ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
ሐበሻዊቃና አንደኛ ዓመት ቁጥር 004
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ፍቅርተ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር qየባህል ልብሶችና ማንኛውም የባልትና ውጤቶች በጅምላና በችርቻሮ መሸጫ qባህላዊ ምድላው መግብን፤ ክዳውንትን ብጅምላን ብንጽልን መሸጢ ድኳን
ስልክ-0712360631, 0701726165 ቁ 1- ካሳንጋ፣ ካባላጋላ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ ቁ 2 ናኩላቢ፣ ቡኬሳ ጋፕኮ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት
ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ
በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከንግድ ባንክ ብድር እንዲያገኙ ሊደረግ ነው በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና በደቡብ ሱዳን ቅርንጫፍ ከፍቶ የሚ ሰራው መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግ ድ ባንክ በሀገሪቱ ለሚኖሩ ኢትዮጵያው ያን የብድር አገልግሎት መስጠት ሊጀ ምር ነው፡፡ የብድር አልግሎቱን ለመጀመር የታሰ በው ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ተ ወዳዳሪ አንዲሆኑ በማሰብ እንደሆነ የ
ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም መስፍን በተለይ ለሐበሻ ዊ ቃና ገልጸዋል፡፡ “ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባንክ አለ ን ግድ ባንክ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ውስጥ ትንሽ ኮላተራል ካለቻቸው አገራ ቸው ያለውን ኮላተራል ይዞ እዚያ ብድ ር እንዲሰጥ እናመቻቻለን፡፡ ይህንን ብ ድር ተጠቅመው መወዳደር አለባቸው” ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን
ቅርንጫፉን በይፋ የከፈተው እ.ኤ.አ በ መስከረም 2009 ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ የማስቀመጥ፣ የደመወዝ ክፍያ፣ ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶ ች የዋስትና ሰነድ የመስጠት እንደዚሁ ም የዶክመንተሪ ክሬዲት እና ኮሌክሽን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የ70 ዓመት አንጋፋ ድርጅት የሆነው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላው ኢትዮ ጵያ 401 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በደ ቡብ ሱዳን ያለው ከሀገር ውጭ ያለ ብ
ቸኛው ቅርንጫፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ን ግድ ባንክ በደቡብ ሱዳን ያለውን የባን ክ ቁጥሮች አነሳነት በመመልከት ቅርን ጫፍ ከከፈቱ ሶስት የውጭ ሀገር ባንኮ ች አንዱ ነው፡፡ ተቀማጭነታቸውን ደ ቡብ ሱዳን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እ ና ኤርትራውያን የባንኩ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በከፊል ራሷን ስታስተዳደር የቆየችው ደቡብ ሱዳን በ ሐምሌ ወር ሀገር መሆኗን ተከትሎ ኢት
በ ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሐበሻዊ ቃና
ዘጠና ቀናት በጆበርግ ገጽ 12
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኡጋንዳ ተጓዦች የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢንተቤ ወ ደ አዲስ አበባ ለሚበሩ ተጓዦች የዋጋ ማሻሻያ አደረገ፡፡ አየር መንገዱ ከአርብ እና እሁድ በስ ተቀር በቀን ሁለቴ ከኢንተቤ ወደ አዲ ስ አበባ የሚበር ሲሆን የዋጋ ማሻሻያው ን ያደረገው በለሊት ለሚያደርገው በረ
ወደ ገጽ 2 ዞሯል
በተስፋለም ወልደየስ
ወደ ገጽ 2 ዞሯል
በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ
ዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ባለበብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በሀገሪቱ ለማፍሰስ ጥናቶች እያከሄዱ ይገኛሉ፡፡ ይህንን የኢትዮጵያውያንን ባለሀብቶች ፍላጎት ከግምት ውስጥ መ ንግስት ምን እያደረገ እንደሚገኝ የተጠ የቁት አቶ ኃይለማርያም ሀገራቸው ከደ ቡብ ሱዳን ጋር ስምምነት ለመፈራረም በሂደት ላይ እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ “አጠቃላይ የሆነ ስምምነት እያረቀቅ
ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ቪዛ እና ተደራራቢ ቀረጥ ሊያስቀሩ ነው
በኢትዮጵያ የምግብ የዋጋ ግሽበት መጨመሩን ቀጥሏል በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየው የዋጋ ግ ሽበት አሁንም እየጨመረ እንደሚገኝ የ ኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ባስልጣን የሚ ያወጣው ወርሃዊ ሪፖርት አመለከተ፡፡ በሰኔ ወር የተመዘገበው የ45.3 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 47.7 በመ ቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ አጠቃ ላይ የዋጋ ግሽበቱም በሰኔ ወር ከነበረበ ት 38.1 በመቶ ወደ 39.2 በመቶ ከፍ ብ ሏል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤናማ አ ንዲሆን ከተፈለገ አጠቃላይ የዋጋ ግሽ በቱ ከሁለት ዲጂት በታች እንዲሆን ይ ጠበቃል፡፡ “በምግብ ነክ ዝርዝር ውስጥ ከሚካተ ቱት መካከል በሐምሌ ወር ጭማሪ የታ የው በእህል፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና፣ ቃ ሪያ እና በሌሎችም የምግብ ዓይነቶች ነ ው” ሲል ሪፖርቱ ያትታል፡፡ “ምግብ ነ ክ ያልሆኑ አብዛኞቹ ዝርዝሮችም የመ ጨመር አዝማሚያ አሳይተዋል” ይላል፡ ፡ ጭማሪ ካሳዩት ውስጥ የአልባሳት፣ የ
ራ ነው፡፡ የአየር መንገዱ የለሊት በረራ ከለሊቱ 10 ሰዓት ተነስቶ ከንጋቱ 12 ሰዓ ት ገደማ አዲስ አበባ የሚደርስ ነው፡፡ አየር መንገዱ ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ተ ነስቶ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ገደማ አዲስ አበባ የሚገባ የበረራ ጊዜም አለ ው፡፡ ለዚህ በረራ ደንበኞች እንዲከፍሉ የሚጠየቀው ገንዘብ 517 ዶላር ነው፡፡ የ ለሊት በረራ ዋጋውም ተመሳሳይ የነበረ
ሲሆን አሁን ግን በ50 ዶላር እንዲቀንስ መደረጉን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኡ ጋንዳ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እርምጃቸ ው ረጋሳ ለሐበሻዊ ቃና ተናግረዋል፡፡ “በለሊቱ በረራ የሚሄዱትን ተጓዦ ች ቁጥር ለማሳደግ ሲባል የዋጋ ማሻሻ ያ አድርገናል” ይላሉ ወይዘሮ እርምጃ ቸው፡፡ የለሊቱ በረራ ከአንድ ዓመት በፊት የ
1
ተጀመረው ወደ ምዕራብ፣ መካከለኛ ው እና ደቡብ አፍሪካ ለሚጓዙ ደንበኞ ች ታስቦ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡ወደ እ ነዚህ የአፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞ ች ከዚህ ቀደም ለሊቱን በአዲስ አበባ ያ ሳልፉ እንደነበር የተናገሩት ስራ አስኪያ ጇ ይህም ለተጓዦች የማይመች ከመሆ ኑ በተጨማሪ አየር መንገዱን ለተጨማ ሪ ወጪ ይዳርገው ነበር፡፡
በፖለቲካው ረገድ በምስራቅ አፍሪካ ዋ ነኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት ኢትዮ ጵያ እና ኡጋንዳ ተደራራቢ ግብር እና ቪዛ ለማስቀረት መንገድ የሚጠርግ ስ ምምነት ተፈራራሙ፡፡ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት ስምምነ ት “የጋራ የስትራቴጂክ አጋርነት” በሚ ል የሚጠራ ሲሆን ይህም እንደ ኢንቨ ስትመንት፣ መከላከያ እና ጸጥታ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ እርሻ፣ ውሃ እና ኢነርጂ ዘር ፎች ወደፊት ለሚደረጉ ስምምነቶች መ ሰረት የሚጥል ነው፡፡ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የ ኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እና የኡጋንዳ አቻቸው ሳም ኩቴሳ ነበሩ፡፡ ሁለቱ ባለስልጣናት
ወደ ገጽ 2 ዞሯል
በእዚህ ዕትም የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ በፍቃዱ ጅሬኛ ለማ ይባላሉ። የተ ወለዱት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክል ል ውስጥ ነው። በኡጋንዳ የኦሮሞ ማህብረሰብ ሊቀመንበር ናቸው። የኦሮሞ ማህብረሰብ በሚያደርጋ ቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከ“ሐበ ሻዊ ቃና” ጋር ቆይታ አድርገዋል። l
l
l
ህልም አልባው ኤርትራዊ ወጣት ሰሎሞን ከኤርትራውያን ስደተኛ ቤተሰቦቹ ሱዳን ውስጥ ነው የተወ ለደው። ወላጆቹን ግን አያውቃቸ ውም። አባቱ እርሱ ከመወለዱ በ ፊት ነበር የሞተው። እናቱ ደግሞ እርሱን ስትገላገል በወሊድ ምክንያ ት አርፋለች። እርሱን ያሳደጉት ለነ ፍሳቸው ያደሩ እማሆይ ስላስ የሚ ባሉ እናት ናቸው። l
l
l
አዳም ረታ ይናገራል በክረምት ከሰፈሬ እስከ ወመዘክ ር ድረስ በእግር ሄጄ መፅሐፍ የማ ነብበት ጊዜ ነበር፡፡ ዝናቡ ይደብ ራል፣ የሰፈርህ ሜዳ ጭቃ ነው ኳ ስ አታለፋም፣ ተሰላችተሃል፡፡ አን ብበህ ወደ ቤትህ ስትመለስ፣ አእ ምሮህ ውስጥ የሚንሳፈፈው ልብ ወለድና ፋንታሲ ብቻ አይደለም፡ ፡ በካፊያ መበስበስህን ማማረር፣ ማታ ተኝተህ ‘እዛ ድረስ ምን አስ ለፋኝ?’ እያልክ ራስህንም መቀናቀ ንህ ነው፡፡ ልብስህ ቆሽሿል፣ ያለካ ልሲ ያደረግከው ሸራ ጫማ ረጥ ቦ፣ እግሮችህ ጨቅይተው እውስ ጡ ይንሸራተታሉ፡፡ ከዚህ ነው የ ወጣኸው፡፡ l
l
l
ዳር እና ዛንዚባር ልክ እንደአዲስ አበባ ሁሉ ዳሬሰላ ምም ወደ ጎን እየተለጠጠች የመጣ ች ይመስላል። ረዘም ያሉ ህንጻዎ ችን ግን የምታገኙት በከተማይቱ መሃል ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆ ኑ እንደአዲስ አበቤዎቹ እንኳ አይ ረዝሙም። የከተማይቱ መሃል እን ደ ዳርቻዎቹ ሰፊ ቦታ ያካለለ አይ ደለም። ዛንዚባር ማለት የባህር ዳርቻ እና መዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ተረዳ ሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ከተማ በምጓዝበት ጊዜም የተመለከትኩት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር።
2
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
ዜና
ረሃብ ስንት ቀን ይሰጣል? በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ ባለፉት 60 ዓመታት በምስራቅ አ ፍሪካ ከታዩት የከፋ ነው የተባለለት ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ወደ 10 ሚ ሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተጠቂ ሆኗል፡ ፡ ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያመለክ ቱት ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሩብ ያህል የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ችግሩ የገረፋቸው በምስ ራቅ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አካባቢዎች ናቸ ው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ረሀብ ክፉኛ ያ ጠቃው በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘ ው የሶማሌ ክልል ነው፡፡ በደቡብ ም ስራቅ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስ ጥ የሚገኘው የቦረና አካባቢም እንዲ ሁ ጉዳቱ በግልጽ የሚታይበት ነው፡፡ ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢው እንደወ ትሮው ለምለም ቢሆንም ፈረንጆቹ “ግሪን ሀንገር” በሚሉት ረሀብ የሚ ሰቃዩ በርካታ ሰዎች ያሉበት ነው፡፡ አካባቢዎቹን የጎበኙ ጋዜጠኞች በሄ ዱባቸው ቦታዎች ሁሉ በረሃቡ ምክ ንያት ሰዎች እየሞቱ እንደሆነ መረዳ ታቸውን ለሐበሻዊ ቃና ከአዲስ አበ ባ ገልጸዋል፡፡ “ረሃብ አለ፡፡ በመንደ ሮች ውስጥ በርካታ ሰዎች እየሞቱ ነ ው፡፡ በተለይ ህጻናት፡፡ ነገር ግን የሞ ቱ ሰዎች የሚመዘገቡበት የመረጃ ስር ዓት ስለሌለ ምን ያህል እንደሆኑ ማ ወቅ ያስቸግራል” ሲል አንድ ስሙ እ ንዲጠቀስ ያልፈለገ ጋዜጠኛ ተናግሯ ል፡፡ “በሶማሌ ክልል ባሉ ካምፖች ውስጥ ግን የሚሞቱት ስለሚመዘገቡ ቁጥሩ ይታወቃል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረ መረጃ መሰረት በካምፖ ች ውስጥ ከአንድ ሺህ ሰው 10 ሰው
ይሞታል፡፡ ቁጥሩ 13 ከደረሰ በይፋ ጠኔ (ፋሚን) ደረጃ ደርሷል ይባላል” ሲል ጋ ዜጠኛው ያብራራል፡፡ በሶማሌ ክልል ውስጥ ባሉ ካምፖች ውስጥ ያሉ ሰዎች ምንም እንኳ ከሶማ ሊያ የመጡ ስደተኞች ናቸው ቢባልም ጋዜጠኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎችም እንደስደ ተኛ ተመዝግበው እርዳታ እየተቀበሉ ነ ው፡፡ “ኢትዮጵያውያኑ ካምፕ ለመግባ ት ከሶማሊያ ነው የመጣነው ይላሉ” ይ ላል ጋዜጠኛው፡፡ በሶማሌ ክልል ማንነ ት መለየት አዳጋች እንደሆነው ሁሉ በደ ቡብ በኩል ደግሞ በትክክል የተራበው
ኢትዮጵያ እና... ሐምሌ 15 ቀን በካምፓላው ሙኞንኞ ሪዞርት ማዕከል በተደረገው በዚህ የፊ ርማ ስነስርዓት ላይ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውን ሰነድ በ ፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡ “በሁለቱም ሀገራት ተደራራቢ ግብር ለ ማስቀረት የሁለቱ ሀገራት የገንዘብ ሚኒ ስትሮች መስማማት አለባቸው” ይላሉ አቶ ኃይለማርያም፡፡ “ይህ ጠቅላላ ስ ምምነት ተደራራቢ ግብር ለማስቀረት ወደሚደረግ ድርድር ይመራቸዋል፡፡”
ከገጽ 1 የዞረ ተደራራቢ ግብር ማለት በተመሳሳይ የ ገቢ፣ የንብረት እና የገንዘብ ዝውውሮች ላይ በሁለት እና ከዚያ በላይ ሀገሮች የ ሚጣሉ ታክሶችን የሚገልጽ ነው፡፡ “ይህ ስምምነት እንደሚፈረም ተስፋ አ ደርጋለሁ” ሲሉ እምነታቸውን የሚናገ ሩት አቶ ኃይለማርያም “ነገር ግን በጠቅ ላላ ስምምነቱ መሰረት ድርድር መደረግ ይኖርበታል” ይላሉ፡፡ “የጋራ የስትራቴጂክ አጋርነት” ስምምነ ቱ ሁለቱ አገራት ከተደራራቢ ግብር ባ
በደቡብ ሱዳን.... ከገጽ 1 የዞረ ን ነው” ይላሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፡፡ “አ ጠቃላይ ነገር ስለምንሰራ እዚያ ውስጥ ዜጎ ች ከዜጎች ልውውጥ ይኖራል፡፡ ሁለትዮሽ ነው፡፡ እነርሱም እኛ ጋር መስራት እንዲች ሉ፤ የእኛዎቹ ደግሞ የሀገሩን ህግ ጠብቀው የቻሉትን እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት ይደረ
ሐበሻዊ
ፎቶ (ጎን እና ከላይ) ከሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ ባለችው ታዛ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በምግብ ከተጠቁት የከተማዋ እና አካባቢያዋ ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹ እናቶች እና ህጻናት ናቸው (ግራ ታች) በቦረና ድርቅ በርካታ ከብቶችን ገድሏል፡፡
ን ሰው ቁጥር ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ በ ረድኤት ድርጅቶች እና በመንግስት መ ካከል የሚታየው ከፍተኛ የቁጥር ልዩነ ት አሁንም እንዳወዛገበ ነው፡፡ ከሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ ያለችውን ታዛ ከተማ የጎበኘ ሌላ ጋዜጠኛ በአካ ባቢው ላይ የዳሰሳ ጥናት ባደረገው ወ ርልድ ቪዥን እና በመንግስት የወረዳ ኃ ላፊዎች ዘንድ የቁጥር መፋለሶችን አስ ተውሏል፡፡ “ወርልድ ቪዥን 37 ሺህ ነ ው ሲል መንግስት ደግሞ 10 ሺህ ነው ይላል” ሲል ትዝብቱን ለሐበሻዊ ቃና አ ካፍሏል፡፡
ሻገር በኢሚግሬሽን እና ቪዛ ጉዳይ ላይ “ፕሪንሲፕል ኦፍ ሪሲፕሮሲቲ” እንዲጠ ቀሙ የሚያስችላቸው ነው፡፡“ፕሪንሲፕ ል ኦፍ ሪሲፕሮሲቲ” ተግባራዊ የሚደረ ገው ሁለት አገራት የጉዞ ገደቦች እና ቪ ዛ ለማግኘት መሟላት የሚገባቸውን ጉ ዳዮች ለማላላት ውሳኔ ላይ ሲደርሱ ነ ው፡፡ ይህ መርህ ሁለቱ አገራት በወንጀ ል የሚፈልጓቸውን ሰዎች አንዱ ለአንዱ አሳልፎ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡ መ ርሁ ስራ ላይ እንዲውል ግን በሁለቱ አ ገራት የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አማ ካኝነት ስምምነት ተዘጋጅቶ መፈረም ይ ገባዋል፡፡
ጋል” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ካበረከተ ችው አስተዋጽኦ በመነሳት የተለየ የሆነ መ በረታቻ ለዜጎች እንደማይኖርም ገልጸዋል፡ ፡ “እኛ ኢትዮጵያውያን ሳይወዳደሩ የተለየ ነገር እንዲያገኙ አንፈልግም፡፡ ኪራይ ሰብ ሳቢነት ነው የሚሆነው፡፡ ተወዳዳሪ እንዲ ሆኑ ነው የምንፈልገው፡፡ የላቀ ስራ ለመስ ራት ምን ይጎድላቸዋል ብለን እሱን መደገ ፍ ነው የምንመርጠው፡፡ ሳይወዳደሩ ከሌላ
ቃና
በሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ የሚታተም ጋዜጣ
“በዚህ ስምምነት መሰረት ወደፊት በሁ ለቱ ሀገራት ይፈረማል ተብሎ በሚጠበ ቀው የጋራ መግባቢያ ሰነድ በሚፈረም ጊዜ ዝርዝር ድርድሩ ይካሄዳል፡፡ በሁለ ቱ ሀገራት ፓርላማዎችም በስተኋላ ላይ መጽደቅ ይገባዋል” ሲሉ አቶ ኃይለማር ያም ተናግረዋል፡፡ “በሁለቱ ፓርላማዎ ች ከመጽደቁ በፊት ግን ተፈጻሚነት አ ይኖረውም፡፡” ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የዲፕሎማቲክ ግ ንኙነታቸውን የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1970 ዓ.ም ነው፡፡ ሁለቱ አገራት የግንኙነትና ትብብር ስምምነት የተፈራረሙት ኢት ዮጵያ የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን በኡጋንዳ
ው የተለየ ትርፍ አገኛለሁ ማለት አገርን ይ ጎዳል፡፡ ስለዚህ ራሳችን የማናደርገውን ሌላ ው ጋር አድርጉ ብለን አንሄድም” ሲሉ አብ ራርተዋል፡፡ መንግስት ለባለሀብቶች ከሚሰጠው ድጋ ፍ ባሻገር ብዙዎች እንደሚሰጉት ደቡብ ሱ ዳን በቅርቡ ከተለየችው ሰሜን ሱዳን ጋር ግ ጭት ውስጥ ብትገባ ለዜጎቹ ተገቢውን ድጋ ፍ እንደሚያደረግም ይናገራሉ፡፡ “የኢትዮጵያ መንግስት መጀመሪያ ደቡብ
ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ
ከመክፈቷ በፊት ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒ ስትር መለስ ዜናዊ እና የኡጋንዳው ፕ ሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ስምምነቱን እ.ኤ.አ በህዳር 1993 ፈርመዋል፡፡ ከሁ ለት ዓመት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ቆ ንስላ ጽህፈት ቤቷን በኡጋንዳ ከፍታለ ች፡፡ እ.ኤ.አ በ1995 የቆንስላው ጽህፈት ቤት ወደ ኤምባሲ ደረጃ ከፍ ቢልምና የመ ጀመሪያው አምባሳደር ቢሾምም በሁለ ቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የተፈረመው ስምም ነት እስከአሁንም ድረስ ተግባራዊ ሳይ ደረግ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ከረጅም ዓ
ሱዳን ሰላም እንዲሆን ይሰራል፡፡ ደቡብ ሱ ዳን ሰላም አይሆንም የሚል ግምገማ የለን ም፡፡ ግምገማችን ይሄ ቢሆንም ድንገት የሚ ፈጠር ነገር ካለ የመን እና ሊቢያ ላይ እንዳ ደረግነው ሁሉ እንዳደረግነው ሁሉ እናደ ርጋለን” ብለዋል፡፡ በየመን እና ሊቢያ በተ ቀሰቀሱት ግጭቶች ምክንያት የተወሰኑ ኢ ትዮጵያውያን በዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ድጋፍ ወደ ሀገራቸው ተመ ልሰዋል፡፡
የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ዩጋንዳ ካምፓላ ጋባ ሮድ-ካንሳንጋ ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6
ወደ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የተ ጓዘ ሌላ ጋዜጠኛ በበኩሉ በየመንገዱ ከብቶች ሞተው መመልከቱን ተናግ ሯል፡፡ ጋዜጠኛው የተመለከታቸው የቦረና እና ጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች አርብ ቶ አደሮች ሲሆኑ ህይወታቸው የተ ቆራኘው ከከብቶቻቸው ህልውና ጋ ር ነው፡፡ የከብቶችን ወተት ያጡ እ ና በረሃቡ የተጎዱ በርካታ ህጻናት በእ ነዚህ አካባቢ መሞታቸውን ጋዜጠኛ ው ያስረዳል፡፡ የረሃቡ ሁኔታ በኦሞ ሸለቆ ያሉ ኢት ዮጵያውንን ከጎረቤት ሀገር ዜጎች ጋር እንዲጋጩ እና ደም እንዲቃቡ አድ ርጓቸዋል፡፡ የኢትዮጵውያን ሜርሊ (ኝያንጋቶም) ጎሳ አባላት ዓርብ ሐም ሌ 29 ድንበር ተሻግረው ባደረሱት ጥቃት 20 ኬንያውያንን መግደላቸ ውን የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘ ግበዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ወደ 200 የሚጠጋ ከብቶች መዝረፋቸውም ተ ነግሯል፡፡ ድንበርተኞቹ ኢትዮጵያውያን እ ና ኬንያውያን አርብቶ አደሮች ሲሆ ኑ ከብቶቻቸው ከዘራፊ ለመከላከል ጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀ ሱ ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የ ከብት ዘረፋ የተለመደ ቢሆንም አካ ባቢውን ክፉኛ የጎዳው ድርቅ ግን ግ ጭቱን አባብሶታል፡፡ በርካቶች በድ ርቁ ምክንያት የሚበላ ለማግኘት ወ ደ አሳ ማጥመድ ፊታቸውን እንዲያዞ ሩ አስገድዷቸዋል፡፡ የቱርካና (ሮዶል ፍ) ሀይቅን ለመጠቀም የሚደረገው ሽሚያ ደገም የግጭቶች መነሻ እየሆ ኑ ነው፡፡
መታት በኋላ አዲስ ውጭ ጉዳይ ሚኒ ስትር መሾሟን ተከትሎ ግን ሀገሪቱ ከ አፍሪካ ሀገራት ጋር ላላት ግንኙነት ት ኩረት መስጠት ጀምራለች፡፡ ይህ ትኩ ረት በተለይም በምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ጥላ ስር ላሉ የምስራቅ አፍሪካ ላይ ያይላል፡፡ ሀገ ሪቱ ቀድሞ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳ ደር የነበሩትን አቶ ኃይለኪሮስ ገሰሰን በ ሱዳን፣ የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤ ት አፈ ጉባኤ የነበሩትን ደግፌ ቡላን በ ኡጋንዳ መመደቧ በምስራቅ አፍሪካ ጉ ዳዮች ላይ እየጨመረ የመጣውን ፍላጎ ቷን ያሳያል፡፡
በኢትዮጵያ የምግብ...
ከገጽ 1 የዞረ
ቤት ኪራይ፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና ነዳጅ ይገኙበታል፡፡ ሆኖም የምግብ ዋጋ ዝርዝሮችን በሚያሳየው የሪፖርቱ ክፍል የተ መዘገበው ጭማሪ በሰኔ ወር ከተመዘገበው ረገብ ያለ መሆኑን ያሳ ያል፡፡ በመላው ሀገሪቱ የሚታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ባለፈ ው ዓመት ጋር በሐምሌ ወር ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 19.8 በመቶ መ ጨመሩን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ ምግብ ነክ ባልሆኑ ዓይነቶች ላይ የሚታየው የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጋር ሲነጻጸር በ22.6 በመቶ ጭማሪ ያሳያል፡፡
ስልክ +256-778-693669 ፖ.ሳ.ቁ - 28268 ካምፓላ-ኡጋንዳ
ኢሜይል habeshawikana@gmail.com
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
3
ሐበሻዊ ቃና
ዜና
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በካምፓላ n ኢትዮጵያ ውስጥ ቡና ገዝቶ ለመጠጣት የሚፈልግ ሰው በዓለም ዋጋ ገዝቶ ነው የሚጠጣው n ድሮ በአንድ ብር የምንገዛው ሳሙና አሁን 30 ብር ሆኗል n በምንም መንገድ ጤፍ የዛሬ አምስት አመት 200 ብር የነበረበት ቦታ ጋር ሊወርድ አይችልም
n አዲስ አበባ ላይ ሰው የቤት ሰራተኛ ፈልጎ አያገኝም n ሰው ጅቡቲ ሄደን መምጣት አለብን ማለት ነው ወይ እያለ ነው n ሳዑዲ አረቢያ ላይ ያሉ የእኛ ዜጎች ዘመናዊ ባሪያዎች ናቸው n በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ ነው ሬሳ የምንረከበው
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለስራ ጉዳይ ወደ ኡጋንዳ በመጡበት ወቅት ኡጋንዳ ከሚኖሩ እና በኤምባሲ በኩል ግብዣ ከተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን ጋር አጠር ያለ ውይይት አካሄደው ነበር፡፡ መሃል ካምፓላ በሚገኘው ሴሬና ሆቴል ሐምሌ 15 ቀን በተደረገው ውይይት ላይ ከተገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሁለት ሰዎች ለሚኒስትሩ ጥያቄ የማቅረብ ዕድል አግኝተው ነበር፡፡ ሚኒስትሩ ከሰጡት ምላሽ ረዥም ምላሽ የቀነጨብነውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ ስለ ኑሮ ውድነት ትልቁ ጥያቄ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡ በእ ርግጥ የከተማው ኖሮ የተናጋበት ዋናው ምክንያት እንደምታውቁት የዋጋ ንረቱ መጀመሪያ የሚያጠቃው የመንግስት ሰ ራተኛውን እና አነስተኛ ገቢ ያለውን የ ህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ የመግዛት አቅ ሙን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያሽመደም ድ ማለት ነው፡፡ በእኛ ሀገር ያለውን የ ዋጋ ግሽበት ሁኔታው ምንድነው? የሚ ለውን ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ አንዱ የዋ ጋ ግሽበት ዋናው ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዋጋ ነው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ በተ ፈጠረው ችግር ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በ ከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ እኛ ደግሞ ነ ዳጅ አምራች አይደለንም፡፡ ስለዚህ የዋ ጋ ንረት ቢመጣ ስለዚህ ከውጭ የሚመ ጣ ነው፡፡ ሁለተኛው የዓለም የምግብ ዋጋ ከፍ ብ ሏል፡፡ የዓለም የምግብ ዋጋ ወይም ደግ ሞ የግብርና ምርቶች ቡናን ጨምሮ ከ
ፍ ብሏል፡፡ ቡና ዓለም ላይ የሚሸጥበት ዋጋ “ጉድ” ነው፡፡ ስለዚህ ቡና ዓለም ላ ይ የሚሸጥበት ዋጋ ነው ሀገር ውስጥም ሊሆን የሚችለው፡፡ ከዓለም ዋጋው ጋር ተመሳሳይ ነው ማድረግ እንጂ የምንችለ ው እኛ የምንቆጣጠረው አይደለም፡፡ የ ዓለም የቡና ዋጋ ከፍ ካለ እኛ ሀገርም በ ግድ ነው ከፍ የሚለው ማስቆም አንችል ም፡፡ ስለዚህ የቡና ዋጋ በኪሎ ወደ መቶ ብር ገደማ ደርሷል፡፡ ይሄ የዓለም ዋጋ ነ ው፡፡ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ስለዚ ህ ቡና ገዝቶ ለመጠጣት የሚፈልግ ሰው በዓለም ዋጋ ገዝቶ ነው የሚጠጣው ማለ ት ነው፡፡ እራሱ የሚያመርት ካልሆነ በ ስተቀር፡፡ ለዚህ መንግስት ምን አደረገ ነ ው? መንግስት የዓለም ዋጋን መቆጣጠር አይችልም፡፡ ሁሉንም ነገር ከፍብሏል፡፡ ድሮ በአን ድ ብር የምንገዛው ሳሙና አሁን 30 ብ ር ሆኗል፡፡ ሳሙናን መደጎም ከጀመርን ሌላውንም መደጎም ከጀመርን ማቆሚያ
የለውም፡፡ በምንም መንገድ ጤፍ የዛሬ አምስት አ መት 200 ብር የነበረበት ቦታ ጋር ሊወ ርድ አይችልም፡፡ በምንም ተዓምር፡፡ ሊ ሆን የሚችለው አንድ ዋጋ ላይ ከደረሰ በ ኋላ ተረጋግቶ ሳይጨምር እንዲቆይ ማ ድረግ ነው፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ሂደት ውስጥ ህብረ ተሰቡ በተለይ አነስተኛ ገቢ ያለው የህብ ረተሰብ ክፍል፣ የመንግስት እና ተቀጣሪ ሰራተኛው ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ይህንንም መንግስት ይቀበለዋል፡፡
ስደተኞችን በተመለከተ ሀገራችን ውስጥ የስራ ፈጠራ ይህ ለስ ደተኛ፣ ይሄ ለዳያስፖራ፣ ይሄ ለሴት፣ ይ ሄ ለወንድ እያለን መከፋፈል አንችልም፡፡ ሀገራችን ውስጥ በአጠቃላይ ስራ ሊፈጥ ሩ የሚችሉትን መያዝ ያለብን፡፡ አሁን ዳ ያስፖራውን አነሳስታችኋል (እንባላለን)፡ ፡ አገር ውስጥ ያለው ሰው ደግሞ ተቀይ
ሟል፡፡ ለምንድነው የተቀየመው? “ጅቡ ቲ ሄደን መምጣት አለብን ማለት ነው?” እያለ ነው፡፡ “እኛም ጅቡቲ ሄደን ቆይተ ን ከመጣን መሬት በነጻ ትሰጡናላችሁ” ፣ ሌላም ሌላም ይላል ፡፡ “እኔ ፕሮፌሰ ር ሆኜ እዚህ እየፈጋሁ አገር ጥሎ ለሄደ ሰው እያደላችሁ ነው” እያለ አንገታችን ን ነው የያዘው፡፡ “የምታዳሉ ከሆነ ሀገሬ ን ጥዬ መሄድ አለብኝ ማለት ነው” ይላ ል፡፡ እኛ ላሜቦራዎች እነዚያ ዳያስፖራ ዎች ብለው ነው የሰየሙት፡፡ ስለዚህ ማ ቆም ነበረብን፡፡ ከዚህ በኋላ ዳያስፓራውም ሀገር ውስ ጥ ያለውም በውድድር መሆን አለበት፡ ፡ የነጻ ገበያ የሚፈቅደውን ውድድር ተ ወዳድሮ ያሸነፈ ይወሰድ፡፡ እኛ ግን ለው ድድር የሚያስፈልገውን ሪሶርስ ማቅረብ አለብን፡፡ ከዚያ ውጭ ለስደተኛ ስራ ፈ ጠራ ብለን ብንመጣ እዚያ ያለው ስራ አ ጥ መዓት ነው፡፡ ሀገሩ ብቻ ቁጭ ስላለ የ ተሰደደውን እየለቀምን ስራ እየሰጠን እ
ኔ ደግሞ እዚህ ቁጭ ያልኩት ስራ ሳላገ ኝ የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ በርካታ ወጣ ቶች እኮ አሉ ስራ የማያገኙ፡፡ ስላልተሰደ ዱ አይታዩም፡፡ ግን የስደተኞች መብት እና ጥቅም ባሉ በት ሀገር እንዲጠበቅ አቅደን እየሰራን ነ ው፡፡ ለምሳሌ መካከለኛው ምስራቅ አካ ባቢ እነሱ ባሉበት አካባቢ ቆንስላ ከፍተ ን ጥቅሞቻቸውን እና መብቶቻቸውን ለ ማስከበር እየሄድን ነው ያለነው፡፡ የየሀገ ሩ መንግስታት ግን መፍቀድ አለባቸው፡ ፡ ይሄ ዲፕሎማሲ ነው፡፡ አሸንፈን ነው መብታቸውን የምናስከብረው፡፡ ሳዑዲ አረቢያ ላይ ያሉ የእኛ ዜጎች ባ ሪያዎች ናቸው፡፡ ዘመናዊ ባሪያዎች ናቸ ው፡፡ ፓስፖርታቸው ይይዛል፡፡ ከዚያ በ ኋላ በስሙ ስም ነው ኢንቬስት ቢያደር ጉ፣ ገንዘብ ቢያስቀምጡ፣ እንደፈለገ ነው የሚያደርጋቸው፡፡ ዛሬ ከፈለገ ንግዳቸው ን ዘግቶ ይመልሳል፡፡ ይሄ የመንግስታቸ ው ፖሊሲ ነው፡፡ በቅርቡ ሳዑዲ አረቢ ያ ነበርኩ፡፡ ለንጉሱም ጭምር ይሄን አቀ ረቡ፡፡ “እባክዎን ይሄ ነገር ዜጎቻችንን እየ ጎዳ ነው፡፡ እርሶ አሳቢ ነዎት፣ የበላይ ጠ ባቂም ነዎት፡፡ ስለዚህ እባክዎትን ለዜጎ ቻችን ትንሽ ይከፍትላቸው” አልኳቸው፡ ፡ ከዚያ 30 ሺህ እሺ አሉ፡፡ “ከዚህ በፊ ት የመጣውን ትመልሳለህ፡፡ አዲስ የሚ መጣው ግን ህጋዊ በሆነ መንገድ 30 ሺ ህ ይምጣ” አሉ፡፡ ይሄም አንድ መሻሻል ነ ው፡፡ ከዚህ በኋላ በህጋዊ መንገድ 30 ሺ ህ እንልካለን በሀገሩ ተመዝግበው የሚኖ ሩ እንልካለን፡፡ እዚያ ያሉትን መልሰንም ቢሆን እንደምንልክ እናያለን ብለን መል ሱን ይዘን መጣን፡፡ በየሀገሩ ያለው በጣም አግባብ ያልሆነ ፖሊሲ ነው፡፡ ያ ፖሊሲ ደግሞ የየመን ግስታቱ ስለሆነ ምንም ማድረግ አንችል ም፡፡ ዲፕሎማሲ መስራት ካልሆነ በስተ
ቀር፡፡ ስለዚህ ተዘንግቶ ሳይሆን ችግሩ ይ ሄ ነው፡፡ ሁለተኛው በሀገር ቤት ውስጥ መስራት ነው፡፡ ሁላችሁም እንደምታው ቁት እነዚህ ሰዎች የቤት ሰራተኛ ለመሆ ን ነው የሚሄዱት፡፡ አዲስ አበባ ላይ የቤ ት ሰራተኛ የለም፡፡ አዲስ አበባ ላይ የቤ ት ሰራተኛ ዋጋ 700 ወይም 800 ብር ደ ርሷል፡፡ ሰው የቤት ሰራተኛ ፈልጎ አያገኝ ም፡፡ ነገር ግን አረብ አገር ሄዶ እየተሰቃ የ መስራት ይፈልጋል፡፡ ይሄ የአመለካከ ት በሽታ ነው፡፡ አገሩ ተመሳሳይ ስራ አ ለ፡፡ በእርግጥ እኔ ያልገባኝ ነገር ሊኖር ይ ችላል፡፡ እኛ እንደ ህብረተሰብ የቤት ሰ ራተኞችን በጣም የምንጨቁን ከሆነ ማየ ት አለብን፡፡ ካልሆነ የቤት ሰራተኝነት ኢ ትዮጵያ ውስጥ በታጣበት ሁኔታ ይሄ ሁ ሉ ሴት ለምንድነው ለመሰቃየት የሚጎር ፈው ፡፡ አነጋግረናቸው ነበር፡፡ ከቤት ወ ጥተው አያውቁም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግ ን ብዙ ቤት ውስጥ ማታ ትምህርት እየተ ማሩ ነው የቤት ስራ የሚሰሩት፡፡ ይህን ነ ጻነት ትተው ለምንድነው እዚያ መታሰር የፈለጉት? ይሄ የአመለካከት በሽታ ቢሆ ን ነው እንጂ ምን ማለት ነው፡፡ ከከምባታ እና ሀዲያ አካባቢ ወደ ደቡ ብ አፍሪካ የሆነ ዕድል አለ እያለ የሚጎር ፍ አለ፡፡ ከሞት ተርፈህ የምታገኘው ዕድ ል አለ ብሎ ይህን ሁሉ ስቃይ እየበላ እዚ ያ ድረስ የሚያስኬደው ምን ዕድል ቢኖ ር ነው፡፡ በየቀኑ ነው ሬሳ የምንረከበው፡ ፡ እዚያ ያለው ኤምባሲያችን ሬሳ እየጫነ ይለፋል፡፡ ይህ ለምን ይሆናል? በእርግጥ አንዳንድ የተሳካለቸው አሉ፡፡ ሁሉም መ ጥፎ ነው ማለት አይደለም፡፡ ግን እሱም በጣም ከባድ ነው፡፡ በበቂ መጠን የስራ ዕድል ተፈጥሯል ወ ይ? ገና ነው፡፡ ስራ አጥ አሁንም አለ፡፡ በ በቂ ዕድል ገና አልተፈጠረም፡፡ የስራ አ ጡ ቁጥር በጣም ብዙ ነው፡፡
ማስታወቂያ
ሐበሻዊ ቃና በፌስ ቡክ habeshawi kana ብላችሁ ፈልጉን “ላይክ” () የሚለውን ምልክት ተጫኑ
የሐበሻ ምርቶችን ከፈለጉ ይጎብኙን
q የሴትና የወንድ አልባሳትን q ሻርፖችን q የጠረጴዛና የአልጋ ልብሶችን q የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን ሁሉንም በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ ወቅታዊ ዘገባዎች፣ “ሊንኮች”ን እና ፎቶዎች ያገኛሉ ባለፉ የጋዜጣው እትሞች ላይ የወጡ ጽሁፎችን ያገኛሉ
ሜሪ መጥቶ ምን ጠፍቶ! ስልክ 0702003484 አድራሻችን- ካምፓላ ካሳንጋ ሰንሻይን ሆቴል ፊት ለፊት
4
ደብዳቤዎች የሐበሻ ኑሮ በይስሐቅ ክፍሌ ካምፓላ ኡጋንዳ
ሁ
