መጽሔት ጥር ፣ ቅጽ ፩ >>>>>> GDG Addis devFest '22 ቴክድግስ >>>>>> GraphQL እና RESTAPIs እንዴት በተለያየ መልክ ያነባሉ? አጤሪራ >>>>>> AVATAR 2 BTS መዝናኛAI >>>>>> ከኪሩቤል ፍቅሩ ጋር AWS Expert የቴክኖሎጂስቶች ህይወት ተሞክሮ AI Programming የAI 6 በጣም አሪፍ የ2022 ፈጠራዎች the feature of AI NLP IMPACT IN ETHIOPIA 12
ማውጫ >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> >>>>>>>>>>>>>>>>>>> 04 08 06 12 ከአርታዒው አጭር መግቢያ የቴክኖሎጂስቶች ህይወት ተሞክሮ ከኪሩቤል ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ ቴክ ድግስ DevFest’22 AI ዝርዝር The Feature of AI: NLP Impact in Ethiopia ጥር ፣ ቅጽ ፩ AI ዝርዝር The Feature of AI ቴክ ድግስ
16 18 22 15 አጤሪራ GraphQL እና REST APIs እንዴት በተለያየ መልኩ ያነባሉ? በጣም አሪፍ 6 የ2022 የAI ሶፍትዌር ፈጠራዎች መዝናኛ AI BTS of Avatar ጠቃሚ ጥቆማ GraphQL እና REST APIs
ዚህ እና በየወሩ በሚወጡት የመጪዎቹ ቅጾች ላይ በሚከተሉት ርዕሶች ላይ እናተኩራለን። "ቴክድግስ" ከተማችን ወይም ሀገራችን አልፎም አህጉራችን ላይ የተከሰቱ የቴክኖሎጂ ዝግጅቶች እና ውይይቶች የሚያተኩር ሲሆን “ የቴክኖሎጂስቶች ህይወት ተሞክሮ” ደሞ በቴክኖሎጂ ላይ ጥናታቸውን የሰሩ ወጣቶች ስለ ፕሮጀክታቸው እና ልምዳቸውን ያካፍሉናል፤ “ አጤሪራ” ስለ ተመረጡ ሶፍትዌሮች ቴክኒክ እና አሰራር ዋና- ዋና ምሳሌዎች፤ “ ኤአይ ዝርዝር” ስለ ኤአይ ቴክኖሎጂ ጥልክ ትንተና፤ “መዝናኛኤአይ” መዝናኛ ኢንዱስትሪው ውስጥ ሰው ሰራሽ ማሰብ ችሎታን ተጠቅመው የሚመረቱ የመዝናኛ መሳሪያዎች አሰራርን ይቃኛል፤ በስተመጨረሻም “ጠቃሚ ጥቆማ” ማራኪ ወይም ጠቃሚ መጽሐፎችን እና ድህረ-ገጾችን ይዘረዝራል። ይህችን አጭር መጽሔት ስናዘጋጅ ምንም እንኳን በጥቂቱ በአማርኛ ቋንቋ ብናደርገውም አንዳንድ ጽሑፎችን ከቴክኖሎጂ አዲስነታቸው የተነሳ እና ገና በአካባቢያችን ጥናት እና ምርምር ያልተደረገባቸው በመሆኑ መሐበረሰባችን ቃሎቹንም ሆነ ሃሳቦቹን በቀላሉ ላይረዳው ስለሚችል በእንግሊዘኛ አድርገነዋል። እንግዲህይሄንሁሉካልንዘንዳየወደፊቱንየቴክኖሎጂዕጣፈንታበጋራእንድንቀርጽዘንድይቀላቀሉን! ይህየቴክኖሎጂመጽሔትእየተዘጋጀየሚወጣላቹየስልታዊቻናል በሆነውየኤአይፕሮግራሚንግነው። © 2023 | ALL RIGHTS RESERVED. እንኳን ወደ ኤአይ ፕሮግራሚንግ ወርሃዊ መጽሔት በደህና መጣቹ! የመጽሔታችንን የመጀመሪያ እትም ላይየተካተቱትንበኢትዮጲያእናበውጭሀገራትየተከሰቱየቴክኖሎጂእድገቶች፤ተያያዥየቴክ-ሶፍትዌሮች ትንተና፤ቃለመጠይቅ፤እንዲሁምአዳዲስቴክኒክእናዘዴዎችላይያተኮረዳሰሳስናቀርብላቹበጣምደስ ብሎናል።ልምድያለውፕሮግራመርምሁኑጀማሪይህመጽሔትችሎታዎንየበለጠለማሳደግእናበፍጥነት እያደገ ስላለው የኤአይ ፕሮግራሚንግ መስክ እንዲያቁ የሚያግዙ አስደሳች እና መረጃ ሰጪ ይዘቶችን ያቀርባል። በ ከአርታዒው አጭር መግቢያ AI Programming የዚህንመጽሔትክፍልፎቶኮፒበማረግ፤በመተርጎም፤ወይምበሌላኤሌክትሮኒክ ወይምሜካኒካልሂደቶችከአሳታሚውየጽሁፍፍቃድከሌለእናለሂሳዊግምገማዎች፤ ለሌሎችለንግድላልሆኑአጠቃቀሞችበተጨማሪምእንደማስታወቂያላይከሚውሉ አጫጭርጥቅሶችእናበቅጂመብትህግየተፈቀደላቸውበስተቀርበምንምመልኩ ማሰራጨትምሆነማስተላለፍአይቻልም። አዲሱኃይለማርያም ዋና-አዘጋጅ 4 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine መቅድም
EDITOR IN CHIEF Addisu Hailemariam addishaile@hotmail.com PROJECT MANAGER Abel Berhanu abelberhanu6@gmail.com MARKETING MANAGER Danayit Tesfaye tesfayedanu9@gmail.com CONTRIBUTORS Rediet Dawit Abel Berhanu COVER PHOTO NanoStockk PICTURES COURTESY 20th Century Fox Medafrica Times iStock Photos Benj Edwards GRAPHICS DESIGNER Addisu Hailemariam Rediet Dawit redietdav@gmail.com THANKS TO Kirubel Fikru Tewahido Alemu the Team Never Miss an issue! Follow us on Social Meida & Visit our Website . . . . . .
DEV Fest '22
AN ANNUAL DEVELOPER CONFERENCE HOSTED BY GOOGLE DEVELOPER GROUPS (GDG S ) IN ADDIS ABABA, ETHIOPIA
By Rediet Dawit
DEVFEST ADDIS is an annual developer conference hosted by Google Developer Groups (GDGs) worldwide to bring together developers, students, organizations, and outstanding speakers in one place to share knowledge and experiences.
The Google Developer Group (GDG) Addis Ababa, powered by Ethiotelecom, invited developers to the recently opened Ethiopian Science Museum for the DevFest ‘22 conference.
The event was held on December 10, 2022, in the recently opened Ethiopia Science Museum. It included keynotes on the Google Developer Community, Metaverse, Ethiopian Industrious Engineering, Hacking, Women in Tech, and many other topics to encourage tech companies and enthusiasts to investigate how the applications of the technology are implemented to advance Ethiopia’s development.
