Bahere Hasab (EOTC Calender System)

Page 1

ባሕረ፡ሐሳብ።


ባሕረ፡ሐሳብ። •ይህ፡ርእስ፡ሰፋ፡ያለ፡ትርጕም፡ያለውና፡በውስጡም፡ብዙ፡የሐሳበ፡ዘመን፡ ትንታኔዎች፡የሚታወቁበት፡ዐቢይ፡አንቀጽ፡ነው። •‘ባሕረ፡ሐሳብ’፡መባሉም፡ባሕር፡ጥልቅና፡ሰፊ፥የሰው፡ልጅ፡ባካሉ፡ዋኝቶ፡ ሊሻገረው፡የማይችል፡ታላቅ፡የውሃ፡ክምችት፡እንደ፡ኾነ፡የዘመን፡ ክፍልፋዮችም፡በዕላታት፡በሳምንታት፡በአውራኅና፡በዓመታት፡የየዕለታቱ፡ ድቁቅ፡ጊዜያት፡ሳይቀሩ፥ታትተውና፡ተሰፍረው፥በየቀመራቸው፡ተመድበው፡ የሚገለጹበት፡ሰፊና፡ጥልቅ፥ሰው፡በሐሳብ፡መልሕቅ፡የሚገሠግሥበት፡ የአእምሮ፡መዋኛ፡ስለ፡ኾነ፥ባሕረ፡ሐሳብ፡ተብሏል። •ባሕረ፡ሐሳብ፡በዝርዝር፡ለማተት፡መነሣት፡ዐባይን፡በጭልፋ፡ ይሆናል። ነገር፡ግን፡ባጪሩ፡ቀንጨብ፡አድርጌ፡ለማቅረብ፡ያኽል፡ነው።


በባሕረ፡ሐሳብ፡ውስጥ፡የሐሳበ፡ዘመን፡ትንታኔዎች፡ ለምን፡ እንደተሠሩ፤ • •

ጌታችን፡የሚወለድበትን፡ዘመን፡ለመረዳት፡ በዓላትንና፡አጽዋማትን፡ለክቶ፡ለማወቅ፡ነው።

የሐሳበ፡ዘመን፡ዕውቀት፡በዘመነ፡ኦሪት፡ይሠራበት፡እንደ፡ነበር፡ይታወቃል። ዋናው፡ዓላማ፤ • •

የአይሁድን፡አጽዋማትና፡በዓላት፡ለማወቅ፤ የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ዘመነ፡ሥጋዌ፡ለመረዳት፡ነው።


•በዓሎቻቸው፤ ሀ. በዓለ፡መጸለት፤የቂጣ፡በዓል፡ማለት፡ነው። ይኽውም፡ያልቦካ፡እንጀራ፡ የሚበሉበት፡ነው። ለ. በዓለ፡መጥቅዕ፤የዘመን፡መለወጫ፡በዓል፡ነው። ሐ. በዓለ፡ፍሥሕ፤ከግብጽ፡ባርነት፡ነጻ፡የወጡበት፡በዓል፡ነው። መ. ልበ፡ምድር፤ባሕረ፡ኤርትራን፡በደረቅ፡የተሻገሩበት፡በዓል፡ነው። ሠ. በዓለ፡ሠዊት፤የአዝመራው፡ሰብል፡የሚታይበት፡በዓል፡ነው።

•ጾሞቻቸው፤ ሀ. ጾመ፡አይሁድ፤ ለ. ጾመ፡አስቴር፤ ሐ. ጾመ፡ዮዲት፤ መ. ጾመ፡ነነዌ፡ናቸው።


ዓመተ፡ዓለም፤ ዓለም፡ከተፈጠረ፡ጊዜ፡ዠምሮ፥በፀሓይ፡ላይ፡በተመሠረተው፡ዑደት፡ ሲቈጠር፥እንደ፡ኢትዮጵያ፡የዘመን፡አቈጣጠር፥በዘንድሮው፡መስከረም፥ ጠቅላላው፡ዘመን፡7504፡ዓመተ፡ዓለም፡ይኾናል።ይህ፥እንዴት፡እንደ፡ ሆነ፡ጠቅለል፡ባለ፡መንግድ፡ሲመደብ፥ • ከአዳም፡እስከ፡ኖኅ፡ 2256፡ዘመን፤ • ከኖኅ፡እስከ፡ሙሴ፡ 1588፡ዘመን፤ • ከሙሴ፡እስከ፡ሰሎሞን፡ 593፡ዘመን፤ • ከሰሎሞን፡እስከ፡ክርስቶስ፡ 1063፡ዘመን፡ይኾናል። ጠቅላላ፡ድምር፡5500፡ዘመን፡ይኾናል።


•ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ):

•ዓመተ፡ምሕረት፡ •ዓመተ፡ዓለም፡

5500 ዓመት

2004 ዓመት 7504 ዓመት

ከጌታ፡ልደት፡በፊት፡የተፈጸመ።

ከጌታ፡ልደት፡ወዲህ። ዓለም፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፡ እስካኹን፡ያለው፡ዘመን።

ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ) + ዓመተ፡ምሕረት = ዓመተ፡ዓለም 5500 + 2004 = 7504


መስከረም፤ •ጥንት፥ከሥጋዌ፡በፊት፥ባይሁድና፡በዓለም፡ኹሉ፥አኹንም፡ በኢትዮጵያና፡በግብጽ፡የወርና፡የዓመት፡መዠመሪያ፡መስከረም፡ነው። •በምሥራቅ፡ኦርቶዶክስ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፥መስከረም፡1፡ቀን፡ የቤተ፡ክርስቲያን፡ዐዲስ፡ዓመት፡እየተባለ፡እስካኹን፡ይከበራል። •በዚህም፡ወር፡በዓመተ፡ዓለም፡ውስጥ፡የሚገኙት፡ጥንታትና፡አቅማራት፥ አዕዋዳትና፡ሠግር፥አበቅቴና፡መጥቅዕ፥ስፍረ፡ሰዓትና፡መዛብዓ፡ፀሐይ፥ ሕፀፅና፡የጨረቃ፡ልደት፣ሌሎችም፡ኹኔታዎች፡በየስፍራቸው፡ የሚመደቡበት፡ወቅት፡ነው።


አበቅቴና፡መጥቅዕ፤ • አበቅቴ(epact)፡

ፀሐይ፡የዓመቱን፡ዙር፡በ365፡ከሩብ፡ቀናት፡ ስትጨርስ፡ጨረቃ፡ግን፡354፡ቀናት፡ብቻ፡ይፈጅባታል።ከ365፡ሲቀነስ፡ 354፡የሚገኘው፡ቁጥር፡11፡ስለሆነ፡አበቅቴ፡ከዚህ፡የመጣ፡ነው፡ይላሉ። አበቅቴ = የፀሐይ፡ዓመት፡ዙር - የጨረቃ፡ዓመት፡ዙር 11 ቀን = 365 ቀን - 354 ቀን • መጥቅዕ፡ አበቅቴ፡ተወልዶ፡የመጅመሪያው፡ወር፡ የሚሞላበት፡ቀን፡ደግሞ፡ መጥቅዕ፡ይባላል።


በቀላሉ፡ስለ፡ሐሳበ፡ዘመን፡የድሜጥሮስ፡ድርሻ፤ ድሜጥሮስ፡አቤቅቴን፡እና፡ምጥቅዕን፡በተገቢው፡ቦታ፡እንዲውሉ፡ያደረገ፡ ነው። • አመዳደቡም፡ሱባኤ፡ሲገባ፡በማዕልት(በቀን)፡7x7፡የቀን፡ሱባኤ፡ያዘ፥ ተባዝቶ፡የሚገኘው፡ቁጥር፡49፡ነው። በ30፡ሲገደፍ፡19፡ይቀራል፥ ይህን፡መጥቅዕ፡ብሎታል። • እንደገና፡ከሌሊቱ፡7x23፡የሌሊት፡ሱባኤ፡ያዘ፡ውጤቱ፡161፡ ይሆናል፡በ30፡ሲገደፍ፡11፡ይቀራል፥ይህን፡አበቅቴ፡ብሎ፡ሰየመው። አብቅቴ፡እና፡መጥቅዕ፡የተለየ፡አመጣጥ፡እንዳላቸው፡ብዙ፡ሊቃውንት፡ ይናገራሉ


