AMISOM Magazine - Issue 22 - Amharic

Page 1

www.amisom-au.org |

እትም 22

|

ሽግግሩ

ከጁላይ - ዲሴምበር 2017

አሚሶም መጽሔት

1


ከኤስ.አር.ሲሲ የተላከ

መልዕክት

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለሶማሊያ ልዩ ወኪል፣ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማድሪያ

አሚሶም ቀጣይና ተከታታይነት ያለው የወታደሮች አንቅስቃሴ በተለያዩ ቦታዎች በማድረግ እየተካሄደ ላለው የተጠባባቂ ሀይል የማሸጋሸግ ስራ ላይ በማነጣጠር የሰላምና ደህንነት የሽግግር ዝግጁነት ኦፕሬሽኖችን በመላው ሶማሊያ በማኪያሄድ ላይ ይገኛል” — የአፍሪካ

ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለሶማሊያ ልዩ ወኪል፣ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ካቴኖ ማድሪያ

2

አሚሶም መጽሔት

አሥር አመታት በፊት በችግር ላይ ለሚገኙ አጋሮች የተሰጠው ምላሽ የአልሸባብን አማጺያን ከአገሪቱ ዋና ከተማ ከሞቃዲሾና በደቡባዊ ማዕከላዊ ሶማሊያ ከሚገኙ ሌሎች ቁልፍ ከተሞች ለማስወጣት ከኢትዮጲያ፣ ዩጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጂቡቲ፣ ቡሩንዲና፣ ኬንያ በተወጣጡ ሰላም አስከባሪዎች የተደረገውን በአፍሪካ ትልቁን የድጋፍ ኦፕሬሽን ፈጥሯል፡፡ ዛሬ የሶማሊያን ሰላም ለመመለስ የተደረገውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ወደኋላ መለስ ብለን ስናይ ከፍተኛ እርካታ ነው የሚሰማን፡፡ በአገሪቱ የብሄራዊ ጸጥታ ንድፍና የአገር መከላከያ ስትራቴጂ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የጸጥታ ኃይሎች አላማቸውን ለማሳካት ባደረጉት እንቅስቃሴ ላሳዩት ቁርጠኝነትና ጽናት ያለኝን ልባዊ አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ በታቀደው የመውጣት ዕቅድ መሠረት የአሕ የሰላም አስከባሪዎች የቁልፍ ከተሞችን የጸጥታ ማስከበር ሥራ በሁኔታዎች ላይ በተመሠረተ የሽግግር ዕቅድ መሠረት ለሶማሊያ ኃይሎች ያስረክባሉ፡፡ ከፊታችን የሚጠብቀን ተግባር አስቸጋሪ ሊሆን የሚችል ቢሆንም አሚሶም የሶማሊያን የጸጥታ ፍላጎት የማሳካት አቅም ያለው ጠንካራና አስተማማኝ ኃይል ትቶ እንደሚሄድ እተማመናለሁ፡፡ ይህን አላማ እውን ለማድረግ የአጋሮቻችንን ሙሉ ድጋፍ ይጠይቃል፡፡ ከሁሉም በላይ የጋራ ራዕይ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ጸረ ሽብር ውጊያውን በአሸናፊነት ለመወጣት የአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች የሁሉንም ተራ ዜጎች ሙሉ ድጋፍ ማግኘት አለባቸው፡፡ አሚሶምና የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት አማጺዎችን በማዳከም የተገኘው ድል የማይቀለበስ መሆኑን ለማረጋገጥ ሰላም አስከባሪዎች ለቀው በሚወጡበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ይቀጥላሉ፡፡ በሽግግሩ ጊዜ አሚሶምና የሶማሊያ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይሎች (ኤስኤንኤስኤፍ) የአማጺያንን ለመደምሰስ የሚደረገውን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማጠናቀቅና አዲስ የአቅርቦት መስመር ለመክፈት ከጥምር ኦፕሬሽን ኃይሎች ጋር በትብብር መሥራት ይቀጥላሉ፡፡ በተጨማሪም ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ሌላው ተግባር የሲቪሎች ጥበቃና ህዝቡ ከችግር ወጥቶ ያለምንም እንቅፋት የእለት ተእለት ተግባሩን በነጻነት ማከናወን የሚችልበትን አመቺና አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አሚሶም የጸጥታ ኃላፊነቱን በማሳረከብ ለሚደረገው ሽግግር አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር በመላው ሶማሊያ በሚገኙ በርካታ የግንባር ኦፕሬሽን ቤዞች የሰላም አስከባሪዎችን ተልእኮ ለማጠናከር በርካታ የሰራዊት ንቅናቄ አድርጓል፡፡ በመጪዎቹ ሳምንታት ያለውን የጸጥታ አገልግሎት በማያዛባ ሁኔታ የአሚሶም ኦፕሬሽን ፍሬ ታሳቢ ሆኖ የሚቀጥለውን የሶማሊያን ሕዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ የአሚሶም ስትራቴጂዊ የሠራዊት ንቅናቄ ይቀጥላል፡፡. መልካም ንባብ!


ማውጫ 2.

የኤስአርሲሲ መልእክት

3.

ከዜና ማህደር

8.

ለወታደራዊ ቅነሳ የሚደረግ ሽግግር

10. ወታደራዊ ዘመቻ ሂደት 12. በጠላት ላይ በትብብር መሥራት 14. አሚሶም ጸረ ፈንጂ ጥረቱን አጠናክሯል 16. ሶማሊያ የመጀመሪያውን ከፍተኛ የጸጥታ ኮንፈረንስ አስተናገደች

በየአመቱ ሴፕቴምበር 21 ቀን ለሚከበረውን አለማቀፍ የሰላም ቀን ዝግጅት ላይ አንድ ወጣት የአለምን ቅርጽ በሶማሊያ የወደብ ከተማ ኪስማዮ የባህር ዳርቻ ላይ እንደ ሰላም ተምሳሌትነት በሥዕል መልክ ሲሰራ፤ ሴፕቴምበር 18 ቀን 2017፡፡ ሶማሊያዊያን ለዘላቂ ሰላም መስፈን በህብረት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ፎቶ፡ አህ - የተ.መ. አይኤስቲ

18. የሶማሊያን የጸጥታ ኃይሎች ማጠናከር 20. በግጭት ውስጥ የሕጻናትን ለወታደራዊነት ጥቅም ምልመላን መከላከል 21. አሚሶም ለሶማሊያ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ አስረከበ 23. አይቲኤፍ የሶማሊያን የሲቪል-ወታደራዊ የሥራ ቡድን ሪፖርት ይፋ አደረገ

ዲዛንይና ሌይአውት፡- ኤዩ-ዩኤን አይሲስቲ ፎቶግራፍ፡- ኤዩ-ዩኤን አይሲስቲ ኒውስሩም ¦ thenewsroom@auunist.org ኢ-ሜይል፡ amisommediacentre@gmail.com ፖ.ሣ.ቁ. 20182-00200፣ ናሮቢ፣ ኬንያ፣ ስልክ ቁጥር +254 202 713 755 /56 /58 ፋክስ፡- +254 202 713 766 አሳረታሚ፡ የአሚሶም ፐብሊክ ኢንፎርሜሽን ዩኒት

24. አሕ ለድርቅ ተጎጂዎች አስቸኳይ እርዳታ ላከ 25. አሚሶም በጨረፍታ እይታ 29. የጎሳ ግጭትን ለማስቆም ማኅበረሰቦች እግር ኳስ ይጠቀማሉ 30. ሶማሊያ ከድተው ለሚመለሱ መልሶ ማቋቋም ቀዳሚ ትኩረት ሰጥታለች 31. ፖሊሳዊ አገልግሎት በሶማሊያ 35. የሞቃዲሾ ሶስተኛው አመታዊ የመጻፍት አውደ ርዕይ

አሚሶም መጽሔት

3


ከዜና

ማህደር

2017 ጁላይ

11

የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ለ10 አመታት በቁጥጥሩ ሥር የነበረውን የሶማሌ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተቋም ግቢ በይፋ ለፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣኖች አስረከበ፡ የአፍሪካ ሕብረት የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርሲቲውን በአነስተኛ የግንባር ኦፕሬሽን ቤዝነት በ2007 የተቆጣጠሩ ሲሆን ከዚያ ወዲህ በአልሸባብ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ ለማስተባበር ከዚያም ከሌሎች የአፍሪካ ሕብረት ሰማል አስከባሪዎች ጋር በመተባበር ሚሊሻዎችን ከሞቃዲሾ ለማስወጣት በተደረገው ዘመቻ ወደ ባታሊዮን ዋና መ/ቤት አድጓል፡፡ ርክክቡ በተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ ድጋፍ ጽ/ ቤት የተመራውን የእድሳት ሥራ ተከትሎ ለመማሪያ ተቋሙ እንደገና መከፈት መንገድ ጠርጓል፡፡

2017 ጁላይ

17

2017 ጁላይ

29

4

አሚሶምና ተመድ በጋልካስዮ ትምር የፖሊስ ፓትሮል ሥልጠና ጀመሩ፡፡ በአሚሶምና በተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ የድጋፍ ተልእኮ (አንሶም) የተዘጋጀው ጥምር ሥልጠና አላማው ከፑንትላንድና ከጋልሙዱግ ስቴቶች የተወጣጡ የፖሊስ ኦፊሰሮችን በተኩስ አቅም ስምምነቱ እንደ አንድ አካል በጋልካሲዮ ጥምር ልምምድ እንዲደርጉ ለማዘጋጀት ነው፡፡ ሥልጠናው በፑንትላንድና በጋልካሲዮ ስቴቶች ፕሬዜዳንቶች ጃንዋሪ 1 ቀን 2017 በጋልካሲዮ በተፈረመው የተኩስ አቅም ስምምነት መሠረት ነው የተካሄደው፡፡ በስምምነቱ መሠረት ከሁለቱም ስቴቶች የተወጣጡ የፓትሮል ቡድኖች በሁለቱ አስተዳደሮች መካከል የተኩስ አቁም ለማጠናከር የሚረዳ ሥልጠና ያገኛሉ፡፡

2017

የአፍሪካ ሕብረት ተልእኮና የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጥምር ስብሰባ በሁኔታዎች ላይ በተመሠረተ የአሚሶምን ሰላም አስከባሪዎች መቀነስ በሚቻልበት መንገድ ላይ የጋራ መግለጫ አወጣ፡፡ በአገሪቱ መዲና በሞቃዲሾ የተካሄደው ስብሰባ ተልእኮው የሶማሊያን ብሄራዊ የጸጥታ ኃይሎች (ኤስኤንኤስኤፍ) አቅም በመገንባት የአገሪቱን የጸጥታ ጥበቃ ተግባር ኃላፊነት ለማሸጋገር ዝግጁ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ለአሚሶም “በቂና ተገማች” የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ በማቅረብ ተጠናቋል፡፡

አሚሶም መጽሔት

ኦገስት

13

አለም ጤና ድርጅት (ደብልዩኤችኦ) ሶማሊያ ለሶስት ተከታታይ አመታት ከፖሊዮ ነጻ መሆኗን በይፋ አስታወቀ፡፡ ሆኖም የተመድ ድርጅቱ ቫይረሱ እንደ አዲስ ወደአገሪቱ እንዳይገባ ጠንካራ የመከላከል እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበትም ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህን ያስታወቁት የደብልዩኤችኦ የምሥራቅ ሜዲትራኒያን ክልላዊ ዳሬክተር ዶ/ር መሐሙድ ፊቅሪ እለቱን ለማክበር በሶማሊ መዲና በሞቃዲሾ በተከበረው ሥነ ሥርአት ላይ ባሰሙት ንግግር ነበር፡ ፡ በሁነቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሶማሌ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ‘ፋርማጆ’ ባሰሙት ንግግር. “ዛሬ ትልቅ ክንውን ነው የምናከብረው፡፡ ሆኖም ሥራችን ገና እንዳልተጠናቀቀ መርሳት የለብንም፡፡ አለም ፖሊዮን ለማጥፋት በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ እንደ ሶማሊያ ለመሰሉ አገሮች ፖሊዮ ከፍተና ስጋት ሊደቅን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማድረግ ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡


2017 ኦገስት

24

ተባበሩት መንግሥታት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸኃፊ ጄፍሪ ፌልትማን በሶማሊያ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ለሶማሊያ መንግሥትና ሕዝብ ወዳጅነትን ለማሳየትና የተባበሩት መንግሥታት ለአዲሱ መንግሥት የሚሰጠውን ድጋፍና አገሪቱ በቅርቡ በተከሰተው ድርቅና የጸጥታ ችግር የገጠማትን ተግዳሮት መቅረፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከሚመለከታቸው የአመራር አካላት ጋር ተከታታይ ውይይት አድርገዋል፡፡

2017

ሴፕቴምበር

ሚሶምና አጋሮቹ ባለፉት ሶስት አመታት በሶማሊያ የተደረገው የሰብአዊ እርዳታ እንቅስቃሴ ያስገኘውን ውጤት በዝርዝር የሚያስቀምጠውን የአይቲኤፍ የሶማሊያ የሲቪልና ወታደራዊ የሥራ ቡድን ሪፖርት ይፋ አደረጉ፡ ፡ በአሚሶምና በተመድ የሰብአዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ ቤት (ዩኤንኦሲኤችኤ) በጋራ የተዘጋጀው ሪፖርት ሶማሊያ ፈጣን የአደጋ ምላሽ ለመስጠት በምታደርገው እንቅስቃሴ የአገሪቱን የወደፊት የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽን

7

2017

ሴፕቴምበር

21

በየአመቱ የሚከበረው አለማቀፍ የሰላም ቀን በሶማሊያ ግጭትን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቋምን በሚያራምዱ ወጣቶች በተደረገ የድጋፍ ሰልፍ ተከብሮ ውሏል፡፡ ወጣቶች ሰላምን ለማስፋፋት በግል ቃል ገብተዋል፡፡ አለማቀፍ የሰላም ቀን የአለም ሰላምን ኃላፊነት ለማጠናከር በማሰብ እኤአ በተመድ ውሳኔ ከ1981 ጀምሮ በመላው አለም የሚከበር እለት ነው፡፡

2017

ኦክቶበር

9

የሚመራበትን አቅጣጫ ለመምራት የሚረዳ ነው፡፡ ሪፖርቱ ይፋ በተደረገበት ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙት ምክትል ኤስአርሲሲ ሲሞን ሙሎንጎ ባደረጉት ንግግር “በወታደራዊና በሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች መካከል ምን አይነት የተሻለ የሥራ ግንኙነት መኖር እንዳለበት የሚያጤን የሲቪል-ወታደራዊ የሥራ ቡድን ሪፖርት ሲወጣ በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው፤ ዝግጅቱም በከፍተኛ ጥንቃቄ መከናወን ያለበት ነው” ብለዋል፡፡

2017

ኦክቶበር

አፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ከፍተኛ አመራሮች ለሁለት ቀን በተካሄደው የስትራቴጂያዊ ኮምኒኬሽን ማስተር ክላስ መድረክ የአሚሶምንና የሶማሊያን ስኬቶች ግልጽ ማድረግ የሚቻልበትን ውጤታማ መንገድ ለመፈለግ በሞቃዲሾ ተገናኝተዋል፡፡

3

መሪዎቹ በኮምኒኬሽን በተለይም ገዥ በሌለው የዲጂታል መገናኛ መድረክ ያሉትን የተለያዩ ተግዳሮቶች በመቋቋም የአሚሶም የስትራቴጂያዊ ኮምኒኬሽን ፍላጎት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ፍላጎት ማጣጥም በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ሃሳብ አንሸራሽረዋል፡፡ በማስተር ክላሱ የምክክር መድረክ የመክፈቻ ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙት የፌዴራል ማስታወቂያ ሚኒስትር ሚ/ር አብዲራህማን ዩሱፍ ያሪሶ ባደረጉት በንግግር “የተቀናጀ የኮምኒኬሽን አሠራር እንዲኖረን ማድረግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ጠላታችን አንድ ብቻ ነው፤ ይህም በአልሸባብ ቅርጽ የሚገለጸው ጽንፈኝነት ነው፤ የብተና ምልክት የሚፈልግ ጠላት ነው” ብለዋል፡፡

ኡጋንዳ 55ኛ አመት የነጻነት ቀን የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ሃሰን አሊ ካይሬ በተገኙበት ተከብሮ ውሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት አሠርት አመታት የቆየውን የሶማሊያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆምና በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የኡጋንዳ መንግሥት ላደረገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡ ፡ ይህን የተናገሩት ሞቃዲሾ በሚገኘው የኡጋንዳ ኤምባሲ በተዘጋጀው ሥነ ሥርአት ላይ ነበር፡፡ አሚሶም መጽሔት

5


2017

ኦክቶበር

10

2017

ኦክቶበር

16

የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) በመሠረታዊ የወንጀል ሥፍራ አያያዝ ዙሪያ ለደቡብ ምዕራብ ስቴት የፖሊስ ኦፊሰሮች በክልሉ የአስተዳደር መዲና በባይዶዋ የ10 ቀን ሥልጠና አካሂዷል፡፡ በአሚሶም ፖሊስ የሚሰጥ ተከታታይ ልዩ የሥልጠና ፕሮግራም አካል በሆነው በዚሁ ሥልጠና ከወንጀል ምርመራ መምሪያ (ሲአይዲ) የተወጣጡ ሃያ አራት ኦፊሰሮች ተሳትፈዋል፡፡

አሚሶም ሰላም አስከባሪዎችና ሲቪል ሠራተኞች ኦክቶበር 14 ቀን በሞቃዲሾ ለደረሰው ጥቃት ተጎጂዎች ድጋፍ የሚውል የደም ልገሳ አደረጉ፡፡ በአሚሶም የኃይል ዋና መ/ቤት በተከናወነው በሌ/ጄኔራል ኦስማን ኑር ሱባግሌ በተመራው የደም ልገሳ ዘመቻ ጄኔራሉ አለም ለእነዚህ ተጎጂዎች ድጋፉን በመስጠት ወዳጅነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ “ለሶማሌዎች ማስተላለፍ የምፈልገው መልእክት አልሸባብ የህዝብና የሰብአዊነት ጠላት ነው የሚል ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ጤነኛ ቢሆኑ ኖሮ ተራ ሰላማዊ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ ባላደርጉም ነበር፡፡ አልሸባብ የሚዋጋው ከአሚሶም ጋር ወይም ከሶማሌ የጸጥታ ኃይሎች ወይንም በአገሪቱ ከሚገኝ ለማንኛውም ሌላ ሠራዊት ጋር ነው ብለው የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ማወቅ ያለባቸው አልሸባብ የሁሉም ሱማሌዎች ጠላት መሆኑን ነው” ብለዋል ሌ/ጄኔራል ኡስማን ኑር ሱባግሌ፡፡

2017

ኦክቶበር

25

2017

ኖቬምበር

7

አራተኛው የምርጫ አስፈጻሚ አካላት አመታዊ አህጉራዊ መድረክ በአፍሪካ በሚካሄዱ ምርጫዎች ወጣቶች ለሚጫወቱት ቁልፍ ሚና እውቅና በመስጠት በሩዋንዳ፣ኪጋሊ ተካሂዷል፡፡ በዚህ የሁለት ቀን መድረክ በምርጫ ምርጥ ተሞክሮዎችና በአህጉሪቱ በሚካሄዱ ምርጫዎች አመራር በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ አሚሶም በመድረኩ የሶማሌን ብሔራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን (ኤንአይኢሲ) አባላት ተሳትፎ አመቻችቷል፡፡

6

አሚሶም መጽሔት

የአፍሪካ ሕብረት (አሕ)፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ዩኤን)፣ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት (ኤፍጂኤስ) እና ሌሎች ቁልፍ አጋሮች ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች ተገደሉበትን ኦክቶበር 14 ቀን በሞቃዲሾ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ለመከለስ የቀውስ ስብሰባ አድርገዋል፡፡ በአሚሶም በተዘጋጀው የተመድ ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ምክትል ልዩ ተወካይ (ዲኤስአርኤስጂ) ሬስደን ዜንጋ፣ የመከላከያ ሠራዊት ዋና ኤታማዦር ሹም (ሲዲኤፍ) ሜ/ጄኔራል አብዲዌሊ ጃማ ሁሴንን ጨምሮ የኤፍጂኤስ ከፍተኛ የጸጥታ ኃላፊዎች በተሳተፉበት በዚህ የቀውስ አመራር ቡድን ጥምር ስብሰባ ወደፊት ሊቃጡ የሚችሉ ጥቃቶችን ለማስቀረት መወሰድ ባለባቸው ቁልፍ እርምጃዎች ላይ የጋራ ስምምነት ተደርሷል፡፡


2017

ኖቬምበር

11

በአገሪቱ ጸጥታ አጠቃላይ አቀራረብ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልእኮ ጥምር ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በስብሰባው ሶማሊያ በአገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች፣ በአጠቃላይ የጸጥታ አቀራረብ ዙሪያ በታዩት ለውጦችና አሁን በሚታዩት ክፍተቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በስብሰባው ከፌዴራል የሚኒስቴር መ/ቤቶች፣ ከፌዴራል አባል ክልሎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ከአሚሶምና ከአለማቀፍ አጋሮች የተወጣጡ ልኡካን ተሳታፊ ነበሩ፡፡