The event included keynote addresses from well-known IT leaders, panel discussions with business experts, hackathons, seminars, a Capture the Flag “CTF contest, and a telebirr user interface designing competition aimed at students of computer science. Participants will get access to a range of Tech Berenda lectures and the tools they require to launch prosperous digital professions.
People looking to establish themselves as tech entrepreneurs or professionals in the nation can interact with seasoned digital practitioners from the surrounding countries and overseas through DevFest’22. The GDG facilitates collaborations between technologists already working in Ethiopia and those wishing to get involved in the Ethiopian digital ecosystem from outside regions by establishing these possibilities for learning, networking, and the transfer of skills.
By providing a platform through which participants have access to highcaliber educational resources, DevFest ‘22 offers invaluable insight into current state-of-the-art digital advancements that are shaping many industry fields today – no matter what field someone may find themselves in, ultimately tying together achievements from various backgrounds, including building mobile applications, user experience/interface design concepts, side hustles/online entrepreneurship ventures.
ቴክ ድግስ
< >
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> 06 <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<
and innovation
The ultimate goal is to help Ethiopian developers find their niche in the ever-growing world of technology. To invest in value-added initiatives like software engineering, artificial intelligence/machine learning, or blockchain technologies that are prerequisites for quickly diving into innovative breakthroughs that serve both public and private sectors endeavors that directly stimulate economic prosperity while at once, EthioDevFest serves as a unique platform where ideas exchange can take place between domestic experts as well as expatriate Ethiopians working back home. As a result, various opportunities will be made available to people & companies attending the event as a result of these projects being highlighted at DevFest ‘22!
From this event, I can say it’s a great opportunity for individuals, start-ups, experts, and well-experienced who love to engage in this sector to learn a lot from the expert CEO and founder of Tech companies through this event. As a woman, I want to express my
appreciation for seeing so many women at this event; women empowerment at this event was a good appreciation. I hope to see it for a future event as well. Individuals and companies received an educational resource that was very helpful and motivating for individual startup companies. It was a fantastic networking opportunity, but they should have been more organized, not even mentioning the event opening & start time. For example, the speakers were supposed to speak for 5 minutes, but they spoke for longer and with several resumed speeches due to a cable issue, with less preparation and a lack of organization from the hosts.
“Creativity
are essential for the success of local development “
07 AI PROGRAMMING magazine <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<
የቴክኖሎጂስቶች ህይወት ተሞክሮ “ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ” የመጀመሪያ ዲግሪውን የጨረሰው በኮምፒውተር ሳይንስ ነው፤ ከዛም በኃላ የኦንላይን Cloud Computing ኮርሶችን ወስዶ ሰርቲፋይድ ሆኗል። ኪሩቤል ፍቅሩ ወልደሰማያት ይባላል፤ በዛሬ አምዳችን ትምህርት ቤት ሳለ ስላሳለፋቸው ዝቅታ እና ከፍታዎች፤ ስለሰራው ፕሮጀክት፣ ከትምህት ጎን ለጎን ስላካበተው ልምዱ፤ ከትምህርት በኃላ ስላጋጠመው ነገር እና ልምዱ እናወራለን። ውይይታችን ድርቅ ያለ አይደለም ወጣቶችም አይደል ፈታ የሚያረግና የሚያዝናና ነገር በየመሃሉ ጣል ጣል እያደረግን ነው። ጥያቄ. ኮምፒውተር ሳይንስ ፊልድ የመረጥክበት የተለየ ምክንያት አለክ? የተለየ ምክንያት የለኝም ግን 12 እንደ ጨረስኩ ሌላ ፊልድ ነበር የገባሁት እንደውም ከIT ፊልድጋ አይገናኝም ነበር፡፡ እንደ አሁኑ ጊዜ ኮመን ኮርስ አልነበረም እና የደረሰኝን ከመማር ውጪ ሌላ የመምረጥ እድል አላገኘውም ቢሆንም ግን የምማረውን ፊልድ አቁሜ ወደ IT ፊልድ ገባው፡፡ ጥያቄ. በዚህ ፊልድ ላይ ከባድ ነገር የምትለው ወይም ቻሌንጅ ያደርገህ ነገር አለ? ከባድ የምለው ነገር አለ ብዬ አላስብም በርግጥ ግን እንደመጀምሪያ ኮምፒዩተር ሳይንስ እንደመሆኑ አሪፍ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት ማግኝት ሊከብድ ይችላል ከትምርቱ አንጻር ግን ኢንተርኔት እና ኮምፒውተር ካገኘን ያው ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም አይደል የሚባለው መማር እና መስራት ነው ያን ያህል አልከበደኝም፡፡ በአቤል ብርሃኑ ከኪሩቤል ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ ጥያቄ እሺ አሁን አጀማመራችን ትንሽ ስለፈጠነ እናረጋጋውና ትንሽ ፈታ የሚያደርግህን ጥያቄ ልጠይቅህ እስቲ በጣም የምትወደው ምን ዓይነት እንስሳ እንደሆነ ንገረን? ከቤት እንስሳ ውሻ ከዱር ከሆነ ደሞ ንስር፡፡ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የሚጠቅም የትኛው ፈጠራ ነው ብለው ታስባለክ? እንደኔ አስተሳሰብ እስከዛሬ ድረስ ከተፈጠሩት እሳት ነው የሚገርመኝ። ወደ ድሮ ሄድኩኛ? . . . የሰው ልጆች ከእንሰሳት እንድንለይ አድርጎናል ማለትም እሳትን በመጠቀም ብዙ ነገር ሰርተናል። ለመኖር ምርጫ የምታደርገው ከተማ ነው ወይስ ገጠር? ገጠር ሆኖ ለከተማ የቀረበ ቦታ መኖርን እምርጣለው። ላንተ በጣም አሰልቺ የሆነው የትኛው ስፖርት ነው? አሰልቺ የጎልፍ ጨዋታ ሲሆን አሜሪካን ፉትቦል ደሞ ምንም የማይገባኝ ስፖርት ነው፡፡ እንደ ሶፍትዌር ዴቬሎፐር ምን ሰዓት ነው ለሥራ አመቺ ጊዜ (Productive Time) የምትለው? ቀን ወይስ ማታ የምትመርጠው ? ለኔ ማንኛውም ሰዓት ለመሥራት ምቹ ጊዜ ነው ብቻ ድምጽ ወይም ግርግር የሌለበት ሰዓት እና ፈጣን የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያለበት ቢሆን ይመረጣል፤ እነዚህ መስፈርቶች ደሞ የሚሟሉት ከለሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት ያለው ምቹ ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ቡና ላይ ያለክ አቋም እንዴት ነው? እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀን 1 ሊትር የሚሞላ ሳይሆን እዛ አከባቢ የሚደርስ እጠጣለው ባጠቃላይ ጠጪ ከሚባሉት ውስጥ ነኝ ያለቡና መንቀሳቅስ አልችልም ግን መቀነስ እፈልጋለው። በዚህ ጉዳይ ምን ትላለህ፡ በመደበኛ ዩኒቨርሲቲ መማር እና ኦንላይን መማር ምን አይነት ልዩነት አለው? ሁለቱም የማይገናኝ ነገር ነው ሁለቱንም ስለተማርኩት ልዩነቱን አውቀዋለሁ። በመደበኛ ዩኒቨርሲቲ መማር ጊዜን ይገድላል ብዬ አስባለሁ ከትራንስፖርት ጀምሮ እስከ ትምህርት ሰዓት ድረስ ፤ ኦንላይን መማር ግን ብዙ ጊዜ ስላለክ እና ኦንላይን እንደመሆኑ ሌሎች ነገሮችን የማወቅ እድል ታገኛልክ። 8 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ቃለመጠይቅ
አሁን ላይ እየሰራህበት ስላለው ዘርፍ ጥያቄዎችን ልጠይቅህ በአሁን ሰዓት ምን እየሰራህ ወይም ምን እየተማርክ ትገኛለህ? አንዱን ብቻ የመምረጥ እድል ቢሰጥህ የቱን ትመርጣለህ? ምርጫ ከስልክ እና ከላፕቶፕ? ምንም ምርጫ አያስፈልገውም ላፕቶፕ ነዋ! በዚህ ጊዜ ስልክ የሚመርጥ አለ እንዴ? ከWindows፣ Linux እና ከmacOS Operating System? እስካሁን በWindows እና Linux ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሰርቼበታለው ከሁለቱ ከሆነ Linux እመርጣለሁ ከሶስቱ ከተባለ ግን macOs የምመርጥ ይመስለኛል ተጠቅሜውም ባላውቅም ምርጫዬ እሱ ነው። ከነዚህ Cloud Computing Company ውጪ መስራት አይቻልም ብትባል የቱን ትመርጣለክ (Amazon Web Service(AWS), Google Cloud Platform, or Microsoft Azure)? ብዙ የሰራሁት AWS ላይ ስለሆነ ወደሱ አመዝናለው የጎግልም አሪፍ ምርት ነው። ግን AWS ይበልጠዋል፡፡ ከአይፎን ወይም ከሳምሰንግ? ሳምሰንግ የምመርጥ ይመስለኛል አይፎን የተጋነነ ዋጋ አለው ስለዚህም ሳምሰንግ ይሁንልኝ! ከኢትዮጲያ ውጪ የመኖር እድል ብታገኝ የት ትመርጣለህ? Silicon Valley ( ከፈገግታ ጋር …) ስቀልድ ነው ለመኖር ከሆነ ኒውዮርክ ነው ምርጫ የማደርገው። ሲኒየር ፕሮጀትህ ምን ላይ ነው የሰራኸው? እና አሁን ላይ ከምን ደረሰ? የዛሬን አያድርገውና የመመረቂያ ፕሮጀክቴ ትራፊክ ቅጣት ሲስተም ሲሆን ለትራፊክ ኤጄንሲ ነበር የሰራነው፤ የሚሰራውም ሞባይል አፕ እና ዌብሳይት በመጠቀም የትራፊክ ቅጣት መክፈያ ነበር። አሁን ከምን ደረሰ ከተባልኩ ደሞ . ይገርምሃል እኛ ይሄን ፕሮጀክት ስናበለጽግ ምንም አይነት በሚባል ደረጃ የኦንላይን የትራፊክ ቅጣት መክፈያ አልነበረም ስለዚህም ይህን ችግር ለመፍታት ነበር የሰራነው። ሰዎች በቀላሉ ቅጣታቸውን እንዲከፍሉ የሚያስችል የሞባይል አፕ ነበር አሁን ላይ ግን ቀጥታ ከቴሌ ብር መክፍል የሚያስችል ሲስተም ስለተሰራ እኛ ያበለጸግነው ፕሮጀችት ያን ያህል ጠቃሚ አይደለም ስለዚህም አሁን ላይ እየሰራንበት አይደለም። አሁን ላይ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ክላውድ ኮንሰልታንት ሆኜ ነው የምሰራው ከዚህ በተጨማሪም ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን Startup ድርጅት አቋቁመናል፤ ዋናው አላማው ክላውድ ሰርቪስ Startup ድርጅቶች እና ሌሎች ተቋማት ላይ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ማሳየት እና ከዚህም በተጨማሪም ቀጥታ ደንበኞችን ከድርጅቶችጋ የሚያገናኝ ሲስተም ሰርተናል። ይህ ሲስተም እንደ ኢ- ኮሜርስ ሶስተኛ አካል በግብይቱ ውስጥ የሚሳተፍበት አይደለም፤ ለጊዜው 1 ፕሮዳክት ላይ ብቻ ነው እየሰራን ያለነው። በዚህም ፕሮጀክት ላይ DevOps Engineer እና የድርጅቱም CTO ነኝ። በምድር ላይ የትኛውንም ቦታ መጎብኘት ከቻልክ ወዴት ትሄዳለህ እና በጭራሽ መሄድ የማትፈልግበት ሀገር የትኛው ነው? እእእ አፍሪካ ከሆነ እዚው ጎረቤት አገር ግብጽ ፒራሚዶችን ማየት እፍልጋለሁ ከውጪ ከሆነ ኒውዮርክ ብጎበኝ ደስ ይለኛል በጭራሽ በሄድ የማልፈልገው ደሞ አውስትራሊያ ነው ለምን ካልከኝማ እዛ ያሉት እንስሳት ብዛታቸው እዚህ ምድር ላይ ያሉ ሁላ አይመስለኝም ናሽናል ጆግራፊ ላይ እንዳየውት ከሆነ መሄድ አልፈልግም። 9 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ቃለመጠይቅ
“For any sufficiently advanced technology is indistinguishable from magic”
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> Cloud Computing እና Artificial Intelligence በኢትዮጲያ የቴክኖሎጂ እድገት መፃዒ ጉዞ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ያመጣሉ ብለህ ታስባለህ? ጥሩ ወይም የጎንዮሽ ጉዳቱ? ሁለቱም የተለያዩ ዘርፎች ቢሆኑም ተያያዥነት አላቸው። ለምሳሌ ያህል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በብዛት እየተሰራ ያለው “Cloud Computing” በመጠቀም ነው፡፡ እንደ ሀገራችን ስንመለክት ደሞ “Cloud Computing” አስፈላጊ ነገር ነው በተለይ በዚህ ጊዜ ብዙ Start-Ups እየተፈጠሩ ስለሆነ፤ የሰራናቸውን ፕሮዳክት ለማስቀመጥ እና ለመቆጣጠር ሰርቨር(ቋት) ያስፈልገናል ስለዚህም አሁን ላይ ብዙ የCloud Computing ድርጅቶች አሉ፤ የክፍያም ሥርአታቸው ደሞ በብዛት “Pay As We Go” ማለትም በተጠቀምነው ልክ ነው የምንከፍለው የሰራነው ፕሮዳክት እያደገ ከመጣ የምንከፍለውም እያደገ ይመጣል ወይም