• ዓዋጅ 1፡ “አበቅቴ፡ወመጥቅዕ፡ክልኤሆሙ፡ኅቡረ፡ኢይበዝኁ፡እም፴፡ ወኢይውኅዱ፡እም፴፡ወትረ፡የከውኑ፡፴።” (አበቅቴና፡መጥቅዕ፡ሁለቱ፡በኅብረታቸው፡ከ30፡አይበዙም፥ከ30፡ አይጎድሉም፤ዘውትር፡30፡ይሆናሉ።) አበቅቴ + መጥቅዕ = 30 • ዓዋጅ 2፡ “አበቅቴ፡ከነሐሴ፡8፡አያንስም፤ከጳጕሜን፡5፡አይበልጥም።” • ዓዋጅ 3፡ “መጥቅዕ፡ከመስከርም፡15፡አይወርድም፤ከጥቅምት፡13፡ በላይ፡አይወጣም።”


አጽዋማትና፡በዓላትን፡ምድብ፡ለማወቅና፡ዓመተዓለምንም፡ለመተንተን፡ ይሚረዱን፡7፡አዕዋዳት፡ወይም፡መስፈሪያዎች፡ አሉ፡እነርሱም፤ ሀ. ዐውደ፡ዕለት፤ከእሑድ፡እስከ፡ቅዳሜ፡ያሉት፡7፡ዕለታት፡ናቸው። ለ. ዐውደ፡ወርሕ፤ በወርሕ፡ውስጥ፡የሚገኙ፡30፡ቀኖች። በጨረቃ፡ግን፡ ባንደኛው፡ወርሕ፡30፡በሁላተኛው፡29፡እየሆኑ፡የሚገኙ፡ዕለታት፡ናቸው። ሐ. ዐውደ፡ዓመት፤በፀሐይ፡ዑደት፡አቆጣጠር፡በዓመት፡የሚመላለሱ፡ 365፡ከሩብ፡ዕለታት፡ናቸው። በጨረቃ፡ግን፡354፡ዕለታት፡ናቸው። • ከዚህ፡በታች፡ያሉት፡በዓመት፡የሚቆጠሩ፡ናቸው። መ. ዐውደ፡ፀሐይ፤ይህም፡28፡ዓመት፡ይሆናል። በዚህም፡ዕለት፡እና፡ወንጌላዊ፡ይገናኙበታል(4x7=28)።


ሠ. ዐውደ፡አብቅቴ፤ 19 ዘመን፡ነው።በዚህም፡ፀሐይና፡ጨረቃ፡ የተመደበላቸውን፡መንገድ፡እየፈጸሙ፡በተጠሩበት፡ምስኮት(ኆኅት)፡ ይገናኙበታል። ረ.ዐውደ፡መኅተም፤76(19x4=76)ዘመን፡ነው፡በዚህም፡አብቅቴና(19)፡ ወንጌላዊ(4)፡ይገናኙበታል። ማኅተም፡መባሉም፡አበቅቴው፡ ለአበቅቴ፥ወንጌላዊው፡ለወንጌላውያን፡ፍጻሜ፡በመሆናቸው፡ነው። ሰ. ዐቢይ፡ቀመር፤ 532(19x4x7=532)፡ዘመን፡ነው። በዚህም፡ አበቅቴ(19)፥ወንጌላዊ(4)፥እና፡ዕለት(7)፡ይገናኙበታል። ዕለቱ፡ሰኞ፥አበቅቴው፡18፥ወንጌላዊው፡ዮሐንስ፡ነው።


መጥቅዕ፤ •የዘንድሮውን፡በዓላትና፡አጽዋማት፡በየስፍራቸው፡ለመመደብ፡መጥቅዕ፡ የሚውልበትን፡ማግኘት፡አለብን፤መጥቅዕን፡ለማግኘት፡ወንበሩን፡ማቋቋም፡ ይኖርብናል። ወንበር፡

አበቅቴንና፡መጥቅዕን፡ለማግኘት፡የምንሰፍርበት፡መሥፈሪያ፡ነው።

•ለወንበር፡ማዋቀሪያ፡ደግሞ፡ሦስት፡ቀመሮችን፡እንመድባለን፥ እነርሱም፤ ሀ. ዐቢይ፡ቀመር ፡ 532(19x7x4=532)፡ዘመን፡ነው። ዓመተ፡ ዓለምን፡በዐቢይ፡ቀመር፡ስናካፍለው፡(7504 ፥ 532 = 14 ቀሪ 56)። ለ. ማዕከላዊ፡ቀመር ፡ 76(19x4)፡ዘመን፡ነው። ከ56፡በላይ፡ስለ፡ኾነ፡ ማካፈል፡አያስፈልግም። ቢያስፈልግ፡ግን፡7504፥76= 98 ደርሶ ቀሪ 56 ሐ. ንዑስ፡ቀመር፡ 19፡ዘመን፡ነው። ከላይ፡ያገኘነው፡ቀሪ፡56፡ ሲካፈል፡ ለ19፥ ቀሪ፡18፡ይኾናል። ከ19፡ዘመን፡18ኛው፡ማለት፡ነው። በሌላ፡መንገድ፤ 7504፥19= 394 ደርሶ፡ቀሪ፡18 ይሆናል።


