Habeshawi Kana 002

Page 1

ሐበሻዊ ቃና

ሐበሻዊቃና አንደኛ ዓመት ቁጥር 002

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

m “ይክኣሎ” m ሌላ ዳንስ አለብኝ m የቢግ ብራዘሩ ዳኒ መጨረሻ m ኢትዮ ኤርትራዊቷ ዛላበንሳ

በተጭበረበረ ሰነድ ከኬንያ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሞከሩ ስደተኞች እንዲመለሱ ተደረገ በኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

የተባበሩት መንግስታት የስደተኛ መር ጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ለመልሶ መስፈር ወደ ሶስተኛ ሀገር የመሄድ መ ብት ለሁሉም ስደተኛ የተሰጠ እንዳልሆ ነ አስታወቀ። የድርጅቱ የኡጋንዳ ኃላፊ ካኢ ኤሪክ ኔ ልሰን ለሐበሻዊ ቃና እንደገለጹት የመል ሶ መስፈር መብት የሚሰጠው ለጥቂት ስደተኞች ብቻ ነው። እነርሱም ቢሆኑ በጣም አሳሳቢ የሆነ የደህንነት ችግር ያ ለባቸው እና ከሚኖሩበት ሀገር በቂ የሆ ነ ከለላ የማያገኙ ከሆኑ ብቻ እንደሆነ ያ ስረዳሉ። “ከኡጋንዳ ወደ ሌላ ሀገር ያለው መል ሶ መስፈር በጣም ጥቂት ነው” ይላሉ ኔ ልሰን። ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት የሚ ጠቅሱት ኡጋንዳ አሁን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ሰላማዊ መሆኑን ነው። የዓለም የስደተኞች ቀን ሰኔ 13 ቀን 2003 ዓ.ም በካምፓላ በተከበረበት ዕ ለት የአደጋ ዝግጁነት ሚኒስትር የሆኑት ሞሰስ ኤክዌሩ የተናገሩትን በመጥቀስም

በሀገሪቱ ለስደተኞች ደህነት የሚያሰጋ ነ ገር እንደሌለ አስታውቀዋል። ሚኒስቴር ዴኤታው በዕለቱ እንደተናገሩት ማንኛ ውም ሀገር ወደ ኡጋንዳ የተሰደደ ዜጋ ውን አድኖ ጉዳት ለማድረስ አይፈቀድለ ትም። “ማንም ሀገር በዚህ ጣልቃ እንዲ ገባ አንፈቅድም” ብለው ነበር። ከየሀገራቱ የሚመጡ የደህንነት ሰዎች በስደተኞች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ የሚባ ሉ ወሬዎችን እንደሚሰሙ የዩ.ኤን.ኤ ች.ሲ.አር የኡጋንዳ ኃላፊ ያምናሉ። ሆ ኖም የኡጋንዳ የደህንነት ሰዎች በተለይ ም በወታደራዊ የደህነነት ክፍል ውስጥ የሚሰሩቱ እነዚህን የሌላ ሀገር ደህንነቶ ች ቢመጡ ለይተው የሚያውቋቸው በ መሆኑ ችግር አይፈጠርም ባይ ናቸው። ደህንነታቸው አስጊ የሆነ ስደተኞች በ ቂ ማስረጃ አቅርበውም የመልሶ መስፈ ር ማመልከቻቸው በቶሎ ምላሽ አያገኝ ም በሚል ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ላይ ለሚቀ ርበው ትችትም ችግሩ የድርጅቱ እንዳል ሆነ ምላሽ ይሰጣሉ። እንደእርሳቸው አ ባባል መዘግየቱ ችግር የሚከሰተው በ

m ወግ ከአገረ አሜሪካ

ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ

ወደ ሶስተኛ ሀገር መሄድ ለሁሉም ስደተኛ የተሰጠ መብት አይደለም - ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

በእዚህ ዕትም

1

የዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ኡጋንዳ ኃላፊ ካኢ ኤሪክ ኔልሰን

የኤርትራ የዳያስፖራ መመኪያዎች

የተለያዩ ግለሰቦችን መረጃዎች የራሳቸው በማስመሰል ወደ አሜሪካ ሊገቡ የነበሩ አስራ አንድ ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እንዲመለሱ ተደረጉ፡፡ ምንጮች ለ“ሐበሻዊ ቃና” እንደገለጹት ግለሰቦቹ ወደ አሜሪካ ጉዞ ለማድረግ የተ ሰናዱ ስደተኞችን መረጃዎች በመሰብሰብ እና መረጃውንም የራሳቸው በማስመሰል አሜሪካ ሊገቡ ሲሉ ነው የተያዙት፡፡ ሁሉም ኬንያን ተሻግረው አሜሪካ ገብተው የ ነበረ ቢኾንም ሰነዱ ውስጥ የሚገኘው የአሻራ መረጃ ከተጓዧቹ አሻራ ጋር ባለመመ ሳሰሉ ምክንያት ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ እንዲህ ይነት የማጭበርበር ወንጀል የተለመደ ቢኾንም ይሄን ያህል ቁጥር ያለው የወንጀል ስራ ግን ተሰርቶ እንደማይታወቅ ምንጮች ያስረዳሉ። ላለፉት አራት ወ ራት ተቋርጦ የቆየው ከኬንያ ወደ አሜሪካ ለመልሶ መስፈር የሚደረገውን በረራ የ ተጀመረው ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር። ወደ አሜሪካ የሄዱት ስደተኞች ሙሉ ለሙሉ የመጡት በሰሜን ምዕራብ ኬንያ ከሚገኘው ካኩማ ስደተኞች ጣቢያ ነው። በሁለት አውቶብሶች ተጭነው ናይሮ ቢ የደረሱት ስደተኞች ወደ አሜሪካ ከመብረራቸው በፊት በተለምዶ “ጎል” ተብ ሎ ወደሚጠራው የዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) ቅጥር ግቢ ቆይታ አ ድርገው ነበር። እ.ኤ.አ በ2009 ብቻ 75 ሺህ ስደተኞች በአሜሪካ እንዲሰፍሩ ተደርጓል።

ኦፒየም የይግባኝ ሰሚ ቦርድ አቋቋመ በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

ገጽ 11

ወደ ኡጋንዳ ለሚመጡ ስደተኞችን የ መጠለል መብት የመስጠት አሊያም የ መንፈግ ስልጣን ያለው የጠቅላይ ሚኒ ስቴር ጽህፈት ቤት (ኦፒየም) በሚሰጣ ቸው ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ለሚያሰሙ ወገኖች የይግባኝ ሰሚ ቦርድ አቋቋመ። በኦፒየም የመልሶ ማስፈር ከፍተኛ ኦፊ ሰር የሆኑት ቻርለስ ባፋቺ ለ“ሐበሻዊ ቃ ና” እንደገለጹት ጥገኝነት የማግኘት ጥ ያቄው ውድቅ የተደረገበት ማንኛውም ስደተኛ ወደ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ የመቅ ረብ መብት አለው። ኦፒየም የስደተኞ ችን የጥገኝነት ጥያቄ የሚከታተል ራሱ ን የቻለ ኮሚቴ አለው። የስደተኞች ህጋ ዊነት ኮሚቴ (ሬፊዩጂ ኢሊጂቢሊቲ ኮ ሚቴ) ስደተኞች በሚያቀርቡት መረጃ ላይ ተመስርቶ ጥገኝነት ማግኘት ይገባ ቸው አይገባቸው እንደሆነ ይወስናል። ውሳኔውንም በይፋ በማስታወቂያ ያሳ ውቃል። ይህ ኮሚቴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት፣ የወታደራዊ ደህ

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

በኦፒየም የመልሶ ማስፈር ከፍተኛ ኦፊሰር ቻርለስ ባፋቺ

ንነት፣ የኢሚግሬሽን እና የኡጋንዳ ፖሊ ስ ተወካዮችን ያካተተ ነው፡፡ ኮሚቴው በወር አንድ ጊዜ እየተገናኘ የትኛው ስደ ተኛ እውቅናና ፈቃድ ማግኘት እንዳለበ ትና እንደሌለበት መርምሮ ውሳኔ ይሰጣ ል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) በስ

ወደ ገጽ 2 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

2

ዜና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ኢንተር ኤይድ የተሰኘው የኡጋንዳ ሀገ ር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ለስደተኞ ች ነጻ ህክምናና የምክር አገልግሎት እን ደሚሰጥ አስታወቀ። ድርጅቱ ይህንን ያስታወቀው የኢትዮ ጵያውያን ማህበረሰብ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በቅርቡ ከኢንተር ኤይ ድ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅ ት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤ ች.ሲ.አር) ተወካዮች ጋር የኢትዮጵያው ያንን ስደተኞች መብትና ግዴታ እንዲሁ ም ጥቅማጥቅም በሚመለከት በቅርቡ በ ተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ የማህበረሰቡ የ ስራ ሀላፊዎች በተለይ ለሐበሻዊ ቃና እን ደገለጹት በውይይቱ የስደተኞችን መብ ትና ግዴታ፤ የህግ ድጋፍና የጤና አገል ግሎትን ጨምሮ ከስድስት ነጥቦች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ላይ ኢንተርኤድን በመወከ ል የተገኙት ጠቅላላ አማካሪ ጃኩሊን ሙ ካሳ እና የስነልቦና አማካሪዋ አግነስ ትዌ ባዛ በበኩላቸው ድርጅቱ ለስደተኞች አገ ልግሎቶች በዝርዝር አስረድተዋል። የድ ርጅቱ ተወካዮች እንደገለጹት የስደተኝነ ት መታወቂያ ያለው ሁሉ በሙላጎ ሆስፒ ታልና በካምፓላ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ክሊኒኮች በመሄድ እስከ አንድ መቶ ሺህ የኡጋንዳ ሺልንግ ድረስ ነጻ ህ ክምና ማግኘት ይችላል፡፡ ለህክምናው የሚጠይቀው ወጪ ከአን

ድ መቶ ሺህ ሺልንግ ሲበልጥ ደግሞ ወ ደ ኢንተርኤድ ቢሄዱ ተጨማሪ ህክም ና የሚያገኙበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተወካዮቹ አመልክተዋል፡፡ ከነጻ ህክም ናው በተጨማሪም ለስደተኞች ብቻ የ ተመደበና የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰ ጥ አንድ አምቡላንስ አለ፡፡ በመሆኑም ች ግር የደረሰበት ስደተኛ አገልግሎቱን በ ማንኛውም ጊዜና ሰዓት ማግኘት ይችላ ል ብለዋል፡፡ ኤች አይ ቪ ኤድስ በደሙ ውስጥ የሚገ ኝ ስደተኛም የኢትዮጵያውያን ቀን በሆነ ው ዘወትር ረቡዕ ኢንተር ኤይድ እየሄደ ድርጅቱ ባዘጋጃቸው ሁለት ሐኪሞች አ ማካኝነት ነጻ የህክምናና የምክር አገልግ ሎት የማግኘት ሙሉ መብት አለው፡፡ የ ወባ መከላከያ አጎበርም ከኢንተርኤድ ለ ስደተኞች በነጻ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል ነው፡፡ በአንጻሩ ከግል የህክምና ተቋማት የሚ መጡ የህክምና ማስረጃዎችንም ሆነ የህ ክምና ወጪ ደረሰኞችን ኢንተር ኤይድ እንደማይቀበል ተወካዮቹ ጠቁመዋል፡፡ ከነጻ ህክምናው ባሻገር ለስደተኞች የ ሚዘጋጁ የቋንቋና አጫጭር የሙያ ስል ጠናዎች አሉ፡፡ ኦልድ ካምፓላ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ የማሰልጠኛ ተቋም ከሚሰጡት የሙያ ስልጠናዎች መካከል የምግብ ዝግጅት፣ የጸጉር ስራና አውቶ መካኒክስ ይገኙበታል፡፡ የአንደኛና የሁለ ተኛ ደረጃ ትምህርትም ለስደተኞች በነጻ የተፈቀደ የትምህርት እድል ነው፡፡

ኢንተር ኤይድ የዓለም የስደተኞች ቀንን አስመልከቶ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ያሰለጠናቸው ስደተኞች የሰሯቸውን ጌጣጌጦች እንዲሸጡ ድንኳን አዘጋጅቶ ነበር

ይሁንና ‹‹ብዙ ኢትዮጵያን ስደተኞች የ ህክምናውንም ሆነ የስልጠናውን አገል ግሎት መጠቀም ባለባቸው መጠን እየ ተጠቀሙ እንዳልሆነ የድርጅቶቹ ተወ ካዮች ነግረውናል›› ሲሉ የኢትዮጵያው ያን ማህበረሰብ የስራ አስፈጻሚ ሰብሳ ቢ አቶ ንጉሴ ባልቻ ለ“ሐበሻዊ ቃና” ተ ናግረዋል። ከአጫጭር ስልጠናዎች ባሻገር ያሉ የ ከፍተኛ የትምህርት እድሎች ጠባብ ናቸ ው የሚሉት የኢንተር ኤይድ ተወካዮች እነዚህንም ቢሆን ግን ለስደተኛው ለማ ዳረስ እየሰሩ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ አጫጭር ስልጠናዎች ስደተኞች በሚ ኖሩበት አካባቢ እንዲዘጋጁ የማህበረሰ

ኢትዮጵያ 3000 ወታደሮችን ወደ አቢዬ ልትልክ ነው በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ ኢትዮጵያ ወደ አወዛጋቢዋ የአቢዬ ግዛ ት 3000 ወታደሮችን በሰላም አስከባሪነ ት ልትልክ ነው። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ “የሰሜን እና የ ደቡብ ሱዳን መንግሥታት ወታደሮቻቸ ውን ሙሉ በሙሉ ካስወጡ በኋላ ኢት ዮጵያ አንድ ብርጌድ (3200 የሚደርሱ ወታደሮችን የያዘ) ጦር ወደ አቢዬ ትል ካለች” ብለዋል። ሰሜን እና ደቡብ ሱዳን በቅርቡ በፈረ ሙት የአዲስ አበባው ስምምነት መሰረ ት አወዛጋቢ የኾነችውን የአቢዬን ግዛት ማእከላዊ ክፍል ከጦር ኃይሎቻቸው ነፃ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ጦር ለማስገባት ተስማምተዋል ሲሉ ቃ ል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል። ደቡብ ሱዳን የዓለማችን 193ኛዋ ነፃ አ ገር ለመሆን ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም እ የጠበቀች ባለችበት በዚህ ወቅት ሁለቱ ሱዳኖች በመርህ ደረጃ በአግባቡ ያልተ ከለለውን የድንበር አካባቢ በሦስተኛ አ ካል የማስጠበቁን አስፈላጊነት ተስማም ተውበታል። በአዲስ አበባ በቅርቡ በተፈረመው ስ ምምነት መሰረት በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን መካከል እንደ እውነተኛ ገለልተኛ አካል የተቆጠረችው ኢትዮጵያ ከ3000 የሚበልጡ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን የድንበር አካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበ

ሐበሻዊ

በሥምምነቱ ላይ አፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቢዬ ከጦር ኃይል ነፃ እንድትኾን እና የኢትዮጵያ ወታደሮች መግባት እንዲችሉ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል

ቅ በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወታደራዊ ኃይል ነ ፃ በኾነው አካባቢ ታሰፍራለች። “በሥምምነቱ ላይ አፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቢዬ ከጦር ኃይል ነፃ እንድትኾን እና የኢትዮ ጵያ ወታደሮች መግባት እንዲችሉ እንዲ ያደርጉ ተጠይቀዋል” ሲሉም አምባሳደ ሩ ተናግረዋል።

ቃና

በሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ የሚታተም ጋዜጣ

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳን ት ታቦ ምቤኪ የተፈረመውን ሥምምነ ት ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ከምክር ቤቱ ይሁንታን አግኝቷል። የሰሜን ሱዳን ወታደሮች የነዳጅ አምራ ች አካባቢ የሆነውን የአቢዬን ግዛት በኃ ይል የተቆጣጠሩት በተባበሩት መንግሥ ታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ታጅቦ በ መንቀሳቀስ ላይ በነበረ አንድ ቡድን ላይ ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋ ለመመለስ በሚ ል ነበር። ተቆጣጥረውታል። ሰሜን ሱ ዳን አወዛጋቢውን ቦታ በኃይል መቆጣ ጠሯን ደቡብ ሱዳን እና የተባበሩት መ ንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አው ግዘውታል። የሰሜን ሱዳን ወታደራዊ ኃይሎችን የ ግንቦት ወረራ ተከትሎ ከ100 ሺህ በላይ የሚገመቱ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለ ዋል። እንደ ደቡብ ሱዳን ሁሉ አቢዬም ሕዝበ ውሳኔ በማድረግ በወደፊት እጣ ዋ ላይ እንድትወስን ይጠበቅ ነበር። የደ ቡቡ ሕዝበ ውሳኔ ቀደም ብሎ በጥር ወ ር የተደረገ ሲኾን 98 ከመቶ የሚኾነው ሕዝብ ከሰሜን ሱዳን ለመገንጠል ድም ፅ ሰጥቷል። የአቢዬ ሕዝበ ውሳኔ ያልተካሄደው ደ ቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር ቁርኝት ያ ላቸውን እና አካባቢውን ከዓመቱ በከፊ ል ከብቶቻቸውን ለማሰማራት የሚጠቀ ሙበት ምስሪያዎች በሕዝበ ውሳኔው እ ንዳይሳተፉ በመከልከሏ ነበር።

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

ቡ ስራ አስፈጻሚዎች ላቀረቡት አማራ ጭ መፍትሄም ፕሮጀክት ቀርጸው እን ዲያቀርቡ ከድርጅቱ በኩል ሀሳብ ቀርቧ ል፡፡ ‹‹ሀሳቡንም በቅርቡ ወደ ተግባር ለ መቀየር እየሰራን ነው ››ብለዋል አቶ ን ጉሴ፡፡ የማህበረሰቡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በኩል የሚ ታዩ ናቸው ያላቸውን ችግሮችም በዚሁ ስብሰባ ላይ በመወከል ለተገኙት አሲ ሙዌ ጆን አቅርበዋል። ብዙ ስደተኞች የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መ ርጃ ድርጅት(ዩኤንችሲአር) የኡጋንዳ ቢ ሮ በተለይ ለስደተኞች ተገቢውን አገልግ ሎት አይሰጥም፡፡ ይልቁንም ስደተኞችን

ያጉላላል፡፡ ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው ን ክብር አይሰጥም፡፡ ቢሮውንም ክፍት አያደርግም በሚል ይወቅሳሉ፡፡ ይህንን ተከትሎም ሲውዘርላንድ ጀኔቫ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት የ መጡ የስደተኛ ጉዳይ ተከታታዮች ቡድ ን በኡጋንዳ የሚገኙ ስደተኛ ተወካዮች ን በኡጋንዳ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳ ራሽ አነጋግረዋል፡፡አቶ ንጉሴ እንደሚሉ ት ውይይቱ የኢትዮጵያ፤ ኤርትራ፤ ኮን ጎና ሶማሊያን ጨምሮ የብዙ ሀገር ስደ ተኛ ተወካዮች የተገኙበትና አሉብን ያ ሏቸውን ችግሮችም ለተወካዮች ያሰሙ በት ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብም በው

የማላዊ ፖሊስ 30 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሰረ

ከገጽ 1 የዞረ

በርካታ ኢትዮጵያውያን ማላዊን ከታንዛንያን ጋር በሚያዋስነው ሶንግዌ ወንዝ አድረገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሞክሩ ይይዛሉ

የማላዊ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ሊገቡ ሲሉ ተይዘዋል ያላቸውን 30 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ በሰሜን ማላዊ የምትገኘው ካሮንጋ ከተማ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኢ ኖክ ሊቫሶኒ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ወደ ማላዊ እ ንዲገቡ አግዘዋል ያላቸውን ሁለት የሀገሪቱ ዜጎችንም ፖሊስ ዘብጥ ያ አውርዷቸዋል፡፡ እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ተጠርጣሪ ስደተኞቹ በሰሜን ሮኩሩ በፖሊ ስ በተደረገ አሰሳ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ ስደተኞቹ በህገወጥ መንገድ ወደ ሌላ ሀገር በመግባት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ (በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ)

ወደ ሶስተኛ ሀገር... ከገጽ 1 የዞረ

ይይቱ በመገኘት ስደተኞች በተለይ ከ ዩኤን.ኤች.ሲ. አር የሚደርስባቸውን መ ጉላላትና እንግልት ለተወካዮቹ አሳውቋ ል፡፡ ተወካዮችም በወቅቱ ለቀረቡ ጥያቄ ዎች መፍትሄ ለማፈላለግ ቃል መግባታ ቸውን የሚያስታውሱት ሰብሳቢው ከ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እና ኢንተር ኤይድ የ ኡጋንዳ ቢሮ ተወካዮች ጋር ከሰሞኑ የተ ደረገው ውይይትም የእዚህ ውጤት መ ሆኑን ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያውን ስደ ተኞች ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር የሚወጣ መ ረጃን እንዲሁም መብትና ግዴታቸውን በተመለከተ በቋንቋቸው የተዘጋጀ ነገር ባለመኖሩ የሚፈጠረውን የመረጃ ክፍ ተት አስመልክቶ ከኢትዮጵያውያን ማ ህበረሰብ ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ዩ.ኤን.ኤ ች.ሲ.አር መረጃውን ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እንዲሰጥ እና ማህበረሰቡ ም በዋና ዋና ቋንቋዎች ተርጉሞ ለስደተ ኞች እንዲያሰራጭ በውይይቱ ወቅት ከ ስምምነት ላይ ተደርሷል። እንደ አቶ ንጉሴ ከተወካዮች ጋር የተ ደረገው ውይይት “በአይነቱ የመጀመሪና ስኬታማ ነበር” ይላሉ፡፡ለማህበረሰቡም ለወደፊት መስራት የሚገባውን በርካታ የቤት ስራዎች የሰጠ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ንጉሴ ከእነዚሁ ድርጅቶችና የስደተ ኛ ጉዳይ ከሚመለከታቸው የኡጋንዳ መ ንግስት አካላት ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንናደርጋለን ብለዋል፡፡

ኦፒየም ...

ፎቶ- ቴዎድሮስ ነጋሽ ለኢሪን

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

ኢንተርኤይድ ለስደተኞች ነጻ የህክምናና ስልጠና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ

ተቀባይ ሀገሮች ምክንያት ነው፡፡ ለዚህም በመልሶ ማስፈር ፕሮግ ራም በርካታ ስደተኞችን የምትወስደው አሜሪካንን በምሳሌነት ይ ጠቅሳሉ። “በተለያዩ የሽብርተኝነት ተግባራት ምክንያት በርካታ ሰዎች ለመል ሶ ሰፈራ የሚሄዱባት ዩናትድ ስቴትስ በስደተኞች ላይ የምትወስደው የማጣሪያ ጊዜ ከዚህ ቀደሙ ረዘም ያለ ሆኗል” ይላሉ። “ከቅርብ ጊ ዜ ወዲህ ተቀባይ ሀገራት ባለባቸው ትክክለኛ የደህንነት ችግር ምክ ንያት የሚቀበሉበት ሂደት በእርግጥም ረዝሟል” ሲሉ መዘግየት መ ኖሩን ያረጋግጣሉ።

ብሰባው በታዛቢነት ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኦፒየም የስደተኝነት ፍቃድ ለ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ እንደመጣ ስደተኞች ይናገራ ሉ። በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውን የስደተ ኝነት ማመልከቻቸው ውድቅ እየተደረገ መሆኑንም ይ ጠቅሳሉ። ኡጋንዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ከአለም አቀፍ ህግ ጋር የተጣጣመ ሲል ያወዱሱትን የስደተኞች መ መሪያ ህግ (ሬፊዩጂ አክት) እ.ኤ.አ በ2006 ባጸደቀች ጊዜ እንዲህ ዓይነት አቤቱታዎችን ለመፍታት ይግባኝ ሰሚ መቋቋም እንዳለበት ደንግጋ ነበር። ሆኖም እስካ ሁን ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል። የይግባኝ ሰሚ ቦርዱ ከተቋቋመ ሁለት ወራት ማለፉ ን ባፋቺ ያስረዳሉ። ሆኖም በዚህ ዓመት የተካሄደውን የኡጋንዳ ምርጫ ተከትሎ አዲስ ካቤኒ ተመስርቶ ሚኒ ስቴር እስኪሾም ድረስ የቦርድ አባላቱ ሹመት መዘግየ ቱን ያምናሉ። የቦርዱ አባላት ከህብረተሰቡ ውስጥ የ ሚመረጡ ሲሆን ተሰሚነት ያላቸው እና የተከበሩ መ ሆን አለባቸው። ሹመታቸውን የሚያጸድቀው ጠቅላ ይ ሚኒስቴሩ ነው። የኡጋንዳ መንግስት ቀድሞ ጠቅላ ይ ሚኒስቴር የነበሩትን አፖሎ ሲባምቢን አንስቶ በአ ማማ ምባባዚን በቅርቡ መተካቱ ይታወሳል። ምባባዚ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮውን መረከብ ተከት ሎ የቦርዱ አባላት ሹመት በቅርቡ እንደሚፈጸም ባፋ ቺ ይናገራሉ። የይግባኝ ሰሚ ቦርዱ ከአምስት እስከ አ ስር አባላት እንደሚኖሩት በህግ ተደነግጓል። ስብሰባ ለ ማካሄድ እና በጉዳዮች ለመወሰን ግን የአምስት አባላት መገኘት በቂ ነው። የቦርዱ አባላት ጉዳዮችን የሚመለ ከቱት በኦፒየም በመገኘት ይሆናል። ጉዳያቸው ውሳኔ ሳያገኝ ስለሚዘገይባቸው ስደተኞች ጉዳይ የተጠየቁት ባፋቺ በአሁኑ ወቅት መዘግየት እን ደሌለ ያስረዳሉ። ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ላይ እስኪደረስ ግን “ጥቂት ወራት” እንደሚፈጅ ግን አልደበቁም። ጥ ቂት ወራት ስንት እንደሆነ ለማብራራት ያልፈቀዱት ባ ፋቺ በአሁኑ ወቅት ምንም የተከማቸ የስደተኛ ጉዳይ እንደሌለ ይናገራሉ።

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ዩጋንዳ ካምፓላ ጋባ ሮድ-ካሳንጋ ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6 ስልክ +256-778-693669 ኢሜይል habeshawikana@gmail.com


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

3

ዜና

ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ሱዳን ሁለተኛ መንገድ ልትገነባ ነው

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እየወጡ ነው በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

በጋምቤላ በኩል ከደቡብ ሰዳን ጋር የ ሚያገናኛትን መንገድ በመገንባት ላይ የ ምትገኘው ኢትዮጵያ ከደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የሚነሳ ተጨማሪ ሁለተኛ መንገ ድ ለመስራት ቅድመ ስራዎችን በማጠና ቀቅ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ መንገዶች በላስልጣን ምክ ትል ዳይሬክተር አቶ በቀለ ንጉሴ ለሐበ ሻዊ ቃና እንደገለጹት ኢትዮጵያ ልትገነ ባ ያቀደችው ሁለተኛ መንገድ ከሚዛን ተነስቶ በዲማ አድርጎ ኢትዮጵያን ከደ ቡብ ሱዳን ጋር ወደምታዋስናት ጎማ ይ ደርሳል። “መንገዱ በአስፋልት ኮንክሪት ነው የ ሚገነባው። ወደ 300 ኪሎ ሜትር ይሆ ናል። ትልቅ ፕሮጀክት ነው” ሲሉ አቶ በ ቀለ ከአዲስ አበባ በስልክ ገልጸዋል። የመንገዱ የዲዛይን ጥናት ኤች. ኢ.ቲ ኢ ትዮጵያ በተባለ ኢትዮጵያዊ አማካሪ ድ ርጅት ተከናውኖ መጠናቀቁን የሚናገሩ ት አቶ በቀለ ከዚህ በኋላ የሚቀረው ወ ደ ተግባር መግባት መሆኑን ይናገራሉ። ወደ ተግባር ከመገባቱ በፊት ግን ከደቡ ብ ሱዳን በኩል ያለው መንገድ ለመስራ ት እንቅስቃሴዎች መጀመር እንዳለባቸ ው ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ ወገን ያለው መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት ተሰርቶ እ ንኳ ቢጠናቀቅ በደቡብ ሱዳን በኩል ያ

ፎቶ- ቢቢሲ

በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

ደቡብ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በቂ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሌሉባት ናት

ለው መንገድ በተመሳሳይ ካልተገነባ ትር ጉም የለውም ባይ ናቸው። ከጁባ እስከ ጎማ ያለው መንገድ 500 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ነው። በመጪው ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም ሀገር መሆኗ ን በይፋ የምታውጀው ደቡብ ሱዳን በ ቂ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሌሉባ ት ናት። የሱዳንን የምዕተ ዓመቱ የልማ ት ግቦች አካሄድ የሚገመግም ሪፖርት እንዳስቀመጠው ከሆነ ጦርነት ካበቃበ ት እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በደቡብ ሱዳ ን የተከፈቱ መንገዶች ድምር ርዝመት ሁ ለት ሺህ ኪሎ ሜትር ገደማ ይደርሳል። “የትራንስፖርት እና መንገዶች ሚኒስቴ

PPS

ር በበጋም ሆነ በክረምት የሚሰሩ መንገ ዶች በተለያዩ የደቡብ ሱዳን ክፍሎች እ ያስፋፋ ይገኛል” ይላል ሪፖርቱ። “ሚኒስ ቴሩ ደቡብ ሱዳን ከጎረቤት ሀገራት እና ከሰሜን ሱዳን ጋር የሚያገናኛትን መንገ ድም ይዘረጋል” ሲል የደቡብ ሱዳን መን ግስት በአሁኑ ወቅት እየሰራ ያለውን ያ ብራራል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እ.ኤ.አ በ2010 ለሚገነቡ መንገዶች 463 ሚሊዮን የሱዳ ን ፖውንድ (181 ሚሊዮን ዶላር) መድ ቦ ነበር። ከእዚህ በጀት ውስጥ 275 ሚ ሊዮን የሱዳን ፓውንድ (107.5 ሚሊዮን ዶላር) ለ17 የመንገድ ፕሮጀክቶች ማሰሪ

ያ ተከፋፍሏል። ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገና ኝትን መንገድ በመስራት በኩል አዝጋሚ ብትሆንም በኢትዮጵያ ወገን ያለው የመ ጀመሪያ የመንገድ ፕሮጀከት እየተቀላጠ ፈ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ከጋምቤላ ጂካዎ ድረስ ያለውን 124 ኪሎ ሜትር መንገድ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ማሳደግ ነ ው። ከመንገዱ ውስት 80 ኪሎ ሜትሩ ያህሉ መሰራቱን የሚገልጹት እንደ አቶ በቀለ በአሁኑ ፍጥነት ከተሄደ ፕሮጀክቱ የዛሬ ዓመት ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠና ቀቅ ያስረዳሉ። ይህ መንገድ እየተገነባ የ ሚገኘው በየኢትዮጵያ መንገዶች ባለስል ጣን ሰራተኞች ነው።

በየመን ከወራት በፊት የተጀመረውን ህ ዝባዊ አመፅ ተከትሎ ከተከሰተው አለመ ረጋጋትና ብጥብጥ ለማሸሽ ፈቃደኛ ኢ ትዮጵያውያንን ከሀገሪቱ እያስወጣ መሆ ኑን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት(አ ይ.ኦ.ኤም) አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ እንዳስታወቀው እስካሁን 275 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ እንዲወ ጡ ከተደረጉት ስደተኞች መካከል 34ቱ ሴቶች 115ቱ ደግሞ ህጻናት ሲሆኑ በጥይ ት ተመትው የቆሰሉ ይገኙበታል፡፡በጥቅ ሉ የመንን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ የ ሆኑ 2000 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተ ኞች ተራ እየጠበቁ ይገኛሉ። አይ.ኦ.ኤም ሌሎች 1900 ያህል በሳው ዲአረቢያና የመን ድንበር የሚገኙ ኢት ዮጵያውያን ስደተኞችን የማስወጣት እቅ ድ እንዳለውም አስታውቋል፡ የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚ ያመለክተው በያዝነው የፈረንጆች ዓመ ት ብቻ 37ሺህ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊ ያውያን ስደተኞች ወደ ሳውዲ አረቢያና ሌሎች አረብ ሀገራት ለማቋረጥ የመን ገ ብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙዎች መድረ ሻ በማጣት ከሳውዲአረቢያ በሚያዋስነ ው የየመን ድንበር በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ይገኛሉ፡፡ የስደተኞች መርጃ ድርጅት እንደሚለ

ው ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በሀገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት እንደ መልካ ም አጋጣሚ በመጠቀም ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ የመን እያስገቡ ለእንግል ት እየዳረጓቸው ነው፡፡ ከየመን እንዲወጡ ከተደረጉት ስደተ ኞች መካካል ኢድርስ የተባለ ግለሰብ ለ ቢ.ቢ.ሲ የአፍሪካ ፕሮግራም እንደተናገ ረው በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ስር በነበረበ ት ጊዜ ያሳለፈው ስቃይና መከራ በህሊና ው እየተመላላሰ አስቸግሮታል፡፡ “ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሁላችንን ሰብስ በው ካስቀመጡበትና ሴቶችን ከሚቆጣ ጠሩበት ብሎም ከሚያሰቃዩበት ማዕከ ል አምልጬ ነው የመጣሁት ብሏል” ፡ ፡ “አንድ ሴት በስምንት ወንድ ስትደፈ ር አይቻለሁ” የሚለው እድሪስ ወንዶች ም ከተመሳሳይ ጥቃት እንደማያመልጡ ተናግሯል፡፡ ግብጽና ታንዛንያን ተከትሎ በሰሜን አ ፍሪካ ሀገራት የተቀጣጠለው ህዝባዊ አ መጽ በየመንም ከተከሰተ ወራት የተቆጠ ሩ ሲሆን ይህን ተከትሎ የተከሰተው ግ ጭትም ለበርካቶች ሞትና መቁሰል ምክ ንያት ሆኗል፡፡ ባለፈው ወር ሁለት ሶማ ሊያውያን ስደተኞች በዋና ከተማዋ ሰን ዓ በብጥብጡ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ፕሬዚዳንት አብደላህ ሳለህ የመንን ላለ ፉት 30 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት እየመ ሩ ሲሆን ወራት ለዘለቀው ህዝባዊ አመ ጽ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ስልጣን አልለ ቅም ብለዋል፡፡

Precise Printers & stationeries Ltd

Printing Full colour RBooks RReceipts/ Vouchers RMagazines RBusiness cards RPaper bags RPizza & cake boxes

በሙሉ ቀለም ህትመት አገልግሎታችን

Rመጽሐፍት Rቢዝነስ ካርዶች Rደረሰኞች እና ቫውቸሮች Rካኪ ኪስ ወረቀቶች Rመጽሔቶች Rየፒዛ እና ኬክ መያዣዎች እናትማለን

Other services

ሌሎች አገልግሎቶች

m Type Setting mCutting mStitching mDie cutting mታይፕ ማድረግ mመቁረጥ mመጠረዝ mፐርፎሬሽን mPerforation mThermography (Embossing) etc ADDRESS: Plot 575 Bweyogerere Kampala, Uganda

CONTACT US:

mቴርሞግራፊ (ኢምቦሲንግ) mዳይ ከቲንግ

Mob +256-752-707932 Office +256-414-598512 P.O.Box 26043 Email: precise@preciseprinters.com sales@preciseprinters.com


ሐበሻዊ ቃና

4

ዜና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ለስደተኞች ነጻ የቋንቋና ኮምፒውተር ስልጠና እየተሰጠ ነው በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ቀጣዩ ዙር ስልጠና በነሐሴ ይጀምራል ፓን አፍሪካ የልማት፤ የትምህርትና ቅ ስቀሳ መርሃግብር(ፓዴፕ) የተሰኘ መን ግስታዊ ያለሆነ ድርጅት በኡጋንዳ ለሚ ገኙ ስደተኞች ነጻ የኮምፒውተርና የቋን ቋ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ የቋንቋ ስልጠናው ስድስት ወር መሰረ ታዊ የኮምፒውተር ትምህርቱ ደግሞ ከ ሶስት እስከ አራት ወር የሚፈጅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሁለቱም መስክ እየተሰ ጠ ያለው ስልጠና ነሀሴ አጋማሽ እንደ ሚጠናቀቅ የየመስኩ አሰልጣኞች አስታ ውቀዋል፡፡ በመሆኑም ቀጣዩ ዙር ስልጠና ከነሐሴ መጨረሻ እስከመስከረም ባለው ጊዜ ይ ጀመራል ብለዋል አሰልጣኞቹ፡፡ ድርጅቱ የስነልቦናና የህግ ምክር ለሚ ሹ ስደተኞችም ካባላጋላ ከአብነት ሬስ ቶራንት ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮው አገ ልግሎቱን በነጻ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ልብስ ስፌትና የምግብ ዝግጅትም በድ ርጅቱ አማካኝነት ለስደተኞች የሚዳረስ ነጻ አገልግሎት ነው፡፡ ከሐበሾች መንደር ወይዘሮ እታፈራሁ በቀለ ወደ ኡጋንዳ በስደት ከመጡ አምስት አመት ያህል ሆ ኗቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ለቴ ክኖሎጂ ባዳ ሆኜ ቆይቻለሁ ይላሉ፡፡ አ ሁን ግን ከፓዴፕ ባገኙት ነጻ የኮምፒው ተር ስልጠና ከማያውቁት አለም ጋር ወ ዳጅነት እየመሰረቱ ነው፡፡ ‹‹ኢንተርኔት ም ሆነ ኢሜል የሚባል ነገር አላውቅም ነበር›› የሚሉት ወይዘሮ እታፈራሁ አሁ ን ግን ከስልጠናው የእነዚህንና ተያያዥ

መሰራታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀምን እየተማሩ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ህ ይወቴን በእጅጉ ለውጦልኛል፡፡ ይህ ለእ ኛ ለስደተኞች እግዚአብሔር ያዘጋጀው መንገድ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ መማር እየፈለ ግሁ አቅሙ ስላልነበረኝ ነው ያልተማር ኩት፡፡ አሁን ግን ይሄንን እድል አግኝቼ እየተጠቀምኩበት ነው፡፡ ሌሎችም ይህ ን እድል እንዲጠቀሙ እመክራለሁ›› ብ ለዋል ስልጠናን ሲከታተሉ ላገኛቸው የ ሐሻዊ ቃና ዘጋቢ፡፡ ወይዘሮ እታፈራሁ የኮምፒውተር ስል ጠናውን ሲጨርሱ ደግሞ ቋንቋ ለመማ ር እየተዘጋጁ ነው፡፡ እንደ ወይዘሮ እታፈራሁ ሁሉ ከሀያ የ ሚበልጡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራው ያን በአሁኑ ወቅት እተሰጠ ያለውን የቋ ንቋና የኮምፒውተር ስልጠና እየተከታ ተሉ ነው፡፡ ለቀጣዩ ዙር ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ን ያስታወቁት የእንግሊዘኛ ቋንቋ አሰል ጣኙ ኪባንጋ ጆን ስልጠናውም በሁለት ደረጃ የሚሰጥ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ረፋ ድ ላይ ለጀማሪዎች ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ በትንሹ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ለሚ ችሉ የተመደበ ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ የኮምፒውተር ስልጠናውም ቢሆን በ ቀን ሶስት ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ወዲያ ወዲህ የ ሚሉ ስደተኞችን ከግምት ያስገባ መሆኑ ን የድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አሰልጣኙ ኩባና አሌክስ ይናገራል፡፡ የ ቋንቋ ስልጠናው ለስድስት ወር የሚዘል ቅ ሲሆን የኮምፒውተሩ ደግሞ ከሶስት እስከ አራት ወር በሚደርስ ጊዜ ይጠና

ቀቃል፡፡የቀጣዩ ዙር ስልጠና ከነሀሴ መ ጨረሻ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ው ስጥ እንደሚጀመርም አሰልጣኞቹ ጠቁ መዋል፡፡በማንኛውም ስልጠና ማብቂያ ደግሞ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ይ ሰጣል፡፡ በስልጠናዎቹ ላይ ሐበሾች በተለይም ኢትዮጵያውን ደህና የሚባል ድርሻ ቢ ወስዱም የድርጅቱ አማካሪዎች እንደሚ ገልጹት የምክርና የህግ አገልግሎቱን የ ሚጠቀሙት ግን እጅግ ጥቂት ናቸው፡፡ ስደተኞች የሚደርስባቸውን የስነልቦና ና ማህበራዊ ችግሮች የምታማክረው ካ ያንጋ ሚሪያም እንደምትለው ኢትዮጵያ ውያንም ሆኑ ኤርትራውያን ወደ ቢሮዋ የሚመጡት ከስንት አንድ ጊዜ ነው፡፡ ማሪያም ሐበሻ ስደተኞች ወደ ቢሮዋ የ ማይመጡት የቋንቋ ችግር እንቅፋት ስለ ሚሆንባቸው መሆኑን ትገምታለች፡፡ይ ሁንና እነሱ አገልግሎቱን ከፈለጉና ፈቃ ደኛ ከሆኑ አስተርጓሚ እናዘጋጅላቸዋለ ን ትላለች፡፡ “ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ኤ ርትራውያን ያለምንም መሳቀቅ ወደቢ ሮአችን መጥተው የምክር አገልግሎቱ ን እንዲያገኙ ጥሪ አስተላልፋለሁ፡፡ ም ክሩን ፈልገው በቋንቋ የመግባባት ችግር እንኳን ቢያጋጥም አስተርጓሚ እንመድ ብላቸዋለን፡፡ የእኛን አስተርጓሚዎች ካ ልፈለጉና እነሱ ማምጣት ከቻሉም መል ካም ነው::” የህግ አማካሪው ሉሊናኪ ፍሬድ የሚ ያቀርበው ሀሳብም ተመሳሳይ ነው፡፡ የ እሱንም ቢሮ ሀበሾች እንደልባቸው አይ ገቡ አይወጡበትም፡፡ ‹‹ስደተኞች በርካ ታ የህግ ችግር አለባቸው›› የሚለው ፈሬ

