ንጉሱ በማርቆስ ወንጌል ላይ የተመሰረተ Copyright © 2016 FL Media All rights reserved
ይህ እትም በ2016 ታተመ ጽሁፍ በሮስማሪ ኤንዳኮት ስእል በቴሪ ሊም እና ፀጋው ተስፋ አርት ዳይሬክተር አትላስ አሶሲዬትስ www.mediaserve.org Printed in China ISBN 978-1-906389-54-3 Amharic
ንጉሱ ሌላ መጽሐፍ ወይስ ሌላ ዓለም?
ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱንጉሱ ንጉሱንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ
ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ
ንጉሱ
ሰላም
ሰ
ላም ለእናንተ ይሁን። አንደ እርሱ ያለ ሌላ የሌለ አንድን ንጉሥ ማወቅ ትፈልጋላችሁ? እርሱ በአእምሮአችን ልናስበው በላይ የሆነ እውነተኛ ንጉሥ ነው። እንግዲያውስ በሕይወታችሁ ሊሆን ለሚችል ትልቅና እንግዳ ወደሆነ አዲስ ጉዞ ተዘጋጁ። ታሪኩ የሚጀምረው በመካከለኛው ምስራቅ በምትገኝ በአንዲት ትንሽ ሀገር ነው። ይህች ሀገር በዓለም ላይ ካሉት ህዝቦች ሁሉ ጨካኞች በነበሩት በሮማውያን ወታደሮች ትገዛ ነበር። ሮማውያን እስራኤል የምትባለውን ትንሽ ሀገር ለተወሰነ ጊዜ ወርረዋት ነበር። ሀሳባቸው ዓለምን በሙሉ ለመግዛት ነበር። በዚያን ጊዜ ግን እነርሱ ያላወቁት ለዓለም ከእነርሱ የላቀ ዓላማ የነበረው ሌላ ሰው ነበር።
ማንነው እርሱ?
የእግዚአብሔር እቅድ በጥንታዊ መጽሀፍት ተጽፎ ነበር። እግዚአብሔር ለዚህ እቅዱ ጊዜና ስፍራ መርጦ አንድ ታላቅ ንጉስ ወደ ምድር እያመጣ ነበር። ይህ የሆነው ታዲያ በዚያች ትንሽ ሀገር በእስራኤል ነበር። በሮማውያን ቀንበር ሥር ሁሉም ነገር ከባድ ነበር። ሮማውያን ወታደሮች ማንኛውንም ተቃውሞ በአስፈሪ ትጥቃቸው በጭካኔ ጸጥ ያደርጉት ነበር። የሮማውያን የጦር አለባበስ ጤነኛ ላይመስላችሁ ይችላል፤ የመጥምቁ ዮሐንስን ብነግራችሁስ ምን ትላላችሁ? መጥምቁ የሐንስ የሚባል በእግዚአብሔር የተላከ ሰው ነበር። መጥምቁ የሐንስ በምድረበዳ ይኖር ነበር። ሕዝቡን ማስተማር ሲጀምር ወሬው በሀገሪቱ ሁሉ ተስፋፋ። መጥምቁ ዮሐንስን ለማየት፥ የሚናገረውንም ለመስማት ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ወደ ዮርዳኖስ ይመጡ ነበር። መጥምቁ ዮሐንስ በምድረ በዳ የሚኖር ሰው ነበር፡ ልብሱም እንደሌሎቹ ሰዎች ሳይሆን በምድረበዳ የሚገኘው የግመል ፀጉር ነበር። ይበላ የነበረውን ደግሞ ብትሰሙ የበለጠ ትደነቃላችሁ።
እግዚአብሔር!
ምንድን ነው የሚበላው?
2
አንበጣና ማር። ለዚያውም የበረሀ!
ዋው! መጥምቁ የሐንስ ግን የእግዚአብሔርን እቅድ የሚያውቅ ሰው ነበር። ታላቁ ንጉስ እየመጣ መሆኑንም አውቆ ስለነበር፤ ለዚህ ሲል በምድረበዳ ሆኖ ሰዎች ሁሉ ይህን ታላቅ ንጉስ ለመቀበል እንዲዘጋጁ ያስተምራቸው ነበር።
ለምንድን ነው የሚዘጋጁት?
በ
ሮማውያን ግዛት ብዙ ባሪያዎች ነበሩ። እነዚህ ባሪያዎች የሚባሉት ሰዎች ግን በጦርነት የተማረኩ ሰዎች ሲሆኑ ለማረኳቸው ወታደሮች በነጻ የሚያገለግሉ ምርኮኞች ነበሩ። ዋናው ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ነጻ ነን ቢሉ፤ ቢያውቁትም ባያውቁትም ለሆነ ለአንድ ነገር ባሪያዎች ናቸው። አሁንም እንኳን እኛ እግዚአብሔር ለእኛ ብሎ ያዘጋጀው ማዳን ቢያመልጠን የራሳችን ባሪያዎች ነን። ያ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያዘጋጀውን እቅዱን አልፈልግም ብንል ሀጢአት/ አመጽ ነው። እግዚአብሔር ግን እንዲሁ በጣም ስለሚወደን ለእኛ ያዘጋጀው መልካም ነገር ነው። መጥምቁ ዮሐንስ እግዚአብሔር ለህዝቡ ያዘጋጀው መልካም እቅድ እንዳለው ገብቶታል። ስለዚህ ሰዎችን ከሳቱበት በመመለስ ወደ እግዚአብሔር የልጁ መንግስት እንዲገቡ እግዚአብሔር የሚያድናቸውን የራሱን ልጅ እየሱስ የተባለውን እየላከ ነበር። ንጉሡን!
3
ዮሐንስ በምድረበዳ ለህዝቡ አንድ ልዩ የሆነ ሰው እየመጣ ነውና ተዘጋጁ ይላቸው ነበር። ከዚያ ፈቃደኛ በዮርዳኖሰ ወንዝ ውስጥ ተነክረው እንዲወጡ ያደርግ ነበር። ይህ ስርዓት ጥምቀት ይባላል። ሰዎች ሀጢአታቸው የበዛባቸውና ሕይወታቸውም መልካም እንዳልሆነ አውቀው ለመንጻት ወደ ውሀው ይገባሉ። ከተጠመቁ በኋላ ነጽተው ይወጡ ነበር። ይህም በውሀው ስለታጠቡ ሳይሆን እግዚአብሔር ልባቸውን እንዳነጻላቸው በምሳሌው ስለሚያምኑ ነበር። ከዚህ የተነሳ ብዙ ህዝብ ከብዙ ከተሞች መጥምቁ የሐንስን ለማየትና ሰለሚመጣው ንጉስና ስለእርሱም መንግስት የሚናገረውን ለመስማት ይመጡ ነበር። የሐንስም ሕዝቡን “እናንተ ሰዎች ስሙ፤ ገና ምንም አላያችሁምና። እኔ ንጉሱ አይደለሁም። እናንተ የማታውቁት ንጉሱ ግን እየመጣ ነው። እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳን ማሰር የማይገባኝ የእርሱ መልእክተኛ ነኝ” ይላቸው ነበር። ከዚያም ንጉሱ ወደ ምድር መጣ። ንጉሡ መሆኑን ያወቀው መጥምቁ ዮሐንስ ብቻ ነበር።
ምክንያቱም ንጉሡ ሲመጣ በዚያን ጊዜ እንደነበሩት ነገስታት የንጉስ
ለምን?
ልብስ አልለበሰም። ነገር ግን እንደማንኛውም ተራ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው። ከዚያ ወደ መጥምቁ የሐንስ ሄዶ ለመጠመቅ ጠየቀው። ዮሐንስ ደነገጠ! ”እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባል እንጂ እንዴት አንተ በእኔ ትጠመቃለህ?” አለው። ንጉሡ ግን የግድ አለው።
ከዚያስ? ንጉሡ ወደ ውሀው በገባ ጊዜ ግን እንግዳ ነገር ሆነ። የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ወደ እርሱ መጣ፣ በእርሱም ላይ ተቀመጠ። ከዚያም ከሰማይ የእግዚአብሔር ድምጽ የምወደው ልጄ፣ በእርሱም ደስ የሚለኝ ይህ ነው” አለ።
4
እግዚአብሔር በእርግጥ ትልቅ ነው። እርሱ ህያው ሆኖ የሚኖር ነው። ታዲያ እግዚአብሔር በማይገባን መንገድ አንድ አምላክ ሆኖ በሶስትነት ተገልጧል፦ እግዚአብሄር አብ፣ እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እናም ግሩም የሆነው መንፈስ ቅዱስ። እንግዲህ ጌታ እየሱስ በተጠመቀ ጊዜ እግዚአብሔር አብ ድምጹን ያሰማ ነበር፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይጠመቅ ነበር፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም መጥቶ በእየሱስ ላይ አረፈ። ስለዚህ ሁሉም በዚያ ነበሩ፣ ሁልጊዜም በሶሰትነት ይኖራሉ።
የሚገርም ነው!
ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለሰዎች ሁሉ ሰለመንግስቱ መንገር ጀመረ። ሁሉ ነገር ግን እንዲሁ በቀላሉ አልመጣም። ምንም ንጉስ ቢሆንም ጥቂት ፈተናዎችን ማለፍ ነበረበት።
ምን ዓይነት ፈተናዎች?
ለንጉሱ የቀረበለት ፈተናዎች እናንተና እኔ ብንሆን ልናልፋቸው የማንችላቸው ነበሩ። ንጉሱ የሰይጣንን ፈተና ለማሸነፍ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ ሄደ። ምንም ምግብ አልያዘም ነበር። በዚያ የነበሩ ደግሞ የዱር አራዊት ብቻ ነበሩ። በዚያ በምድረ በዳም ለብዙ ቀናት ቆየ። እግዚአብሔር ንጉሱን ወደ ምድር እንደላከው ለመጥምቁ የሐንስ ነገረው። ስለዚህም ንጉሱ በምድር እንደነበረ ለህዝቡ ይሰብክ ነበር። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ንጉሱ መምጣቱን ያወቅ ነበር።
ማነው እርሱ?
የእግዚአብሔር ጠላት የሆነው ሰይጣን ነበር። ሰይጣን ዱሮ የሚያበራ የእግዚዘብሔር መልአክ ነበር። መላእክት የእግዚአብሔር ልዩ አገልጋዮችና መልእክተኞች ናቸው። ሰይጣን ግን የተሰጠውን ስራ ጠብቆ አልቆየም። ምክንያቱም ልክ እንደ እግዚአብሔር ሃያል መሆንን ስለ ፈለገ ነበር። ከዚህ የተነሳ በእግዚአብሔር ላይ አመጸ። እግዚአብሔርም ከነበረበት ከሰማይ አባረረው። የሰይጣን ተከታዮች የነበሩና አብረው ያመጹ መላእክትም ከእርሱ ጋር ተባረሩ። በሰይጣን ማታለል ሰዎች ሁሉ የሀጢአት ባሪያዎች ሆኑ። እግዚዘብሔር ደግሞ ለሰዎች ስላዘነ ከባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ወደደ። እስራኤላውያን በሮማውያን ቅኝ አገዛዝ ስር ነበሩ። የሃጢአት ባርነት ግን ከዚያም የከፋ ስለሆነ ከንጉሱ ሌላ ማንም ነጻ ሊያወጣ የማይቻለው ባርነት ነው። እግዚአብሔር ልጁን የላከው ለዚህ ነው፤ ሰውን ከዚህ የሃጢአት ባርነት ነጻ ለመውጣት።
ሰ
ይጣን ግን እግዚአብሔርን ስለሚጠላ ሰዎች ሁሉ የክፉ አስተሳሰብና የመጥፎ ባህሪ ባሪያዎች እንዲሆኑ ይፈልጋል። ሰይጣን ንጉሱንም ሳይቀር የእግዚአብሔርን ዕቅድ ትቶ የራሱን ሀሳብ ያደርግ ይሆናል ብሎ በምድረበዳ ፈተነው። ንጉሱ ግን እውነተኛ ነጻነትን ለማግኘት የሚቻለው እግዚአብሔርን ከሁሉ በፊት በማስቀደም፣ ለእግዚአብሔር እቅድ ቅድሚያ በመስጠትና ከእግዚዘብሔር ፈቃድ ቀጥሎ የሌሎችን ሰዎች ፍላጎት ከራስ ፈቃድ በማስቀደም መሆኑን ስለሚያውቅ ንጉሱ በጣም አስቸጋሪ የነበረውን የሰይጣንን ፈተና አሸነፈ።
ከዚያስ? 5
ሠ
ይጣንም በጣም ተቆጥቶ ንጉሡን ትቶ መጥምቁ የሐንስን ለመበቀል ሄደ።
እንዴት? በ
የሐንስ ትምህርት በጊዜው ከነበሩት ገዠዎች መካከል አንደኛውን ሄሮድስ አንቲጳስ የሚባለውን አስቆጣው። ይህ ሰው የወንድሙን ሚስት አግብቶ የማይፈቀድ ነገር አድርጎ ነበር። ዮሐንስ በእግዚአብሄር ፊት እንዲህ ማድረግ ትክክል አለመሆኑን ለሄሮድስ ነገረው ። የሄርዶስ ሚስት ግን በጣም ተቆጣች። መጥምቁ ዮሐንስን ለመበቀል በማሰብ ሴት ልጇ፣ ሶሎሜ፣ በሄሮድስ ፊት እንድትዘፍን አደረገች። ልክ የሄሮድስ ሚስት እንዳሰበቸው ሄሮድስ በልጇ ዳንስ ተማረከና “የምትፈልጊውን ሁሉ ለምኝኝ እሰጥሻለሁ“ አላት። ሰሎሜ ሮጣ እናቷን “ምን ልለምነው” ብላ ጠየቀቻት። እናትዋ አስቀድማ ያሰበችውን የሚዘገንን ነገር እንድትጠይቅ ነገረቻት። የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት ስጠኝ አለችው።
ምንድን ነው?
