Habeshawi Kana 001

Page 1

ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሐበሻዊቃና አንደኛ ዓመት ቁጥር 001

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

1

አስተያየት፣ ጸሁፍ፣ ጥቆማ… በሐበሻዊ ቃና የኢሜይል አድራሻ habeshawikana@gmail.com

አድርሱን። በ+256-778-366936 ይደውሉልን።

ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ

ሳሚ-ዩጋንዳ፣ ተስፋይ-ዛንዚባር

ገጽ 11- 12

ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያንን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው

በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

ነጻነቷን ለማወጅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ የቀ ራት ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ን ለመንግስት ስራ ልትቀጥር ነው። የሰራተኞቹ ቅጥር የምስራቅ አፍሪካ በየነ መ ንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የቀጠና ትብብር አካል ነው። በዚሁ የትብብር “ኢንሼቲቭ” ፕ ሮጀክት አማካኝነትም የኢጋድ አባል ሀገራት ከሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ የተው ጣጡ 200 የመንግስት ሰራተኞች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ኮሚሽኖች እና በክልሎች ተ መድበው እንዲሰሩ ይደረጋል። ሰራተኞቹ ሚቀጠሩት ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት ያለበትን የደቡብ ሱዳን መን

ግስት አቅም ለመገንባት መሆኑን ለፕሮ ጀክቱ መሳካት እገዛ እያደረገ ያለው የተ ባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ገልጿል። ከደቡብ ሱዳን ህ ዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማዕከል የ ተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜ ው ለስራ ከደረሰ የሀገሪቱ ህዝብ መካከል 12 በመቶው ብቻ ተከፋይ ሰራተኛ ነው። 8.26 ሚሊዮን ከሚገመተው የደቡብ ሱ ዳን ህዝብ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ዕድሜያ ቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። “ረጅም ዓመታትን የፈጀው ጦርነት በ መንግስት ስራ እና ትምህርት ላይ ከፍተ ኛ ተጽእኖ በማሳረፉ በስራ ክህሎት እና ልምድ ላይ ትልቅ ክፍተት እንዲፈጠር ሆ ኗል” ይላሉ ጁባ በሚገኘው ዩኤንዲፒ ቢ

ሮ ውስት በኮሚኒዩኬሽን ኦፊሰርነት የሚ ያገልግሉት ናታሊ ዊልኪንስ ለሐበሻዊ ቃ ና በላኩት የኢ-ሜይል ምላሻቸው። “ይ ህ ኢንሼቲቭ የደቡብ ሱዳንን ሲቪል ሰ ርቪስ አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና ይ ኖረዋል።” በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት ኢትዮጵያ ን ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮች የሚመጡ ባ ለሙያዎች ለደቡብ ሱዳንውያን የስራ ላ ይ ስልጠና እንዲሰጧቸው ይጠበቃል። ፕሮጀክቱ የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋ ል ብሎ ከመረጣቸው ቁልፍ ዘርፎች መ ካከል የገንዘብ፣ የሰው ኃይል እና የህዝብ አስተዳደር እንደዚሁም ኢንፎርሜሽን እ ና ኮሚዩኔኬሽን ዘርፎች ይገኙበታል። በ ንግድ እና ኢንዱስትሪ እድገት ዙሪያ የሚ

ሰሩ ኤክስፐርቶች፣ ጂኦሎጂስቶች እና ላ ብራቶሪ ቴክኒሽያኖችም በፕሮጀክቱ የሚ ፈለጉ ባለሙያዎች ናቸው። በፕሮጀክቱ አማካኝነት ወደ ደቡብ ሱ ዳን ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ኢት ዮጵያውያን የመንግስትን ሰራተኞችን የ መመልመል ሂደት መጀመሩን የዩኤንዲ ፒዋ ናታሊ ይገልጻሉ። በጁነዲን ሳዶ የ ሚመራው የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ከደቡብ ሱዳን አቻው የሰራተ ኞች እና የህዝብ አገልግሎት ሚኒስቴር ጋ ር በመሆን የምልመላ እና ቅጥር ሂደቱን ያከናውናሉ። እንደ ናታሊ አባባል ከሆነ በአሁኑ ወቅት የምልምላው ሂደት ወደመ ጠናቀቁ ተቃርቧል። “[የሰራተኞቹ] የመጨረሻ ምርጫ ከሶሰ

ት ሳምንት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበ ቃል። እነዚህ ሰራተኞች በኢትዮጵያ መን ግስት ፔሮል ውስጥ የሚቆዩ ናቸው። ወ ደ ደቡብ ሱዳን የመምጣታቸው አንድም ታ ለአዲሲቱ ሀገር ባለው የገንዝብ እና የ ቴክኒካዊ ድጋፍ ይገለጻል”ይላሉ ናታሊ። በኢትዮጵያ በኩል ያለው የሰራተኞች ምደባ ባይጠናቀቅም በፕሮጀክቱ የተመ ለመለው የመጀመሪያው የባለሙያዎች ቡድን ግን ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ጁባ ገብቷል። ከኬንያ የመጣው ይህ ቡ ድን 42 አባላትን የያዘ ሲሆን ሃያዎቹ የ ጤና መኮንኖች እና ነርሶች ናቸው። ቀሪ ዎቹ የቡድኑ አባላት በአስተዳር እና ቴክ ኒክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ናቸው።


ሀበሻዊ ቃና

2

ዜና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ጽህፈት ቤት ከፈተ በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

መንበር …አልነበሩም፡፡ እሳቸው በድንገት ሀገር [ኡ ጋንዳን] ለቀው ሲሄዱ ደግሞ ማህበሩ ወደመሞት ተ ቃረበ” ይላሉ አቶ ንጉሴ፡፡ ይህ ሲባል ግን ማህረሰቡ ምንም አልሰራም ማለት አይደለም ባይ ናቸው አቶ ንጉሴ፡፡ የኢትዮጵያ ሚ ሊኒየምን በኡጋንዳ በድምቀት እንዲከበር ማድረጉ ን፣ በተለያየ ጊዜ በሞት የተለዩ ወገኖችን የቀብር ስ ነ ስርዓት ማስፈጸሙን፣ ወደ ሀገር ቤት አስከሬናቸ ው የሚላከውንም በአግባቡ መሸኘቱን በምሳሌነት ያነሳሉ። እንዲህ እንዲህ እያለ ለተጓዘው ማህበረሰ ብ ባለፈው ዓመት ወርሃ ሐምሌ በኢትዮጵያ ገጠ ር ምግብ ቤት (ኢትዮጵያን ቪሌጅ) የተከሰተው የቦ ምብ አደጋ የማንቂያ ደወል ነበር፡፡ ከኢትዮጵያው ያን “የእንደራጅ ጥያቄ ያስከተለው” የቦምብ ፍንዳ ታ ወዲያውኑ አጠቃላይ ስብሰባ ለመጥራትም ምክ ንያት እንደነበር የማህበረሰቡ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡ በስብሰባውም የተጓደሉ አባላት ተተክተው ማህበረ ሰቡ በ¬ተደራጀ መልኩ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለው ን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ከተመሰረተ ስድስት ዓመታት ያስቆጠረው የኢት ዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ጽህፈት ቤት ከፍ ቶ የተሟላ ስራ ጀመረ። በኡጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት በማሰብ የተቋቋመው ማህበር እስካሁን የራሱ ጽህፈት ቤት አልነበረውም። ማህ በረሰቡ ከግንቦት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ግን ካምፓላ ካሳንጋ አካባቢ የራሱን ጽህፈት ቤት ከፍቶ አዳዲ ስ አባላትን ህጋዊ የአባልነት መታወቂያ መስጠት ጀ ምሯል፡፡ ከማህበረሰቡ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደ ሚያመለክተው እስካሁን 150 ያህል አባላት መታወ ቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 40 ለሚሆኑ ደግሞ እየተዘ ጋጀላቸው ነው፡፡ ኡጋንዳ ውስጥ በህጋዊነት ስለመ ኖሩ ማስረጃ የሚያቀርብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለመታወቂያ ዝግጅትና ለመመዝገቢያ ሰባት ሺህ የ ኡጋንዳ ሽልንግ በመክፈል ማህበረሰቡን መቀላቀል እንደሚችል የማህበረሰቡ የስራ ኃላፊዎች ለሐበሻ ዊ ቃና ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበሩትን አመራር አባላት በተለያዩ ም ክንያቶች መዳከም የማህበረሰቡን እንቅስቃሴውን አጓቶት እንደቆየ የማህበረሰቡ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ባንቲሁን ኃይሌ ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት በ ካምፓላ የደረሰው የቦምብ አደጋ ማህበረሰቡ በአ ዲስ መንፈስ ተደራጅቶ ለኢትዮጵያውያን ወገኖች አለኝታ መሆን እንዳለበት የማንቂያ ደወል አንደነበ ር ገልጸዋል። በመሆኑም ፍንዳታውን ተከትሎ በተ ጠራው ስብሰባ የተጓደሉ የአመራር አባላት ተተክተ ው እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ማህበረሰብ ለምን?

ከጤና ቡድን እስከ ማህበረሰብ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ምስረታ ታሪክ ከኤ ርትራ ነጻነት በፊት እና በኋላ የተለያየ ታሪክ አለ ው። ከኤርትራ ነጻነት በፊት ተመስርቶ የነበረ ማህ በረሰብ ሁለቱንም ህዝቦች በአንድ ጥላ ስር ያሰባሰ በ ነበር። “ያኔ የተቋቋመው ማህበረሰብ በገንዘብም ሆነ በአደረጃጀት ጠንካራ ነበር” ይላሉ የአሁኑ የኢ ትዮጵያ ማህበረሰብ ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጉሴ ባል ቻ፡፡ ይህ መሰባሰብ ግን ከአንድ ዓመት በላይ መዝ ለቅ አልቻለም፡፡ “በወቅቱ የነበረው በዘርና በጎሳ የ መከፋፈል ችግር ለማህበረሰቡ መፍረስ ምክንያት ነ በር” ይላሉ አቶ ንጉሴ፡፡ ይህ ማህበረሰብ ከፈረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ እ.ኤ.አ በ1996 በኡጋንዳ የሚኖሩ ስደተኞች ማህበ ረሰብ ተመሰረተ፡፡ ይህም ግን ከቀደመው ማህበረሰ ብ ጋር በሚመሳሰል ችግር ብዙም ሳይራመድ በአን ድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመፍረስ በቃ፡፡ ከአራት ዓመ ታት በኋላ ግን ለዛሬው የኢትዮጵያውያን ማህበረ

ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ባንቲሁን ኃይሌ

ሰብ መገኘት አስተዋጽኦ ያበረከተ ማህበር ተመሰረ ተ-የኢትዮጵያ የጤና ስፖርት ቡድን፡፡ ይህ የስፖር ት ቡድን ሲመሰረት አላማው እየተሰባሰቡ እግር ኳ ስና ሌሎች የስፖርት ዓይነቶችን ማዘውተር ነበር፡፡ “[የተሳታፊዎቹ] ብዛት እያደገ ሲሄድ ግን ለምን ወ ደ ድርጅት አንለውጠውም የሚለው ሀሳብ መጣል ን፡፡ እናም [እ.ኤ.አ] በ2003 ለአብያተክርስቲያናት ድጋፍ ለማድረግ፣ የታመሙትን ለመርዳት እና የሞ ቱትን ለመቅበር በሰባት የአመራር አባላት ማህበሩ ተቋቋመ” ሲሉ አቶ ንጉሴ እንዴት ማህበሩ አንድ ር ምጃ ወደ ፊት እንደተራመደ ያብራራሉ፡፡ ማህበሩ በሁለት እግሩ የቆመ ቢመስልም አመራሮ ቹ ግን በአቅም ማነስ ምክንያት እንዳሰቡት ሊራመ ድ አልቻለም፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2005

በኡጋንዳ የሚኖሩ 20 ያህል ታዋቂና ተሰሚነት ያላ ቸውን ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው የገጠማቸውን ፈተና ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ከመ ረዳጃ ማህበር የዘለለ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እንዲሚሰረት ጥያቄ የቀረበው። ጥያቄው ተቀባይነ ት በማግኘቱም ዘጠኝ አባላትን ያካተተ አስተባባሪ ኮሚቴ ተሰየመ፡፡ በዚህ ስብሰባ የተጸነሰው ማህበረሰብ ብዙዎች እ ንደተመኙት ለወገኖቹ የሚጠበቅበትን ያህል ሊያ በረክት አልቻለም፡፡ አሁን በስራ ላይ ያሉት የኢት ዮጵያ ማህበረሰብ የስራ ኃላፊዎች በፊት የነበረውን የቅንጅት ማነስን እንደ ምክንያት ያነሳሉ። “ማህበ ሩ በሶስት የአመራር አባላት ብቻ ነበር የሚንቀሳቀሰ ው፡፡ በዚህ ላይ በወቅቱ የነበሩት የማህበረሰቡ ሊቀ

በካኩማ ያሉ ስደተኞች ለመልሶ ማስፈር ቃለ መጠየቅ እየተደረገላቸው ነው በኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ በዓለም ትልቁ በሆነው የኬንያው የካኩማ ስደተ ኞች ካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሶስተኛ አገር ለ መሄድ የሚያስችላቸውን መስፈርት ማሟላት አለ ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ቃለ መጠየቅ እየተደረ ገላቸው ነው። ቃለመጠይቁ እየተካሄደ ያለው በተባበሩት መንግ ስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አ ር) አማካኝነት ነው። ለመልሶ ማስፈር ብቁ የሆኑ ሰ ዎችን የመለየት ሂደቱ የተጀመረው ከሶስት ሳምንት በፊት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል። እ.ኤ.አ በ2003 እና በ2004 ካኩማን የተቀላቀሉ ስ ደተኞች በሙሉ ለቃለመጠይቁ ተጠርተዋል። ዩ.ኤ ን.ኤች.ሲ.አር እ.ኤ.አ በ2005 ወደ ካምፑ ከከገቡ ስ ደተኞች መካከል የተወሰኑትንም ለመልሶ ማስፈር አነጋግሯል። በአሁኑ ወቅት በካኩማ የስደተኞች ጣ ቢያ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ይኖራሉ። ከ ስደተኞች መርጃ ድርጅት የተገኘ ቁጥር እንደሚያ መለክተው 35 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬ

በኡጋንዳ የሚኖሩ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በተለ ያዩ ምክንያቶች አገራቸውን ጥለው የወጡ ስደተኞ ች እንደሆኑ ይታወቃል። በተባበሩት መንግስታት የ ስደተኞች መርጃ ድርጅትም (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ አር) ሆ ነ በሌሎች የስደተኞችን ጉዳይ በሚከታተሉ ተቋማ ት በተናጠል የሚደርሱባቸው ችግሮች አሉ፡፡ ከዚህ ም ባሻገር በማህበራዊና በኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያ ት ጥቂት የማይባሉት ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ ከእነ ዚህ መካከል ህመም፣ ከስራ መፈናቀልና ሞት ይጠ ቀሳሉ፡፡የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ያኔ መጀመሪ ያ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አላማው እነዚህን ችግ ሮች በጋራ መፍታት ነው፡፡ አቶ ባንቲሁን እንደሚሉት “ለዓመታት ትንሽ እየሰ ራ ብዙ የተኛውን” የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ከ እንቅልፉ ማንቃት የተፈለገውም ለዚሁ ነው፡፡ እንደ እርሳቸው አባባል በአዲስ መንፈስ ተዋቅሮ ጽህፈት ቤት እስከመክፈት የደረሰው የአሁኑ ማህበረሰብ ረ ጅም ራዕይ አለው፡፡ ይህንን ለማሳካትም ከዚህ በፊ ት የነበረው መተዳደሪያ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔ ታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እየተሻሻለ ነው፡፡ ራ ስን አስተዋውቆ የአባላቱን ቁጥር በማሳደግ ብዙ ኢ ትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ማድረግም የማህበረሰቡ ዓላማ ነው፡፡

የማህበረሰቡ ተግዳሮቶች የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ ሶስት ጊዜ ተቋቁሞ ሁለት ጊዜ ፈርሷል፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ቢ ኖርም ህልውናው ፈተና ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡ በ መሆኑም ማህበረሰቡ አሁን ያለበት ደረጃ አራተኛ

ው ምዕራፍ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ምክንያቱ ም የአሁኑ ቢያንስ ጽህፈት ቤት መክፈት፣ መታወ ቂያ ማደልና ከኢትዮጵያውያን ጋር ግንኙነት ካላቸ ው አካላት ጋር መወያየት ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ አ ሁንም ቢሆን ማህበረሰቡ የተጋረጡበት ፈተናዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኡጋንዳ እንደ ብዙዎች በውጭ ሀገራት እንደሚቋቋሙ ማህበረሰቦች በጥ ርጣሬ ከመታየት አላመለጠም፡፡ ማህበረሰቡ በቅር ቡ ያደረገውን ስብሰባ ተካፍለው ሀሳባቸውን ያካፈ ሉ የመኖራቸውን ያክል ከዳር ቆመው የማህበረሰቡ ን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡም አሉ፡፡ በ ማህበረሰቡ ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ የፖለቲካ ወገንተኝነት ጉዳይ ነው፡፡ የማህበረሰቡ የስራ ኃላፊ ዎች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም፡፡ እነርሱ እንደ ሚሉት ማህበረሰቡ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ ዘር እና ሀይማኖት ነጻ የሆነ የኢትዮጵያውያንን ች ግሮች ለመፍታትና በተለይም ለስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት ለማገልገል የተቋቋመ ነው፡፡ “ከፖለቲካ መሸሽ አይቻልም፡፡ ግን የማንንም ፖ ለቲካ ፓርቲ ደግፈን ወይም ተቃውመን አንቀሳቀስ ም” ይላሉ አቶ ንጉሴ “በአንዳንድ የኢትዮጵያውያን ን አንድነት በማይፈልጉ ወገኖች በኩል የሚሰራጭ ውዥንብር” ላሉት ትችት ምላሽ ሲሰጡ፡፡ “ማንኛ ውንም የፖለቲካ ፓርቲ አናስተናግድም፡፡ ይሁን እ ንጂ በጋራ የሚያወያየን ጉዳይ ሲኖር እንወያያለን፡ ፡ ፖለቲካም ከእነዚህ አንዱ ነው፡፡ከዚህም በተጨ ማሪ ለምሳሌ ስደተኞችን የሚጎዳ ጉዳይ ሲኖር ወይ ም ወደ ሀገራቸው መመለስ ሲፈልጉ ከኤምባሲ ጋ ር እንነጋገራለን፡፡ በጋራም መፍትሄ እንፈልጋለን፡፡” የበጀት ውስኑነትና የሰው ሀይል እጥረት ማህበረሰ ቡ አሉብኝ የሚላቸው ችግሮች ናቸው፡፡ የማህበረ ሰቡ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የአባላቱ መዋጮ ሲሆን እ ያንዳንዱ አባል ሲመዘገብ ከሚከፍለው ሰባት ሺህ ሺልንግ በተጨማሪ ቢያንስ ሁለት ሺህ ሺልንግ ወር ሃዊ መዋጮ እንዲከፍል ይጠበቃል፡፡ ይህ ግን የማ ህበረሰቡ አመራሮች እንደሚሉት ለቢሮም ሆነ ተያ ያዥ ወጪዎች ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ኡጋንዳ ለስደተኞች ጊዜያዊ ማረፊያ ከመሆኗ ጋ ር ተያያዞ የሚፈጠረው የሰው ሀይል ውሱንነት እና በቋሚነት ለማገልገል ያለመቻልችግር ለማህበረሰቡ ውጤታማነት የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ኃ ላፊዎቹ ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኡጋንዳ እነዚህን ተግዳ ሮቶች መጋፈጥ ቢጠበቅበትም የማህበረሰቡ ኃላፊ ዎች ግን ከእስካሁኖች የተሻለ ተግባር እናከናውናለ ን ባይ ናቸው።

ኬንያ ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እና ካናዳ እየሄዱ ነው በኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

የካኩማ ስደተኛ ጣቢያ በዓለም ትልቁ ነው

ንያ ይኖራሉ። ከእነዚህ ውስጥ 14 ሺህ ያህሉ ጥገኝነ ት ጠያቂዎች ናቸው። ቃለመጠይቁ የተደረገላቸው የካኩማ ስደተኞች ውጤታቸውን እንደከዚህ ቀደሙ በሁለት ቀን ልዩ ነት ሳይሆን ከሳምንት በኋላ እንዲያውቁ እንደተደ

ሀበሻዊ ቃና በሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ የሚታተም ጋዜጣ

ረገ እንደሆነ በካኩማ የሚገኝ እና ስሙ እንዲጠቀ ስ ያልፈቀደ ስደተኛ ለሐበሻዊ ቃና ገልጿል። ከስደ ተኞቹ መካከል መስፈርቱን አሟልተው የሚገኙቱ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ ወይም ካናዳ እንደሚመደ ቡም ተናግሯል።

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

የአሜሪካ እና ካናዳ መንግስታት በመልሶ ማስፈር ፕሮግራሞቻቸው የመረጧቸው በ ኬንያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የ ሀገራቱ መጓዝ ጀመሩ። ስደተኞችን የመውሰድ ቅድሚያውን የያዘ ችው ካናዳ ስትሆን የመጀመሪያውን የተጓ ዦች ቡድን ከሳምንት በፊት ተቀብላለች። አሜሪካም የካናዳን ፈለግ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተከትላለች። ወደ አሜሪካ የሚሄዱት ስደተኞች ሙሉ ለሙሉ የመጡት በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ከ ሚገኘው ካኩማ ስደተኞች ጣቢያ ነው። በ ሁለት አውቶብሶች ተጭነው ከሳምንት በፊ ት ናይሮቢ የደረሱት ስደተኞች ጊዜያዊ መ ቆያቸው ወደ ሆነው እና በተለምዶ “ጎል” ተ ብሎ ወደሚጠራው የዓለም የስደተኞች ድ

ርጅት (አይ.ኦ.ኤም) ቅጥር ግቢ ተወስደዋል። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል የመጀመሪያዎ ቹ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። ይህ ጉዞ ላለፉት አራት ወራት ተ ቋርጦ የቆየውን ከኬንያ ወደ አሜሪካ ለመል ሶ መስፈር የሚደረገውን በረራ እንደገና ያስጀ መረ ነበር። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆ ነ እ.ኤ.አ በ2009 ብቻ 75 ስደተኞች በአሜሪ ካ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። የአሜሪካ ጎረቤት ካ ናዳ በየዓመቱ ከ10 እስከ 12ሺህ ስደተኞችን በ መልሶ የማስፈር ፕሮግራሟ አማካኝነት ትቀ በላለች። ከኬንያ ወደ ካናዳ የሚደረገው የስደተኞች የ መልሶ ሰፈራ ጉዞ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (ጁን 11) እንዲጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል።

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ዩጋንዳ ካምፓላ ጋባ ሮድ-ካሳንጋ ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6 ስልክ +256-778-693669


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

3

ዜና

በደቡብ ሱዳን ያገረሸው ግጭት ኬንያ ኢቦላ ድንበሯን እንዳይሻገር የጤና የቀጠናውን ሰላም እንዳያናጋው ተሰግቷል ምርመራዋን አጠናክራለች l ኢትዮጵያ በአቤዬ ሰላም አስከባሪ ልታሰፍር ትችላለች l “ቫይረሱ በካምፓላ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እያደረግን ነው” ከንቲባ ኤርያስ ሉካጎ በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ በኡጋንዳ ምድር ለሶስተኛ ጊዜ የተከሰተው ኢቦላ ባለፈው ወር አንዲት የ12 ዓመት ታዳጊ መግደሉን ተከትሎ ኬኒያ የድንበር ላይ የጤና ምርመራዋን ማጠናከሯን አስታውቃለች፡፡ የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚለው ባለፈው ወር ከካ ምፓላ 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሊዌሮ ታዳጊዋ በኢ ቦላ እንደሞተች ከተረጋጋጠ በኋላ ለጉዳዩ የተቋቋመ ልዩ ግብረ ሀ ይል ከሟች ጋር ሊነካኩ ይችላሉ ባላቸው 25 ያህል ሰዎች ላይ ም ርመራ አድርጓል፡፡ ሆኖም ሁሉም ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን ነ ው ግብረሃይሉ ያስታወቀው፡፡ ይሁን እንጂ ኬኒያ ከኡጋንዳ ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞች ከቫ ይረሱ ነጻ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ድንበር አካባቢ ላሉ የጤ ና ባለሙያዎቿ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፋለች፡፡ ይህንን ተከትሎም በተለይ በማላባ ድንበር በኩል ወደኬኒያ የ ሚገቡ መንገደኞች ከወትሮው በተለየ ጥልቅ የጤና ምርመራ እየ ተደረገላቸው ነው፡፡ “ወደ ኬኒያ ድንበር የሚሻገር ማንኛውንም መንገደኛ በሚገባ እየ መረመርን ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አደገኛ በሽታ ነው” ብለዋል የ ቴሶ አካባቢ ሀኪም ዶክተር መልሳ ሉቶሚያ፡፡ በድንበሩ አካባቢ ላሉ ነዋሪዎችም ስለቫይረሱ ምንነትና ስርጭቱን ለመግታት ማድ ረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ እያስተማሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኡጋንዳ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ካምፓላን እንዲያስተዳድ ሩ የተመረጡት ከንቲባ ኤርያስ ሉካጎም ኢቦላ በዋና ከተማዋ እ ንዳይከሰት ጥንቃቄ እያደረጉ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረ ዋል፡፡ ሉካጎ እንዳሉት ቫይረሱ ማንንም የካምፓላ ነዋሪ እንዳያጠቃ ለ ማስቻል አስተዳደራቸው የኢቦላን መከሰት የሚከታተልና የሚያ ጣራ ቡድን አቋቁሟል፡፡ በኢቦላ መያዛቸው የሚጠረጠር ህመም ተኞችን ለማጣራትም በካምፓላ አስተዳደር ሆስፒታሎችና በየክ ፍለከተሞቹ የህክምና ማዕከል መዘጋጀቱን አመልክተዋል፡፡ ኢቦላ መድሃኒት ያልተገኘለት ገዳይ በሽታ ሲሆን ምልክቶቹም ማንቀጥቀጥ፤ተቅማጥ፤ ተከታታይ የደም መፍሰስና ድካም ናቸ ው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም እነዚህ ምልክቶች ያየ ግለሰብ በአ ቅራቢያው ላለ የህክምና ተቋም ማሳወቅ እንዳለበት የኡጋንዳ መ ንግስት አሳስቧል፡፡ በፍጥነት የመዛመት አቅም እንዳለው የሚነገርለት ኢቦላ ከደ ም፤ከሰገራ እንዲሁም በቫይረሱ ከተጠቃው ግለሰብ ከሚወጡ መሰል ፈሳሽ ነገሮች ጋር በሚደረግ ቀጥታ ንክኪ ይተላለፋል፡፡ በኡጋንዳ ኢቦላን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብ ረሃይል በአሁኑ ወቅት በሽታው በቁጥጥር ስር እንደዋለ ቢያስታ ውቅም ድንበር አካባቢ ያሉ የኡጋንዳ ከተሞች ግን በሽታው መከ ሰቱ ከተሰማ ጀምሮ በቻሉት ሁሉ ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ና ቸው፡፡ አሜሪካም በሀገሪቱ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕ ከል አማካኝነት ወደ ኡጋንዳ ለሚጓዙ ዜጎቿ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፡፡ ማንኛውም አሜሪካዊ ወደ ኡጋንዳ ከመሄዱ አስቀድ ሞ ስለበሽታው ግንዛቤ እንዲኖረው በሚል፡፡ መድሃኒት አልባውና ገደዩ የኢቦላ በሽታ በኡጋንዳ ሲከሰት ይህ ለሶስተኛ ጊዜው ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2000 ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ኢቦላ ለ224 ሰዎ ች ሞት ምክንያት ሲሆን በ2007 ለሁለተኛ ጊዜ ተከሰተውና ም ንነቱን ለማወቅ ሶስት ወራትን የፈጀው ደግሞ የ37 ሰዎችን ህይ ወት ቀጥፏል፡፡

ኢቦላ ምን አይነት በሽታ ነው? አልም አቀፉ የጤና ድርጅት የኢቦላን ቫይረስ መጀመሪያ ከተነሳ በት አካባቢ ጋር በማዛመድ ቢያንስ በአምስት ይከፍለዋል፡፡ የዛ የር፤ የሱዳን፤ የኮቲዲቯር፤ የቡንዲቡግዮ እና የሬስተን በሚል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው እ.ኤ.አ በ1976 በያኔዋ ዛየር በዛሬዋ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ኮንጎ ሞንጎላ ግዛት በምትገኝና ያምቡኩ በምትባል መንደር ነው፡ ፡ በወቅቱ መምህር የነበረው ማባሎ ሎሌካ የዚህ ቫይረስ የ መጀመሪያው ተጠቂ በመሆን በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ ከዚያ በኋላ ዝርያውን በተወሰነ መልኩ ቀይሮ ወደ ሱዳን የተሸገረ ው ኢቦላ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1989 በአሜሪካ ቨር ጂኒያ ሬስተን ውስጥ እንደታየ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ የአለ ም አቀፉ ጤና ድርጅት እንደሚለው ይህ በአሜሪካ የታየው ኢቦላ በሰው ሳይሆን በዝንጆሮ ላይ የተከሰተ ነው፡፡ በወቅ ቱም ብዙ ዝንጆሮዎች በቫይረሱ ሞተዋል፡፡ በ1994 ደግሞ ሌላ የኢቦላ ዝርያ በኮቲዲቯር ተከስቶ አን ድ ሰውና ለበርካታ ቺምፓንዚዎችን ገድሏል፡፡ ይህ ከሆነ ከ አንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ኢቦላ መጀመሪያ ወደተከሰተበ ት ኮነጎ ተመልሶ 250 ሰዎች ለህልፈት ዳርጓል፡፡ ኢቦላ በጋ ቦንም በ1994 ተከስቶ የዘጠኝ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

ኢቦላና ኡጋንዳ ጥቂት ኡጋንዳውያን በሩቁ ይሰሙት የነበረውና ብዙዎቹ ምንነቱን እንኳ የማያውቁት ይህ ቫይረስ በጥቅምት 2000 (እ.ኤ.አ.) ድንበራቸውን ተሻግሮ በሰሜን ኡጋንዳዋ ጉሉ ከ ተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰተና 162 ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሰባ ት ዓመታት በኋላ ደግሞ ቡንዲቡግዮ በሚባለው አካባቢ አ ዲስ አይነት የኢቦላ ቫይረስ ተከስቶ እንደመጀመሪያው ሁ ሉ አንድ የህክምና ዶክተርን ጨምሮ 37 ሰዎችን ገድሏል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ኢቦላ በኡጋንዳ ተከስቷል፡፡ በሟቾች ቁጥር የአሁኑ የተሻለ ቢሆንም ገና የቫይረሱ ጨር ሶ መጥፋት ስላልተረጋገጠ ነዋሪዎችንና የህክምና ባለሙያዎ ችን እረፍት መንሳቱ አልቀረም፡፡ አንድ ሰው እንደ እድል ብሎ በቫይረሱ ከተጠቃ የህክም ና ባለሙያዎች ግለሰቡን ለብቻው እንዲቀመጥና ከማንም ጋር ንክኪ እንዳያደርግ ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱም አስቀድ መው ካልተከላከሉት ኢቦላ እንደ ኤች አይቪ ሁሉ መድሀኒ ት የለሽ በመሆኑ፡፡ በጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ብቻ እንደሚገኝ የሚነገረው የ ኢቦላ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ ባለቤት የሆነችው ኡጋንዳ ኢንቴቤ በሚገኘው በዚህ መሳሪያ በጠቀም ለቫይረሱ ክት ባት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ የጀመረች የመጀመሪያዋ አፍሪ ካዊት ሀገር ሆናለች፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጥረት ተሳክቶ ውጤታማ ክትባት ማግ ኘት ቢቻል እንኳን ከ አምስት ዓመት በኋላ እንጂ ከዚያ በ ፊት ለማድረስ የማይታሰብ መሆኑን በምርምሩ የሚሳተፉ ት ባለሙያዎች ለተባበሩት መንግስታት የዜና አውታር ተ ናግረዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ በረጅም ጊዜ እቅዳቸውም ከቫይረሱ ፈዋሽ መድሃኒት ለመቀመም ከተቻለም አንድ ሰው በቫይረሱ ከተ ያዘም በኋላ ሊተርፍ የሚችልበትን መድሃኒት ለመፈለግ እየ ሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአሜሪካ የህክምና ጠበብቶች ያገኙት ክት ባት ከቫይረሱ የመፈወስ አቅም ቢኖረውም ግለሰቡ በኢቦላ ከተጠቃ በ30 ደቂቃ ውስጥ መሰጠት ያለበት በመሆኑ የታ ሰበውን ውጤት አላመጣም፡፡ እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ ኢቦላ ለመጀመ ሪያ ጊዜ ከተከሰተበት እ.ኤ.አ 1976 ጀምሮ 1850 ህመምተ ኞች ሲመዘገቡ 1200 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወ ታቸው አልፏል፡፡

በቃጠሎ የወደመው ኩሽ ሆቴል እንደገና ሊሰራ ነው በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና ከአራት ወራት በፊት በደረሰበት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበ ት ኩሽ ሆቴል በቅርቡ ስራ ሊጀምር ነው። በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ልዩ ስም አትላባራ በሚባለው ቦ ታ የሚገኘው ይሄው ሆቴል በአደጋው ምክንያት አቋርጦት የነበረ ውን የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ለመስጠት እድሳት ሲያከና ውን ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት እድሳቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ስራውንም በዚህ ወር ውስጥ እንደሚጀምር ጁባ የሚገኙ የሐበሻዊ ቃና ምንጮች ገልጸዋል። ኩሽ ሆቴል ንብረትነቱ የአቶ ጌቱ ሽብሩ ሲሆን ለአምስት ዓመታ ት ያህል ለወይዘሮ አብረኸት በኮንትራንት ተከራይቶ ነበር። ሆቴ ሉን ከማስተዳደር ባሻገር ምግብ በማዘጋጀት ለሚሳተፉት ወይዘ ሮ አብረኸት ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ገደኛ ቀን አልነበረም። በዕ ለቱ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ገደማ ምግብ ይሰሩበት የነበረው ሲሊንደር ፈንድቶ ቤቱን በእሳት ያይዘዋል። የመመገቢያ አዳራሹ የባህላዊ ምግብ ቤት መልክ እንዲይዝ ከጣሪያ በላይ ሳር ለብሶ ስ

ለነበር እሳቱ በፍጥነት እንዲቀጣጠል ምክንያት ይሆናል። በዚህ አደጋ ወይዘሮ አብረኸትን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰ ዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተቃጠሉ ሲሆን ሌሎች ሶስት የሆቴ ል ቤቱ ሰራተኞች እሳቱ በከፊል አግኝቷቸዋል። አደጋው የ ደረሰባቸው ሰዎች ወዲያውኑ ወደ ጁባ ቲቺንግ ሆስፒታል ቢወሰዱም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ግን ተጨማሪ እና አፋጣኝ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ስለነበር ወደ አዲስ አበ ባ እንዲላኩ ይወሰናል። በጁባ የኢትዮጵያውያን ማህበር፣ በከተማይቱ የሚኖሩ ኢ ትዮጵያውያን እና የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች በጋራ ባደረጉት ጥ ረት ለአየር ትራንስፖርት የሚያስፈልገውን ወደ አስር ሺህ ዶላር ገደማ ገንዘብ ማሰባሰብ ችለዋል። በተሰበሰበው ገንዘ ብ አማካኝነትም ከፍተኛ ቃጠሎ የደረሰባቸው አምስቱ ተ ጎጂዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከዋል። በየካቲት 12 እና ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኙ ከተደረጉት ተጎጂዎ ች መካከል ወይዘሮ አብረኸት እና ሌላ እንስት ተጎጂ ህይወ ታቸው አልፏል።

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ ደቡብ ሱዳን በሚቀጥለው ወር ዘጠነኛው ቀን ላይ ነጻነቷን በይ ፋ ታውጃለች፡፡ ሀገሪቱ ወደነጻነት ቀኗ እየተጠጋች በሄደች ቁጥር ግን በአቤዬ ያለው ግጭት እየተባባሰ መጥቷል፡፡ የተባበሩት መንግስታት እንደሚለው የያዝነው የፈረንጆች ዓመ ት ከገባ ጀምሮ እስከ አለፈው ወር መጨረሻ ከ1500 በላይ ሰዎ ች ተገድለዋል፡፡ ቢያንስ 96,000 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተ ፈናቅለዋል፡፡ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን በነዳጅ ክምችት የተሞላች ናት የምትባለ ውን አቤዬን ህዝበ ውሳኔ ተካሂዶ የማንነቷ እስኪለይ ድረስ በጋራ ለማስተዳደር እ.ኤ.አ በ2005 ከስምምነት ደርሰው ነበር፡፡ ይህን ስምምነታቸውን መሰረት በማድረግም የባለፈው ጥር ህዝ በ ውሳኔ አቤዬንም እንዲያካትት በ2008 ከስምምነት ተደርሶ ነ በር፡፡ ሆኖም ህዝበውሳኔው በሚደረግበት አካሄድ ላይ ሁለቱ ወ ገኖች(ሰሜንና የደቡብ ሱዳን አስተዳዳር)ባለመስማማታቸው የአ ቤዬ ህዝበ ውሳኔ ላልተወሰነ ጊዜ ሊተላላፍ የግድ ሆነ፡፡ ህዝበውሳ ኔው ተደርጎ አቢዬ የደቡብ ወይም የሰሜን ሱዳን አካል ናት እሲ ኪባል ድረስ ግን በጥምር ሀይል እንድትተዳደር ነበር ውሳኔው፡፡ ሰሞኑን ግን የአልበሽር መንግስት በደቡብ ሱዳን ድንገተኛ ጥቃ ት ተከፍቶ 22 ያህል ወታደሮች ተገደሉብኝ በማለት በታንክ የታ ገዘ ጦሩን ወደ አቢዬ ልኮ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡ ይህን ተ ከትሎ በአካባቢው የነገሰው ውጥረትም ለብዙዎች ሞትና ከቤት ንብረት መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን ቁጥሩ የተባ ባሩት መንግስታት በተጨባጭ አለኝ ከሚለው ቁጥር ጋር ሲነጻጸ ር የሚበልጥ ቢሆንም የደቡብ ሱዳን አስተዳዳር 150 ሺህ ያህል ዜጎች ግጭቱን ለመሸሽ ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው ን አስታውቋል፡፡ “ሁኔታው አስከፊ ነው፡፡ ሰዎች ግጭቱን በመፍራት ማቄን ጨ ርቄን ሳይሉ እየሸሹ ያለመጠለያ ቀርተዋል” ብለዋል የደቡብ ሱዳ ን የሰብኣዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮክ ሩኤአ ለቢቢሲ፡፡ ሊሴ ግራንዴ የተባሉ ሌላ በደቡብ ሱዳን ተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ ጉዳዮች ከፈተኛ ባለስልጠን በበኩላቸው “96 ሺህ ስደተ ኞች እኛ ያረጋገጥነው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎቹ በየጫካው እየ ተደበቁ ስለሸሹ ቁጥሩን ከፍ ሊደርገው ይችላል” ማለታቸውን ሮ ይተርስ አስነብቧል፡፡ ይህን ተከትሎ ሁለቱ ወገኖች በሶስተኛ ወገን አማካኝነት በአዲ ስ አበባ ባደረጉት ወይይት በጋራ ድንበራቸው ላይ ነጻ ቀጠና ለ ማቋቋም ተስማማተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ስምምነቱ አቤየን በስም ካለመጥቀሱም በተጨማሪ ከመቼ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረ ግ ቀን ባለመቆረጡ የሁለቱን ወገኖች ችግር ስለመፍታቱ ጥርጣ ሬ አጭሯል፡፡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ግን “በቂ ጦርነት ስላደረ ግን ምንም ቢሆን ከእንግዲህ ተመልሰን ወደ ጦርነት አንገባም ነጻ ነታችንንም አደጋ ላይ አንጥልም” እያሉ ነው፡፡ እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ አልበሽር ግን ሳልቫኪር አቢዬ ትገ ባኛለች ካለ ለደቡብ ሱዳን እውቅና አልሰጥም ባይ ናቸው፡፡እን ዲያውም ግዛቷ የሰሜን ሱዳን ናት በሚል ጦራቸውንም ከስፍራ ው እንደማያስወጡ አስታውቀዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት የጸ ጥታው ጥበቃ ምክርቤት ጦራቸውን ከአወዛጋቢዋ አቤዬ እንዲ ያስወጡ ያቀረበውን ማስጠንቀቂያም ውድቅ እስከማድረግ ደር ሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የሰላም አስከባሪ ጦር ጥያቄ ከሁ ለቱም ወገኖች ከመጣ አዎንታዊ ምላሽ እሰጣለሁ እያለ ነው፡፡ ሀ ሳቡ በደቡብ ሱዳን በኩል ሙሉ ተቀባይነት ቢያገኝም የአልበሽር መንግስት ግን “ጉዳዩን እያጤንኩት ነው” ብሏል፡፡

አቢዬ ተፈላጊዋ(የሁለት ባል) ሚስት የሰሜንም ሆነ ደቡብ ሱዳን አስተዳዳሪዎች አቢዬ የኔ ናት ይላ ሉ፡፡ ይህ ብዙዎች እንደሚያስቡት በነዳጅ ምክንያት ብቻ የመጣ አይደለም፡፡ ከነዳጅም ባሻገር ጉዳዩ በጎሳዎች መካካል ያለ የይገባ ኛል ውዝግብ ነው፡፡ ከኢኮኖሚም አልፎ የዘር ጥያቄ ነው ለአቢ ዬ እንቆቅልሽ መፍትሄ እንዳይገኝ እንቅፋ የሆነው የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡ አቢዬን ዲንካ ኒጎክ የተባሉ የደቡብ ሱዳን ቡድኖች የእኛ ናት ሲሉ ሚዘሪያ የተባሉት የሰሜን ሱዳን አርብቶአደሮችም አቢዬ የምትገባው ለእኛ ነው ይላሉ፡፡ ሁለቱ ጎሳዎች ብዙ ጊዜ ለከብቶቻቸው በሚፈልጉት ምግብና ው ሃ ሳቢያ ይጋጫሉ፡፡በእርስ በእርስ ጦርነቱ ወቀውትም ሚዘሪያዎ ች ከካርቱም መንግስት በሚታጠቁት መሳሪያ ደቡብ ሱዳንን ያጠ ቁ እንደነበር ይነገራል፡፡ የተባባሩት መንግስታት ሰሞኑን በሄሊኮ ፕተሮቼ ላይ ተኩስ የከፈቱት የሚዘሪያ ሚሊሻዎች ናቸው ሲል ይ ወቅሳል፡፡ የሚዘርያ ጎሳ መሪ ወቀሳውን ቢያጣጥሉትም፡፡ ከሁለቱ ጎሳዎች እስከ መንግስታት የምትፈለገው አቤዬ በቀላሉ እንዱን መምረጥ ወይም በአንዱ መመረጥና ሰላማዊ ትዳር መመ ስረት አልቻለችም፡፡ ይህ ደግሞ በአፍሪካ በስፋቷ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ሱ ዳን ለዓመታት ከነበረችበትና ለ2 ሚሊየን ሰዎች ሞትና ለበርካቶ ች ስደት ምክንያት ከሆነው ግጭት የመውጣቷን ነገር አጣብቂኝ ውስጥ አስገቶታል፡፡ ደቡብ ሱዳናውያንም የሚጓጉለትንና በካርዳችን አገኘነው የሚ ሉትን የነጻነት ቀን ከናፍቆት ይልቅ በስጋት እንዲጠብቁት እያደረ ጋቸው ነው፡፡ተንታኞች እንደሚሉት የአቤዬ ጉዳይ በቶሎው እል ባት ካላገኘ እነዚሁ ወገኖች ነጻነታቸውን ብዙም ሳያጣጥሙ ዳግ

ም ወደ እልቂት መግባታቸው አይቀርም፡፡ ለጋሽ ሀገራት በበኩላቸው የሰሜን ሱዳን መንግስት አቤዬን በሀ ይሉ ከተቆጣጠረ የእርዳታ እጃችን ያታጠፋል እያሉ ማስፈራራት ይዘዋል፡፡ በሱዳን የአሜሪካ መልዕከተኛ ፕሪንስተን ሌይማን አል በሽር በጉልበቱ አቤዬን ከወሰደ ሱዳን ያለባትን በቢሊየኖች የሚ ቆጠር እዳ ለመሰረዝ የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ ይጥለዋል ሲ ሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ አልበሽር ጦራቸውን ከአቢዬ በቶሎ ካላስወ ጡም አሜሪካ አሸባሪዎችን ይደግፋሉ በሚል ከመዘገበቻቸው መ ካከል ሱዳንን የመሰረዟ ነገር አጠራጣሪ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ሰላም ለምስራቅ አፍሪካ በደቡብ ሱዳንም ሆነ በአጠቃላይ በሱዳን የሚሆነው አዎንታዊ ም ሆነ አሉታዊ እንቅስቃሴ በምስራቅ አፍሪካ በተለይ በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ለአመታት የዘለቀው ግጭትም አነዚሁን ሀገራት በእንቅርት ላይ እንዲሉ ጫና አሳድሮ ባቸው ቆይቷል፡፡ ምክንያቱም በተለይ ግጭቱን በመሸሽ የሚሰደ ዱት ሱዳናውያን የመጀመሪያ መዳረሻቸውን የሚያደርጉት በጎረ ቤት ሀገራት በመሆኑ፡፡ ከሰሞኑ ያገረሸው ግጭትም በተለይ ኡጋንዳን ኬኒያንና ኢትየጵ ያን ዳግም የስደተኞች መከማቻ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ ይህንን የፈሩ ብሎም የደቡብ ሱዳን ሰላም ለእኛም የገበያ እድ ል ማስፋት ነው ያሉት እነዚሁ ሀገራትም ለግጭቱ ሰላማዊ(ዲፕ ሎማሲያዊ) መፍትሄ ለመፈለግ እየጣሩ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ከደቡብ ሱዳን ነዳጅ የማስገባት እቅድ እንዳላት በቅርቡ በፕ ሬዚዳንቷ በኩል ያስታወቀችው ኡጋንዳ ከነዚህ መካካል ተጠቃ ሽ ናት፡፡ የኡጋንዳ አለም አቀፍ ግንኙነት ሚንስትር ሄንሪ ኦኬሎ ኦርየም ለእለታዊው የሀገሪቱ ጋዜጣ ኒው ቪዥን እንደተናገሩት የሙሴቬ ኒ መንግስት በአቤዬ ያለው ሁኔታ አሳስቦታል፡፡ እናም ለግጭቱ እ ልባት ለመሻት ዲፕሎማሲያዊ ግፊት እያደረገ መሆኑን አስታውቀ ዋል፡፡ ኦርየም እንዳሉት ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ከደቡብ ሱዳን አ ቻቸው ሳልቫኪር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡ ሀገራቸው ዳ ግም ጦርነት እንደማትጀምርም ገልጸውላቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ከኬ ኒያው ርዕሰ ብሔር ሙአይ ኪባኪ ጋርም በጉዳዩ ዙሪያ መክረዋ ል፡፡ ስለ ውይይቱ ዝርዝር ሚኒስትሩ ለጋዜጣው ያሉት ነገር ባ ይኖርም፡፡ ኢትዮጵያና ኬኒያ በየፊናቸውም ለችግሩ እልባት ያሉትን እሞ ከሩ ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩ ሳሰበው ይመስላል፡፡ ጠቅ ላይ ሚኒስትር መለስ በቅርቡ ከሱዳን ጋር በተደረገ ስብሰባ መንግ ስታቸው ለሱዳን ሰላምና መረጋጋት የቻለውን ሁሉ እንደሚያደር ግ አስታውቋል፡፡ እንደ አቶ መለስ የሱዳን ሰላም ለእነሱ(ለሱዳና ውያን)ብቻ ሳይሆን ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ነው፡፡ አቶ መለስ ሁለቱ ወገኖች በ2005 የተደረሰው አጠቃላይ ሰላም ተፈጻሚነት እንዲጥሩም ጥሪ አቅርበዋል ከሰሞኑ ከሱዳን የመከላ ከያ ሚንስትር ጄኔራል አብደል ራሂም ሁሴን ጋር በአዲስ አበባ ባ ደረጉት ውይይት፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ለደሱዳን ት ሪቢዩን እንደተናገሩት “በአቤዬ የሰላም አስከባሪ እንዲሰፍር ከሰ ሜንና ደቡብ ሱዳን ጥያቄ ከመጣ ኢትዮጵያ ጥያቄውን ከግምት ታስገባለች፡፡” ጁባን መዳረሻቸው ያደረጉ በርካታ ኢትዮጵያውያንም የደቡብ ሱዳንን ሰላም አጥብቀው ከሚፈልጉት መካከል ናቸው፡፡ ምክንያ ቱም ለሁለት አስርት ዓመታት በደቡብና ሰሜን ሱዳን መካከል የ ዘለቀው ግጭት ካስከተለው እልቂት ባሻገር በርካቶች ቤት ንብረ ታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድረጓል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅ ት በደቡብ ሱዳን ይህ ነው የሚባል በቂ የሰው ሀይልም ሆነ የመሰ ረተ ልማት እንዲሁም አገልግሎት የለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም “ሁነኛ ወዳጄ” ወደሚላት ደቡብ ሱ ዳን ዘልቆ መግባት ይፈልጋል፡፡ የእቅዱን መሳካት አሁን ላይ ሆኖ መተንበይ ቢያስቸግርም ከደቡብ ሱዳን አዲስ አበባ የየብስ ትራን ስፖርት በመዘርጋት የሁለትዮሽ የገበያ ትስስርን የማሳደግም ፍላጎ ት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ ገና ብዙ ባልተበላበት የደ ቡብ ሱዳን ገብተው ጉልበትና እውቀታቸውን በማፍሰስ በገፍ ይ ዘዋወራል ከሚባለው ዶላር መጋራት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚ ሆነው ግን የአቤዬ ጉዳይ እልባት አግኝቶ ደቡብ ሱዳን የሰላም አ የር መተንፈስ ከቻለች ነው፡፡ ለኤርትራውያንም ቢሆን እንደ ደቡብ ሱዳን ለንግድ የሚመች ሀ ገር ያለ አይመስልም፡፡ በአንጻሩ የኤርትራ መንግስት ግን የደቡብ ሱዳንን መገንጠል በቀ ና አይመለከተውም፡፡ እንዲያውም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚን ስቴር ያወጣው መረጃመረጃ የኢሳያስ አስተዳደር ለደቡብ ሱዳን እውቅና አልሰጥም ማለቱን ያስነብባል፡፡ እንዲያውም ደቡብ ሱዳ ን መገንጠል አያዋጣም ሲል ይካራከራል፡፡ የሳልቫኪር መንግስት ግን ከውጪም ሆነ ከውስጥ የተደቀነበትን ፈተና ተቋቁሙ በሁለት እግሯ የቆመች ለራሷም ለጎረቤቶቿም የ ምትጠቅም ሀገር ለመመስረት እየተጋ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሁሉም ግን በቀጣዩ ወር ደቡብ ሱዳን በይፋ የምታውጀውን ነጻነት ተከ ትሎ የሚመጣ ነው፡፡ እስከዚያም ሆነ ከዚያ በኋላ ያለው መንገድ ቀና መሆኑን መመለስ የምትችለው ግን የአቤዬ ግዛት ብቻ ናት፡፡


ሀበሻዊ ቃና

4

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

የስደት ዓለም

ወግ ከሀገረ አሜሪካ

በናኦድ ቤተሥላሴ ሁለት ልዩ ጓደኞች አሉኝ፡፡ ሁለቱም የራሳቸው አ ሜሪካ አላቸው፡፡ አንድ ጓደኛዬ ባገኘችኝ ቁጥር ‹‹ከምታስተምረኝ›› ነገር አንዱ ስለ አሜሪካ ነው፡፡ ትምህርቷን የምትጀ ምረው ‹‹አሜሪካን እኮ አታውቀውም…››ብላ ነው፡፡ ሁልጊዜ የሚገርመኝ ግን እስከአሁን ድረስ ገና ዘንድ ሮ አሜሪካን እንደረገጥኩ አድርጋ ማሰቧ ነው፡፡ ባለ ፈው ሳምንት ተደዋወልንና ስናወራ ስለ ሕክምና ው ድነት ማውራት ጀመርን፡፡ ከዚያ ‹‹አሜሪካን እኮ አ ታውቀውም…›› ስትል ቶሎ ብዬ ‹‹አሁንማ ገባኝ! ሰ ሞኑን እኮ የ23000ዶላር ቢል ደረሰኝ›› አልኳት፡፡ ‹‹አላልኩህም! ቀመስከው አይደል›› ትለኛለች ብዬ ስጠብቅ ‹‹ገና ምን አይተህ..›› አለችኝና አረፈችው፡፡ የእርሷ አሜሪካ ስጠጋው የሚሸሽ አይነት ሆነብኝ፡፡ የማላውቀው አሜሪካ እንዳለ የምትነግረኝ ግን እር ሷ ብቻ አይደለችም፡፡ ባለታክሲው ደግሞ አለ፡፡ የ ዚህ ጓደኛዬ አሜሪካ ደግሞ አስደንጋጭ ነው፡፡ ስንገ ናኝ ከሚጠይቀኝ ጥያቄ አንዱ ‹‹እነ ስካርብሮው ም ንም አላሉህም?›› የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ጆ ስካርብ ሮ /Joe Scarborough/ አንድ የአሜሪካ ቶክ ሾው ሆስት እንደሆነ የተረዳሁት በቅርብ ነው፡፡ ጓደኛዬ አሜሪካ የመጣ ጊዜ ዝነኛ የነበረ ሰው ሊሆን ይችላ ል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጓደኛዬ ስካርብሮ ሲል ‹‹ፈ ረንጆቹ›› ማለቱ ነው፡፡ እና ጓደኛዬን ‹‹እስካሁን ም ንም አላሉኝም›› ስለው ማሰስፈራሪያውን ይለግሰኛ ል፡፡ ቆይ ታያለህ! ድንገት We need to talk ወይም can I see you at the conference room ይሉሃ ል፡፡ እንዲህ ሲሉህ ከሥራ ሊያባርሩህ ነው ማለት ነ ው! ቁርጥህን እወቅ! ይለኛል፡፡ ጓደኛዬ ፈረንጅ አለ ቃየን በግሌ የብጽዕና ማዕረግ እንደሰጠሁት ቢሰማ ምን ይሆን ! እላለሁ አንዳንዴ፡፡

አሜሪካዊ መሆን ጨነቀኝ! አለኝ አሜሪካዊ መሆን ጨነቀኝ! ልቤ አመነታብኝ፡፡ አ ለኝ አንድ ጓደኛዬ፡፡ ለምን? አልኩት፡፡ እንደው ኢ ትዮጵያን መክዳት ከበደኝ፤ አለኝ፡፡ ለምን? አልኩት እንደገና፡፡ በቃ! ምን ልበልህ! ፎርም በሞላሁ ቁጥ ር ዜግነት በሚለው ቦታ አሜሪካዊ ብዬ መሙላት ጨነቀኝ አለኝ፡፡ ጭንቀቱ አሳዘነኝ፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር ል ቡ ውስጥ ታማ ተኝታ ስታቃስት የሰማኋት ያህል ተ ሰማኝ፡፡ ጓደኛዬ በእርግጥ ተጨንቋል፡፡ እኔም ጭን ቀቱ ገብቶኛል፡፡ ኢትዮጵያን እስከመጨረሻው ሳያስ ከዳ፤ ኃጢአትንም እስከመጨረሻው ሳያሰራ የማይለ ቅ ሀገር መጥተን! አልኩ በሆዴ፡፡ ቢሆንም፤ ጓደኛዬ ዞሮ ዞሮ ዜጋ መሆኑ እንደማይቀር ስለማውቀው ትን ሽ በጭንቀቱ መቀለድ አማረኝ፡፡ ስለዚህ ትንሽ ጣዕ ሩን የሚያበዛ ነገር ነገርኩት፡፡ ዜግነት ስትቀበል ምን እንደሚደረግ ታውቃለሁ አ ልኩት፡፡ አላውቅም አለኝ፡፡ ባንዲራቸውን ይሰጡኋ ል፤ ከዛ እጅህን ወደላይ አደርገህ፤ ‹‹እኔ….ለሀገሬ ለአ ሜሪካ….እያልክ ትምላለህ…›› ስለው ‹‹ኡ..!›› ብሎ ራ ሱን ያዘ፡፡ ‹‹እልልታ ግን አይፈቀድም›› አልኩት፡፡ ተ ናደደብኝ፡፡ ‹‹እንዴት እላለሁ›› ብሎ፡፡ በድርቅና መ ልሼ ‹‹እውነቴን ነው! በተለይ ኢትዮጵያውያን እና ቶች ዜግነት ሲሰጣቸው፤ እልልታቸውን እያቀለጡ፤ መሬት እየሳሙ፤ ስላስቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊ ዜ ልዩ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል አልኩት፡፡›› ‹‹እው ነትህን ነው! እውነትህን ነው! በጣም ያሳፍራል! ያና ድዳል…እያለ ብዙ ብዙ ነገር ተናገረ፡፡ ትንሽ ካጨናነቅሁት በኋላ ለእርሱ የሚሆን ማበረ

ታቻ መድኃኒት የሚሆን ምክር ነገርኩት፡፡ ምክሬን የ ጀመርኩት ‹‹ኢትዮጵያ ያለችው የት እንደሆን ታው ቃለህ?›› በሚል ጥያቄ ነው፡፡ ለመልሱ ግን ብዙም ሳ ላስጨንቀው ወደ ምክሬ ገባሁ፡፡ ምክሬ ግን እውነ ተኛ ታሪክ ነው፡፡ አንድ መንፈሳዊ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ ይኼ ጓደኛዬ ሃይ ማኖታዊ ምግባሩ፤ተፈጥሮአዊ ጸባዩ፤ መንፈሳዊ እ ውቀቱ ሁሉ እንከን የማይወጣለት ስለሆነ ያስገርመ ኝ ነበር፡፡ እናም አንድ ቀን ‹‹አስፍዬ! ያንተ እኮ ትክ ክለኛ ቦታ ገዳም ነው!›› አልኩት፡፡ ‹‹ገዳም የት እንዳ ለ ታውቃለህ?›› አለኝ አስፍዬ መልሶ፡፡ ታላቅ ነገር ሊመክረኝ እንደሆነ ገባኝ፡፡ እርሱም መልስ ሳይጠብ ቅ ቀጠለ፡፡ ‹‹ገዳም ያለው ልብ ውስጥ ነው!›› አለኝ፡፡ ‹‹ልብህ ውስጥ ገዳም ከሌለ፤ ገዳም ብትገባም ገዳማ ዊ አትሆንም፡፡ ልብህ ውስጥ ገዳም ካለ ደግሞ፤ መ ርካቶ ሱቅ ውስጥ ተቀምጠህም ቢሆን ገዳማዊ ትሆ ናለህ›› አለኝ፡፡ ታሪኩን አሜሪካዊ ለመሆን ለተጨነቀው ተረጎም ኩለት፡፡ ‹‹ኢትዮጵያም ያለችው ልብ ውስጥ እንጂ! ወረቀት ላይ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነትህን ከልብ ህ እንዳይጠፋ ኢትዮጵያውያን ጓደኞችህን አጥብቀ ህ በመያዝ፤ ቤተክርስቲያን በመሄድ፤ በዓላትን በማ ክበር፤ ሀገር ቤት ዶላር በመላክ፤ ስልክ በመደወል ተንከባከበው እንጂ የወረቀት ላይ ስም ብቻ አታድ ርገው፡፡›› ጓደኛዬ ምክሬ ቢያስደስተውም አሁንም ጥቂት ቅ

ሬታ እንዳለሁ ከአነጋገሩ ገባኝ፡፡ ስለዚህ ማንገራገር አላቆም አለኝ፡፡ አሁን ደግሞ መድኃኒት ሳይሆን መርዝ ማሳሳቢያ ጨመርኩለት፡፡ ‹‹ከዚህ በላይ ያለህ ጭንቀት ምጽድ ቅ ይባላል! አሜሪካ ለመምጣት የተሳልከውን ስዕለ ት አታስታውስም፡፡ እዚህ የመጣኸው ለጽድቅ አይ መስለኝም፤ ለጥቅም እንጂ፡፡ ለጥቅም ከመጣህ ደግ ሞ፤ አሜሪካ የሚሰጠውን ጥቅም ሁሉ ማግኘት አለ ብህ፡፡ ግንጥል ጌጥ አያምርም፡፡ ዜጋ መሆን ጥቅም ስ ላለው መሰለኝ ለማመልከት ያመነታኸው! ለጥቅም የ መጣ ለጥቅም አያመነታም፡፡እንዲህ ስትል ሰው ቢሰ ማህ በሆዱ ምን እንደሚልህ ታውቃለህ? ግብዝ! ነ ው የሚልህ››፡፡ ደነገጠ! ሲደነግጥልኝ ጊዜ የስድብ ሞራሌ መጣ፡፡ ‹‹ይሄ የሀበሻ ጉራ ነው!፡፡ የውሸት አሳይለም ሲጠይ ቅ፤ የውሸት ሲያገባ እና ሲጋባ፤ የውሸት ፎርም ሲሞ ላ ይኖርና....እንደ ድመት አፉን እያበሰ…ምንም እንዳ ልሰራ፤ ሀገሩንም መክዳት የጀመረው ገና ኢትዮጵያ እ ያለ መሆኑን ረስቶ…ዜጋ ለመሆን ተጨነኩ ይላል፡፡›› ‹‹ስጋትህን አደንቃለሁ! ከመጠን በላይ ሲሆን ግን ግ ብዝነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆንከው በወረቀት ስላ ልሆነ! በወረቀት ኢትዮጵያዊነትህ አይፋቅም፡፡›› አል ኩ እና ተሰናበትኩት፡፡ የጓደኛዬ ፊቱ ነጭ ሆነ፡፡ እናም አሜሪካዊ ሆነ! በወረቀት ማለት ነው፡፡