አስተያየት q ጸሁፍ q ጥቆማ… q

በሐበሻዊ ቃና የኢሜይል አድራሻ habeshawikana@gmail.com አድርሱን። በ+256-778-693669 ይደውሉልን።

ድ አልፎ አልፎ እርሱ ጋር የሚመጡት ሐበ ሾች ጉዳይም ከሀገር ሀገር ከመጓዝ ፈቃድ ጋ ር በተያያዘ መሆኑን ይናገራል፡፡ ፍሬድ የህግ ድጋፍና ምክር ማግኘት እየቻ ሉ የሚንገላቱ ስደተኞች በርካታ ናቸው፡፡ እንደ እርሱ አባባል አንዳንዶች ጉዳያቸው የ ህግ ድጋፍ እንዳለው ቢገነዘቡም በየትኛው ዘርፍ መመደብ እንዳለበት ግን አያውቁም፡፡ በመሆኑም ፓዴፕ መጥተው ከእርሱ ጋር ቢ ማከሩ ያለምንም ክፍያ መፍትሄ ሊጠቁማቸ ው እንደሚችል ያምናል፡፡ የስልጠናም ሆነ የምክር አገልግሎት ተጠ ቃሚ ለመሆን የስደተኝነት መታወቂያን ብ ቻ የሚጠይቀው ፓዴፕ የስደተኞችን ንቃተ ህሊና ለማሳደግና በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ

ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየጊዜው አውደጥ ናት ያዘጋጃል፡፡ ዘወትር ሰኞ እና ሮብዕ ቢመጡ ቢሮየ ክፍት ነው የምትለው ማርያም ስደተኞ ች ምስጢራቸው ተጠብቆ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ባይ ናት፡፡ የ ህግ አማካሪው ፈሬድ በበኩሉ በሳምን ት አርብ የማማከር ቀኑ እንደሆነ ቢገል ጽም አገልግሎቱን ፈልጎ ለመጣ ሁሉ ለ ሁለቱም በሚመች ቀንና ሰዓት ማማቻ ቻት እንደሚችል ይናገራል፡፡ ፓዴፕ በሰብአዊ መብትና ተያያዥ ጉ ዳዮች ዙሪያ የሚሰራና እ.ኤ.አ በ1997 የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅ ት ነው፡፡


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የአሸዋው ጉም ላንድ ክሩዘሯን እንደ ሸራ አልብ ሷታል። 40 ዲግሪ ሴልሺየስ የሚጠጋው ሙቀ ት እንደ ዕቃ ተጠቅጥቀው የተጫኑትን ተሳፋሪ ዎች ትንፋሽ አሳጥሯቸዋል። አንዳቸውም ከሌላ ጋራ አይነጋገሩም። በረኀውን ሰንጥቆ እንደ ምን ጣፍ የተዘረጋው አስፋልት የት እንደሚያደረሳቸ ው በማሰላሰል አዕምሮአቸውን ያስጨነቁ ይመ ስላሉ። ለሰዒድ ሐጎስ ግን እንዲህ ያለ ጉዞ አዲ ስ አይደለም። ወጣትነቱ ያለፈው ሲኳትን ነው። ቢሆንም የአ ሁኑ ለየት ይላል። በዕድሜ ዘመኑ ከወሰናቸው ሁለት ከባድ ውሳኔዎች አንዱ ስለመሆኑ ጥርጣሬ የለውም። በለጋ እድሜው በትውልድ ቀየው ጠ ግቦ ሳይጫወት የአካባቢው ታላላቆቹ የፈጸሙት ጀብዱ በየጓዳው ሲነገር እርሱም ከእነርሱ አንዱ ለመሆን ጫካ ገብቷል፤ ለኤርትራ “ናጽነት።” ዛሬ ደግሞ ለራሱ ነጻነት። ከመኪናው ፍጥነት እና ከመንገዱ ርቀት እኩል የቀድሞውን ማሰብና ማሰላሰሉን አላቋረጠም። የወጣትነቱ ድካም ሁሉንም እንደዋዛ ርግፍ አድ ርጎ ጥሎ ሌላ የሕይወት ፍልሚያ ለመጋፈጥ መዘ ጋጀቱ በፍርሀት ቢያስውጠውም የተነሳለት ዓላ ማ ብርታት ሆኖታል። ሰዒድ ተወልዶ ያደገው ኢትዮጰያ ውስጥ ነ ው፤በዛሬው አፋር ክልል። አባቱ ደግሞ በግብር ና እና አነስተኛ ንግድ ሳሆ ይኖራሉ-ኤርትራ። ወ ደ እነ ሰዒድ እናት ቤት የሚመጡ እንግዶች ሰለ አባቱ መልካምነት እና የተሻለ ኑሮ ሲያወሩ ሰም ቶ አባቱን ለመቀላቀለ ልቡ ተነሳ። “የምወዳት እ ናቴን ሳልሰናበት ተደብቄ ጠፋሁ “ይላል። በዚያ ው ከእናቱ እንደተለየ ቀረ። አባቱም የሚነገርላቸውን ያህል የተደላደለ ኑሮ ባይኖርቸውም ኑሯቸው ስዒድን “ባልመጣሁ” የሚያስብል አልነበረም። በደስታ እንባ ተቀብለ ው ከንግድ ጋር አስተዋወቁት። ሸቀጣ ሸቀጥ ቀረ ብ ብለው በሚገኙ ከተሞች ይነግድ ጀመረ። የአ ባቱ ጥላ ሆነ። አባቱን በጎረምሳ አይደክሜ ጉልበ ቱ እያገዘ ሳለ ኤርትራን ነጻ ለማውጣት ጫካ ገብ ተው ብረት ስላነሱ የአካባቢው ወጣቶች ወሬ ይ ሰማል። ጓደኞቹ አንድ አንድ እያሉ የሻቢያን ጦር ሲቀላቀሉ የእርሱም ልብ ሸፈተ። በድንገት የተገና ኛቸውን አባቱን በድንገት ጥሏቸው ሄደ። ሰዒድ የትግል ሕይወት እንዳሰበው አልጠበቀ ውም። ልጅ ቢጤ ስለነበር ቶሎ ጥንካሬ ማግኘ ት አልቻለም። ወደ አባቱ መመለስ ደግሞ በፍ ጹም የማይሞከር ነበር። “ከእናቴ ተለይቼ ወደ ዚያ ምድር የመጣሁበትን ቀን የረገምኩት እና የ ተጸጸትኩት ያኔ ነው። ይሁን እንጂ የግዴንም ቢ ሆን ከትግል ሕይወት ጋራ ተላመድኩ “ይላል። ”እኔም ሆንኩ ቤተሰቤ የተሻለ ሕይወት የምናገኘ ው ከኤርትራ ነጻነት በኋላ እንደሆነ አዕምሮዬ አ ምኖ ተቀበለ።” 1983ዓ.ም። ጦርነቱ ሻእቢያ አስመራን፤ወያኔ አ ዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ ተጠናቀቀ። ኤርትራም ተገነጠለች። ሰዒድም ወላጆቹን በይበልጥ አራራ ቀ – እናት ኢትዮጵያ ፣ አባት ኤርትራ። ኤርትራ እንደ ሀገር ከቆመች። በኋላም አንዳንድ ተዳፍነ ው የቆዩ ጥያቄዎች ያቃጭሉብት ጀመር። “ራሴ ን መቼ ነው ከታጋይነት በላይ ከፍ አድርጌ የማ የው” የሚል። ከነጻነት በኋላ በነበሩት ሁለት እና ሶስት ዓመታ ት እነዚህ ስሜቶች አልነበሩትም። “ኤርትራ እን ደሀገር መንቀሳቀስ ስትጀምር የኑሮ እና የሥራ እድገት ፈለግሁ። ሆኖም ግን የእኔ ሐሳብ እና እ ውነታው ለየቅል ሆነ። ከበረኅው ሕይወቴ የሚለ የው ጥይት አለመተኮሴ እና ነገ እሞት፤ ዛሬ እሞ ት የሚለው ስጋት መጥፋቱ ብቻ ነበር።” ከ”ናጽ ነት” በኋላ ስሙ ወደ “ይክኣሎ” (ሁሉ ይቻላዋ ል) ከመለወጡ በስትቀር ጠብ ያለለት ነገር አል ነበረም። ኢትዮጵያ ትቷቸው የሄዱት እናቱ የት እንደሚኖሩ አያውቅም። አሁን እናቱን ስለ ማግ ኘት ማሰብ ይዟል። የሰዒድ ጥያቄዎች ሳይመለሱ የኢትዮጵያ እና ኤ ርትራ የድንበር ጦርነት ትኩስ ዜና ሆነ። የ“ይክአ ሎ” ( ሁሉ ይቻላዋል፣ ምን ይሳንዋል) ጦር ከዋር

ሐበሻ በምስራቅ አፍሪካ

“ይክኣሎ”

ሳይ ( ወራሼነህ-የሳዋ ስልጣኞች) ጀርባ በተጠን ቀቅ እንዲሆን ታዘዘ። እርሱም ሰንዓፌ ላይ ግዳጁ ን ሊወጣ ተሰለፈ። የጥይትን ድምጽ እንደዚያ በ ጋመ ሁኔታ ከሰማ ስምንት ዓመታትን አሳልፎ ነበ ር።ውትድርና ሞያው ሆኖበት እንጂ የልጅነት ወ ኔው አብሮት አልነበረም። “የጦርንቱ ፋይዳ ምን ም ሳይገባን ከ70 ሺህ በላይ ወታደር እልቂት ከታ የበት እሳት ውስጥ ተርፌ ወጣሁ።” የጦርነቱ ቁስ ል ሳይድን ኢትዮጵያዊ ደም ያለባቸውን ዜጎች ከ ኤርትራ ማባረር ተጀመር። ይህን ርምጃውን ቀድማ ኢትዮጵያ ከመውሰዷ ባሻገር አፈጻጸሙ የከፋ ነበር። አምቼዎቹ የኤርት ራን ምድር ሲረግጡ ደግሞ ሁኔታው ተጋግሎ በ ሀገሩ ናኘ። ይኽም አጸፋውን አባባሰው። ከልጅነ ት እስከ እውቀታቸው በኤርትራ የሚኖሩ ኢትዮ ጵያዊ እናት ወይም አባት ያለው ኤርትራዊ ሁላ ጨርቄን ማቄን ሳይል እንዲሰደድ ተፈረደበት። ሁኔታው የበቀልም ጭምር ስለነበር በስሜታዊነ ት የተሞላ ሆነ። እናም የዚህ ጦርነት ጦስ ለሰዒድ ተረፈ። በጦር ሠራዊት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው ወታደ ሮች በይፋም ባይሆን በሌላ ዐይን መታየት ጀም ሩ። ጠንከር ባሉ ጉዳዮች ላይ ከሚደረጉ ውስጥ ስብሰባዎች ወጪ ሆኑ። የወቅቱ ሞቅታ ኤርትራ ውስጥ ለሚኖሩ ቅይጥ ኤርትራውያን ዱባ እዳ ወ

ከዚህ በኋላ ወደ ኤርትራ ሊመለስ አለመቻሉ ን፣ ከአባቱ፣ ከወንድሞቹ እና ለዓመታት አብረው ት በትግል ያሳለፉትን ጓደኞቹን ባልጠበቀው መ ልኩ ሊለይ መሆኑን ሲረዳ አዘነ። ……ከሐሳቡ የ ባነነው የላንድ ክሩዘሯ ሹፌር የጉዟቸው መጨር ሻ መሆኑን እየተናገረ የመኪናውን ሞተር ሲያጠ ፋ ነበር። በነጻነት ትግል ወቅት ወደሚያውቃት ካርቱም ደረሰ።

ጉዞ ወደ “እናት” ሀገር ካርቱም ለሰዒድ አዲስ አይደለችም። ከያዘው በቂ ገንዘብ አንጻር ደግሞ የማደርያና ምግብ ጉዳ ይ ከችግር የሚገባ አልነበረም። የእርሱ ራስ ም ታት ካርቱምን እንደሁለተኛ ከተማቸው የሚ መላልሱባት የአስመራ ደኅንነቶች ናችው። በኢ ትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሰንዓፌ ላይ ውለታ የዋለላ ቸው ወዳጆቹ ወደ ኢትዮጵያ አሻግረው ከእናቱ ሊያገናኙት ቃል ገብተው ሱዳን ቀጠሮ ቢያስይ ዙትም አዲስ አበባ አድርሰው ምን ያደርጉኝ? ይ ሆን ብሎ ተሳቋል። ቢሆንም ዱካቸው ከማይታ የው የኢሳያስ ደኅንነቶች ለመትረፍ ሲል እና አ ስቀድሞ አምኖበት ከወያኔ ሰንሰልት ውስጥ ከ መግባት ውጭ አማራጭ አላገኘም። ብዙም ቀ ናት ካርቱም ሳይቆይ የወያኔ ሰዎች ባዘጋጁለት ስ ም እና ፓስፖርት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲ ስ አበባ ገባ።

ዲማ፣ ቢፍቱ፣ አሊቴና፣ ሚዛን…መስራት ጀመረ። በዚህ ወቅት መረጋጋት ጀምሮ ህይወትን እንደአ ዲስ እየጀመረ ነው። ቡና ቤት ከተወዳጃት አንዲ ት ሴት ወንድ ልጅ አገኘ። ነገር ግን የልጁን ፍቅር በቅጡ ሳያጣጥም ባላሰ በውና ባልጠበቀው ሁኔታ ጅማን ለቀቀ። ወደ እ ስር ቤት ተወረወረ። በታጠቅ እስር ቤት ለአንድ ዓመት ሲታሰር አንድም ሰው የታሰረበትን ምክን ያት የነገረው አልነበረም። ድብደባ እና እንግልት ም አልደረሰበትም። ለአንድ ዓመት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ እስሩ ላይ “ብይን” ተሰጠው። ኢት ዮጵያ ከምትባል ሀገር እንዲወጣ መወሰኑ ተነገረ ው። ውሳኔው ለእርሱ የመለቀቅ ሳይሆን ከድጡ ወደ ማጡ ነበር። አባቱን ትቶ እናቱን ፍለጋ፣ እ ናቱን የማጣቱን ጠባሳ በልጁ ሊሽር ሲጥር ያንን ም እንዲያጣ መሆኑ ጽልመት ውስጥ ከተተው። “በታጠቅ በሁለት ወታደሮች ታጅቤ በሕዝብ ማ መላለሻ አውቶብስ ወደ ሞያሌ ሄድኩ። ረጅሙን ጉዞ እጄ ታስሮ መወሰዴ ግዴታ ቢሆንም ወታደ ሮቹ ጥሩ ሰዎች ስለነበሩ ከካቴና ነጻ አድርገው ሞ ያሌ አደረሱኝ።”

“ካሪቡ” የኢትዮጵያ ሞያሌን ድንበር እንደተሻገረ የኬንያ ሞያሌ ተረከበችው። በባዕድ ሀገር ራሱን ማግኘ ቱ እንግዳ ነገር ባይሆንበትም የመግባቢያ ቋንቋ

ፎቶ- አይነው ኃይለስላሴ ለፎርቹን

ካሳሁን ይልማ አዲስ ነገር ኦንላይን

5

የናይሮቢ የንግድ እምብርት የሆነችው ኢስሊ በርካታ ሀበሻ ስደተኞች ከሶማሊያውያን ጋር ተጎራብተው የሚኖሩባት እና የሚሰሩባት ነች

ረደባችው። ከኢትዮጵያ ተገፍተው የመጡ አም ቼዎች “ልጆቻችን” የሚል አቀባበል ሲደረግላቸ ው ኤርትራ የነበሩት ቅይጥ ዜጎች ግን የበቀል በ ትር እንዲያርፍባቸው ተደረገ። ጎረቤት፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ እነርሱን አሳልፎ መሰጠቱ እንደሀገር ባለው ለተኛ ነጥብ ተቆጠረላቸው። የእርምጃዎቹ አወሳሰድ የእውር ድንበር ስለሆነ ቅይጥ ዜጋ ዋስትና አጣ። የዜግነት ፓስፖርት የነ በራቸው ድብልቅ ኤርትራውያን በአፋጣኝ መብ ታቸው ተገፍፎ ቢጫ መታወቂያ ታደላቸው። “የ ሁለቱ መንግስታት ጭካኔ የተሞላ እርምጃ እንደ እኔ ኢትዮጵያዊ ደም ያለውን ወገን አስደነገጠ”ይ ላል ሰዒድ። ኢትዮጵያ የነበሩት አምቼዎች ንብ ረታቸው ተቀምቶ እጅ እና እግራቸውን ይዘው እንዲመጡ መደረጉ አስመራ ላይ ምላሹን እሳት ን በእሳት አደረገው። “እኔም ኢትዮጵያ ስላለች ው እናቴ ናፍቆት በተደጋጋሚ እናገር ስለነበር ስ ጋት ገባኝ። ሳልቀደም ልቅደም ብዬ ከሠራዊቱ ገ ንዘብ የተወሰነ ወስጄ (ዘርፌ ላለማለት) ከኤርት ራ ኮበለልኩ።”

አዲስ አበባ ሲደርስ ከሱዳን ይዘውት የመጡት ስዎች ለሌሎች አስረክበውት ሄዱ። ለጥቂት ቀና ት በቅጡ በማያስታውሰው አንድ ግቢ ውስጥ ቆ የ። ከዚያም እናቱ ይኖሩበታል ወደ ተባለው የ አፋር ክልል ከተማ ተጉዞ ፍለጋ ጀመረ። “እርሷ ን የሚያውቋት የቀድሞ ጎረቤቶቿ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ አባቷ አገር ወሎ ሄዳ መሞቷን አረዱ ኝ።” ሕይወቴ እንደገና ጨለመ። ግራ ገባኝ። እህ ትና ወንድሞቼን ወይም ሌላ ዘመዶቼን እንዳልፈ ልግ አድራሻቸውን የሚያውቅ አልተገኘም። “ ይ ላል ሰዒድ። “በኅዘን እንደተዋጥኩ ከሕዝብ ጋ ር ተቀላቅዬ እንድኖር ወደተፈቀደልኝ ጅማ ተላ ኩ። ከውትድርና ሙያ ውጪ ያለው ዕውቀት መ ኪና ማሽከርከር ነበር። “ሰራ አልነበረኝም። ተስ ፋዬ በአጠቃላይ የጨለመ ስለነበር ሌት እና ቀን አልኮል መጋት ልማዴ ሆነ። ቡና ቤት ማንጋት እ ና ከሁሉ ጋራ መጋጨትን የዕለት ከዕለት ክንውኔ አደረግኳቸው። “ የመጠጥ ቤቴ ሴቶች ወዳጆቹ ኾኑ። ገንዘቡ እየ መነመነ ሲመጣ የአይሱዙ ሾፌር ሆኖ ተቀጠረ።

ማጣቱ ዱዳ አደረገው። ዐረብኛ ሱዳን ላይ እንደ ረዳው በችግሩ ሰዐት የሚደርስለት ቋንቋ አጣ።ከ መግባቢያ ቋንቋ በላይ ገንዘብ (ሽልንግ) ተናጋሪ በሆነበት ምድረ ኬንያ ሰዒድ አንደበት አጣ። የኬ ንያ ፖሊሶችም በተለመደ አቀባበላቸው “ካሪቡ” (እንኳን ደህና መጣህ) አሉት። ወደ ናይሮቢ ለ መግባት በፖሊሶች የተጠየቀውን 6 ሺህ ሽልንግ የመክፈል አቅም አልነበረውም። ሁለተኛው አማ ራጭ እስር ነበርና ወደዚያው ተወረወረ። ተገቢ የእስረኛ አያያዝ በሌለበት የስምንት ወራት ስቃይ አሳልፈ። በመጨረሻም ወደመጣበት ሀገር እንዲ መለስ (Deport) ተፈረደበት። ነገር ግን በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር እገዛ ወደ ኢትዮጵ ያ መመለስ የማይችልባቸው ምክንያቶች አሳማኝ ሆነው ወደ ናይሮቢ እንዲሄድ ተደረገ። በዋና ከ ተማዋ በሚገኘው ሚሊማኒ እስር ቤት ዲፖርት (Deport) የሚለው ወረቀት እስኪሰረዝ ለተጨ ማሪ ሶስት ወራት በእስር ቆየ። ከዚያም በተባበሩ ት መንግስታት የስደተኛ ጉዳይ ሁኔታውን ተቀብ ሎ ከስደተኛ ጎራ ቀላቀለው።

“ቻይ መንገድ “

ናይሮቢ ከተማ እንድስፋቷ መጠን ስደተኞችን በእቅፏ መያዝ የረጅም ጊዜ ልማዷ ነውና ለሰዒ ድ ቦታ አላጣችለትም። እርሱም ካሉት አማራጮ ች ውስጥ ወደአሻው መሄድ ይችል ነበር። ካኩማ ወደሚባለው የስደተኞች መጠለያ ገብቶ በተባበ ሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን መረዳትን መምራጥ ይችላል። ካልኾነም ቻይ ሮ ድ ወደተሰኘው የኤርትራውያን ሰፈር ከእርሱ ቢ ጤ የናይሮቢ ስደተኞች ጋር መቀላቀል ወይም በ ርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት የናይሮቢ የ ንግድ እምብርት ኢስሊ ሀበሻው ስደተኛ እንደ ሚሆነው ለመሆን መወሰን የእርሱ ፋንታ ነበር። ስለካኩማ ወይም ዳዳብ (ብዙኀኑ ሶማሌያዊ ስ ድተኛ ቢሆንም) ከሰዎች የሰማው ነገር ብዙም አላስደሰተውም። ከዋና ከተማ ያላቸው ርቀት አና የኑሮ ሁኔታ ከባድነት የመሄድ ድፍረት አሳ ጡት። ኤርትራውያን በብዛት የሚኖሩበት የናይ ሮቢ ክፍል እንዳለ ሲሰማ የሚረዳኝ አላጣም ብ ሎ ቻይ ሮድ በተባለው የናይሮቢ አካባቢ ለመ ኖር ወሰነ። ቻይ ሮድ በጣም ብዙ የኤርትራ ስደተኞች ተጠ ጋግተው ስደትን የሚገፉበት አካባቢ ነው። ነገር ግን በኤርትራ ኤምባሲ የሚተዳደረው ኤርትራ ሆቴል ለእርሱ አስጊ ኾኖ አገኘው። “ለእንደኔ ዐ ይነቱ በአገር ሻጭነት ለተፈረጀ አሰቃቂ ነው። “አ ለባበሴን በመለወጥና እንቅስቃሴዬን በመቆጠብ ራሴን ደብቄ መኖር ጀመርኩ። ሆኖም ግን ለልመ ና አስፋልት ዳር መቀመጥ በማይቻልበት ቦታ ያ ለረዳት የዕለት ከዕለት ኑሮን መወጣት የማይታሰ ብ ነበር። ጥቂት ቀናት ሳይቆጠሩ ረኅብ ሲያገኘኝ እስር ቤቱ ናፈቀኝ። በዚያ መጠለያ እና የምትፈ ልገውም ባይሆን ለጊዜው የሚያኖር ምግብ ይቅ ርብልሀል።” ሲል ይገልጻል። ኑሮው ከድጡ ወደ ማጡ የሚሉት አይነት እየኾነ ነው። ጅማ መቀማመስ የጀመረውን ጫት ለችግሩ መ ደበቂያነት መረጠው። ቀን ጫት በሚቃምባቸው የቻይሮድ ስፍራዎች እየተዟዟረ ገረባም ቢሆን እ የቃረመ ማታ እንቅልፍ በመጣበት እና ድካም በ ጣለው ቦታ መተኛትን ለመደ። ጎዳናዎች የእርሱ የመኝታ ክፍሎች ሆኑ። ሲጋራ ብርድልብሱ። ጫ ት ከረፋድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ከአ ፉ አይወጣም። በየቀኑ መመርቀኑና ምርቃናው የ ሚያመጣው የሕይወት ክለሳ ከጭንቀት ወደ ድ ብርት አሸጋገሩት። ለችግር እጅ የማይሰጠው ሰዒድ ከእድሜ መግ ፋቱ ጋራ የጎዳና ተዳዳሪነት ሕይወት ተሰባሪ አደ ረገው። ለአምስት ዓመታት በጎዳና ላይ ማሳለፉ በአዕምሮው ጤናው ላይ ችግር አደረሰበት። ቤተ ሰብ በተለይም የልጁ ናፍቆት ተስፋ እንዲቆርጥ፣ ትናንትን እንዲረግም፣ ዛሬን እንዲጠላ እና ነገን እ ንዳያልም ተጫኑት። በሳንባ በሽታ ተያዘ። ከሞተ በላይ እና ከነዋሪ በታች አደረጎ አስቀመጠው። በጎዳና ሕይወት ቀ ርቶ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ለመፈወስ አድካ ሚ ጊዜያትን የሚያስቆጥረው የሳንባ ነቀርሳ ፋታ ነሳው። ፈጽሞ ተዳከመ። በዚህ ሁሉ መሀል የተ ባባሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት የእርዳ ታ እጁን ዘረጋለት። “ቤት ተከራዩልኝ፣ ምግብም በየወሩ እየሄድኩ በራሽን እቀበላለሁ።” ዛሬ ሰዒድ እድሜው ወደ ኅምሳዎቹ ቢገባም ሕ ይወት ያዘጋጀችለት የማታ ማታ ስጦታ እንዳለ ያስባል። ነገን ማለም ጀምሯል-በተስፋ። አንድ ቀ ን ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ ልጁን በአይነ ስጋ እን ደሚያየው ያልማል፤ ወደ ጅማ- ኩሎ በር ተጉዞ። ምናልባት አንድ ቀን።

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ በ+256-778-693669 ይደውሉልን


ሐበሻዊ ቃና

6

ተምሳሌት

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ሌላ ዳንስ አለብኝ

ስደተኝነት መቼም ቢኾን ሙሉ ደስታን አያጎናጽፍም። አልፎ አልፎ የሚሰሙት ጉዳዮች ደግሞ መረር ይሉና በሰሚው ላይ የሐዘን ድባብ ይፈጥራሉ። ናይሮቢ የሚገኘው የአዲስ ነገር ባልደረባ ጄሪ ከምትባል ኢትዮጰያዊ ጋር ተገናኝቶ የሚከተለውን ሰምቷል።

ሐይ ካዘቀዘቀች በኋላ በከተማ ዋ በሚመዘገበው የወንጀል ሪከ ርድ ምከንያት በምሽት ለመንቀ ሳቀስ ብዙም በማይመከርባት <ናይሮቢ> ለሊቱን እንደደመቀ የሚያነጋ ቦታ ይገኛል። የሀገሬው ሰዎች ቦታው ን <ዌስትላንድ> ብለው ይጠሩታል። የዘወትር የ ቦታው ታዳሚዎች በበኩላቸው <ኤሌክትሪክ ታ ውን> ሲሉ ስም አውጥተውለታል። <ጂፕሲ>፣ <ሀቫና> ፣ <ኬ 50>፣ <ሬዞሮስ>፣ <ሬድ ቴፕ> እና <ብላክ ዳይመንድ>ን የመሳሰሉ የምሽት ክለቦች ስማቸው የገነኑ ዲጄዎችን ይዘው፤ የዳንስ ወለላ ቸውን ለዳንኪራ አዘጋጅተው፤ ደንበኞቻቸውን ከሰኞ እስከ ሰኞ ይጠብቃሉ። አዘውትረው ወደ <ዌስትላንድ> ጎራ በሚሉ ደን በኞች መካከል ያልተጻፈ ግን በየጊዜው የሚተገ በር <ደንብ> ያለ ይመስላል። <ደንቡ> ተግባር ላ ይ የሚውለው ምሽቱን አብረዋቸው የሚያሳልፉ እንስቶችን ለመምረጥ አይናቸው ዙሪያውን መቃ ኘት ሲጀምር ነው። በ<ደንቡ> መሰረት መጀመሪ ያ የ<ሐበሻ ሴቶች> በአካባቢው መኖር አለመኖ ራቸው ይረጋገጣል። እነርሱ ከሌሉ አሊያም በሌ ላ ደንበኛ እቅፍ ውስጥ ከሆኑ ወደ ሁለተኛ ምር ጫ ይኬዳል። በሁለተኛ ረድፍ የሚቀመጡት የ ሱማሊያ ጉብሎች ናቸው። ኬንያውያን እና የጎረ ቤት ሀገር እንስቶች በምርጫው በሶስተኛነት ተ ርታ ላይ ይቀመጣሉ። በዚህ የምርጫ ደንብ የቆረቡ የሚመስሉቱ ከ<ሬድ ቴፕ> እና ከ<ብላክ ዳይመንድ> አይጠፉ ም። በእርግጥም በእነዚህ የምሽት ክለቦች የሐበ ሻ እንስቶች አይጠፉም። ሶማሊያውያን ኮረዳዎ ችም በብዛት አሉ። ሐበሾቹን ቀረብ ብሎ በቋንቋ ቸው ላነጋገረ አጥብቆ ጠያቂ ልብወለድ የመሰለ ታሪካቸውን የማድመጥ እድል ያገኛል። ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን የናይሮቢ የምሽት ክለብ አድማቂ ዎች ያደረጋቸውን የሃላ ታሪክ ያጋራሉ። ጄሪ ከ እነዚህ ሐበሻ ሴቶች መካከል አንዷ ናት። <ስለ እውነተኛ መጠሪያዬ ለማወቅ በጥያቄ አትባዝን> ትላለች ትረካዋን ስትጀምር። × × × ስለእውነተኛ መጠሪያዬ ለማወቅ በጥያቄ አትባ ዝን። ስሜን እንደሻኝ ስለዋውጠው የውስጥ ል ብሴን የመቀየር ያህል አይከብደኝም፡፡ እውነቱ ን ልንገርህ፣ መጠሪያዬን አብሪያቸው ከወጣኋቸ ው ወንዶች ቁጥር ጋር አወዳድረህ ብታሰላው እ ንኳን በእርግጠኝነት በአሥር እጅ ልቆ ታገኘዋለ ህ፡፡ ደግነቱ የወንዶቹን ቁጥር መገመት አይቻለ ኝም፡፡ ከስሜት አልባ ገላዬ ሲላቀቁ ከትውስታ ዬ ማህደር ይፋቃሉ፡፡ የሚተርፈኝ ውጤት አል ባ ፍትጊያቸው የሚፈጥረው ድካም ብቻ ነው፡፡ የምተርክልህን አምነህ መቀበል ከቻልክ ስሜን ከማወቅ በላይ የሚነግሩህ አንዳች ነገር አላቸው፡ ፡ የስደተኝነት ቁዘማ ከሚበላቸው ቀናቶቼ ጥቂ ቱን ቆንጥሬ ብሰጥህ የማተርፈው ባይኖርም የ ማጣው ነገር ያለ አልመሰለኝም . . . ለወግስ ብ ተርፍ ምና’ለ! የነገን እርግጠኛ ባልኾንም፣ ዛሬ ግን እዚህ ነኝ። ናይሮቢ - ኬንያ፡፡ የ27 ዓመታት ዕድሜ ባለጸጋ፤ ያለ ሥራ በእንጥፍጣፊ ተስፋ ቀናቶቼን የምቆጥ ር፡፡ እድሜዬ ላንተ እንዲህ ብዬ ልንገርህ እንጂ በቅርብ በሚያውቁኝ የስደት ጓዶቼ መካከል ግ ን ከ22 ከፍ አያልፍም፡፡ እድሜዬን ቀንሼ መና ገር ልምድ ቢሆንብኝም ደካማ የማስታወስ ብ ቃቴ ግን በተደጋጋሚ ከሰው ፊት አሳጥቶኛል፡፡ ደጋግሜ ማስታወስ ባልፈልግም ለምን እና እን ዴት ከዚህ የቁም እሥረኝነት ካደረገኝ ሥፍራ እ ንደተገኘሁ ባሰብኩ ቁጥር ሲቃ ይተናነቀኛል፡፡ ይኼኔ በልብህ “የመሰደድ ፍቅር ነው፤ ሌላ ምን

አለ?” እያልክ ይኾናል፡፡ እንዲያ ብታስብ ቸግር የለውም፡፡ አንተ ውስጥ ያለው ፍላጎት እኔም ዘ ንድ አለ፡፡ እንደማንኛውም የአገሬ ልጆች አሜሪ ካ በመሄድ ፍላጎት የተሞላሁ ብኾንም ያ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ ባይ ግን አልነበርኩም። ቢኾን ቢ ኾን በዲቪ አልያም ደግሞ በትምህርት ምክንያት ወደ “ተስፋይቱ ምድር” መሄድ እመኝ ነበር፡፡ ይ ህንን ፍላጎቴን ይደግፍ የነበረው አባቴም ትምህ ርቴን አጥብቄ እንድይዝ ይመክረኝ ነበር። እኔም ለትምህርቴ የምሰጠው ትኩረት ላቅ ያለ ነበር፡፡ የተዋጣላት ተማሪ አልነበርኩም። አማካይ ስፍራ ን ለማግኘት ግን አልሰንፍም። ስድስት ኪሎ የሚገኘው የካቲት 12 ሁለተኛ ደ ረጃ ትምርት ቤት (መነን) እማር በነበረበት ጊዜ ትግሌ ከትምህርት ጋር ብቻ አልነበረም፡፡ የእኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሲያዩ ወንድነታቸው የሚታወሳቸው የሚመስሉት የስድስት ኪሎ ዩኒ ቨርሲቲ ተማሪዎች ያስቸግሩን ነበር። “ሹገር ዳዲ ዎች”ም ከሚያማልል ስጦታቸው ጋር በአካባቢ ያችን አይጠፉም ነበር። ይህንን የወንዶች ሁኔታ ከጓደኞቼ ጋር ሙድ እ ንይዝበት ነበር። አራት ነበርን። ተረቡ፣ ቀልዱ፣ “ሙድ መያዙ” ይመቸን ስለነበር ከትምህርት ቤ ት በኋላ ረጅም ጊዜ አብረን እንቆይ ነበር። ለታ ክሲ የተቀበልነውን ለማስቲካ እና ብስኩት ሰው ተን የጎረምሳውን ዓይን እየተመገብን እናዘግማለ ን፡፡ ከማይረሳኝ ነገር ከሚገባው በላይ ድምጽ አ ውጥቶ የመሳቅ ልምዳችን ነው፡፡ እንዲያ ባንስቅ ም እንኳን ከሩቅ የሚስብ ውበት፣ ያም ባይኾን ደግሞ የሚያጓጓ የልጅነት መልክ ነበረን፡፡ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ ያለውን ጎዳና እንደተለመደው እየሳቅን እና እየተጫወትን ተያ ይዘነዋል። በጉዞዬ ላይ እያለሁ ሹክሹክታ በሚ መስል ሁኔታ ስሜ ሲጠራ ሰማሁ፡፡ አራታችንም ተመሳሳይ መጠሪያ ያለን ይመስል ድምጹን ተከ ትለን ዞርን። “መለከፉን” የለመድኩት ቢኾንም በስሜ በመጠራቴ ግን ደንገጥ እንድል አድርጎኛ ል፡፡ የማውቀው ሰው አልነበረም፡፡ ቀውላላ የሚ ሉት ዓይነት ጎንባሳ ብጤ ነበር -ጎረምሳው፡፡ በእ ጁ የጥሪ ምልክት አሳየኝ፡፡ አልቸኮልኩም፤ ለጥያ ቄው ምላሽ ሳልሰጥ ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ልቤ ግ ን በጥያቄ ተሞልቶ ነበር፡፡ ስሜን እንዴት አወቀ ው? በድጋሚ ቢጠራኝ ተመኘሁ . . . እሱ ግን አ ላደረገውም፡፡ ለነገሩ ድጋሚም ቢጠራኝ የቡድና ችንን እሺታ ሳላገኝ አንዲት ውሳኔ በራሴ መወሰ ን አልችልም ነበር፡፡ ኋላ ላይ ያለው ትረባና ማሽ ሟጠጥ እንዲህ ቀላል አይምሰልህ፡፡ ያን ቀን እንዲህ አለፈ፡፡ ልቤ ግን አላረፈም፡፡ ሁለት ሣምንታትም እንደቀላል ነገር ተሸኙ፡፡ ከቀናቶቼ በአንዱ በተለመደው ስፍራ ተገናኘን፡ ፡ በፈጣጣው ሦስቱን ጓደኞቼን ሰላምታ ከሰጠ በኋላ እጄን ጎትቶ ወደ ኋላ አስቀረኝ፡፡ አላንገራ ገርኩም፡፡ ድከም ቢለው ነው እንጂ እኔ እንደው ሮጬ አላመልጥ። ከዛ በኋላ ያው የተለመደውን ወንዶች ለሴቶች የሚያዘንቧቸውን ቃላት አነበነ በልኝ፡፡ ለዓመት ያህል በዓይን ፍቅር ሲጋይ እን ደነበረ ተረከለኝ፡፡ ከፈጣሪው በታች ሊያመልከ ው የሚችል ነገር ካለ እኔ ብቻ እንደምኾን ነገረ ኝ፡፡ በጣም ብዙ ቃላት . . . ። ከጌታቸው ጋር የተገናኘነው በእንዲህ ያለ መ ልኩ ነበር፡፡ ያው ተፋቃሪዎች የሚኾኑትን ኾነ ናል፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል፡፡ ጄሪ እና ጌታቸው መኾናችን ልዩ ካላደረገን በስተቀር ሌሎች እንደ ሚሉት እኛም በፍቅር ከንፈናል፡፡ ሰመመን ይ መስል ነበር፡፡ ከሰመመኑ የባነንኩት ማትሪክ ተፈትኜ ሌላው ን አለም ሳይ ነበር። ለካስ ለዓመታት በትምህርት ሰበብ ታስሬ ነበር። ለካንስ በጌች (አሁን አሁን እ

ከቤተዘመድ ሰባስቤ የቋጣጠርኳትን ይዤ ከናይሮቢ ደረስኩ... ሁለት ወራት ከአመታት በላይ ረዘሙብኝ። ሥራ የለ፣ እንደ ልብ መግባት መውጣት የለ፤ ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋል ብቻ። አልፎ አልፎ ለሸመታ ካልኾነ በስተቀር ውጭውን አናየውም።

ንኳን ላቆላምጠው ሙሉ ስሙን ለመጥራት ይቀ ፈኛል) “ምትኃት” ተጋርጄ ነበር። ውጪው እን ዴት ያምራል። እየተኳኳልኩ የቦሌ ጎዳናዎችን፣ የፒያሳ ኬክ ቤቶችን እና ሲኒማ ቤቶችን ማሰስ ስ ጀምር አንድ ነገር ተገለጠልኝ። ለካንስ ገና ብዙ የ ሚያማምሩ ቃላት፣ ስጦታዎች . . . ይቀሩኛል። አ ይኔን ገለጥኩ፤ የጌች ቃላት ይለዝዙብኝ ጀመር። እንደ ድሮው አልጥምሽ አሉኝ። እውነት ነው ጌች የተቻለውን አድርጓል። አቅ ሙ ብዙ የሚያወላዳ ነው ባይባልም እኔን ለማ ስደሰት የተቻለውን የጣረ ይመስለኛል። ዛሬ ላ ይ ኾኜ ሳስበው ያደርገው የነበረው ሁሉ እውነ ት ከነበረ በጣም ይገርመኛል። ዛሬ እርሱ በጣ ም ሌላ ሰው ነዋ! ከማውቀው ማንነቱ በብዙ የ ሚርቅ። ወደ ጉዳዬ ልመለስ። እናም “የተራብኳቸውን” ቃላት ከተለያዩ ወንዶች አፍ መለቃቀም ጀመር ኩ። የሚጠገቡ አልነበሩም። ሁሉም የየራሳቸው ጣዕም አላቸው። እንደማገኛቸው ባለጉዳዮች ዓ ይነት የሚጎርፉልኝ ቃላት እንዲሁ የበዙ ናቸው። በሒሳባዊ አገላለጽ የእርካታዬ መጠን ከማገኛቸ ው ወንዶች ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አልው። የወን ዶቹ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የእርካታዬ መጠንም እንዲሁ ከፍ ያለ ይመስለኝ ነበር። በሂደት ግን አንድ ነገር አወቅሁ። ይህ ሁሉ ቃ ላት የሚዘንብላት የከተማዋ ሴት እኔ ብቻ አንዳ ልነበርኩ። ጎረምሳው ለፍቅረኛው፣ ጎልማሳው ለ ሚስቱ የሚተርኩትን ነው ለካ ለእኔ መጥተው የ ሚያነበነቡልኝ። ሁሉም ተዋናይ መኾኑን በሚገ ባ መረዳት ጀመርኩ። እኔስ ማነኝ ብዬ ግን ራሴ ን ለአንድ ቀን ለመውቀስ ተዘጋጅቼ አላውቅም። ይልቁንም እኔም “አሪፍ” ተዋናይት መኾን ጀመ ርኩ። ግን እንደቀድሞው የሚጥም አልኾነም። አልፎ አልፎ አበደኩ፣ ከነፍኩ የሚለውን ጌታ ቸውን አስታውሰዋለሁ። የቅርብ ጓደኞች የኾኑ ም በአማላጅነት ተመላልሰዋል። ሰሚ ሲያገኝ አ ይደል? ይልቁንም ለአማላጅ ከመጣው የቅርብ ወዳጁ ጋር “የማይኾን” ሥፍራ አግኝቶናል። በ ደል ከተባለ ይህን መሰል በደል ከህሊና ማኀደ ሩ ከትቧል።