2017

ኖቬምበር

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ጉዳይ ልዩ ተወካይ (ኤስአርሲሲ) እና የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ኃላፊ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይሬ የተመራውን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የልኡካን ቡድን አስከትለው በታችኛው ሸበሌ ክልል በምትገኘው ስትራቴጂያዊ የወደብ ከተማ በባራዌ የጸጥታ ሁኔታ የግምገማ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ልኡካኑ ከአካባቢው ህዝብና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ተገናኝቶ ውይይት አድርጓል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ካይሬ አሚሶም ሱማሌዎች የጸጥታ ማስከበር ሥራውን ኃላፊነት ተረክበው ለመምራት ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ ወደብ ከተማዋን ጸጥታ ለማስከበር የሚያስችለውን ማንኛውንም ድጋፍ ከፌዴራል መንግሥት ማግኘት እንደሚቀጥል ለተሳታፊዎች አረጋግጠውላቸዋል፡፡

16

2017

ኖቬምበር

22

የሴቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥና በማንኛውም ተግባር የሥርአተ ጾታ ጉዳዮችን ማካተት መደገፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ ለሶማሌ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይሎች አባላት በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ የተዘጋጀ የሁለት ቀን አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ከፌዴራል መንግሥትና ከፌዴራል አባል ስቴቶች የተወጣጡ ከ32 የማያንሱ የጸጥታ ሴክተር ሠራተኞች የተሳተፉበት ሥልጠና በሶማሊያ ከእንግሊዝ ኤምባሲ በተገኘ ድጋፍ ነበር የተካሄደው፡፡

2017

ዲሴምበር

4

ሶማሊያ ከፍተኛ የጸጥታ ኮንፈረንስ ዲሴምበር 4 ቀን 2017 ተካሂዷል፡፡ በኮንፈረንሱ የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊነትን ከአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ ወደ ሶማሌ የጸጥታ ኃይል ለማስተላለፍ በሚቻልበት በሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ አስቸኳይ ተግባራዊ የሽግግር ዕቅድ ላይ የጋራ ስምምነት

ተደርሷል፡፡ ዲሴምበር 5 ቀን በተካሄደው የአጋሮች መድረክ ከ25 አገሮችና ከ6 የብዙዮሽ ድርጅቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎች እንዲሁም የአምስት የፌዴራል አባል የክልል መንግሥታትና ሞቃዲሾን ጨምሮ የባናዲር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

አሚሶም መጽሔት

7


የጸጥታ ጥበቃ ሽግግር

በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በሚደረገውና በሶማሊያ የጽጥታ ማስፈን ኃላፊነትን ከአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ወይም በምጻረ-ቃል አሚሶም ወደ የሶማሊያ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይሎች በማስተላለፍ ላይ ትኩረቱን ባደረገው የአሚሶም እና የኤፍጂኤስ የጋራ ኮንፈረንስ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሚሶምና የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት በብሄራዊ ጸጥታ ቅያስ ስምምነትና በአጠቃላይ የጸጥታ አቀራረብ (ሲኤኤስ) በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የብሔራዊ ደህንነት ጥበቃ ኃላፊነትን ለሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ማሸጋገር በሚቻልበት ውጤታማ እቅድ ላይ ተወያይተው ስምምነት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ስብሰባ አካሂደዋል፡፡ ስምምነቱ ዘላቂ የደህንነት ጥበቃ ማሻሻያና የጸጥታ ጥበቃን የመጀመሪያ ኃላፊነት ከአሚሶም ወደ ሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ለማሸጋገር እምብርት ቢሆንም አሚሶም የሶማሊያን ደህንነት ከማስከበር አንጻር ለሚጫወተው ቁልፍ ሚና ቀጣይ ሚና እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ በጁላይ ወር በአገሪቱ መዲና በሞቃዲሾ የተደረገው ስብሰባ የአሚሶምን ተጨማሪ ድጋፍ በማስቀጠል ተልእኮውን ውጤት በሚያስገኝ መንገድ እንዲቀጥል አመቺ ሁኔታ የመፍጠርን አስፈላጊነት

በመገንዘብ ለአሕ ሚሽን በቂና ተገማች የገንዘብ ድጋፍ ለማስገኘት ጥሪ አቅርቧል፡፡ በስብሰባው እንደተገለጸው የገንዘብ ድጋፉ ሚሽኑ የሱማሌን ብሄራዊ ደህንነት ኃይሎች (ኤስኤንኤስኤፍ) አቅም ማሳደግ የሚቻልበትን አመቺ ሁኔታ ለመፍጠርና የደህንነት ጥበቃ ኃላፊነቱን ለመረከብ ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ የሚያስፈልገው ተጨማሪ ድጋፍ ለኤስኤንኤስኤፍ ተጨማሪ ስልጠናና ልምምድ እንዲሁም የቁሳቁስ፣ የመሠረተ ልማትና የንቅናቄ ፍላጎት በማሟላት የደህንነት ጥበቃ ኃላፊነታቸውን በትክክል መወጣት በሚያስችላቸው አቅም ግንባታ ላይ ያተኩራል፡፡ ለአምስት ቀን በተካሄደው ስብሰባ ማብቂ ከላይ በወጣው የአቋም መግለጫ ሁለቱ አጋሮች ሜይ 2017 በለንደን በተካሄደው የሶማሊያ ኮንፈረንስና በአሕተመድ ጥምር የአሚሶም ክለሳ ሪፖርት

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሶሚሊያ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ እና የሶሚሊያ ፌዴራላዊ መንግስት የመከላከያ ሚንስትር አብዲረሺድ አብዱላሂ በአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ሲከናወን የነበረውን የጸጥታ ስራ ወደ የሶሚሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መግባቢያ ስምምነት በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ ከተማ በ22/11/2009 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡ 8

አሚሶም መጽሔት

በተገለጸው የውሳኔ ሃሳብ መሠረት ያለባቸውን ኃላፊነት አረጋግጠዋል፡፡ በሶማሌ ፌዴራል መከላከያ ሚኒስትር ክቡር አብዲራሻድ አብዱላሂ መሐመድና በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ጉዳይ ልዩ ተወካይ (ኤስአርሲሲ) አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ የተፈረመው የጋራ መግለጫ በአልሸባብ ላይ የተገኘው ድል እንዳይቀለበስ ሽግግሩ በሂደት በየደረጃው ተፈጻሚ እንደሚሆን የሚያስቀምጥ ነው፡፡ በተጨማሪም በጋራ መግለጫው አልሸባብን እንደገና ለመበታተንና ለማዳከም በደቡብና ማዕከላዊ ሶማሊያ የሚካሄዱ ወሣኝና አስቸኳይ ኦፕሬሽኖች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡ በንባብ የተሰማው የጋራ መግለጫ “የኤስኤንኤ ሴክተር አዛዦች አልሸባብን ከማዳከም አንጻር የአጭር ጊዜ የኦፕሬሽን እቅዳቸውንና ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫቸውን አጋርተዋል” በማለት ይገልጻል:: አምባሳደር ማዴይራ በአምስት ቀን ስብሰባው መዝጊያ ባደረጉት ንግግር “በስብሰባው የተለያዩ ሃሳቦች አንሸራሽረናል፣ ውሳኔዎቹን በተሻለ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ዙሪያ ወደፊት መግፋት የሚቻልባቸውን አማራጮች ለመለየት ሞክረናል፣ እነዚህ ከአልሸባብ ጋር በሚደረገው ውጊያ ተጽእኖ እንደሚያሳርፉ አረጋግጠናል” ብለዋል፡፡ መከላከያ ሚኒስትሩ ክቡር አብዲረሻድ አብዱላሂ መሐመድ “የስብሰባው ዋና አላማ በተሻለ ደረጃ አቅማችችን ከማሳደግና ይቺን አገር ከማረጋጋት አንጻር የሚጠበቅብንን ውጤት ለማሳካት ትብብር መሥራት የምንችልበትን መንገድ ለመፈለግ ነው” በማለት በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ አሚሶም ለጸረ አመጽ ዕቅዱ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡


አጠቃላይ የደህንነት ጥበቃ አቀራረብ

ሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ተልዕኮና አሚሶም በሶማሊያ ደህንነት አጠቃላይ አቀራረብ (ሲኤኤስ) ላይ ኖቬምበር 11 የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ በሶማሊያ ቀዳሚ ትኩረት የሚሰጣቸው ብሄራዊ ጉዳዮች፣ አጠቃላይ የደህንነት አቀራረብ የደረሰበት የአፈጻጸምና የታዩ ክፍተቶች ተነስተዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይሬ ለስብሰባው ተሳታፊዎች ባደረጉት ንግግር “ደህንነትን ማረጋገጥ ሲባል የማጥቃት እርምጃ መውሰድ ብቻ አይደለም፤ በመልካም

አስተዳደር፣ በጸረ ሙስና ትግል፣ በብሄራዊ እርቅና ላለፈው ፈውስ በመፈለግ ዙሪያ ከህዝባችን ጋር ገንቢ ውይይት ለማድረግ ምንጊዜም ጠንካራ ፍላጎት ባላቸው በፕሬዚዳንታችን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ የተቀመጠውን አጠቃላይ የደህንነት አቀራረብ አስፈላጊነት እናውቃለን” ብለዋል፡፡ መንግሥት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የአልሸባብ ሚሊሻዎችን ሙሉ በሙሉ በሙሉ ለማዳከም ራሱን ዝግጁ ባደረገበት ባሁኑ ወቅት ለሶማሊያ የደህንነት ችግር ምላሽ ለመስጠት በሚደረግ ጥረት አጠቃላይ አቀራረብ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን

በሶማሊያ የሚከናወነውን የጸጥታ ስራ የተሟላ አቀራረብ ባለው ስልት እንዲከናወን ለማድረግ ያስችል ዘንድ እንደ መደላድል ሆነ በተዘጋጀው እና በሞጋዲሹ ከተማ በ2/3/2010 ዓ.ም በተከናወነው የከፍተኛ አመራሮች ጉባኤ ላይ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ተወካዮች እንዲሁም የክልል መንግስታት ተወካዮች እንዲሁም የአለም አቀፍ አጋር ተቋማት ልኡካን ተሳታፊ ሆነዋል፡ ፡ (በስተቀኝ)፣ ክቡር ሀሰን አሊ ከህሪ፣ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር፣ በዚህ የምክክር ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆኑ፣ በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ የመልሶ ግንባታ እና ድጋፍ ተቋም እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ ተልእኮ (አሚሶም) ድጋፍ የተዘጋጀ ጉባኤ ነው፡፡

ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ጉዳይ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍረንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ ጠላታችንን ካወቅን፣ አቅማችንን ካወቅን ምን መደረግ እንዳለበት እናውቃለን

ማለት ነው፡፡ ምን መደረግ እንዳለበት ካወቅን ደግሞ ኃብት ያስፈልገናል፡፡ ይህን ኃብታችንን እንዴት ማንቀሳቀስ እንደምንችል በጋራ ቁጭ ብለን መመካከር ያስፈልገናል፡፡ በተጨማሪም ማዴይራ በአሸባሪዎች የደህንነት አቅም ላይ የተሻለ የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኤስአርሲሲ ማዴይራ ከከፍተኛ የመንግሥት ልኡካን ጋር በባራዊ ተገናኙ

አ.ሕ የሶማሊያ ጉዳይ ልዩ ተወካይና የአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይሬ የሚመራውን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን አስከትለው በታችኛው ሸበሌ ክልል በምትገኘው ስትራቴጂያዌ የወደብ ከተማ በባራዊ ተገኝተው የጸጥታ ሁኔታውን የሚመለከት ኦክቶበር 15 ቀን ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ጉብኝቱ የተካሄደው የአሕ ሰላም አስከባሪዎችን ከደቡብ ማዕከላዊ ሶማሊያ ለማስወጣት በአሚሶም፣ በፌዴራል መንግሥትና በሱማሌ የደህንነት ኃይሎች መካከል የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ነው፡፡ “አሚሶም በዚህ አካባቢ የበለጠ ውጤታማ መሆን የሚችለው የአጋሮቹንና የራቻቸውን የሶማሌዎችን

የጋራ ራዕና ድጋፍ ማግኘት ሲችል ነው፤ ይህ ከሆነ ብቻ ነው አልሸባብን ማዳከምና መደምሰስ የምንችለው” ብለዋል አምባሳደር ማዴይራ፡፡ ሰላም አስከባሪዎቹን ለማስወጣት በተያዘው ዕቅድ መሠረት የአሕ ሰላም አስከባሪዎች የቁልፍ ከተሞችን የደህንነት ጥበቃ ተግባር በሽግግር እቅዱ በተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መሠረት ለሱማሌ ኃይሎች አስረክበው ሥራውን መምራት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ይሠራሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ካይሬ የአካባቢው ኃይሎች ኃላፊነቱን መረከብ እስከሚችሉ ድረስ አሚሶም አገሪቱን ማረጋጋት ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን እንዲችል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ለባራዌ ነዋሪዎች አረጋግጠውላቸዋል፡፡ የባራዌ ልኡካን የደቡብ

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሶሚሊያ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ እናየአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሶሚሊያ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ፍራንሲስኮ ኬይተኖ ማዴይራ እና የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የሶማሊያ ልዩ መልእክተኛ ማይክል ኪቲንግ በስራ ጉብኝታቸው መዳረሻ በሆነችው ሎወር ሸበሌዋ ባረዌ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ በዚህች ሰፊ የቆዳ ሽፋን ካላቸው የሶማሊያ ክልሎች አንዷ በሆነችው ክልል በነበራቸው የስራ ቆይታ በ6/3/2010 ዓ.ም ተገናኝተዋል፡፡

ምዕራብ ስቴት ፕሬዚዳንት ክቡር ሸሪፍ ሃሰን ሼክ አደን፤ በሶማሊያ የአውሮጳ ሕብረት አምባሳደር ቬሮኒክ ሎሬንዞ፣ የተመድ ዋና ጸኃፊ (ኤስአርኤስጂ) የሶማሊያ ልዩ

ተወካይ ማይክል ኬቲንግ፤ በሶማሊያ የኡጋንዳ ምክትል አምባሳደር ሜ/ጄኔራል ናታን ሙጊሻ፣ የተመድ፣ የአሚሶምና የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣኖች የተገኙበት ነበር፡ አሚሶም መጽሔት

9


ወታደራዊ ተልእኮ

ክቶበር 14 ቀን በሞቃዲሾ የደረሰው ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች የተገደሉበትን መጠነ ሰፊ ፍንዳታ ተከትሎ በሶማሊያ የአሸባሪዎችን ተጨማሪ ጥቃት ለመቋቋም አስቸኳይ የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በአፍሪካ ሕብረት (አሕ)፣ በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት (ኤፍጂኤስ) እና የተለያዩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት

የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር ሜጀር ጀነራል አብዲዌሊ ጃማ ጎሮድ በዚህ የምክክር ጉባኤ ላይ በሶማሊያ በ4/2/2010 ዓ.ም በደረሰው የዞቤ የሽብር ጥቃት ዙሪያ ንግግር ሲያደረጉ፡፡ የጸጥታ ጉዳይ ባለሚናዎችን ያሳተፈው ስብሰባው በሞጋዲሹ በሚገኘው አሚሶም ዋና ጽህፈት 15/2/2010 ዓ.ም ተከናውኗል፡፡

የተሳተፉበት የቀውስ ስብሰባ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ስጋትን ለመቀነስ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) የተዘጋጀው የተመድ ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ጉዳይ ምክትል ልዩ ተወካይ (ዲኤስአርኤስጂ) ሬስደን ዜንጋ የተመራ የተመድ ከፍተኛ ኃላፊዎች የልኡካን ቡድን፣ አዲሱን የመከላከያ ሠራዊት ዋና ኤታማዦር ሹም (ሲዲኤፍ) ሜ/ ጄኔራል አብዲዌሊ ጃማ ሁሴንን ጨምሮ ከፍተኛ የኤፍጂኤስ የደህንነት ኃላፊዎች የተሳተፉበት የቀውስ አመራር ቡድኑ ጥምር ስብሰባ ከሌሎች በተጨማሪ የተሻለ የደህንነት መረጃ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልባቸውን መንገዶች ላይ መክሯል፡፡ የአሚሶም የሶማሊያ ጉዳይ ምክትል ልዩ ተወካይ ሲሞን ሙሎንጎ ስብሰባው በተሻለ የደህንነት ቅንጅት አማካኝነት ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ጥቃቶችን ለማስቀረት ፋይዳ እንደነበረው ገልጸዋል፡፡ “በስብሰባው ለወደፊቱ የተሻለ ምላሽ ለመስጠት በመወሰድ ስጋትን ለመቀነስ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል፡፡ የምላሹን ቅርጽ፣ ፍጥነትና የሚያስከትለውን ተጽእኖ በዝርዝር ለይቶ የሚያስቀምጥ የቴክኒክ ቡድን አለን፤ ሁለተኛ የእዝና ቁጥጥር ጉዳዮች በትክክል

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶሚሊያ ጉዳዮች ረዳት ልዩ ልኡክ የሆኑት ሲሞን ሙሎንጎ ድንገተኛ የጸጥታ መደፍረስን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚል የውይይት ርእሰ ጉዳይ በተደረገው የጋራ ጉባኤ ላይ በተለይም በሶማሊያ በ14/10/2017 በደረሰው የዞቤ የሽብር ጥቃት ዙሪያ ንግግር አድርገዋል፡፡ የጸጥታ ጉዳይ ባለሚናዎችን ያሳተፈው ስብሰባው በሞጋዲሹ በሚገኘው አሚሶም ዋና ጽህፈት 25/10/2017 ተከናውኗል፡፡

መከናወናቸውን ለማረጋገጥ በተሻለ ደረጃ በቅንጅት ለመሥራት ጥረት እናደርጋለን” ሙሎንጎ በሰጡት ማብራሪያ፡፡ ኦክቶበር 14 ቀን 2017 አሸባሪዎች በሞቃዲሾ ከተማ ህዝብ በሚበዛበት መንገድ መታጠፊያ ያፈነዱት በተሽከርካሪ የተጠመደ ቤት ሰራሽ ፈንጂ (ቪቢአይኢዲ) ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡ “ባሁኑ ጊዜ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ተግዳሮቶች አሉ፤ ይህም በጋራ መስራት ይጠይቀናል” ብለዋል የሶማሊያ የአገር መከላከያ ሠራዊት (ኤስኤንኤ) ዋና ኤታማዦር ሹም ሜ/ጄኔራል አብዲዌሊ ጃማ ሁሴን፡፡

የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተልእኮ (አሚሶም)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲሁም ሌሎች አጋር ተቋማት ተሳታፊ የነበሩበት፣ በሰድንገተኛ የጸጥታ መደፍረስን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚል የውይይት ርእሰ ጉዳይ በተደረገው የጋራ ጉባኤ ላይ በተለይም በሶማሊያ በ14/10/2017 በደረሰው የዞቤ የሽብር ጥቃት ዙሪያ ንግግር አድርገዋል፡፡ የጸጥታ ጉዳይ ባለሚናዎችን ያሳተፈው ስብሰባው በሞጋዲሹ በሚገኘው አሚሶም ዋና ጽህፈት 25/10/2017 ተከናውኗል፡፡ 10

አሚሶም መጽሔት


በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ ተልእኮ ስር ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ካዋጡት ሀገራት አንዷ ዩጋንዳ ስትሆን፣ አልሻባብን ከሶማሊያ ለማስወገድ፣ በተለይም የሎወር ሸበሌ ክልል ውስጥ የምትገኘውን አፍጎዬ ከተማ ከአልሻባብ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ተጽእኖ በማላቀቅ፣ ሰላሟን ለማጥራት በጥረት ላይ ከሚገኙት ሰላም አስከባሪዎች አንዱ ዬጋንዳዊው ወታደር በ26/2/2010 ዓ.ም ለሰላም ዘብ ቆሟል፡፡

ወታደራዊ ጥምር ተልእኮ በታችኛው ሸበሌ ክልል የ አ.ሕ ሰላም አስከባሪዎችና የሶማሌ ብሔራዊ ጦር ወታደሮች በታችኛው ሸበሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ሚሊሻዎችን ለመደምሰስ ትልቅ ኦፕሬሽን ጀምረዋል፡፡ በኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ሠራዊት (ዩፒዲኤፍ) የ11ኛ እግረኛ ሻለቃ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል እሥራኤል ካሄሩ ባጌንዳ እንደገለጹት ጥምር ኦፕሬሽኑ በኖቬምበር

የመጀመሪያ ሳምንት የተካሄደ ሲሆን በተለያዩ ምዕራፎች ተከፍሎ ክልሉን ከሞቃዲሾ የሚያገናኙ ዋና ዋና የአቅርቦት መስመሮችን ለሰዎችና ለዕቃዎች ነጻ እንቅስቃሴ ክፍት የማድረግ አላማ ያለው ነው፡፡ በማያያዝም “አላማው የአልሸባብን ኃይሎች ባጠቃላይ ከእነዚህ ሙሉ በሙሉ ጠራርገን እንድናስወጣ ነው” ብለዋል ሌ/ኮሎኔል ባጌንዳ፡፡

“ለአልሸባብ ባሉበት ቦታ ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ አለብን፡- አፍጎዬን መልሰው በመያዝ፣ ወደ ባላድ፣ ኢላሻ ቢያሃ፣ ላፎሌ ሾልከው በመግባት ጥፋት መፈጸም መጀመር አንፈቅድቸውም”፡፡ አሚሶም አልሸባብን በአገሪቱ በስፋት ከተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ጠራርጎ አስወጥቷል፤ ይህም በሶስት ዋና ዋና ወታደራዊ

ስር ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ካዋጡት ሀገራት አንዷ ዩጋንዳ ስትሆን፣ አልሻባብን ከሶማሊያ ለማስወገድ፣ በተለይም የሎወር ሸበሌ ክልል ውስጥ የምትገኘውን አፍጎዬ ከተማ ከአልሻባብ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ተጽእኖ በማላቀቅ፣ ሰላሟን ለማጥራት በጥረት ላይ ከሚገኙት ሰላም አስከባሪዎች አንዱ ዬጋንዳዊው ወታደር በአልሸባብ ላይ ለሚወሰደው ጥቃት በዝግጅት ላይ በተጠንቀቅ ሆኖ፡፡

በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ ተልእኮ ስር ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ካዋጡት ሀገራት አንዷ የሆነችው የዩጋንዳ መከላከያ ሚንስትር የፈንጂ እና ከባድ የጦር መሳሪያ ባታሊዮን ኦፕሬሽን ኮማንደር ሌተናል ኮሎኔል እስራኤል ባጌንዳ ይባላሉ፣ አልሻባብን ከሶማሊያ ለማስወገድ፣ በተለይም የሎወር ሸበሌ ክልል ውስጥ የምትገኘውን አፍጎዬ ከተማ ከአልሻባብ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ተጽእኖ በማላቀቅ፣ ሰላሟን ለማጥራት በጥረት ላይ የሚገኙት ኮማንደሩ ተልእኮውን በማስመልከት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ኦፕሬሽኖች፤ ማለትም በኦፕሬሽን ኤግል፣ በኦፕሬሽን ኢንዲያን ኦሽንና በኦፕሬሽን ጁባ ኮሪደር አማካኝነት በሶማሊያ የሚገኙ ቁልፍ ከተሞችን ከአልሸባብ ነጻ ማውጣትን ይጨምራል፡፡ የእነዚህ ኦፕሬሽኖች አላማ ባለ ሶስት ፈርጅ ነበር፡- ከተሞችን ነጻ ማውጣት፤ የአሸባሪዎችን የአቅርቦት መስመሮች መቁረጥ፣ ከአካባቢው ህዝብ ህገወጥ ታክስ እንዳይሰበስቡ ማድረግ፡፡ አሚሶም መጽሔት

11


ጠላትን በአንድነት ማጥቃት የ

ኦክቶበር አሥራ አራቱን ጥቃት የፈጸሙት የህዝቡን ቅስም ለመስበር አስበው ከሆነ በተጨባጭ የሆነው ተቃራኒው ነበር፡፡ በሶማሊያ የነውጥ ታሪክ ከሁሉ አውዳሚ የነበረው

ጥቃት በምትኩ ሱማሌዎች በጋራ ሽብርን ለመዋጋት ከምንጊዜውም በበለጠ አንድነትና ወዳጅነት ያሳዩበት ነበር፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱማሌዎች በቁጣ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው አልሸባብ

በሶማሊያዋ መዲና ሞጋዲሹ በ5/2/2ዐ1ዐ ዓ.ም በአልሸባብ አባላት የከባድ ፈንጂ መሳሪያን በመጠቀም የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ወንዶች እና ሴቶች የህንጻ ፍርስራሾቹን ከመንገዶች ላይ እየጠረጉ ሲያጸዱ፣ እንዲሁም ከተማቸውን ሲንከባከቡ፡፡

ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸመው እልቂት አውግዘዋል፡፡ የአሕ የሶማሊያ ልዩ ተወካይና የአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ ከአሚኦም ሰላም አስከባሪዎችና ኦፊሰሮች ጋር በመሆን ጥቃቱን በጥብቅ በማውገዝ በፍጥነት ወደ ነፍስ አድንና መልሶ ማቋቋም ጥረት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ “ይህ የአሸባሪ ቡድኑ የአልሸባብ ድርጊት የፈሪ ሥራ ነው፣ በሰላማዊውን ህዝብ በሓይል ለማስገደድና በማስፈራራት የእነርሱ ደጋፊ እንዲሆን ለማድረግ የታሰበ ነበር ነገር ግን እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል የኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ሠራዊት (ዩዲኤፍ) ሰላም አስከባሪዎች አዛዥ ብርጋዲዬር ጄኔራል ሙሃንጋ ካያንጃ፡፡ በአሸባሪዎች በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቤት ሰራሽ ፈንጂ ህዝብ በሚበዛበት ከተማ በመንገድ መገንጠያ ፈንድቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ ተልእኮ ስር የዩጋንዳ ጦር ተጠባባቂ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ካያንጃ ሙሀንጋ ሰዎች ላይ የህይወትና የአካል በሶማሊያዋ መዲና ሞጋዲሹ በአልሸባብ አባላት የከባድ ፈንጂ መሳሪያን በመጠቀም የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የጥቃቱን ስፍራ በመጎብኘት ተመልክተውታል፡፡ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡ 12

አሚሶም መጽሔት


ሠላም አስከባሪዎች ያዋጡ አገሮች ለኦክቶበር 14ቱ ጥቃት ሰለባዎች ድጋፍ አደረጉ

አሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ያዋጡ አገሮች ለጥቃቱ ተጎጂዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና በጽኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ለአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ወደየአገራቸው በአየር የማንሳት ተግባር አከናውነዋል፡፡ እርዳታ ከላኩ አገሮች ጥቂቶቹ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣

ኡጋንዳና ጂቡቲ ነበሩ፡፡ “እስካሁን 11 ቶን የታሸገ የመድኃኒት እርዳታ አምጥተናል፡፡ በተጨማሪም 26 በሽተኞችን ወስጄ ኬንያታ ብሄራዊ ሆስፒታል ለማስገባትም ተዘጋጅቻለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአከርካሪ አጥንት ጉዳት የደረሰባቸውን በሽተኞች ናይሮቢ

ወደሚገኘው ብሄራዊ የጀርባ አጥንት ሆስፒታል እወስዳቸዋለሁ፡፡ በጥቃቱ መሪር ሀዘን ለደረሰባቸው ለሁሉም እግዚአብሄር ጽናቱን እንዲሰጣቸው እጸልያለሁ” ብለዋል በሶማሊያ የኬንያ አምባሳደር ጡረተኛ ሜ/ጄኔራል ሉቃስ ታምቦ፡፡

ሶማሊያ በዋና ከተማዋ በሞጋዲሹ ላይ ባነጣጠሩ የሽብር ጥቃቶች በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠማት ሲሆን፣ በ4/2/2ዐ1ዐ ዓ.ም በመዲናዋ የደረሰው የሽብር ድርጊት ተከትሎም፣ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ዜጎቿ የሚሆን የህክምና መሳሪያዎች እርዳት ከጎረቤቷ ከኬንያ በአውሮፕላን ተልኮላታል፤በ7/2/2ዐ1ዐ ዓ.ም በአደን አብዱሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙት የሶማሊያ የፖሊስ ኃይል አባላት ከኬንያ የተላከውን የህክምና መሳሪያ ከእቃ ጫኝ አውሮፕላን ላይ ሲያራግፉ ይታያሉ፡፡

14/10/2017 በመዲናዋ የደረሰው የሽብር ድርጊት ተከትሎም፣ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ሰው ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደሚወሰድበት ኬንያ ለመጓዝ በአደን አብዱሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አውሮፕላን ሲገባ በእስትሬቸር ላይ ሆኖ ይታያል፡፡

የሶማሊያ ጤና ጥበቃ እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ሚንስትር ዶ/ር ፋውዚያ አቢካር ፤በ7/2/2ዐ1ዐ ዓ.ም በአደን አብዱሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ከኬንያ የተላከውን የህክምና መሳሪያ ከተረከቡ በኋላ በስፍራው ለተገኙት የሚዲያ ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች መረጃ ሰጥተዋል፡፡ አሚሶም መጽሔት

13


አሚሶም ለጸረ ቤት ሰራሽ ፈንጂ [አይኢዲ] ጥረት ድጋፍ ሰጠ

ት ሰራሽ ፈንጂዎች [አይኢዲ] በሰላማዊ ህዝብና በጸጥታ ኃይሎች ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ስጋቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት አሚሶም አይኢዲዎች በሚደቅኑት ስጋትና በሚያስከትሉት ጉዳት ላይ ክለሳ ለማድረግና በሶማሊያ የአይኢዲ መከላከል አቅም ለመገንባት በሞቃዲሾ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ በሴፕቴምበር በተካሄደው ሲምፖዚየም ከአሕ ሚሽን፣ ከሶማሌ የጸጥታ ኃይሎች፣ ከተመድና ከእንግዚዝ ኃይሎች የተወጣጡ ተወካዮች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ከዩኬ መንግሥትና በተባበሩት መንግሥታት የጸረ ፈንጂ ድጋፍ ሚሽን (ዩኤንኤምኤኤስ) በተገኘ ድጋፍ የተዘጋጀው የሶስት ቀን ሲምፖዚየም መክፈቻ ላይ የተገኙት የአሚሶም የኃይል አዛዥ ሌ/ጄኔራል ኦስማን ኑር ሱባግሌ ባደረጉት ንግግር “ከኃይል ዋና መ/ ቤት የሚሰጥ የሁሉም ዘርፎች ተግባር የሚመራበትን መመሪያ የሚያዳብርና የአፍሪካ

14

አሚሶም መጽሔት

ሕብረት የሰላም ማስከበር ድጋፍ ኦፕሬሽን ዲቪዝን ሥራ የሚመራበትን አሠራር አቅጣጫ የሚወስን ሊተገበር የሚችል ምክረ ሃሳብ እንዲመጣ እጠብቃለሁ” ብለዋል፡፡ ሌ/ጄኔራል ኦስማን ኑር ሱባግሌ በማያዝም ከዚህ በፊት በአይኢዲዎች ዙሪያ በተካሄዱ አውደ ጥናቶች የተገኘው የተሻለ ግንዛቤና እውቀት በየጊዜው የሚገኙና በአስተማማኝ ሁኔታ የሚወገዱ ፈንጂዎች በጉልህ እየጨመረ እንዲመጣ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ የአሕ ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ በአጽንኦት እንዳስገነዘቡት “የአይኢዲዎችን ስጋት ለመቀነስ የግንዛቤ ማዳበሪያ ትምህርት ፣ ሥልጠና፣ ጥሩ የሪፖርት አቀራረብና የመረጃ ልውውጥ ባጣመረ አሠራር አማካኝነት አሸባሪዎች በመሳሪያው ላይ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት በማዳከም አይኢዲን መዋጋት ይጠይቃል”፡፡ ውይይቱ አልሸባብን በመሰሉ አሸባሪ ድርጅቶች

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ጉዳይ ረዳት ልዩ ልኡክ የሆኑት ሲሞን ሙሎንጎ በከባድ ፈንጂዎች የሚደርሰውን ሽብር እና የጸጥታ መደፍረስን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚል የውይይት ርእስ በሞጋዲሹ በተዘጋጀው የጸጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ለብሪታንያ መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ለሜጀር ዳንኤል ረይሊ የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

እየተስፋፋ የመጣውን የእነዚህ ፈንጂዎች አጠቃቀም በትክክል መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ “ይህን የአይኢዲዎች ተግዳሮት ለመሻገር ቀላል ምትሃታዊ አማራጭ የለም፣ ይሄ ነው የሚባል አንድ

ብቻ መፍትሄ የለም” ብለዋል የእንግሊዝ ሰላም አስከባሪዎች አዛዥ ኮሎኔል ጆን ዌክሊን፡፡ በማያያዝም “አንድ ጊዜ ብቻ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ፤ ወይም ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል አንድ ቴክኒክ ወይም ታክቲክ የለም፡፡ ቅይጥ


የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የሰላም አስከባሪ ቡድኑ አባላት፣ እንዲሁም ሌሎች አለም-አቀፍ አጋር ተቋማት በከባድ ፈንጂዎች የሚደርሰውን ሽብር እና የጸጥታ መደፍረስን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚል የውይይት ርእስ በሞጋዲሹ በተዘጋጀው የጸጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በሲምፖዚየሙ ተስፋፍቶ በጥቅም ላይ ያለውን ፈንጂ ለማቆም በድጋሚ ቁርጠኝነት አሳዩ ነገር ነው” ብለዋል፡፡ ተግዳሮቱን በትክክል መቅረፍ ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ አይኢዲዎችን ለመዋጋት ባለብዙ ፈርጅ አቀራረብ መጠቀም የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ ድጋፍ ጽ/ ቤት (ዩኤንኤስኦኤስ) የሚሽን ድጋፍ ዳይክተር ሚ/ር አማዱ ካማራ “በደቡብ ማእከላዊ ሶማሊያ ደህንነትን ለማረጋገጥ በተቀመጠው አጠቃላይ አቀራረብ አቅጣጫ አንድ አካል አይኢዲዎች የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ትክክለኛ ስትራቴጂ” የመቅረጽን አስፈላጊነት በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ሲምፖዚየሙ እየተስፋፋ የመጣውን የፈንጂዎች አጠቃቀም ከመከላከል አንጻር ተሳታፊዎች ቁርጠኝነታቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ የዩኤንኤምኤኤስ ዳይሬክተር ሚ/ር አላን ማክዶናልድ የአሕ ሰላም አስከባሪዎችን የማስወጣት ተግባር በተያዘለት እቅድ መሠረት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት በሱማሌዎች የሚመሩ ኦፕሬሽኖችን ከመደገፍ አንጻር በሲምፖዚሙ የተገኘውን ጠቃሚ ግንዛቤና እውቀት በግንባር መስመር ለሰላም አስከባሪዎች በተለይም ለሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ማጋራት አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አስገንዝበዋል፡፡ የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች አይኢዲዎችን ችግር ለመቅረፍ መወሰድ ካለባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች እንደ አንድ አካል የአሕንና የሱማሌ የጸጥታ ኃይሎችን የደህንነት መረጃ አሰባሰብ አቅም ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዳ የውሣኔ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ “የሰላምና ጸጥታ ማስከበርን ተግባርና ኃላፊነት ለሱማሌ ብሄራዊ ጦር (ኤስኤንኤ) ማስረከብ የምንችለው ልክ እንደእኛ አይነት

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንኗና ጸሐፊ የሶማሊያ ጉዳዮች ልዩ ልኡል አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ፣ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ድጋፍ እና መልሶ ግንባታ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አማዱ ካማራ በከባድ ፈንጂዎች የሚደርሰውን ሽብር እና የጸጥታ መደፍረስን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል በሚል የውይይት ርእስ በሞጋዲሹ በተዘጋጀው የጸጥታ ጉዳዮች ሴሚናር በ15/1/2ዐ1ዐ ዓ.ም የተለያዩ ማሳሪያዎች ሳምፕል ተመልክተዋል፡፡

እንዲየውም ቢቻል የተሻለ የኦፕሬሽን አቅም ካላቸው ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላም የአሚሶምን ሰላም አስከባሪዎች ስናሰለጥን እንዳደረግነው ለአገሪቱ ብሄራዊ የጸጥታ ኃይሎች ሥልጠና እኩል፣ ምናልባትም የተሻለ ትኩረት መስጠት መቻል አለብን”

ብለዋል የአሚሶም የሶማሊያ ጉዳይ ምክትል ልዩ ተወካይ ሲሞን ሙሎንጎ፡፡ የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ያወጡት የውሳኔ ሃሳብ ለተጨማሪ ውሳኔ ለአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማስከበር ድጋፍ ኦፕሬሽን ዲዚዥን እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ አሚሶም መጽሔት

15


ሶማሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የደህንነት ኮንፈረንስ አስተናገደች

ሶማሊያ ከፍተኛ የደህንነት ኮንፈረንስ በዲሴምበር 2017 የመጀመሪያ ሳምንት ተካሂዷል፤ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የሶማሊያን ብሄራዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃላፊነት ከአሕ የሶማሊያ ተልዕኮ ወደ ሶማሌ የጸጥታ ኃይሎች ማስተላለፍ በሚቻልበት “አስቸኳይ ተግባራዊና በሁኔታዎች የተመሠረተ የሽግግር ዕቅድ” ላይ ስምምነት ደርሰዋል፡፡ ኮንፈረንሱ ሲጠናቀቅ በፌዴራል የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚ/ር አብዲራህማን ኦማር ኡስማን በንባብ የተሰማው የጋራ አቋም

መግለጫ በከፊል “ይህ ዕቅድ በህግ የበላይነትና በሰብአዊ መብት አከባበር መርሆዎች መመራትና ጽንፈኝነትን መከላከልን፣ መረጋጋትና መልካም አስተዳደርን ማስፈንን የሚያካትት መሆን አለበት” ይላል፡፡ በአገሪቱ መዲና በሞቃዲሾ በተካሄደው ኮንፈረንስ “የሽግግር ዕቅዱን ረቂቅ በ2018 ከሚካሄደው የአሚሶም የክለሳ ስብሰባ በፊት ከማጠናቀቅ አንጻር” የሽግግሩን ሂደት ዕቅድ እስከ ዴሴምበር 31 ቀን 2017 ለማዘጋጀት ስምምነት ተደርሷል፡፡ “ይህ ተግባር የሚጠበቀውን ግልጽ ውጤት በተግባር

ለማረጋገጥ በኤፍጂኤስ (በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት) በኤፍኤምኤስ (በፌዴራል አባል ክልላዊ መስተዳድሮች) እንዲሁም በሱማሌ መንግሥትና በአሚሶም መካከል በቅርበት በመተባበር በአጋርነት መሥራት ይጠይቃል”፡፡ በሽግግር ዕቅዱ መሠረት የሽግግሩን ቅድመ ሁኔታዎች ለይቶ የሚያስቀምጥ ዝርዝር ስትራቴጂ ይቀረጻል፡፡ ይህም ከሌሎች በተጨማሪ የደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን በመላ አገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል አቅም የሚፈጥር “አዋጭነት፣ተጠያቂነት ተቀባይነትና አስገዳጅነት

በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በ25/3/2ዐ1ዐ ዓ.ም በተከናወነው የጸጥታ ጉዳዮች የምክክር መድረክ እና ኮንፍረስ ላይ በርካታ አለም-አቀፍ ዲፕሎማቶች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ 16

አሚሶም መጽሔት

የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ፎርማጆ በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በተከናወነው የሶማሊያ ሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ለተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

ያለው” ውጤታማ የሽግግር ሥርአት የሚያስገኝ ይሆናል፡፡ በጋራ መግለጫው እንደተገለጸው “በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 2372 በተቀመጡት ቀዳሚ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት አፈጻጸም አንጻር ለሽግግሩ ዕቅድ ተግባራዊነት አሚሶም የሚሰጠው ድጋፍ ይቀጥላል”፡፡ በአሚሶምና በኤስኤንኤ በጥምር ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የዋና ዋና የአቅርቦት መስመሮች ጥበቃ፣ ህዝብ የሚበዛባቸውን ቁልፍ ሥፍራዎች መጠበቅ፣ እንዲሁም በሶማሌ ወታደራዊና


ከላይ በስተቀኝ በኩል፡ በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በተከናወነው የጸጥታ ጉዳዮች የምክክር መድረክ እና ኮንፍረስ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት አለም-አቀፍ ዲፕሎማቶች በከፊት፡፡

በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በ25/3/2010 ዓ.ም በተከናወነው የጸጥታ ጉዳዮች የምክክር መድረክ እና ኮንፍረስ ላይ በርካታ ባለሚናዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

የፖሊስ መዋቅሮች ሥር የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎችን ማለማመድ ይገኙበታል፡፡ ተሳታፊዎች ዘላቂ የደህንነት ማሻሻያ ከማረጋገጥና የመጀመሪያ ኃላፊነት ከአሚሶም ወደ ሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ከማስተላለፍ አንጻር እምብርት የሆነውን የብሔራዊ ደህንነት ፕላን ንድፍ በአጭር ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

ቀዳሚ ትኩረት የተሰጣቸው ተግባራት ክልላዊ ኃይሎችን ከሶማሌ ብሄራዊ የጸጥታ ኃይሎች ማቀናጀትን ይጨምራሉ፡፡ ለሱማሌ የጸጥታ ኃይሎችና አግባብ ላላቸውን ሌሎች ተቋማት አቅም ግንባታ የሚያስፈልገው ቀጣይ አለማቀፍ ድጋፍም በአጭር ጊዜ ዕቅዱ ተካቷል፡፡ የሱማሌ የጸጥታ ኮንፈረንስ በይፋ ሲከፈት

በክብር እንግድነት የተገኙት የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ፕሬዚዳንት ክቡር መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ “ፋርማጆ” ባደረጉት ንግግር በቁልፍ የጸጥታ ማሻሻያ ሥራዎችን የአፈጻጸም ሂደትና በፌዴራል መንግሥትና በፌዴራል አባል ክልሎች መካከል ያለውን አንድነት ከማሻሻል አንጻር እስካሁን የተደረገውን እንቅስቃሴ በዝርዝር አብራርተዋል፡፡ “የኦፕሬሽን ዝግጁነት የግምገማ ሥራው ተጠናቋል፤ ጥንካሬዎቻችንንና ያሉብንን ክፍተቶች ለይተን ተምረንባቸዋል፤የአገሪቱን የፖሊስና የብሄራዊ ጦር ቁመና ምን መምሰል እንዳለበት ትምህርት አግኝተናል፡፡ ይህንኑ አስፈላጊ የማሻሻያ ፕሮግራሞችን ለይተን ተግባራዊ ለማድረግ እንደ መስፈንጠሪያ ሰሌዳ እንጠቀምበታለን” ብለዋል ፕሬዚዳንት ፋርማጆ በስብሰባው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጸጥታው ዘርፍ የመሪነት ሚናውን

በሶማሊያ መዲና በሞጋዲሹ በ25/3/2010 ዓ.ም በተከናወነው የጸጥታ ጉዳዮች የምክክር መድረክ እና ኮንፍረስ ላይ የክልል ፕሬዝደንቶች እና የሞጋዲሹ ከተማ ከንቲባ ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

