርቅ ኳስ በዱላ ሳይሆን በበሬ ሰፊ አጥንት መትቶ እስክትቀለብ ድረስ በአራት ማዕዘን ምልክት በተደረገባቸው ስፍራዎች ላይ እያቆሙ ወይም ባንዴ መሮጥ ነው፡፡ የክር መጠቅለይ እንጨቱን ለሁለት ከርክሮ ወደታች ወደላይ በሚሳበው ‹‹ዬዬ›› በሚባለው መጫወት ወይም ከተቃጠለ ጎማ ውስጥ በሚወጣው ድቡልቡል ሽቦ ባንድ መግፊያ በመጠቀም ማሽከርከር ወይም እንቆቅልሽ፤ ቁጭ ቁጭ፤ ድብብቆሽ፤ መጫወት ነው፡፡ እኔን አሁን የሚያሳዝነኝ አንድ ላስቲክ ሁለት ጫፍ ያለው ባለ እንጨት ላይ አስሮ የድንጋይ ጠጠር በመወርወር የፈጀናቸው

ወፎች ናቸው፡፡ በዓመት በዓል ወቅት ለቡሄ ራሳችን ጅራፍ እየሰራን ማጮህ ለገና እንደ ሆኬ ዓይነት ያገራችንን ገና ጨዋታ ወይም ለጥምቀት ፈረስ ስለሌለን በእግር እየሮጡ ዘንግ በመወርወር ጉልፍ መጫወት እንችል ነበር፡፡ ውሃ ዋና እንኳን የተማርኩት ጉለሌ ወንዝ ውስጥ ነው፡፡ አብሮኝ ይዋኝ የነበረው ጎረቤቴ በዓል ግርማ ነበር፡፡ ሰውነታችንን በሙቅ ውሃ ለመጀመሪያ ግዜ የታጠብነው የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀልን ፕሮግራም መሰረት እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተማሪ ቤት ተራ በተራ ፍልውሃ ሄዶ መታጠብ የተጀመረ ግዜ ነው፡፡ አለበለዚያ እግርህን ታጠብ ነበር ትዕዛዝ ከዚህም በቀር ቅጫምና ቅማል ልጆቹን ስለሚጠቃ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ በየ ተማሪ ቤታችን እየዞረ ጭንቅላታችን ላይ ዲዲ ይነፉ ነበር፡፡ ዓይናችንንም በየጊዜው እንመረምር ነበር፡፡ ተማሪዎች ሆነን በጣም የሚያስደስተን ለገና በዓል ቤተ መንግስት ሄደን ከጃን ሆይ እና ንጉሳዊ ቤተሰብ እጅ ሹራብን ብስኩት

መሸለሙ ነው፡፡ ለጥምቀት በዓል ጃንሜዳ የዮሐንስ ታቦትን ተከትለን ሄዶ ብርድ ሲነጨን ማደሩም ደስ ይል ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በኋላ ሰዓት ዕላፊ ነበር፡፡ በፖሊስ ብትያዝ ትታሰራለህ ማለት ነው፡፡ የሚገርመው ግን በረመዳን ግዜ እስላሞች እንደፈለጋቸው ይዘዋወራሉ፡፡ ክርስቲያኑ ግን አይችልም፡፡ ስለዚህ ከውቤ በረሃ አምሽተን ስንወጣ የእስላሞች ቆብ እናደርጋለን ወይም ስማችንን ቀይረን አሊባባ በመባል እናመልጥ ነበር፡፡ የትም ተወለድ እድግ አራዳ የተባለው ለዚያ ነው፡፡ አገራችን ከጠላት ወረራ በኋላ የህዝብዋን ደህንነት ለማሻሻል በምታደርገው ጥረት ሁሉም ተካፋይ ነበር፡፡ ጋሼ ይድነቃቸው ፉትቦል በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ በጣም ይታገል ነበር፡፡ እራሱ የሳንጆርጅ ተጨዋች የብሔራዊው ቡድን ተጨዋችና አሰልጣኝ የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ነበር፡፡ በዚህ ላይ የእግር ኳስ ህጎችን ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንቦች ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ በመተርጎምና አዳዲስ ቃላቶች በመፍጠር እና እንዲሁም ሁላችንንም በማስተማር ያልተወጣው ግዳጅ የለም፡፡ እኔም ሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ስፖርት ተምሬ አስተማሪ ሆንኩ በአዲስ አበባ የምናዘጋጀው የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ የአትሌቲክስ

የቅርጫት ኳስ ውድድሮች በጣም አስደናቂ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በአትሌቲክስ የሚወዳደሩት ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶቹም ጭምር ነው፡፡ ውድድሩም እንደ ዓለም ሻምፒዮና ከመቶ ሜተር ሩጫ ዝላይና ውርወራን ያካተተና ጃንሆይና እቴጌ በተገኙበት የሚካሄድ ነበር፡፡ ተወዳዳሪዎቹን ከየትምህርት ቤቱ ሰብስቦ የሚያመላልሰው የክብር ዘበኛ ማክ መኪናዎች ነበሩ፡፡ ያኔ የነበሩት የአጭር ርዝመት ሩጮች አሁን ቢኖሩ ጉድ ይፈሉ ነበር፡፡ ቁመታቸውና ሰውነታቸው የሰጠ ነበረ፡፡ መድሃኔ ዓለም እና ተፈሪ መኮንን፤ ኮተቤ፤ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ፤ ተግባረ ዕድ፤ ሊሴ ገብረማሪያም፤ ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤቶች ብዙ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና አትሌቶች ለኢትዮጵያ ክለቦች አበርክተዋል፡፡


24 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

እኔም ጋሼ ይድነቃቸው የሚያስመጣቸው የፈረንሳይና የጣሊያን ጋዜጦች በማንበብ ዝንባሌዬ ወደ ገፋፋኝ በዜና ማሰራጨት መስክ በጋዜጠኝነት ሙያ ለማገልገል ታጥቄ ተነሳሁ፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ጋዜጣ በአማርኛና በፈረንሳይኛ ነበር የሚታተመው፡፡ የአማርኛ ክፍል ዋና አዘጋጅ የሆኑትን አቶ አሀዱ ሳቡሬ እንዲሁም የፈረንሳይኛውን ክፍል አዘጋጅ ወሊድ ቨንጎልድ ዱፕሬንና የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያን ዲሬክተር አቶ ታደሰ አበባን አነጋግሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው ቋሚ የስፖርት ጋዜጠኛ ሆኜ በኢትዮጵያ ንጉሱ ነገስት መንግስት የጋዜጣና ማስታወቂያ መስሪያ ቤት ተቀጠርኩ፡፡ አቶ አሃዱ ሳቡሬ ለስፖርት እድገት የሚጥሩ ስለነበሩ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተውኝ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ አንድ ሙሉ የስፖርት ገጽ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጰያ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ የስፖርት ፕሮግራም ጀመረ፡፡ ዓ.ምቱ 1950 እስከ 1957 ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ግጥሚያ እ.ኤ.ኡ. 1957 የመጣ ግዜ አንድ የሱዳን ራዲዮ ጣቢያ

ጨዋታው በቀጥታ ለማስተላለፍ አብሮ መጥቶ ነበር፡፡ ጋዜጠኛው ከስታዲየም መስመር እንዲዘረጋለት ፌዴሬሽኑ ጠየቀ ጉዳዩ ተሰምቶ የማይታወቅ ስለሆነ የራዲዮ ጣቢያው ዲሬክተር ጉዳዩን ለበላይ ባለስልጣን ለአቶ ዓምደሚካኤል ደሳለኝ አቀረቡ፤ እርሳቸውም እንዲዘረጋ ፈቀዱ፡፡ በዚያውም ለምን በአማርኛ አይተላለፍም ብለው ጠየቁ፤ አቶ አምደሚካኤል ደሳለኝ በጣሊያን ግዜ ሰለ እግር ኳስ ጨዋታ ይጹፉ የነበሩ ከዚያም እ.ኤ.አ. በ1948 ግርማዊነታቸው የመጀመሪያውን የስፖርት ኮንፌዴሬሽን ሲያቋቁሙ ጀኔራል አብይ አበበ ፕሬዚዳንት፤ አቶ ዓምደሚካኤል ዋና ጸሐፊ ሆነው ተሹመው ነበር፡፡ ስለዚህ የስፖርት ዕውቀታቸው ለኔ ትልቅ መሳሪያ ሆኖኝ ነበር፡፡ የኔ አለቃ በራዲዮ የማስተላለፍ የለም ሲሉ ይድነቃቸው ጠይቁ ተባሉ፡፡ አቶ ይድነቃቸውም የሚያስተላለፍ ሰው አለን ብሎ ስለመለሰ መስመሩ ተዘረጋ፡፡ አለቃዬ እኔን ጠርተውኝ እንደልማድህ ፕሮግራምህ አዘጋጅ ተብዬ እሁድ እለት ወደ

ስታዲየም አመራው፡፡ ትሪቡኑ ላይ ቁጭ ብዬ ወሬዬን እየደለቅሁ መሃል ሜዳው አጠገብ ትናንሽ ሁለት ጠረጴዛዎች ከመናገሪያው መሳሪያ ጋር ተዘጋጅቶ አየሁ፡፡ የሱዳኑ ጋዜጠኛ ከካርቱም ጋር መስመሩ ይሰራ እንደሆነ ሲሞክር የአማርኛው ተናጋሪ አይታይም ጨዋታው ሊጀመር አስር ደቂቃ ሲቀረው በስታዲየም ድምፅ ማጉያ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ባስቸኳይ ይፈለጋሉ የሚል መልዕክት ተላለፈ እኔም ምን መጣ ብዬ ቦታዬን ያዙልኝ ብዬ ወረድኩ ጋሼ ይድነቃቸው ሲያዩኝ ጮኸብኝ የት ነው የጠፋኸው አንተ እኮ ነህ የምታስተላልፈው አለኝ፡፡ እኔ የነገረኝ ሰው የለም ብዬ ብከራከር በል የቡድኖቹ አሰላለፍ ይኸውልህ ብሎኝ ሄደና መስመርህን ሞክር ብሎኝ ተለያየን፡፡ እኔም የመጣው ይምጣ ብዬ ሄጄ ባገራችን ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ ከአዲስ አበባ ስታዲየም በቀጥታ አንድ ኢንተርናሽናል ግጥሚያ አስተላለፍኩ፡፡ ዱሮ ድሬድዋ አሊያንስ ፍራንሴዝ ሳተምር በጅቡቲ ራዲዮ ጣቢያ የፈረንሳይ እግር ኳስ ሻምፒዮና ሲተላለፍ እስማበት ነበር፡፡ ምን መደረግ እንዳለበት አውቅ ነበር፡፡ በዚህ ላይ የፒያሳ ልጅ መሆኔ መረሳት የለበትም፡፡ ስታዲየም ውስጥ የሰማ ሰው ስላልነበረ፡፡ ውጤቱን ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ በዚያን ዘመን

ትራንዚስተ ራዲዮ እስከዚህም አልነበረም፡፡ ከስታዲየም ወጥቼ በሴይቼንቶ ፒያሳ ሄጄ ከዚያም ውቤ በረሃ ገብቼ ሳካልል አድናቆታቸውን በግብዣ የሚገልጹ፤ ስለበዙ ውጤቱ ደህና መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ለመሆኑ እንዴት ባንዳፍታ የተጨዋቾቹን ስም በተለይ የሱዳኖቹን ለማወቅ ቻልክ ወይ ጉድ ይገርማል በማለት ጭምር ልክ እንደ ሜሎቲ ይወርድ ነበር፡፡ ሰዓት እላፊ ባይኖር ኖሮ በጥያቄና መልስ እዚያው አድር ነበር፡፡ ጧት ቢሮ ስገባም ብራቮ የሚል አልጠፋም አለቃዬም ቢሮአቸው አስጠርተው እንዲህ ጥይት መሆንክን አላውቅም ነበር በማለት አመሰገኑኝ ቀጥለውም ካሁን ወዲያ ምርጥ ግጥሚያ እንድታስተላልፍ ተፈቅዶልሃል ተባልኩ እኔም ስታዲየሙ ያተቀረሰፅውን ቀጥታ ደጋግሜ ሰምቼ ለማሻሻል ቻልኩ፡፡ የራዲዮ ጣቢያ ፕሮግራሜን የምከፍተው ስኮኪያን በሚል በጣም በምወደው ዘፈን ነበር፡፡ እኔ የሰማሁት አሜሪካኖች ሲዘፍኑት ነው፡፡


25 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ከ37 ዓመት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ አፍሪካን “ዛዝ” የተባለ የጥቁሮች ኦርኬስትራ በትግላቸው ዘመን የቀረጹት መሆኑን አወኩ፡፡ እ.ኤ.አ. በ1960 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ልኮ ከዘጠኝ ዓመት ጦርዋን ኮሪያ ያዘመተችው ኢትዮጵያ እንደገና ወደ ኮንጎ እንድትልክ ተጠየቀች በማስታወቂያ መስሪያ ቤት ያለ ሹሞቹ በቀር ፈረንሳይ የሚያውቅ እኔ ብቻ ስለነበርኩ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ ረዳትና የኢትዮጵያ ጋዜጦች ወኪል እንዲሁም አስተርጓሚ ሆኜ እንዳገለግል ጃንሜዳ የክብር ዘበኛ ካምፕ ሰልፍና ተኩስ ተምሬ ወደ ኮንጎ ዘመትኩ ከኔ ጋር የነበሩ ጋዜጠኞች የሊሴ ገብረማርያም ባልንጀራ ዘውዴ ረታ እና መስፍን ብርሃነ ለትምህርት ፈረንሳይ አገር ሄደው ነበር፡፡ በመጀመሪያ ዕጩ መኮንን ከዚያ መቶ አለቃ ሆኜ አንድ ዓመት ተኩል ካገለገልኩ በኋላ ኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት ቀጥሮኝ ከኢትዮጵያ መንግስት ማስታወቂያ መስሪያ ቤት ተሰናበትን ኮንጎ በነበርኩበት ወቅት አለቆቼ ጀኔራል ኢያሱ መንገሻ ጀኔራል ወልደዮሐንስ ሽታ፤ ጀኔራል ተሾመ እርገቱ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ጽህፈት ቤት ወደ ነበረው ስታንሌይቪል አሁን ኪሳንጋኒ ወደሚባለው ከተማ ሲመጡ

የተጠቀሙበት ዲሲን አውሮፕላን ኢትዮጵያ አየር ሃይል ለተባበሩት መንግስታት ያዋሰው ነበር፡፡ ሉሙምባ ካረፉ በኋላ አብራሪዎቹን እንዳመሰግናቸው ጥሩልኝ ሲሉ ሄጄ ጠራኋቸው፡፡ ፓይለቱ መቶ አለቃ ፋንታ በላይ ደርግ በግፍ የገደለው ጀኔራል መድሃኒ ዓለም ት/ቤት ሆኖ ነበር የምንተዋወቀው፡፡ ሉሙምባ በኢትዮጵያ ፓይለቶች ትልቁ ኩራት እንደተስማቸው ገልጸው ማታ ራት ይዘኸቸው እንድትመጣ ብለውኝ ተለያየን፡፡ ሉሙምባ በግፍ የተገደሉበት ግዜ ሁኔታውን እንዲያጣራ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ዳግ መርሽልጅ የሾመው ጄኔራል ኢያሱ መንገሻን ነበር፡፡ እኔም ከእርሳቸው ጋር ወደ ኤልዛቤት ቪል አሁን ሉሙምባሺ ካታንጋ ሄጄ ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ የተባበሩት መንግስታት ቀጥሮ የላከኝ ወደ ኮንጎ ስለሆነ የመጨረሻውን ሁለት ዓመት ያሳለፍኩት ኤልዛቤትሹል ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኬኔዲ ማረፋቸውን የሰማሁት እዚያው ሆኜ ነው፡፡ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በነበርኩበት ወቅት ሁሉም ጋዜጦች የስፖርት ገፀ

እንዲኖራቸው ባደረኩት ጥረት መሰረት ሁሉም ላይ እኔው ራሴ እጽፍ ነበር፡፡ እኔ ከተሰናበትኩ በኋላ ሰለሞን ተሰማ እና ነጋ ወልደስላሴ ተክተውኝ ስፖርት ስፍራው እንደያዘ ቀጠለ፡፡ ሰለሞን ተሰማ የስፖት ጋዜጣ ያቋቋመ በጣም ጎበዝ ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ተዛውሮ ሲመጣ አገልግሎቴን ያበረከትኩት ለስፖርት መምሪያዎቹ ነበር፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፤ ብስክሌት ፌዴሬሽን፤ የቴኒስ ፌዴሬሽን፤ የሸዋ እግር ኳስ ሊግ ዋና ጸሐፊ የፊትቦል ፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መስራችና ፕሬዘዳንት ነበርኩ፡፡ ከዚህም በላይ እ.ኤ.አ. በ1968 እና በ1976 በኢትዮጵያ የተካሄደው የአፍሪቃ ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ነበርኩ፤ የደርግ ነፍስ ገዳዮች አገራችንን ሲያተራምሱ ወጣቶቹንና ተማሪዎችን ሲፈጁ ባለስልጣኖቹን ሰብስበው ሲረሽኑ ከሰይጣን ጋር መኖር እንደማልችል በመገንዘብ አገሬን ጥዬ ወጣሁ፡፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሰናብቼ ነጻ ጋዜጠኛ (ፍሬላንስ) ሆኜ እሰራ ነበር፡፡ የዛሬ አርባ ዓመት የአስራ ሁለት ዓመት ልጄን ይዤ ፓሪስ ገባሁ፡፡ የፖለቲካ ጥገኝነት ተፈቀደልኝ ልጄንም አዳሪ ተማሪ አስገብቼ በፈረንሳይ የዕለት ስፖርት ጋዜጠኛ

በየሳምንቱ የሚወጣ ፍራንስ ፉትቦል ጋዜጣ መስራት ጀመርኩ፡፡ የሚከፈለኝ በጻፍኩት ዜና ልክ ስሆነ አዳሪ ት/ቤቶችና ለኔ ሆቴል መክፈል አስቸጋሪ ነበር፡፡ ምግዜም በዳቦና በሰርዲን የተወሰነ ነበር፡፡ ስለዚህም ለቢቢሲ አፍሪካ ክፍል በእንግሊዘኛ ለቮይስ አሜሪካ በአማርኛ ለዶች ቬል በፈረንሳይ ለፈንሳይ የዜና አገልግሎት አ.ኤ.አፍ.ፔ. በመስራት ነፍስ ዘራሁ፡፡ ከዚያም ዞ ጃፍሪካ (የአፍሪካ ጨዋታ) የሚባል ወራዊ ማጋዚን ከፈረንሳይ የእለት ስፖርት ጋዜጣ ሌኪኛ ጋር በመሻረክ አቋቋምን፡፡ ከኔ ጋር የነበረው ያሴኔጋል ተወላጅ ስለበጠበጠን እኔም ፈረንሳዮቹም ጥለንለት ሄድን፤ ከዚያም ግራና ቀኝ ተሯሩጬ ኮንቲኔንታል ስፖርት የሚባል ወራዊ መጽሄት አንድ በፈረንሳይኛ አንድ በእንግሊዘኛ እንዲሁም በየሳምንቱ የሚታደል ደብዳቤ (ኒውስ ሌተር) አቋቁሜ አስር ዓመት ሙሉ ታገልኩ፡፡ ይህ መጽሔት ስፖርት ነክ ያልሆነው የዓለም ዜናዎች ጥናቶች ውድድሮች የሚያሰራና በመሆኑ ተወዳጅ ነበር፡፡


26 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ነገር ግን በአፍሪካና በእስያ የሚሸጠው የውጭ ምንዛሬ በማጣት ገቢ ለማድረግ ትልቅ ችግር ስለፈጠረና ለፈረንሳይም መንግስት የሚከፈለው ቀረጥ ብዛት አላንቀሳቅስም ስላለኝ ማቆም ተገደድኩ፡፡ ከዚያም ኮንሰልትንት ሆኜ መስራት ጀመርኩ፡፡ ኢንቴርናሽናል ካምፔኝ አጌንስት አፓርቴድ (ኢካስ) በደቡብ አፍሪካ ስፖርት ውስጥ ያለውን የዘር ልዩነት ለማጥፋት የሚታገል ድርጅት ፕሬዘዳንት ስሆንኩ ጉዳዩን ለመከታተል ግዜ አገኘሁ፡፡ የኢንቴርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት አማካሪ ሆኜ ከስራ ቆይቼ ወደ ሎዛን ስዊዘርላንድ በመዘወር የፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት የማስታወቂያው ክፍል የኢንተርናሽናል በኦፕሬሽን ክፍል ዲሬክተር የኦሎምፒክ ሪሺም መጽሄት ዋና አዘጋጅ እሰራ ነበር፡፡ በዓለም ስፖርት ድርጅት ጽህፈት ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ለመጀመሪያ ግዜ የተሰጠው ጥቁር ወይም አፍሪካዊ እኔ ነኝ፡፡

የላቲን ቋንቋዎች ተመሳሳይ ስለሆኑ አዲስ አበባ በምኖርበት ዘመን ጣሊያንኛ ስፓኒሽ ማታ ማታ ተምሪያለሁ፡፡ በአማርኛው ፈረንሳዩ እንግሊዙ ላይ ሲጨመሩ ብሰደብ ይገባኛል ማለት፡፡ ደግነቱ ኢትዮጵያን ቋንቋ የመማር ስጦታ አለን ቻይና ጃፓን፤ ኮሪያ፤ ኖርዌይ፤ ስዊድን የሚኖረው ሁሉ ያገሩን ቋንቋ ተፍጨርጭሮ ተምርዋል፡፡ ሰነፉ ብቻ ነው ኦኬ በማለት ወደ ኋላ የቀረው፡፡ የአፍሪካ ስፖርት ድርጅቶች ቢቋቋሙ ዋናው አስተባባሪ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ስለነበረ እሱን በመከተል በስብሰባዎቹ በመካፈል ታሪካቸውን አውቃለሁ፡፡ ሁለታችንም ፈረንሳይኛ እንግሊዘኛ ስለምንናገር መላውን የአፍሪካ የስፖርት መሪዎች እናውቅ ነበር፡፡ እኔም ካርቱም ሱዳን ላይ የአፍሪካ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር መስራችና የመጀመሪያ ዋና ጸሐፊ ነኝ፡፡ ለጊዜው የአፍሪካ ፉትቦል ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አማካሪ እና የልዩ ልዩ ስፖርት ድርጅቶች ኮንሰልታንት ሆኜ አገለግላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሁሉም በአክብሮት ቢያስተናግደኝም አገልግሎት ለማበርከት ግን ተፈላጊው የክልልና የቀበሌ መታወቂያ ወረቀት የለኝም፡፡

በስፖርት ዓለም ውስጥ ብዙ ዓይነት ሽልማቶች ተሰጥተውኛል፡፡ የአሜሪካን የአውሮፓ ዩኒቨርስቲዎች ኦነራሪ ካውዛስ ዶክትሬት ሰጥተውኛል፡፡ ላንድ አብሮ አደጌ ዶክትሬት አገኘሁ ብዬ ብነግረው ለሰው እንዳትናገር ሐኪም መሰለሃቸው መድሃኒት አምጣ ይሉሃል ብሎኛል፡፡ ብዙ ሜዳሊያዎችም ከልዩ ልዩ አገሮች ተሸልሜያለሁ፡፡ በጣም የሚያስደስተኝ ግን የዛሬ ሃምሳ አምስት ኮንጎ ላይ ያገኘሁት የተባበሩት መንግስታት የሰላም ጥበቃ ሜዳሊያን ከንጉስ ነገስቱ የተሰጠኝ የኢትዮጵያ ኮከብ ባለ አምበል ሜዳሊያ ነው፡፡ አሁን በቅርብ የተሸለምኩት ሜዳሊያ በአይቨሪኮስት ፕሬዚዳንት አብጃን ላይ ነው፡፡ ለማንኛውም አንድ ተራ ሰው በራሱ ኃይልና ትጋት ሰርቶ ተከብሮ መኖር እንደሚችል ይህ የጉለሌ ፒያሳ አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጰያ አፍሪካ ዓለም ልጅ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔን የሚቆጨኝ ግን አገሬን በመልቀቄ የተነሳ ለምርጫ የሚያቀርበኝ በመጥፋቱ ከብዙ የአፍሪካና የዓለም ስፖርት

ድርጅቶች የዓመራር አባልነት ስፍራ ተገልያለሁ፡፡ ከእናት አባቴ ቤት ሆነ ከአገሬ የወጣሁት ነጻነቴን ለማስከበር ነው፡፡ አሁንም ሲሆን ያለኝ ሀብት ክብሬን ነጻነቴ ነው፡፡ በህይወቴ ውስጥ ብዙ እድል የገጠመኝ እግዚአብሔር የመረቀኝ ሰው ነኝ ለማለት እችላለሁ፡፡ በስራ የተነሳ መቶ ዘጠኝ አገሮች በዓለም ውስጥ ለመጎብኘት ችያለሁ አሜሪካን አገር ውስጥ አንኳን ሃያ ስድስት ስቴቶች ጎብኝቻለሁ፡፡ እዚህ ዓለም ውስጥ መንገደኛ ለማመላለስ የተሰሩት አውሮፕላኖች በሙሉ ተሳፍሪያለሁ፡፡ ከዲሲ ሶስ አንስቶ ኮንቨር ሰባት መቶ አርባ ሰባ እና ያሁኑ ሰባት መቶ ሰማኒያ ሰባት ቦይንግ የአውሮፕያኖቹ ኮንኮርድ ከብሽፍቱ ኮንጎ የተጓዝኩበት የአሜሪካን የጦርሰራዊት አውሮፕላን ትናንሽ የግል አውሮፕላኖች፤ ሂሊኮፕተርሁሉም ላይ ተጭኛለሁ፡፡


27 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በእግር ማለትም በአስራ አንድ ቀን አውቶብስ ከመጓዝ ሌላ በቅሎ ፈረስ ግመል ዝሆን ሞክሪያለሁ፡፡ ተሸከርካሪ ከቢቢክሌት አንስቶ ጋሪ ሌይቼንቶ አውቶብስ ትሬንታ ኳትሮ መኪና ባቡብ ሳብዌይ ትራምዌይ ሞተር ቢሲክሌት ቬስፓ ላይ ሁሉ ተሳፍሬአለሁ፡፡ አሁን ግን የምንቀሳቀሰው በታክሲ ነው፡፡ በስራ ምክንያት የተነሳ ብዙ የመንግስት መሪዎች ባለሰልጣኞች ተዋውቂያለሁ፡፡ ባጭሩ በኔ ግዜ የነበሩትን የ190 አገሮች መሪዎች ዓይቻለሁ፡፡ ማለት ነው ከነኝህም ውስጥ ብዙ ዲክታተሮች ነበሩ፡፡ ትልቅ አክብሮት ያለኝ ለአውሮፓና ጃፖን ንጉሳዊ ቤተሰቦች ነው፡፡ ለምሳሌ ያሉክ ለአምቡርግ መሪ የኢንተርናሽና ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ የተካቸውም ልጃቸው አባል ነው፡፡ ሁለቱም ከኛ ጋር በአውቶብስ የሚመላለሱ ከኛ ጋር ቁጭ ብለው የሚመገቡ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው፡፡ የሚጨማለቀው ግን ከአፍሪካ ወይም እስያ የመጣው ዲክታተር ነው፡፡ በጣም በቅርብ ከማውቀው ከኔልሰን ማንዴላ ውጭ የማስታውሳቸው ፊደል ካትሮ እና ያሲር አራፉት ነው፡፡ የስዊድን ንግስት ቢል ቪያን

የማውቃቸው አግብተው ከመንገሳቸው በፊት ነው፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ዋይት ሐውዝ እመላለስ የነበረውን ፕሬዚዳንት ክሊንተንን ኢንተርቪዬ ያደረጉት እ.ኤ.አ. 1996 አትላንታ በተካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታ አማካይነት ነው፡፡ ዋናው ወዳጄ ግን አንድሩያንግ የአትላንታ ከንቲባና በተባባሩ መንግስታት ድርጅት የአሜሪካን አምባሳደር የነበረው ነው፡፡ ጃንሆይ እ.ኤ.አ. በ1954 አሜሪካንን በጎበኙበት ወቅት ለሴነትና ኮንግሬስ ተወካዮች ዲስኩር አድርገዋል፡፡ የፕሬዝዳንት ኬኔዲ ቀብር ላይም ተገኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1945 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሳንፍራንሲስኮ ከመሰረቱት አገሮች አንድዋ መሆንና አንዳይዘነጋ የኛ ዴሌጋሲዮን አባሉ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ (በኋላ ጸሐፊ ትዕዛዝ ብላታ ተወልደ መድህን አቶ አማኑኤል አብሩሃም አቶ ተስፋዬ ተገኝ፤ አቶ ምናሴ ለማ ነበሩ፡፡ አለባበሳቸው ሁሉም ሽክ ስላሉ ያስቀኑ ነበር፡፡ እ.ኤአ. በ1980 ሌክ ፕላሲድ 2002 ሶልት ሌክ ሲቲ የክረምት ኦሎምፒክ

ጨዋታዎች እ.ኤ.አ. 1984 ሎስ አንጀለስ በ1996 አትላንታ የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች እ.ኤ.አ. በ1994 የዓለም ዋጫ የእግር ኳስ ውድድር ሎስ አንጀለስ እና ሌሎች ከተሞች በመዘዋወር ተከታትለሁ፡፡ የኔ አለቃ የነበሩት የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ አሃዱ ሳቡሬ በአሜሪካን መንግስት ተጋብዘው ስድስት ወር ሙሉ አገሪቱን እየጎበኙ በሚጹፍት እኛም ከብሉ ጂንስ ሸዊንጎም አሮው ሸርት ቡጊ ዊጊ ሸብሮሌት ጂፒ ትራቭለር ቼክ ውጭ ምንም የማናውቀውን በሰፊው እንድንረዳ ረድተውናል፡፡ በኛ ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኑ ታዋቂ አሜሪካኖች ምክትል ፕሬዚዳንት ኒክሰን ቦክ ኬኒዲ የመጀመሪያዎቹ አስትሮኖቶች ሬቪራንድ ቢሊ ግራሃም፡፡ ከዚያም የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ለመጀመሪያ ግዜ ከኒውዮርክ ውጭ አዲስ አበባ ላይ ሲሰበሰብ በድርጅቱ ዘንድ አምባሳደር የነበሩት ጆርጅ ቡሽ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት መጥተው ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ አዲስ አበባ ኢሲኤ በስራ ተዋውቀው ስለነበር እ.ኤ.አ. በ1998 ሎስ አንጀለስ ብራዚል ጣሊያን የኣለም ዋንጫ ፍጻሜ ግጥሚያ ላይ ከዚያም እ.አ..አ. በ2008 ቤዥንግ በኦሎምፒክ ጨዋታው ከልጄና ከልጅ ልጄ ጋር ራት ለመብላት የገባንበት ሬስቶራንት ውስጥ ተገናኝተን እ.ኤ.አ.

