DC Department of Motor Vehicles Driver Manual: Amharic

Page 1

የሞተር ተሽከርካሪዎች መምርያ

ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ

የአሽከርካሪ መመሪያ


ማውጫዎች

መግቢያ ��������������������������������������������������������������������������������������������� 3 መንጃ ፈቃድ የፈተና ሂደት ������������������������������������������������������������������������11 የመንጃ ፈቃድና የፈቃድ አይነቶች ����������������������������������������������������������������14 ሌላ አገልግሎቶች ����������������������������������������������������������������������������������16 መታወቅ ያለባቸው ጠቃሚ ነገሮች ���������������������������������������������������������������18 የአሽከርካሪ መረጃ ���������������������������������������������������������������������������������19 የማሽከርከር ደንቦች �������������������������������������������������������������������������������39 የፓርኪንግ ደንቦች ���������������������������������������������������������������������������������41 የትራፊክ ደንቦች ����������������������������������������������������������������������������������44 የመብራት ምልክቶች፣ ምልክቶች እና የጽሁፍ ምልክቶች ���������������������������������������48 ምልከቶችን በቅርጽ እና በቀለም መለየት ��������������������������������������������������������50 የመቆጣጠሪያ ምልክቶች �������������������������������������������������������������������������51 የአስፋልት መንገድ መስመር ቀለማት �����������������������������������������������������������55


መግቢያ ተልዕኮ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሞተር ተሽከርካሪዎች ክፍል DC DMV) ተልዕኮ ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የሞተር ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴና ደህንነትና የህዝብ ደህንነትን ከፍ ማድረግ ነው።

ራዕይ የDC DMV ራዕይ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ቀዳሚ መሆን ነው።

የDC DMV አጠቃላይ እይታ በየቀኑ፣ DC DMV ከሁሉም የመንግስት የዲስትሪክቱ ኤጀንሲ በላይ ማለት በሚቻል መልኩ በአማካይ 3,200 የዲስትሪክቱ ነዋሪዎችና ነዋሪዎች ያልሆኑ በቀጥታ ያገለግላል። DC DMV ከ623,000 በላይ ፈቃድ ያላቸው አሽከርካርዎችና ባለ መታወቅያ ካርዶችና ከ310,000 በላይ የተመዘገቡ ተሸከርካርዎች በአራት የአገልግሎት ማእከላት አገልግሎት ይሰጣል። በአመት 2.7 ሚልዮን በላይ ትኬቶች ክፍያዎችን በመሰብሰብ ወይም ዜጎች ለትኬቶች የሚወዳደሩበትን መንገድ በማቅረብ አገልግሎት እንሰጣለን። በተጨማሪም በየአመቱ ከ178,000 በላይ የተሸከርካሪ ምርመራዎችን እናደርጋለን። ተልዕኳችን ለማሳካት ሦሥት የክንውን መርሃ-ግብር ዘርፎች አሉን፦ • የትኬት አገልግለቶች • የአሽከርካሪ አገልግለቶች • የተሸከርካሪ አገልግለቶች

3


የዜሮ ራዕይ (ቪዥን ዜሮ) ዲስትሪክቱ በከተማው መንገዶች የሚጓዙትን ሕይወት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው። የዜሮ ራዕይ የከተማዋን የትራፊክ የሞት አደጋዎች ወደ ዜሮ የመቀነስ አላማን ይወክላል። የትራፊክ ኣደጋ ሞትና ከባድ ጉዳት መከላከል ይቻላል።

ክፍል ሲሆን አምስት ወሳኝ የአጽንኦት ቦታዎችን( CEA’s) ለይቷል። እነዚህ አምስት ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው። • ከፍተኛ ስጋት ያላቸው አሽከርካሪዎች • የእግረኛ እና የብስክሌት ደህንነት

“የዜሮ ራዕይ” ምንድን ነው?

• የምህንድስና/መገልገያዎች መሰረተ-ልማት

የዜሮ ራዕይ በመንገድ ትራፊክ ከሞትና ከከባድ አደጋ የጸዳ የአውራ ጎዳና ስርአት ለማሳካት ያለመ ሁለገብ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ፕሮጀክት ነው። በ1997 በስዊድን ተጀመረ በመቀጠል በኖርወይ፣ ኔዘርላነድስና በዩናይትድ ኪንግደም ድግሞ በኢንተርናሽናል ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ቦስተን፣ ቺካጎ፣ ሎስ ኤንጅለስ፣ ኒው ዮርክ ሲቲ፣ ፖርትላንድ፣ ሳን ፍራንሲስኮ፣ ሲያትልና Washington DC ያካተተ የ U.S. ከተሞች በልማት መስመር እቅድ ውስጥ ይገኛሉ። የራዕዩ አንኳር መርሆዎች በመንገድ ትራፊክ ስርአቱ ውስጥ ማንም መገደል ወይም በከባድ መጎዳት የለበትም የሚል ሲሆን የትግበራ እቅዱ በተለምዶ በአራት ቁልፍ ዘርፎች ዙርያ የተዋቀረ ነው፦

• ልዩ ተሸከርካሪዎች • የልዩ ዒላማ ቦታዎች

የትራፊክ ሞት መቀነስን የሚሻ ከከፍተኛ የአፈጻጸም ግቦችና ሁሉን አቀፍ የድርጊት መርሃ-ግብር በማጣመር ወረዳው ዜሮ ሞትና ጎዳናዎችን አስተማማኝና ለሁሉም መንገድ ተጠቃሚዎች ምቹ ለማድረግ ጥረቶችን ለመጨመር ቁርጠኛ ነው።

የደህንነቱ የጠበቀ የማሽከርከር ተግዳሮቶች አስተማማኝ አሽከርካሪ ለመሆን ብዙ ችሎታ፣ ልምድ፣ ኃላፊነትና አስተዋይነት ይጠይቃል። ሰዎች ከሚሰርዋቸው የተወሳሰቡ ነገሮች ብቻ ሳይሆን ሰዎች ሁሉ ግዜ በሚያደርጉዋችው ጥቂት ነገሮች ሊጎዱን ወይም ሊገድሉን ይችላሉ።

• የደህንነት መረጃ • ትምህርትና ተደራሽነት

ደህንነቱ የተጠበቀ ማሽከርከር አደጋን ቀድሞ የማየት ችሎታ፣ በተለይ ወደ መስቀለኛና እግረኛ መንገዶች በምንጠጋበት ጊዜ የሌሎች ስህተቶችን ጥንቃቄ ማድረግን ይጠይቃል። በተጨማሪም አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለሌሎች ደህንነት ለመጠበቅ በአጠቃላይ ጤነኛ የመሆን ኃላፊነት፣ ስሜታቸው ለማሽከርከር ብቁ መሆንና የሚያሽከረክሩት ተሸከርካሪ በጥሩ ሁኔታ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ትኩረት ማጣትና በተዳከመ ስሜት ማሽከርከር ለአሽከርካሪዉም ሆን ለህዝቡ ደህንነት አደጋ ውስጥ ከሚጥሉ ሁለት ዋና የአደጋ መንስኤዎች ናቸው።

• ማስፈጸም • ምህንድስናና መሰረተ-ልማት

“የዜሮ ራዕይ” ለምን? ትራፊክ ገዳይ ስጋት ነው በዚህም መሰረት Washington DC የትራፊክ ደህንነት በማሻሻል ጉዳቶችና ሞትን የሚቀንስ ሁሉን አቀፍ መርሃ-ግብር ንድፍ በማዘጋጀት ከባድና የሞት አደጋ ቁጥርን ለመቀነስ በመሻት ትገኛለች። ማነኛውም የሕይወት መጥፋት ተቀባይነት የለውም እናበዲስትሪክቱ ከተማ ጎዳናዎች ላይ የአንድ ሰው ሞት ተቀባይነት የለውም!

ትኩረትን ሳይሰበስቡ ማሽከርከር

በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ ልማቶች

ትኩረትን ሳይሰበስቡ ማሽከርከር አደገኛ ወረርሽኝ ሲሆን ከሚሰጡት ብዙ ትርጓሜዎች መካከል ማንኛውም ሰው ዋናው የማሽከርከር ትኩረቱን ወደ ሌላ የሚያዞር ማንኛውም እንቅስቃሴ በማለት ሊገለፅ ይችላል። በየአመቱ ወደ 400,000 የሚገመቱ ሰዎች ትኩረትን ሳይሰበስቡ በሚያሽከረከሩ አሽከርካሪዎች ምክንያት በግጭት ይጎዳሉ። ምንም እንኳን ከስር የተዘረዘሩት ነገሮች ትኩረት የሚበትኑ ናቸው ብለን ላናስብ ብንችልም ሁሉም ትኩረት የሚበትኑ ነገሮች የአሽከርካሪው፣ ተጓዥ፣ ብስክሌትና ተመልካች ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ መሆናቸውን ማስታወስ ጠቃሚ ነው።

የዲስትሪክቱ የትራንስፖርት ክፍል (DDOT) የዲስትሪክቱ የአውራ ጎዳና ደህንነት ፕሮግራም ከህግ አስፈጻሚዎች፣ የፍትህ ሰራተኞች፣ የግል ዘርፍ ድርጅቶችና የማሕበረሰብ ተሟጋቾች ጋር በአጋርነት እንድያስተባብርና እንድያስተዳድር ተልእኮ ተሰጥቶታል። DDOT ከትራፊክ ጋር የተያያዙ ሞትና ከባድ ጉዳቶችን የጸዳ አስተማማኝና ውጤታማ የትራንስፖርት ስርአት ለመፍጠር ከቁልፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ይሰራል። የትራፊክ ደህንነት ለማሻሻልና ሞት ለመቀነስ ሊሳካ የሚችል ቁልፍና ጠቃሚ ሥራ የ DC አውራ ጎዳና ትራንስፖርት ደህንነት እቅድ 4


ምክንያት በተዳከመ ስሜት ሆኖ ሞተር ተሸከርካሪን ማሽከርከር ነው። የእንቅልፍ እጦት ከዋናዎቹ የሞተር ተሸከርካሪ ግጭት መንስኤ ነው። ብዙ ሰው የእንቅልፍ እጦት ልክ እንደ አልኮል አልፎ አልፎም ከአልኮል በላይ ማሽከርከር ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር አይገነዘቡም። “የመስኮት መስተዋት ዝቅ ማድረግና ሙዚቃ መክፈት“ ንቃት ላይ ጥቂት ወይም ምንም ጥቅም የሌለው ሲሆን ቡና ወይም አነቃቂ ንቅረ-ነገሮች ለአጭር ግዜ ብቻ ጉልበት እንደሚሰጡ ጥናቶች አረጋግጠዋል። በድብርት ውስጥ ሆኖ ማሽከርከርን ለመከላከል በቂ እንቅልፍ ማግኘት የተመረጠ መንገድ ነው።

የተለመዱ ትኩረት የሚበትኑ ነገሮች የሚከተሉት ያካትታሉ፦ • መመገብ እና መጠጣት • ተንቀሳቃሽ ወይም ሞባይል ስልክ መጠቀም • አጭር የፅሑፍ መልእክት መፃፍ • መቆነጃጀት • ማንበብ • የአሰሳ(መንገድ ጠቋሚ) ስርአቱን በመጠቀም • ሬድዮ፣ CD ማጫወቻ፣ MP3 ማጫወቻ ማስተካከል/

መነካካት

አሽከርካሪዎች በቂ እንቅልፍ ለማግኘት፣ በእንቅልፍ ስሜት ላለማሽከርከርና የእንቅልፍ ስሜት ሲሰማቸው ከመንገድ ወጣ በማለት አስተማማኝ ቦታ በመቆም በየቀኑ ቅድሚያ መስጠት ይኖርባቸዋል።

• ተሳፋሪዎችን ማነጋገር

በተዳከመ ስሜት ሆኖ ማሽከርከር አልኮል መጠጥ፣ ህጋዊ ወይም ህገወጥ መድሃኒት/ዕፅ ወስዶና በእንቅልፍ ስሜት ሆኖ ሞተር ተሸከርካሪን ማሽከርከር ሁሉም በተዳከመ ስሜት ሆኖ የማሽከርከር አካል ናቸው። በተዳከመ ስሜት ሆኖ ማሽከርከር እጅግ በጣም አደገኛ ብቻ ሳይሆን ለከባድ ቅጣት እና እስር ጭምር ሊዳርግ ይችላል። በተጨማርም ማንኛውም በተዳከመ ስሜት ሆኖ የማሽከርከር ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ወደ ተሽከርካር የማስነሳት መቅለፍያ መሳርያ ፕሮግራም (ኢግኒሽን ኢንተረሎክ ዲቫይስ( IID) መርሃ-ግብር) እንዲመዘገብና እንዲጨርስ ይጠየቃል። ይህ ፕሮግራም አሽከርካሪዎች በሁሉም የተመዘገቡ ተሸከርካሪዎች IID እንዲጭኑ፣ የተገደበ መንጃ ፈቃድ እንድያገኙና IID ብቻ ያላቸው ተሸከርካሪዎች እንድያሽከረክሩ ይጠይቃል። (ስለ IID ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የሚከተለውን ይጎብኙ፡- https:// dmv.dc.gov/service/mandatory-ignition-interlockdevice-iid-program) ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአልኮል ተጽእኖ ውስጥ ሆኖ ማሽከርከር አንድ-ሶስተኛ የትራፊክተዛማጅ ሞት ድርሻ ሲኖረው ዕፅ ደግሞ 18% የትራፊክተዛማጅ ሞት ድርሻንይወስዳል። ጥቂት ቁልፍ ነጥቦች

መንገድን በጋራ መጠቀም ትንሽ መኪና፣ ትልቅ መኪና፣ መካከለኛ መኪና፣ የንግድ መኪና ሲያሽከረክሩ፣ ሞተርሳይክል ሲነዱ፣ ብስክሌት ሲነዱ ሆነ በእግር ሲጓዙ መንገዱን ከሌሎች ተሸከርካሪዎችም አሽከርካሪዎችም ጋር በጋራ ይጠቀማሉ። መንገድ ብዙ ተጠቃሚ ያለው ሲሆን ለደህንነትና የትራፊክ ፍሰትን ላለማደናቀፍ እያንዳንዱ ተጠቃሚ የተወሰኑ የመንገድ ደንቦች፣ ህጎችና መብቶችን ማክበር አለበት።

አሽከርካሪዎች በተለምዶ፣ ስለ አሽከርካሪዎች ስናስብ ትንሽ መኪና የሚያሽከረክሩ ግለሰቦችን ብቻ ነው የምናስበው። ነገር ግን ትርጓሜው ብስክሌት፣ አውተቡሶች፣ ሞተርሳይክል፣ ቀላል የጭነት መኪና፣ የንግድ መኪናና በመሰረቱ ማነኛውም ሀዲድ ላይ የማይጓዝ ተሽከርካሪን ያጠቃለለ መስፋት አለበት። ይህ ሰፋ ያለ ትርጓሜ መጠቀም የትራፊክ ደህንነት አላማና መንገድን በጋራ የመጠቀም አስፈላጊነት ለማስፋት ይረዳል። በአሜሪካ በ2013 ብቻ 5.7 ሚልዮን ሞተር ተሸከርካሪ ግጭት ተከስቷል፣ 32,000 ከሞተር ተሸከርካሪ አደጋ ጋር የተዛመደ ሞትና 2.3 ሚልዮን ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። አሽከርካሪዎች ሁሉ ግዜ የትራፊክ ፍሰትና አከባቢውን መገንዘብ፣ ውሳኔ መውሰድ የሚያስፈልግ ሲሆን ቀድሞ መገመት ያስፈልጋል። ሲያሽከረክሩ ለብስክሌተኞችና እግረኞች ልዩ ትኩረት መስጠትና ከስር የተዘረዘሩት ጠቃሚ ምክሮች ይፈጽሙ።

የአልኮል ተጽዕኖ - የደም የአልኮል ክምችት (ቢ.ኤ.ሲBAC) መጠንን ያቃውሳል ■ በምን ያክል ፍጥነት ይጠጣሉ ■ የሰውነት ክብደት ■ ሆድ ውስጥ ያለ ምግብ ■ የአልኮል ክምችት መጠን ■ መድሃኒቶች

የብስክሌት ነጂዎች የተሽከርካሪ ደህንነት

■ ድካም፣ ጭንቀትና ስሜት

■ ለብስክሌተኞች ቢያነስ 3 ጫማ ርቀት ይስጡ ■ በር ከመክፈትዎ በፊት ብስክሌተኞችን ይመልከቱ

በድብርት ውስጥ ሆኖ ማሽከርከር - በእንቅልፍ እጦት

5


■ ሲታጠፉ ለብስክሌተኞች ቅድሚያ ይስጡ

■ በከተማው መሃል ባሉ የእግረኛ መንገዶች ላይ አያሽከርከሩ

የተሸከርካሪ ደህንነት ለእግረኞች

ለማጠቃለል፣ የዜሮ ራዕይ መንገድን በጋራ ለመጠቀምና የመንገድ ደንቦች ለማክበር የአሽከርካሪዎች፣ ብስክሌተኞችና እግረኞች ጥረት ይጠይቃል። ብዙ ደህንነት-ተዛማች እንቅስቃሴዎች የሆኑት “ደች ሪች”(Dutch Reach") እናHAWK የእግረኛ መብራት ምልክቶች መመርያ (በዚህ የመጨረሻ ምእራፍ የሚገኝ) የዜሮ ራዕይን(ቪዥን ዜሮ) ለማገዝ ተጠቅመንበታል። በዲስትሪክቱ አሽከርካሪ ለመሆን በሚዘጋጁበት ግዜ የሁላችንም ደህንነት ለመጠበቅ የሚጠበቅቦትን ኃላፊነት እንደሚወጡ እናምናለን።

■ ሁሌም ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠት መብታቸውን ማክበር ■ ሲታጠፉ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ■ ወደ መስቀለኛና እግረኛ መንገድ ሲጠጉ ጥንቃቄ መውሰድ ■ እግረኛ መንገድ ላይ የቆመ ተሸከርካሪን በፍፁም አለማለፍ

እግረኞች

የዲስትሪክቱ የዜሮ ራዕይ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ይጎብኙ https://visionzero.dc.gov/

እግረኛ ማለት ማነኛውም በእግር የሚጓዝ፣ በዊልቼር፣ በየህፃናት ጋሪ.፤ የሚራመድ፣ በፍጥነት ወይም በዝግታ የሚሮጥ ሰው ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። US ውስጥ በአማካይ እግረኛ በትራፊክ አደጋ በየ 2 ሰአት ሲገደል በየ 8 ደቂቃ ደግሞ የአካል ጉዳት ይደርስበታል። እግረኞች ለአደጋ ከተጋለጡ የመንገድ ተጠቃሚዎች መካከል ሲሆኑ ህፃናት መጠናቸው በማነስና በልምድ እጥረት ምክንያት በትራፊክ አደጋ ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ወይም ሞት ስጋት የተጋለጡ ናቸው። ማስታወስ ያለብዎትጠቃሚ የእግረኞች ደህንነት ምክሮች፦

Dutch Reach Method (የደች ሪች ዘዴ) ክፍት በሮች ለብስክሌተኞች ያለው አደጋ የተከፈቱ የመኪና በሮች ለብስክሌተኞች እጅግ በጣም ከባድ ስጋት ናቸው። አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች የተሸከርካሪ በር ሲከፍቱ የሚከተሉትን እንዲፈጽሙ ይመከራሉ፦ 1. የኃላ እይታ መስታወትን ያረጋግጡ።

■ መንገድን በእግረኛና መስቀለኛ መንገድ ያቋርጡ

2. የጎን እይታ መስታወትን ያረጋግጡ።

■ ሌላ እንድያይዎት እይታዎን ይጨምሩ አሽከርካሪ እንዲያይዎትም ያድርጉ

3. በሩቅ እጅዎ በሩን ይክፈቱት (ከበር በራቀው እጅዎ) “ደች ሪች” ዘዴ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ከኔዘርላንድስ የመጣ ስለሆነ ነው። ሰውነትዎን እንዲዞሩ ስለሚያስገድድዎ የሚመጡ ብስክሌተኞችን በተሸለ ሁኔታ እንድያዩ ያስችሎታል። በተጨማሪም የተሸከርካሪ በር በፍጥነት እንዳይከፈት ያደርጋል። ብስክሌተኞችን ብቻ ሳይሆን በሚመጣ ተሸከርካሪ የራስዎ በር ሲከፍቱ እንዳይጎዳና እንዳይቀደድ ይከላከልሎታል።

■ እግረኛ መንገድ ሁሌም አስተማማኝ ስለሆነ ይጠቀሙ

ብስክሌተኞች US ውስጥ በየአመቱ በአማካይ 700 ሰዎች በብስክሌት/ ተሸከርካሪ ግጭት ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ይህ በየቀኑ ከሁለት ሰዎች በታች ገደማ ይወጣል። በ2013 ከ66,000 በላይ ብስክሌተኞች በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ብስክሌት መንዳት ጤናማና በተፈጥሮው ደህንነቱ የጠበቀ ቢሆንም ብስክሌት መንዳት ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ጋር መንገድን በጋራ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ አደጋዎች አሉት። ብስክሌት ከተሸከርካሪ እኩል የመንገድ መብት ቢኖረውም ደህንነትን ለመጠበቅ ብስክሌተኞች የሚከተሉትን መፈፀም አለባቸው፦

ብስክሌተኞች የብስክሌት መስመር ያላቸውም ይሁን የሌላቸው መንገዶች ላይ የሚከፈቱ በሮችን ለመሸሽ ከቆሙ መኪኖች ቢያነስ 3 ጫማ ርቀው መንዳት ይኖርባቸዋል። ይህ ብስክሌተኞችን ይጠብቃቸዋል ከ ከ “በር ዞን” ውጭ እና የተሽከርካሪ በሮች በመክፈት እንዳይመታ ይከላከሉ።

■ የመንገድ ደንቦችን ያክብሩ ■ ቀይ መብራትና ቁም የሚሉ ምልክቶች ላይ መቆም ■ የጭንቅላት መከላከያ ሁሉግዜ ማድረግ ■ መኪኖችን ለማለፍ ሲሞክሩ የሚከፈቱ የመኪና በሮችን መጠንቀቅ

6


DDOT የእግረኞች መንገድ የመሻገር ደህንነትን ለማሻሻል በመላ ዲስትሪክቱ ተጨማሪ የHAWK መብራት ምልክቶች ለመትከል እቅድ ይዟል።

የእግረኞች ደህንነት DDOT ለእግረኞች ደህንነት በከፍተኛ መልክ ቅድምያ የሚሰጠው ሲሆን ከመብራት ምልክት ውጪ የሆኑ የእግረኛ መንገዶች ያሉባቸው ተሽከርካሪ በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት በማድረግ ይገኛል። አልፎ አልፎ እነዚህ መሻገርያዎች የተለመደውን የትራፊክ መብራት ለመትከል የሚጠይቀውን የምህንድስና መመዘኛ የማያሟሉ ስለሆኑ DDOT ሌላ አማራጮች ይጠቀማል።

በሩን ይክፈቱ ቅርብ ባልሆነ እጅዎ

የዲስትሪክት ህግ ሞተረኞች እግረኛ መንገድ ላይ የእግረኞች መብትን በማክበርና በህግ መሰረት እነዲቆሙ ይጠይቃል። ሆኖም የDDOT ጥናት የሚያሳየው ስራ የሚበዛባቸውና ብዙ ትራፊክ ባለባቸው መንገዶች 1 ከ 4 አሽከርካሪዎች ብቻ በእግረኛ መሻገርያ ለእግረኞች ለማቆም ፍቃደኝነት የሚያሳዩት። ተገቢ ዋስትና ከተገኘ በእንደዚህ አይነት መንገዶች HAWK የመብራት ምልክት መትከል መትከል ይቻላል።

HAWK የእግረኛ መብራት ምልክቶች HAWK መብራት ምልክት ምንድን ነው? የHAWK(High-Intensity Activated crossWalk) መብራት ምልክት እግረኞች ተሽከርካሪ የሚበዛበት መንገድ ለመሻገር እንድያግዛቸው የተሰራ የመብራት-ምልክት ነው። ለሞተረኞችና ለእግረኞች ሲታይ የተለያየ ቢሆንም ምልክቱ በመጫን በወረዳው ያሉ ትራፊክ ለማስቆም ቀይ መብራት እንዲበራ በማድረግ እግረኞች በWALKምልክት መንገድ እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል። የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ለመሻገር የሚጠብቅ እግረኛ መኖሩን በመለየት በራሱ መብራቱ እንዲበራ ያደርጋል።

ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞች በዲስትሪክቱ ያሉ HAWK የመብራት ምልክቶች በአብዛኛው ግዜ ስለ መብራቱ ለአካል ጉዳተኛ እግረኛች መረጃ የሚሰጥ Accessible Pedestrian Signal (APS) መሳርያ ያላቸው ናቸው። የድምጽ መልእክትና የሚነቀጠቀጥ ቀስት ምልክት WALK(ተራመድ) ምልክት መብራቱን ያሳውቃሉ።

HAWK መብራት ምልክቶች ከመደበኛ የትራፊክ መብራት ጋር የወረዳው የተቀናጀ የመብራት ስርአት አካል ተደርገው ሊተከሉ ይችላሉ።

የጎን መንገድ ትራፊክ HAWK መብራት ምልክት ባለበት የጎን መንገድ ካለ ቁም በሚል ምልክት ቁጥጥር ይደረግበታል።

HAWK መብራት ምልክቶች በDC የዲስትሪክቱ ትራንስፖርት ክፍል(DDOT) በጆርጅያ አቨኑ (መንገድ) እና ሄምሎክ ስትሪት (ጎዳና) በ2009 የመጀመርያ HAWK መብራት ምልክት ተክሏል። ከዛ በኃላ የHAWK መብራት ምልክት (Pedestrian Hybrid Beacon በመባልም ይጠራል) በፌደራል አውራ ጎዳና አስተዳደር አገልግሎት ላይ እንዲውል ፍቃድ ተሰጠ።

ጥያቄዎች አሉ? በዲስትሪክቱ ስለ HAWK መብራት ምልክት ወይም ስለ ማነኛውም የትራፊክ መቆጣጠርያ መሳርያ ጥያቄ ካሎት የሚከተሉትን ይጠይቁ፦

7


እግረኞች

ሞተረኞች

አዝራሩን ይጫኑ ለመጥራት WALK ምልክት

ይቀጥሉ

(አንዳንድ ቦታዎች እግረኞች በቀጥታ ይለያል)

ይጠብቁ

በጥንቃቄ ይቀጥሉ

(የመብራት ምልክቱን ለመቀየር እስከ አንድ ደቂቃ ሊወስድ ይችላል)

(የመብራት ምልክት በርቷል)

ይጠብቁ

ፍጥነት ይቀንሱ እና ለመቆም ይዘጋጁ

WALK ምልክትን ካዩ በኃላ መሻገር ይጀምሩ

ቁም!

(ትራፊክ መቆሙን ያረጋግጡ)

መሻገርን ይቀጥሉ

ቁም!

(የመብራት ምልክት መቁጠርያ)

ከዚያ ግልጽ ከሆነ በ ጥንቃቄ ይቀጥሉ

ለመሻገር ቁልፉን ይጫኑ

ይቀጥሉ

8


የዲስትሪክቱ ትራንሰፖርት ክፍል 55 M Street, SE, Suite 400 Washington, DC 20003 ኢመይል: ddot@dc.gov ስልክ፡ (202) 673-6813 ድህረ ገጽ፡- ddot.dc.gov

9


Rectangular Rapid Flashing Beacon (RRFB) ይጫኑ ቁልፍ ለ ማብራት ማስጠንቀቂያ መብራቶች

RRFB እግረኛ የሚያበራው የትራፊክ መቆጣጠርያ መሳርያ ሲሆን ከተቀለሙ የእግረኛ ማሻገርያ ጋር በጥምረት እግረኞች በአስተማማኝ ብዙ ትራፊክ ባለው መንገድ እንዲሻገሩና የትራፊክ ደህንነት ለማሻሻል ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ RRFBዎች ከየእግረኛ ማቋረጫ ምልክት ስር ከየእግረኛ ማቋረጫ ጠቋሚ ቀስት ደግሞ ከፍ ብሎ በሁለቱም የእግረኛ ማቋረጫ አቅጣቻዎች ይቀመጣል። እግረኞች መሳርያዉን በእጅ አዝራሩን በመጨጫን ወይም በበተገጠመለት እግረኛ የመለየት ስርአት ማብራት ይችላሉ። RRFB አሽከከርካሪዎችን መንገድ የሚያቋርጡ እግረኞችን በቀላሉ እንድያዩዋቸው የሚረዳ ሲበራ በፍጥነት ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ መብራት አለው። ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ መብራት እግረኞች በአስተማማኝ ደህንነት እንዲሸሻገሩ የሚያስችል በቂ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን አሽከርካሪዎች ሙሉ ለሙሉ በመቆም እግረኞች እንዲሻገሩ ማድረግ አለባቸው።

10


መንጃ ፈቃድ የፈተና ሂደት ይህ መመርያ ሁሉም አሽከርካሪዎች ማወቅ ያለባቸው ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ ማሽከርከር ደንቦችና ተግባራት መረጃ ይሰጣል። ይህ መመርያ ስለ የማሽከርከር ሁሉም ገጽታ መረጃ ይሰጣል። ሙሉ መመርያውን በጥንቃቄ ማምበብዎን ያረጋግጡ። መመርያውን ካላነበቡትና ካላጠኑት የDC መንጃ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልገው የእውቀት ፈተናን ማለፍ አይችሉም። ፈተናውን በሚፈተኑበት ጊዜ ይህንን መመርያ መመልከት አይፈቀድም።

• • • • • • •

በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሚገኙ የህዝብ መንገዶች ሞተር ተሽከርካሪ ወይም ሞተርሳይክል ለማሽከርከር መንጃ ፈቃድ ሊኖርዎት ይገባል። ወደ በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ከገቡበት ጀምሮ በ60 ቀናት ውስጥ የDC መንጃ ፈቃድ እንዲኖርዎት ይጠየቃሉ።

በተጨማሪ ፈተናው ስክሪን ላይ በእጅ በመንካት በመመለስ በድምጽና በምስል ይገኛል።

የሚከተሉትን ካሟሉ የDC መንጃ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ፦

ኢንግሊዝኛ ስፓኒሽኛ ፖርችጊዝኛ ፈረንሳይኛ ጃፓንኛ ቬትናምኛ ራሽያኛ

• • • • • • •

መንደሪን ታጋሎግ ኮርያኛ ካንቶኒስኛ አማርኛ ታይኛ ጀርመንኛ

የእውቀት ፈተና ስለ ትራፊክ ህጎች፣ የመንገድ ደንቦች፣ የሞተር ተሽከርካሪ ህጎች እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማሽከርከር ያሎትን እውቀት ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ስለሚፈተኑት መረጃ በዚህ መመርያ ይገኛል።

• ቢያንስ እድሜዎ 17 አመት ከሆነ(ለማጅ ፈቃድ 16 አመት

ላይ)፤

ለደረጃ D የመንጃ ፈቃድ ለማግኘት የናሙና ጥያቄዎች

• ህጋዊ ሙሉ ስም፣ የትውልድ ቀን፣ ሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር እና

1. የትራፊክ መብራት አረንጓዴ እያሳየ ትራፊክ ፖሊሱ እንዲቆሙ ምልክት ቢሰጥዎት፤ ምን ያደርጋሉ፦

ሁለት (2) የDC ነዋሪነት ማረጋገጫ፤

• የእይታ ፈተና፣ የእውቀት ፈተና እና የመንገድ ችሎታ

A. የትራፊክ ፖሊሱ ትእዛዝን መከተል

ፈተናዎች በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ፤

B. የትራፊክ መብራት ምልክትን መከተል

• ከ18 አመት በታች ከሆኑ ደግሞ የወላጅ/አሳዳጊ ፈቃድ

ካልዎት፤

C. መጀመርያ የትራፊክ ፖሊሱን ቀጥሎ መብራቱን

• ከዚህ በፊት የነበሮት መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቅያ

D. ከፊት ለፊትዎ ያለው ተሽከርካሪ የሚያደርገውን ማድረግ

የሚያስረክቡ ከሆነ፤

• ፈቃድዎ ታግዶበት፣ ተሰርዞቦት ወይም ተቀምተው

2. ሌላ ተሽከርካሪዎች ለማለፍ እንደተፈቀደሎት ለመንገር የተሻለው መንገድ ምን ሲያዩ ነው፦

የማያውቁ ከሆኑ፤

• የሕክምና መስፈርቶችን ማክበር;

A. ብልጭ ድርግም የሚል አረንጓዴ መብራት ካለ

ይህ መመርያ የንግድ ያልሆነ ተሽከርካሪ(የሰው መጓጓዣ መኪና) ለማሽከርከር የሚያስፈልግ መረጃ ይሰጣል። የንግድ ተሽከርካሪ መንጃ ፈቃድ ከፈለጉ የንግድ መንጃ ፈቃድ(CDL) መመሪያ ማንበብና ማጥናት ይጠበቅቦታል። ሞተርሳይክል ለማሽከርክር ፈቃድ ከፈለጉ ከዚህ መመርያ በተጨማሪ ሞተርሳይክል ኦፕሬሽን ማኑዋል ማንበብና ማጥናት ይጠበቅቦታል።

B. ከፊት ለፊት ያለው መንገድ ቀጥ ያለ ሲሆን C. ከፊት ያለው ተሽከርካሪ OK (ማለፍ ይቻላል) የሚል ምልክት ሲያሳይ D. ድፍን ወይም የተቆራረጡ የመንገድ መስመር ቀለማት ሲኖሩ 3. ወደ ሀገር አቋራጭ መንገድ በአጭር መግብያ ሆነው የፍጥነት መስመር ከሌለ፤ ምን ያደርጋሉ፦

የአሽከርካሪ እውቀት ፈተና የአሽከርካሪ ፈቃድ እውቀት ፈተና በማነኛውም የDMV አገልግሎት ማእከል መውሰድ (መፈተን) ይቻላል። ፈተናው በሚከተሉት ቋንቋዎች ሊገኝ ይችላል፦

A. ወደ ቀኙ-ጥግ መስመር መግባትና ወደ ትራፊክ ፍሰቱ በፍጥነት መግባት

11


B. የዋናው መንገድ ዳር በመጠቀም ወደ ትራፊኩ ፍጥነት መውጣት C. በትራፊኩ ክፍተት ሲያገኙ ወደ መግቢያው በፍጥነት መግባት መልሶች፦ 1-A፣ 2-D፣ 3-C ተቀባይነት ያለው አለም-አቀፍ የመንጃ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ዜጎች የDC መንጃ ፈቃድ ማግኘት ከፈለጉ የእውቀት እና የእይታ ፈተናዎች መውሰድና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። የDC መንጃ ፈቃድዎ ከ 365 ቀናት በላይ ግዜ ካለፈበት የእውቀት ፈተናው ወይም የDC የኢንተርኔት ትራፊክ ትምህርት ክፍል መውሰድና ማለፍ ይጠበቅቦታል። የDC መንጃ ፈቃድዎ ከ 545 ቀናት በላይ ግዜ ካለፈበት የእውቀት ፈተናው እና የመንገድ ችሎታ ፈተና መውሰድና ማለፍ ይጠበቅቦታል። መንጃ ፈቃድዎ ከተሰረዘ፣ በሚመለስሎት ጊዜ፣ የእውቀት ፈተናው እና የመንገድ ችሎታ ፈተና መውሰድና ማለፍ ይጠበቅቦታል። ከ70 አመት እድሜ በላይ ሆነው የDC መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ወይም ጊዜ አልፎበት ለማሳደስ ከፈለጉ የDC የጎልማሳ አሽከርካሪ የመንጃ ፈቃድ ክፍል ወይም መታወቅያ ካርድ ማመልከቻ ባሎት የህክምና ምርመራ ሞተር ተሽከርካሪ ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ማሽከርከር ይችላሉ የሚል ማረጋገጫ በመስጠት የሚሞላሎት ዶክተር ያስፈልግዎታል። የአሽከርካሪ የእውቀት ፈተናው ካላለፉ ለ3 ተከታታይ ቀናት በድጋሚ ፈተናው እንዲወስዱ አይፈቀድሎትም። የአሽከርካሪ የእውቀት ፈተናው ለስድስት(6) ተከታታይ ጊዜ ከወደቁ(ካላለፉ) መጀመርያ ከወደቁበት ቀን ጀምሮ የሚተሰብ ለ12 ወራት ፈተናው እንዲወስዱ አይፈቀድሎትም።

የእይታ ማስተካከያ ሌዘር(ጨረር) ቀዶ ጥገና ካደረጉ፥ መንጃ ፈቃድዎ ላይ የተፃፈውን የሌንስ ገደብ ለመሰረዝ የዶክተር ምስክር ወረቀት ያስፈልጋል።