ዳዴ እንደተፈሰከ ነ ው። አንድ ወዳጄ መ ጣና “ሰርግ ጋብዤሃለ ሁ” አለኝ። የግብዣ ው ድንገተኝነት አስገ ርሞኝ በለከፋ ልመል ስለት አሰብሁና “እንዴ? ዘንድሮስ እንዲያው የከ ንፈር ወዳጅ መያዝህን እንኳ ሳታበስር ነው እንዴ ሰርግ የምትጋብዘን” አልኩት። ከት ብሎ ሳቀና ፣ “አረ እባክህ የእኔ አይደለም። እኔ ራሴ መናጢ ስ ደተኛ…አረ ያንድ ወዳጄ ነው…ከአሜሪካ ነው የመ ጡት እዚህ ተጋብተው ሊመለሱ” አለኝ። የእርሱ ን ሚና ሳይነግረኝ በደፈናው ብቻ “ቅዳሜ ተጋብ ዘሃል። ሌላ ፕሮግራም እንዳትይዝ፣ እንደው አደ ራ። ፕሪሚየር ሊግ የለ ባርሴሎና…እባክህ እንዳት ቀር፣ የጥሪ ወረቀቱን ነገ አመጣልሃለሁ” አለኝና ሃ ሳብ ውስጥ ጣለኝ። ቅዳሜ ደግሞ ባርሴሎና ማን ችስተር ዩናይትድን “የሚያሽከረከርበት” ቀን ስለ ነበር ሃሳብ ገባኝ። “ምነው ባልጠፋ ቀን…” ብዬ ገ ና ሳልጨርስ “አይ እንግዲህ…ብቻ እንዳትቀር አ ደራህን” አለኝና ጉዳዩ ለውይይትም ክፍት እንዳ ልሆነ ፈርጠም አድርጎ ነገሮኝ ካጠገቤ እብስ አለ። ሰርጉ ታዋቂ በሆነው የ “ኢትዮጵያ ቪሌጅ ሬስቶ ራንት” ነበር የተዘጋጀው። “የኢትዮጵያ ቪሌጅ (ገ ጠር) ሬስቶራንት” የሚለው ስም ሁሌ ግራ እንዳ ገባኝ ነው። በየትኛው የኢትዮጵያ ገጠር ነው ሬስ ቶራንት ያለው እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ። የገጠ ር ሰው ተከፍሎ ገንዘብ የሚበላበት ቤት ከተማ መኖሩን ያውቃል እንጂ በገጠር ውስጥ ሬስቶራን ት የለም። ለማንኛውም ካምፓላ ውስጥ በቀላል አጠራሩ “ቪሌጅ” የሚባለውን ምግብ ቤት ከአን ጀቴ እወደዋለሁ። የምግብ ቤቱ ባለቤት ማሜ ጥ ራ ግራ ሬስቶራንቱን ካምፓላ ውስጥ አሉ ከሚባ ሉ ቤቶች አንዱ በማድረጓ ሁሌም በልቤ “ጎበዝ” እንዳልኳት ነው። ቪሌጅ በራሱ በጣም ደስ ይላል። የውሰጥ አሰራ ሩ ለዓይን ሳቢ ነው። በዚያ ላይ እግር ኳስ እና ዘ ፈን የሚታይበት ትልቅ ስክሪን አለ። ፕሪሚየር ሊ ግንማ እዚያ ካልተመለከትኩ እግር ኳስ ያየሁም አይመስለኝ። እግር ኳስ ላይ በጣም የሚያሰጋኝ ነ ገር የመብራት መቋረጥ ነው። እግር ኳስ እያየሁ መብራት ከጠፋ ጠቅላላ ስሜቴ አብሮ ቁምጥ ይ ላል። ለዚህ ለዚህ ቪሌጅ አስተማማኝ ነው። እና ም ሰርጉ በምወደው ቪሌጅ መሆኑ ደስ አለኝ። የባርሴሎናን ጨዋታና ያንን ሰርግ ማስታረቅ የ ዚያን ሰሞን ከፍተኛው ፈተናዬ ሆኖ ከረመ። “ም ነው እሁድ ቢያደርጉት” እያልኩ ሳማርር አንድ ሃ ሳብ መጣልኝ። ጥሪው ከምሽቱ 12 ተኩል እንድት ገኙ የሚል ስለሆነ በሰዓቱ ተገኝቼ እስከ ሁለት ሰ
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
የካባላጋላው የሐበሻ ሰርግ ዓት ተኩል ግንባሬን አስመትቼ ከዚያ “ላጥ ብዬ” ጨዋታውን ማየትና ሲያልቅ መመለስ። በርግጥ ም ጥሩ ሃሳብ ነበር። በሰዓቱ ተገኘሁ። ስገባ “ም ነው ለማኝ ሳያራ” የተባለ ይመስል ከአስተናጋጆ ቹ በቀር አንድም ተጋባዥ አልመጣም። “ገና አሁ ን ‘ክራይሲስ’ መጣ” አልኩና በሆዴ እንዳመጣጤ ተመልሼ ውልቅ አልኩ። ወደ ሌላ ቡና ቤት ሄጄ ተሰይምኩ። የቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋ ታ 3 ሰዓት የሚጀመር ቢሆንም ዲ.ኤስ.ቲ.ቪ ገና በግዜ ጀምሮ ስለጨዋታው ማስተዋወቅ ጀምሮ ነ በር። ይህንን እየተመለከትኩ አመሸሁ። አንድ ሰዓ ት ተኩል ግድም ሲሆን “አሁንስ እንኳን ተጋባዦ ቹ ሙሽሮቹም ይመጣሉ” ብዬ ወደ ቪሌጅ የሚያ ስኬደውን የካባላጋላ ዳገት ተያያዝኩት። እንዳሰብኩትም ግቢው ግጥም ብሎ መቀመጫ እንኳ አልነበረም። በስተኋላ ላይ አንድ ጠረጴዛ ከ በው ከተቀመጡ ሰዎች ዘንድ አንድ ያልተያዘች ወ ንበር አየሁና ወደዚያው ሄድኩ። “ሰው አለው?” ብዬ ጠይቅኩ። “አረ ይቀመጡ” ተብዬ ቁጭ አል ኩ። የሙሽሮቹ ሰገነት በ“አብዷል ግላሱ” ተንቆጥ ቁጦ በእርግጥም ዙፋን መስሏል። አሁን መሽሮቹ ን መጠበቅ ያዝን። ጠረጴዛው ላይ የተደረደሩት መጠጦች ሙሽሮቹ እስኪመጡ ላይነኩ “ተኮንነ ው” ግን ተሸልመው ተቀምጠዋል። ሙሽሮቹን በ ናፍቆት ስንጠብቅ ጊዜው ገፋ። አብረውኝ የተቀ መጡ በዕድሜ የገፉ ሰው እንደቀልድም፣ እንደቁ ጭትም አድርገው “ምነው አንዳንድ እንኳ ቢፈቅ ዱልን?” አሉ የተኮለኮሉትን ቢራዎች እያዩ። ዓይ ናችን ስር በረድፍ የቆሙትን ቢራዎች ዓይን ዓይ ናቸውን እናያለን። ባንድ ወገን የካምፓላ ሙቀት የፈጠረው ጥማት በሌላው ደግሞ የቢራው አም ሮቱ ይዞ እየወዘወዘን የተከፈተልንን የአማርኛ ዘፈ ን እንኳ በቅጡ ማድመጥ አልቻልንም። ሰዓቴ ሁለት ሰዓት ተኩል መሆኑን ያሳያል። በእ ቅዴ መሰረት ግንባሬን አሳይቼ እሰወራለሁ ያልኩ በት ነበር። ሆኖም ልክ በዚያው ሰዓት ሁለት ነጫ ጭ መኪኖች ሙሽሮቹንና ሚዜዎችን ይዘው ከግ ቢው ሲገቡ ቪሌጅ ያኔ በአሸባሪዎች ፍንዳታ የተ ናጋቸውን ያህል በሆታ ተነቃነቀች። “ክቡራን እድ ምተኞች ሙሽሮችን ለመቀበል እንነሳ፤ በጭብጨ ባ” ብሎ አስተናጋጁ አወጀና ሁላችንም ተነስተን ማጨብጨብ ጀመርን። እኔ ዓይኔ ያለው እነዚያ የ ሚደፍራቸው የጠፉ የመሰሉ ቢራዎች ላይ ነው። ዓይኔን ከቢራው ልንቀልህም ብለው “በፖሊስ እ ንጂ” የሚል ይመስል ይበልጥኑ ትክ ብሎ ቀረ። “ሙሽራዬ” የሚለው ዘፈን እስከመጨረሻው የድ ምጽ ገደብ ድረስ ተለቀቀና ካባላጋላ ብቻ ሳይሆን ሙየንጋና ካንሳንጋም የታመሰ መሰለ። ሙሽሮቹ ጽዋቸውን አንስተው ሲጎነጩ ያ ሁሉ ታዳሚ “አሁን ተፈቅዶልሃል” የተባለ ይመስል ቢ ራውንና ለስላሳውን እያስከፈተ “ምነው’ቴ” በመ ሰለ “ቁጭት” ያንን በድርቅ የተንቃቃ ጉሮሮውን
ያርስ ጀመር። ቢራዎች መከፈት ሲጀምሩ የአስተ ናጋጅ መንጋ ይራወጥ ገባ። ጸጥ ብሎ የነበረው ቤ ት በቅጽበት ተለውጦ ግርግሩ ሌላ ሆነ። ወዲያ ው ዘፈን እየተከታተለ ተለቀቀ እና ሞቅ ሞቅ አ ለ። አስተናጋጆቹ ይራወጣሉ። “እኔ ቢራ አልጠ ጣም ለስላሳ” ለሚሉት ፍላጎታቸውን ለማርካት ጥድፊያ ሆነ። አንድ ሁለት ቢራ እንደተጎነጨን “ራት አንሱ” ተባለ። የጸምና የፍስክ ለየብቻው ተ ደርድሯል። ምግብ በየዓይነቱ ጠረጴዛ ሞልቶ ተ ትረፍርፏል። ራት ተበልቶ እንዳለቀ፣ ሳህን ማንሳቱ ራሱን የቻ ለ ግርግር ሆነ። ከዚያ በኋላማ የአማርኛ ዘፈን በየ ዓይነቱ እየተዘፈነ ገሚሱ በቴፕ፣ ገሚሱ በዲቪዲ ሆኖ “ይኼማ ያለ ዳንኪራ እንዴት ይሆናል?” የተ ባለ ይመስል ታዳሚው ሁሉ እየተነሳ እስክስታው ን ያስነካው ገባ። አንድ ጠረጴዛ የተዳበልኳቸው ወይዛዝርት ቢራውን፣ እስክስታውንም አልነኩት ም። ብቻ! ለስላሳውና የግል ወሬዎቻቸውን ይኮ መኮማሉ። “እንዴት አይነሽጣቸውም?” እያልኩ እገረምና መልሼ ደግሞ “ምናልባት ሃይማኖታቸ ው አይፈቅድላቸው ይሆናል” እላለሁ። ከእኔ ጋር ወሬም አላወሩ። አረ! ዞር ብለውም አላዩኝም። ከ ፊታችን ባለው ጠረጴዛ ዙሪያ ያሉት ኤርትራውያ ን (አምቼዎቹ) ደግሞ አንድ ዘፈን እንዲያመልጣ ቸው የሚፈልጉ አይመስሉም። እየተነሱ እስክስታ ውን ያቀልጡታል። ኤርትራውያን በአማርኛ ዘፈ ን ሲጨፍሩ ማየቱ ደስ ብሎኝ እነርሱን ስመለከ ት ከመካከላቸው አንዷን ሌላ ቦታ እንዳየኋት ት ዝ አለኝ። ከቆንጅናዋ ባሻገር የታወሰኝ እረፍት የ ለሽ ልጇ ነበር። ያየሁትን ሁሉ ካልነካሁ የሚለውን የአራት ወይ ም የአምስት ልጇን ዛሬም እገባበት እየገባች ጎትታ ታመጣዋለች። ደቂቃ ሳይቆይ መልሶ ይጠፋል። ልጇን መጠበቁን እና እስክስታውን አብራ ማስኬ ዷ አስገረመኝ። ለልጇ ያላትን ትዕግስት ደግሞ አ ደነቅሁ። ዛሬም እንደበቀደሙ ከገባበት ስታመጣ ው አቅፋ እያጫወተቸውና እየተሳሳቁ ነበር። ይ ኼኔ እኔ በልጅነቴ ቢሆን ኖሮ በደርግ “የዲሲፕሊ ን መቀስ ፊት” የነበረችው እናቴ መጀመሪያ የምታ ደርገው ለመግረፊያ የሚሆን ሳማ ፍለጋ መሄድ እ ንደነበር አስታውሼ የልጁን እና የእኔን አስተዳደግ ማነጻጸር ጀመርኩ። በልጆች አያያዝ ላይ በትውል ዶች መካከል ያለውን ልዩነት እያሰብኩ ስቆዝም ድንገት ልጇ ከየት መጣ ሳይባል ከእኔ ጋር ሆነ። እንደፈረደባት ልጇ ሰው እንዳያስቸግር ብላ ልት ወስደው ወደ እኔ መጣች። ለካ እኔ ብኣ አይደለም ያስታውስኳት። እርሷም አውቃኝ ኖሮ ፈገግ አለ ች። “እንዴት ነሽ?” አልኳት። በጣም ቀልጠፍ ባ ለ አማርኛ “እግዚያብሔር ይመስገን” ስትለኝ ነው አምቼ መሆኗን ያወቅሁት። የአማርኛው ዘፈን አሁንም ይደለቃል። ዲጄው “የአማርኛ ብቻ” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ የተሰጠው
ይመስል የሌላ ብሔር ዘፈን አያጫውትም። በድ ርጊቱ ተገርሜም፣ አፍሬም ነበር። በዲጄው የዘፈ ን አመራረጥ ምክንያት ይመስላል ተነስተው የሚ ጨፍሩትም ሰዎች አንድ ዓይነት ነበሩ። ወደ መ ጨረሻ ገደማ ግን ማን እንደነገረው ባላውቅም የ ትግርኛ፣ የኦሮምኛ፣ ጉራጊኛ እና ወላይትኛ ዘፈኖ ችን አጫወተና ሰርጉ እንደገና እንደአዲስ ተደበላ ለቀ። ይበልጥ ሞቅ አለ። ራቅ ብሎ ከሚስቱ ጋር ምሽቱን ሲቆዝም የነበረ አንድ የማውቀው ሰው ኦ ሮምኛ ሲዘፈን ደስ ብሎት ከሚስቱ ጋር ተነስተው ጨፈሩ። ትግርኛውም ሲመጣ ትግርኛ ተነጋሪ መ ቀመጫው ላይ አልነበረም። “ያምቡሌ” የሚለው ዘፈን በዲጄ ሲለቀቅ ደግሞ ቪሌጅ የተገለጠ መ ሰለ፡፡ ከዚያ በኋላ ያ ሰርግ እጅግ አስደሳች ሆነ፡ ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተለያዩ ብሔሮችን፣ ኤርትራ ንም ጭምር በስም እየጠራ “የ…ልጅ የለውም አባ ይ” ሲል ያልተደሰተ አልነበረም፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ግን በዚያ ሁሉ የደስታ ሆታ መካከል አንደኛው አስተናጋጅ አንደኛውን ካልገ ደልኩ ብሎ መነሳቱ ነበር፡፡ ረብሻው እኛ የተቀመ ጥንበት አካባቢ ስለነበር ሳያሳዝነን አልቀረም፡፡ ካ ልገደልኩ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ባለ ቁጥር አንዴ የ ቪሌጅ ባለቤት ማሜ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎች በ የተራ እየመጡ ቢለምኑት ሰውየው ባሰበት፡፡ ሌላ ኛው ደግሞ ሳይናገር ሳይጋገር፣ መልስም ሳይሰጥ ስራውን ብቻ ይሰራል፡፡ ይህንን እንደፍርሃት የወ ሰደው ጠበኛ ያዙኝ፣ ልቀቁኝ ማለቱን አላቆም አ ለ፡፡ አሁን ያ ትዕግስተኛው ትዕግስቱ አልቆ ኖሮ እ መር ብሎ ተነሳ፡፡ ጠበኛው በዚህ ጊዜ ድንፋታው ሁለት መልክ ያዘ፡፡ ገላጋይ ሲኖር መደንፋት፣ ገላ ጋይ ሳይኖር ረጋ ማለት፡፡ በደነፋ ቁጥር “እባክህ” ያላለው አልነበረም። አጅሬ እባክህ በተባለ ቁጥ ር እየባሰበት ያንን ቆንጆ ሰርግ ሊያበላሸው ሆነ። “አለጠብ የምናውቀው ነገር ይጥፋ? ምነው ዛሬ እንኳ ቢታገስ?” አለች እኔ ካለሁበት ጠረጴዛ ዙሪ ያ ከተቀመጡት አንደኛዋ። “ኤጭ…ኤዲያ!” አለ ች ደገመችና። ይኼ ሁሉ ሰው “ሃይ” ብሎት፣ በር ካታ ሰው አዝኖበት፣ ይረጋጋል ይተዋል ሲባል ድ ንገት ደግሞ “ግንፍል አለብኝ” ዓይነት ተነስቶ “ና ውጣ!” ይለው ጀመር። ‘አይ እንግዲህ አሁንስ አ በዛው። ይህንን ኩታራ በጥፊ የሚለው ከጠፋ የ ቀረው ምርጫ ያው ባላንጣው አንፈራፍሮ እንዲ ለቀው ማድረግ ነው” አልኩና፣ ‘በል የእኔ ወንድ ም….መደባደብ አይደል የምትፈልገው? አንግዲያ ው ይኼ ሰርግ ነው። ሰው ሊደሰት ነው የመጣ ው። ከሰውየው ጋር ወደ ውጭ ውጡ። ውጭ ያ ለው መንገድ የሰጠ ነው። እዚያ ይለይላችሁ’ ልለ ው እንደወሰንኩ አንድ ሰው ጠጋ ብሎ በጆሮው የ ሆነ ነገር ሹክ አለው። ተናጋሪው ምን እንዳለው ባ ይታወቅም ለጠብ ይጋበዝ የነበረው በቅጽበት አ ደብ ገዝቶ ቁጭ አለ። እኛም ትኩረታችንን ወደ ጭፈራው መለስን።
ማስታወቂያ
q
አስተያየት
q
ጸሁፍ
በሐበሻዊ ቃና ፖስታ አድራሻ ፖ.ሳ.ቁ 28268 ካምፓላ-ኡጋንዳ በኩል ያድርሱን፡፡
q
ጥቆማ…
ምስጋና በጆኒ ሉሉ ካምፓላ ኡጋንዳ ጆኒ ሉሉ የተባልኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡ ፡ በጁላይ 11 ካምፓላ ላይ በተከሰተው ድንገተኛ የቦምብ አደጋ ጉዳተኛ የሆን ኩ ነኝ፡፡ የዚህ ጋዜጣ ያለፈው ዕትም ላ ይ የእኔ ታሪክ ታትሞ ወጥቷል፡፡ ከአዘ ጋጁ ጋር ለመገናኘት ጊዜ ስላልነበር በ አደጋው ጊዜ የረዱኝን ሰዎች የማመስገ ን ዕድል አላገኘሁም፡፡ አሁን ዕድሉ ተ ሰጥቶኛልና ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ለመላው የካምፓላ ነዋሪ ምስጋና የማ ቀርበው ሁሉንም ጉዳተኞች ወክዬ ነ ው፡፡ ሐበሻ በሙሉ ሁሉንም ጉዳተኞ ች በገንዘብ በመደገፍ፣ ሆስፒታል ድረ ስ ተገኝተው በማጽናናት እና ያለመሰል ቸት ሲንከባከቡ ስላየሁ በሁሉም ስም ለማመስገን ነው፡፡ ክስተቱ ምንም እን ኳ የሚያስደነግጥ ቢሆንም ወገናችን እ ንደዚህ ለሰው አዛኝ እና ሩህሩህ መሆ ኑን ማየቴ በጣም በወገኔ እንድኮራ አ ድርጎኛል፡፡ አንዳንዶች ልክ የስጋ ዘመ ድ የታመመባቸው እስኪመስል ድረስ ውለው አድረው ተንከባክበውናል፡፡ በእኔ በኩል በእውነቱ ሰዎችን ለማመ ስገን ቃላት አይኖረኝም፡፡ በሆስፒታል ሆኜ፣ ከሆስፒታል ከወጣሁም በኋላ በ ብዙ ነገር ሲረዱኝ የነበሩ ሰዎች በርካ ታ ናቸው፡፡ መቼም ብዙ ስለሆኑ ስም ለመዘርዘር ይከብዳል፡፡ ግን ያደረጉል ኝን እግዚያብሔር እና እነሱ ያውቃሉ፡ ፡ ለእነዚህ ሰዎች ማለት የምችለው በእ ውነቱ ብድርን የሚከፍል እግዚያብሔ ር ነውና እርሱ ጤናችሁን፣ ቤተሰባች ሁን፣ ስራችሁን፣ ሰላማችሁን ፍቅራች ሁን አብዝቶ አብዝቶ ይባርክ፡፡ ህይወ ታችሁ ሰላምና ደስታ የተሞላው እንዲ ሆን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ በመጨረሻ ግን በግሌ ማመስገን የም ፈለገው እንድ ሰው አለኝ፡፡ በአደጋው ሆስፒታል ገብቼ አራት ቀን ሙሉ ሁ ለት ዶክተሮች እየተፈራረቁ ቢያዩኝም ችግሬን ሊያውቁት አልቻሉም ነበር፡፡ በስተኋላ ላይ ከሌላ ዶክተር እንደሰማ ሁት አራተኛውን ቀን ያለ ህክምና አል ፌ ቢሆን ኖሮ ሟች እንደነበርኩ ነው፡፡ ከዚህ የተረፍኩት እግዚያብሔር በላከ ልኝ ትልቅ ሰው ነው፡፡ አቶ ግዛው ይባ ላል፡፡ የኢትዮጵያ ቪሌጅ ባለቤት የሆ ነችው የማሜ የልጆች አባት ነው፡፡ እ ውነት ለመናገር ይህንን ሰው ባለኝ ቀሪ የህይወት ዘመኔ በሙሉ ልረሳው አልች ልም፡፡ ምክንያቱም ዶክተሮች እየተሰ ቃየሁ እያዩ ደህና ነህ ውጣ ባሉኝ ጊዜ እርሱ ግን በፍጹም አይወጣም ብሎ ህ ይወቴን ያተረፈውን ህክምና እንዳገኝ አስደርጎኛል፡፡ አቶ ግዛው በዚያን ጊዜ በቀላሉ የማይ ገኘውን የካምፓላ ኢንተርናሽናል ሆስ ፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርን ካለበት ፈልጎ አምጥቶ፣ ችግሬን አስረዳልኝ፡፡ የ ጉዳዩን አሳሳቢነት የተመለከተው ዶክ ተር ሞሰስ የተባለው ሚዲካል ዳይሬክ ተር አራት ሰዓት ከ30 ደቂቃ የፈጀ ቀ ዶ ህክምና አድርጎልኝ በድጋሚ ለመኖ ር በቅቻለሁ፡፡ ለዶክተር ሞሰስ በዚህ አጋጣሚ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለ ሁ፡፡ ለአቶ ግዛው ደግሞ አንተን፣ ቤተ ሰብህን እና ልጆችህን እግዚያብሔር ይ ባርክ፡፡ ረጅም እድሜ እመኝልሃለሁ፡፡ እንዲሁም አቶ ማስረሻ በራሱ አነሳሽነ ት በውጭ ሀገር ከሚገኙ ወገኖች ጋር ተገናኝቶ ገንዘብ አሰባስቦ እንድንረዳ እ ድርጎናልና እርሱንም ከልቤ አመሰግና ለሁ፡፡ ቤተሰቤን፣ ባለቤቴን እና ጓደኞ ቼንም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
5
ሐበሻ በምስራቅ አፍሪካ
የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ
በ
ፍቃዱ ጅሬኛ ለማ ይባላሉ። የተወለዱት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ነው። በ1978 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በውጭ ቋንቋዎች እና ስነ ስሁፍ አግኝተዋል። በመንግስት እርሻዎች ልማት ሚኒስቴር በህዝብ ግንኙነት ክፍል የህትመት ውጤቶች አርታኢ ሆነው ሰርተዋል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ውስጥ የህዝብ ግንኙነት እና ስልጠና መምሪያ ተጠባበቂ ኃላፊም ነበሩ። “በመንግስት አድሏዊ አሰራር” ከዚህ ስራ መሰናበታቸውን የሚናገሩት አቶ በፍቃዱ አዳማ (ናዝሬት) በሚገኘው ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ውስጥ ሌክቸረር ሆነው ማገልገል ጀምረው ነበር። ሆኖም ደረሰብኝ በሚሉት እስራት ምክንያት በመስከረም 1999 ዓ.ም አገር ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ያስረዳሉ። ወደ ኡጋንዳ ከመጡ በኋላ ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ጋር በትብብር በሚሰራው ኢንተር ኤይድ ውስጥ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አስተርጓሚነት ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም ባሻገር በኡጋንዳ የኦሮሞ ማህብረሰብ ሊቀመንበር ናቸው። የኦሮሞ ማህብረሰብ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከ“ሐበሻዊ ቃና” ጋር ቆይታ አድርገዋል። ጤማ ሁሉ ይያዛል። እግዚያብሔርን በፈጠረው ነገር እናመሰግናዋለን የ ሚል ሀሳብ እንዳለው ነው የማውቀ ው። ይህንን የሚያሟላ ቦታ ካምፓላ ላይ አግኝታችኋል? ከካምፓላ ዳርቻ ላይ ሉቢሪ የሚባል ሐይቅ አ ለ። መንግስት እናስፈቅዳለን። ሐይቁ አካባቢ እና ከብራለን። በኦሮሞ ባህል ለእግዚያብሔር ምስጋ ና የሚቀርበው በሶስት ቦታ ነው። አንድ-እርጥበት ባለበት፣ ሁለት-ከመሬት ከፍ ባለ ቦታ እንደ ተራ ራ፣ ሶስት-ጥላ ባለበት ነው። እሬቻ ደግሞ የምና ከብረው በአገራችን ክረምት አልቆ መስከረም ሲ መጣ በ17 መስቀል ሲሆን በሳምንቱ በ24 ነው። እሬቻ የሚከበረው ያ ክረምት፣ ያ ጭቃ፣ ያ ጨለ ማ ማለፉን ለማመስገን ነው። በዓሉ የሚከበረው ወደ ብርሃን ስትወጣ ነው። በክረምት የእርሻ ጊዜ ምርት ለማግኘት ዘርተህ ቡቃያው በደንብ ሲወ ጣ ማለት ነው። እሬቻ ሲከበር ቡቃዮች አድገው ያፏጫሉ። የጤፍ ዘለላ አይተህ እንደሆነ በዚያ ን ጊዜ በንፋስ ያፏጫል። ሳሮችም በንፋስ ያፏጫ ሉ። የአበባ ወቅት ነው። ያን ጊዜ ለእግዚያብሔር ምስጋና ለማቅረብ ነው የምናከብረው። ውሃ ዳር የምናከብረው እርጥብ አካባቢ ስለሆነ እና እግዚ ያብሔር የፈጠረው ስለሆነ ነው። በእዚያ ቦታ እ ግዚያብሔርን ነው የምንለምነው። የኢትዮጵያ ማህብረሰብ እያለ የኦሮ ሞ ማህብረሰብ ለብቻው ወጥቶ የራ ሱን ማህበር ለምን ማቋቋም አስፈለ ገው? የኢትዮጵያ ማህብረሰብ አብዛ ኛው አባላትም በተለያዩ ምክንያት ከ ሀገራቸው የወጡ ስደተኞች ነው። ሁለቱም ማህበረሰቦች ይዘው የተነሱ ትም አላማ ተመሳሳይ ነው።
እኛ በኢትዮጵያ ማህብረሰብ ውስጥ ገብተን አ ልወጣንም። መጀመሪያውኑ ድሮም ይኖር ይሆና ል። እኛ ግን እዚህ የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ነው ያቋቋ ምነው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ማቋቋም ያስፈለገበት ምክንያት ሰዎች ችግራቸውንም ሆነ ደስታቸውን ሲገልጹ የሚመሳሰላቸውን ፈልገው ነው። ስለም ንመሳሰል፣ አንድ ዓይነት ሰዎች ስለሆንን፣ ለዚያ ስንል ተፈላለገን በማህበር ተቋቋምን። በኢትዮጵ ያ ውስጥ ብዙ ህዝቦች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የ ተለያየ ዓይነት ዘፈን፣ ለቅሶ እና ቋንቋ አለ። ኢትዮ ጵያ ውስጥ የተለያየ ህዝብ አለ ማለት ነው። እነዚ ህ ህዝቦች በየራሳቸው ሁኔታ ይፈላለጋሉ። የኢት ዮጵያ የፖለቲካ ድንበርን ያልተከተልነው የተለያየ ን ሰዎች ስለሆንን ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድ ንበር አንድ ላይ መቆም በሚያስፈልገን ጊዜ ከኢት ዮጵያም ኮሚዩኒቲ ጋር ሆነ ከሌሎች ጋር አብረን እንቆማለን። እኛ ብቻችንን መቆም አንፈልግም። የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የፖለቲካ ድንበርን ነው የ ተከተለው። የሰዎችን የመተዋወቅ እና የመፈላለግ ሂደት አልተከተለም። አንድ መታወቅ ያለበት ግን እኛ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተቃራኒ አይደለንም። ከኢትዮጵያ የመጣን ኦሮሞዎች ነን። አብዛኛው የ ኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። ግን እዚህ እንደኦሮሞ በቅርበት፣ በጋራ ለመረዳዳት እ ና የሚደርስብንን በጋራ ለመወጣት የተደራጀን ነ ን። የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ድጋፍ በሚፈልጉበት ጊ ዜ እኛም፣ እነሱም አብረን የምንሰራበት አጋጣሚ ዎች አሉ። አሁን ለምሳሌ በኢትዮጵያውያን ላይ የመልሶ መስፈር (ሪሴትልመንት) ጫና አለ። ይህ ንን በማናገኝበት ጊዜ አብረን በጋራ ቆመን ለምን አንጠይቅም ብለን እንጠይቃለን። ሌላው ግን የእኛ ህዝብ ብዙ ስለሆነ አመት በዓ ል እናከብራለን። እሬቻ ስናከብር ኦሮሞዎች ናቸ
ው ገብቷቸው የሚያከብሩት። የእኛን የባህል ዝ ግጅት (ካልቸራል ሾው) ስናካሂድ የእኛን ባህል ነው የምናሳየው። የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ የሚያስደስቱ ወይም የሚያሳትፉ ላይሆኑ ይችላ ሉ። ስለዚህ በራሳችን ተደራጀን ማለት ነው እንጂ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የመውጣት፣ የመገንጠል፣ ያለመፈለግ አይደለም። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ከሌላው ኮሚዩኒ ቲ በተለየ የሚደርስበት ችግር ወይ ም ጫና አለ ነው የምትሉት? እኛ ከሀገራችን ስንወጣ እንደኦሮሞ ተጠቅተን ነ ው። ኦሮሞ መሆን በራሱ ወንጀል አለው። የምን ኖርበት አካባቢ ያስጠቃናል። በ1991 የፌደራል ክ ልሎች አዋጅ ቁጥር ሰባት ሲታዋጅ ኦሮሚያ የራ ሷን ክልል አግኝታለች። በዚህ ክልሏ ውስጥ ያሉ ሀብቶችን ያለህዝቡ ፍቃድ ገዢው መንግስት መ ጠቀም ይፈልጋል። ይህ ሀብት ለተወሰኑ ጥቂት ሰ ዎች መጠቀሚያ ሆኗል። እንደ ወርቃችን እና ጠ ቅላላ መሬታችን ማለት ነው። የኢትዮጵያ መንግ ስት በአጠቃላይ ሳይሆን አንድ ብሔር እንደፈለገ የሚበዘብዘው ነው። ይሄንንም የሚመለከቱ የኦሮ ሞ ምሁራን እና ህዝቡ ጥያቄ እንዳያነሱ ይፈልጋ ል። ይህንን ጥያቄ የማንሳት አቅም አላቸው የሚ ባሉትን ያጠቃል፣ ያስራል፣ ያሰቃያል። ጥቃቱ በ እኛ ላይ ይብሳል ማለት ነው። ብዙ መሞት፣ ብ ዙ መታሰር አለ። በኦፊሴል በማይታወቁ እስር ቤ ቶች ውስጥ እንሰቃያለን። ይህንን በመረጃ የምና ቀርበው ነው። ከዚህ ስቃይ ለመሸሽ ነው እዚህ የመጣነው። ይ ህ በመንግስት የሚደረግብን ልዩ ትኩረት ያሰባስ በናል። አንድ ዓይነት ቋንቋ እና ባህል ስላለን ያ ያ ሰባስበናል። ኦሮሞዎች ፍቅራችን እና ጥላቻችን አ ንድ ዓይነት ስለሆነ እንሰባሰባለን። ይህ ማለት ሌ
ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ
የአሮሞ ኮሚዩኒቲ መቼ ነው የተ ቋቋመው? ለምንስ ማቋቋም አስፈ ለገ? የተመሰረበት ዓላማው ምንድ ነው? የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ የተቋቋመው እ.ኤ.አ በ2004 ነው። ከዚያ በፊት ሙከራዎች ነ በሩ። በ2004 (እ.ኤ.አ) ተደራጅቶ፣ መተዳደሪያ ደንቡን አጽድቆ፣ በመንግስት ፍቃድ አግኝቶ ስራ ውን የጀመረበት ነው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በኡጋንዳ ማቋቋም ያስፈለገበ ት ምክንያት ብዙ የኦሮሞ ስደተኞች እዚህ ተበታ ትነው በሚገኙበት ሰዓት መታመም መቸገር፣ መ ረጃ ማጣት አለ። ስደተኞች የተለያዩ ችግሮች ይ ገጥማቸው ነበር። እነዚህን ችግሮች መነሻ በማ ድረግ የታመመውን ለማስታመም፣ የሞተውን ለ መቅበር በማሰብ ይሄ የኦሮሞ ስደተኞች ማህበር [እ.ኤ.አ] በ2004 ተቋቋመ። የኦሮሞ ስደተኞች ኮ ሚዩኒቲ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ግዛት ወሰንን አይ ከተልም። የተከተለው የኦሮሞ ማህብረሰብን ማ ሰባሰብ ነው። ይህ ያስፈለገበት ምክንያት ምንድነ ው? አንድ ዓይነት ባህል እና ቋንቋ ያለን ሰዎች ስ ለሆንን፣ ደስ የሚለን እና የሚከፋን ነገር የምንጋ ራ በመሆኑ፣ በአገራችንም ውስጥም አንድ ዓይነ ት በደል የምንበደል ሰዎች ስለሆንን በየጊዜው ተ ገናኝተን በደላችንንም፣ ችግራችንንም ለመረዳዳ ት ነው። አልፎም በዚህ በስደት አገር መውለድ፣ ቤተሰብ ማፍራት አለ። ለቤተሰቦቻችን ቋንቋችን ን፣ ባህላችንን አስተላልፈን ለመስጠት ነው። በጋ ራ ችግራችን ላይ በጋራ ለመቆም ነው። ለዚህ ነ ው የተቋቋመው። አሁን ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመ ስላል? የራሱ ጽህፈት ቤት እና የቦ ርድ አባላት አሉት? አባሉትስ ምን ያህል ናቸው? አወቃቀሩ እና አሰ ራሩስ አንዴት ነው? መጀመሪያ ስንገናኝ የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት ወ ደ 150 እንሆን ነበር። በመዋቅራችን የጠቅላላ ጉ ባኤ አባላት አሉ። በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ሰባት ሰዎች፣ በሽማግሌዎች ኮሚቴ ውስጥ ሶስት ሰዎች፣ በኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን [ቁጥጥር] ኮሚ ቴ ደግሞ ሶስት ሰዎች፣ እና የተለያዩ ባህላዊ እና ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚያካሂዱ ኮሚቴ ዎች በስሩ ጠቅልሎ ነው። የቦርድ አባላትን አል ወክልንም። ያለን መዋቅር ይሄ ሆኖ በየጊዜው የአ ባላቱ ቁጥር ይቀንሳል፣ ይጨምራል። አንዳንድ ጊ ዜ የስደተኛ መጠን ወደ ውጭ በመሄድና በተለያ የ ምክንያት ይቀንሳል። በእነዚህ አመታት ውስጥ በየጊዜው በስብሰባዎች ላይ በአማካይ ከ70 ያላነ ሱ አባላት ይገኛሉ። በየጊዜው ስብሰባ ይደረጋል ማለት ነው? የተለያዩ ዝግጅቶች ታዘጋጃላ ችሁ? ይሄ ህዝብ ጥሩ ባህል እያለው ጥሩ ባህሉን እያ ጣ ነው። ኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ይሄንን ባህል ከትው ልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ በየጊዜው በባ ህሉ ውስጥ ያሉትን በዓላት ያከብራል። ለምሳሌ እሬቻ በየዓመቱ ያከብራል። እሬቻ በዓል ማለት ለኦሮሞ በየዓመቱ ለእግዚያብሔር ምስጋና የሚሰ ጥበት “ታንከስ ጊቪንግ” ነው። እኔ ወደ ኡጋንዳ ከመጣሁ ሶስት ዓመት ነው። ሶስቱን አመት አክ ብረናል። በፊትም ቢሆን እንዲሁ ሲከበር ነው። እሬቻ በዓል በባህሉ ውሃ ዳርቻ ያ ለበት ቦታ ተሂዶ ነው የሚከበረው። ቦታውም እርጥብ እና ለምለም መ ሆን አለበት። ለተምሳሌትነትም ቄ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ጁን 20 ታስቦ የሚውለው የዓለም የስደተኞች ቀን በኡጋንዳ ኦልድ ካምፓላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲከበር የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ አባላት የአሮምኛ ዘፈን እና ጭፈራ አቅርበው ነበር
ላውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንጠላለን ማለት አይደ ለም። የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ መቆም ካለበት አ ብረን እንቆማለን። እንደኦሮሞ ደግም እንበደላለ ን። ይህንን ለመቋቋም ደግሞ አንድነት እና መደ ራጀት ያስፈልገናል። ነገር ግን እኛ እዚህ ስደተኞ ች ነን። የፖለቲካ ስራ አንሰራም። ኮሚዩኒቲው ሲቋቋም የወሰን ግዛት ን መሰረት አያደርግም ብለዋል። የኦ ሮሞ ህዝብ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ በተለያየ ቦታ ይገኛል። በኬንያ ድንበ ር አካባቢ ያለውን እንደምሳሌ ብንወ ስድ እንኳ የቦረና ህዝብ ድንበር ተሻ ግሮ በሁለቱም አገራት ይገኛል። አን ድ ዓይነት ቋንቋ እና ባህል ካላቸው ከእነዚህ ኦሮሞዎች ጋር ያላችሁ ግ ንኙነት ምን ይመስላል? ከወሎ እና ቦረና ተሰደው የመጡ ኦሮሞዎች አ ሉ። የማህበራችን አባል ናቸው። በኢትዮጵያ ው ስጥ ኦሮሚያ ተብሎ ከተከለለው ውጭ ያሉትን ም እንረዳቸዋለን። ጥገኝነት ለማግኘት በሚያደር ጉት እንቅስቃሴ እንረዳችዋለን። “ፕሮሰስ” ሲያደ ርጉም እንደዚያው። እነርሱ ሁሉ የእኛ ማህብረሰ ብ አባል ናቸው። የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ በናይሮቢ፣ በሚኒሶታ፣ በአ ውሮፓ እና በአውስትራልያ አለ። ከእነዚህ ኮሚ ዩኒቲዎች ጋር እርስ በእርስ እንተጋገዛለን። ባለፈ ው ዓመት በኡጋንዳ ውስጥ የቦምብ ፍንዳታ ደ ርሶ ነበር። በዚህ ፍንዳታ አራት የኦሮሞ ኮሚዩኒ ቲ አባላት ከሶማሌዎች ጋር ባላቸው የፊት መመ ሳሰል በጥርጣሬ ታስረው ነበር። በዚህ ጊዜ በመ ገናኛ ብዙሃን እና በኢንተርኔት አማካኝነት የታሰ ሩትን ለማስፈታት ጥረት ስናደርግ አብረውን ጥ ረት አድርገዋል። ከእነዚህ ማህበራት ጋር አብረ ን እንሰራለን ማለት ነው። የኢኮኖሚ ችግር ሲገ ጥመን ይረዱናል። የወደፊት እቅዳችሁ ምንድነው? በየ ጊዜው ለሚመጡ ስደተኞች አንድ ቋ ሚ ነገር ለማቋቋም ያሰባችሁትስ ነ ገር አለ? በዚህ ማህበር ሕግ መሰረት አመራር በየሁለት ዓ መቱ ይለወጣል። በመጪው ነሐሴም አዲስ አመ ራር ይለውጣል። እኔ ሁለት ዓመት ስለሞላኝ ጨ ርሻለሁ ማለት ነው። አሁን ባለው ዕቅዳችን መሰ ረት ቀጣዩ ቢሮ መክፈት ነው። ለጊዜው “ቡኬሳ ን” [ምግብ ቤት] እየተጠቀምን ነው። አዲስ የሚ መጡ ስደተኞች መረጃ እንዲያገኙ፣ የት መሄድ እ ንደሚችሉ ኮሚቴዎች ማደራጀት ነው። እነዚህ ኮ ሚቴዎች ስደተኞችን እንዲረዱ ማድረግ ነው። እ ዚህ ስራ አጥ የሆኑ የኦሮሞ ስደተኞች ስራ የሚያገ ኙበት መንገድ ለማመቻቸት አንድ “ፕሮጀክት ፕ ሮፖዛል” እየተሰራ ነው። ለወደፊት ደግሞ እኛ በስደት ዕድሜ ልካችንን እ ንድንኖር አንፈልግም። አገራችንን እንወዳለን። የ አገራችን የአስተዳደር ሁኔታ ሲሻሻል፣ ሰው በእኩ ልነት ሰርቶ መኖር የሚችልበት ደረጃ ሲደርስ ወ ደ ሀገራችን እንመለሳለን። ያ ሁኔታ ካልተቻለ የዓ ለም የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ው ስጥ እየደረሰ ላለው የኦሮሞ በደል ልዩ ትኩረት እ ንዲሰጡ እንፈልጋለን። በብዛት ሰው ይወጣል። በኬንያ ብቻ አይደለም። ኦሮሞ በጅቡቲ፣ በሶማ ሌ፣ በጎንደር ይወጣል። ድንበራችን ብዙ ነው። ለ እነዚህ ዓለም ትኩረት እንዲሰጣቸው እንፈልጋለ ን። መልሶ እንዲያሰፍራቸው እና እንዲያቋቁማቸ ው ወይም ደግሞ በአገር ውስጥ ያለውን በደል እና ስቃይ አለም እንዲያተኩርበት እንፈልጋለን።
6
የስደት ዓለም
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
ትምህርት ቤት ሲዘጋ…
በአሜሪካ
ኤፍሬም እሸቴ በዚህ በአሜሪካ አሁን በጋ (Summer) ነው። ብዙ ሠራተኞች እረፍት ለመውጣት ጥሩ አጋጣ ሚ አድርገው የሚጠቀሙበት ጊዜ ይህ የበጋው ወራት ነው። ትምህርት ቤትም ተዘግቷል። ልጆ ቹ በሙሉ በየመንገዱ፣ በየመዝናኛው ይተረማ መሳሉ። በተለይ ወደ ማታ ላይ ሕጻናቱን አምጥ ቶ የሚያፈሳቸው ማን እንደሆነ እንጃ። ትምህርት ቤት ሲዘጋ ወላጅ ሁሉ ሕጻናቱን የ ሚያስቀምጥበት ሥፍራ መፈለግ አለበት። ትም ህርት ቤት የሚፈለገው ልጆቹ ሔደው ዕውቀት እንዲቀስሙ ብቻ ሳይሆን መዋያም እንዲያገኙ ነ ው። ልጆችህን ትምህርት ቤት ካልላህክ የት ታደ ርጋቸዋለህ? ጎረቤት ትቻቸው ልሒድ ወይም ሠ ራተኛ ልቅጠርላቸው አይባል ነገር። ሠራተኛ እን ኳን አሜሪካ ኢትዮጵያም እየጠፋ ነው። ዕድሜ ለትምህርት ቤት፤ እዚያ አስቀምጦ ወደ ሥራ። እንዲህ ዓይነቱ የአሜሪካው የበጋ ወራት ሲመ ጣ ደግሞ ልጆቹን ማስቀመጫ ቦታ፣ የሚሠሩት ሥራ መስጠት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ትምህር ት ቤት ይዟቸው የነበሩት ልጆች ተለቀው የማይ ሆን ነገር ውስጥ ሊገቡ ይቻላሉ። ይህንን ለመታ ደግ “ልጆቻችሁን እንያዝላችሁ፣ እናስጠናላችሁ፣ ስፖርት እናሰልጥንላችሁ” ወዘተ ወዘተ የሚሉ የ ተለያዩ ማስታወቂያዎችን ማየት የተለመደ ነው። እናም ልጆቻችንን በአንዱ ቦታ በጋውን እንዲያሳ ልፉ በማስመዝገብ፣ ካለችን ቆጥበን በመክፈል ል ጆቹ ትምህርትም መዝናኛም ባለበት ሁኔታ እረ ፍታቸውን እንዲያሳልፉ እናደርጋለን። ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ መቸም እኔ ራሴ ልጅ በነ በርኩበት ጊዜ፣ ትምህርት ቤት ሲዘጋ እንዴት አ ሳልፍ እንደነበር እንዳስታውስኝ ያደርገኛል። ያኔ ትምህርት ቤት መዝጊያ ሰኔ 30 ነበር። “ሰኔ 30፤ የተማሪ አበሳ” ይባልም ነበር። የሚያልፈው እና የሚወድቀው የሚለይበት፤ ካርዳችንን ተቀብለን ግማሹ በደስታ፣ ግማሹ በልቅሶ ወደቤቱ የሚሔ ድበት የልጅነታችን አጓጊ ቀንም ነበር። ተማሪዎች ሲጣሉ እና ቂም ሲያያዙ “ቆይ፣ ሰኔ 30 ያገናኘን” መባባል የተለመደ ነበር። በክረም ቱ ምክንያት ትምህርት ቤት ስለሚዘጋ የተጣሉ ትን ደቁሶ፣ ዓመቱ ሙሉ አንጀት ሲያቃጥል የነበ ረውን ሁሉ ዋጋውን ሰጥቶ እስከ መስከረም ነገሩ ስለሚረሳ ከአስተማሪ ቅጣት ለማምለጥ ስለሚያ ስችል ነበር - ሐሳቡ። አንዳንድ ጊዜ አስተማሪው ም “ሊቀምስ” ይችላል። ተማሪ ጥጋበኛ አይደል? ትምህርት ቤት ከተዘጋ በኋላ ተማሪው ከጭቃ ው እና ከዝናቡ ጋር ጭቃ እና ዝናብ ሆኖ ወደሚ ያሳልፍበት የሁለት ወራት ጊዜ ይገባል። ከገጠር አካባቢ የመጣው ተማሪ ወደ እርሻው፣ ወደ ጉል ጓሎው፣ ወደ ጥጃ ጥበቃው ይመለሳል። የከተማ ውም ልጅ ቢሆን፣ ከጥቂቱ በስተቀር፣ ቤተሰቦቹ ን በአቅሙ ወደ መርዳት የመሔድ ግዴታ አለበ
ት። እንደማስታውሰው ክረምት በመጣ ቁጥ ር ጭቃ መስለን እና ጭቃ ሆነን የአቅማችንን “ለወላጆቻችን ለመታዘዝ” እንሞክር ነበር። ክረምት ለጨዋታ እና ለመዝናናት አይመች ም። ኳስ ለመጫወት ሜዳው በሙሉ በውሃ ይሸፈናል። እንኳን የመንደራችን ሜዳዎች አ ዲስ አበባ ስቴዲየም ራሱ ውሃ ይቋጥራል። የ ቤት ውስጥ መጫወቻ ሥፍራ፣ ኳስ ሜዳ የ ሌለባት ብቸኛ አገር መቸም ኢትዮጵያችን ሳ ትሆን አትቀርም። እንኳን በየመንደሩ ያለን ሕጻናት ብሔራዊ ቡድኑም በክረምት የሚጫ ወትበት ሜዳ የሌለበት አገር ነው። በክረምቱ ትልቁ መዝናኛችን፣ ከቤተሰባችን ም ቁጣ ለመዳን፣ ኩሽኔታችንን እየነዳን የማገ ዶ እንጨት ሰበራ ወደ ጫካ እንወጣለን። ብ ዙ ጊዜ ዝናሙ የሚዘንበው ወደ ከሰዓት በኋ ላ ነው። ለምን በዚያ ፕሮግራም እንደሚመ ጣ እግዜር ይወቀው። ቁልፉ በእርሱ እጅ ነ ው። ብቻ ጳጉሜን ላይ ካልሆነ ዝናቡ በጠ ዋቱ አያስቸግረንም። ቁርሳችንን በልተን ወደ ጫካ የተተኮስን የማታው ዝናብ ሳይጠምደ ን እንመለሳለን። አንዴ ከያዘ የማይለቀው አ ህያ የማይሸከመው ዝናብ ከመጣ የልጅ ጀር ባችን ያጎብጠዋል፤ በረዶው መላጣ ራሳችንን እየቀጠቀጠ መግቢያ ያሳጣናል። ቆረቆራችን ን ያፈርጠዋል። ቢሆንም ቤት ስንደርስ የወላጆቻችን ፈገግ ታ እና ምርቃት ያንን ሁሉ ነገር ያስረሳናል። ትኩስ ትኩሱ ይቀርብልናል። ከትኩስ ሽሮ እ ስከ ትኩስ አሹቅ (ዲዘርት መሆኑ ነው) በደስ ታ ይቀርብልናል። ያንን በራበው ሆዳችን ላክ ላክ እያደረግን እንቅልፍ ሰዓታችንን እንጠብ ቃለን። ቴሌቪዥን የለ፣ ፊልም የለ፣ እንዳሁ ኑ ልጆች “ጌም የለ” ….። ሐምሌን እንዲህ ጨርሰን ነሐሴ ሲመጣ ከ እንጨት ለቀማውም ከሌላውም ሥራ የሚገ ላለግለን የፍልሰታ ጾም ነው። ፍልሰታ የልጆ ች ጾም ስለሚባል አንገታችን ላይ ሚጢጢ ያንገት ልብስ እየጠመጠሙ ወደ ቤተ ክርስ ቲያን ይልኩናል። እውነቱን ለመናገር ከጽድ ቁ ይልቅ ትዝ የሚለን ከቅዳሴ በኋላ የምንበላ ው ንፍሮ እና ቆርበን ስንመጣ እቤት የሚጠ ብቀን እንክብካቤ ነው። የቆረብን ቀንማ ም ን ብናጠፋ ማን ንክች ሊያደርገን? ባይሆን ባይሆን በዕዳ ለሌላ ቀን ያስተላልፉታል። በ ሚቀጥለው ጊዜ በጥፋት ስንገኝ የቆረብን ዕ ለት ያናደድናቸውን ደምረው ቂማቸውን ይ ወጡብናል። እዚህ የፈረንጁ አገር፣ ልጆቹ ትምህርት ቤ ታቸው ሲዘጋ ምን እንደሚሆኑ እና ምን እን ደሚያደርጉ ማሰብ የወላጅ ትልቁ ጭንቀት ነ ው። አንዱ ቦታ አስቀድሞ ተመዝግቦ እና ከ ፍሎ መዘጋጀት የወላጅ ግዴታው ነው። ገና በሙዓለ ሕጻናት ዕድሜ ካሉት እስከ ወጠጤ
ጎረምሳዎቹ (Teenagers) ድረስ የሚውሉበት ሥፍራ አላቸው። ያንን የሚያዘጋጁት ደግሞ የ ግል ተቋማትም፣ የመንግሥት ተቋማትም ጭ ምር ናቸው። መንግሥት ለወጣቱና ለሕጻኑ ካ ላሰበ ምኑን መንግሥት ሆነው? በምኖርበት አካባቢ ልጆችን በዚህ የዕረፍት ወቅት ከሚያስተናግዱት መካከል የአካባቢው መስተዳደሮች (ቀበሌ እንበላቸው?) አንደኛዎ ቹ ናቸው። በመጠነኛ ክፍያ ለሕጻናቱ እና ለወ ጣቶቹ መርሐ ግብሮች ያሰናዳሉ። የተለያዩ ስ ፖርቶች፣ ጉብኝቶች፣ ዋናዎች፣ እንደየዕድሜያ ቸው ከእኩዮቻቸው ጋር ትውውቆች እና ጨ ዋታዎች ያዘጋጁላቸዋል። ለአንድ ልጅ በቀን ከ50 ዶላር ያላነሰ ያስከፍላሉ። የግሎቹ የሚያ ስከፍሉት ከዚህ በጣም ይወደዳል። ይህ የቀበ ሌዎቹ ሰርቪስ ገሚሱም በተለያየ መልኩ ሳይ ደጎም የሚቀር አልመሰለኝም። አለበለዚያ እን ዲህ ርካሽ ሊሆን አይችልም ነበር።
“