ወላጆቻችን በአሜሪካ

ብዙ ወላጆች ሲያረጁ በልጆቻቸው ፈቃድ ላይ ይ ወድቃሉ፡፡ በተለይ ወላጆች አሜሪካ ሲመጡ፤ ል ጆች በወላጆቻቸው ላይ ያለው ስልጣን ገደብ የለ ሽ ነው፡፡ ይህንን ሥልጣናቸውን በቅጡ የሚጠቀ ሙበት እንዳሉ ሁሉ፤ ወላጆቻቸው ‹እምቢ› ለማለ ት እስካይችሉ ድረስ ወላጆቻቸውን የሚጫኑ ልጆ ችም አሉ፡፡ አንዳንዴ ወላጆች ተራ ነገርን እንኳን ለራሳቸው መወሰን እስካይችሉ ድረስ ሥልጣነ ቢ ስ ይሆናሉ፡፡ ጓደኛዬ አባቱን ከኢትዮጵያ ስላመጣ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ወደ ቤቱ ሄድኩኝ፡፡ አባቱን ኢትዮ ጵያ በደንብ አውቃቸው ስለነበረ አባቱን ለማግኘት ም ጓጉቼ ነበር፡፡ አባቱ ደስ የሚል፤ ግርማ ሞገስ ያ ለው፤ ነጭ የበዛበት ረዘም ያለ ጢም አላቸው፡፡ ለ እኔም ሆነ ኢትዮጵያ ለምናውቃቸው ሰዎች ያ ጢ ም መለያቸው ብቻ ሳይሆን ደስ የሚል ግርማ ሞገ ሳቸውም ነበር፡፡ ‹አሜሪካዊ› ልጃቸው ግን ካደረገላ ቸው የመጀመርያ እንክብካቤ አንዱ ጢማቸውን እ ንዲቆረጡ ማድረግ ነበር፡፡ ማለቴ እንዲላጩ፡፡ እኔ በሰው አባት ባያገባኝም..ሽማግሌ ሰላም ልል ሄጄ፤ ወጣት ለመምሰል የሚታገል ሰው አይቼ መመለሱ አላስደሰተኝም፡፡ የልጅ ሥልጣን መስመር የሳተ መ ሰለኝና ቅር አለኝ… በቅርቡ አንድ ጎረቤቴ ደግሞ እናቷን ልታመጣ ጉ ድ ጉድ እያለች ነው፡፡ ለእናቷ ልታደርግ ያሰበችው

ጥቂት ደግሞ ስለ አሜሪካውያን

የአሜሪካ አንደኛ ተሰማሩበት መስክ ‹‹የመጀመርያው ሰው›› መሆን ከባድ ቢመስልም በአ ሜሪካ ባሕል ግን ቀላል ሆኖ ነው ያ ገኘሁት፡፡ በአሜሪካ ሁሉ ነገር ‹‹የ መጀመርያ›› ባይሆንም የመጀመሪያ ነው፡፡ምሥ ጢሩ ሁሉንም ነገር በመስኩ ካለው ዝቅተኛው ሬከርድ ጋር ማነጻጸር ነውና፡፡ ይህንን በቀላሉ የምታስተውሉት የአየር ሁኔታ ሲዘገብ ነው፡፡ 1ኢንች በረዶ ቢዘንብ….በሳምን ቱ የመጀመሪያው ከፍተኛ በረዶ ተብሎ ይዘገባ ል፤ 10 ኢንች ቢዘንብ በወሩ የመጀመርያ ነው፤ 100 ኢንች በረዶ ቢዘንብም….በክፍለ ዘመኑ ‹የ መጀመርያው› ተብሎ ይዘገባል፡፡ሁሉም የመጀ መርያ ነው፡፡ ሩጫ ተወዳድሮ መጨረሻ ስለወጣ አሜሪካዊ ሯጭ ለመዘገብ መጀመርያ ‹አንደኛ› ወይም ‹የመ ጀመርያው› የሚሆንበት መንገድ ይፈለግለታል፡፡ ከጥቂት ምርመራ በኋላ ወይ በዕድሜው፤ ወይ በ ጾታው፤ ወይ በትምህርት ደረጃው፤ ወይ በመጣ በት ሀገር፤ ወይ መጨረሻ በወጣበት ሰዓት የመ ጀመሪያ ሰው እንደሆነ ሲረጋገጥ ‹‹በዚያ ሰዓት ለ መግባት የመጀመርያው የሰባ ዓመት ዓዛውንት እ ንደሆነ ይዘገባል››፡፡ በአሜሪካኛ የመጨረሻውም ሯጭ የመጀመሪያ ነው፡፡ እኔ እንዳስተዋልኩት ይሄ ባሕል ‹‹ብሔራዊ የአ ሜሪካ ሚዲያ አመል›› ነው ማለት ይቻላል፡፡ ም ክንያቱም የአሜሪካ ዜና ማሰራጫዎች የሚዘግቡ ትን ወሬ ‹‹አንደኛ›› ወይ ‹‹የመጀመርያ›› በሚል ቃል የማጀብ የቢዝነስ ሞዴላቸው አካል ነውና፡ ፡ ይህንን ‹መጀመርያ› የማድረግ አመል ያስተዋ ልኩት ባለፈው ግንቦት ወር ነበር፡፡ ዋናው የግን ቦት ዜናው ‹‹ወ/ሮ ኤለና ኬገን የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ተሾሙ›› የሚል ነበር፡፡ ዘ ጋቢው ግን ይህንን ደረጃ የሌለው ዜና ደረጃ ፈጥ ሮለት እንዲህ ብሎ ሲያቀርብ ሰማሁት ‹‹ወ/ሮ ኤ ሊና ኬገን የከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛዋ ሴት ዳኛ ለመሆን የመጀመርያዋ ሰው ናቸው››፡፡ አያ ችሁ አራተኛ ለመሆንም አንደኛ መሆን አለ፡፡ አሜሪካኖች ‹የመጀመርያነትን› በማጉላት የሚፈ ጥሩትን የመንፈስ ኩራት፤ እኛ ኢትዮጵያ ሳለን በ ተቃራኒ መንገድ እናገኘው እንደነበረ ሳስብ ይገር መኛል፡፡ እኛ ‹የመጨረሻነታችንን፤ ታናሽነታችን ን፤ ደካማነታችንን› በማጉላት ከፍተኛ የመንፈስ ኩራት እና የቀዳሚነት ስሜት ይሰማን ነበና፡፡ እ

ኛ በቤተክርስቲያን ትሕትና እንለዋለን ምንም እንኳ ን እነርሱ ‹አይናፋርነት ወይም low self esteem › ብለው ቢያስቡብንም፡፡ በእርግጥ በብዙ ነገር አንደኞች ናቸው፡፡ የእነርሱ ኢምፓየር ተረኛው የዓለም ታላቁ ኢምፓየር ነው ና፡፡ ቢሆንም ግን ለእኔ ‹የመጀመርያ ጉረኛ ሕዝብ ለማየት የመጀመሪያዎቼ›› ናቸው፡፡ ሕግ አክባሪው ‹‹ብጹዕ›› አለቃዬ አለቃዬ ሕግ አክባሪ አሜሪካዊ ነው፡፡ ሥራው ብ ቻ ሳይሆን ጸባዩም በሕግ አክባሪነት ላይ ነው የተመ ሰረተው፡፡ ከእኔ አንጻር ሳየው አለቃዬ ሕግ በሚባ ል ሶፍትዌር የሚንቀሳቀስ ማሽን ነው፡፡ ትሕትናው የሚከብድ አይነት ነው፡፡ ሥራ እንድሰራ ሲያዘኝ እ የተሸቆጠቆጠ ነው፡፡ የሕግ አከባበሩን ደረጃ አንድ ማስረጃ ልስጣችሁ፡ ፡ አለቃዬ ባለፈው ዓመት ለእኔ እና ለስራ ባልደረባ ዬ የገና ስጦታ ሰጠን፡፡ ልክ አለቃዬ ከቢሮአችን ሲ ወጣ በክሪስማስ ዲዛይን የተንቆጠቆጠ ፖስታውን ከፈት አድርጌ አየሁት፡፡ ውስጡ ያለው የ20ዶላር ነ በር፡፡ ለምን 20? ብዬ አሰብኩ፡፡ መልሱ ከሆነ ሕግ ጋር አንደሚገናኝ ግን ጠርጥሬ ነበር፡፡ በሳምንቱ መኪናዬ ውስጥ ሬዲዮ ሳዳምጥ አንድ የ ፌዴራል መስሪያቤት ባልደረባ ስለ ሥጦታ ሕጎች ሲያብራሩ ሰማሁት፡፡ 20 ዶላሬም እዛ ውስጥ ነበረ ች፡፡ ለካ በአሜሪካ ፌዴራል ሕግ መሰረት ቀጣሪ ለ ተቀጣሪ…ከ20 ዶላር በላይ ስጦታ መስጠት አይፈቀ ድለትም፡፡ ከ20 ብር በላይ የሆነ ሥጦታ እንደ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ ይታሰብበታል፡፡ አለያ ጉቦ ሊባል ይ ችላል፡፡ አላልኳችሁም! አለቃዬ ሕግ አክባሪ ነው፡፡ የፈረንጅ ውሸት ኤክስፔንሲቭ ነው… ትልቁ አለቃዬ እና ትንሹ አለቃዬ ሲመካከሩ ጥቂ ት ቆዩና ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች ም በኋላ ትንሹ አለቃዬ ወደ እኔ ቢሮ መጣና ‹‹ሃይ ኔያድ›› አለኝ፡፡ ‹‹ሃይ ..››አልኩኝ መልሼ፡፡ ጥቂት ስለ ዕለቱ ሥራችን፤ ጥቂት ስለ አየሩ ሁኔ ታ ካወራን በኋላ ትንሹ አለቃዬ ‹‹ዶክተሩ፤ ሦስተ ኛ ፎቅ ላይ ከላቦራቶሪው ጎን ያለውን ቢሮ አንተ እ ንድትገባበት ፈልጓል፡፡›› አለኝ፡፡ ከእኔ መልስ ሳይ ጠብቅ ቀጠለ ‹‹በእርግጥ ዞሮ ዞሮ ብዙ ስራህን የም ትሰራው እዚህኛው ቢሮ ስለሆነ ይሄንን ቢሮህን አ ትለቅም፤ ነገር ግን አልፎ አልፎ ላይኛው ላቦራቶ ሪ ለምትሰራው ሥራ አዲሱን ቢሮህን ትጠቀምበታ

አቀባበል ለእርሷ ደስ የሚል ቢሆንም ለእኔ ግን ‹አስ ቂኝ› ነበር፡፡ የእንክብካቤዋ መጀመሪያ የእናቷን ፀጉ ር አሳጥራ፤ ጥቁር ቀለም መቀባት ነው፡፡ እናትሽ ደ ስ ላይላቸው ይችላል እኮ አልኳት… ‹‹ምንም አትል ም›› አለችኝ፡፡ እናቷን ከእርሷ በላይ ባላውቅም፤ እ ሷ የደገሰችላቸውን የቁንጅና ኮተት በቀላሉ የሚቀበ ሉ አይመስለኝም፡፡ ቢሆንም ግን የልጅቷ ‹ሥልጣን› ግን ይገርማል፡፡ የልጅ ሥልጣን መስመር የለቀቀበትም ታሪክ አው ቃለሁ፡፡ ወላጆቹን በክብር ካመጣ በኋላ፤ ሰድቦ፤ አ ዋርዶ፤ ከቤት አስወጥቶ፤ በጎረቤት ብቸኛ እርዳታ ወደቤታቸው እና በክብር ወደኖሩባት ኢትዬጵያ ለ መመለስ የቻሉ ምስኪን ወላጆችንም አውቃለሁ፡፡ ሁሌ ባሰብኩት ቁጥር የሚያናድደኝ ታሪክ ስለሆነ ሳ ልጠቅሰው ማለፍ አልቻልኩም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የእኔ እናት አለች፡፡አሜሪካ ለ ሰጠኝ አዲስ ሥልጣን ገና እውቅና አልሰጠችም፡፡ ሥልጣኔን ለመጠቀም የሞከርኩት ‹‹ሁሌ ነጠላ ለም ን ትለብሻለሽ›› ብዬ ነው፡፡ የአሜሪካ ዊንተር በረዶ ቢዘንብም፤ እንደ ዛሬው ቀን ሙቀቱ ‹80› ቢደርስ ም፤ ነጠላ ወይ ረጅም ሻርፕ ሳታደርግ ከቤት መው ጣት አትፈልግም ‹‹በስተርጅና ራቁቴን አልሄድም›› ትላለች፡፡ በሙቀት ሻርፕ ስታደርጊኮ ሰው ይታዘ ብሻል ስላት..ባሕላችንን ስለማያውቁ ነው ትላለች… እኔ ፍላጎቷን እና እምነቷን መጋፋት ባልወደም የሰ መርን ሙቀት ግን እንዴት እንደምትገጥመው ለማ የት ጓጉቻለሁ፡፡

ምክር በእንግሊዝኛ ቁጣ በአማርኛ ለህ አለኝ፡፡›› ጥቂት ቆይቶ ግን የሆነ ነገርም ነገረኝ፡፡ ቆይ! የነገ ረኝ ምን እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡ በዚያው ሳምነት ውስጥ ቢሮዬን ተረከብኩ፡፡ ስ ሜ በሩ ላይ ተለጠፈ፡፡ ግድግዳው ምን ዓይነት ቀ ለም ይቀባልህ ተባልኩ፡፡ ‹‹አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀ ይ›› ሳልላቸው ቀድመው የቀለም መምረጫ ‹‹ሜ ኑ›› ሰጡኝ፡፡ ቶሎ ብዬ የሌሎቹ ቢሮዎች የተቀቡ በትን ቀለም ኮረጅኩ፡፡ ነጭ ነው፡፡ የቀለም ሜኑው ውስጥ ‹‹ነጭ›› የሚለውን ሳወ ጣ፤ የትኛው ዓይነት ነጭ የሚል ምርጫ ቀረበል ኝ፡፡ ‹‹ነጭም ዓይነት አለው አንዴ?›› አልኩ በሆ ዴ፡፡ ከዚያ በጣም ነጩ ‹‹ሥጋ ቤት›› እንዳይመስ ለኝ ለራሴ ሰግቼ ‹‹ኤግ ዋይት›› የሚል መረጥኩ፡ ፡ በኋላ ሲቀባ ሳየው ‹‹ቆሻሻ ዋይት›› መሆኑን አ ወቅሁ፡፡ ወለሉስ ምን ይሁንልህ፤ ቀለሙስ፤ ኮርነሩስ…ተ ባልኩ፡፡ በዳበሳ እና በአቦ ሰጡኝ መረጥኩላቸው፡ ፡ የፈረንጅ ነገር…ሁሉን ነገር ከምር ይቆጥራሉ…የ መረጥኩትን ስሙንም ቀለሙንም የማላውቀውን ‹‹ታይል›› ወለል አደረጉልኝ፡፡ ለብቻዬ ስልክ መስመር ገባልኝ፤ ተጨማሪ ኮም ፒውተር፤ መጽሐፍት መደርደሪያ ወዘተ..ተደገረል ኝ፡፡ በምርጫዬ ማለት ነው፡፡ ይሄን ሁሉ ሳሰራ እና ስሰራ ግን ፕሮፌሰሩ ለኔ ቢ ሮ ለመስጠት ያሰበበትን ምክንያት ያልሰማሁ መ ስሎታል፡፡ ትንሹ አለቃዬ ወሬውን መጀመርያው ኑ አሾልኮልኝ እንደነበር አያውቅም፡፡ዩኒቨርሲቲ ው የንብረት ቆጠራ ሲያካሂድ፤ ትርፍ ቢሮዎችን እና ከአቅም በታች ጥቅም ላይ የዋሉ ቢሮዎችን አ ብሮ ይገመግማል፡ ከዛም ቢሮ ለቸገረው ይሰጣቸ ዋል፡፡ ተጨማሪ ቢሮ የተለገሰኝም፤ ቢሮው እንዳ ይወሰድ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ሳለን፤ ባለሥልጣን መጣ ሲባል፤ ወይ ም በንብረት ቆጠራ ጊዜ የምናደርገው ሁሉ ትዝ አለኝ እና ‹‹ሰዎች ስንባል መሰረታዊ ጠባያችን አን ድ ነው! አገላለጹ ይለያያል እንጂ›› የሚል ድምዳ ሜ ላይ ደረስኩ፡፡ ቢሮውን ለማዳን ጥሩ ሰበብ ሆ ኜ ባገለግልም፤ ልጠቀምበት ግን አልቻልኩም፡፡ ለ ሁለት ቢሮ የሚበቃ ሥራ የለኝምና፡፡ እናም ግርግ ሩ ሲያልፍ፤ ስሜን ከበሩ ላይ ቀ…ስ…አንስቼ፤ አቀ ብለው ለተባልኩት ሌላ ጡረተኛ ፕሮፌሰር አቀበ ልኩት፡፡ አንዳንዴም ፈረንጅ ቤት እንዲህ ይደረጋ ል፡የፈረንጅ ውሸት ግን ኤክስፔንሲቭ ነው፡፡ ቢሮ ውን የእኔ ለማስመሰል የወጣውን ብር አስቡ፡፡

ልጆቼን ይዤ ልጆች ወደ ሚጫወቱበት ሜዳ ወ ጣሁ፡፡ አጋጣሚ በሰፈሬ የነበሩ ሀበሾችም ልጆቻ ቸውን ይዘው ሲያጫውቱ አገኘኋቸው፡፡ የፈረንጁ ም፤ የስፓኒሹም፤ የጥቁሩም ልጅ እንዲሁ በየመጫ ወቻው ላይ ይንጠላጠላል፡፡ የልጆች ጨዋታ መቼም መላ ቅጥ የለው አይደል! አንዱ የአበሻ ልጅ ከመሬት አፈር እየዘገነ የፈረንጁ ን ልጅ ያለብሰው ጀመር፡፡ የፈረንጁ ልጅ በሚወር ድበትን አፍሪካዊ ቦምብ ተደናግጦ እንደ ጨው ሀ ውልት ተገትሮ ቀረ! ቆራጡ አበሻ ግን ‹‹ጣሊያንን›› ያገኘ አርበኛ መስሎ አፈሩን መዛቅ እና መርጨት ብቻ ሳይሆን አንኳር አንኳሩን እያነሳ ፈረንጁ አናት ላይ ለማስቀመጥ ይንጠራራ ጀመር፡፡ የፈረንጁ ወ ላጆች አጋጣሚ የሚሆነውን አይመለከቱም ነበር፡፡ ሀበሻዋ እናት ግን ልጇን አይተዋለች፡፡ ፈረንጅ አ ገር ስለሆነች ግን እንደ ሀበሻ እናት ቁጣዋን በጩ ኸት አልገለጠችም፡፡ መጀመርያ በፈረንጅኛ ለመጥ ራት ሞከረች ‹No Honey! Come here!”፡፡ ቆራ ጡ ሀበሻ ወይ ፍንክች አለና ስራውን ቀጠለ፡፡ አን ድ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሀበሻ እናት ሌላ ቀ ጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች ‘አንተን እኮ ነው come here!”፡፡ ይሄኛው ትዕዛዝ ጉራማይሌ ቋንቋ ነው ስለሆነ ሀበሻውን ልጅ ጆሮ ደረሰ፡፡ ቢሆንም አየት አደርጓት ስራውን ቀጠለ፡፡ ለነገሩ! እኔም ብሆን እ ስካሁን ድረስ በእንግሊዝኛ “አንተን እኮ ነው!” ማ ለት አልችልም፡፡ ያም ሆነ ይህ ቆራጡ አርበኛ ህጻ ን የአፈር ቦንቡን መበተን ጀመረ፡፡ ነገሩ በተጀመ ረ በሶስተኛው ሰከንድ እናት ሦስተኛውን እና ፓ ስ ወርድ ያለበትን ትዕዛዝ ከመቀመጫዋ ብድግ በ ማለት እንዲህ ስትል አሰማች ‹‹አንተ ሰላቢ! በጥፊ እንዳልልህ!››፡፡ ሶስተኛው ትዕዛዝ ሀበሻውን ልጅ ሶኬቱ እንደተነ ቀለበት ሮቦት ድርቅ አደረገው፡፡ ትዕዛዙ በትክክል ሊገባው እንደማይችል እርግጠኛ ብሆንም መልዕክ ቱ ግን ደርሶታል፡፡ ትዕዛዙ ጆሮውን የሚከፍት ፓ ስወርድ ይዞ ነበር እና፡፡ ስገምተው ፓስወርዱ ‹‹በ ጥፊ›› የሚለው ቃል መሰለኝ፡፡ ከሀበሻው ልጅ ተንኮል ይልቅ የገረመኝ የእናትዬ ዋ ቋንቀቋዎች ናቸው፡፡ ከዚያ በላይ ግን የአሜሪካ ን ልጅ መምከር በእንግሊዝኛ፤ መቆጣት ግን በአ ማርኛ ቢሆን እንደሚመረጥ ተማርኩ፡፡ ይህ ጹሁፍ ከናኦድ ቤተሥላሴ ጡመራ ናኦድ ላይቭ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ በ+256-778-693669 ይደውሉልን


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

የዐሥር ዓመቱ አዳጊ እንዲህ ዘወትር እሁድ ኳስ ይዞ ሜዳ መውረድ የ ተጀመረውም ያኔ ነበር። ያኔ በቁጥር አነስተኛ የነበ ሩት ኢትዮጵያውያን በሚገናኙባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ከአፋቸው ከማይነጥሏቸው ወሬዎች መካከል አንዱ እግር ኳስ ነበር፡፡ ስለ አገር ቤትም ኾነ ስለ ው ጭ አገር ቡድኖች ወቅታዊ ውጤቶች እና አቋሞች እያነሱ ከመጨዋወት እና እሰጥ አገባ ከማለት ባሻገ ር ኢትዮጵያ እያሉ በግል ያዘወትሩት ስለነበረው የእ

ከኳሱ ባሻገር

መጫወቻ ምቹ የኾነ ሜዳ እንዳለው እነ አቶ ካሣ ይመለከታሉ። የክለቡን ሐላፊዎች አስፈቅደው የኢ ትዮጵያውያን ጤና ክለብ አባላት እየተገናኙ በቪላ ሜዳ መጫወት ጀመሩ፡፡

ማሕበራዊ ጤና

የጤና ቡድኑ በአነስተኛ ግጥሚያዎችም ኾነ በወዳጅነት ጨዋታዎች አብዛኛውን ጊዜ ድል አይለየውም

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

የካምፓላ መንገዶች ጭር ብለዋል። ቀኑ ዕለተ ሰን በት እንደመኾኑ አብዛኛው የከተማው ማርፈጃውን ከቤቱ እንኳን አልወጣም። ጥቂት ሰዎች በእጃቸው ያንጠለጠሉትን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዙ ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው ያዘግማሉ። በካባላጋላ አቅራቢያ የሚገኘው እና ኪቡሊ ተብ ሎ በሚጠራው የሙስሊሞች አካዳሚ የነበረው ት ዕይንት ግን ለየት ያለ ነው። በትምህርት ቤቱ ውስ ጥ ያለው አቧራማ ሜዳ በስፖርተኞች ተሞልቷል። እዚህም እዚያም ኳስ የሚጫወቱ ሰዎች ይታያሉ። ሰዓቱ ወደ ሦስት ሰዓት ተኩል ግድም ሲጠጋ በቡድን ተከፋፍለው ሜዳው ላይ ሲጫወ ቱ የነበሩ አዳጊዎች ገለል ተደርገው ቦታው ለሁለት ቡድኖች ተለቀቀ። በአንደኛው ወገን ቢጫ ማልያ የለበሱ ዩጋንዳውያ ን ተደረድረዋል። ሁሉም “ሪም ዲስትሪቢዩተር” በ ተባለ የፔፕሲ ኮላ ምርቶች አከፋፋይ ድርጅት ውስ ጥ የሚሠሩ ናቸው። በሌላኛው ወገን ያሉት ደግሞ ቅይጥ ናቸው። ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ዩጋንዳውያን “የኢትዮጵያ የጤና ስፖርት ክለብ” በ ሚል ስያሜ በሚጠራው የእግር ኳስ ክለብ ውስጥ ተሰባስበዋል። ብዙዎቹ ለልምምድ ስሪቱ የተለያ የ ባለ ሰማያዊ ቀለም ማልያ ለብሰዋል። ዕድሜያቸ ው እና አቋማቸውም እንደ መለያ ሹራባቸው የተ ዥጎረገረ ነው። በሰውነት የገረጀፉ፣ ለመንቀሳቀስ የ ሚቸገሩ የሚመስሉ እና በዕድሜ የገፉ እንዳሉ ሁ ሉ፤ ኻያዎቹ ውስጥ እንኳ ያልደረሱ፣ ሮጠው ያል ጠገቡም አሉበት። ጨዋታው ተጀመረ። ሐበሾች የተሰባሰቡበት የጤ ና ቡድን በተቃራኒው ቡድን ላይ ጫናው አይሏል። የዐሥራ ሰባት ዓመቱ ኤርትራዊ ኢሳያስ ዮሐንስ ጥ ሩ ጥሩ ኳሶችን ይሞክራል። እምብዛም ሳይቆይ ከ ሙከራዎቹ መካከል ሁለቱ ኳሶች ወደ ጎል ተቀየሩ። ልጁ ከርቀት አክርሮ የሚመታቸው ኳሶች ለግብ ጠ ባቂዎቹ አስቸጋሪ ናቸው። የሐበሾቹ ቡድን አሁንም ማጥቃቱን ቀጥሏል። ዕረፍት መድረሱን የሚያበስረ ው ፊሽካ ከመነፋቱ በፊት የጤና ቡድኑ በተቃራኒ ው ቡድን ላይ ሁለት ተጨማሪ ጎሎች አስቆጠረ። የተዳከመ ይመስል የነበረው የዩጋንዳውያኑ ቡድ ን በርካታ ተሳላፊዎችን ከከቀየረ በኋላ ነፍስ ዘራ። ሦስት ተከታታይ ጎሎችን በኢትዮጵያውያኑ መረብ ላይ አሳርፎ ድሉን ለመቀማት የተዘጋጀ መሰለ። ጸ ሐይቱ እየከረረች መጥታለች። የጤና ቡድን አባላ ት ሙቀት ያስገራቸው ይመስላሉ። ነገር ግን ወደ ጎ ል እየተጠጉ ማጥቃታቸውን አላቆሙም። ሁለት ተ ጨማሪ ጎሎችን አከሉ። ጨዋታውንም አምስት ለ ሦስት በኾነ ውጤት አጠናቀቁ። በእንዲህ ያሉ አነ ስተኛ ግጥሚያዎችም ኾነ በሌሎች የወዳጅነት ጨ ዋታዎች ቡድኑ አብዛኛውን ጊዜ ድል የማይለየው እንደኾነ የጤና ቡድኑ መሥራች አቶ ካሣ መንግስ ተአብ ይናገራሉ። ከፓኪስታን እና ከሶማልያ ማሕብረሰብ የእግር ኳ ስ ቡድኖች ጋራ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በምሳሌ ነት የሚጠቅሱት አቶ ካሣ ከአንዱ በስተቀር በሁሉ ም ጨዋታዎች ማሸነፋቸውን በኩራት ይገልጻሉ፡፡ “አንዱንም ቢኾን ተጋጣሚያችን የነበረው የሶማል ያ ማሕበረሰብ ሁልጊዜ እያሸነፍነው ሲቸገር ከናይ ሮቢ ፕሮፌሽል ተጫዋች አምጥቶ በማስገባት ነው ያሸነፈን”ይላሉ፡፡ ያም ቢኾን ግን በአንድ ጎል ልዩነ ት ብቻ የተጠናቀቀ ስለነበር “እንደሽንፈት አይቆጠ ርም” ባይ ናቸው። እርሳቸው ቡድኑን እንዲህ ይመ ልከቱት እንጂ ለ“ሪም ዲስትሪዩቢተር” ቡድን ተቀያ ሪ ተሰላፊ የነበረው የሰላሳ ዓመቱ ዩጋንዳዊ ሙሳጃ ያሲን ግን የኢትዮጵያውያኑን ቡድን “ደህና” የሚባ ል ነው ሲል ይገልጸዋል። የአጥቂውን ክፍል እያደነቀ የሚያወራው ሙሳጃ ተከላካዮቹ ጋራ ሲደርስ ግን ሳቅ ይቀድመዋል። ሙ ሳጃ ያልተረዳው ነገር በግንቦት 28ቱ ጨዋታ ወደ ሜዳ የገባው የጤና ቡድን አብዛኞቹ ቋሚ ተሰላፊ ዎቹን አለማካተቱን ነው። ብዙዎቹ ቋሚ ተሰላፊዎ ች ከሁለት ቀን በፊት የኤርትራን የነጻነት በዐል ምክ ንያት በማድረግ በተካሄደው ጨዋታ ላይ በመሳተ ፋቸው ወደ ሜዳ ብቅ አላሉም። የመጡትም ቢኾ ኑ ወደ ሜዳ ለመግባት የሚያስችል ጉልበት አልነበ ራቸውም። በዕለቱ የነበረው ተሳትፎ እና ጨዋታ ከ ወትሮው ቀዝቀዝ ይበል እንጂ ቡድኑ የተቋቋመበት ን ዓላማ ያሳካ ነበር- “ኢትዮጵያውያንን እያሰባሰቡ እሁድ እሁድ ኳስ መጫወት።”

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

የጤና ቡድኑ መስራች አቶ ካሣ መንግስተአብ በጤና ምክንያት እግር ኳስ ጨዋታ ካቆሙ ሶስት ዓመት ተኩል ቢያልፋቸውም ወደ ሜዳ ብቅ ማለትን ግን አልተዉም

ኢሳያስ ዩሐንስ (ከግራ ወደ ቀኝ ሶስተኛው) እና ሌሎች አዳጊዎች የጤና ቡድኑ የወደፊት ተስፋዎች ናቸው

ፎቶ- ካሣ መንግስተአብ

በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

5

የጤና ቡድኑ ሲመሰረት ከነበሩት አባላት አብዛኛዎቹ ወደ አሜሪካ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ ተጉዘዋል

ግር ኳስ ጨዋታ እየተረኩ በትዝታ መቆዘምንም እ ንደ ልማድ አድርገውታል። ከቁዘማ ወጥተው ዳግ ም እግራቸው ከኳስ ጋራ እንዲገናኙ የሚያስችለው ን ሐሳብ አቶ ካሣ አቀረቡት። “አስታውሳለሁ ቀኑ ቅዳሜ ነበር፡፡ ያን ቀን የተለመ ደው ወሬ ሲነሳ ለምን እንዲህ ተቀምጠን ከምናወራ ነገ ጠዋት ተገናኝተን ኳስ እንጫወትም? ሁሉም ሸ ራ ጫማውን ይዞ ይምጣ። ኳሱን መረቡን እና የመ ሳሰሉትን እኔ አመጣለሁ አልኩኝ” ይላሉ አቶ ካሣ ወደ ሁዋላ ተመልሰው ሐሳቡ የተጸነሰበትን ኹኔታ ሲያስረዱ። ሐሳቡን የተቀበሉት ትጥቃቸውን አሟ ልተው ሜዳ ተገኙ። ከእነዚህ ጥቂት ሰዎች መካከል አሁን የሄንከን ዋና አከፋፋይ የኾኑት አቶ ክፍሌ ደ ገፉ ይገኙበታል። የመጀመሪያው ጨዋታም ያለምን ም የቅድሚያ ልምምድ ተደረገ፡፡ ለረጅም ሰዓት በ ሞራል ሲጫወቱ ያረፈዱት ተጫዋቾች ከፍጻሜው በኋላ መራመድ እንኳ አቃታቸው። “ማን ይንቀሳሰቀስ፤ ሁላችንም ‘ስትራፖ’ በ’ስትራ ፖ’ ኾንን፡፡ በዚያ ላይ የአንዳንዶቻችን ዕድሜም ገ ፍቷል፡፡ ሁላችንም የማንደባበቀው ነገር ደግሞ አ ንዳንድ ሱሶችም አሉብን፡፡ እናም እነርሱን ከ‘ስት ራፖው’ ለማስወጣት ሳውና፣ ማሳጅ ማስደረግ እየ

ተባለ ሌላ ወጪ… መከራችንን ስናይ ሰነበትን” ይላ ሉ አቶ ካሣ ጅማሬውን በፈገግታ ታጅበው እያስ ታወሱ፡፡ ተጨዋቾቹ በመጀመሪያው ዕለት ያጋጠማቸውን የሰውነት መሳሳብ እና ድካም በቀጣዩ እሁድ ከሜዳ እንዳይገኙ አላደረጋቸውም። እሁድን እየጠበቁ በየ ሳምንቱ ከሜዳ መገኘት ቀጠሉ። ከእግር ኳስ ጨዋ ታው ባሻገር ያለው ብሽሽቅ፣ ተረብ እና መተሳሰብ እሁድን ተናፋቂ ቀን እንዲኾን አደረገው። ኳሱ ሜ ዳ ላይ ቢያልቅም ጨዋታው ግን ምሳ በጋራ እየተበ ላም ይቀጥላል። በኳስ የደከመ ሰውነትን አሳርፎ ሻ ይ ቡና እየተባለም አይቋረጥም። ስፖርታዊ ወንድ ማማችነቱ የፈጠረው ቁርኝት ሁለት ወራትን ተሻገ ረ። የኑሮ አቅማቸው እምብዛም የማያወላዳ ስደተኞ ችን በአብዛኛው ያካተተው ይህ ስብስብ ከኳስ ጨ ዋታ በኋላ ለ“ላብ መተኪያ” የሚያስፈልገውን ገንዘ ብ ማሟላት እየከበደው መጣ። በዚህ ወቅት ነው አ ቶ ካሣ ሌሎችን ማማከር እንዳለባቸው የወሰኑት። አቶ ንጉሴ ባልቻ፣ አቶ ዘላለም ሀብታሙ፣ አቶ ተ ካልኝ (በቅጽል ስማቸው ሻፍት) ይጠሩና ወደ ቡድ ኑ እንዲቀላቀሉ ይጋብዟቸዋል። አቶ ክፍሌም ከተጋ ባዦቹ መካከል ነበሩ። ሐሳቡ የቀረበላቸው ግለሰቦ

ች ምንም እንኳን የአቶ ካሣን ሐሳብ ቢወዱትም ዝ ም ብለው ሊቀበሉት ግን አልፈቀዱም፡፡ ይልቁንም በቅድመ ኹኔታ ሊያዙ እና ሊታዩ ይገባቸዋል ያሏቸ ውን ሐሳቦች አስቀመጡ፡፡ “ስፖርተኞች ኾነን ስላደግን [ቡድኑን] መቀላቀል እንፈልጋለን። በቴክኒክም ኾነ በገንዘብ ለመርዳት እ ንችላለን። ግን ስደተኛ እየበዛ ከመምጣቱ የተነሳ ‘የ ታባህ’፣ ‘የታባሽ’ መባባል አንፈልግም። ክብራችን እ ና የቤተሰባችንን ክብር መጠበቅ እንፈልጋለን አሉ ኝ” ይላሉ አቶ ካሣ የግለሰቦቹን ቅድመ ኹኔታ መ ለስ ብለው ሲያስታውሱ። አቶ ካሣ የቡድኑን አባ ላት ማማከር ሳያስፈልጋቸው “ሙሉ ሐላፊነት” ለ መውሰድ ይስማማሉ። በስተኋላ የቡድኑ ቁልፍ ሰ ዎች የኾኑት እነዚህ ስፖርት ወዳድ ግለሰቦች በቀ ጣዩ እሁድ ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው ሳምቢያ ሜ ዳ ተገኙ፡፡ ሳምቢያ የሚገኘው ሜዳ የጤና ስፖርት ቡድኑ ጨ ዋታ አሃዱ ተብሎ የጀመረበት ቢኾንም አፈር ይበዛ ው ስለነበር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መለወጡ ግድ ነበ ር። ሌላ ቦታ መፈለግ ተጀመረ። በአህጉራዊ ውድድ ሮች አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክለቦች ጋራ በተደጋጋሚ የተጫወተው “ቪላ” ሳር ያለው እና ለ

ነገሮች ሁሉ መሥመር የያዘለት የጤና ቡድን እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም ከዩጋንዳ መንግሥት ሕጋዊ እ ውቅና አገኘ። ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀረ፤ ሊቀመንበር ሾ መ። የራሱን ጠበቃም ቀጠረ። የጤና ቡድኑ ስኬት በርካቶችን ሳበ። የተጨዋቾቹ ቁጥርም ሦስት እና አ ራት ቡድን መመሥረት የሚያስችለው ደረጃ ድረስ አደገ። “የኢትዮጵያውያን ጤና ስፖርት ክለብ በካ ምፓላ ስሙ ገነነ። በጣም ብዙ ወጣቶች መምጣት ጀመሩ:፡ ቁጥሩ ከአቅም በላይ ኾነ” ይላሉ የአሁ የክ ለቡ ሊቀመንበር አቶ ንጉሴ ባልቻ። የአባላቱ ቁጥር መጨመር በቡድኑ ውስጥ የነበረ ውን የአንድነት መንፈስ ይበልጥ እያጠነከረው መ ጣ። በግል ጉዳይ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት በጠበኝነት የቆዩ ያለማንም ሽምግልና ሜዳው አስታ ራቂ ኾኗቸው በመካከላቸው ጥል ቀርቶ ሰላም ሰፈ ነ፡፡ አንዳንዴ ከከተማ ወጣ እያሉ ኳስ መጫወት እ ና መዝናናትም ታከለበት። ከአባላት መካከል ተሳክ ቶለት ወደ ሌላ አገር የሚሄድ አባል ሲኖር ውሃ ዳር (ቢች) ተወርዶ፣ በግ ታርዶ እና ስጦታ አዘጋጅቶ መ ሸኘት ባህል እየኾነ መጣ። “ካልተሳሳትኩ ከእኛ ጋር ሲጫወቱ የነበሩ 100 ያህ ል ስደተኞችን ወደተለያየ አገር ሸኝተናል፡፡ አቅም ያ ላቸውን ድግስ ደግሰን ስጦታዎችን አበርክተን፣ አቅ ም የሌላቸውን ደግሞ ለትራንስፖርት እና መሰል ነ ገሮች ከቡድኑ አባላት ድጋፍ በማድረግ ሸኝተናል” ይላሉ አቶ ካሣ። በጤና ቡድኑ አባላት ዘንድ የነበረው የእርስ በር ስ መተሳሰብ እና መረዳዳት ትሩፋቱ ወደ ሌሎችም ተሻገረ። ለቤተክርስቲያን እገዛ ሲያስፈልግ በበገንዘብም ኾነ በጉልበት መርዳት፤ የተቸገሩትን በአቅም ማገዝ፤ የ ሞቱትን መቅበር፤ አስክሬናቸውን ወደ አገር ቤት የ ሚሄደውንም ከቤተሰባቸው ጋራ በመካከር መላክ የጤና ቡድኑ ተጓዳኝ ሥራዎች ኾኑ። በዚያ ላይ በየ ጊዜው ቁጥሩ የሚጨምረውን ስደተኛ ተቀብሎ ማ ስተናገድም አለ። ጤና ቡድኑ ከተነሳበት ዓላማ ባሻ ገር ብዙ ሥራዎችን በማከናወን መጠመዱን ያዩ አባ ላት መፍትሄ አፈላለጉ። “የሰው ቁጥር ሲጨምር ማሕበራዊ ችግሮችም በ ጣም እየጎሉ ሲመጡብን ጊዜ ‘ምን እናድርግ?’ አል ን” ይላሉ አቶ ንጉሴ። ይህ ጥያቄ አቅም ያላቸውን የተወሰኑ ኢትዮጵያንን ጠርቶ የማማከር መፍትሄን ወለደ። እናም ስብሰባው ተጠራ። በስብሰባው ላይ የተገኙ እና የማሕበራዊ ችግሮቹን አሳሳቢነት የተረ ዱት ተሰብሳቢዎች በአንድ ድምፅ የኢትዮጵያ ማሕ በረሰብ ራሱን ችሎ መመሥረት እንዳለበት ይወስና ሉ። ይህ ስብሰባ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2005 ዓ.ም ለተመ ሠረተው በዩጋንዳ የኢትዮጵያውያን ማሕብረሰብ የ መሠረት ድንጋይ የጣለ፣ ለጤና ቡድኑ ደግሞ ሸክ ሙን ያቀለለት ነበር። ማሕበራዊ ጉዳዮችን ለማሕበረሰቡ ያስረከበው የ ጤና ቡድኑ የተነሳበትን ዓላማ ወደማስፈጸም አዘነ በለ። “ቡድኑ ኳሱ ላይ ትኩረት አደረገ። የወጣቶ ቹ እና ታዳጊዎቹ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እነ ርሱን ማሰባሰቡ ላይ በጣም ትኩረት ሰጠንበት” ይ ላሉ አቶ ንጉሴ።

ከኳስ በላይ…ኳስ ተሰባስቦ መጫወት እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መታ የት እንደሌለበት የሚናገሩት አቶ ንጉሴ ጨዋታው “የላቀ አስተዋጽኦ” ያበረክታል ባይ ናቸው። “ባህላ ችን ጠንካራ ነው። ነገር ግን የእርስ በርስ ግንኙነታ ችን ደካማ ነው። ጤና ቡድን ማለት መገናኛ ማለት ነው። በኳሱ ሰበብ ተገናኝተን፣ ተጫውተን ግንኙነ ት መፍጠር ነው” ይላሉ። የተለያየ አመለካከት ይዞ ወደዚህ አገር የሚመጣ ው ሰው ከመከፋፈል እና ለብቻ ከመቆም ይልቅ በ እግር ኳስ አማካኝነት እንዲሰባሰብ ይደረጋል ሲሉ ያብራራሉ። “ኳስ ራሱ ፍቅር ነው። ሁሉንም በአንድ ያሰባስባ ል” ይላሉ አቶ ንጉሴ። የዚህን አባባላቸውን እውነተ ኛነት ለማረጋገጥ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። ራሳቸ ው የሚመሩት ቡድን የዜግነት ስብጥር አንዱ ምስክ ር ነው። በጤና ቡድኑ ውስጥ የኤርትራ፤ ኡጋንዳ፤ ሩዋንዳ እና ኮንጎ ተጨዋቾች እንደተካተቱበት ከቡ ድኑ ሰባት የሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ የኾኑት አቶ ካሣ ያስረዳሉ፡፡ በቁጥር ግን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ያመዝናሉ። “ድሮም ጀምሮ ይኼ ኤርትራዊ ይኼ ኢትዮጵያዊ የሚባል ነገር የለም። ያንን ነገር አታስታውሰውም” ይላሉ አቶ ካሣ ከቡድኑ ታሪክ እያጣቀሱ። የወቅቱ የቡድኑ ሊቀመንበር አቶ ንጉሴም “ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚባል ነገር የለም። እከሌ እንደ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል


6

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

ማኅደረ ጊላይ የለጋነት ዕ ድሜ እንዲሁ እንደ ዐይ ን ጥቅሻ እያለፈ ነው። ወ ደ ኋላ ተመልሶ ሲያስብ ደ ስ የሚል ነገር ትዝ አይለ ውም።ሕይወት ልክ ከማ ለዳ ጣፋጭ እንቅልፍ እንደሚያባንኑት አ ስፈሪ የልጅነት የተረት ጭራቆች የተሞላች ትመስለዋለች:: ተረት የሚመስሉ ታሪኮች ን እየኖረ፣ እየሰማ እና እየታዘበ እዚህ ደር ሷል። መባረር፣ ስደት፣ ሞት… እና በትዝ ታ መዋትት በሕይወቱ ውስጥ እስካሁንም ይገለባበጣሉ።

የናይሮቢ እምብርት ሰሞኑን ከናይሮቢ 500 ኪሎ ሜትር ርቀ ት ላይ ከሚገኘው የካኩማ ስደተኞች ካም ፕ ወደ ኬኒያ መናገሻ ከተማ ብቅ ብሏል። ለእርሱ ጉዞ አዲስ አይደለም፤ ስንቱን ተጉ ዟል። ገና የዐሥራዎቹን አጋማሽ በቅጡ ሳ ይደፍን ከተወለደባት እና አፈር ፈጭቶ ካ ደገባት አዲስ አበባ እስከ አሥመራ ያለው ን 1176 ኪሎ ሜትር አይረሴ ጉዞ አድርጓ ል። ጉዞው ግን እንደዚህኛው በፍቃዱ የተ ደረገ አልነበረም። ያልተጠበቀ እና በስሜ ት ምስቅልቅል የተሞላ ነበር። ደም አፋሳ ሹ እና ትርጉም የለሹ የኢትዮ-ኤርትራ ጦ ርነት ሲነሳ ከኢትዮጵያ ተባርሮ አሥመራ ገ ባ። ከአባቱ ጋር። ትውልደ “ኤርትራዊ” በመኾናቸው ምክ ንያት የመባረር ዕጣ እንደገጠማቸው የስ ሚ ስሚ ቢሰማም ለጋ ዕድሜው ከአባቱ ጋራ የተባረረበትን ምክንያት በቅጡ እንዳ ይረዳው አድርጎት ነበር። “እኔ በወቅቱ እን ኳን በሩቅ የማውቃትን ኤርትራን ቀርቶ ተ ወልጄ ያደግኩባት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ም ን እንደሚመስል የማሰላስልበት ብስለት ላ ይ አልደረስኩም። ከትልቁ የዜግነት ጉዳይ ይልቅ የሠፈር ልጅነት ለእኔ ትርጉም ነበረ ው” ሲል ወደ ኋላ ተመልሶ ያስታውሳል። “‘የጨርቆስ ልጅ’ መባል ያኮራ ነበር” ይላ ል ማኅደረ የልጅነት ጣፋጭ ጊዜውን ያሳ ለፈበትን ሰፈር እያሰበ። “የጨርቆስ ልጅ ነቴን የምገልጸውን ያህል እንኳ ዜግነት የ ሚባለው ነገር ሳይገባኝ ነው አሻግረው “አ ባ ሻውል”(አስመራ ውስጥ የሚገኝ ሠፈር) የወረወሩኝ።” ለማኅደረ የአዲስ አበባው ጨርቆስ እና የ አሥመራው አባ ሻውል የሚመሳሰሉበት ነ ገር እንዳላቸው ታይቶታል። ሁለቱ ሰፈሮ ች ስማቸው ከድህነት ጋራ ተያይዞ ይጠራ ል። አባ ሻውል በምርጥ ፕላኗ በማትታማ ው አሥመራ ላይ ያለ ቢኾንም እንደ ጨር ቆስ እና መሰል የአዲስ አበባ ሰፈሮች “የድ ኻ » የሚባል መንደር ነው። ገዛ መንዳ ሐ በሻ ከአባ ሻውል ጋራ የሚጠቀስ ሰፈር ነ ው-በአስመራ። ልክ እንደ አዲስ አበባዎቹ የአራት ኪሎን አሮጌ ቄራ እና የፒያሳው ሠ ራተኛ ሠፈር አይነት። ማኅደረ አባ ሻውልን ለመልመድ አልተቸ ገረም። ድህነቱም፣ የ”አራዳ” ልጅነቱም ረ ድቶታል። ግን አንድ ነገር ሙሉ በሙሉ የ አባ ሻውል ልጅ እንዳይኾን ልጓሙን ይይ ዝበታል። አዲሶቹ ጓደኞቹም እንደ አንዱ የሠፈራቸው ልጅ እንጂ የማንነታቸው አካ ል አድርገው ለመቁጠር አልፈቀዱም። “ለ እነርሱ ኤርትራዊ አይደለሁም፤ ኢትዮጵያ ዊም አይደለሁም” ይላል። “ለእነርሱ ማኅ ደረ “አምቼ” ነው። ብዙዎች የሚጠሩት ም “አምቼው” እያሉ ነው።

“አምቼ”…? የምን አምቼ? “ይኼን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁ ት አባ ሻውል ላይ ነው” አለ ማኅደረ “ስለ አምቼነቱ” የሰማበትን ቀን እያስታወሰ።“አ ንዱ ጓደኛዬ በጨዋታ ላይ እንዲህ አለኝ። “ኻብ ሠፈርካ ዕንታይ ከምዝብልካ ትፈል ጥ ዶ?” (ምን እንደምታባል ታውቃለህ?) እኔ አዲስ መጤ ምን ሊሉኝ ይችላሉ በሚ ል ግርምት “አይፈልጥን” ብዬ መለሰኩለ ት። ያን ጊዜ “አምቼ” መኾኔን ነገረኝ።” የ ጓደኛውን ገለጻ ተከትሎ ማኅደረ ከሌሎች ኤርትራውያን “የተለየ ዜጋ” መኾኑ ይሰማ ው ጀመር። ማኅደረ አይወቀው እንጂ “አ ምቼ” የሚለው ስያሜ እርሱ አዲስ አበባ እ ያለ አገልግሎት ላይ ውሎ ነበር።

ቢኒያም ፍስሐ... ጁባ የሚኖረው የ40 ዓመቱ ቢኒያም ፍ ስሐ ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ጋራ የኖረ ው አዲስ አባባ 22 ማዞሪያ አካባቢ ነው።

ቢኒያም “አምቼ” የሚለውን መጠሪያ በደ ርግ ጊዜ አዲስ አበባ እያለ መስማቱን ይና ገራል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ለተወለደ ኤር ትራዊ የተሰጠ መጠሪያ ነበር። ቃሉ የሚገ ልጸው ኢትዮጵያ ውስጥ መገጣጠሙን ነ ው” ይላል። መጠሪያው በአንድ ወገን ኤ ርትራዊ ከኾኑ ወይም ከሁለት ኤርትራው ያን ወላጆች ለተወለዱ ዜጎች የሚውል ነ ው። ስሙ የተወሰደው አዲስ አበባ ከሚገ ኘው እና በኢትዮጵያ መንግሥት እና በጣ ሊያኑ የመኪና አምራች ድርጅት ፊያት መ ካከል በተደረገው ስምምነት ከተቋቋመው “አምቼ”(AMCE) ኩባንያ ነው። የመኪና ው አካላቶች ጣሊያን ተመርተው ኢትዮጵ ያ ውስጥ እንደሚገጣጠሙ ሁሉ “አምቼዎ ች” ኢትዮጵያ ውስጥ “የተገጣጠሙ” የሚ ል ትርጓሜ ይሰጣል። አምቼነት ከኤርትራ ጋራ ብቻ አይቆራኝ ም። ከኢትዮጵያ በተለይም ከአዲስ አበባ ጋራ ባለው ጥልቅ ትሥሥርም ይገለጻል። አሥመራ ላይ “አምቼዎች” በነገረ ሥራቸ ው ተለይተው ይታወቃሉ። “ብዙ ኤርት ራውያን አማርኛ ቋንቋን የሚናገረው አማ ራ ብቻ ይመስላቸው ነበር። ከ1990 ዓ.ም በኋላ ብዛት ያላቸው አምቼዎች ከኢትዮጵ ያ ተባርረው አሥመራን አጥለቀለቋት” ይላ ል ቢኒያም። ከዚያ በኋላ አምቼዎችን አሥ መራ ውስጥ ለመለየት ቀላል ነበር። አማር ኛ የሚናገሩ፣ በአረማመዳቸው፣ በአለባበ ሳቸው፣ በአንጻራዊ መልኩ በተላበሱት ግ ላዊ ነጻነት ይታወቃሉ። የአማርኛ ሙዚቃ በአሥመራ እንግዳ በኾነ መልኩ በስፋት የ ሚያዳምጡትም አምቼዎች ነበሩ። “አምቼ” መባል የመገለል ስሜት የሚፈ ጥርባቸው እንዳሉ ሁሉ ብዙዎች እንደማ ንነታቸው መገለጫ ይጠቀሙበታል። እን ዲያውም የኩራት ምንጭ አርገው የሚወስ ዱትም አሉ። ኢየሩሳሌም ኀይሌ የከፈተች ው “አምቼነቴን እወደዋለሁ” የሚለው አ ምቼዎች እየተገናኙ የሚጨዋወቱበት የፌ ስቡክ ገጽ በየቀኑ አባላቱን እያበዛ ነው። በ መላው ዓለም የተበተኑ አምቼዎች እየተገ ናኙ ስለገጠማቸው እና ስለኾነባቸው ነገር ሁሉ የሚወያዩበት ገጽ ነው። “አምቼ”ዎች በቁጥር ምን ያህል እንደኾኑ የተጨበጠ ወይም በጥናት የተደገፈ ማስ ረጃ ባይኖርም በስያሜው የሚጠሩ አንዳ ንዶች ግን “አምቼ”ን እንደ የኤርትራ 10ኛ ው ብሔር አድርገው ይቆጠሩታል። የ“አ ምቼ”ዎች ትክክለኛ አኀዝ ባይታወቅም ከ ጦርነቱ በኋላ ከኢትዮጵያ የተባረሩ ኤርት ራውያኖች ቁጥር 75ሺሕ እንደሚደርስ ኦ ፌሲሊያዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ማነው የተባረረው? ይፋዊ መረጃዎች በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነ ት ወቅት የተባረሩ ትውልደ ኤርትራውያ ን መካከል አብዛኛዎቹ ረዥሙን የሕይወ ት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ የተወለዱ እና ያሳለፉ ናቸው። በ1990 ዓ.ም ወደ ኤርት ራ በመጀመሪያ ዙር በተባረሩ ላይ በተደረ ገ ሰርቬይ 59 በመቶ የሚኾኑት ከ25 እስከ 60 ዓመት የሚኾነውን ጊዜያቸውን ያሳለ ፉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ሁሉም በሚ ባል መልኩ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሲ ኾኑ ብዙዎቹም በኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ያ ልተሳተፉ ነበሩ። በ1985 ዓ.ም በተደረገው የሕዝበ ውሳኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ እና ድም ፅ ለመስጠት ከተመዘገቡ 57,710 ትውል ደ ኤርትራውያን መካከል 99.5 በመቶ የ ሚኾኑት ነጻነትን የመረጡ ሲኾን 204 ሰ ዎች ብቻ ከኢትዮጵያ ጋራ መኖርን መር ጠዋል። ከአምስት ዓመት በኋላ የኢትዮጵ ያ መንግሥት ለ“አገር ደኅንነት ስጋት ናቸ ው” በሚል ብዛት ያላቸውን ትውልደ ኤር ትራውያን ከኢትዮጵያ አስወጥቷል። ብዙ ዎቹ ትውልደ ኤርትራውያንን ከአገር እን ዲወጡ የተደረገው ህግሐኤ (ህግደፍ)ን በ ገንዘብ በመደገፍ እና ትሥሥር በመፍጠር ተወንጅለው ነበር። በቀጣዩ ዓመት 1991 ዓ.ም በሳምንት ቢያንስ እስከ 1500 ዜጎች ከኢትዮጵያ ሲባረሩ ነበር። አብዛኛዎቹ ተባራሪዎች ኢትዮጵያ ው ስጥ በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሠማርተ ው የነበሩ ናቸው። የተባበሩት መንግሥታ ት ድርጅት አጣሪ ልዑክ ቁጥራቸው 250 በሚደርስ የትውልደ ኤርትራውያን ቡድን ላይ ባደረገው ማጣራት መምህራን፣ የሲቪ ል ሰርቪስ ሠራተኞች፣ ሜካኒኮች፣ ነጋዴዎ ች እና የዩኒቨርስቲ መምህራንም ጭምር ከ

ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

በ“አምቼዎች” ፖለቲካ ፣ ማንነት

ተባራሪዎቹ ውስጥ ተካተው ነበር። ከዚህ ቡድን ውስጥ አንድ የሕክምና ባለሞያ እ ና ሁለት መነኩሴዎችም ነበሩበት። አብዛ ኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ60 በላይ የነበረ ሲ ኾን ኤርትራን ረግጠው የማያውቁ እና ት ግርኛ ቋንቋ የማይናገሩ ነበሩ።(Case Material on Ethnic Eritrean Deportees from Ethiopia Concerning Human Rights Violations The Uprooted : Case Material on Ethnic Eritrean Deportees from Ethiopia Concerning Human Rights Violations by Prof. Asmarom Legesse on behalf of Citizens for Peace in Eritrea) ተ ባራሪዎቹ ወደ ኤርትራ የሚወሰዱት በአ ራት የድንበር አቅጣጫዎች ነበር። ብዙዎ ቹ ወደ አሥመራ የገቡት በኦምሃጀር- ተሠ ነይ- አሥመራ ሲኾን፣ የተወሰኑ በቀይ መ ስቀል ተባባሪነት በአሰብ በኩል ወደ ኤር ትራ ተሸኝተዋል። ጥቂቶች የጦርነቱ ግንባ ር በነበረችው ዛላምበሳ እና መረብ ዓዲዃ ላ በኩል ወደ አሥመራ ተጉዘዋል። ሌሎች ደግሞ ወደ ኤርትራ ሳይኾን ወደ ኢትዮጵ ያ የጠረፍ ከተሞች ሞያሌ እና ጅቡቲ ተወ ስደው ከአገር እንዲወጡ ተደርገዋል። ይ ህ ብዛት ያላቸውን ዜጎች ከአገር የማስወ ጣት ተግባር በሁለቱም የፖለቲካ ኀይሎች እንደሞያ የተያዘ ይመስላል። በ1983 ዓ.ም ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ሕግሐ ኤ ከኤርትራ ሲያስወጣ በወቅቱ የኢህአዴ ግ መንግሥት ስለ ተፈናቃዮቹ ምንም ዓይ ነት እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረ ም። ከ1990 ዓ.ም የደንበር ጦርነቱ መጀ መር በኋላም የኤርትራ መንግሥትም “ኢ ትዮጵያዊ” ያላቸውን ዜጎችበምላሹ ከሀገር አባርሯል። ከካምፓላ 73 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ ምትገኘው ጂንጃ ከተማ የሚኖሩ እና በወ ቅቱ ወደ ኤርትራ የገቡትን ዜጎች በመቀበ

“ብዙ ኤርትራውያን አማርኛ ቋንቋን የሚናገረው አማራ ብቻ ይመስላቸው ነበር። ከ1990 ዓ.ም በኋላ ብዛት ያላቸው አምቼዎች ከኢትዮጵያ ተባርረው አሥመራን አጥለቀለቋት” ይላል ቢኒያም።

ል ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አንድ ውስጥ አዋቂ ተባራሪዎቹ ወደ አሥመራ ሲገቡ የነ በረውን ስሜት ለአዲስ ነገር እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ፦ “የመጀመሪያውን ዙር ተባራ ሪዎች ስንቀበል የነበረው ከፍተኛ የቁጭት ስሜት ነበር። በከፍተኛ ስሜትም ነበር። የ መጀመሪያዎቹ ተፈናቃዮች አሥመራ ዩኒቨ ርስቲ እንዲያርፉ ተደረገ፤ ዘመድ ያላቸው

በየዘመዶቻቸው እንዲሄዱ ተደረገ። በብ ዙዎቹ ተባራሪዎች ላይ የላቀ ቁጭት እና ግ ራ መጋባት ይታይ ነበር።” ይላሉ። “ሙሉ ቤት እና ሀብት የነበራቸው አባ ዎራዎች ብርድ ልብስ እና አንሶላ ለመቀ በል ሲሰለፉ ለብዙዎቹ አንገት የሚያስደ ፋ ነበር። እስካሁን ድረስ ያልሻረ ጠባሳ ነ ው” ሲሉ የተፈጠረውን ችግር ያስረዳሉ።

የችግሩ መጠን የተባባሰው ደግሞ የተባራ ሪዎች ቁጥር በየቀኑ እየናረ ሲመጣ እና የ አሥመራ አቅም ከሚችለው በላይ ሲኾን ነ በር። ያውም ብዙዎች ከመላው የቤተሰባ ቸው አባላት ጋራ የመምጣት ዕድል ባለገ ኙበት ኹኔታ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃ ናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) በሁለት የተባራሪዎ


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ዓለም ውስጥ እና ስደት

ች መቀበያ ጣቢያ ባደረገው ሰርቬይ በሰ ኔ 1990 ወደ ኤርትራ ከተባረሩት ውስጥ 63 በመቶ የሚኾኑት አዋቂ መላሾች ከል ጆቻቸው ተለያይተው እንደመጡ ተናግረ ዋል። ብዙዎቹም ሀብት እና ንብረታቸው ን በወጉ ለማደራጀት እንኳ ዕድል አልነበ ራቸውም። ይህን መሰሉ ትውልደ ኤርት ራውያንን ሰብአዊነት በጎደለው መልኩ ከ ኢትዮጵያ የማስወጣቱ ሂደት በወቅቱ በኢ ትዮጵያ መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ ነቀ ፋ ያሰነዘረ ነበር። ነቀፋው እና ትችቱ በወ ቅቱ በነበረው ኹኔታ ላይ ብቻ የተወሰነ እ ና ተባራሪዎች ከዓመታት በኋላ ሊገጥማቸ ው የሚችለውን የማኅበራዊ ኑሮ ቀውስ ከ ግምት ውስጥ የከተተ አልነበረም። ይህ ሁሉ ታሪክ ከተፈጸመ ከዐሥር ዓመ ት በኋላ ያለው የተባራሪዎች በተለይም የ“አምቼ”ዎች ሕይወት በምስቅልቅል ኹ ኔታዎች የተሞላ ነው። ለአዲስ ነገር ታሪካ ቸውን ያጋሩ “አምቼ”ዎችም ይህንኑ እው ነታ ይቀበሉታል። ለደኅንነት በመስጋት ስ ማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት ኹኔታውን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ የጂንጃው ው ስጥ አዋቂም ወደ ኤርትራ የገቡት አምቼ ዎች የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እ ና ሥነ ልቡናዊ ችግሮችን መጋፈጣቸው ን ይመሰክራሉ።

የአምቼነት ዕዳ እንደ ማኅደረ ያሉ ብዛት ያላቸው የትው ልደ ኤርትራውያን ልጆች እና ወጣቶች አ ሥመራን ካጥለቀለቁ በኋላ ያጋጠማቸው ያልጠበቁት እና ካደጉበት በብዙ የሚራራ ቅ ነበር። ብዙዎቹ አሥመራን እና ነዋሪዎ ቿን ሲያስተውሉ እጅግ ወግ አጥባቂ እና የ ውጭ ሰው እና አስተሳሰብ በቀላሉ የማያ ስገባ ዝግ ኾነው አገኙት። እነርሱ ካላቸው አንጻራዊ የኾነ “ተራማጅ” ማኅበራዊ መስ ተጋብር አንጻር ከአሥመራ ነባር ነዋሪዎች ጋራ መዋሃድ እጅግ ፈታኝ ነበር። የሚናገ