የንዑስ፡ቀመር፡ዓመቶች 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ 5ኛ 6ኛ 7ኛ 8ኛ 9ኛ 10ኛ 11ኛ 12ኛ 13ኛ

አበቅቴ 0 11 22 3 14 25 6 17 28 9 20 1 12

መትቅዕ 30 መስከረም 19 መስከረም 8 ጥቅምት 27 መስከረም 16 መስከረም 5 ጥቅምት 24 መስከረም 13 ጥቅምት 2 ጥቅምት 21 መስከረም 10 ጥቅምት 29 መስከረም 18 መስከረም


የንዑስ፡ቀመር፡ዓመቶች 14ኛ 15ኛ 16ኛ 17ኛ 18ኛ 18ኛ 19ኛ

አበቅቴ 23 4 15 26 77 18

መጥቅዕ 7 ጥቅምት 26 መስከረም 15 መስከረም 4 ጥቅምት 23 መስከረም መስከረም 23 12 ጥቅምት

የያዝነውን፡ዓመት፡መዠመሪያውን፡እንጂ፡ፍጻሜውን፡ስላላየነው፣ ማለት፡ 2004ን፡ገና፡ጀመርን፡እንጂ፡አልጨረስነውም፣ሰለዚህ፡ከቀሪው፡ቍጥር፡ከ18፡ 1፡ይቀነሳል። 18-1=17። የተገኘው፡17፡ቍጥር፡‘ወንበር’፡ይባላል። በዚህ፡ወንበር፡አማካይነት፡የዘንድሮውን፡አበቅቴና፡መጥቅዕን፡እንመድባለን።


• አበቅቴ፥ ወንበር፡17፤ የአበቅቴ፡መደብ(11)፡በ17፡ሲባዛ፡187፡ይሆናል፡ 11x17=187 187፥30= 6፡ጊዜ፡7፡ቀሪ። አበቅቴ፡ 7፡ኾነ፡ማለት፡ነው። • መጥቅዕ ፥ መጥቅዕ፡መደቡ፡19፡ነው፡ብለናል። 19x17=323 323፥30= 10 ፡ጊዜ፡ 23፡ቀሪ። መጥቅዕ፡ 23፡ኾነ፡ማለት፡ነው።

ዓዋጅ 1፥ አበቅቴ (7) + መጥቅዕ(23) = 30


• በዓዋጅ 3፡መሰረት፤ መጥቅዕ፡ሲአንስ፡(ከ13፡በታች፡ሲሆን፡)የመጥቅዕ፡ ማረፊያ፡ጥቅምት፡ይሆናል፣ከዚያ፡በላይ፡ከሆነ፡በመስከረም፡ላይ፡ያርፋል። መጥቅዕ < 13 መጥቅዕ > 13

የመጥቅዕ፡ማረፊያ፡ጥቅምት፡ይሆናል። የመጥቅዕ፡ማርፊያ፡መስከረም፡ይሆናል።

የዘንድሮ፡መጥቅዕ፡23፡ስለሆነ፥የመጥቅዕ፡ማረፊያ፡መስከረም፡23፡ ይሆናል።


የበዓላትና፡የአጽዋማትን፡ዕለት፡ለማውጣት፡የምንከተላቸው፡ደረጃዎች

1.መጥቅዕ (መስከረም፡ወይም፡ጥቅምት)

2.መስከረም፡1፡ የሚውልበት፡ዕለት፤

5.በዓላትና፡አጽዋማት፡ የሚውሉበት፡ዕለት፤

3.መጥቅዕ፡ የሚውልበት፡ዕለት፤

4.ነነዌ፡ የሚውልበት፡ዕለት፤


መስከረም፡1፡ቀንን፡ለማወቅ(ዕለተ፡ቀመርን፡ለማወቅ)፤ • በባሕረ፡ሓሳብ፡የቁጥር፡ስሌት፡መሠረት፣የመጀመሪያ፡ቀን፡(ጥንተ፡ቀመር) ማክሰኞ፡ነው። • የዘንድሮ፡ዓዲስ፡ዓመት፡የሚውልበትን፡ዕለት፡ለማወቅ፤