እየቀነሰ ከመጣ የምንከፍለውም እየቀነሰ ይመጣል ማለት ነው ስለዚም ለቋት የምናወጣው ወጪ ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡ ወደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስንመጣ ደሞ ዓለም ላይ እራሱ ገና እያደገ የመጣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው፡፡ በሃገራችን ውስጥ በአብዛኛው እየተሰራበት አይደለም ፤ ቢሰራበት እራሳቸውን ከቴክኖሎጂ ያራቁ ሰዎች እና ድርጅሮች ላይ በሥራ ገበያው ውስጥ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ግልጽ ነው፡፡ በዛውም ልክ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ እና እራሳቸውን የሚያሳድጉ ድርጅቶች እና ሰዎች ደግሞ ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ አሁን ላይ ግን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፕሮፌሽን ስራ ያላቸውን ሰዎች ለምሳሌ እንደ Web & Mobile Developer, DevOps ከእነዚህ ዘርፍ ጋር አብሮ የሚሰራ የሚያግዝ እንጂ በራሱ ማገናዘብ የሚችል፣ ካለ- ሰዎች እርዳታ እራሱን የሚያስተምር ፣ የሚወስን እና የሚቆጣጠር ስላልሆነ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም ነገር ግን ወደ መወሰን ደረጃ እንዲሁም እራሱን ማስተማር መቆጣጠር ከጀመረ ከሰዎች ጋር የተለያዩ ግጭቶች ሊያስከትል ይችላል ለዚህ ደግሞ መፍቴሄው አብሮ ከቴክኖሎጂ ጋር መሮጥ ያስፈልጋል። AWS ላይ እንዴት የመማር እድል አገኘህ ? ከጊቢ የወጣው ሰሞን ላይ ነበር ሊንኪዲን ላይ ያገኘሁት አፕላይ ካልኩት በኋላ AWS Restart የሚባል ፕሮግራም እዛላይ ከ3 እስከ 4 ወር ከተማርኩ በኋላ የመጀመሪያውን ሰርቲፊኬት አገኘሁ። በመቀጠልም በዛው በተማርኩበት ተቀጠርኩኝ በዚህ ሂደት ውስጥ ሌሎች ትምህርቶች የመማር እድል አገኘሁ “Solution Architect” እና “AWS Developer” እነዚህንም ተምሬ ሰርቲፋይድ ሆኛለሁ በጥቂቱም ቢሆንም ይሄን ይመስላል። AWS ላይ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች እንዴት የመማር እድሉን ማግኘት ይችላሉ ? AWS ላይ ብቻ ሳይሆን Cloud Computing ለመማር ብዙ አማራጮች አሉ ከዩቲዩብ ጀምሮ እስከ Udemy ድረስ፤ ጠቃሚ ትምህርቶችና መጻህፍቶች ስላሉ በእነሱ መሰረት መማር ይችላሉ። በነገራችን ላይ እንደዚህ አይነት ትላልቅ ድርጅቶች ለምሳሌ “AWS”, “Google Cloud”, ”Microsoft Azure” ብዙ ዴቨለፐሮችን ይፈልጋሉ ጊዜው የውድድር ስለሆነ እነሱም አፍሪካ ላይ በብዛት እየሰሩ ስለሆነ በእነሱ ፊልድ ያስተምራሉ እንዲሁም ስራ ይቀጥራሉ ያው ጥቅሙ በሁለቱም በኩል ነው፤ ማለትም በነሱ ፊልድ ወይም ፕሮዳክት “Specialize” ያደረገ ሰው ያገኛሉ በዚህም ምክንያት ፕሮዳክታቸው ወደ ስራ ይገባል የሚማረውም አካል ስራ ያገኛል ስለዚህ በነጻ ያስተምራሉ ይደግፋሉ፡፡ የት ማግኘት እንችላለን ለሚለው ደሞ Linkedin ላይ በብዛት ማግኘት እንችላለን እንዲሁም ቴሌግራም ላይ ደሞ የቴክ ቻናሎች ላይ ማግኘት እንችላለን። ለምሳሌ AI Programming እና እንደነዚህ አይነት ቻናሎች ላይ ስለሚለቀቁ እዛ ላይ ጠብቆ ማግኘት ይቻላል። አሁን እየሰራህ ባለህበት ዘርፍ የሚያጋጥመው ትልቁ ፈተና ምንድን ነው? እና እንዴት ነው እየተወጣኸው ያለከው? ዋናው ፈተና የክፍያ ስርዓቱ ነው ማለትም "Credit Card" ጉዳይ ነው። ኢንተርኔት ላይ እንደመስራታችን የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈጸም ሀገራችን ውስጥ አመቺ አይደለም ፤ እኔ እንደማስበውም ከዓለም ጋር የተሣሠረ የክፍያ ስርዓት ባለመኖሩ ምክንያት ብዙ ወደኋላ ቀርተናል። ከትምህርት ጀመሮ ኦንላይን ላይ ስራዎችን በቀላሉ እንዳንሰራ ተግዳሮት ይመስለኛል። እንዴት ፈተናውን አለፍከው ለሚለው ያው Free Trial እና ቅናሽ ክፍያዎች እያፈላለኩ ነበር የምጠቀመው በተጨማሪም አልፎ አልፎ የተለያዩ ስልጠናዎች ላይ የማገኛቸው አካውንቶችን በአግባቡ በመጠቀም ፈተናዎችን ለማለፍ ችያለሁ፤ አሁን ላይ ግን ከብዙ ልፋት በኋላ ቢሆንም የራሴ "Credit Card" አለኝ በሱ ነው የምጠቀመው። 10 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ቃለመጠይቅ
Arthur C. Clarke
AWSExpert ሰዎች ስለ ምትሰራው ስራ ምን እንዲረዱክ ትፈልጋለህ ? ብዙ ሰዎች ምንድነው የምትሰራው ሲሉኝ Amazon Web Service ላይ ስላቸው አማዞን የምሰራ እየመሰላቸው ብዙ ጥያቄ ይጠይቁኛል ግን እውነታው እንደዛ አይደለም የምሰራው አማዞን ሳይሆን የአማዞን ፕሮዳክት በሆነው Amazon Web Service በCloud Computing ላይ ነው። ይህም ማለት በሌላ ድርጅቶች እንደ "Google Cloud" ሆነ "Microsoft Azure" ሌላም እንደነዚህ አይነት ሰርቪስ የሚሰጡ ላይ መስራት ይቻላል። በዚህ አጋጣሚ እኔ አማዞን እንደማልሰራ ይታወቅልኝ ከገባው ግን እነግራቹሃለው። በዚህ የሙያ ዘርፍ ውስጥ ላለ ወይም ለጀማሪ ሰው የምትሰጠው አንድ ምክር ምንድን ነው? አሁን ላይ በዘርፉ በመማር ደረጃ ያለ ሰው የሚያድግ ፕሮጀቶች ቢጀምር ጥሩ ነው ብዬ አስባልሁ። ለምሳሌ አሁን ላይ ብዙ በቴክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያልተፈቱ ችግሮች ላይ መስራት ይቻላል በዛውም ብዙ ልምድ ስለምናገኝ በሥራ ዓለም ውስጥ ወደ ገበያው ለመግባት አንቸገርም። አዳዲስ ሃሳቦች ላይ በጋራ መስራት በዚህ ዘርፍ ላይ ያሉ የማኅበራዊ ሚዲያዎችን መከታተል እንዲሁም ትምህርት ከጨረስን በኋላ የኢንተርንሺፕ እድሎችን ስናገኝ በአግባቡ መጠቀም በተጨማሪም እውቀታችንን ሊያሳድግ፣ ሊፈትነን እና በስራ ሊያጨናንቀን የሚችሉ ነገሮች ላይ መሳተፍ እና መስራት አስፈላጊ ነው ማለት እፈልጋለሁ። በመጨረሻም ካነበብከው ከተማርከው ይጠቅማል ብለህ የምታስበው ነገር ካለ? ምን መሰላቹ በጣም የሚመቸኝ አባባል አለ Arthur C. Clarke የሚባል የጻፈው "Any sufficiently advanced technology is indistinguish -
from magic" ይህም ማለት ምን ያህል የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ለማያቀው ሰው አስማት እንደሆነ ነው፡፡ እንዲው ስናስበው ከዛሬ 100 እና 200 ዓመት በፊት የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ቢያዩ አስማት ነው የሚመስላቸው ስለዚህ በዚህ ዘርፍ ላይ ያለን ሰዎች አስማት የሆኑ ፕሮጀችቶችን እንስራ በመጨረሻም “AI Programming” ን ማመስገን እፈልጋለው። 11 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ቃለመጠይቅ
able
BY THE EDITORIAL TEAM
The Feature of
NLP IMPACT IN ETHIOPIA
IN today’s world, technology plays a significant role in our day-to-day life, and one of the instruments is Artificial Intelligence (AI) and its subfield, Natural Language Processing (NLP).