የመንገድ ችሎታ ፈተና የመንገድ ማሽከርከር ችሎታ ፈተና የመንቀሳቀስ፣ በትራፊክ ማሽከርከር፣ የመታጠፍያ ምልክቶች የመጠቀም ችሎታ፣ ተሽከርካሪውን በአስተማማኝ የመቆጣጠርና በትይዩ መኪናን ማቆምያ ላይ ማቆም ያጠቃልላል። የመንገድ ችሎታ ፈተና በDC መንገዶች የሚከናወን ይሆናል። ለእያንዳንዱ የመንገድ ችሎታ ፈተና $10 ክፍያ ይከፈላል። በአጠቃላይ ተቀባይነት ያለው አለም-አቀፍ የመንጃ ፈቃድ ካልዎት ለተመሳሳይ የመንጃ ፈቃድ ደረጃ የመንገድ ችሎታ ፈተና አይፈተኑም እና ወደ የDC መንጃ ፈቃድ ይቀየርሎታል። የDC መንጃ ፈቃድዎ ከ 545 ቀናት በላይ ግዜ ካለፈበት የእውቀት ፈተናው እና የመንገድ ችሎታ ፈተና መውሰድና ማለፍ ይጠበቅቦታል። የመንገድ ችሎታ ፈተናዎች በቀጠሮ ብቻ ይሰጣሉ። በDMV ለአሽከርካሪ ፈቃድ የመንገድ ችሎታ ፈተና ቀጠሮ ለማስያዝ ተቀባይነት ያለው የለማጅ ፈቃድ መያዝ ያስፈልጋል። የመንገድ ችሎታ ፈተና በኢንተርኔት ላይ www.dmv.dc.gov ወይም 311 ላይ በመደወል ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል። የመንገድ ችሎታ ፈተና ያስያዙት ቀጠሮ በሁለት የስራ ቀናት ውስጥ መሰረዝ ካልቻሉ $30 የቀጠሮ ማሰረዣ ክፍያ ይከፍላሉ። ያስመዘገቡት ቀጠሮ በሁለት የሥራ ቀናት ውስጥ ካሰረዙት ወይም DMV ከሰረዘው ይህ ክፍያ አይከፍሉም። 311 ላይ በመደወል ቀጠሮውን ማሰረዝ ይችላሉ። በተያዘሎት የመንገድ ፈተና ቀን፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለቦት፡ • ከቀጠሮዎ ቢያንስ 10 ደቂቃ ቀድመው ይድረሱ፤

የእይታ ማጣራት እይታዎን ለመፈተን፤ ወደ ማሽን እንዲመለከቱ ከተደረጉ በኋላ የፊደላት መስመር/ቅርፆች ለDMV ተወካይ እንዲያነቡ ይጠየቃሉ። የ ማጣራት ሂደቱ የማየት ችሎታዎና ተጓዳኝ እይታዎ የዲስትሪቱ ሞተር ተሽከርካሪን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሽከርከር የተቀመጠ መመዘኛ መስፈርቶች ሟሟለትዎን ይወስናል። የህክምና ምርመራ አይደለም። የእይታ ማጣራት ፈተናውን ከወደቁ፥ ከአይን ህክምና ባለሞያ የአይን ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። የእይታ ማጣራት ፈተናውን መነፅር ወይም ኮንታክት ሌንስ ተጠቅመው ካለፉ ስያሽከረክሩም እነዚህን መጠቀም ይገደዳሉ እና መንጃ ፈቃድዎ ላይም ይህንን ገደብ እንዲታይ ይደረጋል።

• የተሸከርካሪ መስፈርት በሚያሟላ ተሸከርካሪ ይድረሱ፤ • ተቀባይነት ያለው የለማጅ ፈቃድ ይዘው መቅረብ፤ • 21 አመት እድሜና ከዛ በላይ የሆነ ሙሉ መንጃ ፈቃድ

ያለው ሰው ጋር ይዘው መምጣት፤

• የተመዘገበና የተረጋገጠ ኢንሹራንስ ያለው ተሽከርካሪ

ይዘው መምጣት፤ እና

• የደህንነትዎን ቀበቶ ይታጠቁ።

ግራድ(GRAD) ፕሮግራም (ከ16 - 20 አመት እድሜ) ከሆኑ ለጊዜያዊ መንጃ ፈቃድ ብቁ መሆንዎ የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ከተሞላ ውል/ቅፅ ጋር ይዞ መምጣት።

12


የለማጅ ፈቃድ ኖርዎት በራስዎ እያሽከረክሩ ያለ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ያለው 21 አመትና ከዛ በላይ እድሜ ያለው ሰው የመንገድ ችሎታ ፈተናን መውሰድ አይችሉም። የመንገድ ችሎታ ፈተና ከወደቁ፥ ፈተናውን ከወደቁበት ጀምሮ ያለውን ለ72 ሰአታት ድጋሚ መፈተን አይችሉም። የመንገድ ችሎታ ፈተናው ለስድስት(6) ተከታታይ ጊዜ ከወደቁ(ካላለፉ) መጀመርያ ከወደቁበት ቀን ጀምሮ የሚተሰብ ለ12 ወራት ፈተናው እንዲወስዱ አይፈቀድሎትም።

በሚከተሉት የተዘረዘሩት አንድ ወይም ከዛ በላይ ምክንያቶች የመንገድ ችሎታ ፈተናዎ ሊሰረዝ ይችላል፦

ለመንገድ ችሎታ ፈተና የሚጠቀሙበት ተሽከርካሪ ማሟላት ያለበት፦

• እርስዎና ተሽከርካሪዎ ሁሉንም የመንገድ ፈተና

• በወንበሮቹ መካከል የአደጋ ግዜ ፍሬን ሊኖረው ይገባል።

DC DMV የመንገድ ችሎታ ፈተናውን በDMV የመንገድ ፈተና ተሽከርካሪ እንዲፈተኑ አማርጭ ይሰጣል።

በወንበሮቹ መካከል ከሚገኝ የአደጋ ግዜ ፍሬን ምትክ ተሽከርካሪው በተሳፋሪው በኩል ሁለተኛ መሪ እና/ወይም ፍሬን ወይም መንጃ ፈቃድ ፈታኙ በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል ሌላ ለአደጋ ግዜ የሚያገለግል የደህንነት መሳርያ ሊኖረው ይገባል።

• ፈታኙ የአደጋ ጊዜ ፍሬን ለመድረስ ተቸገርኩ ብሎ/ላ

ካመነነ/ች ወይም በአስቸጋሪ ጊዜ ተሽከርካሪውን ለማቆም ከተቸገረ/ች፤

• ከDMV ቁጥጥር ውጪ የሆነ መንገዱን አደገኛ የሚያደርጉ

መጥፎ አየር ፀባይ ወይም ሌላ ሁኔታዎች ካጋጠሙ፤ ወይም መመዘኛዎች አላሟሉም።

• የመንገድ ችሎታ ፈተና በቀጥታ ከዲሲ DMV የሚወስዱ

ከሆነ ወደ ፈተና ቦታ እንደደረሱ በራስዎ ወይም በDMV ተሽከርካሪ የመፈተን አማራጭ አልዎት።

• በሶስተኛ ወገን ቀጠሮ የሚያዝላቸው የመንገድ ችሎታ

• ከማንኛውም ግዛት ወቅታዊ ምዝገባ ይኑርዎት;

ፈተና የDMV ተሽከርካሪ መጠቀም አይችሉም።

• የሞተር ተሽከርካሪ ዋስትና ካርድ ወይም ፖሊሲ ያለው፤

• የDMV የመንገድ ፈተና ተሽከርካሪ ለመጠቀም ተጨማሪ

ክፍያ የለውም።

• ካርዱ/ፖሊሲው የተሽከርካሪው መሆኑን የሚያመለክትና

የሚያገለግልበት የጊዜ ገደብ የሚያሳይ መሆን አለበት፤

• DMV የመንገድ ፈተና ተሽከርካሪ ለመጠቀም የመረጡ

ደንበኞች ከፈተና በፊት "ስምምነት፣ ያለመክፈልና፣ የካሳ ክፍያ" ቅፅ መሙላት ይጠየቃሉ።

• ተቀባይነት ያለው የምርመራ ተለጣፊ ማሳየት

አለበት(ተሽከርካሪው በተመዘገበበት ግዛት የሚጠይቅ ከሆነ)፤

• የፊትና የኃላ ፈቃድ መለያ ማሳየት አለበት(ተሽከርካሪው

በተመዘገበበት ግዛት የሚጠይቅ ከሆነ)፤

• በአግባቡ የሚሰራ መብራት፣ የመብራት ምልክቶች፣

ጥሩምባ እና የአሽከርካሪ/ተሳፋሪ መስኮትና በሮች፤

• በአግባቡ የተቀመጠ የኃላ እና የሁለቱም ጎን ማሳያ

መስታወት፤

• ምንም አይነት ስንጥቅ ሆነ ቆሻሻ የሌለውና ግልፅ እይታ

የሚሰጥና ከኃላ መስታወት ምንም ያልተንጠለጠለበት፤

• ጥሩ ይዞታ ላይ ያለ እና ንፋሱ የተስተካከለ ጎማዎች

ይኑርዎት። መለዋወጫ (ዶናት) ጎማዎች ተቀባይነት የላቸውም፤

• የኪራይ ተሽከርካሪዎች ለመንገድ ችሎታ ፈተና የሚፈቀደው

ተፈታኙ በኪራይ ውሉ ላይ እንድያሽከረክር የተፈቀደለት መሆኑን እና ተገቢ የሆነ የዋስትና ሽፋን ካለው፤ እና

• የአገልግሎት ወይም ማስጠንቀቂያ መብራቶች ከዳሽቦርዱ

ያልጎደለበት፣ የጋዝ እጥረትን ጨምሮ

13


የመንጃ ፈቃድና የፈቃድ አይነቶች የለማጅ ፈቃድ ከ21 አመት እድሜ በታች ከሆኑ፤ በGradual Rearing of Adult Drivers (GRAD) ፕሮግራም (ጀማሪ) ማሽከርከር ይጠበቅቦታል። የGRAD ፕሮግራም ለጀማሪ አሽከርካሪዎች(ከ16 - 20 አመት እድሜ) ሙሉ የመንጃ ፈቃድ መብት ከማግኘታቸው በፊት ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ የማሽከርከር ልምድ እንድያገኙ የሚፈቅድ ነው። የለማጅ ፈቃድ 21 አመት እድሜና ከዛ በላይ በሆነ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ያለው ሰው ከጎንዎ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ሆኖ ቁጥጥር እያደረገሎት የሞተር ተሽከርካሪ እንድያሽከረክሩ የሚያስችሎት ነው። የለማጅ ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 16 አመት እድሜ መሆን፣ የእውቀት ፈተና እና የእይታ ማጣራትን ማለፍ ያስፈልጋል። ከ18 አመት እድሜ በታች ከሆኑ በወላጅ/አሳዳጊ የተፈረመ የወላጅ ፈቃድ/ ስምምነት ያስፈልጋል። የለማጅ ፈቃድ ለአሜሪካ ዜጎች ለሁለት አመት ብቻ ያገለግላል አይታደስም። የለማጅ ፈቃዱ አንዴ ግዜው ካለፈበት አዲስ የለማጅ ፈቃድ ለማግኘት እንደገና የእውቀት ፈተናውን ተፈትነው ማለፍ ይጠበቃል። ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ለመሆን ለስድስት(6) ተከታታይ ወራት በሚገመገም ነጥብ ከሚያስቆጥሩ የእንቅስቃሴ ደንብ ጥሰት ነጻ መሆን አለቦት።

ጊዚያዊ የመንጃ ፈቃድ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ቢያንስ 16 አመት ከ 6ወር እድሜ መሆን አለቦት። ቢያንስ ለ6 ወር ነጥብ ከሚያስቆጥር የእንቅስቃሴ ደንብ ጥሰት ነጻ የሆነ የለማጅ ፈቃድ ሊኖርዎት ያስፈልጋል። 21 አመትና ከዛ በላይ እድሜ የሆነ ሙሉ ህጋዊ መንጃ ፈቃድ ባለው ሰው ክትትል ቢያንስ 40 ሰአት የማሽከርከር ልምድ እንዳሎት የሚያሳይ የተፈረመ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ የማግኘት የ40 ሰአት ብቁነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ። የመንገድ ክህሎት ፈተና መውሰድና ማለፍ አለብህ። ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ለአንድ አመት የሚያገለግል ሲሆን ይታደሳል። ከ18 አመት እድሜ በፊት ለካሳ ተሽከርካሪ ማሽከርከር አይፈቀድሎትም።

ሙሉ የመንጃ ፈቃድ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድዎን ቢያንስ ለ 6 ወር ከያዙ በኃላ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅቦዎታል፦ • ቢያንስ ለ12 ተከታታይ ወራት ነጥብ ከሚያስቆጥር

የእንቅስቃሴ ደንብ ጥሰት ነጻ መሆን፤

• 21 አመትና ከዛ በላይ እድሜ የሆነ ሙሉ ህጋዊ መንጃ

ፈቃድ ባለው ሰው ክትትል ቢያንስ 10 ሰአት በማታ የማሽከርከር ልምድ እንዳሎት የሚያሳይ የተፈረመ ሙሉ መንጃ ፈቃድ የማግኘት የ10 ሰአት ብቁነት ማረጋገጫ

ምስክር ወረቀት ማቅረብ ከቻሉ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ሊሰጥዎት ይችላል። GRAD ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉ የማይገደዱ ከሆነና ለለማጅ ፈቃድ የሚያስፈሉጉት መስፈርቶችን ሁሉንም ካሟሉ በኃላ የመንገድ ችሎታ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ሊሰጥዎት ይችላል። በመደበኛ መንጃ ፈቃድ ከ26,001 ፓውንድ በታች የተሽከርካሪ አጠቃላይ ክብደት ምዘና(GVWR) ያላቸው ለንግድ አገልግሎት የማይውሉ፣ በሞተር የሚንቀሳቀሱ ብስክሌቶችና እሰከ አስራ አምስት(15) የተሳፋሪ ወንበር ያለው ሚኒባስ ማሽከርከር ይችላሉ። መንጃ ፍቃድዎን ይዘው እንዲቆዩ ደህንነቱ የጠበቀና ኃላፊነት የሚሰማው አሽከርካሪ መሆን ይጠበቃል።

Gradual Rearing of Adult Drivers (GRAD) መርሃ-ግብር ለGRAD የሚፈቀዱ የማሽከርከር ሰአታት የለማጅ ፈቃድ 21 አመትና እና ከዛ በላይ እድሜ ያለው አሽከርካሪ ከጎንዎ መኖር አለበት በየቀኑ፥ ከጠዋት 6:00 እስከ ማታ 9:00 ጊዚያዊ ፈቃድ መስከረም - ሰኔ ሰኞ - ሐሙስ፥ ከጠዋቱ 6:01 - ማታ 10:59 አርብ - እሁድ፥ ከጠዋቱ 6:01 - ሌሊት 11:59 ሐምሌና ነሐሴ በየቀኑ፥ ከጠዋት 6:01 - ሌሊት 11:59 ሙሉ ፈቃድ ሆኖ ከ17 - 18 አመት እድሜ ለሆኑት መስከረም - ሰኔ ሰኞ - ሐሙስ፥ ከጠዋቱ 6:01 - ማታ 10:59 አርብ - እሁድ፥ ከጠዋቱ 6:01 - ሌሊት 11:59 ሐምሌና ነሐሴ በየቀኑ፥ ከጠዋት 6:01 - ሌሊት 11:59 ከ ወይም ወደ ስራ፣ ትምህርት ቤት ያዘጋጀው እንቅስቃሴ፣ ሐይማኖታዊ ወይም ስፖርታዊ ዝግጅት፣ ወይም ተሳታፊ የሆኑበት የልምምድ ክፍለ ጊዜ፣ በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የተዘጋጀ፣ ሲቪክ ድርጅት፣ ወይም ለጥቃቅን ኃላፊነት የሚወስድ 14


ሌላ ተመሳሳይ አካል፣ ወይም ከጎንዎ የተሳፋሪ ወንበር ላይ የደህንነት ቀበቶ የታጠቀ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ያለው 21 አመትና ከዛ በላይ እድሜ ያለው ሰው ከታጀቡ ለGRAD በተከለከሉ ሰአታት ሞተር ተሽከርካሪ ማሽከርከር ይችላሉ። 21 አመት ላይ፥ GRAD አሽከርካሪዎች ከፕሮግራሙ ይለቀቃሉ። በለማጅ ፈቃድ ደረጃ ሆነው፥ 21 አመት እድሜ ከደረሱ፥ ለመንገድ ችሎታ ፈተና በቀጥታ ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። የማሽከርከር ምስክር ወረቀት ቅጽ ወይም ስድስት(6) ወር ጊዜ የመጠበቅ አይጠበቅቦትም። በጊዜያዊ የመንጃ ፈቃድ ደረጃ ሆነው፥ 21 አመት እድሜ ከደረሱ፥ ወደ DMV አገልግሎት ማእከል በመሄድ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ። የማሽከርከር ምስክር ወረቀት ቅጽ ወይም ስድስት(6) ወር ጊዜ የመጠበቅ አይጠበቅቦትም።

የGRAD ፕሮግራም ክልከላዎች የለማጅ ፈቃድ፦ ብቻዎን ማሽከርከር አይችሉም። ከጎንዎ የፊት ተሳፋሪ ወንበር ላይ 21 አመትና ከዛ በላይ እድሜ የሆነው ሙሉ መንጃ ፈቃድ ያለው ሰው ታጅበውና መመርያ እየተቀበሉ መሆን አለበት። ለማጅ ፈቃድ ለያዙ የማሽከርከርያ ሰአታቱ ክልክል ነው። እርስዎና ተሳፋሪው ሁሉ ጊዜ የደህንነት ቀበቶ መታጠቅ አለባችሁ። ለካሳ የሞተር ተሽከርካሪ ማሽከርከር አይችሉም። የንግድ ተሽከርካሪ ማሽከርከር አይችሉም። እያሽከረከሩ የሞባይል ስልክ ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መሳርያ (በእጅ ወይም ከእጅ ንክኪ ውጪ) መጠቀም አይችሉም። ሌሎች ተሳፋሪዎች ያሉበት ተሽከርካሪ ማሽከርከር አይችሉም።

ጋር ማሽከርከር ይችላሉ። ይህ ክልከላ ወንድሞች/እህቶች ወይም ልጆች ለሆኑ ተሳፋሪዎች አያጠቃልልም። ከ18 አመት በታች ከሆኑ፥ ለካሳ ሳይሆን ለመዝናኛ ብቻ ከሚጠቀሙበት የመንገደኛ ተሽከርካሪ ወይም ሞተርሳይክል ውጪ ሌላ የሞተር ተሽከርካሪ ማሽከርከር አይችሉም። እርስዎና ተሳፋሪዎቹ ሁሉ ጊዜ የደህንነት ቀበቶ መታጠቅ አለባችሁ። ከ18 አመት በታች ከሆኑ፥ ለሚፈፅሙት የGRAD ደንብ ጥሰቶች ለወላጅ/ህጋዊ አሳዳጊ እንድያውቁት ይደረጋል። ከ17 - 18 አመት እድሜ ለሆኑ ባለ ሙሉ መንጃ ፈቃድ አሽከርካሪዎች የማሽከርከር ሰአታት ክልክል ነው።

GRAD ፕሮግራም ማስፈጸሚያዎች በለማጅ ፈቃድ ደረጃ፦ ከ18 አመት በታች ከሆኑ፥ ለሚፈፅሙት የGRAD ደንብ ጥሰቶች ለወላጅ/ህጋዊ አሳዳጊ እንድያውቁት ይደረጋል። ላመኑበት፣ ወይም ተጠያቂ ለሚደረጉበት፣ ወይም ለተፈረደብዎት ማነኛውም ነጥብ የሚያስቆጥር የእንቅስቃሴ ደንብ ጥሰት ለጊዜያዊ መንጃ ፈቃድ ለማመልከት የሚጠብቁት የጊዜ ወረፋ ያራዝመዋል። ወደ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ደረጃ ከመመረቅዎ በፊት ለስድስት(6) ተከታታይ ወራት በሚገመገም ነጥብ ከሚያስቆጥሩ የእንቅስቃሴ ደንብ ጥሰት ነጻ መሆን አለቦት። በየለማጅ ፈቃድ ደረጃ/ጊዜ፥ 8 ወይም ከዛ በላይ ነጥቦች ከተገመገሙቦት ወይም የGRAD ፕሮግራም ክልከላዎች ጥሰው ከተገኙ የለማጅ ፈቃድዎ ለ90(ዘጠና) ቀናት ይታገዳል እና የመልሶ ማቋቋም ክፍያ ይከፍላሉ። ጊዚያዊ ፈቃድ ደረጃ፦

ከ18 አመት በታች ከሆኑ፥ ለሚፈፅሙት የGRAD ደንብ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ለ 16 ከግማሽ - 20 አመት እድሜ ጥሰቶች ለወላጅ/ህጋዊ አሳዳጊ እንድያውቁት ይደረጋል። ላሉ አሽከርካሪዎች፦ ላመኑበት፣ ወይም ተጠያቂ ለሚደረጉበት፣ ወይም ለተፈረደብዎት ማነኛውም ነጥብ የሚያስቆጥር የእንቅስቃሴ ብቻዎን ማሽከርከር ይችላሉ። ከጎንዎ የፊት ተሳፋሪ ወንበር ደንብ ጥሰት ለሙሉ መንጃ ፈቃድ ለማመልከት የሚጠብቁት ላይ የደህንነት ቀበቶ የታጠቀ ሙሉ መንጃ ፈቃድ ያለው 21 የጊዜ ወረፋ ያራዝመዋል። ወደ ሁኔታዎች የተቀመጡበት ሙሉ አመትና ከዛ በላይ እድሜ ያለው ሰው እና ሌላ ወንድም/ የመንጃ ፈቃድ ደረጃ ለማደግ ለ አስራ ሁለት (12) ተከታታይ እህት፣ ልጅ ወይም ወላጅ ጋር ማሽከርከር ይችላሉ። እርስዎና ወራት ከደንብ ጥሰት ነጻ መሆን አለቦት። በጊዚያዊ ፈቃድ ተሳፋሪዎቹ ሁሉ ጊዜ የደህንነት ቀበቶ መታጠቅ አለባችሁ። ደረጃ እያሉ፥ ማንኛውንም የGRAD ፕሮግራም ደንብ ከጣሱ ጊዚያዊ መንጃ ፈቃድ ለያዙ የማሽከርከርያ ሰአታቱ ክልክል የመጀመርያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ወይም ብዙ የGRAD ፕሮግራም ነው። ከ18 አመት እድሜ በታች ከሆኑ ለካሳ የሞተር ተሽከርካሪ ጥሰቶች ላይ በመመስረት ጊዚያዊ ፈቃድዎ ለሰላሳ(30)፣ ማሽከርከር አይችሉም። ወደ ሁኔታዎች የተቀመጡበት ሙሉ ስልሳ(60)፣ ወይም ዘጠና(90) ቀናት ይታገዳል። እነዚህ የመንጃ ፈቃድ ደረጃ ለማደግ ለ አስራ ሁለት (12) ተከታታይ ቅጣቶች ሌላ ሊሚወሰንቦት ከሚችል ቅጣት በተጨማሪ ነው። ወራት ከደንብ ጥሰት ነጻ መሆን አለቦት። በተጨማሪም፥ እንደማንኛውም ሌላ አሽከርካሪ፥ የቅጣት ሁኔታዎች የተቀመጡበት ሙሉ መንጃ ፈቃድ(ከ18 አመት ነጥብዎ 10 ከደረሰ በቀጥታ ይታገዳሉ። ከእግዱ በኃላ ጊዚያዊ ፈቃድዎ መልሰው ለማግኘት የመልሶ ማቋቋም ክፍያ ይከፍላሉ። በታች)፦ ብቻዎን ማሽከርከር ይችላሉ። ከ18 አመት እድሜ በታች ከሆኑ ከሁለት (2) የማይበልጡ 21 ያልሞላቸው ተሳፋሪዎች 15


ሌላ አገልግሎቶች አካል(የሰውነት ክፍል) ለጋሽ አካል ወይም ህብረህዋስ(ቲሹ) ለመለገስ የመረጡ ሰዎች ልገሳ አለም ላይ ልዩነት መፍጠርያ መንገድ ነው ብለው ይመለከቱታል። የህክምና ሳይንስ እድገቶች የሰው አካልን ወደሌላ በመትከል የሰዎች ጤናን ወደ ነበረበት ለመመለስ አስችሏል። አንድ ለጋሽ እስከ ስምንት ለሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማዳንና እስከ ሃምሳ ለማደርሱ ሰዎች ጤናቸውን ማሻሻል ይችላል። ይህንን ያውቃሉ? • በሁሉም የእድሜ ክልልና የጤና ሁኔታ ያሉ ሰዎች ለጋሽ

መሆን ይችላሉ፤ የስኳር፣ የሄፒታይተስና ሌላ የጤና እክል ያሉትንም ጨምሮ።

• ለለጋሽ ቤተሰብ የሚከፈል ወይም የአካል ልገሳ ሂደት

ወጪዎችን የሚከፈል ክፍያ የለም።

• አብዛኞቹ ዋና የአሜሪካ ሐይማኖቶች የአካልና የህብረህዋስ

ልገሳን ይደግፋሉ።

የተመረጠ አገልግሎት ስርአት የDC መንጃ ፈቃድ በሚወስዱበት ጊዜ በDMV ለተመረጠ አገልግሎት መመዝገብ ይችላሉ። DC DMV ከ18-25 አመት ያሉ ወንዶችን በ ልዩ አገልግሎት ይመዘግባል፤ በDC DMV የመንጃ ፈቃድ ማመልከት ሂደት መመዝገብ መተው የሚል ካልመረጡ በስተቀር።

• ልገሳ የክፍት-ሳጥን ቀብር አማራጭን አይከለክልም።

ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ይጎብኙ፦

• የአካልና የህብረህዋስ ማውጣት የሚጀመረው ሁሉንም

የምዝገባ መረጃ ፅሕፈት ቤት

የሕይወት አድን ጥረቶች ተደርገው ማዳን ሳይቻል ሲቀርና ምትን ከተረጋገጠ በኃላ ነው።

እንዴት መመዝገብ ይቻላል? በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ፥ ከ18 አመት እድሜ በላይ ከሆኑ፥ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት በሚሞሉት ማመልከቻ የልገሳ ጥያቄው ላይ መለገስ የሚፈልጉትን የአካል/ህብረህዋስ ሳጥን ውስጥ "YES" የሚለውን በመምረጥ ማሳየት ይችላሉ። ለቤተሰብዎ እና ለሚቀርቧቸው ወዳጆች በሚሞቱበት ግዜ በእርስዎ ቦታ ሆነው ውሳኔዎን እንዲፈፀምና እንዲናገሩሎት መለገስ እንደሚፈልጉ ቀድመው ማሳወቅ ሁሌም ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም የመለገስ ውሳኔዎን ለሐኪምዎ፣ የሐይማኖት መሪዎ እና ለየህግ ጠበቃዎ ማጋራት አለቦት። ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ይጎብኙ፦ • የአሜሪካ የጤናና የሰው አገልግሎቶች

መምርያ በ www.organdonor.gov

• Washington DC ሕይወት ይለግሱ በ

www.donatelifedc.org/ ወይም 1-866-BE-A-DONOR

የተመረጠ አገልግሎት ስርአት የወሂብ አስተዳደር ማእከል ፖ.ሳ. ቁጥር 94638 Palatine, IL 60094-4638 ስልክ፡ 847-688-6888 TTY፦ 847-688-2567 www.sss.gov FAQ’s

የመራጭ ምዝገባ በDC DMV የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ያስገቡ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች አልፈልግም የሚል ካልመረጡ በስተቀር መራጭ እንዲሆኑ በቀጥታ ይመዘገባሉ። በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ለመራጭነት እንዲመዘገቡ ማሟላት ያለቦት፦ • የ U.S ዜጋ መሆን፤ • የDC ነዋሪ መሆን፤ 16


• ከምርጫው አንድ ቀን በፊት ወይም በምርጫው ቀን

ቢያንስ 18 አመት እድሜ መሆን፤

• በፍርድ ቤት "mentally incompetent"(የአእምሮ

ብቃት የሌለው) ተብለው ያልተፈረደቦት መሆን፤ እና

• ከD.C ውጪ በሌላ ቦታ የመምረጥ መብት የሌለው።

ማመልከቻውን ካስገቡበት በስስት(3) ሳምንታት ውስጥ የመራጭ ምዝገባ ካርድ ይደርሶታል። ለተጨማሪ መረጃ የምርጫና ስነምግባር ቦርድ(Board of Elections and Ethics) በ www.dcboe.org ወይም 202-727-2525 ይጎብኙ። • FAQ’s

17


መታወቅ ያለባቸው ጠቃሚ ነገሮች • በተሽከርካሪ ውስጥ የሚገኙ አሽከርካሪ እና ሁሉም

• 10 ወይም 11 ነጥብ ከተመዘገበብዎ የDC መንጃ ፈቃድዎ

ተሳፋሪዎች የደህነት ቀበቶ መታጠቅ አለባቸው።

የማሽከርከር መብት ለዘጠና(90) ቀናት ይታገድቦታል። በይፋ እስኪመለሱ ድረስ የመንዳት መብቶችዎ ይታገዳሉ።

• በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ሲያሽከረክሩ ከሞባይል ስልክ

የእጅ ንክኪ ነጳ መሆን አለቦት።

• 12 ነጥብ ከተመዘገበቦት የDC መንጃ ፈቃድዎ ይሻራል እና

ለስድስት ወራት ወደ ነበረበት ለማስመለስ አይችሉም። የማሽከርከር ልዩ መብትዎ በይፋ ወደ ነበረበት እስኪመለስ ድረስ ይሻራል።

• ነዋሪዎች የአድራሻ ለውጥ ሲያደርጉ ለሞተር ተሽከርካሪዎች

መምርያ (DMV) በ ስልሳ(60) ቀናት ውስጥ ማሳወቅ አለባቸው።

• ሰክረው ወይም በተጽእኖ ስር ሆነው ሲያሽከረክሩ

• ተሽከርካሪው የተመዘገበ እስከሆነ ድረስ ዋስትና

ያጠቃለለ የትራፊክ ወንጀል ጥሰት ፈፅመው ከተፈረደቦት ለመጀመርያ ወይም ለቀጣይ አልኮል ተዛማች ጥፋቶች ወደ IID ፕሮግራም እንዲመዘገቡ ይገደዳሉ። ሽረቱ ለመጀመሪያ ጥፋት በትንሹ ለ 6 ወራት፣ ለሁለተኛ ጥፋት ለ 1 አመት፣ ለሶስተኛና ከዛ በላይ ጥፋት ለ 2 አመት ጊዜ ይፀናል። የማሽከርከር ልዩ መብትዎ በይፋ ወደ ነበረበት እስኪመለስ እና የመመለሻ ክፍያ እስኪ ከፈል ድረስ ይሻራል።

ሊኖረው ይገባል። ያለዋስትና ክፍተት ከተገኘ ያስቀጣል። የተሽከርካሪዎ መለያ ወደ DMV እስኪመለስ ድረስ ዋስትናውን መሰረዝ አይችሉም።

• በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ሞተር ተሽከርካሪ

ሲያሽከረክሩ ህግ አስፈፃሚዎች ሲያስቆምዎ ትክክለኛ መንጃ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪ ምዝገባ እና የዋስትና ማረጋገጫ የማሳየት ግዴታ አለቦት። ይህን ለማድረግ ካልቻሉ ለቅጣት እና/ወይም እስር ይዳረጋሉ

• የልጅ ማሳደግያ አለመክፈል መንጃ ፈቃድና የተሽከርካሪ

ምዝገባ ሊታገድ ይችላል።

• በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ እያሽከረከሩ ከኃላ የሆነ ነገር

ማያያዝ ወይም የኃላ ማሳያ መስታወት ላይ ማንጠልጠል የደንብ ጥሰት ነው።

• DC DMV ብዙ ጠቃሚ የህዝብ አገልግሎት ማሳወቅያ

(PSA) ቪድዮዎች አዘጋጅቶ በDC DMV ዩቱይብ ቻናል ይገኛሉ፦

Judy Doe

■ "REAL ID! (ትክክለኛው መታወቂያ) Know Before You Go" (ከመሄድህ በፊት እወቅ) ■ "Documents Needed to Renew Your DC Driver License or ID Card"(የDC መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቅያ ለማሳደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች)

• አሽከርካሪዎች የተወሰኑ የመንቀሳቀስ ደንብ

ጥሰቶች ሲፈፅሙ ነጥብ ይመዘገብባቸዋል፤ ጥሰቱ የፈፀሙት በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ይሁን በሌላ ግዛቶች(states)። በፍርድቤት ከተጠሩ፣ ከተፈረደቦት ወይም ቲኬት ከከፈሉ(መክፈል ጥፋትን ማመን ነው) DMV ነጥቦችን ይመረምራል። የሚያዝቦት የነጥብ ብዛት በፈፀሙት የጥሰት አይነት ይመሰናል።

• የተያዘቦት ነጥብ በማሽከርከር ማህደርዎ ለ ሁለት አመት

ስራ ይቆያል።

• በትክክለኛ የDC መንጃ ፈቃድው በተንቀሳቃሽ ደንብ

ጥሰቶች ነጥብ ሳይመዘገብቦት ለአንድ ሙሉ አመት ከዘለቁ በየማሽከርከር ማህደርዎ በጎ ነጥብ(Good Point) እንዲመዘገብልዎ ብቁ ይሆናሉ። 18


የአሽከርካሪ መረጃ ለማሽከርከር በጥሩ አቋም መገኘት ማሽከርከር ሰዎች ከሚሰርዋቸው በጣም ውስብስብ ነገሮች አንዱ ሲሆን በመንገድ ደህንነቱ የጠበቀ ለመሆን ሁሉ ጊዜ ቀላል አይደለም። ማሽከርከር ሰዎች በመደበኛ ከሚሰርዋቸው ሊጎዱን ወይም ሊገድሉን ከሚችሉ ጥቂት ነገሮች አንዱ ነው። አስተማማኝ አሽከርካሪ ለመሆን ብዙ ችሎታ፣ ልምድ፣ ኃላፊነትና አስተዋይነት ይጠይቃል። ማሽከርከር እየተለማመዱ ይህ ኃላፊነት/ስራ የበለጠ ከባድ ነው። የሞተረኛ ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ የማሽከርከር ችሎታ በግልጽ የማየት፣ በጣም ሳይዳከሙ መሆን፣ ዕፅ ተጠቅመው ባለማሽከርከር፣ በአጠቃላይ ጤነኛ በመሆንና ለማሽከርከር አእምሮአዊ በቁነት ላይ የተመሰረተ ነው።

DC DMV - ወደ ላቀ ደረጃ የሚሳድግ DC DMV ለደንበኞቹ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት፣ ደህንነቱን የጠበቀ የማሽከርከር አከባቢ በማስተዋወቅ እና የደንበኞች ፍላጎት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው።

የማሽከርከር መብት በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ሞተር ተሽከርካሪ ማሽከርከር መብት ሳይሆን ልዩ መብት ነው። መንጃ ፈቃድዎ ደህንነት በጠበቀና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መንገዶች ላይ የሞተር ተሽከርካሪን የማሽከርከር ልዩ መብት ይሰጦታል።

የውሸት ወይም የተጭበረበረ የመታወቂያ ካርድ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም የለማጅ ፈቃድ መያዝ የውሸት ወይም የተጭበረበረ የመታወቂያ ካርድ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም የለማጅ ፈቃድ ለመያዝ ከሞከሩ ወይም እያወቁ የውሸት ወይም የተጭበረበረ የመታወቂያ ካርድ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም የለማጅ ፈቃድ ይዘው ከተገኙ ህጉ በሚለው መሰረት ለቅጣትና ለእስር ይዳረጋሉ።

የመንገድ ምልክቶች ሁሉንም የአውራ ጎዳና ምልክቶች ማንበብና ማብራራት መቻል አለቦት። የእውቀት ፈተናው ብዙ የሰፈርና የአውራ ጎዳና ምልክቶች ያጠቃለለ ሲሆን የDMV ፈታኝ በማሽከርከር ፈተና ወቅት ለምልክቶቹ በቂ ትኩረት መሰጠቱን ክትትል ያደርጋል።