በ1962 የተባበሩት መንግስታት ሰራተኛ ሆኜ ስቀጠር ነው ዕቁብ ሳልገባ በቀጥታ ኒውዮርክ የባንክ ሂሳብ ከፍቼ አረንጓዴዋ ዶላር መቁጠር የጀመርኩት፡፡ አዲስ አበባ ለእረፍት ስሄድ ትራቭለር ቼክ መንዝሬ ሰለነበርኩ ከኔ ጋር ውቤ በረሃ ይጨፍሩ የነበሩት ተቀዳድመው በአሜሪካን ዶላር ወይም በትራቭለር ቼክ መክፈል ይቻላል ወይ በማለት ይዘንጡ ነበር፡፡ ምን ይሆናል አንድ ካሬ ሜትር መሬት እንኳን ሳልገዛ የመጣው ይምጣ በማለት ዝም ብዬ በመደሰት ብቻ አረጀሁ፡፡ ለማንኛውም እኔ የወረስኩት ነገር ስለሌለ የማወርሰውም የለኝም፡፡ ያሁኖቹ ልጆች ያለ ስማርትፎን የሚያውቁት ወይም የሚወዱት ስለሌለ የኔ መጽሐፎችና ዲስኮች ፈላጊ የላቸውም፡፡ አያታቸውና አባታቸው እነ ኬኒያ ዮጋንዳ፤ ታንዛኒያ፤ ሩዋንዳ፤ ቡሩንዲ፤ ዛምቢያ ዚምባብቄ፤ አንጎላ ነጻ ሳይወጡ ምስራቅ አፍሪካ ውሰጥ ያለኢትዮጵያኖች በቀር ጥቁሮች ሆቴል በማይገቡበት ግዜ አፍሪካን የቃኘ መሆኑን አያውቁም፡፡


28 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ዳሩ ግን እኔ እስካሁን ድረስ አስራ ሶስት የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታ ዘጠኝ የክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታ በጠቅላላው 22 ጨዋታዎች እንዲሁም አስራ ሶስት የዓለም ዋንጫ እግር ኳስ ውድድሮች ተከታትያለሁ፡፡ ልጄና የልጅ ልጆቼም የመመልከት ዕድል ገጥሞአቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተቋቋመው ጀምሮ አስራ አምስቱን ውድድር በመከታተል ላገሬ አትሌቶች አጨብጭቢያለሁ፡፡ አሁንም በእርጅና ዘመን የሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ውድድርን በዓመቱ እየሄድኩ እመለከታለሁ፡፡ እንዲያውም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ የኑክሌር ሴኩሪቲ ኤክስፐርት የሆነው ለስራ ጉዳይ የሚኖረው ፓሪስ ስለሆነ አብረን ጠበል እንቀምሳለን፡፡ ማረፊዬን አላውቅ ተጉዤ ተጉዤ እስከ መቼ ድረስ እንዲህ ተወዝውዤ ማለት ላይ የደረሰው የፒያሳ ሽማግሌ አጭር ታሪክ እዚህ ላይ አበቃል፡፡ አዲስ አበባ ቶሮንቶ ሪዮ ዲጀኔሮ እስክንገናኝ ድረስ ደሃና ሁኑ፡፡


29 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

መልካም ምኞት ከፍቅሩ ኪዳኔ

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የጥንት የኢትዮጵያ ቡድኖች ተጫዋቾችና የእግር ኳስ ጨዋታን በልዩ ልዩ መልኩ የሚደግፉ ተሰብስበው የበጎ አድራጎት ማህበር አቋቁመዋል፡፡ እኔም በየዓመቱ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን የእግር ኳስ

ውድድር ስለምገኝ የማህበሩ አባል ሆኛሁ፡፡ መዋጮም እከፍላለሁ ይህ ማህበር ከተመሰረት ጀምሮ ለብዙ ኳስ ተጫዋቾች ለነበሩ ጥገኞችም ሆኑ ችግረኞች በያሉበት ማለትም በአሜሪካ አውሮፓ አፍሪካ እንዲሁም ኢትዮጵያ ድረስ እርዳታ በመስጠትና ኑሮአቸውን ለማሻሻል የተቻለውን ጥረት በማድረግ ብዙ ውለታ ውለዋል ለዚህ ማህበር አገልግሎት የሚያበረክቱት ሁሉ በመልካም ፍቀዳቸው ነው፡፡ ይሄም ሊያስመሰግናቸው ይገባል፡፡ የስፖርት ህብረተሰብ ወዳጅነት ሁልግዜም የጸና ነው፡፡ ማህበሩ በየዓመቱ በሚያቀርበው የስራ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሁሉም አቅጣጫ ጥረት መደረጉንና እንቅፋት ቢያጋጥምም እርዳታ ለመለገስ ችሎታ እንደሌለ ነው፡፡ ማህበሩ ሰፊ ምኞት ቢኖረውም ያለ ማህበርተኞች መዋጮ በስተቀር ቋሚ ገቢ የለውም በዚህም የተነሳ ምኞቱን በእርዳታ መልክ ለመተርጎም መቸገሩ አልቀረም፡፡ ነገር ግን የማህበርተኞች ቁጥር ከጨመረና ገቢውም ከፍ ካለ እርዳታ

ከማበርከት ውጭ የአሜሪካን ወጣት ኢትዮጵያኖችን ኳስ ጨዋታን እንዲያዘወትሩ የጥንት ተጫዋቾች በአስተማሪነትና በአሰልጣኝነት እንዲያገለግሉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን መንደፍ ያስችላል በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ውድድር ጊዜ አባሎችን ለመመልመልና ለማሰባሰብ ቋሚ ዘመቻ ማድረግ ያሻል፡፡ ከዚህም በቀር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስርት ፌዴሬሽን ጋር ተባብሮ መስራት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያቀራርብ የሚያገናኝ በባህሉ ኮርቶ እንዲደሰት ከየስቴቱና ከካናዳም ጭምር የሚያሰባስበው የእግር ኳስ ዓመታዊ ውድድርና የሙዚቃ ምሽቶች ስለሆኑ የስፖርት ፌዴሬሽኑ እንዲጠነክር ሁላችንም መደገፍ አለብን፡፡ አልፎም ተርፎም ለማዳከም ለማፍረስ ለመቆጣጠር የሚጥሩትን ሁሉ በጋሻ መመከት ያስፈልጋል፡፡


30 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከኢንተርናሽንል ዳኛ ኪነ ጥበቡ ኢንተርናሽንል ዳኛ ኪነ ጥበቡ፤ ጥሪያችንን አክብረህ ስለመጣህ እናመሰግናለን፤ መልስ፤ እኔም ይህንን እድል ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ፤ ጥያቄ፤ ወደ አሜሪካን አገር የመጣኸው መቼ ነው? ኢንተርናሽንል ዳኛ ኪነ ጥበቡ፤ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. ጥያቄ፤

ኑሮ ምን ይመስላል በአሜሪካን? ኢንተርናሽንል ዳኛ ኪነ ጥበቡ፤ ብዙ ጥረትና ትግል የሚጠይቅ ነው፤ ጥያቄ፡ አንተ በሙያህ ኢንተርናሽናል ዳኛ የነበርክ ነህ እዚህ ሀገር እየሰራህበት ነው ወይንስ ከሙያው እርቀሃል፤ ኢንተርናሽንል ዳኛ ኪነ ጥበቡ፤ ወደ አሜሪካን እንደመጣሁ በሙያዬ ለመቀጠል አመልክቼ ነበር እነሱም ማንነቴን ከአረጋገጡ በኋላ እንድመጣ ደብዳቤ

ጽፈውልኝ ነበር፤ ነገር ግን ካለው የስራ ሁኔታ ጋር ሊመቻችልኝ አልቻለም ምክንያቱም ሙያው በራሱ ግዜ ይፈልጋል፡፡ ከእንቅስቃሴ ጋር በተያያዙ እራሱን ማዘጋጀት አለብህ፤ ነገር ግን ያንን ለማድረግ በቂ ግዜ ስላላገኘሁ መቀጠል አልቻልኩም በተረፈ ግን የሰሜን አሜሪካ ዋናው ውድድር ከመጀመሩ በፊት እዚህ ዲሲ፤ ሜሪላንድ፤ ቨርጂንያ አካባቢ ያሉ ቡድኖች የሚያደርጉትን ውድድር አለ በዛ ላይ በመገኘት አጫውታለሁ፡፡ ጥያቄ፡ ኢትዮጵያ በነበርክበት ጊዜ የማን ቡድን ደጋፊ ነበርክ፤


31 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ኪነ ጥበቡ ዳኛ ሆነህ የአንድ ደጋፊ አትሆንም ነገር ግን ወደ ዳኝነት ሙያ ከመግባቴ በፊት ግን የጊዮርጊስ ቡድን የምወደው ቡድን ነበር አባቴም ሲያወራ እሰማ ስለነበር እንደዚህ አይነት ነገር ተጽዕኖ ያደረጉ ይመስለኛል፡፡ ጥያቄ፤ ብዙ ዳኞች የጊዮርጊስ ደጋፊ ናቸው በመባል ትታሙ ነበር በአንተ አመለካከት ይሄ ምን ያህል እውነት ነው ትላለህ፤ ከሆነስ በምትዳኝበት ሰዓት ተጽዕኖ አድርጎብኃል፤

ኪነ ጥበቡ፤ ይኸ በጭራሽ ትክክል አይደለም ይህንን በተመለከተ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን፤ እንድ ተጫዋች የተለያየ ቡድኖች ውስጥ ሊጫወት ይችላል፤ በተጫወተበት ክለብ በወቅቱ ላለበት ቡድን የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረግ አለበት የሚታየው ይኸ ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት ሲጫወትበት የነበረውን ዘንድሮ ከሌላ ቡድን ጋር ሆኖ ቢገጥመው ባለፈው ዓመት እዚህ ቡድን ስለነበርኩ በእነርሱ ላይ ጎል አላገባም የሚል አቋም ሊኖረው አይችልም ሁልጊዜ በወቅቱ ላለበት ቡድንና ለለበሰው ማሊያ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት እኛም ሙያችን በራሱ የሚጠብቁን ነገር ስላለ ማንኛውም ቡድን ማንኛውንም ዓይነት ጨዋታ ብናጫውት ነገሮችን የምናደርገው ማድረግም ያለብን ሙያው ከሚጠይቀው አንጻር ነው፡፡

ጥያቄ፤ ካልተሳሳትኩ ጊዮጊስ ጎል ሲያገባ የማራገቢያ እንጨቱን በብቱ ውስጥ አድርጎ የአጨበጨበ የመስመር ዳኛ እንደነበረ ይነገራል ይሔ ደጋፊነትን አያሳይም፤ ኪነ ጥበቡ፤ በወቅቱ ይህንን አድርጓል፤ የተባለውን ዳኛ በዚህ ጉዳይ ላይ መጠየቅ ተደርጎለት መልስ ሰጥቶበታል እኔም በግል አነጋግሬዋለሁ በእኔ እምነት ደጋፊነትን የሚያሳይ ነው አልልም ምክንያቱም ምን ነው በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታ ነው አስመራ ላይ ጊዮርጊስና እምሶይራ ይጫወታሉ፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የቀረው 15 ደቂቃ አካባቢ ነው፤ እምባሰይራ 3ለ0 እየመራ ነው ይሄ ውጤት ደግሞ አዲስ አበባ ስታዲም ላለው ተመልካች በድምጽ ማጉያ ይነገራል፤ በቀሪው 15 ደቂቃ ውስጥ ጊዮርጊስ ቡድን 4 ጎል አግብቶ በ4ለ3 ውጤት የጊዮርጊስ ቡድን አሸናፊ ሆነ ይሄ ውጤት ሲነገር በመደነቅና በመገረም ዓይነት እንዳጨበጨበ ተናግሯል ምን አልባት ለሌላም ቲም ቢሆን ሊያደርገው ይችላል፡፡ በእርግጥ ጊዮርጊስን እንደሚወድ ተናግሯል በውጤቱ የነበረው መገረምና መደነቅ ግን የጊዮርጊስ ደጋፊ ባልሆሱ ሰዎች ዘንድም የታየ ነበር፡፡ እምባሰይራ ጠንካራ ቡድን ከመሆኑ አንጻር፤ ጥያቄ፡ በኢንተርናሽናል ዳኝነት የገጠመህ ነገር ካለ እስቲ ትንሽ አጫውተን፤


32 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የኢንተርናሽናል ጨዋታ አብዛኛው ማለት ይቻላል ሰላማዊ ነው፤ አንድ ጊዜ ማስታውሰው የአልጄሪያንና የኮንጎ ክለብ የአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ጨዋታ ነው የመጀመሪያው ጨዋታ ተካሂዷል የመልሱ ጨዋታ ኮንጎ ላይ መካሄድ ነበረበት ኮንጎ ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት ነበር ጨዋታውን የምንመራው እኔ በመሃል ዳኝነት እረዳቶች መቶ አለቃ ወርቁና አቶ ይግዛው ብዙአየሁ ነበርን ይህ ጨዋታ እያጫወትን የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር ከእነርሱም ምንም ዓይነት ነገር እስካልመጣ ድረስ እኛ ጨዋታውን እናጫውታለን ብለን ቀጠልን ጨዋታው እንዳለቀ ነገሩ በጣም እየተባባሰ ስለመጣ እዛው ማደር አልቻልንም ቡሩንዲ ወጥተን አድረን ነው በነጋታው ወደ ኢትዮጵያ የመጣነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ አምልጠን የመጣነው ይሄ አንድ ለየት ያለ ሁኔታ ነው በጭራሽ የማይረሳኝ ነው፡፡ በምንቀሳቀስበት ቦታ ሁሉ በወታደርን ታጅበን ነው መቼም የማይረሳኝ ነው፡፡ ጥያቄ፤ በአንድ ወቅት የሞሮኮውን ካዛብላካና የጋናውን ቲጌስ የክለቦች ሻምፒዮና ጨዋታ ያጫወትከው አንተ ነበርክ እና በዚህ ጨዋታ ላለ በስህተት የፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተሃል ይባላል ስለዚህ ምን ትላለህ፤ ኪነ ጥበቡ፤ በዳኝነት ስራ ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶች ይኖራሉ አንዱም በእኔ ላይ የተፈጠረው ይኸ ነበር፡፡ እኔም በኋላ ላይ ፊልሙን ሳየው ነገሩ ስህተት እንደነበረ ማየት ችያለሁ፤ በስህተቱም ሁለት ዓመት ተቀጥቻለሁ፡፡ ይኸ ነገር ባይከሰት ኖሮ በቀጥታ በዋናው የዓለም ዋንጫ ላይ በዳኝነት መሳተፍ እችል ነበር፡፡ ግን ይህ ነገር በመከሰቱ ምክንያት ቀደም ብዬ

እንደገለጽኩት 2 ዓመት ተቀጣሁ ከሁለት ዓመት ቅጣት በኋላ እንደገና ወደ ኢንተርናሽናል ዳኝነቱ ተመልሼ ነበር ግን ከዛ በኋላ በቂ ግዜም አልነበረኝም ወደዚህም አገር ስለመጣሁ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ጥያቄ፤ በዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና አርጀንቲና ላይ ውድድር ነበር እና ለዚህ ውድድር ተመርጠህ ነበር በዛ ውድድር ላይ እንዳትገኝ ያደረገው በመቀጣትህ ምክንያት ነው፤ ኪነ ጥበቡ፤ የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ሳይሆን ከእዛ በፊት የነበረው የዋናው የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ነው፡፡ በዋናው የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የተመቻቹ ሁኔታዎች ነበሩ እዛም ያሉት ሰዎች ከአሁን በኋላ ቀጥታ በኣለም ዋንጫ ላይ ለመዳኘት እደምችል የተመቻቸ ነበር እንዳለ ነበር የሚነግሩኝ፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ እራሱ አቶ ተስፋዬ ገ/የሱስ ከአጫወተ ከ21 ዓመት በኋላ ነበር እኔ በአፍሪካ ዋንጫ መገኘት የቻልኩት በወቅቱም የነበሩት በጣም ጥሩ ችሎታ የነበራቸው የሞሮኮው ዴልፕላት ዳንዱ እና ማጋሳ የሚባል የማሊ ዳኛ ለማቆም አንድ አንድ ዓመት ነበር የቀራቸው፡፡ ስለዚህ ወደ ዋናው የዓለም ዋንጫ ለመሄድ ጥሩ የተመቻቸ ነበር ነበር፡፡ ነገር ግን በቅጣቱም በሌላም በሌላም ምክንያት አልሆነም አርጀንቲና ላይ በተካሄደው የወጣቶች የዓለም ዋንጫ ላይ የሄደው ሀይለመላክ ነው የእኔ ግን ከዛ በፊት ነው፡፡


33 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ደረጃ በቂ ዳኞች አሏት ማለት ይቻላል፤ ከሌላው አገር ጋር ስታነጻጽረው በእኛ ሀገር በፌዴሬሽኑም በተጫዋቹም በተመልካቹም ዘንድ ስለ ዳኞቻችን ያለው እይታ ምን ይመስላል ትላለህ፤ ከሌላው አገር ጋር አነጻጽረህ ብትነግረን፤ ኪነ ጥበቡ፤ የዳኞች እጥረት የለብንም በቂ የሆኑ ዳኞች እንዳሉን ነው የማምነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ መታወቅ ያለበት ነገር የአልቢትር ኮሚቴው መመራት ያለበት በሙያው ውስጥ ባለፉ ሰዎች መሆን አለበት፡፡ ቀደም ብሎ ስትመለከት

አርቢትር ኮሚቴ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በሙያው ውስጥ የነበሩ ሰዎች በመሆናቸው የዳኛውን ስህተት በትክክለኛው መንገድ ከማረም ጀምሮ ዳኛው ላይ የሚመጣውንም ሙያዊ ያልሆነ ትችትም የመከላከልና ስህተቱንም ከምን አንጻር ሊታይ እንደሚገባው የማሳየት ሂደት ነበርላለፉት 10 ዓመታት፡፡ ግን በዘፈቀደ ሀላፊነት በጎደለው መንገድ የሚሰራበት ሁኔታ ነበር የነበረው አሁን ወደ መጨረሻው ላይ የተሻለ ነበር ያለ ይመስላል፡፡ ልዑልሰገድ የአርቢትር ኮሚቴ ሊቀመንበር ነው በተጨማሪም የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል ነው፡፡ በትክክል በሙያው ውስጥ ያለፈ ሰው ሀላፊነት ቦታ ላይ ሲቀመጥ የተሻለ ነገር ማየት ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ እኔ ኳስ ጨዋታ ስመለከት የዳኛውን ስህተተት የቱ ጋ እንደሆነ ከምን አንጻር ውሳኔዎችን እንደሚሰጥ ከኔ የተሻለ ሊያርመው የሚችል ሰው የለም፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩልህ በሙያው ውስጥ ያለፍኩ በመሆኔ አጠቃላይ ከዳኛው ጋር በተያያዘ ሜዳ ውስጥ የሚፈጠረውን ነገር የመገንዘብ አቅም አለኝ፡፡ ደረጃ ያለው ስትመለከት በአርቢትር ኮሚቴ ውስጥ የሚሰሩት በሙያው ያለፉ ሰዎች ናቸው፡፡ እኛም ጋር በተመሳሳይ መንገድመስራት ከተቻለ በዳኞቻችን ዘንድ የተሻለ እድገት ይኖራል፡፡ አሁን አንዳንድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ልጆች አሉ በአምላክና በሴቶች በኩል ሊዲያ በትክክል ሙያዊ የሆነ እገዛ ከተደረገላች እነሱም ሆኑ ሌሎች ወደ ተሻለ ደረጃ ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጥያቄ፤ በዳኝነት ዘመንህ ይኸ ጨዋታ ከብዶኝ ነበር የምትለው አለህ ብዙ ተመልካች የተገኘበት ቢሆን ይችላል ወይም ለዋንጫ የሚደረግ የፍጻሜ ጨዋታ፤

ኪነጥበቡ፤ እኔ የሚገርምህ ነገር እንደዚህ አስቤ አላውቅም በኢንስትራክተርህ የሚሰጥህ ስልጠና በትክክል የምትሰማ ከሆነና ትምህርቱ ከምን አንጻር እንደሚሰጥህ ማስተዋል ከቻልክ ከእንደዚህ ዓይነት አመለካከት ይጠብቅሃል፡፡ እኔ የፍጻሜ ጨዋታዎችንም ሆነ ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር የተገኘበትን ጨዋታዎች በዋና ዳኝነት መርቻለሁ፡፡ ለምሳሌ በካይሮ በኮንጎ፤ በሞሮኮ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የሆነ ህዝብ የተገኘበትን ጨዋታዎች ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ ከትምህርትህ ውስጥ ያለው ነገር በጨዋታ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ መቆጣጠር የምትችለው ጨዋታውን ከህጉ አንጻር ብቻ መተርጎም እንዳለብህ ስታውቅና ያንን ለመተግበር ወስነህ ስትገባ ነው የህዝቡ ቁጥርና የፍጻሜ ጨዋታ መሆኑ ምንም የሚያመጣብህ ፍርሀትም ሆነ ክብደት የለም፡፡


34 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በዳኝነት ዘመኔ ምንም ዓይነት ጨዋታ ቢሆን የቀበሌም ውድድር ሆነ ወይም ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ የሚደረግ ጨዋታ ለሁለቱም ያለኝ ዕይታ እኩል ነው ምክንያቱም ሁለቱም ጋር ተግባራዊ የምታደርገው ህጉን ነው፡፡ ከዛሬ 11 እነ 12 ዓመት በፊት በዳኝነት የያዝኩት ሪከርድ አለ በአንድ ዓመት ውስጥ በክልልና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ኮከብ ዳኝ ተብዬ ተሸልሜአለሁ፡፡ ይኸ እንግዲህ ማንኛውንም ጨዋታ ከህጉ አንጻር በመተግበር የምታገኘው ክብር ነው፡፡ ጥያቄ፡ አንዳንድ በተጨዋቾች መጎሸም የደረሰባቸው ዳኞች አሉ አንተ ይኸ አላጋጠመህም፤ ኪነ ጥበቡ፤

እንዲህ ዓይነት ነገር አላጋጠመኝም አንዳንድ ነገሩንም ስታየው ከጊዜውም ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ ምን አልባት የስፖርት ፍቅር ካልያዘው በስተቀር በድሮ ግዜ የነበረው ተጨዋች ከጥቅም አንጻር ይኸ ይቀርበኛል የሚል ነገር የለም በመሰረቱም ስፖርት መደበኛ የሆነ ስራቸው አልነበረም ሌላ ስራ እየሰሩ ነበር የሚጫወቱት ከስፖርቱም የሚያገኙት ጥቅም አልነበረም፡፡ በጣም አነስተኛ የሆነ ክፍያ ነው ስለዚህ በዳኛው ተሰርቷል የሚሉትን ስህተት አንዳንድ ጊዜ ባለመታገስ ዳኞች ላይ ዱላ ያደረሱ ተጫዋቾች እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ እኔ በማጫውትበት እኔ በነበርኩበት የዳኝነት ዘመኔ ግን ይሄ ነገር አልነበረም፡፡ ለተጫዋች ስፖርቱ ስራው ስለሆነ መተዳደሪያው ስለሆነ አንዳዴ ከዳኛ ጋር ከሚፈጥራቸው እሰጣ ገባ በስተቀር ሁሉም እራሱን ለህጉ አልገዛ ነበረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ጥያቄ፤