AI TECHNOLOGY HAS REVOLUTIONIZED THE TECHNOLOGICAL SPACE
IN
MANY PARTS OF THE WORLD,
AND ETHIOPIA IS NO EXCEPTION. Ethiopian innovators are looking towards AI-powered solutions to accelerate the nation’s shift towards a digital economy.
You may all remember Sophia, an AI-driven social humanoid robot armed with a plethora of features like NLP, facial recognition, and voice commands. Sophia aims to make conversational interfaces easier to use. It can assist with business queries, help navigate through banking and financial services, provide customer service assistance and answer general questions about people’s culture, language, and more. But after all the media publicity and the hype, even getting the first robot citizenship, Sophia was said to be indistinguishable from a chatbot ELIZA, one of the first attempts at simulating a human conversation according to Quartz, experts who have reviewed the robot’s opensource code state.
“ ”
>>>> >>>>>>>> >>>> >>>> >>>>>>>>>>>>
AI ዝርዝር Sophia is best categorized as a chatbot with a face. Quartz, Worldwide View 12 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine AI ዝርዝር
NEVERTHELESS, it made significant contributions to the development and the future of NLP today. Since then, various software engineers in Ethiopia have done a handful of NLP projects. One of them is Lisan.ai, a machine translation company for Ethiopian languages built by developers who knew how many languages in Ethiopia are not currently served well by Google Translate or other providers.
The Future of AI & NLP holds tremendous potential for Ethiopian software engineers.
AI
<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine AI ዝርዝር 13
THE FUTURE OF AI AND NLP HOLDS TREMENDOUS POTENTIAL FOR ETHIOPIAN SOFTWARE ENGINEERS
AI and NLP technology, by nature, is designed to mimic human intelligence, making it a powerful tool for automating many repetitive jobs associated with software engineering and development. By leveraging these advances in AI and NLP, Ethiopian engineers can elevate the quality of their work by reducing tedious process management manual labor.
AI-DRIVEN AUTOMATION CAN INCREASE PRODUCTIVITY BY ALLOWING ETHIOPIAN SOFTWARE ENGINEERS TO FOCUS MORE ON HIGH-LEVEL PROGRAMMING TASKS RATHER THAN MUNDANE DEVICE CONFIGURATION OPERATIONS.
For instance, software development portals like GitHub offer AI-driven feature recommendations, which can help reduce the time Ethiopian developers need to spend coding data into a user-friendly interface. Moreover, automated debugging and testing systems are becoming increasingly popular among software engineers as they can detect errors or defects in code much faster than humans can.
Besides automated processes and tools, AI can enable developers in Ethiopians to perform tasks using data gathered from sources all over the world in real-time. NLP is a technology that allows AI applications to understand conversational commands given in natural language by a human user. These technologies allow Ethiopia’s software engineers to provide feedback quickly on complicated questions asked by users, enabling them to build better applications with fewer iterations needed for successful results. Additionally, AI and NLP tools provide detailed explanations of certain features whenever a specific target language is required, allowing Ethiopians to localize their projects for different countries faster and with greater accuracy than traditional localization methods.
IN CONCLUSION , Artificial Intelligence & Natural Language Processing technologies are expected to revolutionize the way Ethiopian engineers develop applications and manage crucial system processes in the near future. By leveraging these advancements in machine intelligence ethical & professional manner, Ethiopian software development teams can achieve unprecedented heights more rapidly than traditional methods used hitherto!