ከመወጣት አንጻር መንግሥታቸው ያለውን ቁርጠኝነት በአጽንኦት በመግለጽ የጸጥታ ጥበቃውን ኃላፊነት ለሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ከመተላለፉ በፊት አቅማቸውን መገንባት በኩል ያለውን አስቸኳይ ፍላጎት ጠቁመዋል፡፡ የአሕ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ካቴኖ በሶማሊያ ዘላቂ ሰላም ከማረጋገጥ አንጻር እንደ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ የሱማሌ መሪዎች አንድነታቸውን ማጠናከር እንደሚያ ስፈልጋቸው በአጽኦት ገልጸዋል፡፡ በማያያዝም አንድነት በሌለበት የሶማሊያ የጸጥታ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በትክክል ተግባራዊ ማድረግ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡ “እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍና ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት የሱማሌን የአመራር አንድነትና ከዚሁ ጎን ለጎን ቁርጠኝነትን እንደገና ማረጋገጥ ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡ በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት፣ በአሚሶምና በተመድ የተደረገው ኮንፈረንስ ዋና አላማ ሜይ 2017 የተካሄደውን የለንደን ኮንፈረንስ ተከትሎ በአገሪቱ የጸጥታ ጥበቃ ሁሉን አቀፍ አቀራረብ አፈጻጸም ሂደት የተደረገውን እንቅስቃሴ ለመከለስ ነበር፡፡ በአጋሮች መድረኩ የሶማሊያ የልማት አጋሮች ለአገሪቱ ተገማችና ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡ በከፍተኛ መድረኩ ከ25 አገሮች፣ ከ6 የብዙዮሽ ድርጅቶች የተወጣጡ ልዑካን አምስቱ የአገሪቱ የፌዴራል አባል ክልሎች ፕሬዚዳንቶችና ሞቃዲሾን ጨምሮ የቤናዲር ክልላዊ አስተዳደር ኃላፊዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ አሚሶም መጽሔት

17


የሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ቀጣይ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም

ንድ አካል ሆኖ በሱማሌ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ (ኤንአይኤስኤ) የተዘጋጀ ትጥቅ በፈቱ የቀድሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች ማጣሪያ ላይ ያተኮረ አውደጥናት በሞቃዲሾ ተካሂዷል፡፡ ከሁሉም የአገሪቱ የፌዴራል አባል ክልሎች የተወጣጡ የኤንአይኤስኤ ኦፊሰሮች የተሳተፉበት አውደ ጥናት አላማው የኤንአይኤስኤን የኦፕሬሽንና አሠራር ደረጃዎችና የቀድሞ ታጣቂዎች የማጥራትና አቅም ግንባታ ፍላጎት ለመከለስ ነው፡፡ የማጣራት ሥራው የሶማሊያ የቀድሞ ተዋጊዎች የህክምናና የአያያዝ ብሄራዊ ፕሮግራም አንድ አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ በአውደ ጥናቱ ሽብርን መዋጋትና ወደየማህበረሰባቸው መቀላቀል የሚፈልጉ የቀድሞ የአልሸባብ ሚሊሻዎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ማግኘት በሚችሉባቸው የተለያዩ መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

በሶማሊያ በትጥቅ ትግል ላይ ከሚገኙት ቡድኖች ተነጥለው የሰላሙን የትግል ጎዳና ለሚቀላቀሉ ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ አላማ በሀገር ውስጥ ጸጥታ ሚንስቴር ስር የተዋቀረው ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺ ኢብራሂም ሞሐመድ በሞጋዲሹ በ27/10/2009 ዓ.ም በተከናወነው የሶማሊያ የጸጥታ ተቋማት የአቅም ግንባታ ዎርክሾፕ ላይ ተገኝተው ለተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ የድጋፍ እና የመልሶ ግንባታ ተልእኮ ስር የትጥቅ ማስፈታት ፣ የመልሶ ሰፈራ እና የእርቀ-ሰላም ሂደት ዋና ኃላፊ የሆኑት ዘነይድ ጌታሊ፣ በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ በ28/10/2009 ዓ.ም በተከናወነው የሶማሊያ የጸጥታ ተቋማት የአቅም ግንባታ ዎርክሾፕ ላይ ተገኝተው ከተሳታፊዎች መካከል ለአንዱ የምስክር ወረቀት ሲሰጡ፡ 18

አሚሶም መጽሔት


የጎሳ ግጭትን ለማስቆም ማኅበረሰቦች እግር ኳስ ይጠቀማሉ

ርነት የመረራቸው አንዳንድ የሶማሊያ ማህበረሰቦች ትጥቅ ለመፍታትና በምትኩ ከባላንጣዎቻቸው ጋር የስፖርት ውድድር ለማድረግ ደፋር እርምጃ ወስደዋል፡፡ ከሰላም ትሩፋት ተጠቃሚ ለመሆን ማህበረሰቦቹ ጥሩ ምርጫ አድርገዋል- ከግጭት ይልቅ አንድነትን መርጠዋል፡፡ በታችኛው ሸበሌ ክልል በማርካ ከተማ የሚገኙ ማህበረሰቦች በድርድር ተሳታፊ ለመሆንና እርቅን ለማራመድ የእግር ኳስ ውድሮችን በመሳሪያነት በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ የሁለቱ ባላንጣ ጎሳዎች አባላት ለአመታት እርስ በርስ ተዋግተዋል፤ አሁን ግን ልዩነታቸውን ወደጎን በመተው እግር ኳስ ውድድር አንድ ሆነዋል፡፡ በቢመ፣ልና በአቢርጊዲር ጎሳዎች መካከል የተደረገው የወዳጅነት ውድድር በሲጃሌ በመስከረም ወር በማህበረሰቡ ተሳትፎ በተሠራው የማዘውተሪያ ሜዳ ተካሂዷል፡፡ የእግር ኳስ ሜዳው የተሠራው በአካባቢው ማህበረሰብ ሲሆን የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የሲቪልና ወታደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቡድን ሜዳውን በመጥረግና

በማስተካከል እገዛ አድርጓል፡፡ ሜዳው በአገር ሽማግሌ የተለገሰ ነው፡፡ ቀደም ሲል ባላንታ የነበሩ ጎሳዎች አሁን በአንድ ላይ ተሰባስበው በመክፈቻው ውድድር ለየቡድኖቻቸውለማርካ አዩብ የእግር ኳስ ቡድንና ለሲጃሌ የእግር ኳስ ቡድን ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ ውድድሩ ባዶ ለባዶ ተጠናቋል፡፡ ውድድሩ በአሚሶም የሲቪል-ወታደራዊ ማስተባበሪያ ቡድንና በአካባቢው በተሰማራው የኡጋንዳ 22ኛ ተዋጊ ቡድን አዛዥ ኮሎኔል ቦኒ ኦግዋል መካከል የተደረገውን የድርድር ሰብሰባ

በሶማሊያ፣ ማርካ ተገኝተው የቀድሞ ባላንጣ ጎሳዎች ለነበሩ፣ ነገር ግን በቅርቡ እርቅ ለፈጸሙ ጎሳዎች አባላት የማዘውተሪያ ስፍራ እንዲሆን የተገነባውን ስቴዲዮም የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ልዩ ተልእኮ (አሚሶም) የግንባት ሳይቶች ላይ መሬት የመቆፈር እና የማስተካከል ተግባር የሚያከናውኑ ማሽሪዎች እያስተካክሉ፡፡ ሁለቱ ጎሳዎች እርስ በእርስ የሚዋጉ በመሆን የሚታወቁ ነበሩ፣ የኋላ ታሪካቸው አሉታዊ የነበረ ቢሆኑም በአሚሶም አባላት አደራዳሪነት በተደረሰው የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነት መሰረት አሁን ላይ በአብሮነት እየኖሩ ናቸው፡፡

ተከትሎ ነበር የተካሄደው፡፡ “እንደዚህ አይነት የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሰላምን ለማረጋገጥ በምናከናውነው ተግባር ከአካባቢው ህዝብና ጋር ዘላቂ ግንኙነት ለመፍጠጠር የምናደርገው ቀጣይ ጥረት አንድ አካል ነው፡፡ የእግር ኳስ ውድድሩ የተካሄደው ዛሬ በሶማሊያ በተፈጠረው አንጻዊ ሰላም ሕዝቡ በማህበራዊና

በሶማሊያ፣ ማርካ የቀድሞ ባላንጣ የነበሩ ጎሳዎችን ወክለው የእግር ኳስ ግጥሚያ ያደረጉ ሁለት ቡድኖች በ18/1/2010 ዓ.ም ከግጥሚያቸው አስቀድመው ፎቶግራፍ ተነስተዋል፡፡ሁለቱ ጎሳዎች እርስ በእርስ የሚዋጉ በመሆን የሚታወቁ ነበሩ፣ የኋላ ታሪካቸው አሉታዊ የነበረ ቢሆኑም በአሚሶም አባላት አደራዳሪነት በተደረሰው የተኩስ አቁም እና የሰላም ስምምነት መሰረት አሁን ላይ በአብሮነት እየኖሩ ናቸው፡፡

በስፖርት እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ እንዲሆን በተፈጠረው አመቺ ሁኔታ ነው” ብለዋል በአሚሶም የኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ሮበርት ካማራ፡፡ የእግር ኳስ ውድድሩን የማካሄድ ሃሳብ እንቅስቃሴውን ለመደገፍ የአካባቢው የአገር ሽማግሌ ጥቅም ላይ ያልዋለ የመሬት ይዞታቸውን በስጦታ ካበረከቱ በኋላ በታችኛው ሸበሌ የአካባቢ አስተዳደር አካባቢውን በማጽዳት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ለማዘጋጀት የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ አቀውሙን በማስተባበር የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ አዘጋጅቷል፡፡ በአሚሶም ድጋፍ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታውን ለማስተካከል ቡልዶዘር በመጠቀም ተመራጭ የእግር ኳስ ሜዳ ማዘጋጀት ችለዋል፡፡ እግር ኳስ በሶማሊያ በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጅ ስፖርት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሰላምን ለማራመድ ወጣቶችን ለማንቀሳቀስ በመሳሪያነት ያገለግላል፡፡ አሚሶም መጽሔት

19


በግጭት ውስጥ የሕጻናትን ለወታደራዊነት ጥቅም ምልመላን መከላከል

ሚሶም በትጥቅ ትግል የሕጻናት ወታደሮችን ምልመላና አጠቃቀም በመከላከል ዙሪያ ከሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች ለተወጣጡ ስልሳ ኦፊሰሮች ሥልጠና ሰጠ፡፡ ከእንግሊዝ መንግሥትና በካናዳ የዳልሃውስ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ከሮሚዮ ዳሌይር የሕጻናት ወታደሮች ምልመላ መከላከል ኢኒሼቲቭ በተገኘ ድጋፍ በሴፕቴምበር ወር የተካሄደው የሁለት ቀን ስልጠና ከሱማሌ ሚሊተሪ፣ ፖሊስና የደህንነት አገልግሎት ክፍሎች እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት የተወጣጡ በአውደ ትናቱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በአቅም ግንባታ አውደ ጥናቱ በክብር እንግድነት የተገኙት በአሕ ኮሚሽን ሊቀመንበር የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ልዩ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ካቴኖ ማዴይራ ባሰሙት ንግግር “እነዚህ ሕጻናት ተመልምለው ጽንፈኝነትን እንዳይቀላቀሉ፣ ተመልምለው በራሳቸው ህዝብ፣ በራሳቸው አገር፣ በራሳቸው ጎረቤቶች ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ ማዳን አለብን” ብለዋል፡፡ የአሕ ልዩ ተወካይ በግጭት ውስጥ ሕጻናት ወታደሮችን መልምሎ

በሶማሊያ የጸጥታው ዘርፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የጸጥታ አስከባሪ አባላት በ4/1/2010 ዓ.ም በሶማሊያ ሞጋዲሹ በተደረገው የአሚሶም የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፣ ስልጠናው በትጥቅ ትግል ላይ እድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናትን የሚመለምሉ እና ህጻናትን በወታደርነት የሚያዋጉ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን ለመከላከል በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ያተኩራል፡፡

መጠቀም በሶማሊያ ተስፋፍቶ የሚገኝ ችግር መሆኑን በመጠቆም የችግሩን መጠን ለመለየት የሚረዳ ስታቲስቲካዊ መረጃ ሥርአት ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “በውጊያ ተሳትፎ ያላቸው ሕጻናት ምን ያህል እንደሆኑ በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፤፤ ሆኖም ችግሩ በአልሸባብ ውስጥ ተስፋፍቶ የሚገኝ መሆኑን መናገር እንችላለን” ብለዋል አምባሳደር ማዴይራ፡፡ ሥልጠናው በሕጻናት

ወታደሮች ልየታ፣ ምልመላቸውን በመከላከልና መልሶ በማቋቋምና ከህብረተሰቡ ማቀላቀል በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ አምባሳደር ማዴይራ ሥልጠናው ቀደም ሲል በአሚሶም የተሰጡ ሌሎች ስልጠናዎችን በወሰዱ ሶማሌዎች አመቻችነት የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “ዕቅዱ የአሚሶም የመውጫ ስትራቴጂ አንድ አካል ሲሆን አላማውም ሱማሌዎች የራሳቸውን

በሶማሊያ ሞጋዲሹ የተደረገው ስልጠና በትጥቅ ትግል ላይ እድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናትን የሚመለምሉ እና ህጻናትን በወታደርነት የሚያዋጉ ጸረ-ሰላም ኃይሎችን ለመከላከል በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ያተኩራል፣ የአሚሶም የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ የክብር እንግዳ የነበሩት የሮሚዮ ዳሌር ቻይልድ ሶልጀርስ ኢንሼቲቭ የስልጠና አስተባባሪ፣ ማክኔል ጄኒፈር ለሰልጣኞች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ 20

አሚሶም መጽሔት

አቻዎች ማሰልጠን የሚችሉበትን አቅም ለማሻሻል” ነው ብለዋል፡፡ በሶማሊያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሚ/ር ዴቪድ ኮንካር በሶማሊያ ተስፋፍቶ የሚገኘው የሕጻናት ወታደሮች ምልመላ በአልሸባብ ታጣቂዎች ከሚካሄደው ጽንፈኝነትን የማስፋፋት እንቅስቃሴ ተያያዥነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “ችግሩ በዚህ የአፍሪካ ክፍል ማሕበረሰቡን በከፍተኛ ደረጀ የሚጎዳ የሰላምን አላማ የሚያደናቅፍ ነው” ብለዋል ሚ/ር ኮንካር፡፡ አክለውም “በዚህ ምክንያት ለችግሩ ትልቅ ትኩረት መስጠት አለብን፡፡ የሆነ ነገር ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህ ነው ለዚህ ልዩ ሥልጠና የገንዘብ ድጋፍ ለማስገኘት በአሚሶም አማካኝነት ከአፍሪካ ሕብረት ጋር እንዲሁም ከሱማሌ ፌዴራል መንግሥት ጋር በትብብር የምንሰራው” ብለዋል፡፡ ሚ/ር ግቦው ሲናገሩ “የስልጠናው አላማ በጥቅምት ወር በሚካሄደው የአሠልጣኞች ሥልጠና የሚሳተፉ ዕጩ ሰልጣኞችን በቅድሚያ ለመለየት ከሥልጠናውን ከወሰዱ በኋላ በቀጣይነት በመላ አገሪቱ ለሚገኙ አቻዎቻቸው መልእክቱን ማዳረስና ማሰልጠን የሚችሉበትን አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ነው” ብለዋል፡፡


አሚሶም ለሶማሌ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ መልሶ አስረከበ

ሚሶም ላለፈው አሠርት በቁጥጥሩ ሥር ይዞት የቆየውን የትምህርት ተቋም የሶማሌ ብሄራዊ ዩኒቨርሲቲን ግቢ መልሶ ለፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣኖች አስረከበ፡፡ መጀመሪያ በአሕ የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች በ2007 የተያዘው ዩኒቨርሲቲ በፊት ግንባር አነስተኛ ኦፕሬሽን ቤዝ ጀምሮ በኋላ በአልሸባብ

ላይ የሚካሄደውን ኦፕሬሽን ለማስተባበር በመቀጠልም በሌሎች የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጋር በመተባበር የአልሸባብ ሚሊሻዎችን ከሞቃዲሾ ጠራርጎ ለማስወጣት በተካሄደው ጥምር ኦፕሬሽን ወደ ባታሊዮን ጠቅላይ ጦር ሠፈር አድጓል፡ ፡ ጁላይ 11 ቀን የተደረገው ርክክብ ለትምርት ተቋሙ የመማር ማስተማር

በሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የተገነቡት አዲስ የመማሪያ ክፍሎች ወይም ሌክቸር ክላስ ገጽታ፣ በ4/11/2009 ዓ.ም፡፡

ተግባር እንደገና መጀመር አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ የሶማሊያ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚ/ር አብዲራህማን ዳሂር ኦስማን በክብር እንግድነት በተገኙበት በተከናወነው የርክክብ ሥነ ሥርአት ላይ የአሕ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ ባሰሙት እንግዶች ባደረጉት ንግግር “በዚህ

በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ በ4/11/2009 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ርክክብ በተከናወነበት ወቅት በስፍራው የተገኙ እንግዶች፡፡ አሚሶም መጽሔት

21


በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ በ4/11/2009 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ርክክብ በተከናወነበት ወቅት በስፍራው የተገኙ እንግዶች፡፡የሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ሞሐመድ አህመድ ጂማሌ፣ የዩኒቨርሲቲው ርክክብ በተከናወነበት ወቅት በስፍራው ለተገኙ እንግዶች ንግግር አድርገዋል፡፡

Mohamed Ahmed Jimale, Rector of Somali National University, speaks during the handover ceremony of the Somali National University held in Mogadishu, Somalia

ሁነት አሚሶም የሱማሌዎችን ሽግግር መጀመሩን በግልጽ አሳይቷል፡፡ የሶማሊያን ዩኒቨርሲቲ ከጦር ምሽግነት እንደገና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት በሶማሌዎች እጅ ማስገባት መጀመራችንን ያሳያል” ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው ግቢ የጦር ካምፕ የመሠረቱት ሰላም አስከባሪዎች በኤፕሪል 2016 ልምምድ ሲጀምሩ ጆሃር ወደሚገኘው የአሚሶም ሴክተር 5 ዋና መ/ቤት ተዛውረዋል፡ ፡ የአሕ ልዩ ተወካይ በቁጥጥራቸው ሥር የነበረውን ዩኒቨርሲቲ መልሰው ማስረከባቸው “የደህንነት ጥበቃውን ኃላፊነት ቀስ በቀስ ለሱማሌ ብሄራዊ ጸጥታ ኃይሎች የማስረከብ ሂደት መጀመሩን ያሳያል” ብለዋል፡፡ በማያያዝም ሶማሌዎች አገራቸውን መልሶ በመገንባት ጥረት የመሪነት ድርሻ መውሰዳቸውን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ጉዳይ ልዩ ልኡክ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ እና የሶማሊያ የትምህርት ሚንስትር አብዲራህማን ዳሂር ኦስማን፣ በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ በ4/11/2009 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ርክክብ በተከናወነበት ወቅት በስፍራው ተገኝተው ኦሪሴላዊ ርክክር መፈጸሙን ለማብሰር ሪባኑን ቆርጠዋል፡፡ 22

አሚሶም መጽሔት

“የርክክቡ ሥነ ሥርአት አልሸባብ እድሜ በጣት የሚቆጠር መሆኑን ያሳያል፡፡ ለበርካታ አመታት ይህቺን ከተማ ሲቆጣጠሩ ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ግን የት ነው ያሉት? ጫካ ገብተዋል” ብለዋል አምባሳደር ማዴይራ፡፡ በ1954 የተቋቋመው ይህ ዩኒቨርሲቲ በ1991 በአገሪቱ በተቀጣጠለው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ተዘግቷል፡፡ ሆኖም በሥሩ የሚገኙት ኮሌጆች በሶማሊያ አንጻራዊ ሰላም ከተመለሰ በኋላ እንደገና ተከፍተው ልዩ ሥልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ (ኤስአርኤስጂ) ሚ/ር ማይክል ኪቲንግ ባርጉት ንግግር እዚህ የምናከብራቸው ሶስት እጥፍ ድርብ ሁነቶች አሉ፡፡ አንዱ በዚህ ሁኔታ ለአሚሶም ሚና፣ ቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ፣ ባጠቃላይም ባለፉት 10 አስቸጋሪ አመታት የሶማሊያን ሰላም ለማረጋገጥ በተደረገው ፈታኝ ትግል ከአሚሶም ጋር በአጋርነት ለሠሩ የሱማሌ የጸጥታ ኃይሎች አስተዋጽኦ እውቅና መስጠት ነው” ብለዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሚ/ር አብዲራህማን ዳሂር ኦስማን በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር ርክክቡን “የሶማሊያ ዳግም መወለድ ተምሳሌት” በማለት ገልጸውታል፡፡ “ለአገሪቱ ጸጥታ፣ ለኦኮኖሚ ልማትና ከሁሉም በላይ ደግሞ ለትምህርት ቀዳሚ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ ትምህርት የዘላቂ ልማት መሠረት ነው” የትምህርት ሚኒስትሩ፡፡ ይህንኑ ስሜት የሚጋሩት የዩኒቨርሲቲው ሬክተር ሚ/ር መሐመድ አህመድ ጅማሌ የዩኒቨርሲቲው ግቢ ለፌዴራል መንግሥት መመለስ የሶማሊያን፣ “ሰላም፣ ጸጥታና መረጋጋት መመለስ” ያሳያል ብለዋል፡፡