በአባልነት ወደምትገኝበት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ልመልስ መቼና እንዴት ወደ ማህበሩ ገባህ ስለማህበሩስ እንዴት ሰማህ፤ ኪነጥበቡ፤ ስለማህበሩ የሰማሁት ከታዱ ነው ማለትም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊ ከሆነው ከታደሰ ተክለጻድቅ እንዴት ገባህ ለሚለው ጥያቄ አንድ በጎ ስራን ከሚሰራ ማህበር ጋር አቅሙና ችሎታው እስካለ ድረስ መተባበር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ በእርግጥ በዚህ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ያሳለፍን ነን ያ በይበልጥ ያለውን ግንኙነት ቀላል ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በጎ ስራን ለመስራት ከሚነሱ ሰዎች ጋር መተባበር አስፈላጊ ነው በጎ ስራን ለመስራት የማታውቀውንም ሰው ቢሆን ስለዚህ ወደ ማህበሩ የገባሁት በአላማው ስለአመንኩበት ነው፡፡


35 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አብሬ በስፖርት ህይወት ውስጥ ያሳለፍኳቸውን ዛሬ ባልተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ወንድሞቻችንን በመርዳት የበኩሌንም ለማድረግ በዚህ ማህበር ውስጥ አባል ሆኖ መገኘት አስፈላጊም ስለሆነ ነው፡፡ ጥያቄ፤ እንደገና ወደ ሀገርህ ገብተህ በሙያህ ማለትም በኢንተርናሽናል ዳኝነቱ የመቀጠል ሀሳብ አለህ፤ ኪነጥበቡ፤ የለኝም በመጀመሪያ ደረጃ ህጉም አይፈቅድልህም፤ እድሜህ 45ን ካለፈ በኋላ በኢንተርናሽናል ዳኝነት ደረጃ መቀጠል

አትችልም በተጨማሪም አሁን ካለው ሁኔታ እኔም አልችልም፡፡ ሁኔታዎች ተሳክተው ወደ አገር ቤት ከገባሁ ያለኝ ሀሳብ ካለኝ ልምድና እውቀት በመነሳት በሙያ ብቁ የሆኑ ተተኪ ዳኞችን ለማፍራት ነው፡፡ ጥያቄ፤ የጡረታ ገደባችሁ 45 ላይ ከሆነ 20 ዓመት ቀነሱባችሁ ማለት ነው ከመደበኛው የጡረታ ግዜ፤ ኪነጥበቡ፤ በኢንተርናሽንል ደረጃ ከ45 በላይ መቀጠል አትችልም ይቆማል በአገር ውስጥ ውድድሮች ግን አቅሙ ካለህና መሮጥ እስከቻልክ ድረስ እስከ 50ና 55 ድረስ ማጫወት ትችላለህ፡፡ በኢንተርናሽናል ግን ከተቀመጠው የእድሜ ገደብ ካለፈ

ትወጣለህ ለዚህ ነው በአለም ላይ ታዋቂ የሆኑ ዳኞች እና ኮሊን አዋርድ በአለፈው ዓመት ነው 45 የሞላው ስለዚህ መውጣት ነበረነበት ወጣ፡፡ ጥያቄ፤ በኢንተርናሽናል ዳኝነት ብቁ ሆነህ ለማጫወት የምትወስዱት ያለ ስልጠና ወይም እንደመመዘኛ የሚቀመጥ ነገር አለ ምክንያቱም በሜዳ ውስጥ አንዳንድ ግዜ ከተጫዋች ያልተናነሰ ስትሮጡ ነው የሚታየው፤ ኪነጥበቡ፤ በመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ምርመራ አለ ከዚህ ጋር ተያይዞ የዳኛው ብቃት ችሎታ ይታያል ይህ ብቃቱና ችሎታው ማለት ግጥሚያን የመቆጣጠር አቅምህ ብስለትህ ነገሮችን የማገናዘብ ችሎታ ለምሳሌ እኔ በነበርኩበት ጊዜ የማደንቀው ዳኛ ሰለሞን አለምሰገድ ነበር ነገር ግን ሰለሞን አለምሰገድ ብዙ ግዜ ኩፐር ቴስት አያመጣም አይሞላለትም ነበር ኩፐር ቴስት ላይ የሚቀመጠው መመዘኛ በእኛ ግዜ 50 ሜትሩን በ8 ሰኮንድ በታች መግባት አለብህ ይህንን ሁለት ግዜ እናደርጋለን በመቀጠል 200 ሜትር ከ30 ሰኮንድ በታች መግባት ይጠበቅብሃል ይሄም ሁለት ግዜ በመጨረሻ በ12 ደቂቃ 2700 ሜትር መሸፈን አለብህ በእርግጥ የኛ ዳኞች በደንብ ስለሚሰሩ በ12 ደቂቃ እስከ 3000 ሜትር የሚሮጡ እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ ይሄ አንዱና ትልቁ መመዘኛ ነው፡፡ ይሄንን እስካላለፍክ ድረስ ስምህ ለፊፋ አይተላለፍም ምክንያቱም አንድ ዳኛ በ90 ደቂቃ የጨዋታ ግዜ ከ9 እስከ 12 ኪሎ ሜትር ያካልላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ደግሞ በብቃቱ ለመሸፈን ቀደም ብሎ ተቀመጠው መለኪያ ነው እንደመመዘኛ የተቀመጠው፡፡ ስለዚህ ያንን ማለፍ ግድ ነው፡፡


36 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የኛ ዳኞች በኢንተርናሽናል ዳኛ ውጭ ለማጫወት ሲሄዱ በሩጫ በኩል ችግር አልነበረባቸውም ቀሏቸው እንደልባቸው ሮጠው በብቃት ጨርሰው ነው የሚመለሱ በዚህ የእኛ ሀገር የአየር ሁኔታ ጠቀሜታ አለው ሌሎች የአፍሪካ ዳኞች ይህንን ኩፐር ቴስት ማለፍ እያቃታቸው የሚወድቁ አሉ፤ ኪነ ጥበቡ፤ አንተ በሁለት የተለያዩ የተጫዋቾች ዘመን የነበርክ ዳኛ ነህ ማለት ይቻላል፤ በ80ዎቹና በ90ዎቹ በመጨረሻም ደግሞ ወደዚህ ልትመጣ አካባቢ በነበረው ግዜ ማለት እንግዲህ የመጀመሪያዎቹን ተጨዋቾች እስከ ኢንተርናሽናል ዳኝነት በመሄድ አይተሃል፤ እንደገናም ደግሞ በኋላ ላይ የነበሩትን ተመልክተሃል እንዴት ነው፤ የቡድኖቹ ጥንካሬ የምታየው

ከዳኝነት አንጻር፤ ኪነ ጥበቡ፤ በእርግጥ አሁን ክህሎቱ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ ነገር ግን ቀደም ብሎ በተለይ በ80ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ስትመለከት እንደ አሁኑ በፕሪሚየር ሊግ ተብሎ ሳይቀየር በፊ በዲቪዚዮን ደረጃ 1ኛ ዲቪዚዮን፤ 2ኛ ዲቪዚዮን ተብሎ ሲጠራ በ1ኛ ዲቪዚዮን 10 ቡድኖች በነበሩበት ግዜ ቢያንስ 5 እና 6 ቡድኖች ለብሔራዊ ቡድን ብቁ የነበረ የተጫዋቾች ስብሰባ የነበረበት ቡድን ነበር በወቅቱ ወደ ነበሩት ግብ ጠባቂዎች እንኳን ብትመጣ አንዱን ትተህ አንዱን ለመያዝ የምትቸገር ግዜ ነበር ለብሔራዊ ቡድን ብቁ አድርጎ ቢያስመርጣቸው የሚችል ብቃት የነበራቸው ግብጠባቂዎች በየክለቡ የነበረበት ግዜ ነው አሁን ግን ግብ ጠባቂዎች ከአገር ውጭ እየመጡ በየክለቡ እየተጫወቱ ነው ያሉት፡፡ ይኸ አንዱ እግር ኳሱን

የሚያዳክመው ነው ብዬ የማስበው የኛ ልጆች የመጫው እድላቸው እየጠበበ ነው የሚሄደው በኋላ ላይ በጨዋታ ልምድ የሌለው ተጨዋች ከተቀያሪ ወንበር ላይ እየመረጥክ ለብሔራዊ ቡድን ወደ ማሳለፍ ነው የምትመጣው በአጠቃላይ በፊት ከነበረው ጋር ያለውን የተጨዋቹንም ሆነ የቡድኖች አቅም ስትመለከት እየወረደ የመጣ ነገር ነው የምትመለከተው፤ ጥያቄ፤ በመጨረሻ ማለት የምትፈልገው ነገር ካለህ፤ ኪነጥበቡ፤ በዚህ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የምታሰሩትን ላመሰግን አወዳለሁ፤ በአሜሪካን ባለው የኑሮ ሁኔታ ግዚያችሁን መስዋእት አድርጋችሁ ለዚህ ማህበር መጠናከር ስለምታደርጉት ሁሉ ከልብ በግሌ ማመስገን እፈልጋሁ፤ በተጨማሪም ለዚህ ማህበር ጥንካሬና አንድነት የሚጠበቅባቸውን በትክክል እየተወጡ ያሉትንም የማህበሩን አባላት ላመሰግን እወዳለሁ፡፡


37 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከሙሉጌታ ብርሃኔ

NAESPASA ሙሉጌታ እንኳን ደህና መጣህ፤

ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፤ NAESPASA ለረጅም ግዜ ድምጽህን ሳተሰማ ቆይተሐል እስቲ የተወሰነ ነገር ስለራስህ ነግረህን ብንጀምር፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ መልካም ስሜ ሙሉጌታ ብርሃኔ ይባላል ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ውስጥ ገነት ሰፈር በሚባል አካባቢ ነው ኳስ መጫወት የጀመርኩት እዛው ገነት ሰፈር ለወጣቶች ክለብ ነው ከዛ በኋላ በመርካቶ አካባቢ ለሚገኘው ጥቁር አባይ

ቡድን በሲ ቡድን መጫወት ጀመርኩኝ እዛ በመጫወት ላይ እያለሁ የምድር ጦር መገናኛ መሞሪያ አዲስ አበባ የሚገኘው በውትድርና አገልግሎት ይቀጥር ስለነበር በውትድ ለማገልገል ተቀጠርኩ በምድር ጦር መገናኛ መምሪያ ውስጥ እየሰራ የጥቁር አባይ ቡድን ሼል ተብሎ በሚጠራው የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ተጠቃሎ ስለነበር እኔም ለዚህ ቡድን እጫወት ነበር ከዛ በኋላ በ1966 የመቻል ቡድን ከሲቪል ወይም ህዝባዊ ከሚባሉት ክለቦች ጋር ተቀላቅሎ እንዲጫወት ሲወሰን እኔም በምድር ጦር በዚያው ክፍል ውስጥ ያለነው ከአዲስ አበባ፤ ከድሬድዋ ከአስመራ ተመራርጠን ለመቻል መጫወት ጀመርን እንግዲህ ከዚህ ግዜ ጀምሮ ኳስ እስካቆምኩበት ግዜ ድረስ ለመቻል ቡድን ነው የተጫወትኩት፤ NAESPASA እንግዲህ የወታደሮች ከሲቪል ቡድን ጋር አንድ ላይ ተቀላቅሎ እንዲጫወቱ ሲወሰን ከነበሩት የመጀመሪያዎቹ ገቢዎች

አንዱ ነበርክ ማለት ነው፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ አዎ ከመጀመሪያዎቹ አንዱ ነበርኩ፤ NAESPASA ለመቻል (ለምድር ጦር) መጫወት ከጀመርክ በኋላ ለብሔራዊ ቡድን ተመርጠህ ብዙ ግዜ ተጫውተሃል በተጨማሪም የአስረኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተመራጭ ውስጥ አንዱ ነህ እስቲ ስለዚህ አጠቃላ የነበረውን ሁኔታ ብትነግረን፤


38 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ እንግዲህ የመቻል ቡድን በ1966 መጨረሻ ላይ ነው ከሲቪል ቡድን ጋር አንድ ላይ ተቀላቅሎ እንዲጫወት የተወሰነው በ1967 ዓ.ም. የውድድር ተካፋይ ሆነን መጫወት ጀመርን፤ በዛው ዓመት የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ሆንን ለመጀመሪያ ግዜ ከመቻል ቡድን ብቸኛ የብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ሆንኩ እንግዲህ ለተወሰነ ወራት ነበር ከዛ በኋላ እና አሰፋ ባዩ አረፈ አይኔ ከኤርትራ በመምጣት የመቻል ቡድን ተቀላቀሉ እነሱም የብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ሆኑ በኃላም እነ ተስፋዬ (ቼንቶ) ተወልደ፤ ወንድሙ፤ ወደ ቡድኑ መጡ እንግዲህ የአስረኛው የአፍሪካ ዋንጫ በ1968 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ነበር ባሳየነውም የሜዳ ላይ ብቃት የብሔራዊ ቡድን አባል ለመሆን

ቻልን በወቅቱ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጀርመናዊው ፒተር ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ NAESPASA በአስረኛው የአፍሪካ ዋንጫ የነበረውን ቡድንና የተጫዋች ስብሰባ በአጠቃላይ በእናንተ ግዜ የነበረውን አጠቃላይ ብቃት ተመልክተህ ዛሬ ደግሞ ያለውን የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ከውጭ ተጫዋቾች ጋር አነጻጽረህ በእግር ኳስ የተሻለ ደረጃ መድረስ የሚቻልበት ሁኔታ ነበር ብለህ ታስባለህ፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በእኔ እምነት እኛ በምንጫወትበት ግዜና ከዛ በፊትና እና መንግስቱ ወርቁ በሚጫወቱበት ግዜ ፕሮፌሽናሊዝም

የሚለው በእግር ኳስ ውስጥ ያለው ስርዓት እኛ ሀገር አይሰራም ነበር፡፡ አማተር የእግር ኳስ ተጫዋቾች ነን፤ እግር ኳሱን እንደመደበኛ ስራህ አይደለም የሚታየው በወቅቱ ከነበረው የተጫዋቾች ስብስብና ብቃት አንጻር ይሄ እድል ቢኖር ኖሮ ማለትም በሙያህ ባለህ የእግር ኳስ ችሎታ ተከፍሎህ አገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ እንደልብህ ተዟዙረህ መጫወት የምትችልበት አሰራር ቢኖር በእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑ ተጫዋቾች ይኖሩ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ ወጣቶችን ወደ ስፖርቱ ያመጣል በዚህ ውስጥም የሚመጣው እድገት ይኖር ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በዛን ወቅት በእግር ኳስ ላይ እንከተል የነበረው አማተሪዝም ስርዓት ጎድቶናል ብዬ አስባለሁ፡፡ NAESPASA ምን አልባት በወቅቱ አጠቃላይ በእግር ኳስ ዙሪያ ያለ በተገቢው መንገድ የሚያየው ባለማግኘቱ እንጂ የውጭ ምንዛሪያችን ቡና ብቻ ሳይሆን ተጫዋቾች መሆን ይቻል ነበር ማለት ይቻላል፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ ትክክል ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ነገር ላንሳልህ በ1974 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ይመስለኛል የመቻል ቡድን የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮናን ሆነን ነበር በተጨማሪም በምርጥ ክለቦችና በመከላከያ መካከል ውድድር ተካሄዶ ያንን ሁሉ አሸነፍን በመጨረሻ ጃንሜዳ በሚገኘው የክብር ዘበኛ ክበብ ውስጥ ግብዣ ተዘጋጅቶ ምክትል የአስር አለቃ ማዕረግ ከተሰጠን በኋላ የገንዘብ ሽልማት ይሰጥ አይሰጥ የሚለው ነገር ከተነሳ በኋላ በመጨረሻ ዋናው የምድር ጦር አዛዥ የገንዘብ ሽልማት ይሰጣቸው ብሎ ስለወሰኑ እንዲሰጠን ተደረገ የተሰጠን የገንዘብ ሽልማት ግን ሃምሳ ብር ነበር፡፡


39 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ይሄ የሚያሳየው ለስፖርቱ ይሰጥ የነበረው ትኩረት እጅግ ዝቅተኛ ነበር በእርግጥ ዛሬ የተሻለ ትኩረት አግኝቷል፡፡ በእርግጥ ነገሮችም ከዛሬ ጋር የሚሄዱ ስሆኑ በአንድ በኩል ትቀበለዋለህ፤ በለላ በኩል ግን ስትመለከተው በወቅቱ ለስፖርተኛው ይደረግ ከነበረው የተሻለ ነገር ማድረግ የሚቻልበት አቅም ነበር ግን ለስፖርቱ ይሰጥ የነበረው ትኩረት ያ እንዳይደረግ አድርጎታል፡፡ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ብዙ አገሪቱን ሊጠቅሙ ይችሉ የነበሩ ተጫዋቾችን ከመኮብለል መታደግ ይቻል ነበር፡፡ ብዙዎቹም ያላቸውን ችሎታ ማሳየት የሚችሉበት ሁኔታ ይመቻች ነበር፡፡ NAESPASA ለምድር ጦር ስትጫወት ኳስ ከመጫወትህ ጋር ተያይዞ የሰራዊቱ አባል ነህ የማዕረግ አሰጣጡ

እንዴት ነበር በማዕረግህ ምን ደረጃ ላይ ደርሰህ ነበር፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በወቅቱ የነበረኝ ማዕረግ በተመለከተ ማለትም ኳስ ላይ ሆኜ የባሻ ማእረግ ላይ ነበር ቆምኩ ምክትል አስር አለቃ ከዛም አስር ሃሳ አለቃ እያለ ባሻ ላይ ደርሼ ነበር በወቅቱ ያቆምኩት ስለዚህ ነገር ሳስብ በወቅቱ አንዳንድ ትክክል ያልነበሩ ነገሮች ነበሩ ለረዥም ግዜ የመቻልን ቡድን አገልግዬ ግልጽ ባልሆነ አሰራር ውስጥ ለውስጥ በሚደረጉ በደሎች ባሻ ሆኜ ነው ከኳስ የወጣሁት የሰዎችን ስም መጥቀስ ብዙም አስፈላጊ ስላልመሰለኝ ነው ከላይ

እንደገለጽኩልህ በባሻ ማዕረግ እያለሁ ኳስ አቆምኩ ከዛ በኋላ ተመልህ ግባ የሚል ጥያቄ መጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ያቆምኩት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ስለነበረ ተመልሼ ለመግባት ፍቃደኛ አልሆንኩም ኳሱን ካቆምኩ በኋላ እንደገና ኮርስ ወስጄ የምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ ከዛም የመቶ አለቃ ማዕረግ ላይ ደርሼ ነው ኢህአዲግ የገባው፤ NAESPASA የመጨረሻ ማዕረግህ መቶ አለቃ ነው ማለት ነው፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በትክክል፤

NAESPASA ከስፖርት በዛው ተለያየህ ወይስ ከዛ በኋላ በአሰልጣኝነት ወይም በሌላ መንገድ ከስፖርት ጋር ግንኙነት ነበረህ፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በጣም የሚገርምህ ነገር ከዛ በኋላ እንኳን በስፖርት ውስጥ መሳተፍ አይደለም ማየቱም ነው ያስጠላን፤ ምክንያቱም ከመቻል ቡድን ያን ያህል አገልግዬ ምንም በማላውቀው ነገር ነው ብዙ በደል የደረሰብኝ፤ ስለዚህ መራቁን መርጬ በራሴ በግል ስራ ላይ ተሰማርቼ ነበር የምሰራው በአሰልጣኞቹም አካባቢ የምታየውና የምትሰማው ነገር የሚያራርቅህ ብቻ ሳይሆን የሚያባርር ነበር፡፡


40 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

NAESPASA ወደ ማህበራችን ልመልስህና በተጫዋችነት ዘመናቸው ብዙ ተቀባይነት የነበራቸው ኳስ ካቆሙ በኋላ ግን ተቸግረው በብዙ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ አሁንም በዛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በዙ ተጫዋቾች አሉ የዚህ ማህበር መኖር ምን ያህል ጠቀሜታ ይኖረዋል፤ ትላለህ ይህንን ችግር ለማገዝና ለመቅረፍ፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ እኔ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ብዙ አሳልፋለሁ ብዙ አድናቂዎችም ነበሩኝ፤ ብዙ ነገርም በስፖርቱ ውስጥ ተመልክቻለሁ፤ እንደዚሁም እኔ በነበርኩበት ግዜ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ብዙ ተቀባይነት የነበራቸው ተጨዋቾች

ኳስ ከአቆመ በኋለ ተቸግረው አንዳንዶቹም በህመም ውሃ የሚያቀብላቸው አጥተው እንደሞቱ እናውቃለን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የራሴ ልምድ ልንገርህ እኔ የምኖረው አየር ጤና አካባቢ ነበር፤ ኳስ ከአቆምኩ በኋላ ወደ ስታዲየም ወደ ኳስ አካባቢ አልመጣም ነበር፡፡ በተጨማሪም ኢህአዲግ ከገባ ኋላ ተፈናቅዬ ስለነበር አብዛኛው ግዜ የማሳልፈው እዛው አየር ጤና ሰፈር ነው፡፡ ግን አንዳንድ ግዜ በፊት በተጫዋችነት ዘመነህ የምታውቀው የሚያደንቅ ሰው መንገድ ስታገኘው እንዳላየ ሆኖ ሲያልፍ የሚያሳዝን ነው፡፡ ምን አልባት እንዲህ እርዳታ በመጠየቕ እንዳታስቸግረው በመፍራት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ባለቤቴን ማመስገን እፈልጋሁ በሷ ብርታትና ጥረት እኔ አንድም ቀን ተቸግሬ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ከዚህ በመነሳት ማለት የሚቻለው ስፖርተኛው በመጀመሪያ ለራሱ ማወቅ አለበት የወደፊቱን በማሰብ ኑሮውን በአግባቡና በስርዓት መምራት አለበት ከነሱ በፊት ከነበሩት ስፖርተኞች ውድቀት ሆነ ጥንካሬ መማር አለበት፡፡ ሁለተኛው የዚህ ማህበር መኖር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብዙ ሰዎች በዚህ ማህበር እንደተረዱ

አውቃለሁ ምን አልባት ይህ ማህበር ወይም እንደዚህ አይነት ማህበር ቀደም ብሎ ተቋቁሞ ቢሆን ኖሮ በተለይ በተለይ የህክምና እርዳታ ያለፉትን ጓደኞቻችንን ማገዝ ይቻል ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ማህበር ቅድሚያ በመስጠት ትብብራችንን ልናሳይ ይገባል ነው የምለው፡፡ NAESPASA ስለዚህ ማህበር እንዴት ሰማህ ወደ ማህበሩስ እንዴት ገባህ፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ እኔ እንግዲህ እዚህ ሀገር የመጣሁት በ2003 ነው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ማህበሩ ከተመሰረተ በኋላ

የዚህን ማህበር መኖር የማህበሩን አላማ የነገረኝ ታዬ ወግደረስ ነው ለእኔና ለሙሉዓለም እጅጉ ወደ ማህበሩ መግባት እንዳለብኝ እንደውም የመጀመሪያ ክፍያውን እንደሚከፍልና እኛ ለእሱ መስጠት እንደምንችል በመንገር ቶሎ የማህበሩ አባል መሆን የምንችልበትን መንገድ አቅሎልን ነበር፡፡ በወቅቱ ግን አንዳንድ ያልጨረስኳቸው ነገሮች ስለነበሩ ማለትም ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘት የመሳሰለው ስለነበር ትኩረቴ እዛ ላይ ነበር እና ቶሎ ምላሽ አልሰጠሁም፡፡ NAESPASA ቀደም ብሎ አንተም ያነሳኸው ጉዳይ አለ ህክምና የማግኘት አቅም አጥተው በተወሰነም ደረጃ እንኳን ሊረዳቸው የሚችል ባለማግኘት በህይወት የሌሉ በተጨማሪም በችግር ውስጥ እያለፉ ያሉ አሊ፡፡ እነዚህ ከመርዳት አንጻር አሁን በዚህ ማህበር ውስጥ ለሌሉ ስፖርተኞች እንደገና ለስፖርት ቤተሰቡ ምን ትላለህ


41 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በዚህ ማህበር አማካኝነት በህመም ውስጥ የነበሩ ህክምና አግኝተው ከህመማቸው አገግመው በሌላም በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ስፖርተኞች የማህበሩ አቅም በፈቀደ መጠን የተወሰነ እርዳታ አግኝተው ያየንበት ነው፡፡ ከእኔ ጋር ተጫውቶ በኋላ በህመም የነበረው በድሉ ሀይሌ ህይወቱ እስካለፈበት ግዜ ድረስ በዚህ ማህበር ሲረዳ ነበር የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኖ በሞት ቢለየንም በህመም በነበረበት ግዜ ግን የህክምና እርዳታ ማግኘት የቻለው በዚህ ማህበር አማካኝነት ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ይሄ ማህበር ለብዙዎች መድረስ እንዲቻል የማህበሩ አባል ያልሆኑ ስፖርተኞችም ሆኑ የስፖርት ቤተሰቡ የማህበሩ አባል በመሆን ትብብራቸውን ማሳየት አለባቸው እኛም የማህበሩ አባል የሆንን ሰዎች ቅድሚያ ለማህበሩ በመስጠት የሚጠበቅብንን ማድረግ አለብን፡፡ NAESPASA ወደ አሜሪካን የመጣኸው በ2003 ዓ.ም. ነው ምን ትላለህ ስለ አሜሪካን፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ በአጠቃላይ በህግና በስርዓት የምትኖርበት አገር ነው ህጉን እስካከበርክ ድረስ በነጻነት ስራህን ሰርተህ መኖር ትችላለህ የኑሮውን ስርዓት ስትመለከተው በትጋት ሰርተህ እንድትኖር የሚያደርግ ነው፡፡ የአንተን የለት ዕለት ትጋት ይጠይቃል፡፡ ይህ ከበድ ያደርገዋል፡፡ ለእኔ በግሌ አሜሪካ ተስማምቶኛል የአሜሪካንን ክፉ መስማት አልወድም በተረፈ በአየሩም ጸባይ አንጻር ባለው በሌላው በሌላውም ሁሉም ነገር ያለበት ሀገር ነው፡፡ NAESPASA በመጨረሻ ለስፖርተኛው ይሔንንም መጽሔት ለሚያነቡ ለአባላቱም የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ፤ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ ስፖርተኛውን በተመለከተ ማለት የምፈልገው አሁን ስፖርት መደበኛ ስራ ነው መተዳደሪያውም ስለሆነ ከወደፊቱ አንጻር ህይወቱን በመመልከት ዛሬ ላይ ሆኖ ነገሮችን ማስተካከል አለበት፡፡ ቀደም ብለው በችግር ውስጥ ካለፉት ስፖርተኞች መማር አለበት፤ መጽሄቱን ለሚያነቡ የስፖርት ቤተሰቦች የማህበሩ አባል በመሆን ትናንተ ሲጫወቱ ያዩአቸውን ወይም በመገናኛ ብዙሀን ስማቸው ሲጠራ ይሰሙ የነበሩትን ዛሬ ግን በችግር ውስጥ ያሉትን ስፖረተኞች ለመርዳት ማህበሩን እንዲቀላቀሉ ነው ጠሪዬን የማስተላልፈው፡፡ የማህበሩ አባል እኔን ጨምሮ እንደ አባል