የወጥመድ “ጎጆ” ዓመታት ጨምረዋል። በሁሉም ትወና ባይዋጣ ልኝም የተሻልኩ ተዋናይት መኾኔ አልቀረም። ከ ጌታቸው ይመጣ የነበረ የአማላጅ ግርግር እና ወ ከባም ጋብ ብሏል። ሜዳው ሠፊ ነበር። ዕድሜ ዬ ይኹን ተፈጥሮዬ ባላውቅም ለፈንጠዝያ የም ጣደፈውን ያህል ለሌላ ጉዳይ ሲኾን ቀዝቃዛ ነበ ርኩ። ለሁለት አመታት ያህል ከጌች ጋር መተያየ ትም አለመቻሌ ቢያንስ ቢያንስ ከስጋት እና ከሰ ቀቀን አትርፎኛል። እንደሰማሁት ከኾነ ወደ ውጭ አገር ተጉዟል። ከእርሱ አንደበት እስክሰማው ድረስ ግን የት እን ደሚገኝ አላውቅም ነበር። ለአይን መተያየት እን ኳን ከተጠፋፋን ሦስት አመታት በኋላ ይመስለ ኛል አንድ ቀን ምሽት የእጅ ሞባይሌ አንጫረረ። የሚገርም ነው መርሳት “ያልኾነለት” ጌች ነበር። አላመንኩም።ብዙ አወራኝ . . . አሁንም ፍቅሩ እ ንዳለቀነሰለት ተረከልኝ። ከሁሉ ትረካዎቹ ግን ናይሮቢ እንደሚኖር ፣ በቀ ጣዮቹ ሁለት ወራት ወደ ካናዳ እንደሚበር እና እኔንም በሚስትነት ሊወስደኝ የሚችልበት አጋ ጣሚ እንዳለው የተናገረው ልቤ ውስጥ ቀረ። በ ሁለት ወራት ውስጥ ካናዳ?! ይሄ ሊታመን የሚ ችል ጉዳይ አይደለም። ከዚያማ በኋላ ከሱ በላይ ደዋይ እኔው ኾኜ ቀረኹ። እሱ አገረሸብኝ ያለው ን ፍቅሩን ያወራል እኔ ደግሞ ስለ `ፕሮሰሱ` ደጋ ግሜ እጠይቃለኹ። አይ ፈንጠዝያ መውደዴ! ጌች ላይ የፈጸምኩ

ትን ኹሉ ረስቼ ስለ ካናዳው ጉዞዬ ብቻ ማሰብ ተረፈኝ። በርግጥ በጋብቻ ተሳስሬ እኖራለሁ የ ሚል እምነት ልቤ ውስጥ አላሰፈርኩም። የወደ ፊቱን “የላይኛው” ያውቃል በሚል የጉዞዬን ጉ ዳይ ብቻ አጣደፍኩት። በእውነት ሲበዛ ችኩ ል ነበርኩ። ጎረቤት እልል ብሎ ሸኘኝ። “በድል ተመለሽ . ..” ከቤተዘመድ ሰባስቤ የቋጣጠርኳትን ይዤ ከና ይሮቢ ደረስኩ። ጌች በፈገግታ ተቀበለኝ። አንዲ ት የተሟላች ባለአንድ ክፍል መኝታ ተከራይቷ ል። ለሁለት ወር ቆይታ ብቻ! ከበቂ በላይ ነች አልኩ። መኖር ስንጀምር ሁለት ወራት ከአመታ ት በላይ ረዘሙብኝ። ሥራ የለ፣ እንደ ልብ መ ግባት መውጣት የለ፤ ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋ ል ብቻ። አልፎ አልፎ ለሸመታ ካልኾነ በስተቀር ውጭውን አናየውም። እርሱ `ፕሮሰሱን` ለማስ ጨረስ በሚል ሰበብ ወጣ ገባ ማለቱ አልቀረም። ቀናቱ እየረዘሙ ሲመጡ መነጫነጭ ጀመርኩ። ሁለት ወራት የተባለው ጉዳይ ሦስት . . . አራት . . . አምስት እያለ መቁጠሩን ተያያዘው። ስጠይ ቀው በእኔ ምክንያት እንደተራዘመበት ይነግረኛ ል። ተጨማሪ ምክንያት የለም። አገር ቤት ያሉ ዘመዶች ደግሞ ጭቅጨቃቸው የሚያባራ አይደ ለም። ሆድ ያስብሳል። ስለቤተሰብ ማሰቡ በራሱ ሌላ ራስ ምታት ኾነብኝ። ለጌች ግን የሚደንቀው ነገር አልነበርም። “ከአስ ር አመት በላይ እዚህ የተቀመጡም አሉ፤ ምን ያ ስቸኩላል” ይለኛል። ይህ አባባሉ ንዴቴን ይጨ ምረዋል። በልመና የሚመጣውን ዶላር መጠበቅ ም ሰቀቀን ነው። “ወንድም” ጌታቸው ግን ሥራውን እየሰራልኝ ነ በር። በርግጠኝነት ባላስታወሰውም የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይመስለኛል። እን ዲህ የሚል የስልክ ጥሪ ተቀበልኩ። “አዝናለሁ ብድር በምድር ይሏል እንዲህ ነው።” ጌታቸው በዚያ የስልክ ጥሪው ወደ ካናዳ ለመብረር ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ እንደሚገኝ አረዳኝ። በወቅቱ ስሰማው “አፕሪል ዘ ፉል” ዓይነት ምና ምን ነበር የሚመስለው። ጌች ግን ከምር ሥራው ን ሠርቷል። ማንም ሊያስበው ከሚችለው በላ ይ ተበቅሎኛል። የብቀላው ብትር ከእኔ ተሻግሮ ብዙ ተስፋ ሲ ያደርጉ የነበሩ ቤተሰቦቼን ይበልጥ ተሰምቷቸዋ ል። በወቅቱ በቅርቤ አይዞሽ የሚል ሰው አልነበ ረም። ለአንዲት ሴት ልጅ ይህ ምን ማለት እንደ ኾነ አስበው። ከሁሉ የሚከፋው ግን ወደ አገሬ ለመመለስ የሚኾን ወኔ ማጣቴ ነው። ባዶ እጅህ ን?! ለዚያውም ከጎረቤት አገር። ቆየት ሥል ግን የሴት ልጅ ብልኀት ፈጠርኩ። የ ከተማውን ዳንስ ቤቶች ማሰስ ጀመርኩ። ከዚያ ሥፍራ ሥጋ ከሸጥክ ገንዘብ ታገኛለህ። በእርግጥ የሚዘገንን ኃሳብ ይመስላል-በወቅቱ። በይፋ ባ ይኾንም አገር ቤትም እንዲሁ ነበርኩ ብዬ ራሴን ለማጽናናት ሞከርኩ። ችግሩ ግን እራስህን እንደ ሴተኛ አዳሪ ለመሸጥ አለመቻልህ ልብህ ውልቅ እስኪል እንድትደንስ ያስገድድሃል። አሁን አሁን ተስፋ ማድረግ ጀምሬያለሁ። ጥቂ ት ዶላሮችም መቋጠር ስጀምር ወደ ደቡብ አፍ ሪካ የመጓዝ ፍላጎት አድሮብኛል። “ጨደዳ” ይባ ላል። አራት ሺህ ዶላር ከፍለህ ወደማታውቀው አገር ደግሞ ሌላ የስደተኝነት ጭምብል መልበስ ነው። ጉዞው ግን በአደጋ የተሞላ እንደኾነ ብዙ ታሪክ ሰምቻለሁ። አሁን ካለሁበት ግን የሚብስ አይመስለኝም፤ እሞክረዋለሁ። በአማርኛ ማውራት ብዙ ናፍቆኝ ነበር ልበል? ብዙ የለፈለፈኩ መሰለኝ። እሰኪ ልዘገጃጅ . . . ሌ ላ ዳንስ አለብኝ።


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

7

ተምሳሌት

ትጋት የማያልቅበት ያለፉትን 35 ዓመታት በስደት ዓለም በትጋት አ ሳልፏል፡፡ ዛሬም አይደክመውም፤ ነገም ቢኾን የ ሚደክም ደግሞም ሕይወትን የሚሰለች አይመስ ልም፡፡ የእፅዋት መናኸርያ በሚመስለው የተንጣ ለለ ግቢው ወዲህ ወዲህ እየተንጎራደደ ደንበኞ ቹን ይጎበኛል፣ ታታሪ ሠራተኞቹን ይቆጣጠራል አልፎ አልፎም አረፍ እያለ ወደፊት ለመሥራት ስ ለሚፈልጋቸው ጉዳዮች ያወጣል ያወርዳል፡፡ ለእ ርሱ ስለንግድ ማሰላሰል እንዲሁም ትርፍና ኪሳ ራን መቀመር ከኑሮ መደገፊያነት ባሻገር የሕይወ ት ፍልስፍናው ነው፡፡ ሥራው የእርካታው ምን ጭ ነው፡፡ ያሰላስላል፣ ይወስናል እናም ይፈጽማ ል፡፡ ይህ አቶ ቶልቻ ማሞ ነው- የናይሮቢው የሐ በሻ ሬስቶራንት መሥራችና ባለቤት፡፡ ናይሮቢን በተለያየ ጊዜ የጎበኘ ኢትዮጰያዊም ኾ ነ የሌላ አገር ዜጋ የአቶ ቶልቻን ቤት ሳይጎበኝ ወ ደመጣበት ይመለሳል ማለት ዘበት ነው፡፡ ከአገር ‘ርቆ የሐበሻ ምግብ ለናፈቀው፣ አዲስ ነገር ማወ ቅ ለሚያጓጓቸው ጎብኚዎች እና ለኬንያውያን በ ናይሮቢ ቀዳሚው ባህላዊ ምግብ ቤት በመኾን ሁሉንም ያስተናግዳል፡፡ ዛሬ የናይሮቢው የሐበሻ ሬስቶራንት በጥራትም ኾነ በአይነቱ የመጀመሪያ ዎቹን ደረጃዎች ከያዙት ሬስቶራንት ውስጥ የሚ መደብ ነው፡፡ የ “Nairobi Star” ጋዜጣ እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም “ምርጥ 10 የኬንያ ሬስቶራንት” ከ ተባሉት መካከል “ሐበሻ ሬስቶራንትን” አንዱ ማ ድረጉ ትልቁ ምስክር ነው፡፡ የዛሬ የአቶ ቶልቻ ስኬት ግን በአንድ ጀንበር የ መጣ አይደለም፡፡ እድሜ ተከፍሎበታል፡፡ ትዕግ ስትን የፈተኑ ተደራራቢ ችግሮች ተስተናግደውበ ታል፡፡ ዛሬ ሕልም የሚመስሉ ጀብዱዎች ተከው ነዋል፡፡ ሁሉንም በብልሃት እና በፅናት አልፏቸዋ ል፡፡ እናም ዛሬ በምስራቅ አፍሪካ ተበትነው ለሚ ገኙ የኢትዮጰያ ስደተኞች የስኬት ተምሳሌት በ መኾን ስሙ ይጠራል፡፡

የኤስሊ ፋኖ

የኤስሊ “እንጀራ” ሁሌም ቢኾን ተስፋን ስንቁ አድርጎ የሚጓዘው ቶልቻ ለሽንፈት ጊዜ አልነበረውም፡፡ ፈተናዎች ግን የእለት ተእለት ገጠመኞቹ ነበሩ፡፡ በአንድ ወ ቅት የ100 ሺህ ሽልንግ እቃ ይሸጥና 15 በመቶ ድ ርሻ ለመካፈል ቢሻም ዋናው አሰሪው የተጠቀሰ ውን ያህል ገንዘብ ለቶልቻ ለመስጠት እጁ ሊፈ ታለት አልቻለም፡፡ ቶልቻ አልተለማመጠም፡፡ 15 ሺህ ሽልንግ ውሃ እንደበላው ቢረዳም ነገ አዲስ ኃሳብ ይዞ ኑሮን እንደሚጋፈጥ ተስፋ በማድረግ ወደ ቤቱ አቀና፡፡ 15 ሺህ ሽልንጉን ያጣው ቶልቻ ሁሉን ረስቶ የ70 ሽልንግ ሻሽ ገዝቶ ኤስሊ ላይ በበነጋው ይ ገኛል ብሎ የጠበቀ አልነበረም፡፡ እርሱ ግን አደ ረገው፡፡ “ሕይወት ልምምድ ነች” የሚለው ቶል ቻ፣ ከሻሽ ንግዱ ያን ያህል ትርፍ ይገኛል ብሎ ባ ያስብም “ፈጽሞ ከመውደቅ” የመረጠው ነበር፡፡ ጊዜዎች ሲጓዙ እርሱም መላ ለማምጣት አልሰ ለቸም፡፡ በ1978 የመጀመሪያውን የሐበሻ ምግብ ቤት በኤስሊ በመክፈት የኢትዮጰያን ባህላዊ ም ግቦች ማስተዋወቅ ጀመረ፡፡ 20 ኢንች ዲያሜት ር ያለው ምጣድ በመስራት በሩዝ ዱቄት እንጀ ራ በመጋገር ለሙያው ፋና ወጊ ኾኗል፡፡ የሱማ ሌያ ስደተኞች እና ኬንያውያን ከባህላዊ ምግቦች ጋር እንዲተዋወቁ ማድረጉን በኩራት ይናገራል፡ ፡ “የእንጀራ አቆራረስን ጭምር የማሳየው እኔው ነበርኩ” ይላል፡፡

100 ሺህ ዶላር በአንድ ጀንበር በአንድ ነገር መወሰን የሚቸግረው ቶልቻ፣ ከም

ፎቶ- አይነው ኃይለስላሴ

በ1970ዎቹ (እ.ኤ.አ) የኢትዮጰያ ፖለቲካ በተማ ሪዎች እንቅስቃሴ የሚናጥበት ወቅት ነበር፡፡ ተ ማሪው፣ ወታደሩ፣ ሠራተኛው እናም የተቀረው የኀብረተሰብ ክፍል ለውጥን የሚያቀነቅንበት ነበ ር፡፡ አዳጊው ቶልቻም “ለውጥ ለውጥ” ከሚሉት ጋር በመኾን ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየ ቱ አልቀረም፡፡ ይማራል፣ ይነግዳል ጎን ለጎን ደግ ሞ የለውጥ አቀንቃኞቹን መፈክር አንግቦ “ወደፊ ት በሉለት” ይላል፡፡ የኢሕአፓን ፖለቲካዊ አቋ ም ያደንቃል፡፡ ማድነቅ ብቻም አልነበረም ተሳት ፎው የጎላ ነበር፡፡ ይህ የእርሱ ፖለቲካዊ ማንነት ግን አንዱ ክፍል ነው፡፡ ጎን ለጎን ታታሪ ተማሪ እንዲሁም ነጋዴ ነ በር፡፡ ራስን በመቻል ያምናል፡፡ ከአያቱ የሥራ ት ጋትን ወስዷል፡፡ ለችግር እጅ መስጠት የማይወ ዱት አያቱ ራሰን ስለመቻል ከሐልዮት በላይ በ ተግባር አሳይተውታል፡፡ አዳጊው ቶልቻም ራስ ን መቻል የሚለውን መርህ በልቡ ሰንቆ ገና በማ ለዳው ነበር በወሊሶ ከተማ በ20 ሳንቲም 12 እን

ቁላል ገዝቶ የጎዳና ላይ ንግድን የጀመረው፡፡ ሥ ራ እንደማይንቀው ሁሉ ከመጀመሪያ ንግዱ ያገ ኛትን የ10 ሳንቲም ትርፍ እንደ ትንሽ አላያትም፡ ፡ ይበልጡንም ተነቃቃባት፡፡ ጎን ለጎን ሎተሪ አ ዙሯል፣ የጋዜጣ ወኪልም በመኾን አገልግሏል፡ ፡ ከናዝሬት ኬሻ በማምጣትም በወሊሶ ጎዳናዎ ች ላይ ሸጧል፡፡ ታታሪው ቶልቻ የንግዱን ዓለም እንዲህ ሲዘው ረው፣ አገሪቷ ደግሞ በለውጥ ማዕበል ትናጥ ነበ ር፡፡ ይህ የፖለቲካ ግለት የበለጠ ምክንያት የኾነ ው ቶልቻ እ.ኤ.አ 1976 ዓ.ም ድንበር ተሻግሮ የ ኬንያን ምድር ረገጠ፡፡ ድንገት የተገኘባት ናይሮ ቢ ግን የእድገት ጭላንጭልን እንጂ አልጋ በአልጋ የኾነ ሕይወት ይዛ አልጠበቀችውም፡፡ የሱማልያ ስደተኞች እና ኢትዮጰያን በብዛት በ ሚኖሩባት ኤስሊ ነበር ያረፈው፡፡ ዘመድ አዝማ ድ የለም፡፡ በቅርብ አለሁ የሚለውም ወዳጅ አል ነበረም፡፡ እርሱ ግን ተስፋ አልቆረጠም፡፡ ከአንድ ኬንያዊ ነጋዴ ዘንድ ቀርቦ የመጀመሪያውን “ሱ ቅ በደረቴ” በኤስሊ ጀመረ፡፡ በመጀመሪያ የወሰደ ው 36 የኬንያ ሽልንግ ብቻ የሚያወጣ የጸጉር ቅ ባት ነበር፡፡ እሱን አዙሮ በመሸጥ ተአማኒነቱን አ ስመሰከረ፤ በቀጣይም ከፍተኛ መጠን ያለው ሽያ ጭ እንዲያካሂድ ፍቃድ አገኘ፡፡ ከ10 ደርዘን በላ ይ መሸጥ ከቻለም 15 በመቶ ያህል ትርፍ መካፈ ል የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ፡፡ ይህ ተዓ ማሚነቱ የፈጠረለት አጋጣሚ መኾኑን በኩራት እንዲናገር አድርጎታል፡፡

አቶ ቶልቻ ከባለቤታቸው ጋር

ግብ ቤቱ የሚያገኘው ትርፍ በመጠኑም ቢኾን ከፍ ሲል ፍላጎቱ ም መጨመሩ አልቀረም፡፡ ገንዘቡ ጠርቀምቀም ሲልም ወደ የመ ን ባህር ዛፍ ለሚልኩ ነጋዴዎች የአገር ውስጥ አቅራቢ ሚናነትን ወሰደ፡፡ በዚህም ናኩሩ፣ ሞሎ፣ ጆሮ ፣ ኤልባጎን፣ ቱሪ፣ ማጅ መ ዙሪ፣.ሎንዲያሊ፣ ናርሞሮ ፣ ኪጋንጆ ፣ ናኙኪ፣ ዳጎሬቲ እና ካሩ ራ ከተባሉ ደኖች በመዘዋወር በሳምንት 150 ፉርጎ የመሙላት ግ ዴታውን ይወጣ ነበር፡፡ አይሰለችም፡፡ ሳምንቱን ሙሉ በየደኖቹ ሲዞር፣ ሲቆርጥ ሲያስቆርጥ ይከርማል፡፡ ከእንጨቱ ሽያጭ የሚገኘው ትርፍ ቀላል የሚባል አልነበረም፡፡ ውጣ ውረዱን የሚያስረሳ ትርፍ ያገኝበት ስለነበር በደስታ ነበር የሚሠራው፡፡ ይህ ግን የሞይ መንግስት ዛፍ መ ቁረጥ የሚከለክለውን ደንብ እስከሚያወጣ የቀጠ ለ ነበር፡፡ ደንቡ እ.አ.አ በ1982 ተግባራዊ ሲኾን አቶ ቶልቻ 100 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ዛፍ አስቆ ርጦ ነበር፡፡ ደንቡ አላወላዳውም፣ ከአገር ለማ ውጣት አልተቻለም፡፡ የአልቤርጎ መክፈል እስ ኪያቅተው ለወራት ናኩሩ ተቀምጦ ተስፋ አ ድርጎ ነበር፡፡ ሁሉም አልተሳካም፡፡ ገንዘቡን ውሃ በላው፡፡ እርሱ ግን ለውድቀት ፊት አይሰጥምና ወ ደ ገመና ከታቿ ኤስሊ ተመልሶ የግለሰቦች መኪና ውስጥ እያደረ አዲስ የሕይወት ም እራፉን ለመክፈት ያስብ ጀመር፡፡ “ፍጹም አልወድቅም” ይላል፡፡ ከዛም በኋላም ቢ ኾን ደላላ ኾኖ ኑሮውን ለመሻሻል ታግሏ ል፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካም በመሄድ የባህ ል እቃዎችን እና ውድ ጌጦችን ሸጧል፡ ፡ ሩጫው ከበድ ሲለውም በናይሮቢ ከ ፍ ያለ ሱቅ ገዝቶ ከህንዶች እየተጫረ ተ ታሪካዊ ቁሳቁሶችን መነገድ ጀምሮ ነ በር፡፡ እስከ 800 በመቶ ትርፍ የሚያገ ኝበት ሥራም በመኾኑ በትጋት ነበር የ ሚሰራው፡፡ ይሁንና ፈተና ሁሌም ከእግሩ የማይ ጠፋው ቶልቻ በዚህም ንግድ ከፍተኛ ኪሳራን አስተናግዷል፡፡ የሞይ መንግስ ት ሕገ ወጥ ያላቸውን 600 ሱቆች ሲ ያፈርስ የቶልቻም ሰለባ ኾኗል፡፡ በዚህ ም 6.4 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ኪሳራ ገጥሞታል፡፡

አዲሱ ጉዞ. . . ዛሬ ወደኋላ መለስ ብሎ ሲመለከት ያለ ፋቸውን ፈተናዎች እንደ እድል እንጂ እ ንደ ሰንኮፍ አይቆጥራቸውም፡፡ የሚያስ በው እርካታ ላይ ባይደርስም እስከ 300 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቤት ለቤተሰቡ በ አዲስ አበባ መገንባቱ፤ እንዲሁም 30 ሚ ሊዮን ሽልንግ የሚያወጡ ቤቶችን በናይ ሮቢ እያሰራ መኾኑ ስኬቱን የሚያሳዩ ና ቸው፡፡ ለዚህ ስኬት ደግሞ በመጨረሻ ላይ በ አዲስ መንፈስ የጀመረው የሐበሻ ሬስቶ ራንት ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ በ2004 ዓ.ም የተመሰረተው ሐበሻ ሬስ ቶራንት እንዲሁ የባለቤቱን እመቤት አበ በን እና የእርሱን ድካም በእጅጉ ጠይቋ ል፡፡ ባለቤቱን ምግብ ስታበስል እሱ በአ ስተናጋጅነት ሠርቷል፡፡ ለሦስት ወራትም ሁ ለቱ ብቻቸውን ፈተኙን ጊዜ አልፈውታል፡፡ ዛሬ ግን ሐበሻ የሁ ለቱ ብቻ አይደለም፡፡ 75 ያህል ሠራተኞችም የጥረቱን ፍሬ እየ ቀመሱ ነው፡፡ 80 በመቶ ያህሉ ደግሞ ኢትዮጰያውያን ወጣቶች መኾናቸው ትልቁ ስኬቱ ነው፡፡ ለአብዛኛው ስደተኛ ኬንያ የመሸጋገርያ ድልድይ ነች፡፡ ብዙዎ ች በኬንያ ሠርቶ መለወጥን የሚያምኑበት ጉዳይ አይደለም፡፡ በ ተለያየ መንገድ ወደ ሦስተኛ አገር መጓዝ የማይቀር ጉዳይ ነው፡ ፡ ቶልቻ ግን የተለየ ነው- “በገንዘቤ ባርነትን አልገዛም” ይላል፡ ፡ ብዙ ካሰሱ የማደግ ዕድሉ ኬንያም ቢኾን የሚለው አቋሙ ከ ብረት የጠነከረ ነው፡፡ እናም ወጣቶችን “ሞታችሁ ሞትን አትጠ ብቁ” ይላል፡፡ በንግዱ ላይ ከሚያሳየው ስኬት ባሻገርም በአኗኗር ሁኔታውም ላይ የእለት ተእለት ለውጥ ማምጣትን እንደ ስኬት ይቆረዋል፡፡ ለዚህም ለ40 አመታት የፈተነውን የሲጋራ ሱስ ሰሞኑን ማቆሙ ን ይጠቅሳል፡፡ በሙሉ ጤንነት እስካለም ነገ የሚሰራቸው ን ተግባራት ዛሬ ያቅዳል፡፡ “ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ከብት እርባታው እሄዳለሁ” ይላል፡፡ ለእርሱ የሚያልቅ ዕድል የለም!!!

ፎቶ- አይነው ኃይለስላሴ

በኬንያ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ


ሐበሻዊ ቃና

8

የስደት ዓለም

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ወግ ከሐበሾች በዳንኤል ክብረት መጀመሪያ ጉዞዬ ከስካንድኒቫያን ሀገራት አንዷ የሆነችው የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ነበር። ለ ጥቆ በሀገሪቱ በትልቅነት አራተኛ ወደ ሆነችው ስታቫንገር አመራሁ። በዚያም አንድ ሳምንት ያ ህል ከቆይሁ በኋላ አስራ አምስት ቀን ያህል ወ ደ ምቆይባት ማልታ በፍራንክፈርት በኩል አድ ርጌ ተጓዝኩ፡፡ የእኛ መጽሐፍ ቅዱስ “መላጥያ” የሚላት ይህቺ ደሴት በጀልባ ሜዲትራንያን ለሚያቋርጡ ስደተ ኞች ወገኖቻችን መጠለያ ናት፡፡ በሊቢያ እና ጣ ልያን መካከል መገኘቷ እንደ መንገድ ማረፊያ እ ንድታገለግል አድርጓታል፡፡ ስደተኞች ወገኖቻች ን ታዲያ እዚህች ሀገር የሚደርሱት ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈው ነው። በሱዳን በረሃ ተጉዘው የሰሐራን በረሐ እንደ ግ መል ያቋርጣሉ፡፡ ረሃቡ፣ ጥማቱ በትግል እና በ ወኔ ይታለፋል፡፡ በየመንገዱ መኪና ሲበላሽ መ ቆሙ፣ ከፖሊሶች ለመደበቅ በየተራራው ሥር ከ አንድ ቀን እስከ ለሁለት ሳምንት ያለ ምግብ መ ቀመጡ፤ በየቀኑ ብር ጨምሩ ከሚሉ አሻጋሪዎ ች ጋር መጨቃጨቁ ይታለፍና ሊቢያ ይገባል፡፡ ከሊቢያ ፖሊሶች ተደብቆ፤ በማይታወቅ ቤት ውስጥ ከርሞ፣ በሌሊት ጀልባ ላይ ወጥቶ በሜ ዲትራንያን ባሕር ላይ ጉዞ ይጀመራል፡፡ በሕይወ ት እና በሞት መካከል እየተጓዙ፣ ከተሰበረ ኮም ፓስ ጋር እየታገሉ፤ ልምድ በሌለው ካፒቴን እየ ተመሩ፤ በእግዚአብሔር ቸርነት ከባሕር አውሬ ተርፎ ማልታ ይገባል፡፡ ማልታ ላይ ደግሞ በፖሊስ ተይዞ መጀመርያ “ሐል ፋር” እሥር ቤት (detention center) መቆየት አለ። ከዓመት እና ከሁለት ዓመት በኋላ ሲወጡ ደግሞ ወደ “ሐል ፋር “ መጠለያ (የድን ኳን ካምፕ) ይገባል፡፡ እሥር ቤቱ ዙርያው በግ ንብ እና በሽቦ የታጠረ ሲሆን አንዳንዶች እየዘለ ሉ፣ ሌሎች ዘመናቸውን ጨርሰው ወጥተው በአ ሁኑ ጊዜ ምንም አበሻ በውስጡ የለበትም፡፡ የመጠለያ ጣቢያው ውስጡ በኮንቴይነር እና በ አረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው፡፡ ኮንቴይነሮቹ በ ቅርብ እንደ መጡ ሰምቻለሁ፡፡ ድንኳኖቹ ግን ራሳቸው እርጅናቸውን ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ ም በዚህ ያረጀ ድንኳን ውስጥ አጥንት ድረስ በ ሚገባውና «ያገሬ ብርድ ማረኝ» በሚያሰኘው የ ማልታ የክረምቱ ብርድ እንዴት ሆኖ ሊኖርበት

መንገድ ማረፊያ የእኛ መጽሐፍ ቅዱስ “መላጥያ” የሚላት ማልታ በጀልባ ሜዲትራንያን ለሚያቋርጡ ስደተኞች ወገኖቻችን መጠለያ ናት

እንደሚችል መድኃኔዓለም ይወቅ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እዚህ መጠለያ የሚኖር አበሻ የለም፡፡ ሁሉም ጥ ለውት ወጥተው በየሥራቸው ተሠማርተዋል፡፡ እንዲህ ተሰቃይተው እና መከራ ተቀብለው እ ዚህ ማልታ የደረሱት ሁሉ በአንድ ነገር ያስገር ሙኛል፡፡ ሁሉም ለወላጆቻቸው እና ለእኅት ወ ንድሞቻቸው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ያዩትን መከራ ሳ ያዩ እዚያው በሀገራቸው ሊረዷቸው ደፋ ቀና ይላሉ፡፡ እንዲህ በመከራ ደርሰው ለቤተሰቦቻ ቸው ገንዘብ ይልካሉ፡፡ ከዚህ በላይ ምን ደግነ ት አለ? የሚልኩት ገንዘብ እኮ የላብ ሳይሆን የደ ም ዋጋ ነው፡፡

ሐበሾች በማልታ በማልታ ሐበሾች ዘንድ፣ ፍቅር ይጋገራል፤ ፍቅ ር ይቀርባል፤ ፍቅርም ይበላል፡፡ ዘረኛነት እና ፖ ለቲካዊ ልዩነት ሜዲትራንያን ባሕር ገብተዋል፡፡ ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ለመለየት ለየት ያለ ጥናት ይጠይቃችኋል፡፡ እነዚህም ትግ ርኛ እነዚያም አማርኛ ያቀላጥፋሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን የስብከት ጉባኤ የአማርኛም

ይሁን የትግርኛ መዝሙር ከተዘመረ ሁሉም በ እኩልነት ይሳተፋሉ፡፡ ጉባኤውን የሚመራው ኮ ሚቴም ከሁለቱም የተውጣጣ ነው፡፡ የሁለቱ ሕ ዝቦች የፍቅር ውሕደት የሚታይ ነው፡፡ “የታለ ድንበሩ? ሰላም አስከባሪውስ የታለ? ድንበር ጠ ባቂ ወታደሮችስ የታሉ? ጦርነቱስ የት ገባ?” ትላ ላችሁ ማልታ ላይ ስትሆኑ፡፡ እዚህ ቁስል የለም፡ ፡ ቢኖርም የሻረ ቁስል ነው፡፡ እዚህ ልዩነት የለ ም፤ ቢኖርም ውብ የሆነ ልዩነት ነው፡፡ መከራ ከሆነ እንዲህ ያደረጋቸው፤ ስደቱ ከሆ ነ እንዲህ ያስተሣሠራቸው፤ በረሃው ከሆነ ያፋ ቀራቸው፤ ሁላችን ይድረሰን እንበልን? ያሰኛል፡ ፡ አንዱ ከሌለው ከሌላው ተጠግቶ ይኖራል፡፡ ያ ለው ለሌለው ያበላል፡፡ ያገኘ ላላገኘ ያካፍላል፡ ፡ ብዙዎች ዕድል ደርሷቸው ማልታን ለቅቀው አ ውሮፓ እና አሜሪካ ከሄዱ በኋላ ይህንን እንደ ገ ና ዳቦ የሚገመጥ የማልታ ፍቅር ለምደው ኑሮ ው ይሰለቻቸዋል፡፡ አንዳንዶችም ተመልሰው ይ መጣሉ፡፡ እዚህ የሚሰሙ ፊልሞች አሉ፡፡ ትራዤዲ፣ ኮ ሜዲ፣ ዶክመንታሪ፣ በያይነቱ ፊልም አለ፡፡ በሱ

ዳን፣ በሊቢያ፣ በሜዲትራንያን የተከናወኑ የሀገር ልጅን ታሪክ የያዙ ፊልሞች፡፡ ይተርኩላችኋል፡፡ መከራውን ወደ ሳቅ፣ ስቃዩንም ወደ ቀልድ ለው ጠው ያቀርቡላችኋል፡፡

የአዛውንቶች ሀገር እኔ እንዳየኋቸው ማልታዎች የሚመሰገን ብዙ ጠባይ አላቸው፡፡ ለሚሸጡላችሁ ዕቃ ታማኞች ናቸው፡፡ የሆነውን ብቻ ይነግሯችኋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ዕቃ የምትፈልግ ከሆነ ከእኔ ሱቅ ከምት ገዛ ከእገሌ ሱቅ እዚህ ቦታ ብትገዛ ይሻልሃል ይላ ሉ ማልታውያን፡፡ እንደ ገጠር ባልቴት ወሬ የሚወድዱ ቢሆኑም ማልታውያን እህ ብለው ከሰሟቸው ምሥጢር የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ የውስጣቸውንም ሆነ የውጫቸውን ያወሯችኋል፡፡ በማልታ «አንዲት ሴት እስክታገባ፣ አንድ ወንድ ደግሞ ካገባ በኋላ ይሰቃያል« ይባላል፡፡ ለማልታ ሴቶች ወንድ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ የ ወንዶች እጥረት አለ፡፡ እናም እስኪጋቡ ድረስ ሴቷ ወንዱን ትለማመጣለች፡፡ ሴቷ ብቻ ሳትሆ

ፎቶዎች- ዳንኤል ክብረት

ን የሴቷ ቤተሰቦች ጭምር እስኪያገባት ድረስ ይ ከባከቡታል፡፡ ከጋብቻ በኋላ የቤቱ ንብረት እና ገንዘብ በሴቷ እጅ ይወድቃል፡፡ ወንዱ ገንዘቡን አምጥቶ ለሴቷ ያስረክብና በየጊዜው እያሰበች የ ምትሰጠው እርሷ ናት፡፡ ከዚያም በተራው እር ሱ ማልቀስ ይጀምራል፡፡ በማልታ መንገዶች አሥር ሰው ካያችሁ ሰባቱ ሽማግሌዎች እና ባልቴቶች ናቸው፡፡ አገሪቱ የ አረጋውያን ሀገር ናት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከ ማልታ መንገዶች በሠላሳ ሴንቲ ሜትር ርቀት ላ ይ ከተሠሩ መደዳ ቤቶች በራቸውን ከፍተው ወ ጭና ወራጁን የሚያዩ የማልታ አረጋውያን ያጋ ጥሟችኋል፡፡ ለሁለት ሳምንት ያህል ስቀመጥ የፖሊስ መኪና ሳይረን እና የፖሊስ ግርግር ያላየሁባት ሀገር ማ ልታ ናት፡፡ ፖሊሶቹን ያየኋቸው ክብ ሠርተው ሲጫወቱ ነው፡፡ ሀገሪቱ የሰላም ሀገር ናት፡፡ መ ጀመርያ ወደማልታ የመጣሁ ቀን ከአውሮፕላን ወርጄ ሻንጣዎቼን በመያዝ በቀጥታ ወደ በሩ ሳ መራ ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡ በአካባቢው “ከየት መጣህ? ወዴትስ ትሄዳለ

የኢምግሬሽን ጥሬ ዕቃዎች

ንድ ፋብሪካ ጥሬ ዕ ቃ የሚያስገባው ለ ምንድን ነው? ፈጭ ቶ፤ አቅልጦ፤ ጠፍ ጥፎ፤ሰፍሮ እና ቆ ጥሮ የሚፈልገው ን ዓይነት ምርት ለማምረት እና ለመሸ ጥ ነው፡፡አሜሪካም በዲቪ የጠራቸው ንም፤ በአሳይለም ያጎራቸውንም፤ ከኬ ንያ የሰበሰባቸውንም መጻተኞች የሚቀ በላቸው ልክ እንደ ጥሬ ዕቃ ነው፡፡ በ ዘረጋውም ‹‹ሲስተም›› ኩራታቸውን አ ጥፍቶ፤ ማንነታቸውን ደምስሶ፤ ትዝታ ቸውን አደብዝዞ፤አስተምሮ፤ አስቦርቆ፤ አስጨንቆ፤ አደባልቆ እና አሳቆ፤ አዲ ስ ማንነት፤ አዲስ ዓይነት ኩራት እና አ ዲስ ዓይነት ትዝታ ይሰራባቸዋል ከዚ

ያም አሜሪካውያንን የሚመስል መሆ ን ግን የማይችል አገልጋይ ዜጋ ይፈጥ ርባቸዋል፡፡ ይህን የኢምግሬሽን ኢንደስትሪ በጅም ላ መኮነንም ማመስገንም ይከብዳል፡፡ ‹‹ምርቅ እና ፍትፍት›› እንደማለት ነው፡ ፡ እንዳንተፋው ፍትፍት አለው፤ እንዳ ንውጠው ምርቅ አለው፡፡ በዚህ አይነት መንታ ስሜት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ን ጥቂት አይደሉም፡፡ አንዱም እኔ ነኝ፡ ፡ ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ ግን የኢም ግሬሽን ኢነደስትሪ እየቀጠቀጠው ያለ፤ ማንነቱ ከምላሱ ላይ ጠፍቶ ስልኩ ላይ ብቻ የቀረ ሰው ታሪክ ነው፡፡ ይህን ጥሬ ዕቃ የተዋወቅሁት ባቡር ላ ይ ነው፡፡ አሜሪካ ከመጣ ዓመት ባይሞ ላውም የራሱ ስልከ ለማውጣት፤ የባን

ክ አካውንት ለመክፈት እና አሜሪካን ለ ማማረር ግን ደርሶ ነበር፡፡ ባቡር ውስጥ ሲያየኝ ሳያመነታ ነበር ሰላም ብሎኝ አ ጠገቤ ቁጭ ያለው፡፡ ወዲያውኑ ‹እዚህ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን እንዴት ሰላ ም እንደማይባባሉ እና ፍቅር እንደሚጎ ላቸው አስረዳኝ…፡፡እኔም ከርሱ ቀደም ብዬ መጥቼ፤ ፕሮሰስ እየተደረኩ ያለሁ ጥሬ ዕቃ ስለሆንኩ ዘፈኑ ገብቶኛል፡፡ አጋጣሚ ባቡር መውረጃችን አንድ ጣቢያ ስለነበረ አብረን ወረድን፡፡ ወጉ ም ቀጠለ ‹‹ኢምግሬሽን ፕሮሰስ አልቆልሃል?›› አ ልኩት፡፡ ጥያቄው ዱብ እዳ አልሆነበት ም፡፡ እስከ አሁን የዘበዘበኝ ስለ ኢምግ ሬሽን ችግሩ ሊያዋየኝ ፈልጎ እስኪመስለ ኝ ድረስ ያለ የሌለውን ነገር ዘከዘከልኝ፡

አሜሪካ በውሸት ሳያሰለጥን አይቀበልም፡፡ በዲቪ የመጣው ዘመዱን አግብቶ ለማምጣት፤ እናት አባቱን ለማስመጣት ይዋሻል፤ የውሸት ያገባል፤ የውሸት ይፋታል፡፡

በናኦድ ቤተሥላሴ (ሜሪ ላንድ፣ አሜሪካ) ፡ በአንድ ጥያቄ እጅ ሰጠ፡፡ እንደ ማንኛውም መጻተኛ ታሪኩን መ ተረክ የጀመረው ኢትዮጵያ ከፈጸመው ገድል ነው፡፡የእርሱ ገድልም መንፈሳዊ፤ በጣም መንፈሳዊ ነበረ፡፡በኢትዮጵያ በ አንድ ቸርች መስራች እንደነበረም አስረ ግጦ ነገረኝ፡፡አሳይለም ለመጠየቅ ያሰበ ው ሳይፈልገው እንደሆነ ነገር ግን እንደ ጠየቀ፤ ኬዙን የጻፈለት ሰው በደንብ እ ንዳልጻፈለት፤ መጀመርያ ዙር ኢንተር ቪው እንደወደቀ እና ጉዳዩ ፍርድ ቤት እንዳለም ነገረኝ፡፡ የጥሬ ዕቃዎች ታሪክ ሁሉ ፎርሙላው አንድ ነው፡፡ በማጽናናት እና በመዝናናት መንፈስ ‹‹እንተርቪው ላይ ችግሩ ምን ነበር?›› አ ልኩት፡፡ ‹‹ምን ባክህ ኬዝ የጻፈልኝ በደ ንብ አላሳሰረኝም›› አለኝ፡፡ ነገሩ ቢገባኝ

ም ይውጣለት ብዬ ‹‹እንዴት?›› አልኩ ት፡፡ ‹‹ኬዙ ላይ ሦስቴ አሳስረኝ እያልኩ ት ሁለቴ ይበቃሀል አለኝ፤ ይኸው እም ቢ አሉኝ!›› አለ በቂ ውሸት ባለመናረሩ እየተፀፀተ፡፡ ወይ! የቸርች መስራች!፡፡ አሜሪካ በውሸት ሳያሰለጥን አይቀበል ም፡፡ በዲቪ የመጣው ዘመዱን አግብቶ ለማምጣት፤ እናት አባቱን ለማስመጣት ይዋሻል፤ የውሸት ያገባል፤ የውሸት ይ ፋታል፡፡ በሰላም የሚኖረው እንኳን ወ ይ ታክስ ያጭበረብራል፤ ወይም ሎው ኢንካም ተብሎ ጥቅም ለማግኘት ይዋ ሻል፤ የሚዋሽበት ካጣ ደግሞ ኢትዮጵ ያ ሄዶ የሌለውን አለኝ፤ ያልሆነውን ሆ ኛለሁ ብሎ ይዋሻል፡፡ፕሮሰስ ላይ ያለ ጥሬ ዕቃ አንዲህ ነው፡ የሚኖረው፡፡ አ ይ ጥሬ ዕቃ!