አይኤፍቲ የሶማሊያን የሲቪል-ሚሊተሪ የሥራ ቡድን ሪፖርት ይፋ አደረገ

ሚሶምና አጋሮቹ የሶማሊያን የሲቪል-ሚሊተሪ የሥራ ቡድን ሪፖርት ሴፕቴምበር 8 ቀን ይፋ አደረጉ፡፡ ሪፖርቱ ባለፉት ሶስት አመታት በሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ መስክ የተከናወኑትን ተግባራት በዝርዝር የሚያስቀምጥ ነው፡፡ በአሚሶምና በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ ቤት (ዩኤንኦሲኤችኤ) በጥምር የተዘጋጀው ሪፖርት ሶማሊያ ፈጣን የአደጋ ምለሽ መዋቅሮቿን የተባበሩት መንግስታ ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽ የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) የተውጣጡ ባለሙያዎች ለመዘርጋት በሶማሊያ ሞጋዲሹ በሲቪል ዜጎች አማካይነት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ዙሪያ በሚያጠነጥነው ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በምታደርገው እንቅስቃሴ የወደፊቱ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ በሚሊተሪና ወደመከላከል ማዞራችንና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሥራ የሚመራበትን መመሪያ በሲቪል ኤጀንሲዎች መካከል አስፈላጊ የእርዳታ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማስቀመጥም የሚረዳ ነው፡፡ የተሻለ ቅንጅት መፍጠር አቅርቦትን ተደራሽ ባልሆኑ የአሠራር መመሪያ ማዘጋጀት የአሚሶም ከፍተኛ እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል፡፡ አካባቢዎች ተደራሽ እንደሚስፈልግ ይጠይቃል፡፡ ባለሥልጣኖች፣ የተመድ “በዚህ ሚሽን ሥር ማድረግ በጣም አስፈላጊ በተጨማሪም አሚሶም ኤጀንሲዎች ተወካዮችና የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ በመሆኑ የረሃብ አደጋን በሲቪል-ሚሊተሪ የሥራ የኮር ዲፕሎማቲክ አባላት እርዳታ ተዋንያን ቁጥር ለማስቀረት ለማህበረሰቡ እገዛ ቡድን (ሲኤምደብልዩጂ) በተገኙበት ሥነ ሥርአት በየጊዜው እየጨመረ ማድረጋችንን ለማረጋገጥ ድጋፍና መመሪያ እየታገዘ ላይ ምክትል ኤስአርሲሲ መምጣት አሚሶምና ከሚሊተሪው ጋር ጥሩ የሥራ እንደመጨረሻ አማራች ሲመን ሙሉንጎ ባደረጉት ኦሲኤችኤ ውጤታማ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ከመቼውም የሚሽኑን ሃብት ተጠቅሞ ንግግር “በሚሊተሪና በሰብአዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው ጊዜ የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ እርዳታን ለሚያስፈልጋቸው ድርጅቶች መካከል ሊኖር ማድረግ ይጠይቃል፡፡ በእኛ የሚገኝበት ሁኔታ ይታያል” ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ የሚገባው የተሻለ የሥራ በኩል ይህ ጥምር ጥረት ብለዋል ብራዲ፡፡ ሁኔዎችን በማመቻቸት በኩል ግንኙነት ምን መምሰል የሚያመሳስሉንን ጉዳዮች ሆኖም ሶማሊያ ገና ከጫካ ውጤታማ ሚና ከሊጫወት እንዳለበት ለመወሰን በመነሻነት ለመረዳት ብቻ ሳይሆን ያልወጣች አገር በመሆኗ እንደሚችል በተግባር እንዳሳየ የሚያገለግለው የሲቪልልዩነቶቻችንን ለመፍታትም ከረሃብ ስጋት በተያያዘ ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ ሚሊተሪ የሥራ ቡድን ሪፖርት እንደሚረዳን እርግጠኛ ነን” አገሪቱ አሁንም በሰብአዊ ከዚህም ሌላ ሪፖርቱ ሲወጣ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ብለዋል ምክትል ኤስአርሲሲ፡፡ ድርጅቶችና በሚሊተሪው ሶማሊያን በመሰሉ አገሮች በመሆኑ ለሪፖርቱ ዝግጅት የተባበሩት መንግሥታት መካከል በተሻለ ደረጃ በቅንጅት የኦፕሬሽን ከባቢው ፈታኝ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት ድርጅት የሶማሊያ የሰብአዊ መሥራት እንደሚያስፈልጋት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ አለበት” ብለዋል፡፡ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ አስጠንቅቀዋል፡፡ በቅርበት በመቀጀትና በአሚሶምና በሰብአዊ ጽ/ቤት (ዩኤንኦሲኤችኤ) “”አሁንም ገና ብዙ ርቀት በመተባበር መሥራት እርዳታ ድርጅቶች መካከል የሶማሊያ ኃላፊ ጀስቲን ብራዲ ይጠብቀናል፡፡ ምናልናት ለረሃብ እንደሚጠይቅ ያለመክታል፡፡ ያለውን መልካም የሥራ “በሶማሊያ የሚገኙ የሰብአዊ አደጋ በተጋለጡ አካባቢዎች በ2014 የተደረገውን ሰፊ ግንኙነት በማድነቅ ይህ እርዳታ ድርጅቶች ትኩረት ጉዳቱን ቀንሰን ሊሆን ውይይት ተከትሎ አሚሶምና ግንኙነት ለአካባቢው ረሃብን ወደ መከላከል የዞረ ይችላል፤ ነገር ግን አሁንም ተመድ ከሰብአዊ እርዳታ ማህበረሰቦች በጣም በመሆኑ እርዳታን በርቀት ስጋቱ ያለ በመሆኑ ሰብአዊ አጋሮች ጋር የሰብአዊ የሚፈለገውን የእርዳታ ለሚገኙ በረሃብ የሚሰቃዩ ተደራሽ ለማድረግ በተሻለ ደረጃ እርዳታ ተዋንያንና የአሚሶም አቅርቦት በተሻለ ደረጃ ማህበረሰቦች ተደራሽ ማድረግ የአሠራር ቅንጅት መፍጠር ኦፕሬሽን የሚመራበትን ለማስተባበር እገዛ አድርጓል ከተፈለገ ከሚሊተሪ ጋር የተሻለ አስፈላፈጊነት ይቀጥላል” በሶማሊያ ተጨባጭ ሁኔታ ብለዋል፡፡ የሥራ ግንኙነት መፍጠር ብለዋል፡፡ ላይ የተመሰረተ መመሪያ በማያያዝም በሶማሊያ የግድ ይላል ብለዋል፡፡ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ፈርመው አጽድቀዋል፡ የሚታየውን ተለዋዋጭ ሁኔታ “ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘርፍ ከታየው እንቅስቃሴ ፡ በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ተከትሎ የሰብአዊ እርዳታ በሶማሊያ የምንገኘው ዝርዝር ሌላ ሪፖርቱ ወደፊት ላይ የተመሠረተው የኦፕሬሽን ተዋንያን ቁጥር በየጊዜው በተራዘመ አይነተኛ ቀውስ ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን መመሪያ በሶማሊያ በሲቪልና እየጨመረ በመጣበት ባሁኑ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በትክክል ለመፍታት በሚሊተሪ መካከል የሚኖረው ወቅት ሰብአዊ እርዳታን ትኩረታችንን ረሃብን የሚረዳ በሶማሊያ ተጨባጭ ቅንጅት የሚገዛበት ነው፡፡ አሚሶም መጽሔት

23


በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ በሶማሊያ ሞጋዲሹ ተገኝተው በእርዳታ መልክ የተበረከተውን የምግብ ይዘቶች ከጭነት መኪና ላይ እንዳለ ለሶማሊያ መንግስት አስረክበዋል፡፡

አ.ሕ ለድርቅ ተጎጂዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ላከ

አፍሪካ ሕብረት ለሶማሊያ የድርቅ ተጎጂዎች 100,000 ዶላር የሚያወጣ የምግብ እርዳታ አደረገ፡፡ የተልእኮው ኃላፊ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ማዴይራ በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃመት ሥም 67 ሜትሪክ ቶን የሩዝ፣ ባቄላና የአትክልት ዘይት ምግብ እርዳታ በይፋ ኦክቶበር 10 ቀን ለፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣኖች አስረክበዋል፡፡ ሚ/ር ማህማት ባለፈው ማርች በሶማሊያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት አለማቀፍ የአስቸኳይ እርዳታ ጥሪ ከቀረበ በኋላ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ ቃል ገብተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የእርዳታ ጥሪው በሶማሌ ሕዝብና በአለማቀፍ ማህበረሰብ በኩል ባስገኘው ያልተጠበቀ ምላሽ ድርቁን ለመከላከል የሚውል በጠቅላላው 1.1

ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ “የድርቁ አሁን የሚገኝበት ሁኔታ መጠነኛ ለውጥ ያሳየ ቢሆንም የሶማሊያ ችግር አሁንም የተጠናከረና ቀጣይ የድጋፍ ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ የድርቅ ተጎጂዎችን ለመርዳት በኮሚሽኑ ሊቀመንበር ቃል የተገባውን 100,000 ዶላር ባስታወቁበት ወቅት አምባሳደር ማዴይራ ባደረጉት ንግግር “ሌሎችም ይህንኑ አርአያነት መከተል እንዳለባቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል” ብለዋል፡፡ በማያያዝም የሶማሊያ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ኤስአርሲሲ ማዴይራ አሚሶም የሶማሊያን መንግሥትና የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች እርዳታ ለሚያስፈልገው ህዝብ ድጋፍ ለመስጠት የሚያደርገውን ቀጣይ ጥረት ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡ “ድጋፍ ለሚያስፈልገው ሕዝብ

በእርዳታ መልክ የተበረከተውን የምግብ ይዘቶች ከጭነት መኪና ላይ እንዳለ ለሶማሊያ መንግስት የማስረከቡ ስራ ሲከናወን የአፍሪካ ህብረት የሶማሊዮ ጉዳይ ተልእኮ(አሚሶም)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በ30/1/2010 ዓ.ም በሶማሊያ ሞጋዲሹ ተገኝተው በህብረት ተመልክተውታል፡፡ 24

አሚሶም መጽሔት

የምግብ እርዳታ በአግባቡ መከፋፈሉንና መድረሱን ለማረጋገጥ አሚሶም ከሰብአዊ ጉዳዮችና የአደጋ ማኔጅመንት ሚኒስቴር እንዲሁም ከአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎች ጋር በቅርበት ይሠራል” ብለዋል፡፡ የሰብአዊ ጉዳዮችና የአደጋ ማኔጅመንት ሚኒስቴር ቋሚ ጸኃፊ ሚ/ር ሞአሊም መሐመድ እርዳታውን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር ምስጋናቸውን ገልጸው ከተለያዩ አጋሮች በተገኘው ድጋፍ አማካኝነት በሶማሊያ ረሃብን ማስቀረት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ “በመላው አለም የሚገኙ ሶማሌዎች ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለመርዳት በገቢ አሰባሰብ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ አለማቀፉ ማህበረሰብም ለሶማሌ ሕዝብ የሚያስፈልገውን አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ በኩል ከፍተኛ ሥራ አከናውኗል” ብለዋል ሚ/ር ሞአሊም፡፡ በማያያዝም ሶማሊያ የበለጠ ምርታማ ለማድረግ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ተጽእኖ ለመቀነስ መንግሥት የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡ የተመድ ዋና ጸኃፊ የሶማሊያ ምክትል ልዩ ተወካይ (ዲኤስአርኤስጂ) ፒተር ዴ ክለርክ የአፍሪካ ሕብረት ያደረገውን ወቅታዊ እርዳታ አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሶማሊያ መንግሥትና ሕዝብ ለድርቁ በሰጡት ምላሽና እርዳታ ለሚስፈልጋቸው ወገኖች ላደረጉት ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ “በአፍሪካ ሕብረት እጅግ እንኮራለን፣ ምክንያቱም ባደረጉት እርዳታ ብቻ ሳይሆን ክፍለ አህጉሩ የራሱን ችግር ለመፍታት በሚደረገው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ተሳታፊ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዚህ አገር የእርዳታ ተደራሽነትና ሰላም ከፍተና ሚና በመጫወቱና የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽኑን ስኬት ማሳየት በመቻሉም ነው” ብለዋል ዴ ክለርክ፡፡


አሚሶም በጨረፍታ እይታ የኃይል አዛዡ በአሚሶም ሥር በሶማሊያ የሚሠሩትን የኬንያ ሰላም አስከባሪዎች ጎበኙ

አሚሶም የኃይል አዛዥ ሌ/ጄኔራል ኦስማን ኑር ሱባግሌ በሴክተር 2 ጁባላንድ ስቴት የሚገኙትን በአሚሶም ሥር የሚንቀሳቀሱትን የኬንያ ሰላም አስከባሪዎች በኦክቶበር ወር ጎበኙ፡፡ የኃይል አዛዡ በዶብሌ፣ አፍማዶውና ኪስማዮ ተመድበው የሚሠሩትን ሰላም አስከባሪዎች በበጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በሶማሊያ ሰላም ለማምጣት ላደረጉት ጥረትና ለከፈሉት መስዋእትነት ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሴክተር ሁለት አዛዥ ብርጋዲየር ዊሊያም ሹሜና ከሌሎች የአሚሶም ኃይል ዋና መ/ቤት ከፍተኛ መኮንኖች ጋር በመሆን ባደረጉት ጉብኝት ሌ/ጄኔራል ሱባግሌ ሰማል አስከባሪዎቹ ባከናወኑት ተግባር የተሰማቸውን እርካታ ገልጸዋል፡፡ በአፋምዶ የኬዲኤፍ ሰላም አስከባሪዎች የግንባር ኦፕሬሽን ቤዝ (ኤፍኦቢ) የኃይል አዛዥ በኮማንዲንግ ኦፊሰር ሌ/ኮ ፒዮኒ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በመቀጠልም በኬዲኤፍ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሲቪል- ወታደራዊ ግዳጅ የእድሳት ሥራው የተጠናቀቀውን የአፋምዶው ሆስፒታል ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ሌ/ጄኔራል ሱባግሌ ሆስፒታሉን ሥራ ካስጀመሩ በኋላ ለአፋምዶ ነዋሪዎች ባሰሙት ንግግር “ለአፋምዶው ሕዝብ ምስጋናዬን እገልጻለሁ ለሰላምና ጸጥታ ድርሻችሁን ስትወጡ ቆይታችኋል፤ አሁኑም የሚቻላችሁን ሁሉ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎችና የጁባላንድ ኃይሎች ያደረጋችሁትን አስተዋጽኦ ያደንቃሉ፤ ከእናንተ ጋር በመሥራታቸው ደስተኛ ናቸው” ብለዋል፡፡ የኃይል አዛዡ በወታደሮች የተበረከተ

በአሚሶም ስር በሶማሊያ በሚሰራው የሰላም ማስከበር ስራ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ ኮማንደር ሌተ. ጄኔራል ኦስማን ኑር በ27/2/2010 ዓ.ም በዶብሌይ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ኮርፖራል ማርታ ማሮአ ከአሚሶም የሴክተር

ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚከፋፈል ምግብና መድኃኒት ለአፋምዶው ዲስትሪክት ኮሚሽነር ለመሐመድ ሼክ ዳካኔ አስረክበዋል፡፡ “የሰው ልጆች የተሟላ ኑሮ ለመኖር ሰላም ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰላም ካገኛችሁ ትምህርት፣ የጤና እንክብካቤ፣ የእርሻ ልማት መፈለግ ትችላላችሁ፣ በንግድ ሥራም መሠማራት ትችላላችሁ” ብለዋል የዲስትሪክት ኮሚሽነሩ፡፡ የአፋምዶው የአገር ሽማግሌዎች ለአሚሶም ምርቃት በማሰማት

ሰላም አስከባሪዎቹ ከአማጺያን ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አበረታተዋቸዋል፡፡ የአካባቢው የአገር ሽማግሌ አብዲ ኦላል “ለኃይል አዛዡ በሶማሊያ የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች አዛዥ እንደመሆንዎ መጠን ዘላቂ ቅርስ እንድትተዉልን እማጸናለሁ፤ አልሸባብን ማዳከም አለባችሁ” ብለዋል፡፡ ጄኔራል ሱባግሌ ከዶብሌ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የታድባ የግንባር ኦፕሬሽን ቤዝ ባደረጉት ጉብኝት ሠላም አስከባሪዎቹን አነጋግረዋል፡፡.

በታችኛው ጁባ ክልል በዶብሌ የሚገኙ ማህበረሰቦች በአሚሶም ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነዋል

ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በታችኛው ጁባ ክልል በዶብሌ የሚገኙ የሶማሌ ማህበረሰቦች በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር በሚንቀሳቀሱት በኬንያ መከላከያ ኃይል (ኬዲኤፍ) ሰላም አስከባሪዎች በተከናወኑ የተለያዩ የሥራ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ሰላም አስከባሪዎቹ በሚቆጣጠሩት አካባቢ ለሚገኙ እርዳታ

ለሚያስፈልጋቸው ማህበረሰቦች ድጋፍ የህክምና ካምፕ፣ የትምህርት ቤት እድሳት፣ የአምልኮ ሥፍራና የትምህርት መሳሪያዎች እርዳታ ሥራዎች አከናውነዋል፡፡ ዋና መ/ቤቱ በዶብሌ የሚገኘው የሴክተር 2 ሰላም አስከባሪዎች ለቡሳር ነዋሪዎች የተለመዱ በሽታዎች ህክምናና ቀላል የቀዶ ጥገና አገልግሎት በነጻ የህክምና ካምፕ አደራጅተዋል፡፡

ኮማንደርብርጋዴር ዊሊያም ሹሜ እጅ የተበረከተላቸውን ሚዳሊያ ተቀብለዋል፡፡2. በአሚሶም ሰላም አስከባሪ ጦር ስር የሰላም አስከባሪ ቡድኑ አባላት የሆኑ የኬንያ ሰላም አስከባሪዎች ከሰላም ማስከበሩ ተልእኮ ባሻገር በሌሎች የበጎ አድራጎት ተግባራት፣ ለምሳሌ በጤና ምርመራ፣ በግርዛት እና ሌሎች ጎጂ ባህሎች ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ በአካባቢው ለሚገኝ መስጅድ ግንባታ የሚውል ሲሚንቶ እና ቀለም፣ እንዲሁም ቁራን በነጻ በስጦታ በማበርከት ህዝቡን በማገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሚሶም መጽሔት

25


በተጨማሪም ሰላም አስከባሪዎቹ በቡሳር ለሚገኝ መስጊድ እድሳት የህንጻ መሳሪያ ልገሳ አድርገዋል፤ የቅዱስ ቁርአን ቅጂዎችና ለነዋሪዎች የማህበረሰብ ስብሰባዎች የሚገለግል የአዳራሽ ሲስተም ለግሰዋል፡፡ ሰላም አስከባሪዎች በዶብሌ ከተማ በሚገነው ዋሞ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ቤቱን መግቢያና ዙሪያ አጥር ቀለም ቀብተዋል፤ 100 ዴስኮች እንዲሁም የመጻህፍት መደርደሪያዎች ለግሰዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በጠቅላላው 350 ተማሪዎች አሉት፡፡ በዚሁ ሴክተር በአብደሌ ቢሮሌ ሥፍራ

የኤዲኤፍ ሰላም የሕክምና ባለሙያዎች ለነዋሪዎች ነጻ የጤና ምርመራና የህክምና አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡

ባለፉት ወራት የኬንያ ሰላም አስከባሪዎች ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በመተባበር በድርቅ ለተጎዱ የክልሉ

በአሚሶም ሰላም አስከባሪ ጦር ስር የሰላም አስከባሪ ቡድኑ አባላት የሆኑ የኬንያ ሰላም አስከባሪዎች ከሰላም ማስከበሩ ተልእኮ ባሻገር በሌሎች የበጎ አድራጎት ተግባራት፣ ለምሳሌ በጤና ምርመራ፣ በግርዛት እና ሌሎች ጎጂ ባህሎች ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ በአካባቢው ለሚገኝ መስጅድ ግንባታ የሚውል ሲሚንቶ እና ቀለም፣ እንዲሁም ቁራን በነጻ በስጦታ በማበርከት ህዝቡን በማገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታና የንጹህ መጠጥ ውሃ አከፋፍለዋል፡፡ በተጨማሪም ሰላም አስከባሪዎቹ የሶማሌ ብሔራዊ ጦር (ኤስኤንኤ) አቻዎቻቸው በኤስኤንኤ ካምፖች ዙሪያ አጥር በማጠርና ምሽግ በመቆፈር ቤት ሰራሽ ፈንጂ የተጠመደባቸው ተሽከርካሪዎች (ቪቢአይኢዲ) የመከላከያ ወረዳቸውን ጥሰው እንዳገቡ ለመከላከል በሚደርጉት እንቅስቃሴ እገዛ አድርገዋል፡፡ አሚሶም በደቡብ ማዕከላዊ ሶማሊያ በተለይም በግንባር የኦፕሬሽን ቤዞች የሶማሌዎችን የሰላም ጥበቃና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በሴክተር ሶስት የ14 ወር ተልእኳቸውን ላጠናቀቁ የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ግብዣ ተደረገላቸው

ቤይ፣ባሉልና ጌዶ ክልሎች ተልእኳቸውን ያጠናቀቁ የኤኤንዲኤፍ-አሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ለክብራቸው በደቡብ ምዕራብ ስቴት አስተዳደራዊ መዲና በባይዶዋ ከተማ ግብዣ ተደረገላቸው፡፡ በሥነ ሥርአቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ጊዜያዊ አስተዳደር (ኤኤስደብልዩኤ)፣ የዩኤንሶም፣ የዩኤንሶስ፣ የዩኤን ማስ የፖሊስ ባለሥልጣኖች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሴቶች ተወካዮች፣ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞችና የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ ሰላም አስከባሪዎቹ ወታደሮች በሶስት ክልሎች በተሰናባቹ የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ጄኔራል ገብረመስቀል ገብረእግዚአብሄር አመራር ሥር