ድሮ ድሮ ወፍራም ልጅ ስናይ “የሀብታም ልጆች” እያልን ስንቀናባቸው ኖረን አሁን ቀጭን መሆን ዋጋ ያለው አገር መጣንና በተራችን ልጆቻችን እንዳይወፍሩ እንጨነቃለን። ከወደድኩላቸው ዝግጅት አንዱ ሕጻናቱን እ ና ወጣቶቹን ይዘው ወደ ሙዚየም ጉዞ ማድ ረጋቸው ነው። እንደየዕድሜያቸው የሚመጥ ናቸውን ያሳዩዋቸዋል። ስለ አገራቸው እንዲያ ውቁ ያስተምሯቸዋል። በዚያ ዕድሜ “ሙዚየ ም መሔድን” እንዲለምዱም በልቡናቸው ይ ቀርጹባቸዋል። እዚያ ባለው ቤተ መጻሕፍትም እንዲያነቡ ያበረታቷቸዋል። መሸት ሲል ወላጅ ሁሉ ልጁን ከያስቀመጠበ ት ይሰበስባል። ወራቱ በጋ ስለሆነ ፀሐይ ቶሎ አትጠልቅም። ይህንን ጽሑፍ እየጻፍኩ ባለሁ በት ሰዓት (ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ) ውጪው ወ ከክ ብሎ ይታየኛል። ፀሐይ ወደ ቤቷ ተጠቃ ላ ለመግባት ትንሽ ይቀራታል። ስለዚህ ልጆቹ ን ወደ ውጪ ይዞ መውጣት ለሚችል ወላጅ ጊ ዜው ይመቻል። ሳይመሽ ወደቤት ከገቡ ተሽቀ
ዳድመው እዚያው ቴሌቪዥኑ ላይ እንዳያፈ ጡ ወላጅ የቻለውን ያህል ይሞክራል። አሜ ሪካ ላለ ልጅ መቸም ጠላቱ ቴሌቪዥን እና ይ ኼ ስኳር የሚበዛበት ጣፋጭ ምግብ ነው። የዚህን የቴሌቪዥንን ነገር፣ በየጣራቸው ላ ይ ዲሽ የሰቀሉ የአገር ቤት ወላጆችም ሊያስ ቡበት ይገባል። ዲሽ መግጠማቸውን እንጂ ልጆቻቸው ምን እንደሚያዩ ሳያዉቅ የልጆቻ ቸው መጥፊያ እንዳይሆንባቸው ብርቱ ጥን ቃቄ ይፈልጋል። ቴሌቪዥን ሕጻናቱን ያደን ዛል። ያደነዝዛል። ከማንበብ ይልቅ ፊልም እ ና “ጌም” ብቻ የሚወዱ ስልቹዎች ያደርጋቸዋ ል። ብዙ ሰዓት ቁጭ ስለሚሉም ሰውነታቸ ው አላስፈላጊ በሆነ ውፍረት ይወጠራል። ገ ና በልጅነታቸው የበሽታ ዓይነት ይሸከማሉ። ድሮ ድሮ ወፍራም ልጅ ስናይ “የሀብታም ል ጆች” እያልን ስንቀናባቸው ኖረን አሁን ቀጭ ን መሆን ዋጋ ያለው አገር መጣንና በተራችን ልጆቻችን እንዳይወፍሩ እንጨነቃለን። በየጊ ዜው የነርሱን ኪሎ መለካቱ፣ ወፈሩ አልወፈ ሩ እያሉ ማሰቡ የአሜሪካ ወላጅ አንዱ ግዴ ታ ነው። ድሮ አገር ቤት “ምነው ልጄ ወፍራ ም በሆነልኝ” ሲባል ሰምተን አሁን ደግሞ (አ ሜሪካ) “ኧረ ልጄ ወፈረብኝ/ እየወፈረብኝ ነ ው/ ሊወፍርብኝ ነው” የሚል ጭንቀት መስ ማት ግርምት ይፈጥራል። በሁሉም በሁሉም፣ በአሜሪካ ትምህርት ቤ ት ሲዘጋ፣ ከውፍረታቸው እስከ መዋያ ቦታቸ ው፣ ከትምህርታቸው እስከ መዝናኛቸው ወ ላጅ የቤት ሥራ የሚበዛበት ጊዜ ይሆናል። እ ናም አንዳንዴ “ምናለበት የሀገሬ ልጆች እንዲ ህ ዓይነቱን የልጆች መዋያ በየመንደሩ ባገኙ” የሚል ቁጭት ውስጤን ይበላኛል። ሜዳው ሁሉ ዛኒጋባ እየተቀየሰበት፣ ልጆቹን አንድም ለሥራ ፈትነት፣ አንድም ለጫት ቃሚነት፣ አ ሁን እንደምሰማው ደግሞ “ለሺሻ ሱሰኝነት” አሳልፈን እየሰጠናቸው ነው። ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ አሁን የሚገነቡትን “ኮንዶሚኒየም” ሕንጻዎች እና አዳዲስ መንደ ሮች እንኳን በሕግ ደረጃ ለሕጻናት መጫወ ቻ የሚሆን ቦታ እና አረንጓዴ ሥፍራ እንዲኖ ራቸው በማስገደድ ልጆቻችን እንደ ማንኛው ም ልጅ የሚቦርቁበት፣ የሚጫወቱበት፣ ወደ አስፓልት ከመውጣት ይልቅ ከመንገድ የሚ ርቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል። ተደርጎ ከሆነም ደግሞ እሰየው ደስ ያሰኛል። እንቅፋ ት የእግራችንን ጥፍር እየነቀለውም ቢሆን፣ የ ወዳደቁ ነገሮች እየወጉንም ቢሆን ኳስ ያንከ ባለልንበት “እንትና ሰፈር ሜዳ፣ ቀበሌ ምንት ስ ሜዳ” ናፈቀኝ። ለአሁኖቹም ሕጻናት ተመ ኘሁላቸው።
ማስታወቂያ
በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ
በ+256-778-693669 ይደውሉልን
ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም የተወሰደ ነው
A break from every thing በናኦድ ቤተሥላሴ (ሜሪ ላንድ፣ አሜሪካ) ዕለት ከዕለት፤ ሳምንት ከሳምንት አንድ ዓይነት ነገር እ ያሰቡ እና እየሰሩ ለመኖር አልተፈጠርኩም ብየ ሳምን የቆየሁ ቢሆንም አሜሪካ ግን ሳልወድ በግዴ በተመሳሳ ይ ሳምንታዊ ፕሮግራም እና ልማድ እንድኖር አስገድዶ ኛል፡፡ ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለምጀው ተፈጥሮዬ ላደርገ ው ትንሽ ሲቀረኝ፤ ሰሞኑን ልጄ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፡፡ የነገሩ መነሻ መጪው የሰመር ዕረፍት ነበር፡፡ “Abuka! When will your summer break starts?” I asked my son. “You are Dady!, you’r suppose to know it.” he replied. He is trying to remind me about my own Ignorance. Then he continues “Any way, summer break will begin after a couple of weeks. But it offcially starts on June 21st” “It is good to know” I replied. The I added “I think we need to have a paln for the summer break” This time my son switched in to his angry mode. “ Dadyeeee! I am tried of this planning thing. Summer break means a break from EVERY THING. I don’t want to plan any thing” My son’s frustration reminded me my self imposed ‘planning obssession’. ሁሉም ኢትዬጵያዊ ይህንን ግብ የሚፈጽምበት መን ገድ የተለያየ ነው፡፡ የእኔም እንዲሁ፡፡ ከሰኞ እስከ አር ብ ልጆች ትምህርት ቤት ስለሚውሉ፤ የቤት ሥራ ከማ ሰራት ውጪ ብዙ ሥራ አይጠበቅብኝም፡፡ ቅደሜ እና እሁድ ግን ከባድ ቀኔ ነው፡፡ የተለመደው የሰንበ ት ቃ ሌ አንድ ነው፡፡ ‹‹ልጆች! የዛሬ ዕቅዳችሁን ጽፋችሁ አምጡ!›› እላለ ሁ፡፡ እንደተለመደው ‹‹በቃላችንን ብንነግርህስ?›› ይላሉ፡ ፡ ግን እንደማይሆን ስለሚያውቁ ባላቸው አቅም ሞ ጫጭረው ያመጣሉ፡፡ በዕቅዳቸው ወስጥ ምን ማካተት እንዳለባ ቸው ስለለመዱ፤ የሚጽፉት አያጡም፡፡ -መኝታ ማንጠፍ፤ ክፍላቸውን ማጽዳት -ቴሌቪዥን ማየት -ማንበብ -ስዕል መሳል -ብስክሌት መንዳት -ላይብረሪ/ፓርክ መሄድ -ሂሳብ መማር -ሀ ሁ ሂ መማር (በእነርሱ አገላለጽ) -ፕሮጀክት የሚሉት ነገር መስራት -መጫወት - የመሳሰሉ ነገሮችን ይደረድራሉ፡፡ ዋናው ዓላማዬ ‹‹ደበረኝ›› እና ‹‹ምን ልሥራ›› ማለትን እንዳይለምዱ ነው እንጂ ቀኑን ሙሉ ሲጫወቱ የሚው ሉበትም ጊዜ አለ፡፡ በሌላ አንጻርም ይህን ማድረጌ ለራ ሴም በግሌ የምሰራውን የምሰራበት ነጻ ጊዜ እንዲኖረ ኝ ለማድረግም ጭምር እንጂ፡፡ ለልጆች ቅዱስ የሰመር ፕሮግራም የሚሆነው ኢትዬ ጵያ ሄደው ቢከርሙ ነበር፡፡ ሁሉም ወላጅ በግሉ የ ሚመኘው፤ ቀን ጠብቆም የሚያደርገው ይሄንኑ ነው፡ ፡ እንደ እኔ ላሉ የዲቃላ ባሕል ልጆች ግን አንድ የተቀ ናጀ መላ የሚያስብ ሰው ወይም ቡድን ቢኖር ግን ቅ ዱስ ነገር ነበር፡፡ ልክ እንደ ‹‹ሀገርህን እወቅ›› ፕሮግራ ም ወይም ‹‹የአሜረካ ፒስ ኮር›› ዓይነት ድርጅት ቢኖ ረን ተመኘሁ፡፡ ይህ ጽሁፍ የተወሰደው ከናኦድ ጡመራ ናኦድ ላይቭ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም ነው
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
7
ሐበሻዊ ቃና
የስደት ዓለም
ህልም አልባው ኤርትራዊ ወጣት ሊቢያ እና ግብጽ ድንበር የ ምትገኛዋ ሳሉም በረሃማ ነ ች። በዚያ ምህረት አልባ በ ረሃ ላይ አንድ ትንሽዬ እና ደ ካማ ፍጡር ራሱን ከአሸዋ እ ና ንፋስ ለመከላከል እየሞከ ረ ይንከላወሳል። ትግሉ ግን ከተፈጥሮ ጋር ብቻ አልነበረም። ውስጡን ከሚያብሰከስከው ስጋት እና የደህንነት ማጣት ስሜት ጋርም ነው። ይህ ፍ ጡር ሰሎሞን ይባላል። የራሴ የሚለው ምንም ነ ገር የሌለው፣ ብቸኛ፣ የ17 ዓመት ወጣት ኤርትራ ዊ ስደተኛ ነው። ከዕድሜው በላይ ቁም ነገረኛ የሆነው ሰሎሞን ህይወቴ የተገረመ ነው ብሎ ያምናል። “ከውልደ ቴ ጀምሮ ጨምሮ አስቸጋሪ ህይወት ነው ያሳለፍ ኩት። የህጻንነት ጊዜ የሚባል አልነበረኝም። ትም ህርት ቤትም አልገባሁም” ይላል ስለ ህይወቱ ሲ ያስረዳ። ሰሎሞን ከኤርትራውያን ስደተኛ ቤተሰ ቦቹ ሱዳን ውስጥ ነው የተወለደው። ወላጆቹን ግን አያውቃቸውም። አባቱ እርሱ ከመወለዱ በ ፊት ነበር የሞተው። እናቱ ደግሞ እርሱን ስትገላ ገል በወሊድ ምክንያት አርፋለች። እርሱን ያሳደ ጉት ለነፍሳቸው ያደሩ እማሆይ ስላስ የሚባሉ እ ናት ናቸው። ነፍስ ሲያውቅ ጀምሮ ኑሮን ለማሸነፍ ውሃ መሸ ጥ የጀመረው ሰሎሞን በ12 ዓመቱ ሌላ ትልቅ መ ከራ ወደቀበት። እንደእናት ያሳደጉት እማሆይ ስ ላስ ሞቱ። ብቻውን ቀረ። “አሁንም ድረስ በጣም ትናፍቀኛለች። ያለችን አንድ ቤተሰብ እርሷ ነበረ ች” ይላል በሀዘን ስሜት ተውጦ። ከእማሆይ ስላስ ሞት በኋላ አንድ ሱዳናዊ ሊያ ሳድገው ይስማማል። ሆኖም የሚከተለውን የክር ስትና ሃይማኖት በእስልምና እንዲለውጥ ያስገድ ደዋል። “ገና ከስላስ ሞት ሳላገግም ግፊት ያሳደር ብኝ ጀመር። ይሄኔ ጥዬ ወጣሁ” ይላል ለምን ከአ ዲሱ አሳዳጊ እንደሸሸ ሲተርክ። ሽሽቱ ከነበረበት አነስተኛ ከተማ ከፍ ወዳለችው አል ፋው አደረ
ሰው። በእዚያ ለስድስት ወር ያህል ቆየ። ቀን ቀን ያደገበትን ውሃ መሸጥ ሲያከናውን ይውልና ማ ታ ላይ ጎኑን ለማሳረፍ ወደ አውቶብስ ማቆሚያ ዎች ጎራ ይላል። እንዲህ እንዲህ እያለ ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚወስደው ገንዘብ አጠራቀ መ። ካርቱም ለአንድ የህግ አገልግሎት በሚሰጥ ድርጅት የጽዳት ስራ አገኘ። ሰሎሞን ጎሮሮውን መድፈን ባያቅተውም የተሻ ለ ኖሮ ፍለጋ በአንድ ሆቴል ውስጥ ካገኛቸው ኤ ርትራውያን ጋር ወደ ሊቢያ ለመሻገር ተስማማ። እ.ኤ.አ በ2009 ሊቢያ ሲደርስ ዕድሜው ገና 15 ነበር። “ሌላ ቦታ ያለውን ስለማላውቅ ሊቢያ የ ተሻለ ህይወት ያለ መስሎኝ ነበር። ዕቅዱ ግን ከ ትሪፖሊ ባህር አቋርጦ ወደ አውሮፓ መሄድ ነበ ር። ነገር ግን እንዲያ ለማድረግ ዋጋው የሚቀመ ስ አልነበረም።” አብረውት ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ የገቡ ተ ሳክቶላቸው ጣሊያን ገቡ። ደጋፊ እና አጋዥ የሌ ለው እርሱ ግን ብቻውን ቀረ። ትሪፖሊ ያለው የ ወታደር ብዛት ያሰጋው ሰሎሞን ቤንጋዚ ወደተሰ ኘችው ከተማ ሄደ። እዚያም በካፌ ውስጥ ስራ አ ገኘ። አብዛኛውን ጊዜ ስራ ላይ የሚያሳልፈው ሰ ሎሞን ከተማይቱን ለመመልከት ወጣ የሚለው ከስንት አንዴ ነበር። ከእነዚህ አጋጣሚዎች በአን ዱ ግን ለእስራት በቃ። ምክንያቱ ደግሞ በአንገቱ ላይ ያንጠለጠለው መስቀል ነበር። በእስላማዊቷ ሊቢያ መስቀል አድርጎ በመገኘቱ ብቻ ወደ እስ ር ቤት ተወረወረ። “ለማየት ያህል በአነስተኛ ቀዳዳ ብርሃን በሚገ ባበት ትንሽዬ ጨለማ የእስር ክፍል ውስጥ አስ ቀመጡኝ” ይላል የታሰረበትን ክፍል ሲያስታው ስ። “ወደ እስር ክፍል ስገባ ዓይኔ እንዳላይ ተሸብ ቦ ስለነበር የት እንደታሰርኩ አንኳ አላወቅኩም ነ በር። ከእስራኤል እንደመጣሁ ደጋግመው ይናገ ሩ ነበር። በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃዩኝ ነበር። በጣም ፈርቼ ነበር” ሲል እየተንቀጠቀጠ የነበረበ ትን ሁኔታ ይተርካል።
ፎቶ- ናያና ቦሴ
በ
በናያና ቦሴ ሳሉም-ግብጽ
በረጅሙ እና የማይገፋ በሚመስለው ቀን ሰሎሞን በበረሃማዋ ሳሉም ከመንገድ ጠርዝ ተቀምጦ ይተክዛል
እስካሁንም እልባት ያላገኘው የሊቢያ አብዮት በየካቲት ሲፈነዳ ሰሎሞን ከሌሎች እስረኞች ጋ ር ተለቀቀ። ተለቅቆም ግን ሰላም አላገኘም። ሙ አመር ጋዳፊ መልካቸው ጠቆር ያሉ ቅጥረኞችን አሰልፏል በሚል ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች የመ ጡ ስደተኞች ላይ ጥቃት መፈጸም ተጀመረ። የ ጋዳፊ ተቃዋሚዎች ዋነኛ ቦታ በሆነችው ቤንጋዚ ስደተኞች የጥቃቱ ዋና ኢላማ ሆኑ። ለህይወቱ የ ሰጋው ሰሎሞን የሊቢያ ቀይ ጨረቃን ሙጥኝ አ ለ። የዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) በ መጋቢት ወር ስደተኞችን ከሊቢያ ሲያስወጣ ሰ ሎሞንም አንዱ ሆነ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተ ኞችን ተከትሎ በሰሜን ምስራቅ ግብጽ ወደምትገ ኘው ሳሉም ተጓጓዘ። በሳሉም በያዝነው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ የ ቀሩ የሊቢያን ጦርነት የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠ ሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ነበሩ። ምን ም እንኳ በእርሱ ዕድሜ ያሉ ሌሎች ኤርትራውያ ን ስደተኞች በሳሉም መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ ቢ ኖሩም ሰሎሞን ግን አሁንም ብቻውን ነው። ከተ ባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ባገኘው ፕላስቲክ አነስተኛ ድንኳን ቀልሶ በእርሷ
እንደ ገበቴ ውሃ... የዓለም ትኩረት በምስራቅ አፍሪካ ስለተከሰተ ው ድርቅ እና ስለሚያስከትለው ተጽእኖ በሆነበት በአሁን ወቅት ሌላ ቀውስ በአንድ የኢትዮጵያ ጥ ግ ድምጽ አጥፍቶ ሊፈነዳ እየተንተከተከ ይገኛል። ቀውሱ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ከሚጎርፉ ኤርትራ ውያን ጋር የተያያዘ ነው። ማለቂያው የማይታወቅ የወታደራዊ አገልግሎት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ሽሽት ነው ያሉ በመ ቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በየወሩ ወደ ኢ ትዮጵያ ይመጣሉ። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን በቅርቡ የጎበኙት የ ተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ረዳት ኮሚሽነር ኤሪካ ፌለር የተመለከቱትን “የወጣት ፊቶች ባህር” ሲሉ በድን ጋጤ ገልጸውታል። ከሶማሊ እና ሱዳን በርካታ ስደተኞች በተጨማ ሪ ኢትዮጵያ 48 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን መ ጠጊያ ሆናለች። ከእነዚህ አብዛኞቹ ኤርትራውያን ስደተኞች ወጣት፣ የተማሩ እና ገና ያላገቡ ወጣት ወንዶች ናቸው። የስደተኞቹ ቁጥር በየወሩ ማሻቀ ቡን ቀጥሏል። በየወሩ ከ800 እስከ አንድ ሺህ የ ሚጠጉ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። ከ
ፎቶ- ክሱት ገ/እግዚያብሔር
በክሱት ገ/እግዜያብሔር ሽሬ-ኢትዮጵያ
ረዳት ኮሚሽነር ኤሪካ ፌለር እና የዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር የኢትዮጵያ ተወካይ ሞሰስ ኦኬሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ስደተኛ ጣቢያዎችን በጎበኙበት ወቅት ጠባቂ ከሌላቸው ኤርትራውያን አዳጊዎች ህጻናት ጋር ተገናኝተዋል
እነዚህ መካከል ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አለ ጠባቂ ድንበር የሚሻገሩ ህጻናት ይገኙበታል። እስ ከ ስድስት ዓመት ያላቸው ህጻናት ሁሉ ተሰድደው ይመጣሉ። እነዚህ ለጋ ህጻናት እንክብካቤ የሚያ ገኙት በመጡበት ቡድን ውስጥ ባሉ በዕድሜ ከፍ ባሉ ሌሎች ህጻናት ነው።
የማያቋርጠው የስደተኞች ጎርፍ በአሁኑ ወቅት ካለው የስደተኞች አገልግሎት መስጫ አቅም በላ ይ ሆኗል። የችግሩን መጠን የተመለከቱት ፌለር ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር የረጅም ዓመት የስራ ቆይታቸ ው ይህን የመሰለ ነገር አለማየታቸውን ተናግረዋ ል። ረዳት ኮሚሽነሯ እና አብረዋቸው የመጡ የል
ውስጥ ይኖራል። ሰሎሞን እንዲህ ገለልተኛ እን ዲሆን ያደረገው ያለፈበት መራራ ህይወት ነው። አሁንም ቢሆን የደረሰበትን ማሰቃየት ትውስ እ ያለው ይረበሻል። በዚህ ምክንያትም ከሰዎች ጋር ተቀራርቦ መነጋገርም ሆነ ጓደኛ ማፍራት አልቻለ ም። ሰዎችን ለማመንም ይቸገራል። “ጥሩ የህጻንነት ጊዜ አልነበረኝም። ዕድሉን ሳገኝ ጓደኛ አፈራ ይሆናል” ይላል እርግጠኛነት በማይ ነብበት ድምጽ። “ነገር ግን ምን የምናገረው ይኖ ራል? ከችግሮቼ በቀር የማጋራው ምንም ነገር የ ለኝም። ስለሳለፍኩት ህይወት ልነግራቸው እችል ይሆናል ነገር ግን ስለወላጆቼ እና ስላስ በፍጽም ትንፍሽ አልልም። ስለእርሱ ሳስብ አሁንም ድረስ ህመም ይሰማኛል። ገና አልተፈወስኩም” በሰው መሃል እንዲህ በብቸኝነት የሚሰቃየው ሰ ሎሞን ከስደተኛ ጣቢያው ጥሩ ነገር የሚለው ነ ገር የግብጽ ባለስልጣናትን ብቻ ነው። “በሳሉም ያሉትን ወታደሮች ላደንቃቸው እወዳለሁ። ያል ተገባ ጸባይ ብናሳያቸውም እንኳ ጫፋችንን አይነ ኩንም” ይላል። ከዕድሜው በላይ ብልህነት በሚ ታየበት አነጋጋርም እንዲህ ይላል። “ግብጽ በአስ ቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነች። ያለመንግስት ያለች ሀገር
እኛን በአግባቡ እንድታስናግደን አልጠብቅም።” ለተሻለ መጻኢ ህይወት ገንዘብ ማጠራቀም ለ ሚመኘው ሰሎሞን ሕይወት አስቸጋሪ ነበረች። “ዕቅዶች አሉኝ። ገንዘብ አጠራቅሜ ጥሩ ትምህ ርት ለመማር ከዚያም የተሻለ ህይወት መኖር እ ፈልጋለሁ። ይህንን ዕድል እስካሁንም አላገኘሁ ም” ይላል። ሰሎሞን ወደፊት ጥሩ ዕድሎች እን ደሚያጋጥሙት ያምናል። “በህይወት ውስጥ ም ንም ነገር እንደነበረ አይቆይም። ነገሮች ባልተጠ በቀ ሁኔታ በበጎ መልኩ ሊለወጡ ይችላሉ” ሲ ል ይተነብያል። የሰሎሞን ትንበያ በስተመጨረሻ እውን ሆኗል። የስዊዲን መንግስት ከሳሉም ስደተኛ ጣቢያ ለመ ልሶ ማስፈር ለመውሰድ ከተስማማባቸው 145 ስ ደተኞች መካከል አንዱ ሰሎሞን ሆኗል። ሰሎሞ ን ይህን ዕድል ቢያገኝም ነገ የሚያመጣለትን ደፍ ሮ ማሰብ አልሆነለትም። “በስተመጨረሻ ወደተ ሻለ ቦታ ለመሄድ ይህንን ዕድል ለማግኘት በመ ቻሌ ደስተኛ ነኝ። ነገር ግን እዚያ እስከድርስ ድ ረስ አላምንም። ህይወቴ እንደድሮው ሊቀጥል ይ ችል ይሆናል” ሲል ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ያስረዳል።
ዑካን ቡድን አባላት በሰሜን ኢትዮጵያ ሽሬ አካባ ቢ የሚገኘውን የምዝገባ ጣቢያ ተዘዋውረው ጎብ ኝተዋል። እንደባጉና ተብሎ በሚጠራው ቦታ ወዳ ለው የምዝገባ ቦታ በቅርቡ የመጡ ስደተኞችንም አነጋግረዋል። አዲ ሀሩሽ እና ማይ ማኒ የተባሉትን የስደተኛ ጣቢያዎችንም ተመልክተዋል። በሁለቱ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞች ችግራቸ ውን ዓለም ያውቅላቸው ዘንድ ረዳት ኮሚሽነሯ እንዲረዷቸው ተማጽነዋል። “የወጣትነታችንን ሩ ብ ማብቂያው በማይታወቅ ወታደራዊ አገልግሎ ት በአገር ቤት አሳልፈን። ሌላኛውን ሩብ ደግሞ በስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ፈጀን። ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ልጆቻችንን እንደወላጆቻቸው ዕድሜያቸውን በስ ደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲፈጁ መፈቀድ አለበ ትን?” ስትል የሴቶች ተወካይ የሆነች አንዲት ስደ ተኛ ፌለርን ጠይቃለች። ፌለር በበኩላቸው የስደተኞች ካሰቡት ጊዜ በላ ይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው እንደሚሰማቸው ገ ልጸውላቸዋል። ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኢ ትዮጵያ መምጣት የጀመሩት እ.ኤ.አ ከ2000 ጀ ምሮ ነው። በመጀመሪያ የደረሱት በስደተኛ ጣቢ ያ ያሳለፉት ጊዜ ሲሰላ አንድ አስርት ተሻግሯል። “እነዚህ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች ቢሆኑም ተስፋ ግን እየታያቸው አይደለም” ይላሉ ፌለር። “የዓለ ም አቀፍ ማህበረሰቡ እነዚህን ወጣቶች መንከባከ ብ ላይ ከማተኮር ይልቅ ያለውን ችግር በደንብ ተ መልክቶ በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ጥሪቱን ማ ፍሰስ ይገባዋል።” በአሁኑ ወቅት ወደአገር ቤት በፍቃደኝነት መመ ለስ ከምርጫ ውስጥ የሚገባ ባለመሆኑ ዩ.ኤን.ኤ
ች.ሲ.አር ለኤርትራውያን ስደተኞች እየተከተለ ያ ለው ብቸኛ ቋሚ መፍትሔ መልሶ ሰፈራ ብቻ ነ ው። ፌለር ለስደተኞች እንዳብራሩት ከሆነ በተለ ያዩ አገራት የሚሰጠው የመልሶ ማስፈር ዕድል ው ሱን ነው። ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እነዚህን የመልሶ ማ ስፈር ዕድሎች ለመጨመር ይሰራል። “ሕይወት በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ከባድ ነው” ይላል ከሁለት ወራት በፊት ወደዚህ ቦታ የመጣ ው የስምንት ዓመት አዳጊ። እዚህ ረጅም ጊዜ ለ መቆየት “እምብዛም የሚያጓጓ” ነገር እንደሌለም ያክላል። በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ባለው አስ ቸጋሪ ኑሮ እንደዚሁም ራስን ለመቻል እና የከፍ ተኛ ትምህርት ለመቀጠል ያለው ዕድል ውሱን መ ሆን በሺህዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን እንደገ ና ወደ ሶስተኛ አገራት እንዲሰደዱ እያደረጋቸው ነው። ብዙዎች ሱዳን እና ግብጽን ወደ አውሮፓ እ ና መካከለኛው ምስራቅ መሸጋገሪያ አድርገው ይ ጠቀማሉ። ወደእነዚህ ሀገራት በህገወጥ አጓጓዦ ች የሚደረገው ጉዞ ግን በአብዛኛው አደገኛ ነው። ይህንን ዳግም ስደት ለማቆም አንድ እርምጃ መ ወሰድ እንዳለበት የሚያሳስቡት ፌለር ለዓለም አ ቀፉ ህብረተሰብ ጥሪ ያቀርባሉ። “የዓለም አቀፉ ህ ብረተሰብ ኢትዮጵያን እና እንደ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእነዚህ ሰዎች ሁነኛ አማራጭ እንዲያቀርቡ እርዳታ ሊሰጧቸው ይገባ ል። ይህ የሚሆን ከሆነ እነሱም ራሳቸውን ለህገ ወ ጥ አዟዟሪዎች አሳልፈው በመስጠት ራሳቸውን አ ደጋ ላይ አይጥሉም።” ሁለቱም ጽሁፎች የተወሰዱት ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ኦፌሲሊያዊ ድረ ገጽ ነው
8
ሐበሻዊ ቃና
የስደት ዓለም
በዳንኤል ክብረት መጀመርያ ወደ ሱዳን ኤምባሲ ሄዳችሁ ሱዳን የ መግቢያ ቪዛ ታወጣላችሁ፡፡ ከዚያ በጎንደር በመ ተማ በኩል ወደ ሱዳን ትገሠግሣላችሁ፡፡ ‘የሱዳን ሕዝብ ጥሩ ነው፣ለስደተኞች ይራራል‘ ይላሉ ጣ ልያን የገቡት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞ ች፡፡ እዚያ የታወቁ ሁለት አሸጋጋሪዎች አሉ፡፡ በ አካል አታገኟቸውም፡፡ ስልካቸውን ከሀገር ሳትወ ጡ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ አለበለዚያም ጣ ልያን የገባ ሰው ሊነግራችሁ ይገባል፡፡ አንዳች ሰዋራ ሥፍራ ተደብቃችሁ በስልክ ታገ ኟቸውና የጉዞ ዋጋ እና ቀን ትነጋገራላችሁ፡፡ እነር ሱም ገንዘቡን ይዛችሁ የምትመጡበትን ቦታ እና ቀን ይነግሯችኋል፡፡ በተባላችሁት ሌሊት እቦታ ው ስትደርሱ እንደ እናንተ በቀጠሮ የመጡ ሌሎ ች ስደተኞችን ጨምረው በጭነት መኪና ወደ ሊ ቢያ ድንበር ትወሰዳላችሁ፡፡ ጉዞው ሌሊት ሌሊ ት፣ ያውም አብዛኛው በእግር፣ ጥቂቱ ደግሞ በመ ኪና ስለሆነ ከሃያ ቀን እስከ አንድ ወር ይፈጃል፡፡ ሊቢያ ድንበር ስትደርሱ የሱዳን አሸጋጋሪዎች ለ ማስታወቂያ
ሊቢያ አሸጋጋሪዎች ያስረክቧችኋል፡፡ ዋጋ ተነጋ ግራችሁ አሁንም ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ ግማሹን በእግር ግማሹን በፒክ አፕ መኪና፡፡ ደረቅ ዳቦ እ ና ውኃ ይሰጣችኋል፡፡ መንገድ ላይ የሚሞቱ ል ጆች ይኖራሉ፡፡ አሸዋውን ማስ ማስ አድርጎ በመ ቅበር ጉዞ መቀጠል ነው፡፡ «በእግር ወይንም በመኪና ስትጓዝ በእንጨት የ መስቀል ምልክት የተሠራበት ነገር ካየህ እዚያ ቦ ታ አንድ አበሻ ስደተኛ ተቀብሯል ማለት ነው፡፡» ብሎኛል ጣልያን ያገኘሁት ልጅ፡፡ «ሰው ከታመ መ እንደ በሽታው ነው፡፡ መጠነኛ ከሆነ በድጋፍ ይሄዳል፡፡ ከባድ ከሆነ ግን ቁርጥ ወገን ያስፈልገ ዋል፡፡ ከቡድኑ ከተቆረጥክ ችግር ስለሚያጋጠም ህ አንዳንዱ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የቂር ቆስ ልጆች ይተዛዘናሉ፡፡ እንዲያውም ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ ተብሎ ተዘፍኖላቸዋል፡፡» አለኝ ሮም ያገኘሁት የአዲስ አበባው የቂርቆስ ልጅ፡፡ አዲስ አበባ ስ ለ ቂርቆስ ሠፈር ልጆች አያሌ አስገራሚ እና አስ ቂኝ ነገሮች እሰማ ነበር፡፡ እዚህ ጣልያን ደግሞ አገር ጉድ የሚያሰኝ ገድላቸውን መስማት ጀም ሬያለሁ፡፡ ሊቢያ ስትገቡ የተቀበሏችሁ አሸጋጋሪዎች ከትሪ ፖሊ አጠገብ የገጠር መንደር ውስጥ በተሠራ አ ዳራሽ አስገብተዋችሁ ይጠፋሉ፡፡ ከዚያ ሌሎች አ ሸጋጋሪዎች ደግሞ ይመጡና «ትሪፖሊ ሩቅ ስለሆ ነ እንድንወስዳችሁ መቶ መቶ ዶላር ክፈሉ» ይሏ ችኋል፡፡ ታድያ የቂርቆስ ልጆች ምን አደረጉ መሰ ላችሁ፡፡ የተወሰኑት ልጆች ሌሊት ተደብቀው ይ ወጡና እግራቸው ወዳመራቸው ሲጓዙ ለካስ ትሪ ፖሊ ቅርብ ነው፡፡ ተመልሰው ይመጡና ሌሎችን ልጆች ነጻ ያወጧቸዋል፡፡ ከእነርሱ በኋላ ለሚመ ጡት ስደተኞች ደግሞ ግድግዳው ላይ በአማርኛ እንዲህ ብለው ይጽፋሉ «እንዳት ሸወዱ፣ ትሪፖ ሊ ቅርብ ነው፡፡ ብር ስጡን ቢሏችሁ አትስጡ፡፡ በዚህ እና በዚያ አድርጋችሁ ጥፉ» ይሄ ማስታወ ቂያ አያሌ ስደተኞችን ታድጓቸዋል፡፡ አይ የቂርቆ ስ ልጆች፡፡ ነፍስ ናቸውኮ፡፡
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
አፍሪካውያን ስደተኞች እንዲህ በተጨናነቀ ሁኔታ፣ በአነስተኛ ጀልባ ታጉረው፣ ሜድትራንያን ባህርን አቋርጠው፣ ጣሊያን ለመግባት ይሞክራሉ
ፎቶዎች- ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር
መመረሽ፣መፈረሽ፣
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
በባህር ተሻግረው ጣሊያን የሚገቡ ስደተኞች በፖሊሶች ከተያዙ ላምፔዱሳ በሚገኘው እስር ቤት ይታሰራሉ
ጣሊያን ላምፔዱሳ የሚገኘው የእስረኞች ማረፊያ ይህን ይመስላል
መደንበሽ ማስታወቂያ
9
ሐበሻዊ ቃና
ትሪፖሊ ገብታችሁ የመርከብ ወረፋ መጠበቅ ነ ው፡፡ ክፉ ፖሊሶች ካገኟችሁ በመኪና ጭነው እ ንደ ገና ወደ ሱዳን ድነበር ወስደው ያሥሯችኋል፡ ፡ እዚያ እሥር ቤቱ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡ እዚያ ም ቢሆን የቂርቆስ ልጆች ካሉ መከራው ይቀልላ ል፡፡ ከእሥር ቤቱ ለመውጣት የገንዘብ ጉቦ ያስፈ ልጋል፡፡ ያንን ደግሞ ለማግኘት ወይ አስቸጋሪ ሥ ራ መሥራት ያለበለዚያም ደውሎ ከዘመድ ማስ መጣት ያስፈልጋል፡፡ እዚያ እሥር ቤት ብዙ ልጆችን ያስፈታ አንድ የ ቂርቆስ ልጅ ነበር፡፡ ሥራ ይወዳል፡፡ ሲጋራ፣ ብስ ኩት እና ሳሙና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ በዚያ እሥ ር ቤት ብዙ ጊዜ የቆየው ሌሎችን ሲያስ ፈታ ገን ዘቡ እያለቀበት ነው ይባላል፡፡ ሌሎች ደግሞ በሌ ላ ነገር ይተርቡታል፡፡ ከእሥር ቤቱ ሊወጣ በር ላይ ሲደርስ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚል ገዥ ሲ መጣ ለርሱ ሊሸጥ እየተመለሰ ነው፡፡ እንዲያው ም አንድ ጊዜ በአጥር ዘለሎ ሊያመጥ ሁሉም ነገ ር ተስተካክሎለት ነበር፡፡ ሊዘልል አንድ እግሩን እንዳሣ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚለውን ሲሰማ ተ መልሶ መጣ ይባላል፡፡ በቤንጋዚ ወደብ አሻጋሪዎች እና ተሻጋሪዎች አ ይገናኙም፡፡ ሃያ እና ሰላሣ ሰው እስኪሞላ የሚመ ዘግቡ ሰዎች አሉ፡፡ የቡድኑ አባላት ሲሟሉ ገንዘ ብ ይከፍሉና ወደሚሻገሩበት ወደብ ይወሰዳሉ፡፡ የመሻገሪያዋ ጀልባ ብዙ ጊዜ ከቆርቆሮ እና ከእን ጨት የምትሠራ ናት፡፡ ለአንዱ ስደተኛ አሻጋሪዎ ቹ የመርከቧን አነዳድ ያሳዩታል፡፡ ትምህርቱ ቢበ ዛ ከአንድ ቀን በላይ አይሰጥም፡፡ ለዚያ መከረኛ «ካፒቴን» የጀልባዋን ኮምፓስ አ ሥረው ካርታውን ያስረክቡታል፡፡ ምግብ እና መ ጠጥ ይጫናል፡፡ እንደ ጀልባዋ ስፋት ከሃያ እስ ከ ሠላሳ ስደተኛ ይሳፈራል፡፡ በሌሊት የጣልያንን መብራት በሩቁ እያዩ ጉዞ ይጀመራል፡፡ አሻጋሪዎ ቹ ጀልባዋ ስትነሣ ይመለሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ዕዳ ው የስደተኞቹ ነው፡፡ ጉዞው እስከ አስራ ሰባት ሰዓት ይፈጃል፡፡ የአን ዱ እግር ከሌላው ጀርባ ጋር ተሰናስሎ ተኮራምቶ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ ሙቀቱ እና ተስፋ መቁረጡ አ
የስደት ዓለም ንዳንዶችን ራሳቸውን ወደ ባሕሩ እንዲጥሉ ያደ ርጋቸዋል፡፡ በተለይም መርከቡ መንገድ ከሳተ፡፡ የሚያስጎበኘኝን የቂርቆስ ልጅ «ለምንድን ነው ጣልያን ውስጥ የቂርቆስ ሠፈር ልጆች የሚበዙ ት፡፡ እንዲያውም ሮም ውስጥ የቂርቆስ ልጆች ብ ቻ ያሉበት አንድ ሕንፃ አሳይተውኛል፤» አልኩና ጠየቅኩት፡፡ «ምናልባት የሱዳን ኤምባሲ ሠፈራ ችን ውስጥ ስለሆነ ይሆናል በሱዳን በኩል እያቋ ረጥን የመጣነው» አለና ቀለደብኝ፡፡ «ቆይ ግን ለ መንገዱ ብዙ ዶላር ያስፈልጋል ሲባል ነበር የም ሰማው፤ እንዴት ነው ጉዳዩ» አልኩት፡፡ «ቂርቆ ስ የድኻ ሠፈር ነው ብለው ስማችንን ያጠፉት ኮ የቦሌ ልጆች ናቸው፤ እነርሱ አውሮፕላን ሲያ ዩ ስለሚውሉ የገዙ እየመሰላቸው ነው፤ እንዲያ ውምኮ መንግሥት ሀብታም ገበሬዎችን ብቻ ሳ ይሆን እኛንም መሸለም ነበረበት፤ የመረጃ እጥረ ት ነው» አለኝ፡፡ «እንዴት?» አልኩት፡፡ «እስኪ ተመልከት እኛ የ ቂርቆስ ልጆች የመንግሥትን እጅ ሳንጠብቅ፤ አነ ስተኛ ፣ጥቃቅን ሳንል፤ ራሳችንን በራሳችን ረድተ ን እዚህ መድረሳችን አያሸልመንም» አለና ሳቀ፡፡ «ሀብታም ገበሬዎች ራሳቸውን ቻሉ እንጂ የሕዝ ብ ቁጥር አልቀነሱም፤ እኛ ግን ራሳችን ንም ቻል ን፣ከሀገር በመውጣታችን ደግሞ የሕዝብ ቁጥር ቀነስን፡፡ ከዚህ በላይ ምን የሚያሸልም ነገር አለ፡ ፡ አየህ እኛ እንደ ቦሌ ልጆች ጆግራፊን በቲቪ ሳ ይሆን በተግባር ነው የምንማረው» «ደግሞምኮ የአባቶቻችንን ደም የመለስን እኛ ነ ን» አለኝ እየሳቀ፡፡ «እንዴት?» «ጣልያን ባሕር አቋርጦ ሀገራችንን ወረረ፡፡ እኛ ደግሞ የአባቶቻችንን ደም ለመበቀል ባሕር አቋር ጠን ሀገሩን ወረርነዋ፤ አንተ ቂርቆስኮ የጀግና ሠፈ ር ነው» አለና ሳቀ፡፡ «እውነት ግን ለምንድን ነው የቂርቆስ ልጆች እ ዚህ የበዛችሁት?» «ምን መሰለህ ይህንን በረሃ ለ ማቋረጥ ከሁለት እስከ ሦስት ወር ይፈጃል፡፡ የ ገንዘብ፣ የምግብ፣ የውኃ ችግር አለ፡፡ ካልተዛዘ ንክ በቀር ይህንን በረሃ ልታልፈው አትችልም፡ ፡ እኛ ደግሞ ከልጅነታችን ተዛዝነን መኖር ለም
ደናል፡፡ ስለዚህ እየተደጋገፈክ መጓዝ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ባሕር ኃይልም አየር ኃይልም እየመጣ ይቀጥላል» «የቀድሞ ወታደሮችም ይመጣሉ ማለት ነው» «አይ እነርሱ አይደሉም፡፡ በአውሮፕላን ጣልያን የገባው ስደተኛ አየር ኃይል ይባላል፡፡ በባሕር የ ገባው ደግሞ ባሕር ኃይል ይባላል፡፡ ታድያ አየር ኃይሉ ባሕር ኃይሉን ይንቀዋል፡፡» «ለምን?» «ያው መከፋፈል ለምዶብን ነዋ፤ አታ ይም መንገድ ላይ እንኳን ጉስቁል ያለ አበሻ ካዩ ሰላም አይሉንም፡፡ ጣልያኖች እንደሆኑ አየር ኃ ይልም ሆንክ ባሕር ኃይል ሚኒስትር አያደርጉህ ም፤ ሁሉም ያው ሲኞራ ቤት ነው የሚሠራው፡፡ «ሲኞራ ቤት ደግሞ ምንድን ነው?» «ሰው ቤት ተቀጥሮ መሥራት ማለት ነው፡፡ እዚህ ብዙው አ በሻ እንደዚያ ነው የሚሠራው፡፡ ያውም ለሴቶች እንጂ ለወንዶች ሥራ አይገኝም፡፡ ድድ ስታሰጣ መዋል ነው፡፡» «ግን ምን ላይ እየኖርክ ድድ ታሰጣለህ» አልኩ ት፡፡ «እዚህ አበሻ ከድንኳን ሰባሪነት ወደ ሕንፃ ሰ ባሪነት ተሸጋግሯል» «እንዴት እንዴት ሆኖ» «ያ ንን ሁሉ በረሃ አቋርጠህ፤ ባሕር ሰንጥቀህ ጣልያ ን ስትገባ ምንም ነገር አታገኝም፡፡ ከምግብ በቀር ቤት እንኳን የሚሰጥህ የለም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ መ ጠለያ ውስጥ ያስገቡህና በኋላ ሠርተህ ብላ ብለ ው ያሰናብቱሃል፡፡ ያን ጊዜ ችግር ውስጥ ትወድ ቃለህ፡፡ አበሻ ታድያ ይሰባሰብና በልዩ ልዩ ምክን ያት የተዘጋ ሕንፃ ያስሳል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ሁኔታው ን ታይና ሃያ ሠላሳ ሆነህ በሩን ሰብረህ ትገባለህ፡፡ ከዚያ ክፍሎቹን መከፋፈል ነው፡፡» «ባለቤቶቹስ» «ባለቤቶቹ ኡኡ ይላሉ፡፡ ፖሊስ ይመጣል፤ ግርግር ይፈጠራል፡፡ የሰው ልጅ ሜ ዳ ላይ ወድቆ እንዴት ሕንፃ ተዘግቶ ይኖራል ብለ ህ ትከራከራለህ፡፡ መቼም የሰው መብት በመጠኑ ም ቢሆን የሚከበርበት ሀገር ነውና የሰው መብት ተከራካሪድር ጅቶችም አብረውህ ይጮኻሉ፡፡ በ መጨረሻ ታሸንፍና ትኖርበታለህ፡፡»«መብራት እ
ወደ ገጽ 21 ዞሯል
10
ሐበሻዊ ቃና
ጥበብ
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ጄነፌር ሎፔዝ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ፊልም እየሰራች ነው
ከ
ዝነኛው አቀንቃኝ ማርክ አንቶኒ ጋር ለሰባት አመታት የነበራትን ትዳር በ ማፍረሷ እና በአሜሪካን አይዶል ዳኝ ነቷ ምክንያት የብዙሃን መገናኛን ቀል ብ ስባ የከረመችው ድምጻዊት እና አክተረስ ጄኔፈ ር ሎፔዝ ሰሞኑን ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ስሟ ተደ ጋግሞ ይነሳ ይዟል፡፡ ጄነፈርን ከኢትዮጵያ ጋር ያገ ናኛት የፊልም ስራ ነው፡፡ “ዘ ባክ አፕ ፕላን” የተሰ ኘውን ሮማንቲክ ኮሜዲ ፊልም ከሰራች በኋላ ከስ ክሪን ርቃ የነበረችው ጄነፈር አሁን “ሁዋት ቱ ኤ ክስፔክት ሀዌን ዩ አር ኤክስፒክቲንግ” የተሰኘ ፊል ም እየሰራች ነው፡፡ የፊልሙ ርዕስ የተወሰደው በመ ላው ዓለም 16 ሚሊዮን ኮፒ ያህል በመቸብቸብ የ ምርጥ መጽሀፍት ዝርዝር ውስጥ ካለው እና እርጉዝ ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምክር ከሚሰጠ ው መጽሐፍ ነው፡፡ የፊልሙ ታሪክም ከእርጉዝ ሴ ቶች ጋር ይይዛል፡፡ ፊልሙ ወላጅ ለመሆን በመዘጋጀት ላይ ስላሉ አራ ት ጥንዶች የሚተርክ ነው፡፡ ጄነፈር ከባሏ ልጅ ማ ግኘት ባለመቻሏ ጉዲፈቻ ፍለጋ ዓይኗን ወደ ኢትዮ ጵያ የምትጥል እንስት ሆና በፊልሙ ላይ ትጫወታ ለች፡፡ የፊልሙ አዘጋጆች ጄነፈር ከኢትዮጵያ በጉዲ ፈቻ የምትወስድበትን ትዕይንት ለመቅረጽ ወደ ኢ
ትዮጵያ ለመሄድ አልመረጡም፡፡ ይልቅስ እዚያው አሜ ሪካ አትላንታ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚመስል ቦታ ገንብ ተው ቀረጻውን አካሂደዋል፡፡ ለዚህ ትዕይንት ሲባልም የ ፊልሙ ሰሪዎች በርካታ ኢትዮጵያውያንን በአጃቢ ተዋ ናይነት ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥተው ነበር፡፡ በማ ስታወቂያው መሰረት በፊልሙ ላይ መሳተፍ ከቻሉ ሰዎ ች ውስጥ አትላንታ የሚገኘው የአድማስ ሬድዬ አዘጋጅ ቴዎድሮስ አንዱ ነበር፡፡ ቴዎድሮስ አዲስ አበባ በሸገር ኤፍ ኤም ለሚተላለፈው “ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም እንደተናገረው ቀረ ጻው ባለፈው አርብ ሐምሌ 29 ቀን የተካሄደ ሲሆን ከ ቀኑ ስምንት ሰዓት እስከ ለሊቱ ስምንት ሰዓት ቆይቷል፡፡ በፊልሙ ላይ በእውኑ ዓለም አትላንታ ላይ ፓስተር የሆ ኑ አባት የኦርቶዶክስ ቄስ ሚና ተሰጥቷቸው መስራታቸ ውንም ተናግሯል፡፡ ቀረጻው የተካሄደበት ቦታ ኢትዮጵ ያ ውስጥ የሚገኝ የገጠር አውሮፕላን ለማስመሰል እንደ ተሞከረ አስረድቷል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ከጄነፌር ሎፔዝ በተጨማሪ ካሜሮን ዳያዝ እና ክሪስ ሮክ ይተውኑበታል፡፡ ፊልሙ እ.ኤ.አ በ2012 የእናቶች ቀን በሚከበርበት ሳምንት በግንቦ ት ወር ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይ ጠበቃል፡፡
የታደለ... የማይጣላ ህሊና ያለው! እንዴት የታደለ ነው? ህሊናውን የገደለ ሰው! ማን ሊቀረው? ማን ሊያቅተው? የጉልበቱ መሣሪያ ነው ጊዜ ጉልበቱን እስቲሰብረው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም u
u
u
ምን ይኾን አንድምታው?