የሚጠበቅብን በማድረግ ማህበሩ ከዚህ የበለጠ መዘርጋት የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅብናል የሚለውን ማሳሰብ ነው የምፈልገው፡፡ NAESPASA ሙሉጌታ ብርሃኔ ጥሪያችንን አክብረህ ስለመጣህ በማህበራችን ስም እናመሰግናለን፡፡ ሙሉጌታ ብርሃኔ፤ እኔም ይህን እድል ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ፡፡


42 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከሙሉጌታ ወ/የስ ጥያቄ፤ የኢትዮጵያ የስፖርት አፍቃሪ አንተነህ ለመጨረሻ ግዜ ያየህ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስትጫወት የተጎዳህ ግዜ ነው ወደ ኋላ ልመልስህና ከተጎዳህ በኋላ በቀጥታ ወደ ጀርመን ሀገር ነበር የሄድከው፡፡ ከዛ በኋላ ወደ አሜሪካን ሀገር መጣህ አሁን ያለህበትን ሁኔታ የስፖርት አፍቃሪ የማያውቀው ጉዳይ ስለሆነ እስቲ ስለሱ አውራን፤ ሙሉጌታ ወ/የስ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ይህንን እድል ስለሰጠኝ በቅድሚያ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ በማስከተልም የስራ አመራር አባሎች እስካሁን ድረስ ያደረጋችሁት ስራ በተለይም ብዙ ተጫዋቾች ከነበሩበት ችግር ወጥተው እራሳቸውን ቀይረው ይህ ማህበር ያዳናቸውን በአይኔ በማየቴ በራሴ በኩል ከዚህ ማህበር እኮራለሁ፡፡ የማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴ የስራ ሰዓታችሁን ቤተሰቦቻችሁን አሜሪካን ሀገር ነው ያለነው ሁላችንም በሀገሩ ሲስተም ነው የምንኖረው ይህንን ሁሉ አቻችሎ የተጎዳ ተጫዋቾችን ፈልጎ በማግኘት በመርዳትና በማስከም ግምባር ቀደም ሆናች ላደረጋችሁት ስራ በዚህ አጋጣሚ በእውነት ሳላመሰግናችሁ አላልፍም፡፡

ብዙዎቻችን በሀገር ቤት የተለያየ ክለብ ውስ የተለያየ ማልያ ለብሰን ነው የተጫወትነው፡፡ አሁን ደግሞ በአሜሪካ ሀገር በዚህ ትልቅ ዓላማ ባለው ማህበር ስር አንድ ማሊያ ለብሰን የተጎዱ ጓደኞቻችን እየረዳን እንገኛለን፡፡ እኔ እግሬን የተሰበርኩት ኳስን ጠግቤ ሳልጫወት ነው፡፡ ጥሩ ፉትቦል ተጫውቻለሁ ማለት አልችልም ገና ጥሩ ፉትቦል መጫወት ስጀምር ነው የተጎዳሁት ከእኔ በፊት ይጫወቱ የነበሩት ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ኳስ ተጫዋቾች አይ ነበር፡፡ እነዛ ተጫዋቾች የተጫወቱትን ፉትቦል መጫወት እመኝ ነበር፡፡ እንግዲህ እንደምታውቁት በዛ አጋጣሚ ተጎድቼ ከኳስ ዓለም ተለይቻለሁ፡፡ ሁላችንም በያለንበት እስቴት ከስፖርት ብዙም ሳንርቅ ያለንን ልምድ ለወጣቶች ባለን ትርፍ ግዜ ለማካፈል እኛ

ያለፍንበትን መጥፎ ነገር እኛ የተሳሳትነው ስህተት እንዳይደግሙት ሁላችሁም የተመሳሰለ ነገር እንደምትሰሩት እኔም በዛ ነገር ተሰማርቻለሁ፡፡ በተለይም በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስና ባህል ፌዴሬሽን በሚዘጋጀው ውድድሮች ውስጥ በምንገኝበት አካባቢ ያሉትን የእግር ኳስ ቡድኖች በማሰልጠን በስፖርት ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ ላይ ነን፡፡ በግል ህይወቴ በሌላ ስራ ተሰማርቼ እገኛሁ፡፡ ጥያቄ፤ ያኔ ስትጎዳ በእግር ተነስተህ የምትሄድ አይመስልም ነበር፡፡ አሜሪካን ከመጣህ በኋላ ኳስ ተጫውተህ ታውቃለህ፡፡ አሰልጣኝ እንደሆንክ እናውቃለን የጤንነትህ ሁኔታ እንዴት ነው፡፡ ለራስህ እዲህ ዱብዱብ ትላለህ፤


43 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሙሉጌታ ወ/የስ፤ እንግዲህ እዚህ ሀገር ከመጣሁ በኋላ ሁለት ግዜ ህክምና አድርጋለሁ ወደ ኳስ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ መመለስ እንደማልችል በግዜው ሳውቀው በጤንነት ራሴን መጠበቅ ያለብኝ አንዳንድ ሁኔታዎች ስለነበሩ ጉልበቴንም ለማጠንከር የማደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከእግር ኳስ ጨዋታ ለጊዜው ቢለየኝም በአካባቢ የስፖርት ጤና ቡድኖች ውስጥ ራሴን ቀለል ባለ ያጨዋወት ሁኔታዎች ከኳስ ላለመራቅ በነበረኝ ፍቅር ስሳተፍ ቆይቻለሁ፡፡ በእግሬ ላይ ያለው ጉዳት ሙሉ በሙሉ ድኗል ባልልም በእውነቱ የነበረኝ በህክምና ያገኘሁት ውጤት ትልቅ ነው፡፡ ምን ግዜም የኢዮጵያ ህዝብ ባለውለታዬ ነው፡፡ የምረሳው አይደለም በእውነት እድለኛ ነኝ የምለው እግዚአብሔር ላደረገልኝ ታላቅ ስጦታ ነው፡፡ በህይወቴ ውስጥ እንደዚህ አይነት እድል ለራሴሁሌ ያልጠበቁት ነገር ስላልሆነ

ተመልሼ ኳስ ባልጫወትም ምንም የቀረብኝ ነገር የለም ነው የምለው፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሚቀጥሉትን ተተኪ ተጫዋቾችን ለማፍራት የነበረኝ ትኩረት ከጨዋታ ወይም ከስፖርት ሜዳ አላላቀኝም፡፡ ጥያቄ፤ አንተ የነበርክበት ክለብ ትልቅ ክለብ ነበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ነበርክ እንዳንተ በትልቅ ደረጃ ሳይጫወቱ ተጎድተው ኳስ ያቆሙ ተጫዋቾች አሉ ምንም እርዳታ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ይህ ማህበርም የተቋቋመውና በአሁኑ ሰዓት እያደረገያለው በጉዳት ከኳሱ ተሰናብተው ከችግር ላይ የሚገኙ ሌላው በእድሜ ምክንያት ኳስ አቁመው ምንም ስራ የሌላቸውን ተጫዋቾች ለመርዳት ነው፡፡ እስቲ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለህ፤ ሙሉጌታ ወ/የስ፤

ለእኔ እኔ እዳልኩህ እድለኛ ነኝ ይህ አጋጣሚ ከስንት ግዜ አንድ ግዜ የሚሆን ነው ይህ አጋጣሚ ደግሞ እኔ ላይ ደርሷል፡፡ ብዙፈ ተጫዋቾች ተጎድተው ከኳስ ዓለም ሲወጡ አይተናል እነዛ ልጆች እንኳን ወደ ኳስ ሜዳ ሊመለሱ አይደለም እንደሚታወቀው በዛ ሰዓት ኳስ ተጫውተን ነበር ይህወታችንና ቤተሰቦቻችን እየረዳን የነበረው ብዙ ነገር የተያዘው ከዚሁ ስራ ጋር ነው፡፡ አንድ ተጫዋች በተለይም በወጣትነት እድሜው ላይ ከኳስ አለም ከወጣ የሚገጥመው ችግር መናገር አያዳግትም፡፡ በብሔራዊ ቡድንም በክለብም ተጫውተው ያለፉ ኳስ ተጫዋቾች ከዚህ በአሜሪካን ሀገር ውስጥ በተለያዩ ስቴት ይኖራሉ፤ ይህ የማህበር አላማ ለእያንዳንዱ ተጨዋች በመግለጽ ጥሪ በማድረግ የምንችለውን ያህል ለዚህ ማህበር ኮንትሩብሽን ማድረግ አለብን፡፡ በርግጥ ይህ ማህበር የሚሰራው ትልቅ ስራ የሚታይና ግልጽ ነው የሚሰሩትም ነገሮች

ውጤታማ ሆኖ በግልጽ እየታየ ነው፡፡ የስፖት አመራሮችንም ተጫዋቾችንም ቢሆን በስልክ እየደወልን ኮምንኬት በማድረግ ይህ ማህበርን እንዴት የምናሰርው የተለያዩ አስተያየቶች ጥያቄዎችን በግምባር ቀርበው እንዲጠይቁና፤ እንዲያውቁ በሚተዋወቁ ልጆም ቢሆን ይህን ማህበር ጆይን ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡ ጥያቄ፤ ከ2 ዓመት በፊት የማህበሩን ዓላ ለማሳካት አብዛኛው የማህበሩ አባላት በራሳቸው ወጭ እቦታው ድረስ በመሄድ የተጎዳውን ተጫዋች ከርቀት ሳይሆን በቅርበት እናያለን ብለው እርዳታ ለማሰባሰቢያና ማህበሩን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አስተዋውቀው ተመልሰዋል፡፡ በዛ ግዜ ያለው ሁኔታ ምን ይመስል ነበር የአንተስ አስተያየት ምንድን ነበር በዛ ወቅር፤


44 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሙሉጌታ ወ/የስ፤ ይህንን ጉዳይ በዛው ዓመት በጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተነጋገርንበት ይመስለኛል በዛ ወቅት መሄድ የሚችሉ አባሎች መሄድ የማይችሉ በግል ጉዳዮች ምክንያት በሚል ተነጋግረንበት ነበር፡፡ በእኔ በኩል ይህ ዓላማ ዞሮ ዞሮ የተጎዱ ተጫዋቾችን በማሰብ እነሱን ለመርዳት የተደረገ ጉዞ ነው፡፡ በእውነት በዚህ አጋጣሚ ያንን ሁሉ መስዋትነት ከፍለው ሁኔታዎች ባይሳኩም ግን ለነበረው ዓላም በዛ ጉዳይ ላይ የተሳተፉ የማህበሩን አባላቶች በሙሉ ሳላመሰግናቸው አላልፍም፡፡ ምክንያቱም ቀላል መስዋትነት አልነበረውም በዛ አጋጣ የነበረው ሁኔታ ለግዜው የተለያዩ ችግሮች ነበሩ ግን ዋናው ሁኔታ ተሳካም አልተሳካ ይህ ማህበር ለትክክለኛ ዓላማ የቆመ ስለነበረ ማህበሩ የሚችለውን አድርጎ ተመልሷል፡፡ ከሁሉም በላይ ለዓላማው ጠንካራ መሆንን ያሳ የማህበሩ አባላት ስለነበሩ ለልዑካ ቡድኑ በዚህ አጋጣሚ

አድናቆቴን ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ ጥያቄ፤ ማህበሩ በገንዘብ ማሰባሰብ ደረጃ በተፈጠሩ ሁኔታዎች ገንዘብ ማሰባሰብ ባይቻልም ማህበሩን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለስፖት አፍረቃሪው በማስተዋወቅ አንጻር የተሳካ ነበር የሚል እምነት አላቸው የስራ አመራር ኮሚዎች አንተ ይህንን ሀሳብ ትጋራለህ፤ ሙሉጌታ ወ/የስ፤ ዓላማው ጥሩ ዓላማ ነበር ተጨዋቾችን ለመርዳት የተደረገ ጉዞ ነበር፡፡ እንግዲህ ይህንን ተጫወቾችን ለመርዳት

የሚያስችል ነገር አላገኘንም ስለዚህ ጉዞን በሁለት መንገድ ማየት ይቻላል አላማ ነበር አላማው ሙሉ ለሙሉ የተሳካ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም የተለያዩ ችግሮች የተጠበቀው ያልተጠበቀው ነበር ግን አንድ ነገር ስትሞክት ሊሳካም ላይሳካም ይችላል፡፡ የማህበሩ ዓላማ ያልተሳካው እንደገና አስተካክሎ እንዲሳካ ማድረስ እስከሆነ ድረስ ብዙ ግዜ ሁሉም ያደርግናቸው ነገሮች ይሳኩልናል ብለን አናምንም፡፡ ግን ስላለተሳካም ደግሞ ማህበሩ የሚሄደው ሮንግ ነው ብለን አንልም፡፡ በያንዳንዱ ነገር ላይ ሪስክ ትወስዳለህ ከተሳካልህ ትክክል ነህ ትባላለህ ካልተሳካልህ ትክክል አይደለም ትባላለህ፡፡ በያንዳንዱ ድርጊቶች ላይ የምትማራቸው ልምዶች የሚሆኑ ነገሮች አሉ እንግዲህ እነዚህ ገንዘብ እንዳሆነ እንዳለለናስብ ያደረጉ ችግሮች በመንም መልዕክ ቢሆን ነበር ማቆም ይቻል የነበረው፡፡ ችግሮችን ማቆም አንችልም ነበር ወይ ያ የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡ ግን ትልቁ ስራ ሀሳቡ ነበር ያልተሳካበት ነገርም ቢኖር ግን አላማው ነው ዋናው መታየት ያለበት ሙሉ ለሙሉ አሳክተናል ባንልም በአንድ ኮፒ ግን በሀሳብ ደረጃ ያ ሀሳብ ሄዷል

ማህበሩን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የማስተዋውቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ በገንዘብ አሰባሰብ ደረጃ የመጣው ሀሳብ ደግሞ አላሳካንም በጠቅላላ ግን ማህበሩን የሚጎዳ ነገር የለም፡፡ ጥያቄ፤ ብዙ የስፖርት አፍቃሪ አንተን በዚህ አጋጣሚ ይመጣል የሚል ግምት ነበረው ባለመሄድህ ለአድናቂዎችህና ለስፖርት አፍቃሪው የምታስተላልፈው መልዕክት አለህ፡፡


45 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ሙሉጌታ ወ/የስ፤ ብዙ ግዜ ለእንደዚህ ያሉ ነገሮች እንደምታውቁት እዚህ ሀገር ብዙዎችን ነገሮች የምናደርጋቸው ባለን ትርፍ ግዜ ነው፡፡ በቤተሰብ ውጥረት በግል ጉዳይ በተለያዩ ነገሮች የምንመርጣቸው ግዜዎች አሉ፡፡ እኔም በዛ ግዜ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረኝ በዛ ምክንያት በጉዞው ላይ እንደማልገኝ በወቅቱ ለስራ አመራር ኮሚቴ አሳውቃለሁ፡፡ ያም ሆኖ ግን መሄድ ባለመቻሌ በራሴ አዝኛለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ተሳክቶላቸው ለሄዱ የማህበራችን አባላቶች ምስጋና አቀርባለሁ፡፡


46 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በራሴ በኩል የምጠይቀው ብዙ የሚረዱ ተጫዋቾች ሳይረዱ እስካሁን ቀርተዋል፤ ምክንያቱም ይህ ማህበር ካለበት የገንዘብ አቅም አኳያ ስለዚህ እኛ እዚህ ያላነው ተጨዋቾች የእነዚህን ተጨዋቾች ህይወት መቀየርም መወሰንም የምንችለው በእውነት ይኸ ሁላችንም ያለፍንበት ህይወት ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ሀገር የምንኖር ኳስ ተጨዋች የነበርን ብዙ ተጨዋች አሉ ኢንፎርሜሽኑን ከማህበሩ ዌብሳይት ላይ ማግኘት ይችላል እና ሁሉም ወደ ዚህ ማህበር አባል እንዲሆኑ በራሴ በኩል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ እና በዚህ ጉዳይ ላይ የምችለውን ለማድረግ ነው ቃል የምገባው፡፡ ጥያቄ፤

ወደ ኋላ ልመልስህና እንደዚህ ማህበር ከዚህ በፊት ተቋቁሞ ነበር በተለያዩ ስቴቶች ግን ብዙም ሳይቆዩ ፈርሰዋል፡፡ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ግን በ2007 ዓ.ም. ተቋቁሞ እስካሁን ድረስ ታላላቅ ስራዎችን እየሰራ በጥንካሬ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ማህበር እስካሁን መቆየት ምክንያት ምን ይመስልሃል፤ ሙሉጌታ ወ/የስ፤ ለእኔ በራሴ ግልጽና ቀላል አመላለስ የማህበሩ አባላቶች ፍቅር አላቸው እውነቴን ነው ከልብ የሆነ ፍቅር አለ እንደ ርቀታችን እንደምንኖርበት የተለያየ የአኗኗር ሁኔታዎች ቢያራርቀንም በማህበሩ ውስጥ ያለው ፍቅር ትልቅ ስልሆነ ሁልግዜ አንረሳሳም ያም መሰረታዊ ትልቁ ሚስጥር ነው፡፡ በውስጣችን በተለይ በማህበሩ ውስጥ ያለውን ችግር

የምንፈታበት መካኒዝም ከፍቅር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለሆነም እንደ ቤተሰብ ነው የምንተያየው ያን አይነት መካኒዝም እና አካሄድ የማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴዎች ስለፈጠራችሁ አባላቱ ማህበሩ የሚያድግበት ያለብንን ድክመት ጠንካራ ጎኑን በሙሉ ልብ የመናገር ቤተሰባዊ ስሜትን የሚፈጥር አካሄድ፤ ስላለ ነው፡፡ ሌላው ይኸ ማህበር በወሬ ሳይሆን በአክሽን ላይ ተግባራዊ ያደረጋቸው ስራዎች በማህበሩ አባላት ላይ እምነትን ስላሳደረ ይህ ማህበር ወደፊት እየሄደ እያየን ስለሆነ ከሌሎች ማህበሮች የተለየና በጥንካሬው እስካሁን የቆየበት ሚስጥር በእኔ በኩል ይኸ ይመስለኛል፡፡ ጥያቄ፤ ይህ ማህበር በዚህ ባሳለፍሳምንት ዓመት ውስጥ ብዙ ተጨዋቾችን ረድቷል ግን የማህበሩ ወራዊ መዋጮ አስር ዶላር ነው ይኸ የሚያንስ አይመስልህም፤ ሙሉጌታ ወ/የስ፤ በርግጥ ያንስል ምናልባት ማህበሩ በእንደዚህ ዓይነት መንገድ ክፍያ የተጓዘው ከነበሩበት አንዳንድ ችግሮች ይመስለኛል፡፡ እንደምታስታውሱት በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስና ባህል ፌዴሬሽን የነበሩት ችግሮች ይህንን ማህበር ጎድቶታል፡፡ ይህ ማህበር እራሱን በማቆም ላይ እራሱን በማጠናከር ላይ እንደገና በመገንባት ላይ ብዙ ነገሮች ስለነበሩ ማህበሩን የማቆየት ሁኔታ ነው፡፡ የመጀመሪያ ቅድሚያ የተሰጠው ይኸም ትክክል ነበር፡፡ አሁን ምናልባት ወደፊት አንድ ሌላ ሀሳብ መጥቶ ይህን ወራዊ መዋጮ የምናሻሽልበትን መንገድ ብናይ ጥሩ ይመስለኛል፡፡


47 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ ይኸ ማህበር ካለው ሶስት ዓላማዎች አንደኛው አቅማችን በፈቀደ ግዜ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የህጻናት ሶከር አካዳሚ መክፈት ነው፡፡ ይህ ማህበር ይህንን ማሰቡ በአንተ በኩል ምን አስተያየት አለህ፤ ሙሉጌታ ወ/የስ፤ ይኸ ሰፋ ያለ ጥያቄ ነው በርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ሰፋ ባለ ሁኔታ አስበንበት ብንነጋገር የተሻለ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የእግር ኳስ ሁኔታ እየወረደ ነው፡፡ በተለይ ግዜ በተለያየ ሚዲያ ስለ ሁኔታው እንደምንሰማው ወደ መጥፎ ሁኔታ እያቆለቆለ ነው፡፡ ከላየ አንደተጠቀሰው የማህበሩ አላማ በዚህ ውስጥ የተካተተ

ነው ያለው በርግጥ ያንን እንዴት እንደምናደርገው እንጃ እንጂ ሶከር አካዳሚው በሀገራችን ውስጥ መክፈት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ከ15—16 ዓመት ክለብ እስከገባን ድረስ በአብዛኛው በራሳችን ጥረት ነው የመጣነው እና ብዙ ግዜ ትልቁ ችግር በክለብ ደረጃ ስንሄድ ከልጅነታችን መሰረታዊ ስልጠና ስላላገኘን በሲስተም ውስጥ የመጫወት ችሎታችን ጠንካራ አይደለም፡፡ ብዙም ልምድ የለንም፤ እንግዲ በቢ ቡድን በሲ ቡድን የነበረው አሰለጣጠን በፍቃደኝነት በሚሰሩ ሰዎች ነው፡፡ ወደ ዋናው ቡድን ስትገባና ለብሔራዊ ቡድን ስትመረጥ ብዙ ልምድና ችሎታ ባላቸው አሰልጣኞች መሰልጠን የምትጀምረው በሌሎች ሀገሮች 11—12 እድሜ ላይ ያሉ ተጫዋቾች ሜንታሊ ምን ያህል በሲስተም ውስጥ የመጫወት አድቫንስድ እንደሆኑ እያየለን ከተለያዩ ሀገር ተጨዋቾች ጋር የመጫወት ልምድ ትልልቅ

አሰልጣኞችም እነዚህ ተጫዋቾች ሱፐርቫይዝ እያደረጉ ስለሚመጡ ይመስለኛል፡፡ በናሸናል ቲም በክለብ ገብተው ሲጫወቱ የተለየ ፉትቦል የሚያሳዩት፡፡ በእኛም ሀገር ይኸ አካዳሚ ጠቃሚ ነው ብዙ ግዜ በሀገራችን ለይስሙላ ተብሎ የተቀመጠ ቦታ ነው አሁን አሁን ምናልባት ይኸ ነገር በስፋትም ባይሆን እየተሰራበት ይመስለኛል፡፡ እዛ ቦታ ላይ ትልቅ ትኩረት ተደርጎበት ቢሰራ እነዛ የሚያድጉ ልጆች ወደፊት በክለብም ወደ ውጭ ወጥተው የሚጫወቱበት እድል የሚያገኙበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በርቀትም ቢሆን ስለሀገራችን ኳስ እንከታተላለን የምንሰማው ነገር ጥሩ ነገር አይደለም፡፡ ጠንካራ ክለብ የለንም ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን እንዲኖር ጠንካራ ክለብ መኖር አለበት፡፡ ክለቡ ደግሞ ከታች ከህጻናት ፕሮጀክት ከቢ ከሲ ከሚመጡ ተጨዋቾች እየተገነባ መሄድ አለበት፤ እንግዲህ ይኸንን ለማድረግ ችግሮች ይኖራሉ በአመራርም በአሰራርም ግን የስፖርት አካዳሚው መኖሩ ጥሩ ነው በምን መልኩ ይሆናል የሚለው ነው ትልቁ ነገር፡፡ እኔም የምደግፈው ትልቅ ሀሳብ ነው እንዴት ይጀመር የሚለው ደግሞ ወደፊት የሁሉም

ሀሳብ የሚወስነው ይሆናል፡፡ ጥያቄ፤ ጥሪያችንን አክብረህ ይህንን ቃለ መጠይቅ በማድረግ በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር አመሰግናለሁ፡፡ ሙሉጌታ ወ/የስ፤ እኔም ይህንን እድል ስለሰጣችሁኝ በድጋሚ አመሰግናለሁ፡፡


48 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከአፈወርቅ ከበደ (ካቻ) ጥያቄ፡ ዛሬ በቀጠሮአችን መሰረት እንኳን ደህና መጣህ ካቻ፡፡ ለረጅም ግዜ በእግር ኳስ ጨዋታ ያሳለፍክና የዚህ ማህበራችንም መስራች እንደመሆንህ መጠን ትንሽ ስለ አንተ የኳስ ታሪክና ስለማህበራችን አመሰራረት ብታብራራልን፤

አፈወርቅ (ካቻ) በመጀመሪያ ደረጃ ማህበሩ ይህንን እድል ስለሰጠኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ በመቀጠልም እኔም እንደማንኛውም እግር ኳስ ተጨዋች በሰፈር ውስጥ ከጨርቅ ኳስ አንስቶ እስከ ትልቅ ኳስ በመጫወት እንዲሁም ከዛው ከሰፈር ውስጥ ጨዋታ ወደ ቀበሌ ታዳጊ ቡድን ከዛ ወደ ዋናው የቀበሌ ቡድን እንዲሁም በትምህርት ቤት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለትምህርት ቤት ተጫውቼ አሳልፋለሁ፡፡ በዛውም ለቀጠናችን ተመርጬ ለመጫወት በቅቻለሁ እዛው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ ለኢካፍኮ ለሚባል የፋብሪካ ቡድን ተጫውቻለሁ፤ በመጨረሻም ለእርሻ ሰብል ቡድን ከ1979 እስከ 1983 ድረስ ተጫውቻለሁ፡፡ በዚህ በተጫወትኩባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ በመጀመሪያ ዓመት ለኢትዮጵያ ወጣት ታዳጊ ቡድን ተመርጬ ተጫውቻለሁ፡፡ ከዛም ለአዲስ አበባ ምርጥና ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጫወት እድል አግኝቻለሁ፡፡

ጥያቄ፡ ከቻ የሚለው የቅጽል ስምህን እንዴት ሊሰጥህ እንደቻለ ለአንባቢ ብትገልጽልን፤

አፈወርቅ (ካቻ)፡ እኔ እግር ኳስ በምጫወትበት ወቅት በጣም ፈጣን ነበርኩኝ እና ካቻ ማለት ደግሞ በወቅቱ በጣም ፈጣን አውሮፕላን ነበር እና የሠፈራችን ሰው ነው ይህንን ቅጽል ስም አውጥልኝ እነሆ እስከዛሬ ድረስ መጠሪያዬ ሆኖ የቀረው፡፡

ጥያቄ፡ ካቻ ወደ አሜሪካ አገር ጠፍተህ ነው ወይስ በሌለ ነገር ነው ወደ እዚህ የመጣኸው እስቲ አመጣጥህን ብትገልጽልን፤

አፈወርቅ (ካቻ) ወደ አሜሪካን አገር ልመጣ የቻልኩት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣት ቡድን ተመርጬ ግብጽ ላይ ጠፍቼ ነበር ከዛ ወደ አገራችን ተይዘን ተመልሰን እያለ እኔ ፍላጎት ደምሴ እና ርሶሞ እዚህ አሜሪካን ሀገር አላባማ ዩኒቨርስቲ የእግር ኳስ ቡድን ተጋብዘን ልንመጣ ችለናል፡፡

ጥያቄ፡ ግብጽ አገር ተጫውተን ከዛ ጠፍተን ነበር ብለሃል ከዛ ደግሞ እንደገና ተመልሰን አልክ እንዴት ነው አመላለሳችሁ እስቲ ለአንባቢያን ግልጽ ብታደርግላቸው፤


49 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አፈወርቅ (ካቻ) በወቅቱ እኔ የተመረጥኩት የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ግብጽ ላይ ለሚደረገው ከስምንቱ የኛ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አንዱ ነበር እዛ በሄድንበት ሰዓት ውድድራችንን ጨርሰን ከ22 (ሃያ ሁለት) ተጨዋቾች አስራ አምስታችን እዛው ግብጽ ውስጥ ጠፋን እኛ በጠፋንበት ወቅት ግብጽ ውስጥ ኦል አፍሪካን ጌም ይዘጋጅ ነበር በወቅቱ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት (ደርግ) ለግብጽ መንግስት የጠፉት ተጨዋቾች ካልተመለሱ በስፖርቱ ውድድር ላይ እንደማይሳተፍ ለግብጽ መንግስት አስታወቀ በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ቻርተር አይሮፕላን ልኮ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በቅተናል፡፡

ጥያቄ፡ ዓመተ ምህረቱ መቼ ነበር፤

አፈወርቅ (ካቻ) በኢትዮጵያን አቆጣጠር 1983 ዓ.ም. ነው፡፡

ጥያቄ፡ ኢህአድግ ከገባ በኋላ ነው?