ትክክል አይደለም! ሄሮድስ ግን አደረገው?
አዎን! ሄሮድስ በእርግጥ አዘነ። ምክንያቱም ዮሐንስ እውነትን ሳይፈራ ቢናገርም የእግዚአብሔር ሰው እንደሆነ ስለሚያውቅ ያከብረው ነበር። ነገር ግን ሄሮድስ በህዝቡ ዘንድ ተወዳጅ ስላልነበረ በዚህም በዙሪያው በነበሩ ሰዎች ፊት ደካማ መስሎ መታየት አልፈለገም። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስን እንዲገድሉት አዘዘ ራሱንም አስቆርጦ ለሰሎሜ ሰጣት።
ትክክል አይደለም!
6
ደስ የሚለው ዜና ግን ንጉሱ በዚያ ዙሪያ ማስተማር ጀምሮ ነበር። ንጉሱ ተከታዮች ያስፈልጉታል፤ ስለዚህ የእርሱን መንገድ እየተማሩ የሚያደርጉ ተከታዮችን በጥንቃቄ መረጠ። በባህር ዳር ሲሄድ ሁለት ወንደማማቾችን ስሞኦንና እንድርያስ የሚባሉ አሣ አጥማጆችን አየ። ”ከእኔ ጋር ኑ“ በማለት ጠራቸውና “ሰዎችን እንዴት እንደምታመጡ አሳያችኋለሁ አላቸው።
እነርሱስ ተከተሉት?
አዎን ስምኦንና እንድርያስ መረቦቻቸውን ጥለው ንጉሱን ተከተሉት። ከዚያ ንጉሱ ሌሎች ሁለት ወንደማማቾችን ያዕቆብንና ዮሐንስን አገኘ። እነርሱንም እንደዚሁ “ኑ ተከተሉኝ” አላቸው። አባታቸውን፣ የዓሣ ማጥመድ ድርጅታቸውንም ሁሉ ትተው ተከተሉት።
ከዚያስ?
7
አያችሁ! ንጉስ የሆነ ሁሉ መንግስት አለው። ሰው ሁሉ በራሱ ህይወት ንጉስ እንደሆነ ይመስለዋል። ያላወቁት ነገር ቢኖር ሰዎች ሁሉ ባያውቁትም እንኳ ባሪያ መሆናቸውን ነው። እግዚአብሔር እየሱስን ወደ ምድር የላከው ለሰዎች ያዘጋጀውን መንግስት እንዲያሳያቸውና ሰዎች ሁሉ እርሱን በማገልገል ከሃጢአት ባርነት ነጻ እንዲያወጣቸው ነው።
ምን ማለት ነው? የእግዚአብሄር መንግሥት ስትመጣ ነገሮች መለወጥ ጀመሩ። ንጉሱ በዙሪያው የነበረውን ነገር ሁሉ መለወጥ ጀመረ። የታመሙ ሰዎችን ይፈውሳቸው ነበር። በንጉሱ ቃል የሰዎችን ህይወት ይለውጥ ነበር። ብዙ ሰዎች ግን ንጉሱ መምጣቱን አላወቁም። ንጉሱ መሆኑን ባያወቁም እያደረገ የነበረውን ግን ያስተውሉ ነበር። እየሱስ ቅፍርናሆም በምትባል ከተማ ነበር አይሁዳዊ ስለነበረ የአይሁድን ባህል ያከብር ነበር። በሳምንት አንድ ቀን ሰንበት በሚባለው ልዩ ቀን አይሁድ ሁሉ ወደ ምኩራብ ሄደው የእግዚአብሄርን ቃል ይሰሙ ነበር። እየሱስም ወደዚያው ሄዶ በዚያ የተገኙትን አይሁድ አስተማራቸው። በጣም የሚያስደንቅ መምህር ነበር። እየሱስ እንዳስተማረው ያለ ትምህርት ከዚያ በፊት ማንም ሰምቶ አያውቅም። ንጉስ ስለሆነ የሚያስተምረው በሙሉ ስልጣን ነበር።. እየሱስ ንጉስ ስለሆነ መንግስቱን ይዞ ነበር የመጣው። ይህ ደግሞ ርኩሳን መናፍስትን እናወጣቸው። እነዚህ ርኩሳን መናፍስት ሰውን ሁሉ ያውኩ የነበሩ መናፍስት ናቸው። የሚገርመው ደግሞ ተራ ሰዎች እየሱስ ማን እንደሆነ ሳያውቁት አነዚህ ርኩሳን መናፍስት ግን አውቀውታል። በዚያ በምኩራብ ሲያስተምር አንድ ርኩስ መንፈስ “ልታጠፋን መጣህን፥ አንተ ከእግዚአብሔር የተላክኸው ቅዱሱ ነህ“ ብሎ ጮኸ።
ይገርማል? ከዚያ ቀጥሎስ ምን ሆነ? 8
ከዚያ ግን አንድ የሚያስደንቅ ነገር ሆነ። ክፉው መንፈስ ሰውየውን መሬት ላይ ጣለውና ለቆት ሄደ። ምክንያቱም ንጉሱ መጥቷል፤ የእግዚአብሔር መንግስትም መጥታለች። ስለዚህ ክፉ መናፍስት መሸሽ ነበረባችው። እየሱስ የሚያስደንቅ መምህር ብቻ አልነበረም፤ ርኩሳን መናፍስት እንኳ በፊቱ መቆም የማይችሉ ታላቅ ንጉስ ነው።
እየሱስ ሌላስ ምን አደረገ? እየሱስ ብዙ ሰዎችን ፈውሷል። ከአይሁድ ምኩራብ ሲወጣ እየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ፣ ወደ ስምኦንና ወደ እንድሪያስ ቤት ሄደ። የስምኦን አማት ደግሞ በትኩሳት ታሞ ተኝታ ነበር። እየሱስ ወደ እርሷ ቀርቦ ሰዎች ሁሉ የሆነውን ሲሰሙ ጸሐይ ስትገባ ብዙ ህዝብ እጇን ያዛት። እርሷም ወዲያውኑ ዳነችና በቤቱ ዙሪያ ተሰበሰቡ። ብዙ የታመሙ ሰዎች በርኩሳን ተነሳች፣ ጤነኛ ከመሆኗም የተነሳ ለሁሉም መናፍስት የሚስቃዩ ሁሉ መጡ።. ምግብ አዘጋጀችላቸው።.
በጣም የሚደንቅ ነው!
እየሱስ ታዲያ ምን አደረገላቸው?
9
እየሱስ ሁሉንም ፈወሳቸው። በማግስቱ ግን ገና ፀሐይ ስትወጣ ተነሳና ሊፀልይ ፀጥ ወዳለቦታ ሄደ።
ምን ማለት ነው? እየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው አባቱን በጣም ይወዳል ስለዚህ ከአባቱ ጋር ብዙ ጊዜ ያሳልፍ ነበር እየተነጋገረ ብቻውን የሚሆንበት ጊዜ ጸሎት ይባላል።
አይደለም እየሱስ የሚሰራው ሥራ ነበረው
እየሱስ በቅፍርናሆም ነው የኖረው?
ለተከታዮች ወደሌላ ስፍራ ደግሞ እንሂድ መንግስትን ወደዚያ ሥፍራ ላመጣ ይገባኛል የመጣሁት ለዚህ ነውና ብሎቸዋል እርሱም ተከታዮቹን አስከትሎ በየምኩራኑ እያስተማረና በሸተኞችን እየፈወሰ ይጎዝ ነበር አንድ ጊዜ ለምጻም የሆነ ሰው በእየሱስ ፊት ተንበረከከና ችንዲፈውሰው ለመነው በዚያን ዘመን ለምጻም የሆኑ ሰዎች ከጤነኛ ሰዎች ጋር ለመኖር አይፈቀድላቸውም ነበር ምክንያቱም ለምጻን ይስፋፋል ስለሚባል ነበር እየሱስ ግን ሰውየውን ፈወሰውና መፈወሱን አንዲመሰክርና ወደ ህብረተሰቡ ለመመለስ እንዲችል ራሱን ጌዶ ለካህኑ እንዲያስይ ነገረው፡ይህ ሰው ታዲያ በመንገድ ላይ ለማንም እንዳይናገር ጌታ አዞት ነበር እርሱ ግን ጌታ ያደረገለትን ላገኘው ሰው ሁሉ እየተናገረ በዙሪያ ባሉ ከተሞች ሁሉ ዞረ። ከዚያ የተነሳ እጅግ ብዙ ሰዎች እየሱስን ለማየት ይሯሯጥ ነበር። ወደ አንድ ከተማ መጣ የሚል ወሬ ከተሰማ በአካባቢው ከሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሰዎች አለ ወደተባለበት ስፍራ በእግርና በጀልባ ይመጡ ነበር። እየሱስ ግን ከከተማዎች ወጣ ብሎ ይሄድ ነበር። አንድ ቀን ታዲያ ወደ ቅፍርናሆም መምጣቱ ተሰማ። ከዚያ ወደገባበት ቤት ሰዎች ሁሉ ተከትለው በመግባት ቤቱ በሰዎች ከመሞላቱ የተነሳ ምንም መፈናፈኛ አልነበረም።
10
አራት ሰዎች አንድ ሽባ በአልጋ ይዘው መጡ። እነዚህ ሰዎች ቦታ ያለመኖሩን ቢያውቁም በሽተኛውን ወደ እየሱስ ለማስገባት ቆረጡ። ከዚያ ወደቤቱ ጣራ ወጥተው የጣራውን ጡብ በማንሳት በሽተኛውን በገመድ ከጣራው ወደታች በእየሱስ ፊት አወረዱት። እየሱስም የሰዎችን እምነት አድንቆ በሽተኛውን “ሀጢአትህ ተሰረዘልህ” አለው።
የሚገርም ነው!