(ዓመተ፡ዓለም +መጠነ፡ራብዒት) ፥ 7

1 2 3 4

ቢተርፍ ቢተርፍ ቢተርፍ ቢተርፍ

ማክሰኞ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ

5 ቢተርፍ 6 ቢተርፍ 0 ቢተርፍ

ቅዳሜ እሑድ ሰኞ


(ዓመተ፡ዓለም +መጠነ፡ራብዒት) ፥ 7

ዓመተ፡ዓለም = ዓመተ፡ፍዳ(ዓመተ፡ኵነኔ) + ዓመተ፡ምሕረት 7504 = 5500 + 2004 መጠነ፡ራብዒት = 7504፥4 = 1876 (7504 +1876) ፥ 7 = 1340 ትርፍ 0 0 ቢተርፍ

ሰኞ


• መስከረም፡ሰኞ፡ይብታል፣ስለዚህ፡የመስከረም፡23ኛው፡ዕለት፡(መጥ ቅዕ፡የሚውልበት)፡ለማወቅ፤ መስከረም፡1 ሰኞ መስከረም፡2 ማክሰኞ መስከረም፡3 ረቡዕ መስከረም፡4 ሐሙስ . . . . መስከረም፡22 ሰኞ መስከረም፡23 ማክሰኞ ፡ነው።

• ስለዚህ፡መጥቅዕ፡መስከረም፡23፣ማክሰኞ፡ዕለት፡ይውላል።


• መጥቅዕ፡ይሚውልበት፡ዕለት፡ታይቶ፡ከመጥቅዕ፡እስከ፡ ነነዌ፡ስንት፡ቀን፡እንዳለ፡በሕግ፡የተወሰነ፡ነው። የመጥቅዕ፡ዕለት ቅዳሜ እሑድ ሰኞ ማክሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ኀሙስ ዓርብ

ከመጥቅዕ፡እስከ፡ነነዌ 128፡ቀን = 4ወር፡8ቀን 127፡ቀን = 4ወር፡7ቀን 126፡ቀን = 4ወር፡6ቀን 125፡ቀን 125 ፡ቀን = 44ወር፡5ቀን ወር፡5ቀን 124፡ቀን = 4ወር፡4ቀን 123፡ቀን = 4ወር፡3ቀን 122፡ቀን = 4ወር፡2ቀን

ተውሳክ 8 7 6 5 4 3 2


• ዓዋጅ ፤ የነነዌ፡ጾም፡የሚጀምረው፡በጥር፡(ወደ፡መጨረሻው)፡ወይም፡ በየካቲት፡(ወደ፡መጀመሪያው)፡ነው። ነነዌ፡የግድ፡ሰኞ፡መዋል፡አለባት። የማክሰኞ፡ተውሳክ + መጥቅዕ = መባጃ፡ሐመር 5 + 23 = 28 ጥር፡ማክሰኞ፡ይብታል፡የጥር፡28ኛው፡ቀን፡ሰኞ፡ስለሆነ፡በዚኽ፡ቀን፡ ነነዌ፡ትውላለች። ለነነዌም፡መሠረቷ፡ይህ፡መባጃ፡ሐመር፡ነው። የማክሰኞ፡ተውሳክ፡5፡ነው፤ ከመጥቅዕ፡23፡ጋራ፡ሲደመር፡28፡ይኾናል። (ድምሩ፡ከ30፡ቢበልጥ፡30፡ይገደፍለትና፡ቀሪው፡መባጃ፡ሐመር፡ ይሆናል። ለምሳሌ፡ ድምሩ፡ 32፡ቢሆን፡ መባጃ፡ሐመር፡ 30-32=2፡ ይሆን፡ነበር፤ ነነዌም፡የካቲት፡ውስጥ፡ታርፍ፡ነበር)። መጥቅዕ (መስከረም 23)+ 4ወር + 5ቀን = ጥር፡28