ትራፊክ ሊያዘገዩ ወይም ቲኬት(ቅጣት) ይቆረጥቦታል እና/ ወይም ይቀጣሉ።

አራት የማሽከርከር አበይት አካላት መመልከትና ማየት በአይንዎ ሲመለከቱ በአእምሮዎ ያያሉ በአከባቢዎ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ለመገንዘብ ንቁ አእምሮ ሲኖርዎት ሲያሽከረክሩ ለሚወስዱት ጠቃሚ ውሳኔ ያዘጋጀዎታል። ማሰብ እና መወሰን ጠቃሚ የሆነ ነገር ካዩ በኃላ ስለሱ ያስባሉ እና ምን ማድረግ እንዳለቦት ይወስናሉ። ለራስዎ እና ለሌሎች ደህንነት የሚጨነቁ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለቦት አነስተኛ የአደጋ ስጋት ባለው መሰረት ይወስናሉ። አነስተኛ የአደጋ ስጋት ማለታችንን ያስተውሉ። ሁሉም ማሽከርከር የተወሰነ የአደጋ ስጋት ያካተተ ነው። ብልህ አሽከርካሪ ሁኔታውን በፍጥነት ተገንዝቦ ሊያደርጋቸው/ልታደርጋየው የሚችሉ ብዙ የተለያዩ ነገሮች እንዳሉ ተገንዝቦ/ባ አነስተኛ የአደጋ ስጋት ያለውን ለማድረግ ይወስናል/ትወስናለች። ለማድረግ ያሰብከውን ሌሎች እንዲያውቁ ማድረግ መንገድ ላይ ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎችና እግረኞች ከመንገድህ/ሽ እንዲርቁ ከተፈለገ ለማድረግ ያሰብከውን/ ያሰብሺውን ማወቅ አለባቸው። በእጅ ምልክት፣ የመታጠፍያ መብራት ምልክቶች፣ የፊት መብራት፣ የፍሬን መብራት እና በተሽከርካሪዎ አቀማመጥ እንድያውቁ ማድረግ ይችላሉ። ውሳኔ ማድረግ ለማድረግ ያሰቡትን ከወሰኑ በኃላ ያሎት የማሽከርከር ልምድና ችሎታ ተቅመው መፈጸም አለቦት።

የትራፊክ ህጎችን ማክበር ሁሉም የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የትራፊክ ህጎች ማክበር አለቦት። የመንገድ ምልክቶች፣ የትራፊክ የመብራት ምልክቶች፣ የመንገድ መስመር ቀለማት፣ የፖሊስ መኮንኖች ትእዛዝ እና በአደጋ ጊዜ ሁኔታዎች የእሳት አደጋ ትእዛዛት የማክበር ኃላፊነት አልዎት።

አጠቃላይ ህጎች • አጠቃላይ ህጎችን ማወቅ አለቦት

የትራፊክ ህጎች

• ህግ የሚጠይቀውን የሆነ ነገር ባለመፈጸም ወይም

ማንኛውም የትራፊክ ህግ መጣስ ጥፋት ወይም ወንጀል ይፈጽማሉ።

የትራፊክ ህጎች ግጭት ለመከላከል እና የትራፊክ ፍሰት እንዲቀጥል ያለመ ነው። ህግ ከጣሱ፥ ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ፥ 19


• የፖሊስ መኮንን መመርያዎች ህግን፣ ምልክቶችን፣

ከአደገኛ አሽከርካሪዎች እራስዎን እንዴት ይጠብቃሉ፦

የመብራት ምልክቶችን እነ ቀለማትን የሚፃረሩ ቢሆኑም እንኳን መፈጸም አለቦት። እንደነዚህ አይነት መመርያዎች ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ የትራፊክ ፍሰቱ እንዲቀጥል አስፈላጊ ይሆናሉ።

• ከመስመሩ በመውጣት አደገኛ አሽከርካሪው እንድያልፍ

ማድረግ

• ከነሱ ጋር አለመፎካከር • የዓይን ግንኙነትን ያስወግዱ

• መንገዱን ትተው በግል ይዞታ በመጓዝ የትራፊክ መብራት

ምልክት ወይም የመንገድ ምልክት ለመሸሽ መሞከር አይቻልም።

በአደገኛ ማሽከርከር በአደገኛ ማሽከርከር በግድየለሽነት የማሽከርከር አካል ነው። የብሔራዊ አውራ ጎዳና ትራፊክ ደህንነት አስተዳደር እንደገመተው 2/3ኛ የሞት ግጭቶች በአደገኛ አሽከርካሪዎች ምክንያት የሚከሰት ሲሆን ከጠቅላላ ግጭቶች ወደ 35% ገደማ በእነሱ ምክንያት የሚከሰት ነው። አንድ ሰው ከሚከተሉት የትኛውንም ከፈጸመ የአደገኛ ማሽከርከር ጥፋተኛ ይሆናል፦

• ሁሉ ጊዜ ጨዋ አሽከርካሪ መሆን

አደገኛ ማሽከርከርን ለመከላከል ማገዝ፦ • አደገኛ ማሽከርከር አጋጣሚዎችን ወደ ፖሊስ ሪፖርተር

ማድረግ

• ለታናናሽ ተሳፋሪዎችን አርአያ መሆን

በግድየለሽ ማሽከርከር አንድ ሰው ሞተር ተሽከርካሪን እንደሚከተለው ካሽከረከረ የግድየለሽ ማሽከርከር ጥፋተኛ ይሆናል፦ • ለሰውና ለንብረት ደህንነት እያወቁ አለመጨነቅ፤ ወይም

• በቋሚ RED(ቀይ) የትራፊክ መብራት ማለፍ • ተሽከርካሪዎችን መቅደምና ማለፍ • በቀኝ በኩል ማለፍ

• ለሰውና ለንብረት ደህንነት እያወቁ እንደማይጨነቁ ማሳየት

ቸልተኛ ማሽከርከር

• ከፍጥነት ገደብ በላይ ማሽከርከር

አንድ ሰው ሞተር ተሽከርካሪውን በቸልተኝነት ወይም ንቀት በሚያሰይ ሁኔታ እያሽከረከረ/ች የየትኛውም አይነት ንብረት ወይም የማንኛውም ሰው ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል/ የምትጥል ከሆነ/ች የቸልተኛ ማሽከርከር ጥፋተኛ ይሆናል/ ትሆናለች።

የአደገኛ ማሽከርከር በምን ይከሰታል?

እሽቅድድም

• የመንገድ መስመር በፍጥነት መቀየር • ተጠግቶ መከተል • ቅድሚያ የሚሰጡ ቦታዎችን አለመስጠት

• የተጨናነቁ መንገዶች • ችኮላ ላይ መሆን • የመንገድ ስራ • በሌላ የሕይወት ውጣውረድ የሚመጣ ውጥረት • አደገኛ የማሽከርከር አመለካከት • ራስ ወዳድነት

አደገኛ አሽከርካሪ ከመሆን እንዴት መዳን ይቻላል፦

በማንኛውም አይነት የተሽከርካሪ እሽቅድድም፣ የፍጥነት ኤግዚቢሽን፣ ወይም የፍጥነት ውድድርና በተለምዶ የህዝብ ጎዳና፣ መንገድና አውራ ጎዳና ላይ የሚደረጉ እሽቅድድሞችን ጨምሮ መሳተፍ የለብዎትም።

ግጭቶች በህጉ መሰረት ግጭት በሚያጋጥሞት ጊዜ የተወሰኑ መፈጸም ያለቦት ግዴታዎች አሉ። ግጭት ውስጥ የተሳተፉ የማንኛውም አሽከርካሪ ዋና ተግባራት-፦ • ማቆም

• ቀድሞ ማቀድ

• መቆየት፦ የተጎዳ ሰው እርዳታ እስከሚሰጡ እና እራስዎን

• የፍጥነት ገደብ ማክበር

እስኪለዩ ድረስ ባጋጠመበት ቦታ በቅርበት መቆየት። ከቻሉ ከትራፊክ መስመሩ ተሽከርካሪውን ገለል ማድረግ።

• አማራጭ መስመሮች/መንገዶች መለየት • ማርፈድ

• የተጎዳ ማንኛውንም ሰው መርዳት በግጭቱ ለተጎዳ

ማንኛውም ሰው ለመርዳት ፍቃደኛ መሆን። እንደ ጉዳቱ

• ጨዋ እና ትዕግስተኛ አሽከርካሪ መሆን

20


ደረጃ በአብዛኛው ግዜ እርዳታ መስጠት የሚፈጸመው አምቡላንስ በመጥራት ነው። በተለምዶ ራሱን የሳተ ወይም በከፍተኛ የተጎዳ ሰው ለማንቀሳቀስ መሞከር የለብዎትም።

ደህንነትዎን ለማረጋገጥ መሰረታዊ የደህንነት ደንቦች በጣም ጠቃሚ ናቸው። • የተሽከርካሪው የውጪው አካል ሁኔታ መመልከት -

ጎማዎቹን መመርመር፣ የተላቀቁ ክፍሎች፣ ፍሳሽ ማየት፣ ወዘተ፤

• እራስህን መለየት/ማወቅ ግጭት ላይ የተሳተፉ

አሽከርካሪዎች ስማቸው፣ አድራሻቸው እና ሲያሽከረክሩት ስለነበረው ተሽከርካሪ የምዝገባ መረጃ መስጠት አለባቸው። በሚጠየቁበት ጊዜ፥ መንጃ ፈቃድዎን ግጭቱ ላይ ለተሳተፈ/ፉ ሰው(ሰዎች) ማሳየት።ሲጠይቋዋቸው ማንም ሰው መረጃ መቀበል የሚችልበት ሁኔታ ከሆነና ፖሊስ በቦታው ከሌለ፤ በሚችሉት ፍጥነት በቅርበት ለሚገኝ የፖሊስ መምሪያ መረጃውን ሪፖርተር ማድረግ።

• መንበሩን ያስተካክሉ፤ • መስታወቶችን ያስተካክሉ፤ • የደህንነት ቀበቶን በአግባቡ ይታጠቁ፤ • ቁልፍ አስገብተው ሞተር ያስነሱ፤ • ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት፥ ሁኔታዎች ምን ያክል መጥፎ

እንደሆነ ያስቡ ለምሳሌ መብራት፣ የአየር ሁኔታ፣ መንገዱ እና የትራፊክ ሁኔታ ጉዞዎ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፤ እና

• የዋስትና መረጃ መስጠት፦ ዋስትና የሚሰጦት ኩባንያ

ስምና አድራሻ፣ የአከባቢው ወኪል ወይም የአከባቢው ፅሕፈት ቤት ስምና አድራሻ እና ፖሊሲ ቁጥርዎ ወይም መለያ ቁጥርዎ መስጠት አለብዎት።

• የተፃፈ ማስታወሻ ማስቀመጥ፦ ባለቤቱ ያልተገኘበት

ጉዳት የደረሰበት ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ካለ ባለቤቱን ለማግኘት ጥረት ማደረግ አለበት። ባለቤቱ ካልተገኘ ከላይ የተጠቀሱት የመለያ መረጃ ያለበት የፅሑፍ ማስታወሻ በተጎዳው ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ጎልቶ በሚታይና ጥብቅ ቦታ ትቶ መሄድ።

• ማሽከርከር ከመጀመርዎ በፊት የተሽከርካሪ የፍሬን

መብራትና የመብራት ምልክቶችን ይመርምሩ

መታጠፍ ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ለመታጠፍ ማቀድ ይስፈልጋል፤ • መታጠፍያ ቦታ ከመድረስዎ ቀድመው አእምሮዎን ዝግጁ

ማድረግ። የመጨረሻ ደቂቃ ውሳኔዎች ብዙ ጊዜ ግጭቶችን ያስከትላሉ።

• የሚጠበቀውን ሪፖርት ማድረግ፦ እርስዎ የተሳተፉበትና

• መታጠፍ ከማሰብዎ በፊት ቀድመው ወደ ትክክለኛ

የትኛውም የተጋጨ የሞተር ተሽከርካሪ ዋስትና ወደ ሰጦት ኩባንያ ሪፖርት መደረግ አለበት።

የመንገድ መስመር መግባት አለብዎት። የትራፊክ ፍሰቱ ፈጣን በሆነ ቁጥር ቀድመው ወደ ትክክለኛ መስመር መግባት ይጠበቅቦታል።

በሞተር ተሽከርካሪ የቤት እንስሳን የገጨ ሞተረኛ ግዴታ

• የኃላ እና በሁለቱም ጎን በኩል መመልከት። መስመር

በሞተር ተሽከርካሪ የቤት እንስሳ ከገጩ እና ከጎዱ ወድያው ግጭት የደረሰበት አከባቢ ስልጣን ያለው የፖሊስ መምርያ ማሳወቅ አለብዎት። ፖሊስ እንስሳው የህክምና እንክብካቤ እንዲያገኝ የሚመለከተውን ኤጀንሲ ያነጋግራል።

• ተገቢ ወደ ሆነው የመታጠፍያ ፍጥነት ያቀዝቅዙ ግን

ከመቀየርዎ በፊት ህጉ በሚጠይቀው መሰረት ያሰቡትን በመብራት ምልክት ይስጡ። (የማሽከርከር ደንቦችን ይመልከቱ) በዝግታ ያድርጉት። ከሀገር-አቋራጭ ሌላ የመስመርገደብ አውራ ጎዳና ሲወጡ ብቻ ነው ለየት ነገር ያለው። (የሀገር-አቋራጭ እና ሌላ የመስመር-ገደብ አውራ ጎዳናዎች ይመልከቱ)

ደህንነቱ የጠበቀ የማሽከርከር ልምዶች አእምሮዎ በማሽከርከር ያተኩሩ፣ ህጎችን ማክበር ለሌሎች የአውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ጨዋ መሆንተ ምንም እንኳን የትራፊክ ህጎችን ማክበር ቢችሉም፣ አሁንም በትራፊክ አደጋ ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ። ሌሎች አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህጎችን ላያከብሩ ይችላሉ ወይም ንቁ ላይሆኑ ይችላሉ ወይም ተሽከርካሪያቸው በደካማ የቴክኒክ ሁኔታ ላይ ሊሆን ይችላል። ደህንነቱ የጠበቀ አሽከርካሪ ለመሆን ንቁ መሆን፣ አደጋን ቀድሞ ማየት እና ሌሎች ሊሰሩት ለሚችሉ ስህተቶች ክፍተት መስጠት። ይህ ምዕራፍ ግጭቶችን ለመከላከል ወይም ማስወገድ የማይቻልበት ከሆነ ደግሞ የአደጋ መጠናቸው ለመቀነስ የሚረዱ የደህንነት ልምዶች ያስተምራል።

• በህጉ መሰረት ይታጠፉ

ወደ ኃላ መጓዝ ተሽከርካሪን ወደ ኃላ ማሽከርከር ችሎታና አስተዋይነት ይጠይቃል። የሚራመዱ፣ የሚሮጡ ወይም በአሻንጉሊት መኪና ወይም ባለ ሶስት እግር ብስክሌት የሚጫወቱ ህፃናትን ያስተውሉ። በአብዛኛው ሁኔታ፥ ጭንቅታትዎን አዙረው በኃለኛው መስታወት ወደ ኃላ እና ሁለቱም የጎን መስታወቶች መመልከት ደህንነትን ይጨምራል። በአንድ የኃላ መስታወት 21


ብቻ አይተማመኑ በፍጥነት ወይም ሩቅ መንገድን ወደ ኃላ አያሽከርክሩ፤ በምትኩ ዞረው የሚመለሱበት አማራጭን ይፈልጉ። ከ ወይም ወደ መስቀለኛ መንገድ ወደ ኃላ በፍፁም እያሽከረከሩ፤ በምትኩ ወደ ጎን መንገድ በመታጠፍ ታጠእዛው ታጥፈው ይመለሱ ወይም በሰፈር ውስጥ እያሽከረከሩ። ዞሮው ለመመለስ ከዋናው መንገድ ወደ ጎን ገባ ያለ መንገድ ከተጠቀሙ ለመግባትም ሆነ ለመውጣት ደህንነት የጠበቀ ነው። ማእዘን ካላቸው የተሽከርካሪ ማቆምያ ቦታዎች በጥንቃቄ ይውጡ።

የጥሩምባ ጥቅም ጥሩምባን በአደጋ ስጋት ጊዜ እግረኛች፣ ብስክሌተኛች ወይም የሌላ ተሽከርካሪ አሽከርካሪን ለማስጠንቀቅ ብቻ ይጠቀሙ። ጥሩምባ ፍሬንን ለመተካት አይደለም የተሰራ። በአደጋ ጊዜ ካልሆነ በስተቀር "Quiet Zone" (የፀጥታ ቦታ) ላይ መጠቀም አይቻልም። ጥሩምባን የአደጋ ስጋት በሌለበት ጊዜ ሞተረኛ፣ ብስክሌተኛ፣ ወይም እግረኛን ለማስጠንቀቅ አይጠቀሙ። ጮክ ያለ ጥሩምባ ብስክሌተኛን ሊያስደነብር ይችላል።

ከጋራጅ(ተሽከርካሪ ማቆምያ) ወይም የውስጥ መይገድ ሲጀምሩ • በአቅራቢያው ያሉ ተሽከርካሪዎች እና እግረኞችን

ይመልከቱ

• ወደ ትክክለኛ የትራፊክ ፍሰት ፍጥነት ለመግባት በጥንቃቄ

ይንቀሳቀሱ

• ወደ ኃላ ሲወጡ ከተሽከርካሪዎ ጀርባ ያለውን መመልከት

የቤት እንስሳ ሲያሽከረክሩ የቤት እንስሳን ከአጠገብዎ ያርቁ። እቅፎዎ ላይ እንዲቀመጡ ወይም የተሽከርካሪ መስኮት በኩል ንፁህ አየር እንዲያገኙ መፍቀድ የለብዎትም። በተሽከርካሪዎ ውስጥ የቤት እንስሳ ብቻውን መተው የለብዎትም።

የተላቀቁ ነገሮች የተላቀቁ ነገሮች በተለይ የፊት ዳሽቦርድ እና የኃላ መስኮት መደርደሪያ በግጭት ጊዜ ሊፈናጠሩ ይችላሉ። የለቀቁ ነገሮች የኃላ እቃ ማስቀመጫ ወይም ወለል ላይ ያስቀምጡ ምክንያቱም ወንበር ላይ ከሆኑም ተፈናጥረው እርስዎንም ተሳፋሪንም ሊመቱ ስለሚችሉ። የሚወድቁ ነገሮች ለምሳሌ የአስቤዛ ዘንቢል ሊያስደነግጦት ይችላሉ እና ትኩረትዎን ከመንገድ ሊነቅሉ ወይም እጅዎን ከመሪ ሊነቅሉ ይችላሉ። ወለል ላይ የሚቀመጡ ነገሮች የፍሬን ወይም ነዳጅ መስጫ ፔዳልን ሊረብሹ ስለሚችሉ ከዛ ማራቅ ያስፈልጋል።

የማቆምያ ቦታ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ማለፍ የማቆምያ ቦታ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን በሚያልፉበት ጊዜ የሚከፈቱ በሮች፣ ከመኪኖች መካከል የሚወጡ ወይም የሚሮጡ እግረኛ(በተለይ ህፃናት) እና ብስክሌተኞችን መመልከት አለብዎት።

የማሽከርከር ሁኔታዎች ፍጥነት መቼ ይቀነሳል የሚከተለውን ሲያጋጥም ፍጥነት ይቀነሳል፦

መቻልዎን ያረጋገጡ። በመንገድዎ ምንም እንደሌለ ለመረጋገጥ ከመኪናዎ መውጣት ሊያስፈልግ ይችላል።

• ወደ መስቀለኛ ሲጠጉ፣ የባቡር ሐዲድ መሻገርያ፣

ኩርባ(ከርቭ) ወይም የዳገት ጫፍ፤

• ወደ ኃላ ሲወጡ ከተሽከርካሪዎ ጀርባ ያለውን

• የህፃናት መጫወቻዎች፣ ትምህርት ቤት ወይም ህፃናት

ለመመልከት በጎን መስታወቶችና ጭንቅላቶን አዙረው በኃለኛ መስታወት በጥንቃቄ ይመልከቱ

የሚጫወቱበት ቦታ አጠገብ፤

• በጠባብና ጠመዝማዛ መንገድ ሲጓዙ፤

• ወደ መንገድ ሲገቡ አቁመው እንደገና በማየት ይቀጥሉ

• ለእግረኞች የአደጋ ስጋት ካለ፤ እና

የእጅ ምልክቶች በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ

• የአየር ሁኔታ ወይም የአውራ ጎዳና ሁኔታዎች፥ ወይም

የራስዎ ሁኔታ ለደህንነት ሲባል ፍጥነት መቀነስ ያስፈልጋል። በጣም በዝቅተኛ ፍጥነት በፍጹም ማሽከርከር የለብዎትም ምክንያቱም በመደበኛ ፍጥነት የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ስለሚረብሽ። በጣም በዝቅተኛ የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ትራፊክ ፍሰቱን ስለሚዘጉ ወይም ስለሚያስተጓጉሉ ግጭት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በከፍተኛ የፀሐይ ብርሃን እና ከጀርባዎ ያለ ሽከርካሪ የመብራት ምልክቱን ከሸፈነብዎት ከየመታጠፍያ መብራት ምልክቶች በተጨማሪ የእጅ ምልክት ይጠቀሙ።

በተሽከርካሪ ውስጥ መጨናነቅ ሲያሽከረክሩ በተሳፋሪዎች ወይም በእቃዎች በፍጽም መጨናነቅ የለብዎትም። በሁሉም አቅጣጫ እይታዎን የሚከለክል በፍጹም መፍቀድ የለብዎትም። እያሽከረከሩ የኃላ መስታወት ላይ የሆነ ነገር ማያያዝ ወይም ማንጠልጠል የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ደንቦች የሚፃረር ነው።

እርጥብ አስፋልት መንገዶች እርጥብ አስፋልት መንገድ ከደረቅ አስፋልት መንገድ በብዙ እጥፍ ያንሸራትታል። መንገዱ እርጥብ ከሆነ፥ ኩርባ ላይ 22


ከመንገድ ለላመውጣት ከበድ ያለ ሲሆን ለማቆምም ረጅም ርቀት ይፈልጋል። በተለይ ቀላል ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ምክንያቱም መንገድ ላይ የዘይትና የውሃ ቅልቅል አደገኛ ስለሆነ። የዘይትና የተሽከርካሪ ፍስሾች ከብዙ ሰአት ዝናብ በኃላ እንደማሆነው ተጥቦ ስላልሄደ። በተመሳሳይ፤ በመኸር ወቅት አስፓልት ላይ እርጥብ ቅጠሎችን ይጠንቀቁ

ሃይድሮፕላኒንግ እና ጎርፍ በ35 መይል በሰአት ፍጥነት ሸንተረር ያላቸው አብዛኞቹ ጎማዎች መንገዱን ዝናብ መጥረግያ መስታወቱን እንደሚጠርገው "ይጠርጉታል"። ፍጥነት በጨመረ ቁጥር ግን ጎማዎቹ መንገዱን የመጥረግ አቅማቸው ይቀንሳል እና ጎማዎቹ በውሃ ንጣፍ ላይ መሽከርከር ይጀምራል ልክ የውሃ ጀልባ እንደሚሆነው። ይህ "Hydroplaning"(የውሃ እቅድ) ይባላል"።

የፊትና የኃላ ግጭቶች በቅርብ ርቀት ተከታትለው በመሄድ የተፈጸመው ናቸው። ከፊት ለፊትዎ ያለውን ተሽከርካሪ የምልክት ቦታ ለምሳሌ የትራፊክ ምልክት ወይም ከላይ የሚያልፍ ድልድይ ሲያልፍ መመልከት ያስፈልጋል። በመቀጠል "ዋን ታውዘንድ ዋን፣ ዋን ታውዘንድ ቱ፣ ዋን ታውዘንድ ትሪ፣ ዋን ታውዘንድ ፎር" ብለው ይቁጠሩ። የምልክት ቦታው ዋን ታውዘንድ ፎር ብለው ከመቁጠርዎ በፊት ካለፉት ተጠግተው እየተከተሉ ነው ማለት ነው። አልፎ አልፎ የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች (አውቶቡስ፣ የፖስታ ቤት ሚኒባሶች) ተከትለው ሲጓዙ ተጨማሪ ረቀት ተሰጥተው ማሽከርከር ይገባል። በመጥፎ አየር ፀባይ ሲያሽከረክሩ በተሽከርካሪዎ እና ከፊት ለፊትዎ ካለው ተሽከርካሪ ጋር ያለውን ርቀት ከአራት እስከ አምስት ሴኮንዶች መጨመር አለብዎት።

ይህ ሲከሰት ፍሬን መያዝ፣ ፍጥነት መጨመር ወይም በአግባቡ መታጠፍ አይችሉም። መቆጣጠር አለመቻልዎን ባወቁበት ሰአት እግርዎን ከነዳጅ ፔዳል በማንሳት መሪውን አጥብቀው በመያዝ ወደ ሚሄዱበት መስመር መሄድ ነው። ተሽከርካሪዎን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር በጀመሩበት ወቅት ተሽከርካሪዎን ፍጥነቱ እንዲቀንስ ያድርጉ። ጎርፍ በከባድ ዝናብ ጊዜ ይከሰታል። የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳይታሰብና በፍጥነት ሊመጣ ይችላል። በከባድ ዝናብ በጥቂት ወይም በሰአታት ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ በጎርፍ በተጥለቀለቀ አካባቢዎች ማሽከርከር አይቻልም። የፊት ለፊት መንገድዎ በጎርፍ ተጥለቅልቆ ካዩት ወደ ኃላ በመመለስ ወደሚፈልጉት ቦታ የሚወስዶት ሌላ መንገድ ይፈልጉ። በተለይ እይታን በሚቀንስበት በማታ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ወሃው የተሽከርካሪዎ የታችኛው ክፍል እስከ ስድስት ኢንች ከደረሰ ከቁጥጥር ውጪ ሊያደርግ ወይም መቆምን ሊያስከትል ይችላል። ሁለት ጫማ ጥልቀት ያለው የሚንቀሳቀስ ውሃ ብዙ ተሽከርካሪዎችን የስፖርትና ፒክአፕ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሊወስዳቸው ይችላል። በጎርፍ የተጥለቀለቀ ግን ለመሻገር ጥልቀት የሌለው የሚመስል መንገድ ለመሻገር መሞከር የለብዎትም። ውሃ ጉድጓዶችን ይደብቃል ባስ ሲል ደግሞ የመንገዱ ንጣፍ በማፍረስ ጠራርጎ ሊወስድ ይችላል። ሌላ አማራጭ መንገድ ከሌለ ከፍ ወዳለ ቦታ በመንቀሳቀስ ውሃው እስኪቀንስ መጠበቅ።

ያስታውሱ የጭነት ተሽከርካሪን ማቋረጥ አይቻልም። የጭነት ተሽከርካሪ ለመቆም ብዙ ጊዜና ርቀት ይፈልጋል።

ከሶስት እስከ አራት ሴኮንድ የመከተልና የመቆም ርቀት ደንብ ተሽከርካሪዎን ለማቆም የሚያስፈልግዎ ርቀት ማወቅ ደህንነቱን የጠበቀ የማሽከርከርያ ፍጥነት ለመምረጥ ይጠቅማል። የሚከተሉት መመርያዎች እንደመነሻ መውሰድ ይቻላል ነገር ግን የመቆም ርቀትዎ በብዙ ምክንያቶች ይወሳናል፥ ለምሳሌ፦ • አሽከርካሪው አደገኛ ሁኔታን ለማየትና ለመገንዘብ

የሚወስድበት የጊዜ መጠን

• አደጋን አይቶ ፍሬን ለመያዝ የሚወስደው የጊዜ መጠን -

ከ 3-4 ሴኮንዶች

• የአስፋልት መንገዱ አይነትና ሁኔታ • የመንገዱ የዳገትና ቁልቁለት መጠኑ • የጎማዎቹ ሸንተረር አይነትና ሁኔታ • የተሽከርካሪ ንድፍ ስሪትና መንገጫገጭ የመሸከም ሁኔታ • የፍሬን አይነትና ሁኔታ

የመከተል ርቀት

• የንፋስ ፍጥነትና አቅጣጫ

በተሽከርካሪዎ እና ከፊት ለፊት ካለው ተሽከርካሪ ጋር በደንገት ለማቆም የሚያስችል በቂ ርቀት መስጠት አለብዎት። አብዛኞቹ

የመቆም ርቀት የ U.S. ትራንስፖርት መምርያ ባከናወነው ቤተ ሙከራ መሠረት ነው። አሽከርካሪ ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ በምላሽ መስጫ 3-4 ሴኮንዶች ጊዜ መሰረት ነው።

23


ትኩረትን ያጣ አሽከርካሪ የበሽታ ምልክት

ድካም

ችግሩ

ለረጅም ርቀት ማሽከርከር የመጨጫን ስሜት ይፈጥራል ወይም ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እንዳያውቅ ያደርጋል። የመጨጫን ስሜት(drowsy) እንቅልፍ ውስጥ ለመግባት መነሻ ነው። ምን እየተፈጠረ እንዳለ አለማወቅ "Highway hypnosis" (የመንገድ ሰመመን ውስጥ መግባት) ተብሎ ይጠራል። በድግግሞሽ - የንፋስ፣ ጎማ ድምጽ እና የተረጋጋ የሞተር ህም የሚል ድምጽ ምክንያት ይከሰታል። "የመንገድ ሰመመን" ለማስወገድ የሚቀጥሉት ቅድመ ጥንቃቄዎች ይውሰዱ፦

ማሽከርከር አደገኛ ስራ ነው። በየአመቱ ከ40,000 በላይ ሰዎች በሞተር ተሽከርካሪ ግጭት ይገደላሉ እና ከ ሶስት ሚልዮን በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ይደርስባቸዋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ 50 በመቶ በላይ ግጭቶች የአሽከርካሪዎች ትኩረት ማጣት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ምክንያት ነው። የአሽከርካሪ ትኩረት ማጣት የማሽከርከር ብቃት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራል? የማሽከርከር አስተማሪዎች አንድ አሽከርካሪ በየአንዳንዱ ማይል ወደ 200 ገደማ ውሳኔዎች ይወስናል ይላሉ።

• በመጀመርያ የመጫጫን ስሜት የሆነ አወንታዊ ነገር

ይስሩ። እዛው ቁጭ ብለው ለመታገል አይሞክሩረ።

እያሽከረከሩ በአእምሮዎ ቢዝነስ አያሰሉ ወይም የቤተሰብ ችግር እያሰላሰሉ ከሆነ ለአእምሮዎ ተጨማሪ የስራ ሸክም እየጨመሩ ነው። በ55 ማይል በሰአት እየተጓዙ አይኖን ከ ሶስት እስከ አራት ሴኮንዶች ከመንገድ ከነቀሉ ተሽከርካሪዎ የአንድ እግርኳስ ሜዳ ርቀት ይጓዛል።

• በመጀመሪያ የእረፍት ወይም የመፈተሻ ቦታ ከአውራ

ጎዳናው ገለል ብለው ናፕ መውሰድ፣ ትንሽ ማፍታታት፣ እረፍት መውሰድ ወይም ከተቻለ አሽከርካሪዎች መቀያየር

• "stay-awake" (አነቃቂ) ዕፆች መሞርከዝ የለብዎትም።

የማሽከርከር ስራዎን የበለጠ አደገኛ ያደርጉታል።

ሌሎች ምክንያቶች ማለትም ድካም፣ አየር ሁኔታ፣ እና የትራፊክ ሁኔታ በማሽከርከር ብቃትዎ የትኩረት ማጣት አሉታዊ ተጽዕኖ ይጨምራሉ። ሁሉንም እተናቸዋል- ጋዜጣ እያነበቡ በመንገድ የሚያሽከረክሩ፣ ሜክአፕ የሚያደርጉ ወይም በሞባይል ስልክ በማነጋገር የተመሰጡ። እነኚህ በጣም ግልፅ የሆኑ የአሽከርካሪ ትኩረት ማጣት ምሳሌዎች ናቸው። ብዙ ሰዎች ሊያስገርም የሚችል ቢኖር ሌሎች መኪናችን ውስጥ የምንሰራቸው ከዋና የማሽከርር ስራ ትኩረታችን የሚወስዱ ብዛት ነው።

• የውስጠኛው የመኪና ክፍል በተቻለ መጠን ቀዝቃዛ

ማድረግ

• የመንገድ ሰመመን ለማሸነፍ ንቁ ለመሆን ጥረት ማድረግ • አይንዎን ከየመንገዱ አንደኛ ክፍል ወደ ሌላኛው፣ ከሩቁ

ወደ ቅርብ ግራና ቀኝ የንቀሳቅሱ። ወደፊት ቀጥ ብሎ መመልከትን ማስወገድ።

• ወንበር ላይ አቀማመጥዎን መቀያየር

• መመገብ፣ መጠጥ መጠጣት ወይም ማጨስ

• የጉዞ ጓደኛዎን ማናገር ዘይም ሬድዮ ማዳመጥ

• ሬድዮ፣ ሲዲ ወይም ቴፕ መቀየር • መላጨት፣ ሜክአፕ ማድረግ፣ ወይም በሌሎች የመቆነጃጀት

ስራዎች መሳተፍ

• ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሽከርካሪዎ ፍጥነት በትንሽ መቀያየር

አደገኛ የአሽከርካሪዎች የመጨጫን ምልክቶች

• በኃይለኛ፣ ውስብስብ፣ ስሜታዊ ወይም በሞባይል ወይም

• የአይንዎ መዘጋት ወይም በራሳቸው ግዜ ከትኩረት ውጪ

ከተሳፋሪዎች ረጅም ንግግር መሳተፍ

መሆን

• የመንገድ ካርታ፣ ጋዜጣ ማንበብ ወይም ማስታወሻ መፃፍ

• ጭንቅላትዎን ከፍ ለማድረግመቸገር

• በልጆች ወይም የቤት እንስሳት በተለይ የሚረብሹ ላይ

• በተደጋጋሚ ማዛጋት

ትኩረት መስጠት

• የሃሳብ መንከራተት፥ የተቆራረጡ ሃሳቦች ሲኖሩ

• ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጭነት ወይም ዕቃዎችን በማምጣት

• ያለፉት ጥቂት ማይላት ማሽከርከርዎን አለማስታወስ

ላይ

• መውጫ መይገድዎን መዘንጋት

• የማያውቅት ተሽከርካሪ መስታወትና ወንበርን

ሳያስተካክሉ ማሽከርከር፣ የመዝናኛ አማራጮች መምረጥ እና መብራት፣ የመታጠፍያ መብራት ምልክቶችና ዝናብ መጥረግያ መፈለግ

• ሞባይል ስልክ መጠቀም

• ከመስመርዎ ውጪ ማሽከርከርን መቀጠል • ፍጥነትዎ ተለዋዋጭ መሆን

እያሽከረከሩ ከደከምዎ ወይም ካንቀላፉ ማረፍ ከተቻለ ደግሞ አሽከርካሪ መቀየር ይመረጣል። ድካም ስሜት አእምሮን ያሰለቻል እና የመልስ ምት መስጠትን ያዘገያል ማለትም

24


ማሽከርከርን አደገኛ ያደርገዋል። ሕይወት በአደጋ ላይ መሆኑን ያስታውሱ

• ተሳፋሪ ትኩረቱን እየረበሸ ከሆነ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና

ትኩረት መስጠት

• ሁኔታውን ሳይቆጣጠሩ ማሽከርከር አይጀምሩ

ትኩረት መስጠት ደህንነቱ ለጠበቀ ማሽከርከር አስፈላጊ ነው። ማሽከርከር የሙሉ ሰአት ስራ ነው። ሁሉ ጊዜ ስለ መንገዱ እና ስለ በዙርያዎ ያሉ ተሽከርካሪዎች በንቃት መከታተል አለብዎት። ንቁ ሆነው ይቀጥሉ ምናልባት ግጭትን ቀድመው አይተው መከላከል ይችላሉ። እያሽከረከሩ ሬድዮ እያስተካከሉ፣ አያንብቡ፣ ሜክአፕ አያድርጉ፣ አይላጩ፣ ወይም ሞባይል ስልክ ከእጅ ንክኪ ነጻ ከሚያደርጉ መሳርያዎች ውጪ አይጠቀሙ። በቀጣይነት ከኃላ፣ ከፊትና በጎን በኩል ያሉ ተሽከርካሪዎችን ቦታቸውን ይከታተሉ።

ህጋዊ በሆነበት ቦታ ይጎትቱ

• ሲርብዎት ወይም ሲጠማዎት እረፍት ይውሰዱ

የመንገድ ቁጣ እና በአደገኛ ማሽከርከር የዛሬዎቹ አሽከርካሪዎች እጨመረ በሄደ መልኩ በመደበኛታት ከ20 አመት በፊት ከነበሩ የመኪና ብዛት በእጥፍ ቁጥር በሚያስተናግደው መንገድ ላይ እየተበሳጩ ነው። የስራ መግቢያና መውጫ ሰአት ትራፊክ፣ እየጨመረ እየሄደ ያለው የግንባታ ጣብያዎች(የስራ ቦታዎች) ቁጥር እና የትራፊክ ግጭት አደጋዎች ለአሽከርከሪዎች ብስጭት ጨምሯል።