በ
ዚያ የነበሩትም አንዳንድ ሰዎች እንደናንተው ነበር ያጉረመረሙት። የአይሁድ ሀይማኖት መምህራንም በዚያ ሰለነበሩ ይህን ሲሰሙ እርስ በርሳቸው “ይህ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው፤ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሀጢያትን ይቅር ለማለት ማን ይችላል?” ተባባሉ። ለእስራኤላውያን እግዚአብሔርን መሳደብ ከሀጢአት ሁሉ የከፋ ወንጀል ነው። የእግዚአብሔርን ስም ማዋረድ ማንም አይሁዳዊ በሕይወቱ የሚፈራው ሀጢአት ነበር። ለዚህ ነው እየሱስ የእግዚአብሔር ስልጣን አለኝ ማለቱ ስለገባቸው ነበር እነዚያ የህይማኖት መሪዎች የተቆጡት።
እየሱስ ግን የሚሉትን ከሰማ በሁዋላ ”ይህ እንዴት እግዚአብሔርን መሳደብ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ሀጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል ከማለትና ተነሳና ሂድ ከማለት የትኛው ይቀላል?” አላቸው። ከዚያም ሀጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለኝ እንድታውቁ“ ብሎ ወደ በሽተኛው ዞረና በሽተኛውን ”ተነሣ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፤ ተፈውሰሃል“ አለው። ሰውዮውም ዘሎ ተነሳና አልጋውን ተሸክሞ በህዝቡ መካከል ሄደ።
ይገርማል! እርግጠኛ ነኝ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አይተው አያውቁም! 11
እውነት ነው። ጌታ እየሱስ ከሀይማኖት መሪዎች ጋር የነበረው አለመግባባት ግን እየከፋ ሄዶ ነበር። አንድ ቀን ማቴዎስ የሚባል ግብር ሰብሳቢ (ቀራጭ) አገኘ። እየሱስም ”ና ተከተለኝ“ አለው ማቴዎስም የግብር መሰብሰቢያውን ትቶ ተከተለው። በዚያኑ ቀን ማቴዎስ ለጌታ እየሱስና ለተከታዮቹ በቤቱ የእራት ግብዣ አዘጋጀላቸው።
ታዲያ ይህ የሀይማኖት መሪዎችን ለምን ያናድዳቸዋል?
በዚያ ግብዣ ላይ ሌሎች ሰዎችም ተገኝተው ነበር። አንዳንዶቹ ታዲያ ቀራጮችና በህዝቡ ዘንድም የሚጠሉ ሀጢአተኞች ነበሩ። እየሱስ በሚሄድበት ስፍራ ሁሉም ዓይነት ሰዎች በዙሪያው ይሰበሰቡ ነበር። የእግዚአብሔር መንግስት ለሰዎች ሁሉ ክፍት ነው፣ ንጉሱን እስከተቀበሉ ድረስ። ይህ ግን የሀይማኖት ሰዎችን በተለይ ፈሪሳውያንን የሚያስቆጣ ነበር። ”እየሱስ ለምንድን ነው ከእንደነዚህ ዓይነት ሀጢያተኞች ጋር የሚበላው?” እያሉ ደቀ መዛሙርቱን ይጠይቁ ነበር። ጥያቄአቸውን ሲሰማ “ሀኪም የሚያስፈልጋቸው በሽተኞች እንጂ ጤናማ ሰዎች አይደሉም። እኔ የመጣሁትም ለዚህ ነው፤ መልካም ነን የሚሉትን ሳይሆን ሀጢአተኞችን ለማዳን መጥቻለሁና” አላቸው።
ፈሪሳዊ ምን ማለት ነው?
ፈሪሳውያን የተወሰኑ የሀይማኖት ህጎችን የሚከተሉ የአይሁድ የሀይማኖት ሰዎች ነበሩ። በህዝቡ መካከልም ህግን የሚጠብቁ ሰዎች መስለው ለመታየት ይወዳሉ። እየሱስ ግን የተወሰኑ ህጎችን መጠበቅ ሳይሆን እግዚአብሔርን መውደድና በሙሉ ልብ ማክበር ነው የሚበልጠው ይላቸው ነበር። ፈሪሳውያን ግን ይህን የእየሱስን ትምህርት አልወደዱትም ነበር ምክንያቱም ፈሪሳውያን ራሳቸውን ንጹሀንና ጻድቃን እያስመሰሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ግን የማይፈጹሙ ነበሩ።
ምን ማለት ነው?
12
እነዚህ ፈሪሳውያን ሰለመብል ሰለመጠጥ ሰለበዓላት የራሳቸው ህጎች ነበራቸው። የእየሱስ ተከታዮች ደግሞ እነዚህን የፈሪሳውያን ህጎች አይከተሉም ነበር። ስለዚህ ለእየሱስና ለተከታዮቹ ጥላቻ ነበራቸው። ይህንንም ጥላቻቸውን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይገለጹ ነበር።እየሱስም ጥላቻችውን ያውቅ ነበር፤ እርሱ የሰዎችን ሁል ልብ ያውቅ ነበርና።
ቆት ስር
“ከዚህ የተነሳ እነዚህን ፈሪሳውያን “እናንተ ግብዞች የእናንተ አምልኮ ማስመሰል ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ትታችሁ የራሳችሁን ህጎች አወጣችሁ። የሚቸገሩትን ወላጆቻችሁን ለእግዚአብሔር ከሰጠን እነርሱን ለመርዳት ግዴታ የለብንም እያላችሁ፤ የራሳችሁን ህጎች ታክብራላችሁ የእግዚአ|ብሔርን ትእዛዛት ግን ትሽራላችሁ። ግብዝነት ነው ብሏቸዋል።
ከባድ ቃል ነው! ህዝቡ እንዴት ወደደው?
ስድብ
ግድያ
ህዝቡ በጥንቃቄ ያደምጡት ነበር። እየሱስም በእግዚአብሔር መንግሥት የሚታሰበው የምትበሉትና የምትጠጡት ሳይሆን በቃላችሁ የምትናገሩትና የምታደርጉት ነው የሚቆጠረው አላቸው። ለተከታዮቹ እንዲህ በማለት አብራራላቸው፦ ”ህይወታችሁን የሚያቆሽሽ ከልባችሁ አስባችሁ የምታወጡትና የምታደርጉት ነገር ነው። የዝሙት ሀጢአት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ክፋት፣ ስስት፣ ጥላቻ፣ ሀሜት፣ ትእቢትና ሞኝነት ይወጣሉ። እነዚህ ሀጢአቶች የሚመነጩት ከውስጥ ከልብ እንጂ ከውጭ አይደለም።”
ኩራት
13
እየሱስ ንጉሱ ሰለሆነ ለህዝቡ በእርሱ መንግስት እንዴት መኖር እንዳለባቸው ያስተምር ነበር። አንተ ንጹህ ልብና ንጹህ ህይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ወደ እየሱስ መምጣት ያስፈልግሃል። እርሱ ብቻ ነው ልብህን ሊያነጻና ንጹህ ህይወት ሊሰጥህ የሚችለው እየሱስ ብቻ ነው። ለዚህ ነው የመጣው፦ አንተን ልብህን በመለወጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን እንድታገኝ። አንተ በራስህ ይህን ማድረግ አትችልም።ምክንያቱም የተወሰኑ ህጎችን ወይንም ሓይማኖትን በመከተል የሚገኝ አይደለምና። ፈርሳውያንና ሌሎች የሐይማኖት ሰዎች ታዲያ ይህን የእየሱስን ትምህርት መስማት አልፈለጉም። በዚህም ምክንያት እየሱስ በሚሄድበት ሁሉ እየተከተሉ የሚያስተምረውንና የሚያደርገውን ሁሉ ይቃወሙ ነበር።
ምን ማለት ነው?
ከፈርሳውያን ሕግ መካከል አንዱ በሰንበት ማረፍ አለብህ ይላል። ይህም ማለት በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትሠራም ማለት ነው። ለፈሪሳውያን ደግሞ ሥራ ማለት በጣም ሰፊ ነገር ነው። በአንድ የሰንበት ቀን ታዲያ እየሱስ በምኩራብ ነበር። በዚያም አንደ እጁ ሽባ የሆነ ሰው ነበር። በዚያ ሥፍራ ፈሪሳውያንም ነበሩና እየሱስ ምን ያደርግ ይሆን ብለው እንደሚጠባበቁት አውቆ ራሳቸውን በህጋቸው ያዛቸው። እነዚህን ፈሪሳውያንን ጠራና “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ?” ሲል ጠየቃቸው። ነገር ግን አንዳቸውም አልመለሱለትም። ከዚያም ወደ ሰውየው ዞሮ ”እጅህን ዘርጋት“ አለው ሰውየውም እጁን ዘረጋት ወዲያውኑ ተፈወሰ።
14
ዋው! እንዴት ደስ ይላል!
አውነት ነው። ፈሪሳውያን ግን በጣም ስለተናደዱ እየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ከሌሎች የሀይማኖት ግሩፖች ጋር ተመካከሩ። በጣም እየተናደዱበት ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ ብዙ ህዝብ ይከተለው ነበር። ከእስራኤል ከተማዎችና ገጠሮች ሁሉ ሰዎች እርሱን ለማየት ይመጡ ነበር። ንጉሱ መንግስቱን ይዞ መጥቶ ነበርና ስለዚህም እንደ ሀይማኖት መምህራን የህግ ዝርዝሮችን ሳይሆን ፈውስና ታእምራቶችን፣ ለታሰሩ ነጻነትን ለህዝቡ በነጻ ይሰጥ ነበር። የሚገርመው ነገር ደግሞ የእየሱስ የራሱ ቤተሰቦች ሳይቀሩ እየሱስ እያደረገና እያስተማረ የነበረውን ለመቀበል ተቸግረው ነበር። እየሱስ ግን ከሚከተለው ብዙ ህዝብ መካከል አስራ ሁለቱን ከእርሱ ጋር ሁልጊዜ አብረውት እንዲሆኑ አደረገ። በጥንቃዌ ያስተምራቸው ነበር ። በመንግስቱ እንዴት መኖር እንዳለናቸውና የመንግእቱንም ስራ እንዴት መስራት እንዳለባቸው አስተማራቸው። ከዚያ ስልጣኑን ሰጣቸው። እነዚህም የእየሱስ ደቀመዛሙርት ይባሉ ነበር። ትርጉሙም ተማሪዎች ማለት ነው።
እነማን ናቸው?
ዝርዝራቸው ከስምኦን ይጀምራል። (እየሱስ ግን ሰምኦንን ጴጥሮስ ብሎ ጠራው።) ዎስ ዮሐንስ በርተሎሚ ያስ ፊሊጶስ ር ድ ን ማ እ ቴ ዎስ ዕቆብ፣ ከዚ ያ ያ ሌላኛው ያዕቆብ ታዲዎስ ቀናተኛ ው ስምዖንና ቶማስ የአስቆሮቱ ይሁዳ (በሁዋላ እየሱስን አሳልፎ የሰጠው)
እነዚህ ደቀመዛሙርት የተማሩት ምንድነው?
ንጉሱ ትምህርት ብቻ ሳይሆን ማዳንንም ይዞ ነበር የመጣው። ሲያስተምር ህዝቡ በሚያውቋቸው ቀላል ምሳሌዎች ይጠቀም ስለነበር ሕዝቡ ምሳሌዎችን ስለሚያወቁ ይሰሙት ነበር። አንድ ቀን ዘር ሊዘራ ስለወጣ ገበሬ ምሳሌ እንዲህ ሲል አስተማራቸው፦ “ገበሬው ዘሩን በመሬት ላይ ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው ለቀሙት። ሌላውም ብዙ አፈር በሌላው ድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ። ዘሩም ወዲያው በቀለ። ነገር ግን ብዙ አፈር ስላልነበረው ፀሐይ በወጣ ጊዜ ደረቀ። አንዳንዱ ዘር ደግሞ እሾህ ባለበት መሬት ላይ ወደቀ። በበቀለ ጊዜ ግን እሾሁ አነቀውና ፍሬ ሊያፈራ አልቻለም። ጥቂት ዘር ግን በመልካምና ለም አፈር ላይ ወደቀ። እነዚህ ዘሮች ታዲያ መቶ ዕጥፍ ፍሬ አፈሩ።” አላቸው።
ታዲያ ይህ ምን ማለት ነው? 15
እየሱስ ይህን ምሳሌ ታዲያ ለአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ሲሆኑ አብራራላቸው።
“ገበሬው የእግዚአብሄርን መልእክት ለሰዎች ያመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያሳየው የእግዚአብሔርን መልእክት ሲሰሙ የማያስተውሉትን፣ ሰይጣን ወዲያውኑ መጥቶ የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው። ብዙ አፈር የሌለው ድንጋይማ መሬት ደግሞ፥ ቃሉን በደስታ የሚሰሙ ሰዎች ሲሆኑ ፤ ቃሉን ግን በደንብ ስለማያሰላስሉት ችግር በመጣ ጊዜ ወዲያውኑ ይደክማሉ። እሾሃማ መሬት ደግሞ የእግዚአብሄርን መልእክት ሰምተው የሚቀበሉት ሰዎች ይመስላል። እነዚህ ሰዎች ግን የኑሮ ጭንቀትና የዓለም ቁሳቁስ ሰለሚገዛቸው ፍሬ ሳያፈሩ ይቀራሉ። መልካምና ለም መሬት ደግሞ የእግዚአብሄርን መልእክት ሰምተው የሚቀበሉና ብዙ ፍሬ የሚያፈሩ አማኞችን ይመስላል።“
የሰናፍንጭ ቅንጣት ዘር
ከዚያ ቀጥሎ እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የእርሱ መንግስት እንደ ሰናፍጭ ፍሬ እንደምትመስል ያስተምራቸው ነበር።
በጣም ትንሽ ናት ማለት ነው?