•ለአጽዋማቱም፥ነነዌን፡መሠረት፡አድርገው፥ለየራሳቸው፡ተውሳክ፡ አላቸው።

አጽዋማትና፡በዓላት ነነዌ ዐቢይ፡ጾም ደብረ፡ዘይት ሆሳዕና ስቅለት ትንሣኤ ርክበ፡ካህናት ዕርገት ጰራቅሊጦስ ጾመ፡ሐዋርያት ጾመ፡ድኅነት

ከነነዌ፡እስከ፤ 14፡ቀን = 0፡ወር፡14ቀን 41፡ቀን = 1፡ወር፡11፡ቀን 62፡ቀን = 2፡ወር፡ 2፡ቀን 67፡ቀን = 2፡ወር፡ 7፡ቀን 69፡ቀን = 2፡ወር፡9፡ቀን 93፡ቀን = 3፡ወር፡3፡ቀን 108፡ቀን = 3፡ወር፡18፡ቀን 118፡ቀን = 3፡ወር፡28፡ቀን 119፡ቀን = 3፡ወር፡29፡ቀን 121፡ቀን = 4፡ወር፡1፡ቀን

ተውሳካቸው (መባጃው፡ሐመር) 14 11 2 7 9 3 18 28 29 1


የአጽዋማት፡ ወይም፡ + መባጃ፡ሐመር = አጽዋማቱ፡ወይም፡በዓላቱ: የበዓላት፡ተውሳክ የሚውሉበት፡ቀን፡ይሆናል • ዐቢይ፡ጾም ፤ ተውሳኩ፡14፡ነው፤ ከነነዌ፡እስከ፡ ዐቢይ፡ጾም፡14፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ጥር፡28(ነነዌ) + 14ቀን = የካቲት 12 የካቲት፡12፡ቀን፡ዐቢይ፡ጾም፡ይውላል። • ደብረ፡ዘይት ፤ ተውሳኩ፡11፡ነው፤ ከነነዌ፡እስከ፡ደብረ፡ዘይት፡41፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ጥር፡28(ነነዌ) + 41ቀን = መጋቢት 9 መጋቢት፡ 9፡ቀን፡ደብረ፡ዘይት፡ይውላል።፡ • ሆሳዕና ፤ ተውሳኩ፡2፡ነው፤ ከነነዌ፡እስከ፡ሆሳዕና፡62፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ጥር፡28(ነነዌ) + 62ቀን = መጋቢት 30 መጋቢት፡ 30፡ቀን፡ሆሳዕና፡ይውላል።


• ስቅለት ፤ ተውሳኩ፡7፡ነው፤ከነነዌ፡እስከ፡ስቅለት፡67፡ቀን፡ብለን፡ ነበር፡ስለዚህ፤ ጥር፡28(ነነዌ) + 67ቀን =ሚያዝያ 5 ሚያዝያ፡ 5፡ቀን፡ስቅለት፡ይውላል። • ትንሣኤ፤ ተውሳኩ፡9፡ነው፤ ከነነዌ፡እስከ፡ትንሣኤ፡69፡ቀን፡ብለን፡ ነበር፡ስለዚህ፤ ጥር፡28(ነነዌ) + 69ቀን = ሚያዝያ 7 ሚያዝያ፡7፡ቀን፡ትንሣኤ፡ይውላል። • ርክበ፡ካህናት ፤ ተውሳኩ፡3፡ነው፤ከነነዌ፡እስከ፡ርክበ፡ካህናት፡ 93፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤ ጥር፡28(ነነዌ) + 93ቀን = ግንቦት 1 ግንቦት፡1፡ቀን፡ርክበ፡ካህናት፡ይውላል።


• ዕርገት ፤ ተውሳኩ፡18፡ነው፤ከነነዌ፡እስከ፡ዕርገት፡108፡ቀን፡ብለን፡ ነበር፡ስለዚህ፤

ጥር፡28(ነነዌ) + 108ቀን = ግንቦት16 ግንቦት፡16፡ቀን፡ስቅለት፡ይውላል። • ጰራቅሊጦስ ፤ ተውሳኩ፡28፡ነው፤ ከነነዌ፡እስከ፡ጰራቅሊጦስ፡118፡ቀን፡ ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤ ጥር፡28(ነነዌ) + 118ቀን = ግንቦት 26 ግንቦት፡26፡ቀን፡ትንሣኤ፡ይውላል። • ጾመ፡ሐዋርያት ፤ ተውሳኩ፡29፡ነው፤ከነነዌ፡እስከ፡ጾመ፡ሐዋርያት፡ 119፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤ ጥር፡28(ነነዌ) + 119ቀን = ግንቦት 27 ግንቦት፡27ቀን፡ርክበ፡ካህናት፡ይውላል።