ራሱን ጁባ ከማግኘቱ በፊት ከአገር አገር ዞ ሯል። ካርቱም- አዲስ አበባ- ናይሮቢ-ሉዋ ንዳ -ካምፓላ። አሁን ኬንያ የሚገኘው ማኅደረ ድንበር ከመሻገሩ በፊት ኤርትራውያንን እና አም ቼዎችን ማስኮብለል ሥራው ነበር። ከባድ የኾነበትን የአሥመራ ኑሮውን ትንሽ መል ክ ያስያዘው ይኼው ሥራው ነበር። ወደዚ ህ ሥራው ደግሞ ያመጣው የ“ኮምቢሽታ ቶው ጮሌ” ሚካኤል ነበር። ሚካኤል የአ ባ ሻወል ሠፈር ልጅ ነው። ነገር ግን ውሎ ው እና ተግባሩ ኮምቢሽታቶ በመኾኑ ነበ ር ሚካኤል ኮምቢሽታቶ የሚል ስያሜ ያ ገኘው። በጣም ተግባቢ ነው። ሚካኤል እና ማኅደረ የተግባቡት የ“ኮም ቢሽታቶው ጮሌ” ማኅደረ ዘወትር ከማይ ጠፋባት “በረኸት ሻይ ቤት” በትዝታ ሲና ውዝ ያገኘው ቀን ነበር። “አንቺ አምቼ አሁ ንም ሠፈር አልለመድሽም ?” አለው ማኅደ ረን! በቀላሉ ተግባቡ። ወዳጅነታቸው ጠነ ከረ። ሳምንቱን ሙሉ አይነጣጠሉም። ው ሏቸው “ካምቦሎ”፣ “ትራቮሎ”፣ “ፊያት”፣ “ሳንፍራቼስኮ”፣ “አክሪያ” እና ሌሎች ሠፈ ሮች ኾነ። ማኅደረ አዲስ አባባ እያለ ወደ ሲኒማ ኢትዮጵያም ኾነ ሲኒማ አምባሳደ ር ብቅ የማለት ልምድ አልነበረውም። በ አሥመራ ግን ደንበኛ ኾነ። በ“ሲኒማ አዝ መሪኖ” እና በ“ሲኒማ ካፒታል” በየቀኑ ይ ታደማል። ሚካኤል ይከፍላል፤ ማኅደረ ይዝናናል። አንድ ቀን የአሥመራ መለያ የኾነው ካቴ ድራል ወደ ሚገኝበት ኮምቢሽታቶ ተያይ ዘው ነጎዱ። አምባሳደር ሆቴል እዚሁ አቅ ራቢያ ይገኛል። በአቅራቢያው ወደሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ወዳለው ቤት ተያይዘው ሄ ዱ። “ፈጠን ብለህ ግባ” አለው ሚካኤል ኋላ እና ፊቱን እየተገላመጠ። “የሕንጻውን ዋና በር እንዳለፍኩ ግድግዳ ተደገፌ ጠበ ቅኹት። ‘ተከተለኝ’ የሚል ትዕዛዝ ብቻ ሰ

ልዩ ጥንቅር አዲስ ነገር ኦንላይን

ጥቶኝ ነጠር ነጠር እያለ ከፊት ለፊቴ ይመ ራኝ ጀመር” ይላል ማኅደረ ። የገቡት ከሕንጻው ጀርባ ካለች አነስተኛ ክ ፍል ነበር። ሦስት ወጣቶች አትነጋገሩ የተ ባሉ ይመስል በፀጥታ ተቀምጠዋል። ሚካ ኤል ንግግር አላበዛም። “በማለዳ ተነስታች ሁ እዚሁ እንገናኛለን፤ ቻው” የሚል ቃል እንደተናገረ አንደኛው ወጣት ለሚካኤል በእጁ አንድ ነገር አስጨበጠው። “ተረጋግ ታችሁ ውጡ” የሚል ትዕዛዝ ብቻ ሰጥቶ በጥንቃቄ ሕንጻውን ለቀቀው ወጡ። የኮ ምቢሽታቶውን ጮሌ ዋነኛ የገቢ ምንጩ በድብቅ ከኤርትራ የሚወጡ ዜጎች “መር ዳት” መኾኑን ማኅደረ ያወቀው በዚያ አ ጋጣሚ ነበር።

አሥመራ ከተማ የኮምቢሽታቶው ጮሌ ዋና ሥራ ተጓዦ ቹ ከአሥመራ እንዲወጡ መርዳት ነው፤ ከ ዚያ በሻገር ስላለው ደግሞ ሌሎች ባልደ ረቦቹ ይጨነቁበታል። ከተሳካ እስከ ኢት ዮጵያ ወይም ሱዳን ድንበር ያደርሳሉ። ከ ዚያ በኋላ ያለው ጣጣ የስደተኛው ይኾና ል። በወቅቱ በርካቶች በውትድርናው ሥ ራ የመረራቸው፣ ሳዋን የሚሸሹ እና የተሻ ለ ኑሮ የሚፈልጉ ወጣቶች ነበሩ። ውቧ ግ ን ሕይወት አልባዋ አሥመራም ሰልችታቸ ው ነበር። ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለብዙ አ ምቼዎች። የመንግሥት ቁጥጥር ከፍተኛ በ መኾኑ ዜጎችን ማስኮብለል ቀላል ሥራ አ ልነበረም። እጅግ ጥንቃቄን የሚሻ ነው። ከሞት ጋራ አንገት ለአንገት ተናንቆ የሚ ሠራ ነው። ከቀናት ምክክር እና ልምምድ በኋላ ማኅ ደረ የሚካኤል ረዳት ኾነ። የተሰጠው ሚ ና ደግሞ ከኢትዮጵያ የተባረሩ እና መመ ለስን የሚሹ አምቼዎችን ማገናኘት ነበር። ሥራው መልካም ነበር፤ ገቢ አለው። ነገር ግን ሕይወት ከወዲህ ወዲያ የሚያላጋቸ ውን ለጋ ወጣቶች አደጋ ባለው ጉዞ ማሾለ

ክ ለህሊናው ፈታኝ ኾኖበታል። ግን ሕይ ወት ሌላ የተሻለ ምርጫ አልሰጠችውም። “አስገራሚው ነገር በየቀኑ ከሁለት ያለነሰ ሰው ለመኮብለል እንደሚፈልግ ማወቄ ነ በር። አገር የሚሰደድ ነው የሚመስለው። እንደዚህ ጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥርም እ ያለ የሚኮበልል ሰው ማግኘት ሳይኾን እን ዴት ለማስኮብለል እንደሚቻል ነው የሚ ቸግረው” ይላል። ማኅደረ በመጨረሻ ራሱን ለዳግም ስደት አጨው። አሥመራ ቢቆይ ከአባ ሻውል እ ስከ ኮምቢሽታቶ…እንደ ልብ ወዲህ ወዲያ ሲል እንደማይኖር ያውቀዋል። ሳዋ አፉን ከፍቶ ይጠብቀዋል። “በአዝመሪኖ ያለው ቆይታዬም በሳዋ ግዞት መጠናቀቁ ስለማየ ቀር ከወዲሁ ልኮብልል ስል ራሴን መከር ኩት” ይላል ውሳኔ ላይ ስለደረሰበት ወቅ ት እና ኹኔታ ሲያብራራ። ለስደት የመረጠ ው መንገድ ግን ሌላ ፈተና ይዞ መጣ። ኢ ትዮጵያን እንደ መሸጋገሪያ ድልድይነት ቢ ወስዳትም የኤርትራን ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የማንነት ጥያቄው አፍጥ ጦ መጣበት “እኔ የማን ነኝ?” የሚል። “አሥመራን እስከምለቅ በስጋት ውስጥ ጥ ያቄውን አዳፈኜው የነበረ ቢኾንም አክሱ ም ከተማ ስደርስ ዐይኑን አፍጥጦ መጣብ ኝ” ይላል። ከማኅደረ ጋራ አብረው የኮበ ለሉት ወደ ሽመልባ መጠለያ ካምፕ ሲገቡ እርሱ ግን ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ። አዲስ አበባ ጥቂት ከሰነበተ በኋላ ወደ ኬኒያ አቀ ና። ብዛት ያላቸው አምቼዎችም የማኅደረ ን መንገድ ተከትለዋል።

ሥርጭት በምሥራቅ አፍሪካ አምቼዎች ከአዲስ አበባ እና አሥመራ ውጭ በመላው የምሥራቅ አፍሪካ ከተሞ ች ተበትነዋል። በተለይ በምሥራቅ አፍሪ ካ ከተሞች ካርቱም፣ ጁባ፣ ካምፓላ፣ ናይ ሮቢ፣ ሞምባሳ፣….እና በመላው ዓለም ይ ገኛሉ። ምሥራቅ አፍሪካ ላይ ደግሞ በብ

7

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

ሩት ቋንቋ አማርኛ በመኾኑ አምቼዎች ሙ ሉ በሙሉ ከአሥመራ ነዋሪዎች ጋራ እንዳ ይዋሃዱ አርጓቸዋል። “በአረማመድ ሳይቀር ማን አምቼ እንደ ኾነ ትለያለህ” ይላል ቢኒያም። “አምቼ”ዎ ች በሚሰሙት ሙዚቃም ተነጠለው ይታ ወቃሉ። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጫፍ በ ደረሰበት ሰሞን እንኳን በአሥመራ እንዲ ሁም ከረንን በመሰሉ አነስተኛ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ትናንሽ የመዝናኛ ቤቶች ውስጥ ሳይቀር የአማርኛ ሙዚቃ እንደል ብ ማጫወታቸው በጤና አልታየም። ይህ ንን ተከትሎም የአማርኛ ሙዚቃዎችን በ የምሽት ክበቦች ማጫወት እንዲቀር ታግ ዷል። “ከመባረሩ ሂደት ጋራ በተያያዘ ብዙዎቹ የሥነ ልቡና ተጽዕኖ ውስጥ ነበሩ።” ይላል ቢኒያም። ማንነታቸው ሁለት ቦታ የተሰፋ ነው። አዲስ አበባ እና አሥመራ። ማኅደረ ም ከዚህ አልወጣም። ከአደገበት ቀዬ ተነ ቅሎ ያለ ውዴታ እና ፈቃዱ፤ በሚያዋርድ እና የሰውነት ክብርን በሚነካ መልኩ ወደ ኤርትራ መላኩ ያብሰለስለዋል። ዛሬ ልቡ ለኤርትራዊነት ያጋድላል። ግን ኤርትራዊ በመባልም ምሉዕነት አይሰማውም። “የጓ ደኞቼ ፍቅር እና ወዳጅነታቸው ለአፍታ ባ ይጓደልብኝም ስያሜዋ(”አምቼ” ) አንዳች ክፍተት በልቤ ውስጥ ፈጠረች። ኤርትራን ም እንደ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ መጠለያዬ እን ጂ ቋሚ አገሬ ለማለት የማልደፍራት እንደ ኾነች ገባኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ እንዳልል መ ባረሬ መልሱን ሰጥቶኛል” ሲል የተፈጠረ በትን ግራ መጋባት ያስረዳል። “የማልክደ ው ነገር ከኢትዮጵያ በመባረሬ ለኤርትራ ያለኝን ፍቅር መጨመሩ ነው።” ማኅደረ ያንን ጊዜ የሕይወቱ “አስጨና ቂ” እና “አስቸጋሪ” ወቅት አድርጎ ይቆጥረ ዋል። ከሁሉ ፈተና የኾነበት ገቢ ማግኘት አለመቻሉ ነበር። የአባቱ ዘመዶች የመረዳ ዳት ጠንካራ ባህል ታክሎበት እንኳ ኑሮን መግፋት እንደ አለት ጠጥሮበት ነበር፡፡ ተ ንቀሳቅሶ ለመሥራትም የሚያስችል ምንም ዐይነት ቀዳዳ አልነበረም። ለአብዛኛዎቹ “አምቼ”ዎችም ሕይወት እ ንዲያ ነበረች። ከብሔራዊ አገልግሎት ከተ ረፉ አሥመራ ውስጥ አለ የተባለውን ማን ኛውንም ሥራ በመሥራት ይታወቃሉ። በ ብዙ የአሥመራ ነዋሪዎች የማይደፈሩ እን ደማስተናገድ ያሉ ሥራዎችን ሳይቀር ይሠ ራሉ። አንዳንድ እንስቶችም ተገደው ወደ ሴተኛ አዳሪነት ገብተዋል። አንዳንዶችም በአሥመራ ባልተለመደ ኹኔታ ለአደገው ዝርፊያ ተጠያቂ የተደረጉት እነርሱው ናቸ ው። “ሌብነት፣ ማታለል እና በቡድን መ ደባደብ ከአምቼዎች ጋራ ብቻ እየተያያዘ የሚነሳ ነገር ኾኖ ነበር” ይላል መኖሪያው ን ናይሮቢ ያደረገው በፀጋ ሳህለ። ይህ ተደ ራራቢ ከመጥፎ ነገሮች ጋራ የመዛመድ ች ግር የገጠማቸው አምቼዎች የመገለል እና የራሳቸውን ክበብ በመሥራት መራቅን እን ዲመርጡ አድርጓቸዋል። የኤርትራ መንግሥት የሚከተለው ዜጎች ን በወታደራዊ አመለካከት የመቅረጽ ሁሉ ን አቀፍ እንቅስቃሴ ለአምቼዎች የሚመች አልኾነም። የኤርትራ መንግሥት መሪዎች አክራሪ የኤርትራዊ ብሔርተኝነት አቀንቃ ኞች ናቸው። ይህ የአምቼ ማንነት ከተገነ ባበት መሠረት ጋራ የሚፋለስ ነው። የአም ቼዎች ብሔራዊ ማንነት በኢትዮጵያም በ ኤርትራም ፖለቲከኞች እና ልሂቃን ዘንድ እውቅናም ገና አልተሰጠውም። አምቼዎ ች ማንነታቸው የተገነባው በሁለት ጠንካ ራ ብሔርተኛነትን በሚያቀነቅኑ (ኢትዮ ጵያ እና ኤርትራ) ወገኖች መካከል ነው። ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትም ኾነ የኤርት ራ ብሔርተኝነት አንዱ ለአንዱ እውቅና የ ሚሰጡ አይደሉም። ተፎካካሪ ናቸው። የ ሁለቱም ብሔርተኝነት አቀንቀኞች “ቀናተ ኞች” ናቸው። አንደኛው ሌላውን አይቀበ ልም። አሥመራ የሚናኘው የብሔርተኝነ ት አመለካከት “ለ30 ዓመት ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት በተደረገውን ጦር ነት እና ድል “ ውስጥ የበቀለ እና ያደገ ነ ው። የኢትዮጵያ ብሔርተኝነትም ለኤርት ራ ብሔርተኝነት እውቅና የሚሰጥ ሳይኾን እንደ ስኅትት እና ክህደት ይቆጥረዋል። የ አምቼዎች ማንነት የተገነባው ደግሞ የአን ዱን የብሔርተኝንት እንቅስቃሴ በመናድ እና የሌላኛውን በመደገፍ ሳይኾን በሁለ ቱ የብሔርተኝነት አጽናፎች መካከል ያለ

ውን መካከለኛ ቦታ ይመርጣል። አምቼዎ ች ማንነታቸውን የሚገልጹት በሁለቱ ብ ሔራዊ “ቤቶቻቸው” ነው። ሁለቱንም እን ደቤታቸው ያያሉ። ብዙዎቹ ከሁለቱም ቤ ቶቻቸው ርቀዋል። ነገር ግን ደግሞ ከሌ ላኛዋ “ቤታቸው” ኢትዮጵያ በግድ የተነቀ ሉም ናቸው።

አዲስ አበባ አምቼዎች ኑሮ በአሥመራ እጅግ ፈታኝ ኾኖባቸዋል። ኢኮኖሚው እና ማኅበራዊ ው ችግርም ቶሎ ሊቀረፍ ያልቻለ ነበር። ብዙዎቹ ከድንበር ጦርነቱ በኋላም አሁን ም ብሔራዊ አገልግሎት ከመስጠት አል ወጡም። መቼ እንደሚወጡም አቶ ኢሳ ያስ አፈወርቂ እና እግዜር ብቻ የሚያው ቁ ይመስላል። አሥመራ ላይ ያለው የአቶ ኢሳያስ አስተዳደር በየጊዜው ፍፁም አም ባገነንነቱን እያጠናከረ መሄዱ የአምቼዎች ን ሕይወት መፈናፈኛ እንዳይኖረው አድ ርጎታል። እንደ ማኅደረ ያሉት ግን ተሳክ ቶላቸው አገራቸውን ጥለው ዳግም ስደት ገብተዋል።

ዳግም ስደት……ዘጸአት ለአምቼ? አሥመራም ያልተመቻቸው ብዙ “አምቼ ዎች” ኤርትራን ለመልቀቅ ድንበር ማቋረጥ ጀመሩ። መጀመሪያ ወደ የመን፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን። ለደላሎች ብዙ መክፈል ግድ ይላል። ገንዘብ ያላቸው ብቻ ለቀናት የእ ግር ጉዞ በማድረግ ከኤርትራ ደንበር ጠባ ቂዎች ተደብቀው ወደ ከሰላ (ሱዳን) በሕ ገ-ወጥ መንገድ ለመውጣት ይሞክራሉ። የ ተሠነይ-ከሰላ መንገዱ አንዱ ሲኾን ከኤር ትራ ለመውጣት እስከ 4ሺሕ ዶላር የሚቀ በሉት አስተላላፊዎች ሌሎችም በሮች አሏ ቸው። የቻሉ ይወጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ተ ይዘው ይታሠራሉ ወይም ይገደላሉ። በዚህ መልክ ኤርትራን ለቀው ከተሰደዱ ት መካከል አንዱ ቢኒያም ነበር። እርሱ እ ንደ አብዛኛዎቹ አምቼዎች በድንበር ግጭ ት በተነሳው ጦርነት ምክንያት ራሱን አሥ መራ ላይ አላገኘውም። በ1983 ዓ.ም ደር ግ ሲወድቅ ወደ ኤርትራ ሄደ። ከአዲስ አ በባ አስመራ በአውቶብስ እየተመላለሰ የኤ ሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ሲጋራ እና ማስቲ ካ ይነግድ የነበረው ቢኒያም የኢትዮ-ኤር ትራ ጦርነት ሲነሳ አሥመራ ላይ ነበር፤ ድ ንበርም ተዘጋ። ብዙዎችም ተባረሩ። ያኔ አ ሥመራ ላይ መቅረት ግድ ኾነ። ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት የነበረ ው ቢኒያም ንግዱን ቢቀጥልም ከአንድ አ ስቸጋሪ ነገር ጋር ተፋጠጠ። እንደ ደንቡ የ ብሔራዊ አገልግሎት ግዴታውን መወጣ ት ነበረበት። በኤርትራ መንግሥት ሕግ መሠረት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 40 ዓመ ት የኾናቸው ዜጎች የብሔራዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸው። ሦስተኛ ል ጁን እርጉዝ የነበረችውን ባለቤቱን ጥሎ ላ ለመሄድ ያልፈለገው ቢኒያም ከባለሥልጣ ናቱ ጋራ ድብብቆሽ ጀመረ። ቁጥጥሩ ጥብ ቅ እየኾነ ሲመጣ የቀረው ሁለት አማራጭ ነበር። ወደ ብሔራዊ አገልግሎት መሄድ ወይም ከሀገር መውጣት። አገር ጥሎ መውጣት ግን ቀላል አልነበረ ም። በየቦታው ያሉትን ኬላዎች ማለፍ፣ በ አልሞ ተኳሽ ወታደሮች የሚጠበቅ ድንበ ርን ማለፍ ይጠይቅ ራሱን የቻለ ፈተና ነበ ር። ከአሥመራ ተሰነይ በአውቶብስ የተጓዘ ው ቢኒያም ድንበር አቋርጦ ከሰላ ለመግባ ት የ17 ሰዓት የእግር ጉዞ መሄድ ግድ ኾኖ በታል። “እኛ የወጣንበት መንገድ አሪፍ ነ በር” ይላል ቢኒያም። የወታደሮች አፈሙ ዝ የሌለበት፤ ይህን መንገድ የሚያውቁ ሰ ዎች ግን በወቅቱ “ጫን ያለ” ክፍያ ነበር የ ሚጠይቁት። የተጠየቀውን 1500 ዶላር ከፍሎ የሱዳን የድንበር ከተማ የኾነችው ከሰላ የደረሰው ቢኒያም በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች እጅ ላይ ይወድቃል። “ከሰላ ስገባ ጀለቢያ አድርጌ ነ በር። ጸጉረ ልውጥ ስለኾንኹ በፖሊሶች ተ ያዝኩ። በኪሴ 3000 ዩሮ እና 200 ዶላር ነበረ። ፖሊሶቹ ራቁቴን አድርገው ፈተሹ ኝ” ይላል። የኮሎኔል ማዕረግ ካለው ፖሊ ስ ፊትም እንዲቀርብ ተደረገ። “የሚያውቁ ት ገንዘብ ዶላር ስለነበር የያዝኩትን 200 ዶላር ሰጠኋቸው። ዩሮውን ስላላወቁት ለ ቀቁኝ” ሲል እንዴት ለመቋቋሚያ ብሎ የያ ዘው ገንዘብ እንደተረፈለት ይናገራል። ዛሬ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል


8

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካ

ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ተስፋ የማይጨልምበት የስደት ህይወት (ታሪኩ አዳፍሬ ከኬንያ) አዲስ ነገር ኦንላይን

ፍሏን ለመግለጽ ጠባብ የሚለው ቃ ል ብቻውን የልብ አያደርስም። በአ ጭሩ የበሬ ግንባር የሚሏት ዐይነት ና ት። ጥበቷ እና የታቀፈቻቸው ሰዎች ብዛት ግን ለተመጣጥኖሽ እንኳ የሚከብድ ነው። በ ሦስት ማእዘናት የተዘረጉ ፍራሾች፣ ከአንድ ጥግ መ ደገፍ እንጂ በወጉ መቀመጥ ያልቻለ ቴሌቭዥን፣ ተ ደራርበው የተቀመጡ ሻንጣዎች፣ ከሻንጣው በላይ የተደረቡ ቀለም ዐልባ ድሪቶዎች . . . መሀል ላይ በ ትሪ ላይ የተደረደሩ የቡና ስኒዎች፣ ዕጣን ማጤሻ፣ የከሰል ምድጃ . . . ምሽቱ ለብርሃን ተራውን ከለቀቀ አስር ሰዓታት ተ ቆጥረዋል። በኬንያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተ ኞች አቆጣጠር ግን “ከማለዳው” ሁለት ሰዓት ሊኾ ን ነው። በዚሁ ፀሐይ እያዘቀዘቀች በመጣችበት ሰ ዓት ገና እየነጋ የሚመስለው እና የጠዋቱ አራት ሰ ዓት የሚታሰበው ስደተኛ ካለ በታታሪዎቹ የኬን ያ ስደተኞች አቆጣጠር “ማልዶ” ከቀኑ ስድስት ሰ ዓት ላይ ተነስቷል ማለት ነው። ይህ ቀትር ላይ ከ እንቅልፍ የመንቃት ልምድ የራሱ የኾኑ መላምቶ ች አሉት። ከአገር ያፋታው እና ቀን ከሌት ሕልም ኾኖ የሚያ ባዝነው የምዕራብ አውሮፓ እና የሰሜን አሜሪካ ጉ ዞ ስኬታማ እስኪኾን ድረስ “ጊዜ መግደያ ነው” የ ሚለው የመጀመርያው መላምት ነው። በዚህኛው መላምት አብዛኞቹ ስደተኞች ይስማማሉ። ሁሉም በሚባል ደረጃ ውጭ በሚኖር የወዳጅ ዘመድ ድጎ ማ የሚኖሩ እንጂ የተለየ የገቢ ምንጭ የሌላቸው ና ቸው። ስለዚህ ማልዶ ለመነሳት ምክንያት የላቸው ም። ሁለተኛው መላምት ባለሙሉ ተስፈኞች የሚ ያቀነቅኑት ዐይነት ነው። ወደፊት ምርታማ አሜሪካ ዊ ዜጋ የመኾን ራዕይን ያዘለ መላምት። በኬንያ ከ ቀኑ ዐሥር ሰዓት ሲኾን አብዛኛው የአሜሪካ ግዛት ንጋትን የሚያይበት ነው። ቀኑ ሳያመልጠው ራሱን የሩጫው አካል ለማድረግ የሚራወጥበት እና ለመ ኳተን የሚዘጋጅበት ሰዓት ነው። በኬንያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችም በአሜሪ ካ ኑሮ ማልዶ የመንቃት ጥቅም የገባቸው ይመስል እኩል ሰዓት ላይ ይባንናሉ። እናም በተመሳሳዩ ሰዓ ት አርፍደው (ተግተው) በመነሳት ልምምዳቸውን በኬንያ ምድር ከወዲሁ ተያይዘውታል። በርካታ ሐ በሻ በሚኖርባቸው እንደ ኢስሊ ባሉ አካባቢዎች ያ ሉ የሐበሻ ሱቆች በማለዳ የማይከፈቱትም በእነዚህ እና በእነዚህ መሰል ምክንያቶች ጭምር ነው። “አ ውሮፓ እና አሜሪካ የሚኖር ዘመድን ለማግኘት አ መቺው ሰዓት ከዐሥር ሰዓት በኋላ ነው” የሚለው የተለመደ ንግግር በሦስተኛ ደረጃ የሚገኝ ሌላኛው መላምት ነው። አብዛኞቹ ኬንያ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስ ደተኞች በአዲስ አበባ ወንደላጤዎች እና ዘመናዊ ቆጣቢዎች ዘንድ “ቁ-ምሳ” (በምዕራባውያን ዘንድ “ብራንች” ተብሎ ይታወቃል) የሚል ማእረግ የተሰ ጠው ቁርስንም ምሳንም ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላ ይ የመመገብ ልማድን ቢኮርጁም የሚጠቀሙበት በራሳቸው የሰዓት አቆጣጠር ነው። የሐበሻዋ “መክ ሰስ” “የቁምሳን” ቦታ ወስዳለች። እራት ደግሞ በው ድቅት ሌሊት ተተክቷል። ድንገት ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ አንድ ስደትን የሚጋራ የአገር ሰው በራች ሁን አንኳኩቶ “በዚህ ሳልፍ ሰላም ሳልላችኹ አላል ፍም ብዬ ነው” ቢላችኹ ሊገርማችኹ አይገባም። የ እራት ሰዓት ላይ መገናኘታችኹ እንጂ። ከረፋዱ አ ምስት ሰዓት ላይ ተመልሶ ቢመጣ ግን ለጠብ ፈል ጎዎታል ወይም እነደ አገር ቤት ይትበኻል “መርዶ ነጋሪ” ነው ማለት ነው። ደግነቱ እርሱም “በውድቅ ት ማለዳ”አይሞክረውም።

ስደት እና ቅፈላ . . . በዚህ ሰዓት እንግዲህ ማለዳ ለእንቅልፍ ያገለገሉ ፍራሾች አሁንም ብቻቸውን አይኾኑም፤ አይደሉም ም። ዘወትር የሚጎበኟቸው እንግዶች ቢያንስ ቀጣ ዮቹን ስምንት ሰዓታት እንዳሻቸው ያሹዋቸዋል። እ ረፍት የለሾቹን ፍራሾች። በዚያች “የበሬ ግንባር” በ ምታህል ክፍል ስምንት ወጣቶች ጥግ ጥጋቸውን ይ ዘዋል፤ የመንታ ያህል በሚያመሳስላቸው አቀማመ ጥ። ቡና የምታፈላው ወጣት ከጊዜያዊ ረኸቦቷ ጋራ ለማዕከላዊነት የቀረበውን ሥፍራ ይዛላች። በእያን ዳንዱ ተቀማጭ ጭን ሥር በጥቁር ላስቲክ የተቋጠ ረ ጫት ይገኛል። ሚራ ይሉታል ኬንያውያን እና የ ምሥራቅ አፍሪካ አገራት ሰዎች። አዲስ አበቤዎች ከ ሚያወቁት የተለየ ጫት ነው። ከካርቶን የሚወፍር

ቅጠል፣ ማንጠልጠያ እንጨት እንኳ የሌለው። በሁ ለት ጣቶች እየተቆነጠረ የሚሰፈር። ከሰላሳ የኬንያ ሽልንግ (አምስት የኢትዮጵያ ብር) ጀምሮ ይገኛል። ለአብዛኛው ስደተኛ ያለ ጫት የምታልፍ ቀን እንደ ባከነች ትቆጠራለች። ጫት እና ሕይወት ያላቸው ት ሥሥር እንደ ሳንቲም ገጽታ ያለ ነው። የሌለው ቢቻ ል ቀፍሎ (ለምኖ) አልያም ዱቤ የማያውቁትን የኬ ንያ ጫት ሻጮች አሳምኖ ዕለታዊ ምሱን ያደርሳል። ደምስ ከፕሮፌሽናል ቀፋዮች (PK) የአንደኛነትን ደረጃ ከሚይዙት መካከል የሚመደብ ነው። ወደጆ ቹ “ሲቀፍል ጉርሻም ቢኾን አይቀረው” ሲሉ መረር አርገው ይቀልዳሉ። ዛሬም ቡድኑን ለመቀላቀል የዘ ገየ ቢኾንም በ100 ሽልንግ ለሌሊቱ የሚበቃውን ያህ ል ጫት አግኝቷል። የደምስ ኑሮ ላለፉት አምስት ይ ችኑ መደጋገም ብቻ ነው። ቀፍሎ የቤት ኪራይ ይከ ፍላል፤ ቀፍሎ ይመገባል፤ ቀፍሎ ይጠጣል፤ ቀፍሎ የመረጣትን ኬንያዊ ሴት ይዞ ያነጋል፤ ቀፍሎ ይቅማ ል . . . በቃ ቅፈላ እስካለ ሕይወት ለደምስ ጎድላለ ች የምትባል አይደለችም። የኬንያ ምድርን ከረገጠበት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ለ ስድስት ዓመታት የቤተዘመዶቹን ድጎማ አልተነፈገ ም ነበር። በየወሩ እስከ ሦስት መቶ ዶላር ያህል እየ

ተደጎመ ስደተኛ ሳይኾን አምባሳደር መስሎ አሳልፏ ል። በዓመታቱ ርዝመት ወደ አውሮፓ የመሄዱ ሕ ልም የከሰመ የመሰላቸው ለጋሾቹ እጃቸው እያጠረ መጣ። ከሦስት . . .ወደ ሁለት . . . አንድ እያለ ወደ ኪሱ ሲገባ የነበረው ዶላር ወደ ዐልቦነት ተሻገረ። በ ወቅቱ ወደ አገር ቤት የመመለሱም ፍላጎት ተኖ ጠ ፍቶ ነበርና ኬንያን ከቅፈላ ጋራ እንደ አዲስ ይለማ መዳት ጀመር። ሲነቃ ስለ ጫቱ አብዝቶ ያስባል፣ ይ ጨነቃል፣ ሲለው ይተጋል፤ ሲመረቅን ለአንገት ማስ ገቢያ የሚላትን ኻያ ሽልንግ ለመጠጡ በመፈለግ ይ ባትላል። ሲሰክር ደግሞ ቤቱ እንዳይቀዘቅዘው በጭ ኗ የምታሞቀው ሴት ከንጋቱ 11 ሰዓት ያስሳል። “ሳይ ደግስ አይጣላም” የሚለው አባባል ለደምስ የተሠራ እስኪመስል ጠይም የሐበሻ መልኩ አግዞት አንዷን ሳያስከትል ገብቶ አያውቅም። ይህ የኑሮ ዑደቱ ለአ ንድም ቀን እንኳ አልተዛነፈበትም። የሚዛነፍበትም አይመስለውም። ደምስን መሰል አንዳች ደጋፊ የሌላቸው ስደተኞች ዕለታዊ ዕድላቸውን ተጠልለው በናይሮቢ በሽ በ ሽ ኾነዋል። ሐበሻ በአብዛኛው በሚኖርባቸው እን ደ ኢስሊ፣ ፓንጋኒ እና ሐርሊንግሃም አካባቢዎች አ ይጠፉም። ብዙዎች ከዐሥር ዓመታት በላይ የቆዩ

በመኾናቸው ዘመድ አዝማድ እጁን ማስረዘም ሰል ችቶት የተዋቸው ናቸው። ወደ አገር ቤትም የመመ ለስ ሐሳብ ለብዙዎቹ እንደ መርግ ከብዷቸዋል። አ ንዳንዶቹ ነገን ተስፋ በማድረግ ቀሪዎቹ ደግሞ “ም ን ይዤ ልመለስ” በሚለው ሐሳብ ራሳቸውን እየሞ ገቱ ጭንቅላታቸው ውስጥ የ”መመለስን” አራት ነ ጥብ አትመዋል። በፖሊቲካ ጉዳይ የተሰደዱት ደግ ሞ በአማራጭ ዕጦት ውሳኔያቸው አየር ላይ ነው።

የዐዩ መንገድ . . . ይህ ሁሉ ሕይወት እና ሐሳብ በሚናጥበት የስደተ ኞች ምድር ወደ አገር ቤት ለመመለስ “የዐዩን ድፍረ ት ይስጥህ” የምትል ቀልድ ትደመጣለች። ዐዩ ከሁ ለት ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ 15 ሺሕ ዩ ሮ ከቤተሰቡ ይዞ የመጣ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነው። 15 ሺሕ ዩሮው በአጠቃላይ ለአሜሪካ ጉዞው (ፕሮ ሰሱ) ማስፈጸሚያ የተመደበለት ሲኾን ለዕለታዊው ወጪው ደግሞ እስከ አራት መቶ ዶላር የሚደርስ ገ ንዘብ በየወሩ ይላክለት ነበር። ካልበቃው ደግሞ እ ጅግ የሚሳሱለት ዘመዶቹ ፈጥነው ይጸድቁበታል። ከቁጠባ ይልቅ አለማባከንን የሚያስተምረው ዐ ጣ። ለወትሮው የስደተኞችን አርፍዶ መነሳትን የለ መደ ቢኾንም ከብክነት አልታደገውም። አራት መ

ቶ ዶላር ለወር አልበቃ እያለው ተቸገረ። ቀዳዳ ለመ ሸፈኛ ተብለው የሚላኩ ዩሮዎች ሊበግሩት አልተቻ ላቸውም። ወጪው ባስ ሲልበት ለአሜሪካ “ፕሮሰ ስ” የተባለችውን 15 ሺሕ ዩሮ ይዳብሳታል፤ ገንዘብ ይላካል- እርሱ ያጠፋል። ከተቀማጭ ዩሮ ላይ ይመ ዛል። በቀን ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ያስጨነቀው አ ስቀማጭ ባንክ ተቀማጭ ገንዘቡን እንዲወስድ ዐዩን እሰከ መገሰጥ የደረሰበት ጊዜም ነበር። ለዐዩ ገንዘብ የልውውጥ ሳይኾን የነውጥ መሣርያ ኾነ። በሄደበት መሸታ ቤት ዶላር ይተኩሳል፤ ዮሮ ይወረውራል። የሚላከውን ጨምሮ ተቀማጩን ዩ ሮ ለማሟጠጥ ግን ስድስት ወራት በቂ ነበሩ። ይኼ ን የሰሙ ቤተሰቦች አንድ ዶለርም አንልክ ወደሚል ውሳኔ ተዛወሩ። ለወር ያህል የገዛቸውን የቤት ቁሳቁ ሶች በመሸጥ ኑሮን ታገላት፤ አልቻለም። አንድ ማለ ዳ ቆረጠ። የናይሮቢ ቆይታው ዓመት እንኳ ሳይኾነ ው ወደ እናት ምድሩ ተመለሰ። ለብዙዎች ዐዩ የተጓዘው መንገድ ቀላል እና እኛም ልንከተለው እንችላለን የሚሉት ዐይነት አይደለም። ፖለቲካው ያስፈራቸዋል፤ ባዶ እጅ መመለሱ አንገ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል


ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሀበሻዊ ቃና

9

ተምሳሌት

ወይዘሮ ፍቅርተ ሙላት ጋር ቀጠሮአችን እሁድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነበር፡፡ ካሳንጋ አካባቢ ከሚገኘው ቤቷ 200 ሜትር ያህል መጥታ ተቀበለችኝና ወደ መኖሪያ ቤቷ አመራን፡፡ እሷን ተከትየ ወደ ቤት ስዘልቅ ቡናው ተፈልቶ ቄጠማው ተጎዝጉዞ እውነትም እሁድ ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእሁድ መዝናኛ ዜና እየተነበበ ነበር የደረስነው፡፡ አንባቢዋ በአሜሪካ ታዋቂዋና የመጀመሪያዋ ሴት የቶክሾው አዘጋጅ ኦፕራ ዊንፈሬ ለ25 ዓመታት ከቆየችበት የቶክሾው አለም መሰናበቷን እያነበበች ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ገና ያልተሰናበተች ይልቁንም ከትንሽ ተነስታ በሰው ሀገር በስኬት ጉዞ ላይ ስላለች የ35 ዓመት ወይዘሮ የህይወት ተሞክሮ ቃለመጠየቅ ላደርግ እየተዘጋጀሁ፡፡ ቆይታችን ይህን ይመስላል፡፡

መታመኔ ለዚህ አድርሶኛል

ሐበሻዊ ቃና፡-ወይዘሮ ፍቅርተ ከሀገርሽ መቼ እና እንዴት ወጣሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- በመጀመሪያ የሄድኩት ወደ ናይ ሮቢ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የሄድኩት በአጋ ጣሚ ነው ፡፡ ከዚያ በፊት አዲስ አበባ ዜኒት ኮስሞ ቲክስ የተባለ ድርጅት ውስጥ በተለያየ ስራ ሀላፊነ ት አስራ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ናይሮቢ ትኖር የነበረች ው እህቴ በአጋጣሚ ልትጠየቀን አዲስ አበባ መጣ ች፡፡ እህቴ ጠይቃን ስትመለስ ታዲያ እኔም ለእረፍ ት በሚል የእሷን ልጅ ይዤ ወደ ናይሮቢ ሄድን፡፡ በ ዚህ መካከል ናይሮቢ ሆኜ ካናዳ ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመርኩ፡፡ የአሁን ጊዜ ፕሮሰስ እንደምታውቀው ነ ው፡፡ ከአንድ ዓመት እስከ አራት ዓመት ይፈጃል፡፡ የኔ አራት ዓመት ነበር የፈጀው፡፡ በዚያ ሁሉ ጊዜ ግ ን ቤተክርስቲያን ውስጥ በስነጽሁፍ፡ ድራማና በመ ሳሰሉት ነገሮች ከማገልገል ውጪ ምንም ስራ አልነ በረኝም፡፡ያው ቤት ወስጥ ነበር ቁጭ የምለው፡፡ ም ክንያቱም በዚያን ወቅት ናይሮቢ የምትወጣበት ሀገ ር አይደለም፡፡ስትወጣ በፖሊስ ትያዛለህ፡፡ከአንዴ ም ሁለት ጊዜ በአጋጣሚ ሱቅ እቃ ልገዛ ስወጣ በፖ ሊስ ተይዤ ታስሬአለሁ፡፡ በተለይ አንድ ጊዜ ለስለ ሳ ልገዛ ስወጣ በአጋጣሚ ፖሊሶች ሰዎችን እያፈሱ እስር ቤት ያስገቡ ነበርና እኔም ተይዤ እስር ቤት ገ ባሁ፡፡ያኔ እጄ ላይ የነበረው 70 የኬኒያ ሽልንግ ብ ቻ ነበር፡፡ከዚያም ተፈተሸን ያለንን ካስረከብን በኋ ላ ወደ እስር ቤት ገባን፡፡ገና በሩ ሲከፈት በጨለማ ቤት ውስጥ የታፈገ ሙቀት ከመጥፎ ሽታ ጋር ተቀ በለኝ፡፡ከቤት በድንገት እንደወጣሁ ስለነበር ምንም የለበስኩት ነገር አልነበረም፡፡በባዶው መቀመጥ ሲ

ያቅተኝ ብትክትክ ያለ ብርድልብስ አገኘሁና እሱ ላ ይ ተቀመጥኩ፡፡ እሱም ግን ተባይ የሞላበት በመሆ ኑ እንዲሁ ቆሜ አደርኩ፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አ ካባቢ ደግሞ ሴተኛ አዳሪዎችን ሰብስበው ይዘዋቸ ው መጡ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእነሱ ጋር ቀላቀሉኝ፡፡ ሴተ ኛ አዳሪዎቹ በጣም ጠጥተው ስለነበር ያስመልሳቸ ው ነበር፡፡በህወቴ ከተማረርኩባቸው ጊዜ አንዱ ነበ ር፡፡ ጥዋት ደግሞ ውጡ ተባልንና ሽንትቤት እንድ ንጠርግ ታዘዝን፡፡ ቤተሰቦቼ ደግሞ የት እንደታሰር ኩ እንኳን ጠፍቼባቸው በስንት ሰው አፈላልገውኝ በታሰርኩ በሳምንቱ 3 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ ከፍየ ከ እስር ቤት ወጣሁ፡፡ይህ ጊዜ በጣም አስከፊ ጊዜ ነበ ር፡፡በዚህ መሃል አብሬአቸው እኖር የነበሩት እህቴ ና ወንድሜ በሰራ ምክንያት ወደ ኡጋንዳ መጡ፡፡ እ ኔ ግን የጀመርኩትን የካናዳ ፕሮሰስ መጠበቅ ስለነበ ረብኝ ብቻየን ናይሮቢ ቀረሁ፡፡አራት ዓመት ሙሉ ጠብቄ ውጤቱ ስመጣ ግን ጥያቄየ(ፕሮሰሱ) ውድ ቅ ሆነ፡፡ ቃለ ምልልሱን አላላፋችሁም ተባልን፡፡ከዚ ያ የነበረኝ አማራጭ እህትና ወንድሜ ወዳሉበት ካ ምፓላ መምጣት ነበር ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡-ካምፓላ እንዴት ተቀበለችሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ካምፓላ መጥቼ አንድ ዓመት እ ንደቆየሁ እህቴ ከባለቤቷ ጋር ወደ አሜሪካ ወንድ ሜ ደግሞ ወደ ካናዳ ሄዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ህይወት በ…ጣም አስከፊ ነበር፡፡ በተለይ ምርር ብየ ያለቀስ ኩት እህቴ ስትሄድ ነበር፡፡ልገልጽልህ ይከብደኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የምትገልጸው አለ አንዳንዴ ደግሞ መ ግለለጽ የማትችለው አለ፡ ውስጥህ ዝም ብሎ የሚቀ መጥ፡፡ ማንም አጠገቤ አልነበረም፡፡ ያደግሁት ከቤ

ተሰብ ጋር ነው…እና…(አይኗ እንባ አቅርሮ ንግግሯን አቋርጣ ነበር)፡፡መጀመሪያ ያገባሁት ባል ነበር፡፡ እ ሱም….(አሁንም ንግግሯን መጨረስ አልቻለችም)፡ ፡ አስበው እዚህ ጋር አይዞህ ባይ ቤተሰብ የለህም፡ ፡ እዚህ ጋር ባል ብየ ያገባሁት ከድቶኛል፡፡ ምን ው ስጥ ነው ምገባው? በቃ ብቻ በጣም ችግር ውስጥ ነበርኩ፡፡ በጣም መራራ ህይወት ነበር፡፡ የማደርገ ው ሳጣ ፋሲካ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ተቀጠርኩ፡ ፡ ያም ሁሉ እየሆነ ግን ስራየን በደንብ እሰራ ነበር፡ ፡ ይሄ የሰው ቤት ነው ይሄ የኔ ነው አልልም ነበር፡፡ ጭንቅላቴም በጣም ፈጣን ስለሆነ ነገሮችን በደንብ ና ቶሎ ቶሎ መስራ እችላለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የማገ ኘው ገንዘብና የቤት ኪራይ የምከፍለው ሊመጣጠ ንልኝ አልቻለም፡፡ፋሲካ አራት ወር ያክል እንደሰራ ሁ የሆነ ሰው በሀሳብ እረዳኝ፡፡ ‹‹ፍቅርተ ለምን የሆ ነች ትንሽ ምግብ ቤት ለራስሽ አታቋቁሚም፡፡ በጣ ም ጎበዝ ስለሆንሽ ይሳካልሻል››ሲለኝ እሺ አልኩ፡፡ ከዚያ ኪሲኒ አካባቢ ናይል ኮች የሚባል ጋራዥ አ ለ፡፡ጋራዡ ውስጥ ትንሽ ሜዳ ሰጡኝ፡፡ሜዳዋን እ ኔ ራሴ ጣራ ሰርቼ በሰሌን ሸፍኜ ምግብ ማብሰል ጀ መርኩ፡፡ ብዙ ተመጋቢዎች ነበሩ፡፡ በተለይ ሾፌሮ ች ይሄዳሉ፡፡ ይመጣሉ፡፡ ቁርስ ምሳ ራት ይበላሉ፡፡ ይህም ሁሉ ሲሆን ግን ብቻየን ነበርኩ፡፡ገባህ? አን ዱ እንጀራ አዝዞኝ ሳልጨርስ አንዱ አምባሻ ሲለኝ በጎን ደግሞ እንጀራ እጋግራለሁ፡፡ ያቺ ጊዜ በጣም የውጥረት ነበረች፡፡ ለሁለት ወር ያህል በዚህ መል ኩ እንደሰራሁ ወደ ኮቦኮ(ሱዳን መስመር) ሄድኩ፡ ፡ በዚያም የጋራ ስራ አግኝቼ እየሰራሁ ጥሩ ገበያም እያገኘሁ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ሶስት ወር ያክል እ

ንደሰራሁ ግን ሰውየው(አከራዩ) በጣም የቤት ኪራ ይ ጨመረብኝ፡፡በቃ ከዚያ ትቼው ወደዚህ(ካምፓ ላ) ተመለስኩኝ፡፡ ከዚያ እንደገና ደግሞ ዝም ብየ ቁ ጭ አልኩ፡፡ ስራ የለ ምን የለ፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵ ያ የደህና ቤተሰብ ልጅ ነኝ፡፡ ግን እንዴት ብየ እንደ ገና ከኢትዮጵያ ወደዚህ ገንዘብ ላኩ እላለሁ? እኔ ሰ ው አልመለከትም፡፡ እዚህ ጋር ወንድም አለኝ እዚህ ጋር እህት አለኝ አልልም፡፡ ነገሮችን በራሴ ማድረግ እንጂ ሰው ማስቸገር አልፈልግም፡፡ አንድ ቀን በጣ ም ምርር ብሎኝ በረንዳ ላይ ወጥቼ እያለቀስኩ አካ ራያችን ‹‹ፍቅርተ ምን ሆነሻል?›› አለችኝ፡፡ እስኪ ሱ ቅ ካለ ትንሽ ሱቅ ፈልጊልኝ አልኳት፡፡ ከዚያ አሁን ያ ለሁባትን ሱቅ አገኘችልኝ፡፡ግን ገንዘብ እጄ ላይ የለ ኝም፡፡የተረፈችኝ ገንዘብ 200 ሺህ ሽልንግ አካባቢ ብቻ ነበረች፡፡ሰዎቹ ደግሞ የአራት ወር ካልከፈልሽ አሉኝ፡፡ከዚያም እሺ ላምጣ ብየ ወደ ቤት ስሄድ ሌ ሎች ሰዎች ቦታውን አይተውት ሄደዋል፡፡እዚህ ሀገ ር ደግሞ ቦታ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡በዚህ ጊዜ ቤ ት ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብ ነበር ሰርቼ እከፍላላሁ ብየ በድፍረት ገባሁና ሱቁን ጀመርኩ፡፡ከዚያ በኋላ ያለውን ታሪክ እኔ አላውቀውም፡፡ሁሉን ነገር የሰራ ውም ሆነ የሞላው መድሃኒዓለም ነው፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡- የሱቅ ህይወትስ ስትጀምሪ ምን መልክ ነበረው? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ሱቁን ስጀመር መጀመሪያ በሸቀ ጣ ሸቀጥ ነበር፡፡ከዚያ እንጀራ አስገባሁ፡፡እንጀራ ም ጋግረው ራሴ ነበርኩ፡፡ከጧት እስከማታ ሱቅ ስሰራ እውላለሁ፡፡ ማታ ቤት መጥቼ ሊጥ አቦካለሁ፡፡ አብ ሲት እጥላለሁ፡፡ እንጀራው ይጋገራል፡፡የነገውም እ

ንደዚያ እየሆነ ይቀጥላል፡፡ አንድ ጊዜ የሆንኩትን ወ ይም የገጠመኝን ላጫውትህ፡፡ ሌሊት እንጀራ እየጋ ገርኩ ምጣዱን አስምቼው ቁጭ እንዳልኩ ከመድከ ሜ የተነሳ እንቅልፍ ወስዶኛል፡፡ ብንን ስል የምጣዱ ቫልቮላ ነዶ ቤቱ በጪስ ታፍኗል፡፡ ቤቱን ከፍቼ እን ዳልወጣ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ሆኗል፡፡ ፈራሁ፡፡ያ ለኝ አማራጭ አፌን በትራስ አፍኜ እንደምንም ታ ግየ ማሳለፍ ነበር፡፡ ይህን ጊዜ መቼም አልረሳውም፡ ፡አሁን ግን እግዚአብሄር ይመስገን ጠንክሬ በመስራ ቴ እዚህ ደርሻለሁ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡- የት ደረስሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- አሁን ያለሁበት (ረጅም ሳቅ…)

ሐበሻዊ ቃና፡-ወይዘሮ ፍቅርተ መርካቶ ማለት ናት ይባላል፡፡ አውነት ነው? ወይዘሮ ፍቅርተ፡-አዎ! የሌለ ነገር የለም፡፡ እቃዎ ችን በሙሉ አስገባለሁ፡፡ ብዙ መደርደሪያ ነው ያለ ው፡፡ እነዚያ መደርደሪያዎች ጾማቸውን እንዲያድ ሩ አልፈልግም፡፡እያንዳንዱን እንደ ልጆቼ ነው የማ ያቸው፡፡ ለስራየ ትልቅ ትኩረት አለኝ፡፡ ሌላ ነገር ብ ወድም ቅድሚ ግን ሁሌም ለስራየ ነው፡፡ሁሌም ስ ራየን አክብሬ ስለምሰራው የማከብረውን ያክል ው ጤት ይሰጠኛል፡፡ይህ ለነገ ይሄ እንዲህ ይሆናል አ ልልም፡፡ ሁሉንም በፍጥነት እሰራለሁ፡፡ የስራ ሀሳቦ ችን የመፍጠር ችሎታም አለኝ፡፡ከሰዎች በቀጥታ አ ልገለብጥም፡፡ለሌላው የማይታየውን ነገር ይሄን እን ዲህ ባደርገው እንዲህ ይሆንልኛል ብየ ያንን አደርጋ ለሁ፡፡ ውጤትም አገኝበታለሁ፡፡ ከምንም በላይ እ

ወደ ገጽ 18 ዞሯል


10

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሳሚ-ኡጋንዳ ተስፋይ-ዛንዚባር በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

ፎቶ- ከቪዲዮ ክሊፑ

ቡ ጥፍት እስኪል ድረስ ሙዚቃ ይ ወዳል። የ23 ዓመት ኡጋንዳዊ ወጣ ት ነው። ሪቻርድ ቱኻሂሮ ይባላል። የሙዚቃ ዝግጅቶችን ሥራውን ትቶ ም ቢኾን ያያቸዋል። እንደ ጆሴ ካሚሊዮን ያለ ዘፋ ኝ የሚገኝበት ከኾነ ደግሞ ከዝግጅቱ ላይ ተዐምር እ ንኳ ቢፈጠር አይቀርም። ባለፈው ጥር መጨረሻ ኢ ንቴቤ ወደሚገኘው ሪዞርት ቢች ሲሄድም የዘፋኞቹ ን ማንነት ተመልክቶ ነበር። “ባትል ኦፍ ዘ ቻምፒዩን ስ” (የአሸናፊዎቹ ጦርነት) የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ሁለቱ እውቅ የኡጋንዳ ዘፋ ኞች ካሚሊዮን እና ቦቢ ዋይን አብረዋቸው የሚጫ ወቱ ዘፋኞችን አስከትለው መድረክ ላይ ተሰየሙ። የካሚሊዮን ወገን በኾነው “ሊዮን አይላንድ” በኩ ል በኡጋንዳ መድረክ ያልተለመደ ፊት ታየ። በዚህ ወጣት ዘፋኝ የሚቀርበው ሙዚቃ ያልተለመደ ም ት ያለው ነው። ቋንቋውም የተለየ። ዳንኪራ ወዳዶ ቹ ኡጋንዳውያን ቋንቋውን ከቁብ ሳይቆጥሩ ምቱን እየተከተሉ ለመውረግረግ ሞከሩ። ለሪቻርድ ግን የ ወጣቱ አዘፋፈን በአገሩ ዘፋኞች እንደለመደው ፈጠ ን ያለ አልነበረም። ዘፋኙ ሙዚቃውን ሲያበቃ ታዳ ሚው በድጋፍ ጩኸት አጀበው። ይኼኔ ካሚሊዮን ወደ መድረክ ወጥቶ ወጣቱን አስተዋወቀው። ሪቻር ድ የዘፋኙን ስም በቅጡ አልሰማም። ዜግነቱን ግን አልዘነጋውም። ኤርትራዊ። ይህ በኾነ በወሩ የዚህን ኤርትራዊ ዘፈን እንደገና ሰ ማ። ምክንያቱ አሁንም ካሚሊዮን ነበር። ከበርካታ የውጭ አገር አቀንቃኞች ጋራ በጋራ የሚዘፍነው ካ ሚሊዮን ከኤርትራዊው ጋራ አዲስ ነጠላ ዜማ በመ ሥራቱ ነበር ሪቻርድ ዘፈኑን ሊሰማ የቻለው። ሪቻር ድ ዘፈኑን አብዝቶ ከመውደዱ የተነሳ ሞባይሉ ላይ አስጫነው። ዘፈኑ “ክበቡዋ” ከሚለው ርዕሱ ጀምሮ በአብዛኛው በትግርኛ ቋንቋ የተዜመ ቢኾንም ሪቻር

ኢትዮጵያዊው ተስፋይ ከታንዛኒያዊው ማቶና ጋር የተጣመረበት ሙዚቃ በአድማጭ እና ተመልካች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል

የታንዛኒያ አካል በኾነቸው ዛንዚባር የሚኖረው ማቶና ቫዩሊን እና ኡድ የተሰኙ መሣሪያዎችን ይጫወታል

ድን ከማድነቅ አላገደውም። “የማውቀው ነገር ቢኖር ስለፍቅር እንደሚዘፍን ነ ው” ይላል ኤርትራዊው ዘፋኝ በስንኞቹ ውስጥ የሚ ለውን እየገመተ። ግምቱ ደግሞ ካሚሊዮን በዘፈኑ ጣልቃ እየገባ በእንግሊዘኛ ከሚያዜመው የተመዘዘ ነው። ካሚሊዮን “አንቺ ንግስቴ ስትኾኚ እኔ ደግሞ ንጉስሽ እኾናለሁ” ሲል ሪቻርድም አብሮት ይወጣዋ ል። ካሚሊዮን ይቀጥላል። “በፍቅር ስታከንፊኝ ያለ ኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ። ዳይመንድም ቢኾን።” ሪቻር ድ እነዚህን ስንኞች ቃል በቃል ይላቸውና አዝማች የኾነውን “ክበቡዋ”ላይ ሲደርስ ቀጥ ይላል። ግን ዘ ፈኑን ከመስማት አያቋርጥም። “ቤቴ ደግሞ የዘፈኑ ቪዲዮ ክሊፕ አለኝ” ይላል። ሪ ቻርድ የዘፋኙን ስም ያወቀው በዚያ የሙዚቃ ቪዲ ዮ ላይ ተጽፎ ካነበበ በኋለ ነበር። የዘፋኙ ስም ተ ጽፏል። ለማስታወስ ቀለል ያለ ስም ነው። ሳሚ።

ከ“ክበቡዋ” እስከ “ፎር ኦል ታይም”

ፎቶ- ከቪዲዮ ክሊፑ

ፎቶ- ሴንትሪክስ ፊልምስ

ጥበብ

ሀበሻዊ ቃና

የ“ክበቡዋ” ዘፈን የሙዚቃ ቪዲዮ የቀረበው የካሚ ሊዮን በኾነው የሙዚቃ አሳታሚ “ሊዮን አይላንድ” ነው። የሙዚቃ ቪዲዮው የሚጀምረው “ምሥራቅ አፍሪካን እመራለሁ” የሚል ጽሑፍ ያለበትን ቲሸር ት ያደረገውን ካሚሊዮንን በማሳየት ነው። እንደካ ሚሊዮን ሁሉ መነጽር ያደረገው ሳሚ ተከትሎት ይ መጣል። ስሙ እና የኤርትራ ባንዲራም አልቀረም። ቪዲዮው በጥቁር እና ነጭ ቢጀምርም ቀለም ያለባ ቸውን ትዕይንቶች እያሳየ ይቀጥላል። ሳሚ እና ካ ሚሊዮን እየተፈራረቁ በሚያቀነቅኑበት በዚህ ክሊ ፕ የዩጋንዳውያን እንስቶች ምስል በየጣልቃው ይገ ባሉ። በዘፈኑ መጨረሻ ለኤርትራዊው ዘፋኝ ዮሐን ስ ትካኽቦ (ወዲ ትካኽቦ) ምስጋና የሚቀርብበት ጽ ሑፍ ይነበባል። ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ ለሳሚ የመጀመርያው አይደ ለም። ይህ ሙዚቃ ለሕዝብ ዕይታ ከመብቃቱ ሁለ ት ወራት በፊት ሳሚ ከሌላ እውቅ ኡጋንዳዊት ዘፋ ኝ ጋራ የቪዲዮ ክሊፕ ሠርቶ ነበር። አብራው የሠራ ችው አቀንቃኝ ጃኪ ቻንዱሩ ትባላለች። “ብሉ 3” ተ

ብሎ የሚታወቀውን የሴቶች የሙዚቃ ቡድን ከመ ሠረቱ ዘፋኞች አንዷናት። ሲንዲ የተባለችው የቡድ ኑ አባል ለብቻዋ መዝፈን መጀመሯን ተከትሎ ዝና ው የደበበዘውን “ብሉ 3” ገሸሽ አድርጋ የራሷን ሥራ ዎች እያቀረበች የምትገኝ ነች። ካሚሊዮንን ጨምሮ ከተለያዩ ዘፋኞች ጋራ በጥምረት የምትሠራው ጃኪ ከሳሚ ጋራ የተገናኘችው በአጋጣሚ ነው። ጃኪን ከሳሚ ጋር ያገናኛት የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሯ ነ በር። ያን ጊዜ ጃኪ እና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሯ ለየት ያለ ነገር ለመሥራት የተነጋገሩበት ወቅት ነበር። መነ ሻቸው ደግሞ እንግሊዛዊው ሙዚቀኛ ስቲንግ ከአል ጄሪያዊው ሼብ ማሜ ጋር በጋራ የተጫወቱት “ዴዘ ርት ሮዝ” (የበረሃ ጽጌረዳ) የተሰኘ ዝነኛ ዘፈን ነው። እ.ኤ.አ በ1999 የተሠራው ይህ ዘፈን በዐረብኛ እና እንግሊዘኛ ቅልቅል የተሠራ ነበር። በአንድ ወቅት በ አሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ ከምርጥ ዐሥሮች ተርታ ውስጥ መግባት የቻለ ነበር። “መቀየጡን ወደድኩት” ትላለች ጃኪ ስለዘፈኑ ስ ታነሳ። ጃኪ እንዲህ ዐይነት ቅይጥ ዘፈን ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት የተረዳው ፕሮዲዩሰሯ በሥራ አጋ ጣሚ የሚያውቀውን ሳሚን አግኝቶ እንዲያነጋግራ ት ይመክረዋል። ሳሚ እንደተባለው ያደርጋል። ጃ ኪም ከሳሚ ጋራ በጥምረት የመሥራት ሐሳቡን ትቀ በላለች። በምን ጉዳይ ላይ አተኩረው እንደሚዘፍኑ ከሳሚ ጋራ ከተነጋገሩ በኋላ ዜማውን ደርሳ፣ ራሷ የ ምትዘፍነውን ግጥም ጽፋ፣ የዘፈኑን አዝማች አውጥ ታ በአጭር ጊዜ ጨረሰች። ሳሚ በበኩሉ በትግርኛ የሚያወርደውን ስንኝ አዘጋጅቶ አመጣ። ስቲንግ ሼ ብ ያዘጋጀውን የዐረብኛ ስንኞች መረዳት እንደማይ ችል ሁሉ ጃኪም የሳሚን የትግርኛ ግጥም አንዱንም ቃል አታውቀውም። ልክ እንደ ስቲንግ እና ሼብ የየድርሻቸውን ይዘው የመጡት ሳሚ እና ጃኪ ስቱዲዮ ተገናኙ። ከሦስት ሰ ዓት ቆይታ በኋላ “ፎር ኦል ታይም” የተባለው ዘፈን በጃኪ ፕሮዲዩሰር አቀናባሪነት ለጆሮ የሚመች ጥዑ ም ዘፈን ኾኖ ብቅ አለ። ሁሉም ሙዚቃውን ወደዱ


ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሀበሻዊ ቃና

11

ጥበብ

ት። እናም የሙዚቃ ቪዲዩ ሊሠሩለት እዚያው ስቱ ዲዮ እያሉ ወሰኑ። “የተለየ ዐይነት ሙዚቃ በመኾኑ ይበልጥ በቪዲ ዮ ለመግለጽ ፈለግን። በኡጋንዳ ሰው ሙዚቃህን የ ሚቀበለህ በቪዲዮ አስቀረጽህ ካቀረብክለት በኋላ ነ ው” ስትል ክሊፑን ወዲያውኑ መሥራት ያስፈለገበ ትን ምክንያት ለሐበሻዊ ቃና ታስረዳለች።

ጥታ ተላልፏል። ሳሚ አብሯት ወደ ኤርትራ ባለመ ጓዙ ምክንያት የጋራ ዘፈናቸውን ሳታቀርብ ብትቀር ም በዳንስ የታጀበው የጃኪ እንቅስቃሴ ከተመልካች አድናቆትን አስገኝቶላታል። እርሷም ከሕዝቡ ባገኘ ችው አቀባበል ደስ መሰኘቷን ገልጻለች። “በኤርትራ የነበረኝ ቆይታ አስደሳች ነበር። በሌላ ጊ ዜ ተመልሼ እሄዳለሁ” ትላለች።

ከባዱ ቀረጻ

ፔንታቶኒክ ወንዝ ይሻገራል?