ስሜት የማሽከርከር ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል

ትልቁ ጥፋተኞች የሚከተሉትን ያካትታል፦

ከተበሳጩ ወይም ከተናደዱ ከማሽከርከርዎ በፊት ለመረጋጋት የተወሰነ ጊዜ ይውሰዱ ወይም ሌላ ሰው እንዲያሽከረክር ያድርጉ። ስሜታዊ ሆነው በተናደዱበት ጊዜ ባያሽከረክሩ ይመረጣል። እያሽከረከሩ ስሜትዎን ማንፀባረቅ አደገኛ ነው።

• ጅራት መግጠም

ሞባይል ስልኮች በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ሲያሽከረክሩ ከሞባይል ስልክ እጅ ንክኪ ነጻ መሆን አለብዎት። ያስታውሱ፥ እያሽከረከሩ አጭር መልእክት መፃፍ በፍጹም አይፈቀድም።

• ደህንነቱ ያልጠበቀ የመንገድ መስመር መቀየር • ፍጥነት • ቀይ መብራትና ቁም የሚል ምልክቶችን መጣስ

የመንገድ ቁጣ እና በአደገኛ ማሽከርከርን ለመቀነስ ቀላል ደንቦች • ተጨማሪ የጉዞ ጊዜ ሁሌም መፍቀድ • መሪ ይዘው በአንድ ጊዜ ከሶስት ሰአት በላይ አይቆዩ

ለትኩረት መከፋፈል መፍትሄዎች

• በጊዜ በመቆም ግጭትን ለማስወገድ እንድያስችሎት ከፊት

ደህንነት በጠበቀ መልኩ የትኩረት መከፋፈልን ለመቆጣጠር የሚረዱ ጥቆማዎች፦

ካለው ተሽከርካሪ በቂ የሆነ ርቀት ይጠብቁ

•

• ተሽከርካሪውን ከማንቀሳቀስዎ በፊት የሁሉም ሰውና

ነገሮች ደህንነት ይጠብቁ

ሲታጠፉ ወይም መስመሮችን ሲቀይሩ ሁል ጊዜ ያሰቡትን በመብራት ምልክት ይስጡ

• ቀይ መብራትና ቁም የሚል ምልክቶች ላይ ሁሉ ጊዜ

• የአየር ንብረት መቆጣጠርያዎች፣ ሬድዮ እና የካሴትና

መሉ ለሙሉ መቆም አለብዎት። በቢጫ መብራት ማለፍ የለብዎትም

ሲዲ ማጫወቻን አስቀድመው ያዘጋጁ። የተሽከርካሪዎ የመታጠፍያ መብራት ምልክቶች፣ የዝናብ መጥረግያ እና መብራቶች የሚገኙበት ማወቅ።

• ሌሎች አሽከርካሪዎች ስርአቱን በጠበቀ መልኩ ወደ

ትራፊክ እንዲገቡ ይፍቀዱ

• ጋዜጣ፣ የቢዝነስ ሪፖርት ወይም የቀን እቅድ አውጪ

• የማለፍያ መስመርን መዝጋት የለብዎትም

ለማየት የሚያጓጓዎት ከሆነ የሚሄዱበት ቦታ እስኪደርሱ በተሽከርካሪው የኃላ እቃ ማስቀመጫ ያስቀምጥዋቸው

• የተለጠፉ የፍጥነት ወሰንን ያክብሩ • በሞባይል ስልክ፣ ማጫወጫ፣ ተሳፋሪዎች ወይም ሌላ

• መሪ ላይ ሆነው መቆነጃጀት የለብዎትም

ትኩረትን የሚከፋፍሉ ሳይሆን - ትኩረትዎን በማሽከርከር ላይ ያድርጉ

• መንገድዎን ለማቀድ እስኪያሽከረክሩ ድረስ አይጠብቁ።

ከመሄድዎ በፊት ያቅዱ። ጥቂት ቀድመው ከተነሱ ደህንነትዎን ጠብቀውና ሳይጨነቁ ያሰቡት ቦታ ይደርሳሉ።

• ጥሩምባን አሽከርካሪዎችን ወይም እግረኞችን በአደጋ ጊዜ

ብቻ ለማስጠንቀቅ ይጠቀሙ

• በስልክ ወይም ከተሳፊሪ ጋር የሚያደርጉት ውስብስብ

• ተገቢ ያልሆኑ ባህርያት ላይ አይሳተፉ ለምሳሌ ፊትን

ወይም ስሜታዊ ንግግሮችን ያሰቡት ቦታ እስኪደርሱ ያቆዩት

መኮሳተር ወይም ትህትና የጎደለው፣ የብልግና ምልክቶች

25


■ በማታ ለእግረኞች እና ለቆሙ ተሽከርካሪዎች የተለየ ጥንቃቄ ያድርጉ

• የዓይን ግንኙነትን ያስወግዱ • ሁሉ ጊዜ ለሌሎች አሽከርካሪዎች የተለመደ ጨዋነት

■ ለምንም ምክንያት መንገዱ ላይ እንዲያቆሙ

ያሳዩ። ማሽከርከርን ደህንነቱ የጠበቀ ለማድረግ፣ ያነሰ ውጥረት፣ እና የበለጠ አስደሳች ተሞክሮ ለማድረግ ሁሉም አሽከርካሪዎች የራሳቸው ድርሻ መወጣት አለባቸው።

■ በመንገዱ ላይ መቆምን አማራጭ የሌለው ከሆነ ቀይ የአደጋ ምልክት ወይም የሚያብረቀርቅ መብራት በመያዝ ይጠቀሙ

ልዩ የማሽከርከር ሁኔታዎች

■ በዝግ መስኮት ተሽከርካሪ እያሽከረከሩ ማጨስን ያቋርጡ

በማታ ማሽከርከር በማታ ማሽከርከር በቀን ከማሽከርከር የበለጠ ከባድ ሲሆን የበለጠ አደገኛም ነው። በአገሪቱ ደረጃ በግጭት ምክንያት ለሚከሰቱ የሞት አደጋ በእያንዳንዱ ማይል ማታ የሚደርሰው ሁለት ተኩል እጥፍ ቀን ከሚደርሰው ይበልጣል። በማታ አሽከርካሪ ሩቅ፣ ተሎ እና በግልጽ ማየት አይችልም እና ሁሉም ነገር ደግሞ የተለየ መልክ ነው ያለው። ከፊት ለፊት የሚመጡ ተሽከርካሪዎች የመብራት ነጸብራቅ ከፊት ምን እንዳለ ለማየት የበለጠ አዳጋች ያደርገዋል በተለይ እድሚያቸው ተለቅ ያሉ አሽከርካሪዎች። ነጸብራቁ የአይን ብሌንን እንዲጠብ ያደርገዋል እና ወደ ቀለል ያለ መብራት ሲያጋጥም ለመመለስ ጊዜ ይፈልገዋል። ከፊት ለፊት የሚመጡ የመብራት ነጸብራቅን ለማስወገድ የመንገዱ ጎኑን ወደፊትና ወደ ኃላ እና ቀጥ ብለው ፊት ለፊት መመልከት። በዚህ መልሶ የማግኘት ሙከራ ወቅት፣እይታዎ ሊቀንስ ይችላል። በማታ ማሽከርከርን በሚከተሉት መሰረት ደህንነቱን መጠበቅ ይችላሉ፦

በክረምት ማሽከርከር በክረምት ማሽከርከር የተለየ ቅድመ ጥንቃቄ ይፈልጋል። • ሰንሰለቶችን፣ የበረዶ ጎማዎች ወይም ራድያል ጎማዎችን

ይጠቀሙ። ሰንሰለቶች መጎተትና በረዶ ላይ እና በረዶ ወስጥ ለማቆም ይረዳል። ቢሆንም ግን ሰንሰለቶችን ይሁን የበረዶ ጎማዎች ወይም ራድያል ጎማዎችን በረዶ ላይ ወይም በበረዶ የሸፈነ መንገድ ላይ በተለመደ ፍጥነት ለማሽከርከር የደህንነት ዋስትና አይሆኑም። ፍጥነትዎን መቀነስ አለብዎት።

• የበረዶ ስጋት እንዳላቸው የተሰየሙ መንገዶች ላይ በረዶ

እንዳለ ሲተወጅ ሰንሰለቶችን፣ የበረዶ ጎማዎች ወይም ራድያል ጎማዎችን መጠቀም አለብዎት

• መስኮቶችን እና መብራቶችን ያፅዱ። ሁሉም የበረዶ ግግርና

የበረዶ ነጠብጣቦችን ያስወግዱ። በረዶ መፋቅያ ተሽከርካሪ ላይ ያስቀምጡ።

• ፊት ለፊት በሚያዩት ርቀት ለመቆም የሚያስችሎት ዝቅ ያለ

ፍጥነት ይጠቀሙ

• የመንገዱን ስሜት ይወቁ። በጣም በዝግታ ይጀምሩ።

• ፊት ለፊት የሚመጣ ተሽከርካሪ መብራት ላይ አይመልከቱ

ፍሬኖች ምን ያክል ማቆም እንደሚችሉ በእርጋታ ይፈትሹ። ወደ መስቀለኛ ወይም መታጠፍያ ከመጠጋትዎ በጣም ቀድመው ፍጥነት ይቀንሱ

ፈጣን ምልከታን ለሚከተሉት ይጠቀሙ፦

■ ከፊት ለፊት የሚመጣውን ተሽከርካሪ የመንገድ መስመሩን ለማወቅ

• በቂ ርቀት ይጠብቁ። በበረዶ እና ጭፍግግ ባለ የበረዶ ጊዜ

■ የራስዎን መስመር ማወቅ

በእርስዎና ከፊትዎ ካለው መኪና መካከል የሚያስፈልገው ርቀት ከወትሮው በጣም የበለጠ ነው። የበረዶ ጎማዎች፣ ራድያል ጎማዎች እና ሰንሰለትም ቢሆን በሮዶ ላይ እና ጭፍግግ ባለ በረዶ ጊዜ ይንሸራተታሉ

■ የመንገዱ የቀኝ ጥግ እርግጠኛ መሆን ■ ከፊትዎ ምንም ነገር አለመኖሩን መመልከት ■ የፊት መስታወቱ ንጹሕ ማድረግ። በንጹሕ መስታወት የሚመጡ ተሽከርካሪዎች መብራት ብዙም አያስቸግሮትም።

• ፍሬን ላይ በኀይል አይርገጡ • በፍጥነት መሪ አያዞሩ ወይም በቶሎ ፍጥነት አይቀይሩ • የድንገተኛ ኪት ተሽከርካሪ ውስጥ ያስቀምጡ።

■ በማታ መነጸርን አይጠቀሙ

የሚከተሉትን ማካተት አለበት፦

■ ንቁ እና ጠንቃቃ ይሁኑ ንጹሕና ቀዝቃዛ አየር ያግዛል።

■ አብለጭላጪ

■ ለመመርያ የመንገድ የጥግ መስመርን ይጠቀሙ የመንገድ የጥግ መስመር ከሌለ የመካከለኛው መስመር ለመመሪያ ይጠቀሙ።

■ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ኪት ■ ብርድ ልብስ

■ የአውራ ጎዳና ምልክቶችን በጥንቃቄ ያስተውሉ። በማታ ለማየት የበለጠ ያስቸግራሉ።

■ የኪት ጠጠሮች ወይም አሸዋ - ጭጋግ/በረዶ ላይ ለመጎተት 26


■ ትንሽ አካፋ

• በኃይለኛ ፍሬን አይርገጡ እና ጎማዎቹን አይቆልፉ

ጎማዎቹ መዞር ካልቻሉ ተሽከርካሪዎን ከቁጥጥርዎ ውጪ ሆኗል ማለት ነወ። ፀረ-መቆለፊያ ፍሬን ስርአት ያልተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች ፍሬን ፔዳሉን ደጋግመው ይርገጡት።

■ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎን ሙሉ ማድረግ ■ የዝናብ መጥረግያ ውሃውን ሙሉ ማድረግ በረዶ ላይ ዘይም የበረዶ ጭጋግ ላይ "completely safe" (ሙሉ ለሙሉ ደህንነቱ የጠበቀ) ፍጥነት የሚባል ነገር የለም። በክረምት አየር ሁኔታ እያንዳንዱ የከተማ ክፍል እና እያንዳንዱ የአውራ ጎዳና ክፍል በፀሐይ፣ ጥላ፣ የሚደረገው የጨው መጠንና እና በሌሎች ምክንያቶች የተለያየ ሊሆን ይችላል። አደጋ ቦታዎችን ቀድመው ያስተውሉ። ጥቁር መንገዶች(የአስፋልት አውራ ጎዳናዎች) በመቅለጥና ደግሞ በመቀዝቀዝ ምክንያት የሚፈጠር ቀጭን የበረዶ ግግርን (አልፎ አልፎ ጥቁር በረዶ በመባል ይጠራል) በቀላሉ መደበቅ ስለሚችሉ ይህንን ቀድመው ካልተጠነቀቁ ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ያስታውሱ፦ መውጫና መውረጃዎች እና ድልድዮች ከአውራ ጎዳናዎችና መንገዶች ቀድመው በረዶ ይሰራሉ። በተጨማሪም የቆፋፈረ መንገድ ማታ ላይ በረዶ ሊጋግር ወይም በየቀን ብርሃን በቀለጠው በረዶ የበረዶ ንጣፍ ሊሰራ ይችላል። ባለ አራትጎማ ድራይቭ ተሽከርካሪዎችም በረዶና የበረዶ ጭጋግ ላይ ይንሸራተታሉ። ባለ አራት-ጎማ ድራይቭ ተሽከርካሪ ሲያሽከረክሩ በደረቅ የአስፋልት መንገድ ላይ እንደሚያሽከረክሩት በረዶና የበረዶ ጭጋግ ላይ ማሽከርከር እችላለሁ ብለው እንዲያስቡ።

• መጥፍ የመንገድ ሁኔታዎች ሲኖሩ በመደበኛ ጊዜ

ከሚነሱበት ቀደም ብለው የነሱ ችኮላን ለማስወገድ

ኩርባዎች ኩርባዎች መንሸረተትና ያለ እንቅስቃሴ ጎማ ማሽከርከርን ስለሚፈጥሩ መጠንቀቅ ያስፈልጋል በተለይ የመንቀሳቀሻ ኃይል ደካማ በሆነበት ጊዜ። ኩርባወችን በእርጥብ አየር በበለጠ፣ በበረዶ ጭጋግ ጊዜ በጣም በበለጠ እና በበረዶ ግግር ጊዜ ደግሞ እጅግ በጣም በበለጠ መልኩ ይጠንቀቁ። ወደ ኩርባ ከመግባትዎ በፊት ደህንነቱ ወደ ጠበቀ ፍጥነት ቀድመው ይቀንሱ። በጥሩ አየር ሁኔታ 35 ማይል በሰአት የፍጥነት ገደብ የተለጠፈበት ኩርባ ላይ በእርጥብ አየር 20 ማይል በሰአት ብቻ ደህንነት የሚጠብቅሎት ፍጥነት ሲሆን በበረዶ ግግር እና ጭጋግ ጊዜ ደግሞ 5 ማይል በሰአት እና ከዛ በታች ብቻ ሊሆን ይችላል።

ከመንሸራተት መመለስ • አይደንግጡ እና ፈሬን አይያዙ • ወድያውኑ ወደ ሚንሸራተቱበት አቅጣጫ መሪ

ያዙሩት። የኃላ ጎማዎቹ ወደ ቀኝ መሄድ ከጀመሩ የፊት ጎማዎቹንም ወደ ቀኝ ያዙሩት። እግርዎን ከነዳጅ መስጫ ፔዳል(ማፍጠኛ) ያንሱ።

ጭጋግ ላይ ማሽከርከር Anti-Lock Brake Systems (ፀረ-መቆለፊያ ፍሬን ስርአት) ተሽከርካሪዎ መንሸራተት ከጀመረና ተሽከርካሪዎ ፀረመቆለፊያ ፍሬን ስርአት የተገጠመበት ከሆነ ፍሬኑን በኃይል ለመርገጥ አይሞክሩ። በምትኩ፥ ተሽከርካሪዎን ከመንሸራተት መልሰው ለመቆጣጠር በፍሬን ላይ የማያቋርጥ ግፊት ያድርጉ።

መንሸራተትን መከላከል

ጭጋግ የመሬት ደመና ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። የሙቀት መጠኑ ወደ የጤዛ ነጥብ(አየር የመጨረሻ ወደ ውሃ የሚቀየርበት የሙቀት መጠን) ሲወርድ ይፈጠራል እና የሚታይ ወሃ አየር ላይ እየተነነ እየቀዘቀዘ የተንጠለጠሉ የውሃ ጠብታዎች ይፈጥራል። ጭጋግ እይታን ወደ ሩብ ማይል ወይም ከዛ በታች ይቀንሳል፥ ከደገኛ የማሽከርከር ሁኔታ ይፈጥራል። ጭጋጋማ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ባያሽከረክሩ ይመረጣል ግዴታ ከሆነ ግን የሚቀጥሉ የደህንነት ቅድመጥንቃቄዎች ይጠቅማሉ፦ • መደበኛ የሚያሽከረክሩበት ፍጥነት ይቀንሱ የፊት ወይም

• ድንገት የፍጥነትና የአቅጣጫ ለውጥ አያድርጉ። በነዳጅ

የኃላ መብራት ሲያዩ ደግሞ የበለጠ ፍጥነትዎን ይቀንሱ።

መስጫ ወይም ፍሬን መያዣ ፓዳል እና በእግርዎ መካከል እንቁላል እንዳለ በማሰብ እያሽከረከሩ።

• የፊት መብራቱ የመንገዱ መሀል ላይ እየተሽከረከረ ያለ

ተሽከርካሪ ሊሆን ይችላል። የኃላ መብራት ደግሞ ከፊት ለፊት የቆመ ወይም በዝግታ መንገዱ ላይ እየተጓዘ ያለ ተሽከርካሪ ሊሆን ይችላል።

• በበረዶ ክምርና በበረዶ ላይ ለማሽከርከር ከመሞከርዎ

በፊት ደህንነቱ በጠበቀ የግል ይዞታ ቦታ ላይ ዝቅ ባለ ፍጥነት ለማቆምና መንሸራተትን ለመመለስ ይለማመዱ

• ከመቆምያ ቦታ በፊት በደንብ አስቀድመው ፍጥነት ይቀንሱ 27


• አጭር የፊት መብራት ወይም ካልዎት ልዩ የጭጋግ መብራት

ይችላሉ። ለምሳሌ ከፊት ያለው ተሽከርካሪ ቀይ ወይም ቢጫ መብራት አብርቶ ከታዘቡ መንገዱ ላይ ነገሮች ወይም ሰዎች ካሉ ይመልከቱ። ግጭት ማስወገድ የማይችሉ ከመሰልዎት፥ አይደንግጡ። ከዛ ለመሸሽ ለማዞር ይሞክሩ። ተሽከርካሪን ወይም የሆነ ነገር ፊት ለፊት ከመግጨት በጎን በኩል ለመግጨት የቻሉትን ያድርጉ። አማራጭ ካሎት ሌላ ተሽከርካሪ ከመግጨት ወደ የመንገድ ፍሳሽ መስመር(ቦይ) መሸሽ ሊመረጥ ይችላል።

• ብዙ ጊዜ ረጅም መብራቶች ተመልሰው አይንዎ ላይ

ከኃላ ከመገጨት እንዴት መዳን ይቻላል

• በማታ ሲያሽከረክሩ ለመመርያ የመንገድ ዳር መስመሮች

ከኃላ ግጭቶች በጣም የተለመዱ አይነት የሞተር ተሽከርካሪ ግጭቶች ናቸው። ከኃላ የሚከተል ተሽከርካሪ ያለው አሽከርካሪ እንደሆንዎ መጠን፥ ከኃላ የመገጨት እድልዎን እንዲቀንሱ የሚከተሉትን ያድርጉ፦

• ለድንገተኛ መቆም ይዘጋጁ • ጭጋጉ በጣም ወፍራም ከሆነ ቢያንስ ከ10 ማይል በሰአት

እንኳን መጓዝ አይችሉም፥ መሉ ለሙሉ ከአውራ ጎዳናው ይውጡ ወይም የማረፍያ ቦታ፣ መፈተሻ ቦታ ወይም ሌላ የማቆምያ ቦታ ላይ ያቁሙ ይጠቀሙ

በማንጸባረቅ አይንዎን ይሸፍናሉ

ወይም የመንገዱ የቀኝ መስመር ይጠቀሙ። እስከ መጨረሻ የአውራ ጎዳና ምልክቶችን ላያዩዋቸው ይችላሉ። ቢጫ የአስፋልት መንገድ መስመሮች በፍጹም በቀኝዎ በኩል መሆን የለበትም ግን ሀሉ ግዜ በግራዎ በኩሉ ይሆናል።

• የቁም የሚል የተሽከርካሪዎ መብራትዎን ንጹሕ

መሆናቸውን ያረጋግጡ እና እየሰሩ መሆናቸው

• ከኃላዎ ምን እየተካሄደ መሆኑን ለመገንዘብ በየጊዜው

• ቢጫ ሁለት ወደ ተቃራኒ መስመር የሚጓዝ ትራፊክ

የኃላ መስታወትን ይመልከቱ

ለመለየት የጠቅማል እና የመንገዱ የግራ በኩል ጥግን ያሳያል። ነጭ የአስፋልት መንገድ መስመር ቀለም የመንገዱ የቀኝ በኩል ጥግን ያሳያል።

• የኃላ መስታወቱ ንጹሕ እና ከጉም ነጻ መሆን አለበት

የውጭ መስታወቶች አጋዦች ናቸው።

• ችኮላን ለማስወገድ በደንብ ቀድመው ይነሱ

• በደንብ ቀድመው ምልክት ይስጡ ለመቆም፣ ለመታጠፍ

በመከላከል ያሽከረከሩ

• ፍጥነትን ቀስ በቀስ ይቀንሱ፣ በድንገት ሳይሆን

ሌላ አሽከርካር ማድረግ የሚጠበቅበትን ያደረጋል ብለው እንዲያምኑት ወይም እርስዎ በሱ/ሷ ቦታ ሆነው ሊያደርጉት የሚችሉትን ያደርጋል ብለው እንዳያስቡ። ለምሳሌ የሰውየው የመታጠፍያ መብራት ምልክት ስለበራ አሽከርካሪው ይታጠፋል ብለው እንዳይገምቱ። አሽከርካሪው የመታጠፍያ መብራት ምልክቱ ወደ ሚያሳየው አቅጣጫ ካልታጠፈ ቀድመው ያስቡ ወይም ምን ማድረግ እንዳለብዎ ይወስኑ። ቁም የሚል ምልክት ወይም ቀይ የትራፊክ መብራት ሲኖር ሁሉም አሽከርካሪ ይቆማል ብለው አይገምቱ። የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ቁም የሚል ምልክት ወይም ቀይ የትራፊክ መብራትን እያወቁ ጥሰው ያልፋሉ። ሲያሽከረክሩ ያለማቋረጥ "የመውጫ መስመርን" ያስቡ። ከጥቂጥ ሳምንታት ልምምድ በኃላ ይህ "ሁለተኛ ተፈጥሮ" ይሆናል። ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም ዝግጁ የሆነ የድርጊት መርሀግብር አልዎት። ለምሳሌ፥ ከፊት የሚመጣ መኪና ለማለፍ ከጀመረ እና አሽከርካሪው ወደ ትክክለኛ መስመሩ የሚመለስበት በቂ ሁኔታ የለውም ብለው ካሰቡ ፍጥነት ቀንሰው የመንገዱ ዳር እና በቅርብ ያለው ቦታ ይመረምራሉ። በዚህ መሰረት አስፈላጊ ከሆነ ወዴት መሄድ እንዳለብዎት ያውቃሉ። በሚችሉት የርቀት መጠን ይመልከቱ። በዚህ መሰረት ከፊት ለፊት ያለው አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በድንገት ሊያጠማዝዝበት ወይም በድንገት ሊያስቆመው የሚችለው ችግር በመፈጠር ላይ መሆኑን ሊያዩ

እና መስመር ለመቀየር

• ከትራፊክ ፍጥነት ጋር ይቀጥሉ • የሆነ አሽከርካሪ ተጠግቶ ከተከተልዎ ፍጥነት ቀንሰው

እንድያልፍ ያድርጉ

የሀገር-አቋራጭ እና ሌላ የመስመር-ገደብ አውራ ጎዳናዎች የሀገር-አቋራጭ አውራ ጎዳናዎችን እንዴት በትክክል መጠቀም እንዳለብዎት ካወቁ መሄድ ወደሚፈልጉት በቶሎ፣ በቀላልና ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ያደርስዋችኋል። ነገርግን የአውራ ጎዳናዎቹ የደህንነት መጠበቅያ ልምዶችን ማወቅ ያስፈልጋል።

ከመጀመርዎ በፊት ጎማዎቹ ለከፍተኛ ፍጥነት በሚሆን ሁኔታ ላይ ናቸው? በቂ የሆነ ዘይትና ማቀዝቀዣ ውሃ ይዘዋል? ተሽከርካሪዎ አደገኛ ሊሆን የሚችል የቴክኒክ ችግር አለበት? ይህ ጉዞ ለማድረግ በጥሩ ሁኔታ መሆንዎ ይሰማዎታል? በቂ ነዳጅ አልዎት? በቂ እንቅልፍ ተኝተዋል? የሚጓዙበት መስመር ቀድመው ያዘጋጁ እና ከመጀመርዎ በፊት ይገምግሙ። እነዚህ ደህንነቱ የጠበቀና አስደሳች ጉዞ ያደርጉላቸዋል።

ወደ ሀገር-አቋራጭ/አውራ ጎዳና ሲገቡ 28


የሀገር-አቋራጭ እና ሌላ የመስመር-ገደብ አውራ ጎዳናዎች የሚገቡት በመውጫ/መውረጃ እና በማፍጠኛ ወይም ፍጥነት መቀነሻ መስመር ነው። የመግቢያ መውጫ/መውረጃ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ያስገባዎታል እና የማፍጠኛ መስመሩ ደግሞ የትራፊኩ ፍጥነት ጋር ቶሎ ለመድረስ ይረዳል። ወደ ሀገር-አቋራጭ ሲገቡ መግብያ እና ሀገር-አቋራጩን የሚከፍሉ ያልተቆራረጡ የመስመር ቀለሞች መታለፍ የለባቸውም። አጭር የሀገር-አቋራጭ መግቢያ ከሆነና የማፍጠኛ መስመር ከሌለው የትራፊክ ክፍተት ሲያገኙ ብቻ መግቢያው ላይ ፍጥነት ይጨምሩ። በአጠቃላይ፥ ወደ ሀገር-አቋራጭ ከመግባትዎ በፊት የትራፊክ ክፍተት እስኪያገኙ አቁመው ይጠብቁ። ወደ ሀገር-አቋራጭ በግራ በኩል ሲገቡ በመስታወትዎ የሚያዩትና በትከሻዎ በላይ ሲመለከቱ የሚያዩትን ያወዳድሩ።

ከሀገር-አቋራጭ/አውራ ጎዳና ሲወጡ መውጫው የመንገዱ በቀኝ በኩል ከሆነ መውጫ ቦታውን ከመድረስዎ በፊት በደንብ ቀድመው ወደ ቀኙ መስመር ይውጡ። ዋናው አውራ ጎዳና ላይ ፍጥነት አይቀንሱ። ፍጥነት መቀነሻ መስመር እንደገቡ ፍጥነት ይቀንሱ እና እስከ መውጫ መንገዱ ድረስ ፍጥነት መቀነስዎን ይቀጥሉ። ወደ ተለጠፈው የመውጫው የፍጥነት ገደብ ፍጥነትዎን ይቀንሱ ካልሆነ ኩርባዎች ላይ ይቸገራሉ። በተሳሳተ መውጫ ከሀገር-አቋራጩ ከወጡ ከመውጫ መስመሩ እስኪወጡ ድረስ ጠቅልለው ከወጡ በኃላ ተመልሰው የሚገቡበትን መስመር ይመልከቱ።

በሀገር-አቋራጭ/አውራ ጎዳና መስመር መቀየርና ማለፍ

አለብዎት። • ወደ ሌላ መስመር ከመቀየርዎ በፊት በውጪኛው

መስታወት ወይም ፊትዎን በማዞር የኃላ ቀኝና የኃላ ግራን ይመልከቱ።

• ከፊት ያለ ተሽከርካሪ ወደ የማይታዮት ቦታ በፍጹም

እያሽከረከሩ

አደባባዮች አደባባዮች መሃል ላይ ደሴት ያለው አንድና ከዛ በላይ መስመሮች ያሉት ክብ መስቀለኛ ነው። ወደ አደባባይ የሚገቡ አስፋልት መንገዶች ቅድምያ ስጥ የሚል ምልክት ያላቸው እና አስፋልቱ ላይ ቅድምያ ስጥ የሚል ቀለምም ሊኖራቸው ይችላል። አሽከርካሪዎች ለምልክቶች ትኩረት ሊሰጡና ሊያከብሩ ይገባል። አሽከርካሪዎች ወደ አደባባይ ከገቡ በኃላ የሰአት ተቃራኒ አቅጣጫ መጓዝ አለባቸው። ወደ አደባባይ ሲጠጉ ፍጥነትዎን ይቀንሱ። ወደ ሚሄዱበት ለማሳየት የመታጠፍያ የመብራት ምልክቶችን ይጠቀሙ። ወደ ቀኝ የሚታጠፉ ከሆነ ወደ አደባባይ ሲገቡ በቀኝ በኩል ይቆዩ። ቀጥ ብለው መሄድን ካሰቡ በፈለጉት መስመር መቆየት ይችላሉ(ባለ ሁለት መስመር ክብ መስቀለኛ ከሆነ)። ወደ ግራ የሚታጠፉ ከሆነ ወደ አደባባይ ሲገቡ በግራ በኩል ይቆዩ። አደባባይ ከደረሱ የሞተርሳይክል፣ እግረኞች እና ብስክሌተኞች መስመር ቅድሚያ ይስጡ። አደባባይ ውስጥ ላሉ ማናቸውም ተሽከርካሪዎችንም ቅድሚያ ይስጡ። አልፎአልፎ የመግቢያ ቦታ በቁም ወይም ቅድምያ ስጥ የሚል ምልክት ወይም የትራፊክ

በሀገር-አቋራጭ እና ሌላ የመስመር-ገደብ አውራ ጎዳናዎች ላይ ባለው ከፍተኛ ፍጥነት ምክንያት በጥንቃቄ መስመር መቀየርና ማለፍ አስፈላጊ ነው። እርስዎን የሚረዱ ጥቂት ጥቆማዎች የሚከተሉ ናቸው፦ • በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ በግራም በቀኝም ማለፍ

ህጋዊ ነው ነገር ግን ቀስ ብለው የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ቀኙ መስመር ላይ መሆን አለባቸው። ስለዚህ በአብዛኛው የሚያልፉት በግራ በኩል ይሆናል። በተጨማሪ በመንገዱ የውጪ ክፍል ማለፍ አይቻልም።

• ደህንነቱ የጠበቀ ማለፍ በሁለቱም አሽከርካሪዎች ትብብር

ይወሰናል። እየታለፉ ፍጥነት እንዳይጨምሩ።

• በከፍተኛ ፍጥነት ላይ የሚደረጉ ፈጣን እንቅስቃሴዎች

ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዳለፉ ቶሎ ወደእዛኛው መስመር አይመለሱ። መስመር ከመቀየርዎ በፊት የተሽከርካሪው መብራት በየኃላ መስታወትዎ መየት መቻል አለብዎት።

• መስመር ሲቀይሩ ሁሉ ጊዜ ምልክት ይስጡ • በመስታወት የማይታዩ ቦታዎች በትከሻዎ እየዞሩ ማየት 29


መብራት ምልክት ቁጥጥር ይደረጋል። መንገዱ ኮፍት ከሆነ ወደ አደባባዩ መግባት ይችላሉ።

• የድንገተኛ ችግር ጊዜ ፍሬን(ማቆምያ) ፍሬን ያጠቀሙ

አደባባይ ውስጥ ሲሆኑ ለመውጣት እስኪዘጋጁ በመስመርዎ ይቆዩ። የተሽከርካሪዎ የቀኝ መታጠፍያ መብራት በመጠቀም በዙርያዎ ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ምን ማድረግ እንዳሰቡ ያሳውቁ።

• ካስፈለገ የጎማዎቹ ጎን ከመንገድ ጠርዝ ጋር ያፋፍቁት።

• ከቻሉ ወደ ከባድ ማርሽ ይቀይሩ

ትላልቅ ተሽከርካሪዎችን አይቅደሙ። ትላልቅ ተሽከርካሪዎች(ለምሳሌ የጭነት መኪናና አውቶብሶች) ሲገቡ ወይም አደባባይ ውስጥ እያሉ አሰፍተው ሊዞሩ ይችላሉ። ለሚያሳዩት የመታጠፍያ መብራት ምልክቶች ትኩረት ያድርጉ እና ብዙ ክፍተት ይሰጧቸው ምክንያቱም ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ሊሸፍኑ ስለሚችሉ። ትላልቅ ተሽከርካሪዎች የመንገዱ ሙሉ ስፋት መጠቀም ሊያስፈልጋቸው ይችላል ወደ የሚጠጠሙ የአደባባይ መግቢያዎችን ጨምሩ።

በፀረ-መቆለፍያ የፍሬን ስርአቶች (ABS) ፍሬን መያዝ ጎማዎች ፍሬን በሚያዝበት ወቅት እንዳይቆልፉ የተሰራ ነው። የተሽከርካሪው ኮምፒውተር አንድ ወይም ከዛ በላይ ድጎማዎች መቆለፍ መጀመራቸውን ሲያውቅ ABS ፍሬኑን አሽከርካሪው ደጋግሞ ሊጫነው ከሚችለው ፍጥነት በላይ እየተጫነ እንዳይቆልፍ ይከላከላል። ABS ስራ ሲጀምር ከፍሬኑ የሚጮህ ድምጽ ይሰማል እና ደግሞ የፍሬን ፔዳሉ እግርዎ ስር ይንቀጠቀጣል። ሁሉም አሽከርካሪዎች ማድረግ ያለባቸው የፍሬን ፔዳሉን በደንብ ረግጠው መያዝና መሪውን መሄድ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ማዞር። የABS ኮምፒውተሩ መንሸራተትን ለመከላከል የትኛው ጎማ ፍሬን እየያዘ እንደሆነ ይቆጣጠራል።

በአደባባይ የሚዞሩ ወይም ከእርስዎ ቀጥሎ ያለው መስመር ወይም ከኃላዎ ሳያዩ መስመር እንዳይቀይሩ። በጎን መስታወት ወይም በኃላ መስታወት ሊታይ የማይችል ቦታ ላይ ተሽከርካሪዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠብቁ። የማይታይ ቦታ ላይ ፈጥነው ዞረው በትከሻዎ በማየት ምንም ተሽከርካሪዎች አለመኖራቸውን ያረጋግጡ።

ABS እየሰራ እግሮን ለማንሳት ቢፈታተኖትም አለመልቀቅ። የፍሬን ፔዳሉ ላይ የማያቋርጥ ግፊት ይጫኑ። አሽከርካሪዎች የማያቋርጥ ግፊት መስጠት ማቆም ወይም ፍሬንን ደጋግመው መጫን ABS ስራው እንድያቋርጥ ወይም እንደሚያጠፋው ማወቅ አለባቸው።

ማቆም የአውራ ጎዳና የመሄጃ ክፍሉ ላይ መቆም ክልክል ነው። ተሽከርካሪዎ መንቀሳቀስ ወይም ሌላ ችግር ውስጥ ከሆነ ከመንገዱ ውጪ ያለው ክፍል ላይ ማቆም ይቻላል። ይህ ሲያጋጥምዎ ኮፈኑን ያንሱ ወይም ነጭ ጨርቅ የግራ በር መክፈቻ ላይ ወይም ሬድዮ አንቴና ላይ ይሰሩ። ከተሽከርካሪዎ ጋር ይቆዩ፥ በሀገር-አቋራጭ እና ሌላ የመስመር-ገደብ አውራ ጎዳናዎች ላይ በእግር መንቀሳቀስ አይቻልም።

ወደ ኃላ መጓዝ በማነኛውም አውራ ጎዳና በማንኛውም አይነት ሁኔታ ወደ ኃላ ማሽከርከር አይቻልም። የአሽከርካሪዎች ወደ ኃላ ሲያሽከረክሩ ከሚፈፅሙት በጣም የተለመደ ስህተት የኃላውን ሁለቱም መስመር ማየት አለመቻል ነው። መስታወቶች ሙሉ እይታን አይሰጡም። የሚቻለውን ያክል ለማየት ሰውነትዎንና ጭንቅላትዎን ወደ ቀኝ በማዞር በኃለኛው መስኮት ይመልከቱ። በዝግታ ወደ ኃላ ያሽከርክሩ እና በሁለቱም በኩል በፍጥነት እግረኞችና የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ይመልከቱ።