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

9

የስደት ዓለም ወግ ከአገረ አሜሪካ

ተስፋዬ-ከአሜሪካ በማልታ ያለው መጠለያ ጣቢያ ውስጡ በኮንቴይነር እና በአረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው

ህ?” የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ውጭ ወጥቼ እንኳን መውጣታቴን አላመንኩትም ነበር፡፡ ለማልታዎች አገ ር ሰላም ነው፡፡

“ቫሌታ” እና “ጉዞ” በጥንታዊው እና ቢጫማ መልክ ባለው (ማልታዎ ቹ ሲያቆላምጡት «የማር መልክ» ያለው ይላሉ) የማ ልታ አውቶቡስ ተሳፍረን ወደ ቫሌታ እየሄድን ነው፡፡ ቫሌታ የማልታ ዋና ከተማ ነች። የማልታ ሕንፃዎች ከ አራት እና አምስት ፎቅ የማይበልጡ፣ መልካቸው ደ ብዛዛ ቢጫ ወይንም ቢጫማ መልክ ያለው ነው፡፡ ይ ህም ከተማዋን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ውበቷን እንዳታ ጣ አድርጎታል፡፡ የሕንፃዎቿ አሠራር ከሀገሪቱ ጥንታዊ ነት እና ቅርስነት ጋር የተስማማ፣ ነገር ግን ዘመናዊነቱ ን የጠበቀ ነው፡፡ ይህንን የማልታ የሕንፃ አደራደር ሳይ የጎንደር፣ የሐረ ር፣ የአኩስም እና የላሊበላ ሕንፃዎች እና ቤቶች ይታሰ ቡኛል፡፡ ከከተሞቹ ባህል፣ ታሪክ እና ዘመን አይሽሬ የ ሕንፃ ጥበብ ጋር የማይሄዱ፤ ተመጣጣኝ ምግብ እንዳ ጣ ልጅ አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ያሉ፣ የቀለም ኤግዚቢ ሽን እንዲያሳዩ የተፈረደባቸው ይመስል ዝብርቅርቃቸ ው የወጣ ሆነው ይታዩኛል፡፡ ባለሥልጣኖቻቸው እንደሆኑ ብዙ ጊዜ ውጭ ሀገር ሄደው አይተው መጥተዋል፡፡ ዕውቀቱን ቀስመው ሊ ተገብሩት አልቻሉም እንጂ፡፡ እስኪ የሚሻል ከሆነ ከ ተሞቹን ራሳቸውን ውጭ ሀገር ወስደን እናሳያቸው! እስቲ ጉዞአችንን ከማልታ ደሴቶች መካከል በስፋት ሁለተኛዋ ደሴት ወደ ሆነችው “ጉዞ” እናድርግ፡፡ “ጉ ዞ” ከዋና ከተማይቷ ከቫሌታ በመኪና የሰላሳ ደቂቃ ከ ዚያም በመርከብ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ ያህል ትርቃለ ች፡፡ ሕዝቦቿ ሰላማውያን እና ሃይማኖተኞች ናቸው፡፡ አንዲያውም አንዳንድ መጻሕፍት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ተመልሶ ቢመጣ አንዳስተማራቸ ው የሚያገኛቸው የጉዞን ሰዎች ብቻ ነው ይላሉ፡፡ የማልታ እና የጉዞ ሰዎች ልዩነታቸው ከደሴቶቹ ር ቀት በላይ ነው፡፡ የማልታ ሰዎች የግሪክ እና የጣልያ ን ሰዎች ክፉ በሽታ ተጋብቶባቸው አንድ ነገር ሲሆ ኑ እግዚአብሔርን እና ማርያምን መሳደብ ይወዳሉ፡ ፡ ነገር ግን 90 በመቶ የማልታ ሕዝብ ክርስቲያን ነ ው ይባላል፡፡ የማልታ ሽማግሌዎች የሚደግሙት ዳዊት ሳይሆን የ ሀገር ቤት «ዱርዬ» የሚሳደበውን የእናት እና የአባት ስድብ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ንግግራቸው ስድብ ካልጨ መሩበት የተናገሩ አይመስላቸውም፡፡ የጉዞ ሰዎች ግን ከአፋቸው ክፉ አይወጣም፡፡ በሁለቱ ደሴቶች መካከል አያሌ አፍሪካውያን ስደተ ኞችን የበላው፣ ያሰቃየው እና ያጓጓዘው የሜዲትራን ያን ባሕር ተንጣልሏል፡፡ ጠቅላላ ስፋቱ 2.5 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሆነውና አፍሪካን፣ እስያን እና አውሮፓን የሚያገናኘው ይህ ባሕር በዓለም ላይ የተ ከናወኑትን ዋና ዋና ጦርነቶች ከሰባት ሺ ዓመታት በላ ይ ያስተናገደ ባሕር ነው፡፡ ሜዲትራንያን የሚለው ቃል ከሁለት የላቲን ቃላ ት የተገኘ ስም ሲሆን ትርጉሙም በመሬት መሐል ያ ለ ውኃ ማለት ነው (from medius, “middle” and terra “earth”):: ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የማልታ መንግሥት የጉዞን እና የማልታን ደሴቶች በድልድይ ለማገናኘት በጃፓን ባለሞያዎች አስጠንቶ ነበር፡፡ ጥና ቱ ድልድዩ ሊገነባ እንደሚችል ቢያሳይም በገንዘብ እ

ወደ ማልታ በባህር የሚገቡ ስደተኞች የመጀመሪያ ማረፊያቸው ዙርያው በግንብ እና በሽቦ የታጠረ እሥር ቤት ነው

የአገሬው ሰዎች የማር መልክ አላቸው እያሉ የሚያቆላምጧቸው የማልታ አውቶብሶች

ማልታ እና መጽሐፍ ቅዱስ q ማልታ ከሜዲትራንያን ደሴቶች መካከል ት ልቁ ሲሆን በሜዲትራንያ ባሕር ማእከላዊ ቦታ ላ ይ ከሲሲሊ በስተ ደቡብ 96 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገ ኛል፡፡ ጠቅላላ የደሴቱ ስፋት 246 ስ.ኪ.ሜ. ነው፡፡ q ፊንቄያውያን በዘጠነኛው መ/ክ/ዘመን /ቅ.ል.ክ/ ደሴቲቱን በቅኝ ግዛት ይዘውት ነበር፡፡ በ ስድስተኛው መ/ክ/ዘ /ቅ.ል.ክ/ ደግሞ ኙኒኰች ያ ዙት፡፡ በሁለተኛው የፑኒክ ጦርነት /218 ቅ.ል.ክ/ ሮማውያን ደሴቱን ያዙ፡፡ ከዚያም ከሌሎች የአካባ ቢው ደሴቶች ጋር በአንድነት በሮም ንጉሥ በሚሾ ም ሀገረ ገዥ ትተዳደር ነበር፡፡ q መላጥያ በቅድመ እና ድኅረ ክርስትና ቅርሶች እና ሙዝዬሞች የተሞላች ደሴት ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታሥሮ ወደ ሮም ሲጓዝ በቄዳ ደ ሴት አካባቢ መርከብ ተሰበረባቸውና ሁሉም በመ ላጥያ ደሴት ዐረፉ፡፡ ሐዋርያው ያረፈባት ቦታ በደ ሴቲቱ ሰሜናዊ የባሕር ወሽመጥ ከአሁኗ ቫሌታ / Valetta/ 13 ኪ.ሜ ሰሜን ምዕራብ ርቀት ላይ ተገ ኛለች፡፡ ወደ ደሴቲቱ የገባበት በዓል ለደሴቲቱ ዓ መታዊ ክብረ በዓል ሆኖ በየዓመቱ ፌብርዋሪ 10 ቀን ይከበራል፡፡ q ቅዱስ ጳውሎስና ሌሎች ተጓዦች በደሴቲቱ ሦስት ወራት ተቀምጠዋል፡፡ በዚያ ደሴትም ከእፉ ኝት መርዝ ድኗል፡፡ በዚህም የተነሣ «ይህ አምላክ ነው» ብለውት ነበር፡፡ የደሴቲቱን አለቃ የፑፕልዮ ስን አባት ከወባ በሽታ ፈወሰለት፤ በዚህም የተማረ ኩ ብዙ ሰዎች ድውያንን አመጡና ፈወሰላቸው፡፡

ጥረት ሳይሳካ ቀረ፡፡ በዚህ ጊዜ የጉዞ ደሴት ነዋሪዎች ጮቤ ረገጡ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ደሴቱ በቀላሉ የ ሚደረስበት ከሆነ የማልታ ሰዎች ክፉ ጠባይ ወደ እ ኛም ይጋባል ብለው ፈርተው ነበርና፡፡

«ቱርክ ወለደች» የማልታ ቆይታዬ ተጠናቀቀ፡፡ ከከተማው ስንወጣ ፀሐይ እና ዝናብ አብረው መንገድ ላይ እየተዝናኑ ነበ ር፡፡ በእኛ ሀገር ዝናብ እየዘነበ ፀሐይ ከወጣች «ጅብ ወለደች» እንላለን፡፡ ማልታዎች ደግሞ «አንዲት ቱር ክ ወለደች» ይላሉ፡፡ በሁለታችንም ባህል ነገሩ ከመ ውለድ ጋር መገናኘቱ አስገርሞኛል፡፡ ማልታን ተሰናብቼያት እየወጣሁ ነው፡፡ ትዝታዋ መቼም አይለቀኝም፡፡ እስካሁን በብዙ ሀገሮች ስዞር እንደ ማልታ ከነ ሆድ ዕቃዋ ያየኋት ሀገር የለችም፡፡ አዲስ አበባን እንኳን የማልታን ያህል የማውቃት አ ይመስለኝም፡፡ ሽሮ መልክ ያላቸው ሕንፃዎቿ፤ እዚህ ም እዚያም እንደ ከዋክብት ብቅ የሚሉት አብያተ ክ ርስቲያናቷ፡፡ በሚገባ የተዘጋጁት ሙዝየሞቿ፡፡ ተጎ ብኝተው የማያልቁት መዳረሻዎቿ፤ እንደ ተሰለፈ ወ ታደር በንቃት የተደረደሩት የመንገድ ዳር ዛፎቿ፤ «ኦ ልራይት» እያሉ የሚተላለፉት መንገደኞቿ፤ ዙርያዋ ን የከበባት የሜዲትራንያን ባሕር፤ ከዘመነ ፊንቄያው ያን እስከ አውሮፓ ኅብረት የሚደርሰው ታሪኳ የማ ይረሱ ናቸው፡፡ ይህ ጹሁፍ ከዳንኤል ክብረት ጡመራ (ዳንኤል ክብረት ዶት ኮም ) የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል። ጽሁፉ በየካቲት 2003 ዓ.ም ለንባብ የበቃ ነው።

በቅርቡ ነው የመጣሁት፡፡ እንደ መታደል ሆኖ አበባ ይዞ የሚቀበል ቤተሰብ ስ ለተቀበለኝ ዱላስ አውሮፕላን ማረፊያ ኧረ ውሃ በላኝ ብዬ አልጮሁኩም፡፡ ተ መስገን ልበላ፤ ለካ ይህም አለ፡፡ እርግጥ በአሜሪካ ፍቅር ጥንብዝ ብዬ የሠከር ኩ አልነበርኩም፡፡ ሰው ሆኖ ሆድ የማይብሰው የለምና አንዳንድ ቀን ሆድ ሲብሰ ኝ የነበርኩበትን ከተማ ብቻ ሳይሆን የምር የማልጨክንባትን እንደ ስዕለት ልጅ የምሳሳላትን ኢትዮጵያን ሳይቀር ጥዬ መውጣት እመኛለሁ፡፡ የምለምነው ነገር ደረሰ፡፡ በአሥራ አንደኛው ሰዓት የሞላሁት ዲቪ መጣ፡፡ ሲ ያመጣው አንዳንድ ጊዜ … እንዳለው መሆኑ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ቪዛ ለማ ግኘት መረጃ ማዘጋጀት የጀመርኩት ቀጠሮው ሊያበቃ 10 ቀን ብቻ ሲቀረው ነ በር፤ ግን ተሳካ። ቪዛው ለ6 ወር እንደሚያገለግል ተነገረኝና ረዥም ጊዜ ተሰጠ ኝ፤ ደስ አለኝ አገሬ ለመቆየት፡፡ የጊዜ ባቡር አይቆምምና ቪዛው ሊቃጠል 17 ቀ ን ሲቀረው በስንት ውትወታ በዕለተ ቅዳሜ አገሬን ለቅቄ ዋሽንግተን ዱላስ ዓለ ም አቀፍ አውሮፕላን አረፍኩ፡፡ እንደ እድል ሆኖ ኢትዮጵያ እያለሁ፤ ከረዥም ልፋትና ጥረት በኋላ ከጓደኞ ቼ ጋር የጀመርናት አነስተኛ የአገልግሎት ሰጪ ንግድ ቡቃያ ላይ ደርሳ ለፍሬ በቃሁ እያለች ነበርና በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የድርሻችሁን ማለቷ የሚቀር አ ልነበረም፡፡ እንደ እድል ሆኖ አሜሪካ የገባሁት ደግሞ የኢኮኖሚው ቅራሪ ላይ መሆኑ ነ ው የሚገርመኝ፡፡ ይቺ የዓለም ቁጥር አንድ ሃብታም አሜሪካ በበጀት ጉድለት ተዘፍቃ፣ በሥራ አጥ ቁጥር ተጥለቅልቃ፣ ዲሞክራቶቹ የሚሉት እውነት እየሆነ ከመጣ ደግሞ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ምሰሶ ነው የሚባለው የመካከለኛ ገቢ ክፍል (middleclass) እየጫጨ ባለበት ጊዜ ነው፡፡ እዚያ ሆነን እገሌ ዶላር ላከ፣ ከአ ሜሪካ መጣ፣ የአቶ(ወ/ሮ) እገሌ ልጅ ለቤተክርስቲያን ማሠሪያ በዶላር ይህን ያ ህል ላካች ተብሎ ለዶላሩ ይሁን ለስዕለቱ ግልጽ ባልሆነ መልኩ ዶላር በእልልታ ስም ስንቱን ኢትዮጵያዊ ልቡን አሸፍቶታል መሰላችሁ፡፡ በዚሀ ዓመት ብቻ ኢትዮጵያውን ዲቪ አመልካቾች ቁጥራቸው ከ500ሺህ በ ላይ ሆኖ የአሜሪካንን መንግሥት በማስገረሙ ይመስላል የአንድ ሰሞን የአፍ ማሟሻ ዜና እርሱው ነበር፡፡ ለምን ብለን ስንጠይቅ ግን መልሱ ሁለት ይመስ ለኛል፤ በእኔ አመለካከት፤ 1. የውጪው ዓለም አኗኗር የአእምሮ ሰለባ መሆናቸን ነው፡፡ ፊልሙ፣መኪና ው፣አለባበሱ፣ ሙዚቃው፣ ስታዲየሙ፣ ማስታወቂያው፣በፊልም ውስጥ የሚታ ዩት የረቀቁ የመሠረተ ልማት ጥልፍልፎች፣ ኮምፒውተርና የሞባይል ቴክኖሎ ጂ፣ ወደ አገር ቤት ብቅ የሚለው ጅንኑ ኢትዮጵያዊ ተደማምረው ገነትማ ያለች ው አሜሪካ ነው ብለን እንድንደመድም አድርጎናል፡፡ 2. ኢትዮጵያ አምራች ለሆኑት ዜጎቿ በሚያመረቃ ደረጃ የሥራ መስክ መክፈ ት ያለመቻሏ ናቸው እኔም ብሆን ከዚህ አላመለጥኩም። የዲቪ ውጤት ሆኜ አሜሪካ ተገኘሁ። ቶሎ አልሞቅም፤ እንኳን በማይክሮ ዌቭ፣ በጋዝም ያው ነኝ፡፡ አዲስ አካባቢ ን፣ አዲስ ሰውን ለመለማመድ ጊዜ የሚያስፈልገኝ ነኝና ቨርጂኒያ፣ዲሲ፣ ሃገረ ማ ርያም ግጥግጥ ያሉትን ከተሞች ጋር ለመዋሃድ እንዲህ በቀላሉ የምሞክረው ዓ ይነት አልሆነም። በራስ መተማመን የሚባለው ነገር በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ጭራሽ አብ ሮኝ የተፈጠረ አልመስልህ እስኪለኝ ሸሸኝ፡፡ አሁን አሁን በጥቂቱ ልቅረብህ እ ያለኝ መሆኑ ደግሞ መልካም ዜና ነው፡፡ ለእኔ ሁሉም ነገር አዲስ ነው፡፡ ባን ክ ቤቱ ኤሌክትሮኒክስ ነው፤ አውቶቡሱ ኤሌክትሮኒክስ ነው፣ ሰው ራሱ ኤሌክ ትሮኒክስ ነው። ሞባይል፣ ኮምፖውተር፣ ሪደር ላይ ቸክሎ ነው የሚውለው፡፡ የፖሊስና የ“ሜትሮ አክሰስ” የሚባሉት፣ የእሳት አደጋ መኪኖች ጩኸት ልቤን ያርዱታል፤ አደጋ ሳይሆን የጥፋት ቀን ያስመስሉታል፡፡ በሩ ደስ ሲለው ተሽቀን ጥሮ ይከፈታል፣ ሲለው ደግሞ ለመክፈት መታገል ነው። ወደ ውስጥ ይሁን ወ ደ ውጪ ወደየትኛው እንደሚሳብ ያደናግራል፡፡ አሜሪካ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ በማስታወሻ ተመዝግቦ ሊያዝና ሊጠና የሚች ል መረጃ ጥቅም ላይ የሚውልበት አገር መሆኑን እየዋልኩ እያደርኩ መገንዘብ ችያለሁ። ስመጣማ ወንድሞቼ ከእኔ ባይርቁም ቅሉ ብቻዬን ሳስበው ለእኛ መ ረጃ የሚሰጥና የአገር ልጅ የሚያለማምድ፣ ሆድ ሲብሰን፣ በቡና የሚያብሰን ተቋ ም እንኳን በቅጡ አለመኖሩ ገርሞኛል፡፡ አይ እግሊዘኛ! እንግሊዝኛማ ተጉመጥምጣ ተፋችኝ አለቅልቃ ደፋችን ማለቱ ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ለእንግሊዝኛ ሩቅ አይደለሁም ያልኩት ሰው የአነጋገሩ ዘይቤ ተለወጠና የወፍ ቋንቋ ሆነብኝ። አንድ ደንበኛ ሃንድከርቺቭ (handkerchief) ስትለኝ “አቤት” ያልኩት እስኪበቃኝ በሳቅ አንፈቅፍቆኛል፡፡ ይህ ጹሁፍ ከኤፍሬም እሸቴ ጡመራ (አደባባይ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም ) የተወሰደ ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል


ሐበሻዊ ቃና

10

ዳኒ በተባረረበት ዕለት ከፕሮግራሙ አስተናጋጅ ሴልማ ጋር አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አካሂዶ ነበር

ፎቶ- ቢግ ብራዘር አፍሪካ

ሳምንቱን ሙሉ ሃያ አራት ሰዓት ያለማቋረጥ ለ ሚተላለፈው የ“ቢግ ብራዘር” የቴሊቪዥን ፕሮ ግራም ተከታታዮች እንደ እሁድ ስሜታዊ የሚ ያደርግ ቀን የለም። እሁድ በ“ቢግ ብራዘር” ላይ የተሳተፉ የየሀገራቸው ተወካዮች አሊያም ፕሮግ ራሙን መመልከት ከጀመሩ በኋላ የወደዷቸው ተወዳዳሪዎች ይባረሩ አይባረሩ እንደው የሚያ ውቁበት ቀን በመሆኑ ነው። በእርግጥ እንዲባረ ሩ የታጩ የ“ቢግ ብራዘር” ተሳታፊዎች ስማቸው ይፋ የሚደረገው ከሳምንት በፊት በመሆኑ ተመ ልካቾች ማን ሊባረር እንደሚችል የሚገምቱበት ዕድል አላቸው። የ“ቢግ ብራዘር” የየዕለት ውሎ ዎችን ስራዬ ብለው በሚዘግቡ ጋዜጦች እና ድረ ገጾች የሚወጡ አስተያየቶችን በመመልከት አዝ ማሚያውን መጠርጠር አያቅታቸውም። የ34 ዓ መቱ ኢትዮጵያዊ ዳኒ ወዳጆች እና አድናቂዎች ም ባለፈው ሳምንት ይህንኑ ስሜት ተጋርተዋል። የዳኒ ስም ከተባባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ለሁለተ ኛ ጊዜ መካተቱን ተከትሎ ቢባረር ግድ እንደማ ይላቸው የጻፉ ብዙ ነበር። ከመባረሪያው ቀን ሶ ስት ቀን ቀደም ብሎ የወጣው የኡጋንዳው ዕለታ ዊ ጋዜጣ “ኒው ቪዥን” እንዲህ አይነት አስተያየ ቶችን ካስተናገዱ ሚዲያዎች አንዱ ነው። የጋዜ ጣው ጸሀፊ የሆነችው ካሮል ኪዛቡ ለመባረር በ እጩነት የቀረቡትን ዳኒን፣ ደቡብ አፍሪካዊውን ሉክሌይን፣ ኬንያዊውን ኒክ፣ ዛምቢያዊቷን ኪም ን እና ናይጄሪያዊቷን ካረንን አነጻጽራ የሚሰማ ትን እንዲህ በግልጽ ጽፋዋለች። “ማን ወደ ቤቱ እንዲጓዝ እንደሚፈረድበት እ ሁድ ዕለት መመልከት ያጓጓል። ሉክሌይ እና ካረ ን ኃይለኛ የቁጡነት ጸባይ ቢኖርባቸውም ቤቱን ስለሚያማሙቁት እንዲባረሩ አንፈልግም። የኪ ን እና የኪም የፍቅር ግንኙነት ብሬንዳ በኪን ላይ ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ ትኩረት የሚስብ ሆኗ ል። የሶስትዮሽ ፍቅር እየመጣ ያለ ይመስላል። ቀ ሪው እንግዲህ ዳኒ መሆኑ ነው። ለቤቱ ምንም የ ሚስብ ነገር ያላመጣ በመሆኑ እኔ ቢሄድ ግድ የለ ኝም” ስትል አስተያየቷን አስቀምጣለች። እንደ ካሮል የሚሰማቸው ብዙ ነበሩ። ተመልካ ቾች እንዳይባረር የሚፈልጉትን የ“ቢግ ብራዘር” ተወዳዳሪ በአጭር የሞባይል የጽሁፍ መልዕክት (ኤስ.ኤም.ኤስ) በሰጡት ድምጽ ያድናሉ። እሁ ድ ሲመጣ ግን ዳኒ ጓዙን እንዲጠቀልል ተወሰነ።

ፎቶ- ቢግ ብራዘር አፍሪካ

ጥበብ

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የዳኒ መጨረሻ የዳኒ የጎረቤት ሀገር ልጅ ኒክም አልቀረለትም። የ ኡጋንዳው ሌላኛው ዕለታዊ ጋዜጣ “ዴይሊ ሞኒ ተር” ከማባረር ስነስርዓቱ በኋላ ባወጣው ዘገባ በሁለቱ መባረር ያዘኑት ጥቂቶች ናቸው። ይልቅ ስ ብዙዎች የተደሰቱት በደቡብ አፍሪካው ሉክሌ ይ መባረር ነው። ዳኒ ለምን ተባረረ? የዘገባው ጸሀፊ ሮበርት ካሉምባ የአሁኑ የ“ቢግ ብራዘር” ፕሮግራም ሲጀምር ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጋብዘው ካቀኑ ጥቂት ጋዜጠኞች አንዱ ነው። ስለ ፕሮግራሙም ተከታታይ ዘገባዎችን በ“ዴይ ሊ ሞኒተር” ላይ ያወጣል። ዳኒን ከተባረረ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ደውሎ የማናገር ዕድልም አግኝቷ ል። “ዳኒን ለምን አፍሪካውያን አንዲባረር ድም ጽ እንደሰጡ ጠይቄው ነበር። አስገራሚ ምላሽ

ሰጥቶኛል። አፍሪካውያን ከኢትዮጵያውያን ጋር ገና አልተግባቡም። ከኢትዮጵያ ይልቅ ከናይጄሪ ያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ጋር መግባባት ይቀ ላቸዋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም ወዲያውኑ ወ ደ አእምሮአቸው አይመጣም ብሎኛል” ይላል ከ ዳኒ ጋር ስላደረገው የስልክ ቆይታ ለ“ሐበሻዊ ቃ ና” ሲያብራራ። “ዳኒ ትሁት ሆኖ ነው እንጂ ማለ ት የፈለገው ለድምጽ ሰጪ አፍሪካውያን ኢትዮ ጵያ ምን ሳያስቡ በቀላሉ ኢላማ ውስጥ የሚያስገ ቧት ሀገር ነች” ይላል ካሉምባ። በጋዜጠኛው አስተያየት ግን ለዳኒ መባረር ዋነ ኛ ምክንያት “ጥብቅ ሃይማኖተኛ” መሆኑ ነው። “ክርስቲያናዊነት እና ‘ቢግ ብራዘር’ የማይዋሃዱ ነገሮች ናቸው” ይላል ካሉምባ። “ክርስቲያን ሆነ ህ ረጅም ርቀት በቢግ ብራዘር ለመጓዝ በጨዋታ

ው ምርጥ መሆን አለብህ።” ዳኒ ጨዋታውን በ ደንብ አልተጫወተም። ካሉምባ ለዚህ በምሳሌነ ት የሚያነሳው ተወዳዳሪዎቹ ዘወትር አርብ የሚ ያደርጉትን በመጠጥ መሳከር እና መሳሳምን በመ ጠቅስ ነው። ዳኒ በእነዚህ ድርጊቶች ሲሳተፍ አ ለመታየቱ በተመልካች ዘንድ እንደ “ደባሪ” እንደ ሚያስቆጥረው ካሉምባ ይናገራል። “ለአፍሪካው ያን ተመልካቾች አዝናኝ ማለት በቴሌቪዥን ወ ሲብ ሲፈጽም የሚታይ ነው። አሳዛኝ ነው ግን እ ውነታው ይህ ነው።” እንደ “ቢግ ብራዘር” አይነት የቴሌቪዥን ፕሮግ ራም ላይ ስትሳተፍ እንደ “እብድ” መሆን አለብህ ይላል ጋዜጠኛው። “ከየሰው ጋር መጣላት ይኖር ብሃል።። ወሲብ እስከ መፈጸም መሄድ ይጠበቅ ብሃል። በአጭሩ ወደ እንስሳ የተጠጋህ መሆን አ

ለብህ” ሲል አንድ የ“ቢግ ብራዘር” ተወዳዳሪ ማ ድረግ ስለሚጠበቅበት ያስረዳል። የዳኒ ጸባይ ግ ን ከዚህ በተቃራኒው እንደሆነም ይገልጻል። ትሁ ት፣ ሃይማኖታዊ እምነቱ የተጫነው እና ሴቶች ለ ትዳር የሚመርጡት ዓይነት እንደሆነ ይገልጻል። ምርጡ አባወራ እና ሰነፍ ይህ የትዳር ጉዳይ ዳኒ በተባረረ ዕለት ከፕሮ ግራሙ አስተናጋጅ (ሆስት) ጋር ባደረገው ቆይ ታም ተነስቶለት ነበር። ናሚቢያዊው የፕሮግራ ሙ አስተናጋጅ ሴልማ በርካታ አፍሪካውያን ሴ ቶች ዳኒን ምርጥ ባል ሊሆን እንደሚችል እንደ ሚያስቡ ከነገረው በኋላ አግብቶ እነደሆነ እነ ስ ለጋብቻ ያለውን አመለካከት ጠይቆቷል። አፍሪካ ውያን ሴቶች ለእርሱ ባላቸው አመለካከት መደነ ቁን ያልሸሸገው ዳኒ እስካሁን አለማግባቱን ተናግ ሯል። ወደፊት ማግባቱ እንደማይቀር ገልጾ ታም ኖ መኖር ለትዳር መታመን የሚያስፈራው ነገር እ ንዳልሆነ አብራርቷል። ሴልማ ሙገሳዎችን ብቻ አልነበረም ለዳኒ የነገ ረው። ሌሎች የ“ቢግ ብራዘር” ተወዳዳሪዎች ስ ለእርሱ የሚያስቡትንም አልደበቀውም። “ሰነፍ ነ ህ ይሉሀል” ሲል ሚሊዮኖች ፊት በግልጽ ጠይቆ ታል። “ይህ በጣም የተሳሳተ ነው” ሲል ነበር ዳ ኒ ምላሹን የጀመረው። “በሁሉም ነገር ስሳተፍ እ ና ማድረግ የቻልኩትን ሁሉ ሁሌም ለማድረግ ስ ሞክር ተመልክተኸኛል። አንድን ሰው ሰነፍ ብሎ መጥራት አስቸጋሪ ነው። በቤቱ ውስጥ ስሜታች ን ሲደፈርስ እና ውጥረት ሲነግስ አንዳችን በአን ዳችን ላይ እንነሳለን። ለዚያም ይመስለኛል ሰነፍ ያሉኝ” ሲል ራሱን ተከላክሏል። በ “ቢግ ብራዘር” ሰባት ሳምንት ያህል ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየቱ በራሱ ጥንካሬውን እንደሚያሳይ የ ገለጸው ዳኒ ወደፊት በፕሮግራሙ ያገኘውን የሚ ዲያ ሽፋን ወደ ገንዘብ መቀየር እንደሚፈለግ ተና ግሯል። ለጊዜው ግን በባለቤትነት ወደሚያስተዳ ድረው እና አዲስ አበባ ወደሚገኘው የልብስ መ ሸጫ ሱቁ ይመለሳል።

ሄለን በርሄ አሜሪካንን እየዞረች ነው በአፍሪካ የሙዚቃ ዝግጅት የማቅረብ ሃሳብ አላት

2003 አዲስ ዓመት የለቀቀችው አልበም ከፍተ ኛ ተወዳጅነት ያገኘላት ሄለን በርሄ ዕረፍት አጥ ታለች። ለፈረንጆች አዲስ አመት ሸራተን አዲ ስ ላይ በተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት አድናቂ ዎቿን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘችው ሄለን ለጠቀ ችና ከእጅጋየሁ ሽባባው ጋር በአንድ መድረክ ታየች። የካቲት ላ ይ ባህር ዳር ወረደች። የሀገር ቤት አፍቃሪዎቿ እምብዛም ሳይ ጠግቧት ለውጭ ሀገር የሙዚቃ ጉዞ ተሰናዳች። የመጀመሪያ ማ ረፊያዋ ዱባይ ነበር። ከህዝብ ጋር ያስተዋወቃትን “ኡዛዛ አሌና” የሚለውን ዘፈን የጠ ነሰሰችው እዚሁ ዱባይ ነበር። ሄለን “ታስፈልገኛለህ” የሚለውን አልበሟን ከማውጣቷ በፊት ዱባይ በሚገኘው “ፓልም ሆቴል” ዘፋኝነት እና ተወዛዋዥነትን ደርባ ትሰራ ነበር። ከህዝብ ጋር ያ ስተዋወቃትን ሱዳንኛ እና አማርኛ ቅልቅል ነጠላ ዜማ የጠነሰሰ ችውም እዚያው ዱባይ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። የ“ኡዛዛ አሌና” ኦሪጅናሌ ዘፋኝ የሆነችው ሱዳናዊቷ ናዳ ሄለን ወደምትዘፍንበት ሆቴል ትመጣለች። ሄለንንም ሱዳንኛ ዘፈን ስትጫወት ትመለከ ታታለች። የዘፈን ዝግጅቱ ሲያበቃ ሱዳናዊቷ ሄለንን ታገኛት እና በእርሷ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ እንድትሳተፍ ትጠይቃታለች። ሄ ለን የእሺታ መልስ ትሰጣለች። ዱባይ በሚገኘው ሸራተን ጌራ ሆቴል በቀረበው በዚህ ዝግጅ ት ላይ ናዳ “ኡዛዛ አሌናን” ስትጫወት ሄለን በተራዋ ትመለከታ ለች። ዘፈኑን በጣም ስለወደደችው ወደ አማርኛ ተርጉማ እንድ ትጫወተው ናዳን ታስፈቅዳታለች። ናዳ ትስማማለች። ሄለን ወ

ደ አዲስ አበባ ስትመለስ ግጥሙ ይጻፍና ሙዚቃው ይቀና በራል። ክሊፕም ይሰራለታል። ሄለን ክሊፑን ይዛ ወደ ዱባ ይ ትበራለች። ድምጻዊት ትዕግስት ወይሶ ወደ ዱባይ በተ ጓዘች ጊዜ የሄለንን ክሊፕ ትመለከት እና ትገረማለች። ከሊ ፑንም ከሄለን ተቀብላ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትሰጣለች። በዚህ ዓይነት ህዝብ ልብ የገባችው ሄለን ሙሉ አልበሟን ያወጣችው ሶስት ዓመት ዘግይታ ነው። ከነጠላ ዜማ ተነስ ታ በአልበሟ የተካተቱት አብዛኞቹ ዘፈኖቿ ቃል በቃል የ ሚዘፈኑላት ዘፈኝ ሆናለች። ይህንን ስኬቷን ለማጣጣም ደ ግሞ ከመነሻዋ ነበር የጀመረችው- ከዱባይ። ከዚያ ፋሲካ ን በለንደን አከበረች። ዳግማ ትንሳኤን ደግሞ በአሜሪካ። በአሜሪካ እስካሁንም የቀጠለው የሙዚቃ ጉዞዋ አሀዱ ያ ለው በርካታ ኢትዮጵያውያን ባሉባት ዋሽንግተን ዲሲ ነበ ር። ግንቦት ላይ አትላንታ ተሻገረች። በዚሁ ወር ሲያትል እ ና ላስ ቬጋስ ዝግጅቶቿን አቅርባለች። ቅዳሜ ሰኔ 18 ቀን ደ ግሞ ከመሐሙድ አህመድ ጋር ኒው ዮርክ ላይ ትዘፍናለች። በሳምንቱ ካምብሪጅ ማሳቹሴትስ ዝግጅት አላት። የአሜሪካ ጉዞዋን እንዲህ አንዲህ እያለች የቀጠለችው ሄለን ወደ ካና ዳ ተሻግራ ቶሮንቶ ያሉትን የሙዚቃ አፍቃሪያን ለማዝናና ት ቀጠሮ ይዛለች። በስተመጨረሻም ወደ አፍሪካ ሀገራት ፊ ቷን ለማዞር እቅድ አላት። በኡጋንዳ፣ ኬንያ አሊያም ደቡብ ሱዳን ያሉ የሙዚቃ ፕሮሞተሮቸ ከሄለን ጋር ከተስማሙ ቢ ያንስ ከሶስቱ ሀገር በአንዱ ያሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን ዝግጅ ቷን የመታደም ዕድል ያገኙ ይሆናል።


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

11

ጥበብ

የኤርትራ የዳያስፖራ መመኪያዎች ኤ

1.ኤሪአም ሲስተርስ ገና 18 ዓመት አንኳ ያልደፈኑ እህትማማቾች ና ቸው። ሃበን፣ ሳሊና እና ሊንዳ ይባላሉ። ወላጆ ቻቸው አብርሃም ሙሉጌታ እና ትብለጽ መለስ ይሰኛሉ። አብርሃም እና ትብለጽ እ.ኤ.አ በ1983 ከኤርትራ ወደ ሆላንድ ይሄዳሉ። እዚያም ሳሊና እና ሊንዳ ይወለዳሉ። የአሁኑ መኖሪያቸው ወደ ሆነው አሜሪካ የመጡት እ.ኤ.አ በ1996 ይመጣ ሉ። ከዓመት በኋላ ቤተሰቡ ሌላ ሴት ልጅ ያገኛ ል- ሃበንን። ሃበን እንደስሟ ትርጓሜ ለቤተሰቧ ኩራት የሆነችው ገና “አንድ ፍሬ” እያለች ነበር። ሃበን የሙዚቃ ተሰጥኦ እንዳላት የታወቀው በመ ጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ አስተማ ሪዋ ከተመሰከረላት በኋላ ነበር። ያኔ የሰባት አመ ት ልጅ የነበረችው ሃበን ከዚያ በኋላ የሚያቆማ ት አልተገኝም። መጀመሪያ በምትኖርበት ከተማ ሲያትል በሚ ዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ የአሜሪካንን ብሔራዊ መ ዝሙር አሳምራ በመጫወት እውቅና አገኘች። የ

ህጻንነት ተስራቅራቂ ድምጿ የሳባቸው የዝግጅ ት አሰናጂዎች በበጎ አድራጎት ገንዘብ ማሰባሰቢ ያ ፕሮግራሞች ላይ ይጋብዟት ጀመር። ይህንን የ ተመለከቱት በመላው ሀገሪቱ የሚተላለፉ የቴሌ ቪዥን የልጆች ፕሮግራም አዘጋጆች ሃበንን ወደ ስቱዲየአቸው ጠርተው ከአሜሪካ ህዝብ ጋር አ ስተዋወቋት። ይህ ሁሉ ሲሆን ሃበን አስር ዓመት እንኳ አልሞላትም። ሃበንን እና እህቶቿን ዝነኛ ያደረጋቸው ግን በአ ሜሪካ እና የኡጋንዳውን ኤን.ቲ.ቪ ጨምሮ በመ ላው ዓለም ባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚተ ላለፈው “አሜሪካስ ጋት ታለንት” ሾው ላይ ሲያ ትልን ወክለው ከቀረቡ በኋላ ነበር። እህትማማ ቾቹ በዚህ ፕሮግራም ላይ ያቀረቡት ዝግጅት በ ዳኞቹ ሳይቀር አድናቆትን አትርፎላቸዋል። የዛ ሬ ሁለት ዓመት ገደማ ከተላለፈው ከዚህ ዝግጅ ት በኋላ “ኤሪአም ሲስተርስ” የሚለው ስም በሲ ያትል ዝነኛ ሆነ። ታዋቂው “ሲያትል ፖስት ኢ

ንተለጀንሰር” ጋዜጣን ጨምሮ የሲያትል ሚዲ ያዎች ስለ ሶስቱ እህትማማቾች በተደጋጋሚ ዘ ግበዋል። እ.ኤ.አ በ2009 የወቅቱ የሬንተን ከተማ ከንቲ ባ እህትማማቾቹ በልጅ እድሜያቸው ለከተማይ ቱ ባበረከቱት አስተዋጽኦ የከተማውን ቁልፍ በ ስጦታ አበርክተውላቸዋል። ሴፕቴምበር 21 ቀን ም የ“ኤሪአም እህትማማቾች ቀን” እንዲሆን አ ውጀዋል። ከንቲባው ይህንን ያደረጉት እህትማ ማቾቹ በበጎ አድራጎት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮ ግራሞች ላይ በመገኘት ሙዚቃዎቻቸውን የሚ ያቀርቡ በመሆናቸው እና ሲያትልን በተለያዩ መ ድረኮች በማስጠራታቸው መሆኑን በወቅቱ ተና ግረው ነበር። ሬንተን ከሲያትል 21 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች። “ኤሪአም” በተለያዩ መድረኮች ላይ መሳተፋቸ ውን ቀጥለዋል። እንደ ስያሜያቸው “ኤሪ አም” የኤርትራ (ኤሪ) እና የአሜሪካ (አም) ዝግጅቶች ላይ እየተገኙ ያዝናናሉ። ከኤርትራ መልስ ሁለ ት ዝግጅቶች ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል። በሐ ምሌ ወር ኦክላንድ ላይ በሚካሄደው የኤርትራ

ሳሊና

ሃበን

ውያን የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከተሳተፉ በኋ ላ በቀጣዩ ወር አባታቸው በኢንጂነርነት በሚሰ ራበት የ“ቦይንግ አውሮፕላን” ፋብሪካ ዘፈኖቻቸ ውን ያቀርባሉ። እንዲህ በዝና ላይ ዝና እና እየደረቡ የሚገኙት “ኤሪአም” ሲስተርስ የሚያልሙት እንደ “ዴስቲ

ሊንዳ

ፎቶ- ከ“ኤሪአም ሲስተርስ” ዌብሳይት

ርትራ ሃያኛ የነጻነት በዓሏን በቅርቡ ስታከብር ዋነኛ ከነበሩ ስነ ስርዓቶች መካከል የሙዚቃ ድግሶች ነበሩ። ግንቦት 5 ቀን 2003 ዓ.ም በአሰብ የተጀመረው ፌስቲቫል አስመራ በሚገኙት “ባህቲ መስ ከረም” አደባባይ እና የ“ነጻነት ጎዳና” ቀጥሎ ለአንድ ሳምንት ያህል ቆይቷል። የሙዚቃ ዝግጅቶች እንዲቀርብባቸው ከተመረጡ ቦታዎች ሮማ ሲኒማም ይገኝበታል። በሮማ ሲኒማ እና “ባህቲ መስከረ ም” የቀረቡ ዝግጅቶች በኤርትራ መንግስታዊ ቴሌቪዥን (ኤሪ ቲቪ) በቀጥታ ተላልፈዋል። ሀገሪቱ ይህንን ዝግጅት እንዲያደምቁላት በዳያስፖራ የሚገኙ ወጣት ዘፋኞችን ጋብዛ ነበር። አምስቱን ከአሜሪካ እና ሶስቱን ከስዊዲን ጠርታለች። ከፖፕ እስከ ሬጌ፣ ከ አር ኤንድ ቢ እስከ ራፕ ስልቶችን የሚጫ ወቱት እነዚህ ዘፋኞችም ጥሪውን ተቀብለው ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል። በኤርትራ የነጻነት ቀን በአስመራ ስቴድየም በተካሄደው ዝግጅት ላይም በጋራ ያዘጋጁትን ዘፈን እየተቀባበሉ አቀንቅነዋል። የዛሬ ዓመ ትም በተመሳሳይ “ሳዋ” ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተገኝተው ወጣት ኤርትራውያንን አዝናንተዋል። የ”ሐበሻዊ ቃናው” ተስፋለም ወልደየስ የእነዚህን ድምጻውያን ታሪክ በአጭሩ ያስቃኘናል።

ኒስ ቻይልድ” ያለ ቡድን መሆንን ነው። “ዴስቲ ኒስ ቻይልድ” ቢዮንሴ እና ጓደኞቿ ያቋቋሙት ቡድን ነበር። ኋላ ላይ ቡድኑ ፈርሶ የባንዱ አባላ ት በየፊናቸው መስራት ቀጥለዋል። ከሁሉም ል ቃ የወጣችው ግን ቢዩንሴ ነች። ሀበን እንደ ቢዮ ንሴ ብቻዋን ገንና ትወጣ ይሆን?

ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ የሚኖረው ላይኔ ታደሰ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ነው። አስራ ዘጠኝ ዘፈኖ ች የተካተቱበት “ራይዝ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም አለው”” በጥርስ ህክምና ቴክኖሎጂ የተመረ ቀው ላይኔ ሙዚቃ የሚጫወተው ከመደበኛ ሙያ ጎን ለጎን ነው። ከአስመራ ወደ ምጽዋ በሚወ ስደው መንገድ ላይ ባለችው ጊንዳ ተወልዶ ያደገው ላይኔ ቤተሰቦቹን ተከትሎ መጀመሪያ አው ሮፓ ቀጥሎም ወደ አሜሪካ አቅንቷል። ሙዚቃን የጀመረው ሙዚቀኛ የሆነ ወንድሙን ምሳሌ አድርጎ ነው። ራፕ፣ ሂፕ ሆፕ እና አር ኤንድ ቢ ስልቶችን የሚጫወተው “ብላክ ፉጂቲቭስ” የተ ሰኘ ቡድን አባል ነበር። ከቡድኑ ጋር አሁንም ቢሆን አጋጣሚ ሲያገኝ ይጫወታል።

ፎቶ ራይሞክ ዶት ኮም

3. ላይኔ ታደሰ

“ኤን ጆይ” ሶስት የልጅነት ጓደኛሞች ያቋቋሙት የሙዚቃ ቡድን ነው። ሁለቱ ሩት ሙሴ እና እየሩሳሌም የማነ ኤርትራውያን ሲሆኑ ኤሪና ክሪስቴቫ ደግሞ ከሰርቢያ ነች። እ.ኤ.አ በ2003 ቡድናቸውን የመሰረቱት እነዚህ ወጣቶች ነዋሪነታቸው ያደረጉት ባደጉበ ት ስዊዲን ጎንተንበርግ ነው። በፖፕ እና አር ኤንድ ቢ የሙዚቃ ስልት ዘፈኖችን ይጫወ ታሉ። የመጀመሪያ ነጠላ ዜማቸው የሆነው “ሺዞ” በስዊዲን ተቀባይነት አግኝቷል። በቅ ርቡ የለቀቁት ሌላ ዘፈናቸው የቪዲዮ ክሊፕም በስዊዲን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚታይ ሆኗል። በስዊዲን በሚዘጋጁ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ የሚሳተፉት አነዚህ ወጣቶች በአ ሁኑ ወቅት ሙሉ አልበማቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። “ኤሪ አም ሲስተርስ” እንደ“ዴስቲኒስ ቻይልድ” መሆን ያልማሉ። “ኤን ጆይ” ግን እነ ዴ ስቲኒስ ቻይልድ ወደ ደረሱበት ደረጃ መጠጋታቸውን በ“ኪንግ ሳይዝ” ለተሰኘው መጽ ሔት ሃያሲ የሆነው ካሌ ፍሉር ይመሰክራል። “ስዊዲን የራሷን ዴስቲኒስ ቻይልድ የምታገ ኝበት ጊዜ አሁን ነው” ሲል በሙዚቃ ቡድኑ ተድምሞ ጽፏል።

የሳዶር ሕይወቱ ታሪክ ልብወለድ እንጂ እውነት አይመስልም። በ25 ዓመት ዕድሜው ብ ዙ ነገር አይቷል። ብዙ ነገሮችም ደርሰውበታል። ሳዶር የተወለደው በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ቡልጋሪያ ውስጥ ነው። ገና ጨቅላ እያለ ወላጆቹ ከቡልጋሪያ ወደ ሱዳን እንዲመለሱ ተደረገ። በሰባት ዓመቱ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አሜሪካ ተጓዘ። መቀመጫው ሎስ አንጀለስ ካ ሊፎርኒያ ሆነ። ከአራት ዓመት በኋላ እንደ አርአያ የሚያየው ታላቅ ወንድሙ በጋንግሪን ሲ ሞት የሳዶር ዓለም ተለወጠ። የደረሰበትን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ “ራፕ” ማድረግ ጀመረ። በሙዚቃ ላይ ያተኮረው ሳዶር ትምህርቱን ረሳ። በቤተሰቡም ላይ አመጸ። በአስራ ሁለት ዓመቱም ጎዳና ወጣ። በአስራ ዘጠኝ ዓመቱ በስርቆት ተጠርጥሮ ታሰረ። ወራትን በእስር ቤ ት አሳልፎ በነጻ ተለቀቀ። ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ እስር ቤት ተመለሰ። ከእስር መልስ የመ ጀመሪያ አልበሙን መስራት ጀመረ። ነሐሴ 2008 ግን ህይወቱን ሊያሳጣው ይችል የነበረ አ ደጋ ተከሰተ። ስቱዲዮ ደርሶ ሲመለስ ያገኙት በቡድን የተደራጁ ወጣቶች ጋር በተከሰተ አለ መግባባት በጥይት ይመቱታል። ዘጠኝ ቦታ ተመትቶ፣ ለ26 ቀናት በኮማ ውስጥ ቆይቶ ከሞ ት ተረፈ። ድኖ በተነሳ በሁለት ወር ውስጥ የመጀመሪያ የሙከራ አልበሙን አስቀረጸ። በዚ ህ አልበም ውስጥ ለተካተቱ ዘፈኖች ቪዲዮ ክሊፕም አስቀረጸ። በዘፈኖቹ ውስጥ ኤርትራን የሚያነሳው ሳዶር በተለያዩ መድረኮች እየተገኘ መዝፈኑን ቀጥሏል።

5 ቤቲ ዘረ የ19 ዓመት ወጣት ናት። ተወልዳ ያደገችው በስዊዲን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ውስጥ ነው። ስዊዲን ብትወለድም የሙዚቃ ቋንዋ የጠራ እንግሊዘኛ ነው። ድምጿን እንዳሻት ማዘዝ የምትችለው ቤቲ ከጃዝ እስከ ፊዩዥን ከአር ኤንድ ቢ እስከ ሶል ባሉ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶች ዘፈኖችን ትጫወታለች። “ዩ ቲዩብ” ላይ በራሷ ስም በከፈተችው “ቻናል” ላይ ግን የምትከተለው የሙዚቃ ስልት ፖፕ እንደሆነ ጽፋለች። ለዚህ መጠናከሪያ የሚመስሉ በሁለት እንስት እንግሊዛውያን አቀንቃኞች የተዜሙ ፖፕ ዘፈኖችን መልሳ ስትዘፍን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በ“ቻናሏ” ላይ ጭናለች። የአሁን አያያዟን ያዩ ወደፊት በዚሁ ከቀጠለች ዝነኛ ድምጻዊት ትሆናለች ይላሉ።

ፎቶ- ዩ ቲዩብ

2. ኤን ጆይ

ፎቶ- ከሳዶር ዌብሳይት

ፎቶ- ከኤን ጆይ ዌብሳይት

4. ሳዶር ፍስሃዬ(ሳንድማን ንጉስ)


ሐበሻዊ ቃና

12

ጥበብ

ኤፍሬም እና ጎሳዬ በአንድ መድረክ ሊዘፍኑ ነው

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የካምፓላው ሲኒፕሌክስ በ“ስሪ ዲ” ፊልም ማሳየት ሊጀምር ነው

ፎቶ- ማሲንቆ ኢንተርቴይመንት

ሁለቱም በየራሳቸው ቁጥሩ የበዛ አድናቂዎች አሏቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ በዘፈን የተጣመሩት የ አብርሃም ወልዴ ተከታታይ ስራ በሆነው “ባላገሩ” ነው። ይሄው ዘፈናቸው በብዙዎች ዘንድ ተወ ዶላቸዋል። አሁን ደግሞ መድረክ ተጋርተው ተወዳጅ ዘፈናቸውን ሊያቀንቅኑ ቀን ተቆርጦላቸዋ ል። ቦታው አሜሪካ ነው። አትላንታ። ቀኑ ደግሞ አሜሪካኖች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዋዜማ እሁድ ሰኔ 26።

አትላንታ ዘንድሮ በየዓመቱ የሚከበረውን የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር አዘጋጅ መሆኑ ን ተከትሎ ነው የኤፍሬም ታምሩ እና ጎሳዬ ተስፋዬ የሙዚቃ ድግስ የተሰናዳው። በሰሜን አሜሪ ካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ለ28ኛ ጊዜ በሚዘጋጀው በዚህ የስፖርት እና ባህል ዝ ግጅት ላይ ወደ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዓመታዊው ዝግጅት ላይ ሙዚቃቸውን እንዲያቀርቡ የሚጋበዙ ድምጻውያን ወቅታዊ ዝናቸው ከፍ ያለ አሊያም የምንግዜ ም ተወዳጅ የሆኑ ዘፋኞች ናቸው። ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ መሐሙድ አህ መድ በክብር እንግድነት እንዲገኝ ተጋብዟል። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት እና በአሁኑ ጊዜ ለትምህር ት አሜሪካ የሚገኙት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳም ከተጋበዙ እንግዶች መካከል አንዷ ናቸው።

የግጥም ጥግ

ምፓላ ጋርደን ሲቲ ውስጥ የሚገኘው “ሲኒፕሌክስ” ለሲኒማ አፍቃሪያን ሁለት አ ስደሳች ዜናዎች ይዞ መጥቷል። የመጀመሪያው መንትያውን ከጋርደን ሲቲ አጠ ገብ በሚገኘው “ናኩማት ሆል” ውስጥ ሊከፍት መሆኑ ነው። ሁለተኛው አዲሱ ሲኒማ በ“ስሪ ዲ” የፊልም ቴክኖሎጂ የተሰሩ ፊልሞች ማሳየት እንሚጀምር ማሳወቁ ነው። አዲሱ ሲኒማ ቤት አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ከወር በኋላ እንደሆነ የ“ሲኒፕሌክስ” የማርኬቲንግ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ሚስስ ዲዛየር ባርጋሃሪ ለሐበሻዊ ቃና ገልጸዋል። ድርጅ ታቸው ሶስት የፊልም ማሳያ አዳራሾች ያሉትን አዲሱን ሲኒማ ቤት በይፋ ሊከፍት ያሰበው በዚህ ወር ቢሆንም በ “ስሪ ዲ” የተሰሩ ፊልሞችን ከማስመጣት ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክ ንያት በአንድ ወር ለማዘግየት መገደዱን ተናግረዋል። የ“ናኩማቱ” አዲስ ሲኒማ ቤት ሶስት የፊልም ማሳያ አዳራሾች ይኖሩታል። ከአዳራሾቹ ት ልቁ 200 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን አነስተኛው 168 አሉት። መሀከለኛ የሚባለው ደግሞ 180 ሰዎችን ይይዛል። አሁን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው 185፣ 140፣ 135 እና 85 ተመል ካቾች የማስተናገድ አቅም ያላቸው አራት አዳራሾች አሉት። በአዲሱ ሲኒማ ቤት ከ “ስሪ ዲ” ባሻገር በ“ሃይ ዴፍኔሽን” የተሰሩ ፊልሞችም ይታያሉ። “ስሪ ዲ” ስሪ ዳይሜንሽናል የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃላቶች አሳጥሮ ለመጥራት የሚውል ነው። ስያሜው በፊልም ቴክኖሎጂ ፊልሞችን በከፍተኛ ጥራት ከመቅረጽ እና ማሳየት ጋር የተያ ያዘ ትርጓሜን ይሰጣል። ከዚህ ቀደም በሲኒማ ቤቶች የሚታዩት ፊልሞች በ“ቱ ዳይሜንሽና ል” የተቀረጹ ብቻ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የ“ስሪ ዲ” ፊልሞችን መመልከት ተ ጀምሯል። በ“ስሪ ዲ” የተቀረጹ ፊልሞችን በሰኒማ ቤት ለመመልከት ለዚሁ ቴክኖሎጂ ተብ ሎ የተሰራ መነጽር ያስፈልጋል። የ“ስሪ ዲ” ፊልሞችን በባዶ ዓይን ሲመለከቷቸው ደብዛዛ እ ና ጥራት የለሽ ይመስላሉ። ይህንን ቴክኖሎጂ ጎረቤት ሀገር ኬንያ፣ ታንዛንያ እና ኢትዮጵያ መጠቀም ከጀመሩ ሰነበ ቱ። ኡጋንዳን ከእነዚህ ሀገራት ተርታ ጋር ያሰለፋት “ሲኒፕሌክስ” ለእነዚህ ፊልሞች መመል ከቻ የሚጠይቀው ዋጋ አሁን ፊልሞች እየታዩበት ካለው ዋጋ በእጥፍ ገደማ ይጨምራል። “ስሪ ዲ”ን ፊልሞችን ለመመልከት 30 ሺህ የኡጋንዳ ሽልንግ መክፈል ግድ ይላል።

ዝምተኛ ልቦች የተመረኮዙት ልብ ታጥፎባቸው ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?

ጌትነት እንየው u

አለማልቀስ ነው ጭንቁ አለማሳቅ አኮ ይቻላል- አለማልቀስ ነው ጭንቁ፤ የመንፈስን እንጉርጉሮ-በመንፈስ አምባ ማመቁ፣ ውስጥ ውስጡን እየደሙ-በቀቢጸ ተስፋ መድቀቁ፣ ለተስለመለመች እውነት-የደም ደብዳቤ ማርቀቁ፣ በቅሬታ ሰደድ እሳት-ህዋሳትን መጨፍለቁ፣ አለመሳቅ እኮ ይቻላል-አለማልቀስ ነው ጭንቁ።

ደበበ ሰይፉ u

ፎቶ- ሮዝ መጽሔት

ረጀ ኃይሌ፣ የ“ወንዶች ጉዳዩ” ዘሪሁን አስማማው፣ በ“ተጨቆ ኑ ቀልዶች” ላይ የምናውቀው ወንድወሰን ብርሃኑ፣ “አያስቅም” ላይ ከደረጀ ጋር የምናየው ፍቃዱ ከበደ እና “ፈንጂ ወረዳ” ላ ይ ያስፈገገን ዩሀንስ ተፈራ እና ሌሎችም በፊልሙ ላይ ከስብሐ ት ጎን ይተውናሉ። የፊልሙ አዘጋጆች ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠር ተው ነበር። ፊልሙን ሊያስተዋውቁ። አዘጋጆቹ የፊልሙን መ መረቂያ ትክክለኛ መናገር ተስኗቸዋል። ምናልባት እሁድ ሰኔ 19 ቀን ሊመረቅ ይችላል ባይ ናቸው። ስለ ፊልሙ ታሪክም ከም ረቃው በፊት አንናገርም ብለዋል። በማስተዋወቂያው ላይ የተ ገኘ አንድ ጋዜጠኛ ለ“ሐበሻዊ ቃና” እንደተናገረው ፊልሙ በኮ ሜዲ ዘውግ የተሰራ ሆኖ ሴቶች የወንዶችን ቦታ ይዘው የሚታ ዩበት ነው። በሴቶች ላይ ጥቃት እና ጭቆና ያደርሳሉ የሚባሉት ወንዶች በተገላቢጦሽ ምን እንደሚሆኑ የሚያሳይ ነው ብሏል።

“ህመሜ” የተሰኘ ጥሩ ነጠላ ዜማ የሰራችውና የአንድ ወቅት የኮራ ተሸላሚ የነበረችው ድምፃዊት ፀደኒያ ሰሞኑን መንታ ወንድ ልጆችን ተገላግላለች፡ ፡ ፀደኒያ መንታ እንደምትወልድ ቀደም ብሎ ትገምት እንደነበረ ለኢትዮፒካሊንክ መናገሯን ጠቅሶ አዲስ ነገር ኦንላይን ዘግቧል፡፡ የዚህም ምክንያቱ በቤተሰባቸው ብዙ መንትዮዎች በመኖራቸው ነው፡፡ በእርሷ ቤተሰብ ውስጥ ቀደም ብሎ ሁለት መንታ ታናናሾችና ሁለት መንታ ታላላቆች የነበሯት ሲሆን የርሷን መንታዎች ጨምሮ ቤተሰቡ ውስጥ በጠቅላላው ስድስት መንታዎች ይገኛሉ፡፡

ድምጻዊት ፀደኒያ ገ/ማርቆስ መንታ ወለደች

u

u

u

ምን አገባኝ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሀረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ የሚል ግጥም ልጽፍ ልቤ ተነሳና ምን አገባኝ ብዬ ተውኩት እንደገና።

ኑረዲን ኢሳ u

u

u

ሲያልፍ የንጋቱ ዜማ፤ የአባባ የእማማ በዘመኑ እርሾ ፣ተጋግሮ ተቦክቶ ከህሊናሽ ጓሮ ቃልሽ ተፈብርኮ፣ የማይጠገበው የጥንቱ ቀረርቶ እንደ አላዝኝ ውሻ፣ ወፍሮ ጎርንቶ ሰማሁ ከድምጽሽ ውስጥ፤ሙዚቃ ሸብቶ።

ግርማ ተስፋው u

u

u

አስተያየት

ፎቶ-ዮርክ ታይለር

ፎቶ- ሰሎሞን ሹምዬ

ሰውዬው የማይገባበት የሙያ ዘርፍ ያለ አይመስልም። ኤሌ ክትሪሽያን ነበር፣ የባንክ ባለሙያ ሆኖ ሰርቷል፣ አስተማሪም ነ ው። “እጄን ሰጥቼያለሁ” የተሰኘ ሙሉ የሙዚቃ አልበም በራ ሱ አቀንቃኝት ሰርቷል። ገጣሚ ነው። የልቦለድ መጽሐፍም አ ሳትሟል። በንግዱ ዘርፍም ሁለት ሶስት ነገር ሞክሯል። የባህላ ዊ ጌጣ ጌጦች እና አልባሳት መሸጫ ሱቆች ነበሩት። ወደ ምግ ብ እና መጠጥ ሽያጭ ገብቶም ምግብ ቤት ከፍቶ ነበር። ሚሊ ዮኖች የሚያውቁት ግን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበ ረው “ሻይ ቡና” በተሰኘው የቲቪ ቶክ ሾው አዘጋጅነቱ ነው። ሰ ሎሞን ወደ ቲቪ የመጣው “ውሎ” የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪ ዥን ዶክመንተሪ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ ነበር። “ሻይ ቡና” ሲቋረጥ ፊቱን ወደ ሬድዮ አዞረ። የአየር ሰዓት ገዝ ቶ የራሱን ፕሮግራሞች ያቀርብ ገባ። በእርሱም ብዙ አልዘለቀ ም። ለማቋረጥ ተገደደ። የቲቪ እና የሬድዮ ፕሮግራሞቹን የሚ ሰራለትን “ገበያኑ ፕሮዳክሽን” የተሰኘ የራሱን ድርጅት ተጠቅ ሞ ማስታወቂያ መስራት ቀጠለ። አሁን ደግሞ ወደ ፊልም አለ ም መጥቷል። የፊልሙ ርዕስ “የተሳሳተ ጥሪ” ይሰኛል። በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ማለፉ በፊልም ስራ ውስጥ እንደጠ ቀመው ለሐበሻዊ ቃና በስልክ ከአዲስ አበባ የገለጸው ሰሎሞን “ፊልም የቴክኒካል ዕውቀት ይፈልጋል” ይላል። የፊልሙ ዘው ግ “የፍቅር” እንደሆነ ከመናገር ውጭ ቅንጭብ ታሪኩን ለመና ገር ያልፈቀደው ሰሎሞን አንድ ሰዓት ከ45 ደቂቃ የሚፈጀውን ፊልም ለመስራት አንድ ዓመት ገደማ እንደፈጀበት ይናገራል። ከዚህ ጊዜ ውስጥ ግማሹን የሰጠው ለፊልም ስራ የመለመላቸ ውን ተዋንያን ሲያሰለጥን እንደነበር ይገልጻል። ከችሮታው ከል ካይ ሌላ በፊልሙ ውስጥ የተሳተፉት ሁሉም ተዋንያን “አዳዲ ስ” እንደሆኑ ያስረዳል። በፊልሙ ውስጥ ጎላ ያለ ሚና ያላቸው ተዋንያን 15 ይደርሳል። አዲስ አበባ፣ ሞጆ፣ ላንጋኖ እና ወሊሶ ቀረጻው የተከናወነው ይህ ፊልም በቀጣዩ ሐምሌ ወር ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

u

ንብ ኑሮ ለውጣ መብከንከንን መርጣ ቀዬዋን ቀየረች አበባ መቅሰምን ርግፍ አርጋ ተወች። ጣፋጭ ወለላዋን ማመንጨቷን ትታ በየጉራንጉሩ ለከንቱ አዳር ውሎ ከዝንብ ተጋፍታ ለውሽልሽል ኑሮ ማስና ዋትታ ዋትታ ስኳር ትልሳለች ብርጭቆ ውስጥ ገብታ። ግርማ ተስፋው u

የ“ሻይ ቡናው” ሰሎሞን ሹምዬ ፊልም ሰራ

u

ለውጥ

ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚያብሔር ፊልም ላይ ተወነ

ሰሞኑን ከሀገር ቤት ስለ ስብሐት ገብረ እግዚያብሔር የሚ ሰሙ ዜናዎች ጥሩ አልነበሩም። የ75ኛ ዓመትልደት በዓሉን አራት ሰዎች ብቻ በተገኙበት ማክበሩ በሬድዬ ተነገረ። በዓ ል ላይ ከዓመታት በፊት ያገባት እና ከእርሱ በእድሜ በሶስ ት እጥፍ የምታንሰው ባለቤቱ አለመገኘቷም አነጋጋሪ ነበር። ጥቂት ቆየት ብሎ ደግሞ “ዛዚ” የተባለ መጽሐፍ ከፈረንሳይ ኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ መጽሐፉ ታትሞ ገበያ ላይ ከዋለ በ ኋላ ሊከፈለኝ ይገባ የነበረውን 55 ሺህ ብር ተከለከልኩ ብ ሎ ጋዜጣ ላይ ወጣ። ከሚቀጥሉት ሳምንታት በኋላ ግን የስ ብሐትን ስም የምንሰማው በትወና ብቃቱ ወይም ቀሽምነቱ ሊሆን ከሚሰጡ አስተያየቶች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል። ስብሐትን ወደ ትወና መድረክ ያመጣው “መፈንቅለ ሴቶ ች” የተሰኘው ፊልም ነው። ፊልሙ በሀገሪቱ ውስጥ በአሁ ኑ ወቅት “አሉ” የተባሉ ኮሜዲያን የተሰባሰቡበት ነው። ደ

u

‹‹ዓለም ጨለማ ነው፤ ቀለም አልባ ሕይወት ብርሃን የጠፋው፤ ደስ የማይል ቅዠት›› እያሉ ሲነግሩኝ፤ እኔም ጨለማ አየሁ የእኔን ዓይን ትቼ፤ በእነርሱ ስላየሁ፡፡ የእነርሱን ተውኩና፤ በእኔ ዓይን ሳያት፤ ዓለም የእኔን ብርሃን፤ ለብሳ አገኘኋት፤ ስለዚህ ወደድኳት፤ ሳያት እኔን መስላ፤ ከራሴ ነጥዬ፤ እንዴት እኔን ልጥላ፡፡ ናኦድ ቤተሥላሴ ሲልቨር ስፕሪንግ-ሜሪ ላንድ የካቲት 06 2011


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

13

ጥበብ ሰሞነኛ ፊልሞች ያ ልጅ ተዋንያን፦ ማክዳ አፈወርቅ፣ ሃኒባል አበራ፣ ሚካኤል ታምሩ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ እና ሌሎችም ዳይሬክተር፦ በሀይሉ ዋሴ የፊልሙ ዘውግ፦ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ41 ደቂቃ

ፎቶዎች- “ክፍል 3” ኦፌሲሊያዊ ማስታወቂያ

የቀድሞዋ ሚስ ኢትዮጵያ ሳያት አዲስ አልበም አወጣች በተስፋለም ወልደየስ ሐበሻዊ ቃና

ሰባት ዓመት በፊት በተካሄ ደ የቁንጅና ውድድር “ሚስ ኢትዮጵያ” የሚለውን ማዕ ረግ የተጎናጸፈችው ሳያት ደ ምሴ የመጀመሪያዋ የሆነው ን የሙዚቃ አልበም ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ለገበያ አብቅታለች። የሳያት የሙዚቃ አልበም 13 ዘፈኖችን ያካተ ተ ሲሆን በናሆም ሪከርድስ ፕሮዲዩሰርነት እ ና አከፋፋይነት ሰኔ 8 ቀን 2003 ዓ.ም በኢት ዮጵያ ገበያ ላይ ውሏል። ሳያት አልበሟን “ክ ፍል 3” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች። “በክፍል 3 አልበም ውስጥ የተካተቱት አብዛ ኛዎቹ ዘፈኖች በውሎዬ፣ ባሰለፍኩት የሕይወ ት ተሞክሮዬ፣ አዳዲስ ሰዎችን ስተዋወቅ፣ በ ስራ ምክንያት ወደ ተለያዩ ክፍለ ሀገሮች ስጓ ዝ ያየኋቸው፣ የሰሟኋቸው እና ያስተዋልኳቸ ው ነገሮች ናቸው። እናም ከዘፈኖቹ ውስጥ ከ እያንዳንዳችሁ ህይወት ጋር የሚመሳሰል ታሪ ክ ታገኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለ ች ሳያት በአልበሟ የውስጥ ሽፋን ላይ ባሳፈረ ችው መልዕክት። “እጅግ የምወደውን ስራ እየሰራሁ እንድኖር የሆነው በእናንተ በስራዬ ወዳጆች ምክንያት ነ ውና እጅግ አመሰግናለሁ” ስትል ለአድናቂዎ ቿም ምስጋና አቅርባለች። ሳያት “የምወደውን ስራ” ስትል የገለጸችውን ድምጻዊነትን የጀመ ረችው በቁንጅና ውድድር ካሸነፈች ከአራት አመት በኋላ ነው። በእነዚህ አራት አመታት ከሞዴሊንግ እስከ ፊልም ትወና ያሉ ዘርፎች ላይ ተሳትፋለች።

የቀች ጊዜ የመለሰችው መልስ ነበር። እንኳን እርሷ አካል ጉዳተኞችም ያለጭንቀት እየኖሩ እንደሆነ መናገሯ በአንዳንድ አካል ጉዳተኞች አልተወደደላትም። ይህንኑ አስመልክቶ ለሚ ዲያዎች መግለጫ የሰጡ አካል ጉዳተኞች “በ ይፋ ይቅርታ ልትጠይቀን ይገባል” እስከማለ ት ሄደው ነበር።

እየተወኑ መዝፈን በስተኋላ ላይ ጉዳዩን ለማስተባበል የሞከረ ችው ሳያት ድምጿን አጥፍታ ከርማ ወደ ሚ ዲያ ዳግም ብቅ ያለችው በነጠላ ዜማ ስራዋ ነ በር። ነጠላ ዜማውን የሰራችው “ተው ማነህ” የተሰኘውን የህዝብ ዘፈን ከራሷ ግጥምና ዜማ ጋር በማዋህድ ነበር። ዘፈኑ በኤፍ. ኤም ጣቢ ያዎች በተደጋጋሚ የሚደመጥ ሆነ። ወዲያው ኑ የተለቀቀው የዘፈኑ ቪዲዮ ክሊፕ ደግሞ የ “ተው ማነህ”ን ተወዳጅነት ጨመረው። መዝፈን እንደምትችል በዚህ ነጠላ ዜማዋ ያ ስመሰከረችው ሳያት ሌላ ተደግማለች ተብላ ስትጠበቅ ፊቷን ወደ ፊልም አዙሯ ክሌቱ አ ለች። ሳያት ዳግም ወደ ነጩ አቡጀዲ የመጣ ችው ከሁለት ዓመት በፊት በሰራቸው “ስላን ቺ” ፊልም ነው። አስቂኝ የፍቅር ፊልም በሆነ ው “ስላንቺ” ላይ ሳያት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆና ትጫወታለች። በፊልሙ ላይ የነበራትም ድርሻ የረዳት ተዋናይነት ሚና ነበር። ይህ ፊ ልም በአራተኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ ሶስት ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ሳያትም በረዳት ተዋናይነት ዘርፍ እን ድትታጭ አድርጓታል። የዛሬ ዓመት ያመለጣትን ይህን ሽልማት በሶ ስተኛ ፊልሟ በዚህ ዓመት አግኝታዋለች። ለ ሽልማት ያበቃት ፊልም “ላውንደሪ ቦይ” የሚ

የ“ክፍል 3” አልበም ሽፋን

ሰኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ለህዝብ እየታየ ይገኛል። ሳያት እንደተለመደው በዚህ ፊልም ላይም የተሰጣ ት ገጸ ባህሪይ የአፍቃሪ ረዳት ተዋናይነት ድ ርሻ ነበር። ሳያት ለዚህ ፊልም የማጀቢያ ሙ ዚቃም ሰርታለች። ማጀቢያ ሙዚቃው “ከእኔ ጋር ነው” የሚሰኝ ሲሆን ከፊልሙ የተቀነጨ ቡ ትዕይንቶች የተካተቱበት ቪዲዮ ክሊፕም ተሰርቶለታል።

ክፍል ሶስት አሁን ሳያት የሰራቻቸውን ፊልሞች ቁጥር ሶ ስት አድርሳለች። ነጠላ ዜማዋቿም ሁለት ሆነ ዋል። በሙሉ የሙዚቃ አልበሟ ደግሞ ሰልሳ ለች። ክፍል ሶስት። ሳያት በ “ክፍል ሶስት” አ ልበሟ እንደ “ተው ማነህ” ሁሉ የህዝብ ዘፈን የሆነውን “መላ መላ” ተጫውታለች። ይህንን ም በአልበሟ ዕውቅና ሰጥታለች። “መላ መ ላ”ን ከዚህ ቀደም ጠላላ ከበደ፣ አስናቀች ወር ቁ፣ ሰይፉ ዩ ሐንስ እና መሀሙድ አህመድ እና ሌሎችም ዘፋኞች መጫወታቸውን ሳያት በአ ልበሟ የውስጥ ሽፋን ላይ በጉልህ አስቀምጣ

ለች። ይህንን ዘፈን መታሰቢያነቱን “ለቀደሙ ት ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች” ይሁንልኝም ብ ላለች። በዚህ ዘፈን ላይ ማሲንቆን አካታለች። እንደማሲንቆ ሁሉ ክራርንም “አያሳስበኝም” በሚለው ዘፈኗ ተጠቅማለች። ማሲንቆውን የተጫወተላት አስራት ቦሰና ሲ ሆን ክራሩን የገረፈላት ደግሞ ታመነ መኮንን ነው። ወንድሜነህ ሲሳይ የሳያትን አስራ ሶሰት ዘፈኖች የማቀናበር ኃላፊነት ተወጥቷል። ሳያ ት አብራቸው የሰራቻቸውን ባለሙያዎች በአ ልበሟ ጠቅሳ ብታመሰግንም የዘፈን ግጥሞቿ ን እና ዜማዎቿን እራሷ ትሆን ሌላ ሰው ያዘ ጋጀላት በገልጽ አታብራራም። “ሀሳብን መስ ረቅ”፣ “ምን ተሻለው” እና “እኔ መረጥኩ” የ ተሰኙት ግጥሞቿ የተጻፉት በራሷ ነው። “የ ኔ ቤት” የሚለውን ዘፈን ኪሩቤል ከሚባል ሰ ው ጋር በጋራ እንደሰራች ገልጻ “ምልክት ስጠ ኝ” እና “እኔ ጋር ነው” ከሚሉት ዘፈኖቿ አጠገ ብ ምንም ሳታስቀምጥ ታልፋለች። “ታውቃለ ህ”፣ “መርማሪ” እና “ሴትነት” የተሰኙት ዘፈኖ ቿም ማን እንደጻፋቸው እና ማን ዜማቸውን እንደደረሰው መረጃው አልተጻፈም። ፈጠን ያሉ ምቶች ያሉባቸውን ዘፈኖች የሚ በዙበት የሳያት አልበም ለአድማጭ ጆሮ መ ድረስ ለቀዘቀዘው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢን ዱስትሪ አነቃቂ ይመስላል። በዚህ ዓመት አ ልበሞቻቸውን ለገበያ አብቅተው የሙዚቃው ን መንደር ነቃ ነቃ ካደረጉ እንስት ድምጻውያ ን ዘንድም ተሰልፋለች። ቀጣዩ ጥያቄ የአልበ ሟ ተወዳጅነት የትኛዋ ድምጻዊት ጋር ይስተ ካከላል የሚል ይሆናል። ከአስቴር አወቀ፣ ሄ ለን በርሄ፣ ትዕግስት ወይሶ ወይስ ፍቅረ አዲ ስ ነቃ ጥበብ?።

አወዛጋቢዋ ሳያት ሳያት በፊልም ብቅ ያለችው ከአራት አመት በፊት ለዕይታ በበቃው “ሳራ” ፊልም ላይ ነበ ር። የጥላሁን ጉግሳ ባለቤት በሆነችው የ“ሳ ራ” ፊልም ዳይሬክተር ሄለን ታደሰ አማካኝነ ት ነበር በዚህ ፊልም ላይ ለመሳተፍ የበቃች ው። ሳያት በዚህ ፊልም ላይ እናቷ ከሞተች በ ኋላ በእንጀራ አባቷ አስገድዶ መድፈር የተፈ ጸመባት ወጣት ሆና ትተውናለች። ይህ የአስ ገድዶ መድፈር ታሪክ በእውነተኛ ህይወቷ እ ንደደረሰባትም በአንድ ወቅት ለ“ኢትዮፒካሊ ንክ” የሬድዬ ፕሮግራም አዘጋጆች ተናግራ ነበ ር። ሳያት ተማሪ በነበርኩበት ወቅት ነው ተገ ድጄ የተደፈርኩት ብላለች። የቴሌቪዥን ቶክሾው አዘጋጅ የመሆን ሀሳብ የነበራት ሳያት በዚያው ፕሮግራም ላይ በተና ገረችው አባባል አካል ጉዳተኞችን አስቆጥታለ ች በመባሏ ሳይሳካለት ቀርቷል። ውዝግቡን ያ ስነሳው አስገድዶ መድፈር ያደረሰባትን የህሊ ና መረበሽ እንዴት እንደተቋቋመችው በተጠ

ሳያት በአዲሱ አልበም ከተካተቱት ዘፈኖች አንዱን መርጣ የቪዲዮ ክሊፕ ሰርታለታለች

ኤፍሬም ኮምፒዩተሮችን በቋንቋቸው “የሚያናግር” የሶፍት ዌር ባለሙያ ነው። በማህበራዊ ህይወቱ ግን ሴት ልጅን ማናገር የሚፈራ አይናፋር ነው። ለቤተሰቦቹ ብቸኛ በመሆኑ ደግሞ “አግብተህ ወጋችንን” አሳየን የሚለው የዘወትር ጎትጎታቸው ረፍት ነስተውታል። በሌላ በኩል ከኤፍሬም ጋር የልጅነት ታሪክ የምትጋራው ሐና በሚሰራበት መስሪያ ቤት ባልደረባው ሆናለች። የልጅነት ትዝታ የሚወዘውዛት ሐና ኤፍሬምን አፍቅራዋለች። ኤፍሬምስ ለሐና ፍቅር እና ለቤተሰቦቹ ውትወታ ምላሽ ይሰጥ ይሆን? ፊልሙ ምላሽ አለው።

እቴጌ ቁ.2 ተዋንያን፦ ሰይፈ አርአያ፣ ሚካኤል ሚሊዮን፣ ቶማስ ቶራ እና ሌሎችም ዳይሬክተር፦ አብይ ፈንታ የፊልሙ ዘውግ፦ ድራማቲክ ኮሜዲ የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ

“እቴጌ” በሚል ስያሜ ከአመታት በፊት የተሰራው ፊልም ለጣቂ እንደሆነ ቁጥር 2 በሚለው ቅጽሉ ያስተዋውቃል ። በፊልሙ ላይ አዲስ የተሰኘው ገጸ ባህሪይ ከሶሰት ጓደኞቹ ጋር “ታላቅ” የሆነ ዘመቻ ሲያካሂድ ይታያል። ዘመቻው ድንግል ሴት ፍለጋ ነው። ድንግል ለመፈለግ ደግሞ ሆነኛ ቦታ ነው ብለው ያሰቡት ወደ ገጠር መጓዝ ነበር። እናም አደረጉት። “የተቀደሰ” በተባለው ዘመቻቸው የሚያጋጥማቸውን ፊልሙ ያሳያል።

አባይ ወይስ ቬጋስ ተዋንያን፦ ቴዎድሮስ ተሾመ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ብሌን ማሞ፣ ግሩም ኤርሚያስ እና ሌሎችም ዳይሬክተር፦ ቴዎድሮስ ተሾመ የፊልሙ ዘውግ፦ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 2 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ በአሜሪካ ላስ ቬጋስ የሚኖረው ሳልሳዊ የራሱ ድርጅት ያለው እና ለቁማር ጨዋታ የሚያጠፋው ብር የተረፈው ነው። ያያትን ሴት ሁሉ አትለፈኝ የሚል ጸባይ ያለው ሳልሳዊ ከነጭ እስከ ጥቁር ሁሉንም ሞክሯል። ሆኖም ልቡ የምታሸፍተው ማግኘት አልቻለም። ለስራ ወደ ሀገሩ በተመለሰበት ወቅት ባህር ዳር ላይ መና የተሰኘች ቆንጆ ይተዋወቃል። ባረፈበት ሆቴል አስተናጋጅ የነበረችው መና ከሳልሳዊ ጋር ለመወዳጀት ጊዜ አልፈጀባትም። የሁሌም ህልሟ እና ጥረቷ የሆነውን ወደ አሜሪካ መጓዝ በሳልሳዊ በኩል እንደምታሳካ አልተጠራጠረችም። ለራሷ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልግው የአይነ ስውሩ ወንድሟ አደራ አለባት። ከሳልሳዊ ጋብቻ ፈጽማ ወደ አሜሪካ የምትጓዝበትን ቀን ስትቆጥር ንጉስ ከሚባል ገበሬ ጋር አባይ ፏፏቴ አካባቢ ትተዋወቃለች። መና በቆፍጣናው ንጉስ ፍቅር ትወድቃለች። ይሄኔ የአሜሪካ ጉዞ ይመጣል። ፊልሙ የመናን አጣብቂኝ እና የሳልሳዊን የአሜሪካ ብልጭልጭ የአሜሪካ ኑሮ እያፈራረቀ ያሳያል። ይህ ፊልም ቀረጻው የተከናወነው በላስ ቬጋስ፣ ባህር ዳር እና አዲስ አበባ ነው።