ፎቶ- ሴንትሪክስ ፊልምስ

የሳሚ እና የጃኪ ቪዲዮ ክሊፕ ሥራ እንደ ዘፈን ቀ ረጻው በቀላሉ የተከናወነ አልነበረም። የሙዚቃ ክ ሊፑን እንዲሠራ የተመረጠው “ሴንትሪክስ ፊልምስ” የተሰኘው ድርጅት ነበር። ከተመሠረተ ስድስት ዓመ ት ያስቆጠረው ይህ ድርጅት የጃኪን እና የ“ብሉ 3”ን ቀደምት ሥራዎች የቀረጸ ነው። የዚህ ድርጅት መሥ ራች እና የጀርባ አጥንት የኾነው ዴኒስ የአገሪቱን እ ውቅ ዘፋኞች ሙዚቃ ቪዲዮ ያዘጋጀ ነው። የጃኪ እ ና ሳሚ ምርጫም ኮምፒዩተር ኢንጀነሪንግ አጥንቶ ሙዚቃ ክሊፕ ወደማዘጋጀት የዞረው ዴኒስ ነበር። “በጋራ ኾነው ደወሉልኝ እና ስለዘፈናቸው ነገሩኝ” ይላል ዴኒስ የመጀመሪያ ቀን ግንኙነታቸውን ለ“ሐ በሻዊ ቃና” ሲያስታውስ። “ሁሉንም ነገር ተነጋገር ን።” ቪዲዮውን እንዴት እንደሚቀርጽ የተለያዩ ሐሳቦ ችን ሲያወጣ እና ሲያወርድ የሰነበተው ዴኒስ በስተ መጨረሻ በሁለት አማራጮች ይረጋል። ከሁለቱ ዘ ፋኞች ጋራ በተደረገ ውይይት አንዱ ይመረጥ እና ወ ደ ቀረጻ ለመግባት ቦታ መረጣ እና መሰል ዝግጅቶ ች ይጀመራሉ። ከሦስት ሳምንት ዝግጅት በኋላ በአ ንድ ቀዝቃዛ ምሽት ሳሚ እና ጃኪ “ካዌምፔ” ተብሎ ወደሚጠራው የካምፓላ ክፍል ያመራሉ። መዳረሻ ቸው ፋብሪካ ነው። በቦታው ሲደርሱ አካባቢው በ መብራት ደምቆ ካሜራዎች ተጠምደዋል። የዕለቱ የአየር ጸባይ ግን ቀረጻውን ለማከናወን አመ ቺ አልነበረም። በቪዲዮ ክሊፑ ለተካተተው ወገብ ንቅናቄ ሲባል የተመረጡት አልባሳት ደግሞ ሰውነት ን የሚያጋልጡ ነበሩ። “ይዘንብም ስለነበር አየሩ ቀዝቃዛ ነበር። አካባቢ ውም ጭቃማ ኾኗል። ሁሉም ነገር በተሳሳተ አቅጣ ጫ የሚሄድ ይመስል ስለነበር በጣም ተናድጄ ነበ ር። ደስተኛ አልነበርኩም” ትላለች ጃኪ በዕለቱ ስለነ በረው ኹኔታ ስታስረዳ። ቀረጻው ግን በዚያው ዕለት መካሄድ ነበረበት እና ተደረገ። አብዛኛው ቀረጻም በትልቅ የብረት ቱቦ ው ስጥ እና አጠገብ ተከናወነ። ጃኪም ልብሶቿን እየለ ዋወጠች፣ የሳሚን ስም በቁልምጫ እየጠራች፣ ሲያ ሻትም ፊቱ እየተውረገረገች ተቀረጸች። ሙሉ ጥቁር ኮት እና ሱሪ የለበሰው ሳሚም የት ድረስ መተወን እ ንደሚችል አሳየ። ቀረጻው አበቃ።

ጃኪ ከሳሚ ጋር በተጫወተችበት ቪዲዩ የተካተተውን የወገብ ንቅናቄ ዳንስ ከዩ-ቲዩብ ተመልክታ የተለማመደችው ነው

ቀረጻው የተጠናቀቀው እ.ኤ.አ ነሐሴ 2010 አካባቢ ቢኾንም ተመልካቾች ዘንድ ለመድረስ ግን አምስት ወር ግድም ዘግይቷል። መውጫው ቢዘገይም ለመ ጀመሪያ ጊዜ በ“ዩ ቲዩብ” ድረ ገጽ ሲለቀቅ የአድናቆ ት አስተያቶች ጉረፉለት። ወራት ዘግየት ብሎ በቴሌ ቪዥን ለተመልካች ሲቀርብም ከፍተኛ ተወዳጅነት ን አተረፈ። እንደ ኤን.ቲ.ቪ የመሳሰሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሙዚቃ ዝግጅቶቻቸው ደጋግመው የ ሚመርጡት ዘፈን ኾነ። ዘግይቶ ተወዳጅነት ማትረ ፉን በተመለከተ ጃኪ የምትለው አላት። “በኡጋንዳ በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ የሙዚቃ ቪዲ ዮዎች ስለሚወጡ የተመልካቾችን ቀልብ ለመግዛት ከባድ ነው” ትላለች። የቪዲዮው ተወዳጅ መኾን ሳሚን በበርካታ መድ ረኮች ላይ ከጃኪ ጎን እንዲቆም አደረገው። የግል ድ ርጅቶች በባለ ኮኮብ ሆቴሎች በሚያዘጋጇቸው ድ ግሶች ላይ ጃኪን የሚጋብዙ ከኾነ ሳሚ የማይቀር ተ ጣማሪ ኾነ። ከመጀመሪያው ቪዲዮ በኋላ ጥቂት ቆ የት ብሎ የወጣው “ክበቡዋ”ም እንዲሁ ተወዳጅነት በማትረፉ የሥራ ጥሪዎች ይበዙለት ጀመር። የሁለ ቱ ሙዚቃዎች ተወዳጅነት ይበልጥኑ ሳሚን ተጠቃ ሚ ቢያደርጉትም ለካሚሊዮን እና ጃኪም ያልተጠ በቀ ግብዣ አምጥቶላቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው። ኻያኛውን የኤርትራ የነጻነት በ ዓል በደመቀ ኹኔታ በአሥመራ ለማክበር ከታቀዱ ት ዝግጅቶች አንዱ ከውጭ አገር የሚመጡ አርቲስ ቶች የሚሳተፉበት ታላቅ ኮንሰርት ማዘጋጀት ነበር። ካሚሊዮን እና ጃኪ ከሳሚ ጋራ ያስቀረጹትን ቪዲዮ የተመለከቱት የኮንሰርቱ አዘጋጆች ሁለቱን ኡጋንዳ ውያን ለነጻነት በዐሉ ይጋብዟቸዋል። “ኤኬ 47” በ ተሰኘው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው የካሚሊዮን ወንድም እና ዲጄ አሉዳ ከኡጋንዳ የተጋበዙ ሌሎች ሙዚቀኞችም ነበሩ። እነዚህ አራት ኡጋንዳውያን ዝ ግጅቶቻቸውን ለማቅረብ ከፍተኛ ክፍያ መቀበላቸ ውን የኡጋንዳ ሚዲያዎች ቢዘግቡም ወደ አሥመራ የተጓዘችው ጃኪ ብቻ ነበረች። ጃኪ ከኤርትራ የነጻነት ቀን አራት ቀናት ቀደም ብ ሎ በሮማ ሲኒማ በተካሄደው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የራሷን ዘፈን አቅርባለች። የመግቢያ ዋጋው 700 ና ቅፋ የነበረው ይኼው ዝግጅት በኤርትራ መንግሥ ታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ኤሪ ቲቪ) አማካኝነት በቀ

ፎቶ- ሴንትሪክስ ፊልምስ

የዝና ጣሪያ

ጃኪ እና ሳሚ የሙዚቃ ክሊፑ ዳይሬክተር ዴኒስ የቀረጻውን ወዲያውኑ እየተመለከቱ ለዳግም ቀረጻ ይዘጋጁ ነበር

ጃኪ በአንድ ነጠላ ዜማ ምክንያት በሌላ አገር ያገኘ ችው ተቀባይነት አስደምሟታል። በትግርኛ፣ በአማ ርኛም ኾነ በሌላ ቋንቋ ከሚዘፍኑ ዘፋኞች ጋራ በጥ ምረት እንድትሠራ ማበረታቻ ኾኗታል። ተጨማሪ ሥራዎችን ለመሥራት ግን የሚጣመሯት አርቲስቶች ለአዲስ ዐይነት የአዘፋፈን ስልት የተዘጋጁ መኾን እ ንዳለባቸው ትናገራለች። ኤርትራውያንም ኾኑ ኢት ዮጵያውያን የሚከተሉት የሙዚቃ ስልት “ፔንታቶኒ ክ” እንደመኾኑ መጠን ሌሎች አድማጮችን ለመሳ ብ ዘፈናቸውን ከሌሎች የዘፈን ስልቶች ጋራ መቀየ ጥ እንዳለባቸው ትመክራለች። “እኔ የተለያየ ሙዚቃ መስማት ስለምወድ የፔንታ ቶኒክ ሙዚቃ እወዳለሁ። በፔንታቶኒክ ስልት የሚ ቀርብ ዘፈን ሳቢ ቢኾንም ሁሉም የሚደስትበት አይ ደለም” ትላለች። ለዚህ መፍትሄው “መካከለኛውን መንገድ” ማግኘት እንደኾነ ታብራራለች። መካከለ ኛ መንገድ የምትለውን ለማብራራት የእርሷን እና የ ሳሚ ቅንጅት ትጠቅሳለች። የሁለቱንም አገራት የአዘ ፋፈን ስልት ያለቀቀ ግን ደግሞ የተቀየጠ ዘፈን መሥ ራት ወንዝ ያሻግራል ባይ ነች። እንደሳሚ ሁሉ በዚህ ፈለግ የተመራው ኢትዮጵያ ዊው ተስፋይ ገብረ ዮሐንስ ወንዝ ተሻግሮ ተሳክቶለ ታል። ከታንዛንያዊው ሙዚቀኛ ጋራ በሠራው “ቢን ቲ ዛንዚባር” ዝነኛ ኾኗል። ዘፈኑ ብዙዎቹ የምሥራ ቅ አፍሪካ አገራት በሚጋሩት በኪስዋሂሊ ቋንቋ እና በትግርኛ ተቀይጦ የተሠራ ነው። ሁለቱንም ቋንቋዎ ች የሚጫወተው ተስፋይ ይኹን እንጂ የኪስዋህሊ ው የዘፈኑ ክፍል ድርሰት የአገሬው ሰው በኾነው ሙ ሐመድ ማቶና የተሠራ ነው። ማቶና የታንዛኒያ አካ ል በኾነቸው ዛንዚባር የሚኖር ሲኾን የሙዚቃ አስ ተማሪ ነው። ቫዩሊን እና ኡድ የተሰኙ መሣርሪያዎች ንም ይጫወታል። የተስፋይ እና ማቶና ጥምረት የተወለደው “ኡሞጃ” በተሰኘው የሙዚቃ ቡድን አማካኝነት ነው። “ኡሞ ጃ” በሰባት አፍሪካ አገራት ያሉ በባህል እና ጥበብ ዙ ሪያ የሚሠሩ ቡድኖች ያቋቋሙት ነው። ኢትዮጵያ ን ወክሎ የ“ኦሞጃ” አባል የኾነው ሰርከስ ኢትዮጵያ ነው። ከመንፈቅ በፊት የሰርከስ ኢትዮጵያ ዳይሬክ ተር ኾኖ የተሾመው እና የሰርከስ ትግራይ መሥራች የኾነው ተስፋይ ለልምድ ልውውጥ ታንዛኒያ ይጓዛ ል። የ“ኡሞጃ” አባል በኾነው እና ተቀማጭነቱን ዛን ዚባር ካዳረገው “ዳው ካንትሪስ ሚዩዚክ አካዳሚ” አስተማሪዎች ጋር ይገናኛል። ማቶና ከተባለው ሙ ዚቃ አዋቂ ጋራ ይግባባል። መግባባቱ ሙዚቃ በጋ ራ የመሥራት ሐሳብን ይወልዳል። የታንዛኒያ ቆይታውን ያጠናቀቀው ተስፋይ የሙዚ ቃውን ሐሳብ ከግብ ሳያደርስ ወደ አገሩ መመለስ ነ በረበት። ሙዚቃ የመሥራት ሐሳቡን በቁም ነገር የ ወሰደው ተስፋይ ማቶናን ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣ እና በጋራ ወደ ስቱዲዮ ይገባሉ። ቫዮሊን እና ኡዱን ተሸክሞ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ማቶና ሁለቱን የክ ር መሳሪያዎች ተጠቅሞ አረብኛ ቅላጼ ያለው የትግ ርኛ ሙዚቃ ከተስፋዬ ጋር ሰርቶ አጠናቀቀ። ሙዚቃው ዛንዚባር በሄደ ጊዜ የአገሬውን ቆንጆ ዐ ይቶ በፍቅሯ ስለወደቀ ኢትዮጵያዊ የሚተርክ ነው። ፍቅሩን መግለጽ ግን አቃተው። ኪስዋህሊ ቋንቋ አ ያውቅ ነገር ምን ብሎ ያናግራት። መፍትሄ መስሎ የ ታየው ቋንቋውን ማጥናት ነው። እናም አደረገው። አጥንቶም ፍቅሩን በኪስዋህሊ ተነፈሰ። “ናኩፔንዳ” እያለ። እንዲህ ለተሠራ ሙዚቃ ከመልእክቱ ጋራ የ ሚሄድ ጥሩ የሙዚቃ ቪዲዮ ለማዘጋጀት ተስፋይ ይ ወስናል። እንደገና ወደ ታንዛኒያ እና ዛንዚባር ሲጓዝ ከነማቶና ጋራ ኾኖ ክሊፑን ቀረጸ። ለሥራ ጎራ ያለባ ቸውን ኬንያ እና ሞዛምቢክም አልቀሩት። የክሊፑ ሥራ አንድ ዓመት ግድም ፈጅቷል። የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ተጠናቆ ለዕይታ ሲበቃ ግን በአ ጭር ጊዜ ተወዳጅ ኾነ። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እ ና በታንዛኒያ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቪዲዮው መተ ላለፍ ሲጀምር ደግሞ የተስፋይን ስም አገነነው። በ ተለያዩ አገራት ያሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን አድናቆታ ቸውን ገለጹ። “ዘፈኑን ብዙዎች ወደውታል። መዓት ሰው ነው የ ሚጽፍልኝ” ሲል ተስፋይ ከመቀሌ በስልክ ለ“ሐበ ሻዊ ቃና” ተናግሯል። ተስፋይ ይህን ዘፈኑን የሠራ ው የአፍሪካን አንድነት ለማሳየት እንደኾነ ይገልጻ ል። “ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ ኾና ሳ ለ በአፍሪካ አንድነት ዙርያ ግን ምንም የተሠራ ሙ ዚቃ የለም” ይላል። ተስፋይም ኾነ ሳሚ ድንበሩን ሻገር ብለው ከምሥራቅ አፍሪካ አርቲስቶች ጋራ በ ጥምረት የመሥራትን ጅምር አሳይተዋል። ሌላው ን የአፍሪካ ክፍል ማዳረሱን እንደ ቤት ሥራ ወስ ደው . . . ።


12

ጥበብ

ፎቶ-ሊበን ወርድፕሬስ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ደህና አይደለም

ቴዎድሮስ ታደሰ በአእምሮ አለመረጋጋትና የድብታ ስሜት እየተሰቃየ ነው

ከሶስት አመት በፊት የረዥም ጊዜ የአሜሪካ ቆይታውን በመቋ ጨት ለእናት ሀገሩ በቃ፡፡ ‹‹አገሬ›› የሚል ነጠላ ዜማ ይዞ መጣ፡፡ ኑሮውንም በእናት አገሩ አደረገ፡፡ አዲስ አልበም አጠናቆ በመስራ ት ለአምባሰል ሙዚቃ ቤት አቀረበ፡፡ ከዛሬ ነገ ይወጣል የሚለው ይህ የቴዎድሮስ አልበም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ለሁለት አመ ታት ዘግይቷል፡፡ ‹‹ጓዳ›› የተሰኘው አዲሱ አልበሙ መስከረም ላይ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቴዎድሮስ አገር ቤት ጤናው ብዙም አልተመለሰለትም፡፡ ዳግም ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ ከሰሞኑ ታዋቂ የሙዚቃ ባልደረቦቹ ሊጠይ ቁት ወደ ቤቱ ሄደው ነበር፡፡ ከበር መልሷቸዋል፡፡ እኔ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኜ እንድታዩኝ አልፈቅድም ነው ያላቸው፡፡ እነርሱም ይህን ን ሰምተው ከደጅ ተመልሰዋል፡፡ ቴዎድሮስ ታደሰ በመጠነኛ የአእምሮ አለመረጋጋትና የድብታ ስ ሜት እየተሰቃየ ነው፡፡ ቀን ቀን በር ዘግቶ ብቻውን ነው የሚኖረ ው፡፡ በፋና ኤፍ ኤም ሬድዬ የሚተላለፈውን የ “ኢትዮፒካሊን ክ” “ውስጥ አዋቂ” ፕሮግራምን ጠቅሶ ይህንን የዘገበው አዲስ ነ ገር ኦንላይን ነው።

ዋቂው ኤርትራዊ ዘፋኝ ዳዊት ሽላን የሙዚቃ ዝግጅቱ ን በካምፓላ አቀረበ። ዳዊት ዝ ግጅቱን ያቀረበው ኤርትራ ነጿ ነቷን ያገኘችበትን 20ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀው የ ሙዚቃ ድግስ ላይ ነው። ዝግ ጅቱ የቀረበው በሎጎጎ ሾው ግ ራውንድስ ኢግዚቢሽን አዳራ ሽ ውስጥ አርብ ግንቦት 28 ቀን 2003 ዓ.ም(ጁን 3 2011) ከም ሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነው። ዳዊት በብዙዎች የሙዚቃ አ ፍቃሪዎች ዘንድ የሚታወቀው በፍቅር ዘፈኖቹ እና ባለስድስ ት ስትሪንግ ክራር ተጨዋችነ ቱ ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ ከዳዊት ሽ ላን በተጨማሪ ሳሙኤል ተአገ ስ፣ ይስሐቅ ገብረ እግዚኣ፣ ገላን እድሪስ እና ሾንቂ ተሳትፈዋል። ይህንን ዝግጅት ለመድረክ እ ንዲበቃ ያደረጉት የኤርትራ ቆ ንስላ ከኤርትራውያን ማሕብረ ሰብ (ማሕብረኮም) ጋር በመተ ባበር ነው።

ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

የግጥም ጥግ በፈረሰው መንገድ ሳዘግም…

ዳዊት ሽላን

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

በካምፓላ የሙዚቃ ዝግጅት አቀረበ

…. ቅንጣት ነ ኝ ላገሩ ሰበዝ ነኝ ለምድሩ። “እፉዬ ገላ” ነኝ ነፋስ የሚነዳኝ…. ነፋስ የሚመራኝ….. *** ጤዛ እየላሰ፣ ዳዋ ተንተርሶ፣ከሰው ተለይቶ፣ ዓለም በቃኝ ብሎ፣ ሌላ ብርሃን ሽቶ፣ በባዕት ተከቶ እንደ ሚኖር መናኝ፣ ሱባዔ እንደያዘ፣ስለዓለም ሞቶ “እግዚኦ ውስተ መንሱት..” እያልኩ እኖራለሁ.. የዚህ አገር መንገድ፣ የዚ’ አገር ጎዳና ወዴት ተሸሸገ በስንተኛው ቀን ነው…ወደ ምድረ ራማ፣ በለቅሶ ያረገ.. ስል እቆዝማለሁ…. * * *

በአቀራረቡ ለየት ፊልም እየተሰራ ነው

ግሩም ኤርሚያስ በዚህ ፊልም ላይ ከተሳሉት ሁለት ዋና ገጸባህሪያት የአንዱን ወክሎ ይጫወታል

ሀገሩ እንግዳ ነው፣ ነፋስ ነው ሙዚቃው ሹክሹክታ ቀረርቶው፣ ትካዜ እንጉርጎሮው ነፋሱ እያፏጫል፣እያንጎራጎረ ትዝታ እያዜመ አንቺ ሆየ፣ ባቲን በፉከራ መንፈስ እያጉረመረመ ሲጠራኝ ሰማሁት…. መናኒ ሆይ ስማ መናኒ ሆይ ስማ….. “ድንጋዮች አመፁ ድንጋዮች ሮጡ ከድንጋይ ተፈጥሮ፣ አፈንግጠው ወጡ” …..መናኒ ሆይ ስማ “ከጥንት መሠረቱ ሰው መሆንን ሸሽተው ድንጋይ መሆን ጓጉተው… ከመጡ በኋላ…. እንዴት ወደ ኋላ…..” … ይመስለኝ ነበረ ሰው ብቻ የሚመንን ለካ ሀገር ሲከፋው ሀዘን ሲጫጫነው ይሸሻል ከአድባሩ ይደበቃል ከሰው ….. ሰውም አልነበረው? ይህ ባእድ መሬት እንክርዳድ የሞላው፣ቁጫጭ የናኘበት አሻራ እንዴት አጣ፣ ሕልሙስ የት ደረሰ መንገዱ ፍኖቱ፣እረ እንዴት ፈረሰ…..?

የሰራዊት ፍቅሬ “ሂሮሽማ” ፊልም በቅርቡ ተመረቀ

ነኛው የማስታወቂያ ስራ ባለሙያ እና ተዋናይ ሰራዊ ት ፍቅሬ “ሂሮሽማ” የተሰኘ አዲስ ፊልሙን ሰኞ ግንቦ ት 29 ቀን በተለያዩ የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስመረ ቀ። ፊልሙ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ የኒውክለር ቦምብ በመጣል ከፍተኛ ጉዳት ካደረስባቸው ሁለት የጃፓን ከተ ሞች በአንዷ ስም የተሰየመ ነው። ሰራዊት ፊልሙን “ሄሮሽማ” ሲ ል ስያሜ የሰጠውም ጭብጡ ከኒውክለር ጋር ስለሚገናኝ ነው። የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በ“ሂሮሽማ” የሚተውነው ሰራዊት የ ኒውክለር ዝቃጭ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ ሲጠየቅ አስቀድ ሞ በተለቀቀው የፊልሙ ማስታወቂያ ላይ ይታያል። በፊልሙ ላይ ወታደራዊ ትዕይንቶች ተካተውበታል። ሰራዊት ከፊልሙ ተቀን ጭቦ በተሰራው ማስታወቂያ ላይ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአ ብሔር እንጂ ወደ ኤ.ፍ.ቢ. አይ እና ሲ.አይ.ኤ አይደለም የምትዘረ ጋው” እሺ ብሎ በኃይለ ቃል ሲነገር ይደመጣል። በቅርቡ የለቀቀ ው የ“ትዝታ” ነጠላ ዘፈኑ ተወዳጅነት ያስገኘለት ሚኪኤል በላይ ነህም ይህንኑ ዘፈን በመድረክ ሲያቀነቅን በፊልሙ ላይ ይታያል። በዚህ ዓመታትን በፈጀው ፊልም በ“ገመና” ድራማ ምርጥ ተዋና ይት ተብላ የተሸለመችው መሰረት መብራቴ፣ በ“ኦቴሎ” ትያትሩ የሚታወቀው የሕግ ባለሙያው አበበ ባልቻ፣ በአምስተኛው የኢ ትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ረዳት ተዋናይ ሆኖ የተሸለመው ፈ ለቀ አበበ ይተውኑበታል። “ስምንቱ ሴቶች” በተሰኘው ትርጉም ት ያትሯ የምትታወቀው አዜብ ወርቁም ከፈረንሳዊው ባሏ ጋር በዚ ህ ፊልም ተጫውታለች። “ሂሮሽማ” ከ“ሰማያዊ ፈረስ” ቀጥሎ ለሰራዊት ሁለተኛ ፊልሙ ነው።

ግርማ ተስፋው

ቁጠባ ብዙ አላስብም፤ ሃሳብ እፈራለሁ፤ አብዝቼም አልወድም፤ መውደድ እሸሻለሁ፤ የልቤንም እምነት፤ በአፌ እክደዋለሁ፤ ፎቶ- ሰራዊት መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን

ፎቶ- ትዝታህ ፊልም

“የጸሀይ መውጫ ልጆች” የሚል ርዕስ የተሰጠው እና አዲስ አቀ ራረብ ይዞ እንደመጣ የተነገረለት ፊልም በኢትዮጵያ እየተሰራ ነ ው። ፊልሙ የሁለት ሰዎች ታሪክ ሲሆን መንገድ ላይ ተጀምሮ መ ንገድ ላይ የሚያልቅ ነው። የመንገድ ጉዞው ናዝሬት ተጀምሮ መተ ሃራ፣ አዋሽ፣ አፋር እና ሂርናን ያካትታል። “አባይ ወይስ ቬጋስ” በ ተሰኘው የቴዎድሮስ ተሾመ ፊልም ላይ በጋራ የተወኑት ሰለሞን ቦ ጋለ እና ግሩም ኤርሚያስ የሁለቱን ዋና ገጸ ባህሪያት ሚና በመያዝ በ“የጸሀይ መውጫ ልጆች” ላይ ይተውናሉ። ሰለሞን አሁን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እየታየ ባለው “ሰው ለሰ ው” ድራማ ጨምሮ በበርካታ ፊልሞች ላይ የተጫወተ ወጣት ተ ዋናይ ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ በተሰራው “ሄርሜ ላ” ፊልምአድናቆትን ያገኘው ግሩም በተከታታይ በሰራቸው ሌ ሎች ፊልሞች በአጭር ጊዜ ዝናን ለመጎናጸፍ የበቃ ነው። በዚህ ዓመት በተካሄደው አምስተኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊል ም ፌስቲቫል ላይ “ትዝታው” እና “ይሉኝታ” በተሰኙት ሁለት ፊ ልሞች ላይ ባሳየው አተዋወን “የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ” ተብሎ ተ ሸልሟል። “የጸሀይ መውጫ ልጆች” የጻፈው ቢኒያም ወርቁ ሲሆን ሰሞኑ ይሰማል አዘጋጅቶታል። ፊልሙ ሰማንያ በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆ ን ከሁለት እስከ ሶስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ለዕይታ ይበቃል ተ ብሎ ይጠበቃል።

በፍኖት አልባ አገር በጎግ ማንጉግ ምድር እግር በጣለው ወፍ፣ በጠፋው መድረሻ ምንጩን በማይለይ፣ በዐልቦ መነሻ እንዲሁ ተጸነስኩ፣ ከአለት ጋር ከተምኩ ከገደል ሣር ጋራ፣ ወዳጅነት ጀመርኩ። እንዲህ ነው የሰው ልጅ ፣ከአረም ይወለዳል በወፍ አር ተረግዞ እንደ መጋቢት ጠል ከሰማይ ይዘ ንባል። የዘሪው ግምት ነው ፤ሲገኝ ከጎዳናው፤ ሲወድቅ ከመ ሬቱ ሲቆራኝ ከጭንጫው፣ ሲጠጋ ከአለቱ ።

ሰራዊት ፍቅሬ አዲስ ፊልም ኦፊሴላዊ ፖስተር

ራሴን ቆጥቤ፤ አዋድደዋለሁ፤ ስበዛ እንደምረክስ በዕድሜዬ ስላየሁ፡፡ ናኦድ ቤተሥላሴ ሲልቨር ስፕሪንግ-ሜሪ ላንድ ጃንዋሪ 29 2011


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

13

ጥበብ

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ”

ሰሞነኛ ፊልሞች

በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

“ታላቁ ወንድም” በአፍሪካ እንዲህ ዐይነት ሽፍንፍን የሌሉባቸው ትዕይን ቶች በ42 አገራት ለየአገራቱ በሚስማማ መልኩ እየተዘጋጀ ለተመልካች መተላለፍ ከጀመረ ዓ መታት ተቆጥረዋል። “ቢግ ብራዘር” ወደ አፍሪ ካ የመጣው ከስምንት ዓመት በፊት ነበር። ፕሮ ግራሙን በተለያዩ አገራት የሚሠራው “ኤንዴሞ ል” የተሰኘው ድርጅት መቀመጫውን ደቡብ አ ፍሪካ ላይ አድርጎ ወጣት አፍሪካውያንን ማወዳ ደር ጀመረ። ውድድሩን ለሚያሸንፉም ዳጎስ ያለ ገንዘብ ይበረከት ጀመር። ተሳታፊነቱን እና አሸና ፊነቱን ተከትሎ የሚመጣው ዝናም ሌላው የፕ ሮግራሙ ማማለያ ነበር። ፕሮግራሙ ለሦስት ተከታታይ ሲዝኖች ሲተላ ለፍ ከ12 አገራት የመጡ 12 ተሳታፊዎችን ብቻ ነ

አማላዩ ተዋንያን፦ ግሩም ኤርሚያስ፣ ሃረገወይን ተሾመ፣ ቴዎድሮስ ስዩም፣ ዋሲሁን በላይ እና ሌሎችም ዳይሬክተር፦ አንተነህ ግርማ የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ፎቶ- ቢግ ብራዘር አፍሪካ

ሃኒ እና ዳኒ ይባላሉ፤ የቁልምጫ ስማቸው ነ ው። በትምህርት ቤትም መዝገብ ላይም ኾነ ፖ ስፖርታቸው ላይ የተጻፈው መጠሪያቸው ግን ሐና መኩሪያ እና ዳንኤል ካሣ በሚል ነው። ሃ ኒ የ22 ዓመት ወጣት ስትኾን ዳኒ ደግሞ 34 ዓ መቱ ነው። ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸ ው። በመላው አፍሪካ በርካቶች ወጣቶች በሚከ ታተሉት ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ ናቸው። ከተጀመረ አንድ ወር ያለፈው ይህ የቴሌቭዥ ን ፕሮግራም ከ14 አገራት የመጡ 26 ወጣቶች ን በአንድ ግቢ ያሰባሰበ ነው። ከዚህ ቀደም ፈ ጽሞ የማይተዋወቁት እነዚህ ወጣቶች ለ91 ቀና ት በአንድ ግቢ ተቆልፎባቸው እያንዳንዷን ደ ቂቃ እና ሰዓት በጋራ ለማሳለፍ የተስማሙ ናቸ ው። በሦስት ወር ቆይታቸው ከውጭው ዓለም ጋራ ምንም ዐይነት ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድ ላቸውም። ሞባይል፣ ጋዜጣ፣ ቴሌቭዥንም ኾነ ሬድዮ በአጠገባቸው የለም። በቴሌቪዥን ፕሮግ ራሙ ደንብ መሠረት ብቻቸውን እንዲኾኑ የተዘ ጋባቸው ናቸው። ብቻቸውን ቢኾኑም ሚሊዮኖች ግን አብረዋቸ ው አሉ። በሚኖሩበት ቤት የተገጠገጡት 54 ካ ሜራዎች እና 120 ማይክራፎኖች የሚሉ፣ የሚያ ደርጓትን ሳምንቱን ሙሉ፣ 24 ሰዓት ያለማቋረ ጥ ለሚልዮኖች ያስተላልፋሉ። ይህ ቢግ ብራዘ ር አፍሪካ ነው። እውነተኛ ትዕይንቶች እና ድር ጊቶች በቀጥታ የሚተላለፉበት የቴሌቭዥን ፕ ሮግራም። ከቢግ ብራዘር አፍሪካ ምንም የሚደበቅ ነገር የ ለም። ከከንፈር ለከንፈር ግጥሚያ እስከ ሻወር ቤት የራቁት ቆይታ ድረስ ሁሉም በቢግ ብራዘር ካሜራ ዐይን ውስጥ ናቸው። ማን አንድ ብርጭ ቆ መጠጥ ጠጥቶ ከ“ጨዋታ ውጭ” እንደሚኾ ን በቀጥታ መኮምኮም ይቻላል። እዚህ ምስጢ ር የለም። ናሚቢያን ወክላ በቴሌቪዥን ፕሮግ ራሙ ላይ የምትካፈለው ብሬናዲና ድንግል መ ኾኗን ስትናገር ሚልዮኖች እየሰሟት ነው። በር ግጥ የአምስተኛ ዓመት የሕግ ተማሪዋ ኢትዮጵ ያዊቷ ሃኒም ድንግል መኾኗ ቀደም ሲል ታውቋ ል። ታንዛኒያዊቷ ሎተስ ደቡብ አፍሪካዊውን ሉ ክሌይ በጥፊ ስትማታም በርካቶች የአገሯ ዜጎች በድንጋጤ ተመልክተዋል። በፕሮግራሙ ደንብ መሠረት አንድ ተሳታፊ ሐይል የተቀላቀለበት ድ ርጊት በሌላኛው ላይ ከፈጸመ ከውድድሩ በቀጥ ታ ይባረራል።

ሃኒም ኾነች ዳኒ ለጊዜው ከመባረር ቢተርፉም የ“ቢግ ብራዘር” የየዕለት ውሎዎችን ሥራዬ ብለው በሚዘግቡ ድረ ገጾችም ኾነ ጋዜጦች ያላቸው ዝና ያን ያህል መኾኑ ግን አደጋውን ቅርብ ያደርገዋል

በር የሚያካትተው። እ.ኤ.አ በ2009 የነበረው አ ራተኛው ሲዝን የአገራቱን ቁጥር በሁለት ጨም ሮ የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ 25 አሳደገ። ኢትዮ ጵያ ወደ ቢግ ብራዘር አፍሪካ የተቀላቀለችው በ ዚህኛው ሲዝን ነበር። የኢትዮጵያን ወክሎ የተ ሳተፈው ደግሞ ያዕቆብ ነበር። ያዕቆብ የቀስተ ደ መና ስፖንጅ ፋብሪካ ባለቤት የኾኑት የአቶ አቢ ሴሎም ይህደጎ ልጅ ነው። ኢትዮጵያዊ ተወካይ የሌለበት ባለፈው ዓመት ሐምሌ የተካሄደው አምስተኛው ሲዝን ከዚህ ቀ ደም በተለያዩ ሲዝኖች የተሳተፉ 14 ምርጦች የ ተሳተፉበት ነበር። የያዕቆብ ፈር ቀዳጅ ተሳትፎ ሃኒን እና ዳኒን በስድስተኛው እና “ቢግ ብራዘ ር” አምፕሊፋይድ እንዲሳተፉ አነቃቅቷቸዋል። ለዚህም ነው እስከዛሬ ከነበሩ የቢግ ብራዘር ተሳ ታፊዎች ማንን ታደንቃላችሁ ሲባሉ ሁለቱም የ ያዕቆብን ስም የሚጠሩት።

ሁለቱ ወጣቶች እነማን ናቸው? በአዲስ አበባ የተወለደችው ሃኒ እንደብዙዎቹ እንስት ኢትዮጵያውያን ራሷን ለመግለጽ የምት ቸገር ዐይነት አይደለችም። “ጨዋታ ወዳድ፣ አስ ቂኝ እና ተወዳጅ” እንደኾነች ትናገራለች። ለጓደ ኛነት የምትመች እና ለአዳዲስ ፈተናዎች ምንጊ ዜም ራሷን አዘጋጅታ የምትጠብቅ መኾኗንም አ ትደብቅም። መዝፈን የምትወደው ሃኒ ለሬጌ ሙ ዚቃ ጥልቅ ፍቅር አላት። የ“ፉጂስ” የሙዚቃ ቡ ድን አባል የነበሩትን እና በየግላቸው የተዋጣላቸ ው ዘፋኝ ለመኾን የበቁት ላውረን ሂል እና ዋይ ክሌፍ ዣን፣ የቦብ ማርሌይን ልጅ ዳሜይን ከም ትወዳቸው ዘፋኞች ይመደባሉ። ከፊልም ኮሜ ዲ፣ ከመጽሐፍ ደግሞ የዳን ብራውንን ድርሰቶ ች ትመርጣለች። አሁን ያለችበት ወቅት ስለራሷ ይበልጥ ማወቅ የምትፈልግበት እንደኾነ የምት ናገረው ሃኒ በዚህም ምክንያት በ“ቢግ ብራዘር” መወዳደር እንደፈለገች ታስረዳለች። የግሉን ሥራ እንደሚሠራ የሚናገረው ዳኒ እን ደ ሃኒ ሁሉ አላገባም። “ጀብድ ወዳድ፣ ተጨዋ ች፣ ተግባቢ፣ የሁሉ ወዳጅ እና የሚመኩበት ዐ ይነት” ሰው እንደኾነ ይናገራል። ኢ-ልቦለድ ሥ ራዎችን ማንበብ የሚያስደስተው ዳኒ ከዜና እስ

ከ መዝናኛ፣ ከስፖርት እስከ እውነተኛ ትዕይን ቶች የሚስተናገዱበት “ሾው” ድረስ ያሉ የቴሌ ቪዥን ፕሮግራሞችን መከታተል ያዘወትራል። በድርጊት የተሞሉ እና ጅብድ ቀመስ ፊልሞችን መመልከት ይወዳል። ባራክ ኦባማ፣ ኔልሰን ማ ንዴላ እና ዲያጎ ማራዶና የሚያደንቃቸው ዝነ ኛ ሰዎች ናቸው። የ“ቢግ ብራዘር” ቀረጻ የሚከናወንባት ደቡብ አፍሪካ ለዳኒ እንግዳ አይደለችም። ከዚህ ቀደም ለዓመታት በአገሪቱ ኖሯል። ወደ ደቡብ አፍሪካ ከማቅናቱ በፊት በናይሮቢ ኬንያ ለጥቂት ጊዜያ ት መቆየቱን እና ዝቅተኛ በሚባለው የሕይወት ጎዳና ሳይቀር ያለፈ እንደነበር የሚናገሩ አሉ። በ ዚህ ፈታኝ ሕይወት ውስጥ ያለፈው ዳኒ ለ“ቢግ ብራዘር” መድረክ በመመረጡ መገረሙን ተናግ ሯል። ውድድሩን ካሸነፈም በእውቅ ዲዛይነሮች የተሰፉ ልብሶች የሚሸጡበት ሱቅ በአዲስ አበባ ላይ የመክፈት የሁልጊዜም ህልሙን እውን የማ ደርግ ሐሳብ አለው።

አያያዛቸው እንዴት ነው? በ“ቢግ ብራዘር” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ደንብ መሠረት በተሳታፊዎች በራሳቸው በሚሰጥ ድ ምፅ ከመካከላቸው የተወሰኑት ከውድድሩ እን ዲወጡ በዕጩነት ያቀርቧቸዋል። በእነዚህ እን ዲወጡ በተፈረደባቸው ተሳታፊዎች ላይ ድም ፅ እንዲሰጡ ተመልካቾች ይጋበዛሉ። ተመልካቾ ች በከፍተኛ ድምፅ ይባረር ያሉት ከውድድሩ የ መሰናበት ዕጣ ይገጥመዋል። ሚያዝያ 23 ቀን 2003 ዓ.ም የተጀመረው የቴሌቭዥን ፕሮግራ ም በሳምንቱ ስድስት ዕጩ ተባራሪዎችን አቀረ በ። ኢትዮጵያዊው ዳኒ አንዱ ነበር። ድምፅ ተሰ ጠ። ፍርዱ የናሚቢያው ጆሲ ላይ ደረሰ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ደግሞ ሃኒ ዕጣው ደረሳ ት። በተባራሪ ዝርዝሮች ውስጥ ብትገባም በወቅ ቱ የተሳታፊዎቹ ቤት አለቃ በነበረው ሰው ከዝ ርዝሩ ውጭ ተደርጓል። በዙር የሚደርሰው ይ ኼ የአለቃነት ሹመት ዕጩ ተባራሪዎችን የማዳ ን ሥልጣን ያጎናጽፋል። እስከባለፈው እሁድ ግ ንቦት 28 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ከ25ቱ ተሳታ ፊዎች መካከል ስድስቱ ለቀጣይ ሁለት ወራት

ከዓለም ተገልሎ ከሚቆየው ቤት ተባረዋል። ሃ ኒ እና ዳኒን ጨምሮ ዐሥራ ዘጠኝ ተሳታፊዎች ተፋጠዋል። ሃኒም ኾነች ዳኒ ለጊዜው ከመባረር ተርፈዋ ል። የ“ቢግ ብራዘር” የየዕለት ውሎዎችን ሥራ ዬ ብለው በሚዘግቡ ድረ ገጾችም ኾነ ጋዜጦች ያላቸው ዝና ያን ያህል መኾኑ ግን አደጋውን ቅ ርብ ያደርገዋል። ከእነዚህ ድረ ገጾች አንዱ የኾነ ው ዩጋንዳ ኦንላይን ከአንባቢዎቼ ሰበሰበኩት ባ ለው ነጥብ አሰጣጥ መሠረት አንዳንድ ተሳታፊ ዎች ምንም ዐይነት ነጥብ ማስዝገብ እንዳቃታቸ ው አንዳንዶቹ ደግሞ አንድ ወይም ሁለት ፐርሰ ንት የኾነ ነጥብ ብቻ ማግኘታቸውን ጠቁሟል። ምንም ነጥብ ካለስመዘገቡት መካከል አንዱ ዳኒ ሲኾን አንድ ፐርሰንት ካስመዘገቡት መካከል ደ ግሞ ሃኒ ተቀምጣለች። አዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊው የእንግ ሊዘኛ ጋዜጣ “ፎርቹን” የሃኒን እናት ስለ ልጃቸ ው ምን እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው ነበር። የ ሃኒ እናት ወይዘሮ በላይነሽ አባተ ይባላሉ። ከል ጆቻቸው ሁሉ የመጨረሻዋ የኾነችውን የሃኒን ውሎ በየዕለቱ በዲ.ኤስ.ቲ.ቪ ቻናል 198 ይከታ ተላሉ። ወይዘሮ በላይነሽ ፕሮግራሙ የተጀመረ ዕለት በልጃቸው መሳተፍ መደሰታቸውን ቢናገ ሩም በመመረቂያ ዓመቷ ላይ የምትገኘው ሃኒ ት ምህርቷን ጨርሳ ማየቱን ይበልጥ እንደሚፈልጉ ለ“ፎርቹን” በስተኋላ ገልጸዋል። “እርሷ መደሰት እንደምትፈልግ ነው የነገረች ኝ። ለጓደኞቼም ኾነ ለዘመዶቼ አሊያም ለጎረቤ ቶቼ እየተሳተፈች እንደኾነ አልተናገርኩም” ይላ ሉ የልጃቸውን ምርጫ ያከበሩት ነገር ግን ተሳት ፎዋን ምስጢር ያደረጉት እናት። ፕሮግራሙን ሲከታተሉ ምን እንደሚሰማቸውም ለጋዜጣው ሳይደብቁ ተናግረዋል። “የሚነጋገሩበትን ቋንቋ አላውቀውም። የሚተረጉምልኝም የለም። ነገር ግን ሌሎቹ ሴቶች በተደጋጋሚ ሃና እያሉ ሲያወ ሩ እሰማቸዋለሁ። እርሷን እያሙ እንደኾነ ስለም ረዳ ለልጄ እሰጋላታለሁ። ምክንያቱም አግኝቼ ምክር ልሰጣት አልችልምና። ምን እንደሚሏት ስታውቅ እንድትጎዳብኝ አልፈልግም” ይላሉ።

ሁለት ወጣት ድምጻውያን አዲስ አልበሞቻቸውን አወጡ

ሚኪያስ ቸርነት

ፎቶ- ንግስት መጽሔት

አቤል ሙሉጌታ

ፎቶ- ላይፍ መጽሔት

ህግ ወጥ መንገድ እየተባዙ ገበያ ላይ በሚውሉ ዘፈኖች ምክንያት መቀዛቀዝ ለሚታይበት የኢት ዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ማነቃቂያ የሚሆኑ ሁለት አልበሞች ከሰሞኑ ገበያ ላይ ውለዋል። የ ሁለቱም አልበሞች ባለቤቶች ወጣቶች ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በሰሯቸው ነጠላ ዜማዎች ይታወቃ ሉ። ድምጻውያኖቹ “ነይ ማታ ማታ” እና “ነይ ሳሚኛ” በተሰኙት ዘፈኖቹ ይበልጥ የሚታወቀው አቤል ሙ ሉጌታ እና “የኔ ድሃ” እና “ዽሬ ድሬ” በተባሉት ነጠላ ዜማዎቹ ህዝብ ጆሮ የገባው ሚኪያስ ቸርነት ናቸው። አቤል ሰሞኑን ያወጣው አልበም “ተገርሜ” የሚል ስያሜ የሰጠው ሲሆን አስራ ሁለት አዳዲስ ዘፈኖችን ይዟል። ከአንድ ዘፈኑ በስተቀር የሁሉኑም ዘፈኖች ግጥም እና ዜማ የደረሰው ራሱ ነው። የሙዚቃ ቅንብሩ ን ግን በአራት ሰዎች አሰርቷል። አስቻለው ዲሮ እና ሚካኤል ኃይሉ አስር ዘፈኖች ሲያቀናብሩ ታዋቂው ኤ ልያስ መልካ አንድ ኪሩቤል ተስፋዬ ደግሞ ቀሪውን ሰርተውታል። የሙዚቃ ቅንብሩ እንደ አብዛኞቹ የዘመ ኑ ዘፈኖች በኪቦርድ ተጀምሮ በኪቦርድ መጨረሱን ያልወደደ የመሰለው አቤል ሊድ ጊታር፣ ሳክስ፣ ማሲን ቆ ተጨዋቾችን በአልበሙ አካትቷል። “ተገርሜ” ለአቤል ሁለተኛ አልበሙ ነው። የአልበሙን መጠሪያ “ሰላም አላት” ሲል የሰየመው ሚኪያስ እንደ አቤል ሁሉ አስራ ሁለት ዘፈኖችን ይዞ መጥቷል። ግሩም ታምራት፣ መላኩ ጥላሁን፣ ኤሊያስ አሰፋ እና ድምጻዊ ቴዎድሮስ ሞሲሳ በግጥም ደራሲነ ት ተሳትፈዋል። የሙዚቃ ቅንብር እና ሚኪሲንጉን የወሰደው መሀመድ ኑር ሁሴን ነው። በቮካል ሪከርድስ አማካኝነት ለገበያ የዋለው ይህ አልበም ሚኪያስን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቁትን “የኔ ድሃ” እና “ዽሬ ድሬ”ን አካትቷል። አልበሙ በፍቅር ዘፈኖች የተሞላ ነው።

ይህ ፊልም ሳምሶን ስለሚባል እና ሴቶችን የማማለል ብቃቱ ከፍተኛ እንደሆነ ስለሚነገረለት ወጣት የሚተረክ ነው። ሳምሶን ከኢትዮጵያ ውጭ በነበረበት ወቅት የተመኛትን ሴት እንደልቡ የሚያገኝ ነበር። ወደ ሀገር ቤት ሲመለስም ተመሳሳይ አቀባበል ነበር የጠበቀው። የሀገሩ ሴቶች በቀላሉ የማይበገሩ መሆናቸውን ከጓደኛው ቢያደምጥም መቀበል አልፈለገም። በእርግጥም ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ያሰበውን አሳካ። በራሱ ድርጅት ውስጥ በህግ ባለሙያነት ተቀጥራ ከምትሰራው ማህደር ዘንድ ሲደርስ ግን እንደለመደው አልሆነም። የጓደኞቹን ተረብ መቋቋም ያቃተው ሳምሶን ማህደርን ሊያንበረክክ በአምስት ሺህ ብር ተወራረደ። ከዚያስ…? መልሱን ከፊልሙ ለማግኘት በቪሲዲ እና በዲቪዲ እስኪወጣ መጠበቅ ነው።

ፔንዱለም ተዋንያን፦ እጸህይወት አበበ፣ አማኑኤል ይልማ፣ ረቂቅ ተሾመ፣ መስፍን ኃይለእየሱስ፣ ሚካኤል ሚሊዮን እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ሄኖክ አየለ የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ግሩም የተሰኘ ወጣት የፋሽን ዲዛይነር በአንዲት ሞዴል ፍቅር ይወድቃል።። ያፈቀራት ልጅ ለማግኘት ወደ መኖሪያ ህንጻዋ ሲሄድ ከእርሷ ስመ ሞክሼ ጋር ይተዋወቃል። በሙያዋ አርክቴክት የሆነችው ይህቺ እንስት ደግሞ ቀስ በቀስ ግሩምን ትወደዋለች። ፊልሙ እንዲህ በሶስትዮሽ ስለተሰናሰለው የፍቅር ሁኔታ የሚተርክ ይሆናል። ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ በዚህ ፊልም ላይ ግሩምን ሆኖ ይጫወታል። በወንዶች ጉዳይ ፊልማቸው ዕውቅና ያተረፉት ረቂቅ፣ መስፍን እና ሚካኤል በዚህ ፊልም ላይ ሳቅ ለማጫር ተጣምረዋል።

ኤፍ.ቢ.አይ ተዋንያን፦ ነጻነት ወርቅነህ፣ ቤተልሄም ደምሴ፣ ህይወት አበበ፣ ግርማ ታደሰ እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ነጻነት ወርቅነህ የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ

ኤፍ.ቢ.አይ የሚባል የግል ድርጅት አለ። ኤፍሬም (ነጻነት ወርቅነህ) የድርጅቱ ቁልፍ ሰው ነው። የማይሰራው የ “ቢዝነስ” ዓይነት የለም። የሞባይል ካርድ ከመሸጥ ጀምሮ የጠፋ ውሻ እስከ ከማፈላለግ ድረስ ይሰራል። በ“ቢዝነሱ” እንዲጠቀሙ ሴቶችን “ያበረታታል”። አግልግሎት እየሰጠ ሞባይል ቁጥራቸውን መቀበሉን አይረሳም። እንዲህ አንዲህ እያለ በርካታ ሴቶችን ይተዋወቃል። ከአንዲት እንስት ጋር የነበረው ትውውቅ ግን ጣጣ ያመጣበታል። አፍሬም ከጣጣው እየሸሸ የእንስቱን ጓደኝነት የሚያጠብቅበት አካሄድ ካልተለመደው የ“ቢዝነሱ” አሰራር ጋር ተመልካችን ለሳቅ ይጋብዛሉ።


ሀበሻዊ ቃና

14

ትረካ

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

እንዲህም ይፈቀራል እሙ

ድሬ “Number One” በፍቅር ድብን ብዬ የ ሰከርኩባት መንደር ብቻ አይደለችም፤ የልጅነ ት ቡረቃዬን በመንደሩ ሰዎች አጀብ እና ልዩ ቤ ተሰባዊ ፍቅር ያጣጠምኩባት ሰፈሬ ነች፡፡ እንደ እኔ ደስተኛ ማን ነበር?! ሕይወት እንዴት እንደ ምትጣፍጥ ለማሳየት ከኔ በላይ ምስክር ያለ አይ መስለኝም፡፡ ባለ ክንፍ ሕጻን ነበርኩ፤ አዎ የም በር እንጂ የምራመድ አልመስልም ነበር፡፡ የረገ ጥኩት ሁሉ ያነጥረኝ ይመስል ከፍልቅልቅ ፈገግ ታ ጋር ጉዞዬ ከአንዱ እቅፍ ወደ ሌላው እቅፍ የ ታጀበ ነበር፡፡ Y Y Y ትንሿ “እሙ” የሠፈሩ ፈርጥ የኾነች ያህል እ ንዲህ እንደፈነጠዘች፣ ከአንዱ እቅፍ ወደ አንዱ እቅፍ እንደተሸጋገረች 16ኛውን የልደት ሻማ “እ ፍ” አለች፡፡ የፍቅር ዘመን እንዴት አጭር ነው ‘ባካችሁ! የ17ኛው ጉዞ ታዲያ እንዲህ በብዙ መታቀፍን፣ በብዙ ጉያዎች መሸጎጥን ያስከተለ እንዳይመስላ ችሁ፡፡ የያኔው የ“እሙ” ዘመን’ኮ የልጅነት ወዟ ን እና ጠረኗን ለማየት እና ለመካፈል በሚሹ ቤ ተሰባዊ ፍቅር ባነወዛቸው ወዳጆች የደመቀ ነበ ር፡፡ ብዙሃን ለአንዲት የሰፈሩ ትንሽ “ጣዖት” ያ ላቸው ፍቅር በሉት፡፡ 17ኛው የእመቤት ዘመን ግን አንድ ትንፋሽን የሚናፍቅ ነበር፡፡ በአንድ ት ከሻ ላይ መንተራስን፤ መሳ’ምን ብቻ ሳይኾን መ ሳምን የሚሻ ነበር፡፡ Y Y Y

እሙ

ድንገት እድግ አልኩኛ! እናም በፍቅር ክንፍ አ ልኩ-ከአቤልዬ ጋር! ከብዙ እቅፍ ወደ አንድ እ ቅፍ-ግን የሚነዝር እቅፍ፡፡ እንዴት ያለ የሚጣ ፍጥ ፍቅር ነበር?! አሁንም በፍቅር ክንፍ አወጣ ሁ፡፡ እናም እንደ ትንሿ “እሙ” ክንፍ አልኩ፡፡ የድሬዋ ትንሽ መንደር “Number One” ጥብ ብ አለችኝ፡፡ በወቅቱ አቤል በአሥር አመት የ ሚበልጠኝ መልከ መልካም ነበር፡፡ በቃ “የእኔ ጌታ” ብዬ ስጠራው ብውል የማልጠግበው ለ ግላጋ ወጣት፡፡ አቤል ኤርትራዊ ነው፡፡ ለወሬው ነው እንጂ የ ዜግነት ጉዳዩን ማንሳቴ፤ “ማፍቀርም መፈቅርም የሚችል ሰው” የሚለውን ስያሜ ብሰጠው በቀ ለለኝ ነበር፡፡ በርግጥ ለእኔ ከሁሉም በላይ አቤል ብቻ መኾኑ በቂ ነበር፡፡ ሲበዛ አፈቀረኝ፤ ትንሿ ልቤ የዘወትር ሥራዋን ታቆም ይመስል ትርታዋ ን በእጥፍ እንደጨመረች የእኔንም የፍቅር ብር ታት ገለጸችልኝ፡፡ አዬ የልጅነት ነገር፣ ዓለም ሁ ሉ ቢደመር አንድ አቤልን የሚሠራ አይመስለኝ ም ነበር፡፡ አንዳንዴ የፍቅር ድራማ በቴሌቪዠ ኑ መስኮት ስመለከት የኾነ ነገር የጎደለው ይመስ ለኛል፡፡ አዎ አቤል! እንዴ ከምሬ’ኮ ነው፡፡ አቤ ል የሌለበት የፍቅር ታሪክ የባዶ ገረወይና ጩኸ ት ይመስለኛል፡፡ አቤል ለእኔ ሙሉ ነበር፡፡ ግን ደግሞ አልጠግበውም፡፡ ፍቅር ስስት ነው ለካ! በሙሉ መዳፍ የሚፈልጉ ትን አስገብቶም ያለመርካት፡፡ በእጁ ያለውን መ ጨዋቻ ላለማጣት ከሌላ ሰው እጅ ያለውን እን ደሚሻ ሕጻን መኾን፡፡ አቤልን አቅፌ በሙሉ እ ጄ የያዝኩት ያህል አይሰማኝም ነበር፡፡ ከደረቱ

ተለጥፌም ጥሎኝ የሚበር ያህል ጥፍሬ እንደ ምስ ማር አካሉን ዘልቀው ሊገቡ ምንም አይቀራቸው ነበ ር፡፡ የትንፋሹ ግለት ነፍሴን እንዳሞቃት ቀኑ መሽቶ ይነጋ ነበር፡፡ ሁሌ የሚቆጨን ነገር “አፈቅርሃለሁ” የ ሚለው ቃል ከእሱ የአፍታ እቅፍ የማገኘውን እርካ ታ ያህል እንኳ ሚዛን ላይ ሳስቀምጠው የልቤን አ ለማድረሱ ነው፡፡

ጦርነት እና ፍቅር ቀደም ሲል አቤል ኤርትራዊ ነው አይደል ያልኩ ት!? ይህ ለእኔ ምን ስሜት ነበረው? ምንም፡፡ የእኔ አይደል ከየትም ቢኾን፡፡ ይህ ስሜት ግን ከእኔ ምስ ኪኗ ግለሰብ አልፎ ለሌሎች ምንም አይደለም፡፡ በ ተለይ ደግሞ ለመንግስታት፡፡ በተለይ. . . በተለይ . . . በተለይ. . . ደግሞ ለሻቢያ እና ለወያኔ፡፡ የሁለቱ አገር ጉዳይ እንግዲህ ትልቁን ጦርነት ወለ ደ፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ሕይወት ቀጥ ፎ አለፈ፡፡ ዛሬም ድረስ የማይሽር ጠባሳ ደግሞ በእ ኔ የፍቅር ሕይወት ላይ ጥሎ አለፈ፡፡ “የአይነ ውሃቸ ው ያላማረ” ሁሉ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ማማር ብቻ ሳይኾን የፍቅር ጨረር የሚያንጸባርቁ መኾናቸውን ሚልዮን ጊዜ የምመሰክርለት አቤልም “አይኑ አላማ ራቸውም” መሠል ከአገር እንዲወጣ ተገደደ፡፡ ቀድ ሞ የመንግስትን አዝማሚያ የተገነዘቡት ዘመዶቹ በ ሞያሌ በኩል የኬንያን ድንበር እንዲሻገር አደረጉ፡፡ ናይሮቢ በሠላም መድረሱን መስማቴ በጎ ቢኾንም ለእኔ ግን ዓለም ጨለመች፡፡ የፍቅር ከዋክብት ረ ግፈው ሰማዩ ጥላቻን የሚያንጸባርቅ መሰለኝ፡፡ ዘ ወትር “ጌታዬ” የምለውን ፍቅሬን ከእኔ ነጠቁ፡፡ ሁ ሉን ነገር ጠላሁ፡፡ ያለ ፍቅር መኖር ማለት ያለው ን ባዶ ስሜት ተከናነብኩት፡፡ መብላት መጠጣት ያለፍቅር ሲኾኑ ምን ያህል አስጨናቂ እንደኾኑ ያ ንጊዜ አየሁ፡፡ አምስት ዓመታት ያህል “በልምጣ አትምጪ” ትግ ል ቆየሁ፡፡ አቤል ከእኔ ቢርቅም ለእኔ ያለውን ፍቅ ር ዘወትር ሳይገልጽ አድሮ አያውቅም ነበር፡፡ ዘመዶ ቹ ድጎማ ብለው ከሚልኩለትም እየቆነጠረ እኔን ለ ማስደሰት መላኩ አልቀረም ነበር፡፡ ነገር ግን “ወደ አ ንተ መጥቼ አብረን እንኑር” የሚለው ጥያቄ ዘወት ር አይቀበለውም ነበር፡፡ “ለአንቺ አ ይመችም፣ ያለ ሥራ መቀመጥ መቆ መጥ ነው” ዓይነት ምክንያት ነበር የ ሚሰጠኝ፡፡ ለእኔ ግን ከአቤል ጋር ኾኜ ውሃ እ ና መብል መቼ ይታየኝና! እናም ሦ ስት ዓመታት ያህል “አብረን እንኑር” ከሚለው ኃሳቤ ጋር ከታገልኩ በኋላ ጥያቄውን ችላ ብዬ በልቤ ውስጥ ያለ ውን ፍቅር ብቻ ማብሰልሰል ጀመር ኩ፡፡ አቤልም ዘወትር መደወሉን አ ላቆመም፡፡ ይህ ለእኔ ትልቅ ደስታ ነ በር፡፡ ርቀቱን የሚያቀርብልኝ በየም ሽቱ የምሰማው የፍቅር ትረካው ነበ ር፡፡ ያዜምልኛል ማለት ሳይቀል አይ ቀርም፡፡ ፍቅር ለካ እያደር እየጨመረ ይሄዳ ል! በቃ “ውድድድ” አደረኩት፡፡ እያ ደር ፍቅርቅርቅር . . . እነሱ በጦርነት እኛን ለያዩ ደግሞም አገር አፈረሱ፣ እ ኛ ደግሞ በቃላት እያደር ፍቅር እን ገነባለን፡፡

በናይሮቢ ሰማይ ሥር

ከተለያየን አምስተኛው ዓመት አካባቢ መቼም አ ስበውኝ የማያውቁት የአቤል ዘመዶች አልፎ አልፎ መደወል ጀመሩ፡፡ በተለይ ካናዳ የምትገኘው ታላ ቅ እህቱ አልፎ አልፎ ገንዘብ ትልክልኝ ጀመር፡፡ስ ትደውልም አቤል ጋር መሄዴን እንደምትሻ ሳትገል ፅልኝ አታልፍም ነበር፡፡ በካናዳ “ፕሮሰስ” ውስጥ እ ኔን አግብቶ የሚሄድበት ኹኔታ እንደሚኖርም ትገ ልጽልኝ ያዘች፡፡ ‹‹አቤል ስለእኔ እየደጋገመ ነግሯታ ል ማለት ነው›› አልኩ፡፡ ‹‹አቤል ናፍቆቴን መሸከም አቅቶታል ማለት ነው›› ብየ ትራስ አቅፌ አነባሁ፡፡ የኔው ሳያንስ እሱም በሰው ሃገር በፍቅሬ እየተሰቃ የ መሆኑን ሳስብ ክንፍ አውጥቶ መብረር አማረኝ፡ ፡ ዘወትር የድኻዋ እናቴ ጉዳይ ቢያሳስበኝም ከካና ዳው ጉዞው ይልቅ አቤልን ማግኜቴ ትልቁ ድል ሆ ኖ ተሰማኝ፡፡ ‹‹አቤል የኔ ተስፋ ሩቅ ሀገር ያለኸው በርሬ ልምጣና ትንፋሽህን ልማገው›› እያልኩ አን ጎራጎርኩ፡፡ ‹‹ከቀይባህር ማዶ ያገኘሁህ ቆንጆ ውሰድና አኑረኝ በትንሿ ጎጆ›› ብየ ምኞቴን በዜማ ለወፏ ተናገርኩ፡፡

እንጉርጉሮየን የሰማች ወፍ ሄዳ ነገረችው መሰል አ ቤልም እኔን ለመቀበል ዝግጁ መኾኑን ነገረኝ፡፡በ’ቅ ፉ የገባሁ ያክል በጣም ተደሰትኩ፡፡ በቃ አዲስ ሕ ይወት አዲስ ፍቅር በናይሮቢ ሰማይ ሥር፡፡ ዘወትር ታዛዡ ኾኜ ለማገልገል የምሻውን ፍቅሬን ማግኘቴ ልዩ ደስታ ነበር ያጎናጸፈኝ፡፡ ወዳጅ ዘመድ በወጉ ስ ለመሰናበቴ የማስታውሰው ነገር የለም፡፡ ማቄን ጨርቄን ሳልል ከነፍኩ- ወደ ናይሮቢ፡፡ አቤ ልን ለማየትና በፍቅር እንደገና ለመክነፍ፡፡ ጆሞኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ደረ ስኩ፡፡ ከአውሮፕላኑ እየወጣሁ አቤል እንዴት እየ ጠበቀኝ እንደሆን መሳል ጀመርኩ፡፡ በእቅፉ የያዘ ው አበባ፤ አበባውን ያቀፈባቸው ለዓመታት የናፈቁ ኝ ክንዶቹ፤ በሰው መካከል ሁሉ ነግሶ የሚታየኝ ግ ርማ ሞገሱ፤ ሁሉም ከደቂቃዎች በኋላ የእኔ መሆና ቸውን እያሰብኩ ዳግም ፈነደቅሁ፡፡ ከአውሮፕላን

‹‹አቤል የኔ ተስፋ ሩቅ ሀገር ያለኸው በርሬ ልምጣና ትንፋሽህን ልማገው›› ‹‹ከቀይባህር ማዶ ያገኘሁህ ቆንጆ ውሰድና አኑረኝ በትንሿ ጎጆ››

ናፍቆት ኢንተርኔት ካፌ ከምርጥ የኢትዮጵያ ቡና እና ማኪያቶ ጋር -ፈጣን ኮኔክሽን - ፎቶ ኮፒ - የሕትመት አገልግሎት - ስካኒንግ አድራሻ፦ ካሳንጋ/ ጋባ መንገድ ከጆን ሱፐር ማርኬት አጠገብ