•ጾመ፡ድኅነት ፤ ተውሳኩ፡1፡ነው፤ከነነዌ፡እስከ፡ጾመ፡ሐዋርያት፡ 121፡ቀን፡ብለን፡ነበር፡ስለዚህ፤

ጥር፡28(ነነዌ) + 121ቀን = ግንቦት 29 ግንቦት፡29፡ቀን፡ርክበ፡ካህናት፡ይውላል። •ሕፀፅ፡ደግሞ፡መስከረምና፡ጥቅምት፡1፤ኅዳርና፡ታሕሣሥ፡2፤ጥርና፡ የካቲት፡3፤መጋቢትና፡ሚያዝያ፡4፤ግንቦትና፡ሰኔ፡5፤ሐምሌና፡ነሐሴ፡6።

1. 2. 3. 4.

ተሡዑ፡ሠርቀ፡ሌሊት፡(7+1+1)=9 አሚሩ፡ሠርቀ፡መዓልት(1) ዐሥሩ፡ወሠሉስ፡ሠርቀ፡ወርሕ(13)=9+4 ሠኑየ፡(2)፡ሠርቀ፡ዕለት።


ወንጌላዊውን፡ለማወቅ። ወንጌላዊውን፡ለማወቅ፡ዓመተ፡ዓለሙን፡ማለት፡7504፡ለ4፡ማካፈል፡ ይኖርብናል። 1፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ማቴዎስ። 2፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ማርቆስ ።

3፡ቢተርፍ፡ይሆናል፡ሉቃስ። 0፡ቢተረፍ፡ይሆናል፡ዮሐንስ።

7504፥4= 1876 ደርሶ፡ቀሪ፡0። ስለዚኽ፡ዮሐንስ፡ወንጌላዊ፡ዘንድሮ፡ይውላል።

ዘመነ፡ዮሐንስ፡ኾኖ፥በ7504፡ዓመተ፡ዓለም። በ2004፡ዓመተ፡ምሕረት፥ባጪሩ፡የቀረበው፡የባሕር፡ሐሳብ፡ትንታኔ፡ ይኸው፡ነው።


በስመ፡አብ፡በዘንዜከር፡ሐሳባተ፡ሕጉ፡ወትእዛዛቲሁ፡ለእግዚእነ፡ወአምላክነ፡ ወመድኃኒነ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፣ሐሳበ፡ነቢያት፡ወሐዋርያት፣ሐሳበ፡ጻድቃን፡ ወሰማዕት፣ሐሳበ፡ኄራን፡መላእክት፣ እንዘ፡ሀሎነ፡በዘመነ፡ዮሐንስ፡ወንጌላዊ፡ቡሩክ፡ያብጽሐነ፡እስከ፡ዘመነ፡ ማቴዎስ፡ዜናዊ። (በዘመነ፡ዮሐንስ፡ወንጌላዊው፡እንዳለን፤እንዲሁ፡እስከ፡ዘመነ፡ማቴዎስ፡ዜናዊ፡ በሰላም፡ያድርሰን።)

በ ወበ ፡ኮነ፡ዓመተ፡ፍዳ፣በ ወ ፬ (ወረቡዑ)፡ኮነ፡ዓመተ፡ምሕረት፣ በ ወበ ወ፬(ወረቡዑ)፡ኮነ፡ዓመተ፡ዓለም። ሠረቀ፡ለነ፡ወርሐ፡ መስከረም፡ቡሩክ፡ያብጽሐነ፡እስከ፡ወርሐ፡ጥቅምት፡አሜን። (ዓመተ፡ፍዳ፡5500፡ሆነ፤ ዓመተ፡ምሕረት፡2004፡ሆነ፤ ዓመተ፡ዓለም፡ 7504፡ሆነ። የመስከረም፡ወር፡ገባልን፤እስከ፡ጥቅምት፡ወርም፡ በሰላም፡ያድርሰን፡አሜን።)


ወስብሐት፡ለእግዚአብሔር፤ አነሣሥቶ፡ላስጀመረን፥አስጀምሮ፡ላስፈጸመን፥ለእግዚአብሔር፡ክብርና፡ ምስጋና፡ይድረሰው። አሜን።


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.