14 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine AI ዝርዝር
በኤዲቶሪያልቡድን >>>>>>>>>>>>>>> REST APIs VS GraphQL ታች ያለው ማጠቃለያ ምስል እንደሚያሳየው ደንበኛው የሱቅ ምርት መረጃን የሚያሳይ ገፅ ሲጠይቅ እና መረጃው ሲደርስ ያሳያል። መረጃው መለያው 7 ቁጥር የሆነ ምርትን ስም፣ ብዛት እና ዋጋ የሚጠይቅ ሲሆን በRestAPI በሶስት እና በGraphQL ደሞ በአንድ ጥሪ ብቻ ሲስተናገድ ያሣያል። { products ( id, ‘7’ ) { title quatity price } } ክላይንቱ (Client) ከቋቱ (Server) ተለይቶ ከተቀመጠው የAPI መጨረሻ ቦታ ላይ ግብአቱን ይጠይቃል። እያንዳንዱ ግብአት(Resource) የተለየ መጨረሻ ቦታዎች ይኖራቸዋል። ልክ በሰዕሉ ላይ እንደሚታየው ደንበኛው ከቋቶቹ ላይ ያሉትን ሶስት ግብአቶች ለማግኘት ሶስቴ ግኑኝነቱ ተመስርቷል። ይህ ማለት ሁለት ግብአት ከፈለግን ሁለቴ መጠየቅ ይኖርብናል ማለት ነው። የGraphQL Functions አንድ ነጠላ መጨረሻ ቦታ የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ደንበኞች ከአንድ በላይ ግብአቶችን በአንድ ጥሪ ብቻ መጠይቅ ይችላሉ። - GraphQL በጠንካራ የቋንቋ ትርጉም ተተይቦ የተጻፈ ኖዶችን(Nodes) ተጠቅሞ Objectቶችን የሚወክል ነው። - የGraphQL ቋቶች Nested በሆኑ Objecቶች ስብስብ ምላሽ ይሰጣሉ። ከ 1 2 1 2 በRESTAPIላይ በGraphQLላይ >>>> >>>> ደንበኛ ግብአት 1 ግብአት 2 ግብአት 3 አጤሪራ GraphQL እና REST APIs እንዴት በተለያየ መልኩ ያነባሉ? ደንበኛ ግብአት 2 ግብአት 1 ግብአት 3 ደንበኛ ደንበኛ /TEG P r do u c t s / i d / 7 / t itle GET/ Pro du c t s / i d / 7 /pir ec GET/Products/id/7/quantity 3 15 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine አጤሪራ
6 >>>>>>>>>>>>>>>>>>>> + ሶፍትዌር ፈጠራዎች በጣም አሪፍ ሚድጆርኒ በሐምሌ ወር 2014 ዓ ም የወጣ ሲሆን ይሄን ለየት የሚያረገው እራሱን በራሱ የሚደጉም እና ኢንዲስትሪያችን ላይ አሉ በተባሉ እንደ APPLE፣ AMD ፣ TESLA፣ INTEL CTO እና GITHUB CEO ዎች ባሉ አማካሪዎች እየታገዘ ያለ ተቋም መሆኑም ነው። አሁን የዚህ ተቋም ሞዴል በሙከራ ደረጃ በዲስኮርድ መተግበሪያ በኢንቪቴሽን ሊንክ እየሰራ የሚገኝ እና በአገራችንም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እያገኘ ያለ ነው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) ባገባደድነው የፈረንጆች ዓመት ረጅም መንገድ ተጉዟል። በAI ከሚሰሩ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች እስከ ሮቦቲክስና ሌሎች ውስብስብ ማሽኖች ድረስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ባለፈው ዓመት ብቻ በAI ቴክኖሎጂ አንዳንድ በጣም የሚያስደምሙ ያልተለመዱ እድገቶችን አይተል፤ እና ይህ ጅማሮ ደሞ AI ገና ምን ያህል ሊጓዝ እንደሚችል የሚጠቁም ፍንጭ ነው። በዚህ አጠር ያለች ጽሑፍ በ2022 ከወጡ የAI ሶፍትዌር ፈጠራዎች ውስጥ በጣም አነጋጋሪ እና መሃበረሰባችን ላይ ተፅእኖ የፈጠሩትን 6 ቱን መርጠን ባጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን። በኤዲቶሪያልቡድን የAI የ2022 ሚድጆርኒ ልክ እንደ OpenAI ምርቶች DALL-E እና Stable Diffusion ተመሳሳይ የሆነ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ሲሆን፤ አዳዲስ የአስተሳሰብ ዘዴዎችን የሚመረምር እና የሰውን ምናባዊ ሃይል የሚያሰፋ ገለልተኛ የምርምር ላብራቶሪ ነው። መቼም እስካሁን ድረስ የአእምሮ ነርቭ መረባችንን ከማሽኖች ፕሮሰሰር ጋር አገናኝተን ምን እየተከሰተ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም። ታዲያ በማሽኖች እየተካሄደ ያለው ስርዓት በሰዎች እሴት እና ፍላጎት መሰረት የሚሰራ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በAI ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ GPT-3 ያሉ በጣም ኃይለኛ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው እና አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሊያመነጩ ከሚችሉት ነገሮች የማይለይ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው ሞዴሎች አሉን። ግን እኛ እንደምንፈልገው አርገው ነገሮችን ፈተውልናል ልንል አንችልም። ለምሳሌ ለአንድ የ5 ዓመት ህጻን “ጦርነት ምን ማለት እንደሆነ አስረዳ” ብንለውስ ወይም “ ህጻናት ከየት ነው የሚመጡት ወይም እንዴት ይፈጠራሉ” እና የመሳሰሉትን ብንለው ማሽኑ የሆነ ድግግሞሽን በማጥናት እና በመተንበይ “ እንዴት የኢንፊኒቲ ጽንሰ ሃሳብን(INFINITE THEORY) ለ5 ዓመት ልጅ ማስረዳት ይቻላል” ሊለን ይችላል። እኛ ግን እንዲህ እንዲለን አንፈልግም እውነተኛ መልሱን እነሱን በሚመጥን ሁኔታ እንዲመልስልን ነው የምንፈልገው። ታዲያ እነዚህን ሁኔታ ባማከለ እና የተለያዩ የሰዎች ግብረመልሶችን በመጠቀም GPT-3 ትእዛዞችን እንዴት ማስተናገድ እንደሚችል InstructGPT የሚል ሞዴል ተሰራ። ኢንስትራክትGPT በOpenAI በጥር ወር 2014 ዓ ም የወጣ ሲሆን ከGPT-3 ጋር ሲነፃፀር የእንግሊዝኛ መመሪያዎችን በመከተል የኢንስትራክትGPT ሞዴሎች የተሻሉ ናቸው፤ የተሳሳቱ መረጃዎችን እና ቢያንስ በትንሹ መርዛማ ውጤቶችን የማሳየት ዕድላቸው በጣም አነስተኛ ነው። 2 1 MIDJOURNEY INSTRUCT GPT 16 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< <<<<<<<<<<<<<<<<<<<< ገረፍ ገረፍ
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> + 5 >>>>>> ዊስፐር ከድህረ-ገጽ በተሰበሰቡ የ680,000 ሰዓታት የተለያዩ ቋንቋዎች ስብስብ የሰለጠነ እና ብዙ እንዲተገብር ክትትል የሚደረግበት አውቶማቲክ የንግግር ማሳወቂያ (ASR) ሲሆን የተለቀቀውም በOPENAI በመስከረም ወር 2015 ዓ ም ነው። የዊስፐር አርክቴክቸር እንደ ኢንኮደር(ENCODER) እና ዲኮደር(DECODER) ከጫፍ- እጫፍ ያሉ አቅርቦቶችን በቀላሉ የሚለውጥ እና የሚተገብር ነው። የግብአት ድምጹን ወደ 30 ሴኮንድ የተለያዩ ክፍሎች ከፍሎ ወደ ሎግ-ሜል ስፔክትሮግራም(LOG-MEL SPECTROGRAM) ይቀይራል እና ከዚያም ወደ ኢንኮደር ይተላለፋል። ዲኮደሮች እነዚህ የተከፈሉትን የሚዛመደውን የጽሑፍ መግለጫ ለመተንበይ የሰለጠኑ ናቸው፤ ልክ እነዚህን የተከፈሉ ነጠላ ልዩ ምልክቶች ጋር የሚመሳሰል እንደ ሐረግ፣ ሰዓቶች የተለጠፉባቸው(TIME-STAMP)፣ ጉራማይሌ ቋንቋዎች ያገኙና ከዚያም ወደንግሊዘኛ ይተረጎማሉ። ይህን ከሌላው የትርጉም እና ጽሑፍ ጀነሬተሮች የሚለየው ሞዴሉ ድምጾችን የማወቂያ ዘዴ አብሮት በመካተቱ ነው፤ ከዚህም በተጨማሪ ፈጣን ነው። ይህ ሞዴል OPENSOURCE ስለሆነ ከGITHUB የሙከራ ኮድ ወስደን በራሳችን ድምጽ ወደ ጽሑፍ እንዲቀይርልን አጭር ኮድ እየጻፍን መሞከር እና ከዚያም በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ፕሮዳክቶች ላይ መተግበር እንችላለን። ቻትGPT ተጠቃሚዎች ከደንበኞች ጋር በተፈጥሯዊ የንግግር ዘይቤ እንዲግባቡ የሚያስችል አውቶሜትድ የውይይት መሳሪያ ነው። በማንኛውም አይነት የመልእክት መለዋወጫ መድረክ ላይ የተጠቃሚ ጥያቄዎችን ለመረዳት እና ምላሽ ለመስጠት የላቀ የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ እና የማሽን መማሪያ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። ይህም ልክ እንደ WHISPER የተለቀቀው በOPENAI ህዳር ወር 2015 ዓ ም ሲሆን የተሰራውም በGPT-3 ትልቅ የቋንቋ ሞዴል ላይ ነው። GPT-3 ከ45GB በላይ በሆነ ሰፊ የውይይት መረጃ ከድህረ-ገጾች፣ ከመጻሕፍት፣ ብሎጎች፣ ዊኪፒዲያ እና ሌሎችም ሠልጥኗል። በተጨማሪም ሞዴሉ ረጅም ንግግሮችን የመረዳት ችሎታውን የሚያሻሽሉ ሞዴሎች እና ቴክኒኮችን አካቷል። በእነዚህ ባህሪያት እገዛ ቻትGPT አውዱን በመረዳት እና የተለያዩ ጥያቄዎችን ሰፋ ባለ መልኩ ምክንያታዊ ምላሾች በትክክል የመመለስ አቅሙ ከፍተኛ ነው። የቻትGPT ዋና ባህሪያት ያካተቱት ፡ የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀናበር(NLP)፤ በማሽን መማር ላይ የተመሰረተ ምላሽ ጀነሬተር (ML)፤ እውቀትን መሰረት ያረግ ውህደት፤ በፍቃደኝነት የተመሰረተ የሰዎች እርዳታ እና ትንተናዎችን ያካትታሉ። DALL·E በOPENAI በጥር 2014 ዓ ም የወጣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስርዓት ሲሆን ይህ አዲስ አይነት ስርዓት የተጠቃሚዎችን የተለየ የአይምሮ ፈጠራ አስተሳሰብ በጽሑፍ መልክ ተቀብሎ ከዚህ በፊት ወዳልነበረ የፎቶግራፊ ምስሎች ይለውጣል ለምሳሌ “ ጉንዳን ባስኬት- ኳስ ዳንክ ስታረግ” ብለን ማለት ነው። በ ህዳር ወር 2015 ዓ ም ጀምሮ ደግሞ በአዳዲስ ባህሪያት ልክ እንደ ኢን-ፔንቲንግ(IN-PAINTING) እና እነዚህን ስርአቶች መጠቀሚያ API ተጨምሮ ወጥቷል ይህም ማለት ከተጠቃሚው ምስል ወስዶ የተወሰነ ቦታን ምንም በማያስታውቅ መልኩ በሌላ የሚተካበት እና የተለያዩ አይነት አማራጮችን ጀነሬት የሚያደርግበት። ስቴብል ዲፊውዥን ማንኛውንም አይነት ጽሑፎች ወደ ምስል መቀየር እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ሞዴል ነው። በቀላሉ የምንፈልጋቸውን ምናባዊ ምስሎችን በመጻፍ ብቻ አስደናቂ የሆኑ ምስሎችን መስራት እንችላለን። ምንም እንኳን ስራቸው ከሚድጆርኒ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ይሄ ለየት የሚያረገው ኢን-ፔንቲንግ እና አውት-ፔንቲንግ(in-Painting & out-Painting) ስዕሎችን ኤዲት በማረግ እና በሰጠነው በመመስረት ተመሳሳይ ምስሎችን በተለያየ አኳኋን ጀነሬት በማድረጉ ነው። ይህ ሞዴል በሐምሌ ወር 2014 ዓ ም ከStability.ai እና Runway በተጨማሪ ሙኒክ ውስጥ ከሚገኘው Ludwing Maximilian ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው የመጀመሪያ ሞዴሉ የተለቀቀው። 3 4 6 STABLE DIFFUSION WHISPER CHAT GPT DALL·E + API 17 <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine
AVATAR Behindthe Scene of The Way of Water
By now, you have seen Avatar: The Way of Water film in theaters or, like most people waiting for the February digital release to see it at home. In this article, we will explore the BTS (Behind the Scenes) of Avatar 2, and don't worry, I will not disclose the storyline, or it's free from a spoiler alert. So buckle up, and let's dive into it.
by Addisu Hailemariam
vatar 2 is the sequel to James Cameron’s 2009 Oscar-winning science fiction movie Avatar. Although it is not like the first film, this sequel is making a significant record, more visually spectacular experience as it makes use of cutting-edge artificial intelligence technology.
In Avatar 2, the filmmakers have incorporated AI technology to create a more believable and detailed world for viewers. Instead of relying on CGI (computer-generated imagery) alone, the team has created an AI system that can detect and recreate minute details such as individual strands of hair, wrinkles in clothing, and realistic facial expressions.
This allows them to create a more immersive, lifelike experience than ever before.
The advances in AI technology are vital in bringing Cameron’s vision to life and making it possible for him to produce a film with such an enormous scope.
For example, instead of using their time creating thousands of detailed sets or costumes by hand, the AI system can quickly generate accurate 3D models from existing blueprints, allowing production to move forward faster.
Furthermore, Cameron can interact with characters directly through motion capture technology, enabling him to direct his actors without having them physically present on set.
A >>>>>>>>>>> >>>>>>>>>>> 18 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< <<<<<<<<<<<<<<<<<<<< መዝናኛAI
>>>>>>>>>>> 19 <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine
The implications of Avatar 2’s use of artificial intelligence technology go far beyond just this film: it can revolutionize filmmaking on a large scale as Hollywood directors become increasingly reliant on high-tech computer systems. Future films may use powerful deep learning algorithms that can analyze audience data and enable filmmakers to craft stories explicitly tailored towards their target audience efficiently. Similarly, motion capture technologies could bridge the gap between traditional live-action shooting and CGI animation – providing studios with cheaper alternatives for scenes that would otherwise be uneconomical or impossible due to cost constraints.
How Technology is Revolutionizing Filmmaking in Hollywood
20 መዝናኛAI
Furthermore, AI techniques developed for Avatar 2 may end up helping other industries, such as architecture and interactive visualizations, giving them access to powerful digital tools that can shape their future projects with amazing speed and accuracy. In other words, Avatar may become one of the most influential films of its time – not just for movie-making but also for other industries that take advantage of digital technologies such as artificial intelligence in innovative ways.