ሐበሻዊ ቃና

14

ትረካ

አገሬ መውጣት አስ ቤ አላውቅም። ዓለ ምን የማውቃት በት ምህርት ቤት ጂኦግ ራፊ እንጂ በምኞቴ አልነበረም። እዛ ጋ አውሮፓ አለ። እ ዚያ ጋ እስያ አለ። እዛ ጋ አውስትራል ያ አለ። በቃ። እዛ ጋ ቻይናና ሕንድ አ ሉ። ምን ይጠበስ? ሰው ደሞ ሲኖር በሶስት የጊዜ ክፍፍ ል ውስጥ ነው። እነዚህ መስማማት አ ለባቸው። የመጀመሪያው ሃላፊ ጊዜ ነ ው፡ ያለፈው ታሪኩ። ሁለተኛው ዛሬ ነው፡ አሁን። ሶስተኛው ትንቢት ነው፡ ነገ ከነገወዲያ ከዚያ ወዲያ ብቻ ቀመሩ ባይረጋገጥም፣ ባይደረስበትም። ያለፈ ው ዘመኔ መልካም ነበር። ፖለቲከኞች ልምዴ ውስጥ ገብተው እሱን እንዲመ ዝኑልኝ አልፈልግም። ዛሬ ባይከፋም ከዛሬ ነገን አጮልቄ የማይበት ቀዳዳ አ ልነበረኝም። ዕውቀት እንደማለት። ማ ንስ ይችላል? ‘ነገ እንዲህ ይሆናል’ ቢ ሏችሁ ተጠራጠሩ። የታሪክ ስሌት እና ውቃለን የሚሉ ነጋ ጠባ ቢዘባርቁም፣ የነገ ሂሳብ የሚወራረደው ዛሬ ነው። ‘የትኛውም ባዕድ አገር ከእኔ አገር ይ ሻላል’ ሲባል ምኞቱና ትንቢቱ ነው። ምክንያቱም እነሱና ሌሎቹ ሁሉ፣ ኸረ ማንም ሳይቀር እነዛ ባዕድ አገሮች ወደ ፊት ሄደዋል ይሉናል። እኔም እላለሁ፡ ባቡሩን፣ አይሮፕላኑን ምኑን መስራት አልመን ያልቻልንበት አይደል። ኮምፒ ዩተሩ ምኑ። ይሄ ሁሉ ትንቢት ነው። አላማረብንም እንጂ…..አልቻልንበትም እንጂ…ወደ ሄዱበት እንሂድ ብለን አይ ደል የምንነካከሰው…….. ስለሰለጠኑት ባዕድ አገሮች መጥፎ ነ ገር ሰምቼ አላውቅም። ለምሳሌ ስለ አ ሜሪካ የምሰማው ነገር ሁሌ መልካም ነው። ሀብታቸውና ዲሞክራሲው ሞ ልቶባቸው ገንፍሎ ወደ አፍሪካ እየፈሰ ሰ ይሄም ይሰፋና ‘ልግባ ልግባ’ የሚለ ው ለዚህ ነው ይላሉ። ነጻነት በሽበሽ ነ ው ይሉናል። ይኼን ሁሉ አምናለሁ። አለነገር ሀይለኛ ሆኑ? አለነገርስ እኛ ቂ ጣ ለማኝ ሆንን? ታድያ የልጅነት ወዳጄ መቅደስ መጥ ታ ተጋብተን ኔዘርላንድ ደንሀግ እንግባ ስትለኝ ተደሰትኩ። መቅደስ ከስንትስ አመታት በፊት ለሶስት አመታት ያህል ሴት ጓደኛዬ ነበረች። መቼም የአዲስባን መሿለኪያ ያወቀ አይከራከረኝም። ብኩን ነበርኩና ለክ ፉ ጊዜ የሚሆን ጥሪት አላስቀመጥኩ ም። ያን ማንም ያውቃል። በዙን የሚ ያውቅ። ‘በዝሽ’ ነበር የምባለው። ባን ኮኒ ተደግፌ መንጌን ማማትእንጂ ምን ይመጣልን አላሰብኩም። ቢያንስ ቢያ ንስ ጫቱ ጥርሴን ብቻ ሳይሆን የፊቴን ቆዳ አረንጓዴ ሳያደርገው መቅረቱ ተአ ብ ነው። የሲዳሞን ጨንጌ ሳላምግ አ ወራርጄአለሁ፣ በለጬና አወዳይ ጭ ኔ ላይ አስቀምጬ መልካም ያልተከለ ከለ ቅዠት ስቤአለሁ። ሉሉ ባዳከመ ው ወንድነቴ ሰንጋ ተራ ናዝሬት ባር ተ ደፍቼአለሁ። ታዲያ ይህም እንዳነሰኝ ሁሉ ከምሰራበት የአዲስባ ማዘጋጃ ቤ ት ከስራ ተባረርኩ። ጨካኝ የሚያደር ግ ጊዜ ነበር። ወደ ውጭ ለመሄድ የተ መኘሁትም ይኼኔ ነው። ከልቤ ተመ ኘሁት። እንደ ብዙዎቹ ግን ወደ ጉረ ቤት ሀገር ለመሰደድ ሐሞቱ አልነበረ ኝም። ምናልባት ችግሬ ጥልቅ ስላልሆ ነ ይሆናል። አልወለድኩም፣ አልተሳል ኩም። በዚያ ዘመን ድብርትና ወጣ ገ ባ አብሮ አደጌ የክፍሉ ሚስት አለምጸ ሐይ ነበረች ደግፋ የያዘችኝ። ገንዘብ ሲቸግረኝ፣ ስራ ፍለጋ ስማስን ለአው ቶብስና ለቡና እያለች ትረዳኝ ነበር። ችግር እያነጫነጨኝና እያነደደኝ እያለ መቅደስ መጣች። መቅደስ ለረዥም ጊዜ ፍቅረኛዬ የነበ ረች፣ በድንገት አገር አስጠላኝ ብላ (ም ናልባት እኔ ሳልሆን አልቀረም ያስጠለ

ኋት) ከቸገር የወጣች ልጅ ናት። እስከዛ ሬ የምጠላው ቃል ‘ፕሮሰስ’ የሚባል ነ ው። ትታኝ እንደምትሄድ እያወቅሁ ኢ ሚግሬሽን ድረስ በየሳምንቱ ወይም በየ ቀኑ ‘ፕሮሰስ’ እንድታደርግ አጅባት ነበ ር። መንገድ እንዲሳካላት ምናልባት ያን ሰሞን የደርግ ባለስልጣን ወይም አንዱን እዚያ የሚሰራ ወይም ስለዚህ ነገር የሚ ያውቅ ሌላ ወንድ ሳታወጣ አልቀረም። ግን የሰውን እግር ማሰር አይቻልም። ከ ሸኘኋት በኋላ ያን ዕለት ማታ ‘በዙ ያራ ዳው ልጅ’ ፍቅር ሰብሮት ለብቻው ተ ደበረ። ከማንም የበለጠ እወዳት ነበር። መቅደስን ከሆላንድ መጥታ ሳያት ሌላ ሰው ለመምሰል ትንሽ እስኪቀራት ወፍ ራ ነበር። የገረመኝ መወፈሯ ብቻ ሳይሆ ን ያ ቀጫጫ አጥንቷ ያን ሁሉ ስጋ መሸ ከም እንዴት እንደቻለ ነው። ጠይም ነበ ረች፤ ቀልታለች። ለአንድ ወር ያህል በአ ሷ ወጪ በአዲስ አባ እና ክፍለ ሀገር ዞር ን። የልብ ተጨዋወትን። አልነገርኳትም እንጂ በግሌ የተገነዘብኩት ቁምነገር ቢ ኖር ሁለታችንም በተለያየ መንገድ ተሸ ናፊዎች እንደነበርን ነው። ደንሀግ ውስ ጥ ሁለት የተለያዩ ክሊንኮች ውስጥ በሺ ፍት የጤና እረዳት ሆና ትሰራለች። እን ዳይኋቸው አገር ጎብኚ የአሜሪካ “ዋትዝ አፖች” ጉራ አልነበራትም። በየቦታው በ ዱርዬነት የቂጣችን ዋንጫ እስኪወልቅ እንዳልተልከሰከስን፣ አሁን ቁጥብ ነበረ ች። ምናልባት እኔን የማግባት አላማ ስለ ነበራት ከርሜ በውሸቷ እንዳልይዛት ይ ሆናል ብዬ ነበር። ዕድሜ አብስሎን ይ ሆናል ተረጋግተን የተያየነው። ጨዋታ ዋ የማውቀው የተሟላ መፍለቅለቅ አል ነበረበትም። በተደበረ ልቦና እያየኋት ይ ሆናል አልኩ። ገባ ወጣ ትል ነበር። ትር ጉሙ ከማይገባኝ ዝምታ እንደገና ትርጉ ሙ ወደማይገባኝ መፍለቅለቅ። ምናልባ ት ከእሷ ጋ መጣበቄን ረሐብ ጠርዝ ላይ ስለነበርኩ ለመኖር ያደረግኩት የሚመስ ላቸው ነበሩ። እሱ ትንሽ አለበት። አብረ ን ወዲህ ወዲያ ያልንባቸው የልጅነታች ን ሶሰት ዓመቶች የማይረቡ፣ ትልቅ ቁ ምነገር ሳንሰራባቸው ተረጋግተን የሳቅን ባቸው፣ እንደውም የዋሸንባቸው ዘመና ት ነበሩ። በትንሽ ገንዘብ ክትፎ በልተን፣ በትንሽ ገንዘብ ኬክ በልተን እርካሽ አል ቤርጎዎች ውስጥ ያለሃሳብ ‘ነገ ምን ልን ሆን ነው?” ሳንል የስጋዎቻችንን የመጨ ረሻ መጠን ስላየንባቸው ይሆናል። አሁ ን ከንፈሮቻችን በጉልምስና የሳሱ፣ በጥር ጣሬ የተረጋጉ፣ ደረቶቻችንም በክፉው ም በደጉም ታሽተው የረገቡ ሆነዋል። ሆላንድ ገብታ ለመቀመጥ እና ስደተኛ ሆና እንዲቀበሏት ለማድረግ ሁለት አገ ሮች አቋርጣለች። ስለዚህ ዘርዝራ ልታ ወራኝ አትፈልግም። ሆዴ ለማወቅ በትን ንሹ ቢጓጓም ያለፈችበትን ውርደት ወይ ም መከራ ይቅር ልላት፣ ልሰርዝላት ላላነ ሳባት ለራሴ ምያለሁ። ያን ዘመን ከመሰ ደዳቸው በፊት ሴቶቻችን ይንቁን ነበር። አገራችን የሌላትን ነገር እንዲኖረን ይፈ ልጋሉ። መኪናውን አምጣው፣ ቪላውን አምጣው፣ ምቾቱን አምጣው ይሉናል። እንዲህም ነበረች እሷ። አንድ የተግባረዕድ ሰርቬየር እንዴት ይ ኼን ሁሉ የማድረግ አቅም አለው? ከእኔ የሚበልጡስ ያደርጋሉ? ሚሊዮኖች በ ረሃብ የሚጠፋባት አገር ምን ምቾት አላ ት? ቡና ተቀምጠን ስንጠጣ መኪና አይ ታ ትቋምጥ ነበር። ምኞት ይከለከላል? ደጋግማ እጇን ከእጆቼ አላቃ ከሩቅ የ ምናያትን ሴትዮ ውድ አለባበስ አሳይታ ደካማነቴን በአሽሙር ነግራኛለች። እየገ ባኝ ከኔ የበለጠ ሃብት ካላቸው ጋር ደጋ ግማም አምታኛለች። ያልገባው መስያለ ሁ። ያለማፈር ክብሬን ተጭና እንዲገባኝ አሽሟጣኛለች። ከዕለታት አንድ ቅዳሜ በለመድኩት ሰ ዓት ልጠራት ቤቷ ስሄድ ‘የለችም’ ተባል ኩ። ለፕሮሰስ አብሬአት ስንጦለጦል ከር ሜ የመሄጃዋን ቀን አልነገረችም ነበር። ቀሽም ቢያደርጋትም ከትዕዝብት በላይ

* ልፎ በአዳም ረታ

ሽሽት የማያመልጥ ሐበሻ ነው። እግራችን ለስደት አይደለም የተሰራው። እዚሁ ለመሮጫ ነው። ባንዳው እንኳን ተመልሶ ይመጣል። ተጽፏል እኮ፣ የተጻፈ ነው። ውሐ ከሰማይ ቀልበን እንጠጣለን። አፈራችንን ብንቅመው አይፈልጥ አይቆርጥ።

አልሄድኩም። እናቷ እንኳን ፡ (የእናት ጸባይ ይለወ ጣል) “ከዚህ አገር የማይሻል የለም” አሉኝ። ሰማዩን እያዩ። (ለምን ሰማይ ሰማይ ያያ ሉ? እያወሩኝ ሲጸልዩ ነበር?) እሳቸውን ሳስብ ይሄ ትኩስ ይዘቱን ያ መነ ይፋ ንግግራቸው ብቻ ይታወሰኛ ል። ብዙ አውቃቸዋለሁ። ብዙ አውር ተናል። ግን ያ ያወራነው ሁሉ ‘ከዚህ ሀገ ር የማይሳል የለም’ በሚለው አረፍተ ነገ ር ተውጦ ይጠፋል። እና ለምን ሰማይ አ ዩ? አደጋውን አሽትተውት ነበር? ግን እ የካዱት? ግን እየደበቁት? ከዛ አፋቸውን ም ሳይዛቸው፡ “ወታደር ከመገዛው አገር……..”ፖለቲ ከኛ ሆኑ። እሷ ከሄደች በኋላ ‘ተፈነገለ’ ተብዬ ት ንሽ ሳምንታት ተስቆብኛል። ‘በዙን ለመ ፈንገል ከራሱ ከሰይጣን ቴክኒክ መነገር አለብህ’ እየተባለ ተሾፈ። ‘ሴቶቹ ስማር ት ሆነው በዙን መፈንገል ሁሉ ቻሉ’ ተ ባለ። ‘ያን ነገር በደንብ ስላላደረግሻት ነ ው’ ተባልኩ። የዕውነት እወዳት ነበር። ከማንም [በላይ]እወዳት ነበር። የአራዳ አፍ የማይሰራበት ጊዜ አለ። በፉገራ ‘አ ይ ላቭ ዩ’ ማስቀረት ካልቻልኩ በሰንሰለ ት አላስራት። መቼም ‘ከአባታችን ሆይ’ ቀድሞ ‘ከመሿለኪያ ተረበኛ ይጠብቀኝ’ የጸሎታችን መግቢያ መሆን አለበት። ክ ብሬን ለመከላከል ስድብ መሳደብ ነበረ ብኝ። ባለጌ ባለጌ ዐይነት። አልፎ አልፎ ጤንነቷን ልጠይቅ ቤቷ ስ ሄድ የእናቷ የአካል መጠን እያነሰ፤ ቅላ ታቸው እየጠፋ፣ አይናቸው እየተንጮ ለጮለች እና ሹክክ ያሉ እየመሰሉ ሲሄ ዱ ይታወቀኛል። ለምን አንደሆነ አልገ ባኝም። ‘አሮጊቷ ኤድስ መታቸው?’ እ ላለሁ ለራሴ። “እንደው እኮ ከራስ አገር የሚሻል የለ ም” ይላሉ። ደብዳቤ ጽፋልኝ አንደሆነ ስጠይቃቸ ው፣ ‘የለም አልጻፈችም’ ይሉኛል። በግ ምቴ መጥፎ ነገር እንደአጋጠማት አው ቄአለሁ። ቀላል ነበር። ከአገር ከወጣች በሶስተኛው አመት እናቷ አልጋ ላይ ቀ ሩ። መሞት ሳይሆን ተነስቶ አንድ ነገር የማድረግ አቅሙን አጡ። እንደነገሩኝ። “ሁሉ ነገር ትርጉም የለውም ልጄ” ምን እንደሆነች በትክክል መገመት ግ ን ከብዶኛል። “ምን እየሆነች ይሆን? ታውቃለህ ምን እየሆነች እንደሆነ?” እሳቸውን ‘እግዜር ይማርዎ’ ብዬ ወደ ቤቴ ስመለስ፣ የልጃቸውን እጅ ይዤ (እ ጇን መያዝ እወድ ነበር) ሲመሽ ክዋክ ብት የሚፍለቀለቁባት ኩል የመሰለች የ አዲስአባ ሰማይ….በዚያች እግዜር በሰራ ት ግብታዊ ከተማ….የተረጋጋ ደህነቷ ይ ተረተር የነበረው ሳቋ ትዝ ይለኛል። መ ልካም ቂጧ ከስስ ቀሚሷ ውስጥ እየሞ ቀ አፈንግጦ። ያ የሚያደናብረኝ። በእሱ ገፍታኝ በሚሞቅ ሁለመናዋ ስትደገፈኝ ትዝ ይለኛል። ግን አላለቅስም። እግዜር መልካም ነገር ሰጥቶን እሱን ንቀነው ብን ሸሽ፣ ብንሰወር ከዚያም በደል ቢደርስብ ን፣ የምናለቅሰው በማን ላይ ነው?

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

* * * አለብላቢት ነበረች። ዛሬ አስባ የምትና ገር ትመስላለች። ወይስ ማሰብ ከብዶአ ት ነበር። ከገንዘብ በላይ፣ ከመልበስ በላ ይ፣ ከመመኘት በላይ እኔን ጨምሮ ሌላ ነገር እንዳለ ስለገባት ነው? መሰለኝ። እ ንደ አንዳንዶቹ ተሰዶ ተመላሾች ሆቴል ሳይሆን እናቷ ጎን መሬት ወድቃ ተኝታ፣ በከሰል የፈላ ሻይ ጠጥታ፣ ቅባቱ ለቆ ባ ልጸዳ ሰሀን ላይ በልታ፣ ድሮ የምንቀመ ጥባቸው ሻይ ቤቶች ኬክ በልታ ነው የ ሄድነው። ባልጠበቅኩት ጊዜ፣ ምከንያቱ ሳይገባኝ፣ ባረፍንበት ጸጥተኛ አልጋ ላይ ፊቷን ደፍታ ታለቅሳለች። ከማባባል ሌ ላ የምሰራው አልነበረኝም። ሆላንድ ቁስሏን አጠበው እንጂ አላዳነ ውም። ገላዋ እንደ ባሕርይዋ ቢለወጥም አላሳ ሰበኝም። ብዙ ነገሮችም ስላዳከሙኝ ሳ ይሆን አይቀርም። ግዙፍ ገላዋን ሳቅፋ ት ሁለታችንም ስጋ ውስጥ ጥርጣሬ ነ በር። ትውውቃችን በረዥም ጊዜ ውስ ጥ ጠፍቷል፡ እኔም ይሁን እሷ ወደንም ይሁን ተገደን በወደቅንባቸው አልጋዎች ላይ ያጋጠሙን ወዳጆቻችን ወይም ጠላ ቶቻችን፣ እንደ ሊጥ እያገላበጡ ያልጠበ ቅነውን ዐይነት ቅርጽ ሰጥተውናል። ቀ ጥ ያለው ያልጨርሰነውን የወጣትነት ል ምዳችንን፣ ወደ ረባና ወደ አልረባ አቅ ጣጫ ጠመዛዘውታል። እኔ ከአገሬ አል ወጣሁም ማለት አልተበላሸሁም ማለት ነው እንዴ? አገሬን መተው አልፈለግሁም ነበር። ግን ትቼ መሄድ ነበረብኝ። ከባድ ምር ጫ ነው። አዲስአባ ተወልጄ ያደግሁ ነ ኝ። ከስራዬ እስከተባረርኩ ድረስ ሐዘን ና ብስጭት የሚባል አላውቅም። በትክ ክል በከባድ ያዘንኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝ ም። የዓይን በሽታዬ ከብሔራዊ ውትድ ርና ስላራቀኝ አይደለም። ፖለቲካ የለው ም። በፍልሰታ ጦም መሐል ተወልጄ፣ በ ተቅለጠለጠ መስከረም የምታምር ጸሐ ይ በፈነተወችበት ጠዋት ክርስትና የተነ ሳሁ ነኝ። ይኼም መመረቅ ነው። ባለቀ ጫማ ኳስ ስጫወት በተገጠቡ ሜዳዎች ላይ ምስማር እግሬን ወግቶኛል። ይኼ ም መመረቅ ነው። ስድሳ ተማሪዎች ባ ሉበት ክፍል የሶስት ሽፍት ትምህርት ቤ ት ውስጥ በጩኸታችን የአስተማሪ ጆሮ በጥሰናል። እንደመዶሻ የጠነከረ ኩርኩ ም ወርዶብኛል። አልቅሻለሁ። እንባ ጨ ው ጨው እንደሚል ቀምሻለሁ። ይኼ ም መመረቅ ነው። እራሴን ግን አልጠላሁም። እዚያ ሰድቦኝ የሄደውን ሰድቤ አሹፌ አለሁ እንጂ፣ ልቦናዬን ጥላቻ አልነገር ኩትም። የተለየ አለም ነበር። ታድያ ‘እንሂድ’ ስትለኝ ስታባብለኝ ጥ ቅም ሳይሆን የታየኝ ‘ግልግል’ ነበር። ይ ህም ያሳዝነኛል። እነዚህ ሳንባዎቼ ወዳ ጆቼ ሆይ ያለአዲስ አባ አየር ይሰራሉ? ቅመም የሌለበት አየር ያውቃሉ? ድንገ ት ደንሀግ ስገባ ‘የታለ ፌጦ የተለሰነበት አየር?’ ቢሉኝ፣ ‘የታለ በክረምት ሰማይ የሚያንባርቀው ጅራፍ?’ ቢሉኝ፣ ወይ በ ጋ ሲገባ ነጭ በርኖሱን መስከረም ላይ ሲ ጥል፣ ጸሐይ አይተው ደካማ አይኖቼ ያ ለመስቀል አበባ ሁሉ ከበደን ቢሉ፣ ወ ጨጫን መብላት ለምደው ቁልቁለት ዳ ገትስ መውጣት የለመዱ እግሮቼ በዚያ የሆላንድ ጠፍጣፋ ተበሳጭተው በቁጭ ት ቢሰባበሩስ?... “እየው ልጄ እየው ችግርህ ይገባኛል። ግን አየህ የተወለዱበት ያደጉበት ያው አይለወጥም። የተወለዱበት ያደጉበት ነ ው እ? እስኪ እየው…ችግርና መከራ የማ ይነቅለው የለም፣ ክርስቶስ ተሰዷል፣ ነ ቢዩ ተሰደዋል….ግን ያባባል። እንደምሰ ማቸው እንደ አንዳንዶቹ እንዳትሆን። እይማ ያ ጥድ ይታይሀል? እ? እትብትህ ን እዛ ነው የቀበርኩት። ያ ዛፍ የበቀለው እትብትህ ላይ ነው። ወሬ አይደለም። ከ ፈለግህ እናትህን ጠይቃት። አይደለም እ

ንዴ ሜቲዬ? አይደል?” “አዎ” “እኛ ሀገራችንን ጥለን ስንሄድ እነሱ ሊወስዱብን ነው። እነማን እንደሆኑ አናውቅም፣ ሊወስዱብን ነው። የተሰ ጣ ልብሳቸውን ያውም ያረጀ ሸሚዝ በወንጨፍ የሚጠብቁ፣ ሀገራቸውን ግን አሳልፈው ይሰጣሉ። ሽሽት እንደ ምርቃትና ባህል ተቆጠረ። ማን እንዲ ያ አደረገው? አየህ እስኪ ማልልኝ ይህ ች እትብትህ የተቀበረባትን መሬት እን ደማትረሳ። ሰው ያልፋል፣ አየህ ሰው ሁልጊዜ በረባው ባልረባው ነገር ይሞ ታል። በአባላዘር በሽታ ይሞታል። ይ ህች ሀገር ግን አትሞትም። ደካማዎች ም ነን። ጠንካራዎችም ነን። ያ የሚታ ወቀው በፈተና ነው። መሰደድ አየህ እ ንግዳ አገር ሄዶ መኖር ተስማምቶ የመ ኖር ፈተና ብቻ ሳይሆን፣ እትብትህ የ ተቀበረበተን እንዳትረሳ መታገልም ነ ው። እስኪ እየው የማይገባኝ ነገር፣ መ ቅደስ ስለብርዱ ስትነግረኝ፣ ስለሚበላ ው ስትነግረን እኔ አላማረኝም። የእግ ዜር ስራ ያልሆነ ነገር ያስፈራኛል። እግ ዜር የሰራው ነገር እዚሁ ነው ያለው። እግዜር የሰራው ሰው። የማያምር ከሆ ነ ለምን እንድንጠላው ነጋ ጠባ ይለፋ ሉ? መሬታችንን ካልፈለጉ ለምን ይቀ ናቀኑናል? ብዙ አላውቅም ግን እጠራ ጠራለሁ። እትብታቸውን እንደእኛ ጓ ሮ ይቀብራሉ? ጽድ ይተክሉበታል? ዝ ም ብለው በየቆሻሻ ቦታ አይደለ የሚጥ ሉት? እትብት የተከበረ ነው። ጠግበ ህ ብታድር እንኳ አትርሳው። መቅደስ ለምን መጥታ አንተን ፈለገችህ? ፍቅር ብቻ መሰለህ? ሁሉ ነገር ነው የተሰማ ት። የደረሰባትን እግዜር ያውቃል፣ ለ ሴትም ለወንድም ስደት ይከብዳል። አ ንተ ትዝ ስትላት አገሯ፤ አገሯ ትዝ ሲላ ት አንተ፣ አየህ ማምለጥ አልቻለችም። ሽሽት የማያመልጥ ሐበሻ ነው። እግራ ችን ለስደት አይደለም የተሰራው። እ ዚሁ ለመሮጫ ነው። ባንዳው እንኳን ተመልሶ ይመጣል። ተጽፏል እኮ፣ የ ተጻፈ ነው። ውሐ ከሰማይ ቀልበን እ ንጠጣለን። አፈራችንን ብንቅመው አ ይፈልጥ አይቆርጥ። ልንገርህ ታውቃ ለህ። ስጋዬን አልተመቻትም ግን ከስ ቼ ተርቤ የምሞተው እዚሁ ነው። ስ ለምትሄድ እወዳለሁ? አልወድም። እ ትብትህን ብቻ አልቀበርኩም እዚያ። ልፎህንም። ስትገረዝ የወሸላህን ቁራ ጭ ቀብሬያለሁ እዚያ። ጠይቅ እናት ህን። አትሳቅ። ሳይቸግረኝ ኖሬአለሁ? ቸግሮኛል እንጂ። ስማርስ ስለፈረንጅ አገር ታላቅነት ሳልማር ቀረሁ መሰለ ህ? በወረቀትና በመጽሐፍ አምኜ አላ ውቅም። ጋዜጣ አላነብም። ግን ተጨ ባጭ ነገር አያለሁ። ለምን ፈረንጅ ሀገ ሬን ይጎዳል? ቢፈልጋት አይደለም? አ ንድ ከረሜላ በአደባባይ ይሰጡንና የ እኛን አራቱን ተደብቀው ይወስዱብና ል። ስለዚህ የተማርኩት ሁሉ ስህተት ነው። ለምን ይብረድህ? ብልጦች ወደ ጸሐይ ሲመጡ ጅሎች ወደ ብርድ ይሄ ዳሉ። ጉድ። አትሂድ አይደለም የምል ህ። እዚህ ብዙ ነገር ሆነ ተብሎ ተበላ ሽቷል። እየው ያን ዛፍ ባንተ እትብትና ባንተ ልፎ ያደገ ነው። ውሸት አይመሰ ልህ እንዳትረሳው።” እንዲህ አለኝ አባቴ ጠጅ በማንቆርቆ ሪያ መጥቶለት እየጠጣ። እኔ ነበርኩ፣ የመቅደስ እናት አባት ነበሩ። መቅደስ ነበረች። አይነስውር እናቴ ሜቲ ነበረ ች (እኔም እንደእሷ የምሆንበት ጊዜ እ ሩቅ አይደለም)፣ ወይዘሮ አስካለ ነበ ሩ (ወጣት ልጃገረዶችን እየሰበኩ ሽር ሙጥና ይመለምላሉ እየተባለ ይታማ ሉ)። ሌሎች ጥቂት ጎረቤቶቻችን ነበ ሩ። ሶስት ጓደኞቼ ነበሩ። እንደ ድሮው አናወራም፣ አንስቅም። የመለያያ ሶስት ጓደኞቼ ነበሩ። እንደ ድሮው አናወራ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የያኔዋ ሸገር መጽሐፏን የጻፉት አዶልፍ ፓርላሳክ ሁለት ጊዜ ያህል ወደ ኢትዮጵያ በመም ጣት ቆይታ አድርገዋል። በ14 ዓመት ዕ ድሜያቸው ሀገራትን መጎብኘት የጀመ ሩት አዶልፍ ፓርላሳክ በርካታ ሀገራት ን የተመለከቱ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ለ መጀመሪያ ጊዜ የመጡት ከግብጽ ሲሆ ን ምክንያታቸውም የአባይን ወንዝ ፈለ ግ መከተል ነበር። በሱዳን በኩል አድር ገው ወደ ኢትዮጵያ የዘለቁት ፓርላሳክ በሰሜን ኢትዮጵያ ረዘም ላለ ጊዜ ሲዘ ዋወሩ ቆይተው ወደ ኤርትራ ሄደዋል። ፓርላሳክ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮ ጵያ የተመለሱት ሀገሪቱ በጦርነት ዋዜ

የሐበሻ ጀብዱ የመጽሐፍ ዳሰሳ በተስፋለም ወልደየስ- ሐበሻዊ ቃና

ደራሲ፦ አዶልፍ ፓርለሳክ ተርጓሚ፦ ተጫኔ ጆብሬ መኮንን አሳታሚ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የታተመበት ዓመት፦ 2003 ዓ.ም ማ ላይ ሆና ነበር። ከሀገራቸው ተወላ ጅ እና ጓደኛቸው ጋር በጅቡቲ በኩል አ ድርገው አዲስ አበባ የደረሱት ፓርላሳክ ወደ ጦር ሜዳ ከመውረዳቸው በፊት በ አዲስ አበባ ጥቂት ቆይታ አድርገው ነበ ር። በመዲናይቱ የነበራቸውን ቆይታ እ ና የያኔዋ አዲስ አበባ ኑሮ እና ሁኔታ ም ን ይመስል እንደነበር የታዘቡትን በመጽ ሀፋቸው በሁለት ምዕራፍ አቅርበዋል። ጸሀፊው “ዋናው አደባባይ” ሲሉ በጠሩ ት እና የት እንደሆነ ባላመለከቱት ቦታ ላ ይ በሚገኝ አንድ ፎቅ ህንጻ ውስጥ ከጓደ ኛቸው ጋር ቤት መከራየታቸውን ይነግ ሩን እና ስለአዲስ አበባ አጠቃላይ ገለጻ ይሰጡናል። “መካከለኛው ከተማ ባለ አ ንድና ሁለት ፎቅ የድንጋይና የእንጨት የመኖሪያ ቤቶችና የግሪክ ነጋዴዎች ሱ ቆች እንዲሁም የሌሎች አውሮፓውያን መኖሪያ ቤቶች ተሰርተውበት ደመቅመ ቅ ብሏል። ከእነዚህ የቆርቆሮ ቤቶች ዙ ሪያ ጥንታውያኑ እና ክቦቹ የኢትዮጵያ ውያንም ጎጆዎች በረጃጅሞቹ የባህር ዛ ፎች ተከበውና ተውጠው ቦታ ቦታቸው ን ይዘዋል” ሲሉ ሸገር በ1920ዎቹ መጨ ረሻ የነበራትን መልክ ይገልጻሉ። “አዲስ አበባ በርከት ያሉ ሰፋፊና ጥሩ ሆነው የተሰሩ የአስፓልት የመኪና መን ገዶች አሏት። በሁሉም መስቀለኛ መንገ ዶች ላይ የኢትዮጵያ ፖሊሶች ቆመው ባ ለ መኪናውንም፣ እግረኛውንም ስርዓት ባለው መንገድ እንዲጓዝ ይረዳሉ” ይሉ ና በወቅቱ የትራፊክ ስነስርዓት ለባላገሩ ሕዝብ ለማስረዳት የነበረውን ችግር በዝ ርዝር ያስቀምጣሉ። ደራሲው የከተማይ ቱን ሕንጻዎች፣ መኖሪያ ቤቶች እና መን ገዶችን ተመልከተው ብቻ አላቆሙም። ወደ ገበያ ወርደው የግብይት ስርዓቱን እና ችግር ቢፈጠር በአፋጣኝ እዚያው ኑ የሚፈታበትን የፍርድ አሰራር ተመል ክተው የተሰማቸውን በመጽሐፋቸው አ ካትተዋል። “ከጠዋት ጀምሮ በየቀኑ ከአዲስ አበባ ና አካባቢዋ ገበያተኞች ወደገበያ ይወ ጣሉ። ምንም ዓይነት ሱቅም (መደብ ርም) ሆነ በረንዳ የለም። ብቻ እንዲያ ው ባዶው ሜዳ ላይ ነጠላቸውን ዘርግተ ው እቃዎቻቸውን ይዘረግፉና ይገበያያ ሉ። ሁሉም የራሱ የሆነ የተወሰነ ቦታ አ ለው። ጨርቅ ተራ፣ እህል ተራ፣ እንጨ ት ተራ፣ ከብት ተራ፣ በግ ተራ ወዘተ እ የተባለ ተከፋፍሏል። ከእነዚህ ገበያተኞ ች አመዛኞቹ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚኖሩ ኦሮሞዎች ናቸው” ይላሉ ስለ ገ በያው ሲያስረዱ። የግብይት ሁኔታውን ከሀገራቸው ጋር ማነጻጸራቸው አልቀረ ም። “በኢትዮጵያ እስካሁንም ብትን ጨ ርቆች የሚለኩት በክንድ ነው” ይላሉ በ ግርምት። “በአዲስ አበባ የቤት ዕቃ ገዝ

ቶ ቤት ማደራጀት ቀላል አልነበረም። አ ንድም በአዲስ አበባ የአውሮፓውያን የ ቤት ዕቃዎች ማግኘት በጣም ሲበዛ ከባ ድ ነው። ሁለትም እቃዎቹ ሲገኙ ዋጋቸ ው የክርስቲያን ልጅ ከፍሎ የሚወጣው አይነት አልነበረም” ሲሉ አይቀመሴውን የገበያ ዋጋ ያስቀምጣሉ። ከአምስት ዓመት በፊት የተመለከቷት አዲስ አበባ በለውጥ ጎዳና ላይ እንደሆ ነች የሚመሰክሩት ደራሲው ለዚህ የመ ሻሻል ሙከራ የአንበሳ ድርሻውን ለ”አዲ ሱ ንጉስ” ይሰጣሉ። “አዲሱ ንጉስ ሬጀን ት ራስ ተፈሪ (ልዑል ራስ ተፈሪ መኮን ን ባለ ሙሉ ስልጣን እንደራሴ) በነበሩ በትና አውሮፓን በሰፊው በጎበኙበት ወ ቅት ስልጣኔ የቱን ያህል ጠቃሚ እንደ ሆነ ጠንቅቀው ስላወቁ ለሀገራቸው ዕድ ገት ሌት ተቀን ሲጥሩ ይታያሉ” ሲሉ አ ጼ ኃይለ ስላሴን ያሞካሻሉ። ደራሲው ለ ንጉሱ ያላቸው አድናቆት ከፍተኛ ነበር። በመጽሀፉ የተለያዩ ምዕራፎች ንጉሱን የ ሚያወድሱ አንቀጾችን አስነብበዋል።

ውዳሴ ለግርማዊነታቸው “በ1930 ከነገሱበት ቀን ጀምሮ ዘላለማ ዊ እንቅልፍ የተኛች የምትመስለውን ው

ዷን ሀገራቸውን ከዚህ እንቅልፏ ለመቀ ስቀስና ወደፊት መራመድ እንድትችል የ ውጪ ዲፕሎማሲ ምን ያህል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠንቅቀው ያወቁት ንቁው እና ብልሁ ንጉስ የዲፕሎማሲ ስ ራውን ከሁሉም ነገር በፊት አስቀድመ ው አጠናከሩት” ይላሉ ደራሲው መወ ድሳቸውን ሲጀምሩ። ንጉሱ ረጅም ሰዓ ት ያለማቋረጥ ይሰሩ የነበሩ ታታሪ እን ደነበሩም በዓይናቸው ያዩትን ምሳሌ ይ ጠቅሳሉ። “የኢትዮጵያው ንጉሰ ነገስት ደከመኝ ሰ ለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን ከተለያዩ የሀገሪ ቱ ግዛቶች የሚመጡትን ሹማምንቶች እየተቀበሉ ያነጋግራሉ፣ ይመክራሉ። የ ውጪ ዲፕሎማቶችንም እየተቀበሉ ለረ ጅም ሰዓታት ያነጋግራሉ፣ ይመክራሉ፣ ይደራደራሉ። ጣልያኖችንና ጠብ ጫሪ ነታቸውን በተመለከተ እያንዳንዷን ነገ ር ሳይቀር ራሳቸው ንጉሰ ነገስቱ ይወስና ሉ። ሰላምን ለማስፈን ሌት ተቀን ይሰራ ሉ፣ ይለፋሉ” ሲሉ በጦርነት ዋዜማ ንጉ ሱ የነበሩበትን ሁኔታ ይገልጻሉ። ደራሲ ው ከንጉሱ ጋር የነበራቸው የመጀመሪያ ቆይታም የጦርነት ደመና ጥላውን አጥል

ፎቶ- ፒክቸር ሂስትሪ ብሎግስፖት

ምስራቅ አውሮፓ በም ትገኘው ቼክ ሪፐብሊ ክ ኑሯቸውን ያደረጉ ሐበሾች አንድ ልማድ ነበራቸው። ወር በገባ በመጀመሪያው አርብ በሀገሪቱ ዋና ከተ ማ ፕራግ ባለች አንዲት “ቢራ ቤት” ይ ሰባሰቡ ነበር። በቁጥር አንድ መቶ እንኳ የማይሞሉት እነዚህ ሐበሾች ታዲያ በ ተገናኙ ቁጥር ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው ሁሌም የሚያነሱት የሀገራቸውን ጉዳይ ነበር። በሀገር ቤት ጉዳይ ላይ ዋና ተከራ ካሪ ከነበሩ ሰዎች መካከል ፕራግ በሚገ ኘው የቻርለስ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህር ታቸውን ያጠኑት እና የቼክ ቋንቋን አቀ ላጥፈው የሚናገሩት አቶ ተጫኔ ጆብሬ አንዱ ናቸው። አቶ ተጫኔን ከተከራካሪ ነታቸው ባሻገር የሚታወቁበት ሌላ መ ለያም አላቸው። የትም ሲሄዱ ከእጃቸው የማይነጥሏት መጽሐፍ ነበረች። በየወሩ ወደ “ሐበሾ ቹ ቢራ ቤት” ጎራ ሲሉም ይችኑ መጽ ሐፍ አንጠልጥለው ነው። መጽሐፏ የ ቼክ ተወላጅ በሆኑት አዶልፍ ፓርለሳክ ከ63 ዓመት በፊት የተጻፈ ነበር። “ሐበ ሽስካ ኦዴሳ” (Habesska Odyssea) በ ሚል ርዕስ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት ጊዜ የተታተመችው ይህቺው መጽሐፍ ኢት ዮጵያውያን በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመን ከ ኢጣሊያን ጋር ያደረጉትን መራር ጦር ነት የምትተርክ እውነተኛ የታሪክ ማስ ታወሻ ናት። አቶ ተጫኔ ይህቺን መጽሐፍ ይዘው እ የዞሩ በውስጧ ስለያዘችው “ድንቅ” ታሪ ክ በመዘርዘር ብቻ አልቆሙም። ለበርካ ታ ሰው መድረስ እንዳለበት በማመን ከ መጽሐፉ በጥቂት በጥቂቱ እየቀነጨቡ በመተርጎም “ሳይበር ኢትዮጵያ” በተሰ ኘ ድረ ገጽ ላይ ያወጡት ጀመር። ቅን ጭብ ታሪኮቹን ያነቡ የነበሩ የድረ ገጹ ተከታታዮች ሙሉ ታሪኩን በመጽሐፍ መልክ እንዲያሳትሙ ተርጓሚውን ያበ ረታትቷቸዋል። የመጽሐፉን የመጀመሪ ያ እትም ሙሉ ትርጉም መስራት የጀመ ሩት አቶ ተጫኔም መጽሐፏ በሀገር ቤት ለህትመት እንደምትበቃ ለ“ቢራ ቤት” ሐበሻ ወዳጆቻቸው ይፋ አደረጉ። የተር ጓሚውን እቅድ ሁሌም የሚያደምጡት ሐበሻ ወዳጆቻቸው ግን ሀሳባቸው ከዳ ር ይደርሳል ብለው አላመኑም። ሶስት ዓመታት አለፉ። በአራተኛው አ መት ከወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግድ ም ዜና መጣ። ለታሪካዊ መጽሐፍቶች ልዩ ትኩረት የሚሰጠው የዩኒቨርስቲው መጽሐፍ አሳታሚ ክፍል የአቶ ተጫኔን ትርጉም በ349 ገጽ ሸክፎ “የሃበሻ ጀብ ዱ” በሚል ስያሜ ለህትመት አበቃው። “የሃበሻ ጀብዱ” እንደሌሎቹ የአዲስ አበ ባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ መጽሐፍት ሁሉ ታ ሪካዊ ፋይዳው የጎላ ነው። ኢትዮጵያው ያን የጣሊያንን ወረራ ለመመከት ያደረ ጉትን ተጋድሎ ከመዘከር ባሻገር በወቅ ቱ የነበረውን አስተሳሰብ፣ አኗኗር፣የከተ ሞች ሁኔታ፣ ባህል እና ትውፊት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የጦርነቱም ሁኔታ በዝ ርዝር የተተነተነበት እና ኢትዮጵያውያ ን የፈጸሟቸውን ወታደራዊ ስህተቶች ያ ፍረጠረጠ ነው። ለዚህ ደግሞ የጸሐፊ ው የዕለት ውሎ ማስታወሻ (ዳያሪ) የመ ያዝ ልማድ ጉልህ አስተዋጽኦ አደርጓል።