ማህበረሰቦችን አገልግለዋል፡፡ ወታደሮቹ ሜዳልያና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ ጄኔራል ብርሃነመስቀል በሥነ ሥርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር “አይኤስደብልዩኤን (ደቡብ ምዕራብ ስቴትን) እና የሴክተር ሶስት ነዋሪ ማህበረሰቦች ከወታደሮቻችን ጋር እጅና ጓት በመነሆን ላከናወኑት አኩሪ ተግባር ማማስገን እወዳለሁ” ብለዋል፡፡ የኤኤስደብልዩኤ ተወካይ ሚ/ር መሐመድ ሃሰን ፋቂ በበኩላቸው ባደረተጉት ንግግር ሰላም ተሰናባቾቹ ሰላም አስከባሪዎች ለሶማሊያ ሰላም ለከፈሉት መስዋእትነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ በማያዝም “ከኢኤንዲኤፍ-

የሴክተር 3 ኮማንደር ጀነራል ገብመስቀል (የእግረኛ ጦር) በባይዶአ የስራ ስንብታቸውን ሲያጠቃልሉ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ሐምሌ 8 የተፈጸመ ነው፡፡

አሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ጋር ላለፉት 14 ወራት በጥሩ ሁኔታ አብረን ሠርተናል፡ ፡ ከአልሸባብ ጋር በተደረገው ውጊያ ያልተቆጠበ ድጋፋቸው አልተለየንም፡፡ ሰላም አስከባሪዎቹ በድርቅና ከዚሀ ተይያዞ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ በተደረገው የሰብአዊ ምላሽ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ

አድርገዋል” ብለዋል ሚ/ር ፋቂ፡፡ በሥነ ሥርአቱ ላይ የተገኙት የአሚሶም የኃይል አዛዥ ሌ/ጄኔራል ኡስማን ኑር ሱባግሌሰላም አስከባሪዎቹ በሰላም ማስከበርና በድጋፍ ኦፕሬሽኖች ላደረጉት ተጽእኖ ፈጣሪ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢኤንዲኤፍ የአሚሶም ወታደሮች የግነቦት 20ን ሀያሰባተኛ አመታዊ በአል አከበሩ

ኢኤንዲኤፍ የመጡ የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ሜይ 28 ቀን በኢትዮጵያ የደርግ ሥርአት የወደቀበትን የግንቦት 20 ቀን 26ኛ አመት መታሰቢያ በአል አከበሩ፡፡ በደማቅ ሁኔታ በተከበረው በዚህ በአል ላይ የአሚሶም የኃይል አዛዥ ሌ/ጄኔራል ሱባግሌና ሌሎች አጋሮች ተገኝተዋል፡፡

26

አሚሶም መጽሔት


የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ካል-ፉርዴርን ነጻ አወጡ

አሚሶም ሰላም አስከባሪዎችና የሱማሌ ጥምር የአገር መከላከያ ሠራዊት በጥምር ኦፕሬሽን ባደረጉት በአልሸባብ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ መንደሮችን ነዋሪ ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ባደረጉት መተነ ሰፊ ጥምር የማጥቃት ዘመቻ ኦገስት 3 ቀን 2017 ካል ፎርዴርን ነጻ አውጥተዋል፡፡ የቢኤንዲኤፍ 3ኛ ባታሊዮን ወታደሮች ከሱማሌ የአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት ያካሄዱት በኮሎኔል ሊኢኒዳስ ኒንዴሬዬ አዛዥነት የተመራው ጥምር የማጥቃት ዘመቻ የአልሸባብ አማጺዎችን

ከማሃዴይ ጠራርጎ ለማስወጣት በተዘጋጀ የጋራ ዕቅድ መሠረት የተመራ ነበር፡፡ ኮሎኔሉ ባደረጉት ንግግር “የዚህ ኦፕሬሽን ዋና አላማ በሴክተር 5 ለቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ነጻ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ዋና የአቅርቦት መስመሮች (ኤምኤስአር) ክፍት ለማድረግ፣ እንዲሁም በአልሸባብ አሸባሪዎች ታግቶ የሚገኘውን የአካባቢውን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ነበር” ብለዋል፡፡ አሸባሪዎቹ የሰከላም አስከባሪዎቹን እንቅስቃሴ ለማሰናከልና ለማጓተት ቤት

ሰራሽ ፈንጂ (አይኢዲ) አጥምደው ነበር፤ ሆኖም የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ባሳዩት ንቁ ተሳትፎና ሙያዊ ብቃት እነዚህን ፈንጂዎች ማስወገድና የሰራዊቱን ኦፕሬሽኖች ቀታነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የካል ፎርዴር አካባቢ ማህበረሰብ ከአማጺዎች ምንም መቋቋም በሌለበት ነጻ ወጥቷል፣ አማጺዎቹም ወደ ጂምቢሎ ጫካ ተበታትነዋል፡፡ የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎችና የሱማሌ የአገር መከላከያ ሠራዊት አሸባሪዎቹን ለቀናት እግር በእግር ካሳደዱ በኋላ መጨረሻ ላይ በጥቅጥቅ ጫካ ገብተው ጠፍተዋል፡፡ ሰላም አስከባሪዎቹ አሸባሪዎቹ ሊደበቁ በሚችሉበት በማንኛቸውም ኪስ ቦታዎች አሰሳ ቀጥለዋል፡፡ ኦፕሬሽኑ በአሚሶምና በሶማሌ ፌዴራል መንግሥት መካከል በጁላይ ወር በሞቃዲሾ የተደረገውን ጥምር ስብሰባ ያሳለፈውን የውሳኔ ሃሳብ ተከትሎ የተከናወነ ነበር፡፡ በዚህ ጥምር ስብሰባ አልሸባብን ሙሉ በሙሉ በማዳከም ዋና የአቅርቦት መስመሮች ለትራፊክ ክፍት የሚሆኑበትን አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር በሁሉም ሴክተሮች ጥምር ኦፕሬሽኖች እንዲካሄዱ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ዋና የአቅርቦት መስመሮች በሱማሌ ሕዝብ መካከል የንግድ እንቅስቃሴም የሚሳልጡ ናቸው፡፡

ኡጋንዳ በሶማሊያ አዲስ ተዋጊ ቡድን አሰማራች

ኡጋንዳ ሕዝባዊ መከላከያ ሠራዊት የመጣ አዲስ ተዋጊ ቡድን (ተዋጊ ቡድን 22) ተዋጊ ቡድን 19ን በመተካት በጁላይ ወር በሶማሊያ ተሠማርቷል፡፡ ወታደሮቹ ሞቃዲሾ እንደደረሱ በኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ካያንጃ ሙሃንጋ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሃንጋ ባሰሙት ንግግር “ከተዋጊ ቡድን 19 እንኳን በጣም የተሻለ ስኬታማ ውጤት እንዲያመጡ እንጠብቃለን፡፡ በእግርጥ በዋና ዋና የአቅርቦት መስመሮች

(ኤምኤስአር) ጸጥታ ማረጋገጥ ትልቅ ተግባር ቢሆንም የህዝቡን ሰላምና ጸጥታ ማረጋገጥና አልሸባብን መዋጋትና ማዳከም የበለጠ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ የሶማሊያን መንግሥትና ሥራዎቹን ለመደገፍ እዚህ የተገኘነውም ለዚሁ ነው” ብለዋል፡፡ ተዋጊ ቡድን19 የአንድ አመት ግዳጁን ካጠናቀቀ በኋላ ጁላይ 21 ቀን ሶማሊያን ለቆ ወጥቷል፡፡ ሠላም አስከባሪዎቹ በአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልእኮ በማራካ፣ በታችኛው ሸበሌ ክልል ግዳጃቸውን ተወጥተዋል፡፡ ግዳጃቸውን

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰላም ማስከበር ስራ ላይ አዲስ የተሰማሩት ወታደሮች በሶማሊያ ሞጋዲሹ የአደን አብዱሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው በአውሮፕላን ሲወርዱ ይታያሉ፡፡

የፈጸሙ የመጀመሪያው ዙር ተሰናባች ሰላም አስከባሪዎች ከብርጋዲየር ጄኔራል ሙሃንጃ

እጅ ሜዳልያና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ “ተዋጊ ቡድን 19 አሚሶም መጽሔት

27


በታችኛው ሸበሌ ክልል በማርካ ዲስትሪክት እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ነበር ሲንቀሳቀስ የነበረው፡፡ በዚያ አካባቢ ጥሩ ተግባር አከናውነዋል” ብለዋል የሰላም አስከባሪዎቹ አዛዥ፡፡ አክለውም “ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ አድርገዋል፡፡ እንደምታውቁት በአገር ውስጥ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች (ኤዲፒ) አሉን፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለያዩ የአይዲፒ ካምፖችና በማዕከል ለህዝቡ የጸጥታ ጥበቃ አድርገዋል” ብለዋል፡፡

የአሚሶም ሴክተር 1 ተጠባባቂ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ካያንጃ ሙሀንጋ በሱማሊያ የአንድ ዓመት የሰላም ማስከበር ግዳጁን ላጠናቀቀው ሰላም አስከባሪ ወታደር የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

በድርቅ ክፉኛ ከተጎዱ የሶማሊያ ክልሎች አንዱ የታችኛው ሸበሌ ክልል ነበር፡፡ በድርቁ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቀዬአቸውን ለቀው የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ለመሆን ተገደዋል፤ ባሁኑ ጊዜ ሰብአዊ እርዳታ በቀላሉ ማግኘት በሚችሉባቸው መጠለያ ካምፖች ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ የአይዲፒ ካምፖች በሱማሌ የጸጥታ ኃይሎችና በአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች በጥምር ጥበቃ የሚደረግላቸው ናቸው፡፡

አዲሱ የቡሩንዲ ተዋጊ ቡድን ሶማሊያ ደረሰ

ቡሩንዲ የአገር መከላከያ ሠራዊት (ቢኡንዲኤፍ) አዲሱ ተዋጊ ቡድን የአንድ አመት ግዳጁን ለመጀመር በኦገስት ሶማሊያ ደርሷል፡፡ በሌ/ኮሎኔል ፊፕበርት ሃቱንጊማና የሚመራው 39ኛ ባታሊዮን የቢኤንዲኤፍን 45ኛ ባታሊዮን ተክቷል፡፡ “በዚህ ተልዕኮ የምጠብቀው የሶማሊያን ሰላምና መረጋጋትና የሶማሊያን ሕዝብ ሰላም ለመመለስ መርዳት ነው” ብለዋል፡፡ ሌላው ባታሊዮን 44ኛ ባታሊዮን ሲሆን የ38ኛ ባታሊዮንን ይዞታ ለመረከብ በኦገስት ወር ሶማሊያ ደርሷል፡፡ ከኡጋንዳ በመቀጠል በሶማሊያ ከተራዘመ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት አስከባሪ ወታደሮች ካዋጡ አገሮች ሁለተኛዋ አገር ቡሩንዲ ነበረች፡፡ በሶማሊያ ተልእኮ ሰላም አስከባሪዎች ያዋጡ አገሮች (ቲሲሲ) ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ ነበሩ፡፡

አዲስ ወደ ሰማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይልን የተቀላቀሉት የቡሩንዲ ወታድች በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ስር ለማገልገል 14/12/2009 ዓ.ም ሞጋዲሹ ደርሰዋል፡፡

የአሚሶም ሰላም አስከባሪዎች ከመካከለኛው ሸበሌ ክልል የወዳጅነት ስጦታ ተበረከተላቸው

መካከለኛው ሸበሌ ክልል ሙስሊም ማህበረሰብ በመካከለኛው ሸበሌ ክልል ተመድበው ለሚሰሩ የአሚሶም የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች የኢድ አልፈጥር

በአልን ምክንያት በማድረግ አሥር ላሞች በስጦታ ለገሰ፡፡ ይህ ስጦታ የወዳጅነት ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ ብቻ ሳይሆን በአሚሶም የቡሩንዲ ሰላም አስከባሪዎችና

የአሚሶም ሰላም አስከባሪ ጓድ አባላት በሶማሊያ የሚድል ሸበሌ ክልል ሲደርሱ ከማህበረሰቡ መልካም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ 28

አሚሶም መጽሔት

በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ላለው መልካም ግንኙነት መገለጫም ነበር፡፡ የመካከለኛው ሸበሌ ገዥና የማሃዳ ዲስትሪክት ኮሚሽነር በተገኙበት ሥነ ሥርአት የ10ኛው ኮንቲንጀንት ኤታማዦር ሹም ኮሎኔል አልፎንሴ ርዊንታዊ በአሉን ምክንያት የአካባቢው ማህበረሰብ ለሰላም

አስከባሪዎቹ ላበረከተው ስጦታና ላሳየው ትህትና በኮንቲንጀንቱ አዛዥ ስም ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡ ገዥው ባደረጉት ንግግር “በአስቸጋሪ ሁኔታ ሌት ከቀን ሠርታችኋል፡፡ የሶማሌ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት እንዲያገኝ የህይወት መስዋእትነትም ከፍላችኋል፤ እናመሰግናችኋለን” ብለዋል፡፡


የኡጋንዳ አዲሱ የመከላከያ ዋና ኤታማዦር በሶማሊያ ጉብኝት አደረጉ

ኡጋንዳ ሕዝብ መከላከያ (ዩዲዲኤፍ) የመከላከያ ዋና ኤታማዦር ሹም (ሲዲኤፍ) ጄኔራል ዴቪድ ሙሁዚ በኦገስት ወር በሶማሊያ ይፋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ጄኔራሉ በሶማሊያ ያደረጉት ጉብኝት የመደበኛ የሚሽን ክትትል አካል ሲሆን የአገሪቱ መከላከያ ዋና ኤታማዦር ሹም ሆነው ከተሾሙ ወዲህ ይህ ጉብኝት የመጀመሪያቸው ነው፡፡ በጉብኝታቸው ወቅት ከሰላም አስከባሪዎች ጋር የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል፤ ካምፖቻቸውን ጎብኝተዋል፣ ከተለያዩ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ የሶማሊያ ባደረጉት ጉብኝት የዩፒዲኤፍ ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን አስከትለዋል፡፡

የዩጋንዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ እታማጆር ሹም ጀኔራል ዴቪድ ሙሆዚ በአፍሪካ ህብረት የሶላሚያ ሰላም አስከባሪ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ጄኔራል ሙሁዚ ሞቃዲሾ እንደደረሱ በሰጡት መግለጫ “የዚህ ጉብኝት አላማ ሰላም አስከባሪዎቹን እንቅስቃሴ ለማጣራት ነው፤ የመበደኛ ጉብኝት አካል ሲሆን ሆኖም በቅርቡ በጎሪዮወይን የተከሰተውን ሁነትም ተከትሎ

የተደረገ ጉብኝት ነው፡ ፡ እዚህ መጥተን በሚሽኑ አካባቢ ከኦፊሰሮችና ከሰላም አስከባሪዎች ለመገናኘት በታቀደው መሠረት የተደረገ ጉብኝት ነው፤ ዛሬ እዚህ የተገኘሁትም በዚህ ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡

ጄኔራል ሙሁዚ የኦፕሬሽኑን ቁመና በተሻለ ደረጃ ለመረዳት ከአሚሶም የኃይል አዛዥ ከሌ/ጄኔራል ኦስማን ኑር ሱባግሌ እና ከአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ልዩ ተወካይና ከአሚሶም ኃላፊ አምባሳደር ፍራንቺስኮ ኬታኖ ማዴይራ ጋር ተከታታይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ በሶማሊያ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና የሰላም ሂደቱን ለመደገፍ በመወሰደድ ላይ ያለውን እርምጃ በሚመለከት ተነጋግረዋል፡፡ ኡጋንዳ በሶማሊያ ማርች 2017 ሰላም አስከባሪ ካዋጡ አገሮች የመጀመሪዋ ስትሆን በአፍሪካ ሕብረት ተልእኮ ሥር ቢያንስ 6000 ሰላም አስከባሪዎች አዋጥታለች፡፡

የሶማሊ እና የጂቡቲ ፓርላመንት አፈ-ጉባኤ በበለድ-ወይን ጉብኝት፤

ሶማሊያው ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፕሮፌሰር ሞሀመድ ኦስማን ጃዋሪ እና አቻቸው የጂቡቲው ክቡር ሞሀመድ አሊ ሃሚድ በቅርቡ በመአከላዊ ሶማሊያ በሂራን ክልል በምትገኘውን በለት ወይን የምትባለውን ከተማ የአካባቢያውን አስተዳደሮቺን እና ህግ አርቃቂዎችን ሲያነጋግሩ፡፡ ሁለቱም ባለስልጣናት በተጨማሪም በመአሚሶም ስር የሚመራውን በሂራን የሚገነውን የጂቡቲ ተጠባባቂ ሀይል አራተኛ ክፍለ ጦር ጎብኝተው ከጂቡቲ የጦር አዛዦች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ጂቡቲ አሸባሪውን አልሸባብ ለመዋጋት ለአሚሶም ወታደሮችን ካበረከቱት አገራት

ኢትዮጲያ፣ቡሩንዲ፣ኬንያ እና ኡጋንዳ መካከል አንዳ ስትሆን የጉብኝቱም አላማ በአካባቢው ሰፍረው ለሶማሊያ ህዝብ ደህንነት መስዋትነትን ለሚከፍሉት ወታደሮች ማበረታታተን ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ የሂራ-ሸበሌ ክልላዊ መንግስተ ፕሬዚደንት የተከበሩ ሞሀመድ አብዲ ዋሬ የቃል አቀባዪን ጉብኝቱን ተቀላቅለዋቸው ነበር፤ የሶማሊያው ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፕሮፌሰር ሞሀመድ ኦስማን ጃዋሪ የጂቡቲው አቻቸውን ክቡር ሞሀመድ አሊ ሃሚድ አጂበው ከሂራንን አስተዳደሮች ጋር በጉብኝታቸውም ለነበረው ስብሰባ ልክ በበለት-ወይን እንደደረሱ ሲያመሩ፡፡ ሁለቱ መሪዎችም ከክልሉ ወቅት ከአካባቢው ፕሬዚደንት ክቡር ሞሀመድ አብዲ ዋሬ ተቀብለዋቸዋል፡፡ አመራሮች ጋር ሰፋ ባለ ጉዳዪች ላይ ወቅት በሶማሊያ ምክር ቤት ምክክር አድርገዋል፡፡ ሂደት ላይ ተገኝተው ንግግር የጂቡቲው አፈ ጉባኤ በዚሁ አድርገዋል፡፡ መንግስታዊ ጉብኝታቸው

የጂቡቲው ሰራዊት የአገልግሎት ግዴታውን ጨርሶ፤

በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ስር የጂቡቲ ሰራዊት በሴክተር 4 ስር የተሰማሩ ሲሆን፣ በ8/4/2010 ዓ.ም በሶማሊያ የነበራቸው የግዳጅ ቆይታ ሲጠናቀቅ ይህንኑ አስመልክተው በበለጥ ወይኒ ትርኢት አሳይተዋል፡፡ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባላት ለሰጡት ከፍ ያለ አገልግሎት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ጂቡቲው ተጠባባቂ ሰራዊት በሶማሊያ ግዴታቸውን ለተወጡ ወታደሪች ደማቀ አከባበር አደረጉ፡፡ የጂቡቲው ዋና አዛዥ ሀሰን ጃማ በአሚሶም አራተኛ ክፍለጦር የሺኝቱን ስነስርአት መርቀው ከፍተዋለል፡፡ በምረቃውም ስነስርአት ወቅት ወታደሮቹ የፓሬድ በማድረግ ለአገልግሎታቸው የምርቃት የእውቅና ሰርቲፊኬት ተቀብለዋል፡፡

አሚሶም መጽሔት

29


ሶማሊያ ከድተው ለሚመለሱ መልሶ ማቋቋም ቀዳሚ ትኩረት ሰጥታለች

ሶማሊያ የከጂዎች መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም (ዲአርፒ) ከታጣቂ ተቃዋሚ ቡድኖች የሚመጡ ከጂዎችን ከህብረተሰቡ የማቀላቀልና መልሶ የማቋቋም ዝርዝር መርሃ ግብር አውጥቷል፡፡ ቀዳሚ ትኩረት የተሰጠው እቅድ ከጂዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ማህበረሰቡን በአካባቢ ደረጃ በውይይት ተሳታፊ ማድረግ፣ ለዲአርፒ ሥልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፣ ግንኙነት መፍጠር፣ ፋይናንስና ሃብት ማንቀሳቀስ፣ ውትወታና ክትትል፣ ተገቢ ተግባቦትና የሪፖርት አቀራረብ ሥርአት መፍጠር፣ የከጂዎች ማቋቋሚያ የመረጃ ሥርአት መፍጠርና የመስክ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ይጨምራል፡፡ የግንኙነትና ሪፖርት አቀራረብ ሥርአቱን ለማሳለጥ ለዲአርፒ ዝግጅት ከብሔራዊ ደህንነት አገልግሎትና ከሌሎች የመንግሥት ኤጀንሲዎች የተወጣጣ ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡ ዝርዝር መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ከሚቀጥለው ጃንዋሪ እስከ ዲሴምበር 2018 ይተገበራል፡፡ እነዚህ የትኩረት ምሶሶዎች አራት ቀን በፈጀ የከጂዎች መልሶ ማቋቋምና ማቀላቀል ፕሮግራም ሥልጠና በተገኘ ግብአት ተቀጸዋል፡፡ አውደ ጥናቱ ከዴንማርክ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በዲአርኬና በአሚሶም አዘጋጅነት በኖቬምበር በኬንያ መዲና በናይሮቢ የተካሄደ ነው፡፡ ሰኞ በተከፈተው አውደ ጥናት ከዲአርፒ የመጡ 11 ሠራተኞችና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ማለትም ከአለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ከኖርዌጂያን የአለማቀፍ ጉዳዮች ተቋም፣ ከተመድና ከብሪቲሽ ኤምባሲ የተወጣጡ