ግርማ ተፈራ ካሳ በአዲስ አልበም መጣ ለበርካታ ዓመታት ኑሮውን በለንደን አድርጎ ቆይቶ የነበረው አሁን በሕ
የ “ዴርቶጋዳ” ደራሲ ሶስተኛ ልቦለድ መጽሐፉን ለንባብ አበቃ “ዴርቶጋዳ” የተሰኘውን አነጋጋሪ መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ይስምዐከ ወርቁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ “ተልሚድ” የተሰኘ መጽሀፉን ለገበያ አውሏል፡፡ “ተልሚድ” ከመጀመሪያ መጽሀ ፉ “ዴርቶጋዳ”ም ሆነ ቀጥሎ ካሳተመው ተመሳሳይ ጭብጥ ይ ዞ ካሳተመው “ራማቶሓራ” የቀጠለ አለመሆኑን ይስምዐከ በ መግቢያው ላይ ጽፏል፡፡ የሁለቱ ተከታይ የሆነ መጽሐፍ በመ ጻፍ ላይ እንደሆነም ገልጿል፡፡ “በእርግጥ ይብሰል በማለት እ ጅ ሳበዛበት ከእኔ ጋር ቆየ እንጂ ‘ተልሚድ’ ከሁለቱ ተከታታይ ልቦለዶቼ ቀዳሚ ነበር” ሲል አብራርቷል፡፡ ሁለቱ ተከታታይ መጽሐፍት በሺህዎች የሚቆጠሩ ኮፒዎች እንደተሸጡ ቢነገርም የመጽሐፉ ጭብጥ ግን በሃያስያን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተተችቷል፡፡ መጽሐፍቶቹ የያዙት “የልጅ ሀ ሳብ” ነውሲሉ ያጣጡለትም አሉ፡፡ ይህ ትችት የሸነቆጠው የ ሚመስለው ይስማዕከ ድፍረት የታከለበትን እና ትህትና የለሽ አስተያየቱን አንዲህ ሲል በመግቢያው ላይ አስፍሯል፡፡ “ (ተ ልሚድ) እንክት ብሎ በስሏል ማለቴ አይደለም፡፡ ሆኖም ይህ ችን በትህትና ብልም በዚህች ቀዳዳ ልግባ የሚልን አላስገባም፡ ፡ እንዲህ ባለች የትህትና ቀዳዳ የሚገቡ፣ ቢችሉ መልሰን እን ፍጠርህ የሚሉ ደፋሮች አይታጡም፡፡ ያገኘኝ ሁሉ እንደ እር ጥብ ጭቃ ጠፍጥፎ በራሱ አምሳል እንዲሰራኝ የምፈቅድ አይ ደለሁም” ብሏል፡፡ “ተልሚድ” ቀድሞ የደርግ ወታደር፣ በስተኋላ ላይ ደግሞ ደ ራሲ የሆነን ሰው ዋና ገጸ ባህሪው ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡ መ ጽሐፉ ገበያ ላይ በዋለ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 20 ሺህ ገደማ ኮፒዎች መሸጡን የአዲስ አበባ ምንጮች ለሐበሻ ዊ ቃና ተናግረዋል፡፡ መጽሐፉ የገበያ ዋጋው 40 ብር ነው፡፡
የግጥም ጥግ
ይወት የሌለው የአንጋፋው ድምጻዊ ተፈራ ካሳ ልጅ ግርማ አዲስ አልበ ሙን ባለፈው ሳምንት ለአድማጮች አቀረበ፡፡ “እኔ አይደለሁማ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኸው አልበም በቮይስ ሙዚቃ ቤት አማካኝነት ነው ለገበያ የዋለው፡፡ ግርማ በዚህ አልበሙ “ስራ ፈቶ ሲያሽ” የሚለውን የአ ባቱን ዜማ መልሶ ተጫውቶታል፡፡ ይህ ዘፈን የቀድሞ ለዛውን በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ በማለትም አባቱን በወቅቱ አጅቦት የነበረውን መሐ ሙድ አህመድን አሁንም በድጋሚ እንዲያጅበው አድርጓል፡፡ በሞት የተ ለዩትን እንደእነ ጥላሁን ገሰሰ ያሉትን አጃቢዎች ደግሞ በጎሳዬ ተስፋዬ እ ና ማዲንጎ አፈወርቅ ተክቷቸዋል፡፡ የዘፈኑ አቀናባሪ አበጋዙ ክብረወርቅ ደግሞ ኖታውን መልሶ በመጻፍ እንዲሰራ አድርጓል፡፡ በዚህ ዘፈን ላይ ሳ ክስፎን ተጫዋቹ ያሬድ ተፈራ እና ጊታሪስቱ ፋሲል ውሂብ ተሳትፈዋል፡ ፡ ለ“እኔ አይደለሁማ” አልበም በዕውቀቱ ስዩምን ጨምሮ አሉ የተባሉ ገ ጣሚያን ስራዎቻቸውን እንዳዋጡ የ“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮገራም አዘጋጅ ተወልደ በየነ ተናግሯል፡፡
አዲስ አኩስቲክ ባንድ አልበም ሊያወጣ ነው
በ
1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ ተዝፈነው እስካሁንም ተወዳጅ የሆኑ ዘፈኖችን የቀድሞ ለዛውን ሳይለቅ መልሶ በመጫወት የሚታወቀው “የአዲስ አኩስ ቲክ ፕሮጀክት” ባንድ ስራዎቹን በአልበም አቀና ብሮ ሊያወጣ ነው። ለባንዱ የመጀመሪያ የሆነው እና “ትውስ ታ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አልበም ነሐሴ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ገበያ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል። አልበሙ የጥላሁ ን ገሰሰን “ኡኡታ አያስከፋም”፣ አሊቢራ እና መሐሙድ አህመ ድ የተጫወቱትን “ሃማሌሌ” እና የምኒልክ ወሰናቸውን “ትዝ ታ አያረጅም” እና አንድ የሶማሊኛ ዘፍን ጨምሮ አስር ጥኡመ ዜማዎች የተካተቱበት ነው፡፡ አዲስ አኩስቲክ ባንድ ኤሌክትሪክ የማይጠቀሙ አኩስቲክ የ ሙዚቃ መሳሪያዎችን በሚጫወቱ ሙዚቀኞች የተዋቀረ ነው፡ ፡ የባንዱ መሪ ታዋቂው ጊታር ተጫዋች ግሩም መዝሙር ነ ው፡፡ ግሩም የሸዋንዳኝ ኃይሉን ሙሉ አልበም ያቀነበረም ነ ው፡፡ በባንዱ ውስጥ አኩስቲክ ጊታር እና አኮርዲዮን ለባንዱ ይጫወታል፡፡ ታዋቂው ጊታሪስት ተጫዋች ሄኖክ ተመስገን በ ቤዝ፣ አንጋፋው ድምጻዊ ተጫዋች አየለ ማሞ መለያቸው በሆ ነው ማንዶሊን፣ በህይወት የሌለው የሀገር ፍቅሩ ድምጻዊ ፍሬ
ው ኃይሉ ልጅ ዳዊት በክላርኔት፣ ወጣቶቹ ናትናኤል ተሰማ እ ና ምሳሌ ለገሰ በድራም፣ ከበሮ እና ፐርከሽን ባንዱን ህይወት የሚዘሩበት ናቸው፡፡
ሳሚ እና ካሚሊዮን እንደገና ኤርትራዊው ሳሚ ብርሃኔ እና ዝነኛው ኡጋንዳዊ ዘፋኝ ካሚ ሊዮን ዳግም በነጠላ ዜማ ተጣመሩ፡፡ ሳሚ እና ካሚሊዮን ባ ለፈው ሳምንት በጋራ የለቀቁት ነጠላ ዜማ “ቢዩቲ” ይሰኛል፡፡ ሁለቱ ድምጻውያን ከዚህ ቀደም እንደሰሩት እና ተወዳጅ እን ደሆነው “ክበብዋ” ሁሉ እንግሊዘኛ እና ትግርኛ በማፈራረቅ ነ ው የሚያቀርቡት፡፡ ሃይቅ ዳርቻ ቀረጻው የተከናወነውን ይህን ን ሙዚቃ ዳይሬክት ያደረገው ዲዳክ የሚባል ባለሙያ ሲሆን የካሚዮሊን ድርጅት የሆነው “ሊዮን አይላንድ” ከዝግጅቱ ጀር ባ አለ፡፡ ሳሚ በዚህ ሙዚቃ ቪዲዮው ኤርትራዊ እንስቶችን አ ሳትፏል፡፡ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚወጣው የኡጋንዳው “ዘ ኦ ብዘርቨር” ጋዜጣ የሙዚቃ ቪዲዮውን “እንደ ርዕሱ ሁሉ ቆን ጆ የሆነ ሲል አሞካሽቶታል፡፡
በዘመን ተገፍቶ እምቧለሌ ብሎ ቀንበር ተቆራኝቶ ከ’ርፍ ተዋውሎ ከመሬት ጋር ታስሮ፤ በማቲ ተከቦ በልጅ ተቀይዶ፤በትላንት ተሰልቦ ለዘመናት ሲያዘግም ሲኳትን የመጣው ቢያርስ ቢኮተኩት ከጥግ የማይደርሰው ፤ የሀገሬ ገበሬ የበሮቹ ጌታ የአድባሩ አለኝታ የቤቱ መከታ ከመስኩ መዋሉ ፤ ከመስኩ ማደሩ ከብቱን መከተሉ ጥጃውን ማሰሩ በተስኪያን መሳሙ ጥዋውን ማድረሱ በሰርክ በሰዓታት መቆም መጎንበሱ ምንድን ነው ውጤቱ? በአይናችን ያየነው የዚህ ትሩፋቱ?
ግርማ ተስፋው u
u
u
ፍቺኝ ይወዘውዘኛል ያላጋኛል ምነው ከወዲያ ከወዲህ ማረፊያ እንደጠፋው እንደ በረሃ ርግብ ጨለማ እንደዋጠው ክንፉ እንደረገፈ ልክ እንደ ሌሊት ወፍ ያርደኛል ምነው? ሳልወድ እየሞትኩኝ በናፍቆት ላልቅ ነው። ባልተፈጠርኹብሽ ምነው ባለወቅኹሽ ባይጠራ ስሜ ባልታወቅ ባንቺ - የሚያስብለኝ በዝቶ አንቅሬ እንዳልተፋሽ-አውጥቼ እንዳልጥለሽ የሚያረገኝ ማነው ከፍቅርሽ ቡትቶ? የማላውቀው ፍቅርሽ - ጥሱን ጥቡሳሱን አሸክሞኝ ኖሮ- ለምን አልተውኩሽም? ለምን አትበቂኝም- ለምን አትፈቺኝም? እትብቴን በልተሻል መንታ ወንድሜንም ነጥለሽ ወስደሻል የ‘ንግዴ ልጅ እና እትብቴን ገብሬ ነጻ ካልለቀቅሽኝ ባንቺው ፍቅር አዚም ሁሌም ካታለልሽኝ የኔም ፍቅር ይግባሽ እባክሽን ፍቺኝ። ማስረሻ ማሞ u
u
u
ገመድ ለላሚቱ ለጋው የጭረት ዛፍ ፤ በስለት ተፍቆ ጅማቱ ተፈትሎ ፤ እርስበርስ ተጣብቆ ባንገትሽ ላይ ታስሮ ፤ በእግርሺ ላይ ተጠልቆ ከእበት ካዛባው ጋር ፤ አብሮሽ ተጨማልቆ ...መሄድሽን ለማቆም ፤ ተጣብቆሽ ቢውልም ገመድ አሰረ እንጅ ፤ ታሰረ አይባልም። በይርጋ ገላው
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
11
ሐበሻዊ ቃና
አዳም ረታ ይናገራል
ጥበብ
ስድስት መጽሐፍትን ጽፏል፡፡ “ማህሌት”፣“ግራጫ ቃጭሎች” ፣ “አለንጋና ምስር” ፣ “እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ” እና “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ይሰኛሉ፡፡ የተለያዩ ደራሲዎችን ስራዎች በያዘው “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ልቦለዶች” ውስጥም የእርሱ ስራዎቹ ተካትተዋል፡፡ አዳም ረታ ይባላል፡፡ የ52 ዓመቱ አዳም ከአገሩ ከወጣ በኋላ ለረጅም አመታት በሆላንድ እና ካናዳ ኖሯል፡፡ አዲስ አበባ እያለ እና ወደ ውጭ አገር ከሄደ በኋላ የጻፋቸው ታሪኮች በየዓመቱ ልዩነት ታትመው ለንባብ እየበቁ ይገኛሉ፡፡ የራሱ የሆነ የአጻጻፍ እና የአተራረክ ስልት የሚጠቀመው አዳም በቅርቡ ወደ አገር ቤት ተመልሷል፡፡ ወደ አዲሳባ መምጣቱን አስመልክቶም የስነ ጽሁፍ ባለሙያዎች በስራዎቹ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡበት ውይይት ተካሂዷል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አዳምን በጽሁፎቹ እና በፎቶ ብቻ የሚያውቁት አድናቂዎቹ ከእርሱ ጋር የመገናኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡ የሰሞኑ መወያያ ሆኖ የከረመው አዳም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ በቀረቡለት ጥያቄዎች ላይ ተንተርሶ ረዘም ያለ ጽሁፍ ከሚኖርበት ካናዳ ልኮ ነበር፡፡ አዳም በብዕሩ ስለራሱ የተናገረውን ለዚህ ጋዜጣ በሚስማማ መልኩ አሳጥረን አቅርበነዋል፡፡
ፎቶ- ኢዮብ ምህረተአብ
ጅማሬ አምስተኛ ከፍል እያለሁ በትምህርት ቀን መጨ ረሻ አርብ አርብ ከሰአት በኋላ ተማሪዎች ሪፖር ት እናቀርባለን፡፡ ደንቡ ከጋዜጣ ያነበብነውን ወ ይም ከሬድዮ የሰማነውን በራሳችን አማርኛ አሳ ጥረን ፅፈን ክፍል ውስጥ ቆመን ማንበብ ነው፡፡ ሁልጊዜ የምናቀርብባቸው ዝርዝር አርዕስቶች ታ ዲያ የጃንሆይ ጉብኝት፣ የአዲስአባ አንደኛ ዲቪ ዚዮን እግር ኳስ ጨዋታ ውጤትና የመካከለኛ ው ምስራቅ ግጭት ነበሩ፡፡ በእነዚህ አርዕስት ሚ ሊዮን ሪፖርቶች ነው የፃፍኩት ማለት እችላለሁ፡ ፡ ባይሆንም እንደዛ ተሰማኝ፡፡ በዚህ ሰበብ ሰለቸ ኝ፡፡ እግር ኳስ እወዳለሁ ግን ስፅፈው ሰለቸኝ፡፡ ሰለቸኝ ስልህ ቀላል አይደለም፡፡ አሁን ድረስ የእ ዚያ ደለል አልፎ አልፎ ይሰማኛል፡፡ የተለመደው አርብ መጣና ሬድዮ አዳምጬ ወይም ጋዜጣ አ ንብቤ ሪፖርት ማቅረብ ነበረብኝ፡፡ ያው ስለተሰ ላቸሁ አልፅፍም ብዬ ለራሴ ወሰንኩ፡፡ ከቤቴ ወ ደ ትምህርት ቤት ስሄድ (በዚህ ውሳኔዬ መንስኤ ስለማደርስብኝ የቅጣት ስታይል እያሰብኩ) አን ድ አስቂኝ ነገር መንገድ ላይ ታዘብኩ፡፡ የሆኑ ዶ ሮ ነጋዴዎች አንድ ድልድይ አጠገብ ቆመው እያ ለ አውሎ ነፋስ (ጠሮ) ተነስቶ ሲያተራምሳቸው ና ዶሮዎች ከቅርጫቶቻቸው አየበረሩ ሲወጡባ ቸው፣ እነሱን ለመያዝ ሲወድቁና ሲነሱ አየሁ፡፡ ያ ን የመሳሰለ፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ጉዳይ፡፡ መሃል መ ንገድ ትምህርት ቤት ሳልደርስ ‘ለምን ይሄን መን ገድ ላይ ያየሁትን ሪፖርት አላደርግም?’ አልኩ፡፡ ምክንያቱ፣ ገጠመኙ ጨዋታ አለው፡፡ አስፈግጎኛ ል ወዘተ...፡፡ መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ የማስታውሰ ውን ሁሉ ሉኬ ላይ ሞልቼ ክፍሌ ገባሁ፡፡ ተራዬ ደርሶ አንብብ ስባል በትምክህት ከጋዜጣ ላይ ያ ገኘሁት ነው አልኩና ቆሜ የፃፍኩትን አንቸለቸል ኩ፡፡ ክፍሉ ትንሽ ተዝናና፡፡ አስተማሪዬ ግን ጨ ርሼ ስቀመጥ ‘ጢሜን’ አበረሩኝ፡፡ «ይሄን ከጋዜጣ ላይ ያነበብከው?» አሉኝ፡፡ «አዎ» «እንዲህ አይነት ወሬ ጋዜጣ ላይ አይወጣም፡፡ ራስህ ያደረግከው ነው» አሉኝ፡፡ ያልተገነዘብኩት ነው፡፡ ቀሽምነቴ ነው፡፡ መዋሸ ት አልችልም፡፡ «አዎ» አልኩ፡፡ ከዛ ወደ ክፍሉ ዞር አሉና «አዳሙ ደራሲ ይሆናል» አሉ፡፡ ደራሲ እራሱ በትክክል ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ አስተማሪ ዬ ለምን ከጋዜጣ እንዳልገለበጥኩ አልጠየቁኝ ም፡፡ በትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉአልገባኝ ም ነበር ያኔ፡፡
አዳም ከረጅም ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ ያገኙት አድናቂዎቹ ፊርማውን በመጽሀፍቶቹ ላይ እንዲያሰፍርላቸው ተሻምተዋል
ስልቹው አዳም
ቃላት ወስደህ እነሱን ጠፍጥፈህ ኮሳሳ የሆነች የ ራስህን መጠለያ ታበጃለህ፡፡ ዙሪያህን ከሚነፍሰ ው የማይመች ዶፍ ተጋርደህ የትም ባይደርስም ነፃነትህን ታውጃለህ፡፡ ደራሲ ገና ብዕሩን ሲያነሳ ወደደም ጠላም ገባው ም አልገባውም በዚያን ጊዜ ‘ጎታች’ ነው ብሎ ለ ተሰማው፣ መሆኑን እንኳን ባላወቀው ነገር/እሴት ላይ ተቀናቃኝ ነው (subversive)፡፡ መሰላቸት ወደ ተቀናቃኝነት፣ ተቀናቃኝነት ወ ደ መድረስ ወሰደኝ? የምክንያት ግኑኝነት ይኑራ ቸው እንጃ፡፡ ይሄ በልጅነቴ የበቀለው ነገር ሳድግ አበበብኝ? እንጃ፡፡ በተጨማሪም ገና በልጅነቴ አ ንዳንድ ነገሮች መፃፍ ስለጀመርኩ ያኔ መፃፍ ጥ ሩ ነው ብሎ የነገረኝ ሰው ይኑር አይኑር ወይም ደ ስ ብሎኝ እንደዛ ለመፃፍ በራሴው ልነሳሳ አላው ቀውም፡፡ እላይ ካነሳሁልህ አይነት መሰል ሳያባሩ ከኖሩ ገጠመኞች የተጠፈጠፈም ላይሆን ይችላ ል፡፡ ይሄን የሚፃረሩ ሌሎች ገጠመኞች ቢኖሩም ረስቸአቼው ይሆናል፡፡
እዚህ ላይ ቀላል ብትሆንም ሳከብራት የኖርኩት ን ትዕዛዝ ጥሼ ስፅፍ ከውስጤ የተሰማኝ ነገር ቢ ኖር ነው፡፡ ያ የተሰማኝ ነገር ስልቹነት ሳይሆን አ ልቀረም፡፡ የእኔ አንዱ የበላይ ጠባቂ ማን መሰለ ህ? የመሰላቸት ስሜት፡፡ እንዳንድ ሃያሲያን ስል ቹነት የፈጠራ ስራ እንድትሰራ ይተነኩሳል ይላ ሉ፡፡ Boredom provokes. ምናልባት ይሄ መሰላቸት የመጣው የምኖርበት ሕብረተሰብ ሁለንተና በሕግ የተሳሰረ፣ በአመክን ዮ የተታመ፣ መነሻውንና መድረሻውን ቀድሞ የ ደነገገ፣ ባለው አቅም በደንብ የተደራጀ ስለሆነ ይ ሆናል፡፡ በረባም ባልረባም ጉዳይ ከመስመር አ ውቀህም ይሁን ሳታውቀው ብትወጣ የሚሰጥህ ምላሽ አድማ ይመስላል፡፡ አንደኛው ‘ሰው ምን ይላል?’ ነው፡፡ ይሄ ምድርን ይቆጣጠራል፡፡ ሁለ ተኛው ‘እግዜር ይይልህ’ ነው፡፡ ከመሃል አንተ ነ ህ፡፡ በዚህ አጣብቂኝ መሃል ምን ታደርጋለህ? የ ተቃርኖዎች ሕግ ማማሩ ያው የሚያሽህ ሕብረተ ሰብ በፈጠረው ቃልና ሰዋሰው ቢያንስ አእምሮሀ ን ነፃ ታወጣለህ፡፡ ያው ሕብረተሰብ ካሳደጋቸው
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስገባ መፃፍ እፈ ልጋለሁ ግን ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ደቃቃ ዕ ውቀት የለኝም፡፡ ጥያቄው እዚህ ላይም ይመጣ ል፡፡ ለምን ለመፃፍ እርሳስ ይዤ ቁጭ አልኩ? ም ን ነገረኝ? ምናልባት ሃሳቤን እንዳልገልፅ የሚያስ ረኝ አካባቢ ነበርኩ (ለምሳሌ ማሽሟጠጥ) እን ጃ፡፡ ማንም ደራሲ በል ተቀመጥና እንዲህ አድር ገህ ፃፍ አላለኝም፡፡ ታዲያ ለመፃፍ ስቀመጥ በትክከል ምን ማድረግ እንደሚገባኝ አላውቅም፡፡ ድርሰት መጀመሪያ ማ ዕከልና መጨረሻ አለው ይላሉ፡፡ መለስተኛ ሁለ ተኛ፣ ሁለተኛ ደረጃም ትማራለህ፡፡ ይሄ ራሱ አ ይገባኝም ነበር፡፡ አንድ ነገር መቼ ነው እንዴት ነ ው ማዕከል የሚሆነው? እላለሁ፡፡ እንዴት ነው የ ምትፅፈው? ለምንና መቼ ትጨርሰዋለህ? እንዴ ት ትጀምረዋለህ? የምትጀመረው በምን ነው? መ ፃፊያ ጉዳይ የት ታገኛለህ? ልፈታው የማልችል ቋ ጠሮ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ቢሆኑ ም መልስ የሚሰጥህ የለም፡፡ መልስም የሚገኝለ
የመጽሐፍት ዓለም
ት አይመስልም፡፡ ዕደሜዬ 13 እያለ (አልረሳውም) አንድ ቀን የታ ደሰ ሊበን ‘ጅብ ነች’ የተባለው አጭር ታሪክ ክፍ ል ውስጥ በአስተማሪያችን ተነበበ፡፡ በታሪኩ አ ጨራረስ ልረሳው የማልችል መደነቅ ተሰማኝ፡፡ እንዲህ ነው የሚፃፈው አልኩ፡፡ በትንሹ የነቃኁ ት ያኔ ይመስለኛል፡፡ ቆይቶም ታደሰ ሊበን ይዞኝ አልሄደም፡፡ ምክንያቱም ልጅ ነህና ትረሳለህ፡፡ ዛ ሬ ምን-ምን ታሪኮች ከእሱ እንዳነበብኩ ትዝ የ ሚሉኝ ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ከዛ የቀረኝ አምልኮ የአንዱ መፅሐፍ አርዕስት ብቻ ነው (ሌላው መን ገድ)፡፡ እንደዛ የሚያምር አርዕስት በአማርኛ ስነ ፅሑፍ እስከዛሬ አላጋጠመኝም፡፡ በሁለት ቃላት ቀውስና እርጋታ (chaos and order) ተጠቅልለ ው ተቀምጠዋል፡፡ ይሄን አርዕስት ሲሰሙ አይኖ ቼ ዕንባ ቢያቀሩ አይግረምህ፡፡ በዛን ጊዜ ያላነበብኳቸው የአማርኛ ልብወለድ መፃሕፍት አልነበሩም ማለት እደፍራለሁ፡፡ ቢረ ቡም ባይረቡም፡፡ ቢደነቁም ባይደነቁም፡፡ አነባ ለሁ እንጂ የስነፅሑፍ አለም ይኑር አይኑር አላው ቅም፡፡ በታሪኩ እደሰታለሁ ወይም እደበራለሁ እንጃ? ለምን? እንዴት? የመሳሰለ ትንተናም አላ ደርግም፡፡ ምክንያቱም አልችልም፡፡ ትንተናም አ ላነበብኩም፡፡ አልተማርኩም፡፡ “ራሴላስ”ን ትም ህርት ቤት እንዳነበብን ትዝ ይለኛል፡፡ በዝርዝር ግን አላስታውስም፡፡ ባስታውስ ደረቅ ፍልስፍና መሆኑ ነው፡፡ ከዛ በኋላም አላነበብኩትም፡፡ ያንጊዜ አካባቢ በእንግሊዘኛ የግሪክና የሮማን ሚቶሎጂ፣ የተለያዩ አገር ተረቶች (ጀርመን፣ እ ንግሊዝ፣ ጃፓን፣ ቻይና ወዘተ.....) አነባለሁ፡፡ የ ትምህርት ቤታችን ቤተመፃሕፍት ከሲታ ቢሆን ም እነዚህ አይጠፉም፡፡ በካሪኩለም ከተደነገጉል ን ከ“ራሴላስ”፣ ከ“አርአያ”፣ ከ“እንደወጣች ቀረ ች” ከከበደ ሚካኤል የ“ሮሚዮና ጁሊየት” ትርጉ ም የበለጠ እነዚህ ተረቶች ይመስጡኝ ነበር፡፡ በ ዚህ ዘመን ውስጥ የመጀመሪያ የእንግሊዘኛ ልብ ወለዴን አነበብኩ፡፡ ‘ዘ ዊዛርድ ኦፍ ኦዝ‘ የሚባ ል፡፡ ይሄም ረዥም ተረት በለው፡፡ ፋንታሲው ል ቤን ሰውሮት ነበር፡፡ ተረትና ሚቶሎጂ ስለምወ
ድ (ያን ጊዜ ብዙ ልዩነታቸው አይገባኝም) እንደ እነሱ ለማድረግ አስራ አምስት አመት ሳይሞላኝ ብዙ ተረቶች ፅፌ ጠፍተውብኛል፡፡ ለዚህ ስራዬ በተለይ የሶስት ወር የክረምት እረፍት ሙሉ ነፃነ ት ይሰጠኝ ነበር፡፡ በትምሀርት ጊዜ ስፅፍ ከያዘኝ አባቴ አይፈቅድም፡፡ ብዙ ዕውቀት በንባብና በማዳመጥ ከሌሎች ት ሰበስባለህ፡፡ በሬድዮ ድርሰትና ተረት ሲነበብ ት ያትር ሲሰራ ትሰማለህ፡፡ የሉተራን ብስራተ ወን ጌል ሬድዮ ጣቢያ ነበረ በዚህ የማልረሳው፡፡ በተ ጨማሪም በዛን ጊዜ ብዙ ባይባሉም የትርጉም መ ፃሕፍት ነበሩ፡ ‘እንደ ሰው በምድር እንደአሳ በባ ሕር’፣ ‘ሳይላኩ የቀሩ ደብዳቤዎች’ (አርዕስቱን ል ክ ነኝ?) ‘ታራስ ቡልባ’ የመሳሰሉ፤ ሁለት ሶስቴ የ ምታነባቸው እንደ ‘ዛዲግ ወይም ዕድል’ (ቮልቴየ ር) ‘ሞንተክሪሰቶ ካውንት’ የመሳሰሉ፡፡ ባጠቃላ ይ ይሄን ይመስላል፡፡ ያልተቀናበረ ያጋጠመኝን መፅሐፍ ብዙ ጊዜ በ መዋስ የማነብበት ወቅት ነው፡፡ ከፈጣን ፍስሃ በ ላይ አትሄድም፡፡ ይሄ ደሞ በተራራቀ ጊዜ ስለሚ ሆን ማንበብህንም ባትረሳውም ምን እንዳነበብክ ግን ልትረሳው ትችላለህ፡፡ ያገኘሁትን በማነብበ ት በራሴ ልብወለድ የማፍቀር ልፋት ውስጥ ሰር ጎ ገብቶ ስርአት የሚያስዝልኝ መሰረተ ልማቱ አ ልነበረም፡፡ ቢኖርም እንዳለ አላውቅም፡፡ (ደስታ ተክለወልድ የሚባሉ ታላቅ ሊቅ እንዳሉ ያወቅሁ ት በ1970 ዎቹ መሃል ከአስራ አምስት አመታት በኋላ ነው) የሚያሳዝን ነገር አለው፡፡ በግል የማ ውቀው ደራሲም ይሁን በማንበብ እንዲህ አድር ግ ብሎ የመከረኝ ሰው አልነበረም፡፡ እንደዛሬ ተ ሰባብሰቦ መነጋገሪያ ቦታና ጊዜ ነበር? ቢኖርም አ ላውቅም፡፡
የመንፈስ አባቶች የማነበው መፅሐፍ ካጣሁ ብዙ ጊዜ በክረምት ዘነበወርቅ ከብስራተወንጌል ሬድዮ ጣቢያ ጀም ሮ(ሰፈሬ እዛ ነበር) እስከ ብሄራዊ ወመዘክር ድ ረስ በእግር ሄጄ መፅሐፍ የማነብበት ጊዜ ነበር፡፡ ዝናቡ ይደብራል፣ የሰፈርህ ሜዳ ጭቃ ነው ኳስ አታለፋም፣ ተሰላችተሃል፡፡ አንብበህ ወደ ቤትህ
ስትመለስ፣ አእምሮህ ውስጥ የሚንሳፈፈው ልብ ወለድና ፋንታሲ ብቻ አይደለም፡፡ በካፊያ መበስ በስህን ማማረር፣ ማታ ተኝተህ ‘እዛ ድረስ ምን አ ስለፋኝ?’ እያልክ ራስህንም መቀናቀንህ ነው፡፡ ል ብስህ ቆሽሿል፣ ያለካልሲ ያደረግከው ሸራ ጫማ ረጥቦ፣ እግሮችህ ጨቅይተው እውስጡ ይንሸራ ተታሉ፡፡ እግርህን ታጥበህ መተኛት አለብህ፡፡ እ ና በርዶሃል፡፡ እንደበረደህ አትናገርም ምክንያቱ ም ‘ጥጋበኛ’ ትባላለህ፡፡ ከዚህ ነው የወጣኸው፡፡ በፀጥታ ወደ ራስህ ገብተህ ፔርሱስ አንድሮሜዳ ን እንዴት ደራጎኑን ገሎ ከሰንሰለቷ ነፃ እንዳወጣ ት ታስባለህ (በኋላ ከርሞ ከርሞ ይሄ የግሪክ አም ላክ ቅዱስ ጊዩርጊስ እንደሆነ አንድሮሜዳም ብሩ ታዊት እንደሆነች ተረዳሁ)፡፡ ዝናብ፣ ለምሳ ስለ ጠፋህና ልብስህ ስለቆሸሸ በወላጆችህ መተረብ፣ እና የመንፈስ አባቴ ይሄ ነው፡፡ እግረመንገድህን ልብ ሳትል በማንበብ ሂደት የ ምትማራቸው አስፈላጊ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ለምሳ ሌ አንዳንድ መፃሕፍትን ለማንበብ የቃላት ሃብት ግድ ይላል፡፡ ከፍቅር እስከመቃብር (ፍእመ) የተ ማርኩት አንዱ ትልቁ ነገር ቃላት ነው፡፡ ቃላቱ ይ ከብደኝ ነበር፡፡ እና ስራዬ እሱን ሳነብ ቃላት እየለ ቀምኩ ለብቻ እያወጣሁ አባቴን መጠየቅና ማጥ ናት ነበር (አባቴ የዲማ ሰው ነው)፡፡ ‘ዋሽንት’ ለ ማለት ‘አንዲር’ ይላል ፍእመ (ያኔ ‘ለምን አንዲር ይላሉ? ዋሽንት አይሉም?’ እል ነበር ‘ለምን ቀላል አያደርጉትም?’ ግን ይሄ ከቀላልና ከከባድነት ጋር አይያያዝም)፡፡ ከዚህ በኋላ ወጣ ብለህ ማዘጋጃና ብይ ትጫወታለህ፡፡ በአይንህ ቂጥ ሚንስከርት ያ ደረገች የጋሼ ማንትስ ልጅ ስታልፍ ታያለህ፡፡ እ ትዬ ወርቄ አስነጥሶአቸው ሲምሉ ትሰማለሀ፣ ፍ ስሃና አብዱራህማን ከቤት ጀርባ ተደብቀው ሲጋ ራ ይለምዳሉ፣ እነዚህ የትዕምርት ግጭቶች ናቸ ው ራሴን የሰጡኝ፡፡ አእምሮህ በልቦለድ ገፀባህር ያት ተመስጦ እያለህ የምትቀሰቀሰው ግርማ የተ ባለ ልጅ ኳስ ሲደርብህ ነው፡፡ ይሄ ብውዝ ነው የመንፈስ አባትህ፡፡ ዩንቨርሲተ ስገባ በትርፍ ጊዜዬ አነባለሁ፡፡ የተገ ኘውን እሞክራለሁ፡፡ ግን ይሄ ደራሲ ደስ ብሎኛ ል ብዬ የፃፋችውን ሁሉ ላነብ አልነሳም፡፡ ምክን ያቱም የዩንቨርሲቲው ኬኔዲ ላይብረሪ መፃሕፍ ት መደርደሪያ አለም የተሰበሰበበት ነው፡፡ አዳል ተህ አትችልም፡፡ በዚያ ዘመን ዛሬም ደጋግሜ ባ ነባቸው ቅር የማይሉኝ ጥሩ ደርሰቶች አንብቤአ ለሁ፡፡ የብርሃኑ ዘሪሁን “የቴዎድሮስ ዕንባ”፣ የበአ ሉ “ከአድማስ ባሻገር”ና “የሕሊና ደወል”(ሃዲስ) ልብወለዶች፣ “እሳት ወይ አበባ” ፣ የዳኛቸው “እ ምቧ በሉ ሰዎች”ና “አደፍርስ”፣ “ልጅነት”፣ የፀጋ ዬ “እሳት ወይ አበባ”ና “የከርሞ ሰው” የመሰሉ ድ ራማዎች የሰይፉ መታፈሪያ “አፈር ያነሳ ስጋ”፣ የ ደበበ ግጥሞች ወዘተ፡፡ የማነበው ግን የፈጠራ ስ ራዎችን ብቻ ነው፡፡
የአብዮት ጊዜ አብዮት ሲመጣ(እንዲመጣ ሲደረግ) ልብወለ ድ መፃሕፍት ቢረባም ባይረባም በፓምፍሌት ተተኩ፡፡ መጀመሪያ ሰሞን ደስ የሚል ነገር ነበረ ው፡፡ ምክንያቱም አዲስ ነው፡፡ (እዚህ ዘመን ላይ ቦታ ስለማይበቃን ልዝለለው እንጂ በሰፊው የም ለው ኑዛዜያዊ ግለሂስ ነበር) ብዙ ሳልቆይ ሲጀመ ር መሰላቸቴን ያጠፋው የመሰለኝ ለአብዮት/ለት ግል ማሟያ የተፈጠረው ስነፅሁፍ ወደ አሰልቺ ነ ገር ተለወጠ፡፡ ከላይ ያነሳሁልህን ‘ሰው ምን ይላ ል’ ና ‘እግዜር ምን ይላል’ ን ፖለቲከኞች ከሕዝብ ነጥቀው ‘ድርጅቴ ምን ይለኛል?’ በሚለው ተኩ ት፡፡ እግዚአብሄር ከስልጣን ወረደ፡፡ ባህላዊው የ ተባለው ሕብረተሰብ ኋላቀር ነው ተባለ፡፡ እግዚ
ወደ ገጽ 13 ዞሯል
12
ሐበሻዊ ቃና
ጥበብ
ዘጠና ቀናት በጆበርግ
ኡጋንዳ ካምፓላ ቺቲንታሌ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የ ሚገኘው እና “ቨርጅን አይላንድ” የሚል ስያሜ የተሰጠ ው መዝናኛ ቦታ ዘወትር እሁድ ምሽት በሰዎች ይሞላ ል። “እንቅልፍ በማይተኛባቸው” አርብ እና ቅዳሜ ስራ የሚበዛበት “ቨርጅን አይላንድ” ላለፉት ሶስት ወራት በሰ ንበት ምድርም አያርፍም። ምክንያቱ ደግሞ ደቡብ አፍ ሪካ ጆሃንስበርግ ከሚገኝ አንድ ትልቅ ግቢ ሃያ አራት ሰ ዓት ሙሉ በቀጥታ የሚተላለፈው የ“ቢግ ብራዘር” የቴ ሌቭዥን ፕሮግራም ነው። በጎጆ ቤት መልክ የተሰራው ይህ መዝናኛ ቦታ በሁለ ት ተቃራኒ ጥጎች ላይ ካንጠለጠለው ፍላት ስክሪን ቴሌ ቪዥኖች ባሻገር አንዱን ግድግዳ አቡጀዲ አልብሶ ፕሮ ግራሙን በፕሮጀክተር አማካኝነት በትልቁ ያስተላልፋ ል። “ቨርጅን አይላንድ” ሌሎች መዝናኛ ቦታዎች እንደ ሚያደርጉት የቴሌቪዥን ምስሉን እያሳየ ድምጹን አይነ ፍግም። ለዚህም ይመስላል የፕሮግራሙ “ቁርጥ ቀን” በሆነው እሁድ ዕለት በርካቶች ወደ እዚህ መዝናኛ ቦ ታ መሄድ የሚመርጡት። እሁድ በመላው አፍሪካ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፕሮግራሙ ተከታታዮች በሚሰ ጡት ድምጽ ከተወዳዳሪዎች መካከል የሚባረረው የሚ ታወቅበት ነው። የመጨረሻው የ“ቁርጥ ቀን” በ“ቨርጅን አይላንድ” ልዩ ነ በር። ከ14 ሀገራት የመጡ 26 ወጣቶችን በአንድ ግቢ በ ማሰባሰብ ከዛሬ ሶስት ወራት በፊት የተጀመረው ይህ ፕ ሮግራም በየሳምንቱ እሁድ ከተወዳዳሪዎች መካከል በ ድምጽ የተፈረደባቸውን እያባረረ ለመጨረሻው ዕለት የ ደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር። ለመጨረሻ ው ዙር ካለፉ ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል የኡጋንዳ ተ ወካይ መገኘት ጉዳዩ የብዙዎችን ትኩረት እንዲስብ አድ ርጓል። ዕለታዊ የሀገሪቱ ጋዜጦች እና ኤሌክትሮኒክስ ብ ዙሃን መገናኛዎች ስለተወካያቸው “ሻሮን ኦ” ሳምንቱን ሙሉ ጽሁፎች ሲያስነበቡ፣ የሀገሬውም ሰው ድምጽ እ ንዲሰጣት ሲቀሰቅሱ ከርመዋል። ተከታታይ ዘገባዎቹ የፈጠሩት ትኩሳት በርካቶች ለጉዳ ዩ ትኩረት እንዲሰጥ አደረገ። “ኦብሴሽን” የተሰኘው ዝነ ኛ የሙዚቃ ቡድን አባል የሆነችው ተወካያቸውን መጨ ረሻ ለማየትም በየመዝናኛ ቦታዎች ተሰበሰቡ። በ“ቨርጅ ን አይላንድ” የፕሮግራሙን ማጠናቀቂያ ለመመልከት የ መጣው ተመልካች ከመብዛቱ የተነሳ መቀመጫ ሁሉ ጠ ፍቶ ነበር። በቦታው የነበረው ድባብ ካምፓላ በዓለም እ ግር ኳስ ዋንጫ የመጨረሻ ቀን ያሳለፈችበትን ጊዜ ያስ ታውሳል። ይህ ግን ለኡጋንዳውያን አንድን ዓለም አቀፍ አሊያም አህጉር አቀፍ ውድድር ከመመልከት የዘለለ ነበ ር። የትም አትደርስም ብለው የገመቷት የሀገራቸው ልጅ ከመጨረሻዎቹ ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል መገኘቷ ለ ሀገራቸው ክብር እና ኩራት እንዲጨነቁ አድርጓቸዋል።
ሃኒም እንደ ዳኒ? እንደ ኡጋንዳዊቷ ሻሮን ሁሉ ኢትዮጵያዊቷ ሃኒም ሳት ጠበቅ ነበር ለመጨረሻ ዙር የደረሰችው። የሀገሯ ልጅ ዳ ኒ በውድድሩ አጋማሽ ላይ መሰናበቱ የእርሷም እጣ እን ደእርሱ ይሆናል ተብሎ ተገምቶ ነበር። በኡጋንዳ ዕለታ ዊ ጋዜጣ “ዴይሊ ሞኒተር” ላይ ስለ የ“ቢግ ብራዘር” ተ ከታታይ ዘገባዎችን የሚያወጣው ሮበርት ካሉምባ ሃኒ ለ መጨረሻው ውድድር ሳትደርስ እንደምትባረር ተንብዮ ነበር፡፡ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሃኒም ቆን ጆ ነች ብሎ የሚያምነው ካሉምባ ጠንካራ ጎኗ በውይይ
ቶች ላይ በደንብ መሳተፍ መቻሏ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ከዚያ ባሻገር ግን እንደ ዳኒ ሁሉ በአፍሪካውያን ተመልካ ቾች የሚፈለገውን “እብደት” እና “ወሲብ ቀመስ” ትዕይ ንቶችን አለማሳየቷ እንደሚጎዳት ገምቶ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳ እንግሊዘኛ ቢናገሩም ቋ ንቋው የአፍ መፍቻቸው ባለመሆኑ እንደሌሎቹ እንደል ብ ሀሳባቸውን ለመግለጽ የሚከብዳቸው ናቸው ብሎ ያ ምናል፡፡ ይህንንም ዳኒ ሆነ ሃኒ ላይ ማስተዋሉን ይናገራ ል፡፡ በእነዚህም ምክንያቶች ኢትዮጵያውያን ወደራሳቸ ው መሰብሰብ ወይም ቁጥብ መሆን እንደሚያዘወትሩ ያ ስረዳል፡፡ ይህ በተመልካች የማይወደድ በመሆኑ ዳኒ ለ መባረር መብቃቱን ሃኒም ተከታይ እንደምትሆን እርግ ጠኛ ነበር፡፡ ስለ “ቢግ ብራዘር” የሚዘግቡ የተለያዩ ድረ ገጾችም ይህንኑ ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ የካሉምባም ሆነ የድረ ገጾቹ ግምት ግን አልሰራም፡፡ በፕሮግራሙ አሰራር መሰረት ተወዳዳሪዎቹ እርስ በእ ርስ በሚሰጣጡት ድምጽ ከውድድሩ እንዲባረሩ የሚፈ ልጉትን ይጠቁማሉ፡፡ ለመባረር በዕጩነት የሚቀርቡ ተ ወዳዳሪዎች ሳምነቱን ሙሉ በተመልካች ድምጽ እንዲሰ ጥባቸው ይደረጋል፡፡ ዘወትር እሁድም የሚባረረው ይ ለያል፡፡ ሃኒ በተደጋጋሚ ለመባረር እጩ ሆና ቀርባለች፡ ፡ ሆኖም በአብዛኛው ከኢትዮጵያውያን ተመልካቾች በ ምታገኘው ድምጽ ስትተርፍ ቆይታለች፡፡ ለመጨረሻው ሳምንት ውድድር ለማለፍ በተደረገው ትንቅንቅም የሆነ ው ይሄ ነው፡፡ ሃኒ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል የሚባረረ ውን መጠቆም አልፈልግም ብላ እራሷን ለዕጩነት ብታ ቀርብም የሀገሯ ዜጎች ድምጽ ሰጥተው ለመጨረሻው ዙ ር አሳልፋዋታል፡፡
የመጨረሻው መጨረሻ ለመጨረሻ ዙር ያለፉት ሃኒን ጨምሮ ሰባት ተወዳዳሪ ዎች ነበሩ፡፡ ካረን አን ቪና የተሰኙት ሁለት ናይጄሪያው ያን እንስቶች፣ አልቃሻው እና አወዛጋቢው ደቡብ አፍሪ ካዊ ሉክሌይ፣ ጎረቤቱ ዜምባቢያዊ ዌንዳል፣ ያያትን ሁ ሉ የሚወድ የሚመስለው የማላዊ ዜጋ ሎምዌ እና ምን ም አታውቅም ተብላ በሀገሯ ሰዎች ሳይቀር የምትሸነቆ ጠው ሻሮን ኦ ከሃኒ ጋር ለመጨረሻ ውድድር ያለፉ ናቸ ው፡፡ እነዚህ ተወዳዳሪዎች ለመጨረሻው ዙር በመድረ ሳቸው ብቻ 10 ሺህ ዶላር ይሰጣቸዋል፡፡ ሳምንቱን ሙ ሉ ከተመልካች በተሰበሰበ ድምጽ ከፍተኛውን ቁጥር ያ ገኙት ሁለት ተወዳዳሪዎች ደግሞ 200 ሺህ ዶላር ወ ደ ኪሳቸው በማስገባት የአሸናፊነት አክሊል ይደፋሉ፡፡ ከውድድሩ ማጠቃለያ አስቀድሞ በተሰበሰበ የህዝብ ድ ምጽ መሰረት ሃኒ ዝቅተኛውን ድምጽ በማግኘት መጨ ረሻ ሆና ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ደረጃዎች የተ ቆጣጠሩት ደግሞ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ብዙ ድራማ መሳይ ትዕይንቶችን ሲያሳዩ የከረሙት ናይጄሪያዊቷ ካ ረን እና ደቡብ አፍሪካዊው ሉክሌይ ነበሩ፡፡ ውጤቱ ሐ ምሌ 24 ይፋ ሲደረግ ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፡፡ ሃኒ እንደተገመተው መጨረሻ መሆኗ ቀርቶ ናይጄሪያ ዊቷን ቪናን በልጣ ስድስተኛ ሆነች፡፡ ያሸንፋል ተብሎ የተገመተው ሉክሌይ ደግሞ ደረጃውን የግል አውሮፕላ ን አብራሪ በሆነው ዜምባቤያዊው ዌንደል ተነጠቀ፡፡ ደ ቡብ አፍሪካውያን ያዩትን ማመን አልቻሉም፡፡ ውድድ ሩ በሀገራቸው የሚካሄድ ለስለነበር በ“ቢግ ብራዘር” ስ ቱዲዮ የተገኙት በርከት ብለው ነበር፡፡ በሉክሌይ መሸነ ፍ ቁጣቸውን የገለጹት ታዲያ መድረኩ ላይ በመውጣት
ጭምር ነበር፡፡ ግርግሩ የበረደው ፖሊስ በስፍራው ደር ሶ ካስታገሳቸው በኋላ ነበር፡፡
አወዛጋቢው ውጤት ውጤቱን ያጣጣሉት ግን ደቡብ አፍሪካውያን ብቻ አልነበሩም፡፡ ሌሎች አፍሪካውያንም የሉክሌይ መሸነ ፍ አልተዋጠላቸውም፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆ ነው ታዋቂው የኡጋንዳ ስታንድ አፕ ኮሜድያን ዳንኤ ል ኦማራ ነበር፡፡ በናይጄያዊቷ ካረን ማሸነፍ የሚስማ ማው ኦማራ ሉክሌይ ሶስተኛ መውጣት አልነበረበትም ባይ ነው፡፡ “ በካረን መሸነፍ ላይ ችግር የለበኝም፡፡ እር ሷ ለውድድሩ የሚሆን ሰብዕና እና አመለካከት አላት፡፡ ነገር ግን ከእርሷ ጋር ማሸነፍ የነበረበት ሉክሌይ ነው” ለ ሐበሻዊ ቃና ተናግሯል፡፡ “አስቀድሞ የሚገመት ነገርን አ ልወድም፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ነገሮች ግልጽ የሚሆኑበ ት ጊዜ አለ” ሲል የደቡብ አፍሪካዊው ለአሸናፊነት ያደርጋቸው የነበሩ ትዕይንቶች በግልጽ የሚታዩ እንደነበር ያብራራል፡፡ ሃኒ ልክ እንደ ስሟ “ጣፋጭ” ነበረች የሚለ ው ኦማራ በቆይታዋ መደሰቱን ይገልጻል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ስድተኛ መውጣቷን ሲመ ለከት የሀገሩ ልጅ ሻሮንም ብዙ እንደማ ትራመድ መገመቱን ይናገራል፡፡ “እንደ ሃኒ አይነት ሴት እንዲህ አይነት ደረጃ ከሰጡ ሻሮንም ብዙ እንደማትቆይ ገም ቼ ነበር” ይላል፡፡ ግምቱ ትክክል ነበር፡ ፡ ኡጋንዳዊቷ ሻሮን ከሃኒ ከፍ ብላ በ አምሰተኛነት ውድድሩን ጨርሳለች፡፡ “ሃኒ ጥሩ ሰብዕና ያላት፡፡ ነገር ግን በ ቢግ ብራዘር አፍሪካውያን ድምጽ የ ሚሰጡት ጥሩ ላልሆኑ ሰዎች ነው፡፡ የ ናይጄሪያ ወይም የሌላ አፍሪካ ሀገር ፊ ልሞችን ብትመለከት ብዙ ጩኸት፣ ለ ቅሶ፣ ውዝግቦች እና ጥሎች የተሞላ ሆ ኖ ታገኘዋለህ፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ካረ ን ልታሸነፍ የቻለችው” ሲል የናይጄሪያ ዊቷን አሸናፊ ሞገደኛ ባህሪ ዕርጋታ ከነ በራት ሃኒ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ በኋላ ሃኒን በ ደቡብ አፍሪካ ያገኘቻት ኡጋንዳዊት ጋዜ ጠኛ ኒጄል ናስርም በኢትዮጵያዊቷ መደ መሟን ለሐበሻዊ ቃና ገልጻለች፡፡ የውድ ድሩን ማጠናቀቂያ ለመዘገብ ደቡብ አፍሪ ካ ተገኝታ የነበረችው የ ኡጋንዳው ዕለታዊ ጋዜጣ “ኒው ቪዥን” ዘጋቢ ናይጅል በቲቪ ታያት በነበረችው እና በአካል ባገኘቻት ሃኒ መካከል ልዩነት ማየቷን ትናገራለች፡፡ “በአ ካል ስታገኛት እንድትግባባት የሚገፋፋህ የ ሚስብ ነገር አላት፡፡ በቲቪ ከምትጣው ይል ቅ በአካል ይበልጡኑ ተግባቢ ናት” ትላለች፡ ፡ ሃኒ የምትናገራቸው ቁም ነገሮች ከህግ ተ ማሪነቷ ጋር ተዳምሮ ከሌሎች ለየት እንደሚ ያደርጋት ናይጅል ታስረዳለች፡፡ “ ሌሎች ተ ወዳዳሪዎች ስለሀገራቸው ከሚያውቁት በላ ይ ሃኒ ስለ ሀገሯ ጠንቃቃ ታውቃለች” ስትል የኢትዮጵያዊቷን ጉብዝና ትመ ሰክራለች፡፡
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
አዳም ረታ ይናገራል...
