የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው ? የህዝቡስ ኑሮ ተሻሽሏል ወይ ? ወይስ ጥቂቶች የደለቡበት ሁኔታ ነው የሚታየው ?

Page 1

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው ? የህዝቡስ ኑሮ ተሻሽሏል ወይ ? ወይስ ጥቂቶች የደለቡበት ሁኔታ ነው የሚታየው ? -ዶ/ር ዳንኤል ተፈራና ዶ/ር ፀሀይ ለኢሳት ጋዜጠኛ ለአቶ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጧቸው መልሶች የቀረበ አስተያየት- ከፈቃዱ

በቀለ

መግቢያ በቅርቡ ሁለት በአሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶችን የኢሳት የቴሊቪዝን ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ፋሲል የኔ ዓለም ኢትዮጵያ ከውጭ የምትበደረው ብድር መጠን እያደገ ስለመምጣቱና ስለኢኮኖሚው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በመጋበዝ በመሰላቸውና በሚታያቸው፣ እንዲሁም ከተማሩት የኢኮኖሚ ትምህርት አንፃርና ከዕምነታቸው በመነሳት ለተደረገላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል። ፕሮፊሰር ዳንኤል ዕዳንንም ሆነ፣ የሚሰሩትን ፕሮጅክቶች ወደ ፊት ሊገኝ ከሚችለው ውጤትና አትኩሮ ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን፣ ነገር ግን የሚታለፈው አንገብጋቤ ጥያቄ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት በንጽጽር መልክ ለማሳየት ሲሞክር፣ ዶ/ር ፀሀይ ደግሞ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ቢሰሩ ጥቅማቸው እንደሚያመዝንና ለዕድገትም አስፈላጊ መሆናቸውን ለማመልከት ሞክሯል። በመሰረቱ በሁለቱ ኢኮኖሚስቶቸ መሀከል ያለው ልዩነት በዚህ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን፣ በመንግስት ሚናና መንግስት አትኩሮ ስለሚሰጠው ጉዳይ፣ በመንግስት ቁጥጥር ስር ስላሉ „የልማት አውታሮች“ በሚባሉት እንደ መብራት ኃይል፣ ቴሌኮሙኒኬሽንና የአውራ ጎዳና ባለስልጣን ጉዳይና፣ ሰለኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ስለነዚህ „ትርፋማነትና“፣ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ በኩል፣ እነዚህ ድርጅቶች የሚበደሩት ብድር በመንግስት ብድር ውስጥ ተጠቃሎ መታየት ስላለበት ጉዳይና፣ እንዲሁም ወደ ግል ስለመዘዋወራቸው፣ ወይም አለመዘዋወራቸው፣ በመንግስት ላይ ስለሚያደርጉት ጫና፣ ሁለቱም ኢኮኖሚስቶች የተለያየ ግምትና አስተያየት ሰጥተዋል። እንዲሁም መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ሰለሚጫወተው ሚና፣ ስለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ስለመሬት ይዞታና ወደ ግል ሀብትነት ስለመዘዋወር ጉዳይ የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው ከቃለ-ምልልሱ መረዳት ይቻላል። በሁለቱ ኢኮኖሚስቶች ስለተሰጠው የቃለ-ምልልስና ገለጻ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ቢያስመስልም፣ የሁለቱም ምሁሮች የኢኮኖሚ ትንታኔ የቲዎሪ መነሻ አንድ ነው ። ይኸውም የኒዎ-ሊበራል ወይም የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊስ ላይ ይስማማሉ። ሁለቱም አቀራራባቸው የተለየ ቢመስልም፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ችግር በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ አማካይነትና በውጭ መዋዕለ-ነዋይ(Foreign Direct Investment) እንደሚፈታ ያላቸውን አቋም፣ ከዚህ አስተያየታቸውም ሆነ አልፈው አልፈው ለሚዲያ ከሚያቀርቡት ጽሁፎቻቸው መገንዘብ ይቻላል። የመንግስት ጣልቃ ገብነት ዛሬውኑ መቆም አለበት፣ ሁሉም ነገር በነፃ ገበያ አማካይነት ሊወሰን ይችላል በሚለው ላይ በመሀከላቸው ያለው የጊዜ እንጂ ፣ በመሰረቱ የአቋም ልዩነት እንደሌላቸው መገንዘብ ይቻላል። በሌላ በኩል የሁለቱን ኢኮኖሚስቶች አስተያየት ለተመለከተ ተፍታቶና ተብራርቶ ቀለል ባለ መልክ የቀረበ አይደለም። ከመስራት፣ ገንዘብ ከማግኘትና በገንዘቡ ገበያ ላይ ወጥቶ የሚፈልገውን ነገር ለመግዛትና በመጠቀም ለሚኖር ሰውና፣ የኢኮኖሚን ትርጉም በሚገባ ለማይረዳ የሁለቱ ኢኮኖሚስቶች አቀራረብ ቀለል ብሎ ማንኛውም ሰው ሊረዳው በሚችለው መልክ የቀረበ አይደለም። አቀራረባቸውም ከንጹሁ የኒዎ-ሊበራልና የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ በመነሳት የቀረበ አስተያየት ስለሆነ የኢኮኖሚን ፅንሰ-ሃሳብ ትርጉሙንና በተግባር በሚመነዘርበት ጊዜ ሊያስከትል የሚቸለውን አዎንታዊና አሉታዊ ውጤት ለመረዳት ለሚፈልግ በቀላሉ ትምህርት ሊቀስም በፍጹም አይችልም። በተጨማሪም፣ ሁለቱም ኢኮኖሚስቶች የኢኮኖሚን ጥያቄ ከሌላው የህብረተሰብ ጥያቄ፣ የፖለቲካ፣ የማህበረሰብና የህብረተሰብ ግንባታ፣ እንዲሁም የህብረ-ብሄር ግንባታና የባህል ሁኔታ ነጥለው በማየታቸውና፣ ኢኮኖሚን በአየር ላይ የሚንቀሳቀስና የሰውም ልጅ ፍላጎት ገንዘብ ከማግኘት ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም የሚል አቀራረብ ስለሰነዘሩና፣ እንደዚህ ዐይነቱ አመለካከት ቶሎ ብሎ ካልታረመ ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊመራን ስለሚችል ነገሩን ጠለቅ ብዬ እንድመረምር ተገደድኩኝ። ከዚህም በላይ፣ ሁለቱም ኢኮኖሚስቶች በንጹህ መልኩ በኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚክ ቲዎሪ የሰለጠኑ ስለሆነ ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት ትርጉምና ስለ ህብረተሰብአዊ የሀብት ክምችት ፈጠራና ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚ ዕድገትና የህብረተሰብ ግንባታ ሊናገሩ 1


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.