ማረፊያው ወጥቼ አይኖቼ አቤል ላይ እንዲያርፉ በ ግራና በቀኝ ላክኋቸው፡፡ አይኖቼ በሁሉም አቅጣ ጫ ተንከራተቱ፡፡ እንዳሰብኩት ግን አቤል ላይ ማ ረፍ አልቻሉም፡፡ አቤል ሊቀበለኝ አልመጣም፡፡ ጓደኞቹን ልኮ ኖሮ እኔነቴን አረጋግጠው ጓዜን ተቀበሉኝ፡፡ ለምን እር ሱ እንዳልተገኘ መጠየቄ አልቀረም፡፡ “ትንሽ አመም አድርጎት ነው” የሚል ምላሽ ብቻ አገኘሁ፡፡ ቅር አ ላለኝም፡፡ እንዲያውም ምን ኾኖ ይኾን ስል ስጋት ገ ባኝ፡፡ ጉጉቴ አሁንም ጨምሯል፡፡ ልክ እንደተገናኘ ን በመንፈስ ሀይል ከደዌው እንደተፈወሰው ሰው ከ አልጋው ዘሎ ላየ ላይ ሲጠመጠም፤ ለህመሙ መ ድሃኒት ስሆን፤ እኔም ለዓመታት ከቆየሁበት የናፍ ቆት እስርቤት ስፈታ እያለምኩ ጉዞየም የልብ ትር ታየም ፈጠነ፡፡ ናይሮቢ የጠበቅኳትን ያህል በትላልቅ ሕንዎችና ውብ ሠፈሮች አልተቀበለችኝም፡፡ ይልቁንም አቧራ መንገዶች እና ወከባ የበዛባቸው ተራ መንደሮች፡፡ ቀጥታ ብዙ ሐበሻ ወደሚኖርበት “ቻይሮድ” ነበር ያ መራነው፡፡ የማየው ነገር ሁሉ ባይማርከኝም፣ ጉጉ ቴ አቤልን በማየት ላይ ነበርና ሁሉን ዋጥ አድርጌ በ ዝምታ እርሱ ካለበት “ቻይሮድ” ደረስን፡፡ አቤል አንድ ክፍል ውስጥ አልጋ ላይ ጥቅልል ብሎ ተኝቶ አገኘሁት፡፡ ደነገጥሁ፡፡የኔው አቤል እንዲህ አይደለም፡፡ የኔው አቤል ከአልጋ ይልቅ ሳር የሞላበ ት ሜዳ እጅጉን ይመቸዋል፡፡ እኔ ደግሞ ከለምለሙ ሜዳ ይልቅ ሰፊው ደረቱ ላይ ፈልሸሽ ብሎ መተኛ ት እስከ ዓለም ፍጻሜ ደረስ ለእኔ ተብሎ የተቀመጠ ውን ደስታ ሁሉ በአንድ ጊዜ ይሰጠኛል፡፡ ለእኔ የአ ቤል ደረት ከስፕሪንግ ፍራሽ ምቾት ጋር ሊነጻጸር ቀ ርቶ ከእግሩ ጫፍም አይደርስም፡፡ አሁን ፊት ለፊት የማየው ደረት ግን ይህ አይደለም፡፡ በእንባ በተጋረደ ዓይኔ እያሁት በትዝታ የኋልዮሽ ተጓዝኩ፡፡ ያኔ ዘመኔን እንዳዲስ በጀመርኩበት በፍ ቅራችን ዘመን “እሙ” ብሎ ሲጠራኝ “ወየ ጌታየ” ብ የ ዞር ስል የናፍቆት ህመም በሚፈውስው ፈገግታ ው ውስጥ የበረዶ ያህል ነጽተው የሚያጓጉኝ ጥርሶ ች በህሊናየ ተመላለሱ፡፡ አሁን እነርሱ የሉም፡፡ ሙ ቀቱ በዶሮ እቅፍ እንዳለ እንቁላል፣ የሚ መቸው ትንፋሹ የሚጣደፍ መንገደኛ መ ስሏል፡፡ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩ ም፡፡ አልጋውን ተደግፌ ተንሰቀሰቅሁ፡፡ እጅጉን አዘንኩ፡፡ የእንባየ ዘለላዎች ሀዘኔ ን ብቻ ሳይሆን የመጣሁበትን ምክንያት ም አውጥተው ነገሩኝ፡፡ ለካ የአቤል ቤተ ሰቦች ነገሮችን ሁሉ ቶሎ ቶሎ ያጣድፉ የ ነበሩት እርሱን እንዳስታምምላቸው እን ጂ ለፍቅራችን አስበው አልነበረም፡፡ በድ ርጊታቸው ብበሳጭም አቤልን ማግኘቴ ለእኔ ትልቅ ደስታ ነበር እና ስለፍቅር ሁ ሉን ቻልኩት፡፡

አራት የጭለማ አመታት እንግዲህ የ”ቻይሮድ”ን ኑሮ “ሀ” ብዬ አቤልን በማስታመም ጀመርኩ፡፡ በየቀ ኑ ሐኪም ዘንድ ማመላለሱ የእኔ ብቻ ስ ራ ኾነ፡፡ ከእኔ ውጪ አጠገቡ ሰው አ ልነበረም፡፡ ጊዜ እየገፋ ሲሄድ ሰዎች ዘወትር ሲያሽ ሟጥጡ እና ለእኔ ከንፈራቸውን ሲመጡ እመለከት ጀመር፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ሆኖ ነ

ገሩ ለእኔ ባይገባኝም መናደዴ አልቀረም፡፡ የኋላ የኋላ ግን መርዶውን ራሴ አረጋገጥኩ ‐ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ እንደሚገኝ፡፡ ይህ ለእኔ ትልቁ መርዶ ነበር፡፡ ቢኾንም ተስፋ አልቆ ረጥኩም፡፡ አሁንም አቤል ለእኔ የፍቅር ምሳሌ ነ ው፡፡ ሀገሬን በፍቅሩ የለወጥኩበት፡፡ ድሃ እናቴ ን የተካሁበት፡፡ መሞትን ሳይሆን ዘላለማዊነት ን የተማርኩበት ነው፡፡ እናም ከጎኑም መሬትም እየተኛሁ አራት አመታትን አብረን አሳለፍን፡፡ አሰገራሚው ነገር የሰው መጠቋቆሚያ መኾኔ ነ ው፡፡ ብዙዎች ከእሱ ጋር አንሶላ የምንጋፈፍ ይ መስላቸዋል፣ እናም ሕመምተኛ፡፡ አቤል ስህተ ት ሰርቶ ለሕመሙ ቢዳረግም ለእኔ ግን እጅጉ ን ይጠነቀቅ ነበር፡፡ አራት አመት ሙሉ ስንኖር አንድም ቀን ሰዎች ያሰቡትን አልፈጸምንም፡፡ ይ ልቁንም የሰዉን አፍ ችዬ ለፍቅር ታማኝ ኾኜ ማ ስታመሜን ቀጥያለሁ፡፡ የጉድ ቀን ቶሎ አይመሽም እንደሚባለው የካና ዳውም ፕሮሰስ ሳይሳካ ቀረ፡፡ እንግዲህ የእኔ ሕ ይወትም ለፍቅር መቅለጥ ኾኖ ድኻ እናቴን አን ድ ቀን ሳልረዳ እያልኩ በሃሳብ ማዕበል እዋልላ ለሁ፡፡ ስለራሴ የኑሮ ለውጥም ማሰቤን አልተው ኩም፡፡ ብዙ አሰልቺ ነገሮች ውስጥ ኾኜም ቢኾ ን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የኑሮ ነገ እና የፍቅር ፈተና አቤልም ይሄ የኑሮ ለውጥ መሻቴ የገባው ይመ ስል አዲስ አመል አመጣ፡፡ ዘወትር እርሱን ት ቼ፤ ሌላ ሰው አግብቼ፤ ለተሻለ ኑሮ ወደ ሌላ አገ ር እንድሄድ ይገፋፋኝ ጀመር፡፡ ነጋ ጠባ ይወተ ውተኛል፡፡ በርግጥ ይህ ግፊት ከእርሱ ዘንድ የበ ረታ ይኹን እንጂ በቅርብም በርቀትም ያሉ ወዳ ጅ ዘመዶች የእለት ተግባር ነበር፡፡ አቤል ሌላ ሰው በ“ፕሮሰስ” አግብቼ ወደ ው ጭ አገር መሄድ እንዳለብኝ ግትር አቋም ያዘ፡፡ ከዚህ በኋላ እኔም ልቤ ለሁለት ይከፈል ጀመር፡ ፡ ቢያንስ የፍቅር ሕይወቴ የተዋጣለት ባይኾን እንኳን ስለ ነገው ኑሮዬ ማሰብ እንዳለብኝ ህሊ ናዬ ይሞግተኝ ጀመር፡፡ ፈተናው ለአእምሮዬ ከ ምችለው በላይ ነበር፡፡ ግን መወሰን ነበረብኝ፡፡ እናም በመጨረሻ ወሰንኩና አንድ ፕሮሰሱ የተ ጠናቀቀለት ሰው አግኝቼ የቀለበት ሥነ ስርዓት ለማድረግ ተገደድኩ፡፡ በመጀመርያ ገንዘብ ልከ ፍለው ነበር የተስማማነው። ነገር ግን በጊዜ ሂደ ት “ተላመድንና” ክፍያው ቀርቶ በወዳጅነት ተ ጠናቀቀ፡፡ እግዜር ይመስገን የውጭ ጉዞዬም ከ ጫፍ ደረሰልኝ፡፡ ነገሮች እንዲህ ቢሄዱም ሙሉ ደስታ አልነበረኝም፡፡ በ“ፕሮሰሱ” ምክንያት የተ ለየሁት አቤል ጥሩ ነገር አልተሰማውም ነበር፡፡ ከእለት እለት ህመሙ እየባሰበት ከአልጋ የሚነ ሳበት ቀናት እየመነመኑ መጡ፡፡ የእኔ ከእርሱ ዘ ንድ መራቅ ህመሙን እንዳባሰበት አልክድም፡፡ በመጨረሻም እኔ ወደ ሶስተኛ አገር ለመሻገር በማኮበኩብበት ወቅት አቤል በሞት ተለየኝ፡፡ ሞቱ የፈጠረብኝን መረራ ሐዘን በምን ቋንቋ መ ግለጽ እንደምችል አላውቅም፡፡ ልቤ ክፉኛ ተሰ በረ። እንባዬ ተዥጎደጎደ። ሁሉ ነገር አስጠላኝ። ከአቤል ጋር በነበረኝ ፍቅር አልቆጭም። በሚ ገባ አፍቅሬዋለሁ፡፡ ለፍቅርም የሚከፈለውን ያ ህል ከፍያለሁ፡፡ “ጌታ ሆይ ነፍሱን በገነት ተቀበላት”።

በቅርብ ቀን


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ወንጀለኛ ታሪክ››

በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

2010 ዓ.ም በበለፀገችው እና በታላቂቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳች አስደንጋጭ ዜና ተሰማ፡፡ የልማትና የትራንስፎርሜ ሽኑ እቅድ እውን ሆኖ ሕዝቡ በታላቅ ተድላ በሚኖርበት፣ ድህነት ተረት በሆነበት፣ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ እንደ ል ቧ መጠቀም በጀመረችበት በዚያ ዓመት አንድ ግለሰብ ድሃ ሆኖ መገኘቱ የኢትዮጵያውያንን አንገት ያሰበረ አሳዛኝና አሳፋሪ አጋጣሚ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የምንጨዋወተው 2010 ዓ.ም ላይ ቆመን ይሆናል፡፡ አንድ ደሃ በኅብረተሰቡ ድጋፍና በፖሊስ ያላሰለሰ ጥረት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ‹‹ድሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል ፈፀመ›› ተብሎም ሕ ግ ፊት ቀረበ፡፡ የወቅቱ የፕሬስ ነፃነት የወለዳቸው፣ በሚሊዮን ኮፒ የሚሸጡት ጋዜጦችና መጽሔቶች ዜናውን በፊት ገፆቻቸው ይዘውት ወጡ ፡፡ አንድ፡- ድህነትን ተረት ባደረግንበት በዚህ ጊዜ አንድ ድሃ ሆኖ የተገኘ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ሁለት፡- ድሃ ሆኖ በመገኘት ያገራችንን መልካም ገፅታ ያጠፋው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፤ ሦስት፡- ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ያወጣነውን ‹የትራንስፎርሜሽን› እቅድ በቸልታ በመመልከት እስከ ድህነቱ የዘለቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ! ወንጀሉም ከአገር ክህደት የማይተናነስ ትልቅ ወንጀል ነው ተባለ፡፡ እነዚህ ዘገባዎች በወጡ በሳምንቱ የወንጀለኛውን የሕይወት ታሪክ የያዘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ወንጀለኛው አንገቱን በታላቅ እፍረት ወደ ምድር ሰብሮ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ ታየ፡፡ ርእሱ፣ ‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ወንጀለኛ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ›› ይላል፡፡ እነሆ ከመጽሐፉ የተቀነጨበ ታሪክ፤ ‹‹ስሜ ሙሉነህ ይባላል፡፡ ተወልጄ ያደኩት በቀድሞው ቅጠል ሰፈ ፖሊሶች ነበሩ፡፡ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ፡፡ ሦስት ከረቫት ያሰሩ ዘናጭ ር በአሁኑ ኢንቨስተር ሰፈር ነው፡፡ ለረዥም ዓመታት ከድህነቴ ጋር ፖሊሶችና ድንበር የሚጋራኝ ጎረቤቴ ወደ ቤቴ ዘልቀው ገቡ፡፡ በላዬ ተስማምቼ የኖርኩት በዚህ የበለፀጉ ግለሰቦች በሚጠሩበት ስም ተ ላይ ያለቀ ግልገል ሱሪ እንደለበስኩ፣ ከወገብ በላይ ራቁቴን እንደሆ ከልዬ ነው፡፡ ‹‹ሙሉነህ›› ተብዬ ያልሞላ ኑሮ መኖሬ ብቻ ሳይሆን ድ ንኩ ፈዝዤ ቀረሁ፡፡ ሃ ሆኜ መገኘቴ ወንጀል መሆኑን አምኛለሁ፡፡ ለረዥም ዓመታት ደ የሠራሁትን ወንጀል አላወቅሁም ነበርና፣ ‹‹ምነው ምን አደረግኩ?›› ሃ ሆኖ የመኖር ወንጀልን ስፈፅም የኖርኩት የሞላለት ሐብታም በመ አልኩ፤ ‹‹ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል በመፈፀምህ በቁጥጥር ስር ውለ ምሰል ነው፡፡ ነጋ ጠባ ተመስገን ስል የአካባቢያችን ነዋሪዎች ቢሞላለ ሃል!›› አለኝ አንዱ ፖሊስ፡፡ ቅድም ሳማርር ጎረቤቴ ሰምቶኛል ማለ ት ነው ፈጣሪውን የሚያመሰግነው ብለው በቸልታ ያልፉኝ ነበር፡፡›› ት ነው፡፡ ‹‹እሺ›› ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ የድህነት አከርካሪ በማያዳግ ‹‹አንድ ቀን፤ ንጋት ለፀሐይ ቦታዋን ልልቀቅ አልልቀቅ ብላ በምትሟ ም መልኩ በተመታበት በዚህ ዘመን እኔ ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ ገትበት ማለዳ ከቤቴ ወጥቼ የሚያማምሩ የመኖሪያ ህንፃዎች በተገነ መኖሬ ታላቅ ወንጀል ነውና ጥፋቴን አምኜ ለፖሊሶች ቃሌን ሰጠ ቡበት በኢንቨስተር ሰፈር መሃል በመሄድ ላይ ነኝ፡፡ ራትም ሆነ ቁር ሁ፡፡ መጀመሪያ ፍርድ ቤት የቆምኩ ዕለት እንዲህ ሲል ነበር ጎረቤ ስ አልበላሁም፡፡ በባዶ ሆዴ አልጋዬ ላይ ስገላበጥ ወይም የደሃ እንጉ ቴ ቃሉን የሰጠው፡፡ ርጉሮ ሳሰማ ወይም ስነጫነጭ ጎረቤቶቼ እንዳይሰሙኝ በጠዋት ከቤ ‹‹በእውነቱ ይሄ ተዓምር ነው፡፡ /ከራቫቱን እያስተካከለ/ ማመን አቅ ቴ ወጣሁ፡፡ በጉዞዬ ላይ በጣም ራበኝና ድንገት አዛጋሁ፤ በእድሜ ጠ ቶኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት ወንጀለኛ በጉያችን መኖሩ ገርሞኛል፡፡ …ይኸ ና ያሉ አንድ አዛውንት አይተውኝ ተገረሙ፡፡ ‹‹ይህ የምን በሽታ ምል ው ግለሰብ በተያዘበት ምሽት አልጋው ላይ እየተገላበጠ ኑሮውን ሲ ክት ነው?›› አሉኝ ግራ ተጋብተው፡፡ ደነገጥኩ፡፡ በዚህ ድህነት ተረት ያማርር በመስማቴ ደነገጥኩ፡፡ ‹‹ከድህነቴ ጋር ተስማምቼ ለዓመታት በሆነበትና ጥጋብ በየቤቱ በገባበት ዘመን ተርቦ መገኘት ወንጀል መ ኖርኩ፤ አሁን ግን አልቻልኩም! አልቻልኩም!›› ሲል ሰማሁት፡፡ ወዲ ሆኑን አውቃለሁና በጣም ደነገጥኩ፡፡ ያው ፖሊሶችን በመጥራት ቤቱ ይዤያቸው ገባሁና ላሲዘው በቃሁ፡ ‹‹ማታ ትንሽ አንድ አሥር መለኪያ ውስኪ ጠጥቼ ነበር፡፡ እቤቴ ከገ ፡” ባሁ በኋላ ምሳ ሰዓት ላይ ያስተረፍኩትን ቅቤ የበዛበት ክትፎ በዛ አ ደሃ ሆኖ የመኖርን ወንጀል ለመፈፀም የበቃሁት የፀረ ልማት ኃይሎ ድርጌ በልቼ ተኛሁ፡፡ አሁን ደግሞ ከቤት ስወጣ ቤት ያፈራውን ክሽ ችንና የነጭ ለባሾችን ፕሮፓጋንዳ በመስማት ነው፡፡ የፀረ ልማት ኃይ ን ተደርጎ የተሠራ ሁለት ሰሃን ሙሉ ጥብስ ፍርፍር ነገር በላሁና ጭ ሎችና የነጭ ለባሾች ፕሮፓጋንዳ ድህነትን የሚያበረታታ፣ የልማት እ ማቂ ነገር ጠጥቼ ወጣሁ፡፡ የማታው ውስኪ ክትፎውን አልወደደው ቅዱን የልፋት እቅድ ብሎ የሚያጣጥል፣ ብልፅግናን እንደ ኩነኔ የሚ ም መሰል ይኸው በየደቂቃው ያዛጋኛል!›› ቆጥር፣ የልማት እቅዶች ላይ የሚያሾፍ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የትራንስፎር አዛውንቱ በጥሞና ከሰሙኝ በኋላ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተመገበ ሜሽን እቅዳችን እውን ሆኖ ሳይና ከእቅዱ ጋር አብሬ ባለመጓዜ የሠ ያለው አሁን አንተ እንዳልከው ነው፤ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ሰምቼ ራሁት ወንጀል በእጅጉ ሲፀፅተኝ ይኖራል፡፡ አላውቅም!›› ብለው ትተውኝ ሄዱ፡፡ እንዲህ ባለው ታላቅ ማጭበርበር ከርሃቤ ጋር ተስማምቼ በዋልኩበ ሰበር ዜና፡- ደሃ ሆኖ የመኖር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ ት በዛ ምሽት ቤቴ ገባሁና ቀኑን ሙሉ እህል ያላየ ሆዴን እያሸሁ ተኛ መኖሪያ ቤት፣ በፖሊሶች ሲፈተሽ ባለአንድ ሺህ ብር የአባይ ሁ፡፡ እንቅልፍ ከየት ይምጣ? ብገላበጥ ብገላበጥ እንቢ አለኝ፡፡ በጣ ግድብ ማሠሪያ ቦንድ መገኘቱን የኢንቨስተር ሰፈር ፖሊስ ም ከመበሳጨቴ የተነሳ ኑሮዬን አማረርኩ፡፡ ‹‹ከድህነቴ ጋር ተስማም ጣቢያ አስታወቀ፡፡ የቦንዱ ወረቀት ግንቦት 11 ቀን 2003 ቼ ለዓመታት ኖርኩ፤ አሁን ግን አልቻልኩም! አልቻልኩም! እውነቱ ዓ.ም የተገዛ እንደነበረ ምርመራውን ሲያካሂድ የነበረው ይውጣ፤ አልቻልኩም!›› አልኩ በታላቅ ሃዘን፡፡ ኢንስፔክተር አስታውቋል፡፡ ከአምስት ደቂቃ በኋላ በሬ ተንኳኳ፡፡ ‹‹ማነው?›› አልኩ ደንግጬ፤

15

የከተማ ቧልት

ቢላደን አልሞተም!

እንደ ትናንት ምሳ የተመገብንባት ቤት እንደ ዛሬ ሄደን ም ሳ አዘዝን፡፡ ከሌሎች ምግብ ቤቶች አንፃር ዋጋዋ ደህና ናት ተብሎ በኛ ዘንድ ሞገስ ያገኘች ቤት ነበረች፤ ይህቺ ምግብ ቤት፡፡ ከአቅም አንፃር ደግሞ በጣም ደህና እንዲሆንልን አ ምስት ስድስት ሆነን በማኅበር አዝዘን እንመገብ ነበር፡፡ ም ግቡ መጣ፤ ከጥሩ የምሳ ጨዋታ ጋር ተበላ፤ በጥርስ እንጨ ት ጥርሳችንን እየጎረጎርን ሂሳብ እንዲቀበለን አስተናጋጃችን ን ጠራን፡፡ እስኪመጣም ዐይናችንን ወደ ተከፈተው ቴሌቪ ዥን ሰደድን፡፡ “የቢን ላደን ሞት አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው!” ይላል ዘገባ ው፡፡ ለበላነው ምግብ ማወራረጃ ይሆን ዘንድ የኛም የውይ ይት ርዕስ ቢን ላደን ሆነ፡፡ “ለመሆኑ ቢን ላደን የሚባል ሰው በህይወት ነበረ?” “እንዴ ምን ነካህ አለ እንጂ!” “እውነት ግን ለምን ሬሳውን አያሳዩንም?” “ያልነበረ ሰው መቼም ሞተ ተብሎ አይነገርም!” “ቢን ላደን ለኦባማ ስልጣን ማራዘሚያ ጠቀመው!” አስተናጋጁ ከቆይታ በኋላ እንደ መጽሐፍ ተገላጭ የሂሳብ መቀበያ ውስጥ ቢል ሸጉጦ ሰጠን፤ ቢሉ ቢነበብ ትናንት በ በላነው በእያንዳንዱ ምግብ ላይ በትንሹ ስድስት ብር ተጨ ምሯል፡፡ “ምንድነው ይሄ?” ቢሉን እያየ ያለው ወዳጃችን ፊቱን አኮሳ ትሮ ጠየቀ፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች የተሰላቸው አስተና ጋጅ ፊቱን አዙሮ የዋጋ ዝርዝር የተጻፈበትን ነጭ ሰሌዳ አሳየ ን፡፡ የዋጋ ጭማሪው እውነት ነው፡፡ 34 ብር የነበረው የበግ ጥብስ 40 ብር ብሎ ይጀምራል ዝርዝሩ፡፡

መስተንግዶ ከስጋ የተወደደበት ሀገር በናዝሬት (አዳማ) የሚገኘው ይልማ ስጋ ቤት ከአዲስ አበባ ጭምር ስጋውን ፈልገው የሚመላለሱለት ደንበኞ ችን ያፈራ አንጋፋ ድርጅት ነው። ይሄው ስጋ ቤት በዋና ከተማይቱ አዲስ አበባ እንኳ ባሉ በርካታ ስጋ ቤቶች በ ማይታይ ሁኔታ የተደራጀ ነው። ዘመናዊ ህንጻ፣ ንጹህና ማራኪ ስጋ መደርደሪያ፣ አፍንጫ የማይቆርጥ ሽንት ቤ ት፣ ከተፎ አስተናጋጆች ይዞ አፍ ውስጥ የሚሟሟ ስጋ ለተመጋቢዎች እንደየምርጫቸው ያቀርባል። ይሄ ተወዳጅ ስጋ ቤት ታዲያ በቅርቡ በመላው ኢትዮ ጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የዋጋ ተመን መቋቋም ያቃ ተው ይመስላል። በኪሎ ይህን ያህል ብቻ መሸጥ የሚ ቻለው ተብሎ ከመንግስት የወረደውን ትዕዛዝ ላለመጣ ስ ተጠንቅቆ ግን ደግሞ የሚሰጠውን አገልግሎት ባገና ዘበ መልኩ የገንዘብ ማካካሻ ጨምሮ ማስታወቂያ ያዘጋ ጃል። ማስታወቂያው የአንድ ኪሎ ጥሬ/ጥብስ ስጋ ዋጋ 40 ብር መኾኑን ይገልጽ እና የስጋውን ዋጋ ያህል ክፍ ያ ከደንበኞቹ ይጠይቃል። የይልማ ደንበኞች በ90 ብር ብቻ አልተገላገሉም። 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ም በቢሉ ውስጥ ይካትታል።

ዝናና?

ሙዚቃ

ዩጋንዳ

ኮሜዲ

ን የት ሄደን እ

በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

“ለምንድነው በአንድ ቀን ይሄ ሁሉ ጭማሪ!?” “ቢል መቁረጥ ዛሬ ስለጀመርን!” በታከተ ድምጽ አስተናጋጁ መለሰ፡፡ “ቢል ከምትሉት ቢላ ብትሉት አይሻልም!?” በምሬት ተናገረ ሌላው ወዳጃችን፡፡ ሻዩ፣ ማኪያቶው፣ ሽሮው፣ ቀይ ወጡ… /ሆድ ስለባሰኝ በዚሁ ልቀጥልበት፡- ትራንስፖርቱ፣ ስኳሩ፣ ዘይቱ፤ ወይ ዘይት፤ ዘይ ት የቅቤ ረዳት ተዋናይ ተደርጎ መጠራት ከጀመረ ጀምሮ ዋጋ ው የማይቀመስ ብቻ ሳይሆን በፈለጉት ዋጋ ታስሶ የማይገኝ ሆ ኗል፡፡ “ሸኖ ቅቤ፤ ሸኖ ለጋ፣ ሻዲ ለጋ…” ያኔ ሲሉት መጠርጠር ነበረብን፡፡ …ነዳጁ፣ ሰዉ፣ ሥጋው፣ ግብረ ሥጋው… አዪዪ… ም ን ይሻላል?/ ሁሉ ነገር በየቀኑ ይጨምራል፤ “የዚህ የኑሮ ውድነ ት ጦስ መጨረሻው ምን ይሆን?” ስጋት ባጀበውና ዝግ ባለ ድ ምፅ ራሴን ጠየቅኩ፡፡ “ወይ ጉድ!” አለ አንዱ ወዳጃችን በመሃል አንዳች የታወሰው ነ ገር ያለ በሚመስል፡፡ “ምን ሆንክ?” “ቢል ላደን መቼ ሞተ?” “እንዴት?” “በህይወት አለ እኮ፤ ያውም እዚችው እኛው ምድር!” “ምን ማለት ነው?” “ቢል ላደን መጥቶ ይኸው እኛን እየጨረሰን እኮ ነው፡፡” አለ ንግግሩን ይበልጥ እያሻሻለ፡፡ የጓደኛችን ንግግር ሁላችንም የገባ ን ዘግይቶ ነው፡፡ ነገሩ ቅኔ መሆኑ ነው፤ ቢል ላደን፡፡ እውነት ም ቢል ለአደን፡፡ “እንገዛ ነበረ እቃ በጥሩ ዋጋ፣ ቢል ላደን መጣና ኑሯችን ተናጋ፡፡”

መቼ፦ ዘወትር ማክሰኞ እና ሀሙስ የት፦ ናኩማት ሞል አጠገብ ካለው ኤፌንዲስ (ሴንቲነሪ ፓርክ) እና ከብሔራዊ ትያትር ታችኛው መግቢያ በተቃራኒ ባለው ፓን ወርልድ የመኪና መሸጫ ቦታ ሰዓት፦ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ 10ሺህ ሽልንግ እና አምስት ሺህ ሽልንግ

>>>ሾን ኪንግስተን በካምፓላ ጃማይካዊው የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሾን ኪንግስተን ከካምፓላ ሙዚቃ አፍቃሪያን ጋር ለመገናኘት ለጁላይ 29 ቀጠሮ ይዟል። በቅርቡ በደረሰበት አደጋ የካምፓላውን ዝግጅት ሊሰርዘው ይችላል የሚል ግምት አሳድሮ ነበር። ሆኖም ከኮንሰርቱ አዘጋጆች የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው አቀንቃኙ በተያዘለት ቀን ዝግጅቱን ያቀርባል። ቦታው ሎጎጎ የሚገኘው የክሪኬት መጫወቻ ሜዳ ነው። ታዋቂው አሜሪካው አቀንቃኝ አር ኬሊ በካምፓላ ዝግጅቱን ያቀረበውም በዚሁ ቦታ ነው። “ክለብ ቢራ” ስፖንሰር ያደረገው ይሄው ዝግጅት የመግቢያ ዋጋው ስንት እንደሆነ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

የዩጋንዳ ታዋቂ “ስታንድ ኦፕ” ኮሚዲያን የሆነው ፓብሎ በበሳል ቀልዶቹ ይታወቃል። ከእንግሊዘኛ ጋር ሉጋንዳ እና ሌሎች የሀገሪቱን ቋንቋዎች እየቀላቀለ በሚያቀርባቸው ቀልዶች ጥርስ አያስከድንም ይሉታል። ፓብሎ በ“ኦብዘርቨር” ጋዜጣ የሐሙስ እትም ላይ የራሱን አምድ ከፍቶ አንባቢዎችን ዘና ያደርጋል። በአብዛኛው ወጣቶች የተሰባሰቡበት የ“ፈን ፋክተሪ” አበላት ድራማዊ ይዘት ባላቸው ቀልዶቻቸው ይታወቃሉ። እንግሊዘኛ እና የተለያዩ የዩጋንዳ ቋንቋዎችን የሚጠቀሙት “ፈን ፋክተሪዎች” በእንቅስቃሴያቸው ብቻ ሳቅ የሚያጭሩ ናቸው። አብዛኞቹ የ“ፈን ፋክተሪ” አባላት በአሁኑ ወቅት በ“ኤንቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ እየተላለፈ በሚገኘው “ሆስቴል” ድራማ ላይ ይተውናሉ።

ፊልም መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ጋርደን ሲቲ ከኡቹሚ ሞል በላይ አንደኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ) ለካምፓላ ብቸኛ የሆነው ሲኒማ ቤት ሲኒፕሌክስ በሶስት የተለያዩ አዳራሾቹ የአሜሪካ እና የህንድ ፊልሞችን ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች ያቀርባል። በጁን ወር ከሚያስመጣቸው ፊልሞች ጥቂቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ናቸው።

ፍቅር፣ፖለቲካ እና ድርጊት የተሞላበት ፊልም

የኩንጉ ፉ ፓንዳ ቀጣይ ክፍል፤ ለህጻናት እና ካርቱን ፊልም ለሚያፈቅሩ

የአፍሪካ አሜሪካውያንን ፊልም ለሚወዱ የሚመረጥ በሁለት ፍቅረኛ ቤተሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ሁነቶች ዙሪያ የሚያጠነጥን

ኮሜዲ አፍቃሪ ለሆኑ


ሀበሻዊ ቃና

16

መጽሐፍ

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

የወሲብ መጻሕፍት የገበያ ሃድራ ሙሳ ያሲን አዲስ ነገር ኦንላይን

ሙሉ ጊዜ ስመ ጥር ደራ ሲ ነው። አሳታሚዎች ሰ ላምታ ካቀረቡለት በኋላ የሚያስከትሉት የሁልጊዜ ምክር ተመሳሳይነት ይገር መዋል። “ጎበዝ ደራሲ ነህ ግን… እንዲህ ብጥስጥስ ያለ ሳንቲም ከም ትሰበስብ ለምን ሸጋ የኾነ የወሲብ ሳይኮሎ ጂ አትጽፍም። ላንተም ለኛም ጥሩ የሚኾ ነው እርሱ ነው፣ ካንተ ያነሰ ችሎታ ያላቸ ው ልጆች ይኸው ለገበያ የሚኾን ነገር እየ ጻፉ ቀድመውህ ሀብታም እየኾኑ ነው፤ እ ስኪ ስብበት።” ይህ አሳታሚዎች ለደራሲዎች የሚያቀር ቡት አባታዊ ምክር እንደዋዛ የሚታይ አይ ደለም፡፡ የኅብረተሰባችንን ድብቅ ሥነ-ል ቡናዊ ፍላጎት የሚያመላክት ነው። የምክ ሩ ትርጉም ግን ከዚህም ይዘላል።

የወሲብ ሰልፍ

የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በ1980ዎቹ አጋማ ሽ እና መጨረሻ በተለምዶ “ወመዘክር” በ ሚባለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻ ሕፍት እና ቤተ-መዛግብት የጋዜጣ ክፍል ውስጥ የነበረውን ኹኔታ ፈጽሞ አይዘነጋ ውም። በጣውላ የታነጸው በቢጫማ ቀለ ም የተዋበው ክፍል በወቅቱ በአገሪቱ የሚ ታተሙትን የመንግሥት ኾኑ የግል ጋዜጦ ችን እና መጽሔቶችን ለጋዜጣው ክፍል ታ ዳሚ ያቀርብ ነበር። ኾኖም በወቅቱ ይወ ጡ ከነበሩት የኅትመት ውጤቶች አንባቢ ው ቀዳሚ ትኩረት ይሰጥ የነበረው እንደ “ጥንቅሽ”፣ “ማዶና”፣ “የፍቅር ማኅደር”፣ “ኤሮቲካ”፣ “እንኮይ” እና “እውነተኛ ፍቅ ር” ላሉት ወሲብ ተኮር ጋዜጦች እና መጽ ሔቶች ነበር። በዚሁ ጋዜጣ ክፍል ውስጥ ይታደሙ ከነበሩት መካካል 75 መቶ የሚ ኾኑት ወሲብ ነክ የኅትመት ውጤቶችን የ መኮምኮም ልማድ አዳብረው ነበር። የጋዜ ጣ ክፍሉ በጊዜ ስለሚሞላ ብዙ አንባቢያ ን በመጡበት እንዲመለሱ ይገደዱም ነበ ር። አንዳነድ ደንበኞች ግን እነዚህን የወሲ ብ ጋዜጦች ለማግኘት በትእግስት ይጠባበ ቃሉ፤ እየተፋፈሩ። ኹኔታው የወሲብ ፊል ምን ለመታደም በአንድ ክፍል እንደመገኘ ት ዐይነት ስሜት ነበረው። በወቅቱ “ማዶና” ጋዜጣ የአንዲት ኢትዮ ጵያዊት ሴትን በእውን ዓለም ይሆናል የማ ይባል የወሲብ ገድል የሚተርክ “ኢትዮጵያ ዊቷ ማዶና” የሚል ዐምድ የነበረው ሲኾን የቅንዝረኛዋን ሴት ገድል ከሰማንያ ሳምን ት በላይ በጋዜጣው ላይ ተስተናግዷል። ጋ ዜጣው በወሲብ አራራ በእጅጉ የተለከፈች

ውን ሴት አንድ ልዩ ገድል በየሳምንቱ ይዞ ይቀርብ ነበር። “ጥንቅሽ” ጋዜጣ በበኩሉ “የሴተኛ አዳሪዋ ገመና” በሚለው ዐምዱ ወጣ ያሉ እና ማኅበረሰቡ ዘንድ ፀያፍ ተደ ርገው የሚቆጠሩ ወሲባዊ ኹነቶችን ልብን በሚሰቅል እና ለወሲብ በሚያማልል ኹኔ ታ ያቀርብ ነበር። ለእነዚህ ሁለት ዐምዶች ነበር የወመዘክር ቤተ መጻሕፍት በወሲብ ሲቃ ጡዘት ላይ ትዋልል የነበረው። የጋዜ ጣው ክፍል ታዳሚዎች እነዚህን ወሲባዊ ትርክቶች ቀድሞ ለማንበብ ብርቱ ትግል ያደርጉ ነበር። ከቤተ መጻሕፍቱ አስተናጋ ጆች እስከመሻረክ ድረስ። እነዚህ ጋዜጦች ከሌሎች በዚህች ክፍል ይገኙ ከነበሩ ጋዜ ጦች በተለየ መልኩ ይሟሽሹ ነበር። የሰው እጅና ዐይን ስለሚበዛባቸው።

የሌተናል ኮሌኔሉ መፈንቅለ- ወሲብ

በሕይወት የሌሉት ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው መኮንን ሐሰን ከላይ ከተጠቀሱት ወሲብ ተኮር የኅትመት ውጤቶች በዋናዎቹ ውስ ጥ የመሥራችነት እና የባለቤትነት ሚና ነበ ራቸው። በ1987 ዓ.ም አካባቢ በርካታ ሴ ቶች “እንኮይ” መጽሔትን ጨምሮ ሌሎች ወሲብ ነክ ጋዜጦች “ሴቶችን ወሲባዊ ሸቀ ጥ አድርገው ያቀርባሉ” በሚል “በሴቶች እ ኩልነት የሚያምነው መንግሥታችን በአሳ ታሚዎች እና በአዘጋጆች ላይ ሕጋዊ ርም ጃ ይውሰድልን” ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እስ ኪወጡ ድረስ ኮሎኔሉ በኢትዮጵያ የጋዜ ጣ እና የመጽሔት ኅትመት ታሪክ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ትርፍ አጋብሰዋል። በወቅ ቱ ከነበሩት ወሲብ ተኮር ኅትመቶች ከሲሶ በላዩ የሌተናል ኮሌኔሉ ንብረቶች ነበሩ። ሌ/ኮሎኔል ጌታቸው ከጋዜጦች እና መ ጽሔት ዕገዳ በኋላም ቢኾን እጃቸውን አ ጣምረው አልተቀመጡም። በወሲብ ተኮ ር ጋዜጦቹ እና መጽሔቶቹ የተደረገባቸው ን መፈንቅል ለመቀልበስ ወጠኑ። የወሲብ ነክ የኅትመት ውጤቶችን ገበያ እና የኅብ ረተሰቡን ታማኝ አንባቢነት በዉሉ ያጠኑ ት ሌ/ኮሎኔሉ ማርሻቸውን ወደ መጻሕፍ ት ቀየሩት። ኮሎኔሉ ቀድሞ እጃቸውን ያሟሹባቸው ን የነአጋታ ክሪስቲን፣ ሼርሎክ ሆልምስን እ ና ሌሎችም ዝነኛ ወንጀል ነክ ታሪኮችን ወ ደ አማርኛ የመተርጉሞን ነገር ለጊዜው ጋ ብ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወሲብ ዘመ ም መጻሕፍት አዞሩ። በመጀመርያ ወደ አማርኛ የተረጎሙት የ ኸርቪንግ ዋላስን “የደፈረሰ እንባ” ሲኾን መጽሐፉ ዐሥራ አንድ ጊዜ ኅትመት ቤት ን ጎብኝቷል። የዚህ መጽሐፍ ሽፋን ከወገ ቧ በላይ ርቃኗን የኾነች ወጣት በወሲባዊ

አቀማመጥ ጡቶቿን ወድራ የምትታይበት ምስል ነበር። የመጽሐፉ ጭብጥ አንዲት ወጣት ሴት ወሲብን እንደምትወድ በሚ ዲያ ከገለጸች በኋላ በአራት ወንዶች ተጠ ልፋ ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት ሲደርስባ ት እና ከዚህ ለማምለጥ የምታደርገውን ብ ርቱ ትግል ይተርካል። ይህ የትርጉም መጽ ሐፍ በወቅቱ ብዙ ሺሕ ኮፒ በመሸጥ መነ ጋገርያ ኾኖ ቆይቷል፡፡ ኮሎኔሉ ከዚህ መጽሐፍ በኋላ የተረጎሟ ቸው “የባሎች ገመና” እና “የዘቪራ ሆላደ ርን” ግለታሪክ ናቸው። ዛቬራ ለዚህ ግለ ታሪክ መጽሐፍ የሰጠችው ኦሪጅናል ርእ ሰ “the happy hooker” ይሰኛል። ከዚህ ሥራ በተጨማሪ “አልሎት” /the bitch/፣ “መንታዋ አነር” /13 at dinner/ እና “ኮር ማው” /the stud/ የተሰኙት ወሲብ ተኮር የኾኑት የትርጉም ሥራዎቻቸው በተደጋጋ ሚ ታትመውላቸዋል። የኮሌኔሉ ሁሉም የ ትርጉም ሥራዎች ጡት መያዣ እና የውስ

d

ማ ለመኾን ችለው ነበር። በ1994 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ ለኅትመት የበቃው “የፍቅር ጥበብ” የተሰኘው መጽሐ ፍም ቢኾን አሁን 12ኛ ዕትም ላይ ነው ያ ለው። ይኸው ማኅሌት ጥላሁን በሚል የ ብእር ስም የተተረጎመው መጽሐፍ ልቅ የ ወሲብ መጽሐፍ ባይኾንም በርካታ ገጾቹን ለወሲብ ተኮር ጉዳዮች ሰውቷል። በተመሳ ሳይ የወሲብ ተኮር ሥነ-ጽሑፍ ላይ የተሰ ማሩ አሳታሚዎች እና አስተርጓሚዎች እን ደሚያምኑት የትኛውም የፖለቲካም ኾነ የ ታሪክ መጽሐፍ እንደ ወሲብ ተኮር መጻሕ ፍት ሰፊ ገበያን ማሸነፍ አልቻሉም።

የ“ዘ” ዘመን

የካዛንቺስ ሴተኛ አዳሪዎች እና የደንበኞ ቻቸውን ግንኙነት በተዋንያኑ ልቅ ቋንቋ የሚተርክው “መኀልየ መኀልየ ዘ-ካዛንቺ ስ” ለኅትመት ገብቶ ለገበያ በቀረበ ጊዜ በ ኅትመት ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ ውዝ ግብን አስነስቶ ነበር። መጽሐፉ በፊት ገ

c

ባሳለፍነው ክረምት ለገበያ የቀረበው እና በጋዜጠኛ ሚልዮን ሹሩቤ የተጻፈው “ወሲባዊ ውስልትና ዘ አዲስ አበባ” የተሰኘው መጽሐፍ የመጀመርያ ዕትም በአከፋፋዮች ዘንድ ያለቀው ዐሥር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር።

a ት ሱሪ ባደረጉ እጅግ አማላይ እና ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶች የተሞሉ ነበሩ። የፊት ገ ጽ ሽፋኖችን አማላይ አድርጎ የማቅረብን ስልት በስፋት ያስተዋወቁት ኮሎኔሉ እንደ ኾኑ መጻሕፍት አሳታሚዎችም አሌ ሳይሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው።

ድኅረ ኮሎኔል

ከኮሎኔሉ መፈንቅለ ወሲብ ቀጥሎ የእርሳ ቸውን አርዐያ ይዘው የቀጠሉ ብዙ ደራሲ ዎች እና ተርጓሚዎች ተፈጠሩ። የወሲብ ተኮር መጻሕፍት የገበያ ሃድራ የማያባራ እ ንደኾነ የተረዱ አያሌ አሳታሚዎች ውጭ አገር የሚሄዱ ነጋዴዎችን እና የበረራ አስ ተናጋጆችን ወሲባዊ መጻሕፍት እንዲያመ ጡላቸው በማባበል ሥራ ተጠመዱ። የሚ መጡላቸውን መጻሕፍት ገነጣጥሎ ለብዙ ወጣት ተርጓሚዎች በማደል ቶሎ “ለጥብ ስ” የማድረስ ሥራ ላይ ተሰማሩ። ስኬታ

b ጹ ላይ “ከ17 ዓመት በታች የኾኑ ሰዎች እ ንዲያነቡት አልተፈቀደም” የሚል ማስገን ዘብያ ቢኖረውም በልቅ የቋንቋ አጠቃቀ ሙ ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞት ነበር። መ ጽሐፉ ከልማዳዊው የማኅበረሰቡ የወሲ ብ አመለካከት የሰማይ ያህል የራቁ፣ ያፈ ነገጡ እና የተቃረኑ የካዛንቺስ የሌሊት የ ወሲብ ገጠመኞችን በካዛንቺስኛ የቡና ቤ ታ ቋንቋ ይተርካል። በቶሎ ከገበያ እያለቀ አሁን 6ኛ ዕትሙ ላይ ደርሷል። አሳታሚ ዋ ስንዱ አበበ “የአገራችን ወጣት በኤድ ስ እየተቀጠፈ ያለው ግልጽነት በማጣቱ ነ ው” የሚል ይዘት ያለው የሞራል ማለዘቢ ያ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የጻፈችበት ቢ ኾንም ውዝግቡን ለማብረድ በቂ ማስተባ በያ ኾኖ አልተገኘም። ውዝግብ ለመጽሐ ፍ ገበያ የማቀጣጠያ አንዱ ስልት መኾኑ ን የሚያውቁ የመጽሐፍ አከፋፋዮች ይህ

ን ፈር ቀዳጅ መጽሐፍ በብዛት ሸጠዋል። አሁንም ድረስ መጽሐፉ በገበያ ላይ በቀላ ሉ አይገኝም። በአዲስ አበባ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸ ው መጻሕፍት አከፋፋይ መደብር ባለቤ ት ከኾኑት አንዱ እንደሚሉት የአሳታሚ ዋ የስንዱ አበበ ቸልተኝነት እና ስንፍና እ ንጂ መጽሐፉ እስከአሁን ከዐሥር ዕትም በላይ መሄድ ይችል ነበር። “ይህ ሥራ ያ ለውን ሰፊ ተቀባይነት ስለማውቅ ሙሉ የ ኅትመት ወጪውን እኔ እንድሸፍን ጠይ ቄ ምላሽ አላገኘሁም” ይላሉ እኒሁ አሳታ ሚ። ውልደቱ እና እድገቱ ካዛንቺስ የኾነ ው የመጽሐፉ ደራሲ ተድባበ ጥላሁን ይ ህንኑ ሥራውን ከአመርቂ ክፍያ ጋራ ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ መመለሱ ይታወቃል። የዚህን የ“ዘ”ዘመን መሥራች ወሲብ ሙ ሊት ሥራ ስኬት የተረዱ አሳታሚዎች የደ ራሲ ያለህ ማለት ጀመሩ። በዚህም የ“ዘ” ዘመን መጀመር ታወጀ። የቼቺንያን የሌሊት ግብር በቺቺንያ ወሲ ብ ሸማች ደንበኞች ልቅ ቋንቋ የሚተርከ ው እና በደረጄ አያሌው የተጻፈው “መኀ ልየ መኀልየ ዘ ቼቺኒያ” የወሲብ ገበያው ውስጥ ለመግባት የመጀመርያው ነበር። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አሁን አራተኛ ዕትም ላይ እንደደረሰ ለአሳታሚው ቅር ብ የኾኑ ምንጮች ይገልጻሉ። መጽሐፉ የሰፈሩን የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች አስከ ፊ ገጽታ በጥልቀት ለማሳየት ይሞክራል። የዚህን መጽሐፍ ስኬት ተከትሎ ከጥቂ ት ወራት በኋላ ለገበያ የቀረበው እና ት ኩረቱን በተመሳሳይ መቼት ላይ ያደረገ ው “የቺቺኒያ ምስጢራዊ ሌሊቶች” የተሰ ኘው መጽሐፍ አሁን ሦስተኛ ዕትም ላይ ደርሷል። የዚህ መጽሐፍ ባለታሪኮች ጥቂ ት ቢኾኑም በሤራ አወቃቀር፣ በገፀ-ባሕ ርይ አሳሳል እና በሥነ-ጽሑፋዊ ዉበቱ ሲ መዘን ይህ መጽሐፍ ከሁሉም ወሲብ ተኮ ር መጻሕፍት የላቀ እንደኾነ የሚናገሩ ጥ ቂት አይደሉም። ባሳለፍነው ክረምት ለገበያ የቀረበው እና በጋዜጠኛ ሚልዮን ሹሩቤ የተጻፈው “ወ ሲባዊ ውስልትና ዘ አዲስ አበባ” የተሰኘ ው መጽሐፍ የመጀመርያ ዕትም በአከፋ ፋዮች ዘንድ ያለቀው ዐሥር ቀናት ባልሞ ላ ጊዜ ውስጥ ነበር። ይህ መጽሐፍ እስከ አሁን ከጠቀስናቸው በተቃራኒ መልኩ የ ሚተርከው ስለ ቤት ልጆች እና ባለትዳሮ ች ወሲባዊ ሕይወት ነው። መጽሐፉ አሁ ን ሁለተኛ ዕትሙ እየተሸጠ ይገኛል። ደ ራሲው ከሚተርካቸው እውነታዎች በተ ጨማሪ ከበርካታ የቤት ልጆች እና ባለት ዳሮች ጋራ በቴፕ የተቀረጸ ቃለ-መጠይቅ አድርጓል።

ወሲብ ያበላል

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለገበያ ከ ቀረቡ የወሲብ ሥነ-ልቡና መጻሕፍት በአ መዛኙ ኤሮቲክ ፊልሞች እንዲመስሉ አ ድርጎ ማቅረብ ተጨማሪ ገበያን እንደመ ፍጠር እየታየ ነው። በጨዋ ቃላት እና መ ንገድ ወሲብን ማውራት በአዋጅ የታገደ ይመስል የብዙዎቹ መጻሕፍት አፈጣጠ ር ልቅነት ይታይበታል። ይህም ከልባሳ ቸው ይጀምራል። ፈረንጅ ሴት ሞዴሎች ጡቶቻቸውን ወድረው የሚታዩባቸው መጻሕፍትን ቁጥር ሼልፍ ይቁጠረው። በቅርብ ጊዜ በትርጉም ሥራዎች ደረጃ ያሉትን እንኳ ብንቆጥር ከ20 በላይ እን ሄዳለን። ከኒኮል ቤላንድ “the girl next door” የሚለው መጽሐፍ “የሴቶች ገመ ና’ በሚል ርእስ ወደ አማርኛ ከተመለሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምንተኛ ዕት ም ላይ ደርሷል። የዚህ መጽሐፍ ቋሚ ደ ንበኞች የሁለቱም ፆታ አባላት ናቸው። የ ጆን ግሬይ “Mars and Venus in the Bedroom” የተሰኘው መጽሐፍ “የወሲ ብ ጥበብ” በሚል ርእስ በመዓዛ ቴዎድ ሮስ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲኾን ገና መንፈቅ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛ ዕ ትም ደርሷል፡፡ በኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ላይ ሰዓት እላ ፊ በሚለው “ተወዳጅ” ዐምድ ሥር ለአ ንድ ዓመት የቀረቡትን የአዲስ አበባ ሴ ተኛ አዳሪዎችን ሕይወት የሚዳስሱ ስብ ስቦች “ሰዓት እላፊ” በሚል ርእስ በመጽ ሐፍ ያሳተመው የዐምዱ አዘጋጅ ኤርም ያስ ስዩምም ገበያው ሰምሮለታል። ጋዜ ጣው በሁለት እግሩ እንዲቆም ያስቻለው ም ይኸው ዐምዱ እንደኾነ የሚናገሩ ብ ዙ ናቸው። አንጋፋው ደራሲ ስብኀት ገብረ እግዚአ ብሔር የጀመረው የ“እንደወረደ” የወሲብ ሥነ-ጽሑፍ ዛሬ ዛሬ ተስፋ የሚጣልባቸ ው ወጣት ደራሲያን ሳይቀሩ የብእር ስ ም እየፈጠሩ እንዲገቡበት እያደረጋቸው ነው። ስብኀት በዚህ ርእስ ሥር መጠራ ት ከሌለባቸው ኾኖም የወሲብ ወላፈን ከ ነካቸው ድንቅ ሥራዎቹ መሀል አምስት ጊዜ የታተመለት “ሌቱም አይነጋልኝ” እና ሦስት ጊዜ የኅትመት ብርሃን ያገኘለት “ት ኩሳት” ይጠቀሳሉ። እነዚህ ወጥ ድርሰቶ ቹ ያገኙት ተቀባይነት በወሲብ ሥነ-ጽሑ ፍ የራሳቸውን ተጽዕኖ አልፈጠሩም ለማ ለት ግን ያዳግታል። ኾነም ቀረ የኢትዮጵ ያ የኅትመት ታሪክ በኮሎኔሉ አብዮት ተ ጀምሮ፣ በ“እንደወረደ” የስብኀት መንገድ አሳብሮ ዛሬ የ“ዘ”ዘመን ላይ ደርሷል። የ ሚያቆመው ያለ እስከማይመስል ድረስ፤ የኀትመት ዋጋ መናርም እንኳ ቢኾን።

ቋንቋ በየፈርጁ ትንሽ ስለ ስዋሂሊ ቋንቋ ስዋሂሊ ባንቱ ከሚባለው የቋንቋ ምድብ የሚገኝ ሲሆን ለመማር ብዙም ከባድ ያልሆነ ቋንቋ ነው፡፡ የጾታ ገላጭ እና መስተዋድድ እጥረት ከቋንቋው መለያ ባህሪያት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ስዋሂሊ የሚለው ስም ራሱ ሳዋሄል ከሚለው የአረበኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም ጠረፍ እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም ስዋሂሊ በምስራቅ አፍርካ ጠረፍ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች በብዛት የሚነገር የጠረፍ ቋንቋ ነው፡፡

ሰዋሂሊ ከ G(g) በስተቀር ሁሉ ም ተነባቢ ፊደላት የሚነበቡት ልክ በእንግሊዘኛው እንደሚነበ ቡት ነው፡፡ እንደ እንግሊዘኛ ሁሉ ስዋሂሊም አምስት አ ናባቢዎች አሉት፡፡ እነሱም a,e,I,o,u ሲሆኑ እያንዳንዳቸው አንድ ድምጽ ብቻ አላቸው፡፡ ምሳሌ፡Baba ባባ አባት Wewe ዌዌ አንተ/አንቺ Sisi ሲሲ እኛ Soko ሶኮ ገበያ Kuku ኩኩ ዶሮ አንዳንድ ጊዜ ሁለት አናባቢዎች በተከታታ

ይ ይመጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ሁለቱም አና ባቢዎች የየራሳቸው ድምጽ ስላላቸው በተና ጠል መነበብ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የ ትርጉም መዛባትን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ፡Kufa (ኩፋ) የሚለው ቃል kufaa (ኩፋአ) ከሚለው ጋር የተለያዩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያው “ለመሞት” ማለት ሲሆን ሁለ ተኛው ግን “ይጠቅማል” እንደማለት ነው፡፡ ለመግቢያ ያህል ስለስዋሂሊ ቋንቋ መሰረ ታዊ ነግሮች በጥቂቱ ይህን ያህል ካልን በዚ ህ የመጀመሪያ እትማችን የሰላምታና ተያያ ዥ ቃላትን ትርጉም እንደሚከተለው እናስከ ትላላን፡፡

የሰላምታ ቃላት

ጃምቦ፡ ይህ ቃል በምስራቅ አፍሪካ እጅግ የተለመደና ከወዳጅ ዘመድ ጓ ደኛ ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ የሚያገ ለግል ሲሆን ጥያቄውም ምላሹም ራ ሱ ጃምቦ ነው፡፡ በአማረኛ ጤና ይስጥ ልኝ እንደማለት፡፡ ይህ ቃል የተወሰደ ው ሁጃምቦ ከሚለው ሙሉ ሰላምታ ነው፡፡ ይህንና ሌሎችን የሰላታ ቃላት እንደሚከተለው እንመልከት፡፡ Hujambo ሁጃምቦ - እንደምን አለ ህ/አለሽ Sijambo ሲጃምቦ - ደህና ነኝ፡፡ Hamujambo ሀሙጃምቦ -እንደም

ን ናችሁ? Hatujambo ሀቱጃምቦ - ደህና ነን Umzima ኡሙዚማ- ደህና ነህ/ነሽ? Nimzima ኒሙዚማ -ደህና ነኝ Vipi ቪፒ - እንዴት ነህ/ታዲያስ? Sawa ሳዋ - ደህና ነኝ/አለሁ Habari yako ሀባሪ ያኮ -እንዴት ነህ/ ነሽ? Nzuri/Njema ንዙሪ/ኒጄማ - ደህና ነኝ Subalkheri ሱባሊሄሪ- እንደምን አደር ህ/አደርሽ? (ምላሹም ራሱ ነው) Subalkheri habari asubuhi ሱባሊሄ ሪ ሃባሪያ አሱቡሂ - እንደምን አደርህ/ሽ? ደህና ነህ/ሽ? Njema ኒጄማ -ደህና ነኝ Masalkheri ማሳልሄሪ - እንደምን ዋል ህ/ሽ?/ እንደምን አመሸህ/ሽ? Lalaselama/Alamsiki/Usiku Mwema ላላሰላማ/አላሙሲኪ/ኡሲኩ ሙዌ ማደህና ደር/ሪ/ሩ ለማለት የሚያገለግሉ ቃ ላት ሲሆኑ ምላሸቸውም አላሙሲኪ ነ

ው፡፡ አሜን ሰላም እደሩ አንደማለት:: Shikamoo ሺካሞ- በእድሜ ለገፋ ወ ይም በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ ላ ለው ሰው የሚቀርብ ሰላምታ ነው ፡ ፡ ምላሹም፡ Marahaba መርሃባ ነው፡፡ Kwaheri ኩዋሄሪ -ደህና ሁን/ኝ/ኑ ቻ ው Kwaheri yakonana ኬዋሄሪ ያኮናናደህና ሁን/ኝ/ኑ ቻው በሰላም ያገናኘን Asanti አሳንቲ - አመሰግናለሁ Karibu ካሪቡ - እንኳን ደህና መ ጣህ/ሽ Karibuni ካሪቡኒ - እንኳን ደህና መ ጣችሁ Karibu ndani ካሪቡ ኒዳኒ - ወደ ቤ ት ግባ/ኖር/ጎራ በል Karibu kiti ካሪቡ ኪቲ - ተቀመጥ እ ንጂ/አትቀመጥም? ( እነዚህ እንግዳ ሲመጣ ለመቀበል የሚውሉ የሰላምታ ቃላት ናቸው)

ምራቂ

onasi)

(ቦናሲ-B

Hodi ሆዲ - ሰው ቤት ሄደው በር ሲያንካኩ የ ሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ “እዚህ ቤ ት ወይም ቤቶች አላችሁ?” እንደማ ለት n Hongera ሆንጌራ - እንኳን ደስ ያለህ/ያለሽ/ያላችሁ n Pole ፖሌ - አዝናለሁ(ያዘነን ወይም የተጎዳን ሰ ው ለማጽናናት) n Penda ፔንዳ - ፍቅር(መውደድ) n Kupenda ኩፔንዳ - ማፍቀር n Na kupenda ናኩፔንዳ - አፈቅርሻለሁ/ አፈቅርሃለሁ n


ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሀበሻዊ ቃና

17

የሀገር ቤት ጨዋታ

ሐሳብ ተከሰተ

ሰሞኑን ባልተለመደ ኹኔታ የምኖረው ኑ ሮ እጅግ መረረኝ፤ አንገሸገሸኝ፡፡ አንድ ነገ ር ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ ኾኖም እንደ ድንገት ድንቅ ሐሳብ ተከሰተልኝ፡፡ ዲቪ መሙላት፡፡ ቢንጎ!! ይህ ሐሳብ ለም ን እስከዛሬ እንዳልተከሰተልኝ ገረመኝ፡፡ ያ ን ቀን ምሽት ደስ ብሎኝ አመሸሁ፡፡ ለመጀ

(ፎቶ - ፍሊከር)

ፎቶ - ሆቦ ትራቭለር

በገጠራማይቱ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ፍጥነት ቀን ቀን ቀርፋፋ ስለሆነ ኢንተርኔት ቤቶቹ ዲቪ ፎርሙን በወረቀት ብቻ እያስሞሉ ሌሊት ሌሊት በኢንተርኔት ይልኩታል

እንደ ላሊበላ ባሉ ገጠራማ ቦታዎች ከጎጆዎች አጠገብ ዳሳሳ ኢንተርኔት ካፌዎችን መመልከት እንግዳ መሆኑ ቀርቷል

በዲቪ ሰሞን ወደ ኢንተርኔት ካፌ ጎራ ያለ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዲቪ ለመሙላት ተገጥግጦ ይመለከታል