All these factors indicate that with the increased use of artificial intelligence technology brought by films like Avatar 2, cinema-goers should expect much more realistic effects when they watch films in the future. Leading us further into unchartered territory as we explore new possibilities made available by this cutting-edge technology used creatively within movies today.
HAVE A BREAK HAVE A FUN
>>>>>>>>>>>
21
“By leveraging deep learning algorithms and analyzing audience data, filmmakers of the future will be able to quickly and efficiently create cinematic stories that are tailored to their target audiences.”
በብዛት በጥር ወር መጨረሻ የትምህርት ቤቶች ግማሽ አመት መገባደጃ ስለሆነ ብዙዎቻችሁ ከፈተና መልስ እስከ ታህሳስ ሁለተኛ ሳምንት ድረስ እረፍት ታረጋላችሁ አንዳንዶቻችሁ ደሞ የፈረንጆች አዲስ አመት፣ የገና በዓል እና ጥምቀት በዓል እረፍት ወደ ቤተሰቦቻችሁ ቤት ትሄዳላቹ። ታዲያ በዚህ እረፍት እና ጉዞ እነዚህን ጥቆማዎች እንደ ብልህ ሰው እራሳችሁን በራሳችሁ ለማስተማር እና ከተለያዩ የኢንዱስትሪ ባለሟሎች ልምድ ለመቅሰእም ልትጠቀሙባቸው አልፎም አንዳንዶቹን ደሞ የቀንተቀን ስራቹ ላይ ልትተገብሯቸው ትችላላቹ። በኤዲቶሪያል ቡድን ይህመጽሐፍስለ ዌብሳይት ማበልጸግም , ሆነ ስለምንም ኮድ መጻፊያ መሳሪያዎች አይደለም " " ይህ መጽሐፍ ለዌብ ዲዛይነሮች፣ ፍሪላንስ ዲዛይነሮች፣ ዌብሳይት አበልጻጊዎች፣ እና በጠቅላላው Creative ስራ ላይ ተሰማርተው ላሉ የሙያ ባለድርሻዎች የተለያዩ መለማመጃ ፋይሎች፤ የዲዛይን ኮንትራቶች እና Briefings ፤ ከዊብሳይት አበልጻጊዎች ጋር በቀላሉ ለመግባባት እና ችሎታችሁን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለማሳደግ በጣም ተመራጭ ነው። ይህ በዋናነት ስለ ዌብሳይት ዲዛይን እና ፊግማ(Figma) ነው። እናንተ ሊኖሯቹ የሚችሉትን ሁሉንም የዲዛይን ነክ ጥያቄዎች እና የፍሪላንስ ስራ ለመስራት ባጠቃላይ በዌብሳይት ዲዛይን የተሻለ ለመሆን ይረዳቹኋል። 1. THE ULTIMATE GUIDE TO WEB DESIGN መጽሐፍውስጥስለተለያዩየWebsiteDesignFrontend ቴክኒኮችእናስለFreelancingስራመንገዶች በስፋትይተነተናል። በተጨማሪም በፊግማ App የተለያዩ ዌብሳይቶችን የብራንዲንግ ጽንሰ ሀሳብን በመንተራስ እንደ ከለር፤ መልከ ፊደል (Typography) አቀማመጥ እና አጠቃቀም ከአዳዲስ ቴክኒኮች ጋር ጥሩ በሆነ ሁኔታ ይተርካል። ጠቃሚ ጥቆማ >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> ዓመተ ምህረት፡ 2022 GC የገጽ ብዛት፡ 348 የፋይል ትልቀት፡ 76.3 MB የፋይል አይነት፡ PDF ዋጋ፡ $40 22 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ጠቃሚ ጥቆማ
2. MILANOTE ሜላኖትሰዎችየፈጠራ ፕሮጀክቶቻቸውንእንዲያደራጁ ለመርዳትታስቦየተሰራነው። በተለይ ለCreative ሰዎች በጅምር ደረጃ ላይ ያለ ሃሳቦቻቸውን እቅድ ለማውጣት ሲፈልጉ እና Flexible የሆነ ቦታ ሲፈልጉ ለምሳሌ የፕሮጀክት ወይም የተለያዩ ሃሳቦችን Brainstorm ለማድረግ፣ መነሳሻዎችን ለመሰብሰብ ወይም እቅድ ለማውጣት በመጀመሪያ ደረጃ ተስማሚ የሆነ መተግበሪያ ነው። ይህGuideወይምመጽሐፍልትሉትትችላላቹለማንኛውምWebsite Developerልምድያለውምሆነየሌለውየሚሆንነው። በዚህ እጥር ምጥን ያለች መጽሐፍ ውስጥ ስለ ተለያዩ የWebsite Development መንገዶች እንደ Frontend, Backend, FullStack, Freelancing በስፋት ይተነተናል በተጨማሪም ስለህይወቱ ተሞክሮ እያወራ ምን አይነት RoadMap (ፍኖተ- ካርታ) ብንከተል መልካም እንደሆነ ይዘረዝርልናል። የዚህ መጽሐፍ ጸሀፊ Brad Traversy (ብራድ ትራቨርሲ) ይባላል ብዙዎቻቹበተለያዩፕላትፎርሞችላይሲያስተምርታቁታላቹ፤ለፕሮግራመሮች ስለሱከዚህበላይማውራትለቀባሪውሞትንማርዳትይሆናል።ብራድይሄን ሲጽፍለሚሰራቸውቪዲዮዎችእንደማስረጃGuideአርጎስለሆነእንደሌሎቹ መጽሐፎችፎርማቲንግእናኤዲትላይእንደጠበቃችሁትላይሆንይችላልግን ዋናውአላማእኛእንድንረዳውማድረግስለሆነችግርየለውም። 3. BRAD TRAVERSY'S WEB DEV GUIDE ዓመተ ምህረት፡ 2022 GC የገጽ ብዛት፡ 306 የፋይል ትልቀት፡ 7.7MB የፋይል አይነት፡ PDF ዋጋ፡ $9.99 23 running title <<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<< AI PROGRAMMING magazine ጠቃሚ ጥቆማ
to “AI Programming Community ”
We released this issue which explores a range of topics from cutting-edge AI technologies to the NLP impact on Ethiopian software engineers. Also, it’s the first magazine for us.
To deliver this top-notch publication, we leveraged the latest research from our own team insights, analysis, and opinion pieces from our little AI community leaders. Through these efforts, we hope to create an inclusive platform utilizing passionate writers from Ethiopia to share their perspectives on critical technological advancements and, of course, to improve the country’s AI technologies.
We aim to reach out to the community to foster engaged readers eager to learn more about rapidly evolving digital technology. We encourage conversation with technical professionals and nonexperts alike, and you are all welcome to send us your thoughts and feedback through our contact methods and emails below. We couldn’t have completed this issue without the dedication of our team.
While we move to the next issue, we are confident that we will continue delivering engaging content that touches new topics changing our world daily.
AI Programming
THIS TECHNOLOGY MAGAZINE IS PUBLISHED BY SILTAWI’S GROUP AI PROGRAMMING. © 2023 | ALL RIGHTS RESERVED.