ማስታወቂያ
ከገጽ 13 የዞረ
የገባቸው? እንደ አቤ ጉበኛ እንደ ሃዲስ አለማየሁ ያሉ ደራስያን ነበሩ፡፡ ‘አድሃሪ’ በተባለ ቃል ተቀ ንብበው እንዲሰወሩ ሆነ፡፡ የገባው ጥቂት ነው፡፡ አዲስ የነበሩት ‘የትግል’ ቃላቶች አውዳቸው ቀ ስበቀስ መለወጥ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ክሊ ሼ ሆኑ፡፡ ቦታው በሸርና በሴራ ምናብ ተወሰደ፡ ፡ ግጥም በጣም አፈቅር ነበር፡፡ ቀላል ፍቅር አል ነበረም፡፡ ግጥም ካየሁ የፖለቲካ ካምፕ አልለይ ም ነበር፡፡ ያኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማድረግ ፍ ርድቤት ሳትሄድ ያስቀጣሃል፡፡ ትክክል ሆነም አ ልሆነም በራስ መረጃ ያለመነቃነቅ የባርነት መሰ ረት መሆኑን በጭላንጭልም ቢሆን የምትረዳው ያኔ ነው፡፡
እንቅፋቱ መአት በነዚህ ሁሉ ሳልፍ ተከትሎኝ የመጣ ደራሲ አል ነበረም፡፡ ምናልባት በዛን ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔ ታ የሚያብራራ ልብወለድ የፃፈ ቢኖር ኖሮ ልከተ ለው ምክንያት ሊያሳድገኝም መንደርደሪያ ይኖረ ው ነበር፡፡ ግን የትኛውም ልብወለድ በስሜት ህ ዋሳቶቼና በሕልሞቼ ከለቀምኳቸው እኩል አልነ በሩም፡፡ ሁልጊዜ በቃል ልናገረው የማልችል ነገ ር አለ፡፡ ደራሲዎቹ ሁሉ ቢዘሉም ባይዘሉም የሆ ነ ነገር የሚዘሉ ይመስለኛል፡፡ በሆነ መልክ የእኔ አይደሉም፡፡ ምናልባትም የልጅነት ልምዴ ጥቅ ጥቅ (intense) ወይም ‘ልዩ’ ስለነበረ ይሆናል፡፡ ስራ ስገባ እንደ ጠበቅሁት አልነበረም፡፡ በሙያ ዬ አንድ ነገር ለመስራት እለፋለሁ፡፡ ግን እንቅፋ ቱ መአት ነው፡፡ አፍጥጬ እያማሁ መቀመጥ አ ልወድም፡፡ በስፋት ማንበብ የጀመርኩት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ አንደንዴ በማንበብ ላይ እያለ ሁ የልጅነቴን የተረት ድርሰቶቼን እያሰብኩ ለም ን እንደዛ ጊዜ አልዕፍም እላለሁ፡፡ ግን ጊዜዬን የ ኑሮ እንቅፋትና ቸልተኛ የሚያደርግ መዝናናት ይ ሻማኛል፡፡ ማምለጥ ነበረብኝ፡፡ ሁልጊዜ ‘ምናለበ ት ብፅፍ?’ እያልክ መኖር አትችልም፡፡ መፃፍ ከጀመርኩ በኋላ ስራ ላይ ባጋጠመኝ ቀ ናሽ ልምድ ድርሰቶቼ ይታተማሉ ብዬ አስቤ አላ
ፎቶ- ሪፖርተር ጋዜጣ
አብሄር ቢሞትም የነበረው ቢናቅም ቦታውን የነ ዚህን ሁለት ስራ መስራት እንችላለን የሚሉ ድር ጅቶች ወሰዱት፡፡ በልጅነቴ ያስደስተኝ የነበረው ግን ልብ ያላልኩ ት ያለማንም ቁጥጥር ማሰብ መፈለጌ ከፈተናው አላመለጠም፡፡ እንደውም ፈተናው በፒር ፕሬዠ ር (peer presure)ታጠቀ፡፡ በተለያየ አቅጣጫ የአብዮቱ ግራኞች (ተቃዋሚ የሚባለውም ሁሉ ም) ደራስያንና ድርሰትን አጥፍተው ነው ለተሰ ሚነት የሰሩት፡፡ ማለት ከ “ኢማጂኔቲቭ ሊትሬ ቸር” ወደ ፕሮፓጋንዳ ተሄደ፡፡ ቀደምት ደራሲ ያን በተለያየ ስየማ እየተቀነበቡ (ፍሬምድ አየሆ ኑ) ዝም እንዲሉ ሆነ፡፡ የዚያን ጊዜ ድርሰቶች/ግ ጥሞች በአብዛኛው ፕሮፓጋንዳ ነበሩ፡፡ ፕሮፓጋ ንዳ ታዲያ ብዙ ጊዜ ስለአለቀ እውነት ደጋግሞ የ ሚያወራ ነው፡፡ ፖርኖግራፊክ ነው፡፡ በተቃራኒ ው የፈጠራ ደራሲና የፈጠራ ድርሰት ቢዋጣም ባይዋጣም በምናባቸው አማራጭ ማሕበራዊ አ ሴት ያሳያሉ፡፡ የፀጋዬ ገብረመድህን ግጥሞች ከፀጋዬ ደብተራ ው ግጥሞች የበለጠ ደስ ይሉኛል ካልክ ባንዳ ነ ህ፡፡ በተገላቢጦሽ ካልክ አናርኪስት ነህ፡፡ የፈለ ከውን የወደድከውን ለመውደድ በየትም አቅጣ ጫ መናገር የማትችልበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሄን የተ ረዳሁት ረቂቅ ፈላስፋ ስለነበርኩና ሁሉ ነገር ስለ ገባኝ አልነበረም፡፡ ተደጋግሞ ስሰማውና በቀጥታ ና በተዘዋዋሪ ስከለከል ሰለቸኝ፡፡ በቀጥታም ይሁ ን በተዘዋዋሪ መከልከል ይሰለቻል፡፡ ልክ ተደጋግ ሞ እንደተጠጣ አጃ ወይም ጠዋትና ማታ እንደ ተበላ ካሮት ወይም የፈለግከውን፡፡ ምናልባት የገ ጠመኝ የተለየ ነገር ይሆናል፡፡ የሩስያ ልብወለድ ካነበብክ፣ የደባሪ ሩስኪ(ሶሻል ኢምፔሪያሊዝም) ታነባለህ፣ የአሜሪካን ደራሲ ካነበብክ በኢምፔሪ ያሊዝም ልትለከፍ ነው፡፡ ወይም ጆሊ ጃክ ነህ፡፡ ዋናው ማንበብህ አሳስቧቸው ሳይሆን የዛን ዘመ ን ትውልድ ለማጥፋት ሆነ ብለው ታጥቀው የተነ ሱ ሰዎች ያሉ ይመስላል፡፡ ማን ገባው? ምናልባት
13
ሐበሻዊ ቃና
አዳም ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በቅርቡ ባደረገው ቆይታ 3 ሺህ ገጽ የሚፈጅ መጽሀፍ ጽፎ እንደጨረሰ ተናግሯል
ውቅም፡፡ ምክንያቱም ያለሁበት የኑሮ መስመር ውስጥ የእንቅፋት ኪነት የሚሰሩ ይሄንንም እን ደልዩ ሃብት(ውርስ) የሚቀባበሉ ስለነበሩ ነው፡ ፡ ይሄ የደርግ ወይም የኢሰፓ ስርአት ነው ብዬ አ ላሳብብም፡፡ ማንም የተዘፈቀበትና ማንም ከማን ም የሚጋሩት መጣኝ ባህል ነው፡፡ የሚሰድበው ን ካልሰደብክለት፣ የሚያማውን ካላማህለት ታላ ቅ እውነት እንደተበላሸበት ሁሉ ቅር የሚለው ብ ዙ ነው፡፡ ምቀኝነትና እንቅፋትነት በፖለቲካ አጀ ንዳ ስር ተጋርደው ሕብረተሰቡ ውስጥ የገቡበት ዘመን ነው፡፡ አንዳንዱ ምቀኝነቱን ትግል ነው ቢ ል፣ ይሄንንም አሸሼ እያለ የሚያጅበው መአት ዘ ማሪ ዕንጥል አይጠፋም፡፡ በጂኦግራፊ ሙያዬ ያ ኔውኑ ብቀጥል ኖሮ ምናልባት ብፅፍም ወደ ደራ ሲነት አላጋድልም ነበር፡፡ ብቻ ምን ይታወቃል፡ ፡ ስለዚህ ለመተንፈስ ወደ ሌላ ተፈጥሮዬ ወደሚ ያዳላበት ወይም ወደ ልጅነቴ ፣ ወደ አደግሁበት ወደነካካሁት ማንም ወደማይነዘንዘኝ ወረቀትና ብዕር ዞር አልኩ፡፡
ጠረጴዛ ላይ የተኛ ነጭ ልሙጥ ወረቀትና እላዩ ላይ ተቀርፆ የተጋደመ እርሳስ እጅግ ማራኪ ምስ ል አላቸው ለእኔ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሬ ስራ እስክይዝ ድረስ እየሰራሁ ም እያለሁ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር የተለወጠ ቢመስልም የብዙ ነገሮች ውስጠት እንዳልተለወ ጠ ነበር፡፡ መአት ሰው በተከታታይ ሕይወቱ ያል ፍና ግን እንቅፋትነት እነበረችበት ኩርሲ ላይ ጥ ርሷን እየፋቀች ተቀምጣለች፡፡ አንደ ምሳሌ አድርጌ አንድ በደራሲዎች የተዘለ ለ ሴማ ባነሳ እወዳለሁ፡፡ በሃይለስላሴ አስተዳደ ር የወጣቶች አንዱ ባህርይ እርስ በርስ የመተማ መን ነበር፡፡ የሃይለስላሴ/ ፊውዳል ስርአት ለዛን ጊዜ ታዳጊ ትውልድ የሰጡት ትልቅ ስጦታ የመ ተማመን ካፒታል ነበር፡፡ ይሄ ስጦታ ከስድሳ ስድ ስት በኋላ በመጡ ፖለቲካና ፖለቲከኞች በተለያ ዩ የድርጅቶች ምሕፃር ስር እየተሸነሸነ ጠፋ፡፡ ይ ሄን የጠፋ ካፒታል ወደ ነበረበት ለመመለስ በተ ለያየ መልክ የተቀናበሩ የኑዛዜ ልብወለዶች ትል
ቅ ማዕከል ሆነው ማገልገል ይችሉ ነበር፡፡ ግን አ ልሆነም፡፡ እንዲህ የሆነበት ምክንያት እንደሚመ ስለኝ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ስላሌሉ ሳይ ሆን ሆን ተብሎ እንዲጠፉ/እንዲገለሉ ስለተደረገ ነው፡፡ ራሱን ከታሪክ አውጥቶና እንዳልነበረበት ሁሉ ተነጥሎ ስህተተኛነትና ሐጢያተኛነትን ወደ ሌላ የሚያሸጋገር የናስ (escapegoat) ባህል ሌላ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ይሄ ፓቶሎጂ ዛሬም ድረ ስ አለ፡፡ ስለ እኔ ጥሩ ካልጣፍክ በነገር እጥፍሃለ ሁ የሚል ድርጅት እንደ አፈር ነው፡፡ ከተናዛናዥ ሃያሲ ከመሰሉ ግለሰቦች ጀርባ በአጎዛ ተጋርዶ ያ ሌለ የሚመስል ሁልጊዜ ምላሱን እንደ እርሳስ እየ ቀረፀ የተቀመጠ ድርጅት አለ፡፡ ልበልህ በዛን ሰሞን የዚህ አይነት ድርሰቶች ቢያ ጋጥመኝ ያ ደራሲ ደፋር ጭብጥ አንስቷልና ላመ ልከው ወይም እሱን ለመምሰል እጥር ነበር፡፡ በ ዚያ ዘመን እስከዛሬ ባነባቸው ቅር የማይሉኝ ጥሩ ደርሰቶች አንብቤአለሁ፡፡ ግን ጥቂት ናቸውና ያ ልቃሉ፡፡ ሃያሲ አይደለህም፡፡ ስታነባቸውም አት ኖርም፡፡ ብዙዎቹ የሚያጋጥሙኝ የማይመስጡ ናቸው፡፡ የምልህ ዛሬ ሳነብ ልጅ ሆኜ ያነበብኩት ከመሰለኝ አርፌ ጠላ አልጠጣም? እድሜህ አስር ሳይሞላ የሰማኸውን የሳቅህበትን የአለቃ ገብረሃ ናን ቀልድ እያዳነቀ የሚንከተከት በእድሜ የአንተ እኩያ የሆነ የሰላሳ አመት ሰው ሲያጋጥምህ ያኔ ሆ ስፒታል ውሰዱኝ ትላለህ፡፡ ከስራ ውጭ ባለኝ ጊዜ የእንግሊዘኛ ትሪለር (thriller) ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ቀስ በቀስ ሳይን ስ ፊክሽን፡፡ ብዙ ባይሆንም ‘ስነፅሁፍ’ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በተፅዕኖ ደረጃ (ማለት ቢያንስ በጉዳ ይ) ሊኖርብኝ ይገባ የነበረው ሳይንስ ፊክሽን ነበ ር፡፡ ግን አይደለም፡፡ ምናልባት የወደድኩት እን ዳሻ ከ ‘ማነብ ነፃነት’ ጋር ስላገናኘኝ ይሆናል፡፡ ይ ሄ ደሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ተረቶች ስለምወድ የእነ ሱም ተፅዕኖ ይሆናል፡፡ ዛሬ እንኳን ሲኒማ በተለ ይ በሲ.ጂ.አይ ከተሰራ (ለእኔ ገነት ነገር ነው) ተሻ ምቼ የማየው ሳይንስ ፊክሽን ነው፡፡ ግን ይሄ ሁ ሉ ከማየው፣ መሬት ላይ እግሬ ስር ካለ ዕውነታ
ወደ ገጽ 21 ዞሯል
14
ሐበሻዊ ቃና
ትረካ
የ
መጀመሪያ ልጃችንን ለመውለድ ሽር ጉድ ትላለች። ዝሆን አክ ላለች። ግራና ቀኝ ጎ ንጮቿ የበሰለ ሾላ መስለዋል። እንደማ ለች ነበረች። ትንሽ ዓለም ሰርታ እኔ፣ እሷና ልጇ ብቻ እንድንኖርባት። በዘ ሮቿ ምን እንደምትባል ስለምታውቅ እንደሆነ የገባኝ በኋላ ነው። አረብ የ ተጫወተባት እንዴት ቀና ብላ ሰው ን ታያለች ይሆን? ከመቅደስ ሁኔታ የተረዳሁት የአረብ ስም እንዲነሳ አለ መፈለጓ ነው። ከአረብ ጠመንጃና ፈ ንጂ እየተቀበሉ ወገናቸውን ሲገሉ ከ ነበሩት የበለጠ ማን ሸርሙጣ አለ? ያውም ነፍስ የሚያጠፋ ሽርሙጥና። መንጌ ዕውነቱን ነበረ እንዴ? ‘የአረብ አገር እግዜር የሌለበት ቦታ ነው’ ትላ ለች። ‘እግዜርን አያውቁም’ ትላለች። እንድጠላት ጠብቀው ይሆን? የወለ ደችልኝን እንድጠራጠር? ሆስፒታል በጀርባዋ ተኝታ ማደንዘ ዣ አሸንፋ የወለደችውን ወንድ ልጅ ነርሷ ክንዷ ላይ ስታሳቅፋት ፊቷ በዕ ንባ ታጠበ። ነርሷ እንደ እህቷ እያባ በለቻት፤ በዚህች የመተዛዘን ትዕይን ት የዳች (ሆላንድ) ሴቶችን ሁሉ ወደ ድኩ። ሚስቴ በአገሯ አሉባልተኞች ተላግጦባት እንደተኛች፣ በአረብ ወን ዶች ሲገሰስና ሲደፈር ከነበረ የነጠፈ ከመሰላት ማሕጸንዋ፣ ከተመሰቃቀለ ዘመን በኋላ፣ ወርቅ የመሰለ ወንድ ል ጅ ተፈልቅቆ ሲወጣ፣ አብራት ያለቀ ሰችው፣ እንግዳ በሆነ መልክ የምጠ ረጥራትና ችላ የምላት የፈረንጅ ነርስ ነበረች። መቅደስን ሳይሆን አቅፌ ለ ማባባል የፈለግሁት ‘አነከ’ የምትባለ ዋን ያቺን የዳች ነርስ ነበር። ያን ዕን ባ የጠረጉ የሚያምር ቀለም የተነከሩ ጥፍሮቿን አልረሳም። ግራና ቀኝ ወ ደ ላይና ወደታች የቆመ ቢጫ ጸጉር ያላትን ልጅ-እግር ሴት አልረሳትም። ትግላችን ከራሴና ከወገኔ ጋር ነበር። ወገኔ ከተባለ። መቅደስ ለምን አለቀሰች? በደከመ ድምጽ “መንገዱ” አለች ኝ። ይሄንንም መልስ አልረሳም። ጉ ዞው። ምጡ አልነበረም። መንገዱ። ወዙን ካጣ ከደረቀ ነፍሰጡር አፏ ይኼ ቃል ወጣ። የተነፈሰ ሆዷን ሳ ምኩላት። ልጁን አቅፌ አልጋዋ ዙ ሪያ መነጽሬ ዘሎ እስኪወድቅ ደነስ ኩ። እርግማናችንን አብረን እንድንሰ ርዝ ላሳያትም ነበር። አነከ ነርሷን ለ እኔም ለመቅደስም ዘመዳችን ሆነች። ለልጃችን ለቶማስ እናት ሁኚው አል ናት። ትንሽ ቤታችን ወስደን እጇን ይዤ በተሰባበረ እንግሊዘኛና ዳች እ ጆቿ የተባረኩ እንደሆኑ ነገርኳት። የ ሰንጋ ተራ ትዕቢቴን ደንሀግ ሆስፒታ ል አንዲት ሴት ፈረንጅ እግር ስር ጣ ልኩ። ልጁ መጀመሪያ የሰማው ድም ጽ ‘የአንቺና የእናቱ ዕንባ ሲወድቅ ነ ው አልኳት። በአስራ አምስት ቀኑ የ ቶማስ እትብት ደርቆ ሲወድቅ ለቅ ሜ ያዝኩት። አስገርዤም ልፎውን ‘ፎርምሊንዲሃይድ’ በተሞላ ትንሽ ብ ልቃጥ አስቀመጥኩት። ጊዜ አልፎ ይሔ ልጅ ሲቆም የደንሀ ግን አየር እየጠባ ከጎሮሮ የሚወጣ ቋ ንቋ ይናገራል። የተሻለ ይማራል፣ ይ በላልም። የሆላንድን ሳቅና ለቅሶ ይኖ ራል። እና እዚህ ይረጋል። የሆላንድ ን ጦርነቶች ሊዋጋ ይወጣል። ሕይወ ት በፍጹም ልምድ ትዋጥና የአባቱን ና የእናቱን አገር ይረሳል። ይፈረድበ ታል? እኛን ያጋጠመችን ዓይነት ነር ስ ያጋጥመዋል፤ ይህችን ትንሽ አገር ም በቀለሙ ይሞላታል። ‘የኢትዮጵ ያ ዋና ከተማ ማነው?’ ተብሎ ሲጠ የቅ በጉብልነቱ ‘ክሎትዛክ’** ቢል ይ ፈረድበታል?
በመቅደስ እየተተቸሁ የልጄን ልፎና እ ትብት መኝታ ቤቴ ሳጥን ውስጥ አስቀ ምጩአለሁ። አልፎ አልፎ እሷ በሌለች በት ከተደበቁበት አውጥቼ የስጋ ቁራጮ ቹ መልካቸው እንዴት እንደተለወጠ አ ጠናለሁ። የስጋ ቁራጮቹ የሚያስተምሩ ኝ ነገር ቢኖር እንግዳ በሆነ መልክ ተስ ፋ እንድቆርጥ ነው። ከዕለታት አንድ ቀን የመቅደስ እናት በ ጠና እንደታመሙ የሚነግር ደብዳቤ ደ ረሰን። በጋራ የደረሰን ወሬ ይኼ ነው። በግል ስልክ በቅሎ ቤት እናቴ ጋር ስደ ውል የተነገረኝ ከዚህ ዓለም በሞት መ ለየታቸውን ነው። ‘በቃ እንደተኙ ቀሩ?’ ‘ግራ የሚያጋባ ዘመን ነው፣ ጋደም ብሎ መሞት? በትንታ መሞት ድሮ ሰምቼ አ ላውቅም፣ እንዲህ ያለ ለነጋሪ ያስቸገረ ነ ገር፣ ወጣቱማ ረገፈ ረገፈ ልጄ፤ እሳቸ ውማ ከታመሙ ከረሙ እኮ፣ ከረሙ። ውስጣቸውን የሚበላ ነገር ነበር። አይ ናገሩ አይጋገሩ። እሳቸው ነፍሳቸውን ይ ማር እንጂ ያው መቼም።እናንተስ? ልጁ ስ? ማን ነበር ስሙ ልጄ፣ ያ ጓደኛህ ማ ሞ ልጅ ወለደ እኮ! በዚህ ሲሄድ በዚህ ይመጣል። መጣጣፍ አቆማችሁ? አሁን እሷ መሞቷን እንዳትነግራት። ብቻ ከቻ ላችሁ ይዘሃት ና። ካልቻላችሁ ያው በአ ገሩ ደንብ ፈረንጅ አገር አርዳት?’ እንደሞቱ ባልነግራትም መሞታቸውን ጠርጥራ ‘ለማንኛውም ልያት’ ብላ ተነሳ ች። አነከን ከተዋወቅናት ጀምሮ መቅደ ስ የምትሄድበት የዳች ሪፎርም ቤተክር ስቲያን የትኬት ወጪዋን ቻሏት። አፍ አ ውጥታ አትንገረኝ እንጂ ‘ታመሙ’ ብዬ ከነገርኳት ጀምሮ ልጇን እያጠባች ባዶ አየር ውስጥ ዕንባ ባቀረሩ አይኖቿ ታፈ ጥ ነበር። ‘ልጁን ይጎዳዋል’ እንኳን ብላ ትም እህል የመብላት ወስፋቷ ተቆረጠ። ድብን ባለ ሌሊት ተነስታ ‘ልጁን አለቀሰ ብኝ ላጥባው’ ብላ በማመሃኘት ማድ ቤ ት ገብታ ስታለቅስ ሁለት ሶስቴ አግኝቼ አታለሁ። ያፈላሁትን ቡና ሳትጠጣው (‘ቡናና ፍቅር በትኩሱ ነው’ ብላ እንዳ ልተረተች) ያልተቀመሰለት የቀዘቀዘ ቡ ና ከፊቷ አነሳለሁ። ‘እማማ ቶማስን ሳታየው’ በሚል የእሮ ሮ ሽፋን፣ የግል ለቅሶዋን ታለቅሳለች። ይኼ ቁጭቷ የወጣላት መቃብራቸው ን ሳታይ ነው። የመቃብር ሲሚንቶው ላ ይ ወደቀች። ነጠላዋን ግራና ቀኝ ዘረጋ ች። በዚያ ጸጥታ ሰው ባልነበረበት ባሜ ኬላና በሌሎች ሙታን መሃል እርሟን አ ወጣች። ፊቷን በጥፍሮቿ ቀደደች። ጸጉ ሯን በጭብጥ ከአናቷ ላይ ነጨች። ከራ ሷ ቁጣ ላድናት ስይዛት ትግሌን እየጣሰ ች። ወደ እናቷ መቃብር እየቀረበች እ የተጠጋች እንዲህ እንዲህ እያለች ልቤ ን ሰበረችው። ‘እኔ ነኝ የገደልኩሽ!’ ‘እማማ እኔ ነኝ ሐጢያተኛዋ!’ ‘ተቃጥዬ ያቃጠልኩሽ!’ ‘እኔ የማልረባ ልጅሽ ነኝ ማሪኝ እማ ማ!” ‘ይቅር በይኝ እማማ አሳልፍልሻለሁ መ ስሎኝ ነው፤ ባላውቅ ነው!’ ‘እማማዬ ብዙ አላውቅም እማምዬ!’ ‘ልደፋልሽ በአንቺ ቦታ!’ ‘ባጠባሽኝ የበደልኩሽ፣ ባጠባሽኝ የራ ቅሁሽ!’ “በጥጋቤ እኔ ነኝ የገደልኩሽ!’ ‘እኔም አልተመቸኝም እኰ!’ ለእኔም ያለቀሰች መሰለኝ። ገና አንድ እግራችን ከአገር ሲወጣ የእናቶቻችን የልብ ምት አፍታ ይወርዳል፣ አዲስ በ ሽታ ይበረታባቸዋል፣ ሊነኩን እጃቸው ን ሲዘረጉ ሲያጡን፣ ጣቶቻቸው በቆፈ ን ይረግፋሉ። ፊቴን በአንድ እጄ ጋርጄ ልቤን በለቅሶ ቀደድኩ…….. ምናለ እነ እንትና ከእሷ ቢማሩ……. እንትና………. ያ…….. ***
* ልፎ በአዳም ረታ (ክፍል ሶስት)
“
እግዚያብሔር አንድ ነው፣ አየህ። ስሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብትል እግዚያብሔር ብትል አንድ ነው። ቅደመ አያቴ እስላም ነበሩ። ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ ክርስትናው ቤታችን ገባ።
አንድ ቀን ሆስፒታል ሆስፒታል በሽ ተኛ ሆኖ ተኝቶ ሚስቴን ‘የአረብ ሸር ሙጣ’ ብሎ ያማት ስልክ ደወለ። ከር ሞ ከርሞ። “ታዲያስ ጠፋህ ምነው?” አፉ ውስጥ ‘ተሳስቼያለሁ’ የሚል ቃ ል የሚወጣበት አይነት ሰው አይደለ ም። ኩፍ ያለ ነው ድምጹ። የሆነ ውስ ጡ ነፋስ ያረገዘ። ‘ደርግን እቃወም ነበ ር’ በተባለ ቋንቋ የተለጠጠ…..ባረጀ በ ሬ የሚንገታገት…… “አልጠፋሁም” “በሽተኛ አንዴ ብቻ ነው የሚጠየቀ ው?” “ልጅ መጣ፣ አልተመቸኝም” “ለመሆኑ ባለቤትህ ደህና ናት?” “ደህና ናት” “ላያት እፈልግ ነበር። በባሕላችን አራ ስ መጠየቅ ይገባታል። በተለይ በስደት ላይ ዘመድ የለ፣ ምን የለ……እኛው ዘ መድ ካልሆንን….” “እሱስ አዎ” “የሚቀጥለው ሳምንት አመጣለሁ” “ያኔ አንኖርም” “እንዴት?” “ኢትየጵያ እንሄዳለን” “ለምን ደህና?” “የመቅደስ እናት ታመዋል” “ለማንኛውም ከሰው መውራት ጥሩ ነው……….ነገ ብቅ እላለሁ” ምን ማለት ነው ማውራት ጥሩ ነው ማለት? እምቢ አላልኩትም። ማለት ይገባኝ ነ በር። ግን የአዲስ አባ ማህበራዊነቷና ሰውን አለመደበር ገና ከደም ስሬ ተቀ ርፎ ተንጠፍጥፎ አልወጣም። መቅደስ በሸቀች። “ማንም ሃበሻ ደጄ እንዳይደርስ” “ሊጠይቅሽ ነው፣ ለሌላ ነገር አይደ ለም” “አሁን አንድ ነገር ውሰድልኝ ሊልህ ነ ው። ራሱ አይልክም? የሰለለበትን ገን ዘብ ምን ያደርገዋል? አታምነኝም እን ጂ አገር ቤት እንደምንሄድ ሰምቶ ነው ‘ልምጣ’ የሚለው” “ምን? ማን ይነግረዋል? ለማን ነግረ ሻል?” “ለማንም። ግን ያውቃሉ እንጃ። እና ቴ ምን እንደታመመች በዝርዝር ያው ቃል ይሄኔ” አለች በብስጭት “ከሰው ካልሰማው ታዲያ? ቢሰማ ስ። ከፈለግን ‘ዕቃህን አንወስድም’ ማ ለት እንችላለን” “ይቀፈኛል” “አንቺ ዝም ብለሽ ነው” “ለምን ሙጭጭ ይላል?” “አዲስ አባ እየናፈቀችው ይሆናል” “አውትኬሪንግ አዳክሞት ነገር ነገር እያለው ፖሊተከኛ የሆነ ነው” አልሰማኋትም። በበነጋታው ሲመጣ በፖስታ የታሸ ገ ነገር ለአባቱ እንድሰጥለት ጠየቀኝ። መቅደስን ሳያያት አኩርፋ መኝታ ቤት እንቅልፍ እንደያዛት ሁሉ ተኝታ ቀረ ች። ትንሽ አወራርቶ ቡና ጠጥቶ ሊሄ ድ ሲል፤ ክፉን በክፉ መቃወም ባልፈ
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ልግም “ምንድነው ውስጡ ?” አልኩት። “ስኮች ቴፕ አለህ?” አለኝ ያልጠየቅ ሁትን። “አዎ” ክርታሱን ክፈተና አሳየኝ። “ባታየው አትወስደውም ነበር?” አ ለኝ “አልወስድም። ድራግ ቢሆንስ? እ?” “በዚህ እንኳን አንጠረጠርም” ሁለት ትልልቅ ካፖርቶች ናቸው። ሆ ን ብዬ አተኩሬ አየሁት። ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅሁት መሰለኝ። የአዲስ አባን ትዝታ ከዚህ ሰው ማግኘት እንደማል ችል ገባኝ። በመልሴ የተከፋ አይመሰ ልም፡ ቢገባውም ያልገባው ዓይነት ተ ዋናይ ሆነ። *** አዲስ አባ አስራ አምስት ቀን ያህል ቆ ይተን ለመመለስ ሁለት ቀኖች ሲቀረን ፖስታዬን እና ክርታሴን አንጠልጥዬ እ ንትና በሰጠኝ አድራሻ ታክሲ ይዤ ሄ ድኩ። ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካ ባቢ ነበር። በር ሳንኳኳ የከፈቱልኝ ጥ ምጥም ያደረጉ፣ ጺማቸውን የተላጩ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ገጽ ያላቸ ው መልከ መልካም ጠይም ሽማግሌ ነ በሩ። መምጣቴን ቀደም ብዬ ስልክ ደ ውዬ ነግሬያቸው ስለነበር፣ በስሜ ጠ ርተው በትህትና እንድገባ ጋበዙኝ። ቤ ት ውስጥ እርሳቸውና ፊታቸው ብቻ እስኪቀር የተከናነቡ ሌላ ሴት ነበሩ። ገ ና እንደተቀመጥኩ ራት በልቼ (ማታ ላ ይ ነበር የደረስኩት) እንድሄድ ሲጠይ ቁኝ፣ በስነስርዓት ተከላክዬ ፖስታውን ና ዕቃቸውን በእጃቸው ሰጠኋቸው። ስለልጃቸው ጤንነት ከጠየቁኝ በኋላ የሚያበረታታቸውን መልስ ሰጥቼ ከተ ቀመጥኩበት ስነሳ፣ አንድ የሚያጫው ቱኝ ነገር ስላለ በጥሞና እንድሰማቸው አግባቡኝ እና ተመልሼ በመቻቸት ተ መልሼ ተቀመጥኩ። “እግዚያብሔር አንድ ነው፣ አየህ። ስ ሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብ ትል እግዚያብሔር ብትል አንድ ነው። ቅደመ አያቴ እስላም ነበሩ። ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ ክርስት ናው ቤታችን ገባ። የድሮ ሰዎች ናቸ ው። ለምን? በለኝ። አላህ በለው እግ ዜር በለው ያው ነው። ልጄ ሆላንድ የ ቤተክርስቲያን አመራር ይሰራል ሲባል ሰምቼያለሁ፣ እሱም አንዴ ሰላም ሊል ደውሎ አጫውቶኛል። ልክ ነው? (‘አ ረ የማይገባበት ቦታ የለም’) አንድ ነገ ር ልንገርህ እኔ ወደ ቅድመ አያቶቼ ሃ ይማኖት ተመልሻለሁ። ግድግዳ ላይ በመስታወት ውስጥ ሆ ኖ የተሰቀለው ዳንቴል የመሰለ የአረብ ኛ ነገር የተጻፈበት ነገር አሳዩኝ። “ አረብኛውን ባለውቀውም አላህ ከ ሰዎች ጋር በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራ ል። ነብዩም እንዲህ ነው የሚያስተም ሩት፤ ስማቸውን ይባርክና። ግን ልጄን እንዲከፋው አልፈልግም ‘አባቱም እና ቱም ሰለሙ’ ተብሎ ቢሰማ ያዝናል፣ ይበሳጫል (አረ ካሽ ካገኘ ግድ የለው ም)። ግን እዚያም ስገዱ ነው፣ እዚህም ስገዱ ነው። ‘አለማየሁ’ የተባለ ስሜ ‘አ ብዱላሂ’ አሰኝቼዋለሁ። የሰፈር ሰው ገ ና ‘አለማየሁ’ ነው የሚልኝ። ክፋት የ ለውም። እንዲህ ያደረግነው ለጥቅም አይደለም። ለእሱ ነው። ለእመነቱ ነ ው። ታዲያ ከልጄ ጋር ተገናኝታችሁ ድንገት ወሬ ቢነሳ መነሳቱ መቼም አ ይቀር፣ እንደሰለምኩ አትንገረው። ይ ሄን ቃል ግባልኝ። ያለዛሬ አይቼህ አላ ውቅም። መቼም ታምነህ የተላክ ሰው ስለሆንክ፣ ብትግባቡ ነው መቼም (‘ከ ቴም ተግባባን’) ቢሰማ ችግር ይኖረዋ ል? እንጃ እንግዲህ ባትነግረው፣ ባታ ወራው ይመረጣል። እንዳይሳትህ ብ ዬ ነው። ሴትየዋ/ ባለቤታቸው ከእኛ ራቅ ብ ለው በጋቢያቸው ተሸፋፍነው ታስረ
ው የተቀመጡ መስለዋል። ቃል አ ውጥተው አይነገሩኝ አንጂ ከአስተያ የታቸው፣ ከአንገት አደፋፋቸው እየ ተለማመጡኝ እንደሆነ ይገባኛል። የ ሰውዬው ከአፌ ቃል እንደማይወጣ ኝ በተፈጥሮዬ (ምናልባት ስወለድ ጀ ምሮ ወይም ከእናቴ ሆድ ጀምሮ ለሃ ይማኖት ግድ እንደሌለኝ፤ እንደው ም እሳቸው ያሉት የእግዜር መመሳ ሰል ትልቁ እውነት እንደሆነ አንስቼ) ሳይሆን አይቀርም ምስጢር ቀርቃሪ በመሆኔ ትንፍሽ እንደማልል፣ አንዲ ት ቃል ከአፌ ጠብ እንደማትል ቃሌ ን ሰጠሁዋቸው። ክርስቶስን ጠርተ ው መረቁኝ። ከተቀመጡበት ተነስተው ትከሻዬ ላ ይ ሳሙኝ። ሲሰናበቱኝ እና ሲሸኙኝ ሽማግሌ ው አይኖች ውስጥ ሊሸፍኑት ያልቻ ሉት ወፍራም እፍረት ነበር። ለመቅደስ ይሄን ሁሉ አልነገርኳት ም። *** ግን ነገ ልሄድ ዛሬ፣ አንድ የቀረኝን ነ ገር ማድረግ ነበረብኝ። ከሰዓት በኋ ላ ላይ ሻንጣዬን በርብሬ የልጄን “ል ፎ” እና እትብት ያለባቸውን ብልቃ ጦች ይዤ ወደ ጓሮ ወጣሁ። መቅደ ስ ቆማ ታየኛለች። ቶማስ ደረቷ ላይ ያለቅሳል፣ አዲስ አባ ከገባሁ ጀምሮ ያለቅሳል። አዲስ አባን አልወደደው ም ወይም አየሩ ቀጥኖበታል። ከቤ ቱ ጀርባ ረግረግ የመሰለች ቦታ አለ ች። ረባዳ በመሆኗ ውሃ ስለምትሰበ ስብ ይሆናል። መሬቱን በገሶ ቆፈርኩ ና ቆዳዎቹን በህብረት የአጥቅ ርዝመ ት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ከጠርሙ ሳቸው አውጥቼ ቀበርኳቸው። ጥላ ስር ያስቀመጥኩትን፣ ለዚህ ጉዳይ ያ መጣሁትን የቀርከሃ ፍል ወስጄ እዚ ያ ተከልኩትና በባልዲ ውሃ እያመላ ለስኩ አጠጣሁት። በድንገት መቅደ ስን ዞሬ አየኋት ግንባሯን በሀሳብ ከ ስክሳለች። ‘ምነው ሳቅሽ ጠፋ?’ ብዬ ልጠይቃት ፈለግሁ። ልጁ ከደረቷ ወ ርዶ መሬት ለመሬት ሊንቧች ይንፈራ ገጣል። በጠዋት አይሮፕላን ላይ ወጥተን ሳ ይ፣ አዲስ አባ ወደታች የተተመተመ ች አረንዛ ቦታ እንደምትመስል አየ ሁ። መሬት ላይ ቆሜ አረንጓዴ የሚ መስሉኝ ዛፎች እንኳን ከዚያ ርቀት አመዳም ናቸው። በሀሳቤ በስሜት ከ ረሳሁት፣ ስጋ ከቀበርኩበት መሬት ረ ግረጉን የጠባ በእፍኝ የሚያዝ ወፍራ ም መለሎ ቀርከሃ ሲበቅል ታየኝ። እ ምቢልታ የሆነ ዕለት እንደተረቱ ዋሽ ንት ግጥም የሚያንቸረችር። ‘እዛም የለሁ እዚህም የለሁ ባሌለሁበት ያሌለሁበትን እየተመ ኘሁ’ *** ደክንሀግ ስገባ ስለሰለሙት የእን ትና እናት እና አባት አላወራሁም። ማውራት የአራዳ ልጅ ደንብ አይደ ለም። አዲስ አባ ባቡር ጣቢያ ጠይ ቁ። ያ ብቻም አይደል። ክፉን በክፉ አትቃወሙ ይላል ቁልቁሉ መጽሀፍ ት ሁሉ።
(ተፈጸመ) * ልፎ ማለት ወንዶች ሲገረዙ ከብ ልታቸው ተቆርጦ የሚቀበረው (የሚ ጣለው) ቁራጭ ነው። ** ‘** ‘ክሎትዛክ’ (Klootzak) ማ ለት በዳች ቋንቋ ቆለጥ የሚቀመጥበ ት የቆዳ ኮሮጆ ነው
ይህ አጭር ልቦለድ የተወሰደው አዳም ረታ በቅርቡ ካሳተመው አምሰተኛ መጽሀፉ “ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ” ነው
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
15
ሐበሻዊ ቃና
መጽሐፍ
ይህ ጹሁፍ ከዳንኤል ክብረት ጡመራ (ዳንኤል ክብረት ዶት ኮም ) የተወሰደ ነው
በቅርብ ለንባብ የበቁ መጽሐፍት
ደራሲ፡- ዳንኤል ተፈራ ጀ.