ፎቶ-አፍሪካ ኒውስ

ፎቶ - ሪቻርድ ሁባታካ

ገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነ ኝ፡፡ መታወቂያዬ ላይ ከስሜ ት ይዩ “ሌክቸረር” የሚል ማዕረግ አለበት፡፡ ኑሮ እና ሕይወቴ ግን ማዕረግ አልባ ነው፡፡ ደሞዜ ሁለት ሺሕ ስ ድስት መቶ ብር ይደርሳል፡፡ ይህ ብር ግር ማ ሞገሱ አፍ ይሞላል፡፡ ሲኖሩበት ግን ወ ፍ ነው፤ ይበራል፡፡ እውነት እውነት እላች ኋለሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድሮ የገቡትን ቃል እሳቸው ባያሟሉትም እኔ በራሴ ልወ ጣላቸው ብዬ በቀን ሦስቴ ያማረኝን ልብ ላ ብዬ በተውተረተርሁ ቁጥር ወር ሳይደር ስ በዱቤ እጥለቀለቃለሁ። አስተማሪ ካል በላና ካላነበበ ራሱንም ትውልድንም ይገድ ላል፡፡ በርግጥ ማንበብ ከተውኩ ዘመን የለ ኝም፡፡ መብላት ግን መተው የማኢቻል ኾ ኖብኝ ይኼው አለሁ። በደሞዜ ላይ 160 ብር የቤት አበል ጠብ ይደረግበታል፡፡ አንዲት አነስተኛ ክፍል ተ ከራይቼ፣ አነስተኛ ምግብ በልቼ፣ ጎረቤት ቲቪ እያየሁ እኖራለሁ፡፡ ለነገሩ የተከራየ ሁት ክፍል ብቻም ሳይኾን እውቀቴም አ ነስተኛ ነው፤ በግሌ ለዩነቨርሲቲ መምህር ነት የሚያበቃ ዝግጅትም ኾነ ክምችት ኖ ሮኝ አያውቅም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ት ችላለህ ካለኝ ግን ምን አደርገዋለሁ፡፡ ለም ን መንግሥትን “ዋሾ” አስብላለሁ፡፡ ትችላ ለህ ካለኝ እችላለሁ፡፡ እኔ ከመንግሥቴ በ ላይ ስለ’ኔ ካወቅኩ ቡዳ ነኝ ማለት ነው፡፡ የገጠር የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ በመኾኔ ብቻ ሰዎች ትልልቅ ጉዳዮችን ያማክሩኛ ል። እናቴ ሲያማት ሐኪም ቤት ሄዳ ላል ተፈለገ ወጪ መዳረግ አትወድም፡፡ የተማ ረ ልጅ አለኝ እያለች ሰፈራችን አቅራቢያ በ ሚገኝ “ኪዮክስ” እየሄደች “ሚስኮል” ታደ ርግልኛለች፡፡ ለእርሷ እኔ ዶክተርም ጭም ር ነኝ፡፡ እስካሁን ያልተገለጠላት ነገር ቢ ኖር ለምን በየወሩ ብዙ ብር እንደማልክላ ት ነው፡፡ ለምን ትልቅ ቤት እንደማልገዛላ ትም በደንብ አልገባትም፡፡ ግን ተስፋ ታደ ርጋለች፡፡ በእውነት እላችኋለሁ እንኳን ቤ ት ባለቆቡን ሚስማር ልገዛላት አልችልም፡ ፡ ለእማዬ ግን ይህን ማስረዳት ቅስሟን መ ስበር ነው፡፡ አሁን አሁን ዩኒቨርሲቲ ማስተማሬን ተከ ትሎ ሰዎች በተዘዋዋሪ በሚያሳዩኝ አክብ ሮት እጅግ እየተሰቃየሁኝ እገኛለሁ፡፡ ቢያ ንስ ክብሬን የሚስተካከል ብር ሊኖረኝ ይገ ባል ስል አስባለሁ፡፡ በዚህ ረገድ መንግሥ ትን ተቀይሜዋለሁ፡፡ ደመወዝ እጨምራ ለሁ እያለ ሲያወራና ሲያስወራ ይኸው ስ ንት ዘመኑ፡፡ አብረውኝ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋራ በትርፍ ሰዓታችን ስለ ደመወዝ ጭማሪ ማ ውራት አይታክተንም፡፡ ሁለት ዓመት ሙ ሉ እንዴት ሰው ስለደሞዝ ጭማሪ ብቻ ያ ወራል? ወሬውን ማን እንደፈጠረው አላ ውቅም፡፡ ሆኖም ከአጎራባች ዩኒቨርስቲዎ ች እንደተሰማ እገምታለሁ፡፡ ወይም ደግ ሞ ለማስተርስ ትምህርት አዲስ አበባ ሄደ ው የተመለሱ መምህራን ወሬውን ከዲግሪ ያቸው ጋራ ይዘውት መጥተው ሊኾን ይች ላል የሚል መላምት አለ፡፡ ምንም ይኹን ምን እንዴት ለሁለት ዓመ ት ሰው አንድ ወሬ ያመነዥካል? ደመወዝ ጭማሪ፤ ደመወዝ ጭማሪ፣ ደመወዝ ጭ ማሪ. . .፡፡ አንድ ወቅት ሁላችንም ተሰላች ተን ይህን ጉዳይ ላናነሳ ተማምለን ነበር፡፡ አዲስ የተቀጠረ አንድ “ጥላቢስ” የኾነ አ ስተማሪ “ጓደኛዬ ጋዜጣ ላይ ደመወዝ እ ንደሚጨመር አነበበ” ብሎ በማውራቱ የ ደመወዝ ወሬ በዩኒቨርሲቲው ዳግም አገረ ሸ፡፡ ጋዜጣውን አነበበ የተባለውን ልጅ ስ ልክ እንዲሰጠን ተማጸንነው፡፡ በጄ አላለ ም፡፡ “ላውድስፒከር” አድርጎ ራሱ ጓደኛ ውን እንዲያወራው ለመንነው፡፡ በሰበብ ላ ይ ሰበብ እያበዛ ነገ ዛሬ እያለ አሸን፡፡ በዚ ሁ ተናደን አገለልነው፡፡ ሲያንሰው ነው፤ በ ሰው ሕይወት ይቀልዳል እንዴ፡፡ ገጠር ው ስጥ ማግለልን የመሰለ ቅጣት አይገኝም፡፡

<<< ወደ 14 ሚሊዩን የሚጠጋ ህዝብ ይህንን ካርድ ለማግኘት እ.ኤ.አ በ2010 የዲቪ ማመልከቻ ሞልቷል

ዲቪ እና ሲቪ አሮን ፀሐዬ- አዲስ ነገር ኦንላይን

መርያ ጊዜ የገጠር ሕይወቴ በተስፋ ተሞላ ች፡፡ ሌሊቱን ደስ ደስ የሚሉ ህልሞችን አየ ሁ፡፡ በተከታታይ ያየኋቸው ህልሞች መቼ ታቸው ሁሉ በአሜሪካ ከተሞች ላይ ኾነ፡፡ በነጋታው ጠዋት ስነቃ ግን ሞራሌና ወኔ ዬ ከዳኝ፡፡ እንዴት ዲቪ እሞላለሁ፡፡ የት ሄጄ እሞላለሁ፡፡ ሰው ቢያየኝስ፡፡ ደግሞ የ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እንደ ተራ ሰው ዲቪ ይሞላል እንዴ! በመሠረቱ ዲቪ ከእኔ ስብእና ጋራ በፍፁ ም አይሄድም፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ መለመን ና የሰው መመኘት አልወድም፡፡ እናቴ እን ጀራ ከጎረቤት ተበድረህ ይዘህ ና ስትለኝ እ ንኳ በጀ ብያት አላውቅም፡፡ ጦሜን ማደ ር እመርጣለሁ፡፡ ትምህርት ቤትም ቢኾን ላጲስ ተውሼ አላውቅም፡፡ የተሳሳትኩትን ጽሑፍ በምራቄ አክኬ ፈትጌ አጠፋለሁ፡፡ እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እውነ ቱ ይኸው ነው፡፡ ሁለተኛ ክፍል አብረው ኝ ይቀመጡ የነበሩ ልጆችን መቅረጫ ብያ ቸው አላውቅም፡፡ እርሳሴን ከግድግዳ ጋ ር እያፋጨሁ አሾላለሁ፤ እቀርጻለሁ፡፡አሁ ንም እከካም ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ግን እ ውነታው ይኸው ነው፡፡ ዲቪ አገርህን ትተህ የሰው አገር አኑሩኝ እያልክ የምትለማመጥበት ሕጋዊ ማመል ከቻ ነው፡፡ ይህን ማመልከቻ ሞላሁ ማለ ት የአሜሪካ መንግሥትን ተንበርክኬ ውለ ታ ዋልልኝ እያልኩት ነው ማለት ነው፡፡ ይ ህ ደግሞ ፍፁም ከኔ አፈጣጠር እና ስብዕ ና ጋራ አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡ የአሜሪ ካ መንግሥትን በማመልከቻ ከምለምን በ እግር ወደ አሜሪካ ብሄድ ይቀለኛል፡፡ የዲ ቪ መሙላት ሐሳብ ውስጤ ላይ ከፍተኛ መናወጥን ሊያስከትል የቻለው በዚህ የተነ ሳ ነው፡፡ ራሴን የከዳሁት ያህል ተሰማኝ፡፡ የተፈጠረብኝን ድብታና የስሜት መላሸ ቅ ለማስታገስ የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ሄድ ኩኝ፡፡ የዲቪ ወሬን እንዴት ብዬ እንደማ ነሳባቸው እያውጠነጠንኩ፡፡ ቀድሜ ጉዳ ዩን እኔው ካነሳሁት “አጅሬው! ዲቪ ሞላ ሽ እንዴ” እያሉ ዓመቱን ሙሉ መዘባበቻ ሊያደርጉኝ ይችላሉ፡፡ በዘዴ ነገሩን ማንሳ ት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ዘወትር የምንጎ ለትበት ቦታ ደረስኩ፡፡ ሁሉንም እዚያው

ተሰብስበው አገኘኋቸው፡፡ ያው እንደተለ መደው የደሞዝ ጭማሪን ጉዳይ እያመነዠ ኩ ነበር፡፡ ጋሽ ግርማ ወ/ጊየርጊስ በፓርላ ማ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ የደሞዝ ጭ ማሪ ጉዳይን አንስተዋል የሚል አዲስ መ ረጃ በመሰማቱ የሁሉም ፊት ፈካ ፈካ እ ንዳለ ለማስተዋል ቻልኩ፡፡ ኾኖም ጭማ ሪው ለዩነቨርሲቲ መምህራን ብቻ ሳይኾን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሠራተኛ መኾኑ ከጥ ቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አንዳንድ ሂሳ ብ-ዘመም መምህራን ለጉባዔው ለማስረዳ ት ሞከሩ፡፡ በደስታችን ላይ ዉኃ ቸለሱበ ት፡፡ የደሞዝ ጭማሪው ወሬ እየበረደ ሲ መጣ የዲቪውን ጉዳይ ለኮስ ማድረግ እን ዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ “አናንተ! የዘንድሮ ተማሪዎች ደግሞ ጭ ራሽ የእንግሊዝኛ ፊደል ሳይጨርሱ ነው እ ንዴ ዩኒቨርስቲ የላኳቸው?” አልኩ ድምፄ ን ጎላ አድርጌ፡፡ ቀጥል የሚል ምልክት ተ ሰጠኝ፡፡ አንዱ ስሙን ሲጽፍ አይቼው በ ጭራሽ “ቫውል” አይጠቀምም፤ ታምናላች ሁ? ስሙ ተሻለ ነው፡፡ እንዴት “ስፔል” እ ንዳደረገ ታውቃለህ “ቲ፣ኤስ፣ኤች፣ኤል”፡ ፡ ባወራሁት ነገር ማንም አልተገረመም፡፡ ይልቁንም ሁሉም ከዚህ የባሰ የሚሉትን እ ያነሱ ማስረዳት ጀመሩ፡፡ አሁን ወደ ዲቪ ው ጉዳይ መግቢያ ሰዓት እንደኾነ ተሰማ ኝ፡፡ የ“ስፔሊንጓን” ወሬ ኾነ ብዬ እንጀመ ርኳት አልገባቸውም፡፡ “ስሙኝማ! ከተማ ትናንት ተለጥፎ ያየሁ ትን ልንገራችሁ፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚለ ው ጽሑፍ ላይ “Good Luck” የሚለውን ቃል እንዴት ጽፈውት ዐየሁ መሰላችሁ፣ “Good Lack”፡፡” ከገመትኩት በላይ ሳቁ ልኝ፡፡ ሳቃቸው እንደበረደ ከመሐላችን አ ንዱ “ዲቪ ተጀመረ እንዴ?” ሲል ጠየቀ፡ ፡ በቀጥታ ሊመልስለት የደፈረ ግን አልነ በረም፡፡ ቀለል አድርገው፣ “እኔንጃ”፣ “መ ሰለኝ”፣ “ኸረ!”፣ “ይባላል” አሉ፤ የተወሰኑ ት፡፡ አውቀው ነው፡፡ ሁሉም መቼ እንደተጀ መረ አይደለም ስንት ሰዓት ላይ እንደተጀ መረ ያውቃሉ፡፡ ዲቪ ሞላ ላለመባል ነው፡ ፡ ተነቃቅተናል፡፡

ዲቪ በቁጥር

7.67 ሚሊዮን

ባንግላዴሻውያን ዲቪ ሎተሪን በመሙላት እ.ኤ.አ በ2010 የመሪነት ደረጃውን ተቆጣጥረዋል

58,0000

ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ በ2010 ዲቪ ሞልተዋል። ግማሽ ሚሊዮን የደረሰው የኢትዮጵያውያን አመልካቾች ቁጥር ከዓለም በአራተኛነት ተመዝግቧል።

50,000

ዕድለኞች ብቻ ናቸው በዓመት ዲቪ ሎተሪን ማሸነፍ የሚችሉት

8,752

ጋናውያን እ.ኤ.አ በ2010 ዲቪን በማሸነፍ ከዓለም አንደኛ ሲሆኑ ጎረቤታቸው ናይጄሪያውያን በሁለተኛነት ተከትለዋቸዋል።

7%

ከአንድ ሀገር የሚመረጡ የዲቪ ዕድ ለኞች ቁጥራቸው ከአጠቃላይ አሸና ፊዎች ከሰባት በመቶ በላይ እንዳይበ ልጥ ገደብ ይጣልበታል ምንጭ፦ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ስቴት ዲፓርትመንት፣

DV regardless of CV ያለንባት ከተማ በኦባማ ፎቶዎች ከተጥ ለቀለቀች ሁለት ሳምንታት አልፈዋታል፡፡ ዲቪ እንሞላለን የሚሉ ማስታወቂያዎች የ ትም ነው የተሰቀሉት፡፡ ከሁሉም የገረመኝ ግን ይህን ማስታወቂያ ዩኒቨርስቲያችን ው ስጥ በትልቅ ባነር ተሰቅሎ ማየቴ ነው፡፡ የ ተማሪዎች ካውንስል በቅናሽ ዋጋ ዲቪ መ ሙላት በመጀመሩ የካፌ ሰልፍን የሚያስን ቅ ረዣዥም ሰልፎች በዩኒቨርስቲው ተፈ ጥረዋል፡፡ ዲቪ ለመሙላት ረዥም ሰልፍ፡ ፡ ልክ አዲሳባ ኢሚግሬሽን ጠዋት ጠዋት አየው የነበረውን ሰልፍ አስታወሰኝ፡፡ ይህ ን ያየሁ ቀን ከፍተኛ ድንጋጤም ከፍተኛ ግርምትም ተፈጠረብኝ፡፡

ነገሩ ስላስደነቀኝ ተጨማሪ ነገር ለማግ ኘት በዩኒቨርስቲው ግቢ መዘዋወር ጀመ ርኩ፡፡ የዲቪ ማስታወቂያዎች በተማሪዎ ች ካፌ፣ በመማርያ ክፍሎች ደጅ ባሉ የ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ወዘተ ተለጣጥፎ አየሁ፡፡ የማስ ታወቂያው ይዘት ተማሪዎች ዕድሉ እንዳ ያመልጣቸው እና እንዲጠቀሙበት የሚያ ባብል ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል ነው ይህንን የሚስተባብረው፡፡ በኔ ጊዜ የነበረ ው የተማሪዎች ካውንስል የመንግሥት ለ ውጥ እንዲመጣ ያስተባብር እንደነበር ት ዝ አለኝ፡፡ ወደራሴ ጉዳይ ተመለስኩ፡፡ በእርግጥ አ ሳፋሪ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሳያውቅ ዲቪ መሙላት አለብኝ፡፡ እንዴት? በትንሽ ከተ ማ ውስጥ እንኳን እኔ ያለሰፈሯ የመጣች ዝንብ እንኳ ትታወቃለች፡፡ ለማንኛውም አማራጮችን ለማየት ከዩኒቨርሲቲው ወደ መሀል ከተማ የሚወስድ ታክሲ ለመያዝ ተንቀሳቀስኩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዋና በር ላይ ታክሲው እስኪሞላ ብዙ ነገር ለመታዘብ ቻልኩ፡፡ ቀድሞ የተማሪ “ሃንድአውት” በ ማባዛት ይጠመዱ የነበሩ ፎቶኮፒ ቤቶች መስኮቶቻቸው በዲቪ ማስታወቂያ አሸብ ርቋል፡፡ እዚህም ዲቪ ለመሙላት ብዙ ተ ማሪዎች ተሰልፈዋል፡፡ በእጆቻቸው የሚ ባዙ ሃንድ አውቶች ሳይኾን የዲቪ ፎርሞ ችን ነበር የያዙት፡፡ ከተማ ደርሼ ከታክሲው እንደወርድኩ ወደ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ጎራ አልኩኝ፡ ፡ ከተደረደሩት ኮምፒውተሮች ወደ አንዱ ጠጋ ብዬ ኢንተርኔት የምበረብር መስዬ የ ቤቱን ደንበኞች መበርበር ጀመርኩ፡፡ ሰዎ ች ነጭ አቡጀዲ እየተደገፉ በወረፋ ፎቶ “ቀጭ” ይደረጋሉ፡፡ ብዙ ወጣቶች፣ ጥቂ ት ጎልማሶች፣ ጥቂት ትልልቅ ሰዎች፣ ባል ና ሚስት፣ ባል ሚስት እና ሰባት ልጆቻቸ ው፣ ጋዝ ልትገዛ የተላከች የቤት ሰራተኛ፣ መካኒክ ከነሽርጡ፣ ያስተማርኳቸው ተማ ሪዎች ወዘተ፣ ቤቱ የማያስተናግደው ዐይነ ት ሰው የለም፡፡ ሁሉም ለዲቪ የጭንቅ አ ማላጇን ስም ይጠራል፡፡ ይህ ሕዝብ አገሪ ቱን አይፈልጋትም እንዴ፡፡ ለምን አንድነ ቱን በግልፅ ጨረታ ሽጧት አይሄድም?

በዚህ ኢንተርኔት ቤት ጠረጴዛ ላይ ዲቪ የተሞላበት ወረቀት ተከምሯል፡፡ በአመቱ መጨረሻ የማርማቸውን የተማሪዎቼን ፈ ተና ወረቀቶች አስታወሰኝ፡፡ ለነገሩ የዚህ ን ዘመን ተማሪዎች ፈተና ከማረም የሰሊ ጥ እርሻ ማረም ይሻላል፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን የዲቪ ክምር ማረም ሳይሻል አይቀ ርም፡፡ ሁለቱም ‹‹ስቤሊንግ›› ማረም ስለሆ ነ ብዙም አይራራቁም፡፡ የአሜሪካ መንግስ ት ዲቪ አራሚ አድርጎ ቢቀጥረኝስ ብዬ አ ሰብኩ፤ ለአፍታ፡፡ ሐሳቤ በራሱ ፈገግ አሰ ኘኝ፡፡ አይ አሜሪካ ስላንቺ ማሰብ በራሱ ፈገግታን ይፈጥራል ለካ፡፡ በዚህ ኢንተርኔት ካፌ ብዙ ሰው ዲቪ ለ መሙላት የሚሽቀዳደመው ከዚህ ቀደም በዚህ ቤት ዲቪ የሞሉ አራት የከተማዋ ነ ዋሪዎች ዲቪ ደርሷቸዋል በመባሉ ነው፡፡ ገድ አለው ይባላል ይህ ቤት፡፡ ወደራሴ ጉዳይ ልመለስ፡፡ ዘንድሮ እንዴ ትም ብዬ ዲቪ መሙላት እንዳለብኝ የተነ ጋገርን መሰለኝ፡፡ ስለዚህ እዚሁ ገድ አለ ው የሚባልለት ቤት ለምን አልሞላም፡፡ የ ማስተምራቸው ልጆችና የሚያውቀኝ ሰው በቤቱ አንደሌለ ሳረጋግጥ ፎቶ የምታነሳዋ ን ልጅ ዲቪ መሙላት ፈልጌ እንደመጣሁ ነገርኳት፤ የሞት ሞቴን፤ በሹክሹክታ፡፡ “ይቻላል፣ አስር ብር ከፍለህ ፎቶ ትነሳ ና ይህን ፎርም ሞልተህ ነገ ማረጋገጫ እ ንሰጥኻለን፡፡” አለችኝ ጮኽ ብላ፡፡አሳቀቀ ችኝ፤ምን አለ እኔ እንደማወራው ቀስ ብ ላ ብታወራ፡፡ ተማሪዎቼ እንዲሰሙ ነው? ምቀኛ! እንደተረዳሁት ከሆነ የኢንተርኔት ፍጥነ ቱ ቀን ቀን ቀርፋፋ ስለሆነ ኢንተርኔት ቤ ቶቹ ዲቪ ፎርሙን በወረቀት ብቻ እያስሞ ሉ ሌሊት ሌሊት በኢንተርኔት ይልኩታል፡ ፡ በነጭ ወረቀት ለሞሉት ሰዎች በነጋታው የማረጋገጫ ደብዳቤ ይታደላቸዋል፡፡ በዚ ህ መሀል የስም ስህተት ቢከሰት ግን ማን ተጠያቂ እንደሚሆን አልገባኝም፡፡ እድሌ ን ማበላሸት የለብኝም፡፡ “እመለሳለሁ” አ ልኩና ሹልክ ብዬ ወጣሁ፡፡ በከተማዋ ያሉ ሁሉም ኢንተርኔት ቤቶች ደንበኞቹ እያዩ ዲቪ እንደማይልኩ ተረዳ ሁ፡፡ ይህ መልካም ነገር አይደለም፡፡ ስለዚ ህ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ በከተ ማዋ ወደሚገኘው አንድዬ ፖስታ ቤት አ መራሁ፡፡ በሩ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅና ፀ ብ የሚመስል ግርግር አየሁ፡፡ በቅርቤ ያገ ኘኃትን የገጠር ልጅ ስለጉዳዩ ጠየቅኳት፡፡ ዲቪ ለመሙላት ጠዋት ወረፋ የያዙ ሰዎ ች ጎረምሶች ያለወረፋቸው እየገቡ አስቸግ ረዋቸው ረብሻ እንደተፈጠረ ነገረችኝ፡፡ የ ፖስታ ቤቱ ሰራተኞች ደግሞ በስነስርዓት ወረፋ ካልተያዘ አናስተናግድም ብለው ማ መፃቸውን ጨምራ አብራራችልኝ፡፡ ፖስታ ቤት በር ላይ ያሉትን ማስታወቅ ያዎች ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ዲቪ ዘንድሮ ለአንድ ወር ብቻ እንደሚቆይ፣ የቀሩት ቀ ናት ጥቂት እንደሆኑ፣ ዲቪ በፖስታ ቤት መሙላት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት፣ ለም ሳሌ ዲቪው ሲመጣ የስም ስህተት ቢኖረ ው ፖስታ ቤት ለአሜሪካ ኤምባሲ ቀጭ ን ደብዳቤ የመፃፍ ብቸኛ ባለመብት እን ደሆነ ወዘተ ይናዘዛል፡፡ፖስታ ቤት መንግ ስታዊ ድርጅት ነው፡፡ ዜጎቹን በተዘዋዋሪ ሌላ አገር እንዲሄዱ ተግቶ እየሰራ እንደሆ ነ ነቃሁበት፡፡ ለነገሩ እኔ ብቻ ሳልሆን የመንግስት ባለስ ልጣናትም ዲቪ ይሞላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ዲቪ ደርሷ ቸው ቀስ ብለው ሊሄዱ ሲሉ አይደል እ ንዴ የተደረሰባቸው፡፡ እኔ የምሰራበት ዩኒ ቨርሲቲ የ‹‹ሪሰርች›› ፕሬዝዳንትም ሰሞኑን ዲቪ ሲሞሉ እንደታዩ በወሬ ወሬ ሰምቻለ ሁ፡፡ ሰውየው እድሜያቸው ገፍቷል እኮ፡፡ በዚያ ላይ አሜሪካ ነው የተማሩት ሲባል ነ በር፡፡ ተንቀዥቅዠው መጥተው ነው ጉድ የሆኑት ማለት ነው፡፡ ዲቪ ሲቪ እንደማይ መርጥ ተረዳሁ፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዲቪ መሙላት ይፈልጋል፡፡ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሚባለው ውስጥ ደግሞ እኔ እገኛለሁ፡፡ ስለዚህ ዲቪ እሞላለሁ፡፡ ቅድም ወደነበር ኩነት ኢንተርኔት ካፌ ሄድኩኝ፡፡ ፈገግ ብ ዬ ፎቶ ተነሳሁ፡፡ኮስተር ብዬ ፎርሙን ሞ ላሁ፡፡ ከኢንተርኔት ቤቱ ስወጣ ከሸሌ ጋር ያደርኩ ያህል ቀፋፊ ስሜት ተሰማኝ፡፡ አ ገሬ ኢትዮጵያ ሆይ አንቺም ዲቪ ሞልተሸ ብትሄጂ ይሻልሻል አልኩ በሆዴ፡፡


18

ሀበሻ በምስራቅ አፍሪካውያን ዓይን

ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ኢትዮጵያውያን ባያገልሉ ጥሩዎች ነበሩ

ፒተር ኦክዋሊንጋ *

ግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው አድርጎ ፈጠረው የሚለው ቃል በሰዎች መካከል ያሉ ተመሳሳይነቶችን እና ልዩነቶችን እስክ ንመለከት ድረስ እንደ አፈ ታሪክ የሚቆጠር ነበር። ዓለማችን ቁጥራቸው የበዛ ጎሳዎች የሚርመሰመሱ ባት፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም እና ሃይማኖት ባላቸው ሰዎች የተሞላች ነች። ስለ እነዚህ ሰዎች ግን አብራ ችሁ መኖር እስክትጀምሩ ድረስ የምታውቁት ነገር ጥቂት ብቻ ነው። ባለፉት ዓመታት ዩጋንዳ የስደተ ኞች መናኸሪያ በመኾን አገልግላለች። ከታላላቅ ሐ ይቆች አካባቢ የሚመጡ ስደተኞችንም አስተናግዳ ለች። የኢትዮጵያውያን በኡጋንዳ መገኘት ግን ሁሌ ም ተፈላጊ ነው።

ማህበራዊ ህይወት ኢትዮጵያዊ ጓደኛዬ ስለ አገሬ እንዲህ አለኝ “ዩጋን ዳ በዓለም ላይ ካሉ አገሮች ነጻነት የተሞላባት አገር ናት።” ይህን ሲነግረኝ ከፊቱ ላይ ምቾት እና መፍለ

መታመኔ ለዚህ... ከገጽ 9 የዞረ ... ምነት አለኝ፡፡ ከምንም በላይ መታመንን በ ጣም እፈልገዋለሁ፡፡በመታመኔም እዚህ ደ ርሻለሁ፡፡ሰዎች በስም አውቀው ብቻ እቃ በዱቤ ይሰጡኛል፡፡ ያንን እቃ ሸጬ እመ ልሳለሁ፡፡ በዚህ በኩል በተለይ እዚህ ደረ ጃ እንድደርስ በጣም የረዳኝ አሁን ካናዳ የ ሚገኝ አቶ ቹቹ የሚባል ሰው አለ፡፡ እቃዎ ችን በሙሉ በዱቤ ሰጥቶኝ ሸጬ እመልሳ ለሁ፡፡ በዚያ ላይ በጣም በብዙ ሚሊየኖች ነው የማንቀሳቅሰው፡፡ አቶ ንጉሴ የሚባል ም እንዲሁ ቀይ ልሁን ጥቁር ሳያውቀኝ ለ ሁለት ዓመት ያክል በስልክ ብቻ እየተገናኘ ን በዱቤ እቃዎችን ይሰጠኝ ነበር፡፡ እንዲ ሁም አቶ ይደግ ከናይሮቢ እዚህ ደረጃ እን ድደርስ ብሎም ለህይወቴ ከፍተኛ እገዛ አ ድርገውልኛል፡፡እናም እምነትን በጣም እ ወደዋለሁ፡፡ መታመንን እግዚአብሔር የሰ ጠኝ ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ለወደፊቱም እን ዳይቀይርብኝ ምፈልገው እምነትን ነው፡፡ እምነት ካለ ሁሉም ነገር አለ፡፡ መታመን በእግዚአብሔር፡መታመን በራስ፡ መታመ ን በሰዎች ዘንድ ካለ ሁሉ ነገር አለ፡፡አሁን በህይወቴ ከሚገባው በላይ ደስተኛ ነኝ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡ ያኔ የቤት ኪራይ እንኳ ን ለመክፈል እስከመቸገር የደርሰችው ፍቅርተ እዚህ ትደርሳለች ብለሽ ታስ ቢ ነበር? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- የቤት ኪራይን ተወ ው፡፡ የምትበላው እንኳን …የሰው ቤት ድ ረስ የተቀጠርኩት እኮ ለዚያ ነው፡፡ ግን ደ ግሞ ትልቁ ነገር ስራን አለመናቅ ነው፡፡ እ ሰታውሳለሁ በቤተክርስቲያን ስርዓት ከገ ባሁት ባለቤቴ ጋር አንድ ቀን አብረን አላ ደርንም፡፡አላውቅም የሞራል መውደቅ ነበ ር፡፡ የአእምሮ መነካት ነበር፡፡የበታችነት ስ ሜት ነበር፡፡ በተለይ በሴት ልጅ ላይ እን ዲህ አይነት ነገር ሲፈጸም ምን ሊሆን እን ደሚችል መገመት ቀላል ነው፡፡ከዚያ በኋ ላ ሰው ሱቅ ሁሉ መጥቶ አንች ነሽ ፍቅርተ ይሉኛል አዎ እላቸዋለሁ አንች ነበርሽ የየከ ሌ ሚስት… በቃ እንደዚህ፡፡ይህ ሁሉ ግን

ቅለቅ ይነበብበት ነበር። በዚህ የተጀመረው ጓደኝነ ታችን እየጠነከረ መጥቶ እንዲህ ነው ብዬ ልኩን ከ ምገልጸው በላይ እየፈካ መጥቷል። ወዳጅነታችን እ ና ዝምድናችን ከቤተሰብ የሚመዘዝ ሳይኾን ከመግ ባባት የመነጨ ነው። ከኢትዮጵያውያን ጋራ ይህን የመሰለ ጓደኝነት እን ዳለኝ ስገልጽ ጥሩ ማሕበራዊ ግንኙነት የሚኖረኝ ይ መስላችኹ ይኾናል። ኢትዮጵያውያን የሚያደርሱ ትን መገለል ያልቀመሰ ነው ይህን ሊል የሚችለው። የትም ቦታ በግልጽ እንደሚታየው ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን ማሳለፍ የሚፈልጉት ከራሳቸው ሰው ጋ ራ ብቻ ነው። ያኔ ነው ለስላሳ እና ረጋ ያሉ ናቸው ብ ዬ ከምገምታቸው ኢትዮጵያውያን ጀርባ ሌላ እውነ ታ እንዳለ የተረዳኹት። ማሕበራዊ ቅርበቱ ወደ ሴቶቹ ሲመጣ ይበልጥ እያ ራቀ ይሄዳል። ከምዕራብ ዩጋንዳ የመጣው እና ሙ ሱዙንጊ የተሰኘው ጓደኛዬ ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶ ች ያለውን ላካፍላችሁ። “ኢትዮጵያዊ የሴት ጓደኛ ማግኘት ከአለት ውሃ እንደመጭመቅ ነው” ነበር ያ ለው። ሴቶቹ ለምን እንደዚያ እንደኾኑ ደግሞ ምክ ንያቱን ያውቀዋል። “ሴቶቹ ከባህላቸው ጋራ እጅጉ ን የተጣበቁ ናቸው” ይላል። በዩጋንዳ ማንኛውም ሰ ው የፍቅር ግንኙነት መመሥረት ይችላል። ቀለም እ ና ጎሳ እንቅፋት አይደሉም። ለዚህም ነው ዩጋንዳዊ ወንዶች ከኢትዮጵያ ሴቶች ጋራ ከሚኖራቸው ግን ኙነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ ወንዶች ከዩጋንዳ ሴቶች ጋ ራ በቀላሉ ግንኙነት የሚመሠርቱት። እንዲህም ኾ ኖ ዩጋንዳውያን በ“ለስላሳዎቹ” ኢትዮጵያዊ ሴቶች ከመማረክ ወደ ኋላ አላሉም። ወደ ሰላምታ አሰጣጣቸው ልሻገር። ወንዶቹ እጅ ለእጅ ይጨባበጡና ትከሻቸውን ያጋጫሉ። ጠንካ ራ ወዳጅነታቸውን የሚያሳየው ይኼ የሰላምታ አሰ ጣጥ በሴቶቻቸው ላይም ይንጸባረቃል። ሴቶቹ ይ ተቃቀፉና ጉንጫቸውን በስሱ ይሳሳማሉ። ይህ ሰ ላምታቸው በከተሞች አካባቢ ለሚኖሩ ዩጋንዳውያ ን እንግዳ ነገር አይደለም። ከከተሞች ውጭ ግን ያ ልተለመደ ነው። እንዲያውም በሁሉም የዩጋንዳ ባ

በውስጤ ጠንካራ እንድሆን አደረገኝ፡፡አን ድ ጊዜ አስታውሳለሁ እንደዚህ አይነት ቤ ት ስራ ተቀጠርኩ ስለው እዚያ ቤት መሄ ድ አቆመ፡፡ ከዚያ ምነው ሲሉት እሷ ሰራ ተኛ የገባችበት ቤት እንዴት እሰደባለሁ ይ ል ነበር፡፡ ያ ነገር የበለጠ እንድተጋና የስራ ክቡርነትን ፤ የሴትነትን ጠንካራ እንዳሳይ አደረገኝ፡፡እኔ ስራ አለመናቄ ለእሱ ውርደ ት ከሆነበት እኔ ደግሞ በስራየ እቀጥላለሁ አልኩ፡፡ይህ ውሳኔየ ዛሬ ትልቅ ቦታ እንድ ደረስ አደረገኝ፡፡ የእኔና የባለቤቴ ግንኑነት ም ያኔ አበቃ፡፡ ሰዎች ለምን ያገኛችሁትን እየበላችሁ አንድ ላይ አትኖሩም ሲሉት እ ንዴት የቤት ኪራይ እየከፈልኩ እሷን አስ ተዳድራለሁ ይል ነበር፡፡ ያ ነገር የሩቅ ቢ መስልም ለእኔ የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ሁሌ ም ጆሮየ ውስጥ ያቃጭላል፡፡ የተጣለች ሴ ት ነበርኩ፡፡ በዚያ ወቅት እነ ማሜ(የኢት ዮጵያ መንደር ምግቤት ባለቤት)ና ሌሎች ም አይዞሽ በርቺ ይሉኝ ነበር፡፡ ሰው በሞራ ል እየመጣ እቃ ይገዛኛል፡፡ስለሁሉም ነገር

ህል ማለት ይቻላል ከተቃራኒ ጾታ ወይም ከአማት ጋራ የሚደረግ የሰውነት ንክኪ ወይም መተቃቀፍ ነ ውር ነው። ቀለል አሊያም ጠበቅ ያለ የእጅ መጨባ በጥ ለተራዎቹ ዩጋንዳውያን ሴቶች እና ወንዶች (በ ገጠር ለሚኖሩት ጭምር) ተቀባይነት ያለው ነው።

ቶች እንዲማረኩ የሚያደርጋቸው። ከልጅነታቸው ጀምሮ እየተንከባከቡ የሚያቆዩት ጸጉራቸውም ለቋ ሚ ውበታቸው ሌላው መገለጫ ነው። በሰብዕና ደ ረጃ ከመዝንናቸው ደግሞ ኢትዮጵያውያን እንስቶ ች በራስ መተማመናቸው ከፍ ያለ፣ ተፈቃሪ እና በ ራሳቸው የሚቆሙ ናቸው።

ቁንጅና አካላዊ ውበትን አደንቃለሁ። በተደላደለ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ እንዳለ ሰው አካላዊ ውበት ብቻው ን ትርጉም እንደማይኖረው አውቃለሁ። ውስጣዊ ውበትም አስፈላጊ ነውና። በኢትዮጵያዊ ሴቶች ላይ በአብዛኛው የሚታዩ የውበት ቅንጣቶች ግለጽ ብባ ል ጸዳል ያለው ፈካ ያለ የቆዳ ቀለማቸውን፣ ጥቁር ዞማ ጸጉራቸውን፣ ለስላሳ እና ቀጠን ያለ ተክለ ቁመ ናቸውን እጠቅሳለሁ። እነዚህ የአካላዊ ውበት መገለ ጫዎች ናቸው የዩጋንዳ ወንዶችን በኢትዮጵያዊ ሴ

ኢትዮጵያዊ የሴት ጓደኛ ማግኘት ከአለት ውሃ እንደመጭመቅ ነው:: ሴቶቹ ከባህላቸው ጋር በጣሙኑ የተጣበቁ ናቸው።

እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡ በሰው ሀገር ስኬታማ መ ሆን ቀላል ነው ትያለሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- በጣም ከባድ ነገር አ ለው፡፡ ለምሳሌ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ይ ደውሉና እቃው መጥቷል አራግፊ እባላለ ሁ፡፡የሚቀጥሩኝ ደግሞ መሀል ከተማ ሊ ሆን ይችላል፡፡ በዚያ ላይ ሰው የለኝም፡፡ ብቸኛ ነበርኩ፡፡ መኪናው ላይ ወጥቼ እ ቃውን አራግፋለሁ፡፡ ምክንያቱም ካልተራ ገፈ በፖሊስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ብዙ ብዙ ችግር አለው፡፡ ሱቅ ውስጥ ተቀምጦ መሸ ጥማ በጣም ቀላሉ ነገር ነው፡፡አንዳንዴ እ ንቅልፍ ከማጣቴ የተነሳ ጧት ስነሳ ሰው ጉ ም መስሎ ይታየኛል፡፡ከዚያ በኋላ ግን ቀስ በቀስ የተወሰነውን ስራ ለሌሎችም ማጋራ ት ጀመርኩ፡፡ ምክንያቱም እኔ ሳገኝ ለሌላ ውም ማሰብ ስላለብኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ ስራው ከባድ ነው፡፡ ግን ተስፋ ካለቆረጡ ና ጠንክረው ከሰሩ ውጤታማ መሆን ይቻ ላል፡፡ ጠንካራ ሴት ደስ ትለኛለች፡፡ እኔም

ዓመት በዓሎች ኢትዮጵያውያን ጓደኞቼ እ.ኤ.አ መስከረም 12 ቀን 2011 የዘመን መለወጫ በዐላቸውን ያከብራሉ። በእ ነርሱ ዓመተ ምህረቱ 2004 ይኾናል። ይህ ለዩጋንዳ ውያን እንግዳ እና አስገራሚ ነው። የዘመን አቆጣጠ ራቸው በሰባት ዓመት ከስምንት ወር የዘገየ ነው። ለ ዩጋንዳውያን አዲስ ዓመት ማለት በየ12 ወራቱ ልዩነ ት የሚመጣ እና ማንም የሚያወቀው ነገር ነው። ያ ው በዓመቱ የመጀመሪያ ወር በኾነው ጥር፣ የመጀ መሪያ ቀን የሚከበር ነው። ርችት፣ ሙዚቃ፣ እንደ ውሃ የሚፈሰው መጠጥ፣ ጭፈራ እና ግርግር በበዐ ሉ ኹነኛ ስፍራ ይሰጣቸዋል። ዘመን መለወጫን እ ንዲህ ለሚያከብሩት ዩጋንዳውያን በመስከረም ላይ ሰዎች ተሰብስበው አዲስ አመት እንደሚያከብሩ ሲ ሰሙ የማይታመን ይኾንባቸዋል።

ምግብ እና መጠጥ አንድ ዩጋንዳዊ ቤተሰብ ወደ ቤቱ ለመጣ እንግዳ ምግብ አዘጋጅቶ የሚያቀርበው በቀላሉ ነው። ምግ ቡም “ማቶኬ” ወይም “ካሎ” ሊኾን ይችላል። ካሎን ለማታውቁ ከካሳቫ ወይም ከዳጉሳ ዱቄት የሚሠራ ምግብ ነው። ይህን ምግብ ግን ለኢትዮጵያዊ እንግ ዳችሁ ብታቀርቡለት ንክች አያደርገውም። የቀረበለ ትን የሚቀምስም ካለ ምናልባት ከምግቡ ጋር አብሮ የሚቀርበውን “ቻፓቲ” ወይም “ሾርባ” ለካክፎ ሊተ ወው ይችላል። አለበለዚያ ግን ባዶ ሆዳቸውን መሄ ድ ይመርጣሉ። በተቃራኒው ግን የእነርሱን “እንጀ ራ” እንድትቀምሱ የተቻላቸውን ጥረት ሁሉ ያደርጋ ሉ። በቀላሉ ሊግባቡ በሚችሉ ማሕበረሰቦች ውስጥ ያለ ትንሽ አለመግበባት ማለት ይኼ ነው።

ሁሌም ስራየን ማየት ስለስራየ ማሰብ ያረ ካኛል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ሱቅ እየመጡ ፍ ቅርተን ፈልገን ነበር ይሉኛል፡፡ እኔ ነኝ ፍ ቅርተ አልመስልም እንዴ እላቸዋለሁ፡፡ እ ንግዲህ እነሱ ሚጠብቁት ዘናጭ ፍቅርተን ይሆናል፡፡ እኔ ደግሞ ዝም ብየ ድብልብል ያልኩ ነገር(ረጅም ሳቅ…)

ሐበሻዊ ቃና፡ በትንሽ ገንዘብ ስራ መጀ መርም ሆነ ስኬታማ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ቢያማክሩሽ ምን ትያቸዋለሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- የራስ ተነሳሽነት መኖ ር አለበት፡፡ እኔ ጋር ብዙ ሰዎች ይመጣ ሉ፡፡ ምን እንስራ ይሉኛል፡፡አንዳንዴ ደር ሰህ እንዲህ ስሩ ማለት ይከብዳል፡፡ በራ ሳቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት የተመሰረተ ከ ሆነ ግን ውጤት ያስገኛል፡፡እንዲህም ሆ ኖ ያልተሰሩ ብዙ ነገሮች ስላሉ እነሱን እ ንዲሞክሩ እመክራቸዋለሁ፡፡አዲስ ስራ ሲ ሆን ትሰራበታለህ ታገኝበታለህ ብዙ ነገር ም ትማርበታለህ፡፡ ብዙ ገንዘብ ስለበዛ ስ ላልበዛ አይደለም፡፡ ቅድም ታማኝነት ብ

“እንጀራ” እና “ወጥ” ለመብላት ከምፈልጋቸው ም ግቦች መካከል ናቸው። “ወጥ” ወፍራም፣ በቅመም የተለወሰ ስጋ እና አትክልት የሚጨመርበት እንደኾ ነ አውቃለሁ። ይህም ጠፍጣፋ ከኾነው፣ ኾምጣጣ ጣዕም ካለው እና ለመብላት ከሚያስጎመጀው “እን ጀራ” ጋር ይቀርባል። ይህን መቅመስ እፈልጋለሁ። ዩጋንዳውያን ኢትዮጵያኖች የራሳቸውን አልኮል መጠጥ የሚያዘወትሩ አድርገው ይወስዷቸዋል። በ ዚያ ላይ እንዲዘወተር “የማይመከር” የትምባሆ ዐ ይነት እንደሚያጨሱ ያስባሉ። እነዚህን የሚጨሱ ነገሮች በቡና ቤቶች እና አልኮል መሸጫዎች ማዘ ውተራቸው ከዩጋንዳውያን ጋራ ያመሳስላቸዋል። ይህን የሚጨስ ነገር መውደዳቸው በተለይ ከዩጋ ንዳ ራስታዎች ጋራ በአንድ ገጽ ላይ ያስቀምጣቸዋ ል። በዐፄ ኃይለ ሥላሴ የሚያምኑ የዩጋንዳ ራስታዎ ች “ራስተፈሪያንስ” መነሻቸው ከኢትዮጵያ ነው ብ ለው ያምናሉ።

ንግድ ዕድሉን ካገኘ ተራው ኢትዮጵያዊ ከአቧራ “ወርቅ” ማውጣት ይችላል። ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ሠራ ተኞች፣ ሐይለኞች፣ ብልጣ ብልጦች እና የሚያዋጣ ንግድን የመለየት ችሎታ ያላቸው ናቸው። ጥሩ ከባ ቢ ካገኙ ወደ ባለጸጋነት በቶሎ የሚለወጡ ናቸው። ይህ የኢትዮጵያውያን ችሎታ ዩጋንዳውያን ለንግድ አጋርነት/ሽርካነት እንዲመርጧቸው ያደርጋቸዋል። በአጠቃላይ ዩጋንዳ ጨዋታ ወዳድ አገር ነች። ኢ ትዮጵያውን ለዚህ ቅመም መኾን ይችላሉ። ይህ ታ ዲያ ማግለላቸውን ከተዉት የሚመጣ ነው። ለኢት ዮጵያውያን ወንዶች ማለት የምፈልገው አንድ ነገር አለ። ይህ ቤታችሁ ነው። ማግባት ካለባችሁ ሴቶቻ ችን እንድታገቡ እጋብዛችኋለሁ። ለኢትዮጵያውያን እንስቶች ደግሞ ይህን እላለሁ። ነጻነት ይሰማችሁ። በቅጡ መወዳጀት እንችላለን። * ፒተር ኦክዋሊንጋ በፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ሥር በሚገኘው ዩጋንዳ ሚዲያ ሴንተር የሚሠሩ ናቸው

ስለእርሱ አጫውችን

የሃለሁ፡፡መታመን ከቻልክ ብዙውን ነገር በዱቤ ማንቀሳቀስ ትችላለህ፡፡ለምሳሌ እኔ ም እስከአሁን ይህንኑ እጠቀማለሁ፡፡ እቀ በላላሁ፡፡ እሸጣለሁ፡፡ እመልሳለሁ፡፡እኔ ሃ ሳቡን አካፍያቸው ከእኔም በብዙ ሚሊየኖ ች የሚቆጠር ገንዘብ በዱቤ የሚወስዱ ብ ዙ አሉ፡፡ለምሳሌ ደቡብ ሱዳን በብዛት እ ልካለሁ ግን አንዳንድ ጊዜ ከሚመጣው የ ሚቀረው ይበልጣል ፡፡ ስለዚህ መታመን ወሳኝነት አለው፡፡

ወይዘሮ ፍቅርተ፡- አዎ አራት ኪሎ ከእነ ሽመልስ አበራ ጆሮ፤ከእነ አልማዝ ልመን ህ፤መሰረት በቀለ፡ ስመኝ ግዛው ከሚባሉ የስነጽሁፍ ሰዎች ጋር የአንድ ክፍል ተማሪ ዎች ነበርን፡፡ አሁን የደራሲያን ማህበር ሊ ቀመንበር የሆነው ጌታቸው በለጠ፤ ደራሲ ና ገጣሚ ፀሀይ መላኩ ደግሞ መምህሮቼ ነበሩ፡፡እነሱ በሙያው ሲቀጥሉ እኔ ይሄው ልህ እሱን ትቼ ወደ ንግዱ አለም ገባሁ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡ ማህበራዊ ህይትሽ ምን ይመስላል?

ሐበሻዊ ቃና: ለየትኛው የስነጽሁፍ ዘ ርፍ ታደያለሽ?

ወይዘሮ ፍቅርተ፡-ማህበራዊ ህይወቴ ቆን ጆ ነው፡፡ እሁድ እለት የታመመ የወለደ ካ ለ እጠይቃለሁ፡፡ የሞተ ካለ ለቅሶ እደርሳ ለሁ፡፡ ካልቻልኩ ደግሞ በስልክ ይቅርታ ስጠይቃቸው ፍቅርተ በአንቺ ማን ቂም ይ ይዛል ይሉኛል፡፡እኔ ለህዝቡ ሳይሆን ህዝ ቡ ለእኔ ነው፡፡ እኔም የካምፓላን ህዝብ በ ፍቅር ነው ምወደው፡፡እቃ እንኳን ገዝተ ው ካልተስማማቸው መልሱት እላቸዋለ ሁ፡፡ ምክንያቱም ገንዘቡን እንዴት እንደ ሚመጡት ስለማውቅ እቃ በሚጨምርበ ት ሰዓት ስቅቅ እላለሁ፡፡ ነጋዴ ብሆንም ከህዝቡ ውስጥ እኔ አለሁ፡፡ከህዝቡ ልወ ጣ አልችልም፡፡ ከሰው ጋር መግባባት አይዞሽ በርቺ በር ታ መባባል ለእኔ ርካታ ይሰጠኛል፡፡ ከህይ ወቴ የተማርኩት ነገር ቢኖር በተለይ አንድ ሰው በተከፋ ሰዓት እነዚህ ቃላት እጅግ ጠ ቃሚ መሆናቸውን ነው፡፡ሰዎች እኔ ጋር ሲ መጡ የምላቸውም ይህንኑ ነው፡፡ አይዟች ሁ በርቱ እጅ አትስጡ፡፡ እኔም ቢሆን አገ ኘሁ ብየ አልኩራራም፡፡ ብዙ ጊዜ የምሄደ ው በእግሬ ወይም በቦዳ ነው ስለሆነ አንዳ ንድ ሰዎች ሲያገኙኝ “ፍቅርተ ዘንድሮም በ እግርሽ” ይሉኛል:: ለአለባበስ ለራስና ለመ ሳሰሉት ከመጨነቅ ይልቅ ብዙ ጊዜ ሀሳቤ ንና ጊዜየን ስራ ላይ ባጠፋ እመርጣለሁ፡፡ ይሄ ሞላ ይህች ጎደለች ሩጫየ እዚያ ላይ ነ ው፡፡ ልጆቼ የምላቸው መደርደሪያዎቼ በ ልተው እንዲያድሩ ማድረግ፡፡

ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ግጥም እጽፋለሁ፡፡ ግ ጥሞች አሉኝ ሌሎች ጽሁፎችም አልፎ አ ልፎ እጽፋለሁ፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡-ቅድም ስናወራ ስነጽሁ ፍ እንደተማርሽ ነግረሽኝ ነበር፡፡ እስኪ

ሐበሻዊ ቃና: የእረፍት ጊዜ ሲኖርሽ ምን ታደርጊያለሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡- ማታ ቤት ስገባ ዜና እ ከታተላለሁ፡፡ ማንኛውም ዜና ለእኔ ጠቃ ሚ ነው፡፡ መጀመሪያ የዚህን ሀገር(ኡጋን ዳን) ዜና አያለሁ ከዚያ ደግሞ የኢትዮጵ ያን ዜና እከታተላለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ከቻ ልኩ አነባለሁ ካቻለኩ እተኛለሁ፡፡አብዛኛ ውን ጊዜ ግን ሱቅ ቁጭ ስል መጽሄቶች አ ነባለሁ፡፡

ሐበሻወዊ ቃና፡ካነበብሻቸው መጽሃፍ ት የምታስታውሽው ይኖራል? ወይዘሮ ፍቅርተ፡-አዎ የፀሀይ መላኩ ቋሳ ና የበዓሉ ግርማ ከአድማስ ባሻገር፡፡ በተ ለይ ከአድማስ ባሻገር ውስጥ ‹‹ከሚያነቡ ጭንቅላቶች የሚሰሩ እጆች ደስ ይሉኛል›› የሚለው አባባል ከእኔ ህይወት ጋር የሚሄ ድ ይመስለኛል፡፡

ሐበሻዊ ቃና፡ የስደተኛ ህይወትን እን ዴት ትገልጭዋለሽ? ወይዘሮ ፍቅርተ፡-በጣም ከሚያሳዝነኝ ነ ገር አንዱ የስደተኛ ህይወት ነው፡፡ አሳዛኝ ም አለ፡፡ አስደሳችም አለ፡፡መካከለኛም አ ለ፡፡ የተለያየ ነው፡፡ በዋናነት ግን በሁለት የተከፈለ ነው ከተማ ያለውና ካምፕ ውስ ጥ ያለው፡፡ እዚህ(ከተማ ውስጥ)ካለው ስ ደት ግን ካምፕ ውስጥ ያለው ስደት በጣ ም የሚያሳዝን ህይወት አለው፡፡እኔም እን ዳየሁት፡፡


ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሀበሻዊ ቃና

19

ቢዝነስ ማን ምን እየሰራ ነው?

ፎቶ ዜድኤ.ኢአር ፒኤልሲ

የአስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ወደ ካምፓላ መጣ

በደቡብ ሱዳን ውስጥ ካሉ ሀገር በቀል አምስት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው “ቡፋሎ” ባንክ ላስመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይመሰክራሉ

የጎረቤቶች ጦርነት በ

በተስፋለም ወልደየስ

ርካታ ደቡብ ሱዳናውያን በብዙዎ ች ዘንድ ሙገሳ ያስገኘላቸውን የሪ ፈረንደም ሂደት ለጦርነት እንደተ ካሄደ የቀብር ሥነ ሥርዐት ቆጥረ ውታል። ምን ያህል በጦርነት እን ደተሰላቹ ከሪፈረንደሙ በፊት፣ በድምፅ መስጫ ቀ ናት እና ውጤቱ እስኪገለጽ ባሉት ቀናት ውስጥ ሲ ያሳዩ ሰንብተዋል። እነርሱ በተደጋጋሚ ወደ ጦርነ ት እንደማይመለሱ ቢያውጁም ደጃፋቸው ላይ ግ ን ሌላ ዐይነት “ጦርነት” ሲካሄድ እያስተዋሉ ነው። ይህኛው ጦርነት ግን ሕይወትን የሚጠይቅ ሳይኾን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ዶላር የሚፈልግ ነው። “ጦርነቱ” የታወጀው ደቡብ ሱዳን ላላት ያልተነካ ቅምጥ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ለድንግል መሬቷ፣ ለ ነዳጇ፣ ብረት እና መዳብ የመሳለሱትን ማዕድኖቿ ን ለመቀራመት የሚደረግ ነው። “ጦርነቱ” ከትም ህርት እስከ ጤና፣ ከግንባታ እስከ ገንዘብ ተቋማት ባሉ የተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመ ሙላት እስከሚደረግ ሩጫ ይዘልቃል። እዚህ “ጦር ነት” ወታደሮች ደግሞ ኢንቨስተሮች፣ የልዩ ልዩ ባ ለሞያ ባለቤቶች እና ኤክስፐርቶች ናቸው። መነሻ ቸው ደግሞ ሩቅ አይደለም። ቅርብ ነው- ከጎረቤ ት አገሮች። በይፋ ያልታወጀው ይህ ጦርነት አሃዱ የተባለው በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ለሁለት ዐሥ ርት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ደም አፋሳሽ ጦርነ ት ሲቋጭ ነው። የሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ወገኖች እ.ኤ.አ በ2005 የሰላም ስምምነት ከተፈራራሙ ወ ዲህ በከፊል ራሷን የማስተዳደር መብት ባገኘቸው ደቡብ ሱዳን ላይ ሰላም ሰፈነ። ይህን ተከትሎም አደጋን ለመጋፈጥ የቆረጡ ባለሀብቶች ወደ አገሪቱ መምጣት ጀመሩ። የደቡብ ሱዳንን በር ለማንኳኳት ከጎረቤቶቹ ዩጋን ዳውያን እና ኬንያውያን የቀደመ አልነበረም። ኤር ትራውያን እና ኢትዮጵያውያንም ዘግየት ብለው የ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ኾና ወደተሰየመችው ጁ ባ መትመም ጀመሩ። በመጀመሪያ ዩጋንዳውያን እ ና ኬንያውያን ነበሩ ሽንኩርት እና ቲማቲም ሳይቀር ሁሉንም የምግብ ሸቀጦች በብቸኝነት ሲያቀርቡ የነ በሩት። በስተኋላ ግን ኤርትራውያን አብዛኛዎቹን የ ንግድ ዐይነቶች ተቆጣጠሯቸው። “ሁሉንም ነገር ማለት ይቻላል ኤርትራውያን ተቆ ጣጥረውታል” ላለፉት ስድስት ዓመታት በጁባ የኖ ረው ኢትዮጵያዊው ቢኒያም ዮሐንስ ነው ይህን የ ሚለው። “ከዩጋንዳውያን እና ከኬንያውያን በተሻለ ነው እየነገዱ ያሉት።”

በ“ቡፋሎ” ባንክ ውስጥ የዋናው ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ሰይፉን ጨምሮ 10 ኢትዮጵያውያን ይሰራሉ

ኤርትራውያን መጀመሪያ የገቡበት የሥራ መስክ የ ሆቴል አገልግሎት መስጠት ነበር። በወቅቱ በጁባ የ ነበሩት ሆቴሎች በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ። ኤርትራ ውያኑ ቆየት ብሎ ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ማስመጣት ተሸጋገሩ። ከደቡብ ሱዳን የሕዝብ ቆጠራ እና የስ ታትስቲክስ ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመ ለክተው ከኾነ በዐሥሩ የደቡብ ሱዳን ክልሎች ው ስጥ ባሉ ዋና ከተማዎች የተመዘገቡ ነጋዴዎች ቁጥ ር 7333 ነው። ከዚህ ውስጥ 84 በመቶውን የሚወ ስዱት ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ናቸው። ከሌሎች ከ ተሞች ጋራ ሲወዳደር የአገሪቱ መዲና በርካታ ነጋ ዴዎችን በማስተናገድ ቅድሚያውን ይዛለች። በጁ ባ 2683 የተመዘገቡ ነጋዴዎች አሉ። ምንም እንኳ የነጋዴዎቹ ቁጥር አናሳ ቢመስልም ጎ ረቤት አገሮች ግን የደቡብ ሱዳንን ገበያ ለመቆጣጠ ር ያለመታከት ሠርተዋል። ከዓመታት በኋላም የላባ ቸውን ፍሬ መቅመስ ጀምረዋል። የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከኾነ ኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን የምትልካቸው ምርቶች ባለፉት አራት ዓመታት ው ስጥ በእጥፍ አድጓል። ኬንያ ከሱዳን ጋራ የነበራት የ ውጪ ንግድ በ2009 እ.ኤ.አ 158 ሚልዮን ዶላር ደ ርሷል። ይህ ቁጥር ከአራት ዓመት በፊት 84 ሚልዮ ን ዶላር ብቻ ነበር። እንደ ኬንያ ንግድ ባንክ (ኬ.ሲ.ቢ) ያሉት ትልልቅ የኬንያ ተቋማት የአገሪቱን ጥቅም በደቡብ ሱዳን ው ስጥ በፊታውራሪነት ያስጠብቃሉ። ይህ የኬንያ ባን

ክ በሱዳን እህት ድርጅቱን ኬ.ሲ.ቢ (ሱዳን) ሊትድ በሚል ስያሜ ያቋቋመው የሰላም ስምምነቱ በተፈረ መ በዓመቱ ነበር። የኢትዮጵያ አቻው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳንን ገበያ የተቀላቀለው ግን ከኬ.ሲ.ቢ ሦስት ዓመት ዘግይቶ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁንም ቢኾን ሥራውን የሚያከናውነ ው ያለምንም ቅርንጫፍ ጁባ ታውን በሚገኘው ዋና መሥርያ ቤቱ አማካኝነት ሲኾን ኬ.ሲ.ቢ ግን የቅርን ጫፎቹን ቁጥር 18 አድርሷል። የኬንያው ባንክ ከአ ራት ዓመታት በኋላ የቅርንጫፎቹን ብዛት ወደ 28 ለማሳደግ ግብ አስቀምጧል። ሌላኛዋ ጎረቤት አገር ዩጋንዳም ብትኾን በደቡብ ሱዳን ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለ ች። ኦፊሴሊያዊ ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ከኾነ አገ ሪቱ ከኬንያም በተሻለ ተጠቃሚ ኾናለች። እ.ኤ.አ በ2009 ብቻ ዩጋንዳ 184.6 ሚልዮን ዶላር የሚያ ወጡ ምርቶችን ወደ ደቡብ ሱዳን ልካለች። በደቡ ብ ሱዳን ምርቶቿን በመላክ የቀዳሚነትን ስፍራ ብ ትይዝም ይኼ ብቻ በቂ ነው ብላ አልተገታችም። ይ ልቅስ እያደገ የመጣውን የደቡብ ሱዳን ገበያ ፍላጎ ት ለማርካት የመሠረት ሥራዎች ከወዲሁ መሥራ ት ጀምራለች። የዩጋንዳ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣ ን ከደቡብ ሱዳን ድንበር 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላ ይ በምትገኘው ጉሉ ከተማ ላይ ለአምራቾች የሚኾ ን “ኢንዱስትሪያል ፓርክ” ለማቋቋም በሂደት ላይ ነ ው። የዚህ ፓርክ ዒላማ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ናት።

“ባለሥልጣኑ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ የሚቋቋምበ ትን መሬት ለማግኘት ከጉሉ ከተማ ምክር ቤት ጋራ እየተደራደረ ነው። ምንም እንኳ ኢንዱስትሪያል ፓ ርኩን እምብዛም ሳይዘገይ ለማቋቋም ዕቅድ ቢኖረ ውም እስካሁን ግን በመሬት ላይ የተሠራ ሥራ የለ ም” ብለው ነበር የባለሥልጣኑ የኮሚዩኔኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የኾኑት ዶሪ ስ ሚቲ ኪሚሉ። የዩጋንዳ መንግሥት ለወደፊቱ ከመዘጋጀት ባሻገር በሁለቱ ጎረቤት አገሮች መካከል የሚካሄደውን ድን በር ተሻጋሪ ንግድ ለማቅለል ርምጃዎችን ወስዷል። በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ መሠረተ ልማቶችን ከመዘርጋት አንስቶ የውጭ ንግድ ማበረታቻ እስከ ማቅረብ ድረስ ያሉ ርምጃዎችን በመውሰድ በደቡ ብ ሱዳን መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ ዩ ጋንዳውያን መንገዱን ጠርጎላቸዋል። “የዩጋንዳ መንግሥት በደቡብ ሱዳን ለመሥራት ለ ሚፈልጉ ነጋዴዎች የውጪ ንግድ ማበረታቻ ይሰጣ ል” ይላሉ ዶሪስ። ይህ ማበረታቻ የሚሰጠው ወደ ውጪ የሚላኩ ም ርቶችን የሚያመርቱ ነጋዴዎችን ለመደገፍ በተነደፈ ው እና “ኤክስፖርት ፕሮሞሽን ስኪም” ተብሎ በ ሚጠራው የዕገዛ ዐይነት ነው። በዚህ ውስጥ ከሚ ካተቱት አንዱ “ማኑፋክቸሪንግ አንደር ቦንድ” የተ ባለው ማበረታቻ ሲኾን ይህም አምራቾች የጉምሩክ ፈቃዳቸውን በመጠቀም ቀረጥ ሳይከፍሉ ጥሬ ዕቃ ከውጭ እንዲያስገቡ የሚያስችል ነው። የገባው ጥ ሬ ዕቃ ግን ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማምረ ት ብቻ የሚውል መኾኑ ይረጋገጣል። ይህ አሠራር በውድ ዋጋ ጥሬ ዕቃ ከውጭ የሚያስመጡ አምራቾ ች ወዲያውኑ ለታክስ ይከፍሉ የነበረውን ገንዘብ በ ማስቀረት የመሥሪያ ገንዘብ (ወርኪንግ ካፒታል) እ ንዲኖራቸው ያደርጋል። ሌላኛው የማበረታቻ ዐይነት ከውጭ ተገዝቶ ለገ ባ ግብዓት የተከፈለን ግብር በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መመለስ ነው። ይህም ግን እንደመጀመሪ ያው ማበረታቻ ሁሉ ተግባራዊ የሚኾነው ግብአቱ ወደ ውጭ ለሚላክ ምርት መዋሉ የተረጋገጠ እንደ ኾነ ብቻ ነው። ብዙዎቹ የደቡብ ሱዳን ጎረቤቶች የአገሪቱን ገበያ እየተቀራመቱ ቢኾንም ኢትዮጵያ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ በጉልህ ስትሳተፍ አትታይም። ኢትዮጵያው ያን ነጋዴዎች ከትልቁ ኬክ እያገኙ ያሉት ትንንሽ ቁ ርስራሾችን ነው። በደቡብ ሱዳን ሁለት ሺሕ የሚኾ ኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገመታል። ከእነዚ ህ ውስጥ አብዛኞቹ የተሠማሩት በሸቀጥ ንግድ አ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