አፈወርቅ (ካቻ) ኢህአድግ ከመግባቱ ከስድስት ወር በፊት፤

ጥያቄ፤ ከስሩ አሥራምስታችሁም ከግብጽ አገር ተይዛችሁ ስትመለሱ ምንም አልሆናችሁም? በዛ ሰዓት መቼም ሰው ሁሉ የሚያስበው አንድ ነገር ይደርስባችኋል ብሎ ነው እና ምንም አልተፈጠረባችሁም?

አፈወርቅ (ካቻ) በቀጥታ በቻርተር አውሮፕላን እንደተመለስን መኪና ተዘጋጅቶልን ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ተወሰድን ከጥቂት ቀናት በኋላ መርማሪዎቹ ከመንግስት መመሪያ በመጣላቸው መሰረት ማን እንዲጠፋ እንዳስተባበረ ለምን ሊጠፉ እንደፈለጉ ወዘተ ውጤቱን አስረክቡ ስለተባሉ ስራቸውን ጀመሩ ለኛ ግን በጣም ጥሩ አጋጣሚ ተፈጠረልን በሙሉ መርማሪዎቹ (ህዝብ ደህንነቶቹ) ያውቁን ነበር ስታዲየም የሚገቡ ነበሩና በነዚህ መርማሪዎች ትብብር ምክንያት የምርመራውን ውጤት ከማህላችን አስተባባሪ እንደሌለና በልጅነት ባለማወቅ እዛው አታለዋቸው ነው የጠፉት ብለው ለመንግስት ባቀረቡት የምርመራ ውጤት በቀጥታ እንድንለቀቅ ተደረገ፡፡ በወቅቱ መርማሪዎቹ ይሄንን ሚና ባይጫወቱልን ኖሮ መጥፎ ነገሮች ሊደረሱብን ይችል ነበር፡፡


50 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፡ ስፖርተኛ መሆን ከእስርም ያድናል ነዋ የምትለን?

አፈወርቅ (ካቻ)፤ አዎ በትክክል እንጂ፤

ጥያቄ፤ ጠፍታችሁ ከተመለሳችሁ በኋላ ወደ ኳሱ አለም እንዴት ተመለሳችሁ?

እንዲሁም

ከፌዴሬሽኑም

ሆነ

ከክለባች

የገጠማችሁ ችግር ካለ ብትገልጽልን?

አፈወርቅ (ካቻ)፤ ጠፍተን ከተመለስን በኋላ ፌዴሬሽኑ ለጊዜው ከጨዋታ አግዶን ነበር ነገር ግን ክለባችን ማለትም የእርሻ ሰብል የእግር ኳስ ቡድን እኛ ሶስታችን (ርዕሶም፤ እኔና ፍላጎት) ተመልሰን እንድንጫወት ኮሚቴዎቹና ተጨዋቾቹ ስብሰባ አድርገው ባደረጉትም መስማማት ወደ ጨዋታችን እንድንመለስ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ በወቅቱ ለነበሩት ኮሚቴዎችና ተጨዋቾች ከፍተኛ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ የክለባችን መሪዎችና ተጨዋቾች ወደ ጨዋታ እንድንመለስ እየታገሉልን ሳለ (ፌዴሬሽኑ ይጫወቱ ብሎ ከመፍቀዱ በፊት ከአሜሪካን አገር ማለትም

ከአላባማ ዩኒቨርስቲ የእግር ኳስ ስኮላር ሽፕ ፕሮሰስ ጀምረን ከአገር ወጣን፤ ነገር ግን ከኛ ጋር ጠፍተው የተመለሱት ተመልሰው ለክለባቸው እንዲጫወቱ ፌዴሬሽኑ ፈቅዶላቸው ነበር፡፡

ጥያቄ፤ እንደገና ወደ ኳሱ ልመልስህና የእርሻ ሰብል እግር ኳስ ቡድን ውስጥ በጣም አስቸጋሪ ተጨዋች አንዱ ነበርክ ይባላል እንደውም ባንተ የተነሳ ብዙ የክለብህ ተጨዋቾች ብዙ ቅጣት ደርሶብናል እያሉ ብዙ የሚያማርሩ ተጨዋቾች አግኝተናል እስቲ ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ብታብራራልን?

አፈወርቅ (ካቻ)፤ አዎ እርሻ ሰብል የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ በነበርኩበት ወቅት ከጨዋታ ከልምምድ በኋላ አንዳንዴ ከተጨዋቾች ጓደኞቼ ጋር መውጣት እወድ ነበር አንዳንዴ አምሽተን በመምጣታችን በሙሉ ማለትም ተጨዋቾቹ በሙሉ አሰልጣኙ በስፖርት ማለትም በኮንድሽን ትሬኒንግ ይቀጣን ነበር ግን ሌላ አይነት ቅጣት አልደረሰብንም፤


51 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፡ ስለማህበሩ ማለትም ስለ እግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ከመስራቾቹ አንዱ አንተ እንደመሆንህ መጠን እስኪ ለአንባቢዎች ይህ ማህበር እንዴት እንደተቋቋመና ስለዚህ ማህበር ያለህን ስሜት አብረህ ብትገልጽልን

አፈወርቅ (ካቻ) በየዓመቱ በሚያገናኘን በESFNA ውድድር ላይ ስንገናኝ ሁልጊዜ ከአብዲ ጋር መቼ ነው ተሰባስበን እራት የምንበላው ብለን ስለማህበር አደረጃጀት ያለንን ሀሳብ እናቀርብላቸዋለን ብለን በ2007 እ.ኤ.አ. ዳላስ ቴክሳስ ላይ በነበረው የESFNA ውድድር የምናውቃቸውን ተጨዋቾች አሰባስበን እራት እንድንበላ ተቀጣጠርን በአጋጣሚ ከኢጣሊያን በዛ ያሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች መጥተው ስለነበረ እሱን አጋጣሚ በመጠቀም በአንድ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ውስጥ ተገናኝተን ይሄንን አላማችንን እኔና አብዲ ገለጽንላቸው እነሱም በዚህ ተስማሙ በዚህ ስብሰባ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ቢተው አብሬ ስለቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋች አብዱልከሪም ኡመር በከንያ ያለበትን ችግርና ስቃይ አስመልክቶ ገለጸልን እዛው እራት ላይ የተገኘነው ተጨዋቾች ብር አዋጥተን ወደ አሜሪካ ሀገር እንዲመጣ ጉዳዩን ጀመርን እነሆ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አሜሪካ አገር አስመጣነው ከዛ በኋላ ነው ሰባት ስራ አስኪያጅ ኮሚቴዎችን መርጠን እነሆ የተለያዩ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ለመርዳት የበቃነው፡፡

ጥያቄ፤ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ለማቋቋም በተለያየ ግዜ ሙከራ ተደርጎ ነበር፡፡ ግን ሊሳካ አልቻለም አሁን ግን ማህበራችን ከተመሰረተ እነሆ ስምንት ዓመት ሊሆነው ነው ታዲያ አንተ ስታስበው አሁን እንደዚህ ጠንካራ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው፡፡

አፈወርቅ (ካቻ)፤ በእርግጥ እንደዚህ ዓይነት የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ለማቋቋም ብዙ ሙከራዎች ተደርገው ነበር አልተሳኩም፡፡ ነገር ግን የመሰረትነው ይህ ማህበር ጠንከር ብሎ ሊቆም የቻለው፤ 1. ስፖርተኛው የቀድሞውን አብሮን ሲጫወት የነበረው እግር ኳስ ተጨዋች በአሁኑ ሰዓት እርዳታ የሚፈልገውን የመርዳት፤የውዴታ ግዴታ እንዳለበት ጠንቅቆ በማወቁ፤ 2. ደጋፊዎቻችን እንደዚሁ እኛ የምናደርገውን በሙሉ ከኛ ጎን ተሰልፈው ድጋፋቸውን በማድረጋቸው፤ በጣም የምናምናቸው እንዲሁም ከሀሉም ስፖርተኛም ሆነ ደጋፊዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ችሎታ ያላቸው እንደ አብዲና ታዱ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ማህበራችን ጠንክሮ በአሁኑ ሰዓት የኛን እርዳታ ለሚጠብቁት የቀድሞው እግር ኳስ ተጨዋቾች ለመድረስ በቅተናል፡፡


52 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ በዚሁ ላይ አያይዤ አሁን በቅርብ ዓመታት የተቋቋመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር እዚህ አሜሪካን አገር ያለው አንዱ ዓላማው የኢትዮጵያ እግር ኳስን በተቻለ አቅም ተጨዋቾች እንደመሆናችን መጠን የእግር ኳስ አካዳሚ መክፈት አለብን የሚል እምነት አለው ታዲያ አንተ ከምትለው ጋር በጣም ተመሳሳይነት አለው፡፡ ስለዚህ ይህ ማህበር ዓላማውን ስታይ ትክክል ነው ብለህ ታምናለህ?

አፈወርቅ (ካቻ)፤ አዎ ሙሉ ለሙሉ ያለውን የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ችግር ይቀርፋል ብዬ ባልገምትም እንደዚህ ዓይነት ማህበር (NAESPASA) ጥሩ ዓይነት ስፖንሰር ቢያገኝ የአገራችንን እግር ኳስ በመጠኑም ቢሆን ይረዳዋል የሚል ሀሳብ አለን፡፡

NAESPASA እዚህ አሜሪካ አገር ውስጥ ብዙ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ይኖራሉ ግን በአብዛኛው በተለያዩ ምክንያቶች እዚህ ማህበር ውስጥ ያልገቡ አሉ መቼም እንደምታውቀው ማህበራችን ውስጥ አባል ለመሆን እና የአንድ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን ህይወት ለማዳን በቀን 0.33 በወር 10 ወይም በዓመት 120 ዶላር ነው፡፡ ታዲያ ለነዚህ ላልገቡ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ምን ብናደርግ ብዙዎቹን በናመጣቸው የምንችል ይመስልሃል እስቲ በአንተ አንደበት ጥሪህን ምን ብለህ ታስተላልፍላቸዋለህ?

አፈወርቅ (ካቻ)፤ በኔ ግምት እዚህ ማህበራችን ውስጥ ያልገቡ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ገንዘቡ በዝቶባቸው ነው ብዬ አላስብም በቂ ኢንፎርሜሽን ባለማግኘታቸው ይመስለኛል፡፡ የዚህ ማህበር የስራ አመራር ኮሚቴ የሆናችሁት ምን ያህል እንደጠራችሁ አውቃለሁ ግን እናንተ ብቻ ብትለፉ ዋጋ የለውም የማህበሩ አባላት በሙሉ ሀላፊነት ቢኖራቸው ይገባል ባለበት ከተማ ኢንፎርሜሽን በማስተላለፍ የማህበራችን አባል በማድረግ ሀላፊነታችንን ብንወጣ ብዙ አባላቶች ቢኖሩ ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡

NAESPASA አሁን ደግሞ ወደ ኳሱ ልመልስህ በዚህ ሀገር ውስጥ ከአንተ በፊት ባንተ ግዜ እንዲሁም ከአንተ በኋላ ካሉ ተጨዋቾች

ጋር ለመጫወት እድሉን አግኝተሃል ለመጫወትና በቅተሃል ታዲያ ይህ ሶስት ጄኔሬሽን ከያዙ ማህበር ጋር ደግሞ አብረህ በመሆንህ ምን ይሰማሃል፤

አፈወርቅ (ካቻ)፤ በእውነት ከዚህ በፊት ስታዲየም ውስጥ ገብቼ እንኳን ለማየት እድሉን ያላገኘዋቸውን ተጨዋቾች ከድሮ ሆነ ካሁኑ ለመጫወት ያበቃኝ እግዚአብሔርን ሳላመሰግነው ማለፍ አልፈልግም እንዲሁም በአንድ ላይ አሰባስቦ የቀድሞውን ተጨዋቾች እንዲረዳ ላደረገኝ ማህበራችን ከፍ ያለ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡


53 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

NAESPASA እንግዲህ ብዙውን ነገር ደባብሰነዋል አሁን ደግሞ አንተ ለአንባቢያን ማስተላለፍ የምትፈልገው ነገር ካሉ እድሉን እሰጥሃለሁ፡፡

አፈወርቅ (ካቻ) በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም እዚሁ አሜሪካን ሀገር ውስጥ አብረውኝ የተጫወቱትንና አሰልጣኞቼን ደጋፊዎቼ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ በተለይም አሰልጣኝ ሳለ ዮሱፍ አሁን በህይወት የለም እዚህ አሜሪካ አገር ለመምጣት የኳስ ስኮላር ሽፕ በመስጠት እድሉን ስለሰጠኝ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ እንዲሁም የዚህ ማህበር የስራ አስኪያጅ ኮሚቴዎች ከ2007 ጀምሮ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ኮረም ባለመሙላቱ ምክንያት ምርጫ ሳይደረግ ይሄንን ሁሉ ዓመት በማገልገላቸው እጅግ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ በተለይ በዚህ ማህበር ውስጥ ተሳትፈው ገንዘባቸውን በየወሩ እየከፈሉ እርዳታ በማድረግ ማህበሩን እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረጉትን የማህበራችን አባላትን በሙሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ አትላንታ የእግር ኳስ ቡድንና ESFNA ለ32 (ለሰላሳ ሁለት ዓመት) ኢትዮጵያኖችን በማገናኘት እዚህ ላደረሰን በጣም ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

NAESPASA ቀጠሮአችንን አክብረህ እዚህ ተገኝተህ ይህንን ቃለ ምልልስ በማድረግ በ NAESPASA ስም አመሰግናለሁ፡፡

አፈወርቅ (ካቻ)፤ እኔም ይህንን እድል ስለሰጣችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፡፡


54 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከመስፍን ገ/ጊዮርጊስ በቀጠሮአችን እንኳን ደህና መጣህ መስፍን፤ ለዚህ ቃለ መጠይቅ በመጋበዜ እኔም ከልብ አመሰግናለሁ፤ ጥያቄ፤ እስቲ የት እንደተወለድክና ስለ ኳስ አጀማመርህ ብትገልጽልን መስፍን ገብረጊዮርጊስ

መስፍን፤ የተወለድኩት አዲስ አበባ አማኑኤል ቶታል ነው ኳስን የጀመርኩት እንደማንኛውም ታዳጊ ወጣት በሰፈር ውስጥ ነው ቤተሰቦቼ በተለይም አባቴ ለኳስ ልዩ ፍቅር ስለነበረው በልጅነቴ ጀምሮ ኳስን እንድጫወት ይገፋፋኝ ነበር እኔም ከእለት ወደለት ያለኝ ፍቅር እየጨመረ በመምጣቱ በሰፈር ውስጥ መጫወት ጀመርኩ በመቀጠልም ወደ ደብረዘይት ከቤተሰቦቼ ጋር ቤት ቀይረን ስለገባን ለደብረዘይት ት/ቤት እንዲሁም ለአየር ሀይል ታዳጊ ቡድን መጫወት ጀመርኩ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነበር ወደ እግር ኳስ የገባሁት፤ ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ እያለህ ለማን ለማን ክለብ ተጫውተሃል፤ መስፍን፤ በደብረዘይት ትምህርት ቤት ስጫወት ነበር ለአየር ሀይል ታዳጊ ቡድን የተመረጥኩት በእውነት ደብረዘይት በጣም ጥሩ ግዜ ነበር እግር ኳስ በፍቅር የሚወዱ ጓደኞች ስለነበሩኝ ብዙ ግዜአችንን የምናጠፋው በልምምድ ነበር ለዛም ነበር በታላቁ አሰልጣኝ ሐጎስ ደስታ አይን ውስጥ ልገባ የቻልኩት ሐጎስ ደስታ ነበር ወደ አዲስ አበባ ይዞኝ የመጣው አግሮ እንድስትሪ ነበር የመጀመሪያ ቡድኔ ኢትዮጵያ ውስጥ የአግሮ እንዱስትሪ፤ ለአየር መንገድ፤ ለፖሊስ እንዲሁም በእግር ኳስ ታሪኬ በጣም የማረሳው ታሪክ የሰራሁበት አዋሳ ዱቄት ተጫውቻለሁ፡፡ ጥያቄ፤ ወደ አሜሪካን የመጣኸው መቼ ነው፤ መስፍን፤ ወደ አሜካን የመጣሁት እ.ኤ.አ. በ2001 ዓ.ም. ሲሆን የምኖረው ኦክላንድ ካሊፎርንያ ነው፡፡ ጥያቄ፤ አሁን ደግሞ ወደ ማህበራችን ልመልስህና አንተ በማህበራችን ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዎ ያደረክና የዚህ ማህበር መስራች ነህ የኛ እህት ማህበር የሆነውን የአውሮፓ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ማህበር እንዲመሰርት ከአደረጉት የሰሜን አሜሪካ የማህበራችን አባሎች ግምባር ቀድሙ አንተ ነህ እስቲ የአውሮፖን ማህበር እንዲመሰረት ያደረገችሁት በምን መልኩ ነው እነማንስ ከአንተ ጋር ነበሩ፤ የትስ ሀገር ነው፤


55 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

መስፍን፤ በአውሮፓ ቁጥራቸው የበዛ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች እንዳሉ ማንም ያውቃል ግን እነዚህ ተጫዋቾች በተለያየ ሀገር ስለሚኖሩ የአውሮፓ የኢትዮጵያኖች የእግር ኳስ ውድድር ጥሩ አጋጣሚ ነበር ሁሉንም አንድ ላይ ለማግኘት በ2011 እ.ኤ.አ. አንድ ቡድን ይዘን ወደ ጀርመን ኑርንበርግ በመሔድ አንድ ስብሰባ በመጥራት ቁጥራቸው የበዛ ተጫዋቾችን በመሰብሰብ የአውሮፓን ማህበር ለመመስረት ችለናል፡፡ በእውነት ይኸ ማህበር በተመሰረተ በአጭር ግዜ ውስጥ ለብዙ የቀድሞ ተጫዋቾች ህይወት የቀየረ ታላቅ ማህበር ነው የከበረ ምስጋና የሚገባውም ትልቅ ማህበር ነው፡፡ እንዲሁም ይህንን ማህበር ስንመሰርት አብረን የነበርን እሱባለው ኦሜጋ ቢንያም ሀይለስላሴ ግሪቲ ገ/መስቀል፤ አየለ መንጃታ ይማም መሐመድ ዳዊት አስመላሽን በማህበሩ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡

ጥያቄ፤ ሌላው ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰብህን ለመጠየቅ በሄደ ጊዜ በአዲስ አበባ ማህበር በነበረው ያለመግባባት የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበርን በመወከል በቦታው ተገኝተህ ነበር፤ በዛን ግዜ አዲስ የስራ አመራር ኮሚቴም እንዲመረጥ በአስመራጭ ኮሚቴነት ሰርተሃል በዛ ግዜ ስለነበረው ሁኔታ ማለትም የበፊቱ የስራ አመራር ኮሚቴ ለአዲሱ አመራር አላስረክብም ማለቱ በምን የተነሳ ነው፤ መስፍን፤ በአጋጣሚ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ከነበሩት የማህበሩ አባላት አንዱ ነበርኩኝ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የሰሜን አሜሪካ ማህበር አዲስ አበባ የሚገኘውን ማህበር በተለያየ ግዜአት ከተለያዩ የቀድሞ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ቅሬታ ይቀርብለት ስለነበረ አዲስ ኮሚቴ እንድናስመርጥ ሀላፊነት ተሰጠን በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ የስራ አመራር አባላት መካከል ጌታ ዘሩና አሰፋ ክፍሌ ሸዋረጋ ደስታ ስለተፈጠረው የስራ ጉድለት በመንገር አዲስ ኮሚቴ እንዲመረጥና

እንዲሁም ላለፉት ረጅም ግዜ ስለሰራቸው ስራዎች በማመስገን አዲስ ኮሚቴ መቋቋም እንደለበት በመስማማት አዲሱን ኮሚቴ ለመምረጥ በቀጠሮ ተለያየን፤ አዲሱን ምርጫ ለማድረግ በተቃጠርንበት ቀን ሸዋረጋ ሳይመጣ ስለቀረ ለሌላ ቀን ተቀጣጥረን ተሌዬን በሚቀጥለው ስብሰባም ባለመገኘቱ ምርጫውን ጌታ ዘሩና አሰፋ ክፍሌ ባሉበት ለማድረግ ተገደድን፤ በምርጫውም 1. ንጉሴ ገብሬ፤ 2. በሀብቱ ገ/ማርያም፤ 3. ጌቱ መልካ፤ 4. ፍታነገስ በርሄ፤ የአዲስ አበባ ኮሚቴ ሆነው ተመረጡ፤ በጣም የሚያሳዝነው ሃገር ይህ ማህበር አላማው አንድ እና አንድ ሆኖ ሳለ ማህበሩን እንደ ግል ንብረታቸው በማድረግ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታ የነበሩ የቀድሞ ተጨዋቾችን እርዳታ በመፈለግ ወደ ማህበሩ በመጡ ግዜ በማንገላታትና ችግራቸውን በግዜው ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ ባለመቻላቸው ለበዙ የተጎዱ

ተጨዋቾች በሰዓቱ መድረስ ሳንችል እንድንቀር ያደረጉት ሳያንሳቸው በቦታቸው ለተተኩት የኮሚቴ አባላት ንብረት አናስረክብም ማለታቸው በእውነት ከአንድ ተጫውቶ ካለፈ ሰው የሚጠበቅ አልነበረም ለሁሉም የአዲስ አበባ ምርጫ ይህንን ይመስል ነበር፡፡ ጥያቄ፤ እስቲ አሁን ደግሞ ስለራሳችን ስለሰሜን አሜሪካ ማህበራችን ልውሰድህ ይህ ማህበር ከተመሰረተ ከስምንት ዓመት በላይ ሆኖታል በአንተ አስተሳሰብ ወይም እምነት ይህ ማህበር የተነሳበትን ዓላማ በትክክል እያሳካ ነው ትላለህ፤


56 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

መስፍን፤ በእውነቱ እንዳሰብነው ብዙ አልሰራንም ቢሆንም የሚያስደስቱ ነገሮችን አድርጓል እስከ 25-35 በሚሆኑ የቀድሞ ተጫዋቾችን በማሳከም ወደ ተሻለ ህይወት በማስገባት እጅግ የሚያስደስት ስራዎችን ሰርቷል ሊመሰገን ይገባዋል እላለሁ፡፡ ጥያቄ፤ በዚህ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የድሮ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቁጥር ከፍተኛ ነው፤ ግን በማህበሩ ውስጥ የሚሳተፉ ጥቂት ናቸው፡፡ የተቀሩት እግር ኳስ ተጫዋቾች ወደዚህ ማህበር ተሳትፎ ያላደረጉት ለምንድን ነው፤ በአንተ በኩል የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ፤ መስፍን፤ በእውነቱ ቁጥራችን እጅግ በዛ የቀድሞ ተጫዋቾች እዚህ ሰሜን አሜሪካ እንገኛለን ይህ ቁጥሩ የበዛ ተጫዋች እንደኔ ይህንን ማህበር ሳይሆን አገራችንንም መቀየር የሚችል አቅም ነበረን ግን ምን ያደርጋል አብሮ መብላት እንጂ አብሮ መረዳዳት አልፈጠረብንም፤ አንድ ሰው አይደለም የአንድ ሀገር ባለውለታ ለነበሩ የቀድሞ ተጫዋቾችን ለመርዳት በወር አስር ዶላር ከከበደን በጣም አዝናለሁ እባካችሁ በጣም እናስብበት ችግር ካለ ቀርበን እንወያይ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና በአንድነት ወንድሞቻችንን እንርዳ እላለሁ፡፡ ጥያቄ፤ ለሰጠህን ቃለምልልስ በNASPAS ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መስፍን፤ እኔም አመሰግናለሁ፡፡


57 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከዳዊት ጌታቸው ጥያቄ፡ ዳዊት ጥሪያችንን አክብረ ስለመጣህ በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር አመሰግናለሁ፡፡ እስቲ በቅድሚያ ራስህን ብታስተዋውቀን፤ ዳዊት ጌታቸው፡ ሙሉ ስሜ ዳዊት ጌታቸው የምኖረው ቦስተን፤ ጥያቄ፡

በክለብ ደረጃ ኳስ ተጫውተህ ታውቃለህ፤ ዳዊት ጌታቸው፡ በትልቅ ክለብ ደረጃ ስታዲየም ውስጥ ባልጫወትም ለፋብሪካ ቡድን ለኢትዮፎምና ለፕላስቲክ ፋብሪካ በዚህ በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስና የባህል ፌዴሬሽን ውስጥ ለሎስ አንጀለስ፤ ለአትላንታና፤ ለቦስተን ቡድኖች ተጫውቻለሁ፤ ጥያቄ፤ በመጀመሪያ እንዴት ነው ስለዚህ ማህበር የሰማኸው፤ ዳዊት ጌታቸው፡ የሰማሁት ከታዱ ይመስለኛል ማህበሩ መቋቋሙን ሰምቻለሁ በተቋቋመ ግዜ ዳላስ አልመጣሁም ግን ከሁለት ዓመት በኋላ ችካጎ በተደገው ጠቅላላ ጉባኤና የስራ አመራር ኮሚቴ ምርጫ ላይ ነበርኩ ከዛው ምርጫ በቦርድ አባልነት