አሽከርካሪዎች ABS መጠቀም መለማመድና ተሽከርካሪዎ በድንገት ወይም በአደጋ ጊዜ ፍሬን እንዴት እንደሚይዝ መለመድ አለባቸው። ይህንን ለመለማመድ የመኪና ማቆምያ ቦታ ተመራጭ ነው። እርጥብ ፍሬኖች በጥልቀ ውሃ ካሽከረከሩ በኃላ ፍሬንዎን መሞከር አለብዎት። ወደ አንዱ ክፍል ሊጎትቱ ወይም ጠቅላላ ላይዙ ይችላሉ። ፍሬኖቹን ለማድረቅ መኪናዎን ወደ ከባድ ማርሽ በመቀየር በዝግታ እያሽከረከሩ ቀለል አድርገው ፍሬን ይያዙ። ፍሬኑን በየ200 ጫማ ይሞክሩት ወደ መደበኛ ስራው እስኪመለስ ፍሬን መያዙን ይቀጥሉ። የመስታወት ዝናብ መጥረጊያ ብልሽት በመጥፎ አየር ሁኔታ የመስታወት የዝናብ መጥረግያው ከተበላሸ መስኮቱን ከፍተው ጭንቅላትዎን በመስኮቱ ወጣ አድርገው ተሽከርካሪዎን ከመንገዱ ውጪ ወዳለው ክፍል ያሽከርክሩ እና ማቆምደ

ድንገተኛ ችግሮች

የፍጥነት መቆጣጠሪያ ፔዳል እንጨቶች

የፍሬን ብልሽት

• በእግርዎ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ፔዳሉን በሀይለኛ ይምቱት

የፍሬን ፔዳሉን ደጋግሞ መጫን(ABS ስርአት ለሌላቸው)። ይህ ፍሬኑን ካላስተካከለው፣

• ወደ ዜሮ ይመልሱ

30


• ፍሬን ይያዙ

• የሞተር እሳት ከሆነ በሚችሉት ፍጥነት ሞተሩን ያጥፉ።

ማስወገድ የሚችሉ ከሆነ ኮፈኑን አይክፈቱት። የእሳት ማጥፊያውን በአየር ማስገቢያ ሳጥን፣ ራድያተርና ከተሽከርካሪው የታችኛው ክፍል ይርጩበት።

• ከመንገዱ ይውጡ እና ያቁሙ

የመሪ ብልሽት መሪውን በድንገት ከቁጥጥርዎ ውጪ ከሆነ ፍጥነትን ይቀንሱ ተሽከርካሪው ሚዛኑን ጠብቆ ከቀጠለ የመንገድ መስመርዎ ላይ በመቆየት ፍጥነት እስኪቀንስ ይጠብቁ ከዛ አቅጣጫ እንዳይቀይር ፍሬን ቀስ እያሉ መያዝ። ተሽከርካሪዎ ከመንገድ መውጣት ከጀመረ ወይም ወደ እግረኛ ወይም ወደ ሌላ ተሽከርካሪ መሄድ ከጀመረ ፈጥነው በሚችሉት የግፊት መጠን ተጭነው ፍሬን ይያዙ። የመሪ እና መቆለፍያ መሳርያ - መቆጣጠር አለመቻል

• ለ ጭነት እሳት በሚኒባስ ወይም ተሳቢ ሳጥን፥ በሮችን

እንደተዘጉ ያቆዩ በተለይ ጭነቱ አደገኛ እቃዎች የያዘ ከሆነ። የሚኒባሱ በር መክፈት ለእሳቱ ተጨማሪ ኦክስጅን መስጠት ሲሆን እሳቱን ያቀጣጣለዋል።

እሳቱን ማጥፋት እሳትን ስያጠፉ መከተል ያለባቸው ደንቦች የሚከተሉት ናቸው፦ • የእሳት ማጥፊያው እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ። ለመጠቀም

ተሽከርካሪው እንቅስቃሴ ላይ እያለ የተሽከርካሪው ቁልፍ "Lock" ወደሚለው ቦታ በፍጹም አያዙሩ። ይህ መሪውን እንዲቆልፍ ያደርገዋል እና መሪውን ማዞር ከሞከሩ ተሽከርካሪውን ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል።

ከመፈለግዎ በፊት በእሳት ማጥፍያው ላይ የታተመው መመርያዎችን ያጥኑ።

• ማጥፊያውን ሲጠቀሙ በቻሉት ርቀት መጠን ከእሳቱ

ይራቁ

የፊት መብራት ብልሽት

• ነበልባሉ ላይ ሳይሆን የእሳቱ መነሻ ወይም መሰረት ላይ

አውራ ጎዳናው መብራት ካለው ከመንገዱ በፍጥነትና ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ወደ የመንገዱ ውጪ ያለው ክፍል ወይም ሌላ የተገኘ ቦታ ይውጡ። አውራ ጎዳናው ጨለማ ከሆነ የማቆምያ መብራት፣ የመታጠፍያ ምልክት መብራቶች ወይም የአደጋ አብለጭላጪዎችን ይሞክሩ እና ከመንገዱ ይውጡ። ሀሉም መብራቶች ከተበላሹ ፍጥነት በመቀነስ ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ከመንገዱ እስኪወጡ መንገዱ ላይ ይጠብቁ።

ያነጣጥሩ

• በንፋስ በኩል ይቁሙ ንፋሱ ነበልባሉን ወደ እርስዎ

ሳይሆን የማጥፊያው ንጥረነገሮች ወደ እሳቱ እንዲወስድ ያድርጉ።

• የእተቀጣጠለ የነበረውን ማነኛውም ነገር እስኪጠፉ

ይቀጥሉ። ጥስ ወይም ነበልባል የለም ማለት እሳቱ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል ወይም ድጋሚ አይጀምርም ማለት አይደለም።

ተሽከርካሪ ላይ እሳት እሳትን እንዴት ማጥፋት እንዲቻል ማወቅ ጠቃሚ ነው። እሳት ምን ማድረግ እንዳለባቸው በማያውቁ አሽከርካሪዎች ሲባባስ ይታያል። እሳት በሚያጋጥምበት ጊዜ መከተል ያለበት ሂደቶች፦ ከመንገድ መውጣት የመጀመርያው እርምጃ ተሽከርካሪውን ከመንገድ ማውጣትና ማቆም ነው። ይህን ሲያደርጉ፦ • ክፍት ቦታ ላይ ማቆም፣ ከህንፃዎች፣ ዛፎች መራቅ፣ ሌሎች

ተሽከርካሪዎችን ወይም ማንኛውም በእሳት ሊያያዝ የሚችል ማሸሽ።

• ወደ ጥገና ቦታ መውሰድ አይውሰዱ። • ሞባይል ስልክ ካልዎት ተጠቅመው ችግርዎንና ያሉበት ቦታ

ለፖሊስ ያሳውቁ።

እሳቱ እንዳይስፋፋ ይከላከሉ እሳቱን ለማጥፋት ከመሞከርዎ በፊት እየተስፋፋ አለመሆኑን ያረጋገጡ።

• የሚያደርጉትን የሚያውቁ ሲሆንና ለማድረግ ደህንነቱ

የጠበቀ ከሆነ ብቻ እሳቱን ለማጥፋት ይሞክሩ።

በመስመርዎ ተሽከርካሪ ሲመጣ ተሽከርካሪ ወደ እርስዎ በመስመርዎ እየመጣ እንደሆነ ከተመለከቱ፣ ወደ ቀኝ ይውጡ፣ ፍጥነት ይቀንሱ፣ ጥሩንባ ያሰሙ እና የፊት መብራት ብልጭታ ያሳዩ። ተሽከርካሪው ወደ ተወው መስመር እንዳይታጠፉ ምክንያቱም አሽከርካሪው ስህተቱን በመገንዘቡ ወደ ትክክለኛ መስመር ሊመለስ ይችላል።

በባቡር ሐዲድ ትራኮች ላይ መቆም ለባቡሮች በሁለቱንም መስመር ይመልከቱ። እየመጣ ያለ ባቡር ካለ፥ ከተሽከርካሪው ይውጡ ከግጭቱ በሚፈናጠሩ ፍርስራሾች ከመመታት ለመዳን በሐዲዱ ጎን ለጎን ወደ ባቡሩ አቅጣጫ ይሩጡ።

እያሽከረከሩ ከመንገድ መውጣት 31


እያሽከረከሩ ከመንገድ ከወጡ ወይም እንዲወጡ ከተገደዱ፥ እነዚህ ደንቦች ሕይወትዎን ሊያድኑ ይችላሉ፦

የወጣለት ጎማዎች የአውቶቡስ የፊት ጎማ ላይ መጠቀም አይቻልም

• አይደናገጡ

የጎማ እና የቸርኬ ችግር

• እግርዎን ከነዳጅ መስጫ ፔዳል ያንሱ

• ችግር ያለባቸው ጎማ ወይም ቸርኬ ግጭት ይፈጥራሉ

• ፍሬን ላይ አይጨናነቁ። ፍሬንን በጥንቃቄ ይያዙ ወይም

• የታጠፈ ወይም የተሰነጠቀ ቸርኬ የጎማ አየር እንዲቀንስ

ጠቅልለው አይያዙ

ወይም እንዲወጣ ያደርጋል

• መሪውን አጥብቀው ይያዙ ምክንያቱም ጎማ ላይ

• የጎማ ቡሎኖች(ኮሎኔት) ዝገት ማለት ቡሎኖቹ ላልቷል

በሚፈጠሩ ወጣ ያሉ ምቶች መሪው ከእጅዎ እንዲወጣ ስለሚያደርግ

ሊሆን ይችላል - መጥበቁን ያረጋግጡ

• ጎማ ከተቀየረ በኃላ ትንሽ ከተሽከረከረ በኃላ የቡሎኖቹ

• ተሽከርካሪውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር እስኪችሉ፣

መጥበቅ ድጋሚ ያረጋገጡ

(ፍጥነት ወደ 15 ማይል በሰአት ወይም ከዛ በታች ሲወርድ) እና ከኃላዎና ከጎንዎ ትሪፊክን እስኪመለከቱ ድረስ ወደ መንገዱ ለመመለስ አይሞክሩ። ከዛ በኃላ ጎማዎቹን ወደ መንገዱ በደንብ ያዙሩ። በመንገዱ መሃል ለመሃል ወይም በተቃራኒ መስመር አለሜድዎን ያረጋግጡ።

• የጠፉ ማሰርያዎች፣ አካፋዮች፣ መሰንጠቅያዎች ወይም

ማጥበቅያዎች አደጋ ማለት ነው

• ተመሳሳይ ያልሆኑ፣ የታጠፉ፣ ወይም የተሰነጠቁ የቸርኬ

ቀለበቶች ከደገኞች ናቸው

• የብየዳ ጥገና ያላቸው ጎማዎች ወይም ቸርኬዎች

ራምብል ስትሪፕስ(ፍጥነት መቀነሻ ሸንተረሮች)

ደህንነታቸው የጠበቁ አይደሉም ራምብል ስትሪፕስ መንገድ ላይ የአጭር ርቀት ሸንተረሮች ሲሆኑ የጎማ ፍንዳታዎች ጎማዎቹ በላያቸው ሲሽከረከሩ በሚፈጥሩት ድምጽ የሚያነቁ ናቸው። ራምብል ስትሪፕስ አደጋ ሊኖራቸው የሚችሉ ለምሳሌ የጎማ ፍንዳታዎች ለስለስ ባለ ከመንገድ ውጪ ያለ ክፍል ላይ አደገኛ መስቀልኛ ወይም ወደ መንገዱ ጠርዝ ተጠግተው እንደመሽከርከር ማለት ነው ጎማዎ ከፈነዳ፦ ሲያሽከረክሩ ያስጠነቅቃሉ። • ፍሬን አይያዙ

ጎማዎች

• መሪውን አጥብቀው ይያዙ

የጎማ ችግሮችን ይመልከቱ። ችግር ባላቸው ጎማዎኝ ማሽከርከር አደገኛ ነው። ይመልከቱ፦

• ወደ ቀኝ መታጠፍያ ምልክትን በማብራት ተሽከርካሪውን

ደህንነትን በጠበቀ መልኩ ወደ መንገዱ የውጪ ክፍል ያውጡ

• በጣም የተበላ ጎማ። በፊት ጎማዎች በእያንዳንዱ ዋና

ሸንተረር ቢያንስ 4/32 ኢንች የመርገጫ ጥልቀት ያስፈልጋል። በሌሎች ድጎማዎች ደግሞ 2/32 ኢንች ያስፈልጋል። ምንም እይነት ጨርቅ በመረገጫው ወይም በጎን መታየት የለበትም።

• ፍጥነት ቀንሰው ከመንገዱ ውጪ ሊያሽከረክሩበት

የሚችሉት የተሻለ ቦታ ይመልከቱ

• ተሽከርካሪው እስኪቆም ድረስ ይጠብቁ

• ቀዳዳ ወይም ሌላ ጉዳት

በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሞተር

• የመርገጫ መለያየት/ክፍተት

• የነዳጅ መስጫ ፔዳሉይ ረግጠው ይያዙ

• እርስ በእርሳቸው ወይም ከሌላ የተሽከርካሪው ክፍል

• ቁልፉ ለማስነሳት አዙረው ለጥቂት ጊዜ ይያዙት(10 - 15

• ተመሳሳይ ያልሆነ የጎማ መጠኖች

• ሞተሩ ሲነሳ የነዳጅ መስጫ ፔዳሉን ይልቀቁት

• ራድያልና ቢያዝ-ፕላይ የጎማ አይነቶችን አንድ አክስል ላይ

• የነዳጅ ፔዳሉን ደጋግመው አይርገጡት፤ ጎርፉን የባሰ

• የተቆራረጡ ወይም የተሰነጣጠቁ የጎማ አየር መሙያ

የተበላሸ ተሽከርካሪ

ሴኮንዶች)

ንክኪ ያላቸው ጥንድ ድጎማዎች

ያደርገዋል

መጠቀም ክዳኖች

• ከተቻለ አራቱም ጎማዎች ከመንገዱ ያውጡ

• እንደገና የጎደጎዱ፣ እንደገና የተሸፈኑ፣ እንደገና ጥርስ

32


ቦታው መግባት የለብዎትም። ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ይታጠፉ ምክንያቱም ወደ ቦታው ማሽከርከር የትራፊክ ደንብን የሚጻረር ስለሆነ።

• የማቆምያ መብራቶች ወይም የአደጋ ብልጭታ መብራቶች

እና ካለ አብለጭላጪ፣ ብልጭ ድርግም የሚሉ ቀይ መብራቶች ያብሩ ወይም አንጸባራቂ ሶስት ማእዘን ያስቀምጡ

• መሃረብ ወይም ነጭ ጨርቅ የሬድዮ አንቴና ወይም የግራ

በር እጀታ ላይ ማሰር እና/ወይም ኮፈኑን ማንሳት

(ራይት-ኦፍ-ወይ) ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች ህጎች ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎችን ያስተዳድራል ነገር ግን እነዚህ ህጎች ከደህንነት በላይ አያስቀምጣቸውም። ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች ማለት አንዱ ተሽከርካሪ ወይም እግረኛ አውራ ጎዳና ላይ በህጋዊ መሰረት ከሌላው ተሽከርካሪ ወይም እግረኛ ቅድሞ የሚገባበት ማለት ነው። ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታ ካሎትና ሌሎችም ሲፈቅዱ ወድያው ይቀጥሉ። • ነገር ግን መስቀለኛ ላይ ቁም የሚል፣ ቅድሚያ

ስጥ የሚልና የትራፊክ መብራት ምልክቶችን ማክበር አለብዎት።

• ወደ መስቀለኛ ከሌላ ተሽከርካሪ በኃላ ከገቡ

ቅድምያ መስጠት አለብዎት።

• መስቀለኛ ላይ ወደ ግራ ሊታጠፉ ከሆነ

ወይም ወደ ሰፈር መንገድ፣ የግል መንገድ ወይም ወደ ቤት መግቢያ መንገድ ለመታጠፍ ለሌሎች እግረኞች እና ተሽከርካሪዎች ቅድምያ ይስጡ ለመታጠፍ ደህንነቱ የጠበቀ እስኪሆን ድረስ።

የእግረኛች ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች የትራፊክ መኮንኖች ወይም የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ትራፊክን ከሚቆጣጠሩ በስተቀር ሁሉም እግረኞች ከተማ ውስጥ ባሉ የመንገድ ማቋረጫዎች ላይ የቅድሚያ መብት አላቸው። እግረኛች ቀይ መብራት ወይም የትራፊክ ፖሊስ ተእዛዝ በመፃረር ካልሆነ በስተቀር መቋረጫ ምልክት የተደረገባቸውም ሆነ ምልክት የሌላቸው የእግረኛ መቋረጫዎች ሲገቡ ቅድሚያ መብት አላቸው።

የእግረኛ መብራት ምልክቶች በአንዳንድ በተለይ ሥራ በሚበዛባቸው መገናኛዎች፣ የእግረኛ ምልክቶች ከመደበኛ የትራፊክ ምልክቶች ጋር ተጣምረው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። አሽከርካሪዎች መደበኛውን የትራፊክ ምልክቶችን መታዘዝ አለባቸው። እግረኞች WALK እና DON'T WALK ምልክቶችን መታዘዝ አለባቸው፡፡

በእግረኛ መንገዶች መቋረጫ መሻገር እግረኛ በእግረኛ በማቋረጫ መንገድ ሲሻገር የተሽከርካሪ አሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መቆም አለበት፡፡ ይህም፡• ተሽከርካሪው በሚጓዝበት የመንገዱን ግማሽ ላይ፤ ወይም • በሌላኛው የመንገዱ ግማሽ ላይ ካለው አጎራባች

መስመር በቅርበት ሲጠጋ አደጋ ላይ እንዲወድቁ የሚያደረግ ከሆነ። ማነኛውም ተሽከርካሪ ምልክት የተደረገበትም ያልተደረገበትም በእግረኛ መቋረጫ ላይ እግረኛ ለማሻገር በሚቆምበት ጊዜ ከኃላ የሚመጣ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የቆመውን መኪና ማለፍ የለበትም። አንድ እግረኛ በድንገት የመንገድ ጠርዝ ወይም ሌላ የደህንነት ቦታ ትቶ መሄድ ወይም ወደ ተሽከርካሪው መንገድ መራመድ ወይም መሮጥ የለበትም ምክንያቱም በጣም ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ ቅድሚያ መስጠት አይቻልም።

• ከግል መንገድ ወይም ከቤት መግቢያ መንገድ ወደ የህዝብ

መንገድ ወይም አውራ ጎዳና ሲገቡ ቆመው ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች እና እግረኞች ቅድሚያ መስጠት አለብዎት።

• ለእርስዎ አረንጓዴ መብራት ቢበራም እንኳን አሁንም

ለእግረኛች እና መስቀለኛ ውስጥ ላሉ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት አለብዎት። ቀይ መብራት የሚጥሱን ይመልከቱ።

የተፈቀደላቸው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ለምሳሌ የፖሊስ መኪኖች፣ አንቡላንሶች እና የእሳት አደጋ ምልክት የድምጽ(ሳይረን) ወይም የሚታይ(በብልጭ ድርግም የሚል መብራት) ሲሰጡ የቅድሚያ ማለፍ መብት አላቸው። ተሽከርካሪ እየመጣ እንደሆነ ሲሰሙ ወይም ሲያዩ ወድያውኑ ወ መንገድ ጠርዝ በማሽከርከር ይቁሙ፥ የአደጋ ተሽከርካሪው እስኪያልፍ ድረስ በዛው ይቁሙ። አደጋን ለመቆጣጠር በመሳተፍ ላይ ያለ ማነኛውም የእሳት አደጋ መሳርያ ከ500 ጫማ በታች መከተል የለብዎትም። የእሳት አደጋ ሞተሮች ወይም የአደጋ ተሽከርካሪዎች ወደ ቆሙበት ቦታ ከተጠጉ ወደ

ከእግረኛ መንገዶች መቋረጫ ውጪ ባሉ ቦታዎች መሻገር የማይመከር ቢሆንም እግረኛ ከእግረኛ መቋረጫ ውጭ ያለውን መንገድ ላይ በሚሻገርበት ጊዜ ተሽከርካሪው ለማንኛውም እግረኛ ቅድሚያ መስጠት አለበት። እግረኛ በእነዚህ አጋጣሚዎች የቅድሚያ መብት ባይኖረውም አሽከርካሪው በእነዚህ አጋጣሚዎች ሁል ጊዜ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት አለበት። 33


በልዩ የእግረኛ ማቋረጫዎች መሻገር አንድ እግረኛ የእግረኛ መሿለኪያ ወይም ከላይ በተዘረጋበት ቦታ ላይ መንገድን ካቋረጠ፣ እግረኛው ወደ መንገዱ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት አለበት። ምንም እንኳን እግረኛው የቅድሚያ መብት ባይኖረውም፣ አሽከርካሪው ሁል ጊዜ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ለእግረኞች ቅድሚያ የመስጠት ሃላፊነት አለበት።

በአጎራባች መስቀለኛዎች መካከል መሻገር የትራፊክ መቆጣጠሪያ ምልክት በሚሰራበት አጎራባች መስቀለኛዎች መካከል አንድ እግረኛ መንገዱን ማቋረጥ ያለበት ምልክት ባለው የእግረኛ መንገድ ላይ ብቻ ወይም በመንገድ ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ ቅድሚያ ከሰጠ በኋላ ነው።

አካል ጉዳተኞች አሽከርካሪ በተለየ መልኩ ንቁ በመሆን ለመስማት ለተሳናቸው፣ ወይም የአካል ጉዳት ኖሮባቸው ዱላ፣ ምርኩዝ፣ መራመጃ፣ የሚመሩ ውሾች/የአገልግሎት እንስሳት፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ ወይም የሞተር ስኩተር የሚጠቀሙ እግረኞች ቅድሚያ መስጠት አለበት። እነዚህ ግለሰቦች የሚመጡትን ትራፊክ ለማወቅ ሊቸገሩ ይችላሉ እና መንገዱን ለማቋረጥ ተጨማሪ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። አሽከርካሪዎች ወደ ህጻናት ወይም ግራ የገባቸው ወይም ለማገናዘብ አቅም የሌላቸው ሰዎች ሲጠጉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ በማድረግ ለማቆም ዝግጁ መሆን ይገባቸዋል። ባለ አምስት ጎን ምልክት የትምህርት ቤት መሻገሮችን ለማስጠንቀቅ ይጠቅማል። የአልማዝ ቅርጽ ያላቸው ምልክቶች የእግረኛ መሻገሪያዎችን ያስጠነቅቃሉ.

አውራ ጎዳናዎች ላይ፣ ባለ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች በአጠቃላይ በመንገዱ መሃል መስመር ይቆያሉ ይህም በአውራ ጎዳና ላይ እና በአውራ ጎዳና ውጪ ያለውን የትራፊክ ፍሰት ለማገዝ ይጠቅማል። በመካከለኛው መስመር ላይ መቆየት ለከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በአደገኛ ሁኔታ ወይም ግጭትን ለማስወገድ መስመር ለመቀየር የተሻለ አማራጭ ይሰጠዋል፡፡ ማለፍ ከባድ ተሽከርካሪ በሚያልፉበት ጊዜ በመጀመሪያ ከፊትና ከኋላ ይመልከቱ እና ግልጽ ከሆነ እና በህጋዊ ማለፊያ ዞን ውስጥ ከሆኑ ብቻ ወደ ማለፊያ መስመር ይሂዱ። የፊት መብራትዎን ብልጭ ድርግም በማድረግ ለከባድ ተሽከርካሪ አሽከርከሪውን ማሳወቅ አለብዎት በተለይ በማታ። አሽከርካሪው ከመስመሩ ራቅ ብሎ በመቆየት ያቀልልዎታል። በተስተካከለ አውራ ጎዳና ላይ ከመኪና ይልቅ ከባድ ተሽከርካሪን ለማለፍ ከሶስት እስከ አምስት ሰከንድ ብቻ ይወስዳል። በቁልቁለት ቦታ ላይ ከባድ ተሽከርካሪው በፍጥነት እንዲሄድ ስለሚያደርገው ፍጥነትዎን መጨመር ሊኖርብዎ ይችላል። ማለፍዎን በፍጥነት ያጠናቅቁ እና ከሌላው ተሽከርካሪ ጎን ለጎን አይቆዩ። ካለፉ በኋላ አሽከርካሪው መብራቱን ብልጭ ካደረገ ለመረጋጋት ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ የሚያሳይ ምልክት ሊሆን ይችላል። በየኋላ መመልከቻ መስታወት ውስጥ የከባድ ተሽከርካሪውን ፊት ማየት ሲችሉ ብቻ ወደ መስመርዎ ይመለሱ። ከባድ ተሽከርካሪውን ካለፉ በኋላ ፍጥነትዎን ከያስተካክሉ። ብዙ የመኪና/የከባድ ተሽከርካሪ ግጭቶች የሚከሰቱት መኪኖች ከከባድ ተሽከርካሪው ፊት ለፊት ፈጣን የመስመር ለውጥ በማድረግ፣ ከዚያም በድንገት ፍጥነት በመቀነሱ ወይም በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በመቆም፣ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪውን ለማስተካከል በቂ ክፍተት ስለማይኖረው ነው።

መንገድ ከሌሎች ጋር መጋራት

ከባድ ተሽከርካሪን መከተል

የመንገድ የትራፊክ ህጎች እና ደንቦች ዋና አላማ ብዙ የመንገድ ተጠቃሚዎች፣ ሞተር ተሽከርካሪዎች፣ ብስክሌቶች እና እግረኞች በማንኛውም ጊዜ መንገዱን በእኩል እና በፍትሃዊነት እንዲጋሩ ማስቻል ነው። የመንገድ ደህንነት መንገዱን ከሌሎች በማጋራት ላይ የተመሰረተ ነው።

ከባድ ተሽከርካሪን እየተከተሉ ከሆነ፣ ከ“Blind spots”(የማይታዩ ቦታዎች) መውጣት አለብዎት፤ ከጋቤናው ፊት ለፊት እስከ 20 ጫማ ርቀት፣ ከተሳቢው በአንደኛው ጎን በኩል፣ በተለይም ከጋቤናው ጎኖች እና ከኃላ እስከ 200 ጫማ ርቀት ድረስ ይቆዩ።

መንገዱን ከከባድ ተሽከርካሪዎች ጋር መጋራት

ከከባድ ተሽከርካሪው ጀርባ ይቆዩ እና በቀኝ በኩል ወደ ትራክተሩ ይጠጉ። የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪው በጎን መስተዋቶች ውስጥ እንዲያየው ተሽከርካሪዎን ያስቀምጡ ፣ ከዚያ ፊት ስላለው መንገድ ጥሩ እይታ ይኖርዎታል እና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ለመቆም ወይም ለመታጠፍ ብዙ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥዎት። ምላሽ ለመስጠት እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማቆም ተጨማሪ ጊዜ ይኖሮዎታል። ሌሊት ላይ የከባድ ተሽከርካሪን ሲከተሉ ሁልጊዜ ደብዛዛ የፊት

የመንቀሳቀስ ችሎታ ከባድ ተሽከርካሪዎች በዋነኝነት የተሰሩት ብዙ ምርቶችን ወደ ወይም ከ ከተሞች ለማጓጓዝ ነው፡፤ እንደ ሌሎች መኪናዎች ለመንቀሳቀስ የተሰሩ አይደለም፡፡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ረዘም ያለ የማቆሚያ እና የመንደርደሪያ ርቀቶች፣ ሰፋ ያለ የመዞሪያ ራዲየስ እና ከፍተኛ ክብደት አላቸው። በባለ ብዙ መስመር

34


መብራቶችን ይጠቀሙ። ከኋላ ካለው ተሽከርካሪ የሚመጡ ደማቅ መብራቶች ከባድ ተሽከርካሪውን ትላልቅ የጎን መስተዋቶች ሲያንጸባርቁ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪን እይታ ይጋርዳል። ዳገት ላይ ከከባድ ተሽከርካሪ ጀርባ ከቆሙ፣ ከፊትዎ ቦታ ያተው ምናልባት ተሽከርካሪው መንቀሳቀስ ሲጀምር ትንሽ ወደ ኋላ የሚመለስ ከሆነ። እንዲሁም የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪው በኋላ እንደቆሙ እንዲያዎ በግራ በኩል ይያዙ፡፡ የከባድ ተሽከርካሪው መስተዋቶን ማየት ካልቻሉ፣ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪውም ሊያይዎት አይችልም!

በ"No-Zone"/"Side No-Zone" (መቆም አይቻልም) መቆም አይቻልም ከባድ ተሽከርካሪዎች እና አውቶቡሶች በሁለቱም በኩል ማየት የማይችሉባቸው ቦታዎች አሏቸው። የጎን መመልከቻ መስተዋት ላይ የአሽከርካሪዎች ፊት ማየት ካልቻሉ ሌላቸው አሽከርካሪ እርስዎን ማየት አይችሉም። ከባድ ተሽከርካሪው መስመሮችን ሲቀይር እርስዎ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ከኃላ መከተል የማይቻልባቸው (Rear No-Zones) ከኃላ ተጠግተው ማሽከርከር ያስወግዱ መኪኖች ይልቅ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና አውቶቡሶች ከኋላቸው በጣም ግዙፍ የመቆም አይቻልም ቦታዎች አላቸው። ከባድ አሽከርካሪ ወይም አውቶቡስ መኪናዎን ከኃላ ሆነው ላያይዎት ይችላል፡፡ የከባድ ተሽከርካሪው ወይም አውቶቡሱ በድንገት ፍሬን ከያዙ የሚሄዱበት የመሄጃ ቦታ ላይነሮት ይችላል፡፡ ከፊት የማይቆምበት ቦታዎች Front No-Zones)

የከባድ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ርቀት ከባድ ተሽከርካሪዎች ለማቆም ብዙ ጊዜ ይወስዳሉ። በሰዓት 60 ማይል የሚጓዝ መኪና በ366 ጫማ ርቀት ላይ ሊቆም ይችላል። በተመሳሳይ ፍጥነት የሚጓዝ ከባድ ተሽከርካሪ ለማቆም ከ400 ጫማ በላይ ይወስዳል። የቀኝ እና የግራ መታጠፊያዎች የከባድ መኪና የመታጠፍያ መብራት ምልክቶች ትኩረት ይስጡ። በመካከላቸው እና በመንገዱ ጠርዝ ያሉ መኪኖችን ማየት አይችሉም። የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ በሚታጠፉበት ወቅት የኃላ ክፍላቸው ወይም ተሳቢቢያቸው የመታጠፍያ መአዝኑ ወይም የቆሙ እንቅፋቶችን ሳይነኩ እንዲዞር ሰፋ አድርገው መታጠፍ አለባቸው። አንዳንድ ጊዜ ሌላኛውን መስመሮች በመጠቀም ማዕዘኖችን ሳይነኩ ለማለፍ ይጠቅማል። ግጭትን ለማስወገድ የማዞሪያው እርምጃ እስኪጠናቀቅ ድረስ አይለፉ። መጥፎ የአየር ሁኔታ በዝናብ ወይም በበረዶ ውስጥ ከባድ ተሽከርካሪ መከተል ወይም ማለፍ(ወይም መታለፍ) የእይታ ችግሮችን ይፈጥራል፡፡ ከከባድ ተሽከርካሪ ወይም ተሳቢ ጎማ የሚፈናጠር ውሃ እይታን ወደ ዜሮ ሊቀንስ ይችላል። እርጥብ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የተሽከርካሪዎ የዝናብ መጥረጊያዎች እየሰሩ መሆናቸውን እና በውሃ መያዣው በቂ ፈሳሽ እንዳለ ያረጋግጡ። የፊት መብራት መብራታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ። በከባድ ተሽከርካሪዎች ዙርያ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ማስወገድ ያለብዎት በጣም የተለመዱ ስህተቶች፦

ከባድ ተሽከርካሪ ወይም አውቶቡስ ካለፉ በኋላ ከፊት ቶሎ ብለው ወደ ቦታ ለመመለስ አይሞክሩ፡፡ ከባድ ተሽከርካሪ እና የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ለማቆም ከመኪና ሁለት እጥፍ የሚጠጋ ጊዜ እና ቦታ ክፍተት ያስፈልጋቸዋል። ከተሽከርካሪው ፊት ከመግባትዎ በፊት በኋለኛው መመልከቻ መስታወትዎ ውስጥ የከባድ ተሽከርካሪዎን የፊት ክፍሉን ሙሉ ለሙሉ መያት አለብዎት እና ፍጥነት መቀነስ የለብዎትም።

• መውጫዎ ላይ ለመድረስ ወይም ለመታጠፍ በትራፊክ

ወደ ኃላ በሚሽከረከርበት ያሉ ቦታዎች (Backing up No-Zones)

• በሚያልፉበት ጊዜ ከከባድ መኪና ጎን ብዙ አይቆዩ።

ወይም በአውራ ጎዳና ላይ ያለውን ከባድ ተሽከርካሪ አያቋርጡ። ከከባድ ተሽከርካሪ ፊት ለፊት ወዳለው ክፍት ቦታ መቁረጥ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪውን የደህንነት መጠበቅያ ክፍተቱን ያጠፋበታል፡፡ ፍጥነትዎን ለመቀነስ እና ከከባድ ተሽከርካሪ ጀርባ ለመውጣት ትንሽ ጊዜ ይጠብቁ - ይህም ጥቂት ተጨማሪ ሴኮንዶች ብቻ የሚወስድ ነው፡፡

ሁልጊዜ የትራክተር ተሳቢን ሙሉ በሙሉ እና ሁልጊዜ በግራ በኩል ይለፉ፡፡ ማንኛውንም ተሽከርካሪ በሚያልፉበት ጊዜ ከዘገዩ እንቅፋት በሚታይበት ጊዜ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪው ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ያሉበት ቦታ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ወደ ኃላ በሚሽከረከር ከከባድ ተሽከርካሪ ጀርባ በጭራሽ አይሻገሩ። በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎች ወደኃላ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ችላ በማለት ይሞታሉ ወይም ይጎዳሉ። የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የኋላ መመልከቻ መስታወት ስለሌላቸው ከኋላቸው ሲገቡ ላያዩዎት ይችላሉ።

• በጣም ተጠግቶ መከተል። ከባድ ተሽከርካሪን ወይም

መኪናን ተጠግተው መከተል አደገኛ ነው ምክንያቱም እየተከተሉት ያለው ተሽከርካሪ ድንገት ቢቆም የራስዎ

35


የደህንነት መጠበቅያ ክፍተት ያጣሉ። ተሽከርካርን ከኃላ ሲከተሉ፥ የከባድ ተሽከርካሪውን አሽከርካሪውን የውጭ መስታወት ላይ ማየት ካልቻሉ የከባድ ተሽከርካሪውን አሽከርካሪው እርስዎን ሊያይዎት የሚችልበት ምንም መንገድ የለም። የሚከተሉት ተሽከርካሪ መንገዱ ላይ የሆነ ነገር ቢመታ፣ የተሽከርካሪዎን ፊተኛው አካል ከመምታቱ በፊት ምላሽ ለመስጠት ጊዜ አይኖርዎትም። • ከፊት ለፊት የሚመጣ ተሳቢ ተሽከርካሪ መጠንም ሆነ

ፍጥነትን በፍጹም አሳንሰው አይመለከቱ።

• ትልቅ መጠን ያለው በመሆኑ፣ የትራክተር ተሳቢዎች

ከሚጓዙበት ፍጥነት በታች የሚጓዙ ይመስላሉ። የመኪናው አሽከርካሪ ከባድ መኪናው ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ወይም በምን ያህል በፍጥነት የመጣ እንደሆነ መገመት ስለማይችሉ በመስቀልኛ መንገዶች ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኪና-ከባድ ሽከርካሪ ግጭቶች ይከሰታሉ።

ለትምህርት ቤት ተሽከርካሪዎች ማቆም የትምህርት ቤት ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ሲቆሞ ወይም ከቆመ እና ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ መብራቶችን እየተጠቀመ ከሆነ፥ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ከት/ቤቱ ተሽከርካሪ በፊት ወይም ከኋላ ቢያንስ 20 ጫማ ርቀት ላይ ማቆም አለባቸው። ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ መብራቱ እስካልጠፉ ድረስ ማንም መቀጠል የለበትም። ብልጭ ድርግም የሚሉ መብራቶች ከጠፉ በኋላ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ማድረጋቸውን መቀጠል አለባቸው። የሌሎች ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በተከፋፈለ አውራ ጎዳና ላይ ሲሆኑ እና የትምህርት ቤቱ ተሽከርካሪ በተከፋፈለ አውራ ጎዳና ማዶ ላይ ከሆነ ማቆም አይጠበቅባቸውም።