አዎን ስትጀምር ትንሽ ናት። ነገር ግን እያደገች ትሄድና ትልቅ ዛፍ ትሆናለች። ትልቅ ዛፍ ለብዙ ወፎች መጠለያ እንደሚሆን በቅርንጫፎቹ ላይ ሁሉ ጎጆአቸውን እንደሚሰሩ እውነተኛ እምነትም እንደዚሁ ነው። ደቀ መዛሙርት ይህን ንጉሱ የነገራቸውን ምሰሌ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአይናቸው ፊት ተፈጽሞ አይተውታል።
አንድ ምሽት እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ጀልባዋ እንዲገቡና ባህሩን እንዲያቆርጡ ነገራቸው። በጣም ብዙ ህዝብ በዙሪያቸው ስለነበረ ትንሽ ጊዜ ለብቻው እንዲሆን ፈልጎ ምናልባትም ማረፍም ፈልጎ ሊሆን ይችላል። እርሱም አብሯቸው ወደ ጀልባዋ እንደገባ ከኋላ በኩል ትራስ ተንተርሶ ተኛ፣ አንቀላፋም።
16
ምንድን ነው ያዩት?
ነገር ግን ገና ብዙ ሳይጓዙ ሀይለኛ ማዕበል ተነሳ። ማእበሉ ሀይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ጀልባዋን በሀይል ይገፋት ነበር። ማእበሉ ውሃውን ወደ ጀልባዋ ያስገባው ነበር። እየሱስ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዝሙርቱ የመጨረሻ ሲጨነቁ እየጮሁ ቀሰቀሱት። “ጌታ ሆይ ልንጠፋ ነው እኮ” አሉት። እየሱስም ነቃና ወደ ባህሩና ወደ ንፋሱ ዞሮ “ጸጥ በል” ብሎ ጮሀ። ድንገትም ንፋሱ፣ ባህሩም ጸጥ አለ። ሁሉም ነገር ባንድ ጊዜ የሚያስፈራ ጸጥታ ሆነ።
ዋው!
“ከዚያ ግን እየሱስ ደቀመዛሙርቱን “ስለምን ትፈራላችሁ? እንዴትስ በእኔ ላይ አምነት የላችሁም“ አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም ”ማእበሉና ነፋሱ ሁሉ የሚታዘዙለት ይህ ሰው ማነው?” ተባባሉ። እየሱስ በእግዚአብሔር እንዲታመኑና በሌላ በምንም ነገር እንዳይጨነቁ እያስተማራቸው ነበር። አያችሁ እምነትን በራሳችሁ ማምጣት አትችሉም። የእግዚአብሔር ቃል እንደ ዘር ስለሆነ እምነትን ሊያመጣ ይችላል። ታምራትም ደግሞ |የሚሆነው እምነታችሁን በተግባር ስታውሉት ነው። እያኢሮስ የተባለው ሰው ይህ የእምነት ሥራ የገባው ሰው ነበር።
17
ኢያኢሮስ ማነው?
እያኢሮስ በጊዜው የተከበረ የአይሁድ ምኩራብ አለቃ ነበረ። ትንሿ ልጁ ደግሞ ታማ ልትሞት ቀርባ ነበር። ኢያኢሮስ ግን ልጁን እየሱስ ሊያድናት ይችላል ብሎ አመነ። ወዲያውኑ ወደ እየሱስ መጣና ”ልጄ ልትሞት ነው! እባክህ ናና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች“ በማለት ለመነው።
አብሮት ሄደ? አዎን፣ አየሱስ ከኢያኢሮስ ጋር ሄደ። ብዙ ህዝብም ተከትሎት ነበር። በህዝቡ መካከል ግን በህመም የተሰቃየች፤ ለ12 ዓመታት ያለማቋረጥ ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ነበረች። ከስቃይዋ የተነሳ ገንዘቧን ሁሉ ለሀኪምና ለመድሀኒት ብትጨርስም ምንም መፍትሄ አላገኘችም ነበር። ስለእየሱስ በሰማች ጊዜ ተስፋዋ እርሱ ብቻ እንደሆነ አመነች። ስለዚህ በህዝቡ መካከል እየተሸሎኮሎኮች ወደ እየሱስ ተጠጋች። በልቧም “የልብሱን ጫፍ እንኳ ብነካ እፈወሳለሁ” ብላ ታስብ ነበር።
አዎን። ከዚያም ቀስ ብላ የእየሱስን የልብስ ጫፍ ዳሰሰች። የሚፈሰው ደሟ ወዲያውኑ ቆመ። እንደተፈወሰችም አወቀች። እየሱስም የፈውስ ሀይል ከእርሱ እንደወጣ አውቆ ወደ ኋላ ዘወር ብሎ ”ልብሴን የዳሰሰ ማነው?” በማለት ጠየቀ። ደቀ መዛሙርቱም “ብዙ ህዝብ ከቦሃል እኮ እንዴትስ ማነው የነካኝ ትላለህ?” ብለው መለሱለት። እየሱስ ግን ቆሞ ይጠባበቅ ነበር። የተፈወሰችውም ሴት ከፍርሀቷ የተነሳ እየተንቀጠቀጠች በእየሱስ እግሮች ስር ወደቀቸና ምን እንዳደረገች ሁሉንም ነገረችው። እየሱስም ”ልጄ ሆይ እምነትሽ አድኖሻል። ተፈውሰሻል። በሰላም ሂጂ“ አላት።
18
እምነት እንዲህ ነው!
በ
ዚህ ጊዜ ግን ከኢያኢሮስ ቤት የተላኩ መልእክተኞች መጥተው ”ልጅህ በቃ ሞተች!“ አሉ።በዚህ ጊዜ ግን ከኢያኢሮስ ቤት የተላኩ መልእክተኞች መጥተው ”ልጅህ በቃ ሞተች!“ አሉ። እየሱስም ሰምቶ ኢያኢሮስን ”አይዞህ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ“ አለው። ከዚያ ህዝቡ እንዳይከተለው ከለከለ። ጴጥሮስን የእቆብንና የሐንስን ብቻ ይዞ ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሔደ። እየሱስም ሰምቶ ኢያኢሮስን ”አይዞህ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ“ አለው። ከዚያ ህዝቡ እንዳይከተለው ከለከለ። ጴጥሮስን የእቆብንና የሐንስን ብቻ ይዞ ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሔደ።
በኢያኢሮስ ቤት ብዙ ሰዎች ያለቅሱና ይጮሁ ነበር። እየሱስም “ለምን ታለቅሳላችሁ? ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። ሲያለቅሱ የነበሩት ሰዎች ሁሉ የእየሱስን ንግግር ሲሰሙ ይስቁ ጀመር። እርሱ ግን ሁሉንም አስወጣና የልጅቷን እናትና አባት ከደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ሶስቱን ብቻ ይዞ ልጅቷ ወዳለችበት ቤት ገባ። የልጁቷንም እጅ ይዞ ”አንቺ ብላቴና ተነሽ“ አላት። የሞተቸውም ብላቴና ወዲያውኑ ተነስታ ወዲያ ወዲህ ማለት ጀመረች። ወላጆቿ ቃላት እስከማይኖራቸው ድረስ እጅግ ተደነቁ። እርሱ ግን የሆነውን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸውና ለልጅቷ የምትበላውን ስጧት ብሎ ወጣ።
ልጅቷ ግን በእርግጥ ሞታ ነበር? አዎን በእርግጥ ሞታ ነበር።
እንዴት የሚደነቅ ታምር ነው! 19
አዎን። ይህ የመንግስቱ አንደኛው ሂደት ነው። አያችሁ! ፍርሀት የእምነት ተጻራሪ ነው። ፍርሀት ታአምራት እንዳይሆን ይከለክላል። ታዲያ መፍራት ስትጀምሩ ቶሎ ብላችሁ እምነታችሁን በንጉሱ ላይ ማድረግ ነው።
ስለዚህ በዚህ መንግስት ለህይወት የሚያስፈልገው እምነት ነው? አዎን። እየሱስ እንኳ በሚቃወሙትና በማያምኑ ሰዎች መካከል ብዙ ታእምራትን አያደርግም ነበር።
ይህ ምን ማለት ነው?
የኢያኢሮስን ልጅ ከሞት ካስነሳ በኋላ፣ እየሱስ
ወደደገባት ከተማ ወደ ናዝሬት ተመለሰ። በሰንበት ቀንም በዚያ በሚገኘው ምኩራብ ውስጥ ማስተማር ጀመረ። በዚያ የተገኙት ብዙዎች ግን ሲሰሙት ግራ ገባቸው። ይህ ሰው ይህን ሁሉ ጥበብና ሀይል፣ ይህን ሁሉ ታምራት ከወዴት አገኘው? ተባባሉ። ይህ አናጺው የዮሴፍና የማርያም ልጅ አይደለምን? ወንድሞቹና እህቶቹ በዚህ በእኛ መካከል አይደሉምን? እያሉ ሊያምኑበት አልቻሉም።
እየሱስ ለናዝሬት ሰዎች አንድ ነገር ነበር
ከዚያስ እየሱስ ምን አደረገ?
የነገራቸው፦ “ ነብይ በራሱ ከተማና በራሱ ዘመዶች ካልሆነ በስተቀር፣ በሁሉ ቦታ ይከበራል።” ባለማመናቸውም ምክንያት በጥቂቶች በሽተኞች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በስተቀር ምንም ታእምራት አላደረገም።
ከዚያስ ምን ሆነ?
እየሱስ ከዚያ ወጣና ደቀ መዛሙርቱን በእርሱ ስልጣን ላካቸው። ለመንገዳቸው ምንም ነገር እንዳይዙ አዘዛቸው። “መቀየሪያ ኮትም ሆነ ጫማ አትያዙ። በምትገቡበት መንደር ካልተቀበሏችሁ አትጨነቁ ነገር ግን የጫማችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ። ከባድ ፍርድ ይሆንባቸዋል።
ከባድ ነገር ነው!
አ
ዎ። የመንግስቱ ነገር ከባድ ጉዳይ ነው።
በ
ታዲያ ደቀ መዛሙርቱ ምን አደረጉ?
የሄዱበት ቦታ ሁሉ የመንግስቱን የምስራች ተናገሩ። ሰዎችን ሁሉ ከሀጢአት መንገዳቸው እንዲመለሱ፣ ንስሀ እንዲገቡ አሳስቡ። ብዙ በሽተኞችን ፈውሱ። አጋንንትም የነበሩባቸውን ሰዎች ነጻ አውጡ። ከዚያ በኋላ እየሱስ አማኞች ሁሉ እንዲህ እንዲያደርጉ አዝዟል።
አዎን። ነገር ግን ወዲያው
እውነት ነው?
አልነበረም፤ መቆየት ነበረበት። ምክንያቱም ከዚያ በሁዋላ ብዙ ነገሮች ተፈጸሙ። የታሪኩ ፍጻሜ በሚገርም ሁኔታ ስለሆነ እስኪ እንከታተለው። ደቀ መዛሙርት ከተላኩበት ሲመለሱ እየሱስ ትንሽ እንዲያርፉ በጀልባ ይዟቸው ሄደ። ነገር ግን ህዝቡ ስላዩአቸው በእግር ተከተላቸው። ከጀልባ ሲወርዱ ብዙ ሰዎች እየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በዚያ እንዳሉ ሰምተው እየተሯሯጡ ደረሱባቸው። እየሱስ ግን ልክ እረኛ እንደሌላቸው በጎች የጠፉና የሚያሳዝኑ እንደሆኑ ስለሚያውቅ አዘነላቸው። ተቀብሏቸውም ስለመንግስቱ ያስተምራቸው ነበር።
21
ከሰዓት በኋላ ግን እየመሸ መሆኑን ስላዩ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እየሱስ ቀርበው “ጊዜው እየመሸ ነውና ህዝቡን ወደ መንደሮች ሄደው የሚበላ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት። እየሱስ ግን እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው አላቸው።
እንዴት?