ደራሲ፡- አበበ ቶላ
አዘጋጅ፡- ጳውሎስ ኞኞ
አታሚ፡- ንግድ ማተሚያ ድርጅት
ዋጋ፡- 26 ብር፣ 15 ዶላር፣ 15 ዩሮ
አታሚ፡- ርኈቦት አታሚዎች
ዋጋ፡- 50 ብር
ገጽ፡- 152
ዋጋ፡- 120 ብር
ገጽ፡- 384
ከመጽሐፉ የተወሰደ
የ“ነጋሶ መንገድ” የተሰኘው እና በሐም ሌ ወር ለንባብ የበቃው መጽሐፍ የቀድ ሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ህይወት የሚያስ ቃኝ ነው፡፡ የመጽሀፉ ደራሲ ዳንኤል ተ ፈራ በመግቢያው ላይ እንደጻፈው የዶክ ተር ነጋሶን ታሪክ ለማዘጋጀት ከእርሳቸ ው ጋር ሶስት ወር የፈጀ ቃለ መጠይቅ አ ድርጓል፡፡ “የ“ነጋሶ መንገድ” በተሰኘው በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነጋሶ የተጓዙበትን ረዥምና አባጣ ጎባጣ የበዛበት የህይወት መንገድ እናገኛለን” ይላል በመጽሀፉ ጀር ባ የተጻፈ ማስተዋወቂያ፡፡ ከባለቤቱ አን ደበት የተቀዳ ነው የተባለለት ይህ መጽ ሀፍ የነጋሶን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያ ለ የህይወት ታሪክ በስድስት ምዕራፎች ከፋፍሎ አቅርቧል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ የ“አባታቸው ልጅ” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን ስለነጋ ሶ የልጅነት ጊዜ፣ የታወቁ የፕሮቴስታን ት ቄስ ስለነበሩት የነጋሶ አባት እና ቤተ ሰቦቻቸው የሚተርክ ነው፡፡ “ላለመስማ ማት መስማማት” የሚል ርዕስ የተሰጠ ው ሁለተኛ ምዕራፍ ነጋሶ ጀርመን ሀገር በነበሩበት ጊዜ እንዴት ኢህአዲግን አን ደተቀላቀሉ የሚያወሳ ነው፡፡ “ስልጣን እ ና ፖለቲካ” በሚለው ሶስተኛ ምዕራፍ ነ ጋሶ ከተለያዩ የመንግስት የኃላፊነት ደረ ጃዎች አንስቶ እስከ ፕሬዝዳንትነት የሰ ሩባቸውን ጊዜያት ይዳስሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ከጀርባው በርካታ ምስጢሮች እ ንደተሸፈኑ ተቀምጠዋል በሚባልለት የ ህወኣት ክፍፍል እና ተሃድሶ ዙሪያ የሚ ያጠነጥነው አራተኛ ምዕራፍ ያልተሰሙ አንዳንድ ነገሮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በ ክፍፍሉ ወቅት ከህወኣት እንዲወጡ ስ
ለተደረጉ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር መ ለስ ዜናዊ የተናገሩትን እና ነጋሶ የመለሱ ት አንዱ ነው፡፡ “መለስ ስለ መቀሌ ውሳኔ ‘ጃኬታቸው ን አስወልቀን ራቁታቸውን አባረርናቸ ው’ እያለ ሲናገር እጄን አነሳሁና ‘ይቅር ታ! አሁንስ መንግስቱን መሰልከኝ’ አል ኩት፡፡ ቤቱ በድንጋጤ ተናወጸ፡፡ በተለ ይ ከጎኔ ተቀምጣ የነበረችው ገነት ዘው ዴ ‘እንዴት ከመንግስቱ ጋር ታወዳድረ ዋለህ’ በማለት ስቅስቅ ብላ አለቀሰች” ይላሉ ነጋሶ በመጽሀፉ፡፡ እንዲህ የተሰማ ቸውን ይናገሩ የነበሩት ነጋሶ በስተመጨ ረሻ ኢህአዴግ በቃኝ አሉ፡፡ ይህን ውሳኔ ያቸውን እና ከዚያ በኋላ ያለውን ህይወ ታቸውን ዋጋ የተከፈለበት የነጻነት መን ገድ በሚል ምዕራፍ ይተነተናል፡፡ ነጋሶ ከፕሬዝዳንት ስልጣናቸው በግል ፍቃዳ ቸው ከለቀቁ በኋላ በተወለዱበት ደም ቢ ዶሎ ለፓርላማ ተወዳድረዋል፡፡ በም ርጫ 97 ብቸኛው የግል ተመራጭ ሆነ ውም ፓርላማ ገብተዋል፡፡ ከአምስት ዓ መት በኋላ ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲ ስር መታገል እንደሚሻል አምነው የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ተቀላ ቅለዋል፡፡ ስደስተኛው እና የመጽሐፉ የመጨረሻ ምዕራፍ አባሪ ሰነዶችን የያዘ ነው፡፡ ዶክ ተር ነጋሶ በየጊዜው የተጻጻፏቸው ደብ ዳቤዎች ከአባሪ ሰነዶቹ መካከል ይገኙ በታል፡፡ መጽሐፉ እንደ አባሪ ሰነዱ ሁ ሉ 41 ፎቶዎችንም በውስጡ አካትቷል፡ ፡ ፎቶዎቹ ከነጋሶ የልጅነት ጊዜ፣ እስከ የ ጀርመን የስደት ህይወት፣ ከቤተመንግስ ት ቆይታቸው እስከ ቤተሰብ ህይወታቸ ው ያለውን ሁኔታ የሚያስቃኙ ናቸው፡፡
“ከዚህ በኋላ በሻዕቢያና በህወሃት መካከል ችግር ተፈጥሮ ወደ ጦርነት የምንገባ ከሆነ የእኛን ህዝብ ሂዱና ተዋጉ ብዬ አልቀሰቅስም! ” አዲሱ ለገሰ (የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር)
ብዙዎች የሚያውቁት አቤ ቶኪቻው በሚለው የብዕር ስሙ ነው፡፡ እውነተኛ የመዝገብ ስሙ አበበ ቶላ ነው፡፡ በአዲስ አ በባ ውስጥ ባለ አንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ የሚሰራው አበበ በ“አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ላይ በየሳምንቱ ያወጣቸው በ ነበሩ ስላቅ አዘል ጽሁፎቹ ይታወቃል፡፡ አበበ በህዝቡ ው ስጥ ያለውን ስሜት በጽሁፎቹ ለማንጸባረቅ ይጥራል፡፡ ሰሞ ነኛ ጉዳዮችን እያነሳ ይተቻል፣ ይቧልታል፣ ይሳለቃል ባስ ሲ ልም ያሽሟጥጣል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከተካተቱት 27 ጽ ሁፎች ውስጥ እብዛኞቹ በ“አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ላይ ወጥተው የነበሩ ናቸው፡፡ ለንባብ በቅትው የሚያውቁት ቀሪ ዎቹ ጽሁፎች ደግሞ አበበ በየወቅቱ የሚሰማውን ለመግለ ጽ እየጻፈ ያስቀምጣቸው የነበሩ ናቸው፡፡ “ጽሁፎቹ ኢትዮ ጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ እና ማህበራዊ ሁኔታ ላይ የሚ ያተኩሩ ናቸው” ሲል አበበ ከአዲስ አበባ በስልክ ለሐሻዊ ቃ ና ተናግሯል፡፡ “ስላቆች ከአቤ ቶኪቻው” የተሰኘው መጽሐፍ መጀመሪያ የ ታተመው በአሜሪካ ሲሆን ሀገር ቤት ከታተመው አምሳያው በሶስት ጽሁፎች የላቀ ነው፡፡ አበበ ከአገር ቤት አስቀድሞ መ ጽሀፉን በውጭ ያሳተመው እርሱ የሚጽፋቸውን ዓይነት ተ ቺ ጽሁፎች የያዘ መጽሐፍ ለማሳተም የሚደፍር አታሚ በመ ጥፋቱ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይህንን የአታሚ ችግር “የአቤ ቶ ኪቻው ሽሙጦች” በሰተኘው የመጀመሪያው መጽሐፉ ጊዜ መቅመሱንም ይናገራል፡፡ “ ‘የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች’ን ማ ተሚያ ቤቶች አልቀበልም ብለውኝ ነበር” ሲል ለሐበሻዊ ቃና ያስረዳል፡፡ የአሁኑን መጽሀፍ አሜሪካ አስቀድሞ ካሳተመ በ ኋላ በኢትዮጵያም ለመድገም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት እንደ ነበር ይናገራል፡፡ ሆኖም በስተመጨረሻ “ስም የለሽ” ማተሚ ያ ቤት ለማሳተም መብቃቱን ይገልጻል፡፡ አበበ በ“አቤ ቶኪቻው” ሰም የሚያቀርባቸውን ጽሁፎች እን ደቀድሞው በ“አውራምባ ታይምስ” ሳይሆን በ “ፍትህ” ጋዜ ጣ ላይ ማቅረብ ቀጥሏል፡፡ ጹሁፎቹን መከታተል የሚፈልጉ በፍትህ ኦፊሴሊያዊ ድረ ገጽ www.feteh.com ያገኟቸዋል፡፡
ከመጽሐፉ የተወሰደ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ጋሽዬ እንዳሉት… (ሁልጊዜ እንደባዳ በማዕረግ ስማቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያልኩ እንዳላርቃቸ ው ሰግቼ ነው ጋሼ ማለቴ!) እናም ጋሽዬ እንዳሉት የሚያመ ጣው ለውጥ ኢምንት በሆነ ኖሮ እርሳቸውም፣ እኔም፣ ድርጅ ታቸውም፣ ድርጅቴም፣ መንግስታቸውም፣ መንግስቴም ምነ ኛ ደስ ባለንና ብርጭቆ ባጋጨን ነበር፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦ ሽ ሆነና ብርጭቆ ለማጋጨት አልታደልንም! በምትኩ በነዳጅ ጭማሪው ሳብያ ብዙ ነገር ጨምረውባቸው ከተከፉ ሰዎች ጋ ር እየተጋጨን እንገኛለን… ( “ለአባይ ያሰብኩትን ነዳጅ ወሰደ ብኝ” በሚል ርዕስ ከቀረበው የተወሰደ)
ገጽ፡- 622 በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ጉልሕ ሥፍራ ያላቸው ዐፄ ምኒሊክ የተጻጻፏቸውን ደብዳቤዎች ጳውሎስ ኞኞ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት አዘጋ ጅቶ ነበር፡፡ ከ1978 ዓም በፊት፡፡ በዚሁ ዓመት መ ጽሐፉ ይታተም ዘንድ ለመነጋገር ጳውሎስ ለኩራ ዝ አሳታሚ ሰጠው፡፡ በኋላ ሲጠይቅ «የበላይ አካ ል ወሰደው» ተባለ፡፡ የበላዩ አካል ማነው? ብሎ ቢ ጠይቅ ግን መልስ ሰጭ አላገኘም፡፡ ይኼ 2245 የዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤዎችን የያዘው መጽሐፍ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በአስቴር አ ሳታሚ ድርጅት አሳታሚነት ሰሞኑን ታትሟል፡፡ በዘመኑ የነበረውን የውስጥ ግንኙነት፣ የመኳንን ት እና የመሳፍንት ሁኔታ፣ የመንግሥትን አሠራር፣ የመሪዎችን አስተሳሰብ፣ የሕዝቡን እና የኑሮውን ሁኔታ እና ሌሎችንም በደብዳቤዎቹ ውስጥ ይገ ኛሉ፡፡ ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያን ነገር በኢትዮጵያኛ ከ ጻፉልን ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው፡፡ ብዙ ዎቹ ምሁራን ለጆርናሎች እና ለወርክሾፖች እንጂ ለሕዝብ የሚሆን ትሩፋት የላቸውም፡፡ ጳውሎስ ኞኞ ግን እኛ የምናነባቸውን ብዙ ሥራዎች አትር ፎልናል፡፡ የጳውሎስ ሥራዎችን ከልጅነታችን ጀም ሮ አንብበናቸዋል፡፡ አስደናቂ ታሪኮችን ብዙዎቻች ን ታች ክፍሎች ሆነን ነው ያነበብናቸው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተካተቱት ደብዳቤዎች መካከል እጅግ ወሳኙ ደብዳቤ ራሱ ጳውሎስ ኞ ኞ ለጓድ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ (ነፍሳቸውን ይማ ርና) የጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ በወቅቱ የኢሠፓ ማ ዕከላዊ ኮሚቴ የፖለቲካ ቢሮ ተለዋጭ አባል፣ የ ሀገር እና ሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስትር ለነበ ሩት ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ጳውሎስ የምሬት ደብ ዳቤ ጽፏል፡፡ በዚህ ደብዳቤው ጳውሎስ ለሀገሬ ልሥራ ባለ የ ሚደርስበትን እና የደረሰበትን መከራ ዘርዝሮታል፡ ፡ በየዘመናቱ ያሉ ደራስያን ያጋጠማቸውን እና የ ሚያጋጥማቸውን መከራ ነው በደብዳቤው ውስ ጥ የምናየው፡፡ ጳውሎስ መጽሐፎቹ ይወሰዱበታ ል፣ “ማን ወሰዳቸው?” ሲል የበላይ አካል ይባላል፡ ፡ ይህ የበላይ አካል ግን አይታወቅም፡፡ የሰበሰብካ ቸውን ማስረጃዎች በአስቸኳይ አስረክብ ይባላል፡ ፡ “ማን አለ?” ሲል የበላይ አካል ይባላል፡፡ በዚህ ምክንያት ካሁን አሁን ያለኝን ሁሉ ማስረ
ጃ ይህ ማነነቱ ያልታወቀ የበላይ አካል ይወስድ ብኝ ይሆን? በሚል ሰቀቀን ውስጥ መግባቱን ይገ ልጣል፡፡ “የኢትዮጵያን ሕዝብ እና መንግሥት አ ልበደልኩምና ከሀገር እንድወጣ ይፈቀድልኝ” ብ ሎ አመለከተ፡፡ በዚህ ማመልከቻው ለመሣፈርያ የሚሆን ገንዘ ብ ለመለመን እንዲፈቀድለት፣ ከሀገር እንዲወጣ እንዲፈቀድለት፣ ከሀገር ሲወጣም ዶክመንቶቹን ይዞ እንዲሄድ እንዲፈቀድለት ለምኗል፡፡ የጳውሎስ ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ የደርግ ዘመ ን አለፈ፣ ደብዳቤው የተሰጣቸው ተስፋዬ ወል ደ ሥላሴ ታሠሩ፤ በኋላም ራሱ ጳውሎስ ኞኞ አ ረፈ፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ ግን መጽሐ ፉ እጃችን ገባ፡፡ ምስጋና ለቤተሰቦቹ እና ለአሳ ታሚዎቹ፡፡ እኔ ግን ሁለት ነገሮች ነገር ቅር አሉኝ፡፡ ምነው ለመጽሐፉ የደከመው፣ ደክሞም ያዘጋጀው፣ አዘ ጋጅቶም ሲታተም ሳያይ ያለፈው የጳውሎስ ኞ ኞ ታሪክ ሲሆን በመግቢያ፣ ካልሆነም በጀርባ ሽ ፋኑ ሳይጠቀስ ቀረ፡፡ ሥራው ያለ ሠሪው ምንድ ንነው? ቢያንስ በቀጣይ ይታተማል የተባለው መጽሐ ፍ ሲታተም ስለ ጳውሎስ ኞኞ አጭር ታሪክ መ ካተት አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዐፄ ምኒሊክ ደብዳቤ የጻፉ በትን ቋንቋ አሁን ባለው አስተሳሰብ ለማረም መ ሞከር ስሕተት ይመስለኛል፡፡ አንደኛ በዘመኑ ስ ላለው አስተሳሰብ ማወቅ የሚቻለው በቃላቱ ነ ው፡፡ አስተሳሰበ በዋናነት የሚገለጠው በቋንቋ ነ ውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ዐፄ ምኒሊክ ስንጽ ፍ በራሳችን ቋንቋ እንጻፍ እንጂ እንዴት ዐፄ ምኒ ሊክን በእኛ ዘመን ቋንቋ እናስጽፋቸዋለን? የአሳታሚዎቹ ችግር ይገባኛል፡፡ ግን ችግሩን ካ ልተጋፈጥነው ለሁለት ሺ ዘመናት የተከማቸውን የኢትዮጵያ ዶክመንት አርመን እንዴት እንዘልቀ ዋለን? እኛ የሞቱ አባቶቻችንን ቋንቋ መረዳት አ ለብን እንጂ እንዴት የሞቱ ሰዎች የኛን ቋንቋ ተረ ዱ እንዴት ይባላሉ? በዚህ ሃሳብ ምክንያት ብዙዎቹ ደብዳቤዎች ም ኒሊክ ሳያውቁ «መታረማቸውን» ጳውሎስ ኞኞ ካሰባሰባቸው መካከልም ሁለቱ ደብዳቤዎች መ ቅረታቸው የችግሩን ሥር መስደድ ያሳያል ፡፡
16
የጉዞ ማስታወሻ
ወ
ደ ታንዛንያ መዲና ዳሬ ሰ ላም ከመጣሁ ሰባት ወር አለ ፈኝ። ወደዚህ ስመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማኝን ግን አሁንም አስታውሰዋለሁ። በዕለ ቱ የነበረው የሙቀት መጠን በዲግ ሪ ሴልሺየስ ሲለካ 37 ደርሶ ነበር። ከወበቁ የተነሳ ልክ ከአውሮፕላን ስ ወጣ ለቅጽበትም ቢሆን ኦክሲጅን የ ተቋረጠ ነበር የመሰለኝ። በውሃ ው ስጥ ለመተፈንስ እንደመሞከር በሉ ት። ራሴን ከሁኔታው ጋር እስካላም ድ ጥቂት ጊዜ ወስዶብኝ ነበር። ሰውነቴ ከሙቀቱ ጋር ሲላመድ አ ይኖቼ ዙሪያ ገባውን ማስተዋል ጀ መሩ። ለአስር ወራት ቤቴ የሚሆነ ውን ሀገር እቃኝ ገባሁ። አፍቃሪዎቿ ዳር እያሉ የሚያቆላምጧት ዳሬ ሰላ ም ውብ ናት። የባህር ዳርቻዋቿ ትን ፋሽ አስቆራጭ ናቸው። በፖስት ካ ርድ ላይ ብቻ ስታዩት የከረማችሁት ቦታ እንደመገኘት ነው። በዚያ ዝና ብ እንኳ ጠብ የማይል በሚመስልበ ት ሞቃታማ አየር ከተማይቱ እንዴ ት በአረንጓዴ እንደተሸፈነች መመል ከት ያስገርማል። ከከተማይቱ እም ብርት በቀር ዛፎች የትም ይገኛሉ። ልክ እንደአዲስ አበባ ሁሉ ዳሬሰላ ምም ወደ ጎን እየተለጠጠች የመጣ ች ይመስላል። ረዘም ያሉ ህንጻዎች ን ግን የምታገኙት በከተማይቱ መሃ ል ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆኑ እን ደአዲስ አበቤዎቹ እንኳ አይረዝሙ ም። የከተማይቱ መሃል እንደ ዳርቻ ዎቹ ሰፊ ቦታ ያካለለ አይደለም። ዳ ርቻዎቹ ሰፋፊና በየጊዜው እንደመ ንግስት እርሻ ወደ ጎን የሚሰፉ ናቸ ው። በርካታ ታንዛንያውያን የስራ ገ በታቸው መሃል ከተማ ቢሆንም የ ሚኖሩት በከተማ ዳርቻዎች ነው። በተጨናነቀው እና ጫጫታ በበዛበ ት የከተማይቱ እምብርት መኖር የ መረጡ ታንዛንያውያን ጥቂት ናቸ ው። አብዛኞቹ የመሃል ከተማ ነዋ ሪዎች ህንዶች እና አረቦች ናቸው። ስለ ህንዶች ካነሳሁ ዘንድ ዳሬ ሰላ ም ከመጣሁ በኋላ የተደነቅሁበትን ነገር ላጫውታችሁ። በመላው ታን ዛንያ ሂዱ ህንዶችን የትም ታገኛላች ሁ። አብዛኛው ንግድ የተያዘው በእ ነርሱ ነው። በህንድ ውቅያኖስ ዳር ቻ የተገነቡትን አብዛኞቹን የዳር ሪዞ ርት በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት እነርሱ ናቸው። የጌጣጌጥ ሱቆች እና ቡቲኮችንም የተቆጣጠሩት ህንዶች ናቸው። ምስራቅ አፍሪካን ለመጀመ ሪያ ጊዜ የሚጎበኝ ኢትዮጵያዊ በዚህ መደመሙ አይቀርም። አብዛኞቹ የ እኛ አገር የንግድ ስራዎች ባለቤትነ ት በራሳች የተያዘ ነው። እዚህ አገር እንደሚታየው ህንዶች የዕለት ተዕለ ት ህይወታችን አካል ሊሆኑ ቀርቶ ከ አስተማሪነት በዘለለ በትልቅ ባለሀብ ት ደረጃም መመልከት የጀመርነው ከቅርብ አመታት ወዲህ ነው።
እንደሰማሁት ከሆነ ህንዶቹ በታንዛን ያ ለዘመናት ከመቆየታቸው የተነሳ ኑሯ ቸውን ሙሉ ለሙሉ በሀገሪቱ መስርተ ው መኖር ከጀመሩ ቆይተዋል። ብዙዎ ቹ ልጆቻቸውን የወለዱት በታንዛንያ ነ ው። በታንዛንያ ተወልደው ካደጉት ህን ዶች ውስጥ አብዛኞቹ እናት ሀገር ህንድ ን ተመልክተው አያውቁም። የታንዛንያ ዜግነት ስላላቸው ከሀገሬው ተወላጆች እኩል መብት አላቸው። በንግድ ስራዎ ች ላይ ባላቸው ብቃት የተነሳም ከታን ዛንያውያን የተሻለ የተደላደለ ኑሮ ለመ ኖር ችለዋል። ህንዶች ታንዛንያን ቤታቸው አድርገ ው መኖር የመረጡት ኑሮ በዚህ አገር ርካሽ በመሆኑ እና የገቢ ግብር ስለማ ይከፍሉ እንደሆነ የአገሬው ሰዎች አጫ ውተውኛል። ህንዶቹ ጥሩ ይከፈላቸዋ ል፤ በርካታ ገንዘብም ይቆጥባሉ፤ ስለዚ ህም አሪፍ ኑሮ ይኖራሉ። ይህቺ አገር በ አገራቸው የማይገኙትን አይነት ኑሮ እ ና መንደላቀቅ ብትሰጣቸውም አብዛኞ ቹ ህንዳውያን ግን ከአገሬው ሰው ጋር አይቀላቀሉም። በሌላው አገር አንደሚ ያደርጉት ሁሉ የሚጋቡት ከመሰሎቻቸ ው ጋር ነው። በአጋጣሚ ያገኘሁት አን ድ ህንዳዊ ያጫወተኝ ለዚህ ሁነኛ ምሳ ሌ ይሆናል። እርሱ እንደገረኝ ከሆነ በህ ንድ የሚኖሩት ቤተሰቦቹ የሚያገባትን መርጠውለታል። በዚያን ጊዜ ከዚህ ቀ ደም አይቷት እንኳ የማያውቀውን ህን ዳዊት ለመግባት ወደ ህንድ ለመጓዝ እ የተዘጋጀ ነበር። ጋብቻውን በህንድ ከፈ ጸመ በኋላ ደግሞ ባለቤቱን ወደ ታንዛ ንያ ይዞ ይመለሳል። ከዚያ ልጆች ይወለ ዳሉ፣ የታንዛንያዊ ዜግነተም ያገኛሉ፣ የ ህንዶች የበላይነትም በተተኪዎቹ እንደ ተጠበቀ ይቆያል። ከህንዶች ቀጥሎ አገሩን የወረሩት ቻይ ናውያን ናቸው። እነርሱም እንደጎረቤቶ ቻቸው የሚቆጣጠሯቸው ንግዶች እና ድርጅቶች አሏቸው። ታንዛንያውያን ከ ዚህ በኋላ ነው የሚመጡት። በክብር ደ ረጃ ካየነው ታንዛንያውያን በገዛ አገራቸ ው ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ናቸ ው። ኬንያውያን እንኳ በብዙ ድርጅቶ ች ውስጥ ከእነርሱ የተሻለ ቦታዎች ይዘ ዋል። እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን ተመ ልክታችሁ ታንዛንያውያን የት ቦታ ላይ እንዳሉ መገመት ትችላላችሁ። ለዚህ ደ ግሞ ታንዛንያውያን ራሳቸው የሚያበረ ክቱት አስተዋጽኦ አለ። ስለታንዛንያውያን ሲነገር እንደምሰማ ው እና ራሴም እንደታዘብኩት ህዝቡ በተፈጥሮ በጣም ዘገምተኛ ነው። ምን ም ነገር ይስሩ ምንም ፈጠን የማለት ሁ ኔታ አይታይባቸውም። ዋና ዋና የንግድ ዘርፎች እና ቁልፍ የሆኑ የድርጅት ቦታ ዎች በውጭ ዜጎች ሲያዙ የበይ ተመል ካች የሆኑበት አንዱ ምክንያት ይህ ይ መስለኛል። ቀላል ምሳሌ ላቅርብ። ታን ዛንያ ላይ ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ አ ላችሁ እንበል። ምግብ ታዛላችሁ። ትዕ ዛዛችሁን የተቀበለው አስተናጋጅ ከምግ ብ ጋር የሚመለሰው ምግብ ማዘዛችሁ ን ከረሳችሁ በኋላ ሊሆን ይችላል። አን ዲት ቀላል ነገር ለማድረግ “ዘመናት” ይ
ሐበሻዊ ቃና
ወስድባቸዋል። ስለምግብ ቤት ካነሳሁ አይቀር ታንዛ ንያውያን ስለሚያዘወትሯቸው ምግቦች ጥቂት ልበላችሁ። እኛ እንጀራ ሳንበላ አንድ ቀን ለማሳለፍ እንደሚከብደን ሁ ሉ ታንዛንያውያንም ኡጋሊ እና ሩዝን ሳይቀምሱ ማደር አይሆንላቸውም። ኡ ጋሊን ለማታውቁ የእኛኑ ገንፎ ማለት ነ ው። ገንፎው የሚሰራው ከበቆሎ ዱቄ ት ሲሆን ለመባያነት መረቅ (ሶስ) ይጠ ቀማሉ። ማባያው ግን እንደ እኛ በበርበ ሬ ወይም በሚያቃጥል ቅመማ ቅመም የሚሰራ ሳይሆን ከስጋ ወይም ከተቀቀለ ባቄላ የሚሰራ ነው። በገጠሪቱ ኢትዮጵ ያ እንደሚዘወተረው ታንዛንያውያን ገ ንፏቸውን የሚበሉት በእጃቸው ነው። ዶሮ ሌላው ተዘውታሪ ምግብ ነው። ዶሮ በኢትዮጵያ የሚያገኘውን “ክብር እና ፍቅር” እዚህ ቢሳል እንኳ ጠብ አይ ልልትም። በኢትዮጵያ አመት በዓል በ ደረሰ ቁጥር ዶሮ ለመብላት የነበረንን ጉ ጉት ሳስበው እና እዚህ ዶሮ ወደ ዕለት ምግብ የወረደበትን ሁኔታ ሳጤን ግር ም ይለኛል። እኛ አገር ዶሮ የምንበላው ግፋ ቢል በዓመት ሶስቴ ወይም አራቴ ነ ው። እዚህ ግን ዋጋው ርካሽ በመሆኑ ከ ዕለት ገበታ ዝርዝር አይጠፋም። አንድ መረሳት የሌለበት ሐቅ ግን አለ። የእዚ ህ አገር ዶሮ በመጠን ከእኛም በጣም ያ ንሳል። ስብ እንዳይከማቹ በሚል ይመ ስላል ዶሮዎቹ እምብዛም እንዲያድጉ አ ይፈልጉም። ገና አደግ ሲሉ ቢላ አንገታ ቸው ላይ ያርፋል። የለጋ መሆናቸው ነገር ዶሮ በአገር ቤ ት የሚያገኘው የነበረውን ሌላ “እንክብ ካቤም” አሳጥቶታል። እኛ አገር ዶሮ ታ ርዶም ቢሆን ተገቢው የ“እጥበት እንክ ብካቤ” ያገኛል። እዚህ እንደዚያ አይደ ለም። አስተጣጠባቸው እንዲያው ለኮ ፍ ለኮፍ ነው። በዚህ ምክንያት ዶሮዎ ቹ ተጠብሰውም ቢሆን ለመብላት አል ደፍርም። አስተጣጠቡን ሳስብ የመብ ላት ፍላጎቴ ይቆለፋል። ሌሎች ምግቦ ቻቸውን ለመብላት ያለኝ ፍላጎትም ተ መሳሳይ ነው። ደግሞ ብቻዬን አይደለ ሁም። በርካታ ኢትዮጵያውያን ከምግ ቦቻቸው ጋር ለመላመድ ሲቸገሩ አስተ ውያለሁ። ኢትዮጵያውያኑ እኔ በአብዛ ኛው እንደማደርገው ወይ የራሳቸውን ምግብ ያበስላሉ አሊያም የአገሬው ም ግብ ምርጫቸው ውሱን ነው። ከታንዛንያውያን ጋር የምግብ አስተጣ ጠብ ላይ የተለያየ አቋም ቢኖረንም የእ ጅ አስተጣጠብ ባህላችን ግን ተመሳሳ ይ ነው። አንድ ሰው ከመብላቱ በፊት እ ና በኋላ የጣት ውሃ ይቀርብለታል። ም ግብ ካዘዙ በኋላ ለመታጠብ ብድግ ማ ለት በአገሬው ምግብ ቤቶች ዘንድ አያ ስፈልግም። በሞቃታማው አገር የሞቀ ውሃ በማስተጠቢያ ተደርጎ ወዲያውኑ ይመጣሎታል። እንደ ዶሮ ምግባቸው ሁሉ ሌላው ል ለምደው ያልቻልኩት ነገር የታንዛንያ የ ታክሲ ትራንስፖርት ጉዳይ ነው። በነገ ራችን ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር በ ታንዛንያ መኪና በጣም ርካሽ ነው። ኢ ትዮጵያ በጣም ውድ የሚባለው ቪት
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ዳር እና በስመኝሽ ይቆዬ በተለይ ለሐበሻዊ ቃና
ዝ የተሰኘው መኪና እዚህ በሁለት ሺ ህ ዶላር አሊያም ከዚያ ባነሰ ማግኘት ይቻላል። መኪና እንዲኖራቸው እየተ መኙ አቅም ላጠራቸው ኢትዮጵያውያ ን ታንዛንያ ህልማቸውን አንዲኖሩ ታ ደርጋለች። ታንዛንያውያን ይህንን የመኪና ዋጋ መርከስ በአግባቡ ተጠቅመውበታል። በርካታ ታንዛንያውያን በቤተሰብ ደረጃ ቢያንስ አንድ መኪና አላቸው። ለዚህ ም ነው የታንዛንያ መንገዶች በተለይ በ ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት በሚያ ስመርር ሁኔታ የሚጨናነቁት። አገሪቱ ከጎረቤቶቿ ኬንያ እና ኡጋንዳ በተሻለ ሰፋፊ መንገዶች ቢኖሯትም ከአንድ ቦ ታ ወደ አንድ ቦታ መንቀሳቀስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። በተለምዶ ከሰባት እስ ከ 10 ደቂቃ መውሰድ የሚገባው መንገ ድ አንድ ሰዓት እና አንድ ሰዓት ተኩል ቢወስድ አይገረማችሁ። ይህ ታዲያ በ ስራ ሰዓት ነው። በስራ መግቢያ እና መ ውጫ ሰዓትማ እንደአገሬው ሰዎች በታ ክሲው ውስጥ ቁጭ ብሎ እንቅልፍ መ ተኛት ሳይሻል አይቀርም። ቢያንስ የእን ቅልፍ ሰዓት እዚህ አካክሶ ቤት ሲገባ ሌ ላ ነገር መስራት ያስችላል። መኪና የሌላቸው የዳሬ ሰላም ነዋሪዎ ች ሶስት የመጓጓዣ መንገዶችን ይጠቀ ማሉ። የመጀመሪያው እና ርካሽ በመሆ ኑ በብዙዎች ዘንድ የሚመረጡት “ዳላ ዳላ”ዎች ናቸው። “ዳላ ዳላ” በሚለው ስያሜ የሚጠቀሙት በእኛ ሀገር ሚኒ ባስ ብለን የምንጠራቸው እና ኮስተር እ ና ሃይገር ባስ የመሳሰሉት ጭምር ናቸ ው። “ዳላ ዳላ”ዎች ለአንድ ጉዞ የሚጠ ይቁት ከ200 እስከ 350 የታንዛንያ ሽል ንግ ነው።በወቅቱ ምንዛሬ መሰረት አን ድ የኢትዮጵያ ብር ከ100 የታንዛንያ ሽ ልንግ ጋር ይመጣጠናል። እንደ “ዳላ ዳላ”ዎች በ“አስገራሚው” የታንዛንያ ትራፊክ ሕግ የተጠቀመ የለ ም። የትራፊክ ሕጉ እንደፈለጉ እንዲጭ ኑ ፈቅዶላቸዋልና ነው አስገራሚ ማለ ቴ። ለ“ዳላ ዳላ”ዎች ትርፍ ሰው ወይም ከአቅም በላይ የሚባል ነገር የለም። በአ ንድ ሚኒባስ ውስጥ ከ25 እስከ 30 ሰው ታጭቆ አስቡት። በዚያ የታንዛንያ ሙ ቀት ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ትንፋሽ ያሳጥራችኋል። በዚያ ላይ የፈለጉበት ቦ ታ ላይ ሲደርሱ ወራጅ ብሎ ዱብ ማለ ት የለም። “ዳላ ዳላ”ዎች ልክ እንደ አዲ ስ አበባ አውቶብሶች ሁሉ ማቆሚያ በእ ነሱ አጠራር “ስቴጅ” አላቸው። ማቆሚ ያዎቹ በየአጭር ርቀቱ መገኘታቸው በ
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
ዛንዚባር ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ
ጀ እንጂ የእርሶ መውረጃ በመሃል ሲሆ ን አንዱ ማቆሚያ ደርሰው ወደ ሚፈል ጉበት ቦታ መመለስ ግድ ነው። “ዳላ ዳ ላ”ዎችን መጠቀም እንግዲህ ይህንን ሁ ሉ ችለው ነው። ተረቱስ “ልጅ ሲወዱ ከነ***” አይደል። “ዳላ ዳላ” አያሻኝም ያለ እንደ ርቀቱ ሁኔታ ከ1500 እስከ 5000 ሺህ የታንዛ ንያ ሽልንግ ከፍሎ በ“ባጃጅ” መሄድ መ ብቱ የተጠበቀ ነው። ባጃጆች በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ በመሆና ቸው ብዙዎች ታውቋችዋላችሁ ብዬ እ ገምታለሁ። ችግሩ ባጃጆች ወደ ከተማ መሃል መግባት አይፈቀድላቸውም። ል ክ እንደ አዲስ አበባ በዳርቻዎች ላይ ብ ቻ ነው የምታገኟቸው። ክፍት በመሆና ቸው ሙቀት ባለባቸው እንደ ድሬዳዋ ባሉ የሀገራችን ክፍሎች ተወዳጅ እንደ ሆኑት ሁሉ ዳሬ ሰላም ላይም ለአየር ጸ ባዩ ተመራጭ መጓጓዣ ናቸው። ከባጃጅ ለጥቆ ያለው ሶስተኛው አማራ ጭ መጓጓዣ እነርሱ “ስፔሻል ሃየር” እ ኛ “ኮንትራት ታክሲ” ብለን የምንጠራ ው ነው። ይህ የመጓጓዣ ዓይነት ከሁሉ ም የሚወደድ በመሆኑ ለአገሬው እንግ ዳ በሆኑ፣ ጥሩ ገቢ ባለቸው ወይም የም ሽት ጉዳያቸውን ከውነው በሚመለሱ ሰዎች ዘንድ ተመራጮች ናቸው። እነዚ ህን የመጓጓዣ አይነቶች እየተጠቀምኩ ዳርን ከላይ ታች አዳረስኩ። ከከተማይ ቱ የአኗኗር ዘይቤ ጋር ለመላመድ አንድ ወር እንኳ አልወሰደብኝም። ሌሎች የአ ገሪቱን ክፍሎች ለመመልከት ግን ወራ ት መጠበቅ ነበረብኝ። በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ቦታዎች ታሪካዊ እንደሆነችው የዛንዚባር ደሴት ልቤን ያ ማለለው የለም። ስለ ዛንዚባር ብዙ ሰ ምቻለሁ። ስለሚያማምሩ የባህር ዳርቻ ዎቿ፣ ስለ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታዎቿ፣ ስለ አይጠገቤ ዙሪያ ገባዋ፣ ስለ ታሪካዊ ህንጻዎቿ እና ዋና ከተማዋ…ብዙ ብዙ ነ ገር። ወደዛንዚባር ለመጀመሪያ ጊዜ የሄ ድኩት እንደ ቱሪስት ለጉብኝት አልነበረ ም። በጋዜጠኝነት ሙያዬ በደሴቷ ላይ በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ የሚደገሰውን የሙዚቃ ዝግጅት እንደዘግብ ተጋብዤ እንጂ። የሙዚቃ ዘግጅቱ በዓለም ዙሪ ያ ስሙ የገነነ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከመ ገኘት በላይ ያጓጓኝ በተንጣለለ ነጭ አሸ ዋ ላይ ሆኖ ህንድ ውቅያኖስ ዳር ላይ ሆ ኖ ለጥ ያለውን ሰላማዊ ውሃ መመልከ ት ነበር። ይህን በአእምሮዬ የታተመ ም ስል በእውን ለመመልከት ጓጉቼያለሁ። ወደ ዛንዚባር ለመጓዝ ያሉት በአየር አ ማራጮች ሁለት ናቸው። ወይ በአየር
አሊያም በባህር። በአውሮፕላን ከሰላሳ ደቂቃ ያነሰ ጊዜ የሚወስደው ጉዞ በባህ ር ሲሆን እንደሚጠቀሙበት ዓይነት የ ጀልባ ዓይነት ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ይፈጃል። ምረጭ ብባል በባህር መጓዝ ን እመርጣለሁ። “ፌሪ” ተብለው በሚ ታወቁ የጀልባ ዓይነቶች የሚደረግ ጉዞ ምን እንደሚመስል ማወቅ ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ጋባዦቼ አስቀድመው የአውሮ ፕላን ትኬት ልከው ነበርና የባህር ጉዞ ሲያምረኝ ቀረ። ከዋናው የታንዛንያ ክፍል በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ደሴት ላይ ባለ ው አነስተኛ እና የተጨናነቀ አየር ማረ ፊያ ስደርስ ዛንዚባር ማለት የባህር ዳር ቻ እና መዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ተረዳ ሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ከተማ በም ጓዝበት ጊዜም የተመለከትኩት ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር። የማርፈበት ሆቴል የሚገኘው በከተማይቱ መሃል ነው። ከ ዛንዚባር ወደብ አቅራቢያ ስለሚገኝ አ ካባቢው ሁሌም እንደተዋከበ ነው። ከ ዳሬ ሰላም ከመነሳቴ በፊት አስበው የነ በረው በባህር ዳርቻ ባለ ሪዞርት እንደ ሚያሳርፉን እና ለማየት የጓጓሁትን እ ንደልብ ለመኮምኮም ነበር። መዝናናቱ ሲቀር ስለዛንዚባር ከዚህ ቀደም ያልሰ ማኋቸውን ነገሮች ለማሰስ ተነሳሁ። ብዙ ርቀት መጓዝ አላስፈለገኝም። ያረ ፍኩበት ሆቴል በራሱ ለካ የሚነገርለት ታሪክ አለው። ግራንድ ፓላስ ይባላል። በዛንዚባር ውስጥ ካሉት ህንጻዎች አሳን ሰር (ሊፍት) የተገጠመለት ብቸኛው ህ ንጻ እንደሆነ ነገሩኝ። ይህንን ስሰማ “ስ ቶን ታውን” ተብሎ የሚጠራውን የከተ ማ ክፍል ለማየት ይበልጥ ጓጓሁ። “ስቶ ን ታውን” የከተማይቱ ጥንታዊ ክፍል ነ ው። ላለፉት 200 ዓመታት እምብዛም ሳይለወጥ እንደነበረ የቆየ ነው። በጠባ ቦቹ የስቶን ታውን መንገዶች ስጓዝ ግን ይህንን ቦታ ከዚህ ቀደም ያየሁት ዓይ ነት ስሜት ተሰማኝ። የመንገዶቹ አቀያ የስ፣ የቤቶቹ አሰራር፣ የሰዎቹ አለባበስ ሁሉም ማለት ይቻላል ለእኔ እንግዳ አ ልነበሩም። ስቶን ታውንን ከዚህ ቀደም ተመልክቼው አላውቅም። በህልሜ እን ኳ እንዲህ ዓይነት አካባቢ መጓዜን አላ ስታውስም። “እና ለምንድነው ያየሁት ያየሁት የመሰለኝ?” ድንገት አንድ ነገር ብልጭ አለለኝ። እ ንዴ!....። አካባቢውን የሚመስል ቦታ የ ት እንደተመለከትኩ አስታወስኩ።....አ ዎ! በእርግጥም ስቶን ታውን የሚመስ ለው ጀጎልን ነው። የሐረሩን ጀጎል። ስ ቶን ታውን የጀጎል ትልቁ ግልባጭ ነው ብዬ ብናገር ስህተተኛ የምባል አይመስ ለኝም። ድንቅ አለኝ። የአገሬን ቦታ ባህ ር ተሻግሬ ስመለከተው እንዴት ድንቅ አይለኝ። በስቶን ታውን ጠባብ መንገዶች መጓ ዜን ቀጥያለሁ። አንዳንዶቹን መንገዶች ብሎ ከመጥራት መተላለፊያ ማለት ይ ቀላል። እንደ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ይ ራመድባቸው የያዘ ደግሞ መደናገሩ አ ይቀርም። ከአንዱ ቅያስ ወደ ሌላኛው እያለ ሲባዝን ሰዓታት መፍጀቱ አይቀር ም። ደግነቱ መተላለፊያዎቹ በራሳቸው
17
የጉዞ ማስታወሻ እና ዳር እና ዳር የተገጠገጡት ቤቶች የሚያፈዙ አይነቶች ናቸው። አብዛኞቹ ቤቶች የተገነቡት ከመቶ አመት በፊት ቢሆንም ምንም ሳይነካኩ እንደነበሩ አ ሉ። ብዙዎቹ በተለያየ ዲዛይን በእጅ የ ተቀረጹ የእንጨት በሮች ያላቸው ናቸ ው። እነዚህ ውብ የኪነ ህንጻ ውጤቶች ሳይሆኑ አይቀርም ስቶን ታውንን እንደ ጀጎል ሁሉ በተባበሩት መንግስታት የባ ህልና የሳይንስ ድርጅት (ዩኔስኮ) አማካ ኝነት በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ እንድ ትሰፈር ያደረጋት። ከተማይቱ ትንሽ እንደመሆኗ መጠ ን እና መንገዶቿም መተላለፊያ የሚባ ሉ ዓይነት በመሆናቸው አብዛኛው የአ ገሪቱ ነዋሪ የህዝብ መጓጓዣ አይጠቀም ም። ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለመሄድ የእ ግር ጉዞ ወይም ብስክሌት መጠቀምን ይመርጣሉ። ራቅ ብለው በመንደሮች ውስጥ የሚኖሩ ወደ ከተማ ለመምጣት “ዳላ ዳላ” ይጠቀማሉ። “ስፔሻል ሃይር” እዚህም አለ። ከአንዱ ሱቅ ወደ ሌላ መ ሄድ የሰነፈ እነዚህን ኮንትራት ታክሲዎ ችን ይጠቀማል። ገና በቅጡ ተደላድሎ በታክሲ ውስጥ ሳይቀመጥ ግን የሚፈል ገው ቦታ ይደርስና ይገላገላል። ስቶን ታውን አንድ የዛንዚባር ምልክ ት እንደሆነው ሁሉ ህዝቦቿም የደሴቲ ቱ መለያ ተደርገው ይወሰዳሉ። ዛንዚባ ሪያውያን ዋናውን የታንዛንያ ክፍል እና ደሴቶችን ያቀፈችው እና በኦፊሴል “ሪ ፐብሊክ ኦፍ ታንዛንያ” በመባል የምት ታወቀው አገር አካል ቢሆኑም ራሳቸው ን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ናቸው። የራሳቸው ፕሬዝዳንት፣ ተቀዳሚ ምክ ትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳ ንት አላቸው። በህዝብ በቀጥታ የሚመ ረጡ 150 አባላት ያሉት ፓርላማም የአ ስተዳደሩ አካል ነው። “ዛንዚባሪ” ተብለው የሚጠሩት የደሴ ቲቱ ተወላጆች 800 ሺህ ይጠጋሉ። ዘ ጠና በመቶ የሚሆኑት ዛንዚባሪያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀ ሪዎቹ የክርስትና እና ሂንዱይዝም ሃይ ማኖትን ይከተላሉ። በዛንዚባር የእስል ምና ተከታዮች እንደመብዛታቸው አረ ብኛ ቋንቋ የሚዘወትር የሚመስለው አ ይጠፋም። ዛንዚባሪያውያን ግን ከታን ዛንያውያን በተሻለ በተሻለ ጥርት ያለ ውን ስዋህሊ የሚያቀላጥፉ ናቸው። በ መላው ዓለም ታንዛንያውያን ትክክለኛ የስዋህሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተደርገው መወሰዳቸው ሲታሰብ የዛንዚባሪያውያ ንን የቋንቋ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። ታንዛንያውያን በእንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ ዘገምተኞች እንደሆኑ አጫውቼያ ችዋለሁ። ዛንዚባሪያውያን ይብሳሉ። አ ረ! አንዳንዶች ለንጽጸር ሁሉ አይቀርቡ ም። እንደ መሃል ሀገር ነዋሪዎች ሁሉ ዛንዚባሪያውያን ንግድ ላይ የሉበትም። እዚህ በህንዶች ምትክ አረቦች አብዛኛ ውን ነገር ተቆጣጥረውታል። ዛንዚባሪ ያውያን ንግድ ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ስራ በቅጡ አይሰሩም። የዛንዚባሪያው ያን የስራ ባህል አስመልከቶ አንድ ጓደ ኛዬ ያጫወተኝን ላካፍላችሁ። እንደአ ርሱ አባባል ከሆነ ዛንዚባሪያውያን በቀ
ኑ ውስጥ የሚሰሩበት ሰዓት ቢደመ ር ሁለት ሰዓት ብቻ ይሆናል። ወደ ቢሮ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት እ ስከ አራት ባለው ጊዜ ይገባሉ። ለሻ ይ እረፍት እና ለምሳ ይወጣሉ። በ ወጡበት የሚከወኑት ዕለታዊ ስራ ደግሞ አለባቸው። ለሚስቶቻቸው አስቤዛ መሸመት። ከሌላ ሰው መረ ጋገጥ አልቻልኩም እንጂ የዛንዚባር ሴቶች ገበያ መውጣት አይፈቅድላ ቸውም አሉ። ባሎቻቸው በምትኩ ሸመታውን ያደርጉላቸዋል። የዛንዚ ባር ወንዶች በሃይማኖታቸው ምክ ንያት ሁለት እና ሶስት ሚስት ማግ ባት ስለሚፈቀድላቸው ያለባቸውን የ“ስራ ጫና” እና የሚያጠፉትን ሰዓ ት መገመት ትችላላችሁ። ከዕለታዊ የገበያ ስራቸው ሲመለሱ ደግሞ የማ ይስተጓጉለው የጸሎት ስነስርዓት አ ለ። ቀኑ እንዴት እንደሄደ እንኳ ሳ ይውቁት ወደ ቤት መሄጃቸው ይደ ርሳል። ህይወት እንዲህ እያለች ትቀ ጥላለች። ዛንዚባሪያውያን ሰላማዊ ናቸው። እንደ ህዝቦቿ ሁሉ የአገሪቱ የጸጥታ ደህንነት አስተማማኝ ነው። ከአገሪ ቱ ይበልጥ የወደደደኩትም ይህንን እንደፈለጉ በማንኛውን ሰዓት፣ ቀን ም ሆነ ማታ፣ ወደየትኛውም ቦታ ቢ ሄዱ ምንም ችግር የማይጋጥም መ ሆኑ ነው። በመንገዶች ላይ ፖሊስ እንኳ አልተመለከትኩም። ወደ ዛን ዚባር ያመጣኝ ነገር የሙዚቃ ድግ ስ ነው ብያችሁም አልነበር። ታዲ ያ ይህ የሙዚቃ ፌስቲቫል የሚካሄ ደው በምሽት ነው። በአብዛኛው እ ስከ እኩለ ለሊት ገደማ ድረስ ይቆ ያል። በዚህ ዝግጅት የሚታደሙ ከ መላው ዓለም የመጡ ሙዚቀኞች እ ና ተመልካቾች ያለምንም ችግር፣ ያ ለምንም ጥበቃ ሲወጡ እና ሲገቡ ተ መልክቼያለሁ። የእጅ ቦርሳው የወደቀበት ሰው ከ ሰዓት ቦታ ወደ ነበረበት ቦታ ተመ ልሶ ፈልጎ የሚያገኝበት አገር ነው። የማያውቁትን እንግዳ ሰው ከመንገ ድ ጠርተው የሚገዙትን ነገር ነግረ ው ገንዘብ አስጨብጠው ይላኩት። አይጨንቁ። ከአዘዙት ነገር ጋር ተ መልሶ ይመጣል። ሌላ ምሳሌ። “ስ ፔሻል ሃየር” ተኮናተሩ እንበል። ሙ ሉ ክፍያውን ለመስጠት ገንዘብ አል በቃዎትም ወይም አልያዙም። ይህ ንኑ ለሹፌሩ አስረድተው ነገ ተመል ሶ እንዲመጣ ይንገሩት። አምኖዎት ይሄዳል። እንዚህ የዛንዚባር እውነታዎች በ ደሴቲቱ ልንመለከተው ከምንቋም ጠው ውጭ ብዙ የሚታይ ነገር እ ንዳለ አስረጂ ይመስሉኛል። ዛንዚ ባር ታሪክ እና ባህል የሞላባት አገር ናት። ይህንን የዛንዚባር ገጽታ ከማ ይጠገበው የባህር ዳርቻ ቆይታ ጋር ማግኘት እድለኝነት ነው። እኔ እድለ ኛ ነበርኩ። በህይወት ሳሉ መታየት ከሚገባቸው ድንቅ ቦታዎች አንዱን ተመልክቻለሁና።
18
የከተማ ቧልት
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና በእግዜር /ከአራት ኪሎ/
ከጥብስ እና ቅቅል እስከ የዘገባ ምህዳር
በጀርባዬ ተኝቻለሁ፡፡ በተንቀሳቃሽ አ ልጋ ላይ ተጋድሜ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እየተነዳሁ ነው፡፡ ብዛት ያላቸው ሐኪሞ ች ያሉበት፣ አጥንት የሚሰብር ብርድ ያ ለበት ክፍል ገባሁ፡፡ አፋቸውን በጨርቅ ያሰሩ ሐኪሞች ከበቡኝ፡፡ “በሽተኛን ክ ፉ ነገር ላለመናገር ይሆን አፋቸውን የሸ ፈኑት?” ብዬ ጠርጥሬ ሳልጨርስ አንዱ ዋዘኛ መሳይ ሐኪም ወደ እኔ ቁልቁል አ ንገቱን ሰብሮ “እሺ አንበሳው!” አለኝ፡፡ እንዳልፈራ ሲያግባባኝ መሆኑ ነው፡፡ በ ሆዴ ታዝቤ ዝም አልኩ፡፡ ይኸው ሐኪ ም ቃሉን ደገመው፤ “አንበሳው!” አሁን አላስቻለኝም፤ “ዶክተር እንዲህ ከተያዙ በኋላ አንበሳነት ምን ዋጋ አለ ው!?” አልኩት፡፡ ሳቀ፡፡ “‹በእናንተ እጅ ወድቄ ምን አንበሳነት አለ› አለኝ እኮ!” በ ማለት አሻሽሎ በመናገር ባልንጀሮቹን አ ሳቃቸው፡፡ ወዲያው ለእኔም ማደንዘዣ ተሰጠኝ፡፡ አንበሳነትም፣ ሰውነትም ቀረ ና ገላዬን ለስለት አሳልፌ ሰጠሁ፤ ለቀዶ ሕክምና፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሮች ሁሉ የሆ ኑት በማይጻፍለት፣ በማይነገርለት ዓለ ም ውስጥ እያለሁ ነው፡፡ እነሆ ነጋዴዎቻችን ሰሞኑን ከፍተኛ ማ ጉረምረም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሞገሳቸው፣ አንበሳነታቸው ጠፍቶ “የተጠየቅነው የ ዓመት ግብር ገቢያችንን ያማከለ አይደለ ም” እያሉ እንደቀውስ ብቻቸውን እያወ ሩ ነው፡፡ ዳቦ ሻጩ፣ ባለጠጅ ቤቱ፣ ፀጉ ር አስተካካዩ፣ ባለ ብስኩት ቤቱ ሁሉ ሳ ይቀር በተጠየቀው ግብር ኀዘን ገብቶት ንግዱን ለመተው እያሰላሰለ ነው፡፡ ከግብር ያለአግባብ መጨመር ጋር ተያ ይዞ ክፍለ ከተማዎች ግብር ከሚከፍሉ ት በላይ የንግድ ፈቃዳቸውን በሚመል ሱ ሰዎች እየተጨናነቁ ነው፡፡ ጉዳችን ፈ ላ! ምን ልንበላ? ምን ልንጠጣ? ፀጉራች ንን ማን ሊያስተካክለን? ቁርስ እና ምሳ ችንን በብስኩት እና በሻይ ለመሸወድ ሲ ያምረን ከየት ልናገኝ ነው? ይሄ ሁሉ ስራ በየቀበሌው በተደራጁት የሸማቾች ኅብ ረት ሥራ ማኅበራት ሊሠራ ታስቦ ይሆ
ን? እንጃ! ነጋዴው እንኳን እንዲህ በግ ብር ተወጥሮ ሳይወጠርም በዋጋ ንረት እኛን ወጥሮናልና ከዚህ ግብር ክፍያ በ ኋላ ወዮልን! ጎበዝ፤ ኧረ ጸልዩልን! ወይዘሮ ንፍሮ በንግድ ሥራ ሰባት ልጆ ቻቸውን የሚያስተዳድሩ እናት ናቸው፡ ፡ ንግዳቸው ደጃፋቸው ላይ የሚካሄድ ቢሆንም “ንግድ ፈቃድ አውጪ፤ ‘ቲን ነ ምበር’ ውሰጂ” የሚል ወዳጅ መሳይ ም ቀኛ መካሪ ገጥሟቸው እንደ ትልቅ ነጋ ዴ ሁሉን ነገር አወጡ፡፡ ዛሬ ታዲያ በግ ብር ጥያቄ ምክንያት መጀመሪያ ደም ፍ ላት፣ ቀጥሎ ደም ብዛት ይዟቸው ለአል ጋ ተዳርገዋል፡፡ ሲያሳዝኑ! “አንድ ቀን ጉልቴ ላይ ከሰል ማንደጃ ዬን እያያዝኩ ሳለ ማስታወሻ ደብተራቸ ውን የያዙ የቀበሌ ሰዎች ወደ እኔ መጡ፡ ፡ “ምን እየሸጥሽ ነው?” አሉኝ፡፡ “ቅቅል እና ጥብስ” አልኩ፡፡ እነሱም ጽፈው ሄ ዱ፡፡ አገር አማን ነው ብዬ ግብር ልከፍ ል ስሄድ ሁለት ሺህ ብር ተባልኩ፡፡ እኔ እኮ የምሸጠው ጥብስ እና ቅቅል የበቆሎ እሸት ነው፡፡” ወይዘሮ ንፍሮ ሲናገሩ እን ባቸው ዐይናቸው ላይ ኳስ ሠራ፡፡ በጣ ም አሳዘኑኝ፡፡ “የተጠየቅኩት ብር ሁለት ሺህ ብር ነ ው፡፡ እኔ ሁለት ሺህ የሚባለውን ቁጥር የማውቀው በዓመተ ምሕረት ላይ ብቻ ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዓ.ም. ስንት ነው? አዬ ጉዴ! ኧረ እሱም ጠፍቶኛል፡፡ በም ን ምክንያት ሁለት ሺህ ብር እንደጠየቁ ኝ አልገባኝም” ይላሉ ወይዘሮ ንፍሮ በኀ ዘን እየደጋገሙ፡፡ ከዚህ ወዲያ ያለውን የወይዘሮ ንፍሮን ንግግር ገጣጥሞ ለመ ረዳት ይቸግራል፡፡ ለማንኛውም እንዲ ህ ዓይነት መዓት ውስጥ ለገባችሁ ነጋዴ ዎች ሁሉ እግዚሃር ይሁናችሁ! ወደ ሕመሜ ልመልሳችሁ፡፡ አንድ ወ ዳጄ ሊጠይቀኝ ወደ ቤቴ መጣ፡፡ ይዞ የ መጣው እንደሌሎች በሽተኛ ጠያቂዎች ሙዝ ወይም ብርቱካን ወይም ጭማቂ / ኡኡይ አጓጉል ነገር እየጻፍኩ ራሴን አስ ጎመዠሁት!/ ሳይሆን ምክር ነበር፡፡ “ለ
የፌስ ቡክ ስላቅ
ፈሰሰህ ደም ሥጋ ነገር ብታገኝበት ጥሩ ነው፡፡ እንደ ቅቅል ነገር፤ ቀይ ወጥም ቢ ሆን፤ መረቅ ወይም ሾርባ፣ በርገር፣ ስጋ ፍርፍር፣ ዶሮ ብታገኝ ቁስልህ ቶሎ ይደ ርቃል፡፡ በተለይ አልጫ ጥብስ ፍርፍር ነገር ወይም ጎመን በሥጋ ዓይነት ለስላሳ ነገር… ” አለኝ፡፡ ሳቄ መጣ፡፡ በጣም ሳቄ መጣ፡፡ በሽታ በሰባበረው ድምፅ እዝን ብዬ፣ “ሌላው ያቅሙን ምናምን ይዞ ይመጣል አንተ “ሜኑ” ይዘህ መጣህ?” አልኩት፡፡ ወዳ ጄ እፍር አለ፡፡ በእሱ እፍረት እኔም አ ፈርኩ፡፡ በዘንድሮ የኑሮ ውድነት ይሄን ሁሉ ከየት ያመጣል? አልኩ፡፡ ቢሆንም ለእኔ ማዘን ነበረበት፡፡ የምግብ ዝርዝር ይዞ መጥቶ ለምን ያስጎመዠኛል? …ኧረ ኑሮ ሊያጠፋን ነው ጎበዝ! ኧረ ሊያጠ ፋን ነው! የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ቀጥሏ ል፤ በዋጋ ንረቱ መጨነቃችንም ቀጥሏ ል፤ ግብሩም ቀጥሏል፤ የሚሊየነር ልማ ታዊ ባለሐብቶች ብዛት ቀጥሏል፤ የሚ ሊዮኖች መራብም ቀጥሏል፤ የተማረ የ ሰው ኃይል ከየዩኒቨርስቲው መውጣት ቀጥሏል፤ ሥራ አጥነቱም ቀጥሏል፤ የመ ብራት አልፎ አልፎ መጥፋትም ቀጥሏ ል፤ መብራት ወደ ጁቡቲም ተቀጥሏል፤ ሁሉ ነገር “እንደገና” ቀጥሏል፡፡ እግዚሃር የተመሰገነ ይሁንና የዘገባ ም ህዳሩ ከበፊቱ ሰፋ ብሎ ቀጥሏል፡፡ ጥጋ ብ እና ረሃብ ጎን ለጎን በመንግሥት ሚ ዲያዎች የሚዘገቡበት ጊዜ ላይ ደርሰና ል፡፡ “በማንትስ ክልል በዚህ በያዝነው ክረምት አጥጋቢ የእህል ምርት እንደሚ ገኝ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ” የመ ጀመሪያው ዜና ቢሆን፣ “በማንትስ ክል ል በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻች ን የእርዳታ እህል ሊከፋፈል ታስቧል ወ ይም እንዴት መከፋፈል እንዳለበት ሰፊ ጥናት እየተደረገ ነው ወይም እየተከፋ ፈለ ነው” የሚለው ዜና ሁለተኛው ይ ሆናል፡፡ ታዲያ የዘገባ ምህዳሩ አልሰፋ ም ትላላችሁ!?
የፌስ ቡክ ስላቅ
ሳቅ ኢትዮጵያዊ አይደለም የወ/ሮ መላ ማመልከቻ ለቀበሌ 18 ጽ/ቤት አስተዳደር፤ አዲስ አበባ እኔ የዚህ ቀበሌ ነዋሪ የሆንኩ ወይዘሮ መላ ጥላዬ ስሆን የማመለ ክተውም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡ እነሆ ፍሬ ነገሩም በትናት ናው ዕለት ጎረቤቴ የሆነችው ወይዘሮ ትጓደድ መንግሥቱ፣ “ነይ ቡ ና ጠጪ!” ብላ ቤቷ ጠራችኝ፡፡ እኔም ከጉርብትናዬና ካለን የቆየ ወዳጅነታችን በመነሳት እሺ ብዬ ሄድኩኝ፡፡ ቡና ስንጠጣ ያለ ስኳ ር እንደማልጠጣ እያወቀች ባዶውን ቡና ሰጠችኝ፡፡ “ምነው አንቺ ዬ?” ስላት፣ “ስኳር ከየት ይመጣል ብለሽ ነው? እንደ ዳቦ በሰል ፍ እየገዛሁ ላምጣልሽ ወይ!?” አለችኝ፡፡ እኔም ተናድጄ፣ ደስ አ ይበላት ብዬ፣ ባዶውን ቡና ያለስኳር ልቤን እያቃጠለኝ ጠጣሁት፡፡ ከዚያ ቡናውን ጠጥቼ በጓሮ በኩል ልወጣ ስል፣ በአንድ ማዳበሪ ያ ሆኖ የታሰረ እህል አገኘሁ፡፡ ቀስ ብዬም ስነካው ጤፍ መሆኑን አ ረጋገጥኩ፡፡ ማዳበሪያውን ፈልፍዬም ሳየው ምን የመሰለ ጥቁር ጤፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ጽህፈትቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ እህል የሚያ ከማቹ ሰዎችን ጠቁሙ በማለት ባስታወቀው መሠረት ይኸው መ ጠቆሜን እያሳወቅሁ እህሉም ሃያ ኪሎ ጤፍ እንደሚደርስ ባለቤ ቷን ወይዘሮ ትጓደድን በብልሃት ጠይቄ ለማወቅ መቻሌን በትህት ና እገልጻለሁ፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዞ አንድ ኪሎ ቡና መቶ ብር እየተሸጠ በሚ ገኝበት በዚህ ወቅትም ወይዘሮ ትጓደድ ከየት አግኝታ እንዳፈላች ማጣራት እንዲካሄድ በድጋሚ እጠይቃለሁ፡፡
የገብሬ ቁምነገር ባንድ ሻሸመኔ አካባቢ በምትገኝ ኩየራ የተባለች ትንሽ ከተማ ውስጥ ብቻውን የሚኖር ሰው ነበር፡፡ የድንች እርሻውን ለመቆፈር ቢፈልግም ከማርጀቱ የተነሳ አቅም ስላጣ በእስር ቤት ለሚገኘው አ ንድ ልጁ ደብዳቤ ፃፈለት፡፡ “ውድ ልጄ ገብሬ፤ በዚህ ዓመት ድንች የምተከል መስሎ ስላልተሰማኝ ሐዘን ተሰምቶኛል፡፡ በእ ርጅና የተነሳ አቅሜ ስለደከመ እርሻው ን ለመቆፈር አልቻልኩም፡፡ አንተ እዚ ህ ብትኖር ኖሮ ትቆፍርልኝ ስለነበር አል ጨነቅም ነበር፡፡ አፍቃሪ አባትህ፤ ከኩየራ” ከ3 ቀናት በኋላ አባትየው ዝዋይ እሥ ር ቤት ውስጥ ከተቀፈደደው ልጁ የተላ ከ ደብዳቤ ደረሰው፡፡
“ውድ አባዬ ስለ እግዚሃር ስትል ያንን መሬት እንዳ ትቆፍረው! አደራ! የገደልኳቸውን 3 ሰ ዎች በሙሉ የቀበርኩት እዚያ ነው! ልጅህ ገብሬ” በማግስቱ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የክልሉ ና የፌዴራል የፀጥታ ሰዎችና ፖሊሶች በ አካባቢው ደርሰው ጠቅላላ መሬቱን ቆ ፍረውና አገላብጠው አስከሬን ፈለጉ፡፡ ነ ገር ግን ምንም ሬሳ ሊያገኙ ስላልቻሉ ሽ ማግሌውን አባት ይቅርታ ጠይቀው ሄ ዱ፡፡ በዚያኑ ቀን ሽማግሌው አንድ ደብ ዳቤ ደረሰው፡፡ “ውድ አባዬ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ላደርግልህ የም ችለው ይህን ብቻ ነው፡፡ አሁን የፈለግኸ ውን መዝራት ትችላለህ፡፡ ልጅህ ገብሬ፡፡”
“ምስኪን ፑር” ሲል ራሱን የሚጠራ ፀሀፊ “ጓደኛዬ የነገረኝ ወሬ ነው” ብሎ በፌስ ቡክ ከጻፈው የተወሰደ
እነሆ ተከፈተ፤ ምኑ? አፋችን፤ ለም ን? ለመሳቅ፡፡ በአፍሪካ የመጀመሪያ ው የሳቅ ት/ቤት በኢትዮጵያ ተከፈ ተ፡፡ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ሰሞኑን ከሚታዩ ማስታወቂያዎች አ ንዱ ይሄ ነው፤ “በአፍሪካ የመጀመሪ ያው የሳቅ ት/ቤት ተከፈተ” የሚል፡፡ ማስታወቂያው ላይ ጥርሶቹ የሚታዩ ጎልማሳ አንድ ፈረንጅ አቅፎ “ሲስቅ” ይታያል፡፡ /የሳቁ ምንጭ እርሷው ት ሆን?/ በሁለተኛው የማስታወቂያ ገጽ ደግሞ ኑሮ እና ዕድሜ ያደቀቃቸው የ ሚመስሉ ባልቴት እንዲሁ አፋቸው ን እንደነገሩ ከፍተው ይታያሉ፡፡ ጥር ሳቸው ስላለቀ እየሳቁ መሆኑን ማወቅ ይቸግራል፡፡ ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ የሳቅ ት/ቤት ባለቤት ሆናለች፡፡ እልልልልልል….! “ሳቅ” የሚለውን ቃል ከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ፈለግ ኩት፤ አጣሁት፡፡ ጉድ እኮ ነው፤ ባለ አንድ ሺ ሦስት መቶ ዘጠና ስምንቱ ገ ጽ መዝገበ ቃላት “ሳቅ” የሚለውን ቃ ል አለማካተቱ አስገራሚ ነው፡፡ “ቃ ሉ አማርኛ አይደለም ማለት ነው?” ራሴን ጠየቅኩ፡፡ ደግሜ “ሳቀ” ወይ ም “ሣቀ” በሚለው በግስ ቅርፁ ፈለ ግኩት፤ አሁንም አላገኘሁትም፡፡ እን ግዲህ “ሳቅ” ኢትዮጵያዊ አይደለም ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም በአፍሪካ የመጀመሪያ ው የሳቅ ት/ቤት ተከፍትዎልዎታል፡፡ የሚፈልጉት በየትኛው ደረጃ ነው? በ ዲግሪ? በዲፕሎማ? ወይስ እንዳቅም ዎ በሰርተፍኬት? …ከእንግዲህ ወዲያ በሆነው ባልሆነው መሳቅ፣ በሳቅ የት ምህርት ዘርፍ የተመረቀ ምሁር መገለ ጫ እንጂ የጤና መራቅ ምልክት ተደ ርጎ አይወሰድም፡፡ በዋጋ ንረት መጨነቃችን ቀጥሏል፤ ግብሩም ቀጥሏል፤ የሚሊዮኖች መራ ብም ቀጥሏል፤ ሁሉ ነገር “እንደገና” ቀጥሏል፡፡ በአፍሪካ የመጀመሪያው የ ሳቅ ት/ቤትም ተከፍቷል፡፡ “የሳቅ ንጉሥ” ተብሎ የሚታወቀ ው ወንድማችን በዓለም ድንቃድን ቅ መዝገብ ላይ ስሙ መስፈሩ ይታ ወሳል፡፡ እኔ መቼም ጠርጣሪ ነኝና፣ “የዚህ ወንድማችን ስም በዓለም ድ ንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረው ረ ዥም ሳቅ በመሳቁ ሳይሆን ኢትዮጵ ያዊ ሆኖ መሳቅ በመቻሉ ይሆን እን ዴ?” እላለሁ፡፡ “ሳር እስቃለሁ እንደ ማሽላ፣ ነገር በሆዴ እየተብላላ!”
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
19
ሐበሻዊ ቃና
የአገር ቤት ጨዋታ
ፎቶ - ኢትዮጵያን ሪቪው
በመሐመድ ሰልማን
ቢኾንም መቀሌ የሚንጧት እና ያለ ዕረፍት የሚያስደንሷት በከበሮ የደመቁ ሙዚቃዎች ናቸው፡፡ የብዙዎቹ ቅኝትና ምንጭ ግን ኤርትራ ነው፡፡
‹‹ሰላም ባስ›› ወደ መቀሌ በየዕለቱ በ ረራ ካላቸው አገር አቋራጭ አውቶቡሶ ች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ መነሻ ውን ከመስቀል አደባባይ አድርጎ የደሴ ን፣ የሐይቅን እና የወልዲያን ከተሞች አ ቋርጦ በአላማጣ እና በማይጨው ጋራ ዎች ሰንጥቅ መቀሌ ለመግባት ሁለት ቀ ናት ይወስድበታል፡፡ ይህን አድካሚ ጉ ዞ ቀላል ለማድረግ ‹‹ሰላም ባስ›› ተንቀሳ ቃሽ ፍሪጅ፣ የሙቀት መቆጣጠሪያ እና የጥንቃቄ ቀበቶ ለተሳፋሪዎቹ አዘጋጅቷ ል፡፡ ከዚህም ባሻገር በውስጡ ሁለት የ ማይታክቱ የቴሌቪዥን ስክሪኖች ተገጥ መውለታል፡፡ ቴሌቪዥኖቹ ከተጨቆኑ ቀልዶች አንስተው ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ውዳሴ እስከተዜሙ የትግ ርኛ ዜማዎች ድረስ ተሳፋሪዎቻቸውን ያስኮመኩማሉ፡፡ በዚህ የ780 ኪሎ ሜ ትር የመቀሌ ጉዞ ተጓዡ ከቴሌቪዥኖቹ በብዛት እንዲኮመኩም የሚጋበዘው ግን የኤርትራ ሙዚቃዎችን ነው፡፡ በአመዛኙ በኤርትራ ሙዚቃዎች የሚ ታጀበው የሁለት ቀናት ጉዞ ሲጠናቀቅ ም ቢኾን ዉቧ መቀሌ የራሷን ዜማዎች አሰናድታ አትጠብቅም፤ ይባስ ብላ እሷ ም በኤርትራ ቅኝት ያለዕረፍት ትደንሳ ለች፡፡ ይህ ኹኔታ አሥመራ ተወልዶ ላደገው ጸጋዬ ገብረ ትንሣኤ የፈጠረበት ስሜት ከአግራሞትም በላይ ነው፡፡ ለ23 ዓመ ታት በኤርትራ ሲኖር ራሱን ከሙዚቃ ነጥሎ አያውቅም፡፡ ከሁለቱ ጎረቤት አገ ራት የከረረ ጦርነት በኃላ ግን ኢትዮጵያ ዊ የትግርኛ ሙዚቃዎችን በአሥመራ ሊ ሰማቸው አልታደለም ነበር፡፡ በኤርትራ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን በይፋ መስማ ት ክልክል መኾኑን የሚናገረው ጸጋዬ ከ
ሦስት ዓመታት በኃላ በቀይ መስቀል እር ዳታ ለእናቱ አገሩ ሲበቃ ተመሳሳይ ኹኔ ታ እንደሚያጋጥመው እርግጠኛ ነበር፡፡ ኾኖም መቀሌ ከተማ ሲደርስ ያጋጠመ ው የተገላቢጦሹ ነው፡፡ ጸጋዬ ‹‹ አርነት እና ሰማዕታት›› በሚባ ሉት የአሥመራ ጎዳናዎች ዘወትር የሚ ንቆረቆሩት የኤርትራ ዜማዎች ‹‹ የጠላ ት አገር›› ተብላ በምትፈረጀው መቀሌ አሁንም አሁንም በየሄደበት ሁሉ ሲደመ ጡ ያለበትን እስኪጠራጠር ድረስ ተገር ሟል፡፡ ጸጋየ ግርምቱን ‹‹ዘይሕሰብ ነገ ር!›› በማለት ነው የሚገልፀው፡፡‹‹ የማይ ታሰብ ነገር!›› ከኢትዮጵያ ታላላቅ ከተሞች ተርታ የ ምትመደበው መቀሌ በ2001 ዓ.ም ይፋ በሆነው የሕዝብ ቆጠራ መሠረት 215 ሺ ህ ነዋሪዎችን ታቅፋለች፡፡ በዛ ካሉ መዝ ናኛ ሥፍራዎቿ በሁሉም አቅጣጫ የሚ ሰሙት በከበሮ የደመቁ ሙዚቃዎች ከ ተማዋን ያለ ዕረፍት ያስደንሷታል፣ይን ጧታል፡፡ ምንም እንኳ የብዙዎቹ ቅኝት ና ምንጭ ከኤርትራ ቢኾንም፡፡ በከተማዋ ዘመናዊ የምሽት ክበቦች ው ስጥ አንዱ በኾነው ‹‹ክለብ አቢሲኒያ›› ሙዚቃ የሚያጫውተው ‹‹ዲጄ›› አማኑ ኤል በከተማዋ ስም ካላቸው የሙዚቃ አጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ ዐማኑኤል በል ዩ ልዩ ዝግጅቶች እና በየምሽቱ ከሚያ ጫውታቸው ሙዚቃዎች በአማካይ 90 ከመቶ የሚኾኑት የኤርትራ ሙዚቃዎች እንደኾኑ ይናገራል፡፡ በስተኋላ ላይ ግን ይህ ኹኔታ የተወሰነ መሻሻል እያሳየ እ ንደ ኾነ ያስባል፡፡ ‹‹ በአንድ ምሽት እስ ከ አምስት የሚደርሱ የእኛን አገር የትግ ርኛ ሙዚቃዎች ለመቀላቀል እሞክራለ ኹ›› ይላል አማኑኤል፡፡
ዲጄ ዐማኑኤል በከተማዋ ያለው የኤር ትራ የሙዚቃ የበላይነት በሙዚቃ ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን ይገልጻል፡፡ እርሱ በንብረትንት የሚያስተዳድረው የቪሲ ዲ ማከራያ እና ማከፋፈያ ማዕከል ብዙ ዎቹ ደንበኞች የሚፈልጉት ከትግርኛ ሥ ራዎች ይልቅ የኤርትራ ድራማዎችን እና ፊልሞችን ነው፡፡ በመቀሌ ከተማ ያሉት የሙዚቃ ቤቶች ከዐማኑኤል ሐሳብ ጋር የሚጣጣም ሥ ራ የሚሰሩ መኾናቸውን የሚመሰክር የ ራሳቸው የዕለት ዕለት ትዕይንት ይስተዋ ልባቸዋል፡፡ ብዙ መደብሮች ‹‹አዲስ የኤ ርትራ ድራማዎች አስገብተናል›› የሚሉ ማስታወቂያዎችን ከደጆቻቸው ያስደም ጣሉ፤ የውስጠኛው ገጽታቸውም ይህን ኑ እውነታ በሚያዉጁ ማስታወቂያዎች የተሞላ ነው፡፡ የከተማዋ ሰፋፊ ካፊቴሪያዎች እና ድራ ፍት ቤቶችም በየሳምንቱ የዕረፍት ቀና ት ደንበኞቻቸውን የሚያስኮመኩሙት ከኤርትራ የሚሠራጨውን ‹‹ሞይዛክ›› የ ተሰኘውን የሙሉቀን የቴሌቪዥን ፕሮ ግራም ነው፡፡ በእነዚህ ቀናት የኢትዮጵ ያ ቴሌቪዥን ሥርጭቶቹን የሚያስተና ግድ ካፌ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ከዓመታት በፊት በኤርትራ ቴሌቪዥን ዘወትር ዐርብ እና እሁድ ይተላለፍ የነበ ረው ተከታታይ ድራማ የከተማዋን ነዋ ሪ ቀልብ ገዝቶ ነበር፡፡ ይህ ‹‹ዝባን ሕጊ›› (በህግ አምላክ እንደማለት ነው) የተሰኘ ው ተከታታይ ድራማ ይቀርብ በነበረበ ት ወቅት ብዙዎቹ የከተማዋ መዝናኛ ቤ ቶች በተመልካች ይጨናነቃሉ፡፡ አንዳን ዶቹም ድራማው በሚታይበት ወቅት ለ ሚሰጡት ማንኛውም አገልግሎት ተጨ ማሪ ክፍያን ይጠይቁ ነበር፡፡ ‹‹ዝባን ሕ
“
‹‹አይደል?›› ለማለት ‹‹ሙሽ?››፣ ‹‹እሺ›› ለማለት ደግሞ ‹‹ሃራይ››…ወዘተ የእኛ ትግርኛ ያልኾኑ ነገር ግን አሁን በስፋት የተለመዱ ውርስ ቃላት ናቸው
ጊ›› የከተማችን ፕሪምየር ሊግ ኾኖ ቆይ ቶ ነበር›› ይላል በወቅቱ የነበረውን ኹኔ ታ የሚያስታውሰው የከተማዋ ነዋሪ አ ታኽልቲ ገብረ ሕይወት፡፡ የመቀሌ የቪሲዲ ማከራያ መደብሮች ም ቢኾን ከአገር ውስጥ የትግርኛ ሙዚ ቃዎች እና ሌሎች የጥበብ ሥራዎች ይል ቅ በኤርትራ ፊልሞች እና የሙዚቃ ክሊ ፖች የተሞሉ ናቸው፡፡ ከኤርትራ ቴሌቪ ዥን እየተቀዱ በሲዲ ተዘጋጅተው በመ ላው ትግራይ በሺዎች የሚሰራጩት እነ ዚህ ልዩ ልዩ የጥበብ ሥራዎች መቀሌን እምብርታቸው ያደረጓት ይመስላሉ፡፡ ዐ ማኑኤል ‹‹ የኤርትራ ‹MP3›ዎች እና የዘ ፈን ክሊፖች ከአዲስ አበባ ጭምር እየተ ዘጋጁ ወደ መቀሌ ይላካሉ›› ይላል በመ ደብሩ የ‹‹ላየንስ›› እና የ‹‹ኢቫንጋዲ›› ሪከ ርድስ ዓርማን የያዙ ብዛት ያላቸው ሲዲ ዎችን እያመለከተ፡፡ እንደ አማኑኤል ገለ ጻ ትልልቅ አሳታሚዎች ጭምር በዚህ ዘ ርፍ መሠማራታቸው የኤርትራ ሙዚቃ ዎች በክልሉ ያላቸውን የገበያ ስፋት እና ተቀባይነት የሚያሳይ ነው፡፡ የመቀሌ ነዋሪ የኾነው አታኽልቲ የኤ ርትራ ሙዚቃ ለትግራይ ሕዝብ ባለው የቋንቋ ቅርበት ምክንያት ተቀባይነት እ ንዳገኘ ይገምታል፡፡ ‹‹ሙዚቃ ድንበር የ ለውም›› የሚለው አታኽልቲ ተመሳሳይ ቋንቋ በሚናገሩ ሕዝቦች መካከል ይህን ያህል መወራረስ መከሠቱ አስገራሚ እ ንዳልኾነ ያምናል፡፡ ከሙዚቃ እና ድራ ማዎች ባሻገር የኤርትራውያን የኾኑ ቃ ላትም ሰርገው እንደገቡ አታኽልቲ እን ደማስረጃ ያቀርባል፡፡ እንደ ምሳሌም በ መቀሌ እና አካባቢዋ የሚዘወትሩ ቃላ ትን ይጠቅሳል፡፡ “‹‹አይደል?›› ለማለት ‹‹ሙሽ?››፣ ‹‹እሺ›› ለማለት ደግሞ ‹‹ሃራ
ይ››…ወዘተ የእኛ ትግርኛ ያልኾኑ ነገር ግ ን አሁን በስፋት የተለመዱ ውርስ ቃላ ት ናቸው፡፡” የኤርትራ ኮከብ ድምፃዊ የነበረው አብ ርሃም አፈወርቂ ድንገተኛ ሞት ሲሰማ በ መቀሌ ትልቅ መነጋገርያ እንደ ነበር የሚ ያስታውሰው አታኽልቲ ይህም የሕዝቦ ቹን ትስስር አጉልቶ የሚያሳይ እንደ ኾ ነ ይሞግታል፡፡ 23 ዓመታትን በአሥመራ ቆይታ ያደረ ገው ጸጋዬ ገብረ ትንሣኤ የግጥም እና የ ዜማ ደራሲ ነው፡፡ ሥራዎቹን ስማቸው ጎልተው ለሚወሱ የኤርትራ ድምፃውያ ን አበርክቷል፡፡ እንደ እርሱ አመለካከት የትግርኛ ዘፈኖች ከኤርትራ ሙዚቃዎች የማይተናንስ አቅም አላቸው፡፡ ‹‹ችግሩ በስፋት ለመደመጥ ቦታ አለማግኘታቸ ው ነው›› ባይ ነው፡፡ ጸጋዬ በኤርትራ ቆይታው የአብረሃም ገ ብረ መድኀንን ‹‹ምግበይ›› የተሰኘውን አ ልበም ከእንግሊዝ አስመጥቶ አሥመራ ውስጥ ለማሰራጨት ቀዳሚ እንደነበር ይናገራል፡፡ ያን ጊዜ የሙዚቃውን ከፍ ተኛ ጥራት እና ተቀባይነት ተከትሎ ሰዎ ች ድምፃዊው ‹‹ኤርትራዊ ልጃችን ነው›› በማለት እስከ መከራከር ደርሰው እንደነ በር ይተርካል፡፡ የትርሃስ ታረቀኝን ‹‹ ኮበለይ›› የተሰኘ ውን ተደማጭ ሙዚቃ የስቱዲዮ ቀረጻ እና የድምጽ ተዋሕዶ (ሚክሲንግ) ሥራ የሠራው የትግርኛ ሙዚቃ አቀናባሪው ፍቅረ ተሾመ በበኩሉ በትግራይ የሚታ የው የኤርትራውያን የሙዚቃ የበላይነ ት ብዙ አይቀጥልም፡፡ ፍቅረ ‹‹ተስፋ የ ሚጣልባቸው ዕምቅ አቅም ያላቸው ዘ
ወደ ገጽ 21 ዞሯል
20
ሐበሻዊ ቃና
በምን እንዝናና?
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሱዶኩ
ና?
ዝና ን እ ን ደ ሄ የት
ከ 1 እስከ 9 ያሉ ቁጥሮችን በባዶ ቦታዎች ውስጥ ያስገቡ፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ መደዳ እና እያንዳንዱ 3 x 3 የሆነ ሳጥን ከ 1 እስከ 9 ያሉ ቁጥሮችን ይይዛል፡፡አንድን ቁጥር በባዶ ቦታዎች ላይ ሁለት ጊዜ ደግሞ ማስገባት አይቻልም፡፡ መልካም ጨዋታ
ዩጋንዳ ሙዚቃ
የወርልድ ሙዚቃ ኮንሰርት
መቼ፦ ነሐሴ 27 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ ካምፓላ ሴሬና ሆቴል ሰዓት፦ ከምሽቱ አንድ ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ 50 ሺህ ሽልንግ
ሞውሪስ ኬይራ የ“ወርልድ ሙዚቃ” ስልትን ከሚጫወቱ ጥቂት ኡጋንዳውያን አን ዱ ነው፡፡ እንደ አማርኛው “ባለ ጋሪው” መልዕክት ባለው “ቦዳ ቦዳ” ዘፈኑ ይበልጥ ይታወቃል፡፡ በቅርቡ “ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል” (አር.ኤፍ.አይ) ከተሰኘው ዕው ቅ የፈረንሳይ ሬድዬ ጣቢያ ሽልማት የተበረከተለት ሞውሪስ በተለያዩ ሀገራት ዝግጅ ቶቹን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ከድምጻዊነቱ ሌላ ጥሩ ጊታር ተጫዋች የሆነው ሞውሪስ የመድረክ ዝግጅቶቹን የሚያቀርበው በጊታሩ ታጅቦ ነው፡፡ ማስታወቂያ
የስራ ማስታወቂያ ሐበሻ ኮሚዩኒኬሽንስ ሊሚትድ በየ15 ቀኑ ለሚያሳትመው “ሐበሻዊ ቃና” ጋዜጣ ዘጋቢዎችን ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ “ሐበሻዊ ቃና” በኡጋንዳ፣ በኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ ሲሆን በሶስቱ ሀገራት ላሉ አማርኛ አንባቢዎች የሚቀርብ ነው፡፡ ድርጅቱ በእነዚህ ሶስት ሀገራት ዘጋቢዎችን ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ፊልም
መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ) ሲኒፕሌክስ በዚህ እና በቀጣዩ ሳምንት ከሚያሳያቸው ፊልሞች መካከል Winnie the Pooh የካርቱን ፊልም እና Super 8 የሳይንስ ፊክሽን ይገኙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የ X-Men ተከታታይ ፊልም የሆነው X-Men፡ First Class እና Hanna ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ኬንያ
ተፈላጊ ችሎታ:l l l l
በሲኒማ ቤት
በየሀገራቱ በየጊዜው የሚደረጉ ክንውኖችን ተከታትሎ መዘገብ የሚችል (የምትችል) መረጃዎችን መሰብሰብ እና ማጠናቀር የሚችል (የምትችል) ጥሩ የመጻፍ ችሎታ ያለው (ያላት) የኮምፒዩተር እና ኢንተርኔት ዕውቀት ያለው(ያላት)
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ:-
ፊልም
የአሲአን ፊልም ፌስቲቫል
መቼ፦ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ አሊያንስ ፍራንሴዝ ሰዓት፦ ከምሽቱ አስራ እንደ ሰዓት ተኩል እና አንድ ሰዓት ተኩል መግቢያ፦ በነጻ
ከታይላንድ- ነሐሴ 10
ከማሌዥያ - ነሐሴ 10
ከታይላንድ - ነሐሴ 11
ከፊሊፒንስ - ነሐሴ 11
ከታወቀ ዮኒቨርስቲ/ኮሌጅ በጋዜጠኝነት፣ ማስ ኮሚዩኔኬሽን፣ ቋንቋ እና ስነ ጽሁፍ ወይም ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች ተመርቆ ቢያንስ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው (ያላት) አስራ ሁለተኛ ክፍል ጨርሶ(ሳ) በዘጋቢነት ቢያንስ ሶስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው (ያላት)
ደመወዝ:- በስምምነት አመልካቾች ካሪኩለም ቪቴ (ሲቪ)፣ የትምህርት እና የስራ ማስረጃዎችን ኮፒ እንደዚሁም ቢያንስ ሁለት የጸሁፍ ናሙናዎችን በድርጅቱ የፖስታ ወይም ኢሜይል አድራሻ አያይዘው እስከ መስከረም 5 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ መላክ ይገባቸዋል፡፡
አድራሻ Habesha Communications Ltd P.O.Box 28268 Kampala, Uganda habeshawikana@gmail.com
የደቡብ እስያ ሀገራት (አሲያን) ቀንን ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2003 ዓ.ም የታይላንድ፣ ማሌዥያ እና ፊሊፒንስ ፊልሞች በአሊያንስ ፍራንሴዝ አዳራሽ ው ስጥ ለዕይታ ይበቃሉ፡፡ በ0727 600622 ወይም በ0727 340045 ደውለው ስለፊ ልሞቹ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
አዳም ረታ... ጋር አይገናኝም፡፡ ወደ ሌላ ጋላክሲ መብ ረርና በሎንቺና ስንዴ ለመግዛት ተፍኪ መውረድ የተለያዩ ናቸው፡፡ በራሴ ማህ በራዊና መልካምድራዊ ማጣቀሻ የሚያ ጫውተኝ ነው የፈለኩት፡፡ ሌላኛው የመንፈስ አባቴ ይሄ ሊሆን ይ ችላል፡፡ ዛሬ በምፅፍበት ጊዜ ያኔ በልጅ ነቴ ምን ምን እንዳሰላቸኝ አውቃለሁ፡ ፡ የምጓዝበት መንገድ ሁሉ በኩርባ የተ ሞላ ነው፡፡ ማንኛውንም ያነበብኩት ደ ራሲ ባለፈበት እንዳላልፍ ስጠመዘዝ ነ ው የምውለው፡፡ ይሳካ አይሳካ ኪዳነም ህረትና ቅን ዚቀኛ ያውቃሉ፡፡ በሆነ አያ ኖ አንዳንድ ያሰላቹኝም ይሁኑ ያላሰላቹ ኝ የቀድሞ ደራሲያን የምጓዝበትን ካር ታ ሰርተውልኛል፡፡ የደረሰብኝ ተፅዕኖ ይሄ ነው፡፡ ‘የበላይ ጠባቂ ደራሲ’ ሲባል ደሞ ከዛ ብዙ የማይርቅ ጥያቄም አለ፡፡ ‘የእሱ ተ ፅዕኖ አለብህ?’ የሚል፡፡ ‘አከሌ ተፅዕኖ አለበት’ ሲባል አሳሳቢ ው ወይም አከራካሪው ተፅዕኖ መኖሩ አ ለመኖሩ ሳይሆን በዚህ አባባል ጠቅላላ የግለሰቡ ወይም የተጠያቂው ደራሲ ል ፋት የሚዘነጋበት ጊዜ ሰለአለ ነው፡፡ ለ መሆኑ አንድ ደራሲ ራሱን መሆን አቁሞ ሌላ ደራሲ የሚመስለው መቼ ነው? የ
“
ከገጽ 19 የዞረ ሚለውን ጥያቄ መመለስ አዳጋች ነው፡ ፡ ከባድ ጥናት ወይ አፍረተቢስ አሉባል ታ ሊመልሰው ግን ይችላል፡፡ ምርጫው እንደግለሰቡ ነው፡፡ ዋናው ነጥብ ግን የ ደራሲውን የመምረጥ ፈቃድ (freewill) መተናኮስ ወይም መዘንጋት ይሆናል፡፡ የ ምንወለድበት የምንማርበት ሕብረተሰ ብ በተለያየ መንገድ የተያያዘና መረጃ የ ሚለዋወጥ አካል ስለሆነ የት ጋ ነው የአ ንዱ ደራሲ ዘይቤና አሰራር በሌላ ደራ ሲ ተጠልፎ የሚወሰደው ብለን ብንጠ ይቅ ከመልሱ ይልቅ ግምቶች ውስጥ አ ንገባለን፡፡ መገንዘብ የሚገባን የመፃፍ አቃቂር ከ “እመ ኅበ አልቦ” አለመፈጠሩ ነው፡፡ ስ ንወለድ ቋንቋ ዘዬና ፊደል ያለበት ህብረ ተሰብ ውስጥ ነው የምንመጣው፡፡ ተረ ት የማውቀው ተረት አንብቤ ወይም ሰ ምቼ ነው፡፡ የተረት ጉርሻ በጉንጬ ይዤ አልተወለድኩም፡፡ ወይም እትብቴ ላይ ቋጥሬ አልወጣሁም፡፡ በተለያየ ደረጃና መልክ ደራሲው ራሱንና ውጩን ነው፡፡ በልማዴ አንድ ሮማንቲክ ደራሲን ወይ ም የሆነ ናቹራሊስት ደራሲ ወይም ሌላ አይነት ባነብና ብወደው ተጠርጌ አልወ ሰድም፡፡ ሁልጊዜ ወደ ራሴ እመለሳለሁ፡ ፡ የምሰፍረው እራሴው ኢጎ(ego) ውስ
21
ሐበሻዊ ቃና
ጥ ነው፡፡ ምናልባት ‘ነፃ’ ደራሲ ለመሆ ን የሆነ ኢጎ ይጠይቃል፡፡ በሌሎች ታላ ቅነት የማይበረግግ፡፡ ከሌሎችም ስማቸ ው ከተጠራ ተወዳጅ ስህተቶችና ስኬቶ ች ጋር አብሮ የማይሄድ፣ ቢረባም ባይረ ባም የራሱን እድሞ ሰርቶ የሚጠለል፡፡ በሕይወቴ ብዙ ሰዎች በህብረት ሲሳሳ ቱ አይቼአለሁ፡፡ ሰዎችን ተከትዬ ተሳስ ቼአለሁ፡፡ ቆይቶ የምረዳው እውነት ግን ይቺ በራሴ የስሜት ህዋሳቶች የተገነዘብ ኳት ናት፡፡ ያቺ ጠይቄ የተሰማችኝና ያሰ ብኩባት ናት፡፡ አልፎ አልፎ በተቀራረበ ሰሞን የምፅፋቸው ድርሰቶች የሚቀባበ ሉዋቸው ቃላት ወይም ድምፆች ይኖራ ሉ፤ አንዳንድ ጊዜም ኩነት ይሆናል፡፡ ከ ራሴ ወደ ራሴ የሚመጣውን ቅብብል እ ንኳን አልወደውም፡፡ ከራሴም ጋር ሳላ ቋርጥ ‘መባጠስ’ አለበኝ፡፡ እና ብዙ ጊዜ አርትኦት ስሰራ አላማዬ ይሄን ዳና የመ ሰረዝ ነው፡፡ የሚገርው ራስህን ለመሆን ከባድ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እ ዚህ ነህ፡፡ ‘ስታይል ሰውዬው ነው’ ይላ ሉ ፈረንጆች፡፡ በንባብ ካሳለፍኩት ልምድ ልርቅ የም ጥርበት አንዱ መንገድ ክሌሼ (ንትብ ቋ ንቋ) ባለመጠቀም ነው፡፡ ግን ከመጠቀ ም ስትገሸሽ ቀድሞህ የነበረውን የአፃፃ ፍ ስርአት ማለት ‘አባቶችህ’ የዘሩትን ሳ ር ከምትግጥበት መስክ በሆነ መልክ ራ ቅህ ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል ዘዬዎ
ችህን ለመቀበል የሚጠበቅብሀን ታሪካ ዊ ሃላፊነትን (እንዲህ የሚከራከሩ ሊኖ ሩ ይችላሉ) መዘንጋትና ለተግባቦት ረዥ ም ጊዜ የተቀመጠውን የልዋጭና የንጽ ጽር መረብ መፈታተን ነው፡፡ ሩሲያዊው ፎርማሊስት ቪክቶር ሽኮሎቭስኪ ዲፋ ሚሊያራዜሽን (defamiliarization) ይ ለዋል፡፡ በአማርኛ ‘እንግዳ ማድረግ’ ልበ ለው? አንድ አባባል ሲለመድ ወይም ሲ ሰለችህ የምትወደውን ነገር ሁሉ ሊያበላ ሽብህ ይችላል፡፡ ኪነጥበብ አንዱ ግቡ በ መሰላቸት የጠፋብህን ነገር፣ ልምድ የመ ሳሰለ መልሶ ሕይወት መስጠት ነው፡፡ እ ንደ ሽኮሎቭስኪ እምነት የኪነጥበብ ዋ ናው ግቡ ይሄ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ፎርግ ራውንዲንግ (foregrounding) ይሉታ ል፡፡ እኔ እዚ ነገር ላይ ብቻ አተኩራለ ሁ ማለቴም አይደለም፡፡ ሃሳቡን ነው፡፡ ሕግ የሚባል እንዳለ ሳላውቅ፣ ቢኖሩ ም ሳይገቡኝ ነው መፃፍ የጀመርኩት፡፡ ያኔ የዘሪሁን አስፋው “የልብወለድ አላ ባውያን”ና የብርሃኑ የግጥም ግንዛቤ መ ስጫ መጽሐፍት አልነበሩም፡፡ አንዳንድ ቢኖሩም ግዕዝኛቸው እንደ ግድግዳ ስለ ሚሆን ብዙ አያስቀርቡኝም፡፡ ለዚያን ጊ ዜው መፃፍ ለጀመረው እኔ ሕጎች የተባ ሉት ልክ እንደ አየር ሕይወቱ ውስጥ በነ ፃ የታደሉ ነበሩ(ዛሬም ጭምር)፡፡ እስከ አሁንም ድረስ የማላውቃቸው ብዙ ሕጎ ች አሉ፡፡ ስላላወቅኋቸውም አላፍርም፡፡
ምክንያቱም የተሰራበት ወይም የሚሰራ በት ቢሆንም በራሴ ልፋት ላገኛቸው እ ንደምችል ስለማምን ነው፡፡ እንዳንዴም ከሰራሁባቸው በኋላ የማውቃቸው ሕጎ ች አሉ፡፡ ድርሰቴን ፅፌው ካለቀ በኋላ የምለካው ውስጤ በሚሰማኝ ስሜት ነ ው፡፡ ያንን ሴንሴቢሊቲ ማንም ቀዳሚ ደራሲ ወይም ሃያሲ ሊያስተምርህ ወይ ም ሊተካው አይችልም፡፡ የማውቀው ያ ንን ነው፡፡ እነ እከሌ ያደርጉታል ብዬ ህ ልዮ ተበድሬ በዛ መልክ ልፃፍ አልልም፡፡ ለምሳሌ ሎሬት ፀጋዬ ‘የፀጋዬ ቤት’ን የ ፈጠረው ከስሜቱ ይመስለኛል፡፡ ከበደ ሚካኤል ‘ከበደ ቤት’ ን ሲገጥሙ ከስሜ ታቸው የመጣ ይመስለኛል (ባልሳሳት እ ሳቸውም ስም አልሰጡትም ነበር መሰለ ኝ)፡፡ እስኪ ‘ከበደ ቤት’ የሚባል ልፍጠ ር ብለው አንድ ጠዋት አልተነሱም፡፡ የ ልብህን ምት ከተከተልክ የምትደርስበት የራስህ ቦታ አለ፡፡ ሰፈሬ ከበቀለ ዋርካ ላይ ዘልዬ ብወርድ እግሮቼ የሚያርፉት ማርስ ወይም ጁፒተር አይደለም፡፡ ዛሬ አንዳንዶቹን ወደርየለሽ ናቸው ብ ዬ አነባቸው የነበሩትን ልብወለዶች ካጋ ጠሙኝ ተመልሼ አነባለሁ፡፡ የሆነ ውለ ታ አለብኝ ማለት ነው፡፡ ውለታቸውን የምከፍልበት መንገድ ግን እንደእነሱ አ ስመስዬ በመስራት አይደለም፡፡ ሳደርግ ራሴን ሰርዤ አይደለም፡፡ በራሴው መን ገድ ነው፡፡
ማንኛውንም ያነበብኩት ደራሲ ባለፈበት እንዳላልፍ ስጠመዘዝ ነው የምውለው፡፡ ይሳካ አይሳካ ኪዳነምህረትና ቅን ዚቀኛ ያውቃሉ፡፡
ቺካሪቶ... ከገጽ 23 የዞረ
ሔርናንዴዝ:- ወደባዕድ ሀገር ሄዶ መ ጫወት ምንጊዜም ካባድ ነው:: ነገር ግን የአባቴ እና እህቴ አብረውኝ ሊኖሩ መ ምጣት ትልቅ እገዛ አደርጎልኛል:: ነገሮ ችን በጣም ወደቀላል ለውጦልኛል:: በ እርግጥ እኔ ከሜክሲኮ የሚናፍቀኝ ነገ ር ምግብ እና ባህል ሳይሆን ቤተሰቤ ነ ው፣ ማታ ማታ ተሰብስበን አንድ ላይ የ ምናወራው::
ጥያቄ:- እንግሊዘኛ ቋንቋ መና ገርህ የረዳህ አይመስልህም?
ሔርናንዴዝ:- እንደመጣሁ ጥሩ እናገ
ር ነበር:: ከዚያም ቀስ በቀስ የተሻለ መር ዳት እና መናገር ጀመርኩ እወነቱን ለመ ናገር እንግሊዝኛ ማወቄ በደንብ ጠቅሞ ኛል:: በመልበሻ ክፍል ከቡድን አጋሮ ቼ ጋራ በቀላሉ እና በፍጥነት እንድግባ ባ ረድቶኛል::
ማንችስተር ስመጣ ደግሞ ይኼው ቁጥ ር ክፍት ሆኖ ጠበቀኝ:: በሚደንቅ ሁኔ ታ አባቴ ከሜክሲኮው ፑኤብላ ጋራ ሻ ምፕዮን ሲሆን 14 ቁጥር ለብሶ ነበር:: እ ና የታሰበበት ጉዳይ ባይሆንም ጥሩ አጋ ጣሚ ነው::
ን አውቅ ነበር:: ከዚያ በተጨማሪ አባቴ ሲጫወት እመለከት ነበር፡፡ አያቴ ደግሞ በእነርሱ ጊዜ ስለነበረው ጨዋታ ይተር ክልኛል:: እንደዚህ አድገህ ደግሞ ኳስ ተ ጨዋች አለመሆን ይከብዳል::
ጥያቄ:- እግር ኳስ እንዴት ጀ መርክ፣ ፍቅሩስ ከየት መጣ?
ጥያቄ:- ልጅ ሆነህ ያንተ ተምሳሌት ወይም ጀግናህ ማን ነበር?
ሔርናንዴዝ:- የእድል ጉዳይ ነው (ሳ ቅ):: መጀመርያ ለቺቫስ ስጫወት 45 ቁ ጥር ተሰጠኝ፣ ከዚያ 25:: ቀጥሎ አንድ ተጨዋች ክለቡን ሲለቅ 14 ቁጥር መል በስ ጀመርኩ:: እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዓለ ም ዋንጫ ላይ ሚጉዌል ሳባህ በመጎዳ ቱ 14 ቁጥር እንድለብስ ተደረግሁ:: ወደ
ሔርናንዴዝ:- ሁሉም የቤተሰቤ አባል እንደሚነግረኝ ከሆነ ከሕፃንነቴ ጀምሮ ኳስ መጫወት እወድ ነበር:: በየሳምንቱ ግጥሚያዎች ለማየት ስታዲየም እገባ ነ በር:: የተጨዋቾችን ስም እና የማሊያ ቁ ጥር እይዛለሁ:: ሕይወቴ በሙሉ በእግ ር ኳስ ዙርያ ያጠነጠነ ነበር፣ ስለጨዋ ታው ከማውራት አልፎ እስከመጫወት ድረስ:: ፕሮፌሽናል ተጨዋች እንደምሆ
ሔርናንዴዝ:- ሁሉንም ተጨዋቾች እ መለከታለሁ፣ አንድ የሆነ የሚያስደስት ነገር ሲያደርጉ ካየሁ እቤት እመጣና ያ ንን ለማድረግ እሞክራለሁ:: የእኔ ጀግኖ ች ሁልጊዜም አባቴ እና አያቴ ሲሆኑ ወ ደፊትም ሆነው ይቀጥላሉ:: ከእነርሱ ባ ሻገር እርሱን ለመምሰል የምጥረው የብ ራዚሉ ሮናልዶን ነው:: ሮናልዶ ታላቅ ተ ጨዋች እንደሆነ አስባለሁ፣ በርግጥ ለዐ
ጥያቄ:- እስኪ ወሬያችንን ቀየ ር እናድርግ:: ለክለብ እና ብሔ ራዊ ቡድን 14 ቁጥር ማሊያ እንዴት ልትለብስ ቻልክ?
የድንቅነሽ...
መመረሽ፣መፈረሽ... ከገጽ 8 የዞረ
ከገጽ 8 የዞረ
ፎቶ - ዴይሊ ኒውስ
ና ውኃ አይቆርጡባችሁም» ?«ብዙ ጊዜ መብራቱን እንጂ ውኃውን መቁረጥ ያስ ቸግራቸዋል፡፡ የሮም ሕንፃዎች የድሮ ሕ ንፃዎች ናቸው፡፡ የውኃ መሥመሩ በቀላ ሉ አይገኝም፡፡ መብራቱን ግን ቢቆርጡ ትም እንቀጥለዋለን፡፡ አንድ ልጅ እንዲያ ውም በዚያ ምክንያት ሥራ አግኝቷል፡፡» «መብራት በመቀጠል?» «አዎ፤ የቤቱን መብራት ሲቆርጡት በመንገድ ከሚያል ፈው መብራት ሌሊት ቀጠለው፡፡ ፖሊ ሶቹ ሲመጡ ይበራል፡፡ ሄደው ከዋናው ማጥፊያ ቢያለያዩትም ይበራል፡፡ አይተ ው ስለማያውቁ ግራ ገባቸው፡፡ በኋላ ከ መንገዱ መብራት መቀጠሉን ሲያዩ እን ዴት ሊቀጠል እንደቻለ ማመን አልቻሉ ም፡፡ እና ትተውት ሄዱ፡፡ ይሄው ፏ ብ ሎልሃል፡፡ ልጁም ታድያ ኤሌክትሪክ ሠ ራተኛ ሆኖ ቀረ» «ሴቶች ሲኞራ ቤት ይሠራሉ አልከኝ፤ ወንዶችስ ምን ይሠራሉ?» «ወንድ ከሆን ክ አልፎ አልፎ ነው ሥራ የምታገኘው፡፡ ችግር አለ፡፡ አንዱ አበሻ ሲርበው ሴት ነ ኝ ብሎ ሲኞራ ቤት ተቀጥሮ ነበር አሉ፡ ፡» «እውነትክን ነው ወይስ ቀልድ ነው» «እኔ ሲያወሩ ነው የሰማሁት፡፡» «እሺ ከ ዚያስ» «ልጁ ጢም የለውም፤ መልኩ የ ሴት ድምጽ ነው፡፡ እንዲያው ልጆች በሌ ላ ነገር ይጠረ ጥሩታል» «ምን ብለ» «ነገ ርዬው የለውም ይሉታል» «እሺ»
በሊቢያ ያለውን አለመረጋጋት የሸሹ 500 የሚጠጉ ስደተኞች ማዕበል ታግለው በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው ባለፈው ግንቦት ጣልያን የገቡት
«እና ጉልበታም ነው፤ ሥራዋን ፉት፣ ጭጭ ነበር አሉ የሚያደርጋት፡፡ አንድ ቀን የሽንት ቤቱን በር ሳይዘጋው ረስቶ ት፣ ቆሞ ሽንቱን ሲሸና ሲኞራው በሩን ሲ ከፍት ፌንት ወጣ አሉ፡፡ ነፍሷ ደሞዟን ሳትቀበል ከቤት ወጥታ ጠፋች፡፡ በኋላ ግን እንደዚያ ያደረገው ሥራ ስላጣ መሆ ኑን ሲኞራው ሲሰማ አድንቆ ካምፓኒው ውስጥ ቀጠረው አሉ» «ተው እባክህ፤ ይሄን የመሰለ ፊልም አ ይቻለሁ፤ ሲኮምኩ ይሆናል» «ኩምክና አይደለም፤ የሆነ ነው ብለውኛል» «እሺ ይህንን ሁሉ ባሕር አቋርጦ የመ ጣ ሰው መጨረሻው ምንድን ነው?» «ወይ ትመርሻለህ፣ ወይ ትፈርሻለህ፣ ወ
ይ ትደነብሻለህ» «ምንድን ነው መመረ ሽ፣ ምንድን ነው መደንበሽ፣ ምንድን ነ ው መፈረሽ» «ጣልያን ለመኖር የሚመጣ የለም፣ ስለ ዚህ ትንሽ ገንዘብ ነገር ቆጣጥረህ ወደ እ ንግሊዝ ትሻገራለህ፤ ይኼ መመረሽ ይባ ላል፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ እዚሁ የመኖርያ ፈቃድ አወጥተህ የተሻለ ሥራ ካገኘህ ት ኖራለህ፤ ይኼ ደግሞ መፈረሽ ይባላል፡፡ ሁለቱም ካልሆነልህ ደግሞ ትጀዝብና ደ ንብሸህ ትኖራለህ፡፡
ሚላኖ፣ ጣልያን ይህ ጹሁፍ ከዳንኤል ክብረት ጡመራ (ዳንኤል ክብረት ዶት ኮም ) የተወሰደ ነው። ጽሁፉ በ2002 ዓ.ም ለንባብ የበቃ ነው።
ለኛ እርምጃ ነው፡፡ በዚህ ውሳኔ ደቡብ አፍሪካዎች እጅግ ቅር ተሰኝተዋል፡፡ በ ፉትቦልና በኢኮኖሚ የተራመድን ነን በ ሚል ከኢትዮጵያ አዎንታዊ ምላሽ ጠብ ቀው ነበር፤ ሳይሆን ቀረ አንጂ፡፡ በዚህ ም የተነሳ በመጀመሪያው ጨዋታ በሉሲ ዎች ላይ ማጉላላቶች እንዳይፈጠሩ ከወ ዲህ ወገብን ጠበቅ ማድረግ ይበጃል፡፡ ባያና ባያና ወይም ልጃገረዶቹ በሚል ቅፅል መጠሪያቸው የሚታወቁት የደቡ ብ አፍሪካ የሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን አ ባላት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሶዌቶ ላይ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር ካከናወኑ በኋላ በጎረቤት ሀገር ሞዛምቢክ በሚካ ሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ይሳ ተፋሉ፡፡ ማፑቶ ላይ በሚካሄደው ውድ ድር ባያናዎች ሶስት ጨዋታዎች ይጠብ ቋቸዋል፡፡ አጋጣሚው ለልጃገረዶቹ ጥ ሩ የዝግጅት ዕድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ በ አንፃሩ ሉሲዎች አንድም የአቋም መፈተ ሻ ጨዋታ ሳያደርጉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የመውረዳቸው ዕድል እየሰፋ መጥቷል፡ ፡ በቡድኑ ዝግጅት ዙሪያ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም ሲናገር የልጆቹን መነሳሳት እ ና ለሥራ ያላቸውን ፍላጎት አድንቆ ስል ጠናውን ለመፈተሸ ግን የአቋም መፈተ ሻ ጨዋታ አለማግኘቱ እንደሚያስጨን ቀው አልሸሸገም፡፡ “የቀረን የሃያ ቀናት ዕ
ይን ከሚስቡ ቡድኖች ውስጥ ብራዚሎ ች ተጠቃሽ ናቸው:: በተለይ በፈረንሳይ 1998 ዓለም ዋንጫ ላይ የነበረው ቡድ ናቸው ብዙ አድናቂ አግኝቷል፣ ምስጋና ለአጨዋወታቸው ይግባና::
ጥያቄ:- በመጨረሻ፣ ዘንድሮ ሜክሲኮ ከ17 ዓመት እድሜ በ ታች ያዘጋጀችውን ዓለም ዋን ጫ መውሰዷን እንዴት አየኸ ው?