ከሞተርሳይክል አሽከርካሪዎች ጋር መንገዱን መጋራት ግማሽ የሚያክሉ የሞት አደጋ ያለባቸው የሞተርሳይክል ግጭቶች መኪና የተሳተፈባቸው ናቸው፡፡ ከሞተር ሳይክሎች ጋር በሚጋጩ ጊዜ አሽከርካሪዎች ሞተርሳይክሉን በጭራሽ አላየሁትም ይላሉ፡፡ የመኪና አሽከርካሪዎች ሁል ጊዜ ለሞተርሳይክሎች ንቁ መሆን አለባቸው ምክንያቱም ትንሽ ስለሆኑ ለማየት ያስቸግራሉ፡፡ ሞተርሳይክል እርስዎን እንደማያልፍ ለማረጋገጥ ድብቅ የማይታዩ ቦታዎችን በተደጋጋሚ በማየት ሁልጊዜ ንቁ ይሁኑ። በመስቀለኛ ላይ በሚታጠፉበት ጊዜ እና ከጎን መንገድ ሲገቡ የበለጠ ለሞተርሳይክሎች ንቁ መሆን አለብዎት። ሞተርሳይክል ሁሉንም የመንገድ መስመር የመጠቀም መብት አለው። ሞተርሳይክሉ በጣም ተንቀሳቃሽ ስለሆነ አሽከርካሪው እንቅፋቶችን ለማስወገድ ከመስመር ወደ መስመር እየቀያየሩ ሊሄድ ይችላል። በሚያልፉበት ጊዜ ለሞተር

ብስክሌቱ በቂ ቦታ ይፍቀዱ እና ሞተር ሳይክልን በተመሳሳይ መስመር ውስጥ ሆነው ማለፍ ወይም መቅደም በህጉ የተከለከለ መሆኑን ያስታውሱ። በተለይም ሞተርሳይክልን ሲከተሉ ይጠንቀቁ፡፡ ሞተርሳይክል ከመኪኖች በበለጠ ፍጥነት ሊቆም ስለሚችል ሲከተሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ርቀትን ይጠብቁ።

መንገዱን በብስክሌቶች መጋራት የብስክሌት ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች ብስክሌቶች በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ እንደ ተሽከርካሪዎች ይቆጠራሉ። ብስክሌቶች እንደ ሞተር ተሽከርካሪ መብቶች እና ግዴታዎች አሏቸው። አሽከርካሪዎች መስቀለቻ ላይ በሚያልፉበት እና በሚታጠፉበት ጊዜ ለብስክሌተኞች ቅድሚያ መስጠት አለባቸው። አብዛኛዎቹ ብስክሌቶች የመታጠፍያ መብራት ምልክቶች የላቸውም እና አሽከርካሪዎቹ ሃሳባቸውን ለማሳወቅ እጅ እና የእጅ ምልክቶችን ይጠቀማሉ። የብስክሌተኛን መከተል ወደ ብስክሌት አሽከርካሪ በሚጠጉበት ጊዜ ፍጥነትዎን ይቀንሱ። ጥሩምባ አይጠቀሙ። ብስክሌተኞች ብዙውን ጊዜ እየቀረበ ያለውን ተሽከርካሪ መስማት ይችላሉ እና ከፍተኛ ድምጽ በሚሰሙበት ጊዜ ሊደናገጡ ይችላሉ፥ ግጭት ያስከትላሉ፡፡ ብስክሌትን በቅርበት አይከተሉ። ብስክሌቶች በፍጥነት ማቆም እና መንቀሳቀስ ይችላሉ እና አንድ ብስክሌተኛ የመንገድ አደጋን ለማስወገድ ፍጥነትን ሊቀይር ወይም ሊለወጥ ይችላል። በተለይ ወጣት ብስክሌተኞች ብዙ ጊዜ ያልተጠበቁ የአቅጣጫ ለውጦችን ያደርጋሉ። የብስክሌተኛን ማለፍ የብስክሌተኛን በሚያልፉበት ጊዜ ደህንነቱ የተጠበቀ እስኪሆን ድረስ ይጠብቁ እና በቂ ክፍተት ይፍቀዱ (ብዙውን ጊዜ ከተሽከርካሪዎ ጎን ሶስት ጫማ ያህል) እና ብስክሌት አሽከርካሪውን በየኃላ መስታወት ውስጥ በግልፅ ማየት ሲችሉ ወደ መስመርዎ ይመለሱ። ብስክሌተኛን ለማስጠንቀቅ ወይም ለማንቃት ጥሩምባን በፍጹም አይጠቀሙ። ደህንነቱ ጠብቀው ማለፍ ካልቻሉ ፍጥነትዎን ይቀንሱ፣ ብስክሌቱን ይከተሉ እና ለማለፍ አስተማማኝ እስኪሆን ይጠብቁ። ብስክሌቶች ወደ ቀኝ የመንገዱ ክፍል በቻሉት መጠይ ተጠግተው መሽከርከር አለባቸው። ነገር ግን ብስክሌተኞች የመታጠፍያ መስመር ሊጠቁሙ ይችላሉ። በሚታጠፉበት ጊዜ ከብስክሌት ትራፊክ ጋር ደህንነት በጠበቀ መልኩ ይወሐዱ። የብስክሌት ትራፊክ ባለው መንገድ ሌይ ወደ ቀኝ አይታጠፉ። ልምድ ያለው ብስክሌተኛ በሰዓት ከ20-30 ማይል ፍጥነት መድረስ እንደሚችል ይጠበቃል እና ከምታስበው በላይ መቅረብ ይችላል፡፡ 36


መንገድ ከአውቶቡሶች ጋር መጋራት አጠቃላይ ደህንነት አውቶቡሶች ከአብዛኞቹ መኪኖች፣ ፒክአፕ መኪናዎች እና ሚኒባሶች ይልቅ በጣም ትልቅ ናቸው። የአውቶቡሱ ስፋት ምክንያት በዙሪያቸው ማየትን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል ምክንያቱም ተሽከርካሪዎች መጠን እየጨመሩ ሲሄዱ እንዲሁ የእይታ ሽፋን ይከለክላል። በአውቶቡስ ዙሪያ የእይታ እገዳዎችን ለማስወገድ በእርስዎ እና በአውቶቡስ መካከል ያለውን ርቀት ጨምረው መከተል ነው። አውቶቡሶችን እና ሌሎች ትላልቅ ተሽከርካሪዎችን ተጠግተው መከተል አደገኛ ነው ምክንያቱም ከተሽከርካሪው ፊት ለፊት ያለውን ነገር ማየት ስለማይችሉ እና ለእነሱ ለመታየት በጣም ቅርብ በመሆንዎ አሽከርካሪው እርስዎ እዚያ እንዳሉ እንኳን ላያውቁ ይችላሉ። እነዚህ ተሽከርካሪዎች ማየት የማይችሉባቸው ቦታዎች አልዋቸው እነዚህም ከፊት ወደ ኃላ የሚዘልቁ እና በሁለቱም ጎኖችን ያካተተ ነው። በአደጋ ጊዜ፣ ያለዎት የማቆሚያ ርቀት በእጅጉ ይቀንሳል እና በእርስዎ ላይ ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ የማቆም ችሎታዎን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ብልጭ ድርግም የሚል መብራት አብርቶ የቆመ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስን ሲያልፉ ደህንነቱ የጠበቀ ፍጥነትዎን መጠቀምዎን እና እግረኞችን በንቃት መከታተልዎን እርግጠኛ ይሁኑ። ከተቻለ ጨዋ ይሁኑ እና ለአውቶቡስ ተጨማሪ ቦታ ለመስጠት መስመሮችን ይቀይሩ። አውቶቡሶች ወደ ትራፊክ ሲገቡ እና ሲወጡ ሁል ጊዜ ቅድሚያ ይስጡ። አንድ አሽከርካሪ መንገደኞችን ለመጫን ወይም ለማውረድ መስቀለኛ ላይ ከቆመ አውቶብስ ፊት ለፊት ወደ ቀኝ መታጠፍ የዲስትሪክቱ ህግ ይከለክላል። ይልቁንስ ተሽከርካሪ ከአውቶቡሱ ጀርባ መቆየት ወይም መቀላቀል አለበት። ህንን ህግ የሚጥሱ ቢያንስ 200 ዶላር ይቀጣሉ። የአውቶቡስ መስመሮች የአውቶቡስ መስመሮች ባልተቆራረጠ ቀይ ንጣፍ እና በአስፋልት መንገድ ላይ Bus Only የሚል ምልክቶች ይታያሉ። አንዳንድ የአውቶቡስ መስመሮች በ24/7 ስራ ላይ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የተለያየ የስራ ሰዓት ሊኖራቸው ይችላል። የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ፣ አስጎብኝ አውቶቡስ፣ የኮንትራት አውቶቡስ ወይም የትምህርት ቤት አውቶቡስ እያሽከረከሩ ካልሆነ በስተቀር በአውቶቡስ መስመር ላይ ማሽከርከር የለብዎትም። ብስክሌቶች፣ በዛ ያለ ተሳፋሪ ያላቸው እና የድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች በአውቶቡስ መስመር ላይ እንዲጠቀሙ ይፈቀድላቸዋል። ወደ ቀኝ መጣጠፍ ይችላሉ የሚል ምልክት ካለ የአውቶቡስ

መስመርን በመሻገር ወደ ቀኝ መታጠፍ ይችላሉ። ምንም አይነት ህጋዊ ምልክት ካልተለጠፈ፣ ከመስቀለኛ 40 ጫማ ርቀት ላይ መታጠፍ ይችላሉ። ከመታጠፍዎ በፊት በመስተዋቶችዎን ከኋላዎ ሊሆኑ የሚችሉ ብስክሌተኞችን እና/ወይም አውቶቡሶችን ይመልከቱ እና ለቢስክሌቶች እና አውቶቡሶች ቅድሚያ ይስጡ። በአውቶቡስ መስመሮች ላይ ያልተፈቀዱ ተሽከርካሪዎች የሚያሽከረክሩ ለትኬት እና ለገንዘብ ቅጣት ይዳረጋሉ። የተለጠፈ የአውቶቡስ መስመር ምልክት የተወሰነ የአውቶቡስ መስመሮች በ 24 ሰአታት ላይ ተፈጻሚ ሊሆኑ ወይም ለተወሰኑ የቀኑ ሰአታት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፣ ለምሳሌ በስራ በመውጫና መግቢያ ሰዓታት። በከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ሰአት መዘግየቶችን በሚያስከትልባቸው ጎዳናዎች ላይ፣ የአውቶቡስ መስመሮች አስተማማኝነት እና የመጓጓዣ ጊዜዎችን ሁለቱንም ያሻሽላሉ። የተለጠፈው ምልክት የአውቶቡስ መስመር የሚሰራባቸውን ቀናት እና ሰአቶችን ጨምሮ የተወሰኑ የአውቶቡስ መስመሮች መኖራቸውን ያሳያል። የአውቶቡስ መብራት ምልክቶች የ"Bus Only" ምልክቶች አውቶቡሶች መብራቱ ወደ አረንጓዴ ከመቀየሩ በፊት በመስቀለኛ መንገድ ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ቀድመው እንዲሄዱ ያስችላቸዋል። አውቶቡስ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ሲቆም፣ የአውቶቡስ-ብቻ የትራፊክ መብራት ምልክቱ መቼ መቀጠል እንዳለበት ለአውቶቡስ እንደ አረንጓዴ መብራት ሆኖ የሚያገለግል ወደ ላይ ቀጥ ባለ መስመር ምልክት ያሳያል። ከሶስት ሰከንድ በኋላ፣ ብልጭ ድርግም የሚል ሶስት ማእዘን የቅድሚያ ይለፍ መብት ሊያልቅ መሆኑን ያሳያል፣ ከዚያም በአግድም አውቶቡሶች ቅድሚያ እንደሌላቸው ያሳያል እና መደበኛ የትራፊክ ምልክቶችን መታዘዝ አለባቸው።

37


የጉዞ ሰአቶችን እና የምልልሶችን በመርሐግብር መሰረት እንዲቀጥሉ ታስቦ የተሰራ ሲሆን የመብራት ምልክት ስርአቱ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች አረንጓዴ መብራት ከመስጠቱ በፊት በ"Bus Only" ምልክት ላይ አጭር "Proceed" ምልክት በማሳየት ለአውቶቡሶች ቅድሚያ ይሰጣል።

የሐዲድ አውቶብስን ማለፍ የቆመ የሐዲድ አውቶብስን በሚያልፉበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ ምክንያቱም ተሳፋሪዎች ወደ ተሽከርካሪው እየገቡ ወይም ከተሽከርካሪው እየወጡ ሊሆን ይችላል። ወደ ተመሳሳይ አቅጣጫ እየተጓዙ የቆመ የሐዲድ አውቶብስን በሚያልፉበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ እንዲሁም ለማለፍ ምቹ የሚሆንበትን ጊዜ ጠብቀው በየሐዲድ አውቶብሱ በግራ ጎን በኩል ይለፉ።

አውቶቡሱ ከሌሎች አሽከርካሪዎች ቅድሚ እንዲሰጠው ሳይጠብቅ ከአውቶቡስ ማቆሚያው እንዲወጣ በማድረግ ደህንነትን ማሳደግ፣ "queue jump” ተብሎ የሚጠራው የትራፊክ ቴክኖሎጂ ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የሐዲድ አውቶብስ መስመር ተሽከርካሪ ማቆም የአውቶቡስ አገልግሎት ይሰጣል። የዲስትሪክቱ ህግ ተሽከርካሪዎች የሐዲድ አውቶብስ መሔጃ ሐዲድ አጠገብ ወይም ጎን ተሸከርካሪ ማቆም፣ማቆየት ወይም የሐዲድ አውቶብስ ጋር መንገድ መጋራት ማስቆም ይከለክላል። ይህንን ሕግ የሚጥስ ተሽከርካሪ ቅጣትና የሐዲድ አውቶብሶች በተወሰነላቸው ሀዲድ መስመር በሕዝብ እገዳ ወይም እስራት የሚጣልበት ይሆናል። መንገድ ላይ ተሳፋሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ተሽከርካሪዎቹ በቅልቅል የትራፊክ መስመር ወይም የራሳቸው ተሽከርካሪዎች የሐዲድ አውቶብስ መስመር አጠገብ ብቻ በሆነ መስመር የሚሰሩ ናቸው። በመደበኛነት ተሳቢ በሚቆሙበት ጉዜ፡ካላቸው አውቶብሶች ጋር ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ሲሆን • ሐዲድ ላይ ማቆም የለባቸውም የሐዲድ አውቶብስ የበለጠ ተሳፋሪዎችን የሚያጓጉዙ ሲሆን በአማካኝ ከ25 እስከ 35 ማይል በሰዓት የጓዛሉ። የሐዲድ • ተሸከርካሪዎን ያልተቆራረጠ ነጭ መስመር በተቀባው ቦታ አውቶብሶች ከመደበኛ አውቶብሶች ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ላይ ያቁሙ ፍጥነት የሚጓዙ ቢሆንም የተለጠፈውን የፍጥንት ወሰን ማለፍ • የተሽከርካሪው በር በሚከፈቱበት እና በሚዘጋበት ጊዜ የለባቸውም እንዲሁም የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት መጠበቅ እየመጣ ያለውን የሐዲድ አውቶብስ በጥንቃቄ መመልከት ይኖርባቸዋል። አሽከርካሪዎች የትራፊክ ምልክቶችን ማክበር ያስፈልጋል እንዲሁም የሐዲድ አውቶብሶች እንቅስቃሴን መመልከት • ተሽከርካሪ ደርቦ ማቆም ሕገወጥ ነው ይኖርባቸዋል።

38


የማሽከርከር ደንቦች የቀኝ መስመር ይዞ መጓዝ

• በአውራ ጎዳና ጫፍ ቀኝ ወይም ግራ ክፍል ላይ

ተሽከርካሪዎ መንገድ ከሚቀይርበት ጊዜ እና ወደ ግራ በመታጠፍ ሌላ ተሽከርካሪ ከሚያልፍበት ጊዜ ውጭ በማንኛውም ጊዜ ቀኝ መስመሩን ይዞ መጓዝ ይኖርበታል። በባለ ሁለት መስመር መንገድ ወይም ሌላ ጠባብ በሆነ አውራ ጎዳና ላይ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የመንገዱን ግማሽ ለሌላኛው ተሽከርካሪ መልቀቅ ወይም ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል።

• ሌላ ተሽከርካሪ ደርቦ በሚያልፍበት ጊዜ ፍጥነቶን

ምልክት መስጠት

በባለ ሁለት መስመር አውራ ጎዳና ላይ መቅደም እና ማለፍ

ከመታጠፍዎ ቢያንስ 100 ጫማ በማስቀደም የመታጠፊያ መብራቶች፣ የእጅ ወይም ሁለቱንም ምልክቶች ማሳየት ይኖርብዎታል። በከፍተኛ ፍጥነት በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ለረዥም ጊዜና በደንብ ረዘም ላለ ርቀት እነዚህን ምልክቶች በቅድሚያ ማሳየት ይጠበቅብዎታል። ይህ አካሄድ በዋነኝነት በአውራ ጎዳናው ላይ አቅጣጫን በሚቀይሩበት ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል። መስቀለኛ እንዳለፉ ወደ ሆነ አቅጣጫ የሚታጠፉ ከሆነ መስቀለኛ ውስጥ እያሉ ጀምረው ምልክቱን ያሳዩ።

ደርቦ ማለፍ ተሽከርካሪው በሚያልፉበት ጊዜ በግራ ጎን በኩል ቢያልፉ ይመከራል። ነገር ግን በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ከአንድ በላይ የትራፊክ መስመር ያለው በባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ ላይ በቀኝም ሆነ በግራ ጎን በኩል ማለፍ ሕጋዊ ነው። በተጨማም አራት እና ከዚያ በላይ መስመር ባላቸው አውራ ጎዳናዎች ላይ በግራም ሆነ በቀኝ ማለፍ በሕግ የተፈቀደ ነው።

በባለ ሁለት መስመር አውራ ጎዳና ላይ ማለፍ የሌለብዎት ጊዜ ከዚህ በታች ባሉት ሁኔታዎች ላይ ማለፍ የለብዎትም፡• እርስዎ በሚጓዙበት አቅጣጫ ላይ ባለው አስፋልት መካከለኛ

ክፍል ላይ ያልተቆራረጠ ቢጫ ቀለም በሚኖርበት ጊዜ

• ሁለት ያልተቆራረጡ የቢጫ መስመሮች በሚኖሩበት ጊዜ • ማለፍ ከሚመጣው ተሽከርካሪ ጋር በሚደራረብበት ጊዜ • የተራራ ጫፍ ወይም መታጠፊያ ቦታ ወይም በግልጽ ከፊት

ያለውን ማየት የማይቻልበት ቦታ ላይ በሚደርሱበት ጊዜ

•

መስቀለኛ ሲያቋርጡ ወይም በ 100 ጫማ ቅርበት ላይ በሚሆንበት ጊዜ

• የባቡር ሐዲድ ሲያቋርጡ ወይም በ 100 ጫማ ቅርበት ላይ

መጨመር የለብዎትም

• የ"no-passing zone" (ማለፍ-አይቻልም ዞን) መጨረሻ

የሚል ምልክት ያለው ቦታ ለማለፍ ደህንነትዎ የተጠበቀ ነው ማለት አይደለም ነገር ግን በእነዚህ ስፍራዎች ላይ ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ ማለፍ ሕጋዊ ነው ማለት ነው።

በባለ ሁለት መስመር አውራ ጎዳና ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ደርቦ ለማለፍ የግራ ጎን መጠቀም ይኖርበታል። የመካከለኛውን መስመር አቋርጠው ለማለፍ ከመሞከርዎ በፊት ከተቃራኒ አቀጣጫ ከሚመጣ ተሽከርካሪ ጋር ሳይገናኙ እና ማለፍአይቻልም ዞን ምልክት ከመጀመሩ በፊት ለማለፍ እና ወደ ትክክለኛ ቦታዎ ለመመለስ በቂ ጊዜ ያለዎ መሆኑን ያረጋግጡ። በሚያልፉበት ጊዜ ከሌላ አቅጣጫ ከሚመጣ ተሽከርካሪ ጋር ከመገናኘትዎ በፊት ሙሉ ለሙሉ ማለፍ የማይችሉ ከሆነ ፍጥነትዎን በመቀነስ ሊያልፉት ከሞከሩት ተሽከርካሪ ጀርባ ወደ አለበት መስመር ይመለሱ። ከኃላዎና ከፊትዎ ያለ አሽከርካሪ ለማሳወቅ ወደ ሚገቡበት መሰመር መሰረት ያደረገ የግራ ወይም የቀኝ መታጠፍያ መብራት ያብሩ። ተሸከርካሪ ደርበው በሚያልፉበት ጊዜ ደርበው ያለፉትን ተሽከርካሪ በየኃላ ማሳያ መስታወት ሁለቱንም መብራቱን ማየት ከቻሉ በኃሉ ወደ ትክክለኛ መስመርዎ ይመለሱ። ሳይክል ደርቦ በሚያልፉበት ጊዜ ቢያንስ ሶስት ጫማ ክፍተት በመካከላችሁ መኖሩን ያረጋግጡ። ሳይክል ደርበው በሚያልፉበት ጊዜ በጥሩንባ አይጠቀሙ። ተሽከርካሪ ደርብዎት በሚያልፍበት ጊዜ እያለፈ ላለ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መንገድ ይስጡ። ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ እስከሚያልፍበት ጊዜ ድረስ ፍጥነትዎን አይጨምሩ። ሊያልፉት ያሰቡት ተሽከርካሪ ወደ ግራ ለመታጠፍ ምልክት ካሳየ ወይም እየታጠፈ ከሆነ ብቻ በቀኝ መስመር ይለፉ። ነገር ግን በመንገዱ የመሄጃ ስፍራ ላይ መሆንዎን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። ሌላ ተሽከርካሪ ለማለፍ ብለው በመንገዱ ጠርዝ ላይ ማሽከርከር አይችሉም።

የቀለም ምልክት ባላቸው የመንገድ መስመር ላይ ማሽከርከር • አንድ መስመር ላይ መቆየት አለብዎት

በሚሆንበት ጊዜ

• በሁለቱም መስመር ላይ እያፈራረቁ ማሽከርከር

• 100 ጫማ ርቀት ውስጥ ባለው በማንኛውም ድልድይ፣

የለብዎትም

ረጅም ድልድይ ወይም ዋሻ ምክንያት ከፊት ያለውን መመልከት በማይችሉበት ጊዜ

• ደህንነትዎ በተጠበቀ መንገድ ማድረግ ካልቻሉ በስተቀር 39


ከአንደኛው ወደሌላኛው መስመር አይቀይሩ

• በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ በቀይ መብራት ወደ ግራ

መታጠፍ በሕግ የተከለከለ ነው።

• መስመር ከመቀየርዎ በፊት 300 ጫማ ባላነሰ ርቀት

መስመር መቀየር ማሰብዎን ምልክት ያሳዩ። ኃላም በፊትም ላሉ አሽከርካሪዎች ትክክለኛውን ድርጊት እንዲፈፅሙ የመታጠፊያ መብራት ምልክት ቀድመው ማሳየት ይመረጣል።

• በእርስዎ አቅጣጫ የሚጓዝ ሁለትና ከዛ በላይ መስመር

ያለው አውራ ጎዳና ላይ ከትራፊኩ ፍጥነት ዝቅ ባለ ፍጥነት ሲያሽከረክሩ ወደ ቀኙ መስመር መጓዝና እዛው መቆየት አለብዎት።

• መንገድ ጠርዝ የቆመ ተሽከርካሪ በሚመለከቱበት ጊዜ

የፊት መብራት አጠቃቀም አጭር የፊት መብራት ሁሌም የግንባር መስታወት መጥረጊያ በሚከፈትበት ጊዜ የፊት መብራትዎ መብራት ይኖርበታል። ወደ ሌላ ተሽከርካሪ በሚጠጉበት ጊዜ ወይም በቅርበት ሌላ ተሽከርካሪ በሚከተሉበት ጊዜ አጭር መብራት ይጠቀሙ። የመንገድ መብርት በሚኖርበት ጊዜ እና ጭጋጋማ የአየር ንብረት በሚኖርበት ጊዜ አጭር መብራት መጠቀም አለብዎት።

ፍጥነትዎን በመቀነስ ከቻሉ ወደ ግራ ወይም ቀጥሎ ወዳለው ቀጣይ ክፍል ማለፍ አለብዎት።

• ፀሐይ ከጠለቀች ከግማሽ ሰዓት በኋላ እንዲሁም ፀሐይ

ከመውጣትዋ ከግማሽ ሰዓት በማስቀደም መብራትዎን ማብራት ይኖርብዎታል።

መታጠፍ

• ሌላ ጊዜ በ500 ጫማ ወይም ከዚያ በታች ባለው ርቀት

ወደ ቀኝ መታጠፍ

በአውራ ጎዳናው ላይ ሰዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በግልጽ መመልከት በማይችሉበት ጊዜ የፊት መብራትዎን ማብራት አለብዎች።

• ከመታጠፍዎ በደንብ ቀድመው ወደ ጥግኛው የቀኝ

መስመር ይግቡ

• ቢያንስ 100 ጫማ በማስቀደም የመታጠፍ ፍላጎት ያለዎ

• ዋሻ ውስጥ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የፊት መብራት

መሆኑን ያሳውቁ

• በእግረኛ መንገድ ላይ ለሚጓጓዙ እግረኞች ቅድሚያ ይስጡ • ከፊትዎ ያሉ መታጠፍ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ይጠንቀቁ • በእርስዎ እና በመንገዱ ጎን ላይ ለሚጓዙ ብስክሌተኞች

ቅድሚያ ይስጡ

• በመስመርዎ ላይ ከተጓዙ በኋላ ወደ ቀኝ ይታጠፉ • በቀይ ላይ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ቀኝ በሚታጠፉበት

ማብራት አለብዎ ረዥም የፊት መብራት ጨለማ መንገድ ላይ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ከፊት ያሉ ሰዎችን እና ተሽከርካሪዎችን ቀድመው ለማየት ረዥም መብራት ይጠቀሙ። ከዚህ በታች የተገለፁት ሁኔታዎች ከሌሉ በስተቀር ከፊትዎ ያሉ ሰዎች ወይም ተሽከርካሪዎች ለማየት ረዥም መብራት ይጠቀሙ። እነዚህም፡-

ጊዜ ከመታጠፍዎ በፊት ሙሉ በሙሉ ቆመው ለእግረኞች ቅድሚያ ይስጡ።

• ከፊት ያሉ ተሽከርካሪዎችን ከመገናኘትዎ ቢያንስ 500

ጫማ በፊት ወደ አጭር መብራት ይቀይሩ

• በ300 ጫማ ወይም ከዚያ በታች በሆነ ርቀት ተሽከርካሪ

ወደ ግራ መታጠፍ

በሚከተሉበት ጊዜ መብራቶን ወደ አጭር መቀየር ይኖርብዎታል

• ከመታጠፍዎ በደንብ አስቀድመው በእርስዎ በኩል

ወዳለው የአውራ ጎዳናው የግራ መስመር ይያዙ

• ቢያንስ 100 ጫማ በማስቀደም የመታጠፍ ፍላጎት ያለዎ

የኃይል መቆጠቢያ ጥቆማዎች

• ለሚመጣ ትራፊክ ብስክሌትን ጨምሮ ቅድምያ ይስጡ

በጥንቃቄ በማሽከርከር ከዚህ በታች ያሉትን ካደረጉ ነዳጅዎን ለተሻለ ርቀጥ ይጠቀሙበታል እና ከነዳጅ ገንዘብ ይቆጥባሉ፡-

• በእግረኛ መንገድ ላይ ለሚጓጓዙ እግረኞች ቅድሚያ ይስጡ

• በሂደት ፍጥነት ከጨመሩ

መሆኑን ያሳውቁ

• የሚመጣውን ተሽከርካሪ በሚጠብቁበት ጊዜ መስቀለኛ

• ፍሰቱ በጠበቀና እና መካከለኛ በሆነ ፍጥነት ካሽከረከሩ

መንገድን አይዝጉ

• ከባድ ፍሬን መያዝን ለመቀነስ አስቀድሞ የማቆሚያ ቦታ

• በመንገድዎ ላይ ከተጓዙ በኋላ ወደ ግራ ይታጠፉ

በመገመት

• ሲታጠፉ በጣም አጥበበውም ሆነ በሚጓዙበት አቅጣጫ

• አላስፈላጊ የማሽከርከር አይነት ማስወገድ

ወዳለው የቀኝ መስመር በሚያስገባዎ መልኩ በጣም አስፍተው አይታጠፉ።

• አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በጋራ መጓዝን መጠቀም 40


የፓርኪንግ ደንቦች ተሽከርካሪዎን መንገድ ላይ በሚያቆሙበት ጊዜ ሞተሩን ማጥፋት የሞተሩን ሥርዓት ማጥፋት ቁልፉን ማውጣት እንዲሁም የፓርኪንግ ፍሬን መሣብ ይኖርብዎታል። በተጨማም ተሽከርካሪውን በሚያቆሙበት ጊዜ የመስኮት መስታወት መዝጋት በሮችን መቆለፍ እንዲሁም ዋጋ ያላቸው እቃዎች በሚታይ ሥፍራ ላይ የሌሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይመከራል። ልጆች፣ ጎልማሶች፣ እንዲሁም እንስሳዎች በቆመ ተሽከርካሪ ውስጥ ትቶ መሄድ አይመከርም።

ወደ ትይዩ የመኪና ማቆሚያ ደረጃዎች፦ 1. ወደፊት አልፈው ተሽከርካሪዎ ከሁለት እስከ አምስት

ጫማ ርቀት እስኪቀረው ድረስ ከቆመው ተሽከርካሪ ጋር ጎን ለጎን ያቁሙ። ከዚህ ርቀት አልፈው ወይም ከዚህ ርቀት በጣም በቀረበ መልኩ ማቆም ከባድ ሊሆን ይችላል። 2. ፍሬን እንደያዙ ማርሽዎን ወደ ኋላ በማድረግ ወደ ኋላ

ዞረው አንቅስቃሴ አለመኖሩን እንዲሁም ለመንቀሳቀስ መንገድ ምቹ መሆኑን ይመልከቱ። 3. ፍሬን ለቀው በጥንቃቄ ወደ ኋላ ይሂዱ በመቀጠል የ“S”

ምልክት ሰርተው ይታጠፉ 4. በሚታጠፉት ጊዜ ያለው ክፍት ቦታ በቂ መሆኑን

ለማረጋገጥ ከፊት እና ከኋላዎ ያሉትን ቦታዎች በተደጋጋሚ ይመልከቱ። 5. የተሽከርካሪዎ ኃለኛው ክፍል አብዛኛው ክፍል ትክክለኛ

ቦታ ላይ ከሆነ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ በመታጠፍ ተሽከርካሪዎን ያቃኑ። 6. እንደአስፈላጉነቱ ተሽከርካሪዎን ትክክለኛ ቦታ ላይ

ለማቆም ያስተካክሉ።

በመንገድ ትይዩ ፓርኪንግ ተሽከርካሪዎን በባለ ሁለት መስመር መንገድ ላይ በትይዩ በሚያቆሙበት ጊዜ በመካከል ያለው ክፍተት ለተሸከርካሪዎ በቂ መሆኑን እና ከጠርዙ በ12 ኢንች ውስጥ መሆኑን የረጋግጡ። እዚህ ቦታ ላይ በሚቃረቡበት ጊዜ ምልክት ያሳዩ እንዲሁም በመስታወት ከኋላዎ ያሉትን ተሽከርካሪዎች ይመልከቱ። ከኋላዎ የሚከተሎት ተሽከርካሪ ከቆመ ከእርስዎ በብዙ ርቀት መቆም አለበት። ነገር ግን ከኋላዎ ያለው ተሽከርካሪ በጣም በቅርበት እየተከተልዎ ከሆነ በድንገድ አይቁሙ፤ ወደ ፈት ሄደው ሌላ ማቆምያ ቦታ ፈልገው ተሽከርካሪዎን ያቁሙ። በድንገት ተሽከርካሪዎን ማቆም ከኋላዎ ያለው ተሸከርካሪ ከእርስዎ ተሽከርካሪ የኋለኛው ክፍል ጋር እንዲጋጭ ሊያደርግ ያደርጋል።

7. የተሽከርካሪዎ ጎማ ከመንገድ ጠርዝ 12 ኢንች ርቀት

ላይ የሚገኝ መሆኑን ያረጋግጡ። ካልሆነ ተሽከርካሪውን በማስነሳት በድጋሚ ይሞክሩ። ሁሌም በር ከመክፈትዎ በፊት የሚያልፉ ተሽከርካሪዎች እና ብስክሌተኞችን ይመልከቱ። ተሽከርካሪዎ ከቆመበት ስፍራ ተነስቶ ወደ መንገድ በሚገባበት ጊዜ የመታጠፍያ መብራት መጠቀም፣ ቅድሚያ መስጠት እና ደህንነቱ የተጠበቀ በሚሆንበት ጊዜ ተሽከርካሪዎን ወደ መንገዱ ያስገቡ። ደርቦ ማቆም በሕግ የተከለከለ ነው ምክንያቱም የተሽከርካሪ እንቅስቃሴን ይገድባል በተጨማሪ ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል።

ዳገት/ቁልቁለት ላይ ተሽከርካሪ ማቆም ተሽከርካሪዎ ፓርክ ላይ መሆኑን እንዲሁም የማቆሚያ ፍሬን በትክክል መሳብዎን ያረጋግጡ። ተሽከርካሪዎ ማንዋል ትራንስሚሽን ካለው ተሽከርካሪዎን ማርሽ ላይ ትተው የእጅ ፍሬን የሳቡ። ተሽከርካሪው ወደኋላ ወይም ወደፊት እንዳይንሸራተት ይረዳል ዘንድ የፊት ለፊት ጎማዎን ከዚህ በታች ባለው መንገድ ያቁሙ፡• ቁልቁለት ላይ በሚያቆሙበት ጊዜ ጎማውን ወደ ጠርዝ 41


አቅጣጫ በማድረግ

በሚወጡበት ጊዜ እና ተሽከርካሪዎ በእግረኛ መንገድ ላይ በማቋረጥ በማጓዝበት ጊዜ በሙሉ በሙሉ ቆመው ለእግረኖች፣ ብስክሌተኞች ወይም ለሌላ በቅድሚያ ወደ መንገዱ ለገቡ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት ይኖርበታል።

• በዳገት ላይ በሚያቆሙበት ጊዜ ከመንገዱ ይራቁ

ተሽከርካሪዎን ዳገት ወይም ቁልቁለት ላይ በሚያቆሙበት ጊዜ ጠርዝ በማይኖርበት ጊዜ የፊት ለፊት ጎማዎን ወደ መንገድ ጫፍ አቅጣጫ (ጠርዝ ይሆን ወደነበረው አቅጣጫ) በመጠምዘዝ ያቁሙ።

• ወደ መስቀለኛ መንገድ ከመግባትዎ ከመስቀለኛ በኃላ

ያለው መንገድ በትራፊክ የተጨናነቀ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ አቁመው የተዘጋጋው መንገድ ነጻ መሆኑን ሲያረጋግጡ ወደ መስቀለኛው ይግቡ ድረስ። የመተላለፊያ መንገድ አይዝጉ! የእግረኛ መንገድ አይዝጉ!