አዶማያስ በኬንያ እየተስፋፋ ነው ፎቶ-ዌስት ጌት ሞል

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

ከፋብሪካው ምርቶች መካከል አንዱ

የአስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶቹን የሚያከፋፍልባቸው ሁለት ዘመናዊ የአልባሳት መሸጫዎች በናኩማት ኦአሲስ ሞል እና ፎረስት ሞል ከፈተ። ሁለቱ የአልባሳት መሸጫዎች በ”ኢ ጣሊያን ስታይል” የተመረቱ እና “ዶልቼ ቪታ” የሚል መለያ የያዙ ሸሚዞችን፣ ሱሪዎችን፣ አንሶ ላዎችን፣ ምቾት ያላቸው ብርድ ልብሶችን፣ ለኩ ሽና ስራ የሚውሉ ሽርጦችን እና ጓንቶችን ለገበ ያ አቅርበዋል። ሱቆቹ ከጠዋት እስከ ምሽቱ አን ድ ሰዓት ክፍት ናቸው። ሃምሳ አምስት አመታት ያስቆጠረው አስመ ራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የተመሰረተው በጣ ሊያናዊው ሮቤርቶ ባራቶሎ አማካኝነት ነበር። እ.ኤ.አ በ1975 ፋብሪካው ሲወረስ ባራቶሎ ሀገ ር ለቆ ቢወጣም እስካሁንም ድረስ ፋብሪካው ያ ለበት ቦታ “እንዳ ባራቶሎ” ተብሎ ነው የሚጠ ራው። በዚያን ወቅት ፋብሪካው ወደ 3 ሺህ የ ሚጠጉ ሰራተኞች ነበሩት። በመንግስት ስር የቆ የው ፋብሪካ እ.ኤ.አ በ2004 ዛምባቲ ግሩፕ ለተ ባለ የኢጣሊያን ኩባንያ ይሸጣል። ፋብሪካው በ አሁኑ ወቅት እየተዳደረ የሚገኘው “ዜድኤ. ኢአ ር” በተሰኘ የዛምባቲ ግሩፕ እህት ኩባንያ ነው። አስመራ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አሊጊደር አካ ባቢ የጥጥ እርሻ አለው። ፋብሪካው ምርቶቹን በአስመራ ከተማ በሚገኙ ሶስት ማከፋፈያዎች ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በከረን፣ ደቀመሃሪ እና መንደፈራም መሸጫ ሱቆች አሉት።

የአዶማያስ የዌስት ጌት ሱቅ

ስያሜው አዶማያስ ይሰኛል። የኢትዮጵያውያን ን የባህል አልባሳት እና እቃዎች ደረጃውን በጠ በቀ መልኩ ለኬንያ ገበያ የሚያቀርብ ድርጅት ነ ው። የቤት ኪራይን እና ተቀማጭ ገንዘብን ሳይ ጨምር ቦታ ለማግኘት ብቻ ወደ 1.2 ሚሊዮን የ ኬንያ ሽልንግ በሚጠየቅበት “ዌስት ጌት” ሞል ው ስጥ ስራ ከጀመረ ቆይት አለ። ጅማሮው በሸማቾ ች መተላለፊያ ኮሪደር ላይ በምትገኝ ኪዮስክ ው ስጥ ነበር። በእዚያ የባህልና የሀይማኖት ቁሳቁሶች ለሽያጭ ይቀርቡበታል። ድርጅቱ በአነስተኛ ሱቅ የተገደበውን ስራውን በ ቅርቡ አስፋፍቷል። የባህል አልባሳት፣ የእጅ ቦር ሳዎች እና ጫማዎች የሚሸጡበት ሱቅ በተጨማ ሪ ከፍቷል። ይህንን ሱቅ ለማግኘት ሩቅ መሄድ አ ያስፈልግም። እዚያው “ዌስት ጌት” ሞል ውስጥ ነ ው የሚገኘው። የእነዚህ ሁለት ሱቆች ባለቤት እ ና ስራ አስኪያጅ ህሊና አሰፋ ትሰኛለች። እ.ኤ.አ በ1998 የኬንያን ምድር ከረገጠችወዲህ ብዙ የ ሕይወት ውጣ ውረድን አልፋለች፡፡ ከብዙ ድካ ም በኋላም በናይሮቢ ካሉ የኢትዮጰያ የባህል ቁ ሳቁሶች፣ አልባሳት እና ምግቦችን ከሚያስተዋው ቁ ጥቂት ኢትዮጰያውያን መካከል ዋነኛዋ ለመኾ ን ችላለች፡፡ በ2006 ዓ.ም ዛሬ “ሐበሻ የኢትዮጵያ ሬስቶራን ት” ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የመጀመሪያውን የባ ህል ቁሳቁሶች መሸጫ ከፈተች፡፡ ዋነኛ አላማዋም የኢትዮጰያውያንን የባህል ቁሳቁሶች ለተቀረው ዓ ለም ማስተዋወቅ እንደነበረም ትናገራለች፡፡ ገበያ ውም አዋጪ መኾኑን ስታስተውል ከአምስት ዓ መታት በኋላ የቱሪስቶች መናኸሪያ በኾነው እና ለአብዛኛው ሸማች እንደ ቅንጦት ወደሚታየው “ዌስት ጌት” ሞል አምርታለች።


ሀበሻዊ ቃና

20

ትዝታ

***

ወቅቱ በመላዋ ኢትዮጵያ “የጦር ወሬ”፣ የ ምጥ ጣር የሚሰማበት ከባድ ወቅት ነበር። መንግሥትም ሕዝቡም ተጨንቋል። የከፍ ተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በአን ድ በኩል የመንግሥት ለውጡ ደግ ነገር ይ ዞ ይመጣ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲጠብቁ ት በሌላ በኩል ደግሞ “ኤርትራ ትገነጠላ ለች” ከሚለው ጀምሮ ሰሜነኞቹ ይዘውት

20

ኛ ጠ ል ሰ ማ ዊ ብላቴ ወታደራ

የዛሬ

ኤፍሬም እሸቴ ብላቴ በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር፣ ከሐዋሳ ከተማ ወደ 90 ኪ.ሜትር, ከአዲ ስ አበባ ደግሞ 395 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚ ገኝ ወታደራዊ ካምፕ ነው። ከባሕር ጠለ ል በላይ 1000- 1400 ሜትር በበረሃማው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ሞቃት ቦታ። በበጋ ወቅት እጅግ በጣም ሞቃት እና ደ ረቅ ሲሆን በክረምት ደግሞ ዝናባማ እና የሚተነፍግ ውሃ አዘል አየር (rainy and humid) ይበዛበታል። የዛሬ 20 ዓመት በወቅቱ በአገራችን የሚ ገኙ የኮሌጆች እና የዩኒቨርሲቲዎች በጠቅ ላላው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪ ዎች በዚህ ወታደራዊ ካምፕ ከትመው ነ በር። በእስክሪፕቶ ፈንታ ጠመንጃ፣ በወረ ቀት ፈንታ ጥይት፣ በዶርሚቴሪ ፈንታ ወ ታደራዊ “ኬስፓኖች”፣ በሲቪል ፕሮፌሰሮ ች ፈንታ መለዮ ለባሽ ወታደሮች ተተክተ ዋል። ተማሪው የቀለም እና የሙያ ትምህርቱ ን ትቶ መሣሪያ መግጠም እና መፍታት፣ መሣሪያ አያያዝና አተኳኮስ፣ የሰውነት ማ ጎልመሻ ስፖርት፣ የቦንብ አያያዝ እና አወ ራወር፣ ድንገተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰበ ት ሰው ሊያገኘው ስለሚችለው ጊዜያዊ ር ዳታ አሰጣጥ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ በምሽ ግ የተደበቀ ጠላት እንዴት ማጥቃት እንደ ሚቻል፣ በፈንታው ራሱ ምሽግ ውስጥ ቢ ሆን እንዴት መከላከል እንደሚችል፣ ሌሊ ት ቢሆን እንዴት እንደሚያጠቃ ወይም እ ንደሚከላከል ወዘተ ወዘተ ትምህርት ይሰ ጠው ነበር። እኔም እዚያ ነበርኩ። ዘንድሮ 20 ዓመት በሞላው በዚያ ለብዙዎቻችን አ ዲስ በሆነ የሕይወት አጋጣሚ ካየሁት እና ትዝ ከሚለኝ ላካፍላችሁ ወደድኹ።

ሊመጡት የሚችሉት መአት እያስፈራው በመንታ ልብ ይጠብቃል። “ከወንበዴዎ ቹ” ከድተው የገቡት ሁለቱ መሪዎቻቸው አብርሃም ያየህ እና ገብረ መድህን አርአያ ይናገሩ የነበሩት ነገር ሊመጣ ያለውን መ ከራ እጅግ አክብደው አቅርበውት ነበር። ሰሎሞን የተባለ ፀሐፊ ከሱዳን ለአዲስ ዘ መን ጋዜጣ ያደርስ የነበረው እና የኢትዮጵ ያ ሬዲዮ ያነበው የነበረው ጽሑፍ ድባቡን በማክበድ ረገድ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል። በዚህ መካከል ኮ/ል መንግሥቱ የአዲስ አ በባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሊያናግሩ ወደ 6 ኪሎ ግቢ ተጓዙ። እናም ተማሪዎቹን በ አንድ ቀን ከፀረ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ነት ወደ ፀረ-“ወያኔነት” ቀይረው “እንዘም ታለን” አስባሏቸው። ፕሬዚደንቱም “ይኼ ው ነው” ብለው ተነሡ። ከዚያማ ምታ ነጋ ሪት ክተት ሠራዊት ተባለ። “ወንበዴዎች” የሚባሉት በረኸኞችም በበኩላቸው “አሁ ን ወደ ብላቴ የሚገባው ወታደር ከሌሎቹ የሚለየው እንግሊዝኛ በመናገሩ ብቻ ነ ው” ሲሉ ቀለዱ ተባለ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “እን ዘምታለን” ማለታቸው እንደተሰማ በብዙ ዎቻችን ውስጥ የፈጠረው የተመሰቃቀለ ስሜት ነበር። አንዳንዱ መንግሥት ሌላው ን ለማበረታታት እንጂ እነዚህን ሕጻናት አ ይማግዳቸውም ሲል ሌላው ደግሞ ሚሊ ሻውንም፣ አባት ጡረተኛውንም፣ ወጣቱ ንም ከላከ በኋላ የቀረው ተማሪው ስለሆነ ያንን ከማድረግ እንደማይመለስ በማስረገ ጥ ጭንቀታቸውን መግለጽ ጀመሩ። ተማ ሪው ግን ድጋፉን በየግቢው መግለጽ ቀጥ ሎ የመዝመቱ ነገር ቁርጥ ሆነ። መንግሥት ም ነገሮችን ቶሎ አመቻቸ። ተማሪው በሁለት የተከፈለ ሐሳብ እንዳ ለው ግልጽ ነበር። መሔድ የሚፈልግ ተማ ሪ ያለውን ያህል መቅረቱን የሚመርጠው ም ብዙ ነው። መሔድ የፈለገው ሁሉ ግን “ወንበዴዎቹን ለመዋጋት” ቆርጦ አልነበረ ም። ከቀረ በኋላ እንደሚባረር እርግጠኛ በመሆን ከዚያ ለማምለጥ መሔዱ ላይ የወ ሰነ ብዙ ነበር። በስንት መከራ የተገኘ ዩኒቨ

ርሲቲ እና ኮሌጅ እንዲህ በቀላሉ የሚተው አልሆነም። እናም ጭንቅ ሆነ። ከቆይታ በኋላ መሔድ የሚፈልገውም ወ ሰነ፤ መቅረት የሚፈልገውም ወሰነ። እኔ መ ሔድ መረጥኹ። ለምን ለመሔድ ወሰንኩ? የማስታውሰው ለመቅረት አስቤ እንደማላ ውቅ ነው። በዚያን ወቅት ግን ብሰለጥንም ጦርነት ውስጥ እገባለኹ የሚል ስጋት አል ነበረኝም። ብዙም አላሰላሰልኩትም ልበ ል። ተማሪው በሙሉ ሲሄድ መቅረት ግ ን ሌላውን ተማሪ እንደመካድ ሳልቆጥር አ ልቀረኹም።

ጉዞ ወደ ብላቴ …

ሽንጣም የክፍለ ሀገር አውቶቡሶች መጥ ተው ኮሌጁ ግቢ ውስጥ ተገጥግጠዋል። ዕ ለቱ ሐሙስ ነው። የቀን ቅዱስ። መጋቢት 19/ 1983 ዓ.ም። የቅዱስ ገብርኤል መታ ሰቢያ። ሻንጣዎቻችንን አሰናድተን በሌሊ ት ተነሥተናል። አውቶቡሶቹ የኮሌጁ ኳስ ሜዳ ላይ ተዘርግፈዋል። ተማሪው ሁሉም ተሰናድቷል። ተሳፈርን። ሁሉም ወጣት ነው። ብዙዎቻችን ገና 20 ዓመት እንኳን አልሞላንም። እኔ የማውቀ ው አብዛኛው ተማሪ ከቤተሰቡ የተለየው ኮሌጅ ሲገባ ነው። ለኮሌጁም ቢሆን መን

ስንታየሁ አባተ(ቀሲስ)-ካይሮ፣ ግብፅ

ዛሬ ሃያ ዓመት ወቅቱ ዘመነ ፋሲካ ነበር። የጂማ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም አስ ተዳደር ድንገተኛ ትእዛዝ አስተላለፈ። በ አዲስ አበባ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማ ት የሚገኙ ተማሪዎች ባደረጉት ዉሳኔ መሠረት ዕ ጩ መምህራኑ ወደ ብላቴ የአየር ወለድ ማሰልጠ ኛ መሄድና መሰልጠን አለባችሁ በማለት ከጭራ የ ቀጠነ ትእዛዝ አስተላለፈ። ለተማሪው የመወያያ ጊ ዜና ዕድል እንኳን አልተሰጠም። በዚህ ዉሳኔ መሠ ረት ወደ 400 የምንሆን ዕጩ መምህራን ከጂማ ወ ደ ብላቴ ተጓዝን። ብላቴ ከደረስን በኋላ መጠሪያ ችን “ብርጌድ አንድ” የሚል እንደ ሆነም ተነገረን። አንደኛ ብርጌድ ልዩ መገለጫዎች ነበሩት። የብርጌ ዱ አባላት ወጣቶች ነን። የምንበዛው የተለያዩ የመ ምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ብንሆንም በተለያዩ የ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ይማ ሩ የነበሩ ነገር ግን ዘመቱ ሲባል በቤተ ሰብ ተፅዕኖ፣

ገድ ተያያዝነው። ከዚያ ጀምሮ ቢያንስ 60 ኪሎ ሜትር የተጓዝን ይመስለኛል። ለእኔ ፍፁም አዲስ አገር ነው የጎጆዎቹ አሠራር፣ የግቢዎቹ ሁኔታ ወዘ ተ ወዘተ እኔ ከማውቀው ገጠራማ አካባቢ የተለየ ነው። ለገጠሩ ለገጠሩ ሴት አያቴን እና ሌሎች ዘመዶቼን ለማየት ከሆለታ ወ ደ ዱፋ (ወደ ሜታ ሮቢ፣ ሙገር መስመ ር) የሦስት እና የአራት ሰዓት የእግር መንገ ድ ስንጓዝ አውቀዋለኹ። ጎጆ ቤቶቹ፣ ማሳ ዎቹ፣ በመንገድ ላይ ለማረፍም፣ ውሃ ለመ ጠጣትም የምንጠጋባቸው “ምንጭ” ያላቸ ው ተረተሮቹ በሙሉ ትዝ ይሉኛል። ብላቴ መስመር ላይ ያሉት የተለዩ ሆነውብኛል። አውቶቡሶቹ ያንን ሞቃታማ አየር እየሰነጠ ቁ፣ የትንባሆውን ተክል አልፈው፣ ተአምረ ኛውን የጨሪቾ ሚካኤልን አልፈው ከብላ ቴ ግቢ ደረሱ።

ዓመት

ይታ ዕ ጅ ሌ ኮ ን ራ ህ ም ብላቴ በጅማ መ

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

በፍርሃት፣ በፖለቲካ አቋም ልዩነት….አንዘምትም ብ ለው ቀርተው የነበሩና በኋላ ደግሞ መንግሥት ርም ጃ ሊወስድባችሁ ይችላል ሲባሉ ዘግይተው የመጡ ዘማቾች ግራ የተጋቡ ግራ የሚያጋቡ መሃል ሠፋሪ ዎች……የነበሩበት ብርጌድ ነበር። ይህ ብርጌድ “ ሽነ ድ” የሚል ምሕፃረ ቃላዊ ስያሜ ተሰጥቶትም ነበር። “ሽነድ” ሽብር ነዢ ድርጅት ማለት ነው። በዘማች ተማሪዎች አካባቢ የሚነገሩ መረጃዎች እውነትም ይሁኑ የተፈበረኩ መነሻቸው ሽነድ ነበር። አንዱ የ ነሣና ዛሬ ወደ ጦር ግንበር ሊያዘምቱን ነው ይላል፤ ሌላኛው ደግሞ ትናንት ማታ የወያኔ ታጣቂ ሰላዮች ቦንብ እንደ ታጠቁ ትምባሆ ሞኖፖል ተያዙ ይላል፤ ሌላኛው ድግሞ ለጥቆ ከዘማች ተማሪዎች መካከል ለወያኔ በመገናኛ ሬድዮ መልእክት ሲያስተላልፉ ተ ያዙ ይላል። አንዳንዱ ደግሞ ከመተኛታችሁ በፊት መኝታችሁን ፈትሹ የወያኔ ደጋፊዎች ፈንጂ ሊያኖ ሩባችሁ ይችላሉና ይላል። ይህ ከሽነድ የመነጨው

ግሥት እንደ ቤተሰብ እንደሚንከባከበው ስለሚታሰብ ወላጅ ልቡ ማረፉ እርግጥ ነ ው። በወላጆቻችን ዘንድ መንግሥት አባት ነው፤ መንግሥት ወላጅ ነው የሚል ጽኑ አ ስተሳሰብ አለ። ለእነርሱ (ፈረንጆቹ እንደ ሚሉት) “we are in good hands”። አ ዬ ቤተሰቦቻችን አለማወቃቸው፣ አንድ ነ ገር ትንፍሽ ካልን የመንግሥት ፖሊስ ቆመ ጥ እንደሚያሯሩጠን። ይህንን ደግሞ በየዓ መቱ ቀምሰነዋል። አውቶቡሶቹ እስከ ቃሊቲ እስኪደርሱ ድ ረስ የሰርገኛ ስሜት አልለቀቃቸውም። ቃ ሊቲ ላይ ስንደርስ ከግቢው ጀምሮ ሊሸኙ ን በአንድ መኪና አብረውን የመጡት መም ህራኖቻችን ተሰናብተውን ተመለሱ። የእኛ የልጆቹ ብቻ ሳይሆን የትልልቆቹም ልብ አ ብሮን ጉዞ ጀምሮ ነበር። ምናልባት እነርሱ ሊመጣ ያለውን ነገር የበለጠ አመዛዝነውት ም ይሆናል። ወይም ወጣቶቹ መምህራኖ ቻችን አንድም ለ“ዕድገት በኅብረት” ፣ አን ድም ለ“መንደር ምሥረታ” “ዘመቻውን” የ ቀመሱ ሆነው አዝነውልን ይሆናል። ለተማ ሪያቸው ለማዘን በርግጥ ከዘመቻ ውለው መከራውን ማየት የለባቸውም። የአስተማ ሪ አንጀታቸው፣ የወንድምነት አንጀታቸው

ከሜንስ ቤት እስከ ኬስፓን

አልችል ብሎም ይሆናል። አንዳንዶቹ መ ምህራን የታላላቅ ወንድሞቻችን እኩያዎች የሚሆኑ “ለጋ ምሩቃን” ስለነበሩም የተማሪ ነቱ መንፈስ ገና ተሟጦ አላለቀባቸውም። እኛም አንድ አራት ዓመት ቆይተን ከአስተ ማሪነት ትውውቅ ወደ ወዳጅነት ትውውቅ ያደረስናቸው አሉን። መምህራኑ ከተመለሱ በኋላ መንገዱ ሰተ ት አድርጎ ይወስደን ጀመር። እስከ ዝዋይ ያለውን መስመር ከዚያ በፊትም አውቀዋ ለኹ። እናም አሁን እስከ ዝዋይ ድረስ ምን ም የባዕድነት ስሜት አልተሰማኝም። ዝዋ ይን አልፈን ስንዘልቅ አየሩም፣ ምድሩም አ ዲስ እየሆነብኝ ሄደ። በዝና የማውቃቸው ን ሻሸመኔን እና አዋሳን (አሁን ሐዋሳ ነው የምትባለው) አልፈን ትንሽ እንደተጓዝን ለ ምሳ እረፍት ሆነ። ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ይሆናል። በርግጥ የሁዳዴ ሰሞን እንደመ ሆኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት አጾሙን ማለት ነው ብዬ ልውሰደው? ነገሩ ምሳ ይሁን እንጂ ምሳ ነው ለማለት ይከብዳል። በቆርቆሮ የታሸገ እንዲሁም ኮ ቾሮ መሰል ኩኪስ ነገር አደሉን። የጠጣነ ውን አላስታውሰም። ጠጥተን ይሆን? መ ቸም ባንጠጣ ውሃ ጥሙ ይገድለን ነበር። ከአዲስ አበባ ስወጣ ሁሌም ጭንቅ የሚለ ኝ የዝዋይ-ማዶ ውሃ ነው። ውሃው ከጉሮ ሮዬ አይወርድም። ይቅርታ የዝዋይ ማዶ ሰ ዎች። ሰው በተለይ የኮተቤ ኮሌጅን (የሆለ ታን) ውሃ ለምዶ የዝዋይን፣ የሐዋሳን ውሃ ልጠጣህ ሲሉት …። መቸም ሰው እንደ ል ማዱ ነው። ሙቀት አገር የመኖር ልማዱ ስ ለሌለን መሰለኝ። አለበለዚያ ከቅንጦት መ ቆጠሩ አይቀርም። በተለይ ነገር ተበላሽቶ አገር ከፈረሰ በኋላ ከብላቴ ስንበተን የጠ ጣነውን ውሃ ሳስታውሰው የዝዋይ ግፍ ነ ው እላለኹ። ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ። ምሳችንን በልተን መጠነኛ ዕረፍት ከተደረገ ዘንዳ ጉዞ ተጀመረ። ከሐዋሳም ከወጣን በኋላ ዋናው ን መንገድ ይዘን ጥቂት እንደተጓዝን ትንሿ ን የሞሪቾን ሰፈር እናገኛለን። እዚያ ላይ ወ ደ ቀኝ ታጥፈን አቧራማውን የብላቴን መን

ብላቴ የገባነው ከመሸ ነው። እንደደረስን አንድ አዳራሽ መሰል ግማሽ ጨረቃ ቅርጽ ባለው የብረት መጋዘን ወይም ኬስፓን ው ስጥ ሰልፍ ይዘን ቆምን። ተራዬ ሲደርስ የ ሚመዘግበን ሰው አንዲት ክኒን እና ውሃ ሰ ጠኝ። የወባ መከላከያ ናት። ዋጥኩ። ዋጥ ን። መዋጥ ነው። ይህ የጦር ካምፕ ነው እ ንጂ ከተማ አይደለም። ገዳይ ቢጫ ወባ ያ ለበት በረሃ እንጂ አዲስ አበባ አይደለም። እኛም ወታደሮች እንጂ “ምሁራን የከፍተ ኛ ትምህርት ተቋም ሊቃውንት” አይደለን ም። ከክኒናው ጋር የሚያስፈልገን ነገር ተሰ ጠን። ሰዓቱ የራት ሰዓት ስለሆነ ወደ “ሜን ስ ሜት” (መመገቢያ ቤት) ሄድን። “ሜንስ ቤት” የምን ቋንቋ ነው? በአማርኛ ችን ውስጥ የተሰባበሩ አረብኛዎች፣ ጣሊያ ንኛዎች፣ ስፓኒሽኛዎች፣ አራማይኩም፣ ቅ ብጡም፣ ግሪኩም፣ ሱርስቱም፣ አረብኛው ም፣ ስለሞላበት አንዳንዱን ቃል ፍቺ ለማ ወቅ ወይ ሊቅ መጠየቅ ወይ መዝገበ ቃላት ማማከር ይጠይቃል። ይቺ “ኬስፓን” እና “ሜንስ ቤት” የምትለው ከየት እንደተገኘ ች አሁን አላወቅዃትም። ሆለታም ሆኜ ወ ታደሮቹ ምግብ ቤታቸውን “ሜንስ ቤት” እንደሚሉ አውቃለኹ። ከሌሎቹ ተማሪዎ ች በዚህ በዚህ “እልቃለኹ” ማለት ነው (ለ ፈገግታ)። ወራቱ ወርሃ ጾም ያውም ዐቢይ ጾም በመ ሆኑ የምግባችን ነገር ጭንቅ ሆነ። ደግሞ ም ጾሙ ሊፈታ አንድ ሳምንት ነው የቀረ ው። ዓይጥ ወልዳወልዳ … እንዳይሆን። ያ ንን ማታ እንጀራ በሻይ እና በውሃ እያማግ ን በላን። ፍርሃታችን “የምን ጾም ነው? ቀበ ጦች!! ትበላ እንደሆን ብላ!!!” የሚል ወፍ ራም የወታደር ድምጽ እና ቁጣ ጠብቀን ነ በር። አልመጣም። ስለዚህ እንጀራ በውሃ እያማግን መብላታችንን እንደ ትልቅ ሥጦ ታ ቆጠርነው። ተመስገን። ከዚያ ወደየተመደብንበት ማደሪያ ቦታ ተ ጓዝን። የደረሰኝ አልጋ ከታች ነው። ከላይ አንድ ልጅ ይተኛል። በኬስፓኑ ውስጥ ብ ዙ ተማሪ ነው ያለው። መኝታ ክፍል ሳይ ሆን የአልጋ አነጣጠፍ ማስተማሪያ ወርክ ሾፕ ይመስላል። ኮተቤ እንደገባኹ ከመኝ ታ እጥረት የተነሣ ብዙ ተማሪ ካለበት ሰፊ ክፍል ውስጥ ማደር ስለለመድኹ አሁን አ ዲስ አልሆነብኝም። እናም ጥቅልል ብዬ ተ

“ሽነድ” እና ፍርሃት የሽብር ወሬ በቀላሉ ወደ ሌሎቹ ብርጌዶች ቀንድና ጭራ ተበጅቶለት ይናኛል። ተኩስ ወረዳ ወርደን ዒላማ ስንለማመድ የሆነው ን ላውጋችሁ። ተኝቶ መተኮስን እየተለማመድን ነበር። በሁለት ተማሪዎች መካከል አንድ አሰልጣኝ ይቆማል። በ ሁለቱ ተማሪዎች መካከል ያለው ርቀት ምናልባት ሜትር ከግማሽ የሚሆን ይመስለኛል። ልምምዱ በ እውነተኛ ጥይት ነበር። ከፊት ለፊታችን በቅርብ ር ቀት የተተከሉ እንጨቶች ላይ የተሰኩ ካርቶኖች ነ በሩ። ልምምዱ እነዚያን ካርቶኖች ዓልሞ መምታት ነበር። አሰልጣኙ “ተዘጋጅ ጀምር” ብሏል፤ ተኩሱ ተጀመረ። ሁሉም እንደየችሎታው እያለመ ይተኩ ሳል። በእኔና በሌላኛው ጓደኛዬ መካከል አንድ ተ ካ የሚባል የግቢያችን ተማሪ ነበረ። እርሱ ገና እያ ነጣጠረ ሳለ ከጎኑ ያለው ዒላማው እንደገባለት ም ላጭ ይስባል። የጥይት እርሳስ ወደ ተላከችበት ስ

ትስፈነጠር ቀለኽ ትፈናጠርና ከተካ አፍንጫ ታር ፋለች። ትኩስም ስለነበረች ትንሽ አፍንጫውን እ ንደማድማት ትላለች። ተካ ጥይት የመታው ይመ ስለውና ደንግጦ “ተሠዋሁ እኮ” እያለ ወደሚተኮ ስበት ሊገባ ሲል ቆሞ የነበረው አስተኳሽ ይዞ አስ ቀረው። በብዙዎች ተማሪዎች ዘንድም ስሙ “ተሠ ዋሁ” ሆኖ ነበር።

የመልስ ጉዞ

ግንቦት 18/1983 ዓ.ም ያ ማሰልጠኛ የኀዘን ድባብ አጥሎበት ነበር። የተወሰኑ ሰልጣኞች ግንቦት 16 ወ ይም 17 ይመስለኛል ከብላቴ የወጡት። ከሽነድ ብ ርጌድ ከነበርነው መካከል ግን ይህን ዕድል ያገኙት ጥቂቶች ናቸው። የሚወራው ነገር ሁሉ መያዣ መ ጨበጫ የሌለው ነበር። እኔ በራሴ የማደርገውን አ ላውቅም። የሽነድ አባላት በዚያች ቀውጢ ሰዓት ስ ንኳ ቀድመው ስለወጡት ተማሪዎች ብዙ ይሉ ነበ ር።አንዱ በሰላም አዲስ አበባ ገብተዋል ሲል ሌላኛ

ው ወያኔ መንገድ ላይ ይዞአቸው ወደ እስር ቤት አ ስገብቷቸዋል ይላል። አዋሳ እየጠበቁን ነው የሚል የመኖሩን ያህል ኬንያ ገብተዋል የሚልም ነበር። ሌ ላው ደግሞ ከደቡብ ዕዝ ጋር ተቀላቅለው ወያኔን ሊወጉ እየተዘጋጁ ነው ይላል። እነዚህን ምንጭ አ ልባ ዜናዎች እየሰማን ቁርስና ምሳ በላን። ከምሳ በኋላ አጭር ስብሰባ ተደረገና ወዲያዉኑ መውጣት እንዳለብን ተስማማን። ወዴት መሄድ እንዳለብን ግን በውል የሚያውቅ ያለ አይመስለኝ ም። ብቻ አዲስ ወደ ተሠራው አውሮፕላን ማረፍያ ሄድን። አንድ ነግር ግን እንዳትረሱ ፤ በዚያች ግቢ ከ17 ጀምሮ ተጠያቂነት ያለው አካል አልነበረም። አንዲት ሄሊኮፕተር እንደምትመጣና ወደ ድሬዳዋ እንደምትወስደን ሲነገር ሰማሁ። እርሷን ጥበቃ በአ ውሮፕላን ማረፍያው ላይ ታች ማለት ጀመርን። ወ ይ የመከራ ጊዜ ሰዓት ርዝመቱ!!! ለስልጠና ብላቴ ከቆየሁት ጊዜ ይልቅ ያቺን ሄሊኮፕተር ጥበቃ እዚ


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

21

ትዝታ

ኛዅ። “እንዴ በር የለውም እንዴ ቤቱ? በ ዚህ በረሃ?” ጉድ ፈላ! ደግነቱ ለመመራመ ር ድካሙ ጊዜ አልሰጠኝም። እንቅልፉ ይዞ ኝ ጭልጥ አለ። ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የፊ ሽካ እና እንደ ብራቅ የሚጮኽ ሰው ድም ጽ ነው። ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት አካባ ቢ። ሥልጠናው ተጀመረ በቃ? ወይኔ እንቅልፌ ….

“ሸርተቴ” እንቅልፍ የምትነሳ፣ ሌት የማታስተኛ ህሊና ሞጋቹ፣ ክፉ ወንጀለኛ መቼም አንላቀቅ፣ አንተ ተንኮለኛ ክስ አቅርቤያለሁኝ፣ ለፈራጁ ዳኛ ሳትታይ አድፍጠህ፣ ተሰውረህ ከ’ኛ ገብተህ የተገኘህ፣ ከዚች ከብላቴ በላ ልበልሃ፣ ተጠየቅ ሸርተቴ! ይዘን የመጣነው፣ የጠራ ሆድ ነበር አምጦ ሚያገሳ፣ ድምፁ የሚያሸብር ሲሻው የሚያሽካካ፣ ልክ እንደመትረየስ አሊያም እንደ ፈንጂ፣ ሙት የሚቀሰቅስ ወይም እንደ ጎማ፣ ምስማር እንደበሳው ብሶት ‘ሚተነፍስ፣ ሰው ሳያይ ሳይሰማው። ሸርተቴ ባንተ ግፍ፣ ተንኮል ሳይሰራ ሆዳችን ነበረ፣ የኮራ የደራ ልሳኑ ያማረ፣ ኮስታራ ቀብራራ፤ ምን ያደርጋል ታዲያ በጦርህ ተወጋ ድምጹ ጥፍት አለ ልሳኑ ተዘጋ ህገ-ሥርዓቱ፣ ፈረሰ ተናጋ።

ሥልጠናው?

ሥልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ ለዚያ የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተው ተሰጥተ ውናል። አንድ ጫማ፣ ቱታ፣ ካልሲ፣ ካናቴ ራ፣ አዣክስ ሳሙና፣ “ብሬዢኒቭ” የሚሉ ት ቁምጣ። ቁምጣውን በቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ፕሬዚደንት ስም ለምን እንደተሰየ መ አላውቅም። አለ ነገር ግን እንደዚያ አላ ሉትም። የኛ ሰው እንዲህ ነገሮችን እያገና ኙ ስም የመስጠት ልዩ ሥጦታ አለው። ይ ቺ ብሬዢኔቭ ቁምጣ ተማሪው በከፍተኛ “የዲያሪያ” (ሸርተቴ) ወረርሽኝ በተቸገረ ጊ ዜ ብዙ ውለታ ውላልናለች። ወታደራዊ ሥልጠና ከሥርዓት ነው የሚ ጀምረው። አስቀድሞ ተማሪው በብርጌድ፣ በሻለቃ፣ በሻምበል፣ በመቶ እና በጓድ ይከ ፋፈላል። የአንድ ሰው ወታደራዊ አድራሻ ው ይህ ነው። ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥ ር … እንደማለት ነው። አንድ ብርጌድ 3 ወ ይም 4 ሻለቃ ሊኖረው ይችላል። ብርጌዱ 4 ሻለቆች የሚኖሩት “አጥሻ” ከሚባለው ከ አስተዳደርና ጥበቃ ሻለቃ ጋር ሲደመር መ ሆኑን አንድ ሰው በቅርቡ ነግሮኛል። አንድ ሻለቃ 3 ሻምበሎች፣ አንድ ሻምበል ደግሞ 3 ወይም 4 የመቶዎች ሊኖሩት ይችላሉ። አንድ የመቶ 32 ሰው ይይዛል። ሁሉም የየ ራሱ ተጠሪ እና ኃላፊ አለው። ጠዋት በሌሊት ስንነሣ የመጣውና ያልመ ጣው የሚታወቀው በዚሁ መሠረት ነው። የታመመው፣ በሥንፍና የቀረው ሁሉም ሁ ሉም “ሪፖርት” የሚደረገው በዚሁ የአደባ ባይ ሥርዓት ነው። ጦርነት ሜዳ ውለን ቢ ሆን ኖሮ የሞተው፣ የቆሰለው፣ የከዳው፣ የገባበት ያልታወቀው፣ የተማረከው በዚሁ ከብርጌድ እስከ ጓድ ድረስ በተዘረጋ የዕዝ ሰንሰለት የሚለይ ይመስለኛል። ጠዋት ተነ ሥተን የምንሰለፍበት እና ቆጠራ የሚደረግ በትን ሥነ ሥርዓት “ፎሌን” ቆጠራ ይሉታ ል። ቦታው ደግሞ “ፎሌን ሜዳ” ይባላል። ትርጉሙን አትጠይቁኝ። ሰልጣኙ በመጀመሪያ ጠዋት የሚያከና ውነው አካል ማጎልመሻ ወይም ስፖርት ነ ው። በወታደር ቤት “ላብ ደምን ያድናል” የሚለው አባባል የተለመደ እና አካል ማጎ ልመሻን የሚያሳይ ነው። በስፖርት ያልተገ ነባ እና በብቃት ያልቆመ ወታደር ዋጋ የለ ውም። በአንድ ጊዜ ከ25 ኪሎ ግራም ያላነ ሰ ሸክም ተሸክሞ ተራራውን ለመውጣት፣ ቁልቁለቱን ለመውረድ ሰውነቱ ብቁ መሆ ን አለበት። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባ ሉ አገራት ያሉ ወታደሮች አብዛኛውን መ ንገድ በእግራቸው የመጓዝ ግዴታ ስለሚኖ ርባቸው ጥንካሬ መኖሩ የግድ ነው። አሜ ሪካን የመሳሰሉ ያደጉ አገሮች ወታደሮቻቸ ው ከ50 እስከ 90 ፓውንድ ሸክም ቢኖራ ቸውም በእግራቸው የሚጓዙት መጠነኛ ስ ለሚሆን ሸክሙ ይህንን ያህልም አይጎዳቸ ው ይባላል። ለዚህ ሁሉ ግን ወታደር እና

ስፖርት መዛመድ አለባቸው። የወታደሮች ስፖርት ትዝ የሚለኝ ገና ከ ሆለታ ጀምሮ ነው። ቤታችን ከከተማ ወ ደ ጦር ካምፑ ባለው ዋና መንገድ ላይ በ መሆኑ ሁል ጊዜ ጠዋት ጠዋት (ከሌሊቱ 10 እና 11 ሰዓት አካካባቢ) ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን አንደኛው የወታደሮቹ ሩጫ ነው። የብዙ ወታደር ኮቴ ከጥቁሩ አስፓል ት ጋር ሲጋጭ የሚፈጠረው ድምጽ ሌሊቱ ን ያደምቀዋል። በመካከል በመካከሉ የአሰ ልጣኛቸው ድምጽ ወይም ፊሽካው ይሰማ ል። ከዚያ ውጪ ያለው “እረም-እረም” የ ሚለው የብዙ ሰዎች እግር ነው። በብላቴ ግን እረም እረም የሚያደርግ አስፓልት የለ ም። አፈር ብቻ። ብላቴ ቀስ ብሎ ከሚደረገው ጉዞ በመለስ ተኛ ሩጫ በ“ሶምሶማ” የሚደረገው ይበል ጣል። ከሥልጠና መልስም ሆነ ወደ ሥል ጠና ሲኬድ ዱብ ዱብ እያሉ መሔድ የተለ መደ ነው። በተለይም ከቀን ሙሉ ድካም በኋላ ወደቤት መልስ ሲሆን “ሞራል እያወ ጡ” (የጋራ ዘፈን እየዘፈኑ) የሚደረገው የሶ ምሶማ ሩጫ መንገዱን አጭር፣ ድካሙን ቀ ላል ያደርገዋል። አለበለዚያ እንደ ከተማ ሽ ርሽር በ“ዎክ” እየተንቀራፈፉ ልሒድ ካሉ ት እግርም ከመሬት አይነሣ፣ መንገዱም ማ ለቂያ አይኖረው። ወታደሮች በጋራ ዘፈን እ የዘፈኑ በሩጫ የሚያደርጉት ጉዞ ነው “ሞራ ል ማውጣት” የሚባለው።

ቢጫ ወባ፣ ሸርተቴ፣ “ሻምበል ደቤ” እና ዱካክ

የትንሣኤ ዕለት ግሩም ምሳ አበሉን። ም ሳ ሰዓት ላይ “የወባ ክኒን ነው” ተብሎ ሁለ ት-ሁለት ክኒን እንድንውጥ ተሰጠን። ዋጥ ን። ከዚያ በኋላ ግን ሁላችንም ደንዝዘን ዋ

ያ አየር ማረፍያ የቆምሁት እንደሚበልጥ ይታሰበኛ ል። ሽነድ አሁንም ይሸንዳል። ከብዙ ጥበቃ በኋላ ሄሊኮፕተሯ በአቧራ ተከባ ዐ ረፈች። ተማሪው እንደ እናት ንብ ከበባት። በውስ ጧ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ መሣርያ የያዛችሁ ተማሪዎች መሣርያችሁን ጣሉ፤ ያለበለዚያ መሣር ያ ይዛችሁ ልናሳፍራችሁ አንችልም” ሲል መመርያ ሰጠ። ተሜ ለሁለት ተከፈለ። መሣርያ የያዘው አን ጥልም፤ ያልያዘው ጣሉ። ስምምነት ጠፋ። ጩኸት ብቻ ሆነ። አብራሪውም ተማሪዎቹ እንዳልተስማ ማን ባየ ጊዜ እየኮበኮበ ጥሎን ሄደ። ቀኑ መሸ፤ ፀሐይም ጠለቀች። አሁን ወያኔ ዙርያ ውን ከብባለች ተባለ፤ ሽነድ። ሁላችንም በፍርሃት ወደ ኬስፓናችን ተመለስን። ግን ምን ተበልቶ ሊታ ደር? ማሠሰልጠኛው አሁን ተፈትቷል። እስቲ ምግ ብ ቢገኝ ብለን ወደ መመገቢያ ክፍል ገባን። ባልተ ከደነ ጎላ ድስት ውስጥ ከምሳ የተረፈ ማካሮኒ በ ነፍሳት ተወሮ አገኘን። ጎበዝ ሳይንስ አሁን አይሠ ራም፤ ሰባ ሰባት ሆነን ያችን ምግብ እንደ ነገሩ ተ ቃመስናት። ሌላው ሥጋት ተረኛ ዘብ የለ፤ ማን ይጠብቅ? ለካ የሽብር ሌሊት ይረዝማል የሚባለው እውነት ነው።

ልን። ግማሹ በመኖሪያው አዳራሽ (ኬስፓ ን) ግማሹ በየዛፉ ሥር ውድቅድቅ ብሎ ዋ ለ። ከመጠን በላይ የሆነ ነገር ሰጥተውን ይ ሁን ወይም ሌላ ምክንያት ይኑረው አላወቅ ኹም። ብቻ ጅላጅል ሆነን ማሳለፋችን ት ዝ ይለኛል። “ቢጫ ወባ እንዳያጠቃችሁ” የ ሚለው አባባል ብዙ ጊዜ ስለሚነገር ከፍተ ኛ ፍርሃት ነበረብን። ዝዋይ ለጥቂት ወራት በነበርኩበት ጊዜ ወባ አልያዘኝም። የብላቴውንም “አውጣ ኝ፣ አውጣኝ” እያልኩ ከረምኩ። በተለይ የብላቴው “ጭንቅላት ላይ የሚወጣ እና ቶሎ ሕክምና ካላገኘ አሳብዶ የሚገድል ነ ው” (cerebral malaria) ስለሚባል በሕ ጻንነታችን እንፈራው የነበረው “ጭራቅ” ዓይነት ስሜት ፈጥሮብን ነበር። በየስድስ

ከአሁን አሁን ወያኔ መጥታ አፈነችን በሚል ስጋት ስንባንን አደርን። ጠዋት ሁሉም ከየኬስፓኑ ወጥቶ ከፎለን ሜዳ ሳንደርስ ዝቅ ብሎ ካለው አዳራሽ መ ሳይ ትልቅ ቤት አጠገብ ተገናኘን። በእግር ወደ አዋ ሳ መሄድ እንዳለብን ተወያየን።

ጥይት እንደ ቆሎ…

የተወሰንን ልጆች ምናልባት ከመንገድ የሚያገኘን ን ስለማናውቅ ጠብ መንጃ መያዝ እንዳለብን ተስ ማማንና ወደ መሣርያ ግምጃ ቤት ተጓዝን። ወደዚ ያ ከመጓዛችን በፊት መጋዘኑ መሰበሩን ሽነድ አብ ስሮናል። መሣርያ ለመውሰድ እንሂድ እንጂ ፍርሃ ት ግን በልቡናችን መልቶ ነበር። ብቻ ስንፈራ ስንቸ ር ከመጋዘኑ ገብተን አንዳንድ ነፍስ ወከፍ መሣርያ (ኤስ ኬ ኤስ?) ወሰድን። የጥይቱን ቁጥር አላስታ ውሰውም። ጠብ መንጃው ከነ ጥይቱ ተስተካክሎ ተያዘ። የቀረው መጓዝ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ጉዞ በአ የር ማረፍያው በኩል አቋራጭ ነው ስለ ተባለ በዚ ያ አቅጣጫ ተጀመረ። አንድ ኪ.ሜ እንደ ተጓዝን ጓ ዝ መቀነስ እንዳለብን ተነጋገርን። ስለዚህ ቅያሪ ል ብስ ብቻ አስቀርተን ሻንጣዎቻችንን ሁሉ ከሜዳው ላይ ወረወርናቸው። ቻዎ ብላቴ!!! ጉዞ ወደ አዋሳ። የግንቦት 19/1983 ዓ.ም ፀሐይ ከወትሮዋ ይልቅ የ

ት ወሩ ለሥልጠና ይገባ ከነበረው በሺዎ ች ከሚቆጠረው ምልምል ወታደር ውስጥ ቁጥሩ ጥቂት የማይባለው በዚሁ “ቢጫ ወ ባ” ያልቅ እንደነበር አሰልጣኞቻችን ሲናገ ሩ ሰምቻለኹ። ከቢጫው ወባ ውጪ የግቢው ዋነኛ በሽ ታ የሆድ መታወክን የሚያስከትለው እና በ ተማሪው አጠራር “ሸርተቴ” የሚባለው ተ ቅማጥ/ Diarrhoea ነው። (በሌላ አማርኛ መግለጽ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። ‘ስለተፈ ጠረው የቴክኒክ ችግር ይቅርታ’ እንዲል የ ኢትዮጵያ ሬዲዮ):: ይህንኑ በሽታ ነፍሱን ይማረውና ገጣሚ እና ጋዜጠኛ የነበረው መስፍን አሸብር ግሩም በሆነው ግጥሙ፣ “ሸርተቴ”፣ በማይጠፋ መልኩ አስቀምጦት አልፏል። ተማሪውም የዚህን ግጥም ዋና ዋ ና አንጓዎች እና አዝማቾች በቃሉ አጥንቶ ት ነበር። በተለይም ከዚህ በታች ያለውን ብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ እናስታውሰዋለን።

“ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት ቀጭን ኩታ መሳይ አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።” እያለ ይ ቀጥላል። (ሙሉውን ግጥም ከጎን ባለው ሳጥን ስር ያንብቡ) መቸም እንዲህ ባለው ነገር፣ ያውም ታሞ ባለ ሰው፣ መቀለድ ደግ አይደለም። ግን ደ ግሞ ችግሩንም በሽታውንም እያሳሳቁ እና እያዋዙ ካላለፉት፣ ቢያለቃቅሱ ምን ይገኛ ል እንጂ ሸርተቴስ ቀላል ተማሪው ላይ አል ተጫወተበትም። ገጣሚው መስፍን እንዳለው “Diar-

ደመቀችና የፈካች መስላለች። ፀሐይ ከማለት ይል ቅ ሀሩር ተብላ ብትጠራ ይሻላል። ላብ እንደ ጅረት በመላው ሰውነታችን እየጎረፈ ሃያ አምስት ኪ.ሜት ሮች ተጉዘን ዲምቱ ከምትባለው መንደር ደረስን። ዲምቱ የገጠር ከተማ ብትሆንም ስደተኛውን ተማ ሪ ለመቀበል ግን አቅም ነበራት። በየ ደሳሳ ቤቶች ውስጥ የመብልና የመጠጥ ንግድ የሚጧጧፍባት መንደር ናት። እህል ውኃ ፈልገን ቀመስን። አሁን ት ንሽ በርትተናል። ከሰውም ተቀላቅለናል። ቀጣዩን ጉዞ ከመጀመራችን በፊት ከፊት ለፊታች ን ስላለው ነገር መረጃ ማግኘት ግድ ነው። ስለሆነ ም የከተማዋን ሰዎች ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ጠየቅ ናቸው። የሚያውቁትን ያህል ነገሩን። ከብላቴ የመ ጡ ጥቂት የአየር ወለድ አባላት ከድልድዩ አጠገብ ሆነው ማንኛውንም ዓይነት መሣርያ ከያዘ ሰው ቀ ምተው እንደሚወስዱ አረዱን። “ጓዛችንን ሁሉ ጥ ለን የያዝነውን መሣርያ፣ ከሃያ አምስት ኪ.ሜትሮች በላይ በዚያ በረሃ በመሸከም የደከምንበትን መሣር ያ እንዴት ይቀሙናል?”፣ “አሁን ምን እናድርግ?”፤ ሌላ ጭንቀት። ጦርነት ልንከፍት? ጊዜው የከፈተብ ንን ጦርነት መች ተወጣነውና? በኋላ መሣርያዎቻችንን መሸጥ እንዳለብን ተስማ

rhoea” የሆድ በሮች እና መስኮቶች የ ማይገቱት ቀጭን እና ፈጣን ሯጭ ነ ው። መጣሁ ሲል ወዲያው ካላስተናገ ዱት፣ በር ካልከፈቱለት “ግምኛ” ሰው ን ያበላሻል፤ ያዋርዳል። ሲመጣ ቦታ አ ይመርጥም። ጊዜ አይለይም። ከች ሲል ታማሚው እንደ ጥይት ተተኩሶ ከሽን ት ቤት ወይም ከአንድ ዛፍ ሥር መገ ኘት አለበት። ለዚህ እንዲረዳ ታማሚ ው ልብሱን ማስተካከል አለበት። አንዳ ንድ ሰልጣኞች “ሽርጥ” ያደርጉ ነበር። ለሌላቸው ደግሞ “ብሬዢኔቭ ቁምጣ” ምቹ ነው። ባለ ሽርጡ ታማሚ ሸርተቴው ሲመ ጣ የሚጠበቅበት ወደ ዛፍ ሥር መሮ ጥ እና ሽርጡን በፍጥነት መግለጥ ብቻ ነው። ሱሪ ማድረግ ለመበላሸት ካልሆ ነ በስተቀር ተመራጭ አይደለም። ብሬ ዢኔቭ ቁምጣ እግሩ ሰፋፊ፣ ቶሎ ለማ ውለቅ ምቹ ስለሆነ የተማሪው ባለውለ ታ ሆኗል። ብዙው ታማሚ ሰልጣኝ ቀ ን ቀን አየር ለመቀበል፣ ለሽንት ቤት እን ዲቀርበውም ውጪ ጎጆዎች ውስጥ መ ቀመጥን ይመርጣል። በዚህ ጉዳይ ላይ “AN INVESTGATION OF DIARRHOEAL DISEASE OUTBREAK AT BILATE MILITARY TRAINING CENTRE” በሚል ጥናት ያደረጉት ዶ/ር መኮንን አ ድማሱ እና አበራ ገይድ (Makonnen Admassu, MD & Abera Geyid, MSc) እንዳስቀመጡት ከሆነ በወቅቱ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

ማን። አንድ ጠብ መንጃ በ250 ብር፣ አንዲት ጥይ ት በ0.40 ሣንቲም ተሽጠ። አሁን ከውትድርና ጋ ር የሚያይዘን ምናልባት ለታሪክ የያዝኳት ቱታ(ሰ ማያዊዋ) ብቻ ካልሆነ እኔ ዘንድ አንዳች ነገር የለ ም። ብቻ በመንገድ የመቁሰል አደጋ ቢደርስብን ለ መጀመርያ ርዳታ መስጫ ይሆናል ብየ የያዝኩት አ ንድ ጠርሙስ አዮዲን እጄ ላይ ነበር። አሁን ሳስበ ው ጠርሙስ ሙሉ አዮዲን ተሸክሜ ያን ሁሉ መ ንገድ መጓዜ ይገርመኛል። ጠብ መንጃችንን ሸጠን ብራችን ቋጥረን ፀሐይ ማዘቅዘቅ እንደ ጀመረች ለ ቀጣዩ ጉዞ ተነሣን።

የቅርብ ሩቅ

እረኞች ከብቶቻቸውን እየነዱ ወደየቀዬያቸው እ የተመለሱ ነው። ከቁመታቸው በላይ ዘለግ ያለና ሰ ፋፊ ጦር የያዙ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ልዩ ፍጥ ረት ተገርመው ያዩናል። ይህ ደግሞ ሌላ ፍርሀት ፈ ጠረብን። ቀደም ሲል ከሞሪቾ እስከ ብላቴ ባለው መንገድ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ከባህል የተነሣ ወ ንድ ገድለው ይሰልባሉ የሚል ዜና ሰምተን ነበር። ይህን ዜና በሚያጠናክር መልኩ ያን አስፈሪ ጦር ያ ዘው በልዩ ትኩረት ሲያዩን ደግሞ በውስጣችን ከ ፍርሃት የላቀ ፍርሃት ተሰማን። ፀሐይዋ ከእኛ ጋር

አቤት ያንተ ተንኮል፣ አቤት ያንተ ሥራ አብሪ ጥይት የለህ፣ መንገድ የሚመራ። ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት ቀጭን ኩታ መሳይ አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት። አይ አወራረድህ፣ አይ አተኳኮስህ ቴትራ ሳይክሊን፣ ሚዝል አይመልስህ “ብሬዢኔቭ ቁምጣ”፣ ሱሪ አያግድህ ሆድን ፈለጥለጥለጥ፣ ቁርጥ ቁርጥርጥርጥ ሸርከት ሸርከትከትከት፣ ዓይናችንም ፍጥጥ ሸራ ለመሸረር፣ ፋታ የማትሰጥ በቀላው አሸዋ፣ በሚቆረቁረው ጀግናን በባዶ እግር፣ ይዘህ ያሯሯጥከው ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ ሸርተቴ ጅንኑ፣ ኩሩ ዘለግላጋው፣ ስንቱን አደረከው አጉል ኩራተኛ? ሰው የማያናግር ሌሊት የማይተኛ። …. ከሞቀ ጨዋታ፣ ወጉ ከደራበት ስንቱ ፈረጠጠ፣ ዘለለ በመስኮት? ከመኖሪያ ታዛ፣ ከኬስፓኑ ነቅለህ ከጎጆ ከተትከው ፍራሽ አስነጥፈህ። ሆዱን ሊያስታግሰው ተርቦ ተጠምቶ እጁን ሲሰነዝር፣ ‘ከሜስ’ ቤት ገብቶ አንተ መጣህና፣ ገበታውን ትቶ ስንቱ ፈረጠጠ፣ ሾርባውን ጎልቶ? አንጀቱን ሰርስረህ፣ ከግርጌ ከስሩ አይ አፈጣጠንህ፣ የሥራህ ነገሩ። ሲሻህ አረንጓዴ፣ ሲልህ ትቀላለህ ወይም ቢጫ ሆነህ፣ ትቀይረዋለህ አንዳንድ ጊዜማ፣ ድብልቅልቅ ትልና ትመሳሰላለህ ከቀስተ ደመና። ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት ቀጭን ኩታ መሳይ አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።” (መስፍን አሸብር፣ በ1983 ዓ.ም ብላቴ ጽፎ ት፣ “ጠብታ ፍቅር” በሚል ከታተመው መ ጽሐፉ የተወሰደ።)

ውድድር የያዘች ትመስላለች። እርሷም ወደ ማደር ያዋ ለመግባት ትቻኮላለች። ዓይኖቻችን በጨለማ ው መያዝ ጀምረዋል። የምናየው ከአጠገባችን ያለ ውን ብቻ ነው። እነዚያ ባለ ጦሮች ይጠራሩ ጀመ ር። ምን እንደሚነጋገሩ አናውቅም። ብቻ ፍርሃት የ ነገሠበት ልባናችን እኛን ሊገድሉ እየተነጋገሩ እንደ ሆነ አድርጎ ነገረን። ተስፋችን ተሟጥጦ የእነዚያ ሰዎች አስፈሪ ጦሮች ካሁን አሁን ተወርውረው ከሰውነታችን ላይ ተተከ ሉ እያልን በምንሸማቀቅበት ሰዓት የቀይ መስቀል ድርጅት ተሳቢ ካላብረስ መኪና ከመቅጽበት ከፊታ ችን ድቅን አለ። ሾፌሩ በዚያ ጨለማና ወጣ ገብ የ ገጠር ማሳ ውስጥ እንዴት እንዳዞረው አላውቅም። ብቻ “ቶሎ ቶሎ በሉና ከላይ ውጡ “’ ሲለን የፍር ሃት ካባዬ ከላዬ ሲወድቅ ታወቀኝ። ሁለተኛው መ ኪና ከኋላ ያሉትን ተማሪዎች ሊሰበስብ ከነፈ። ሾ ፌሩ ከካርቶን ውስጥ ያለውን “ጋሌጣ” ወይም “ኮ ቸሮ” እንድንበላውም አዘዘን። መኪናው ሞሪቾ ከተማ ካለ አንድ የቀበሌ ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ ገባና” ውረዱ” ተባልን። እኛ ወርደን እ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል


ሀበሻዊ ቃና

22

ብላቴ ወታደራዊ... ከገጽ 21 የዞረ በብላቴ ገብቶ የነበረው እንዲህ ቀላል በሽ ታ ሳይሆን “ወረርሽኝ” ነው። ጥናቱ ያተኮረው ከMarch 5 to 22, 1991 ድረስ ብቻ ያለው ጊዜ ላይ በመሆ ኑ ከዚያ በኋላ የታመሙትን አልተመለከ ተም። ለዚያውም ቢሆን 1616 ተማሪ መ ታመሙ ጥቂት የሚባል አይደለም። በዚ ያው ተመሳሳይ ወቅት ደግሞ በሌሎች በ ሽታዎች የተጠቁ 3582 ተማሪዎች መኖራ ቸውን ልብ ይሏል (THE ETHIOPIAN JOURNAL OF HEALTH DEVELOPMENT )። ሸርተቴ ሰው ቢሆን ኖሮ “ም ን አቅብጦኝ እነዚህ ተማሪዎች ጋር መጣ ሁ፣ ምነው ባልያዝኳቸው ኖሮ” ሳይል አይ ቀርም። ምክንያቱስ? ቀለድንበት፣ አሾፍን በት፣ ብዙ ሳቅንበታ። ገጣሚውም በግጥ ሙ እንዲህ አሞግሶ ተሳለቀበታ። ከሸርተቴው እና ከወባው ባሻገር ዱካኩ እና ቅዠቱ ብላቴ ላይ ሰልጥኗል። ወታደ ሮቹ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ መንፈስ “ሻምበ ል ደበበ ወይም ሻምበል ደቤ” ይሉታል። እንደዚያ የተባለበት ታሪክ አለው። ነገሩ እ ንዲህ ነው። በግቢው ውስጥ አንድ ሻምበል ደበበ የ ሚባሉ መኮንን ነበሩ አሉ። መኮንኑ እጅግ ቁጡ እና በበታቾቻቸው ዘንድ እጅግ የሚ ፈሩ ነበሩ። ታሪኩን የተረኩልን ሰዎች እን ደሚያቀርቡት ከሆነ ጥፋት ያለበት ወታደ ር ከተገኘ ሻምበል ደቤ እንዲህ በቀላል አ ይለቁትም። በወታደሩ ቤት እንደተለመደ ው አንድ ሻምበል ወደታች ወርዶ አንድ ተ ራ ወታደር ቁጭ በል፣ ብድግ በል እያለ አ

“ሽነድ” እና ፍርሃት... ከገጽ 21 የዞረ ንዳበቃን መኪናው ለሌላ ተልእኮው ሄደ። የሞሪቾን የአየር ንብረት ሁኔታ ባለውቅም የዚያን ሌሊት ግን ሊዩ የሆነ ብርድ ነበር ያደረባት። ለተማሪው የሚበቃ ክፍል ባለ መኖሩ ያደርነው ሜዳ ላይ ነው። እንኳን ያ ቺን የሞት ቀጣና አለፍናት እንጂ ብርዱስ ምንም እንደማይለን ተረድተናል። ደግሞ ም በመንገድ የዛለ ሰውነት በቀላሉ በእንቅ ልፍ ስለሚሸነፍ ስጋት አልገባንም። ሁላች ንም “ሿ” ብለን ተኛን። እኩለ ሌሊት ካለፈ በኋላ አንድ ኀይለኛ ድምፅ ቀስቀስን። አንድ ተማሪ ነው፤ ያለቅ ሳል፤ ይጮኻል፤ ይስቃል፤ በሀገሪቷ ላይ፤በ ተማሪው ላይ፤ በራሱ ላይ ስለሆነው ነገር ይናገራል።መጀመርያ ላይ እንቅልፍ እም ቢ ብሎት መስሎን ነበር። በኋላ ግን የአ እምሮ ጭንቀት አግኝቶት እንደ ሆነ ተረዳ ን። ያለቅሳል፤ ያንጎራጉራል። የሚናገረው ቃል ሕሊናን ይረብሻል። በዚህ ጉዳይ የም ናደርገው ነገር ጠፍቶን ግራ እንደ ተጋባን ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ሲሆን ሁላችንም ወ ደ አዋሳ ጉዞ ጀመርን። በጧቱ ብዙ ገሰገስን። ፀሐይ ወጥታ ሰማ ይ ምድሩን ስናይ አዋሳ እጅግ ቅርብ ሆና ስ ለ ታየችን በተስፋና በሞራል ብንራመድም እርሷ ግን እንዳንደርስባት የምትሸሽ ይመ ስል በቀላሉ ልትደረስ አልቻለችም። እኛ ም ጉልበታችን መዛል ጀምሯል። መቼም የተጀመረ መንገድ ሳይፈጸም ከመሃል መ ቅረት የለ ጥርሳችንን ነክሰን ተጉዘን አዋ ሳ ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ገባን። ግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም።

ባዶዋ ከተማ

አዋሳ ጭር ብላለች። ምግብ ቤቶቿ ተግ ባራቸውን ያቆሙ ይመስላሉ። ሻይ ለመጠ ጣት ብንፈልግ እንኳ ዬት ተገኝቶ? ቡና ቤ ቶችና ሆቴሎች በፍርሃት ስለ ተዘጉ መኝ ታ ማግኘት አልተቻለም። ስለዚህ ማረፍያ ቢገኝ ብለን ወደ አዋሳ እርሻ ኮሌጅ አቀና ን። ኮሌጁ ከብላቴ የተመለሱ ተማሪዎችን ለመቀበል በሩን ክፍት አድርጓል። ያ ግቢ ላለፉት ሁለት ወራት ግን ዝግ መሆኑን ል ብ ይበሉ። አሁን የሚታየኝ ምግብ ውኃ አ ይደለም፤ ብቻ ጎኔን የማሳርፍበት ቦታ። እ ግሮቼ ተላልጠዋል። ከዚህን በላይ እንኳን መራመድ መቆም ከማልችልበት ደረጃ ላ ይ ደርሻለሁ። ውስጥ እግሬ አብጧል።ከኮ ሌጁ ግቢ እንደ ገባሁ እንደ ምንም ወደ አ ንድ የተማሪዎች ማደርያ ክፍል አመራሁና ካገኘሁት ተደራራቢ አልጋ ከላይኛው ቆጥ ላይ “ዧ” ብዬ ወደቅሁ።