ተመርጫለሁ፡፡ እኔ የሄድኩት ምርጫ ውስጥ እገባለሁ ብዬ ሳይሆን በአባልነት ለማገልገል ነበር፡፡ ጥያቄ፡ ይህ ማህበር የእግር ኳስ ተጫዋች ብቻ ሳይሆን የደጋፊች ማህበርም ጭምር ነው ታዲያ በትክክል ደጋፊዎችን ያካተተ ይመስልሃል፤ ዳዊት ጌታቸው፤ እውነት ነው ይህ ማህበር የእግር ኳስ ተጫዋችና ደጋፊዎች ማህበር መሆኑ ብዙ ኳስ ተጫውተው ሳይጫወቱም በደጋፊ ደረጃም ያሳለፉ አባላት አሉ ዋናው የሚያስተሳስረው ኃላማው ነው፡፡ አላማው ለጥሩ ነገር የተመሰረተ ስለሆነ በትክክል የተጫዋቾችና የደጋፊዎች ማህበር ነው፡፡ ጥያቄ፡

ይኸ ማህበር ካሉት ዓላማዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የስራ መስክ ከፍቶ የተቸገሩ ሰዎች ከተረጂነቱ ወደ ሰራተኝነት ለመለወጥ ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ ነበር በዚህ ጉዞ ላይ አንተም ነበርክ ስለዚህ ጉዞ ምን አስተያየት አለህ፤ ዳዊት ጌታቸው፡ ይህ ጉዞ የመጀመሪያ ስለነበረ ለስራ አመራር ኮሚቴ ብዙ ስራ ነበር ማቀናጀቱ፤ ማስተባበሩ ግን ይህንን ሁሉ ለማድረግ ብዙ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም ማህበሩ ያሰበውን ነገር እስከመጨረሻው ማድረግ ባይችልም ማህበራችንን በትልቅ ደረጃ አስተዋውቆ መጥተናል፡፡


58 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ይህ ማህበር መኖሩን ለኢትዮጵያ ህህብና ለስፖርት አፍቃሪው ህዝብ እንዲያውቅ አድርገናል ወደፊት እንደዚህ ዓይነት ችግር ይገጥመናል ብለው የሚያስቡ የእግር ኳስ ተጫዋች ተስፋ ዘርተን መጥተናል፡፡ ለሚቀጥለው እንደዚህ ዓይነት ስራ ለማድረግ በአብዛኛ ሰው ተቀባይነት ለማግኘት እንዲችልም የተሰሩ ስራዎችን አከናውነን ተመልሰናል፡፡ በአጠቃላይ ጉዞው በእኔ በኩል የተሳካና ትክክል ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጥያቄ፡ አንዳንዶቹ ማህበሩ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ ዓላማውን አላሳካም ሲሉ አንዳዶቹ ደግሞ አንተንም ጨምሮ አላማውን በትክክል አሳክቶ ተመልሷል ይላሉ እስቲ አንተ ዓላማውን አሳክቷል ስትል ከምን ተነስተህ ነው፤ ዳዊት ጌታቸው፤

እኔ እንግዲህ የማየው ገንዘብን በሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ነገር ግን ለሚረዱ ሰዎች ገንዘብ ማሰባሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ማህበሩ ነገም ተነገወዲያም ይህንን ገንዘብ ሊሰራው ይችላል፡፡ ዋናው የዚህን የተቀደሰ ማህበር ዓላማ ህህቡ እንደያውቀው አድርጎ ተመልሷል፡፡ ጉዞው የተጎዱትን ተጫዋቾች ለመርዳት ነው፡፡ እክል እንኳን ቢገጥመን ያ ሁሉ ሳይገድበን በአዲስ አበባ ስታዲየም በመጫወት የድሮ ተጫዋቾችን ሰብስበን የራት ምሽት በማዘጋጀት ለብዙ ዓመታት ያልተገናኙ ተጫዋቾች እንዲገናኙ በማድረግ ትልቅ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዛም የራት ምሽት ላይ ገንዘብ ሊረዱን ቃል የተገባልን ከስታዲየም ገቢ የበለጠ አግኝተናል፡፡ በእኔ በኩል ይህንን ሁሉ አድርገን ስለመጣን ስኬታማ ጉዞ ነበር እላለሁ፡፡ ጥያቄ፤ ችግር ገጥሞናል ስንል ምንድን ነው የተፈጠረው የሚለውን ነገር ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላልና እስቲ ስለ ተፈጠረው ችግር

ምን እንደሆነ ብታብራራልን፤ ዳዊት ጌታቸው፤ እንደመታወቀው የተፈጠው ችግር ይህ የሰሜን አሜሪካ ማህበር መርጦ ባስቀመጣቸው አዲስ አበባ ባሉ ሁለት አባሎቻችን የተፈጠረ ችግር ነው፡፡ ይኸው ችግር የመጣው ከሰሜን አሜሪካ የስራ አመራር ኮሚቴ የተሰጣቸውን ስራ ባለመስራታቸው ነው ሁለት ሰው ማህበር መምራት ስለማይችል በጎደሉ ኮሚቴዎች ምትክ ሌላ የስራ አመራር ኮሚቴ በመምረጥ አሟሉ ቢባሉም እነዚህ ሁለት ሰዎች ይህንን ቢቀበሉ አልፈለጉም ይህንን ባለማድረጋቸው ማህበሩ ሌላ የስራ አመራር ኮሚቴ በመምረጥ እነ ንጉሴ ገብሬ ይህንን አዲስ አበባ ያለውን ማህበር እንዲመሩት አድርጓል፡፡ ከዛ በኋላ ነው እነዚህ ሁለት ሰዎች ዝግጅቱ እንዳይዘጋጅ ከበስተኋላ ሆነው ብዙ መሰናክሎችን መፍጠር የጀመሩት፡፡ ለርዳታ ጨዋታ እንዲጫወቱ የተጠየቁትን ጊዮርጊስና ቡናን እንዳይጫወቱ በማድረግ በየቢሮው እየሄዱ ህጋዊ ማህበር አይደለም ዝግጅቱ

መደረግ የለበትም እያሉ ያሰብነውን ያህል ዝግጅቱ እንዳይዘጋጅ ያደረጉት፡፡ ይህ ችግር እንግዲህ በነዚህ ሁለት የኮሚቴ አባሎች የተፈጠረ ችግር ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት የሰሜን አሜሪካ ማህበር ያላሰለሰ ጥረት አድርጎ ነበር ግን እነዚህ ሰዎች በመነጋገር የማያምኑ ስለሆኑ ይህንን ችግር ለመፍታት አልተቻለም፡፡ ጥያቄ፡ ሰውን ለመርዳት የሚያጣላ ነገር ያለ አይመስለኝም እነሱም የተጎዱ ተጫዋቾችን ለመርዳት እስከሆነ ድረስ እርዳታውን በጋራ ማድረግ አይቻልም ነበር ወይስ እነሱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ ወደ ራሳችን አካውንት ይግባ አሉ፤


59 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ዳዊት ጌታቸው፤ ዋናውና ትልቁ አላማቸው ይህ ማህበር ከኢትዮጵያ ህዝብ እንዲተዋወቅ አልፈለጉም በዛው የምንፈልገውን ዓላማ እንዳናሳካ ማስቆም ነው፡፡ ገንዘቡም ተሰብስቦም ወደ እነሱ አካውንት እንዲገባ ይፈልጋሉ ዓላማውን ያወቁት አይመስለኘም፡፡ እኘ እንደዚህ ዓይነት የተለያዩ የርዳታ ማህበሮች ቢቋቋሙ እንወዳለን በአዲስ አበባም ብቻ ሳይሆን በየክፍለ ሀገሩም እነሱም ቢሆን መርዳት ከፈለጉ የኛን ልፋት ሳያሰናክሉ እነሱም በፈለጉት መንገድ የራሳቸውን ዝግጅት አዘጋጅተው መርዳት ይችሉ ነበር፡፡ እኛ አልተቃወምንም ዋናው የተጎዱ ተጫዋቾችን መርዳት ከሆነ ግን የነሱ ተልዕኮ ይህንን የኛ ዝግጅት ማሰናከል ነበር፡፡ ጥያቄ፡

በዛን ወቅት ተረጂዎችን በግምባር አግኝታችዋል በራት ግብዣው ላይም ተገኝተው የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል በዛል ግዜ የነበረው የስፖርተኛው ስሜት ምን ይመስል ነበር፤ ዳዊት ጌታቸው፤ መቼም እግሩ የተጎዳ ተጫዋች የሚያሳክመው አጥቶ መሄድ አቅቶት ሲንከራተት የነበረ ሰው ይህ ማህበር ባደረገለት እርዳታ እግሩ ድኖ በመሀከላችን ቆሞ የምስክርነት ቃል ሲሰጥ መስማት ከዚህ የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለ፡፡ በእኔ በኩል በስፖተኛ በኩል የነበረው ደስታ እንደዚህ በቃላት መግለጽ ያዳግታል የማይታመን ነበር፡፡ ግን በቦታው የነበሩ የማስሚዲያ ሰዎች ከኛ ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው ይህንን የምስክርነት ቃል በትክክል ለህዝቡ እንዲተላለፍ ባለማድረጋቸው በእኔ በኩል ትልቅ ቅሬታ አለኝ፡፡ ሌላው ግን ከአውሮፓም ከአሜሪካን የሄድን እጅግ ተደስተንና እረክተን ነው የተመለስነው፡፡

ጥያቄ፤ አንተ እንግዲህ አዲስ አበባ ብዙ ግዜ ትመላለሳለህ ከቀድሞ እግር ኳስና ከአሁኑ እግር ኳስ ጋር ስታወዳድር በክፍያም ይሁን በጨዋታ የትኛው የተሻለ ነው የኳሱስ እድገት እንዴት ነው፤ ዳዊት ጌታቸው፤ እውነቱ ለመናገር ቀደም ሲል የነበረውንና የአሁን ግዜ ማወዳደር ትንሽ ይከብዳል፤ የድሮ ኳስ በሁሉም ነገር የተሻለ ነበር፡፡ በጨዋታም ፊዚካልም ጥሩ ነበር፡፡ የአሁኑ ኳስ ግን ወርዷል የክፍያው ሁኔታው ግን በጣም በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ነው፡፡ ኳሱ ሊወርድ የቻለው በአዲስ አበባ ውስጥ የሜዳ ችግር አለ ይኸም አንዱ ምክንያት ነው፡፡ እንግዲህ ወደፊት በህጸናጽ ስልጠና ላይ ክለቦችም ሆነ ፌዴሬሽኑ ካተኮሩ እግር ኳስ የማይሻሻልበት ምክንያት የለም፤ ጥያቄ፤

በመጨረሻ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ፤ ዳዊት ጌታቸው፤ መቼም ይህ ማህበር ጠቃሚ ማህበር ነው፡፡ በተለይ ለእግር ኳስ ተጫዋቾች ከጨዋታ አለም ሲወጡ ምን እንደሚገጥማቸው ስለማያውቁ ይህ ማህበር ደግሞ ከጨዋታ አለም ሲገለሉ ችግር እንዳየደርስባቸው ምክር ከመስጠት አንስቶ እስከመርዳት ድረስ የሚያደርግ ስለሆነ ወደፊት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስተምር ስለሆነ ማንኛውም በመጫወት ላይ ያለም ሆነ ከጨዋታ ዓለም የተገለሉም የዚህ ማህበር አባል እንዲሆኑ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡


60 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከዳዊት አስመላሽ ጥያቄ፡ ይሄን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ጥሪያችንን አክብረህ በመምጣትህ በNASPASA ስም አመሰግንሃለሁ፤ ዳዊት፤ እኔም ለዚህ ቃለ መጠይቅ ስለጋበዛችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ፤ ጥያቄ፤

ስለትውልድ ቦታህና ስለ እግር ኳስ አጀማመርህ ብትገልጽልን፤ ዳዊት፤ ተወልጄ ያደግኩት አዲስ አበባ ጎላ ሚካኤል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ነው፤ እንደማንኛውም ታዳጊ ወጣት ሰፈር ውስጥ ካሉት ጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ እጫወት ነበር፤ ለየት ባለ ሁኔታ ለእግር ኳስ ትኩረት እሰጥ ስለነበር ለት/ቤቴ መጫወት ጀመርኩኝ በመቀጠልም ለቀበሌ ተመርጥኩኝ ከቀበሌ አስከትሎም ለከፍተኛ ከዚያም ለክለብ በመጫወት ነው የእግር ኳስ ዓለምን የተቀላቀልኩት፤ ጥያቄ፤ በልጅነትህ ዘመን ከስፖርት ጋር የነበረህ ትስስር ምን ይመስል ነበር፤ ዳዊት፤

ለምማርበት ት/ቤት እጫወት ነበር ከት/ቤት መልስ ደግሞ ጥናቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ ሰፈር ውስጥም እጫወት ነበር ይህንን ስል ገና የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ ህይወቴ በሙሉ ከእግር ኳስ ጋር የተያያዘ ነበር ማለት እችላለሁ፡፡ ጥያቄ፤ ኢትዮጵያ በነበርክበት ጊዜ ለየትኞቹ ክለቦች ተጫውተሃል፤ ዳዊት፤ በጊዜው በከፍተኛ ውስጥ በቀበሌዎች መካከል በሚደረገው ውድድር ላይ ተሰልፌ ሜክሲኮ ሜዳ እየተጫወትኩ ሳለ የምግብ ድርጅት ቡድን አሰልጣኝ ተስፋዬ ገብሩ ስጫወት ተመልክቶኝ ለምግብ ድርጅት እንድጫወት አደረገኝ በወቅቱ ምግብ ድርጅት ሜዳ ላይ መድን ቡድን ልምምድ ያደርግ ስለነበር የቡድኑ አሰልጣኝ መንግስቱ ወርቁ እኔንና መኮንን

ይመለከተንና የመድህን ቡድንን እንድንቀላቀል ያደርገናል፡፡ ከመድን በኋላ ለባህር ሃይል፤ ለአግሮ፤ ለምድር ጦርና ለአየር መንገድ ተጫውቻለሁ፤ ጥያቄ፤ ወደ አሜሪካ የመጣኸው መቼ ነው፤ የምትኖረውስ በየትኛው የአሜሪካ ግዛት ነው፤ ቤተሰብስ መስርተሃል፤ ዳዊት፤ ወደ አሜሪካ የመጣሁት እ.ኤ.አ. 2001 ላይ ሲሆን የምኖረው ዴንቨር ኮሎራዶ ነው፤ ቤተሰብን በሚመለከት ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነኝ


61 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ በአንድ ወቅት ቤተሰብ ጥያቄ ወደ ኢትዮጵያ በሄድክበት ወቅት በሰሜን አሜሪካና አዲስ አበባ ባለው ማህበር መካከል በተፈጠረው አለመግባባት አዲስ የስራ አመራር ኮሚቴ እንዲመረጥ በተወሰነው መሰረት በሰሜን አሜሪካውን ማህበር በመወከል በአስመራጭ ኮሚቴነት ሰርተሃል፤ እስኪ ስለነበረው ያለመግባባትና ስለምርጫው ግለጽልን፤ ዳዊት፤ እዚህ ላይ በቅድሚያ ስለማህበሩ ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ይህ ማህበር በሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ዋና ተግባሩ በማንኛውም የዓለማችን ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ኳስ ተጫዋቾችን መርዳትና ማገዝ ነው፤ ይህንንም ተግባራዊ በማድረግ ለበርካታ ተጫዋቾች እርዳታ አድርገናል፡፡ አሁን ወደ ዋናው ጥያቄ ልመለስና ሰሜን

አሜሪካ ያለው ኮሚቴ ወደ ኢትዮጵያ እንደምሄድ ያውቅ ስለነበር አዲስ አበባ ያለው ኮሚቴ ስራውን በተገቢው ሁኔታ ስላላከናወነ አዲስ ኮሚቴ እንዳስመርጥ ኃላፊነት ሰጠኝ፤ በዚህ መሰረት በሌላ አጋጣሚ ወደ ኢትዮጵያ በሰሜን አሜሪካ ሄደው ከነበሩ የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ኮሚቴ የአመራር አባላት መካከል ሸዋረጋ አሰፋ፤ ጌታ ዘሩ ተባሉትን አነጋገርናቸው በወቅቱም የአዲስ አበባው ኮሚቴ ስራውን በተገቢ ሁኔታ እንዳልሰራና ለሰራቸውም መልካም ስራዎች ምስጋና አቅርበን እነሱ ረጅም ጊዜ በመስራታቸው ጭምር አዲስ ኮሚ መቋቋም እንዳለበት ተማምነን አዲስ የሚቋቋመውን ኮሚቴም እንደሚረዱት ቃል ተገባብተን ተለያየን፤ ከዚህ በኋላ አዲስ ምርጫ ለማካሄድ በተጠራው ስብሰባ ላይ ሸዋረጋ ሳይገኝ ቀሪ ሌላ ስብሰባ እንዲጠራና ሸዋረጋም እንደሚገኝ ተስማምተን ከተለያየን በኋላ በሁለተኛውም ስብሰባ ላይ ሸዋረጋ አልተገኘም እንደማይገኝም አረጋግጦልን፤ በዚህ መሃል እኔ ወደ አሜሪካ መመለስ ስለነበረብኝ ምርጫውን ጌታ ዘሩ እና አሰፋ በተገኙበት ለማካሄድ ተገደድን፤ ቀስ በቀስ ግን ጌታ

ዘሩም በቀጣዮቹ ተግባራት ላይ ከመገኘት ወደ ኋላ ማለት ጀመረ ጭራሹም ሸዋረጋ ማህበሩ የኔ የግሌ ነው ማህተም አላስረክብም እስከማለት ደረሰ፤ እዚህ ላይ አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር በመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ሸዋረጋ አዲሱን ምርጫ እቀበላለሁ ሲል ከቆየ በላ ቃሉን በማጠፍ እንደግል ንብረቱ ማህተም አልሰጥም ብሎ በመጥፋቱ ብዙ ችግር ፈጥሮብናል፤ በዚህ አጋጣሚ ቃሉን በመጠበቅ እስከመጨረሻ ድረስ ያልተለየንን አሰፋን ማመስገን እወዳለሁ፡፡በአጠቃላይ በሸዋረጋ እምቢተኝነት ብዙ ከተጉላላንና ጊዜያችንን ካጠፋን በኋላ ንጉሴ ገብሬ፤ በሃብቱ፤ ጌቱ መልካ፤ ፍትሃነገስት በርሄ፤ አበበ ሽፈራው የአዲስ አበባው ኮሚቴ ሆነው ተመርጠዋል፤ እነሱም ስራቸውን በተገቢው ሁኔታና በታማኝነት እያከናወኑ ይገኛሉ፤ እነዚህን የኮሚቴ አባላት በዚህ አጋጣሚ ከልብ ለማመስገን እወዳለሁ፡፡ ጥያቄ፤ አሁን ደግሞ ወደ አውሮፓ ማህበር ልውሰድህና የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር እህት

ማህበር የሆነውን የአውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር እንዲመሰረት ካደረጉት መካከል አንዱ አንተ ነህ እስኪ ስለሁኔታው አብራራልን፤ ዳዊት፤ በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያን በየዓመቱ የእግር ኳስ ውድድር ያካሂዳሉ እኛም አንድ ቲም መስርተን ከሰሜን አሜሪካ እየሄድን እንጫወት ነበር፡፡ ይመስለኛል እ.ኤ.አ. በ2011 ላይ ጀርመን ኑረንበርግ ለሚደረገው ውድድር ለመሄድ ስንዘጋጅ እህት ማህበር መስርቼ እንድመጣ ሀላፊነት ተሰጠኝ አውሮፓ ውስጥ ብዙ የቀድሞ ተጫዋቾች ስላሉ በጠራነው ስብሰባ ላይ ወደ 60 የሚጠጉ የቀድሞ ተጫዋቾች ተገኝተው ማህበሩ እንዲመሰረት አደረግን፤ የአውሮፓው እህት ማህበር በአሁኑ ጊዜ ብዙ ተጫዋቾችን እየረዳ ሲሆን ለዚህም ከነሱ ምስጋና ተችሮናል፡፡


62 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በጋራ ከሰሜን አሜሪካው ማህበር ጋር በመሆንም አዲስ አበባ ላይ የገቢ ማሰባሰብ ፐሮግራም አካሂደናል፡፡ ጥያቄ፤ የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ከተመሰረተ ከስምንት ዓመት በላይ ሆኖታል፤ ይህ ማህበር የተነሳበትን ዓላማ በትክክል እያሳካ ነው ትላለል፤ ዳዊት፤ ማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማ በእግር ኳሱ መስክ ለአገራችን አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተው አሁን ግን በተለያዩ ምክንያቶች ችግር የገጠማቸውን መርዳት ነው፡፡ በዚህ በኩል ማህበሩ ለበርካቶች እርዳታ አድርጎአል ተገቢውንም ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ አሁንም እየሰጠ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ዓላማውን በትክክል እየፈጸመ ነው እላለሁ፡፡

ጥያቄ፤ በመጨረሻ ላይ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለ፤ ዳዊት፤ የኛ ማህበር የተመሰረተበት ዓላማ ግልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታ የሆኑ የተጎዱ ተጫዋቾችን መርዳት ብቻ ነው፡፡ ይህንን የማህበሩ አባላትም ሆኑ ሌሎች ሊገነዘቡት ይገባል ማህበሩ ሌላ ምንም ዓላማ የሌለውና ከማንም ያልወገነ ለበጎ ተግባር ብቻ የተቋቋመ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በመጨረሻም ይህንን ማህበር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የስራ ጊዜያቸውንና የቤተሰባቸውን ጊዜ መስዋዕት በማድረግ ሌተቀን በመስራት ላይ ያሉትን ሰባቱንም የኮሚቴ አባላት ሳላደንቅና ሳላመሰግን አላልፍም፡፡


63 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ቃለ ምልልስ ከታዬ ወ/ደረስ ጥያቄ፤ አቶ ታዬ ወግደረስ እንኳን ደህና መጡ እስቲ ለዚህ የመጀመሪያችን ለሆነው መጽሔታችን አንባቢዎች እራስዎን ቢያስተዋውቁልን፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ ታዬ ወግደረስ እባላለሁ ትውልዴም እድገቴም እንደሁም ት/ቤት የሄድኩም

እዛው አዲስ አበባ ‹‹›English School› የሚባለው ቀበና አካባቢ ነው፡፡ እዚሁ አሜሪካን አገርም እስክመጣም ድረስ ኑሮዬም ስራዬም እዛው አዲስ አበባ ከተማ ነበር፡፡ በትራንስፖርት ስራና እንዲሁም በግል ስራ እተዳደርኩ ነበር፡፡ እናንተን (የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች) እንድወድና እንዳውቃችሁ በጣም ያደረገኝ አንድም ጨዋታ ሳያመልጠኝ ስታዲየም በመግባትና ጨዋታውን በመከታተል ነበር፡፡ ነገር ግን እኔም ብሆን ከልጅነቴ ጀምሮ እግር ኳስን እወድና እጫወት ነበር፡፡ በተለይም ከቀበሌ አንስቶ እስከ ት/ቤት ድረስ የመጫወት እድሉን አግኝቼ ተጫውቻለው፡፡ እዚህም ከመጣሁ በኋላ በዲሲ ስታር ቡድን ተጫውቻለው፡፡ እንዲሁም ዩኒቲ የእግር ኳስ ቡድን እና በESFNA የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴነት ያገለገልኩ ሲሆን በተለይ እኔ በምወደው ስፖርት ውስጥ በማገልገሌ በጣም ከፍተኛደስታ ይሰማኛል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ስፖርቱንም ሆነ ይህንን ማህበር የምወድበት ምክንያት አዲስ አበባ

ስታዲየም ላይ በምትጫወቱበት ጊዜ የኢትዮጵያ ባንዲራ ስታውለበልቡት ትዝታዬ የሚጀምረው በሽቦው ውስጥ ሆኜ እናንተን እያየሁ እያደነቅሁ እንዲሁም አልፎ ተርፎ ባላችሁ ትርፍ ጊዜ ከናንተ ጋር በጓደኝነት በማሳለፍ እዛ ላይ ነው፡፡ ከስፖርተኛው ጋር እጅና ጓንት የሆንኩት በአዲስ አበባ ስታዲየም ያለፉትን እግር ኳስ ተጫዋቾች በወንድምነት በጓደኝነት አብሮ በመኖር በማህበራዊ ኑሮ አብሮ በማሳለፍ ህይወትን አብሮ መካፈልን በማድረግ አሁን እንዲዚሁ በመቀጠሌ ውስጤን ደስታ ይሰማኛል፡፡ በአጠቃላይ በህይወቴ ሁለት ፕሮፌሽናል ነገሮችን እወዳለሁ አንዱ እግር ኳስ ጨዋታን ሲሆን ሌላው ደግሞ አርቲስቶችን እወዳለው፡፡ ምክንያቱም ከሁለቱም ወገን የማገኘው ደስታ ወይም እርካታ ወደር የለውም እንዲሁም ከተለያዬ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር የማሳልፉት ደቂቃም ሆነ ሰዓታት ህይወቴ በሙሉ በደስታ የተሞላ ነበር፡፡ እዚህም ከመጣን በኋላ ይህንን የመሰለ ወደር የሌለው ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያዊ የሚያገናኝ ESFNA

መስርታችሁ እነሆ እዚህ ደርሰናል በጣም ላመሰግናቸው እወዳለው፡፡ ለቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋቾች ይሄ ነው የማይባል ምስጋና ለማቅረብ እወዳለው፡፡ ምክንያቱም ይሄንን ፌዴሬሽን ሲመሰርቱ ግሪን ካርድ ሳይኖራቸው አብዛኛው ወርክ ፐርሚት ሳይኖር እንደዛሬ አዲስ መኪና አውጥተህ እንደልብህ በማትጠቀምበት ጊዜ ጥቅምና ብር ሳያታልላቸው ኢትዮጵያዊነትን አስቀድመው ይህን ለፌዴሬሽን (ESFNA) መስርተው ለሁላችንም መሰብሰቢያ ሰጥተው አልፎ ተርፎ ደግሞ የኳስ ተጫዋቾች ማህበርን በመመስረት ጥርጊያ መንገዱን ለመክፈት የተቻለው በዚህ ፌዴሬሽን ምክንያት ስሆነ ሁላችንም እንደጃንጥላ ያቀፈና የሰበሰበን ስለሆነ ልንጠብቀውና ልንከባከበው ይገባል፡፡ ፌዴሬሽናችንንም ሆነ የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች የመረዳጃ ማህበር አሁንም ደከመን ሰለቸን ሳትሉ በዚሁ ቀጥለን ማጠናከር ይገባናል ባይ ነኝ፡፡