አውራ ጎዳናዎች ላይ ማቆም ተሽከርካሪዎ ካልተበላሸ ወይም መጓዝ ካልቻለ በስተቀር የአውራ ጎዳና አስፋልት ወይም መሄጃ ላይ አያቁሙ። እና በተቻለ መጠን ተሽከርካሪዎን ወደ ቀኝ አቅጣጫ በማስጠጋት ያቁሙ። ተሽከርካሪዎን የአውራ ጎዳና ጠርዝ ወይም ጎን ፀሐይ ከምትጠልቅበት እስከምትወጣበት ወይም ነገሮች ወይም ሰዎች በ1000 ጫማ ለማየት በቂ ብርሃን በሌለበት በሚያቆሙበት ጊዜ የአደጋ ምልክት መብራት ወይም የፓርኪንግ መብራት(ተሽከርካሪው ካለው) ማብራትዎን አለብዎት።

• ዝቅ ያሉ ወይም ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ያላቸው

የባቡር ሐዲድ መሻገርያዎች ላይ መቆም ይኖርብዎታል።

መቆም፣ ማቆም- የተከለከለባቸው ቦታዎች ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ጋር ግጭት እንዳይፈጠር ለመከላከል ካለሆነ ወይም የፖሊስ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለማክበር ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በታች ባሉት ቦታዎች እና ሁኔታዎች ተሽከርካሪ አያቁሙ፡• በሕዝብ መግቢያ/መውጫ መንገድ ላይ

የትራፊክ ፍሰት ሊያስተጓጉል ወይም በተሽከርካሪው ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መንገድ የተሽከርሪዎን በር አይክፈቱ። በምትኩ በመንገድ ዳር ባለው በር አቅጣጫ ሰዎች እና እቃዎች እንዲወርዱ ያድርጉ።

• በእግረኞች መንገድ ላይ • መስቀለኛ መንገድ ላይ • እግረኛ መሻገርያ መንገድ ላይ

ማቆም

• በደህንነት መጠበቂያ ዞን እና ጠርዝ አካባቢ ወይም

ማቆም ማለት እንቅስቃሴን ማቆም ሲሆን ምንም የማሽከርከር ማቆሚያዎች የሉም።

ጠርዝ ካለበት ቦታ ጀምሮ 30 ጫማ ርቀት ላይ ባለ ስፍራ በተቃራኒው የደህንነት መጠበቂያ ዞን የሆነበት ቦታ ላይ፤ ይህም የግዛቱ የአውራ ጎዳና አስተዳደር ወይም የአካባቢው ባለሥልጣን ሌላ የርቀት አመልካች ምልክት ካስቀመጡበት ጀምሮ።

• የቁም ምልክት በሚሆንበት ጊዜ ተሽከርካሪዎን ቁም ከሚል

ምልክት በፊት ሙሉ በሙሉ ማቆም ይኖርብዎታል ከሌለ ከእግረኛ ማቀረጫ በፊት ያቁሙ።

• በማንኛውም በሚሄዱበት ወይም በተቃራኒ በኩል ቁፋሮ

• ቀይ መብራት ብልጭ ድርግም በሚበራበት ጊዜ

ወይም እይታን የሚከለከሉ ማለትም ተሽከርካሪ ማቆም፣ መቆም የትራፊት እንቅስቃሴ የሚገታ በሚሆንበት ጊዜ

ተሽከርካሪዎን ሙሉ በሙሉ ማቆም አለብዎት

• በቋሚነት የበራ ቀይ መብራት ምልክት በሚኖርበት ጊዜ

መታጠፍ የሚከለክል ምልክት በቦታው ላይ አለሞነሩን ካረጋገጡ በኃሉ መጀመርያ ሙሉ በሙሉ ከቆሙ በኋላ ተነስተው ወደ ቀኝ ለመታጠፍ ለእግረኞች፣ ብስክሌተኞች አንዲሁም መስቀለኛውን እንዲጠቀሙ በህግ ፈቃድ ለተሰጣቸው ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት ይኖርዎታል።

• ቅድሚያ እንዲሰጡ የማያመለክት ምልክት

እያለ ተሽከርካሪዎች ወይም እግረኛች መንገዱን እንዳይጠቀሙበት በሚመለከቱበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ቆመው መንገዱ ነፃ እስኪሆን ድረስ መጠበቅ አለብዎት።

• በማንኛውም ድልድይ ወይም ሌላ ከፍ ያለ ቦታ ወይም ዋሻ

ውስጠኛ ክፍል ውስጥ

• መቆም በተከለከለባቸው እና ጠቋሚ ምልክቶች ባሉባቸው

ማንኛቸውም ቦታዎች

• የትራፊክ እንቅስቃሴ አቅጣጫ በተቃራኒ አቅጣጫ ላይ

ከዚህ በታች ያሉ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ሁኔታ ቢያዙም ባይያዙም ተሽከርካሪዎን አያቁሙ፡• በሕዝብ የግል መግቢያ መንገድ ፊት ለፊት ወይም 5 ጫማ

ርቀት ክልል ውስጥ

• ከእሳት ማጥፊያ ቧንቧ 10 ጫማ ርቀት ክልል ውስጥ

• ከቅያስ፣ ከግል መንገድ ወይም ከፓርኪንግ ቦታ 42


• ከብልጭ ድርግም የሚል መብራት፣ ማቆሚያ ምልክት

እንዲሁም የትራፊት መቆጣጠሪያ መብራት ምልክቶች ፊት ለፊት 25 ጫማ ርቀት ክልል ውስጥ

• የማንኛውም የእሳት ማጥፊያ መግቢያ መንገድ 20 ጫማ

ርቀት ውስጥ

• በኩርባ ወይም ቁልቁለታማ ስፋራዎች እና ማለፍ

እንደማይቻል ምልክት የተለጠፈባቸው ቦታዎች

• መቆም የተከለከለባቸው እና ጠቋሚ ምልክቶች

የተለጠፉባቸው ቦታዎች

• ተሽከርካሪዎች በቆሙበት የመንገድ ዳር ወይም ጠርዝ

ዳር ደርቦ ማቆም

• መንገድ መዝጊያ የተደረገባቸው ወይም ጠቋሚ ምልክት

የተለጠፈባቸው ቦታዎች ፊት

በጊዜያዊነት እቃዎችን ወይም ተጓዦችን ለመጫን ወይም ለማውረድ አላማ ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በታች ባሉት ሁኔታ እና ቦታዎች ላይ ቢያዙም ባይያዙ ተሽከርካሪዎን ማቆም አይቻልም። • ከባቡር ሐዲድ ማቀረጫ መንገድ ላይ ከሐዲዱ 50 ጫማ

ርቀት ክልል ውስጥ

• ፓርኪንግ በይፋዊነት የተከለከለባቸው እና ጠቋሚው

ምልክት በተለጠፈባቸው ማንኛውም ቦታዎች

• የአካል ጉዳት ካልሆኑ በስተቀር ለአካል ጉዳተኞች ብቻ

የሚል ምልክት የተቀመጠባቸው ቦታዎች ወይም ዞኖች ላይ ተሽከርካሪዎን ፓርክ አያድርጉ።

43


የትራፊክ ደንቦች መዞር

ከዚህ በታች ያሉትን እውነታዎች ይመልከቱ፡-

በማንኛውም ጊዜ ተሽከርካሪዎ በተዘጉ ስፍራዎች ላይ መኪናዎን ማዞር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ለምሳሌ በማሽከርከር ፈተና ጊዜ ወይም ሄዶ በሚቆም/የማይቀጥል መንገድ ላይ።

• በሃያ ማይል በሰዓት በፍጥነት ከሚሄድ ተሽከርካሪ

ይልቅ በስልሳ ማይል በሰዓት በሚሄድ ተሽከርካሪ ላይ የሚፈጠረው ግጭት ወይም አደጋ ስምንት እጥፍ ሞት የማምጣት እድል አለው።

ይህንንም ለማድረግ፡-

• ሁለት ተሽከርካሪዎች ፊት ለፊት ቢጋጩ የግጭቱ ውጤት

• ከመንገዱ የቀኝ ጥግ ክፍል ይጀምሩ። ሌሎች ተሽከርካሪዎች

የሁለቱ ተሽከርካሪዎች ፍጥነት ድምር ነው። ሁለት ተሽከርካሪዎች እያንዳንዳቸው ሃምሳ ማይል በሰዓት ቢሄዱ የሁለቱ ተሽከርካሪዎች ፍጥነት ድምር መቶ ማይል በሰዓት ነው።

አለመኖራቸውን እና መንገዱ ግልጽ መሆኑን በማረጋገጥ ቀስ በቀስ የተሽከርካሪዎን መሪ ወደ ግራ በማዞር ይቀጥሉ። የመንገዱ ጠርዝ ወይም የግራ ጫፍ ላይ ሳይደርሱ በቂ ኢንቾች ሲቀሩ ያቁሙ።

• አንድ የቆመ ይዘት ወይም እቃ ስልሳ ማይል በሰዓት የሚሄድ

• በመጠቀል በጥንቃቄ ወደ ኋላ በመመለስ መሪዎን ወደ

ተሽከርካሪ ማይል ቢገጨው ውጤቱ ከአስረኛ ፎቅ ህንፃ ላይ የመውደቅ ወይም የመፈጥፈጥ ጋር እኩል ነው።

ቀኝ ይጠቅልሉ።

• ወደ ቀኝ ጠርዝ ወይም የመንገድ ጫፍ ላይ ከመድረስዎ

በቂ ኢንቾች ሲቀርዎት ያቁሙ።

• በመቀጠል መሪዎን ወደ ግራ በሚመልሱበት ጊዜ በዝግታ

ይጓዙ ይህ ማዞሪያዎን ማጠናቀቅ አለብዎት። ካልሆነ ይህንን ተመሳሳይ ሂደትን ይድገሙ።

የፍጥነት ገደብ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የትራፊክ ሕግ ጠቅለላ የፍጥነት ገደብ እና ልዩ የፍጥነት ገደቦች ተግባራዊ ያደርጋል። እርስዎም ሁለቱን ሕጎች ማክበር ይኖርብዎታል። በነባራዊ ሁኔታ መሠረት እና በአካባቢው ላይ የሚኖረውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት እንዲሁም ሊደርስ የማችለውን ጉዳት በማገናዘብ ከተቀመጠው ምክንያታዊ ፍጥነት ገደብ በላይ ማንም አሽከርካሪ እንዲያሽከረክር አይፈቀድለትም። በማንኛውም ሁኔታ የተሽከርካሪው ፍጥነት ከሌሎች ተሽከርካሪዎች፣ ግለሰቦች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ማሽኖች ጋር ግጭት በማይፈጥር ሁኔታ ፍጥነት ሉገደብ ይገባል። ተሽከርካሪዎች ሕግ ካልፈቀደ ወይም ተሽከርካሪውን ደህንነቱ በጠበቀ ለማንቀሳቀስ ፍጥነት ዝቅ ማድረግ አስፈላጊ ከሆነበት ጊዜ በስተቀር ማንም ሰው የተቀመጠውን መደበኛ እና ምክንያታዊ የትራፊክ ፍሰትን በሚገድብ ፍጥነት ማሽከርከር የለበትም። ማንም አሽከርካሪ ከተለጠፈውን የፍጥነት ገደብ በላይ ማሽከርከር የለበትም። እስከ ገደቡ ድረስ ደህንነቱ የጠበቀ አሽከርካሪ የትራፊኩ አማካይ ፍጥነት ይጓዛል ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከአማካኝ የትራፊክ ፍጥነት በላይ ወይም ከዚያ በታች በጣም ርቀው ሲያሽከረክሩ ግጭት የመፈጠሩ እድል ከፍተኛ ነው። ገጭት ከፍጥነት ውጭ በሌላ ምክንያቶች በለሻለ ይከሰታል ነገር ግን ፍጥነት የሚደርሰውን ጉዳት እና አደጋ መጠን የከፋ ያደርገዋል።

የፍጥነት ወሰን ሕጎች/ሌላ ምልክት ካልተለጠፈ የዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ ከተሞች የማፈቅዱት ሃያ ማይል በሰዓት ነው የዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች አስራ አምስት ማይል በሰዓት ነው የዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ ትምህርት ቤት አካባቢ አስራ አምስት ማይል በሰዓት ነው መደበኛ አውራ ጎዳናዎች ላይ ከ30-50 ማይል በሰዓት በተከፋፈሉ አውራ ጎዳናዎች ላይ 30-55 ማይል በሰዓት በሀገር-አቋራጭ አውራ ጎዳናዎች 55-75 ማይል በሰዓት ነው

የፍጥነት መልክቶች የፍጥነት ገደብ ምልክቶች የፍጥነት ገደብ ምልክቶች በአራት ማአዘን ቅርጽ ውስጥ በነጭ መደብ በጥቁር ቀለም የተፃፈ ቁጥር ያላቸው ሲሆን በዚህ ውስጥ ተጽፎ የሚቀመጠው ቁጥር በሕግ የሚፈቀደው የፍጥነት ወሰን ነው። ጠቋሚ(የሚመከሩ) የፍጥነት ምልክቶች ጠቋሚ ወይም የሚመክሩ የፍጥነት ምልክቶች በቢጫ ወይም ብርቱካናማ መደብ ላይ በጥቁር ቀለም የተፃፈ ፊደል ያላቸው ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚቀመጡት ከማስጠንቀቂያ ምልክቶች በታች ነው። መካሪ ወይም ጠቋሚ የፍጥነት ምልክቶች በአውራ ጎዳና ጎን ላይ የሚለጠፉ ምልክቶች ሲሆኑ ከዚህ በፍጥነት በላይ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ደህንነትዎን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ሁኔታ ስለመኖሩ ያስጠነቅቃሉ። ምንም እንኳን ጠቋሚ(መካሪ) የፍጥነት ምልክቶች በሕግ ተፈፃሚነት 44


ባይኖራቸውም እርስዎ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ እነዚህን ጠቋሚ ፍጥነትን አልፈው በማሽከርከሪዎ ምክንያት ግጭት ቢፈጠር በአጠቃላይ የፍጥነት ወሰን ሕግን እንደጣሱ ተፈርጎ ይቆጠራል በዚህም ምክንያት ቅጣት ሊጣልብዎ ይችላል።

ባለ ገመድ ወይም ገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች ከሞባይል ስልክ ጋር አገናኝቶ ማሽከርከር ይፈቀዳል። የመስማት ችግር ያለባቸው ግለሰቦች የማዳመጫ መሣሪያ እንዲጠቀሙ ይፈቀዳል።

ሌሎች የትራፊክ ህጎች

የተሽከርካሪ መሣሪያዎች

የደህንነት ቦታዎች የደህንነት ዞን ወይም በመንገዶቻቸው ላይ የእግረኞች መልክት ያለባቸው ቦታዎች ላይ በፍፁም አያሽከርክሩ። ሁልጊዜ ሰዎች በትራፊክ አጠገብ በሚቆሙበት ጊዜ፣ በሚራመዱበት ጊዜ፣ በሚቀመጡበት ጊዜ እንዲሁም ብስክሌተኞች በቅርበት በእርስዎ አጠገብ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ በጥንቃቄ ይለፉ።

ከ1965 ጀምሮ የ U.S. መንግስት ለሽያጭ የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች የተለያዩ የደህንነት መሣሪያዎች ሊኖራቸው እንዲሁም አደጋ እና የአየር ብክለት የሚቀንሱ የመቆጣጣሪ መሣሪያዎች እንዲኖራቸው ያስገድዳል። በፌዴራል ወይም በኮሎምዲያ ዲስትሪክት የተሽከርሪዎች ሕግ መሠረት ከዚህ በታች ያሉትን ድርጊቶች ማከናወን ሕገወጥ ነው፡-

ፍሪሲዮን ይዞ ማሽከርከር

• የህንነት መሣሪያ ወይም ቁሳቁስ ከማንኛውም ተሽከርካሪ፣

ተሳቢ፣ በከፊል ተሳቢ ወይም ከተሳቢ ተሽከርካሪዎች ማለትም በዩናይትድ ስቴትስ ወይም ከኮሎምዲያ ዲስትሪክት ሕግ፣ ድንጋኔ እና ደንብ መሠረት የተገጠሙ መሣሪያዎችን ከተስከርካሪዎች ላይ መንቀል ወይም መቀየር

በዜሮ ማርሽ ወይም ፍሪሲዮን ይዘው ማርሽ ለማስገባት ኪያስፈልገው ጊዜ በላይ ፍሪስዮን ረግጠው አያሽከርከሩ። በፍጥነት መልስ ለመስጠት በሚፈልጉበት ጊዜ የተሽከርካሪዎ ማርሽ ማስገባት እምቢ ሊል ይችላል። የትምህርት ቤት ማቋረጫ መንገዶች ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የማኛውንም የተፈቀደላቸው የትምህርት ቤት መንገድ ማቋረጫ ተቆጣጣሪዎች ወይም የትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች መመሪያ መከተል አለብዎት። የትምህርት ቤት አካባቢ መንገድ ማቋረጫ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ እንቅስቃሴ ተቆጣጣሪዎች የተሽከርካሪዎች የትራፊክ እንቅስቃሴ ማቆም፣ መቆጣጠር እና መምራት ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ተቆጣጣሪዎቹ ትምህርት ቤት አቅራቢያ እንዲሁም እንደ አንድ ክስተቶች በሚካሄዱባቸው ስፍራዎች ወይም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች ላይ ይቆማሉ። ዞሮ መመለስ በሁለቱም አቅጣጫ ማለትም ከፊት እና ከኋላ የሚመጣ ሌላ ተሽከርካሪ ቢያንስ 500 ጫማ ርቀት ባለው ክልል ውስጥ በማይታይበት ሁኔታ በኩርባዎች ወይም በዳገታማ ቦታዎች ላይ ዞሮ መመለስ የተከለከለ ነው። የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ሕግ የትራፊክ መብራት ባለባቸው መስቀለኛ ወይም እግረኛ ማቋረጫ ያለው መስቀለኛ ቦታዎች ላይ ዩ ተርን ማድረግ ይከለክላል። ጭንቅላት ላይ የሚታሰር ፣ ባለ ገመድ ወይም ገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች አድርጎ ማሽከርከር የተከለከለባቸው ቦታዎች ማንኛውም ግለሰብ ተሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ ከሬድዮ፣ ከቴፕ ከሲዲ ወይም ከሌላ የድምጽ መሣሪያ ጋር የተገናኘ የጆሮ ማዳመጫዎች አድርጎ ማሽከርከር አይፈቀድም።

• ከ1968 ጀመሮ በተመረቱ ተሽከርሪዎች ላይ የተገጠሙ

ማንኛውንም የደህንነት ሥርዓት እንዲሁም የተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች ማለትም እንደ ካታላይቲክ ኮንቨርተር የጋዝ ታንከር መሙያ ወይም የክራንክ ቤት ወይም የተሽከርካሪ የአየር ሥርዓት መሣሪያዎችን መንቀል፣ መቀየር ወይም በሌላ መንገድ እንዳይሰራ ማድረግ የተከለከለ ነው፥ በተለይም የፌዴራል ወይም የዲስትሪክቱ ሕግ ተሽከርካሪዎች አንዲህ ያሉ መሣሪያዎች እንዲኖራቸው በሚደነግጉበት ጊዜ መሣሪያዎቹን ከተሽከርካሪዎች ላይ መንቀል በሕግ የተከለከለ ነው።

የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶ ሕጎች /ይታጠቁ ወይም ይቀጡ ከ1997 ጀምሮ ሕጎች ከረቀቁ በኋላ በሀገሪቱ ደረጃ ዲስትሪክቱ ጠንካራ እና ሀሉን አቀፍ የደህንነት መጠበቅያ ቀበቶ ህግን ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም ጊዜ በኋላ የደህንነት መጠበቅያ ቀበቶ መጠቀም ዝንባሌ በ24 በመቶ ጨምሯል። ጉዳቶች ለመከላከል ተችሏል። ሕይወት ለማዳን ተችሏል የደህንነት ቀበቶ ለመታጠቅ ጥቂት ደቂቃ የሚወስድ ተግባር ነው። በጣም ቀላል ነው። ቢሆንም ግን ይህ ቀላል ተግባር የእርስዎን እና የሌሎችን የሚሳሱላቸው ሰዎች ሕይወት ለማዳን ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የደህንነት ቀበቶ መታጠቅ ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ የእርስዎን ሕይወት ለማዳን በከፍተኛ ይጨምራል። በተጨማሪም በስካር፣ በድካም ወይም አደገኛ(ሞገደኛ) የአሽከርካሪን የሚከላከሉበት የተሻለ መሣሪያ ነው። 45


የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶዎች የግድ ማድረግ አለባቸው የኮሎመቢያ ዲስትሪክት ሕግ መሰረት በተሽከርካሪ፣ በጭነት ተሽከርካሪ፣ በትራክተር፣ ለተለያዩ አገልግሎት በሚውሉ ተሽከርካሪዎች ወይም በተጓዦች ባሶች ውስጥ የሚጓጓዙ ተሣፋሪዎች በሙሉ የደህንነት ቀበቶ እንዲታጠቁ ይጠይቃል። እያንዳንዱ ተሳፋሪ የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶን ካልታጠቀ በስተቀር ተሽከርካሪውን ማሽከርከር አይፈቀድም። ይጎተታሉ ልክ እንደሌሎች ግዛቶች የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ሕግ አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች በትክክል ቀበቶ ባለማሰራቸው ምክንያት እንዲቆሙ ፖሊሶች ወይም ትራፊኮች ማስቆም እንዲችሉ ፍቃድ ይሰጣል። የ50 ዶላር ቅጣት እና 2 ነጥብ አሽከርካሪዎች እና ከፊት እና ከኋላ ያሉ ሁሉም የተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ከልዩ ፍቃድ ውጭ ቀበቶ ባለማሠራቸው ምክንያት የሚጣልባቸው ቅጣት ነው። አሽከርካሪዎች የሁሉንም ተሳፋሪዎች ቀበቶ የማሳሰር ኃላፊነት ነው።

ደህንነት መጠበቂያ ቀበቶ ካልታሰሩ በስተቀር እንዲጓዙ አይፈቅድም።

የአየር ቦርሳዎች(Air Bags) የአየር ቦርሳዎች አጅግ አስፈላጊ የደህንነት መሣሪያ ናቸው። ተሽከርሪዎች እና ተሳፋሪዎች በሚቀመጡበት ጊዜ የደረትና የወገብ ቀበቶ አድርገው ራቅ ብለው ሲቀመጡ በተሻለ ሁኔታ ይጠቅማሉ። አማብዛኛዎቹ የአየር ቦርሳዎች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የሆኑ የፊት ለፊት ግጭት አደጋዎች በማፈጠሩበት ጊዜ እንዲነፉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። አንዳንድ ዝቅተኛ ፍጥነትን ተከትሎ የሚፈጠሩ አደጋዎች ጉዳት ሊያጋጥም ቢችልም ግን የአየር ቦርሳዎች ለመከላከል የተሰሩበት ጉዳት ግን አያጋጥመም። የአየር ቦርሳዎች ባለቸው ተሽከርሪዎች ውስጥ ቢሆኑም ሁልጊዜ የደረትና እና የወገብ የደህንነት ቀበቶ መታጠቅ አለባቸው። የአየር ቦርሳዎች ሂወት የማዳን አቅሙ ለመጨመር ከዚህ በታች ያሉትን ይከተሉ፡• በማንኛውም ጊዜ የወገብ እና የትከሻ ቀበቶ በመጠቀም

የደህነት ቀበቶ በአግባቡ ይታጠቁ

አካላዊ ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች

• ነፍጡር ሴቶች በተሻለ መጠን የደህንነት ቀበተውን

በአካላዊ ጉዳት ወይም በሌላ የጤና ምክንያት የመቀመጫ ቀበቶ እንዳያስሩ የሚከለክል ጽሁፍ ፍቃድ ከተሰጠው ፍቃድ ያለው የጤና ባለሙያ ከተጠሰዎ ወይም በጤና ባለሙያ ተረጋግጦ በጤና ባለሙያ የተረጋገጠ ማሰረጃ ካለዎት የመቀመጫ ቀበቶ እንዲያስሩ አይገደዱም። በሕክምና ተቋም የሚሰጠው ምስክር ወረቀት የደረሰውን አካላዊ ጉዳት ተፈጥሮ እንዲሁም የደህንነት ቀበቶ ማድረግ ለምን እንደተከለከለ የሚገልጽ ምክንያት ሊኖረው ይገባል። ይህ ምስክር ወረቀት በተሽከርካሪው ውስጥ ሊቀመጥ ይገባል። እነዚህን ሕጎች የሚጥስ ማንኛዋም ግለሰብ የሕግ ቅጣት ይጣልበታል።

ከሆዳቸው በታች ዳሌያቸው ጋር የእግራቸው ላይኛው ክፍል ላይ ቢያሳርፉ ይመከራል።

• መሪ ካለበት ስፍራ በቻሉት መጠን ራቅ ብለው ይቀመጡ፤

በመሪው እና በደረትዎ መካከል ከ10-12 ኢንቶች ርቀት ይጠብቁ።

• 12 አመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች በኋላ ወንበር

ለእድሚያቸው የሚመች የልጆች የደህንነት ቀበቶ ታስሮላቸው ሊቀመጡ ይገባል።

• ጨቅላ ህፃናት በተሽከርካሪ የአየር ቦርሳ ባለው ፊተኛው

መቀመጫ ላይ ከተጓዦች ጎን መቀመጥ የለባቸውም።

የጭንቅላት መከላከያዎች

• እነዚህን የደህንነት አካሄዶች መከተል ከባድ የሚሆንብዎት

የጭንቅላት መከላከያ የሚገጠመው ተሽከርካሪ ከኋላ በሚመታበት ጊዜ ሊደርስ የማችለውን የአከርካሪ አጥንትና የጀርባ ጉዳት ለመከላከል ነው። ማሽከርከር ከመጀመሩ በፊት የጭንቅላትዎ ማረፊያ በመቀመጫዎ ላይ በቀጥታ ከመከላከያዎ ጋር አቀማመጥ መቀመጥወን ያረጋግጡ። ይህ የአቀማመጥ ሁኔታ እንደአሽከርካሪዎች የሚለያይ ሲሆን ይህም እርስዎን በከፍተኛ ደረጃ ለመጠበቅ በሚረዳ መልኩ ያስተካክሉ። አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ከፍ ያለ የወንበር መደገፍያ ያላቸው ሲሆኑ ለማስተካከል አስቸጋሪዎችም ናቸው።

ከሆነ የአየር ቦርሳዎች እንዳይሰሩ ማጥፋት የተሻለ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በታች በተገለፁት ስጋት ቡድን ውስጥ የሚመደቡ ሰዎች ማጥፊያ ማብርያ ባለው የአየር ቦርሳዎች ማስገጠም አለባቸው። ■ በልጆች ደህንነት መጠበቂያ ቀበቶ አማካኝነት ታስረው ፊተኛው ወንበር ላይ የሚቀመጡ ልጆች የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች

የልጆች ደህንነት ቀበቶ

■ በፊተኛው የተሳፋሪ ወንበር ላይ ከ12 አመት በታች የሆኑ ልጆችን ጭነው የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ማንኛውም አሽከርካሪ ከ3 አመት በታች የሆኑ ልጆችን በተሽከርሪ ኋለኛው መቀመጫ በልጆች

■ የአቀማመጥ ቦታቸውን መቀየር የማይችሉ አሽከርካሪዎች እና በመሪ እና በእነሱ መካከል 10 ኢንች 46


ርቀት መጠበቅ የማይችሉ አሽከርካሪዎች

• ከፊት መንገድ እንደተዘጋ የሚያሳይ ምልክት በሚያዩበት

ጊዜ ወተደዘጋው መንገድ በሚሄደበት ጊዜ ዝግጅት አድርገው ይሂዱ።

■ በሀኪም ትዕዛዝ አማካኝነት ባለባቸው በጤና ችግር ምክንያት በግጭት ጊዜ የአየር ቦርሳዎች ሲሰሩ ጭንቅላታቸው፣ አንገታቸው ወይም ደረታቸው ላይ ጉዳት ሊያመጣባቸው የሚችልባቸው አሽከርካሪዎች

• የዝቅተኛ የፍጥነት ገደቦችን ይመልከቱ ። • ሌሎች አሽከርካሪዎች የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች

በመከታተል ድንገተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ያስወግዱ። ከመስመርዎ ወደ ሌላ መስመር በሞገደኛ አካሄድ አይጓዙ። ከጀርባዎ ያለው ተሽከርካሪ ፋጥነትዎን ለመቆጣጠር ጊዜ እንዲያጠኝ ቀስ በቀስ ፍሬንዎን ይያዙ። ከትራፊክ ፍሰት ጋር ይቀጥሉ።

የሥራ ቦታዎች የሥራ ዞን የሚባለው በመንገድ ላይ ወይም በመንገድ አካባቢ ግንባታ፣ ጥገና ወይም የግልጋሎት ሥራዎች የሚከናወንበት ነው። የሥራ ቦታዎችአንዳንድ ጊዜ ስለማይታዩ ወይም ይኖራሉ ተብለው ስለማይገመቱ እና አንዳንድ ጊዜ መደበኛው የትራፊክ ፍሰት ሊከለክሉ ስለሚችሉ ከፍተኛ ክህሎት ላላቸው አሽከርካሪዎች እንኳን ተግዳሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ለአሽከርካሪዎች እና ለእግረኞች እና ለሰራተኞች ደህንነት ሲባል እንዚህ ቦታዎች ሲጠጉና ሲያልፉ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድያደርጉ አስፈላጊ ነው። እንደዚ ባሉ ቦታዎች ልዩ የሥራ ዞን የትራፊክ ምልክት እና ሌሎች መሣሪያዎች እነዚህ ቦታዎች ሳይደርሱ እና ከለፉም በኃላ መቀመጥ አለባቸው። እንዲህ ያሉት ዞኖች ተንቀሳቃሽ(አስፋልት መንገድ አልፎ አልፎ በሚጠገንበት አቅጣጫ) ወይም ጊዜያዊ(ድልድይ በሚሰፋበት ቦታ) ሊሆኑ ይችላሉ።

• ያልተለመዱ የመንገድ ሁኔታዎች፣ ለምሳሌ ከሮኮንች፣

የብረት ንጣፎች፣ አንድ እይነት ያልሆኑ የአስፋልት መንገድ መስመሮች እና የመንገድ ጠርዝ ጉድጓዶችን ይጠንቀቁ። እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለመቆጣጠር ሁኔታዎች ከባድ እንዲሆኑ ሊያደርጉ ይችላሉ። ሂደታዊ የሆነ እንዲሁም ቀስ በቀስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ማንኛውም ሁኔታ አካሄድዎን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።

• በተሽከርካሪዎች መካከል ምክንያታዊ የሆነ ፍጥነት እና

ክፍተት ይጠብቁ። በፍጥነት ወይም ተጠግተው እየተጓዙ ከሆነ ከፊት ያለ ተሽከርካሪ ፍጥነት ሲቀንስ እና ሲቆም ተሽከርካሪዎን ለማቆም ክፍተት ሊያጡ ይችላሉ።

አብዛኛውን ጊዜ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ምልክቶች፣ ተለዋዋጭ መልዕክቶች የሚያሳዩ ምልክቶች፣ ቀስቶች፣ ምልክቶች እና ወይም መንገድ የሚመሩ መሣሪያዎች (ኮኖች፣ ከበሮዎች፣ የተለያየ ቅርጽ ያላቸው መሣሪያዎች እና የመሳሰሉት) በስራ መንገድ ላይ የሚቀመጡ ናቸው። የስራ ቦታዎች የትራፊክ ማስጠንቀቅያ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ ብርቱካናማ ቀለም ያላቸው ናቸው።

• ሰራተኞች እና ሌሎች መንገድ የሚጋሩ ሰዎች እንቅስቃሴ

በመመልከት በትዕግስት ያሽከርክሩ። በማንኛውም ጊዜ ሥራ በሚሰራባቸው ቦታዎች ላይ ትራፊክ እንዲቆም ይደረጋል። ይህም አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠረው ከሌላ አቅጣጫ የሚመጣው ተሽከርካሪ አንዲት ነጠላ መንገድ በመጠቀም ስለሚያቋርጥ ወይም ስለሚታጠፍ በመሆኑ ወይም ሰራተኞች እና መሣሪያዎች መንገድ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በተሽከርካሪዎች ማለፍ እጅ አደገኛ ሊሆን ይችላል። እንዲህ ያሉ ቦታዎች ላይ ጊዜያዊ የትራፊክ ምልክቶች ሊኖሩ ወይም የትራፊክ ፖሊሶች ቆመው አቅጣጫ መጠቆም ይኖርባቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ የሰለጠኑ እና ሙያው ላይ የተሰማሩ ጠቋሚዎች STOP/SLOW የመሚለል በመያዝ እንዲቆሙ፣ በዝግታ እንዲያሽከረክሩ ሊመርዎት ወይም የትራፊክ እንቅስቃሴን አቅጣጫ ሊያሳይዎት ይችላሉ።

ሥራ የሚሰራባቸው ቦታዎች ጋር በሚደርሱበት ጊዜ ወይም በሚጠጉበት ጊዜ አካሄድዎን መቀየር እንዲሁም በዝግታ ማሽከርከር ወይም መቆም ሊኖር ስለሚችል ንቁ መሆን ይኖርብዎታል። አንዳንድ ጊዜ በመታጠፊያ ወይም ቁልቁለታማ ቦታዎች ላይ የቆመ ተሽከርካሪ ላይታይ ይችላል። በመሆኑም እንደ ኮኖች፣ መጋጫዎች፣ መዝጊያዎች፣ ቀለማት እንዲሁም የትራፊክ ምልክቶች እና ሌሎች መሣሪያዎች ደህንነትዎ በጠበቀ መልኩ እንድያልፉ የሚያስችሉ ስለሆነ ጥንቃቄ ያድርጉ። የፖሊስ እና ጠቋሚ ጠባቂዎችን መመሪያ ይከተሉ።

47


የመብራት ምልክቶች፣ ምልክቶች እና የጽሁፍ ምልክቶች የመቆጣጠሪያ ምልክቶች እነዚህ ምልክቶች አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን እንዲገድቡ እና ሌሎች ሕግ እና ድንጋጌዎችን የሚያስተምሩ ምልክቶች ናቸው። የፍጥነት ገደቦች ሥራ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ሊቀንሱ ይችላሉ።

የማስጠንቀቂያ ምልክቶች የማሰጠንቀቂያ ምልክቶች አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩባቸው ቦታዎች ወይም በሥራ አቅራቢያዎች ላይ የሚኖሩ ያልተለመዱ ወይም አደጋ ሊያደርሱ ስለሚችሉ ሁኔታዎች የሚያስጠነቅቁ ወይም የሚያነቁ ናቸው። እነዚህ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ አውራ ጎዳና እና የሥራ አካባቢዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን ብርቱካናማ ቀለም ያላቸው እና በአልማዝ ቅርጽ ውስጥ የሚዘጋጁ ናቸው።

አቅጣጫ መሪ መሳርያዎች መዝጊያዎች፣ ኮኖች እና ከበሮዎች ሥራ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ላይ አሽከርካሪዎች ደህንነታቸው ጠብቀው ለመምራት ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው። በምሽት ጊዜ ለእይታ እነዚህ መሣሪያዎች የሚያንፀባርቁ ሊገጠምላቸው ይችላል።

ተለዋዋጭ መልዕክት የሚያሳዩ ምልክቶች አነዚህ የኤሌክትሮኒክ ምልክቶች ሲሆኑ ስለ መንገድ ሁኔታ፣ የትራፊክ ችግር፣ ድንገተኛ ሁኔታ፣ ልዩ ሁኔታ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያሳዩ ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ሥራ በሚሰራባቸው ቦታዎች ልዩ ሁኔታዎችን ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የቀስት ፓነሎች ቀስቶች በምሽት እና በቀን ጊዜ በቅድሚያ ስለ አቅጣጫ እና ስለመንገድ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ለመስጠት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ ወይም ወደሌላ መስመር ለመዘዋወር አስፈላጊ ምልክቶች ናቸው።

የትራፊክ መብራቶች የትራፊክ ምልክቶች በመንገድ ወይም በአውራ ጎዳና ላይ ለሚራመዱ፣ ብስክሌት ለሚያሽከረክሩ ወይም ተሽከርካሪ ለሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ ተፈፃሚነት ያለው ነው። እነዚህን የትራፊክ ምልከቶች አለማክበር ከፍተኛ ለሆነ ግጭት መንስኤ ናቸው። በትራፊክ መቆጣጠሪያ መሣሪያ ቁጥጥር የሚደረግባቸው መስቀለኛ ቦታዎች ላይ በሚቃረቡበት ጊዜ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች መመሪያን ለመሸሽ በግል ይዞታዎች ለምሳሌ የነዳጅ ማደያዎች፣ የሱቅ

ፓርኪንግ ቦታዎች ወዘተ ማሽከርከር ወይም መንገዱን መተው ክልክል ነው። አብዛኛውን ጊዜ የትራፊክ ምልክቶች ከላይ ወደ ታች ወይም ከግራ ወደ ቀኝ ቀይ፣ ቢጫ እና አረንጓዴ ቀለም ያላቸው ናቸው። በአንዳንድ መስቀለኛዎች እነዚህ ምልክክቶች በተናጠል፣ ቀይ፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ መብራቶች ብቻ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። አንዳንድ የትራፊክ ምልክቶች በርተው የሚቆዩ አንዳንዶቹ እየበሩ የሚጠፉ ናቸው። አንዳንዶቹ ክብ ናቸው, እና አንዳንዶቹ ቀስቶች ናቸው። ሕጎች የትራፊክ መብራት ወይም መቆጣጠሪያዎች በማይሰሩበት እና በሚበላሹበት ጊዜ ቁም የሚል ምልክት እንደሚቆሙ ሙሉ በሙሉ አንዲቆሙ ያዛሉ። በትራፊክ ፖሊስ ካልተመሩ በስተቀር እነዚህ ቦታዎች ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ለባለመንገዱ ቅድሚያ በመስጠት ይቀጥሉ።