ደቀመዛሙርቱም እየሱስን እንዲህ ነበር የጠየቁት። ”ይህንን የሚያህል ህዝብ ለመመገብ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ያስፈልጋል“ አሉት።
“እየሱስ ግን ”ምን ያህል ምግብ አላቸሁ?” አላቸው። ሄዱና ያለውን ሁሉ ሰብስቡ፣ ያገኙት ግን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሳ ብቻ ነበር። እየሱስም ሁሉንም ሰው በሀምሳ በሀምሳና በመቶ በመቶ እንዲስቀምጡ አዘዛቸው።
ታዲያ ምን ሆነ?
እየሱስ የሰጡትን እንጀራና ዓሣውን ይዞ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም ቆረሰና ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀመዛሙርቱም ለህዝቡ አከፋፈሉ። አዎን። ምግቡ ግን ለሁሉም በቃቸው። ሁሉም ጠገቡ እንዲያውም የተረፈው ቁርስራሽ አስራ ሁለት መሶብ ሙሉ ሆነ። ሌላኛው ህይወት በመንግስቱ ውስጥ ይህን የሚመስል ነው። እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ በማንኛውም ነገር ስትታመኑ፣ እግዚአብሔር ያላችሁን ይባርክላችኋል፤ ለሚያስፈለጋችሁም ሁሉ ይበቃል። ለእግዚአብሄር የማይቻል ምንም ነገር የለም። እርሱ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው። እንደሰው በምድራዊ ህግ የተወሰነ አይደለም።
የሚበቃ ምግብ እኮ የላቸውም!
ከዚህ ቀጥሎ የሆነውን አንድ ሌላ ታሪክ ልንገራችሁ። እየሱስ ህዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ደቀ መዘሙርቱን በጀልባ ባህሩን እንዲሻገሩ አዘዛቸውና እርሱ ሊጸልይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ።
22
የሚገርም ነው!
ወደ ንጋቱ አካባቢ ደቀ መዛሙርቱ የሚያስጨንቅ ማዕበልና ነፋስ መጣባቸው። እየሱስ ጭንቀታቸውን ስላወቀ ከተራራው ወርዶ በባህሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ።
እንዴት? በባህር ላይ እየተራመደ?
አዎን በባህር ላይ እየተራመደ ነው የመጣው።
የማይሆን ነገር ነው! ደቀ መዛሙርቱ በአጠገባቸው በውሀ ላይ እየተራመደ ሲሄድ ስላዩት ሁሉም በፍርሃት ጮሁ። በፍርሀት የጮሁት እየሱስ ሳይሆን የሆነ ምትሀት ስለመሰላቸው ነበር። እየሱስ ግን “አይዞአችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው።
ታዲያ አመኑት? 23
ጴጥሮስ የሆነ ማስረጃ ፈለገ። ስለዚህ እየሱስን “አንተ ከሆንህ እኔም በውሃው ላይ እንድራመድ እዘዘኝ” አለው። እየሱስም “ና!” አለው። ጴጥሮስም ከጀልባው ወጥቶ በውሃው ላይ እየተራመደ ወደ እየሱስ ሄደ። ለጴጥሮስም በጣም የሚያስፈራ ነበር የሆነው። በውሃው ላይ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ዙሪያወን መመልከት ጀመረ። ማእበሉ በጣም ሀይለኛ ነበር። በእየሱስ ማመኑን ትቶ በፍርሀት ተሞላ ወዲያውኑም መስጠም ጀመረ። ጨርሶ ከመስጠሙ በፊት እየሱስ እጁን ዘረጋና አወጣው። እምነት የጎደለው በመሆኑ ግን ነቀፈው።
የሚያስፈራ ነገር ነው!
በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ እርስበርሳቸው ይህ እየሱስ በእርግጥ እርሱ ማን ነው? እያሉ እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ነበር። እየሱስ በሄደበት ቦታ ሁሉ የሚያገኛቸውን በሽተኞዎ ሁሉ ይፈውስ ነበር። ዲዳዎች፣ መስማት የተሳናቸው፣ ዓይነ ስውራንና ሽባዎች ሁሉ ይፈወሱ ነበር። ወደ እርሱ መጥቶ እየሱስ ሳይፈውሰው የቀረ በሽተኛ አልነበረም። ታዲያ አንድ ቀን እየሱስ ደቀመዛሙርቱን ሰዎች ማን ይሉኛል ሲል ጠየቃቸው። ደቀ መዛሙርቱም “አንደንዶቹ መጥምቁ የሐንስ ከሞት ተነስቶ ነው፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነው፣ የቀሩትም ከነብያት አንዱ ነው ይሉሃል” አሉት። ቀጥሎም “እናንተስ አኔን ማን ነው ትላላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስ ፈጠን ብሎ “አንተ መሲሁ ነህ” አለ።
ምን ምን ማለት ነው? ትርጉሙ “በእግዚአብሔር የተቀባው” ማለት ነው። የብሉይ ኪዳን በሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚታደግ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የነበረውን የተበላሸ ግንኙነት የሚያስተካክል ሰው እንደሚልክ ቃል ገብቶ ነበር።
24
ንጉሡ ነው?
አዎን። አንዳንዶቹ መሲህ ይሉታል፤ ግን ያው አንድ ሰው ነው። ጴጥሮስ ይህን ተስፋ ስለሚያውቅ ይህ እየሱስ እርሱ ነው ብሎ አምኗል። እየሱስ ግን “ለማንም አትናገር” አለው።
ለምን?
እየሱስ ከዚህ ቀጥሎ አስጨናቂ ሁኔታ እንደሚመጣ፣ በሀይማኖት መሪዎችና በካህናት፣ በብዙ ሰዎችም እንደሚጠላ አስቀድሞ ያውቅ ስለነበር ነው።
ብዙ መልካም ነገር አድርጎላቸው አልነበረም?
እውነት ነው። ነገር ግን የነገርኋችሁን የእግዚአብሔርን እቅድ አስታውሱ። የእርሱ እቅድ ደግሞ ነጻነት ማለት ነው። ታዲያ ለዚህ ነጻነት ዋጋ መከፈል አለበት። እየሱስ ይህን ሁሉ እቅድ ያውቃል ምክንያቱም ንጉሱ ነውና። እየሱስ ታዲያ ይህን የእግዚአብሔርን እቅድ ለደቀ መዛሙርቱ እስራኤላውያን የሃይማኖት መሪዎች አሳልፈው እንደሚሰጡት፣እንደሚገደልና በሶስተኛው ቀን ግን ከሞት እንደሚነሳ በየጊዜው ይነግራቸው ነበር።
ምን? ይህ ትክክል አይደለም!
ጴ
አይሆንም!
ጥሮስም እንደዚህ ነበር ያለው። ወደ እየሱስ ጠጋ ብሎ “ትክክል አይደለም! እንዲህ አይሆንብህም” አለው።
25
እየሱስ ግን ለምን ወደ ምድር እንደመጣ ያውቃል ስለዚህ ወደ ጴጥሮሰ ዘወር ብሎ “አንተ የምታስበው ስለ ምድራዊ ነገር ብቻ ነው እንጂ የእግዚአብሔርን እቅድ አይደለም በማለት ገሰጸው። ሁሉንም ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠራቸውና ”የእኔ ተከታዮች ልትሆኑ ከወደዳችሁ፣ የራሳችሁን የሥጋ ምኞታችሁን ረስታችሁ እኔን እለት እለት ተከተሉኝ። ከዚህ ውጭ ግን ራሳችሁ ነፍሳችሁን ልታድኑ ብትሞክሩ ታጠፏታላችሁ፤ ነገር ግን ነፍሳችሁን ስለእኔና ስለ መንግስቴ ስትሉ እስከሞት ብትሰጡ እውነተኛ ህይወት ታገኛለችሁ“ አላቸው። ከዚያ ቀጥሎ ግን ትልቅ ጥያቄ አቀረበላቸው፦ ”ዓለሙን በሙሉ ብታገኙ ነገር ግን በዚያ መንገድ ነፍሳችሁን ብታጠፉ ምን ይጠቅማችኋል? በእኔ የሚያፍር ሁሉ እኔ በአባቴ ክብር ከመልኣክት ጋር በምመለሰበት ጊዜ አfርበታለሁ” አላቸው።
በጣም ከባድ ነው ነገር ግን እውነት ይመስለኛል። አይደል?
አ
ዎን። እየሱስን መከተል ሁሉን ነገራችንን ይጠይቃል። ነገር ግን እውነተኛ ህይወት የማግኛው መንገድ ይህ ብቻ ነው። ከሳምንት በኋላ ደግሞ እየሱስ ጴጥርስን ያዕቆብንና የሐንስን ይዞ ወደ ተራራ ጫፍ ወጣ። ብቻቸውን ከእየሱስ ጋር እያሉ በጣም የሚያስደንቅ ነገር ሆነ። እየሱስ ከእነርሱ ጋር ቆሞ እያለ ፊቱ ተለወጠ፣ ልብሱም የሚያንጸባርቅ ነጭ ሆነ፣ ነጭነቱ ሰው የሚገምተው ዓይነት አልነበረም። ከዚያ ሌሎች ሁለት ሰዎች ኤልያስና ሙሴ አብረው ቆመው ታዮአቸው።
እነማን ናቸው? 26
በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔርን ያገለገሉና የእግዚአብሔር እቅድም የገባቸው ሰዎች ነበሩ። በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርት በታላቅ ፍርሃት ነበሩ። ከዚህ የተነሳ ጴጥሮሰ የሆነ ነገር መናገር ያለበት መሰለውና፦ “ጌታ ሆይ እዚህ መሆን ለእኛ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው። ስለዚህ እዚህ ሶስት ዳሶችን ለሶስታችሁ እንስራ” አለ። በእርግጥ የሚናገረው አያውቅም ነበር።
የሀይማኖት ነገር ነው?
አዎን። በመንግስቱ በንጉሡ ፊት ስትቆም፣ ቃላት ሀሳብህን ሊገልጽልህ አይችልም ።
ከዚያ ምን ሆኑ? እየሱስ በመጥምቁ የሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የሆነውን ታስታውሳላችሁ?
አዎን! ል
ክ ያንኑ የመሰለ ሁኔታ ነው የተደገመው። ከሰማይ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” የሚል ታላቅ ድምጽ መጣ።
እንዴት ይገርማል! ደ
ቀ መዛሙርቱም ይህን ሲሰሙ ቀና ብለው ተመለከቱ። ሁለቱ ሰዎች ሄደው እየሱስ ብቻውን ቆሞ ነበር። ከዚያ ሲነጋ ተራራውን መውረድ ጀመሩ። በዚህ ጊዜ እየሱስ ”አሁን ያያችሁትን ከሞት እስከምነሳ ድረስ ለማንም እንዳትናገሩ“ አላቸው።
ምን ማለቱ ነው?
27
ደቀ መዛሙርቱም ምን ማለቱ እንደሆነ ግራ ገብቶቸው ነበር። ነገር ግን ስለዚህ ነገር የሚያስቡበት ጊዜ አልነበራቸውም። ከተራራው ሥር እንደደረሱ እየሱስ ወደ ህዝቡ ቶሎ መድረስ ነበረበት።
ብዙ ህዝብ ተሰብስቦ ነበር። በዚያን ጊዜ ግን ደቀ
ለምን ይሆን?