64 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ ብዙ ሰው ያው ከኳስ ተጫዋቹ ጋር ባለህ ጠንከር ያለ ጓደኝነት እዚህ አገር የመጣኸው ኳስ ለመጫወት ወደ ውጪ አገር ስትወጣ ጠፍተህ ነው የሚባል ወሬ አለ እስቲ ለአንባቢያን በምን ምክንያት እዚህ አገር እንደመጣህ አብራራላቸው ከመጣህም በኋላ ያስደሰቱህ ገጠመኞችህን ብትገልጽልን፡፡ ታዬ ወ/ደረስ፤ እኔ አሜሪካን አገር ለመምጣት ፍላጎቴ እየናረ የመጣው የልብ ጓደኞቼ የምላቸው እነ ሰብስቤ፤ ገብሩ፤ ከጠፉ በኋላ ነበር እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ኳስ ተጫዋች በጠፋ ቁጥር የኔም ልብ አብሮ ይጠፋ ነበር፡፡ ያ ህልም ነው ወደ አሜሪካን አገር እንድመጣ የገፋፋኝ፡፡ ግን ከዚህ ሁሉ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ያለኝ ከልብ የመነጨ ፍቅር እና አክብሮ እዚህ

አገር ስመጣ ምንም ነገር ሳይጎድልብኝ በተለይ ዲሲ አካባቢ ገብሩ፤ ሲራክ፤ እንትዬ፤ ሰለሞን ሽፈራው ከኔ ቀድመው መተው ስለነበረ በመስተንግዶ አንድም ነገር ሳይቸግረኝ አንድ ቋቋም ረድቶኛል፡፡ እንዲሁም ለኔ እስከዛሬ የማይረሳኝ በሽቦው ውስጥ ሆኜ ሳደንቃቸው የነበሩት ዛሬ ግን እዚህ አሜሪካን አገር ላይ አብሬ ልምምድ ማድረግና አብሮ መጫወት ምን ያህል ደስታ ስላገኘሁ እኔ እስከመቼም አልረሳውም እኔ ኢትዮጵያ አደርገው የነበረውን እነሱ እዚህ አርገው ጠበቁኝ በዚሀ አጋጣሚ ለኔ በጣም ባለውለታዎቼ ስሆኑ የዲሲ ስታር ቡድን ውስጥ የነበሩት በሙሉ በህይወቴ ብዙውን ነገር እንዲሳካልኝ በሩን የከፈቱልኝ እነሱ ስለነበሩ እኔም ከነሱ ሳልለይ እስከአሁን ያለሁትም ለዚህ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰብስቤ፤ እንትዬ፤ ሴኮ፤ ገብሩን እና አያያን በጣም ማመስገን እፈልጋለው፡፡ ጥያቄ፡

ከአገር ቤት ከመጣህ ጀምሮ ለአገሩ እንገዳ የሆኑትን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች የምታደርገው የነበረው እንክብካቤ ወደር የለውም ታዲያ ይህ ወደር የሌለው እንክብካቤህ by Nature ነው ወይስ ከእግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ባለህ ጠንካራ ጓደኝነት ነው፤ እንዲሁም ይህንን አንተ የምታደርገውን እንክብካቤ ማድረግ እየቻሉ ለማያደርጉት ምን መልእክት ማስተላለፍ ትፈልጋለህ፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ አንደኛ እንደዚህ ዓይነት እንክብካቤ ለቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋቾች ለማድረግ የገፋፋኝ ጥሩ ጎናቸውን እያወኩኝ ነው ከአገር ቤት የወጣሁት በኳስ ተጫዋችነታቸው ሳይጠገቡ፤ ሳይሰለቹ እንደተናፈቁ ነው የጠፉት እና ምንግዜም ቢሆን በግሩፕ ተጣብቀህ ለረጅም ጊዜ ከኖርክ ነው የምትሰላቸው፡፡ እነዚህ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ግን እዛ

በነበርንበት ሰዓት እንደልብ እንኳን አናገኛቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም 1ኛ በቀን ሁለቴ ልምምድ ይሰሩ ነበር፡፡ 2ኛ. ከወጡ እንኳን በጊዜ ወደ Soccer camp መግባት አለባቸው፡፡ 3ኛ. ከሴት ጋር እንኳን መታየት አይፈልጉም ነበር በጣም ቁጥጥር ይበዛባቸው ነበር፡፡ እኛ ለማለት የፈለኩት የኛ ግኑኝነት በርቀት ነበር፡፡ ብሔራዊ ቡድን ሲመረጡ ደግሞ ይባስ ቁጥጥሩ የበለጠ ነበር፡፡ እኛ ታዲያ የምናገኛቸው ለተወሰነ ሰዓታት ነበር፡፡ ስናገኛቸው ግን በደስታና በሳቅ ነበር የምናሳልፈው እዚህ አሜሪካን አገር ግን ለኔ ትልቁ አድቫንቴጅ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ላሊበላ ሬስቶረንስን ከፈትኩኝ፡፡ ስፖርተኛውን ቀን ከማታ ለማግኘት ቀላል ሆነልኝ፡፡ እኔም ከነሱ ጋር እምወደውን ኳስ እየተጫወትኩ በዙሪያዬም በጣም ጥሩ የሆኑ ጓደኞችንም አፈራሁ፡፡ ለምሳሌ አንድ የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች ቢመጣና እረዳታ ቢፈልግ ለኔ በታም ቀላል ነበር፡፡


65 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ምክንያቱም እነዚህ በዙሪያዬ ያሉት ደንበኞቼም ሆኑ ጓደኞቼ ለመርዳት ወደኋላ አይሉም ነበር፡፡ በተለይ ግን የልጆቼ እናት ሁሉም ነገር እንዳደርግ መቶ ፐርሰንት ፍቃዱዋን ጊዜዋን ሰጥታኝ እቤታችን ውስጥ የማሳድረውን ስፖርተኛ ማነው ሳትል ከጎኔ በመሆኑ ዘወትር ላመሰግናት እወዳለው እና እነዚህ ከላይ የገለጽኳቸው ነገሮች ሁሉ ተስማምረው እግዚአብሔር ያንን እድሉን ስለሰጠኝና ስለተመቻቸልኝ ይሄንን ነገር እንዳደርግ አስገድዶኛል፡፡ የሰጠኝ ልቦና አለ፤ ስፖርተኛወንም ስለምወድ መርዳት ደግሞ ላደርገው ችያለው ወደፊትም አደርጋለሁ፡፡ ጥያቄ፡ እንግዲህ ታዬ እንደሚታወቀው በዲሲና በ Virginia area ቁጥር አንድና ሁለት ላሊበላ ሬስቶራንስ እንዳለህ የሚታወቅ ቢሆንም ሌላ ነገር ደግሞ ልክ እንደስፖርተኞቹ ጨዋታ ትችላለህ፤ እንደውም ብዙዎቹ አንተ ምግብ ቤት

የሚመጡት ለመመገብ ብቻ ሳይሆን ያንተን ቀልድና ጨዋታም ለመስማት ነው ይባላል፤ ይሄ ምን ያል እውነት ነው፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ ለነገሩ እውነት ነው ያም የሆነበት ምክንያት እዛው የመጣሁበት ከተማም (አዲስ አበባ) እንዲሁም ከብዙ ቀልደኞችና ተጫዋቾች ጋር አሳልፍና እጫወት ነበር፡፡ እዚህም ቢሆን በጣም ቀልደኛ የሆኑ ጓደኞችም አሉኝ በዛ ላይ ብዙ በህይወቴ ያሳለፍኩዋቸውንና ገጠመኞቼን አንድ ላይ በማዋሀድ መሳቅና መጫወት እወድ ነበር፡፡ እነዚህን ገጠመኞችና ትዝታዎች ስላሉ እነሱን እያነሳን እንጨዋወታለን እና እነዚያ ትውስታዎችና ገጠመኞች ለኔም ጠቅሞኛል እና እጠቀምባቸው ነበር፡፡

ጥያቄ፤ አንተ በህይወቴህ በጣም አስገራሚና ገጠሞችህንና ወይም ከትዝታዎችህ አንዱን እንኳን ብታካፍለን፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ በመጀመሪያ እዚህ አሜሪካን አገር መጥቼ ድሮ የኢትየለጵያ ሰንደቅ አላማን የውለበለቡ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን አግኝቻቸው ከነሱ ጋር በዲሲ ስታር ቡድን አብሬ ማልያ ለብሼ ልምምድ እንዲሁም ማልያቸውን ለብሼ አብሮ ከጎናች ተሰልፌ የተጫወትኩበትን ቀን በህይወቴ እንደ ትልቅ ነገር ቆጥሬ ደስታን የሰጠኝ ቀን በመሆኑ አስታውሰዋለው፡፡ በህይወቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል በህይወቴ ጥሩ ትዝታን ጥሎብኝ አልፏል ብዬ አምናለው፡፡ ጥያቄ፤

ወደ ዲሲ፤ ቨርጂኒያ እና ማርግላንድ አካባቢ አንድ አባባል አለ አባባሉም የታዬን ቤት የወደደና ቆንጆን ሴት ልጅ የወደደ ቤቱ በጊዜ አይገባም፡፡ የሚባል ምን ያህል እውነት ነው፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ አንዴ የስራ ጸባዬ ነዋ እንዳሁኑ you tube ምናምን የለም ያለኝ እድል ቢዝነሴን ራን ለማድረግ የተለያዩ ቪዲዮ አጫውታለው የተለያዩ የሶከር ቦክስ ነበሩኝ የተለያዩ የእግር ኳስ ፊልሞችም ነበሩኝ፡፡ እንዲሁም የዘፈንና የቀልድ ቪዲዮዎችም እያመጣሁ አዝናናቸው ነበር፡፡ እንደዚህ እያደረግን እናነጋው ነበር፡፡ ለዛ ይሆና ይህን ስም የሰጡኝ እውነታቸውን ነው ታዬ ቤት ከገባን አንወጣም ብለው የማይመጡ ልጆች አሉ ከመጡ ግን አንግተው እንደሚሄዱ ስለሚያውቁ ምንም ሰዓት የለውም እውነት ነው፡፡


66 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ጥያቄ፤ እስቲ ወደ ማህበራችን ማለትም የእግር ኳስ ተጫዋቾችና የደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር ከቋቋሙት ሰዎች አንዱ ነህ እና ያለፈውን 8 ዓመት ስታየው ከረዳነው የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋቾችን፤ የተለያዩ የማህበሩን ስራዎችና አካሄዱ እና አሁን ያለበት ደረጃ ባንተ አስተያየት ምን ይመስልሃል፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ አዎን ይህንን ማህበር ካቋቋሙት ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡ እንግዲህ በአጠቃላይ ስታየው የማህበር ትንሽ የለውም የcommunity service ትንሽ የሚባል ነገር የለውም እንዲሁም የሰውን ልጅ መርዳት ትንሽ የለውም፡፡ ሰዓትህን ለበጎ አድራጎትነት መስዋት ትንሽ የለውም ምንም እንኳን አንድ ቋንቋ ብናወራም ላያግባባን የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ግን

ያንን ሁሉ ነገሮች እና እንቅፋቶችን አልፎ እዚህ ደረጃ ማድረግ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ይህ የመሰባሰቡ ሀሳብ ሲመጣ በርካታ ኳስ ተጫዋቾች ልክ እግር ኳሱን እንደሚወዱት ማህበራቸውን ወደው እኔም ስፖርቱንና ስፖርተኛውን እንደምወደው ማህበራችንን ወድጄው እነሆ በአንድት የቀድሞው ተጫዋቾችን በአሁኑ ሰዓት እርዳታ ወይም እገዛ የሚፈለጉትን እንዲሁም እዚህ አገር አድሉን ሳያገኙ ቀርተው በህመምና በችግር ላይ ያሉትን እየረዳ አርአያ ሆኖ መገኘቱ ከምንም በላይ የሆነ ማህበርበመሆኑ ያለኝ ደስታ ወደር የለውም ከዚህም በበለጠ መስራት ይቻላል፡፡ ወደፊትም በርካታአባላቶችን አቅፈን መጓዝ እንችላለን፡፡ በተለይም አደራ የምላችሁ የፈለገ እንቅፋት ነገሮች ቢያጋጥሙም ጠንካራ ሆኖ የመጣውን ነገሮች መጋፈጥ ነው፡፡ እንጂ አዳዲስ ነገር እየመጣ ከማህበረችን እንዳያለያየን መጠንከር ይኖርብናል፡፡ በተረፈ ይህ ማህበር ብዙ የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋቾችን በችግርና በህመም የሚማቅቁትን ለመርዳት ችሏል፡፡ ከዚህም የበለጠ ማድረግ ይቻላል ብዬ ነው የምገምተው፡፡

ጥያቄ፤ እንግዲህ ብዙ ነገሮችን ዳብሰናል አሁን ግን በስተመጨረሻ ለአንባቢያችን መግለጽ የምትፈልገው መልዕክት ካለህ እድሉን እሰጥሀለሁ፤ ታዬ ወ/ደረስ፤ በዚህ አጋጣሚ በበርካታ ውጣ ውረዶች ጊዜ አብረውኝ የነበሩት በላሊበላ ምግብ ቤት ዙሪያ እና በስፖርቱ መልክ በሚደረጉት በጎ አድራጎቶች በሙሉ አብረውኝ ለነበሩት እንዲሁም የዲሲ ስታር እግር ኳስ ክለብ እና በሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ አካባቢ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያ ጓደኞቼ በማደርገው ነገሮች በሙሉ ከጎኔ ባለመለየታችሁ እንዲሁም አዲስ ስፖርተኞች ሲመጡ አዲስ እንደመሆናቸው መጠን ለሚፈልጉት እርዳታ ከመኖሪያ ወረቀት እስከመኖሪያቸው ድረስ በመርዳት በመተባበር እንዲሁም አዲስ ለሚመጡትም እንደዚሁ እገዛ በማድረግ የገንዘብም ይሁን የሞራል በማድረግ

ከገኔ ላልተለዩኝ በሙሉ በጣም በጣም ላመሰግናቸው እወዳለው፡፡ ዲሲ፤ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ አካባቢ ያሉትን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ማመስገን እፈልጋለው፡፡


67 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

የሰለሞን አቀወ ምስክርነት እኔ ሰለሞን አወቀ ስፖርትን የጀመርኩት በአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ስፖርት ክለብ በሲ ቡድን ውስጥ ሲሆን በዚህ ቡድን ውስጥ ጥቂት ጊዜ ከተጫወትኩ በኋላ ወደ ዋና ቡድን ውስጥ በመግባት ከእንግዳ ወርቅ ሰበታ ጋር አብረን ከተጫወትን በኋላ እንግዳወርቅ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በመሄዱ እኔም መልቀቂያ ጠይቄ በመከልከሌ ለሁለት ዓመት ያህል ከኳስ ተገልዬ ከቆየሁ በኋላ መልቀቂያ ሲፈቀድልኝ ወደ እምወደው ኤሌትሪክ ክለብ ገብቼ ለሶስት ዓመት ያህል ከተጫወትኩ በኋላ የስራ ጥያቄ ባቀርብም ስራ ሊሰጡኝ ባለመቻላቸው ወደ ቀድሞ ክለቤ አንበሳ ክለብ ተመልሼ የስራ መደብ ተሰጥቶኝ ለክለቡ በመጫወት ላይ ሳለሁ ክለቦች ፈርሰው በአዲስ መልክ ሲቋቋሙ ወደፊት ለሚባለው ክለብ ስጫወት ቆይቻለሁ፡፡ በተለይም እነዚህ ክለቦች ፈርሰው አንበሳ እንደገና ተቋቁሞ ሃምሳ ክለቦች በተዋቀሩበት ሰዓት ከተጫወትኩ በኋላ ስፖርትን አቁሜአለሁ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ክለቦች ውስጥ ባሳለፍኩባቸው ጊዜያሮች በኢትዮጵያ ተስፋ ቡድን ተመርጬ ከብራዚል ኤቢሲ አባል ቡድን ከኤሌትሪክ ቡድን ጋር ወደ ናይጄሪያ በመሄድ ከናይጄሪያ ሬንጀርስ ቡድን ከምሶኮ ቡድን ጋር ተጫውቻለሁ፡፡ በተለያየ ጊዜ ለኢትዮጵያ ቡድን ተመርጫለሁ፡፡ ለአስረኛው የአፍሪካ ዋንጫ በህዝብና በጋዜጠኞች ሀይል እንድመረጥ ተደርጎ በማላውቀው ምክንያት በቂ ችሎታ እያለኝ ተቀንሻለሁ፡፡ በዚህ ተበሳጭቼ ከምወደው ስፖርትም ለመለየት በቅቼ ነበር፡፡ አሁን ከጊዜ በኋላ ግን በደረሰብኝ የስኳር ህመም በሁለቱም አይኔ ላይ ደም በመርጨቱ እይታዬን ስለከለከለኝ ከስራ ተገልዬ እቤት በመዋል ፈኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ጓደኞቼናቤተሰቦቼ በአደረጉት ጥረት ወደ ህንድ ሄጄ ህክምና እንዳገኝ ቢደረግም ውጤቱ ጥሩ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ይህን የሰሙ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር የ80000 (ሰማኒያ ሺህ ብር) እርዳታ ያደረጉልኝ ሲሆን ለዚህም አፋጣኝ መረባረብና የእርዳታ እጃችሁን ለእኔ እንደዘረጋችሁልኝ ልዑል እግዚአብሔር የማያልቀውን እድሜና ጤና እንዲሰጣች ከልቤ እየተመኘሁ የቀድሞ ተጫዋች በመሆኔም ኮርቻለሁ ኮርቼባችኋለሁም፡፡

የሰለሞን ወ/አማኑኤል ምስክርነት እኔ ሰለሞን ወ/አማኑኤል /በሶ/ የተባልኩኝ በዚሁ በአዲስ አበባ ተወልጄ ያደጉ ሲሆን በእግር ኳስ ተጨዋችነት ለአግሮ፤ ለባንክ፤ ለኦሜድላ፤ ለአየር መንገድ፤ ለእርሻ፤ ለኒያላ፤ ለመሳሰሉት ክለቦች በተጨዋችነት ያገለገልኩ ሲሆን፡፡ ጉልበቴ ላይ በደረሰብኝ ከፍተኛ ጉዳት ከእግሬም አልፎ

በህይወቴ ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችል የነበረ ሲሆ የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ተጨዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር የእኔን መጎዳት ከሰማ ጀምሮ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ለህክም ከ100000 (መቶ ሺህ ብር) በላይ ወጪ በማድረግና በማሳከም እግሬንና ለአንድ የሰው ልጅ ክቡር የሆነው ህይወቴንም ጭምር በማዳን እድሜ ልኬን ሰርቼ የማልከፍለው ውለታ ማህበሩ ሰርቶልኛል፡፡ በአሁን ሰዓት በተሻለ የጤንነት ሁኔታ ላይ የምገኝ ሲሆን ትንሽ ተንቀሳቅሼ ልጆቼን ለማሳደግ እየጣርኩ በመሆኑ በእኔ መዳን ውስጥ ለተሳተፉ በሙሉ አንድ ሚሊዮን ጊዜ ላመሰግን እወዳለው ውለታችን እግዜር ይክፈላች የናንተው ውድም ሰለሞን ገ/አማኑኤል (በሶ)፡፡


68 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አዘጋጁ፡ የትውልድ ስፍራ ንጉሴ፡

በቀበናና በአዋሬ ማዕከል ልዩ ስሙ ኮሚኒቲ ሜዳ አካባቢ ነው፤

አዘጋጁ፡ የቤተሰብ ሁኔታህ እናት አባት ንጉሴ፡

አባቴ አቶ ግብሬ ቱሉ እናቴ ወ/ሮ ፋንታዬ ቶላ ይባላሉ፡፡

አዘጋጁ፡ መቼና የት ተወለድክ፤ ንጉሴ፡

በ1947 ዓ.ም. ነው የተወለድኩት፤

አዘጋጁ፡ ሌላ ወንድምና እህት አለህ፤ ንጉሴ፡

አሉኝ ለመዘርዘር ጊዜህን ካወሰድኩ፤

ንጉሤ ገብሬ

አዘጋጁ፡ የትምህርት ሁኔታ እንዴት ነው 1ኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ንጉሴ፡

1ኛ ደረጃ ትምህርቴን የተመረኩት ኮከበአጽብሀ የቀድሞው ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው 2ኛ ደረጃ እስከ 10ኛ ክፍል እዛው ቀጥዬ በኋላ የቀድሞው አስፋው ወሰን ኮፕሬሲቪ ነው የጨረስኩት፤

አዘጋጁ፡ ከስፖርት ጋር በተያያዙ የልጅነት አስተዳደግህ እንዴት ነበር፡፡ ንጉሴ፡

እንደማንኛውም ልጅ በሰፈር ውስጥ በጨርቅ ኳስ በመጫወት

አዘጋጁ፡ ከአብሮ አደግ ጓደኞችህ ቅርብ የምትለው፤

ንጉሴ፡

ሁሉም የሰፈር ልጆች ጓደኞቼ ነበሩ አንዱን ጠርቼ አንዱን መተው ይከብደኛል እንዳለዘርዝር ደግሞ ብዙናቸው፡፡

አዘጋጅ፡ ከናንተ ሰፈር ካንተ ሌላ ታዋቂ ተጫዋች የሆነ አለ፤ ንጉሴ፡

አለ ሰብስቤ አሰፋ፤ የቀድው የአየር መንገድ ተጫዋች ገብዬ የአሁኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ወንድም እንዳርጋቸው ሳህሉ የቡናው ጳውሎስ ጌታቸው /ማንጎ/ የኤሌክትሪኩ አበበ ሽፈራው የመኪራያው አበበ ጌታቸው የቅ/ጊዮጊስ ሰለሞን መንገሻ ባዩ ሙሉ የረሳሁት ካለ ይቅርታ፤

አዘጋጅ፡

በትምህርት ቤት የነበረህ የስፖርት ተሳትፎ ምን ይመስል ነበር፡፡

ንጉሴ፡

ድሮ ትምህርት ቤት ውስጥ ስፖርት በጣም ጥሩ ቢሆን ሁኔታ ነበር የሚሰጠው በመሆኑም በስፖርት ክ/ጊዜ ከመሰል ጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ፤ ባስኬት ቦል፤ ቮሊቮል፤ ሩጫ እና የመሳሰሉትን ስፖርቶች እንሰራ ነበር ጅምናስቲክም ነበረው አንተ ለመጫወት ብለህ የምትሰራው ስራ ማርክስላለው ያስደስት ነበር፡፡

አዘጋጁ፡

የመጫወቻ ኳስ ትጥቅ ከየት ታገኙ ነበር፤

ንጉሴ፡

ትምህርት ቤት ውስጥ ኳስ አለ ከዛውጭ ግን ቅድም እንደነገርኩህ የጨርቅ ኳስ በካልሲ አድርገን እንሰራለን እኔ የምሰራው ኳስ ልነግርህ አልችልም ከዛ በተረፈ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በ1 ብር የሚሸጥ ኳስ እንገዛለን የፕላስቲክ ኳስ ነው በሱ ከተጫወትክ ትልቁ ኳስ ላይ አትቸገርም ምክንያቱም ላስቲኩ በጣም ይነጥራል ትንሽ ስትመታው ይበራል፤ እሱን ተቆጣጥረህ መጫወት ከቻልክ ትልቁን መቆጣጠር አይቸግርም ሌላ ትጥቅ ላልከው ትምህርት ቤቤት በምትሄድበት ዩኒፎርምና ጫማ ነው የምትጫወተው ሌላ ትጥቅ የለም፡፡


69 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

አዘጋጁ፡

አንዴት ነው ሁሉንም ስፖርት ጠርተህ ዋና አላልክም የቀበና ልጅ ሆነህ አልዋኘህም፡፡

ንጉሴ፡

ያውም እንደ አሳነዋ የምዋኘው ከኳስ ጨዋታ በኋላ የምንታጠበውም የምንዋኘውም ቀበና ነው ውሃው ኩልል ያለ ነበር ጆሻኒ ባህር፤ ሰው በሌባ ህር ወደላይ ደግሞ ንሰሳ ባህር የሚባሉ ነበሩ፡፡ የጸሐዬ ዮሐንስን ዘፈን ማለትም ወንዜ ቀበና የሚለውን ሰምተህው ከሆነ በሙሉ ያነሳቸዋል እንደውም በዘፈኑ ክሊፕ ውስጥ የኔስም አለበት የአንድ ሰፈር ልጆች ነን፤

አዘጋጁ፡

አዋሬ ቀበና ዘፋኝም አለዋ፡፡

ንጉሴ፡

በደንብ ጸሐይዬ ብቻ አይደለም አረጋህኝ ወራሽም ወደኛው ነው፡፡

አዘጋጁ፡

በመጀመሪያ በፌዴሬሽን የተመዘገበ ቡድን የተጫወትከው ክለብ፤

ንጉሴ

በራሪ ኮከብ

አዘጋጁ

እንዴት ልትገባ ቻልክ

ንጉሴ

በወቅቱ አቶ ኃይለስላሴ ወርቄ የሚባል የኮከበጽባህ ት/ቤት የስፖርት አስተማሪዬ ነበር እሱ የቡድኑ ግብ ጠባቂ ስለነበር እሱ ነው የወሰደኝ እንደገባሁም በቡድኑ ውስጥ ቋሚ ተሰላፊ ሆንኩ፤

አዘጋጁ

በምን ቦታ ነበር የምትጫወተው፤

ንጉሴ

በመጀመሪያ በክንፍ በሰባት ቁጥር ነበር በኋላ ማህልገብቼ በአካፋፋይ ቦታ ስድስት ቁጥር ዘጠኝ ቁጥር ተጫወትኩ፤

አዘጋጁ

በራሪ ኮከብ ስንት ዓመት ተጫወትክ

ንጉሴ

ሁለት ዓመት ብቻ ነው የተጫወትኩት ከዛ በኋላ ወደ ኦሜድላ ቡድን ሄድኩ፤

አዘጋጅ

ኦሜድላ የፖሊስ ቡድን ነው እንዴት ገባህ ፖሊስ ሆነህ ነው፤

ንጉሴ

ኦሜድ ውስጥ በሲቪልም መጫወት ትችላለህ እኔም እስከመጨረሻው ሲቪል ነበርኩ፤

አዘጋጁ

በኦሜድላ ውስጥ የነበረህ ቆይታ እንዴት ነበር፤

ንጉሴ

በጣም አስደሳች ነበር፤

አዘጋጁ

ግን በጣም ብዙ ቡድኖች እያሉ እንዴት ኦሜድላ ገባህ

ንጉሴ

ኦሜድላ የገባሁት በአቶ መስገን ገ/እግዚአብሔር አማካይነት ነው አቶ ይመስገን የበራሪ ኮከብን ቡድን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ ነበር በወቅቱ በራሪ ኮከብ ውስጥ በተፈጠረው ችግር እሱ ወጥቶ ነበር በዚህ ላይ ጓደኞቹ እነኮረኔል ተስፋ እነኮረኔል ለገሰ ተገኝ ነበሩ እሱ ከዛ ሲለቅ በቀጥታ ወደ ኦሜድላ ቡድን እንድመጣ አደሪገኝ፤

አዘጋጅ

ግን ይህ ብቻ አይደለም ከአቶ ይመስገን ጋር ቤተሰብናችሁ ይባላል፡፡

ንጉሴ

ትክክል ነው አቶ ይመስገን ገ/እግዚአብሔር ከወለዳቸው ልጆቹ እኩል ነበር የሚያየኝ እንደውም የሆነ ወቅት ከቤቴወጥቼ እሱጋ እንድኖር ሁሉ አድርጎኝ ነበር ሆኖ ከቤተሰብ ርቄ መኖር በተለይ ከናቴ መለየቴን አለመፈለጌን ሲረዳ እዛው እናቴ ቤት አጠገብ ሁለት ክፍል ቤት እንደሰራ ረድቶኝ ወደ ቤት ተመልሼ ገባሁ፤