በርቶ የሚቆይ የቀይ መብራት ምልክት ቁም። የተለያዩ መስቀለኛ መንገድ ከመድረስዎ በፊት ቁም የሚል መስመር ካለ እዛው ሙሉ በሙሉ ማቆም ይጠበቅብዎታል። ከሌለ ከእግረኛ መሻገሪያ መንገድ ላይ ሳይደርሱ መቆም እና የቀይ መብራት ምልክት እስኪጠፋ ድረስ መቆም ይጠበቅብዎታል። ሙሉ በመሉ ከቆሙ በኋላ በቀይ መታጠፍ የማይከለክል ምልክት ከሌለ ወደ ቀኝ ሊታጠፉ ይችላሉ። ቀይ መብሪት በርቶ በሚታጠፉበት ጊዜ ቅድሚያ ለእግረኞች፣ ለብስክሌተኞች እንዲሁም ለሌሎች ትራፊኮች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅብዎታል። በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ቀይ በሚበራበት ጊዜ ወደ ግራ መታጠፍ ሕገወጥ ነው።

በርቶ የሚቆይ የቢጫ መብራት ምልክት ይህ ማለት መብራት ከአረንጓዴ ወደ ቀይ እየተቀየረ ነው ማለት ነው። የዚህም መብራት አላማ እየቀረቡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆሙ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ደግሞ ቀይ ከመብራቱ በፊት ከመንገድ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ጊዜ መስጠት ነው።

በርቶ የሚቆይ የአረንጓዴ መብራት ምልክት ሌሎች ተሽከርካሪዎች ከመንገድ መውጣታቸውን አይተው በጥንቃቄ ይለፉ ማለት ነው። ለደፊት ለማሽከርከር ምቹ በሚሆንበት ጊዜ ሌሎች ምልክቶች ወይም ተጨማሪ መታጠፍን የሚከለክሉ ምልክቶች ከሌሉ በስተቀር ወደ ፊት ለፊት መሄድ ወይም መታጠፍ ይችላሉ። መስቀለኛ ውስጥ ላሉ እግረኞች እና ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅብዎታል። 48


በርቆ የሚቆይ የቀይ መብራት ቀስት ምልክት

እየበራ የሚጠፋ ቢጫ ምልክት

ቁም። ቀስቱ ወደሚያመለክተው አቅጣጫ ከመድረስዎ በፊት መስቀለኛው፣ የቁም ምልክት መስመር ወይም እግረኛ ማቋረጫ ቀድመው ሙሉ በመሉ ይቁሙ። የበራው ቀይ የአቅጣጫ ምልክት እስከበራ ድረስ ሙሉ በሙሉ ይቁሙ።

ፍጥነት ቀንሰው በጥንቃቄ ይለፉ።

በርቶ የሚቆይ የቢጫ ቀስት ምልክት ልክ በርቶ አንደሚቆየው ቢጫ የመብራት መልክት ቢጫ የቀስት መልክት ማለት መብርት ካአረንጓዴ ወደ ቀኝ እየተቀየረ ነው ማለት ነው። የዚህም መብራት አላማ እየቀረቡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆሙ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ደግሞ ቀይ ከመብራቱ በፊት ከመንገድ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ጊዜ መስጠት ነው።

የተረጋጋ በርቶ የሚቆይ የአረንጓዴ ቀስት ምልክት ቀስቱ ወደ ሚያመለክተው አቅጣጫ በጥንቃቄ ይቀጥሉ። መንገድ ላይ ላሉ እግረኞች እና ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠትን ያስታውሱ።

እየበራ የሚጠፋ የቀይ መብራት ምልክት

በርካታ የመብራት ምልክቶች እነዚህ ምልክቶች በአረንጓዴ መብራት የግራ መታጠፊያን ለመፍቀድ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምልክቶች ናቸው።

የመስመር መጠቀምያ መብራት ምልክቶች በቀን ውስጥ በተለያየ ጊዜ የመንገድ አቅጣጫ በመገልበጥ የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው። መስመሮቹ እና አቅጣጫቸው በምልክቶች ወይም የመብራት ቀስቶች ለመሩ ይችላሉ። የ"X" ምልክት በቀይ በሚበራበት መስመር ላይ ማሽከርከር በፍጹም የለብዎትም። አረንጓዴ አቅጣጫ ምልክት በሚበራበት ጊዜ ለማሽከርከር ፍቃድ ተሰጥቶታል። በርቶ የሚቆይ ቢጫ የ"X" ምልክት ማለት አሽከርካሪው በተቻለ ፍጥነት ከመንገድ ለቆ መውጣት አለበት ማለት ነው። እየበራ የሚጠፋ ቢጫ የ"X" መብራት ምልክት ማለት አሽከርካሪ መንገድ በመጠቀም ወደ ግራ ለመታጠፍ ፍቃድ ያለው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከተቃራኒ አቅጣጫ ወደ ግራ የሚታጠፍ ተሽከርካሪው መስመሩን በጋራ የመጠቀሙ እድል ከፍተኛ ነው።

ሙሉ በሙሉ ቆመው ለሌሎች ተሽከርካሪዎች እና እግረኞች ቅድሚያ ይስጡ። መንገዱ ክፍት ሲሆን ይቀጥሉ።

የባቡር ማቋረጫ መንገድ ላይ እየበራ የሚጠፋ የቀይ መብራት ምልክት እየበራ የሚጠፋ የቀይ ምልክት ባቡር እየመጣ ስለመሆኑ በደወልም ጭምር የሚያሳውቅዎ ማስጠንቀቂያ ነው። በመሆኑም በዚህ ጊዜ ቆመው ባቡሩ እስኪያልፍ ጠብቀው ሌላ ባቡር አለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ ማለፍ ይኖርብዎታል። የባቡር ማቋረጫ ጋር በሚደርሱበት ጊዜ ይህ የማስጠንቀቂያ ሠብራት ይሁን በር ሥርዓት በሌለበት ቦታ ሲደርሱ ፍጥነትዎን ቀንሰው ከሐዲዱ በፊት በማቆም የሚመጣ ባቡር ማየትና ማዳመጥ ያስፈልጋል። ባቡሮች እኛ ከምናያቸው ርቀት በላይ በፍጥነት የሚሄዱ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች ለመቅደም መሞከር የለባቸውም። መንገድ ላይ በነጭ የ"X" ወይም የ"RR" ምልክት ካለ ወደ በፍጥነት የሚጓዝና ቶሎ መቆም የማይችል የባቡር ማቋረጫ መስመር ላይ እንደደረሱ ወድያው መቆም ይጠበቅቦታል።

49


ምልከቶችን በቅርጽ እና በቀለም መለየት ምልክቶችን በቅርፃቸው እና በቀለሞቻቸው እንዲሁመ በውስጣቸው ባሉ ቃላት፣ ቁጥሮች ወይም ምልክቶች መለየት አለብዎት።

የምልክት ቀለሞች የመንገድ ቀለም ምልክቶች በሚመለከቱበት ጊዜ ምን አይነት መረጃ እንደሚያስተላልፉ ማወቅ ይቻላል።

ብርቱኳናማ የግንባታ እና የጥገና ሥራዎች አካባቢ ማስጠንቀቂያ።

ቀይ ቁም፣ ቅድሚያ ስጥ፣ እንዳትግባ ወይም የተሳሳተ መንገድ

አረንጓዴ ሊመሩ የሚችሉ መረጃዎች ማለትም እንደ ርቀት እና አቅጣጫ

ቢጫ በአጠቃላይ ከፊት ስላለው እንደ ትምህርት ቤት ወይም የእግሮኞች መንገድ ማቋረጫ ምን መጠበቅ እንዳለብን የሚያስጠነቅቅ ነው።

ሰማያዊ የሞተር አገልግሎቶች

ነጭ

ቡኒ

አስገዳጅ ምልክቶች ማለትም እንደ ፍጥነት ወሰን ወይም የፓርኪንግ መመሪያዎች።

የመዝናኛ እና ባሕላዊ ክንውኖች አካባቢዎች

የምልክት ቅርጾች አራት ማዕዘን፡ አስገዳጅ ወይም መመርያ ሲጪ

የትራፊክ ምልክቶች ቅርጾች እንደቀለም የምልክቶቹ መልዕክት ምን መሆኑን የሚጠቁሙ ናቸው። አንዳንድ ማየት አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎች ለምሳሌ ከፍተኛ ጭጋግ ባለባቸው ቦታዎች መመልከት የሚችሉት የምልክቱን ቅርጽ ብቻ ሊሆን ይችላል።

መመርያና እና ስለህጉ ለመናገር ወደ ላይ ቀጥ ያለ ምልክት ይጠቀማሉ ወደ ጎን የተቀመጡ ሲሆኑ ትርጉማቸው አቅጣጫን ወይም መረጃን መስጠ ነው።

ኦክታጎን(8 መአዘን)፡ ማቆም

ፔንታጎ(ባለ 5 ጎን)፡ ትምህርት ቤት እና የትምህርት ቤት መንገድ ማቋረጫ

ኦክታጎን ወይም ባለ 8 ማዕዘን ቅርጽ ሁልጊዜ ቁም ማለት ነው። ይህንን ምልክት በሚያዩበት ጊዜ ምልክቱ፣ የቁም ምልክት መስመር፣ የእግረኛ ማቋሰጫ ላይ ወይም ወደ መስቀለኛ ከመግባትዎ በፊት ሙሉ በሙሉ መቆም አለብዎት።

ፔንታጎን (ባለ 5 ጎን ቅርጽ) ስለ ትምህርት ቤት ቦታዎች እና ስለ ትምህርት ቤት ማቋረጫ መንገዶች መረጃን ይሰጣሉ። ክብ፡ የባቡር መንገድ ማስጠንቀቂያ

ሶስት ማዕዘን፡ ቅድሚያ ስጥ

ከፊት ለፊት የባቡር ማቋረጫ መኖሩን ለመጠቆም ጥቁር በቢጫ መደብ ይጠቀማሉ።

ፍጥነት ይቀንሱ ካስፈለገ ይቁሙ እና መንገዱን በማቋረጥ ላይ ላለ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ይስጡ። አልማዝ፡ ማስጠንቀቂያ እነዚህ ምልክቶች ከፊትዎ ስላሉ ልዩ ሁኔታዎች ወይም አደጋዎች የሚያስጠነቅቁ ናቸው። በዚህም ጊዜ ፍጥነትዎት ሊቀንሱ ይችላሉ እና ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል። 50


የመቆጣጠሪያ ምልክቶች ማቆም

በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች

ወደ ቁም ምልክት በሚመጡበት ጊዜ ወደ መቆሚያ መስመር ከመግባትዎ በፊት ሙሉ በሙሉ መቆም ይኖርቦታል። የመቆሚያ መስመር ከሌለ ማቋረጫ መንገድ ላይ ከመድረስዎ በፊት መቆም አለብዎት። የመንገድ ማቋረጫ ከሌለ ከተለጠፈው የቁም ምልክት በፊት መቆም አለብዎት ከማለፍዎም በፊት በመንገድ ላይ ሊያቋርጥ ለሚችል ለማንኛውም እግረኛ ወይም ሳይክል ቅድሚያ በመስጠት ማለፍ ይኖርብዎታል። መንገዱ ክፍት መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ በጥንቃቄ ይለፉ በዚህም ጊዜ መንገዱ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኑን ያረጋግጡ።

እነዚህ ምልክቶች በምልክቶቹ ላይ የተገለፁትን የተሳፋሪ ቁጥር ለሚያጓጉዙ ባሶች እና ተሽከርካሪዎች ለማስተናገድ የተያዙ ናቸው። ቀጥታ ወደ ቀኝ መታጠፍ ይህ መንገዱ ከፊት ወደ ቀኝ በቀጥታ የሚታጠፍ መኖሩን ያሳያል። የቀኝ ኩርባ ከፊት ወደ ቀኝ የሚዞር ኩርባ መኖሩን ያሳያል። የቀኝ እና የግራ ቀጥታ መታጠፊያዎች ከፊት ለፊት ያለው መንገድ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ የሚጠማዘዝ መንገድ ነው።

ቅድሚያ ስጥ ቅድሚያ ስጥ ምልክት ጋር በሚደርሱበት በፊት ፍጥነትዎን ይቀንሱ። ወደ ግራ እንዲሁም ወደ ቀን እንደገና ወደ ኋላ ይመልከቱ። ለማንኛውም እግረኛ፣ ብስክሌተኛ ወይም ተሽከርካሪ ቅድሚያ ይስጡ። ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ መቀጠል ይችላሉ

የማስጠንቀቂያ የትራፊክ ምልክት አብዛኛዎቹ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ጥቁር እና ቢጫ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የአልማዝ ቅርጽ አላቸው። ምልክቱ ዝግ ብለው ሌሎች ምልክቶች እና መልዕክቶችን እንዲከተሉ የሚያሳስብ ነው።

የፍጥነት ወሰን

ከፊት ለፊት የቁም ምልክት አለ

እነዚህ ምልክቶች የትራፊክ ፍሰትን ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ይውላሉ። ይህ ምልክት በተለጠፉባቸው ቦታዎች ከፍተኛው የፍጥነት ገደብ ያሳውቃሉ።

ከፊት ለፊት የቁም ምልክት ስላለ ፍጥነትዎን በመቀነስ ዝግጁ ይሁኑ። 4-WAY STOP(4-አቅጣጫ ቁም)

ፓርኪንግ ማቆምን የሚከለክሉ በርካታ የፓርኪንግ ምልክቶች ይኖራሉ።

4-WAY

ከፊት ያለ መንገድ መጠቀም እነዚህ ምልክቶች መታጠፍ በሚፈለግበት ጊዜ ወይም ያልተፈቀዱ የመተጠፍ እንቅስቃሴዎች የሚፈቀዱበትን ሁኔታ የሚያሳውቁ ምልክቶች ናቸው።

ይህም ምልክት ማለት መስቀለኛ መንገድ ላይ 4 የቁም ምልክት መኖሩን ያሳያል። ከሁሉም አቅጣጫ የሚመጡ እንቅስቃሴዎች በሙሉ መቆም አለባቸው። መጀመሪያ የቆመ ተሽከርካሪ በመጀመሪያ እንዲሄድ ይደረጋል። ሌሎች የቀሩት አሽከርካሪዎች ተራቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል። አንዳንድ ጊዜ 3-WAY፣ 5-WAY ወይም ALL-WAY የሚሉ ምልክቶችን ሊያገኙ ይችላሉ። የትራፊክ መብራት ከፊት ለፊት ፍጥነትዎን በመቀነስ ከፊት ባለው የትራፊክ መብራት ምልክት ላይ ለመቆም ይዘጋጁ።

51


ቅድምያ ይስጡ ከፊት ለፊት

የመስቀለኛ ውህደት

ፍጥነትዎን በመቀነስ ከፊት ለፊት ያለው ቅድሚያ ይስጡ ምልክት ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ለመቆም ወይም ለትራፊክ ፍሰት ምቹ እንዲሆኑ ፍጥነትዎን ማሻሻል ይዘጋጁ።

ወደ አንድ አቅጣጫ የሚሄዱ ሁለት የተለያዩ መስመሮች ከፊት ለፊት አንድ መስመር ይሆናሉ። በመሆኑም በሁለቱ መስመር ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ለማዋሐድ ኃላፊነት አለባቸው።

ጠመዝማዛ መንገድ

"T" መስቀለኛ

ከፊት ያለው ተደጋጋሚ የሆነው ከባድ ኩርባዎች ያለው መሆኑን ያሳያል። ፍጥነትዎን ያስተካክሉ።

ከፊት ለፊት መንገዱን ያበቃል። በመሆኑ ፍጥነትዎን በመቀነስ ለመቆም ወይም ከመታጠፍዎ በፊት ቅድሚያ ለመስጠት ይዘጋጁ።

የጎን መንገድ ወደ አውራ ጎዳና ከቀኝ የሚገባ መንገድ አለ። በመሆኑም ወደ መንገዱ የሚገባ ወይም ከመንገዱ የሚወጣ ተሽከርካሪ መኖሩን ለመመልከት ፍጥነትዎን ያስተካክሉ።

የሚመከር ፍጥነት 35

የመንገድ ማቋረጫ ሌላ መንገድ አውራ ጎዳናውን ያቋርጣል በመሆኑም አስገዳጅ እና የመብራት ምልክቶችን ለማክበር ንቁ ይሁኑ።

ይህ ከሌሎች ማስጠንቀቂያ ምልክቶች በታች የሚነጠፍ በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚገኝ ከፍተኛ የሚመከረው ፍጥነት ስንት እንደሆነ የሚያሳውቅ ነው። የተገለፀውን ፍጥነት ለማክበር ፍጥነትዎን ይቀንሱ። "Y" መስቀለኛ መንገድ ከፊት ለፊት ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ የሚገነጠል መንገድ ይዘጋጁ። ፍጥነትዎን ቀንሰው በንቃት የትራፊክ ፍሰትን ይከተሉ።

ማለፍ አይቻልም ቦታዎች በዚህ ቅርጽ ማለፍ አይቻልም የሚለውን ምልክት አስገዳጅ ማለፍን የሚከለክል DO NOT PASS ምልክት ነው። አብዛኛውን ጊዜ ምልክቱ በገራ ጎን በኩል ሲሆን ማለፍ የማይቻልባቸው ቦታ ላይ እንዳይገቡ ቀድሞ ይጠቁማል።

የተከፋፈለ የአውራ ጎዳና መጀመሪያ ከፊት ለፊት ያለው አውራ ጎዳና ወደ ሁለት የተለየዩ መንገዶች በደሴት ወይም በአካፋይ ይለያያሉ እና ሁለቱም የአንድ አቅጣጫ መንገድ ናቸው። የቀኝ መስመር ይያዙ

የመውጫ ፍጥነት ቀቋሚ

ከፊት ለፊት የተከፋፈል አውራ ጎዳና መብቂያ

ለመግባት ወይም ለመውጣት የሚመከረውን ከፍተኛ ፍጥነት ያሳውቃል።

ከፊት ለፊት አውራ ጎዳና ለሁለት መከፈሉ የሚያበቃበት ነው። ትራፊኩ ወደ ሁለቱም አቅጣጫ ይሄዳል። የቀኝ መስመር ይያዙ

ከቀኝ የሚዋሐድ መንገድ

የቀኝ መስመር ይዞ መጓዝ

ከፊት ለፊት ከቀኝ ጎን የሚወሐድ መንገድ አለ።

ከፊት ለፊት የመንገድ ደሴት፣ አካፋይ ወይም መከላከያ አለ። በቀስቱ ላይ የተገለፀውን አቅጣጫ ይያዙ።

ከግራ የሚዋሐድ መንገድ

ከፊት ለፊት የቀይ መስመር ያበቃል

ከፊት ለፊት ከግራ ጎን የሚወሐድ መንገድ አለ።

የቀኝ መንገድ በቅርብ ያበቃል። በቀኝ አቅጣጫ በኩል ያሉ አሽከርካሪዎች መንገድ ክፍት በሚሆንበት ጊዜ ወደ ግራ ሄደው መጓዝ አለባቸው። በግራ መስመር ላይ ያሉ 52


ባለሁለት አቅጣጫ ትራፊክ

ተሽከርካሪዎች ሌሎች ወደ መንገዱ የሚገቡ አሽከርካሪዎች ምቹ በሆነ መንገድ መንገዱን እንዲጠቀሙ መፍቀድ አለባቸው።

ወደ ሁለት አቅጣጫ መንገድ እየገቡ ስለሆነ ቀኝዎን ይያዙ እንቅስቃሴ በሁለቱም አቅጣጫ ይደረጋል።

ከፊት ለፊት ከፍተኛ ቁልቁለት አለ

ወደ ቀኝ መታጠፍ ክልክል ነው

ከፊት ለፊት ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቁልቁለት አለ ፍሬንዎ መስራት አለመስራቱን ያረጋግጡ።

ወደ ቀኝ መታጠፍ ሕገወጥ ነው። ይህንን ምልክት በሚያዩበት ጊዜ ወደ ቀኝ እንዳይታጠፉ።

የብስክሌት ማቋረጫ/የብስክሌት መንገድ በመደበኛነት እዚህ አካባቢ ላይ ብስክሌት ያቋርጣል ወይም ከጎን ይጓዛል።

U-TURN (ዞሮ-መመለስ) ክልክል ነው ዞሮ-መመለስ ሕገወጥ ነው። ይህንን ምልክት በሚያዩበት ጊዜ ዞሮ-መመለስ እንዳያደርጉ።

በጥንቃቄ ያሽከርክሩ በጥንቃቄ ያሽከርክሩ። ይህ የጥንቃቄ ምልክት በመንገዱ አቅራቢያ እንስሳቶች፣ ስፖርተኞች፣ ብስክሌተኞች እና እግረኞች በመንገዱ አቅራብያ በመኖራቸው ያስጠነቅቃል።

መግባት ክልክል ነው ይህ ምልክት ማለት ወደዚህ አቅጣጫ ማሽከርከር ክልክል ነው ማለት ነው።

እርስጥበት በሚኖርበት ጊዜ ያዳልጣት

የመታጠፊያ መብራት ምልክቶች፣ ድንገተኛ ምልክቶች እና የእጅ ምልክቶች

አስፋልት መንገዶች እርጥብ በሚሆኑበት ጊዜ ፍጥነትዎን ይቀንሱ። ፍሬን በፍጥነት አይያዙ ወይም በድንገት አቅጣጫዎን እይቀይሩ። ከፊትዎ ባለው ተሽከርካሪ እና በእርስዎ መካከል ያለውን ርቀት ይጨምሩ።

ለመታጠፍ እያሰቡ መሆንዎን ለማሳየት የእጅ ምልክት ወይም የአቅጣጫ ምልክት ማሳየት ይጠበቅብዎታል። የመታጠፊያ መብራት አቅጣጫ በሚቀይሩበት ጊዜ ወይም ሌላ ተሽከርካሪ ደርበው ስያልፉ የሚጠከሙት ነው። ከኋላዎ ያሉ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ ለማሳወቅ የመታጠፊያ መብራት መጠቀም በሕግ የተከለከለ ነው። የአደጋ መብራቶች ጥቅም ላይ መዋል የሚገባቸው ተሽከርካሪዎ ሲቆም ወይም በሚበላሽበት ጊዜ ወይም ድንገተኛ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ነው። ብስክሌተኞች ሌሎች አሽከርካሪዎችን ለማሳወቅ የእጅ ምልክት ይጠቀማሉ።

የእንስሳት ማቋረጫ በምስሉ ውስጥ የታየው እንስሳ መንገዱ ላይ አብዛኛውን ጊዜ ስለሚያቋርጥ በተለይም ንጋት እንዲሁም ምሽት ሰዓት ላይ መንገዱን በሚያቋርጡበት ጊዜ እንስሳውን እንዲያቋርጥ ጥንቃቄ ያድርጉ። የእግረኛ ማቋረጫ የእግረኛ ማቋረጫ፦ እግረኞች ካሉ ተመልክተው ለማቆም ይዘጋጁ። በዝግታ ፍጥነት የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች 25 ማይል በሰዓት ወይም ከዚያ በታች የሚጓዙ እንደ የእርሻ ተሽከርካሪዎች፣ በፈረስ የሚሳቡ ጋሪዎች ወይም የአውራ ጎዳና መስሪያ ተሽከርካሪዎች ምልክት በሕዝብ አውራ ጎዳናዎች መቀመጥ አለባቸው። እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሚታዩበት ጊዜ ፍጥነትዎን እና ቦታዎን ለማስተካከል ዝግጁ ይሁኑ።

ወደ ቀኝ መታጠፍ

53

ፍጥነት መቀነስ ወይም መቆም

ወደ ግራ መታጠፍ


ሀገር-አአቋራጭ መንገድ ጠቋሚ ሀገር-አአቋራጭ መንገድ መግባትዎን የሚያሳይ የጋሻ ቅርጽ ምልክት አላቸው። ከላይ የ INTERSTATE ጽሁፍ በቀይ መደብ በነጭ ቀለም ይኖረዋል። ከስር ያለው በሰማያዊ መደብ የመንገዱ ቁጥር በነጭ ቀለም የተፃፈ ነው። የU.S. መንገድ ተቋሚ ቁጥር ያላቸው የ U.S. መንገዶች በጥቁር ቀለም በነጭ መደብ ላይ ቁጥሮቹ የተፃፈ የጋሻ ምልክት ያለው ነው። የግዛት መንገድ ጠቋሚ የገዛት መንገዶች ጥቁር ፊደል በአራት መአዘን ቅርጽ ያለው ነጭ መደብ ላይ የተፃፈ ነው። የDC መንገድ ጠቋሚ DC 295 በሌላ ስሙ Anacostia Freeway በመባል የሚታወቀው በኮሎምቢያ ደስትሪክት ውስጥ ያለ ቁጥር ያለው ብቸኛ የዲስትሪክቱ መንገድ ሲሆን የU.S. ሆነ የሀገር-አቋራጭ አውራ ጎዳና አይደለም።

54


የአስፋልት መንገድ መስመር ቀለማት የአስፋልት መንገድ ቀለማት የመንገድ ቀለማት ምልክቶች መመሪያን የሚሰጡ፣ አሽከርካሪን የሚያስጠነቅቁ እንዲሁም አስገዳጅ ሕጎችን የሚያመለክቱ ናቸው። ቀለማቱ ቀይ፣ ማሰማያዊ፣ ቢጫ ወይም ነጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ብቻቸውን ወይም ተቀላቅለው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። እያንዳንዳቸው የተለያየ ትርጉም አላቸው የቀይ የመንገድ ቀለማት በአጠቃላይ ጥቅም ላይ የማይውል ሲሆን በአንዳንድ ህብረተሰብ ፓርኪንግ በማይፈቀድባቸው ቦታዎች ላይ ቀይ ቀለም ጠርዝ በማስቀመጥ ይከለክላሉ። በአስፋልት መንገድ ላይ ቀይ ቀለም መግባት ወይም መጠቀም የማይቻልባቸውን አካባቢዎችን ያሳያል። በመሆኑም በመንገድ ላይ የሚቀለሙ ስለሆኑ ማነኛውም በተቃራኒ መስመር የሚጓዝ ሊያያቸው ይችላል። ሰማያዊ ቀለም የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች የፓርኪንግ ቦታ የሚያሳዩ ናቸው። ቢጫ የማሐል መስመሮች ማለት መንገዱ የሁለት አቅጣጫዎች መንገድ ማለትም በሁለት ተቃራኒ መንገድ የሚፈሱ መንገዶች ማሳያ ነው። የተቆራረጠ ቢጫ መስመር የተቆራረጡ ቢጫ መስመሮች ማለት ከፊት ለፊት ያለው መንገድ ነፃ በሚሆንበት ጊዜ ከየትኛውም አቅጣጫ በግራ በኩል ማለፍ ይቻላል ማለት ነው። አንድ የተቆራረጠ እና አንድ ያልተቆራረጠ ቢጫ መስመሮች የተቆራረጠ ቢጫ መስመር ከሌላ ካልተቆራረጠ መስመር ላይ መንገድ ላይ በሚኖርበት ጊዜ ትርጉሙ የተቆራረጠ መስመር ካለበት አቅጣጫ ወደሌላኛው አቅጣጫ ማለፍ የሚቻል ነገር ግን ካልተቆራረጠው አቅጣጫ ማለፍ የማይቻል መሆኑን የሚያሳይ ነው። ያልተቆራረጠ የቢጫ መስመር ባለው ያሉ ተሽከርካሪዎች መንገዱን ማቋረጥ የሚችሉት የተቃራኒ መንገድ ነፃ በሚሆንበት ጊዜ እግረኞች፣ ብስክሌተኞች፣ ስኩተር የሚነዱ ወይም ስኬትቦርድ የሚንሸራተቱ ሰዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማለፍ ብቻ ነው።

ወደ ሁለቱም አቅጣጫ ማለፍ የተከለከለ ነው። የግራ መታጠፊያ ወይም የእግረኞች፣ ብስክሌተኞች፣ ስኩተር የሚነዱ ወይም ስኬትቦርድ የሚንሸራተቱ ሰዎችን ለማለፍ እና ተቃራኒ መስመር ክፍት ሲሆንና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማለፍ ብቻ ነው። የተቆራረጠ ነጭ መስመር የተቆራረጠ ነጭ መስመር ወደ አንድ አቅጣጫ የሚሄዱ መንገዶችን መሰመር ለመለየት ይጠቅማሉ። በዚህ ጊዜ በጥንቃቄ መስመሮችዎን ሊቀይሩ ይችላሉ። ያልተቆራረጡ ነጭ መስመር ያልተቆራረጡ ነጭ መስመሮች የሚያሳዩት መታጠፍያ መስመሮች እና ወደ መስቀለኛ፣ መሳለጫ፣ እና መግቢያ መውጫ እና መስመረ መቀየር አደገኛ የሚሆንባቸው ሌላ ቦታዎች መስመር መቀየርን ለመከልከል ነው። ያልተቆራረጡ የነጭ መስመሮች የአስፋልት መንገዶች የቀኝ ጠርዝን ለማስመር ጥቅም ላይ ይውላሉ። በነጭ ቀለም የተፃፉ ቀስቶች የትኛውን መታጠፊያ መውሰድ ወይም ማድረግ እንዳለብን የሚያሳዩ ናቸው። የመቆሚያ መስመር፣ የ የእግረኛ መንገዶች መቋረጫ እና የፓርኪንግ ስፍራዋች በነጭ ቀለም የተፃፉ ናቸው። የነጭ መስመር ቀስቶች ነጭ ቀለም ያላቸው ቀስቶች ቀጥተኛ ወይም የታጠፉ ምልክቶች ሊሆኑ የሚችሉ። የታጠፈ ነጭ ቀለም ቀስት ወይም ታጣፊ ቀስት እና አብሮት ONLY የሚል ቃል ያለው መስመር ላይ ከሆኑ ቀስቱ ወደሚያሳየው አቅጣጫ መታጠፍ አለብዎት። መስመርዎ በቀጥተኛ እና በታጣፊ ቀስቶች ምልክት የተጻፈበት ከሆነ ወደፊት ሊሄዱ ወይም ሊታጠፉ ይችላሉ።

ሁለት ያልተቆራረጡ ቢጫ መስመሮች ሁለት ያልተቆራረጡ ቢጫ መስመሮች በመንገድ መካከለኛው ቦታ ላይ በሚሰመርበት ጊዜ የሁለቱም የትራፊክ አቅጣጫ የሚለይ መስመር ነው። በዚህ ጊዜ 55


ባለ ሁለት ያልተቆራረጠ ነጭ መስመር

መስመር የሞተር ተሽከርካሪ እና ብስክሌቶች ጎን ለጎን ለመጓዝ ለማጥበብ የሚጠቅም ነው። ሻሮው መስመር ቀለም የሳይክል አሽከርካሪዎች መንገድ ላይ እንዲሽከረክሩ የሚያበረታታ እና አሽከርካሪዎች መንገድ ላይ ስለመኖራቸው እንዲያውቁ የሚያሳይ ነው።

ባለ ሁለት ያልተቆራረጠ ነጭ መስመር በአንድ አቅጣጫ የሚሄዱ የትራፊክ ለመክፈል የሚሰራ ነው። በአብዛኛውን ጊዜ እነዚህ የተለመዱ መስመሮች ከለልዩ አገልግሎት መስመሮችን ለመለየት የሚጠቅሙ ናቸው ለምሳሌ ብዙ ተሳፋሪ ይዘው የሚጓዙ ተሸከርካሪዎችን በፈጣን መንገድ ላይ ለመለየት የሚያገለግል ናቸው። እነዚህን መስመሮች ማለፍ አይችሉም። ወደእነዚህ ልዩ መንገዶች መግባት የሚቻለው መግባትን የሚፈቅዱ ምክልክቶች እና ጽሑፎች ሲኖሩ ብቻ ነው።

የብስክሌት መንገድ የብስክሌት መስመሮች ባልተቆራረጠ ወይም በተቆራረጠ ነጭ ወይም አረንጓዴ የአስፋልት መንገድ ላይ የቀለም ምልክቶች የሚለይ ሲሆን በላዩ ላይ የሳይክል ምልክት አለው። የብስክሌት መንገድ የብስክሌት አሽከርካሪዎች በተመራጭነት ለመጠቀም ነው። አሽከርካሪዎች በብስክሌት መስመር ማሽከርከር የለባቸውም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ መታጠፍ ካልሆነ በስተቀር አሽከርካሪዎች ከመታጠፍዎ በፊት የጎን መስታወቶች በመጠቀም ከኋላዎ ሳይክል አለመኖሩን ያረጋግጡ እንዲሁም በመስመሩ ላይ ያሉ ሳይክሎች ቅድሚያ ይስጡ።

የቅድሚያ መስጫ መንገድ ቅድሚያ መስጫ መስመር ባለ ሦስት ማዕዘን መስመሮች ሲሆን በመንገዱ ላይ ከቅድሚያ ይስጡ ምልክት ጋር ቆመው ቅድሚያ የሚሰጡበት መስመር የሚያሳዩ ናቸው። ቅድሚያ መስጫ መስመር አብዛኛውን ጊዜ አደባባይ መግቢያ ላይ ይታያል።

ብዙ ተሳፋሪ ለሚይዙ ተሸከርካሪዎች መስመር (HOV)

ባለሦስት መስመር መንገዶች አንድ ባለ ሶስት መስመር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ ትራፊክ የሚሄድበት መንገዶች ላይ፤ የመስመር ቀለሙ አሽከርካሪዎች የመሃለኛው መስመር መቼ ለማለፍ ወይም ለመታጠፍ እንደሚጠቀሙ የሚያሳይ ነው።

ብዙ ተሳፋሪ የሚይዙ ተሸከርካሪዎች መስመሮች(HOV) በአውራ ጎዳናው መስመር ላይ በአልማዝ ቅርፅ የሚቀለሙ ናቸው። HOV መስመሮች በመንገድ መክፈያ ወይም በመግጫ ወይም በሌላ ባልተቆራረጠ ባለ ሁለት ነጭ መስመር ሊለዩ ይችላሉ። ከፍተኛ ትራፊክ በሚኖረበት ጊዜ HOV መስመሮች ለባሶች፣ ሚኒባሶች፣ የጋራ መጠቀምያ ተሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ብዙ ተሳፋሪ ለሚይዙ ተሸከርካሪዎች፣ ሞተርሳይክሎች እና አንዳንድ ጊዜ ልዩ ንጽህ ጋዝ የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ። እነዚህ መንገዶች ለሚገቡ ተሸከርካሪዎች ሊሸከሙዋቸው የሚገባውን አነስተኛ የተጓዞች ቁጥር የሚጠቁሙ ምልክት (ሞተርሳይክልና ንፁህ ጋዝ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን ሳያጠቃል) የሚያሳይ ሲሆን ሁሌም የHOV ክልከላዎች መከበር ይኖረባቸዋል። እነዚህ መስመሮች በመከለያ ከሌሎች መስመሮች የተከፈሉ በሚሆኑበት ጊዜ በተቃራኒ አቅጣጫ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

መካከለኛው መስመር ባለ ነጠላ የተቆራረጠ ቢጫ መስመር በሁለት አቅጣጫዎች ካሉት በሁለቱም አቅጣጫ እያሽከርከሩ ያሉ አሽከርካሪዎች የግራ መታጠፊያ ለማድረግ የሚፈቅድላቸው ነው። የመሃል መስመሩ በሁለቱም ጎን በኩል ያልተቆራረጡ እና የተቆራረጡ ቢጫ መስመሮች የተቀለመ ከሆነ፤ በሁለቱም አቅጣጫ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች መስሠሩን ወደ ግራ ለመታጠፍ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ መስመር ለ150 ጫማ ርቀት በላይ መጓዝ የለባቸውም። የጋራ መስመር መንገዶች የጋራ መስመር ቀለማት ወይም የተገለበጠ V ምልክት(ሻሮው) የሚያጠቃልለው የብስክሌት ምልክት ከላይ ድርብ V ምልክት(ሼቭሮን) ጋር እና በመሄጃ 56


ይህ ማለት በቀን ጊዜ በሆነ ሰዓት ላይ የትራፊክ ፍሰቱ አንድ አቅጣጫ ላይ የሚፈስ ሊሆን ይችላል ማለት ነው። በሌላ ጊዜ ደግሞ የትራፊክ ፍሰቱ በተቃራኒ አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። የአልማዝ ቅርፅ ያለው ምልክት ማድረጊያ መስመር እንደ አውቶቡስ መስመሩ ሆኖ እንዲቆይ ተደርጓል።

57



Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.