መዛሙርቱ ነበሩ ከፈርሳውያንና ከሀይማኖት አስተማሪዎች ጋር እየተከራከሩ የነበሩት። እየሱስ “ምንድን ነው የሆናችሁት?” ሲል ጮሆ ጠየቃቸው። በዚያን ጊዜ አነድ ሰው ”ልጄን እንታድንልኝ እፈልጋለሁ። በአጋንንት ስለተያዘ መናገር አይችልም። ርኩስ መንፈስ በተነሳበት ጊዜ ወደ መሬት ይጥለዋል፣ አረፋ ያስደፍቀዋል፣ ጥርሱንም ያፎጫል። ደቀ መዛሙርትሀን እንዲያወጡት ጠየቅኋቸው። እነርሱ ግን ርኩሱን መንፈስ ሊያወጡ አልቻሉም“ አለው። እየሱስም ተቆጭቶ “እናንተ የማታምኑሰዎች፣ እስከመቸ ድረስ እታገሳችኋለሁ” አለና ልጁን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። ርኩሱ መንፈስም እየሱስን ባየው ጊዜ በሀይል ጣለው። ከዚያ ”ይህ ከያዘው ስንት ጊዜ ነው?“ ሲል አባቱን ጠየቀው። ”ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የያዘው። እባክህ! ቢቻልህ እርዳው” አለ። እየሱስ ግን “እንዴት ቢቻልህ ትላለህ? ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል” አለው። አባትየው ግን የጌታን ቃል ሰምቶ ወዲያውኑ “አምናለሁ። ነገር ግን እንዳልጠራጠር እርዳኝ” አለ። ከዚያ እየሱስ ርኩሱን መንፈስ ገሰጸው። ርኩሱ መንፈስም በሀይል ጮሆ ልጁን ጣለው። ከልጁም ወጣ። ልጁም እንደሞተ ሰው ጸጥ አለ። እየሱስ ግን እጁን ያዘው፤ ልጁም ተነሳ። ፈጽሞ ነጻ ወጥቶ ነበር።
28
“ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ሲሆኑ ወደ እየሱስ ቀረቡና “እኛ ልናስወጣው ያልቻልን ሰለምን ነው” ብለው ጠየቁት። እርሱም እንዲህ ዓይነቱ በጾምና በፀሎት ካልሆነ አይወጣም“ አላቸው። ከዚያም በዙሪያ ባለው ሀገር ሁሉ ይጎዝ ነበር። እየሱስ ብዙውን ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ብቻቸውን እንዲሆኑ ከህዝቡ ይርቅ ነበር።
ለምን ይሆን?
ምክንያቱም ከፊት ለፊት የሚጠብቀውን ያውቅ ነበርና ነው።
አይ ገና አንድ
ለምን ንጉሡ አይደለም እንዴ? ፈተናዎችን ሁሉ አሸንፏል። አይደል?
የመጨረሻ ፈተና ይቀራል። እጅግ የሚያስጨንቅ እግዚአብሔር ራሱ የላከው ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊያደርገው የማይችለው ፈተና ከፊቱ ነበር። እየሱስ ስለዚህ ፈተና ለደቀ መዛሙርቱ አስቀድሞ ነግሯቸዋል። “ለገዥዎች አሳልፈው ይሰጡኛል፤የገድሉኛልም፣ በሶስተኛው ቀን ግን ከሞት እነሳለሁ” እያለ ይነግራቸው ነበር።
ምንም እልገባኝም!
ደቀ መዛሙርቱም አልገባቸውም ነበር። ምን ማለቱ እንደሆነም ሊጠይቁት አልደፈሩም። ከዚያ ግን እርስበርሳቸው መከራከር ጀመሩ። በመንገድ ወደሚያርፉበት ቤት ሲሄዱ በመንግስቱ ከእነርሱ ማናቸው ትልቅ እንደሚሆን ይከራከሩ ነበር። እየሱስ ሰለምን ይከራከሩ እንደነበር ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ስለምን እንደተከራከሩ ለእርሱ ለመንገር ፈሩ። እየሱስ ግን ተቀመጠና ሁሉንም ወደ እርሱ እንዲመጡ ጠራቸው። ከዚያም እንዲህ አላቸው ፦ ”ስሙ በመንግሥቴ ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግ ሁሉ መጨረሻ ፣ የሁሉ አገልጋይ ይሁን።
29
ከዚያ ትንሽ ልጅ በአጠገቡ እንዲቆም አደረገና፤ እጁን ይዞ “ማንም ታናሽን ልጅ ሰለስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል።የላከኝን አባቴን ይቀበላል። ወደ መንግስቴ ለመገባት እንደ ልጅ መሆን አለባቸሁ” አላቸው። ቀጥሎ ግን ከባድን ማስጠንቀቂያ ነገራቸው፦ ”ከእነዚህ ትናንሽ ብላቴኖች አንዱን የሚያሰናክል ከባድ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ባህር ቢወረሰር ይሻለው ነበር” አለ።
ይህ ምን ማለት ነው? እየሱስ የሀጢአትን መራራነት በምሳሌ እያስረዳ ነበር። በህይወታችሁ ያለ ማንኛውንም ወደ መንግሥቱ እንዳትገቡ የሚከለክላችሁን መሰናክል ሁሉ ማስወገድ አለባችሁ። እየሱስ ደቀመዛሙርቱን እንደ ጨው መሆን እንዳለባቸው አስተምሮአቸዋል።
ለምን ጨው? ጨ
ው ምግብን ሳይባሽ ለማቆየት ያገለግላል ደግሞም ያጣፍጠዋል። ጨው ጣእሙን ቢያጣ መልሶ ጨው ማድረግ አይቻልም።
ገባኝ በመንግስቱ ከኖርህ ልክ እንደጨው ነህ ማለት ነው። ዓለም በሙሉ ጨርሶ እንዳይበሰብስ ትጠብቃለህ። 30
አዎን። እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሉሎችን በመርዳትና ወደ መንግሥቱም እንዲገቡ በማሰየት እንዴት መኖር እንዳለባቸው ይነግራቸው ነበር። እየሱስ ንጉሱ ስለሆነ ወደፊት የሚሆነውን ያውቃል። ቤተ መቅደሱ በእየሩሳሌም የነበረ እስራእላውያን ዋና ዋና የሀይማኖት ሥርዓቶችን የሚፈጽሙበት ግሩም ህንጻ ነበር። ቤተ መቅደሱ ወደፊት እንደሚወድም አስቀድሞ ተናግሯል። እየሱስ ጦርነቶችና የጦርነት ወሬዎች እንደሚመጡ ተናግሮል። ሐሰተኛ መሲሆችና ሀሰተኛ ንጉሶችም እንደሚመጡና ብዙዋችንም ወደ ጥፋት እንደሚወስዱ ተናግሯል። የምድር መናወጥና ረሀብ በብዙ ሀገር ይሆናል ብሏል። በብዙ ስፍራ የምድር መናወጥና ረሃብ እንደሚሆን ተናግሯል። ታዲያ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በጥንቃቄ መጠበቅ እንደሚገባ አስጠንቅቋ፦ “ይህ ሁሉ ግን መጀመሪያው ነው። ተጠንቀቁ! የእኔ ተከታዮች በመሆናችሁ ያስሯችኋል፤ ይከሷችኋል። ይህ ሁኔታ ግን ስለእኔ ለመናገር አጋጣሚ ይሆንላችኋል። ተከሳችሁ ስትቆሙ ግን ምን መልስ ልስጥ ብላችሁ አትጨነቁ። እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ቃል ዝም ብላችሁ ተናገሩ። ጊዜው በጣም አስጨናቂ ይሆናል። የቤተሰብ አባላት እንኳ አንዱ አንደኛውን አሳልፎ ይሰጣል። የእኔ ስለሆናችሁ ብቻ ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል። እስከመጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። እየሱስ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል። እነዚህን ግን ራሳችሁ ፈልጋችሁ ማንበብ አለባችሁ።
የት ነው እነዚህን ማገኘት የምንችለው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በመንግስቱ ስላለ ህይወት መመሪያ ነው። አንድ ለራስህ እንዲኖርህ ያስፈልጋል።
እየሱስ ወደፊት ስለሚመጣው ሌላ ምን አለ? 31
እ
የሱስ ክፉዎች ቀናቶች ሊፈጸሙ ሲሉ ወደ መጨረሻ በጣም የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚሆን ተናግሯል። ፀሀይ ይጨልማል። ሁሉም ነገር ይናወጣል፣ በማለት አስጠንቅቋል። ከዚያም ንጉሱ በታላቅ ሀይልና በብዙ ክብር ይገለጣል። ለእርሱ የተመረጡትንም ከምድር ዳር እስከዳር ድረስ ይሰበስባቸዋል።
ይህ መቼ ነው የሚሆነው?
እየሱስ ይህ የሚሆንበትን ቀንና ሰዓቱን ከእግዚአብሔር አባት በስተቀር ማንም እንደማያውቅ ተናግሯል። ስለዚህም ነቅቶ መጠበቅና ወደእርሱ መጠጋት በጣም አስፈላጊ ነው። የፋሲካ በዓል ሊከበር ቀርቦ ስለነበር እየሱስ በእርሱ ላይ የሚሆነውን ያውቅ ነበርና ደቀ መዛሙርቱን ለዚሁ ያዘጋጃቸው ነበር።
ፋሲካ ምን ማለት ነው?
ፋሲካ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከብዙ ዓመታት በፊት ከግብጻውያን ባርነት እንዴት ነጻ እንዳወጣቸውና መቅሰፍት የግብጻውያንን በኩር ሁሉ ሲገድል እስራኤላውያንን እንዴት እንዳዳናቸው የሚያስታውሱበት በዓል ነው። በዚህ ፋሲካ በዓል ጊዜ የበግ መስዋዕት በማድረግ ያከብራሉ። ታዲያ ይህን የፋሲካ በዓል በቀረበበት ወቅት የእስራኤላውያን የሃይማኖት መሪዎች እየሱስን በመያዝ ለማስወገድ አጋጣሚ ይፈልጉ ነበር።
32
እነዚህ የሀይማኖት መሪዎች አሁንም እየሱስን ይከታተሉታል አዎን። ነገር ግን ህዝቡ ዓመጽ ያስነሳል ብለው ስለሚፈሩ በፋሲካ ወቅት ምንም ማለት ነው? ማድረግ እንደማይችሉ ያውቃሉ።
ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን እየሱስ የት ነበር? ይህ ማባከን አይደለም?
እየሱስ በዚህ ጊዜ ቢታንያ በምትባል ትንሽ ከተማ በእየሩሳሌም አጠገብ የነበረች በዚያ በአንዲት ቤት ውስጥ ነበር። በእራት ግብዛ ላይ በነበረ ጊዜም አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ በእቃ ይዛ መጣችና ሽቶውን በሙሉ በእየሱስ ራስ ላይ አፈሰሰችው።
አንዳንድ ደቀ መዛሙርትም ያሉት እንዲሁ ነበር። እንዲያውም አንዳንዶቹ ብትሸጠው ብዙ ገንዘብ እንደሚያወጣና ገንዘቡንም ለድሆች ቢሰጥ ይሻል ነበር አሉ። እየሱስ ግን የተለየ ሀሳብ ነበረው። “እርሷን ተዎት ለምንስ ታሰቸግሯታላችሁ? ድሆችን ሁልጊዜ ታገኟቸዋላችሁ። እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም” አላቸው።
ምን ማለቱ ነው? ከ
ዚያ ቀጥሎ ምን ማለቱ እንደሆነ ተናገረ፦ “አስቀድማ ለመቃብሬ ስጋዬን ሽቶ ቀባችው። ይህ ወነጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ እርስዎ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዎ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል“ አለ።
አሁንም እንደሚሞት እንዳመነ ነው? 33
አ
ዎ፣ ነገሮችም እየተፈጸሙ ነበር። ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ ከሃይማኖት አለቆች ጋር ተገናኝቶ ነበር። እየሱስንም ለእነሱ አሳልፎ ለመስጠት 30 ዲናር ተቀብሎ ነበር።
አዎን። እየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር
ከደቀ መዛሙርት አንዱ? አይሆንም!
የፋሲካን እራት ለመብላት እየተዘጋጁ ነበር። ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ጠራቸውና ወደ ከተማ እንዲሄዱ አዘዛቸው። “ወደ ከተማ ሰትገቡ በእንስራ ውሃ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። ተከትላችሁት ወደሚገባበት ቤት ሂዱ። ከዚያ የቤቱን ጌታ መምህሩ ከደቀ መዛሙትቱ ጋር የፋሲካን እራት የምበላበት ክፍል የት ነው ብላችሁ ጠይቁት። እርሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ትልቅ አዳራሽ ያሳያችኋል። በዚያም አዘጋጁልን” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ልክ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።
ከዚያም እየሱስና ደቀመዛሙርቱ የፋሲካን በዓል አከበሩ። የፋሲካን እራት እየበሉ ሳሉ ግን እየሱስ ከመካከላቸው አንዱ አሳልፎ እንደሚሰጠው ነገራቸው።
በጣም የሚገርም ነው።
ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ያውቅ ነበር ማለት ነው? አዎን ያውቅ ነበር።
ታዲያ ለምን አላስቆመውም?