አዘጋ

አልተቀየመህም

ንጉሴ

ሃሳቤ ስለገባውና ለጥሩ ነገር መሆኑን ስለተረዳ አልተቀየመም

አዘጋጅ

ሌላ ከአቶ ይመስገን ጋር የማትረሳው ትዝታ አለህ፤


70 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ንጉሴ

ቅድም እንደነገርኩህ አቶ ይመስገን ከልጅነት ጀምሮ ሲረዳኝና ሲያግዘኝ የኖረ ሰው ነው አልፎ ተርፎም ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ከአሁኗ ባለቤቴ ጋር ትዳር እንድመሰርት ያደረገ ትልቅ አባቴ ነው ሰርግ ደግሶ ነው የዳረኝ ነፍሱን በገነት ያኑረው፡፡

አዘጋጁ

ሰርግህ እንኳን እዚህ አሜሪካን ሃገር ያሉ ጓደኞችም አሉበት ይባላል፡፡

ንጉሴ

አልተሳሳትክም በዚህ አጋጣሚ በጣም አመሰግናቸዋላሁ ገንዘብ አዋጥተው ልከውልኝ ነበር፡፡

አዘጋጅ

በኦሜድላ ውስጥ የምትጫወትበት ቦታ የት ነበር ማሊያህስ

ንጉሴ

የምለብሰው ማሊያ 10 ቁጥር ነበር የምጫወትበት ቦታ ግን እንደበራሪ ኮከቡ አልነበረም አጥቂ ቦታ ነበር፤

አዘጋጁ

በዛን ወቅት ከነበሩት ክለቦች ውስጥ ጥቀስልኝኝ

ንጉዜ

ቅ/ጊዮርጊስ፤ ኤሌክትሪክ፤ ቴሌ፤ ሀማሲን፤ እምባይሰራ፤ መቻል፤ ከድሬድዋ ባቡር፤ ኮተን፤ ሰሚንቶ የመሳሰሉ

ነበሩ፤ አዘጋጁ

ዳኝነት እንዴት ነበር ከዳኞቹ እነማን ታስታውሳለህ፤

ንጉሴ

ዳኝነት በጣም ነበር ተስፋጠቴ ገ/እየሱስ፤ አቶ አየ ተሰማ፤ በቀለ ኪዳኔ፤ ጌታቸው ገ/ማሪያም፤ ስለሺ ማደፍሮ፤ ጌታቸው ክቡር ዘበኛ የነበረው ኪነጥበቡ፤ ተድላ ተሰማ፤ መኮን አስረስ፤ ይሸበሩ ብሩ፤ ሸገናው ቱፋ፤ አለም ንጸብህ፤ ግርማ አሁን አሜሪካ የደረሱ አለም አሰፋ፤ ኢንስትራክተር ሽፈራው፤ እሸቱ ከሚል እስማኤል፤ ድሬደዋ ለማኩምሳሳ ከአስመራ የሚመጡ ጎበዝ ዳኞች ነበሩ ስማቸው ጠፋብኝ እነኚህ በሙሉ ኢንተርናሽናል ዳኞች ነበሩ፤

አዘጋጅ

ጨዋታ በምንመልክ ይካሄድ ነበር

ንጉሴ

የድሮው ውድድር መጀመሪያ በየክልሉ ይካሄድ ነበር

አዲስ አበባ የራሱን ድሬደዋ የራሱን አስመራ የራሱን 1ኛ 2ኛ የወጡት ቡድኖች ለኢትዮጵያ ሻምፒዮና አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ፤ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ይሆናል፡፡

ከዛም

ለአፍሪካ

ክለቦች

ሻምፒዮና

ይወዳደራል፡፡ አዘጋጅ

ከክፍለ ሃገር ክለቦች ጠንካሮቹ እነማን ነበሩ፤

ንጉሴ

ሁሉም ጠንካሮች ነበሩ በተለይ ከአስመራና ከድሬደዋ የሚመጡት ቡድኖች በጣም ጠንካራ ነበሩ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ብዙ ተጫዋች ይመረጥላቸው ነበር፤

አዘጋጅ

ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን ተመርጠህ የተሰለፍከው መቼ ነበር በምን ቦታ፤

ንጉሴ

የሚገርምህ ገና በራሪ ኮከብ ስጫወት ነው ለኢትዮጵያ ወጣት ቡድን የተመረጥኩት ከዛ በኋላ ኦሜድላ ገብቼ መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ የብሔራዊ ቡድንም ተጫዋች ነበርኩ፤

አዘጋጅ

ይህን የክልል ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን የመጫወትህ ሚስጥር ምንድን ነው፤

ንጉሴ

ዋናው ነገር ለስፖርቱ ያለኝ ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮ ነው ከአሰልጣኝ የሚሰጠኝን ትምህርት በደንብ ነው የሚደምጠው ተግባራዊ ለማድረግም እጥር ነበር በተለይ ራሴን ለስፖርቱ ዲሲፒሊን አስገዛ ነበር ከአሰልጣኞቹ ውጭ ይጠቅመኛል ብዬ የማስበውን ስራ ሁሉ እሰራ ነበር፡፡ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሆኜ እንኳን ከመደበኛው የልምምድ ፕሮግራም ውጭ የራሴ ፕሮግራም ነበረኝ ለብቼዬ እሰራ ነበር፡፡

አዘጋጅ

ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ቡድን ስትሰለፍ ከማን ጋር ተጫወትክ፤


71 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ንጉሴ

የመጀመሪያ ጨዋታ የተጫወትኩት ኡጋንዳ ካምፓላ ላይ ነው በቋሚ ተሰላፊነት የማህል ሜዳ ተጫዋች ሆኜ ነው፤

አዘጋጅ

ካንተ ጋር እነማን ነበሩ ታስታውሳለህህ

ንጉሴ

አዎን ጌታቸው ዱላ፤ ካሳሁን ተካ፤ አስራት ሀይሌ፤ ገዛሀኝ ማንያዘዋል፤ ሀይሉ ጎሹ፤ ክብሮም ተ/መድህን፤ አህመድ ቡከር እና የመሳሰሉት ናቸው ወቅቱ በጣም ስለራቀ ሁሉንም ማስታወስ ይከብደኛል፤

አዘጋጅ

በዛን ወቅት አሰልጣኝ ማን ነበር፤

ንጉሴ

ጀርመናዊው ሚስተር ፒተርሽንግተር ነበር ረዳቱ ደግሞ መንግስቱ ወርቁ ነው፡፡

አዘጋጅ

የአሰልጣኙ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር፤

ንጉሴ

የሚሰጠን ስልጠና ሳይንሳዊ ነው እንደነገርኩህ ዋናው አሰልጣኝ ጀርመናዊ ነበሩ ረዳቱም ጀርመን ሃገር ሄዶ ተምሮ የመጣ በመሆኑ ወቅቱ የሚፈቅደውን ስልጠና ሁሉ እናገኝ ነበር፡፡ በዚህ ላይ መንግስቱ ወርቁ

በጨዋታ ዘመኑ ምን ዓይነት ተጨዋች እንደነበር ይራወቃል፡፡ የኳስን ሚስጥር ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሁሉም ሰው እንደሱ እንዲሆንለት ይፈልጋል፤ ስለዚህ በደንብ እንሰራ ነበር፡፡ አዘጋጅ፤

አንድ ነገር ትዝ አለኝ ፒታር አበረታች መድሃኒት ይሰጣችሁ ነበር የሚል ነገር በሚዲያ ሰምቻለሁ ይህ እውነት ነው፤

ንጉሴ

እኔም እንዳንተው ሰምቻለሁ ይህ በጣም ውሸት ነው ይህ ሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ለማገዝ በእርዳታ የመጣ አሰልጣኝ ነው ግን በእሱም ሆነ በመንግስቱ ወርቁ ላይ ጥሩ አመለካከት ያልነበራቸው ሰዎች የፈጠሩት ተራ ወሬ ነው፡፡ ቦታዎችን በመቀያየር ያጫወተኝ ነበር እንዲውም አንድጊዜ ከቶጎ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስንጫወት በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ተከላካይ ነበርኩ በሁለተኛው 45 ደቂቃ ከተከላካያ ቦታ አንስቶ አጥቂ ቦታ እንድጫወት አድርጎኝ ሁለት ጎል አግብቼ ሁለት ለቦዶ አሸንፈን ወጣን እዚህ ላይ መረዳት የሚገባህ ነገር የመንግስቱን የአሰልጣኝነት ብቃት ነው፤ በዕለቱ ፊት የነበሩት ልጆች ግብማግባት አልቻሉም ይህንን የተረዳው አሰልጣኝ መንግስቱ ምን ቢያደርግ ግብ ማግኘት እንደሚችል በማወቁና እኔም በጭንቅላት የሚመቱ ኳሶች ላይ ጥሩ ስለነበርኩ ተጠቀመብኝ ስለዚህ የህዝቡም ደስታ ከመጠን ያለፈ ሆነ ጨዋታው እንዳለቀም ሰው ሁሉ ሜዳ ገብቶ አቅፎኝ በመጣል ይስመኝ ጀመር እዚህ ላይ የማልረሳው ነገር ቢኖር ከወደኩበት ስነሳ ልብሴ /ማሊያዬ/ ሽቶሽቶ ይላል የምንሴት ናት መጥታ የሳመችኝ ብዬ ገርሞኝ ቀና ስል የቀድሞው የኤሌክትሪክ ቡድን ደጋፊ ሼኪ አጠገቤ ቆመዋል ወዲያው ሽቶው የእሳች መሆኑን አውቄ ተረጋጋሁ፤

አዘጋጅ

ምነው ሴት ብትሆንስ

ንጉሴ

አይ ምንም አይደለም ግን በዛን ጊዜ ሴቶች ቡዙም ኳስ ሜዳ አይገቡም ስለዚህ ገርሞኝ ነው እንጂ እንደምንኛውም ኢትዮጵያዊ ተደስተው ሊስሙኝ ይችላሉ፤

አዘጋጅ

እስቲ የአፍሪካ ዋንጫ ትዝ ታዎችህን እናውራ እንዴት ነበር፤

ንጉሴ

በመጀመሪያ ተመርጬ የተጫወትኩት 10ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ነው እዚሁ አገራችን ላይ የተዘጋጀ ውድድር የተካፈሉት ሃገሮችም ግብጽ፤ ጊኒ፤ ታንዛያ፤ ሞሮኮ፤ ጋና የመሳሰሉ ቡድኖች ናቸው፡፡ የመጡት በመጨረሻ ጊኒና ሞሮኮ ለዋንጫ ቀርበው ሞሮኮ ዋንጫው ወሰደች፤

አዘጋጅ

ተሰልፈህ ትጫወት ነበር፤

ንጉሴ

በጣም የሚያሳዝነው ወደብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ስመጣ አካባቢ ኦሜድላ ከመኩሪያ ቡድን ጋር ሲጫወት ጉዳት ደርሶብኝ ነበር በዛ የተነሳ የተወሰኑትን ጨዋታዎች መጫወት አልቻልኩም በስተመጨረሻ እኔና


72 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

መሐመድ አሊ /ሽርዳድ/ ተቀይረን ገባን መሐመድ አንድ ግብ አገባ ህዝብ ከመጠን በላይ ተደሰተ እኔም በጣም የሚገርም ኳስ በጭንቅላት ገጭቼ ገባ ሲባል በረኛው መሬት ልሶ ማለት ይቻላል አወጣብኝ፤ ያንን ሳስበው ሁልጊዜ ይቆጨኛል ግን ምን ታደርገዋለህ እግር ኳስ ይሄው ነው፡፡ አዘጋጁ፤

በወቅቱ የኢትዮጵያ ቡድን ወደውጭ ሲሄድ ብዙ ልጆች አይመለሱም ነበር አንተ ግን ትመጣ ነበር ለምንድ ነው፤

ንጉሴ

1ኛ የነበተኝ የቤተሰብና የሃገር ፍቅር ከባድ ነበር ከአገር ወጥቼ ብቀር በተለይ እናቴ አንድ ነገር ትሆንብኛለች ብዬ ነበር የምሰጋው ስለዚህ ወጥቼ በሰላም እንደመለስ እናፍቃለሁ እንጂ ለመቅረት አስቤም አላውቅም፤

አዘጋጅ

አሁን ስታስበው ይቆጭሃል፤

ንጉሴ

ምንም አይቆጨኝም እግዚአብሔር የምት ብትሆን የድርሻህን አይከለክልህም ከምወዳት ባለቤቱና ከልጆቼ ጋር በሰላም በደስታ ከጓደኞቼ ጋር በሰላም ያኖረኛል ከዚህ በላይ ምን ያስፈልጋል ብለህ ነው፡፡ እኔ እኮ ለተከታታይ ለ16 ዓመታት ተጠባባቂ እንኳን ሳልሆን ለብሔራዊ ቡድን ተጫውቼ አገሬን በሚገባ አገልግያለሁ፤ ስለዚህ ደስተኛ ነኝ በዚህም እኮራለሁ፤

አዘጋጅ፤

መጫወት ካቆምክ በኋላ አሰልጣኝ ነው የሆንከው ስራውን እንዴት አገኘኸው፤

ንጉሴ

በመጀመሪያ አሰልጣኝ ለመሆን ሲጀመር ከታች ነው የጀመርኩ የመጀመሪያ ቡድን የኢትዮጵያ ሆቴል ቡድን ነው ሁለተኛ አደይ አበባ ፋብካን ቡድን አሰላጠንኩ ከዛ በኋላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሰራተኛ ቡድን ከዛ ደግሞ የሜታ ቢራን ቡድን እያልኩ ነው ወደ ምወደውና ለዕውቅና ወደ አበቃኝ ቡድን ወደ ኦሜድላ

አሰልጣኝነት የመጣሁት፤ አዘጋጅ

የአሰልጣኝነት ኮርስ ወስደህ ነበር፤

ንጉሴ

የአንደኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ኮርስ ወስጄ ነበር ከዛ በላይ ግን በበራሪ ኮከብ ከነ አቶ ዘገየ ጋር በኦሜድላ ከነ አቶ አለማየሁ /አሌኮ/ ጋር በብሔራዊ ቡድን ከነመንግስቱ ወርቁ ጋር በተጫዋችነት ስለቆየሁ በጣም አስቸጋሪ ነገር አልነበረም፤

አዘጋጅ፤

ከአቶ አለማየሁ ጋር እንዴት ነው ያላችሁ ግንኙነት፤

ንጉሴ

አሌኮ በጣም ጥሩ አሰልጣኝ ነው ትልቅ አቅም ነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ በፊዚካል ኮንዲሽን ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያምናል በመሆኑም የሚያሰራን ስራ አሁን ላለንበት ሁኔታ ሁሉ የጠቀመን ይመስለኛ፡፡ ወንድማዊ ምክሩና ግሰጻው ደግሞ ግሩም ነበር በዚህ ላይ ከነ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር አብሮ የሰራ

ሰውነት ምን ታወጣለታለህ፡፡ አዘጋጅ

ከአቶ ይድነቃቸው ጋር ምን ትዝታ አለህ፤

ንጉሴ

ጋሽ ይድነቃቸው ለኔ በጣም ጥሩና የሚወደኝ የሚያደንቀኝ ሰው ነበር የሚሰጠኝ ምክርና አስተያየት የሚደነቅ ነበር እኔም ለመፈጸም እጣጣር ስለነበር ይወደኛ፡፡

አዘጋጅ

ከአቶ ይድነቃቸው ተግባር የማትረሳው አለ


73 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ንጉሴ

የኢትዮጵያ ቡድን ጊኒን አሸንፈን በነበረበት ወቅት ወደ ሃገር ለመመለስ ከአይቮሪኮስት ነበር የምንነሳው በዛን ጊዜ አቶ ይድነቃቸው ለስብሰባ ሌላ አፍሪካ ሃገር ነበር ያለው ከዛ ተነስቶ አይቮሪኮስት በመድረስ በረታታንን አረሳም የመጣው ይህንን ለማድረግ ብቻ ስለነበር ሁላችንም ተደስተን ነበር፡፡ በተለይ ያኔ የማይረሳው ጊኒ ላይ ልምምድ ስንሰራ ጫማዬን አስቀምጬ ወሰዱብኝ የነበረኝ አንድ ጫማ ብቻ ስለሆነ በነጠላ ጫማ ነው የሄድኩት አስበው በብሔራዊ ቡድን የሚሰጥህ 0.40 ሳንቲም በቀን የኦሜድላ ደሞዝ 100 ብር ታክስ ሚቆረጥበት ከአገር ስትወጣ ደግሞ 5 ዶላር አለች ምንም አትገዛም ስዚህ ያለው አማራጭ ወደ አገር ተመልሶ ያችን ዘርዝሬ አንድ ጫማ እገዛለሁ ብዬ በነጠላ ጫማ ቀረሁ በዚህ ጊዜ ነው አቶ ይድቃቸው አይቶ አቶ ካሳ ገ/ጊዮርጊስን ጠርቶ አቶ ካሳ ንጉሴ ለምን በነጠላ ጫማ ሆነ ሲለው ጊኒ ላይ ጫዋውን ወሰዱበት ሲለው

ታዲያ ለሚቀጥለው ጨዋታ አትፈልገውም ብሎ ጠየቀው አቶ ካሳም ንጉሴ ከሌለማ ምኑን ቡድን ሆነ ብሎ እኔ ፊት መሰከረ እንግዲያው እዚህ ብዙ ተናካሽ ኢንስክቶች አሉ ቢነክሱት ለጨዋታ ስማይደርስልህ ቶሎ ወስደህ ጫማ ግዛለት ብሎ አዘዘው ከዛም ተያይዘን ገበያ ወጣን በየሱቁ ስንመርጥ አንድ ቡትስ ጫማ ላይ አይኔ አረፈ ዋጋው ሲጠየቅ 80 የአሜሪካን ዶላር ነው አቶ ካሳ በዋጋው መደንገጡ ያስታውቃል እንዳይተወው ታዟል ብቻ በመደጋገም ንጉሴ ይኔንን ወደኸዋል ይለኛል አዎን በጣም ነው የወደድኩት ስለው እንደገና ይጠይቀኛል እኔም ድርቅፈ ስላልኩ ተገዛልኝና በጫማ አገሬ ገባሁ ጫማው የፈረንሳይ ሃገር ስሪት ነበር አልረሳውም፡፡ አዘጋጅ

በርካታ ልጆች አይቮሪኮስት ላይ ቀሩ እንዴት ነበር፤

ንጉሴ

አዎን ሰባት ተጫዋቾች ቀሩ፤

አዘጋጅ

እነ ማን ነበሩ ታስታውሳቸዋለህ፤

ንጉሴ

አዎን ንጉሴ አስፋው፤ አፈወርቅ ጠናጋሻው፤ ግርማ ከበደ፤ አያሌው ሞገስ፤ ሸዋንግዛው ተረፈ፤ አቦነህ ማሞ፤ ዳዊት ኃ/አብ ነበሩ፤

አዘጋጅ

ሲጠፉ እንዴት ነበር ምን ተሰማችሁ፤

ንጉሴ

እኔ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሐዘን ነው የተሰማኝ የተመለስንበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሐዘን ቤት ነበር የሚመስለው ኢትዮጵያ ስንደርስ የነበረው ነገርማ ተወው አሸንፈን ስለነበር በጣም በርካታ ሰው ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ ነበር ከዚህ ውስጥ የጠፉት ተጫዋቾች ቤተሰቦችም ነበሩ፤ ብቻ ምን ልንገርህ ኤርፖርቱ በኡኡታ ታመሰ ለቅሶ በለቅሶ ሆነ የማይረሳ ትዝታ ነውው፡

አዘጋጅ

ለመሆኑ ስንት ሃገር ሄደሃል ከአውሮፓ ከአፍሪካ

ንጉሴ

አውሮፖን ጀርመንን ጨምረህ ብዙዎቹን አይቼአለሁ ካፍሪካ ደግሞ ያልሄድክበትን ብትጠይቀኝ ይሻል ነበር፡፡

አዘጋጅ

አሜሪካንስ

ንጉሴ

አሜሪካንን አይቻለሁ የሄድኩትም የሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባደረገልኝ ግብዣ ነው ውድድሩ የተደረገው ካናዳ ላይ ነበር ቪዛ አግኝቼ የሄድኩት እዛ ነበር ጨዋታው እንዳለቀ ግን የልጅነት ጓደኛዬ የላሊበላ ሆቴል ባለቤት ታዬ ወግደረስ ወደ አሜሪካ ይዞኝ ገባ ሌላው አውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ማህበር ግብዣ አድረጎልኝ ሆላንድ ሄጄ ነበር፡፡ በጣም የሚገርም ትዝታ ነው


74 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

ያለኝ እዛ ያሉት የቀድሞ ጓደኞቼ ያደረጉልን አቀባበልና መስተንግዶ በጣምፈ የሚገርም ነበር በህይወቴ መቼም አልረሳውም በዚህ አጋጣሚ በጣም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ አዘጋጅ

በዛ ያለህ ቆይታ እንዴት ነበር

ንጉሴ

በጣም ጥሩ ነበር የሚገርም ነው የቀድሞ ተጫዋቾች ጓደኞቼ በያሉበት ይጋብዘኝ ነበር፡፡ አለሜን ነው ያሳዩኝ በዚህ አጋጣሚ ሁሉንም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

አዘጋጅ

ከዚህ እንውጣና የብሐራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነህ ታውቃለህ፤

ንጉሴ

አዎን የዋናው ብሔራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኜ አውቃለሁ፤ ለወጣት ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ዋና አሰልጣኝኝ

አዘጋጅ

የማትረሳው ትዝታ አለህ

ንጉሴ

በ1991 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኜ የመጀመሪያ ጨዋታችንን ለማድረግ ወደ ግብጽ ተጉዘን በጨዋታው ላይ ጥሩ የነበረን ሲሆን ሁለት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ከሜዳ አስወጣብን በዚህ የተነሳ አምስት ጎል ገብቶብን ተመልሰን መጣን የመልሱ ጨዋታ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ነበር ተጫዋቹቼን በጥሩ ስነልቦና በማዘጋጀትና እኛም እዚህ ከአምስት ጎል በላይ አግብተን ማሸነፍ እንደምንችል ተማምነን ገብተን ጨዋታውን 5ለ0 በሆነ ውጤት አሸነፍን ውጤቱ እኩል ለኩል ስለሚያደርገን የግድ በሪጎሬ መለያየት ነበረብን በመሆኑም እኛ አንድ ስተን እነሱ ሁሉንም ስላአገቡ የአሸናፋችንን ሁኔታ ምንግዜም አልረሳውም፤

አዘጋጅ

አሁን ያለህ የአሰልጣኝነት ደረጃ ምንድነው፤

ንጉሴ

በአዲሱ የኳፍ የአሰልጣኞች ደረጃ አሰጣጥ ከሲ ላይሰንስ ጀምሮ ኮርሱ በአገር ውስጥ ሲሰጥ ተምሬ አሁን ኤ ላይሰንስ ወስጃለሁ ይህደግሞ ለፕሮፌሽናል አሰልጣኝነት አንድ ደረጃ የቀረው ነውው፡

አዘጋጅ

ከዛ በኋላ ብሔራዊ ቡድን አላሰለጠንክም፤

ንጉሴ

በተለያዩ ጊዜያት እየተጠራሁ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን አገልግያለሁ፤

አዘጋጅ

አሁን ያለህበት የኑሮ ሁኔታና የቤተሰብ ሁኔታታ

ንጉሴ

ከባለቤቴ ከወ/ሮ የትምወርቅ ጀጋማ ኬሎ ጋር በፍቅርና በደስታ ነው የምኖረው ባለቤቴ የጀኔራል ደጋማ ኬሎ ልጅ ናት ከባለቤቴ ሶስት ሴት ልጆች አሉኝ፤

አዘጋጅ

ስማቸው ይገርማል ይላሉ ማን ማን ናቸው፤

ንጉሴ

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ ንጉሴ ትባላለች የሃገር ፍቅር ምልክት ናት ንግስት ንጉሴ አንተ ተርጉመው፤ ፍቅር

ንጉሴ የሁላችንም የፍቅር ማሰሪያ ናት፤ አዘጋጅ

በትምህርት ላይ ናቸው፤

ንጉሴ

አዎን ሁለቱ የኮሌጅ ተማሪ ናቸው የመጨረሻዋ ደግሞ የ9ነኛ ክፍል ተማሪ ናት፤

አዘጋጅ

አሁን ያለህ የስራ ሁኔታ

ንጉሴ

በአሁን ጊዜ በላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለተቋቋመው የታዳጊዎች እግር ኳስ ቡድን በበላይነት እየሰራሁ ነው ወደፊት ለብሔራዊ ቡድንም ሆነ ለክለቦች ጠቃ የሆኑ ወጣቶችን ከትምህርታቸው በተጓደኝ ጥሩ ተጫዋች እንዲሆኑና እንዲጠቅሙ ታስቦ የተከፈተ ፕሮጀክት ነው አገር ወዳድ አይጠፋም ይህ ቡድን እንዲቋቋም በተለይ አቶ ጀማል አህመድ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡


75 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ላሰማናቸው እወዳለሁ የአገሪቱ እግር ኳስ እንዲያድግ ከሚጥሩ ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ አዘጋጅ

በናንተ ጊዜ ስለነበሩት ጋዜጠኞች የምትለው አለህህ

ንጉሴ

እኔ በምጫወትበት ወቅት የነበሩት ጋዜጠኞች ውስን ነበሩ ከነ አቶ ሰለሞን ተሰማ ጀምረህ እነ ይንበርበሩ ምትኬ፤ ጸጋ ቁምላቸው፤ ደምሴ ዳምጤ፤ ንጉሴ አክሊሉ፤ ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር፤ አቶ ነጋ ወ/ስላሴ፤ ታደሰ ሙሉነህ ነበሩ እንዳሁኑ ተክኖሎጂውም ባልረቀቀበት ጊዜ ነበር የሚሰሩት በዘገባ በኩል ግን በጣም ጥሩ ነበር ለህዝብ መድረስ የሚገባውን ሁሉ በወቅቱ እንዲርስ ይሰሩ ነበር፡፡ በተለይ በሐገር ውስጥ ውድድር በየቦታው ሁሉ እየተገኙ በመከታተል ነበር የሚዘግቡት፤

አዘጋጅ

በል ንጉሴ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ ይህና ሁን፤

ንጉዜ

በጣም አመሰግናለሁ አስታውሰህ ልትጠይቀኝ ስለመጣህ መልካም ጊዜ ይሁንልህ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፤


76 በሰሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾ ችና ደጋፊዎች መረዳጃ ማህበር

NAESPASA POBOX: 401551 Las Vegas, Nevada 89140 Email: naespasorgec@yahoogroves.com Graphics—Eskinderart(eskproducer@gmail.com/469-733-0116)

ዋጋ : $5


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.