በሶማሊያ ከታጣቂ ኃይሎች ወጥተው ትጥቅ የሚፈቱትን የማቋቋም ስራ የሚያከናውነው ድርጅት ዳይሬክተር አብዲረሻድ ኢብራሂም ሞሐመድ፣ ዶ/ር ሙማ መርቲኖን፣ ዶ/ር ኦፒዮ ኦዶዳ እና ሚ/ር ፋድሂል ካራር በጋራ ሆነው ከኖርዌይ አለም አቀፍ ግኑኝነት ኢንስቲቲዩት ለመጡት ኢንግቪድ ማኜስ ጎእስቪክ በኬንያ ናይሮቢ በተደረገው የሶማሊያ የመልሶ ማቋቋም እንዲሁም የጽንፈኝነት መከላከል ዎርክሾፕ ማጠቃለያ ላይ የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

ተሳታፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የዲአርፒ ዳይሬክተር ካብዲራሺድ ኢብራሂም መሐመድ በመዝጊያው ሥነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር “አውደ ጥናቱ ለቡድኔ ጠቃሚ ነበር” ብለዋል፡ ፡ በማያያዝም “ካገኘነው ትምህርት በተሻለ ደረጃ ተጠቃሚ መሆናችንን ለማረጋገጥ አሚሶም ብዙ ጊዜ ወስዷል” ብለዋል፡፡ ድርጅታቸው ሰፊ የአቅም ግንባታ ፍላጎት እንደነበረው ገልጸዋል፡፡ “አዘጋጆቹ ይህን የመሰለ ግሩም አውደ ጥናት ለማዘጋጀት ብዙ ጊዜ ወስደዋል፡፡ በሶማሌ መንግሥት ሥም አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡ ሥልጠናው በዲአርፒ በእቅድ ከተያዙት ተከታታይ የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች አንዱ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ “ወደፊት ተከታታይ ሥልጠና እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል፡፡ በመዝጊያው ሥነ ሥርአት ሚ/ር ኢብራሂም መሐመድ ባደረጉት ንግግር ፕሮግራሙ ከተጀመረበት ከ2011 ወዲህ እስካሁን 2000 ከጂዎች በተሳካ ሁኔታ

በአሚሶም የሰላም ማረጋጋት፣ መልሶ ማቋቋም እና የጸረ-ጽንፈኝነት ተልእኮ ኃላፊ ዶ/ር ኦፒዮ ኦዶዳ በኬንያ ናይሮቢ በተደረገው የሶማሊያ የመልሶ ማቋቋም እንዲሁም የጽንፈኝነት መከላከል ዎርክሾፕ በቀን 21/3/2010 ዓ.ም ማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ ለታዳሚዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ 30

አሚሶም መጽሔት

ከህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙ በመስክ ሥራዎች፣በከጂዎች ቅበላ፣ በማጣራት ሥራ፣ በመልሶ ማቋቋምና ከህብረተሰቡ በማቀላቀል ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር፡፡ “ከጂዎች በሚገባ ከህብረተሰቡ ካልተቀላቀሉ ሊፈጠር የሚችለውን ስጋት በቀላሉ መረዳት አያዳግትም” ብለዋል ኢብራሂም የአልሸባብን የቀድሞ ተዋጊዎችና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖችን በመጠቆም፡፡ የአሚሶም የሲቪል ጉዳዮች ከፍተኛ ኦፊሠር በተጨማሪም የተልዕኮው የመረጋጋትና መልሶ ማቋቋም ኃላፊ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ኦዶዳ ኦፒያ “በአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች (በራሳቸው) ስምምነት በተደረገበት የጊዜ ሰሌዳ የሚፈጸሙ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ሥራዎች ለይተው ማስቀመጣቸውን” ገልጸዋል፡፡ በማያያዝም አሚሶም የራሱን ተግባራት መደገፍ ጨምሮ የፕሮግራሙን አላማዎች ስኬት ለማረጋገጥ ከዲአርፒ ጋር በቅርበት ይሠራል ብለዋል፡፡ “የራሳችንን አቅጣጫዎች ለይተን ማስቀመጥ የቻልንበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን ደስተኘ ነኝ፡፡ በውይይቱ ሂደት የሚጠብቀንን ቀሪ ሥራዎች (መከናወን ያለባቸውን) ብዛት መረዳት ችለናል”፡፡ በስኬት የተጠናቀቀው ሥልጠና የፖለቲካ ውህደትን፣ የጽንፈኝነት ሂደትና አቀራረቦች፣ የፋይናንስና የኃብት ስምሪት፣ ትትቅ የማስፈታት ሂደት፣ የፕሮፋል አዘገጃጀትና የዲአርፒ ተጠቃሚዎች መረጣ መስፈርት የሚሉ ርዕሶችን የሸፈነ ነበር፡፡ በተመድ ውሣኔ ቁጥር 2372 (2017) መሠረት አሚሶም ከተመድና ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር በቅንጅት በመሥራት በጊዜያዊነት ከጂዎችን ይቀበላል፡፡ የፕሮግራሙ አላማ አልሸባብና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ሊፈጥሩ የሚችሉትን ስጋት ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን የሶማሊያን የጸጥታ ኃይሎች በማገዝ በሶማሊያ ህግና ሥርአት እንዲሰፍን መርዳት ነው፡፡


ፖሊሳዊ አገልግሎት በሶማሊያ የአሚሶም የፖሊስ ኮሚሽነር በሶማሊያ ግዳጃቸውን አጠናቀቁ

ቀድሞው የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) የፖሊስ ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል አናንድ ፒሌ የተሰማሩበትን ግዳጅ ካጠናቀቁ በኋላ ኖቬምበር 29 ቀን 2017 ሚሽኑን ተሰናብተዋል፡፡ ብርጋዲየር ጄኔራል ፒሌይ ከአሕ ሚሽን የተቀላቀሉት በ2014 ነበር፤ ከዚያ ወዲህ በሱማሌ የፖሊስ ዘርፍ፣ በፌዴራል መንግሥትና በክልል ደረጃ በተደረጉት ቁልፍ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ባበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና አግኝዋል፡፡ በእርሳቸው አመራር የአሚሶም ፖሊስ ለሶማሌ የፖሊስ ኦፊሰሮችን ፖሊሶች ማጣሪያ፣ ምልመላ፣ ሥልጠናና ልምምድ ጨምሮ የፖሊስ ኃይል ጉልህ የአቅም ግንባታ ዕቅድ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ከ3,500 በላይ ለሚሆኑ የሱማሌ የፖሊስ መኮንኖች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና እንዲያገኙ አድርገዋል፤

በሱማሌ ፖሊስ ሠራዊት ውስጥ የባዮ ሜትሪክ የመረጃ ቋት ሥራ ላይ ማዋል ጨምሮ የአሠራር ሥርአት እንዲዘረጋ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም በሥራ ጊዜያቸው የአሚሶም ፖሊስ አገልግሎቱን አዲስ ነጻ ወደወጡ አካባቢዎች አስፋፍቷል፤ ኦፕሬሽኑን ወደ ስቴት ዋና ከተሞች በደቡብ ምዕራብ ስቴት ባይዶዋ፣ በሂር ሸበሌ ስቴት ጆዋር፣ዲብሌና ኪስማዮ በታችኛው ሸበሌ ክልልና በበለተወይን እንዲሁም በሂራን ክልል አስፋፍቷል፡፡ የአሚሶም የፖሊስ ሠራዊት ዋና ኤታማዦር ሹም ሚ/ር አሌክስ ዱንዲን በተሰናባቹ ፖሊስ ኮሚሽነር የሽኝት ሥነ ሥርአት ላይ ባደረጉት ንግግር “ያለምንም ጥርጥር እርሳቸው (ፒሌይ) አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል፣ ውጤታማ ስትራቴጂያዊ አመራር ሰጥተዋል፣ ይህን ሁሉም ማየት ይችላል” ብለዋል፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሚ/ስ ክሪስቲን

የቀድሞው የአሚሶም የፖሊስ ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄነራል አናንድ ፒሌይ (መሐል ላ፣ ያለ መለዮ) በስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆኑ ለእርሳቸው የክብር ሽኝት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ኬክ ቆርሰዋል፡፡

አላኦ በበሉላቸው ባደረጉት ንግግር “አዲሱን የፖሊሳዊ አሠራር ሞዴል ለመተግበር እርስዎ የመጀመሪያው ነበሩ ምርጫዎች በሰላማዊ መንገድ በስኬት እንዲጠናቀቁ ሲያደርጉ አይተናል፤ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወደፊት ለመግፋት ባደረጉት ስኬታማ ጥረት ነጻ ወደወጡ አካባቢዎች መንቀሳቀስ ችለናል” ብለዋል፡፡ የአሚሶም የሚሽን ድጋፍ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ፊድዛ

ዲብሉ (ጠረተኛ) ፒሌይ በደቡብ ማዕከላዊ ሶማሊያ በተለይም አዲስ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ህግና ሥርአት ለማስፈን የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በተከናወኑት የግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች ለሰጡት ውጤታማ አመራር ምስጋናቸውን በመግለጽ “በኤስአርሲሲና ባጠቃላይ በአሚሶም ስም ለወደፊቱ መልካም እድል እመኝልዎታለሁ” ብለዋል፡፡

አሚሶምና የ.ተ.መ.ድ በካልካስዮ ጥምር የፖሊስ ፓትሮል ሥልጠና ጀመሩ

ሚሶምና የተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ ድጋፍ ሚሽን (ኡንሶም) በተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደ አንድ አካል ከፑንትላንድና ጋልሙክ ስቶቶች የተወጣጡ የፖሊስ ኦፊሰሮችን በጋልካስዮ ለሚካሄድ ጥምር የፓትሮል ሥራ ዝግጁ ለማድረግ በጁላይ ወር ጥምር ሥልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡ ሥልጠናው የተካሄደው በፑንትላንድና በጋልሙዱግ

ስቴቶች ፕሬዚዳንቶች መካከል ጃንዋሪ 1 ቀን 2017 በተፈረመው በጋልካስዮ የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት ነው፡፡ በስምምነቱ መሠረት የፓትሮል ቡድኖች በሁለቱም ስቴቶች አስተዳደሮች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊነት ለማስፈጸም የሚረዳ ሥልጠና ያገኛሉ፡፡ የጋልካሲዮን የተኩስ አቁም ስምምነት አፈጻጸም የሚከታተሉ ከ100 የማያንሱ

የፖሊስ መኮንኖች በጋልጋሲዮ የማህበረሰብ ማዕከል በተጀመረው ጥምር ሥልጠና መክፈቻ ተሳትፈዋል፡ በጋልካሲዮ የተኩስ አቁም ስምምነት የሁለቱ የክልል መንግሥታት መሪዎችም ሠራዊታቸውን የማስወጣት፣ የተዘጉ መንገዶችን ለሰዎችና ለዕቃ ነጻ እንቅስቃሴ ክፍት የማድረግ ኃላፊነትም አለባቸው፡፡ የፑንትላንድ ስቴት ምክትል ፕሬዚዳንት

አብዲሃኪም ኦማር አሜ ባደረጉት ንግግር “በጥምር የሚካሄደው የፖሊስ ፓትሮል የሶማሊያን አንድነት በመጠበቅ ሂደት ጅማሮ ነው፡፡ ይህን አጋጣሚ ማጣት አንፈልግም” ብለዋል፡፡ በማያያዝም “ፑንትላንድ ከጋልካሲዮ የተኩስ አቁም ስምምነት አፈጻጸም ጀምሮ የመላው ሶማሊያን የአንድነት ሂደት የመምራት ኃላፊነት ወስዶ ነበር” ብለዋል፡፡

የአሚሶም ፖሊስ ለሱማሌ የፖሊስ ሠራዊት የጸረ-አመጽ ሥልጠና ሰጠ

ሚሶም ለሱማሌ ፖሊስ ኦፊሰሮች ሽብርተኝነትን የመዋጋት አቅማቸውን ለማሻሻል የሚረዳ የ10 ቀን የጸረ አመጽ ሥልጠና አካሄደ፡፡ የሥልጠናው ተሳታፊ ኦፊሰሮች በሥልጠናው ሂደት ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም ሴቶችንና ሕጻናትን ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ የክህሎት ማሻሻያ ሥልጠናም አግኝተዋል፡፡. ከጃፓን መንግሥት በተገኘ ድጋፍ በተባበሩት መንግሥታት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽ/ ቤት (ዩኤንኦፒኤስ) አማካኝነት

በተዘጋጀው ሥልጠና መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሱማሌ ፖሊስ ሠራዊት (ኤስፒኤፍ) ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል ሙክታር ሃሰን አፍራና የአሚሶም ፖሊስ አሰልጣኝና የፖሊስ ከፍተኛ ተቆጣጣሪ (ኤስኤስፒ) ክርስቶፈር ካሺታ ተገኝተዋል፡፡ ኤስኤስፒ ካሺታ ባደረጉት ንግግር የሁለቱ ኮርሶች አላማ የኤስፒኤፍን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና የህዝቡን ደህንነት ጥበቃ ለማሳደግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “የመሠረታዊ የጸረ አመጽ ሥልጠና ኮርሱ

የሶማሊያ ፖሊስ መኮንኖች በ16/12/2009 ዓ.ም በሞጋዲሹ በተዘጋጀው የጸረ-ሽብር እርምጃ እና የጥቃት መከላከል መሰረታዊ ስልጠና ላይ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ስልጠናው በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽ የሶማሊያ ተልእኮ የፖሊሳዊ ስራ መምሪያ ድጋፍ የተደረገለት ነው፡፡ አሚሶም መጽሔት

31


አላማ የተሳታፊዎችን አቅም ለመገንባትና በተሰማሩበት አካባቢና ባጠቃላይ በሶማሊያ ውስጥ የተሻለ ውጤት በሚያስገኝ ሁኔታ አመጽን ለመከላከል የሚስችላቸውን አስፈላጊ እውቀት፣ ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ እንዲያገኙ ማድረግ ነው” ብለዋል የአሚሶም ኦፊሰር፡፡

ኤስኤስፒ ካሺታ በሴቶችና በሕጻናት ላይ ያተኮረው የኮርሱ አላማ ተሳታፊዎች በከፍተኛ ደረጃ ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለሴቶችና ለሕጻናት በድህረ ግጭት ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ጥበቃ ማድረግ የሚችሉበትን አቅም ለማሻሻል ላይ ያነጣጠረ

መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “የዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት የሥልጠና ኮርሶችን የሚሸፍን ነው፡፡ አንዱ ቡድን በሕጻናት ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች በተያዙ ጉዳዮች ላይ ይሰለጥናል፤ ሌላው ቡድን ደግሞ አመጽን በመከላከል ላይ ያተኮረ ሥልጠና ያገኛል፤

ሠልጣኞች ከዚህ ሥልጠና ጠቃሚ እውቀት እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ በሶማሊያ የሚገኙ ሁሉም ሕጻናት አስተማማኝ ጥበቃ ማግኘት አለባቸው፤ ከዚህ አንጻር አመጽን መከላከል ወሳኝ ነው” ብለዋል የኤስፒኤፍ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዲየር ሙክታር ሁሴን አፍራ፡፡

አሚሶም ለደቡብ ምዕራብ ስቴት የፖሊስ ኦፊሰሮች የከባድ ወንጀል ምርመራ ሥልጠና ሰጠ

ሚሶም በተሰጠው ተልዕኮ እንደ አንድ አካል ለደቡብ ምዕራብ ስቴት ፖሊስ ሠራዊት የፖሊስ ኦፊሰሮች የተዘጋጀውን የከባድ ወንጀል ምርመራ ሥልጠና በኖቬምበር ወር በደቡብ ምዕራብ ስቴት የአስተዳደር መዲና በባይዶዋ ሰጥቷል፡፡ በቤይ ክልል ከሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ተመርጠው የመጡ ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በሶስት ሳምንት በፈጀው የሥልጠና ሂደት ለወንጀል ሥፍራዎች ትክክለኛ ጥበቃ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ጥልቀት ያለው ኮርስ ተከታትለዋል፡፡ ሥልጠናው የወንጀል ሥፍራ አያያዝና የወንጀል ምርመራ ዋና ዋና ርዕሶችን የሸፈነ ነበር፡፡ በኮርሱ መዝጊያ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ስቴት ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መምሪያ (ሲአይዲ) ኃላፊ ኮሎኔል አብዱላሂ ኢብራሂም አደን ባሰሙት ንግግር “በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ የተካሄደ እያንዳንዱ አሥር ቀን የፈጀ ጠቃሚ አውደ ጥናት ነበር፡ ፡ የመጀመሪያው ክፍል የወንጀል ሥፍራ አያያዝን የሸፈነ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ደግሞ የከባድ ወንጀል ምርመራን የሚሸፍን ነበር” ብለዋል፡፡ ከሥልጠናው ተሳታፊዎች አንዷ ሹክሪ መሐመድ ዋርዴር ከሥልጠናቀው እጅግ ጠቃሚ

እውቀት ማግኘቷን ትናገራለች፡፡ በማያያዝም “በዚህ ሥልጠና የወንጀል ሥፍራዎችን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ተምረናል፡፡ መጀመሪያ የወንጀል ሥፍራ በኮርደን መከለል አለበት፡፡ሁለተኛ ደህንነትህን ማረጋገጥ አለብህ፤ ሶስተኛ በሥፍራው የሚገኙ አደገኛ ሁኔታዎችን መለየት አለብህ፤ እነዚህም ፈንጂዎች፣ ወይም ጉዳት ደረሰባቸው ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ከዚያ በኋላ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ሰው ለመርዳት መሞከር ትችላለህ፡፡ በመጨረሻም ከወንጀሉ በስተጀርባ ባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ ታደርጋለህ” ብላለች፡፡ የሥልጠናው አላማ የወንጀል

በ19/3/2010 ዓ.ም በባይዶአ፣ ሶማሊያ ለሳውዝ ዌስት ግዛት ፖሊስ መኮንኖች በተዘጋጀው የከባድ ወንጀል ምርመራ ላይ ባተኮረው ስልጠና ላይ የሳውዝ ዌስት ግዛት ፖሊስ ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ስልጠናው በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽ የሶማሊያ ተልእኮ ድጋፍ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡

ሥፍራዎችን አያያዝና የወንጀል ምርመራ ገጽታዎችን ማሳየትም ሲሆን ሥልጠናው በአሚሶም የደቡብ ምዕራብ ስቴት የፖሊስ አስተባባሪ ትሬስፎርድ ካሳሌ አስተባባሪነት ነበር የተካሄደው፡፡ በሥልጠናው መዝጊያ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ምዕራብ መስተዳድር የጸጥታ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ሚ/ር አብዲራዛቅ አብዲ አደን ባደረጉት ንግግር ሠልጣኞች በኮርሱ ባገኙት ክህሎት የተሰማቸውን እርካታ ገልጸው ሥልጠናው በሲአይዲ መምሪያ የሚሠሩ ኦፊሰሮችን

ችሎታ ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አሚሶም ከተሰጠው ተልእኮ እንደ አንድ አካል የሱማሌን ፖሊስ ሠራዊት አባላት ምልመላ፣ ሥልጠናና ልምምድ በማከናወን፣ የአገሪቱን የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ማሳደግ እንዲሁም የፖሊስ አባላት በመላ አገሪቱ ህግና ሥርአት የማስከበር ኃላፊነታቸውን በብቃት መፈጸም የሚያስችላቸውን በቂ ክህሎት እንዲያገኙ በሚረዳ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ ያተኮረ ተግባር ያከናውናል፡፡

የአሚሶምና የሱማሌ ፖሊስ ሠራዊት ጥምር ልኡካን የፖሊስ ማሠልጠኛ ሥፍራዎችን ጎበኙ

አሚሶምና ከሱማሌ ፖሊስ ሠራዊት (ኤስፒኤፍ) የተወጣጡ ከፍተኛ የፖሊስ ኦፊሰሮች የሚገኙበት ጥምር የልኡካን ቡድን በሂራንና በመካከለኛው ሸበሌ ክልሎች በሚገኙ የፖሊስ ማሠልጠኛ ሥፍራዎች የሁለት ቀን የግምገማ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በተሰናባቹ የአሚሶም ፖሊስ ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጂኔራል አናንድ ፒሌይና በአኤስፒኤፍ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መሐመድ አብዲ በሽር የተመራው የልኡካን ቡድን በሂራንና በመካከለኛው ሸበሌ ክልሎች መዲናዎች በበለት ወይንና በጆሃር የሚገኙ የፖሊስ

የሶማሊያ ፖሊስ ኃይል ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ባሽር ሞሐመድ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ አማካይነት ለህርሸበሌ ክልል አስተዳደር የተበረከቱትን መሳሪያዎች ተረክበው የእቃዎቹን ሁኔታ የሚገልጸውን የግምገማ ሰነድ በጆውሃር፣ ሶማሊያ ተገኝተው ፈርመዋል፡፡ 32

አሚሶም መጽሔት

ማሠልጠኛ ተቋማትን ጎብኝቷል፡፡ የዩኬ የልማት ክንፍ ከሆነው አለማቀፍ ልማት ዲፓርትመንት (ዲኤፍአይዲ) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አሚሶም ከሂር ሸበሌ ስቴት ለተወጣጡ እስከ 1000 ለሚደርሱ የፖሊስ ኦፊሰሮች፣ በበለተ ወይን ለ600 እና በጆዋር ለ400 ሠልጣኞች ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የሶማሌን የፖሊስ ሠራዊት አቅምና ብቃት ለማሻሻል በሚደረግ ጥረት እንደ አንድ አካል ከጃፓን መንግሥት የተለገሰውን የቢሮ ዕቃዎች እርዳታ ፒሌይ ለጆሃር ፖሊስ ጣቢያ አስረክበዋል፡፡ የመካከለኛው ሸበሌ ገዥ ሚ/ር ማይሬ ማካራን እርዳታውን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር የአሚሶም ፖሊስና