ይቀጣም። ግን ያስቀጣል። ትዝ እንደሚለኝ ሆለታ ጦር ካምፕ ውስ ጥ አስር አለቃ በቀለ የሚባሉ አንድ ረዥም ወታደር፣ በመቅጣት የሚታወቁ ነበሩ። ከ ርሳቸው ከፍ ሲል ደግሞ መቶ አለቃ (ም ትኩ ይመስለኛል ስማቸው) በጣም ይፈሩ ነበር። አስር አለቃ በቀለ ሲቀጡ በመጀመ ሪያ ወታደሩን ቀበቶውን ያስፈታሉ። የጫ ማውን ማሰሪያ ያስወልቃሉ። ከዚያም በ ሩጫም ይሁን ብዙ ፑሽ አፕ በማሠራት ል ቡን ያጠፉታል። አስር አለቃ በቄ የሚታወ ሱት “ኢኔ ዲረስ፣ ቦንባ ዲረስ፤ እኔ ድረስ፣ ቧንቧው ድረስ” በሚለው ወዲያ ወዲህ የ ሚያሯሩጥ ስፖርታቸው ነው። የብላቴው ም ሻምበል ደቤ እንዲሁ የሚፈሩ መኮንን ኖረዋል። ሻምበሉ መቅጣት ከፈለጉ አንዱ ን ሻለቃ ጦር፣ ወይም አንዱን ሻምበል ጦ ር፣ ወይም አንዱን የመቶ ጦር በስፖርት ል ቡን ያጠፉታል። አንድ ወታደር ብቻውን ም እንደዚያው። ታሪኩ እንደሚያትተው፣ አንድ ቀን ጦሩ ሁሉ ለጥ ብሎ ከተኛበት “የሻምበል ደቤ ፊ ሽካ” በቀጭኑ ትሰማለች። ጦሩ በርግጎ ተነ ሥቶ ይወጣል። ሻምበል ደቤ አንድ ሰበብ ፈጥረው ብቻ ያንን ጦር በጭለማ ሲያሯ ሩጡት ያድራሉ። ከዚያም ቅጣቱ ያልቅና ውልቅልቅ ያለው ጦር ወደ አልጋው ተመ ልሶ ይዘረራል። ቆየት ብሎ፣ “ፎሌን ሲነፋ” የሚነሣ ሰው ይጠፋል። አለቆች ወደ ጦሩ ቢመጡ ሁሉም ወዳድቋል። “ተነሥ!” ቢባ ል ማን ይነቃነቅ። “ምን ሆናችሁ?” ሲባል “ሻምበል ደበበ ሲቀጡን አደሩ” ይላል ጦ ሩ። በነገሩ ሻምበል ደበበ ራሳቸው ይገረ ማሉ። ለካስ በሻምበል ደቤ ተመስሎ የመ ጣው “አጅሬ ሰይጤ” ኖሯል። ከዚያን ጊዜ

ወዲህ “ሰይጣን፣ ዱካክ” ማለት ቀረና በቁ ልምጫ “ሻምበል ደቤ” ተባለ። ወታደሮቹ የሚናገሩት ሌላም ብዙ ነገር አላቸው። ለምሳሌ ጦሩ ቀን ቀን ሲዘፍን የ ሚውለውን ዘፈን ሻምበል ደቤ ደግሞ ሌ ሊቱን በሙሉ የራሱን ጦር ሲያዘፍን ሰምተ ናል ይላሉ። “ቡቄሳ ኮረብታ” የምትባለው ና ወታደሩ የሚማርባት ትንሽ ጉብታ መሬ ት ቀን ቀን ጦሩ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የሻ ምበል ደቤ ጦር ይዘፍኑባታል እየተባለ ይ ቀለዳል። እንግዲህ ሰይጣን “ሞራል እያወ ጣ” ወደየትኛው ውጊያ እንደዘመተ እግዜ ር ይወቀው። በደፈናው ግን “ውሸት ነው፤ ሲጋነን ነው፤” ማለቱን አልመረጥኹም። እኔ የማውቀውን ግን ልንገራችሁ። ተማ ሪው ሌሊት ሌሊት በጣም ይቃዥ እንደነ በር ትዝ ይለኛል። ሙቀቱ ይሁን፣ ሻምበል ደቤ ይሁን፣ ወይም የሁለቱ ጥምረት ይሁን እንጃ። እናም ቤተ ክርስቲያን እንደምንሔ ድ የሚያውቁ የሌላ እምነት ተከታዮች ሳይ ቀሩ “እባካችሁ ዱካክ አስቸገረን እኮ” ይሉ ን ነበር። ያለችንን ውዳሴ ማርያም አካፍለ ን “ትራስህ ሥር አድርገኸው ተኛ” እንላቸ ዋለን። እውነትም “ሰላም አደርን ዛሬ” ይላ ሉ - ሌላ ጊዜ። እንደማስታውሰው እኔም ራሴ አንድ ቀን አሞኝ ከሥልጠና ቀርቻለኹ። ሐኪም ቤ ት አልሄድኹም። ለጥ ብዬ ዋልኩ። ጉልበ ት አጥሮኝ ነበር። መቸም የፀሐዩ ነገር አይ ነሣ። ቆዳችን በዋዕዩ ክስል ብሎ ያረረ የጥ ቁር ጤፍ ቂጣ ይመስላል።

እንደ ሞት የከበደ እንቅልፍ ወሰደኝ። ም ን ያህል ሰዓት ወይም ደቂቃ እንደ ተኛሁ አላስታውስም። ብቻ ከዚያ ጣፋጭ እንቅ ልፍ ከታችኛው ተደራቢ ተኝቶ የነበረው ጓደኛዬ (ሲሳይ ለማ) ሲገላበጥ ባንኜ ተነሣ ሁ። “ለምን ቀሰቅስኸኝ?” ብዬም ጮኹበ ት። እስቲ ጎንህን እየው? አለኝ። ልብሴን ገ ልጬ ጎኔን ባየው ጤፍ ላይ ተኝቼ ገላዬ ላ ይ የተደመደመ ይመስል ትኋኑ እላዬ ላይ ተደምድሟል። የመጨረሻ አዘንሁ። አይደል ክፍሉን ግቢውን ጠላሁት። በል ብሴ ውስጥ የተሰገሰጉት ትኋኖች እንደ ረ መጥ ይለበልቡኝ ጀመር። በመቶዎች የሚ ቆጠሩ ትኋኖችን ይዤ ከዚያ ግቢ ወጣን። የት እንሂድ?የት እንግባ? ማን ያስጠጋና ል? ከተማዋ ውስጥ መንከራተት ጀመር ን። ከብዙ ድካም በኋላ አንድ የአኢሴማ ጽ/ቤት (03?) አገኘንና እንዲያሰጠጉን ለ መናቸው። የጽ/ቤቱ ወለል ሊሾ የሚባለ ው ነው። ምንጣፍ ወይም ሰሌን ነገር አል ነበረውም። ሴቶቹም በዚያ ሊሾ መሬት ላ ይ ገብታችሁ ተኙ ማለቱ ከብዷቸዋል። ግ ን የሊሾው ቅዝቃዜ ከድካማችን ስለማይ ብስ እሽ እንዲሉን ተማጸናቸው። ሲፈቅ ዱልን ገብተን አቧራዋን እፍ ብለን ተኛ ን። ግንቦት 20፣21። ደስታ ከረሜላ የምታ ክል ዳቦ በ0.25 ገዝተን ረሃባችንን ማስታ ገስ ጀመርን። ግንቦት 21 ጠዋት ከመኝታችን ተነሥተ ን በር ላይ ቆመን የዕለቱን እንቅስቃሴ እየ ተመለከትን ነው።ከእኛ በፊት ከብላቴ የወ ጡት ተማሪዎች በሰላም ኬንያ መግባታቸ ው ተወራ። አንድ የአየር መቃወሚያ መ ሣርያ ያለበት መኪና ካለንበት በር አጠገ ብ ሆኖ ወደ ኬንያ መሄድ የሚፈልግ እን ዳለ ይጠራ ጀመር። ጓደኛዬ የኔወንድም እ ንየው ካልሄድን ብሎ ሞገተን። ብቻ እን ደ ምንም አሸነፍነውና አስቀረነው። ግንቦ ት 22፣ 23። ወያኔ ሀገሪቱን መቆጣጠሯ እ ውን መሆኑ እየታመነ መጣ። ሌሎች ሰዎ ች ደግሞ እስካሁን ደቡብ ዕዝ እጁን አልሰ ጠም፤ ተማሪውም ወደ ኬንያ አልገባም፤ነ ገር ግን ከደቡብ ዕዝ ጋር ተቀላቅሏል ብለ ው ያወሩ ጀመር። ለእኔ የሁሉም ነገር አል ታይህ ብሎኛል። የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ መኪና አግኝቼ አዲስ አበባ ከ ቤተሰቤ ዘንድ መድረስ።

ባቢ ይመስለኛል። ገና ከመኪናው ሳንወር ድ አንዲት ሚኒባስ ታክሲ አዲስ አበባ ል ትሄድ ረዳቷ ሲጣራ ሰማንና ሃያ ሆነን ተሳ ፈርን። በአርባ አርባ ብር ከፍለን ጉዞ ወደ አዲስ አበባ። አሁንም ግን ፍርሃት በውስ ጤ ነበር። ወያኔ በመንገድ ብትይዘንስ? እ ርሷን ልንወጋ እንደ ዘመትን አይደል የምታ ውቀው? ብታስረንስ? ብትገርፈንስ? ዘማ ች ተማሪዎች መሆናችንን እንዴት ታውቃ ለች? ቢያንስ ለማስታወሻ ብለዬ የያዝኩት ሰማያዊ ቱታ ከእኔ ጋር አለ። ደግሞ ያ ጠ ርሙስ ሙሉ አዮዲንም አልተጣለ። ሌሎ ቹም እንዲሁ አንድ ነገር አያጡ። ብቻ መ ንገዳችን ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥተን መ ጓዝ ጀመርን። ወያኔን በቴሌቪዥን መስኮት ከማየት በስ ተቀር በአካል አይቼ አላውቅም ነበር። በደ ርግ መገናኛ ብዙኃን የሚነገረንም ነገር ወ ያኔን ልዩ ፍጥረት እንደ ሆነች አድርጎ የሚ ያቀርብ ነበር። እንኳን ሌላ “አንቺ” የሚለ ውን ቅጽል እንኳን ውስጤ እንዴት ገብቶ እንደ ቀረ አላውቀውም። ያችን ልዩ ፍጥ ረት አድርጌ የሳልኋትን ጉድ ወያኔን ለመ ጀመርያ ጊዜ ያየኋት በዚያች ሚኒባስ ሃያ ሆንን ወደ አዲስ አበባ እየመጣን ሳለ ሞጆ ን አልፈን ደብረ ዘይት አየር ኀይል ሳንደር ስ በመካከል ካለው ስፍራ ነበር። ልክ ስና ያት ከእኛ የምትለይበትን ነገር ለማወቅ ነ በር የጓጓሁት። ግን ከጠጉራቸው መንጨ ባረር ውጪ የኔው አምሳያዎች ነበሩ። ፊ ታቸው እንደኔው ፊት የማይፈታ ፈገግታ የተለያቸው የዓመታት ጦርነት ያንገላታቸ ው ሰዎች ነበሩ። “ቃል የለም። ሚኒባሷ ከአቅሟ በላይ እስ ቲ መስል ድረስ በሃያ ሰው ታጭቃ ትከንፋ ለች። አዲስ አበባ ጭል ጭል የምትል መ ብራቷን እያበራች በቅርብ ርቀት መታየት ጀመራለች። “ ጓድ መሪ?” አለ አንዱ። ሌላ ኛው ተቀብሎ “ቀጥል ይሰማኛል” ሲል መ ለሰ። የመጀመርየው “አዲስ አበባ መብራ ቷን እያበራች በቅርብ ርቀት ትታያለች” አ ለ። ተቀባዩ ምን ነበር ያለው? ጠፍቶብኛ ል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ግንቦት 23/1983 ዓ.ም እስታዲየም አጠገብ ሃያ ሰ ዎች ከአንዲት ሚኒባስ ተራገፍን። ታክሲ ወደ ቸርችል ጎዳና እንዴት እንደ ያዝኩ አላውቅም። ብቻ ወደ ቀኝ ወደ ግ ራ ገልመጥ ሳልል ተረት ሰፈር ቀበሌ 16 ካ ሉት ቤተሰቦቼ በሰላም መድረሴን ብቻ ነ ው የማውቀው።

እንስቷ “ወያኔ”

ግንቦት 23/1983 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 አካባ ቢ የአንዲት አይሱዙ መኪና ረዳት ሻሻመ ኔ የሚሄድ ሰው እንዳለ ጠየቀን። ጎበዝ ት ንሽም ብትሆን መቅረቡ ይሻላል በሚል አ ሳብ ሦስት ሦስት ብር ከፍለን ወደ ሻሻመ ኔ ተጓዝን። ሻሻመኔ የደረስነው 8፡00 አካ

ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

በ“አምቼዎች”... ከገጽ 7 የዞረ ዛት ይገኛሉ። በተለይ ጁባ እና ናይሮቢ። ናይሮቢን ከሞይ ጎዳና ዳር ቆሞ ለሚመ ለከት በግልጽ በሚታይ ኹኔታ ከተማዋ በሁለት ተከፍላ ትታያለች። ዌስትላንድ (Westland) እና ኢስትላንድ (Eastland) በሚል። ምዕራቡ የከተማዋ ክፍል በአረን ጓዴ የተሸፈነ፣ አልፎ አልፎም ጥቅጥቅ ያ ሉ ደኖች ያሉበት፣ በብዛት ከፍተኛ ገቢ ያ ላቸው የኬንያ ዜጎች፣ ሕንዶች እና የሌሎ ች አገራት ዜጎች የመኖሪያ ሥፍራ እና መ ዝናኛዎች የበዙበት ነው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚኖሩባቸ ው የኬኒያ መንደሮች መካከል አንዱ የኾነ ው “ሐርሊንግሃም” በዚሁ ምዕራባዊ የናይ ሮቢ ክፍል (ዌስትላንድ) ይገኛል። ወደ “ያያ የንግድ ማዕከል” የሚወስደው ን መንገድ ተከትሎ ለሚጓዝ ሁሉ ከዳገቱ ላይ ኾኖ “ሐርሊንግሃም” የሚባለው አካባ ቢ ይቀበለዋል። የአካባቢው ሰላማዊ መኾ ን እና ማራኪነት አቅሙ ያላቸውን ሐበሾ ች የሚስበውን ያህል፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ በ አነስተኛ ዋጋ በጋራ ለመኖር ለቆረጡ የሐ በሻ ስደተኞችም መሰባሰቢያ ስፍራ ነው። ሐርሊንግሃም ለመድኀኒዓለም ቤተክርስቲ ያን ቅርብ ኾኖ መገኘቱም የበለጠ ተመራ ጭ አድርጎታል። ዐይንዎን በአካባቢው በ ማይጠፉት ሐበሾች ላይ ያሳርፉ። ምን አ ልባት ለናይሮቢ አዲስ ከኾኑ ኤርትራዊ፣ ኢትዮጵያዊ ከሚለው መለያ በተጨማሪ ም “አምቼዎችንም” እዚህ ያገኟቸዋል። አ ብዛኞቹ አምቼዎች በሁለቱ ወገኖች መካከ ል የመዋለል ስሜት ይሰማቸው እንጂ ወደ ኤርትራዊነት ማጋደላቸው አልቀረም፡፡ በ ተለይም ግማሽ ኤርትራውያኑ በቂ የሚሉ ትን ምክንያት ያሰቀምጣሉ፡፡ ለአብዛኞቹ ከኢትዮጰያ ወገን ካሉ ዘመዶቻቸው ይል ቅ ከኤርትራ በኩል የሚዛመዱ የመረዳዳት ባህላቸው ጠንካራ መኾን ለዝንባሌያቸው ምክንያት ነው፡፡ በፀጋም ይሄን ሃሳብ ያጠ ናክራል፡፡ “በስመ ኤርትራዊ እርዳታ ብት

ልኩ ከአዲስ አበባው መርካቶ ጋራ ይቀራ ረባል። ይኹንና ኤስሊ የሚንቀሳቀሰውን የ ዶላር መጠን መርካቶ በዓመት ለማንቀሳ ቀስ አቅም ያለው አይመስልም። በዚህ ወ ከባ እና ግርግር በበዛበት ሥፍራ ሐበሾች ም የራሳቸው ድርሻ አቸው። ሁለተኛ፣ ዘ ጠነኛ፣ ዐሥረኛ እና ዐሥራ አንደኛ የሚባ ሉት መንገዶች በብዛት ሐበሾችን የያዙ ክ ፍሎች ናቸው። ሚሚ ሱቅ፣ ቴዲ ሙዚቃ ቤት፣ የባህል መደብር . . የመሳሰሉት የአ ማርኛ ማስታወቂያዎች ጎልተው የሚታዩ ት ግን በተለይ በዘጠነኛ እና በዐሥረኛ መ ንገዶች ነው። በናይሮቢ ጉራንጉሮች ውስጥ የእሱን መ ሰል ታሪክ ያላቸው አሚቼዎች ጉዞ ገታ ያ ድርጉ እና ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁ ባ ይጓዙ። ከናይል ወንዝ አቅራቢያ ከተሠ ራው እና የጁባ ዐይን ከኾነው “ብሪጅ” ሆ ቴል ተነስተው ጉዞዎን ቢያደርጉ እዚህም እዚያም ሐበሾችን ይመለከታሉ። “ኮኞ ኮ ኞ”፣ “ገበል ኩጁ”፣ “ኒው እና ኦልድ ከስተ መስ”..እንዲሁም በመላዋ ጁባ ቢዘዋወሩ እንደልብ የሚያገኙት እነርሱኑ ነው። ጁባ ሮድ በሚገኘው “ኩሽ ሆቴል” ገብተው ዐይ ንዎን ጣል ቢያደርጉ እዚህም እዚያም ሐ በሾች ክብ ሠርተው ሲያወጉ ስልክ ሲደው ሉ፣ ጥሪ ሲቀበሉ ያያሉ።

ጁባ...ደቡብ ሱዳን ጁባ የደቡብ ሱዳን ልብ የኾነች የንግድ ከ ተማ ነች። ወደ ምግብ ቤቶች ጎራ ሲሉ የ ሚያስተናግዱዎትም አዲስ አባባ የሚያው ቋቸው ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ሊኾኑ ይችላሉ። ጁባ ነፍስ የምትዘራው በኤር ትራውያን እና በኢትዮጵያውያን ነው። ከ ከፍተኛ የመንግሥት አማካሪዎች እስከ ሾ ፌር፣ ነጋዴ፣ አስተናጋጅ፣ ወያልነት….ድረ ስ ጁባ ትዘወራለች። አምቼዎች ከኢትዮጵ ያውያን እና ኤርትራውያን መሳ ለመሳ ኾነ ው ሕይወታቸውን ይገፋሉ። ቢኒያም እዚ ህ ይኖራል። ማኅደረ ደግሞ ኬንያ። ብዙ ዎች “አምቼዎች” እንደ ቢኒያም አሊያም እንደ ማኅደረ ዕድለኞች አልነበሩም። ዛሬ በሕይወት ተርፈው ታሪካቸውን ለማውራ ት ዕድሉን አላገኙም።

ማኅደረ- አምቼ ትዝታዎች፤ በናይሮቢ።

ከ10ኛ ብሔረሰብ ወደ አምቼዎች ዓለም? “አምቼ”ዎችን አንዳንዶች “ግራ የተጋቡ” ሲሉ ይገልጿቸዋል። የአዲስ ነገር ዘጋቢዎ ች ይህን ዘገባ ለማጠናቀር በተንቀሳቀሱባ ቸው የምሥራቅ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞ ች ናይሮቢ፤ ካምፓላ፣ ጁባ፤ ካርቱም፣..እ ና ሌሎች ትንንሽ ከተሞች ግን “አምቼ”ዎ ች ያላቸው ማኅበራዊ ፋይዳ አይተዋል። አምቼዎች “ድልድዮች”፣ “ሰላም አስከባሪ ዎች” የሚሉ ስያሜዎች ያገኙትም በማኅ በራዊ መስተጋብር ላይ ባላቸው አበርክቶ ት ነው። “አምቼ”ዎች የኢትዮጵያን እና የ ኤርትራን ሕዝቦች የሚያገናኙ፤ በሁለቱም ውስጥ የሚገኘውን ደካማ እና ጠንካራ ጎ ን የሚረዱ ናቸው። በሁለቱ ሕዝቦች መካ ከል አንዱ ለአንዱ ያለውን አሉታዊ ግም ት ለመፋቅ በአንድ ተመሳሳይ ወቅት ለኤ ርትራም፤ ለኢትዮጵያም ወግነው የሚከራ ከሩ ናቸው። በጁባ፣ ናይሮቢ፣ ካምፓላ፣ በመሳሰሉ የ ምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች በምድር ወገብ ፀሐይዋ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ሐበሾች ወደ ከፈቷቸው ቡና ቤቶች እና ባሮች ጎራ በ ሉ። የአብርሃም አፈወርቂን ሙዚቃ እንደ ሰማችሁ የቴዎድሮስ ካሳሁንን “ኻብ ዳህላ ክን” ወዲያው ልታደምጡ ትችላላችኹ። ሌላም ዘፈን …፤ “አዲስ አበባ ቤቴ” የሚለ ውን ዘፈን ጭምር ሁሉ። እነዚህን ዘፈኖ ች ሲሰሙ ያስከፈቱትን የላጋር ቢራ ቶሎ ቶሎ የሚጎነጩ …ሲጋራቸውንም በላይ በ ላዩ የሚያጨሱ ወጣቶች ልትታዘቡ ትች ላላችሁ። በሙዚቃው ውስጥ ሕይወታቸ ውን እያነበቡ ትላንትን፣ ዛሬን እና ነገን እያ ሰቡ እንደሚኾን አትጠራጠሩ። ብዙዎች “አምቼ”ዎች እንዲህ ዐይነት ሙ ዚቃ ሲያደምጡ በትዝታ እና በቁጭት ወ ደ አዲስ አበባ በሐሳብ መመለሳቸው አይ ቀርም። በአንዳንዶች ሕሊና ከዐሥር ዓመ ት በፊት ያዩዋትን አዲስ አበባ በዐይነ ሕሊ ናቸው ድቅን ትላለች። “አምቼ”ዎች ላደጉ ባት አዲስ አበባ ልዩ ፍቅር እና ግምት አላ ቸው። ከአዲስ አበባ የተነጠሉበት መንገድ

አምቼዎች አንድ ላይ የምንኖርበት ዓለም ቢኖረን እንዴት ደስ ባለኝ

ጠይቀ የሚነፍግህ የለም፡፡ አገር ቤት ብት ሄድ ደግሞ ሰርጉም ሃዘኑም ለብቻህ ስለማ ትወጣው መደጋገፉ የጠነከረ ነው” በናይሮቢ ያለው የስደተኞች የአኗኗር ዘ ይቤም ይሄን የሚያሳይ ነው፡፡ ኤርትራው ያኑ (አምቼዎቹን ጨምሮ) በአንድ ስፍራ አጀብ ብለው መኖርን ይመርጣሉ፡፡ ለአን ዱ በተላከው የድጎማ ገንዘብ የተቸገረ ወ ገናቸውን ጭምር ይረዱበታል፡፡ መጠለያ የሌላቸውን በዙር በየቤታቸው ከማስጠለ ል አንስቶ ወርሃዊ የቤት ኪራይ በመክፈል ጭምር አለኝታነታቸውን ያሳያሉ፡፡

ያያ መድኀኒዓለም- ናይሮቢ የሐርሊንግሃም ጉዳያችንን ከጨረስን “አ ምቼዎች” በስፋት ወደሚኖሩበት ወደ ም ሥራቃዊው ናይሮቢ እናዝግም፤ ከአምቼ ው ማኅደረ ጊላይ ጋራ። የናይሮቢ ምሥራ ቁ ክፍል ከምዕራቡ በተቃራኒው ብዙ ለ ምለም ነገር የማይታይበት፣ ድህነት የደቆ ሳቸው መንደሮች በብዛት የሚገኙበት እን ዲሁም ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካ ሄድባቸውን ሥፍራዎች አካቶ የያዘ ነው። ከ“ኢስሊ” ሌላ “ቻይሮድ” ወደ ሚባለው ሰፈር ቢያቀኑ ብዛት ያለቸውን ሐበሾች ች ምችም ባለው መንደር መካከል ያገኟቸዋ ል። በዚህ ሥፍራ ዳር እና ዳር በአማርኛ የተጻፉ ማስታወቂያዎችን ይመለከታሉ። ከ“ካተሪና ሎጅ” ፊት ለፊት “አሥመራ ሆ ቴል” ጎላ ብሎ ይታያል። ኢትዮጵያውንም በብዛት ቢገኙም የኤርትራውያኑን ያህል አይኾኑም። ብዙኀኑ በምግብ ሥራ፣ በችር ቻሮ እና በመጠጥ ንግድ ራሳቸውን ያስተ ዳድራሉ። አካባቢው ከኪስዋሂሊ እና ከእ ንግሊዝኛ ቋንቋ ይልቅ ትግርኛ እና አማር ኛ ጎልተው የሚነገሩበት ነው። ካሪያኮር እና ፓንጋኒ የሚሉት አካባቢዎ ች በሐበሻ የሚዘወተሩ ቢኾንም የኤስሊን ያህል ግን ሐበሻን አያስተናግዱም። ኤስሊ የሶማልያውያን የበላይነት እየነገሠ የመጣ በት ትልቁ የንግድ ሥፍራ ነው። በብዙ መ

አሳዛኙ ዕጣ አንዳንዶቹ እጅግ ዘግናኝ በሚባለው የባ ድመ ጦርነት ከለብ ለብ ሥልጠና በኋላ እ ንዲሳተፉ ተደርገዋል። የኢትዮጵያ መንግ ሥት ያባረራቸው ብዛት ያላቸው አምቼዎ ች አሥመራ በገቡ በስድስት ወር ጊዜ ወ ስጥ ወደ ሳዋ ወታደራዊ ማሠልጠኛ እን ዲሄዱ ይደረጉ ነበር። የሳዋ ስምንተኛ እና ዘጠነኛ ዙር ሠልጣኞች ብዙዎቹ አምቼዎ ች ናቸው። ሥልጠናውን እንደጨረሱ እ ጅግ ዘግናኝ እና ለሰው ሕይወት ደንታ ባል ነበረው የባደመ ጦርነት ተማገዱ። ብዙዎ ቹም ሕይወታቸውን እና አካላቸውን አጥ ተዋል። አሳዛኙ ዕውነታ ደግሞ “አምቼ”ዎ ች በጦርነቱ ወቅት በሁለቱም ወገኖች የማ ይታመኑ መኾናቸው ሕይወታቸውን የበለ ጠ ያከፋው እንደነበር አዲስ ነገር ዩጋንዳ -ጂንጃ ውስጥ ያነጋገራቸው ለጉዳዩን ቅር በት የነበራቸው ግለሰብ ያስረዳሉ። “ጦር ነቱ ላይ ስለ ተሳተፉት ወጣት ትውልደ ኤ ርትራዊ ዜጎችን (አምቼዎችን) አስብ። በ ተለይ አንዳንዶቹ ወጣቶቹ ኢትዮጵያዊ ነ ን ብለው የሚያስቡ፤ ከአዲስ አባባ ውጭ ሌላ ከተማ ዐይተው የማያውቁ ነበሩ” ይላ ሉ ውስጥ አዋቂው። “በሕይወትህ አስበህ እና ገምተህ በማታውቀው መልኩ ለማታ ውቀው አገር ወታደር ኾነህ ራስህን ብታገ ኘው ምን ይሰማኻል? ከእኛ ወዲያ የአበደ አለ?” ሲሉ በወቅቱ የነበረውን ኹኔታ በጥ ያቄ መልክ ያስቀምጡታል። ማኅደረ ይህን መሰል ታሪኮችን ኖሯቸዋ ል። ተረት የሚመስሉት እውነተኛ የትራጄ ዲ ታሪኮች ቁጥር ስፍር የላቸውም። “ከአ ዲስ አባባ ወጥቶ የማያውቅ የ18 ዓመት ል ጅ ከአባቱ ጋራ ወደ ኤርትራ ተባረረ፤ ለ ምን እንደተባረረም በቅጡ ያልተረዳ ወጣ ት። አሥመራ በገባ በስድስት ወሩ ሳዋ ገባ፤ ባድመ ላይ ሞተ። ለምን ሞተ?…” ማኅደረ ይጠይቃል። አባቱ የልጃቸውን ሞት ከሦስ ት ዓመት በኋላ ሰሙ። ባዶ ሕይወት። የ

ደግሞ አዲስ አበባን በበጎ ብቻ እንዳያስታ ውሷት አድርጓቸዋል። ጁባም ኾነ ናይሮቢ፣ ካምፓላም ኾነ ካር ቱም ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን አ ብረው የሚታደሙባቸው የምሽት ክበቦች አንዳንድ ጊዜ ጸብ አያጣቸውም። በአንድ ዜማ አብረው ሲደንሱ የነበሩት እና ራሳቸ ውን “ሀበሻ “ እያሉ የሚጠሩት ኢትዮጵያ ውያን እና ኤርትራውያን ከአፍታ ቆይታ በ ኋላ ሊጣሉ ይችላሉ-እንደ ድንገት። “በሀበ ሾቹ” መካከል ፀብ ከተነሳ “ሰላም አስከባሪ ዎች” በገላጋይነት ከተፍ ይላሉ። “ጁባ ላይ አምቼዎች ‘ሰላም አስከባሪዎች’ ተብለው ይታወቃሉ” ይላል ቢኒያም። በመላው የምሥራቅ አፍሪካ ከተሞች ተበ ትነው የሚገኙት ከኢትዮጵያውያን እና ከ ኤርትራውያን ስደተኞች ወገኖቻቸው መ ሳ ለመሳ የስደት ኑሮቸውን እየገፉ የሚገ ኙ “አምቼ”ዎች ልክ በመላው ዓለም እንደ ተበተኑ የስያሜ ተጋሪዎቻቸው ሁሉ እርስ በእርስ ባላቸው ትሥሥር ይታወቃሉ። “I Love being Amiche” በተሰኘው የአምቼ ዎች ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አስተያየቱን የሰጠ አ ንድ ወጣት እንዲህ ሲል ምኞቱን አስቀመ ጠ። “አምቼዎች አንድ ላይ የምንኖርበት ዓ ለም ቢኖረን እንዴት ደስ ባለኝ።” ሕልማቸው በእነርሱ ምኞት ብቻ እንደ ማይሳካ ያውቁታል። ሥልጣን ላይ ያሉት የፖለቲካ ቡድኖች ለጥያቄዎቻቸው የሚኾ ን መልስ ይዘዋል። ጉዳዩን ለማየት የሚያ ስችል ፍፁም ፈቃደኝነት ባይታይባቸው ም። ማኅደረ ግን ለማንነት ጥያቄው መፍ ትሄ ያለው ይመስላል። “ከኢትዮጵያዊነት እና ኤርትራዊነት በላይ የጨርቆስ እና የ አባ ሻወል ልጅ መባል ይበልጥብኛል” ይ ላል። ብዙ አምቼዎች በሚገናኙበት የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ሰለሞን ዘርዐይ የሚባል አባ ል ይህችን ግጥም አሰፈረ። ብለነው ብለነው ካልኾነ ነገሩ አምቼና ዶላር የትም ነው አገሩ።


ሀበሻዊ ቃና

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

23

የጎረቤቶች... ከገጽ 19 የዞረ ሊያም በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ ነው። ጥ ቂቶች ብቻ ናቸው ትልልቅ ንግድ ውስጥ የገቡት። በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራ ል የኾኑት ኮሎኔል ነጋሽ ለገሠ ግን ደቡብ ሱዳን እንደ አገር ከቆመች መጪው ዘመን ለኢትዮጵያውያን ብሩህ ነው ባይ ናቸው። “ደቡብ ሱዳን በጦርነት የተጎዳች ናት። ያ ን ያህል ሊጠቀስ የሚችል ኢንዱስትሪም ኾነ መሠረተ ልማት የላትም። የተማረ የሰ ው ሐይል እጥረትም አለ። እኛ በአቅም እ ና ተቋማት ግንባታ ላይ መሳተፍ እንችላለ ን። ወደ ውጭ ለምንልካቸው ምርቶችም ቢኾን እዚህ ሰፊ ገበያ አለ” ይላሉ። ቆንስላ ጄነራሉ ይህን አባባለቸውን በቁ ጥር ያስደግፋሉ። ኢትዮጵያ ከሌሎች አገ ሮች በላቀ ከደቡብ ሱዳን ጋራ ረጅም ድን በር ትጋራለች። የኢትዮጵያ ክልሎች ጋም ቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ እና ደቡብ ሕዝቦች በደ ቡብ ሱዳን ከሚገኙት አፐር ናይል፣ ጆንግ ሌይ፣ ዌስተርን ኢኳቶሪያል እና ብሉ ናይ ል ክልሎች ጋራ ድንበር ይጋራሉ። አሁን በ መሬት ላይ በሚታየው እውነታ ግን ኢት ዮጵያ በዚህ ረጅም ድንበር እምብዛም ተ ጠቃሚ አይደለችም። አብዛኞቹ ኢትዮጵ ያውያን ከድንበሩ ርቅው በከተሞች የተገ ደቡ ናቸው። በሚሠሩት ሥራ ረገድም ቢ ኾን ጥንካሬያቸው ጎልቶ የሚታየው በኤ ክስፐርት ደረጃ በተቀጠሩት ዘንድ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት መን ግሥታት ድርጅቶች እና መንግሥታዊ ባል ኾኑ ድርጅቶች ተቀጥረው ይሠራሉ። አን ዳንዶች ድርጅቶችን ይመራሉ፤ በቁልፍ ቦ ታዎችም ይገኛሉ። ጥቂት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በመንግሥት መሥርያ ቤቶች ውስ ጥ ይሠራሉ። በጣት የሚቆጠሩቱ ደግሞ የ ሚኒስትሮች አማካሪ የመኾን ዕድል አግኝ ተዋል። በአሁኑ ወቅት የደቡብ ሱዳን መ ንግሥት (ጎስ) 31 ሚኒስቴር መሥርያ ቤ ቶች አሉት። የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ኤክስፐርቶች በአገሪቱ ውስጥ መገኘት መንግሥት ያለበ ትን ስር የሰደደ የሰው ሐይል ችግር በመፍ

“ቪቫ ሴል” በጁባ ባሉት ሁለት ቢሮዎቹ እና በመላው አገሪቱ ባሉት መሸጫ ቦታዎቹ ከሌሎች አምስት የሞባይል አገልግሎት አቅራቢዎች ጋራ በመኾን በማገልገል ላይ ይገኛል

ታት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከደቡብ ሱ ዳን ሕዝብ ቆጠራ እና ስታትስቲክስ ማእከ ል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ዕድሜ ው ለሥራ ከደረሰ የአገሪቱ ሕዝብ መካከል 12 በመቶው ብቻ ተከፋይ ሠራተኛ ነው። ደቡብ ሱዳን እንደ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገ ራት ሁሉ ለሥራ ያልደረሱ አዳጊዎች በብዛ ት የሚገኙባት ናት። 8.26 ሚልዮን ከሚገ መተው የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ ግማሽ ያህ ሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። “የቀጠርናቸው ኢትዮጵያውያኖች ኤክ ስፐርቶች ናቸው። የደቡብ ሱዳን መንግ ሥት አማካሪዎች እና ኮንሰልታንቶችም አ ሉ” ይላሉ የሱዳን ሕዝቦች ነጻ አውጪ ጦ ር (ኤስ.ፒ.ኤል.ኤ) ጠቅላይ አዛዥ የኾኑት ጄነራል ጄምስ ሆት ማይ። የኢትዮጵያውያን ኤክስፐርቶች ቁጥር ከ መንግሥት ተቋማት ውጭ በግል ተቋማ ት እየበረከተ መጥቷል። “ቡፋሎ” በተሰኘ ው የአገሬው ባንክ እና የሞባይል ስልክ አገ ልግሎት በሚሰጠው “ቪቫ ሴል” ያሉ ሠራ ተኞችን የተመለከተ ድርጅቶቹ በኢትዮጵ ያውያን ባለቤትነት የተያዙ ሊመስሉት ይ ችላሉ። በደቡብ ሱዳን ውስጥ ካሉ አገር በ ቀል አምስት ባንኮች መካከል አንዱ የኾነ ው “ቡፋሎ” ውስጥ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ

ን ጨምሮ 10 ኢትዮጵያውያን ይሠራሉ። “ቪቫ ሴል” በበኩሉ 30 ኢትዮጵያውያንን ቀጥሮ ያሠራል። በቡፋሎ ባንክ ተቀጥረው ከሚሠሩት መ ካከል አንዱ የኾነው ሙሉጌታ ሰይፉ የዋና ው ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ነው። ወደ ጁባ ከመምጣቱ በፊት በኢትዮጵያ ን ግድ ባንክ ለዐሥር ዓመት ያህል ሠርቷል። ከንግድ ባንክ ቆይታው ከባንክ ክለርክነት አንስቶ እስከ ደንበኞች አገልግሎት ሥራ አ ስኪያጅነት የደረሰው ሙሉጌታ ወደ ጁባ የመጣው በጋዜጣ ላይ የወጣ የሥራ ማስ ታወቂያ ከተመለከተ በኋላ ነው። ከንግድ፣ አቢሲኒያ፣ ንብ፣ ኮንስትራክሽን እና ቢዝነ ስ ባንኮች እንደመጡት የአሁን የሥራ ባል ደረቦቹ ሁሉ ለሥራው ተወዳድሮ ወደ ጁ ባ ለመምጣት ችሏል። እነ ሙሉጌታ እ.ኤ.አ የካቲት 2009 ላይ ጁባ ሲገቡ በዚያች አቧራማ እና ያላደገች ከተማ ረጅም ጊዜ እንደማይቆዩ ነበር የገ መቱት። ከሁለት ዓመት በኋላ ግን ሙለጌ ታ የራሱን “ቢዝነስ” በከተማዋ ስለመክፈ ት የሚያስብ ኾነ። የቡፋሎ ዋና ቅርንጫ ፍ ሥራ አስኪያጅነትን ቦታ ካገኘ በኋላ የ ሚከፈለው ደሞዝ ደግሞ ራሱን የቻለ ማባ በያ ነበር። ሙሉጌታ አሁን የሚያገኘው ደ

ከኳሱ...

ርቱ እና ሌሎችም ወጪዎች መሸፈን አ ለባቸው። በፊት የኑሮውም ኹኔታ እንዳ ሁኑ የጠነከረ አልነበረም። አሁን ኑሮ እየ ተወደደ መጥቷል። ያ ከፍተኛ ተጽዕኖ አ ለው” ይላሉ። አቶ ካሳም በዚህ ይስማማ ሉ። የቡድኑ ገቢ በግለሰቦች መልካም ፈቃ ድ ላይ የተመሠረተ መኾኑ እና ኑሮው እን ደ ጥንቱ የሚያወላዳ አለመኾኑን እንደ ች ግር ያነሳሉ።

ከገጽ 5 የዞረ ዚህ ነው፣ ይኼ ከዚህ ጎሳ መጣ የሚባል ነ ገር የለም” ሲሉ የአቶ ካሣን አስተያየት ያ ጠናክራሉ።

ቀዝቃዛው መንፈስ

የት ይደረሳል? ፎቶ- ካሣ መንግስተአብ

በቡድኑ የሚሳተፉ የተለያዩ አገር ተጫዋ ቾች ቁጥር ይደግ እንጂ አጠቃላይ ቁጥሩ ግን ከድሮው ጋራ ሲነጻጸር ቀንሷል። በአንድ ወቅት 45 የነበረው የተጫዋቾች ብዛት አሁን ወደ 25 አሽቆልቁሏል። ለዚ ህ የሚቀርበው ዋናው ምክንያት የአባላት በየጊዜው ወደ ሌላ አገር የመሄድ ጉዳይ ነ ው። በፍቅር ከቆዩበት ቡድን ወጥተው ወ ደ ሌላ አገር የተሸኙት አባላት ኑሯቸውን ካመቻቹ በኋላ አልፎ አልፎም ቢኾን ኳ ስ እና ትጥቅ ይልካሉ። የገንዘብ ድጋፍም ያደርጋሉ። ብዙ ነገሮች ለማሕበሩ ይልካሉ፡፡ በአብዛ ኛው ወደ ካናዳ፣ አሜሪካ እና አውስትራ ሊያ የተጓዙት አባላት እዚያም ራሳቸውን አደራጅተው መጫወታቸውን ቀጥለዋል። የእነርሱ ከቡድኑ መለየት ጉዳት ቢኾን ም ከዓመታት በፊት የነበረው የጤና ቡድ ን ጥንካሬ እና እንቅስቃሴ አሁን መቀዝቀ ዙን የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች አሉ። ቡ ድኑ ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚዘግቡ ፎቶ ዎችን የያዘው አልበም ለእዚህ ሁነኛ ምስ ክር ነው። ፎቶዎቹ ታሪክ መዝግበዋል። የ ጤና ቡድኑ ወደ ኡጋንዳ ለአህጉራዊ ው ድድር የመጡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (የወንዶች ም፣ የሴቶችም) እና ክለቦችን ተቀብሎ ያስ ተናግድ እንደነበር ያሳያሉ። በአንድ ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ወደ ካምፓላ ብቅ ሲል የጤና ቡድኑ አባላት የክለቡን ማልያ ከዝነኛው “ቪ” አርማው ጋራ አሠርተው ደግፈዋል። በቅርቡ በሞት የተለየው ዝነ ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋ ች መንግሥቱ ወርቁ ለሥራ ጉዳይ ወደ ኡ

ሞዝ አዲስ አበባ ያገኝ ከነበረው ሰባት እጥ ፍ ይልቃል። እንደ እርሱ እምነት ከኾነ አገ ሪቱ ሰላም እንደኾነች ከዘለቀች በደቡብ ሱ ዳን “ቢዝነስ” መሥራት ተስፋ ሰጪ ነው። “አንድ ሰው እንደ ሻይ ቤት ካለ ተራ ንግ ድ እንኳ በቂ ትርፍ የሚያገኝበት አገር ነ ው” ይላል ሙሉጌታ። እርሱ በሚሠራበት ዘርፍም ገና ብዙ ይጠ በቃል። በማደግ ላይ ባለችው ደቡብ ሱዳ ን፤ ከአጠቃላዩ ሕዝብ አንድ በመቶ ብቻ የ ባንክ ሂሳብ ባለቤት በኾነባት አገር፤ የባን ክ ዘርፍ የወደፊት ጉዞ እጅጉን አትራፊ ይ መስላል። ጦርነት ከመፈንዳቱ ከ20 ዓመ ት በፊት በደቡብ ሱዳን አንድ ባንክ ብቻ ነ በር። በጦርነቱ ጊዜ የባንኮች ቁጥር ወደ አ ራት አደገ። የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የአገሬው የአገር በቀል ባንኮች ቁጥር አምስት የደረሰ ሲኾን የኢትዮጵያ ንግድ ባ ንክን ጨምሮ ሦስት የውጭ ባንኮች ዘርፉ ን ተቀላቅለዋል። ቡፋሎ ባንክ በስተመጨረሻ ወደ ዘርፉ ከመጡ ባንኮች አንዱ ነው። በስድስት ደ ቡብ ሱዳናውያን ነጋዴዎች አማካኝነት በ ተከፈለ ስድስት ሚልዮን ዶላር ካፒታል በ እ.ኤ.አ በ2008 የተመሠረተው ቡፋሎ በ አሁኑ ወቅት ሦስት ቅርንጫፎች አሉት።

ፋና ወጊው ቡድን

ጋንዳ በመጣበት ወቅት ተቀብለው አስተ ናግደውታል። የጤና ቡድኑን ለማሳደግ የገቢ ማሰባሰቢ ያ ፕሮግራም አዘጋጅተው ጥሩ ድጋፍ አግ ኝተዋል። ለዚህ ፕሮግራም ድምቀት ሲባ ል የኮሚቴ አባላት በራሳቸው ወጪ የአገ ር ባህል ልብስ እስከማሰፋት ደርሰው ነበ ር። የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ከኪሳቸ ው አውጥተው ናይሮቢ ተጉዘዋል። ዓመ ታዊ በዐላቸውንም በውድድር ያከብሩ ነበ ር። ዛሬ እነዚህ ሁሉ የሉም። ምቾት ያለው የ“ቪላ” ክለብ መለማመጃ በአቧራማው የኪቡሊ የሙስሊም ትምህ ርት ቤት ሜዳ ተተክቷል። አሁን ወደ ውሃ ዳር ወርዶ መዝናናት ታሪክ ኾኗል። ሁለ ት ሺሕ የኡጋንዳ ሽልንግ ብቻ ይጠየቅበት የነበረው መዋጮም እንዲቀር ተደርጓል። አብዛኞቹ መሥራቾችም ወይ ከአገር ወጥ ተዋል አሊያም ከጨዋታ ርቀዋል። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ተካልኝ እና አቶ ደሳለኝ ወደ አሜሪካ እና ካናዳ ተጉዘዋል። በቡድኑ የተከላይ አ

ማካይ ሚና ይዘው ይጫወቱ የነበሩት አ ቶ ካሣ ሜዳ ከገቡ ሦስት ዓመት ተኩል አ ልፏቸዋል። “አሁን 45 ዓመቴ ነው። ከጎረ ምሶቹ ጋራ እኩል አልጋፋም። የኡጋንዳ አ የር ደግሞ ቀላል አይደለም” ይላሉ በቀል ድ መልክ። የዕድሜው ጉዳይ እንዳለ ኾኖ “ታኬታ” የመስቀላቸው ዋና ምክንያት ግን የ“ጤና ጉድለት” እንደኾነ ይገልጻሉ። እንደ እርሳ ቸው ሁሉ መሥራች የነበሩት አቶ ክፍሌ ም ከተጨዋችነት ወደ ተመልካችነት ዞረ ዋል። ሁለቱም ግን ቡድኑን በየሜዳው እ የተገኙ ከማበረታት አልተቆጠቡም። እን ደ ቀድሞው ዘመን አይኹን እንጂ በሥራ አስፈጻሚነት ያላቸውንም ድርሻ ከመወጣ ት አልቦዘኑም። ቡድኑ እንደድሮው ያልኾነበትን አንዱ ም ክንያት የኑሮ ኹኔታ እንደኾነ አቶ ንጉሴ ያ ስረዳሉ። “የአፍሪካ ኑሮ አስቸጋሪ ነው። አብዛኞቹ አባላቶቻችን የዕለት ሩጫቸው ያመዝናል። አብዛኛው ስደተኛ ስለኾነ ኳ ስ ተጫውቶ ደክሞት ምግቡ፣ ትራንስፖ

እንዲህም ኾኖ ጨዋታው ቀጥሏል። ተተ ኪዎችም ማልያቸውን ለብሰው ከቡድኑ ጋ ራ ወደ ሜዳ መውረዳቸውን በደስታ እየተ ገበሩት ነው። አንዳንድ ተሰጥኦ ያላቸው ወ ጣቶችም እግር ኳሱን ከትምህርታቸው እ ና ከስደት ሕይወታቸው ጋራ አጣጥመው ለመሄድ ሲሞክሩ ይታያሉ። እነዚህ ወጣቶ ች መጀመርያቸውም መጨረሻቸውም ጤ ና ቡድን ሊኾን ነው? ወይስ ቡድኑ ወደ ፕ ሮፌሽናል የማደግ ተስፋ አለው? የቡድኑ የ ሥራ ሐላፊዎች ግን ይህ የማይኾንባቸው ምክንቶች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡ “ከእኛ ጋራ የሚጫወቱት ልጆች ዛሬ ይሂ ዱ ነገ አናውቅም” ይላሉ አቶ ካሣ ወደ ሌ ላ አገር ለመሄድ አመልክተው የሚጠባበ ቁ መኾናቸውን በማስታወስ። “ሁለተኛ የ ሚጫወቱት ልጆች ራሳቸው የየዕለት ጉር ሳቸውን ስለሚፈልጉ የልምምድ ሰዓት ሊ ኖራቸው አይችልም።” እነዚህን ወጣቶች መደበኛ ልምምድ አድርጉ ማለት እንደ አ ቶ ካሣ አባባል ጎሮሯቸው ላይ እንደመቆ ም ነው። ማሕበሩ እንደሚያንከባልላት ኳስ መድ ረሻው በቅርብ ያለው የግብ መረብ አይደ ለም፡፡ ሁሉም ካለማንም ግፊት በራሱ የስ ፖርት እና የወገን ፍቅር ያሰባሰበው ነው። ትናንትን እንደኖረ ሁሉ ዛሬንም ተሻግሮ ስ ለ ነገ ማሰብ ይጠብቀዋል። ይኹን እንጂ ለሚመጣው ትውልድ ሐሳቡን፤ አንድነቱ ን እና ፍቅሩን ከኳሷ ጋራ የማስረከብ ራዕ ዩን እንዳነገበ።

ከጥንስሱ ጀምሮ ባንኩ እየተመራ የሚገኘ ው ቀድሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሥራ አስኪያጅነት አገልግለው በነበረው አቶ ዓ ለሙ አበራ አማካኝነት ነው። አቶ ዓለሙ በምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የ ንግድ እና ብሔራዊ ባንኮች ውስጥ ለ30 ዓመታት ያህል የሠሩ ናቸው። አሁን የሚ መሩትን ቡፋሎ ባንክ ደግሞ መደበኛ የባ ንክ አገልግሎት ከኾነው ገንዘብ ማስቀመ ጥ፣ ማውጣት እና ማዘዋወር በተጨማሪ ብድሮች የሚሰጥ እና የንግድ ልውውጦች ን ፋይናንስ የሚያደርግ እንዲኾን አድርገ ውታል። የቡፋሎ ባንክ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የ ኾኑት አንድሪው ማያን አኩአክ ባንኩ ላ ስመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያውያን አ ስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደኾነ ይመሠክራሉ። በተለይም ኢትዮጵያውያኖቹ በዓለም አቀ ፍ ባንኪንግ ዘርፍ ያላቸውን ብቃት ያደን ቃሉ። እንደ እርሳቸው አባባል ከኾነ ኢት ዮጵያውያኖቹ በዓለም አቀፍ ባንኪንግ እ ና “ትሬድ ፋይናሲንግ” ዘርፍ ያላቸው የካ በተ ልምድ በአስመጪ እና ላኪ ንግድ ው ስጥ የነበረው የዘልማድ አሠራር አስቀርቷ ል፡፡ ከዚህ ቀደም አስመጪ እና ላኪ ነጋዴ ዎች “ሌተርስ ኦፍ ክሬዲት” በመጠቀም ፈ ንታ ዕቃ ለመግዛት በርካታ ገንዘብ ተሸክ መው ወደ ዩጋንዳ እና ኬንያ ይሄዱ እንደነ በር መለስ ብለው ያስታውሳሉ። “ኢትዮጵያውያን በሥራቸውም እምነት የማይጎድሉ፣ ታማኝ እና ታታሪ ናቸው” ሲሉ አንድሪው ሠራተኞቻቸውን ያሞካሻ ሉ። “ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለሥራው የሚያስፈልገው በቂ ዕውቀት አላቸው።” ኢትዮጵያውያን የሚደነቁበት በሥራቸ ው ላይ ያላቸው ዕውቀት በቴሌኮሚዩኒኬ ሽን ዘርፉ ይበልጥ የተፈለገ ይመስላል። ለ ዚህም ነው የሊባኖሱ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ድርጅት “ቪቫ ሴል” በርካታ ኢትዮጵያው ያንን ወደ ጁባ በማምጣት በቴክኒክ እና ፋ ይናንስ ክፍል ውስጥ በማሠራት ላይ የሚ ገኘው። በዚህ ድርጅት የኢትዮጵያውያን አሻራ በተለይ ጎልቶ የሚታየው በቴክኒክ ክፍሉ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ከኢንተርኔ ት እስከ ፕሮግራም፣ ከሲስተም አድሚኒ ስትሬሽን እስከ ኔትወርክ ሲስተም ዝርጋታ እና ጥገና ድረስ የማይሠሩት ነገር የለም:፡

ኢትዮጵያውያን በዚህ ድርጅት መሥራት የጀመሩት “ቪቫ ሴል” ሥራውን በደቡብ ሱዳን “ሀ” ብሎ ከጀመረበት እ.ኤ.አ ከየካ ቲት 2009 ጀምሮ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀም ሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዚህ ድርጅት ሲሠሩ የቆዩ ሲኾን የተወሰኑት ለከፍተኛ ት ምህርት ሌሎች ደግሞ ለተሻለ ሥራ ፍለጋ ወደ አውሮፓ እና ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዘ ዋል። በድርጅቱ የሚሠራ እና ስሙ እንዳ ይገለጽ የጠየቀ አንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኞ ች የሚለቁበት ሌላም ምክንያት እንዳለ ያ ስረዳል። “ደምወዙ ያን ያህል ሳቢ አይደ ለም” ይላል። በጁባ ባሉት ሁለት ቢሮዎቹ እና በመላ ው አገሪቱ ባሉት መሸጫ ቦታዎቹ “ቪቫ ሴ ል” ከሌሎች አምስት የሞባይል አገልግሎ ት አቅራቢዎች ጋራ በመኾን በማገልገል ላ ይ ይገኛል። እንደ ባንክ ዘርፍ ሁሉ የቴሌኮ ሚዩኒኬሽን ዘርፍም በደቡብ ሱዳን በአግ ባቡ አላደገም። የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ቆጠ ራ እና ስታትስቲክስ ማእከል ባወጣው መ ረጃ መሠረት በደቡብ ሱዳን 15 በመቶ አ ባ ወራዎቸ (ሀውስ ሆልድ) ብቻ ስልክ አ ላቸው። ይህ ቁጥር በከተማ አካባቢ በሚ ኖሩት ዘንድ ወደ 59 በመቶ ከፍ ይላል። ደቡብ ሱዳን ከታመመችው የጦርነት ሕ መም አገግማ የራሷን ዕድል በራሷ ወደ መ ውሰን በደረሰችበት በዚህ ሰዓት እንደ ዩጋ ንዳ ያሉ የጎረቤት አገሮች የንግድ መስመራ ቸውን በማጠናከር ከእድገቷ ተጋሪ ለመኾ ን አቆብቁበዋል። ኢትዮጵያ እንደ አገር በ ንግድ ትስስር እና በተቋማት ደረጃ ብዙ ገ ፍታ ባትሄድበትም ጥቂት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ግን በራሳቸው ተነሳሽነት ጁባን እያ ሳደጉ ራሳቸውን የመለወጥ ጉዞ ውስጥ ይ ገኛሉ። ብዙዎች የሥራ ዕድልን ለማግኘት እና የተሻለ አማራጭ ፍለጋን እውን ለማድ ረግ የምዕራቡን ዓለም ብዙ ኪሎ ሜትር አ ቋርጠው ያልማሉ፤ በጉርብትናው የእድገ ቱ ጦርነት ተካፋይ እንዲኾኑ ጥሪዋን የም ታስተጋባ የምትመስለው ደቡብ ሱዳን “ከ አፍንጫችሁ ስር ያለሁት እኔም ዕድል መ ስጠትን አውቅበታለሁ” የምትል ትመስላ ለች። ማነው ባለሳምንት?

ተስፋ ...

ብረህ ከመውጣት ውጭ የተሻለ አማራጭ የለህም” ትላለች። ማንም ረዳት ያልነበራ ት ሐረግ ከለላ ለኾናት ኹሉ ጊዜያዊ ሚ ስት በመኾን ስድስቱን ዓመታት አሳልፋለ ች። “የእኔ አይግረምህ፣ ሕጋዊ ባሎቸው እ ንኳን አሜሪካ የሚኖሩ ጓደኞቼ እኔ ባለፍ ኩበት አልፈዋል።” ይህ ዐይነቱ ፈጣን “የትዳር” ዝውውር ግ ን ኹሌ እንደታሰበው ኑሮን በመደጎም ብ ቻ አይጠናቀቅም። በተለይ የትዳር አጋሮ ቻቸው አሜሪካ ወይም ሌላ አገር የሚገኙ ስደተኞች ሌላ ያልተጠበቀ ውጤት በመፍ ጠር ተስፋቸውን ይሠብራል። ወዳጆቻቸ ው ናይሮቢ የሚያደርጉትን በመስማት ቃ ል የገቡትን የአውሮፓ ጉዞ ይሰርዛሉ። ቀ ለበት ያወልቃሉ፤ ትዳርቸውንም ያፈርሳ ሉ። ብዙዎች በጊዜያዊው መፍትሄ ክፍተ ት ዕድሎቻቸውን አበላሽተዋል። ይህ ሁሉ ግን በአብዛኛው የሚኾነው የተገባው የቤ ተዘመድ የዶላር ድጎማ ሲጓደል ወይም ጭ ርሱኑ ሲቋረጥ ነው። . . .

ከገጽ 8 የዞረ ት ያስደፋቸዋል። የያዟት ተስፋ ታጓጓቸዋ ለች፡፡ ያን ተስፋ መጠበቅ ደግሞ የረጂ ወ ገንን እጅ ማየትን ያስከትላል። ዶላርን በተ ስፋ መጠበቅ ለብዙዎች ፈተና ነው። በተ ለይ ዘመድ አዝማድ ለሌላቸው ከሚታሰበ ውም በላይ ከባድ ነው። በስደት ላይ ያለ ሌላ ስደት፤ ሁለተኛ ደረጃ ስደተኝነት የኾ ነባቸው ብዙ ናቸው።

የቢቸግር መፍትሄዎች . . . የሰው እጅ ጥበቃ የሰለቻቸው ብልኀትን ፈጥረዋል። አንዳንዶቹ ብልኀቶች ዛሬ ነፍ ስን ከማዳን ነገን ደግሞ ተስፋ ከማድረግ ብቻ የመነጩ ናቸው። ብዙ የታሰበባቸው የሚመስሉ አይደሉም። ሴቶቹ የምሽት ዳ ንስ ቤቶችን በመጎብኘት የሚመጣውን የ ማታ ሲሳይ ይጠብቃሉ። ጥቂት የማይባሉ ወንዶች ደግሞ በፌስ ቡክ እና መሰል የማ ኅበራዊ ሚዲያዎች አማካይነት አውሮፓ የ ሚገኙ እና ለትዳር እና ለውሲብ የሚጓጉ በ ዕድሜ ገፋ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋ ራ ግንኙነት በመመሥረት ተስፋ ላይ ራሳ ቸውን ይጥላሉ። የዕለት ወጭያቸውን ከ መሸፈን ባሻገር የአውሮፓ ጉዞ ተስፋቸው ን ብሩህ ለማድረግ ያታትራሉ። በአብዛኛውን ጊዜ ጥንድ መኾን በብዙ ዎች የተመረጠ ነው። ጥንዶቹ ፍቅረኛ ወ ይም የትዳር አጋር ከኬንያ ውጭ ሊኖራቸ ው ይችላል። ይህ ግን አብሮ ከመኖር አያ ግዳቸውም። ካልተስማሙ በሳምንት ውስ ጥ በመለያየት ከቅርብ ጓደኛ ጋራ ሌላ ግን ኙነት ቢመሠረት የሚገርም አይደለም። ዋ ናው ኑሮን ማሸነፍ ነው። ለስድስት ዓመታት በናይሮቢ የቆየችው እና ወደ ካናዳ ለመብረር በዝግጅት ላይ ያ ለችው ሐረግ ይኼን መፍትሄ ከተጠቀሙ ት መካከል አንዷ ናት። በአንድ ወር ውስ ጥ ከሁለት ወንዶች ጋራ “ትዳርን” ሞክራ ው ታውቃለች። “ሁሉም በር ሲዘጋብህ ሰ

ይህ ጹሁፍ የተወሰደው ከሳምንታዊው “ፎርቹን” ጋዜጣ ነው

ምርቃና ደጉ አሁን ይህን ሁሉ ባለ ታሪክ ያቀፈቸው የ በሬ ግንባሯ ክፍል መጋል ጀምራለች። ብ ዙኀኑም በቡናው ታጅቦ ወደ ምርቃናው ጥግ እየሄደ ነው። ይኼን ጊዜ ብዙኀኑ ሞ ባይሉን ይጎረጉራል። ፌስቡኩን ይከፍታ ል። የሚጽፋቸውን ቃላቶች ይመርጣል። ጥያቄዎች ከወዲያ ወዲህ ይወናጨፋሉ። “ለዚያች አሮጊት ምን ብዬ ልጻፍላት”፣ “አ ቦ አሁን ምን ኬዝ ፈጥሬ ገንዘብ ልቀበላ ት?” . . . ምርቃና ደጉ ሁሉን ደፋር ያደ ረጋል። ሙሉ ተስፋም ያስታጥቃል። አሁ ን ስለብዙ ጉዳዮች የሚታለምበት፤ ተስፋ የሚደረግበት ነው። ብርሃናማ ነገሮች ብ ቻ ወለል ብለው የሚታዩበት ክፍለ ጊዜ ነ ው። ጎላ ያለ ድምፅ አይሰማም። ሁሉም በ ራሱ ሐሳብ ተውጧል። ቅድምን የሚያስ ታውስ የለም። ነገን ግን በሙሉ ኀይላቸው እየሳሉ ነው፡፡ ዶላር . . . አሜሪካ . . . ካ ናዳ . . . አውስትራሊያ . . . ። ኢትዮጵያ?


ሀበሻዊ ቃና

24

ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2003 ዓ.ም (June 11, 2011)

ሆቴል ሐራምቤ

HOTEL HARAMBE R R R R

ንጹህ እና ምቾት ያላቸው መኝታዎች ከዲ.ኤስ.ቲ.ቪ አገልግሎት ጋር ካፍቴሪያ እጅ የሚያስቆረጥም የኢትዮጵያ ምግብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሰርግ እና ለተለያዩ ድግሶች ብፌ እናዘጋጃለን

Self contained accommodation with DSTV R Bar and restaurant R Delicious Ethiopian food R Cater for weddings and events R

+256 774 883 833, +256 703 944 315 አድራሻ፦ ኡጋንዳ ካምፓላ- ክሎክ ታወር ሾፕ ራይት ሞል አካባቢ- ናቺቩቡ መንገድ ወደ አዊኖ ገበያ መሄጃ

Address:- Nakivubo road, near Shoprite Clock tower Kampala Uganda

Technical Management Solutions Ltd Expert on maintenance and renovations of guest houses, hotels, bars, restaurants, apartments & residential houses

q q q q

General plumbing Carpentry Electrical work Painting

Innovation and Excellence

CALL NOW

+256 777 202833, +256 701 202833 Email: amha2107@yahoo.com


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.