ይህ ሁሉ እግዚአብሔር ህዝቡን ነጻ 34
የሚያወጣበት ታላቅ እቅድ አንዱ ክፍል ነበር። አስታውሱ እየሱስ ወደ ምድር የመጣው የእግዚአብሔርን ዓላማ ለመፈጸም ነው።
ይህ ነው የመጨረሻው ፈተና?
አዎን። ሁሉም ነገር እንደ እግዚአብሔር እቅድ እየተከናወነ ነበር። እራት በሚበሉበት ጊዜ እየሱስ እንጀራውን አንስቶ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም ቆረሰና “ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ወይኑንም ቀዳና ይህ ስለብዙዎች የሚፈስሰው በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የሚሆን የቃል ኪዳን ደሜ ነው“ አላቸው።
እንዴት እንግዳ ነገር ነው? ደ
ቀመዛሙርቱም እንደዚህ ያስቡ ይመስለኛል። ነገር ግን ማንኛቸውም አልተናገሩም። የሆነው ሁሉ የገባቸው ካለፈ በኋላ ነገር ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ነበር። እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በዚያች ሌሊት ሊሆን ያለውን ነገር ይነግራቸው ነበር። ”ሁላችሁም ለብቻዬ ትታችሁኝ ትበታተናላችሁ“ አለ። ጴጥሮስ ግን ”ሁላቸውም ቢተውህ እኔ ግን አልተውህም“ አለው።
እየሱስ ግን ”አዎን ትተወኛለህ። በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለተኛ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትከደኛለህ“ አለው።
ጴጥሮስ ”ፈፅሞ አይሆንም“ ሲል፤ ሌሎችም ደቀመዛሙርት ባንድ ላይ የእርሱን አባባል አስተጋቡ። ከዚያ እየሱስ አስራ አንዱን ደቀ መዛሙርት ይዞ ጌቴ ሰማኒ ወደሚባለው የወይራ አትክልት ሥፍራ ሔዱ። እየሱስ እርሱ ሲጸልይ ሲሄድ በዚያ እንዲቆዩ ነገራቸውና ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሀንስን አሰከትሎ ወደፊት ሔደ።
እነዚህ ሶስት የሞተችዋን ልጅ ሲያስነሳ አብረውት የነበሩት ናቸው?
35
አዎን። እነዚህን ደቀ መዛሙርት በጣም ያቀርባቸው ነበር። ምክንያቱም ቀጥሎ ነፍሱ እንደተጨነቀች ነገራቸው። ሲጸልይም አብረውት እንዲቖዩ ካዘዛቸው በኋላ ትንሽ እልፍ ብሎ በምድር ላይ ወደቀና መጸለይ ጀመረ። ሊቀበለው ያለውን መከራ እግዚአብሔር አባት ከእርሱ ሊወስድ እንደሚችል። ነገርግን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ የእርሱ ፈቃድ እንዳይሆን ጸለየ።
እየሱስ የመጨረሻው ፈተና የሚያስጨንቅ እንደሚሆን ያውቅ ነበር ማለትህ ነው? እንደሚሞትም ያውቅ ነበር? አዎን። ሁሉንም ያወቅ ነበር።
እንዴት ያስጨንቃል! ወዳጆቹ ታዲያ ምን አደረጉ? ምንም። እየሱስ ወደ አባቱ ሲጸልይና ሲጮህ እነርሱ ተኝተው ነበር።
ምን? ተኝተው ነበር?
እ
የሱስ ከፀሎት ተነሰቶ ወደእነርሱ ሲመጣ ፈጽመው ተኝተው ነበር። ¡§ለአንድ ሰዓት እንኳ ከኔ ጋር ልትተጉ አልቻላችሁም¡¨ አላቸው። ከዚምም እንደገና ተመልሶ ሄደና መጸለይ ጀመረ። ደቀ መዛሙርትም ተመልሰው ተኙ። ለሶስተኛም ጊዜ ወደእነርሱ ሲመጣ አሁንም ፈጽመው ተኝተው ነበር። እስከአሁን ተኝታችኋል? በቃላችሁ ሰዓቱ ደርሷል። አሁን አሰልፈው ሊሰጡኝ መጥተዋል¡¨ አለ።
ከዚያስ ምን ሆነ? 36
ይህን እየነገራቸው እያለ ይሁዳ ከጨለማው ውስጥ ሰይፍና ዱላ ከያዙ ከብዙ ሰራዊት ጋር ወጣ። ይሁዳ አስቀድሞ ለሰራዊቱ ¡§ሄጄ የምስመው አርሱ ነውና እርሱን ያዙት¡¨ ብሎ ነገሯቸው ነበር። ስለዚህ ይሁዳ በቀጥታ ወደ እየሱስ ሄደና እየሱስን ሳመው። በዚያን ዘመን መሳም የተለመደ የሰላምታ መንገድ ነበር። ወዲያውኑ ወታደሮች እየሱስን ለመያዝ ከበቡት። ጴጥሮስ ግን ፈጥኖ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን ዘበኛ ጆሮ ቆረጠው። በዚያን ጊዜ እየሱስ ¡§ተዉ!
¡¨ ብሎ ጮኸ። እየሱስ ሊይዙት የመጡትን ወታዶሮችና የካህናት ዘበኞች ¡§ወንበዴ እንደምትይዙ ብዙ መሳሪያ ይዛችሁ መጣችሁ። ዕለት ዕለት በመቅደስ ሳስተምር ለምን አልያዛችሁኝም? ነገር ግን አሁን ይህ ሁሉ የሆነው በቅዱሳት መጽሕፍት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ነው¡¨ አላቸው።
ቅዱሳት መጻሕፍት ምንድን ናቸው? እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚባሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸው ጥንታዊ መጽሐፍት ናቸው። በእየሱስ ላይ የተፈጸመው ሁሉ በእነዚህ መጻሕፍት ይሆናል እየተባለ አስቀድሞ ተነግሮል።
እንዴት የሚገርም ነው? 37
እየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት እንደሚበታተኑ አስቀድሞ እንደነገራቸው፤ ተከታዮቹ በሙሉ ጥለውት ሸሹ። እርሱን ግን ይዘው ወደ ሊቀ ካህኑ ቤት ወሰዱት። በዚያም እየሱስን የማይወዱ፣ ጠላቶቹ ሁሉ ተሰብስበው ነበር። ጴጥሮስም ራቅ ብሎ የሚሆነውን ሁሉ ይከታተል ነበር። የእየሱስ ከሳሾች ብዙ ዓይነት ክሶችን በእርሱ ላይ ይደረድሩ ነበር። ክሳቸው ከመብዛቱ የተነሳ አንዱ ክስ ሌላውን የሚያፈርስ ነበር። በዚህ ጊዜ ሊቀካህኑ ወደ እየሱስ ዞሮ ¡§እነዚህ ለሚከሱህ ክስ መልስ አትሰጥም¡¨ በማለት ጮኸበት። እየሱስ ግን አሁንም ምንም አልተናገረም። በመጨረሻም ሊቀካህኑ ¡§አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን?¡¨ በማለት ጠየቀው። እየሱስም ¡§አዎ እኔ ነኝ። ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ቀኝ ስቀመጥና በሰማያት ደመና ተመልሼ ስመጣ ታያላችሁ¡¨ ብሎ መለሰለት።
እንዴት ግሩም ነው?
ሊቀካህኑ ግን የእየሱሰን መልስ አልተቀበለውም። በጣም ስለተቆጣም ልብሱን ቀደደና ከእንግዲህ ምን እንጠብቃለን? በእግዚአብሔር ላይ የተናገረውን ሰምታችኋል” በማለት እየሱስን የሞት ፍርድ ፈረደበት። የሊቀ ካህናቱ ወታደሮች እየሱስን ተፉበት፣ ደበደቡት። ፊቱንም ሸፍነው “ማነው የመታህ? እስኪ ትንቢት ተናገር” እያሉ ያፌዙበት ነበር። እርሱ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን መልሶ እልተሳደበም።
38
ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ጴጥሮስ በግቢው ውስጥ በምድር ቤት ሆኖ ሁሉንም ነገር ይከታተል ነበር። ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንደኛዋ በዚያ በኩል ስታልፍ ጴጥሮስን ትኩር ብሎ ተመለከተችውና ¡§አንተ ማነ ነህ? እየሱስን ከሚከተሉት ሰዎች መካከል አንዱ ነህ?¡¨ አለችው።
ጴጥሮስ ግን ፈጠን ብሎ ¡§በፍጹም የምትይውን አላውቅም¡¨ ብሎ መለሰና ፈጠን ብሎ ወደ ውጭ ወጣ። በዚያን ጊዜም ዶሮ ጮኸ። አገልጋይዋ ግን ጴጥሮስን ተከትላ እንደገና ጠየቀችው፤ ጴጥሮስ ደግሞ ካደ። ከዚያም ሌሎች ሰዎች መጡና ¡§አንተ ከእነዚያ የገሊላ ሰዎች አንዱ ሳትሆን አትቀርም¡¨ አሉት። እርሱም የምትሉትን አላውቅም እያለ ይምል ጀመር። ጴጥሮስ በዚህ ጊዜ ¡§ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ስስት ጊዜ ተከዳኛለህ¡¨ ያለው የእየሱስ ቃል ትዝ አለውና ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
እየሱስ ይሆናል እንዳለው ሆነ አይደል? ምንም ማድረግ አልተቻለም? እየሱስ በቃ ያለምክንያት ሊሞት ነው? 39
የእግዚአብሔርን ዕቅድ አስታወሱ። እየሱስ የመጣው ነጻነትን ወደ ምድር ለማምጣት ስለሆነ፤ ንጉሱ በዚህ ሁሉ ማለፍ ነበረበት። እየሱስ ያለፈበት ይህ መንገድ የሀጢአትን ዋጋ ለመክፈል ብቸኛ መንገድ ነበር። በነጋ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እየሱስን ወደ ሮማዊው ሀገረ ገዢ፣ ጲላጦስ ዘንድ ወሰዱት። ጲላጦስም እየሱስን ¡§አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?¡¨ ሲል ጠየቀው። እየሱስ ”አዎን እኔ ነኝ“ አለ። ከዚያ ቀጥሎ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች በብዙ ነገር ይከሱት ጀመር።
ታዲያ ምን መልስ ሰጠ? ምን ም!
ምን ማለት ነው?
40
ሮማዊው ሀገረ ገዢ፣ ጲላጦስም በጣም ተገርሟል። ለራሱ እንዲከራከር እንደገና ጠየቀው። እየሱስ ግን አሁንም አልተነገረም። ያ ወቅት ግን የፋሲካ ወቅት ነበር። ጲላጦስም በየዓመቱ በፋሲካ ወቅት ህዝቡ የፈለጉትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር።
ኦ ግሩም ነው ህዝቡ የእየሱስን መለቀቅ ይጠይቅ ይሆናል። አይደለም። የአይሁድ ሀይማኖት መሪዎች በርባን የተባለውን ወንበዴና ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላቸው እንዲለምኑት ህዝቡን አባበሉ።
አዎን። ጲላጦስም እንደዚህ ነበር የተገረመው። ስለዚህ እንዲያስቡ አሁንም እንደገና ለህዝቡ ሌላ ዕድል ሰጣቸው። ¡§እየሱስን ምን እንዲሆን ነው የምትፈልጉት?¡¨ አላቸው።
ይህ ትክክል አይደለም!
ከዚያስ? ህዝቡ ግን ¡§በቃ ስቀለው!¡¨ ብለው ጮኹ።
ስቀለው ማለት ምን ማለት ነው?