የጃፓን መንግሥት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን በመግለጽ የተገኘው እርዳታ የህግ አስከባሪ ኦፊሰሮቹን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እንደሚረዳ ገልጸዋል፡ ፡ በማያያዝም “ለሂርሸበሌ ፖሊስ በተለይም ለመካከለኛው ሸበሌ ፖሊስ ለተደረገው የመገልገያ ቁሳቁስ እርዳታ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መገልገያ ቁሳቁሶቹ አስፈላጊ የመረጃ ቋት ሥርአት ለማደራጀት የሚደረገው ጥረት የሚረዳ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው” ብለዋል፡፡ “የመሣሪያ አቅማችን ውሱን ቢሆንም እስካሁን ላገኘነው ድጋፍ እናንተም ድርሻ አላችሁ፤ የአሁኑ እርዳታም የዚሁ አካል ነው” ብለዋል የሂርሸበሌ ስቴት ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መሐመድ አብዲ በሽር፡፡


ለሶማሌ ፖሊስ ሠራዊት የተደረገ ድጋፍ

ሚሶምና ተመድ አዲስ ዋና መ/ቤት ሕንጻ ለጁባላንድ ስቴት አስረክበዋል፡፡ የጁባላንድ ፖሊስ ኮሚሽነር አህመድናስር ጉሌድ ሃሰን በርክክብ ሥነ ሥርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ህንጻው የወንጀል መከላከል ጥረትን እንደሚያሻሽል ተናግረዋል፡፡ ሚ/ር ሃሰን አዲሱ በፖሊስ ጣቢያው የቢሮ ህንጻና የምረቃ ሥነ ሥርአትና በእርዳታ በተገኘው ተሽከርካሪ ርክክብ ላይ ባደረጉት ንግግር የተገኘው እርዳታ በሱማሌ መንግሥት፣ በለጋሽ ማህበረሰብ፣ በተመድና በአሚሶም መካከል ላለው መልካም የሥራ ግንኙነት መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ በማያያዝም “ከተመድና ከአሚሶም ጋር በቅርበት በመተባበር እንሰራለን፤ ኦፊሰሮቻችንን አሠልጥነውልናል፣ በዚህ ዋና መ/ቤት ለሚገኙ በርካታ ኦፊሰሮች ሥልጠና

ሰጥተዋል፤ አሁንም ተጨማሪ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ መልካም የሥራ ግንኙነት አለን” ብለዋል የጁባላንድ ፖሊስ ኮሚሽነር፡፡ ከአሚሶም በእርዳታ የተገኘው ተሽከርካሪ የጁባላንድ ስቴት ፖሊስ በእለት ተእለት እንቅስቃሴው ያሉበትን አንዳንድ የትራንስፖርት ችግሮች በተወሰነ ደረጃ ለማቃለል ይረዳል፡፡ የጁባላንድ ስቴት ሁለተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዲከድር ሃጂ መሐመድ ሉጃ ዲር ሶማሊያ ህልሟን እውን እንድታደርግ የአለማቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ “አገራችን ለሰላሳ አመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የነበረች አገር ናት፡፡ በመሆኑም ሶማሊያ በሁለት እግሯ ቆማ ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን የእናንተን እገዛ እንጠይቃለን” ብለዋል ሚ/ር አብዲከድር፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ምክትል

የጁባላንድ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዲከድር ሞሐሙድ ሉዳዴሬ በኦሚሶም ምክትል ፖሊስ ኮሚሰሽነር፣ በክርስቲን አለሎ በኩል ለጁባላንድ ፖሊስ ኮሚሽ በእርዳታ የተበረከተውን ተሽከርካሪ ቁልፍ በተረከቡ ጊዜ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ይህም ዳግም የታደሰው በኪስማዩ፣ ሶማሊያ የሚገኘው የጁባላንድ ፒሊስ ጣቢያ ርክክብ ሲፈጸም ነበር፡

ኮሚሽነር ክሪስቲን አላሎ በበኩላቸው ዩኤንኦፒዎች ይህን የቢሮ ህንጻ አሰርተው ለአገልግሎት በማብቃታቸው ምስጋናቸውን ገልጸው ህንጻው የፖሊስ አገልግሎትን በቅርበት ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

“ዛሬ እዚህ የተገኘነው ለአጋሮቻችን በተለይም ይህን ህንጻ ላሠሩት ኤንኦፒዎች ያለንን ወዳጅነት ለማሳየት ነው” ብለዋል ሚ/ስ አላሎ፡፡ የህንጻውን የግንባታና የእድሳት ሥራ ለማጠናቀቅ 12 ወራት ፈጅቷል፡፡

የአ.ሕ ፓሊስ ለባናዲር ፖሊስ የቢሮ መገልገያዎች እርዳታ አስረከበ

አሚሶም ፖሊስ ሴፕቴምበር 18 ለሶማሌ የፖሊስ ሠራዊት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እርዳታ አስከረበ፡፡ ከዴንማርክ መንግሥት የተለገሰውን የተለያየ የቢሮ ዕቃ እርዳታ የአሚሶም ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሚ/ስ ክሪስቲን አላኦ ሞቃዲሾ ለሚገኘው የባናዲር ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ጄኔራል አህመድ ሃሰን በይፋ አስረክበዋል፡፡ ሚ/ስ አላኦ የቢሮ ዕቃ እርዳታውን ባስረከቡበት ወቅት ባሰሙት ንግግር “እዚህ ሶማሊያ ውስጥ የተሰጠን ተልእኮ አለን፤ የእኛ ተልእኮ የሶማሌን የፖሊስ ሰራዊት አቅም መገንባት ነው፡፡ ይህም በሥልጠና፣ በልምምድ፣ በኦፕሬሽን ድጋፍ ይገለጻል፤ ሌት ተቀን የፓትሮል ተግባር የሚያከናውን የሰለጠነ የፖሊስ

ዩኒት (ኢፒዩ) ታገኛላችሁ፡ ፡ በተጨማሪም ስትራቴጂያዊ የማማከር ሥራም እናከናውናለን፤ ከሁሉም በላይ ግን ለእነርሱ የሎጀስቲክስና የመሣሪያ ድጋፍ መስጠት፣ እንዲሁም የፖሊስ ጣቢያዎችን የቢሮ የዕቃ ፍላጎት ማሟላት ይጠበቅብናል” ብለዋል፡፡ በእርዳታ የተገኘው ቁሳቁስ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ታጣፊ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች፣ ካቢኔቶች፣ ሶላር ባትሪዎች፣ ሶላር አምፖሎች የሚጨምር ሲሆን በሞቃዲሾ ለሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ተከፋፍሏል፡፡ ጄኔራል አህመድ ሃሰን መአሊን በእርዳታ የተገኘው ቁሳቁስ የፖሊስ ኦፊሰሮቹን ህግና ሥርአት የማስከበር ተግባር ከማሳለጥ አንጻር

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽር፣ ክርስቲን አለሎ በአሚሶም ለሶማሊያ ፖሊስ የተበረከቱትን የእርዳታ እቃዎች በሶማሊያ፣ ሞጋዲሹ ተገኝተው በ8/1/2ዐ1ዐ ዓ.ም አስረክበዋል፡፡

የሚያደርገው ረጅም ርቀት እንደሚያስኬድ ተናግረዋል፡፡ በማያያዝም “በአሚሶም ፖሊስ ወንድሞቻችን ለተደረገልን እርዳታ እናመሰግናለን፡፡ የተገኘውን

እርዳታ በባናዲር ለሚገኙት አራት ፖሊስ ጣቢያዎች እናከፋፍላለን፤ እርዳታው ኦፕሬሽናችንን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እንደሚረዳ አውቃለሁ” ብለዋል፡፡

አሚሶም ለደቡብ ምዕራብ ስቴት ፖሊስ ሠራዊት የቢሮ ዕቃዎች ለገሰ

አሚሶም ፖሊስ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዳ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እርዳታ በኦክቶበር ወር ለደቡብ ምዕራብ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ አበረከተ፡፡ በልገሳ የተገኘውን ቁሳቁስ ለደቡብ ምዕራብ ስቴት ፖሊስ አዛዥ ለጄኔራል ማሃት አብዲራህማን አደን ያስረከቡት በደቡብ ምዕራብ ስቴት የአሚሶም ፖሊስ ቡድን መሪ ጆን አምባዮ በርክክብ ሥነ ሥርአቱ ላይ ባሰሙት ንግግር

“[የደቡብ ምዕራብ ስቴት የፖሊስ ኦፊሰሮችን] የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም ለመገንባት የምናደርገው ድጋፍ ይቀጥላል” ብለዋል፡፡ የአሚሶም ፖሊስ ለሱማሌ የፖሊስ ሠራዊት ኤስፒኤፍ) የአገሪቱን የጸጥታ ፍላጎትና ለማሟላትና ተግባሩን በአለማቀፍ የፖሊሳዊ አሠራር ደንቦችና ደረጃዎች መሠረት ለማከናወን የሚረዳ የአቅም ግንባታና የኦፕሬሽን ድጋፍ የመስጠት ተልእኮ አለው፡፡

የሳውዝ ዌስት ግዛት ጊዜያዊ አስተዳደር የፖሊስ መኮንኖች በአሚሶም የተበረከቱትን የእርዳታ እቃዎች ተረክበዋል፡፡ አሚሶም መጽሔት

33


39 የግል የፖሊስ ኦፊሰሮች የሚገኙበት ቡድን በሶማሊያ ተሰማራ

ሶማሌ ፖሊሶች የሙያ ማሻሻያ ልምምድ የሚሰጥ አዲስ የግል የፖሊስ ኦፊሰሮች (አይፒኦ) ቡድን በሴፕቴምበር ወር በሶማሊያ ተሠማርቷል፡፡. ከኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ዛምቢያና ናይጄሪያ የመጡት አይፒኦዎች በሶማሊያ የአንድ አመት ቆይታ ያደርጋሉ፡፡ የቀድሞው የአሚሶም የፖሊስ ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል አናድ ፒሌይ ለአዲስ ገቢ ሠልጣኞች የፌዴራል መንግሥትና ከክልል መስተዳድሮች የሚከተሉት አዲስ የፖሊሳዊ አሠራር ሞዴል ተከትሎ የተቀረጸውን አዲስ የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ

አሚሶም ለሴራሊዮን ፖሊስ ኦፊሰርስ የክብር እውቅና ሰጠ

ሴራሊዮን ፖሊስ ኦፊሰርስ ለሶማሊያ አቻዎቻቸው ላበረከቱት ትልቅ የእውቀት ማጋራት ስራ በየግላቸው የእውቅና ሜዳል ተቀብለዋል፡ ፡ አስር የሚደርሱ የግዴታ አገልግሎታቸውን የጨረሱ የሴራሊዮን ፖሊስ ኦፊሰርስ የአውቅና ሜዳል አከባበር በሞቃዲሾ በኦገስት ተደረገላቸው፡ ፡ “የአሚሶም የፖሊስ አስተዳደር ክፍል የላቀ የአፈጻጸም አስተዋጶ ስለማድረጋቸው ደስተኛ ነን” ሲሉ የፖሊስ አዛዡ ሬክስ ዱንዱን በሺኚቱ ስነስርአት ወቅት ገልጸቀዋል፡፡

የሴራሊዮኑ ፖሊስ ተጠባባቂ አዛዥ ሳህር አር ማርካ ተጠባባቂ የፖሊስ ኦፊሰሮቹን ከሴራሊዮን ለቀው በሚሄዱበት የሜዳል ስነስርአት ላይ ንግግር ሲያደረጉ፡፡

በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ “ለዚህ አገር ቀደም ሲል የተወሰነ የፌዴራል ፖሊስ አገልግሎት የአሠራር ሞዴል አለ፤ ስለዚህ በዴዴራልም በፌዴራል አባል መንግሥታትም ደረጃ የፖሊስ ተቋሙን መገንባት አለብን” በማለት ፒሌይ ለአይፒኦዎች ተናግረዋል፡፡ “ወደፊት ብዙ ርቀት ይጠብቀና፤ በፖሊስ የአቅም ግንባታ ሂደት ስኬታማ ውጤት ለማምጣት የተወሰነ ችሎታ ያላቸው ሰዎች እዚህ መጥተው በሥልጠናው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀናል”፡፡

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሶማሊያ ተልእኮ (አሚሶም) ስር የሰላም ማስከበር ግዳጅ የሚወጡት በግል እራሳቸውን ችለው ግዳጅ የሚፈጽሙ ፖሊሶች ለመጀመሪያ ጊዜ በሞጋዲሹ የቅድመ-ስራ ስምሪት ስልጠና ወስደዋል፡፡

የናይጄሪያ ፖሊስ ኦፊሰርስ የሶማሊያን ምርጫ ሂደት አስተማማኝ በማድረጋቸው ተመሰገኑ፤

ጠባባቂው የናይጄሪያ ፖሊስ ኦፊሰርስ የሶማሊያን ምርጫ ሂደትን አስተማማኝ በማድረግ ሂደት ለተጫወቱት ሚና ከፍትኛ አድናቆትን ተቀብለዋል፡ ፡ የግዳጅ አገልግሎታቸውን ለፈጸሙ ኦፊሰርስ የክብር ሜዳልና ሰርቲፈኬት በሞቃዲሾ በሴፕቴምበር በተደረገው የበአሉ ስነ ስርአት ላይ ተበርክቶላቸዋል፡ ፡ ”አገልግሎታቹህ እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዚያህ ሰዐት፤ በተለይም በሶማሊ በተደረገው የተወካዮች ምክር ቤት እነ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት ያደረጋችሁት ድጋፍ ከፍ ያለ ነበር” ሲሉ ፖሊስ ኮሚሺነሩ ብርጋዴር ጀነራለ አናንድ ቢሌይ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሶማሊያ በተደረገው የምርጫ ሂደት ውጤታማነት የነበራቸውን ሀላፊነት በማድነቅ፤ ኦፊሰሮቹ በነበረው አንቅስቃሴ ውስጥ ዋና ተዋናኝ እና እቅድ አውጪ በመሆን ሶማሊያ ውጤታማ ምርጫ እንድታኪያህድ አድርገዋል ሲሉ መስክረዋለ፡ ፡ ነገር ግን አፊሰሮቹ አስተዋጾአቸው እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዚህ ጊዜ በተለይም በዚህ የሽግግር ሰዐት እና በቅርቡ የዪኤን ሴኪውሪቲ

የናይጄሪያ ተጠባባቂ ፖሊሰ ኢፊሰርስ ከናየጄሪያ ሲለቁ በተደረገው የሜዳል ክብረ በአል ላይ ተሳትፎ ሲያደርጉ

ካውንስል ሪዞሉሺን 2372 የአሚሶም ፖሊሶችን ቁጥር ከፍ ስለማድረግ ባስተላለፈው ውሳኔ ዙራቸውን መጨረሳቸው ያሳዘናቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡ ፡ ”በዚህ የሽግግር ጊዜ ስል፤የአሚሶም መለዮ ለባሾች አባላት ቁጥር ቅነሳ ማለቴ ሲሆነ በዚሁም ሂደት ለሀገራዊ ጸጥታ አካላት ሀላፊነታቸውን ማስረከብ ይጠበቅባችሀል፤አዳዲስ አባላትን የምናሰገባበት ሰዐት በመሆኑ እና ብዙ ልምድ ያላቸው አባላት አየሄዱ በመሆኑ ጊዜው ፈታኝ ቢሆንም መወጣት ይኖርብናል” ሲሉ ፒሌይ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዐት የጋራ የፖሊስ አዋጪ ሀገራት ውስጥ ናይጄሪያ አና ኡጋናዳ ብቻ የፖሊስ ዩኒት

እና ገለልተኛ የፖሊሰ ኦፊሰርስ በማዋቀር በአሚሶም ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ”ከአፍሪካ ህብረት በኩል ሆኜ ደግሞ በአሚሶም ውስጥ በመሆን እራሳችሁን ለግልጋሎት ስላበረከታችሁ እና በዚሁም ሰዐት ደግሞ ስለሀገራቺሁ ናይጄሪያ ለሶማሊያ ሰላም ለምታበረክቱት ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል ፒሌይ፡፡ የአይፒዮሰ ተግባራትም የሶማሌን የጸጥታ አካላትን የምክር፣የስልጠና፣እንዱሁም የኩትኮታ ስራን በመስጠት ላይ ቢያተኩርም አብረው በተለያዩ የፌደራል ስቴቶች አና በሞቃዲሾ የፖሊሰ ስቴሺኖች በመዘዋወር ሰርተዋል፡፡

አዲሶቹ የኡጋናዳ ፖሊስ ኦፊሰርስ ማብራሪያ ተሰጣቸው፤

ዲሶቹ የኡጋንዳ ፖሊስ ኦፊሰርስ ቡድን ወደ ስራ እንደተሰማሩ የመጀመሪያ መግቢያ መግለጫ ተደረገላቸው የተሰጣቸውም የስራ ክፍል ከሶማሊ አቻቸው ጋር የጋራ ኦፕሬሺን ላይ በወጣላቸው የስራ መርሀግብር መሰረት፤ ስልጠና በመስጠት የሶማሊ ኦፊሰርስ የብቃት አቅማቸውን ማጎልበት ነው፡፡ “አንድ መናገር እምፈልገው ነገር ቢኖር ሀላፊነታቺንን እየተወጣን ሳለን ዲሲፒሊን ከአፋቺን የማይለይ

34

አሚሶም መጽሔት

ጠባቂ ቃል መሆን አለበት፤የግል ዲሲፒሊናቺንን፣በብዙ የስራ ሂደት አንዲሁም በተለያዩ ስልጠናዎች በውስጣቺን የዳበርነውንና ይዘነው የመጣነውን ዲሲፒሊን አንርሳ“ ሲሉ የአሚሶም ፖሊስ አለቃ ሬክስ ዱንዱን ለአዲሶቹ ፖሊስ ኦፊሰርስ አስጠንቅቀዋል፡፡. የአሚሶም ፖሊስ ክፍል አካል የሶማሊያ ፖሊስ ሀይል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ኦፕሬሺናል ሰፖርት የመስጠት ሀላፊነት አለበት፡

፡ አዲስ የተቀቀመው የፖሊስ ዩኒተ ከሶማሊያ ፖሊስ ሀይል ጋር በጋራ የማህበረስብ ፖሊሲንግ ናይጄሪያንና ኡጋንዳን የፖሊሰ ዩኒት ኦፊሰርስ በቅርቡ እንቅስቃሴ፣ በመመስረት በአሚሶም ስር እንዲያገለግሉ አሰማሩ፡፡ አማጺያንን መዋጋት፣የህዝብ ለአሚሶም ፖሊስ ከሚያዋጡት ሰላምና ጸትታ ተግዳሮት፣የፈንጂ ስድስተ ሀገራት መካከል አንዳ ማስወገድ እናም የኬላና የፍተሻ ናት ከነሱም መካከል ናይጀሪያ፣ አገልግሎቶች ከሚያደርጋቸው ኬንያ፣ሴራሊዮን፣ዛምቢያና ጋና ተግባሮች መካከል ናቸው፡፡ኡጋንዳ ናቸው፡፡


ሞቃዲሾ ሶስተኛውን አመታዊ የመጻሕፍት ሥዕላዊ አውደ ርዕይ አስተናገደች

በ3/1/2010 ዓ.ም በሶማሊያ ሞጋዲሹ በተሰናዳው ዓመታዊው የመጽሐፍት አውደ ርእይ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ እንግዶች የቀረቡትን ልዩ ልዩ መጽሐፍት ጉብኝተዋል፡፡ (ከታች) እንግዶች በዚህ በ3/1/2ዐ1ዐ ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ በተሰናዳው ዓመታዊ የመጽሐፍት አውደ ርእይ ላይ ፕሮግራሙን ተከታትለዋል፡፡

ማሊያ ምሑራን፣ሊቃውንት፣ ደራሲዎች፣ ጸኃፌ ተውኔቶች፣ ገጣሚያን፣ ሙዚቀኞችና የመጻህፍት ወዳጅ አንባቢዎች በተገኙበት ትልቁን የሥነ ጽሁፍ ሥራዎች አውደ ርዕይ በሴፕቴምበር ወር አስተናግዳለች፡፡ ሶስት ቀን በቆየው አውደ ርዕይ 2000 አዳዲስ መጻሕፍት፣ 850 የመጻህፍት አርእስቶች ለእይታ ቀርበዋል፡፡ አዘጋጆቹ እንደገለጹት አውደ ርዕዩ በተካሄደበት ሥፍራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ቢያንስ 4,900 የመጻህፍት ወዳጅ አንባቢያን ከየቦታው ተሰባስበው ታድመዋል፡፡ የአመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕዩ አዘጋጅ መሐመድ ሼክ አሊ አህመድ ‘ዲኒ’ “ይህ ሥፍራ ትምህርትና እውቀት የተጣመሩበት ቦታ ነው” ብለዋል፡፡ ከ2015 ጀምሮ በየጊዜው ሲካሄድ የቆየው የሞቃዲሾ አመታዊ የመጻፍት አውደ ርዕይ አላማው መጻፍትን ለማክበርና በየጊዜው ብዙ ሱማሌዎች የአገራቸውን የበለጸገ የሥነ ጽሁፍ ባህል እንዲቀበሉ ለማነቃቃት ነው፡፡ አውደ ርዕዩን ማስተናገድ የተቻለው በአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪዎች አማካኝነት በአገሪቱ በሰፈነው ሰላምና መረጋጋት ምክንያት ነው፡፡ አሚሶም መጽሔት

35


መስመር ላይ እኛን ያግኙ:


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.