ሔርናንዴዝ:- ከዚህ በፊት እንደተናገር ኩት ለእነዚህ ታዳጊዎች የሚመጥን የአ ድናቆት ቃል ያጥረኛል:: ፔሩ ባዘጋጀች ው የ2005 ተመሳሳይ ውድድር ላይ ብ ካፈልም እነዚህ ልጆች የተቀዳጁትን ድ ል አላገኝሁም:: የሜክሲኮን ስም በየቦታ ው ከፍ ስላደረጉ ኩራት ተሰምቶኛል::
ሉሲዎች አሁንም ድረስ ልምምድ የሚሠሩት በወንዶቹ ማልያ ነው፡፡ እንደውም ማልያው እየሰፋቸው በመርፌ እያጠበቡት እስከ መለማመድ ደርሰዋል ድሜ ብቻ ነው” ሲል የታሪካዊው ጉዞ መጀመሪያ አፍንጫቸው ጋር እንደደረሰ ሁለት ስሜት ውስጥ ሰጥሞ ያስረዳል፡፡ አንደኛው ስሜት የተጫዋቾቹን ለውጤ ት መጓጓት የሚወክል ሲሆን ሌላኛው በ አቋም መፈተሻ ጨዋታ እጦት መራባቸ ውን ያሳያል፡፡ በፉትቦል በተራመዱ ሀገ ሮች ለብርታት እና ፍጥነት በሚል በተ ግባር ላይ የሚውለው የውሃ ውስጥ ል ምምድ በአሰልጣኙ አማካይነት ለሉሲ ዎች እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡ “1 ሜትር በሚጠልቅ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ እየተ ንቀሳቀሱ ፍጥነታቸውን እና ብርታታቸ ውን እንዲያሻሽሉ ያግዛቸዋል” ሲል አ ብርሃም ያስረዳል፡፡ አክሎም ይህን ልም ድ ጋናን ሊገጥሙ ወደ አክራ ባቀኑበት ወቅት ከማርሴይ ዴሳዪ እንዳገኘውና በ ቂ የስልጠና ማኑዋል እንደተቀበለው ተ ናግሯል፡፡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሱት ሉሲዎች በትጋት ልምምዳቸው ቢያካሂዱም በአ ስተዳደራዊው መስመር ያለው ክፍትት
በኤርትራ ሙዚቃ... ከገጽ 19 የዞረ መናዊ ትግርኛ ሙዚቃ መጫወት የሚ ችሉ ወጣቶች ብቅ እያሉ ነው›› ይላል፡ ፡ ኾኖም በኅብረተሰቡ ውስጥ የሠረጸው የኤርትራ ሙዚቃን አልቆ የማየት አባዜ ፍቅረን ያንገበግበዋል፡፡ ሰው አሪፍ የት ግርኛ ሙዚቃ ሠርተን እንኳ የሚያደን ቅልን ‹‹ቁጭ የኤርትራ ዘፈን ነው የሚ መስለው’ኮ በማለት ነው››፡፡ ይላል በቁ ጭት፡፡ ለዓመታት በዲጄነት የሰራው ዲጄ ዐማ ኑኤል በዚህ ይስማማል፤ ‹‹ አገር ውስጥ ጥሩ ጥሩ የትግርኛ ዘፈኖች ተሠርተው የ ኤርትራ ባለመኾናቸው ብቻ ተውጠው ይቀራሉ፡፡›› ዲጄ ዐማኑኤል በሚያዘጋጃቸው የ‹‹ዴ ይ ፓርቲዎች››ም ኾነ በምሽት ክበቦች ታ ዳሚዎቹ የኤርትራ ሙዚቃን እንዲጋብ ዛቸው አስጨንቀው እንደሚጠይቁት ይ ናገራል፡፡‹‹ሰውን የምታዝናናው በሚወ ደው ሙዚቃ ነው፤ በግድ የእኛን ስማ ብለኽ አትግተውም›› ይላል የኤርትራ ሙዚቃዎች በነዋሪዎቹ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ሲያብራራ፡፡ ዲጄ ዐማኑኤል የኤርትራ ሙዚቃዎች በከተማዋ እንዲህ ሥር መስደድ እንደ ዐቢይ ምክንያት የሚያነሣው የኢትዮጵ ያ የትግርኛ ዘፋኞች አዲስ እና ያልተለመ ደ ሥራን ይዘው ለመቅረብ አለመድፈራ ቸውን ነው፡፡ ‹‹የእኛዎቹ ሥራዎች በባህ ል የተደረቱ እና የትግል ዜማዎች የሚበ ዙባቸው ናቸው፡፡›› የ‹‹ሱዳን ትሪቡን›› ድረ ገጽ በ2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጦርነት መልስ ለመጀመርያ ጊዜ የኤርትራ ሙ ዚቃዎችን ማሳየት መጀመሩን ትልቅ ዜ ና አድርጎ ዘግቦት ነበር፡፡ መቀሌን አላያ ትም ማለት ነው፡፡ በእርግጥም መቀሌ በኤርትራ ሙዚቃ ደንሳ የምትደክም አ ትመስልም፡፡ ሙዚቃ ጦርነት አይገባው ም አንዴ? ይህ ፅሁፍ በጥር 2 ቀን 2001 በወጣው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ሶሻል አምድ ላይ ታትሞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የውጭ ሚዲያ ዘጋቢዎች ማህበር ከአሜሪካና ፈረንሳይ ኤምባሲዎች ጋር እ.ኤ.አ በ2009 በመተባበር ባዘጋጀው የሚዲያ ፅሁፍ ውድድርም በጋዜጣ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ግን ያስደነግጣል፡፡ ይህን ቡድን ከወርሃ ታህሣሥ ጀምሮ በማጣሪያው ላይ ለማ ሳተፍ ፌዴሬሽኑ 2.8 ሚሊዮን ብር ማ ውጣቱ ታውቋል፡፡ እስካሁን በድጋፍ መ ልክ የተገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮ ሚቴ በአዘኔታ የሰጣቸው 500 ሺህ ብ ር ብቻ ነው፡፡ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በፋ ይናንስ የመደገፍ ግዴታ የሚኖርበት ቡ ድኑ ለለንደን ኦሊምፒክ ማለፉን ካረጋገ ጠ በኋላ ነው፡፡ እስከዛው ግን ኃላፊነቶ ች ሁሉ ፌዴሬሽኑ ላይ ናቸው፡፡ የእግር ኳሱ አስተዳዳሪዎች ደግሞ በዚህ ጉዳይ ትልቅ ድክመት ይታይባቸዋል፡፡ አብዛኞ ቹ ተጫዋቾች ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚ ገኙ የክልል ከተሞች የመጡ ሲሆን ኑሮ ዋቸውን የሚገፉት በኪራይ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ በየወሩ በነፍስ ወከፍ 300 ብር ይከፍላቸዋል፡፡ ለአንድ የብሔ ራዊ ቡድን ተወካይ ያውም በአሁኑ ጊዜ በወር ከ30 የአሜሪካ ዶላር በታች መክ ፈል እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ሌላኛው የ ሉሲዎች ችግር ትጥቅ ነው፡፡ አሁንም ድ ረስ ልምምድ የሚሠሩት በወንዶቹ ማል ያ ነው፡፡ እንደውም ማልያው እየሰፋቸ ው በመርፌ እያጠበቡት እስከ መለማመ ድ ደርሰዋል፡፡ በዚያ ላይ የማልያው መ ጠን (ሳይዝ) ትልቅ በመሆኑ ይከብዳቸ ዋል፡፡ ይህ ፌዴሬሽኑን ብቻ ሳይሆን አ ጠቃላይ የስፖርቱን አመራሮች ክፉኛ ያ ስወቅሳቸዋል፡፡ ይህ ጹሁፍ ከጋዜጠኛ ኤርሚያስ አማረ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው
22
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
ሐበሻዊ ቃና
ስፖርት
ሃድራው የደራለት ቡና
የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን የ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ማሸነፍ ተከትሎ ለክለቡ ጸ ሀይ የወጣለት ይመስላል፡፡ የክለቡ ደጋ ፊዎች ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሶ ስት ሚሊዮን ብር ያዋጡለት ሲሆን ሀ በሻ ቢራ የተሰኘው ድርጅት ደግሞ አን ድ ሚሊዮን ብር ክፍሎ ክለቡን ስፖንሰ ር እንደሚያደርግ ተሰምቷል፡፡ ናይኪ የ ሰኘው ትጥቅ አምራች ድርጅትም የቡና ገበያ ስፖንሰር ለመሆን መስማማቱ ተ ዘግቧል፡፡ የቡና ደጋፊዎች በማህበራቸው አማካ ኝነት የገቢ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁት ሐም ሌ 16 ቀን 2003 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚ ገኘው ኢንተርኮንቲኔታል ሆቴል ውስጥ ነበር፡፡ ለገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ 200 ያህል ሰው ጥሪ ቢደረግለትም የተገኘው 80 ሰው ብቻ ነበር፡፡ ጥሪ ተደርጎላቸው ከቀሩት መካከል አንዳንዶቹ ባለመገኘታ ቸ ይቅርታ ጠይቀው ድጋፍ እንደሚሰ ጡ አሳውቀዋል፡፡ በፕሮግራሙ ከፍተኛውን ገንዘብ ያዋ ጡት የክለቡ የቦርድ ፕሬዘዳንት አቶ ኤ
ሊያስ ኡመር ሲሆኑ 300 ሺህ ብር ለግ ሰዋል፡፡ የኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል ባ ለቤት አቶ ስማቸው ደግሞ 170ሺ ብር ሰጥተዋል፡፡ ቡናን ስፖንሰር በማድረግ የሚታወቀው ወርቤክ ድርጅት ባለቤት አቶ ወርቅሽት100ሺ ብር አበርክተዋል፡ ፡ በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ ሌሎች 50 ሺህ እና 40 ሺህ ብር የሰጡ ሲሆን በ ግል በአማካኝ የተዋጣው 10 እና 15 ሺ ህ ብር ነበር፡፡ ቡና የገቢ ማሰባሰቢያ ስኬት ዜና ሳይ ቀዘቅዝ ነበር ሀበሻ ቢራ ክለቡን በ2004 ዓ.ም ስፖንሰር ለማድረግ መጠየቁ የተሰ
ከጊዮርጊስ መንደር ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት አዳዲስ ል ጆች አስፈርሟል፤ ሽመልስ በቀለን ከአዋሳ እንዲሁም የአማካይ ተከላ ካዩ ተስፋዬ አለባቸውን ከሰበታ ከ ነማ፡፡ ለአማካይ አጥቂው ሽመልስ 350 ሺህ የፊርማ ሰጥተውታል፡፡ ከ ውጪ ተጫዋቾች ደግሞ ሱላ ማቶ ቩ (ዩጋንዳ)፣ ፕሪንስ ጎድዊን (ጋና) እና አንቶኒ ቦንጎሌ (ዩጋንዳ) ተሰና ብተው በረኛው ሮበርት ኦዳንካራ እና ተከላካዩ አይዛክ ኢሲንዴ (ሁለ ቱም ከዩጋንዳ) ብቻ ከክለቡ ጋር እ ንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአስር ዓመታት በላይ የፔ ፕሲን ማስታወቂያ በማልያው ደረት ላይ ለ ጥፎ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣዩ ዓመ ት ፔፕሲ ቦታውን ለሳዑዲ ስታር እንደሚለ ቅ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ሳዑዲ ስታር የሼ ህ መሐመድ አልአሙዲን ኩባንያ ሲሆን ሙ ሉ መጠሪያው Saudi Star Agricultural Development Plc ይሰኛል፡፡ ኩባንያው በ ጋምቤላ ክልል ሩዝ ለማምረት 10 ሺህ ሄክታ ር በሊዝ ሲረከብ ለእግር ኳስ ክለቡ ሞቅ ያለ ክፍያ ይሰጣል፡፡ ፔፕሲ መተዋወቅ ሲጀምር ሞሓ በዓመት 300 ሺህ ብር ከፍሏል፡፡ ሳዑ ዲ ስታር ለሩዝ ስንት ይከፍል ይሆን?
ማው፡፡ ሀበሻ ቢራ ለክለቡ ለአንድ ዓመ ት አንድ ሚሊዮን ብር ለመሰጠት መስ ማማቱ ነው የሚነገረው፡፡ ሀበሻ ቢራ በ ምስረታና በግንባታ ላይ ሲሆን ቡናን ይ ዞ ወደገበያ ሊገባ እንዳሰበ አይጠረጠር ም፡፡ በ1995ዓ.ም ዳሸን ቢራ የቡና ስፖ ንሰር ነበር፡፡ በ2000ዓ.ም ሜታ ቢራ የ ቡና ስፖንሰር ሆኖ በጋራ ሰርተዋል፡፡ አ ሁን ደግሞ ሀበሻ ቢራ ሲመጣ ቡና በቢ ራ ትሪክ ሰራ ማለት ነው፡፡ የመጠጥ ድርጅቶች ቡና በርካታ ደጋፊ ስላለው ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ተ መራጭ ያደርጉታል፡፡ የቡና የመጀመሪ
ያው ስፖንሰር ራሱ ቡና ነበር፡፡ ድርጅ ቱ ለክለቡ ካምፕ ሰርቶ ቡና በሚል ማ ሊያው ላይ አጽፎ ገባ፡፡ ከዚያ በኋላ ደ ግሞ በ1990 ዓ.ም ከድርጅቱ ውጭ አል ቲሜት ሞተርስ የተባለ የላንድሮቨር እና ቢ.ኤም.ደብሊው አስመጪ ድርጅት ለ ሁለት ዓመት ያሀል ስፖንሰር አደረገው፡ ፡ እስካሁን ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል ክ ለቡን ስፖንሰር ያደረጉ አራት ድርጅቶ ች ናቸው፡፡ ቡና ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን “ወርቤክ” የተሰኘውን የቡና ላኪ ድርጅት ማስታወ ቂያ በማልያው ለጥፎ ታይቷል፡፡ የ“ወር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ፈተና ቤክ” ባለቤት አቶ ወርቅሸት በራሳቸው ወጪ ቡና ለብሶ የሚጫወተውን ማል ያ በውጭ ሀገር አሰርተው በማስመጣት የሚታወቁ ናቸው፡፡ ክለቡ ከዚህ በኋላ ግን ለማልያ መጨነቅ ያለበት አይመስ ልም፡፡ ምክንያቱም ዓለም አቀፉ ትጥቅ አምራች ድርጅት ናይኪ የኢትዮጵያ ቡ ናን ስፖንሰር ለማድረግ ከክለቡ ጋር በ ቅርቡ ስምምነት ላይ በመድረሱ ነው፡፡ ስምምነቱን በመሐል ሆኖ የሚያስፈፅመ ው የአትሌት ዘነበች ቶላ ባለቤት አቶ ወ ንድወሰን ነው፡፡ ዘነበች ዜግነቷን ቀይራ እና ማርያም ዩሱፍ ጀማል ተሰኝታ ለባ ህሬን እየሮጠች የምትገኝ ውጤታማ አ ትሌት ናት፡፡ በኢትዮጵያ ቡና እና የናይኪ ስምም ነት መሰረት ትጥቅ አምራች ድርጅቱ ለ2004 የቡናን ማልያ ራሱ ባዘጋጀው ዲዛይን ሠርቶ ያቀርባል፡፡ ይህ ሰምምነ ት ማልያ፣ ቁምጣ፣ ገምባሌ፣ ካሶተኒ እ ና የመጫውቻ ጫማንም ያጠቃልላል፡ ፡ ናይኪ ቢጫ ቀለም ያለውን የቡድኑን ማልያ እጅጌ ጉርድ፣ እጅጌ ሙሉ እና በ ባለኮሌታ ዓይነቶች ለመስራት ተስማም ቷል፡፡ በተመሳሳይ በቡናማው ቀለምም ሶሰት ዓይነት ማልያዎች ይቀርባሉ፡፡ እ ያንዳንዱ ተጫዋች ስሙና ቁጥሩ የተፃ ፉበት በድምሩ ስድስት ማልያዎች ከና ይኪ በሻንጣ ይላክለታል ማለት ነው፡፡
ቡና የኤርትራን በረኛ ሊያስፈርም ነው?
በ
ስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ የሰሞ ኑ መነጋገሪያ ሆኖ የከረመ ዜና ቡና ኤርትራዊ በረኛ ሊያስፈ ርም ነው የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ቡና ዘ ንድሮ በበረኛ በኩል ብዙ ችግር ገጥሞ ት ነበር፡፡ ሶስት በረኞችን ያህል ቀያይሯ ል፡፡ ቋሚ ተሰላፊነቱን የያዘው ካሜሮና ዊው ሙስጠፋ ነበር፡፡ እሱም ወደሀገሩ ሔዶ ሳይመለስ ቀረ፡፡ የሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት ሲከፈት ነበር የአሁ ንን በረኛ ያገኙት፡፡ በቀጣዩ አመት የበ ረኛ ችግርን ለመቅረፍ በኢንተርናሽናል ውድድር ማለትም በካፍና በሴካፋ ለሚ
ያደርጉት ተሳትፎ ለቡድኑ የሚመጥን በ ረኛ እየፈለጉ ነው፡፡ ይህን ቦታ ለመሸፈ ን የቀይ ባህሩን በረኛ ዳንኤል ጎይቶምን ወደ ቡድናቸው ሊያመጡ ነው እየተባ ለ እየተነገረ ነው፡፡ ዳኤልን ሌላ የኢትዮ ጵያ ክለብ እየፈለገው ነው ቢባልም ወሬ ው በስፋት ያለው ቡና ላይ ነው፡፡ ሶስት የሚያህሉ የቀይባህር ተጨዋቾችም ከኢ ትዮጵያ ክለቦች ጋር ግንኙነት እንደፈጠ ሩ ነው የሚወራው፡፡ የዛሬ ወር ግድም 13 የቀይ ባህር ተጨዋቾች ታንዛኒያ ላ ይ መጥፋታቸው ይታወቃል፡፡ ተጨዋ ቾቹ ወደ ጁባ ሳይሄዱ እንዳልቀሩ ጭም
ጭምታ አለ፡፡ አንድ ተጨዋች አለምአቀፍ ዝውው ር ሲያደርግ የአገሩ ፌዴሬሽን መልቀቂ ያ መስጠት አለበት፡፡ የኮበለሉት የኤር ትራ ተጨዋቾች ፌደሬሽናቸው መልቀ ቂያ አይሰጣቸውም፡፡ ዳንኤል አራት ጊ ዜ ለጎትያ ካፕ ስዊድን ሄዷል፡፡ ከኮበለ ለት ውስጥም አራት ተጨዋቾች የስዊድ ን ጥምር ዜግነት እንዳላቸው ይነገራል፡ ፡ ጥምር ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች መ ልቀቂያ ከአንደኛው ሀገር እንኳን ቢከለ ከሉ በፊፋ ህግ መሰረት ከሌላኛው አገር ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡
ከላይ ያሉት ዘገባዎች የተጠናቀሩት ገነነ መኩሪያ ቀድሞ ያዘጋጀው በነበረው ጋዜጣው ስም ከከፈተው ሊብሮ ዶት ኮም ከተሰኘው ድረ ገጽ እና ከኤርሚያስ አማረ ፌስ ቡክ ገጽ ነው
የድንቅነሽ ፈተና፤ ማልያ እያጠበበች ትለማመዳለች በኤርሚያስ አማረ ቤልጅየም 24 ተጫዋቾች እና 3 አሰልጣኞች ከአ ንድ ወጌሻ ጋር ከአዲስ አበባ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ደብረዘይት ከ ተማ መሽገዋል፡፡ ጉዞዋቸውን የጀመሩት በወርሃ ታህሣሥ ሲሆን መድረሻቸው ደ ግሞ ለንደን ናት፡፡ እነ ዴቪድ ቤካም አ ምባሳደር ሆነው የቀሰቀሱላት ለንደን በ ፓሪስ ላይ የበላይነቱን ተቀዳጅታ 30ኛ ውን የበጋ ኦሊምፒክ ከጁላይ 27 እስከ ኦገስት 12 ቀን 2012 ድረስ ለመደገስ ጎም በስ ቀና በማለት ላይ ትገኛለች፡፡ የእኛም እህቶች በውድድሩ ሀገራቸው ን ሊወክሉ 180 ደቂቃዎች ብቻ ቀርቷቸ ዋል፡፡ አፍሪካ በለንደኑ ኦሊምፒክ በሴቶ ች እግር ኳስ የሁለት ኮታዎች ባለቤት ና ት፡፡ በአንደኛው መስመር ኢትዮጵያ እ ና ደቡብ አፍሪካ ሲፋጣጡ፤ በሁለተኛ ው መስመር ኢኳቶሪያል ጊኒ ናይጄሪያ ን ትፋለማታለች፡፡ ሉሲ ወይም ድንቅነ ሽ በሚል ቅፅል የሚታወቁት የሴቶች ኦ ሊምፒክ ቡድን አባላት ከሐምሌ 1 ጀም ሮ ልምምዳቸውን ቢሾፍቱ መኮንኖች ክ በብ ተቀምጠው እያካሄዱ ናቸው፡፡ የቡ ድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም ተ/ኃይማ ኖት ሲሆን አብረውት ሁለት ረዳቶች ይ ገኛሉ፡፡
ሉሲዎች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ኦ ገስት 27 (ቅዳሜ) ጆሃንስበርግ ላይ ያከ ናውናሉ፡፡ የሚጫወቱት ደግሞ የታዋቂ ው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ኦርላንዶ ፓይ ሬትስ ሜዳ በሆነው ኦርላንዶ ስቴዲየም ላይ ነው፡፡ ስቴዲየሙ 40 ሺህ ተመል ካቾችን ያስተናግዳል፡፡ በእርግጥ ጨዋ
ታው የሚካሄድበት ትክክለኛው ቦታ በ ዘመነ አፓርታድ ጥቁሮች ከጆሃንስበርግ ተገፍተው እንዲኖሩ በተፈረደባቸው የ ትግል ከተማዋ ሶዌቶ ውስጥ ነው፡፡ ሶ ዌት ከእንግሊዝኛው South Western Townships የተወሰደ ሲሆን ከመሐል ጆሃንስበርግ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ
የሚገኝ የጥቁሮች መናኸሪያ ነው፡፡ በሶ ዌቶ 1.5 ሚሊዮን ጥቁር ደቡብ አፍሪካ ዊያን ይኖራሉ፡፡ በቅርቡ ይፋ በሆነ አን ድ መረጃ አርባ ከመቶ የሚሆነው የጆሃን ስበርግ ነዋሪ በሶዌቶ ከትሟል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ሴፕቴምበር 11 ወይ ም በእኛ የእንቁጣጣሽ ዕለት ይካሄዳል፡
፡ እህቶቻችን በአዲስ ዓመት ዋዜማ ታሪ ካዊ ድል ያጎናፅፉናል የሚል ተስፋ በብ ዙዎች ልቦና ውስጥ ተሰንቋል፡፡ የሉሲዎ ች ተጋጣሚ የሆነው ደቡብ አፍሪካ በ መላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የሚካ ፈል ሲሆን ኢትዮጵያን ከመግጠሙ በ ፊት ተከታታይ ጨዋታዎችን ለማድረግ ይገደዳል፡፡ በዚህም የተነሳ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው ጨዋታ የቀን ለውጥ እ ንዲደረግበት ፊፋን ጠይቆ ነበር፡፡ ፊፋ በተጠየቀው መሠረት ኢትዮጵያ ፈቃደ ኛ መሆኗን እንድታሳውቅ ወደ አዲስ አ በባ ደብዳቤ ላከ፡፡ አንዳንድ ማንገራገሮ ች ከታዩ በኋላ የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ከ መስከረም 1 ፍንክች አንልም የሚል ምላ ሽ ሰጡ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ጥቅሙን ለማ ስጠበቅ ሲል በፊፋ በኩል የላከው ልመ ና ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር እንደገና በካ ፍ መስመር ማግባባት ጀመረ፡፡ በዚህ በ ኩል የመጡት ደግሞ የካፍ ዋና ፀሐፊው ሙስጣፋ ፋህሚ ናቸው፡፡ ግብፃዊው የ ካፍ የበላይ በተደጋጋሚ አቶ ሣህሉን በ ስልክ ለማግባባት ቢሞክሩም ሳይሰምር ላቸው ቀርቷል፡፡ አሁን ጨዋታው በተያዘለት ቀን እንዲ ካሄድ ፊፋ አዟል፡፡ በኋላ ለውጥ ተደርጎ ውጤት ቢጠፋ እንኳን ሁሉም ነገር በፕ ሮግራም ለውጡ ላይ ይደፈደፋል፡፡ ስለ ዚህ በመጀመሪያው መፅናታቸው ትክክ
ወደ ገጽ 21 ዞሯል
የ2012 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን ሳንጨርስ የ2014 የዓለም ዋንጫ ማ ጣሪያ ከች ብሎብናል፡፡ የአፍሪካ ዞን የ2014 የዓለም ዋንጫ የቅድመ-ማጣ ሪያ ድልድል ሪዮዴጄኔሮ ላይ ይፋ ሆ ኗል፡፡ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ 3 ዙሮች ይኖሩታል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ወ ደ ምድብ ፉክክሩ ለመግባት በ24 ቡ ድኖች መካከል የደርሶ መልስ ግጥሚ ያ ይደረጋል፡፡ 12ቱ አሸናፊዎች 28ቱ ን ይቀላቀሉና በ10 ምድብ አራት-አራ ት ቡድኖች ተደልድለው የሁለተኛ ዙ ር ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡ በሶስተ ኛው ዙር አስሩ የየምድቡ አሸናፊዎች በደርሶ መልስ እንዲጫወቱ ተደርጎ አ ምስቱ አሸናፊዎች ወደ ብራዚል ያቀና ሉ፡፡ በምድብ ድልድሉ መሰረት ኢት ዮጵያ ከጎረቤት ሶማሊያ ደርሷታል፡፡ የመጀመሪያው ጨዋታ ህዳር 1 በሶማ ሊያ ሜዳ ይሆናል፤ መልሱ ደግሞ በአ ዲስ አበባ ህዳር 5 ይካሄዳል፡፡ ዋልያዎች ለ2012 የጋቦንና ኢኳቶሪ ያል ጊኒ የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ 2 የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያካሄዱ ሲ ሆን የፊታችን ሴፕቴምበር 4 ኮናክሪ ላይ ጊኒን ይገጥማሉ፡፡ በምድቡ የመ ጨረሻ ጨዋታ ኦክቶበር 9 በአዲስ አ በባ ማዳጋስካርን ያስተናግዳሉ፡፡ ም ድቡን ጊኒ በ10 ነጥብ ስትመራ ናይጄ ሪያ በ7 ትከተላለች፡፡ ኢትዮጵያ 4 ይ ዛ ሶስተኛ ናት፡፡ 1 ነጥብ ያላት ማዳጋ ስካር ከታች ተቀምጣለች፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኢትዮጵያ ግማሽ ሊግ በቀጣይ የው ድድር ዘመን በ14 ክለቦች መካከል ይ ካሄዳል፡፡ ግማሽ ሊግ ያልኩት ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ያለው ግዛት ተቆር ጦ ስለሚቀር ነው፡፡ ዋና ከተማዋ በ6 ክለቦች ስትወከል በሕዝብ ብዛት ቀዳ ሚ የሆነው ኦሮሚያ 3 ወኪሎች አሉ ት፡፡ ደቡብም 3 አሉት፡፡ አዲስ አዳጊ ው አርባምንጭ ከነማ ከሁለት ዓመ ት በፊት ስሙን የቀየረው አርባምን ጭ ዳሸን ቢራ ነው፡፡ ይህ ቡድን የዝ ነኛው አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ሕ ጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ወራሽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከሚበ ጠብጡት ነገሮች ጉዞው አንዱ አይደ ለም? በተጠናቀቀው የውድድር ዓመ ት ረጅሙ ርቀት (891 ኪሜ) ወደ አ ዲግራት ነበር፤ እስከ መቀሌ በአውሮ ፕላን ከዚያም በየብስ የሚደረስበት፡፡ ትራንስ በመውረዱና ከታች ቡድን ባ ለመምጣቱ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ሽ ቅብ መብረር ቀርቷል፡፡ በአንፃሩ ደግ ሞ አርባምንጭ ተተክቷል፡፡ ለአዲስ አበባ ክለቦች ቅርቡ ሜዳ ሰበታ ነበር፤ 25 ኪሎ ሜትር ብቻ ይርቃቸው ነበ ር፡፡ ለከርሞ የሰቤን ቦታ ደዘ ወስዶበ ታል፤ ይቅርታ ቢሾፍቱ፡፡ አዲግራት ደግሞ በሐረር ተተክቷል፡፡ በ2004 በአውሮፕላን የሚኬድባቸ ው የሊግ ጨዋታዎች ድሬዳዋ፤ አርባ ምንጭ እና ሐረር ናቸው፡፡ የሐረሩ ቀ ጥታ ሳይሆን ድሬዳዋ በአየር ከተገባ በኋላ በመኪና የሚደረስ ነው፡፡ እስ ቲ በመሬት ላይ ከመዲናዋ ያላቸውን ርቀት እንመልከት፡* ከአዲስ አበባ ደብረዘይት:- 41 ኪሜ * ከአዲስ አበባ አዳማ:- 98 ኪሜ * ከአዲስ አበባ አሰላ:- 175 ኪሜ * ከአዲስ አበባ አዋሳ:- 273 ኪሜ * ከአዲስ አበባ ይርጋለም:- 318 ኪሜ * ከአዲስ አበባ አርባምጭ:- 491 ኪሜ
* ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ:- 494 ኪሜ * ከአዲስ አበባ ሐረር:- 513 ኪሜ ማስታወሻ፡- የአንዳንድ ከተሞች ር ቀት ከመንገድ ግንባታዎች በኋላ በተ ለምዶ ከሚታወቀው ርቀት መጠነኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ይህ ጹሁፍ ከጋዜጠኛ ኤርሚያስ አማረ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
በ
ፍፁም ሜዳ ውስጥ መ ኖር አልነበረበትም:: በ ሁለቱ የመጀመርያ የ ምድብ ጨዋታዎች ከ ቅድሚያ ተሰላፊዎች ውስጥ መካተ ቱ በጣም ይገርማል:: ከቡድን ስብስ ብ አንዱ መሆኑ ልክ አይደለም:: የ ፍፁም ቅጣት ምት ለመምታት በዚ ያ ቦታ መገኘት አይገባውም:: ምክን ያቱም የሚከተለው ውጤት ይታወ ቃላ:: የዑራጋዩ በረኛ ሙስሌራ ደመ ነፍሱ ወደጠቆመው አቅጣጫ ተወ ረወረ:: የዓለም ትልቅ ቡድኖች ካላ ቸው በላይ ምርጥ ስብስብ አለን ብ ለው ደረታቸውን የነፉ የሰማያዊ እ ና ነጭ ለባሾቹ ደጋፊዎች ኩራት በስ ከንዶች ውስጥ ተነነ:: በደጋፊዎች እ ና ሚዲያ ጩኸት ለሀገራዊ ግዴታ የ ተጠራው ካርሎስ ቴቬዝ ተመረጠ ተሰለፈ፣ አንገቱን ደፋ፣ ሀገሩን አሳ ፈረ:: አርጀንቲናውያን በጥፈራቸው ውስጥ መሸሸግ ተመኙ:: የውድቀቱ ዋነኛ ተጠያቂ እርሱ ነ ው፣ የማንችስተር ሲቲዎች ፊትውራ ሪ ካርሎስ ቴቬዝ! ደጋፊው “ኡኡ!” አለ፣ አሰልጣኙ ሰርጂዮ ባቲስታ መ ረጠላቸው:: ያ “የሕዝቡ ሰው” ሕዝ ቡን ቀበረ:: የቴቬዝ ኃጢያት በዛ ሊ ባል ይችላል:: አዎ በዝቷል:: በኮፓ አ ሜሪካ ብቻ ሳይሆን በ2010 ዓለም ዋ ንጫ ማጣርያ ሁለቴ በቀይ ካርድ ሲ ወጣ፣ አንድ ጊዜ ሪጎሬ ስቶ የሀገሩን የ ደቡብ አፍሪካ ጉዞ ምጥ ውስጥ የከተ ተው እርሱ ነበር:: ነገር ግን የሚዲያው እና የሕዝቡ የ ሰላ ትችት ቴቬዝ “ጀግናቸውን” በ ጨረፍታም አልነካም:: ከእርሱ ይል ቅ ዒላማቸው ሁሉ ያነጣጠረው የዓ ለም ቁጥር አንዱ ሊዮኔል ሜሲ ላይ ነበር፡፡ ከባርሳ ጋራ በትንሹ ሶስት የ ሻምፕዮንስ ሊግ እና አራት የላሊጋ ዋንጫ ማግኘቱ እና በተከታታይ የ ዓለም ኮከብ መሆኑ ከሀገሩ ደጋፊዎ ች ብዙ እንዲጠበቅበት አድርጎታል፣ ኃላፊነቱን አብዝቶታል:: በ1993 የ ኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ካገኘች ወዲ ህ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ አንድም ክብር ያላየችው የኳስ ሀገር አርጀን ቲና በርካታ ኮከቦችን ብታፈራም ከ ድል ድርቅ የሚያድናት ልታገኝ አል ቻለችም:: አርዬል ኦርቴጋ፣ ጋብርኤል ባቲስቱ ታ፣ ሁዋን ቬሮን፣ ማርሴሎ ጋያርዶ፣ ሄርናን ክሬስፖ፣ ፓብሎ አይማር፣
23
ሐበሻዊ ቃና
ሀገር “የሌለው” ሜሲ
ሁዋን ሮማን ሪኬልሜ፣ ሀቪዬር ሳቪዮላ፣ አንድሬስ ዲ አሌሳንድሮ እና ሀቪዬር ዜኔ ቲን የመሳሰሉ እንቁዎችን ብታፈራም የል ቧን የሚያደርሱላት ሊሆኑ አልቻሉም:: የ ዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ የሚያንፀባር ቁት ጥበበኞቿ የዋናውን ቡድን ማልያ ሲ ለብሱ ከስመው የውድድር አሟሟቂ እና የግምት ዋንጫ ብቻ ተሸልሞ መመለስ የ ተለመደ ነው:: በእርግጥ አርጀንቲና በእነ ቴቬዝ እና ሜሲ ሁለት የኦሎምፒክ ክብ ር ተቀዳጅታለች:: ያ ድል ግን ለታንጎዎች
ማስተዛዘኛ እንጂ የሚፎከርበት አይደለ ም:: ንጉሳቸው ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ያሳያችውን ጀብዱ እንደምፅአት ቀን ምን ጊዜም በጉጉት ይጠባብቃሉ:: “ አምላካ ቸው” ማራዶና ለቦካ ጁኒየርስ እና ለናፖ ሊ የሰራውን ተዓምር በአልቢቼሌስቴ ቀ ለም ደግሞ ስለፃፈው የሀገሪቷ ዘለዓለማ ዊ ጣዖት አደርገውት ይኖራሉ:: ዓለም ዋንጫ ወደቤታቸው ከመጣ 25 ዓመታት ቢያልፉም ልክ እንደዛሬ ክስተ ት በፍቅር ይተርኩታል:: ማራዶና አሰል
ጣኝ እንዲሆን ጎትጉተው የአርጀንቲና ብ ሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ግጥሚያ በትን ሿ ቦሊቪያ 6-0 መራር ሽንፈት ሲቀምስ እና በዓለም ዋንጫ ላይ ደግሞ በጀርመን 4-0 አሸማቃቂ ውጤት ሲያስመዘግብ ተ መልክተዋል፡፡ ሆኖም ማራዶና አሁንም ቢሆንም በሕዝቡ እንከን የለሽ ሆኖ ይመ ለካል:: ሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ ላይ የጫነ ውን ዘውድ ማንም እንዲነካበት አይፈል ጉም:: ዲዬጎ ለእነርሱ ከእግር ኳስም በላ ይ ነው:: ይህ ልባቸው ነው ለሜሲ ለመራ
ራት ያልፈቀደው:: የሜሲ የባርሴሎና ገድል በሀገሩ ፊት ምንም ነው:: የእርሱ የዓለም ኮከብነት ለ አርጀንቲና ምን ይረባታል?! በእግር ኳሱ ዓለም የአድናቆት ቃላት ቢጠፋለትም በ ሁለት ዓለም ዋንጫዎች እና ኮፓ አሜሪ ካ ውድድር ላይ የተሰለፈው ሜሲ ለሀገ ሩ ከተራ ተጨዋች በታች አስተዋፅዖ ማ ሳየቱ ከታላላቅ ተጭዋቾች ተርታ የመጠ ራቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል:: ችግሩን ለመጠቆም፣ “የአርጀንቲና አጨ
ስፖርት ዋወት ለሜሲ አይመቸው ወይም ሜ ሲ ለአርጀንቲና ያለው ዋጋ ዝቅ ያለ ነ ው” የሚሉ የዋለሉ ስሜታዊ ትንታኔዎ ች ቢሰጡም ያለው ሪከርድ ግን ደካማ እንደሆነ ያሳብቁበታል:: በአራቱ ግዙፍ መድረኮች ያስቆጠራ ቸው ጎሎች ሶስት መሆናቸው መስማ ት ለማመን ያዳግታል:: በባርሳ አድራጊ እና ፈጣሪ የሆነው ጥበበኛው ሊዮ ሀ ገሩ አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካን አዘጋጅ ታ ከደካማዋ ቬኑዝዌላ በታች መጨረ ሷ ጣቶች ሁሉ በእርሱ ላይ እንዲቀሰ ሩ አድርጓል:: በሜዳ ላይ የተቃውሞ ጩኸቶች የተሰሙበትም በዚህ ምክን ያት ነው:: በሁኔታው የተበሳጩት የአ ርጀንቲና ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሁሊ ዮ ግሮንዶና “ይሄ ልጅ ከእንግዲህ ለሀ ገሩ አልጫወትም የሚል ውሳኔ ላይ ሊ ደርስ ይችላል” በማለት ሲያስፈራሩ፣ ማራዶና በበኩሉ “ሜሲ ብቻውን ተ ዓምር እንዲፈጥር የሚፈልጉ ሰዎች ደ ደብ መሆን አልባቸው:: እኔንም በእር ሱ እድሜ ሚዲያው እና የማይረቡ ሰ ዎች ይተቹኝ ነበር:: ከዓለም ዋንጫ ድ ል በኋላ ግን የገቡበት ጠፋ” ሲል ለሜ ሲ ተከላክሏል:: በሶስት የተለያዩ አሰልጣኞች ታክቲክ ውስጥ ጎልቶ መታየት የተሳነው የ24 ዓመቱ ሜሲ ከፊቱ ከባድ ፈተናዎች ይ ጠብቁታል:: አዲስ ከተሾሙት አሰል ጣኝ አሌሃንድሮ ሳቤላ ጋራ በመሆን አ ርጀንቲናን የ2014 ዓለም ዋንጫ ተካፋ ይ ማድረግ የመጀመሪያ ግዴታው ይ ሆናል:: በደቡብ አሜሪካ አገሮች መካ ከል የሚደገረው የዓለም ዋንጫ ማጣ ሪያ ረጅም ጊዜ በመውሰዱ የተነሳ “ማ ራቶን” ተብሎ ነው የሚጠራው፡፡ አ ሰልቺ እና አድካሚው ማጣሪያ እና ለ ዝግጅት በቂ ጊዜ አለመኖሩ ጋር ተዳ ምሮ ተጨዋቾቻቸው በአውሮፓ ለከ ተሙ እንደ አርጀንቲና ላሉ ሀገሮች ያ ልተጠበቀ አደጋ የሚደቅን ነው:: ይህ ን ቀዳሚ መሰናክል በብቃት ማለፍ ለ ሜሲ ከሀገሩ ሕዝብ ጋራ የመታረቂያ መድረክ ሊሆን ይገባል:: ይህን የሚያሳ ካ ከሆነ ብራዚል በምታዘጋጀው የዓለ ም ዋንጫ ላይ አንድ የቀረችውን ሕያ ው ሆኖ የመቅረት እድል በእግር ኳሷ ምድር መጠቀም የእርሱ ፋንታ ይሆና ል:: ወርቃማውን ውብ ዋንጫ ከፍ አ ድርጎ መሳም! እስከዚያ ድረስ ግን የአ ርጀንቲና ጉዳይ እንደ ሕልም እያባነነ ው ይኖራል::
ቺካሪቶ: የማንችስተርን ውለታ መክፈል አለብኝ በዓለም እግር ኳስ ውስጥ በአንድ የውድድር ዓመት ውስጥ ወዲያውኑ አስገራሚ ተፅዕኖ የፈጠሩ ተጨዋቾች በጣም ጥቂት ናቸው:: አንዱ ምሳሌ ደግሞ ሀቪዬር “ቺካሪቶ” ሔርናንዴዝ ነው:: የሚደንቅ ችሎታ ከሞያ አክባሪነት እና ጎል አነፍናፊነት ጋራ አጣምሮ መያዙ በአምና ውድድር ከታዩ ክስተቶች ዋነኛው ያደርገዋል:: ሀገሩ ሜክሲኮን ለጎልድ ካፕ ዋንጫ ድል ካበቃ በኋላ ስላገኘው ስኬት እና ቀጣይ እቅዶቹ ይናገራል:: ጥያቄ:- የሜክሲኮ ውጤታማነት ም ስጢር ምንድነው?
ሔርናንዴዝ:- የቡድኑ ጠንካራ ሰራተኝነት እና ትኩረት መስጠት የማሸነፍ ተነሳሽነት ውስጥ እን ድንጓዝ ረድቶናል:: የጎል እድሎችን በአግባቡ ተ ጠቅመናል:: እንደዛ መሆኑ ሰዎች ቀላል አድርገ ው እንዳያስቡ ውድድሩ ሳይጀመር ምንም ግዴ ታ ወይም ጫና የለብንም ብለን በማሰብ እያንዳን ዱን ጨዋታ ለማሸነፍ እና እያንዳንዱን ውድድር በስኬት ለመጨረስ ተጫውተናል:: ነገር ግን ድ ል የሚገኘው በጠንካራ ስራ ብቻ ነው:: ጥያቄ:- ቢሆንም ከማሸነፍ ውጪ ያ ለ ውጤት ለሜክሲኮዊያን እንደውድ ቀት ነው::
ሔርናንዴዝ:- በዚህ እይታ አልስማማም:: በር ግጥ አሸነፍንም ተሸነፍንም የሚከተለውን እናው ቃለን:: ለዚያም ነው ማሸነፍን ግባችን አድርገን ወደ ውድድሩ የገባነው:: እንዳስብነውም ተሳክቶ ለናል:: ዋናው ቁምነገር ውጤታማ መሆናችን ሲ ሆን ደጋፊያችን የሚጨፍርበት ስጦታ በማበርከ
“
ለመምሰል የምጥረው የብራዚሉ ሮናልዶን ነው:: ሮናልዶ ታላቅ ተጨዋች እንደሆነ አስባለሁ ታችን በጣም ተደስቻለሁ:: በውድድሩ ፈታኝ ሁ ኔታዎችን ማለፋችን ድሉን የበለጠ ጣፋጭ አድር ጎልናል:: ከብሔራዊ ቡድኑ ጋራ ያገኘሁት የመጀ መርያ ዋንጫ በመሆኑ እጅግ አርክቶኛል:: ጥያቄ:- ይህ ቡድን የሜክሲኮ የምንጊ ዜም ምርጡ እንደሆነ ታስባለህ?
ሔርናንዴዝ:- የምጠላው ነገር ቢኖር ማነፃፀር ነ ው:: እንደተጫዋች አሰልጣኝ የሚልህን መተግበ ር ነው፣ በብሔራዊ ቡድን ደግሞ የበለጠ:: በቡድ
ኑ የተደረገልኝ አቀባበል እና እርዳታ በጣም አስ ደስቶኛል:: ለኤልትራይ ከለር [የሜክሲኮ ብሔራ ዊ ቡድን ቅጥል ስም ነው] በእያንዳንዱ ሰከንድ የ ማደርጋት እንቅስቃሴ ታላቅ ስሜት ይሰጠኛል:: ላለፈ ነገር አልኖርም፡፡ የሚያበረታታኝ የዛሬ እና የወደፊቱ ሕይወት ነው:: ጥያቄ:- ስለ ብሔራዊ ቡድንህ በዚሁ እናብቃና ስለክለብህ እንነጋገር
ሔርናንዴዝ:- በማንችስተር አስገራሚ እንክብ ካቤ ተደርጎልኛል፣ ለተሰጠኝ አመኔታ እኔም ምላ ሹን መክፈል እሻለሁ:: የመጀመርያ ዓመቴ የተሳ ካ ነበር:: ዘንድሮም የበለጠ አስተዋፅኦ ማበርከት አለብኝ:: ከዚህ ቡድን ጋራ ወደፊት ብዙ ጥሩ ጊ ዜ እንደሚኖረኝ አስባለሁ፣ በቀጣዩም ውድድር በማገኘው እድል በጣም ደስተኛ ነኝ:: ጥያቄ:- ከዚህ ቀደም ሜክሲካዊ ተ ጨዋቾች በሌላ ሀገር ሲጫወቱ ለመል መድ ሲቸገሩ ይታይ ነበር:: ያንተ ም ስጢር ምንድነው?
ወደ ገጽ 21 ዞሯል
24
ሐበሻዊ ቃና
ሐምሌ 30-ነሐሴ 13 ቀን 2003 (August 6-19, 2011)
VAMBECO ENTERPRISES LTD
As challenging as it is operating in a highly competitive construction sector in a developing country like Uganda, where very many foreign companies from China are competing for any available job, Vambeco Enterprises Ltd, located on Kanjokya Street, in Kamwokya has firmly stood the test of time. This success can be attributed to the high quality of work and commitment. Vambeco Enterprises Ltd was formed in August 1999, as a result of merging Bagatansi Builders Uganda Limited and Viera Sarl Rwanda. Bagatansi Builders Uganda Limited was in the building sector in Uganda for 144 years while Viera Sarl was in Rwanda engaged in the construction of water projects and emergency relief construction projects since 1994.Kampala is their headquarters for thee Great lake region with branch offices in Nairobi, Kenya and Kigali, Rwanda.
With over 20years of experience in Water Engineering, Vambeco endeavors to provide the following activities around the great lake region.
q Supply and Installation of Pre-Paid Water Meters, q Construction of Water and Sanitation Projects, q Building Projects such ass Schools, Hospitals, Churches, Mosques, q Design and Construction of Utilities in Refugee/ IDP camps, q Construction of Water Reservoirs of all sizes, q HHDPE Pipe Laying, q Steel Tower and Water Tank Installation, q River Intake Works, q Slow sand filtration , water intake treatment Works & q Construction of reinforced concrete reservoirs Vambeco is noted for excellence of its work, innovation and experience in tackling both complex and simple projects efficiently. Since we started working in Uganda we have established ourselves as one of the leading credible contractors in the region. We are very pleased to have made such a positive impact in the building and water engineering sector. We work in a manner that protects and promotes the health and well being of the individual and the environment.
For more information, contact us on: Mobile: +256 772748351, 07772 716220, Plot 43, Kanjokya Street, Kamwokya. Fax: +256 414 530136 P.O.Box 166220, Kampala Uganda. Email: vambeco@vambeco.com, Telephone: +256 414 543510, Website: wwww.vambeco.com