ይህ የሚያሳዝን ፍርድ ነው።
ሮማውያን በዚን ዘመን ስቅላት የሚባል የሞት ቅጣት ነበራቸው። ይህ አሰቃቂ የግድያ መንገድ የሚፈጸመው ለከባድ ለነፍሰ ገዳዮችና ዓመጸኞች ሮማውያን ላልሆኑ ዜጎች ብቻ ነበር። የሮማውያን ወታደሮች የሚሰቀለውን ሰው እጆቹንና እግሮቹን ከእንጨት ጋር በትልልቅ የብረት ሚስማር ያጣብቁት ነበር። ከዚያም ግንዱን ከተቸነከረው ሰው ጋር ከመሬት ላይ አንስተው ቀጥ አድርገው በመሬት ላይ ሲተክሉት ሰውየው ከእንጨቱ ጋር እንደተጣበቀ ይሰቀላል። ሰውነቱ እንደተንጠለጠለ መተንፈስ ስለማይችል አየደከመ ይሄድና ተሰቃይቶ ይከሰዓታት በኋላ ይሞታል። በጣም የጭካኔ የግደያ መንገድ ነበር።
ሰለዚህም ጲላጦስ ህዝቡን እንደገና ጠየቃቸው። ¡§እየሱስ የሰራው ወንጀል ምንድን ነው?¡¨ ብሎ ጠየቃቸው። ህዝቡ ግን በቁጣ እየጮሁ ስለነበር አልሰሙትም። ጲላጦስም ጩኸቱን ማስቆም እንደማይችል ሲያውቅ፣ ህዝቡ የጠየቁትን ፈቀደላቸው። በርባንን ፈታው። እየሱስንም ገርፈው እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጠው።
የእየሱስ ስቃይ ከዚህም የከፋ ነበር ከመስቀሉ በፊት ብዙ ስቃይ ድርሶበታል። ወታደሮቹ የንጉስ ልብስ የነበረ ሀምራዊ ቀሚስ አልብሰው ከሾህ የተሰራ አክሊል ሰርተው በራሱ ላይ ካደረጉ በኋላ ¡§የአይሁድ ንጉስ፣ እየሱስ¡¨ እያሉ ያሾፉበት ነበር። ብዙ ሰዓታት ካሰቃዩት በኋላም ሊሰቅሉት ወሰዱት።
ይህ ሁሉ ተፈጸመበት? መቼም ይህ ታላቅ የነጻነት ዕቅድ ነው ብዬ ማመን አልችልም!
አ
ዎን ይህ በእርግጥም የእግዚአብሔር የነጻነት ዕቅድ ነበር። ሮማውያን ወታደሮች እየሱስን ጎሎጎታ ወደሚባል የራስ ቅል ስፍራ አመጡትና በሀሞት የተቀላቀለ ሬት እንዲጠጣ አቀረቡለት። ይህም ሥቃዩ እንዳይሰማው እንደ ስቃይ ማደንዘዣ የሚያገለግል መራራ መጠጥ ነው። እየሱስ ግን አልተቀበለም። ከዚያም እየሱስን የመስቀል ቅርጽ ያለው እንጨት ላይ በሚስማር ቸነከሩት። እየሱስ ሲሰቀል ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ነበረ። በመስቀሉ ላይ ¡§የአይሁድ ንጉሥ¡¨ የሚል ጹሑፍ ሰቀሉ። በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ እያነበቡ ይስቁና ያሾፉ ነበር። ¡§ንጉሥ ከሆንህ ከመስቀል ላይ ውረድና አሳየን¡¨ ይሉ ነበር። ሁለት ወንበዴዎችም አንዱ በግራ ሌላው በቀኙ ተሰቅለው ነበር። እነዚህም ተጨምረው በእየሱስ ላይ ያሾፉ ነበር።
ይህ ሊሆን አይችልም! በቃ መጨረሻው ይህ ነው? 42
አይደለም። እኩል ቀን ሲሆን ሁሉ ነገር ጨለማ ሆነ፤ ዙሪያው ሁሉ ባንድ ጊዜ ጨለማ ሆነ። ከዚያም እየሱስ ¡§አምላኬ ለምን ተውኸኝ¡¨ ብሎ ጮኸ። ከዚያም በሀይል ተነፈሰና ሞተ። በዚህ ጊዜ ግን እንግዳ የሆነ ነገር ሆነ።
ምንድን ነው እሱ?
43
በ
ቤተመቅደስ ውስጥ በጣም ወፍራም መጋረጃ ነበር። ይህም መጋረጃ ቅድስተ ቅዱሳን የሚባለውን ክፍል ከሌላው የመቅደስ ክፍል የሚለይ ነበር። ወደ ቅድሳተ ቅዱሳን ሊቀ ካህናቱ ብቻ በዓመት አንድ ቀን ይገባ ነበር። እየሱስ በሚሞትበት ጊዜ ይህ መጋረጃ ከላይ እስከታች ድረስ ተቀደደ።
ሰው ሁሉ ወደ ውስጥ መግባት ቻለ ማለት ነው?
አዎን። በእየሱስ ሞት በኩል ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ቀጥታ መምጣት ይችላል። አሁን ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት ቄስ ወይም አገናኝ አያስፈልግም። ጊዜው እየመሸ ሲሔድ ዮሴፍ የሚባል የአርማቴያ ሰው ወደ ጲላጦስ ሔዶ የእየሱስን ስጋ ለመቅበር ጠየቀ። ወታደሮች መሞቱን ካረጋገጡ በኋላ ሰጡት። ዮሴፍም የእየሱስን ስጋ ወስዶ በጨርቅ ጠቀለለው። ከድንጋይ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ አኖረው። ጲላጦስ ግን ወታደሮቹ መቃብሩን በትልቅ ድንጋይ እንዲዘጉ አዘዛቸው፤ ምክንያቱም የአይሁድ ሀይማኖት መሪዎች ¡§የእየሱስ ተከታዮች የእየሱሰን ስጋ ከመቃብር ሰርቀው ሊወስዱት ይችላሉ¡¨ ብለው ለጲላጦስ አመልክተው ስልነበረ ነው።
በቃ በዚህ ሁኔታ የእየሱስ ነገር አበቃ ማለት ነው? 44
በዚህ አያበቃም! ሁሉት ሴቶች መቃብሩን አይተው ነበር። ነገር ግን ሰንበት ስለሆን ወደ ቤታቸው ሄዱ። በሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ግን ሽቶና ቅመሞችን ገዝተው ከሌሎች ሴቶች ጋር ወደ መቃብሩ ሄዱ።
ትልቁ ድንጋይስ?
እነዚህንም ሴቶች በጣም ያሳሰባቸው ይህ ነበር፤
ምን?
ወደ መቃብሩ በመጡ ጊዜ ግን ድንጋዩ ተንከባልሎ ነበር።
45
ሴ
ሴቶቹም ደንግጠው ሮጠው ወደ ውስጥ ዝቅ ብለው ሲመለከቱ የእየሱስ ስጋ በቦታው አልነበረም፤ ነገር ግን ነጭ ልብስ የለበሰ መልአክ ከመቃብሩ ውስጥ ተቀምጦ ነበር። መልአኩም “አትፍሩ እየሱስ እንደተናገረ ተነስቷል፣ ስጋው የነበረበትን ስፍራ ኑ እዩ። ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ ‘ተነስቷል፤ ወደ ገሊላም ይቀድማቸኋል። በሏቸው። እንደተናገረም በዚያ ያዩታል” አላቸው።
ሴቶቹም ይህን ሲሰሙ እየተንቀጠቀጡ ከመቃብር ወጥተው ሔዱ። በዚያኑ ማለዳ ደግሞ ከሴቶች አንደኛዋ እየሱስን አገኘችው። ከእርሱም ጋር ተነጋገረች። ወዲያውኑ ያየችውን ሁሉ ለመንገር ወደ ደቀመዛሙርቱ ሮጠች። በነገረቻቸው ጊዜ ግን ማንም አላመናትም።
እውነት ነው ማን ሊያምናት ይችላል? እየሱስ ግን በእውነትም ከሞት ተነስቶ ነበር። መልአኩ የነገራቸው ሁሉ እውነት ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በተደጋጋሚ ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጸ ያነጋግራቸው ነበር።
እንዴት?
እየሱስ ከሞት በተነሰባት ቀን ሁለቱ ደቀመዛሙርት ከእየሩሳሌም ወደ ገጠር ይሄዱ ነበር። እየሱስም አብሮአቸው በመንገድ ላይ መጓዝ ጀመረ። መንገደኛ ስለመሰላቸው ሲያነጋግራቸው እየሱስ መሆኑን አላወቁም። ያወቁት ግን ብዙ ካስተማራቸውና እንጀራን ቆርሶ ባርኮ ከሰጣቸው በኋላ ነበር። እርሱ መሆኑን ባወቁት ጊዜ ግንየመሸ ቢሆንም የሆነውን ሁሉ ለቀሩት ደቀ መዛሙርት ለመንገር ያን ጊዜውኑ ወደ እየሩሳሌም ተመለሱ።
46
ሁ
ሉም ደቀመዛሙርት በእየሩሳሌም ተሰብስበው ስለዚህ ሲነጋገሩ እየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆመና መልአኩ የነገራቸውን አለማማናቸውን እንዲሁም መነሳቱን ሴቶች ሲነግራቸው ባለማመናቸው ነቀፋቸው። ከዚያ ቀጥሎ ግን የመጨረሻ ትእዛዝ ሰጣቸው እንዲህ ሲል፦ ¡§ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ። ይህንንም መልካም የምስራች ለሰው ሁሉ ስበኩ። ያመነና የተጠመቀ ሁሉ ይድናል ለማመን የማይፈልግ ግን ይፈረድበታል።
እንዴት ይገርማል? እየሱስ በእውነትም ከሞት ተነስቷል!
አዎን። የእግዚአብሔር የማዳን እቅዱ ይህ ነበር። እየሱስ ሰዎችን ከሀጢአትና ከሞት ነጻ ሊያወጣቸው መጣ። በሞቱና በትንሳኤው ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያውቁበትን መንገድ ከፈተላቸው። በእየሱስ እመን ህይወትህ ይለወጣል ። እንዲህ ብለህ መጸለይ ትችላላህ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ራስህን ስለገለጽህልኝ ስለእኔም ትክክለኛውን ነገር ስላሳየኸኝ አመሰግንሀላሁ። ስለሀጢአቴም በጣም አዝናለሁ። እባክህ ይቅር በለኝ? አንተ ሰማያትንና ምድርን ፈጥረሃል። አንተ ሁሉንም ፍጥረት ፈጥረሃል። ዛሬም እኔ በውስጤ አዲስ ህይወትን እንድትፈጥር እለምንሃለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህን፣ ንጉሱን እየሱስን ስለ እኔ እንዲሞትና አዲስ ጅማሬ እንዲሰጠኝ ወደ ምድር ስለላክኸው አመሰግንሃለሁ። ንጉሱ እየሱስ ዛሬ ወደ ህይወቴ እንድትመጣ እጋብዝሃለሁ። በመንግስትህ ልኖርና አንተ ለኔ ያለህን ዓላማ መፈጸም እፈልጋለሁ። ለዚህ የሚመራኝን መንፈስ ቅዱስን ስለላክህልኝ አመሰግንሃለሁ። እባክህ የምትሰራውን ሁሉ እንዳይ ዓይኖቼን ክፈትልኝ። የምትነግረኝን ሁሉ እንድሰማ እባክህ ጆሮቼን ደግሞ ክፈትልኝ። ልቤንና ሃሳቤን ሁሉ ባንተ ላይ እንዳደርግ እባክህ እርዳኝ።
47
አሁን ይህን ጸሎት ጸልዬሃል ስለዚህ እንደቃሉ ወደ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ መንግስት እንደገባህ እመን። እንግዲህ በመንግስቱ እንዴት መኖር እንዳለብህ በየቀኑ ከእርሱ ልትማር ያስፈለግሃል።
እንዴት?
በጸሎት ከእርሱ ጋር ተነጋገር። በልብህ ያለውን ሁሉ በማንኛውም ጊዜ
በየትም ቦታ ንገረው። አሁን ከእግዚዘብሔር ጋር የቀጥታ ግንኙነት እንዳለህ አስታውስ።
መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ። ቃሉን ለማንበብ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ
ለምን። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሌላ መጽሐፍ ወይም መጻህፍት ዝም ብሎ መጽሐፍ አይደለም። በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ካነበብኸው በህይወትህ ላለው ማንኛውም ጥያቄ መመሪያ ታገኛለህ።
ሌሎች በእየሱስ የሚያምኑ ሰዎችን አግኝ። ለእየሱስ ፍቅር ያላቸውና በመንግስቱ የሚኖሩ አማኞችን በቤተ ክርስቲያን ታገኛለህ።
በመጨረሻም ስለሁሉ እግዚአብሔርን አመስግነው። እግዚአብሔር ስለሰጠህ ስለ እያንዳንዷ ቀን አመስግነው። እርሱ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር እንዳለ አስታውስ።