15

“ንጉሰ ነገስቱ እንደማንም ተራ ወታደር በጦር ሜዳ ውለው፤ ታግለው አታግለዋል። ተዋግተው አዋግተዋል”

ቶበት ነበር። “ቀደማዊ ሃይለ ስላሴ ንጉሰ ነገስት ዘኢ ትዮጵያ፣ እድል ለዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የመ ረጣቻቸው መሪ፣ በቁመናቸው አጠርና ከሳ ያሉ ናቸው። ይሄ ረዘም ያለ ፊታቸ ው በጥንቃቄ የተከረከመው ሙሉ ጥቁ ር ጢማቸው፣ ምናልባት ለሳይንቲስት፣ ለፈላስፋ ወይም ለደራሲ እንደሆነ እን ጂ አገሩን በደሙና በአጥንቱ ለመከላከ ል ቆርጦ ለተነሳ መሪ የሚሆን አይመስ ልም” ሲሉ ስለንጉሱ ተክለ ቁመና ማብ ራሪያ ይሰጣሉ።“ምንም እንኳ ንጉሰ ነገ ስቱ ከትልቁ ጠረጴዛቸው ኋላ እንደተቀ መጡ ፈገግ ለማለት ቢሞክሩም ገጽታ ቸው በስራ ብዛት እጅጉን እንደደከሙ ያሳብቅባቸዋል። መደዳውን እንደቆሙ ት ሹማምንቶች ሁሉ ንጉሱ ባህላዊውን የኢትዮጵያውያን ልብስ ለብሰው ጥቁር ካባ ደርበዋል። እንዲህ ለስልጣኔ ሌት ተ ቀን የሚለፉት ንጉሰ ነገስት በዚህ አስቸ ጋሪ ጊዜ እንኳን የጥንቱን የጠዋቱን የኢ ትዮጵያውያንን ባህልና ወግ አልረሱም” ሲሉ ያደንቋቸዋል። ባህልና ወጉ ንጉሱ የሚነጋገሩበትን ቋን ቋም እስከመወሰን ይሄዳል። “ምንም እ ንኳ ንጉሰ ነገስቱ ፈረንሳይኛም እንግሊዘ ኛም አቀላጥፈው ቢናገሩም የኢትዮጵያ ውያን የነገስታት ሕግ ከውች ዜጎች ጋር [ሲገናኙ] በአማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ስለ ሚያስገድድ የግድ አስተርጓሚ አስፈላጊ ነው” ይላሉ። ደራሲው ንጉሱ ባህላቸው ን ማክበራቸውን ቢወዱትም እንደልብ ሀገሪቱን ለማዘመን በሚያደርጉት ጥረት ግን እንደ ልብ አላራምድ ብሎ ያስቸግራ ቸው እንደነበር ታዝበዋል። “ምንም እንኳን አውሮፓውያን ከመቶ ዓመት በላይ በፈጀባቸው ስልጣኔ ላይ በ ጥቂት ዓመታት መድረስ ባይቻልም ቢያ ንስ ጫፏን ለመያዝ ለሚጥሩት አዲሱ ን ጉስ ጠንካራው የኢትዮጵያ ባህል፣ ሃይ ማኖትና ልጆቿ ለአዲሱ ስልጣኔ እንቅፋ ቶች እየሆኑ አዲሱ ንጉስ ወደ ስልጣኔ እ ንደፈለጉት አገራቸውን ይዘው እንዳይሮ ጡ መሰናክሎች ሆኑባቸው” ይላሉ። እ ንደምሳሌም ንጉሱ በአዲስ አበባ ያቋቋ ሟቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያ ነሳሉ። በኢትዮጵያ እስካሁንም በዘለቀ ው የአሿሿም ይትባህል መሰረት ዕውቀ ት ሳይሆን ታማኝነት ቅድሚያ ሲያገኝ የ ተፈጠረውን ደራሲው ያብራራሉ። “ለንጉሰ ነገስቱ ታማኝና ቅርበት ካላቸ ው ከየጠቅላይ ግዛቱ የመጡ ጢማም ሹ ማምንቶች በአንድ ሌሊት ሚኒስትር ሲ ሆኑ ችግር መፈጠር ጀመረ። እውነቱን ለመናገር እነዚህ ሹማምንቶች በሚኒስቴ ር መስሪያ ቤቶች ስራው እንዴት እንኳን እንደሚሰራ ምንም የሚያውቁት ነገር አ ልነበራቸውም” የሚሉት ደራሲው ለዚ ህ ግን ንጉሱን ተጠያቂ ለማድረግ ድፍረ ት አንሷቸዋል። ይልቅስ ይህንን ችግር ለ መፍታት ንጉሱ ያመጡትን መፍትሄ እ ንዲህ ሲሉ ያደንቃሉ፤ “እናም እኚህ ታ ታሪ ንጉስ ለእነዚህ አዲስ ለተሾሙ ሚ ኒስትሮች ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ የተ ማሩ ሰዎች አስመጥቶ ስለሚኒስቴር መ ስሪያ ቤቱ አሰራር እንዲያማክሩ ማድረ ግ ተገደዱ።” እነዚህ በውጭ ሀገር ተምረው የመጡ ኢትዮጵያውያን በእርግጥም ለውጥ ማ ምጣት ጀምረው ነበር። “እድለኛ ከሆኑ ና በእነዚህ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በ አውሮፓና አሜሪካ በተለያዩ ኮሌጆች የ ተማሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰሩ ከሆነ እ ና እነሱ ካጋጠሞት የመጡበትን ጉዳይ ቶሎ ይጨርሳሉ” ሲሉ ደራሲው ይመሰ

መጽሐፍ

ክሩላቸዋል። ሆኖም አንዳንድ “ወግ አጥ ባቂ”ና “አዲስ ነገር ተቃዋሚ ሚኒስትሮ ች” በስራቸው ላይ እንቅፋት እንደሆኑባ ቸውም ይገልጻሉ። ንጉሱ የጀመሯቸው ሌሎች ስራዎችም በቅጡ የሚከውናቸው እንዳልነበረ ጸሀ ፊው ያስረዳሉ። “ንጉሱ አዲስ አበባን እ ና ጎጃምን በድልድይ ለማገናኘት አስበ ው ከአውሮፓ ድረስ ያስመጡት ብረታ ብረትና ሲሚንቶ አባይ ወንዝ ዳር ወር ዶ ሲሚንቶውን የአካባቢው ገበሬዎች ጎ ጆአቸውን ሲያሰማምሩበት፣ ብረቶቹ አ ሁንም እዚያው ወድቀው በመዛግ ላይ ና ቸው” ይላሉ። የኢትዮ-ኢጣሊያን ጦርነ ት ከመጀመሩ በፊት የታቀደው ይሄ ድ ልድይ በስተኋላ ላይ በንጉሱ ዘመነ መን ግስት ተሰርቷል። የእዚህን ድልድይ ወ ጪ በጦርነቱ ላደረሰው ጉዳት ካሳ በሚ ል የሸፈነው የጣሊያን መንግስት ነበር። እንደ ፓርለሳክ አባባል አጼ ኃይለ ስላ ሴ ከሀገር መሪነታቸው ባሻገር በወታደ ራዊ መስክም “ጀግና” ነበሩ። “ንጉሰ ነገ ስቱ እንደማንም ተራ ወታደር በጦር ሜ ዳ ውለው፤ ታግለው አታግለዋል። ተዋ ግተው አዋግተዋል። አዎ በማይጨው የ ጦር ሜዳ ከእሳቸው በፊት እንደነበሩት ነገስታት ሁሉ ትልቁን ኃላፊነት ወስደ ው፣ ጠቅላላውን የሀገሪቱን ጦር እየመሩ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ተዋግ ተዋል። ይሄም ታላቅ ጀግና ሊያስብላቸ ው ይገባል” ይላሉ በማይጨው ጦርነት ላይ የተሳተፉት ፓርለሳክ። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የነበረውን የ ንጉሱን የኮረም ከተማ “የዋሻ ቤተ መን ግስት” ቆይታ ምስል ከሳች በሆነ አገላ ለጽ እንዲህ አስፍረዋል። “በአዲስ አበ ባ ቤተ መንግስት ያየሁት ምርጥና ድን ቅ በወርቅ የተሽቆጠቆጠ ጌጣጌጥና ማራ ኪ ነገር ሁሉ እዚህ የለም፤ ጠፍቷል። የ ንጉሰ ነገስቱ ዋሻ ተራ ዋሻ ነች… የንጉሰ ነ ገስቱ ዋሻ በመጠኑም ቢሆን ሰፋና ጠራ ያለች ብትሆንም፣ በውስጧ ግን የኢትዮ ጵያው ንጉስ ነገስት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እንደሚኖሩ የሚጠቁም አንዳች ነ ገር የለም። በዚች ዋሻ ያለ ነገር ቢኖር አ ንድ መናኛ ወታደራዊ ታጣፊ ጠረጴዛ፣ አራት ታጣፊ የሸራ ወንበሮችና ከዋሻዋ የቀኝ ከንፍ ላይ በተራ የወታደር ብርድ ልብስ የተሸፈነ አንድ ተራ የወታደር አል ጋ ብቻ ነበር። ከዚህ ሌላ ወለሏ በተደጋ ጋሚ ተረጋግጣ ወደ መመላለጥ በተቃረ በች የአበባ ምንጣፍ ከመሸፈኑ በቀር ሌ ላ ነገር የለም።” እንዲህ ምቾት በሌለው ዋሻ ውስጥ የ መሸጉትን ንጉስ የአውሮፕላን መቃወሚ ያ መትረየሶች ጠምደው ይጠብቁ የነበሩ ት የንጉሰ ነገስቱ የክብር ዘቦች ነበሩ። ፓ ርለሳክ ጃንሆይን በዚያች ዋሻ ለመጀመሪ ያ ጊዜ ሲያገኟቸው እንደተለመደው በን ጉሱ ሁኔታ ተደንቀዋል። “ከሁሉም በላ ይ ያስገረመኝ ነገር ቢኖር የጃንሆይ ፍጹ ም የተረጋጋ መንፈስ ነበር። በየቀኑ የሚ ደርሳቸው ዜና እንኳን እርሳቸውን ቀር ቶ ከእርሳቸው በአካል ብዙ የሚበረታን ሰው ጭንቅላት አዙሮ የሚጥል ሰው ሆ ኖ ሳለ፣ ፍጹም በተረጋጋና ቁርጠኛ በሆ ነ መንፈስ ፈገግታ ሳይለያቸው ሲቀበሉ ን የመንፈስ ጥንካሬያቸውን አደነቅኩ።” “ያኔ ከአዲስ አበባ ተሰናብቻቸው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ስሄድ ፊታቸው ላይ ያልወሰኑ፣ ርግጠኛ ያልሆኑ ሰው ዓይነ ት ነገር ይነበብባቸው ነበር። ዛሬ ግን ከ እያንዳንዷ ከአፋቸው በምትፈልቅ ቃላ ቸውና እንቅስቃሴያቸው ፍጹም እርግ ጠኛ በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ብርቱ፣ ጠንካራ ቆራጥ ሰው መሆናቸው ይነበባ ል።” ንጉሱ ጸሀፊውን ከአዲስ አበባ ሲያ ሰናብቷቸው ለሰሜኑ ጦር አዛዥ ራስ ካ ሳ የጦር አማካሪነት በመሾም ነበር። ከ ፍተኛውን የኢትዮጵያ የጦር መኮንን ማ ዕረግ የተሾሙት ፓርለሳክ በማይጨው ጦርነት ላይ ከመሳተፋቸው በፊት ለወራ ት ያህል ከራስ ካሳ ጦር ጋር በመሆን ጋ

ወደ ገጽ 18 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

16

የከተማ ቧልት

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ተባለ እንዴ ተባለ፤ ተባለ እንዴ

ከእዚያ ማዶ የፀሐዬ ዮሐንስ ሙዚቃ ይ ሰማል፡፡ “ተባለ እንዴ ተባለ፤ ተባለ እን ዴ ተባለ…” ዘፈኑ የሚመጣው ከቴፕ አ ይደለም፤ ከሬዲዮ አይደለም፤ ከቴሌቪ ዥን አይደለም፤ ከእራሱ ከአርቲስት ከ ፀሐዬ ዮሐንስ አይደለም፡፡ ስካር ከፈተነ ው ከአለሙ ቀጮ አንደበት እንጂ፡፡ “ሰካራም ተባለ አለሙ፤ የሻዕቢያን ወሬ እየሰሙ!” የዘፈኗ ግጥም ይህቺ ብቻ ናት፡፡ “…ተባለ እንዴ ተባለ፤ ተባለ እንዴ ተ ባለ” ደጃፌ ላይ ያለው የቀበሌ መዝናኛ ክበ ብ እንደ ወትሮዋ ሁሉ በአነስተኛ እና ጥ ቃቅን ጠጪዎች ተሞልታለች፡፡ እንዴ! ደግሞ አነስተኛ እና ጥቃቅን ነጋዴ እና አ ምራች “ኃይል” እንጂ ጠጪ አለ እንዴ? ለምን የለም!? የቤተሰቦቻችንን በኑሮ የ ደቀቀ ብስጩ ፊት ጠልተን፤ “ይሄ ነገር ጎደለ፤ መግዣውን ወዲህ በል!” ዓይነት ጥያቄ ሰልችተን ወዲህ ወደ ቀበሌ መዝ ናኛ ክበብ ብቅ የምንለው የዚህ የቅጠል ሠፈር ነዋሪዎች ከአነስተኛ እና ጥቃቅን ውጪ ሌላ ምን ልንባል ነው? “ሰካራም ተባለ አለሙ፤ የነጭ ለባሽ ወሬ እየሰሙ! ተባለ እንዴ ተባለ፤ ተባለ እንዴ ተባለ” ዓለሙ ቀጮ ፈቃድ የተሰጠው እብድ ነው፡፡ ሲሰክር ብቻ የሚለፈልፍ የቅጠ ል ሰፈር እብድ፡፡ የቀበሌያችን መዝናኛ ክበብ የታደመ ው ጠጪ ጨዋታ ደርቷል፡፡ ከመጠጥ አፍቃሪ ይልቅ ጨዋታ ወዳድ ጠጪ የ በዛበት ነውና ሁሉም ሁለት እና ሦስት፤ አራትም አምስትም ሆኖ ስብርብር ብሎ የሚሰማው የአለሙ ቀጮን እንጉርጉሮ ማጀቢያ አድርጎ ወግ መጠረቁን ተያይዞ ታል፡፡ በዚህ ጨዋታ መሃል ለቤቱ እንግ ዳ የሚመስል አንድ ጠጪ ከአስተናጋጁ ጋር የፈጠረው ውዝግብ ጎልቶ ተሰማ፡፡ “ሰባት ጠጥተሃል!” “አልጠጣሁም!” “ጠጥተሃል!”” “ኧረ ተወኝ እቴ፤ ሰባት ከጠጣሁማ

ሰክሬያለሁ ማለት ነው፡፡ ያውም ድብ ን ብዬ!” “ቀልዱን ተወውና ክፈል!” “የጠጣሁት አራት ነው፤ የሰባት አልከ ፍልም!” የቤቱ ጠጪ በሙሉ ውዝግቡን ቢጠላ ውም ማንኛው ትክክል እንደሆነ አያው ቅምና ዝም ብሎ ንትርኩን ለመታዘብ ተ ገዷል፡፡ የቤቱ አዛዥ መጥቶ አስተናጋጁ ን እና ሰውየውን ይዟቸው ባይሄድ ኖሮ ውዝግቡ ከመጠጡ ጋር ተዳምሮ ራሳች ንን ባዞረው ነበር፡፡ ትንሽ ሞቅ ሲለው ለነገሮች ሁሉ ፍቺ መስጠት የሚወደው አስር አለቃ በሰው የው ንግግር ላይ ትንታኔ ለመስጠት ራሱ ን አሰናዳ፡፡ “ህም!” በቅድሚያ ነገር እን ደገባው ሰው ራሱን ወዘወዘ፤ “ሰባት ከጠጣሁማ ሰክሬያለሁ፤ ያው ም ድብን ብዬ! ያለው ምን ለማለት ፈ ልጎ ይመስላችኋል?...ህም!” ያስቀዳው ን ደብል አረቄ ብድግ አድርጎ ተጎነጨ፡ ፡ “ህም! ሰዉ ሁሉ ባለቅኔ ሆኗል!” በእ ርሱ ማብራሪያ ፈገግ ለማለት የቋመጠ ው ቀስቱ፣ “ምን ሊል ፈልጎ ነው?” ሲ ል ጠየቀ፡፡ “ትራንስፎርሜሽኑን እየተቸ እኮ ነው!” መለሰ አስር አለቃ፡፡ “ምን?” ሳቁን አፍኖ ጠየቀ ቀስቱ፡፡ “አገሪቱ አድጋለች፤ ተመንድጋለች እየተ ባለ የሚነገረውን ነዋ! ልብ ብለኸዋል ያለ ውን? ሰባት ከጠጣሁማ ሰክሬያለሁ እኮ ነው ያለው! ወይ ጉድ ሰዉ እንዴት ተና ጋሪ ሆኗል እባካችሁ! …ህም!” “እኮ ምን ለማለት ፈልጎ ነው? አስረዳ ኛ!” ቀስቱ ወጥሮ ያዘው፡፡ “ህም!” አስር አለቃ የአረቄውን ብርጭ ቆ ብድግ አድርጎ ጉሮሮውን አረጣጠበ፤ አቶ ጥጉ እና ናደው ጨዋታውን እየሰ ሙ ነው፡፡ “ይገርማል፤ እድገቱ ካለ፤ ትራንስፎር ሜሽኑ ግቡን ከመታ እኛ ታዲያ ምን ሆ ነን ነው በችግር የምንቆላው ለማለት ነ ዋ!” ሁሉም ሳቁ፤ ቀስቱ መጀመሪያውኑ

ለመሳቅ ነበርና ሲጎተጉት የነበረው ከት ብሎ ሳቀ፡፡ “የኔ ጌታ! አሥር አለቃን እህ ብለህ ከሰ ማኸው ህቅታ እና ሳል ሳይቀር ከፖለቲ ካ አንፃር ይተነትናል!” ናደው ነበር ተና ጋሪው፡፡ አስር አለቃ ግን፣ “…ህም!” እያ ለ ነገር መብላቱን ቀጥሏል፡፡ “ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች /አስር አለቃ፣ ቀስቱ ወደ ፊት የምናገኛቸው አቶ ዘሩ እ ና ናደው፤ እ… እዛ ማዶ ሆኖ፣ “ተባለ እ ንዴ ተባለ…” እያለ የሚያቀነቅነው አቶ አለሙ ቀጮ… / እነማን ናቸው? የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊስ ለምን ከዚህ ሁሉ ጠጪ መርጦ ለእነዚህ ሰዎች ጆሮውን ሰጠ?” ባይ ጠያቂ ካለ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ፡፡ አንደኛ የማውቃቸው የሚያውቁኝ፣ የቅ ርብ ጎረቤቶቼ ስለሆኑ፤ ሁለተኛ ለመስከ ር ሳይሆን ለመጫወት የሚመጡ በመ ሆኑና ጨዋታቸው ደስ ስለሚለኝ፤ ሦስ ተኛ… እ…? በቃ ይኸው ነው፡፡ “እናንተ ሆዬ! ይሄ የሚረጋው ዘይት እ ንደ ጓያ እግር ይሰብራል አሉ!” ተናጋሪ ው አቶ ዘሩ ናቸው፡፡ “ይሄ በቀበሌ የሚሸጠው ባለሃያው ሊ ትር?” አዳማቂው ቀስቱ ነው፡፡ “አዎ!” “ምናለ እንደ ልብ በተገኘና እጃችንንም ጭምር በሰባበረው!” ናደው ነበር መላ ሹ፡፡ “እውነቴን እኮ ነው!” “አቶ ዘሩ ኧረ ዝም በሉ!” አስጠንቃቂ ው ቀስቱ ነው፡፡ “ለምን?” “አዲስ አበባን በወሬ ባግዳድ ሊያደርጓ ት የተነሱ ሽብርተኛ ሽማግሌ ተብሎ ፊ ልም እንዳይሰራብዎ!” ይህን ጨዋታ ለመስማት የታደለው ሁ ሉ ፈገግ አለ፡፡ ከአቶ ዘሩ እና ከአስር አ ለቃ በስተቀር፡፡ አስር አለቃ “..ህም!” እ ያለ ብቻ አረቄውን መከካት ነው፡፡ “… ህም!” “እውነቴን እኮ ነው፤ ጎረቤቴ ቢተው ይ ሄን የሚረጋ ዘይት እየበላሁ ጉልበቴን ያ

ዘኝ ሲል ነበር፡፡” አቶ ዘሩ አምርረዋል፡፡ “ጉልበታቸውን የያዛቸው ዘይቱን ለመ ግዛት ቀኑን ሙሉ ለወረፋ የቆሙበት እ ንዳይሆን!” ናደው መለሰ፡፡ “ዞሮ ዞሮ ለአቶ ቢተው ጉልበት መታ መም ተጠያቂው ዘይቱ ነው!” ቀስቱ አ ከለ፡፡ “…ህም!” አስር አለቃ የቀስቱን ንግግር በህምታው አጀበው፡፡ “ኤዲያ ድሮውንም ከእናንተ ጋር…!” አ ቶ ዘሩ በብስጭት ወደ ድራፍታቸው እ ጃቸውን ላኩ፡፡ “እኔ የምለው…” ናደው ጣልቃ ገብቶ ምሬታቸውን አቋረጣቸው፡፡ “እ!” ጨዋታው እንዲቀየር የጓጓው ቀ ስቱ ጠየቀ፡፡ “የባግዳዱ ፊልም ጉዳይ ግን አልገረማ ችሁም?” “ምን ይገርማል?” ቀስቱ ጠየቀ፡፡

“የተባለው እውነት ቢሆን እስኪ…” የና ደውን ንግግር የቀስቱ ሳቅ አቋረጠው፡፡ ከትከትከት…. “ምነው ሳቅህሳ? አሁን ይሄ ቀልድ ሆኖ ነው?” አቶ ዘሩ ተቆጡ፡፡ “ትዕግስት ኖሯችሁ ፊልሙን እስከመ ጨረሻው ብታዩት ኖሮ የተዋንያኖቹ ስ ም ተጽፎ ታዩት ነበር፡፡” “እና ፈጠራ ነው እያልክ ነው?” አሥ ር አለቃ የመጀመሪያ ጥያቄውን በጉጉ ት ጠየቀ፡፡ “አላልኩም!” “እና ምንድነው?” ናደው አከለ፡፡ “በልቦለድ ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ታሪክ!” ቀስቱ መለሰ፡፡ ዘሩ እና ናደው ግ ራ በመጋባት እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ አስር አለቃ ግን፣ “ህም!” ብሎ ፈገግ አለ፡፡ /ም ን ማለቱ ነው? እኔ አልገባኝም! “በእውነ ተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ…” ሊል ፈል

ትላንት እና ዛሬ

ኤግዚቢሽን

ፊልም መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ጋርደን ሲቲ ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ)

ዩጋንዳ

ና?

ጎ ይሆን? በእውነት አልገባኝም!/ “ህም!” አለ አስር አለቃ ራሱን እየወዘ ወዘ፡፡ “በልቦለድ ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ታሪክ!” ቀስቱ ንግግሩን ደገመው፡፡ አስር አለቃ ግን ፈገግታ ባጀበው ህምታው ቀ ጥሏል፡፡ /እንጃ እንግዲህ! እናንተው እን ደመሠላችሁ ተረዱት/ ሰካራም ተባለ አለሙ፤ የሻዕቢያን ቅጥረኞች እየሰሙ!” አለሙ ቀጮ ከቅድሙ በባሰ ስካር ባበለሻሸው አንደበት ድምፁን ዘለግ አድርጎ እያንጎ ራጎረ ነው፡፡ ”አይ አለሙ ቀጮ! በገዛ ስካሩ ድራሹ ሊጠፋ ደርሶ ምናለ የነሻዕቢያን ስም ባያ ጠፋ!” ራሴው ለራሴው ተናግሬ በውስ ጤ ፈገግ አልኩ፡፡ “ተባለ እንዴ! ተባለ፤ ተባለ እንዴ ተባ ለ…”

ትላንት ይሄን ይመስል ነበር፣ በዛ በበጋ በዛ በበጋ በዛ በበጋ እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ መሸበትና ሰው ቤት ገባ ልጅቷን አያት ተከናንባ ወደደችው ወደዳት ይዟት ጠፋ በለሊት። ደግሞ ደግሞ ብዙ ተጓዙ አባይ ደረሱ በጣም ከሞላ ለመሻገር ሲሞክሩ ሰምጣ ቀረች የሱ ፍቅሩ አለቀሰ ሆዱ ባባ አለቀሰ የፍቅር እንባ የኔ ፍቅር የኔ ፍቅር አረሳሽም እስከ መቃብር ዛሬስ . . . ሄደሻል አንቺ አንድ ቀን ወደ ስራ ልገባ ከሰፈር ስወጣ አንድ የ4 አመት ህፃን “ያኔ ስትጠይቀኝ አትመለሽም። እሺ አለማለቴ- መግደርደሬ እኮ ነው እንደሴትነቴ...ቆጨጨጨጨኝ* ስትል መሞት እንደሆን ሰማኋት በሚያምር ቃጭል ድምጿ፡፡ አይቀርልሽም። (በፍቃዱ በየነ በፌስ ቡክ ከጻፈው) * ቆጨኝ የትዕግሰት ወይሶ ዘፈን ነው

ኮሜዲ

ንዝና የት ሄደን እ

በእግዜር /ከአራት ኪሎ/

ለካምፓላ ብቸኛ የሆነው ሲኒማ ቤት ሲኒፕሌክስ በሶስት የተለያዩ አዳራሾቹ የአሜሪካ እና የህንድ ፊልሞችን ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች ያቀርባል። ከጁን 24 ጀምሮ መታየት የጀመሩ ፊልሞች እነዚህ ናቸው። መቼ፦ ዘወትር ማክሰኞ እና ሀሙስ የት፦ ናኩማት ሞል አጠገብ ካለው ኤፌንዲስ (ሴንቲነሪ ፓርክ) እና ከብሔራዊ ትያትር ታችኛው መግቢያ በተቃራኒ ባለው ፓን ወርልድ የመኪና መሸጫ ቦታ ሰዓት፦ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ 10ሺህ ሽልንግ እና አምስት ሺህ ሽልንግ የዩጋንዳ ታዋቂ “ስታንድ ኦፕ” ኮሚዲያን የሆነው ፓብሎ በበሳል ቀልዶቹ ይታወቃል። ከእንግሊዘኛ ጋር ሉጋንዳ እና ሌሎች የሀገሪቱን ቋንቋዎች እየቀላቀለ በሚያቀርባቸው ቀልዶች ጥርስ አያስከድንም ይሉታል። ፓብሎ በ“ኦብዘርቨር” ጋዜጣ የሐሙስ እትም ላይ የራሱን አምድ ከፍቶ አንባቢዎችን ዘና ያደርጋል። በአብዛኛው ወጣቶች የተሰባሰቡበት የ“ፈን ፋክተሪ” አበላት ድራማዊ ይዘት ባላቸው ቀልዶቻቸው ይታወቃሉ። እንግሊዘኛ እና የተለያዩ የዩጋንዳ ቋንቋዎችን የሚጠቀሙት “ፈን ፋክተሪዎች” በእንቅስቃሴያቸው ብቻ ሳቅ የሚያጭሩ ናቸው። አብዛኞቹ የ“ፈን ፋክተሪ” አባላት በአሁኑ ወቅት በ“ኤንቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ እየተላለፈ በሚገኘው “ሆስቴል” ድራማ ላይ ይተውናሉ።

በቅርብ ቀን


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የአገር ቤት ጨዋታ

ሃና እና የቻይና ግንኙነት

አዲስ ነገር ኦንላይን

“ናዝሬት ፔንስዮን” አዲስ አበባ ኮሜርስ አካባቢ ከቴሌ ባር ገባ ብሎ የሚገኝ ሰፊ የአስረሽ ምቺው ቤት ነው

650 ትጠይቃለች። ከሀበሾች ይልቅ “ዜ ጋዎች” ይንከባከቡኛል ትላለች። በተለ ይ ፊሊፒኖች። ናዝሬት ፔንስዮን ቀኑ ገና ለዐይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ይከፈታል። የመጀመ ርያዎቹ ተስተናጋጆች ግን ቻይናውያን ፊሊፒንሶች ናቸው። አንዳንዴ የሥራ ሽ ርጣቸውን እንኳ ሳያወልቁ ናዝሬት ተን ደርድረው ይገባሉ። ጊዮን አካባቢ አላል ቅ ያለውን የኢትዮጵያ ሰማይ ጠቀሱን ና ኒ ሕንፃ የሚገነቡ ናቸው ብዙዎቹ። ቀሪ ዎቹ ደግሞ ቀለበት መንገድን ለማገናኘ ት የሚተጉ ናቸው። ሃና እና ጓደኞቿ እስ ኪመጡ ቢራ እየቀማመሱ ፑል በመጫ ወት ጊዜ ይገድላሉ። “ናዝሬት ፔንስዮን” ዕድሜ ጠገብ መሸ ታ ቤት ቢኾንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እድሳት አድርጎ በአዲስ የሥራ መንፈስ ነው ገበያውን የተቀላቀለው። የሰከረ ሰ ው ራሱን እያየ የሚደንስበት ስፍራን አዘ ጋጅቷል። በባለጌ ወንበሮች ላይ ቂብ ብ ሎ መጠጣት ያማረው በቤቱ የግራ ማእ ዘን አካባቢ መሰየም ይችላል። ኳስ እያ የ የጀበና ቡና ከቢራ ጋራ እያጣጣመ ከ ቤቱ ሴቶች ጋራ ድርድር ማድረግ የፈለ ገ በረንዳ ላይ በተዘረጋ ሰፊ አዳራሽ ው ስጥ ባሉ ሶፋዎች ላይ መንጋለል ይችላ ል። ቤቱ ውስጥ ቆሞ፣ ቁጭ ብሎ፣ ተን ጋሎ ለመጠጣት የሚያስችሉ ምቹ ስፍ ራዎች ተሰናድተዋል። ሲጋራ፣ ማስቲካ፣ ሶፍት፣ ኮንዶም እና የመሳሰሉትን ለመ ግዛት ወደ ውጭ መውጣት አይጠበቅ ም። “አማረ” የሚባል ልጅ እግር የሚያ ስተዳድራት ትንሽዬ ኪዮስክ ግቢው ው ስጥ ተቋቁማለች። እነ ሃና አሁንም አሁ ንም እየሄዱ አንድ ጊዜ ሲጋራ፣ አንድ ጊ ዜ ኮንዶም፣ ሌላ ጊዜ ሞባይል ካርድ ይ

ሸምታሉ፡፡ “አማረ ቆንጆ፣ እስኪ የሞባይል ካርድ ስጠኝ፤” “የቅድም የሲጋራ አልከፈልሽኝም እ ኮ…፤” “ብር ጨርሻለኹ አንድ “ዜጋ” ላውጣና አሰጥኻለኹ …” “ትናንት ለሜሪ 10 ብር ስጣት ብለሽኝ ሰጥቻታለሁ፣ እሱም አለብሽ።” “አውቂያለኹ! አሰጥኻለሁ አልኩህ እ ኮ፣ ያንን ዜጋ እያዳከምኩት ነው፣” “አሁን ካርድ ባለ ስንት ልስጥሽ፣” “የ‘ተሾመ ቶጋን’ አርግልኝ፤ አዲሱን፣” ለረዥም ጊዜ በገበያ ላይ ያሉት የሞባይ ል ካርዶች ባለ 100፣ ባለ 50 እና 25 ብ ር ብቻ ነበሩ። በቅርቡ ቴሌ ባለ 15 ብር ካርድ ገበያ ላይ እንዲኖር አድርጓል። ‘ተ ሾመ ቶጋ’ የሚል ስም የወጣለት ይኸው በቅርቡ ቴሌ ያስተዋወቀው ባለ 15 ብር የሞባይል ካርድ ነው። ሃናን ለምን የካር ዱ ስም እንደዚያ እንደተባለ ጠየቅኋት። “ሐሳብ አያስጨርስም አለችኝ።” ስቄ ለ ማባራት ጊዜ ወሰደብኝ። ባለፈው አም ስት ዓመት የፓርላማው አፈ ጉባዔ ሲያ ሳዩት የነበረው ጠባይ እና ሐሳብ የማያስ ጨርሱ ናቸው ለማለት ይኼ ካርድ ገበያ ላይ መምጣት ነበረበት ለካ። “ናዝሬት ፔንስዮን” ኪዮስክ ብቻ አይደ ለም ያለው። አይበለውና ተጠናቀው ሲ ወጡ ፓንትዎ ቢበላሽ ደጅ ሳይወጡ እ ዚያው ይሸምታሉ። አይበለውና ለሾርት ሊገቡ ሲሉ የእግርዎ ጠረን አሳሰበዎ። አ ዲስ ካልሲ እዚያው ይሸጣል። ያውም የ ቻይና። ለሴቶች ጡት መያዣ እና ንጽሕ ና መጠበቅያም በግቢው ይሸጣል። “ናዝሬት” ጥሎበት በቻይና እና ቻይና በሚመስሉ ዜጎች ይወደዳል። የቤቱ 60

ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ

ጥራትም ጭምር ይታወቃል። ብዙም ጉ ስቁልና ያልደረሰባቸው፣ ሰውነታቸው ያ ልሟሸሸ እና የጨዋ የሚመስል፣ የዕድ ሜ ኪሎ ሜትራቸው ከሰላሳ ያልዘለለ፣ ብዙ ያልተጎበኙ የሚመስሉ ሴቶች ለወ ንዶች ዐይን ማረፍያ የኾኑበት ቤት መ ኾኑ ተመራጭ ያደርገዋል ይላሉ የረዥ ም ጊዜ ደንበኞቹ። ይህ ቤት ሁለት ዐይነት የዝሙት ዋጋ ሜኑ የሚያቀርብ ነው። ለዜጋ እና ለሀ በሻ። በዚህ ቤት አጠራር ዜጋ የሚባሉ ት ከኢትዮጵያውያን ውጭ ዜግነት ያላ ቸውን ሲኾን በተለይም የቻይና እና የፊ ሊፒንስ ዜጎች ላይ ያተኮረ ዐይነት ነው። አንዲት የቤቱ ኮማሪት አንድ የቻይና ዜ ጋ ለማውጣት መውጫ ግብር 50 ብር መክፈል ሲጠበቅባት ከሀበሾች ጋራ ሲ ኾን ግን 30 ብር ብቻ በቂዋ ነው። በና ዝሬት ፔኔሲዮን ለሾርት/quickie/ አንድ አልጋ ለዜጋ (ቻይና እና ቻይና መሰል ደ ንበኞች ማለት ነው)150 ብር ሲወሰንባ ቸው ሀበሾቹ 100 ብር ብቻ ይከፍላሉ። ሃና ወደዚህ ቤት በከፍተኛ ዝውውር ከመጣች ሁለት ዓመት ለመድፈን ጥቂ ት ሌሊቶች ይቀሯታል። የሕዋ ርቀት በ ብርሃን ይለካል፣ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ በ ማይክሮ ሰከንድ ይቆጥራል፣ ሃና በሌሊ ቶች ብዛት ዕድሜዋን ታሰላለች። የኻያ አራት ወራት ሌሊቶችን ከሞላ ጎደል በና ዝሬት ፔንስዮን አልጋዎች ላይ አሳልፋለ ች። ከዜጎች ጋር። ሃናን ከሌሎች የ“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮ ማሪቶች ልዩ የሚያደርጋት ከቻይናውያ ን እና ከፊሊፒንስ አገር ሰዎች ጋራ ያላት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። ሃና ለሀበሻ ወንድ ጊዜ እና ግድ የላትም። ሁልጊዜ በቁመት ከሚያንሷት የሩቅ ም ሥራቅ ኮበሌዎች ክበብ ሥር ናት፤ ትኾ ናለች፤ ይወዷታል። በጊዜ መጥተው እ ርሷን የእነርሱ ለማድረግ ይሟሟታሉ። ቋንቋ በማይመስል ቋንቋ የኾነ ነገር እያ ሏት ከት ብለው ይስቃሉ። እርሷም በቻ ይንኛ ከት ብላ ትስቃለች። ሳቃቸው ቤ ጂንግ እና ማኒላ ይሰማል። ኾኖም በአንድ ሌሊት ከአንድ አልያ ም ከሁለት ቻይናውያን ጋራ ብታድር ነ ው። ሌሎች ቤቱን የሚሞሉት ቻይና መ ሰል ዜጎች ግን ሃናን በቢራ አታለው፣ ጭ ኗን ደባብሰው ሹልክ ይላሉ። ተንጠራ ርተው አንገቷ ሥር ሳስመው ይሰናበቷ ታል። ሃና ገላዋን ለመጋራት ለሚሹ ዋጋዋ የ ሚያደራድር አይደለም። ለአጭሬ ብር 350፣ እንዲሁም ለአዳር ብር ከ500-

ገዛኸኝ ይርጋ

ፎቶ ዮሐንስ አባይ

ና አገር አይደለችም፤ ኢ ትዮጵያዊት ሴተኛ አዳ ሪ እንጂ። ገላዋን ለቻይ ናውያን እና ለእነርሱው መሰል ዜጎች በማከራየ ት የምትተዳደር የሌት ለፍቶ አዳሪ። የሃ ና እና የቻይናውያን ዲፕሎማሲያዊ ግን ኙነት “ናዝሬት ፔንስዮን” ባለጌ ወንበር ላይ ተጀምሮ ጓሮ 150 ብር በሚከፈልበ ት አልጋ ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። ሁል ጊዜ፤ ማታ ማታ። “ናዝሬት ፔንስዮን” አዲስ አበባ ኮሜ ርስ አካባቢ ከቴሌ ባር ገባ ብሎ የሚገ ኝ ሰፊ የአስረሽ ምቺው ቤት ነው። መ ካከለኛ ገቢ ያላቸው አዲስ አበቤዎች አ ማርጠው ዝሙት መግዛት ሲሹ ሦስት ቤቶችን ያዘወትራሉ። የፒያሳውን “በአ ካል. ፀ”፣ የኻያ ሁለት ማዞርያውን “ሰ ገን”ን እና የኮሜርሱን “ናዝሬት ፔንስ ዮን”ን። ሦስቱም ተመሳሳይ የአስተዳደ ር፣ የአሠራር እና የአመራር ስልትን ይከ ተላሉ። በእነዚህ ሦስት ቤቶች ምን የመ ሰሉ ዲጄዎች ምን የመሳሰሉ ሙዚቃዎ ችን ያጫውታሉ፡፡ ደንበኞችን በሁሉም መልኩ የሚያጫውቱ ብዙ የቡና ቤት ሴቶች ያሉትም በእነዚህ ሦስት የአዲ’ሳ ባ ዝነኛ መሸታ ቤቶች ውስጥ ነው። ነ ጭ ጋውን የለበሱ ተቆጣጣሪዎች፣ ደረ ታቸውን ያሳበጡ ቦዲጋርዶች፣ ቢራ የ ሚያቀርቡ ወንድ አስተናጋጆች በሦስቱ ም መሸታ ቤቶች ተመሳሳይ በሚባል መ ልኩ ይገኛሉ። ናዝሬት ፔንስዮን ይህ ጽሑፍ በሚጻፍ በት ወቅት 27 ኮማሪቶችን ያስተዳድር ነ በር። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ወደ ሥራ የሚገቡት የናዝሬት የምሽት ኮማሪ ቶች ልክ እንደ መደበኛ የመንግሥት መ ሥርያ ቤት የሚተዳደሩበት ያልተጻፈ ሕ ግ እና ደንብ አላቸው። ለምሳሌ ሁሉም ሴቶች ወደ ሥራ ሲገቡ በረንዳው ላይ በ ተቀመጠ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን እና የገቡበትን ሰዓት ያኖራሉ። ባልተጻፈው ሕግ መሠረት ማንኛዋም ሴተኛ አዳሪ ደ ንበኛን ማንጓጠጥ በፍፁም አይፈቀድላ ትም። ለዳንስ ከተዘጋጀው ስፍራ ውጭ በጠረጴዛ ዙርያ ከደንበኛ ጋራ መላፋት ም ኾነ መደነስ አይቻልም። ደንበኛ ለአ ጭሬ /ሾርት/ መስተናገድ ካሻው ሴቷ ለ ሚመለከተው አለቃዋ በቃል ወይም በ ጥቅሻ ማሳወቅ ግዴታዋ ነው። ለአዳር ከኾነ ደግሞ የመውጫ ግብር ብር 30 መክፈል ይጠበቅባታል። ናዝሬት ፔንስዮን በሚያስተዳድራቸው ሴተኛ አዳሪዎቹ ብዛት ብቻም ሳይኾን

17

ቻይኖች ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው። ጥንካሬያቸው ግን ምሽት ላይ አይደገምም

በመቶ ደንበኞች እነዚህ ዐይናቸው ጠበ ብ ያሉ ዜጎች ናቸው። ለምን ይህን ቤት መረጡ ሲባል ግን መልስ የሚሰጥ የለ ም። በየዕለቱ የእነዚህ ቻይና መሰል ፍ ጡሮች ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። የገዥው ፓርቲን የዲፕሎ ማሲ አዝማምያ ተከትሎ የሚሠራ ቤት ይመስላል። የቤቱ ዲጄዎችም ይህንኑ በ መረዳት አንድ መላልሰው የሚያጫው ቱት የቻይና ዜማ እንዳለም ተነግሮኛል። ሁሉም አስተናጋጆች ዐይኑ የጠበበን ሁ ሉ ቻይና እያሉ ይጠራሉ። ሃና ግን ማ ን ምን እንደኾነ ጠንቅቃ ከማወቋም በ ላይ ቋንቋቸውን ትሞካክራለች። ከሁሉ ም ዜጎች ሃና በፊሊፒንሶች ፍቅር የወደ ቀች ይመስላል። እርሷ እንደምትለው ፊ ሊፒኖች ለሴት ልጅ ክብር ይሰጣሉ፣ ጥ ሩ ይከፍላሉ። ጥሩ ይጋብዛሉ፣ ርኅራሄ አላቸው። ፍቅር ይሰጣሉ። ሃና ከእኔ ጋ ራ በነበረችበት ወቅት በተደጋጋሚ ከፊ ሊፒኖች ስልክ ሲደወልላት ሰምቻለኹ። እንግሊዝኛ እና ፊሊፒኖ እየቀላቀለች ታ ወራቸዋለች። ብዙዎቹ ፊሊፒኖች ሜድሮክ ውስጥ ሠ ራተኞች እንደኾኑ ሃና ነግራኛለች። ብስ ራተ ገብርዔል አካባቢ የሚገኘው ዳግም ሚሌኒየም ሆቴል ውስጥ ነው የሚኖሩ ት። የተወሰኑት ደግሞ “ራስ ሆቴል” ያ ድራሉ። ሃና በተደጋጋሚ እዚያ ይዘዋት እንደሚሄዱ ትናገራለች። “አንድም ጉዳ ት አድርሰውብኝ አያውቁም። አብረን አ ድረን፣ ጋብዘውኝ፣ ሸኝተውኝ እንለያያለ ን” ትላለች። የተወሰኑት ቋሚ ደንበኞቿ ን ስም እየጠራች በእርግጠኝነት አግብተ ው እንደሚወስዷትም ትናገራለች። “ጃ ክ በጣም ነው የሚወደኝ፣ እኔም እወደ ዋለሁ፣ የሚስቴን ፍቺ እንደጨረስኩ ይ

ዤሽ እሄዳለኹ ብሎኛል” ትላለች ለእር ግጠኝነት ሩብ በጎደለው ተስፋ። ሃና ከፊሊፒኖ ቋንቋ ወሳኝ የምትላቸው ን ቃላት ነግራኛለች። ልክ ትሁን አትሁ ን ግን የማውቀው ነገር የለም። “ቻካ ቻ ካ” /ጨዋ ያልኾነ ስድብ/፣ “ኢቃው”/ አ ንተ፣ አንቺ ማለት ነው/፣ “ሲራዉሉ”/ እ ብድ፣ “መሃላ ማልጊታ” /እወድኻለሁ/ ፣ “አዲባባህ” /አንተ የኔ ነህ/። የሃና የፊሊ ፒኖ መዝገበ ቃላት ታድያ ከስድብ እና ከፍቅር ቃላት ዘሎ አያውቅም። ሃና ከቻይኖች ጋራ ያላት አግባብም እን ደፊሊፒኖዎቹ አይሁን እንጂ መልካም ነ ው። እንደ ቡና ስኒ ተመሳሳይ የኾኑ ቻ ይናዊያንን አንዱን ከሌላው ለመለየት አ ፍንጫና ፀጉራቸውን አተኩራ ታያለች። ከዚያም በስማቸው ትጠራቸዋለች። ቻ ይኖች ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው። ጥን ካሬያቸው ግን ምሽት ላይ አይደገምም። እንደ ሃና መረጃ ከኾነ ቻይናውያን እን ደሚሠሩት ቀለበት መንገድ ዘለግ ያለ የ ፆታ ባንዲራ/ብልት/ የላቸውም። ሃና መ ጠኑን የምትገልጸው ትንሿን የእጅ ጣቷ ን ለብቻዋ አውጥታ በማሳየት ነው። ይ ህ መልካም ነገር ነው ለሃና። ለእርሷ ከ ዚያ ይልቅ ጠረናቸው ምቾት አይሰጣት ም። “በጡት ፋንታ ሲጋራ ነው እንዴ እያጠቡ ያሳደጓቸው” ስትል ትሳለቃለ ች። ይህን እያወራች “እስኪ ሲጋራ ስጠ ኝ” ትላለች አስተናጋጁን በጥቅሻ እየጠ ራች። ሲጋራው ሲመጣላት ግን አስተና ጋጁ እንዲለኩስላት አትፈቅድም። በአቅ ራቢያዋ እየተዝናና ካለ ቻይናዊ ጋራ ሄ ዳ ለኩስልኝ ትለዋለች። በቻይንኛ ይሽ ኮረመማል። የሃና እና የቻይናውያን ግ ንኙነትም ለቀጣዩ ደረጃ ሰዓቱን ይጠብ ቃል።

ቋንቋ በየፈርጁ ቁጥሮች በስዋሂሊ

ዛሬም ስዋሂሊ ቋንቋ ላይ ነን። ለዛሬ በዕለት ከዕለት ሕይወታችን በተደጋጋሚ ከምንጠቀምባቸው ቃላት መካከል ቁጥሮችን እንመለከታለን

1. Moja ሞጃ- አንድ 2. Mbili ምቢሊ- ሁለት 3.Tatu ታቱ- ሶስት 4. Nne ኢኔ- አራት 5. Tano ታኖ- አምስት 6. Sita ሲታ- ስድስት 7. Saba ሳባ- ሰባት 8. Nane ናኔ- ስምንት 9.Tisa ቲሳ- ዘጠኝ 10. Kumi ኩሚ- አስር 20. Ishirini ኢሽሪኒ- ሀያ 30.Thelathini ሴላሴኒ- ሰላሳ 40. Arobaini አሮባኢኒ- አርባ 50. Hamsini ሀሙሲኒ- ሀምሳ 60. Sitini ሲቲኒ- ስልሳ 70. Sabini ሳቢኒ- ሰባ 80. Themanini ሴማኔኒ- ሰማንያ 90. Tisini ቲሲኒ- ዘጠና

100. Mia moja ሚያ ሞጃ au (ወይም) mia ሚያ- አንድ መቶ 1000. Elfu moja እልፉ ሞጃ- አንድ ሺህ 2000. Elfu mbili እልፉ ምቢሊ- ሁለት ሺህ 10,000. Elfu kumi እልፉ ኩሚ- አስር ሺህ 20,000. Elfu Ishirini እልፉ እሽሪኒ- ሀያ ሺህ እያለ ይቀጥላል። 100,000. Elfu mia moja እልፉ ሚያ ሞጃ- አንድ መቶ ሺህ 200,000. Elfu mia mbili እልፉ ሚያ ምቢሊ- ሁለት መቶ ሺ ህ እያለ ይቀጥላል። 100,000,000. Milioni moja ሚሊዮኒ ሞጃ- አንድ ሚሊዮን 1,000,000,000. Bilioni moja ቢሊዮኒ ሞጃ- አንድ ቢሊዮን ማስታወሻ፡እንደ አማርኛው ሁሉ በስዋሂሊም ከአንድ እስከ አስር ያሉት ቁጥሮች ራሳቸውን ችለው የሚመጡና የሚነበቡ ሲሆን ከአስር እስከ ሀያ ያሉት ቁጥሮች ልክ በአማርኛው አስራ እንደሚባለው በኩሚ(አስር) እና በሚጠራው ቁጥር መካከል አያያዥ “na” ‹‹ና››

እየተጨመረበት ይነበባል፡፡ ከሃያና ከዚያም በኋላ የሚመጡት ተቀጥያዎችም እንዲሁ ይነበባሉ፡፡ Mfano ሚፋኖ (ምሳሌ) m Kumi na moja ኩሚ ና ሞጃ አስራ አንድ m Kumi na mbili ኩሚ ና ምቢሊአስራ ሁለት እያለ ይቀጥላል፡፡ m Ishirini na moja ኢሽሪኒ ና ሞጃሀያ አንድ m Ishirini na mbili ኢሽሪኒ ና ምቢሊሀያ ሁለት m Thelathini na tatu ሴላሴኒ ና ታቱሰላሳ ሶስት m Arobaini na tano አሮባኢኒ ና ታኖ-አርባ አምስት ወዘተ እያለ ይነበባል ማለት ነው፡፡ n n n ቁጥሩ ከአንድ መቶ በላይ ሲሆንም ከፊቱ መቶ

እየተጻፈ ወይም እየተነበበ ቅጥያው ከላይ በተገለጸው መልኩ ይጻፋል ወይም ይነበባል፡፡ ለምሳሌ፡m Mia moja na tano ሚያ ሞጃ ና ታኖ-አንድ መቶ አምስት m Mia moja kumi na mbili ሚያ ሞጃ ኩሚ ና ምቢሊ-አንድ መቶ አስራ ሁሉት ወዘተ… n n n ቁጥሩ በሺዎች ሲገባም በተመሳሳይ መልኩ ይገለጻል፡፡ ለምሳሌ፦ m Elfu mbili na tano እልፉ ምቢሊ ና ታኖ- ሁለት ሺህ አምስት m Elfu tisa mia mbili na sita እልፉ ቲሳ ሚያ ምቢሊ ና ሲታ- ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ስድስት ወዘተ …

ምራቂ

onasi)

(ቦናሲ-B n n n n n

(+) Jumlisha ጁመሊሻ መደመር (-) Toa ቶአ- መቀነስ (X) Zidisha ዚዲሻ- ማባዛት (፥) Gawanya ጋዋኛ- ማካፈል (=) Sawana ሳዋና- እኩል ይሆናል

q Ngapi? እንጋፒ - ስንት ነው? q Ngapi pesa? እንጋፒ ፔሳ- ዋጋ ው ስንት ነው? q Nini? ኒኒ- ምን? q Nani? ናኒ- ማን? q Lini? ሊኒ- እንዴት? q Kwa nini? ኩዋ ኒኒ- ለምን?


ሐበሻዊ ቃና

የሐበሻ ጀብዱ... ከገጽ 15 የዞረ ራ ሸንተረሩን እያቋረጡ በተለያዩ የጦር ሜዳዎች ላይ ውለዋል። በእነዚህ ጦርነቶች ወቅት ታዲያ እንዲ ያ የሚያደንቋቸው ንጉስ ይሰሯቸው የነ በሩ ስህተቶችን ለመታዘብ የቻሉት። ስ ህተቶቹንም በመጽሀፋቸው ላይ በግል ጽ አስፍረዋል። እንዲያውም የኢትዮጵ ያ ጦር የአድዋውን ድል በኢጣሊያኖች ላይ ለመድገም ያስችለው የነበረውን ተ ደጋጋሚ እድል ያጣው በአጼ ኃይለ ስላ ሴ ምክንያት እንደነበር በድፍረት ተችተ ዋል። “ንጉሰ ነገስቱ ኃይለ ስላሴ ለሁሉ ም የጦር አበጋዞቻቸው በሰጡት ጥብቅ ትዕዛዝ ‘ምንጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያ ሰ ራዊት ከመከላከል አልፎ ቀድሞ ጥቃት እንዳይሰነዘር’ ደጋግመው አስጠንቅቀዋ ል። ኃይለ ስላሴ አሁንም የመንግስታቱ ህብረት ‘የጣልያንን ወራሪ ሰራዊት ያቆ ምልናል’ ብለው ያምናሉ። ንጉሰ ነገስቱ በዚህ ስህተት በተሞላበት እምነታቸው ከባድ ጥፋት ሰርተዋል። ልክ እንደገናና ው ምኒልክ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት የ ጣልያንን ሰራዊት ልክ ሊያስገባው የሚ ችልበትን ብዙ ዕድል አሳጥተውታል።”

ወታደራዊ ስህተቶች ፓርለሳክ ንጉሱ ሰርተውታል ብሎ ከ ሚቆጭበት “ከባድ ጥፋት” ሌላ ጦርነ ቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ እስከ ፍጻሜ ው ድረስ በየጊዜው ያስተዋሏቸውን ስህ ተቶች በመጽሐፋቸው አካትተዋል። በ መጽሐፋቸው መጀመሪያ ያነሱት የዝግ ጅት ጉዳይን ነበር። እንደጸሀፊው አባባ ል ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ዳግም ለመው ረር ቅድመ ዝግጅታቸውን ኢትዮጵያኖ ች አፍንጫ ስር ሲያጧጡፉ ሀበሾቹ አ ላስተዋሉም አሊያም ችላ ብለው ነበር። “እውነት ለመናገር ኢትዮጵያ ለጦርነት ዝግጁ አልነበረችም” ይላሉ ጸሀፊው ንጽ ጽራቸውን ሲጀምሩ። “የሞሶሎኒ ሰላዮ ች በሃይማኖትና በተለያዩ የሳይንስ ምር ምሮች ስም ያልዳሰሷት መንደር፣ ቀበሌ፣ አምባ አልነበረችም። ከእነዚህ ተመራማ ሪዎች መሀል አንዳንዶቹ በጦር ሜዳ ታ ላላቅ የጦር መኮንኖች ማዕረግ ይዘው ታ ይተዋል” ይላሉ። ጸሀፊው ጦርነቱ ከመጀመሩ ስድስት ዓ መት በፊት ከጓደኛቸው ጋር ወደ ኢትዮ ጵያ በመጡበት ጊዜ ጣሊያኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ጠንካራ ምሽጎች ሲገነቡ ማየታቸውን እና በወቅቱ መገረ ማቸውን ያትታሉ። እርሳቸው አይተው እንዳለፏቸው አይነት ክስተቶች በየቦታ ው ይከሰቱ እንደነበር በምሳሌ እያስደገ ፉ አቅርበዋል። “የጣሊያን መኮንን የመ ሳሪያ ግምጃ ቤት ሹም አመቱን ሙሉ ወ ደ ኢትዮጵያ ድንበር የጦር መሳሪያ ሲያ ጓጉዝ እንደነበረ፣ ጣሊያኖች በትልልቆቹ የኢትዮጵያ ከተሞች በሙሉ ከፍተኛ ወ ታደራዊ ማዕረግ ባላቸው ሰዎች የሚመ ሩ ቆንስል ቢሮዎችን መክፈታቸውን፣ በ መላው ኢትዮጵያ በቁልፍ ቦታዎች የተሰ ገሰጉ ሰላዮች እንደነበሯቸው እና ሌሎች ንም ሁነቶች እያነሱ የጣሊያንን ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ያሳያሉ። ኢትዮጵያውን በተቃራኒው ከነበራቸ ው የአሸናፊነት ወኔ ባሻገር በቅጡ አለ መዘጋጀታቸውን እርሳቸው የነበሩበት የ ሰሜኑን ዋና ጦር ውሎ እና አዳር ዋቢ በ ማድረግ ያስረዳሉ። “ምንም እንኳ አብ ዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያው ያንና በጣልያኖች መካከል ያለውን የኃ ይል ሚዛን አሳምረው ቢያውቁም አንዳ ቸውም እንሸፋለን የሚል ሃሳብ በፊታቸ ው ላይ አይነበብባቸውም” ይላሉ ፓርለ ሳክ። አንድ የፖስታ ቤት ሰራተኛ “አድ ዋ ላይ እንዳሸነፍናቸው ሁሉ አሁንም እ ናሸንፋቸዋለን” እንዳላቸው ይጠቅሱ እ ና ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የሕዝብ ስ ሜት ያስቃኛሉ። አንዱ “ ጣልያኖች ጦርነቱን ሊያሸንፉ አይችሉም” ሲል ሌላኛው ጦርነቱ መ

ቶ ዓመት እንደሚፈጅ መተንበዩን ቀሪ ው ደግሞ “ኢትዮጵያውያንን በሀገራቸ ው የሚያሸንፋቸው የለም” ሲል መፎከ ሩን ይጠቅሳሉ። በጃንሆይ ሹመት የሰሜ ኑ ጦር መነሻ ወደሆነው ወደ ደብረ ታቦ ር ሲወርዱም የገጠሟቸው ይሄው እንደ ነበር በተደጋጋሚ ጽፈዋል። ከወኔ ባሻገ ር ግን የሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦር በአግባ ቡ የተደራጀ እንዳልነበር፣ በቂ መሳሪያ ም እንዳልታጠቀ፣ የሚጠለልበት ድንኳ ን ቀርቶ ለእግሩ እንኳ መጫሚያ የሌለ ው፣ በወታደራዊ ዩኒፎርም ምትክ እንደ ማንኛውም ባላገር ሸማ የለበሰ እና ትክ ክለኛ ቁጥሩ የማይታወቅ እንደነበር ጸሀ ፊው በሀዘኔታ ያነሳሉ። “አብዛኛው ሰራዊታችን ከየጥሻውና ከ የአምባው የመጣና ጦርና ጎራዴ ብቻ የ ታጠቀ፣ በመጀመሪያው ቀን ውጊያ ጠላ ት ገድሎ ጥሩ መሳሪያ ለመታጠቅ በጽኑ እምነት የቆመ ጀግናና ጉጉ ጦር ነበር” ሲ ሉ የሰሜኑን ጦር ይገልጹታል። ለዓመታ ት ከቤልጄየም እና ስዊዲን በመጡ መኮ ንኖች ሲሰለጥን የከረመው የንጉሰ ነገስ ቱ ጦር ከተደፈረው ድንበር አካባቢ እስ ኪደርስ ጣሊያንን እንዲመከት አደራ የ ተጣለው እንግዲህ ለዚህ ጦር ነበር። ወ ደ ሃምሳ ሺህ እንደሚጠጋ የሚገመተው የሰሜኑ ጦር ከኢጣሊያን አውሮፕላኖች የሚደርስበትን የማያቋርጥ የቦምብ ድብ ደባ ተቋቁሞ እስከ ተንቤን በመጓዝ በእ ርግጥም ጀብዱ ፈጽሟል። ጸሀፊው የሚያደንቁበት ቃላት እስኪያ ጥራቸው ድረስ ደጋግመው የሚገልጹት የሰሜኑ ጦር ጀግንነት ከወታደራዊ ስህ ተት የጸዳ አልነበረም። ከስህተቶቹ አን ዱ እና ዋነኛው ጦሩ ይጠቀምበት የነበ ረው ኋላ ቀር የሬድዮ ግንኙነት ነበር። በእነዚህ ዓይነት ሬድዮ በኦፕሬተሮች አ ማካኝነት የሚደረገው ግንኙነት በቀላሉ ሊጠለፍ እንደሚችል የተገነዘቡት ፓር ለሳክ ራስ ካሳን ያስጠነቅቃሉ። ከሰሜኑ ጦር አዛዥ የተሰጣቸው መልስ ግን አላ ሳመናቸውም። “ራስ ካሳ ሳቅ ብለው ት ከሻዬን ቸብ ቸብ እያደረጉ ‘አይዞህ እኔ ና እርሳቸው የምስጢር ቃል አለን፤ ተነ ጋግረንበታል። ከንጉሴና ተ’ኔ በቀር ማን ም አያውቀውም’ አሉኝ” ይላሉ በመጽ ሐፋቸው። ፓርለሳክ ስጋታቸው ልክ እንደነበር በ ስተኋላ ላይ መረጋገጡን የኢጣሊያን ጦ ር ዋና አዛዥ የነበረውን ማርሻል ባዶሊ ዩ እና ሌሎችንም ምንጮች በእማኝነት ይጠቅሳሉ። “ራሱ ማርሻል ባዶሊዩ ብዙ ጊዜ ከንጉሰ ነገስቱ የሚተላለፉ ወታደራ ዊ አመራሮች በሰሜን ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጦር ሳይደርስ እጁ ይገባ እንደነ በር አምኖ ተናግሯል። የጣልያን ሬድዬ ኦፕሬተሮች ከንጉሱ ለእኛ የሚተላለፉና ለእኛ ቀልጣፋ ኦፕሬተሮች እንኳ ለፍቺ ጊዜ የሚወስዱ መመሪያዎችን ያለአንዳ ች ቁልፍ በቀላሉ ይፈቱ እንደነበር በኋላ ላይ አይተናል” ይላሉ። ይህ መረጃ አስቀድሞ በጠላት እጅ የመ ድረስ ሁነት ለማይጨው የኢትዮጵያ ጦ ር ሽንፈት እንደአንድ ምክንያት ተጠቅሷ ል። “ጃንሆይ ልክ እንደራስ ካሳ ሁሉ ት ልቅ ስህተት ሰሩ። ለማርሻል ባዶሊዮ የ ማይጨው ጥቃት ዘመቻ ምስጢር አል ነበረም። ማርሻል ባዶሊዮ አልገረመው ም” ይሉና ንግግራቸውን በምሳሌ ያስደ ግፋሉ። ጃንሆይ ለእቴጌ መነን አስተላል ፈውት ነገር ግን በጣሊያን ቴሌግራፊስቶ ች እጅ የወደቀን መልዕክትም ቃል በቃ ል በመጽሐፋቸው ያስቀምጣሉ። “ከጠ ላት ጦር ሰፈር ተቃርበን ተፋጠናል፤ እ ርስ በእርስ በጦር ሜዳ መነጽር እየተያየ ን ነው” ሲሉ መልዕክታቸውን የሚጀም ሩት ጃንሆይ በማስከተል ታላቅ ወታደ ራዊ ምስጢር ለባለቤታቸው ያጋራሉ። “ሰዎች አንደሚሉት ከእኛ ጋር ጦር ነት ሊገጥም የተዘጋጀው የጠላት ጦር ከ10000አይበልጥም። የእኛ ሰራዊት [ግ ን] በትክክል 51000 ነው። ግን እንዲያ ው ወደ ጠላት የጦር ሰፈር ስንቃኝ እ ና ስንመረምር በእኛ ግምት የጠላት ጦ

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ፎቶ- ኢትዮጵያን ሪቪው

18

ራስ ካሳ ሃይሉ እ.ኤ.አ ከ1935 እስከ 1936 በተካሄደው የኢትዮ- ጣሊያን ጦርነት ወቅት የሰሜኑ ግንባር አዛዥ የነበሩ ናቸው። ይህንን ፎቶ የተነሱት አጼ ኃይለ ስላሴ ዘውዳቸውን በጫኑበት ዕለት ነው።

ር 20000 ይሆናል እያልን እናስባለን። የእኛ እምነት በፈጣሪ ላይ ነውና እንደ ሚረዳን በጽኑ እናምናለን” ሲሉ መልዕ ክታቸውን ይደመድማሉ። ጣሊያኖች ይህንን ብቻ ሳይሆን ሌላ ጥብቅና ወሳ ኝ መረጃም በገመድ የለሽ ሬድዮ ሲተላ ለፍ እጃቸው ገብቷል። “ቅዳሜ መጋቢ ት 28 ቀን በጠላት ላይ ዘመቻ እናደር ጋለን። ቅዳሜ ባይሆንልን ሰንበትን ውለ ን ሰኞ ማለዳ የማይቀር ጉዳይ ነው” ይላ ል መልዕክቱ። እንዲያም ሆኖ የኢትዮጵያ ጦር በማ ይጨው ጦርነት ብርቱ ተጋድሎ አድር ጎ ነበር። በሶስት ራሶች እና በአንድ የደ ጃዝማቾች ስብስብ የሚመራው ጦር ሶ ስት ጊዜ ያህል ማይጨውን ለመያዝ ጦ ርነት አድርጎ በስተመጨረሻ የተሰካላት መስሎ ነበር። ጣሊያኖችን ማሸነፍ የቻ ለው ጦር ከጣሊያን ጋር ባበሩት ራያዎ ች እና አዘቦዎች በደረሰበት ጉዳት መሸ ነፉን ፓርለሳክ መሰክረዋል። ራያዎች እ ና አዘቦዎች የኢትዮ-ጣሊያን ጦርነት ከ ተጀመረ አንስቶ ከጣሊያኖች በተቀበሉ ት አዳዲስ መሳሪያ ታግዘው ለኢትዮጵያ ጦር የጎን ውጋት ሆነው የቆዩ ነበሩ። በ ስተመጨረሻ የጦርነቱን አካሄድ የሚወ ስኑ ሆነዋል።

አቢቹ ደራ ደራ… በእዚህ ወሳኝ ጦርነት በራሶች ይመራ የ ነበረው ጦር በሁለት ዙር ሲሸነፍ በደጃ ዝማቾች የተመራው ጦር ግን ድል ቀንቶ ት ነበር። ከመሪ ደጃዝማቾች መካከል አ ንዱ በነበረው ደጃዝማች አበራ የሚመ ራው ጦር ለየት ያለ ታሪክ ነበረው። የሰ ሜኑ ጦር አዛዥ የሆኑት ራስ ካሳ ልጅ የ ሆነው ደጃዝማች አበራ በማይጨው ጦ ርነት በወጉ እንኳ ጺም ያላበቀለ ለግላ ጋ ወጣት ነበር። በዚያ ላይ የዕድሜው ን ግማሽ ያህል በአውሮፓ ትልልቅ ከተ ሞች በትምህርት ያሳለፈ እና እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ አሳምሮ ይናገር የነበረ ነ ው። እንደ አባቱ ጦር ሁሉ መነሻው ከሰ ላሌ ፍቼ የሆነውን ወደ 20 ሺህ ግድም ጦር ይዞ ነበር ወደ ጦርነት የዘመተው። በአብዛኛው ፈረሰኛ የነበረው ይሄው ጦር ከራስ ካሳ ጦር ጋር አምባላጌ ላይ ነው ይቀላቀል። ይሄኔ ነበር ፓርለሳክ የ ደጃዝማች አበራን ጦሩ ለመመልከት እ ና ከወጣቱ መሪ ጋር ለመተዋወቅ የበቃ ው። የደጃዝማች አበራ ጦር “ከሌላው የ

ኢትዮጵያ ሰራዊት የሚለዩበት ነገር ቢኖ ር ስነ ስርዓታቸው ነው” ሲሉ ፓርለሳክ ይመሰክራሉ። ጦሩ ጣሊያኖች ድል በተ ነሱበት የአቢ አዲ ጦርነት ላይ ከፍተኛ ሚና ቢጫወትም ሁለቱን ፊታውራሪዎ ች ያጣል። ይሄኔ በደጃዝማች አበራ ጦር ሰፈር ጭንቅ ይፈጠራል። ሁለቱ ፊታውራሪዎች ወንድማማቾች እና ምንጩ ከወረጃርሶ የሆነው የደጃ ዝማች አበራ ቀዳሚ ጦር መሪዎች ነበ ሩ። የእነርሱ ተተኪ በመሆን የጦሩን የፊ ታውራሪነት ሚና እንዲረከብ የሚጠበቀ ው ዕድሜው 17 የሚገመተው ወንድማ ቸው ነበር። እርሱ ደግሞ የአንደኛው ወ ንድሙን አስክሬን ከጦር ሜዳ አስመጥ ቶ ከዋርካ ስር ከቀበረ በኋላ እዚያው አ ካባቢ እንደተቀመጠ ሁለት ቀን በማለፉ ነበር ጭንቁ የተፈጠረው። ይሄ ትንሽ ል ጅ ስሙ አቢቹ ይባላል። ከመሞታቸው በፊት የጃርሶ ጦር ፊታውራሪ የነበሩት አ ባቱ ዘመናዊ ትምህርት ተምሮ ከጊዜው ጋር እንዲራመድላቸው በመሻት በልጅነ ቱ ወደ አዲስ አበባ ይሰዱታል። በአዲስ አበባ ትምህርቱን የተከታተለው አቢቹ በቀጣዩ ዓመት ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ፈረንሳይ ለመጓዝ እየተዘጋጀ እያለ ነበር የኢጣሊያ ወራራ የመጣው። ትምህርት ቀርቶ ሁሉም ነገር ወደ ጦ ር ግንባር ሆነና አቢቹም ሁለት ወንድ ሞቹን ተከትሎ ነበር የዘመተው። ወንድ ሞቹን ሲያጣ በመሪር ሀዘን ምክንያት የ መሪነት ሚናውን መወጣት አቃተው የ ተባለለት አቢቹ ከሁለት ቀን ውሳኔ በኋ ላ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ይደርስ እና ደጃዝማ ች አበራ ፊት ይቀርባል። አቢቹ አስክሬ ኑ ያልተገኘው ሌላው ወንድሙ እንዳል ሞተ ይልቅስ ተሸንፈው በሸሹት ጣሊያ ኖች ቁጥጥር ስር ውሎ እየተሰቃየ እንደ ሆነ አምኗል። ይህንኑ ለበላይ አለቃው አስረድቶ ወንድሙን ነጻ ለማውጣት መ ወሰኑን ጨምሮ ይገልጻል። ለዚህም ይረ ዳው ዘንድ ጥቂት ወታደሮች ይዞ እንደ ሚሄድ ያስረዳል። ወደ ጦር ሜዳ ከመውረዱ አስቀድሞ በ ነበረው ምሽት የራሱ የመጨረሻ ንብረቶ ች የሆኑትን ሶስት በሬዎች አርዶ ጦሩን ይጋብዛል። በእርሱ ምትክ ሌሎች ሰዎች ጦሩን እንደሚሩ ዳጃዝማች አበራን ማስ ፈቀዱን ተናግሮ የራሱን ዕቅድም ለጦሩ ያጋራል። ለዕቅዱ ስኬትም 200 ገደማ

ወዶ ገባ ጥሩ ተኳሽ እና ተዋጊ ጦር ብቻ እንደሚፈልግ ይገልጻል። እነዚህ ወዶ ገ ባ ተዋጊዎች ሚስቴን ጨርቄን ሳይሉ ፈ ጥነው መንቀሳቀስ የሚችሉ ወጣቶች መ ሆን እንዳለባቸው ያስረዳል። ዕቅዱ መ ዋጋት ይሹ የነበሩ ሽማግሌ ሹማምንቶ ችን በመጀመሪያ ቢያስኮርፍም በስተኋ ላ ላይ በተደረሰው ስምምነት ሹሞቹ ወ ጣት ልጆቻቸውን ለአቢቹ ይሰጣሉ። የ ሹሞቹ ልጆች በበኩላቸው ከጦራቸው ወጣት፣ ደፋር እና ጎበዞቹን መረጡ። በዚህ ዓይነት የተዋቀረው 200 ገደማ ምርጥ ተዋጊዎች ያሉበት የአቢቹ ጦር በ ደጃዝማች አበራ ፊት ቀርቦ ተመረቀ እ ና በሌሊት የጦር ሰፈሩን ለቅቆ ወጣ። ከ ዚያን ሌሊት ወዲያ ታዲያ አቢቹን አየ ሁ የሚል ጠፋ። ጥቂት ቆየት ብሎ ግን ስለ አቢቹ ተጋነው የሚወሩ ጀብዱዎች ይሰሙ ጀመር። ጀብዱው የማረካቸው የራስ ካሳ በርካታ ወጣት ተዋጊዎች ዋና ውን ጦራቸውን ትተው ከአቢቹ ጦር ጋ ር መቀላቀል ጀመሩ። በፓርለሳክ በየም ዕራፎቹ የሚጠቅሱት የአቢቹ ጀብዱዎ ች ከዚህ ቀደም በሌሎች የኢትዮ-ጣሊ ያንን ጦርነት በሚዘክሩ መጽሐፎች እም ብዛም ያልተዳሰሱ ናቸው። አስገራሚዎ ቹ ታሪኮችም አቢቹን ከሮቢን ሁድ ጋር ያመሳስሉታል። “አቢቹ መጀመሪያ ላይ ከጦር ሰፈሩ እ ንደወጣ አነስተኛ የተበተኑ የጣልያን ጦ ሮች እየፈለገ፣ በደረቅ ለሊት አደጋ እየጣ ለ፣ ስንቅ እና ትጥቅ እየዘረፈ፣ ጦሩን ዘመ ናዊ መሳሪያ እያስታጠቀ፣ ማደራጀት ጀ መረ። ከዚያ ጦሩን ይዞ የጠላት ጦር ባል ጠበቀው ቦታና ሰዓት ድንገት እየደረሰ ያ ልተጠበቀ እና ያልታሰበ አደጋ እየጣለ፣ ንብረት እየዘረፈ፣ ከጦሩ የተረፈውን እ ና ጦሩ የማይፈልጋቸውን ነገሮች ወደ ዋ ናው ጦር መላክና ማከፋፈል ጀመረ” ይ ላሉ ፓርለሳክ። ተመሳሳይ አደጋዎችን በ ጠላት ጦር ላይ በየጊዜው ማድረሱን የቀ ጠለው የአቢቹ ጦር ዝናው እየሰፋ ቢመ ጣም ጣሊያኖችን ግን ክፉኛ አስቆጣ። አቢቹ አደጋ በጣለ ማግስት የጣልያን አ ውሮፕላኖች በሰሜኑ ጦር ላይ በብቀላ መልክ ድብደባቸውን ያከፉ ነበር። ይህ የአቢቹ ጅብዱ በንጉሰ ነገስቱ ዘንድም አ ልተወደደም። እንዲያውም የሰሜኑ ጦር የበላይ ለነበሩትን ራስ ካሳን እና የትግራ ይ አስተዳዳሪ ለነበሩትን ራስ ስዩምን አ ቢቹን ያቆሙ ዘንድ ትዕዛዝ ላኩ። “እንዲህ እንደአቢቹ ዓይነት አርበኞች የጠላትን ጦር ድንገት እየደረሱ እና አደ ጋ እየጣሉ፣ የገደሉትን ገድለው፣ የዘረ ፉትን ዘርፈው እንዳመጣጣቸው ድንገ ት ውልቅ የሚሉት ነገር ጦርነቱን በሰላ ም እፈታለሁ ብለው ተስፋ ለሚያደርጉ ት አጼው እንቅፋት እንደይሆንባቸው በ መስጋት በቀጭኑ ትዕዛዛቸው ‘ልጁን አ ቁሙት’ ብለው ሁለቱን ራሶች አዘዟቸ ው” ይላሉ ጸሀፊው። ንጉሰ ነገስቱን ተከ ትሎ የአቢቹ ስም ወደ “ልጁ” ተቀየረ። ሁለቱ ራሶችም ጦራቸውን ሊያዘምቱ ዝ ግጅት መጀመራቸው ተሰማ። የራስ ካሳ ልጅ ደጃዝማች አበራ ይሄን ሲሰማ ይ በሳጫል። በያዙት ኃላፊነት ምክንያት “ልጁ”ን በ ይፋ የማይደግፉት ፓርለሳክ እና ደጃዝ ማች አበራ ውስጥ ውስጡን ግን ለአቢ ቹ ከፍተኛ አድናቆት ነበራቸው። ለዚህ ም ነው የራሶቹን ጦር መዘጋጀት ሲሰሙ አቢቹን ለማትረፍ መላ መፈለግ የጀመ ሩት። “ከብዙ ውይይት በኋላ አቢቹን በ ዘዴ ወደ ደጃዝማች አበራ የጦር ሰፈር አ ምጥተን አስረንም ቢሆን ልናስቀረው አ ሰብንና ምክንያት ተፈጥሮ መልዕክተኛ ልንልክበት፣ መልዕክተኛውም አቢቹ የ ሚያምነው ሰው የቅርብ ጓደኛው እንዲ ሆን ተወሰነ” ይላሉ ፓርለሳክ። “አቢቹ ጨለማን ተገን አድርጎ ማታ ሲ መጣ እያንዳንዳችን ምን ምን ማድረግ እንዳለብን ስንወያይ በጠራራው ጸሀይ ድንገት ከች አለ” ሲሉ በወቅቱ በዋሻ ው ስጥ ተሰብስበው ሲመክሩ የነበሩትን ሰ ዎች አፋቸውን አስከፍቶ ያስቀራቸውን

ድርጊት ይተርካሉ። “እንዲህ ሁላችንም ተደናግጠን ዝም እንዳልን ደጃዝማች አ በራ አሽከሩን ባይኑ ጠቀስ ሲያደርገው አ ሽከርዬው ሹልክ ብሎ ወጣ። የአሽከርዬ ው አወጣጥ ከዋሻዋ ደጃፍ ላይ ዘብ የቆ ሙትን ወታደሮች ለመጥራት እንደሆነ ሁላችንም ገብቶናል። እርግጠና ነኝ ከአ ሳሳቁ አቢቹም በደንብ ገብቶታል። ብዙ ም ሳይቆይ አሽከርዬው እጆቹን ወደ ላ ይ አንስቶ ከጀርባው መሳሪያ ተደግኖበ ት ወደ ዋሻዋ ተመለሰ። አሁን አቢቹ ከ ዋሻዋ ውጭ ኃይል እንዳለውና በደንብ አስቦበት እንደመጣ ሁላችንም በዚያ ዋ ሻ ውስጥ ያለን ሰዎች ገባን” ሲሉ የልጁን ጠንቃቃነት ይገልጻሉ። በሁኔታው ያልተደሰተው አቢቹ “ግን ለምን ደጃዝማች? ግን ለምን” ሲል ይጠ ይቃል። ደጃዝማች አበራም ሁለቱ ራሶ ች የተሰናዳለትን ድግስ ፍርጥርጥ አድር ጎ ይነግረዋል። እነ ፓርለሳክም ሁኔታው ን ሊያስረዱት ይሞክራሉ። አቢቹ ግን ጥያቄውን ከመደጋጋም አልቦዘነም። “ግ ን ለምን?”። ይህን ጥያቄ ለመመለስ የቻ ለ ሰው እንዳልነበር የሚናገሩት ፓርለሳ ክ አቢቹ ተሰናብቷቸው ከመሄዱ በፊት እስከሕይወታቸው መጨረሻ የማይረሱ ትን አጭር ንግግር ማድረጉን ያትታሉ። የአቢቹን ንግግርም ቃል በቃል በመጽሐ ፋቸው ያስነብባሉ። አቢቹ ለደጃዝማች አበራ እንዲህ ነበር ያለው። “ገና ከሰላሌ ስንነሳ ታማኝነቴን በምኒልክ ስም ቃል የገባሁት ላንተ እን ጂ ለሽማግሌዎች ወይም ለንጉሱ አይደለ ም። እኔ ንጉስ አይደለሁም፤ ተራ ወታደ ር እንጂ። እና እኔ ሁለት ሶስት ወር ደሴ ተጎልቼ ጣልያኖች እጄን እስኪይዙኝ አ ልጠብቅም። ላንተ ግን አሁንም በምኒል ክ ስም፣ በምኒልክ አምላክ በድጋሚ ቃ ሌን እሰጣለሁ። ለአንተ እሞታለሁ። ተ መለስ ላልከው ግን የት ነው የምመለሰ ው? ምንስ መመለሻ ቤት አለኝና? እዚ ህም እዚያም እሳት እየነደደ እንዴት ቁ ጭ ልበል? ሽማግሌዎቹ ጦር ሊሰዱብ ኝ አስበው ከሆነ ደግ፤ ምንም ችግር የለ ም። ግን እኔ ከእነርሱ ጠብ እንደሌለኝና የሀገሬ ታማኝ ወታደር እንደሆንኩ አስረ ዳልኝ” ነበር ያለው አቢቹ። አቢቹ ደሴን የጠቀሰው በዚያን ወቅት ያለውጊያ ለወ ራት ከንጉሱ ጋር በደሴ የቆየውን ጦር ሲ ወርፍ ነበር። ጃንሆይ ምንም እንኳን በአቢቹ ድርጊ ት ቢቆጡም የ“ልጁ” ሁኔታ ከልባቸው እንደገባ ፓርለሳክ ከንጉሱ ጋር በኮረም በነበራቸው ቆይታ ታዝበዋል። በጨዋ ታ መሀል “ልጁን አይታችሁት ታውቃ ላችሁ?” ሲሉ ከራስ ካሳ ጦር ጋር የነበሩ ትን ፈረንጆች የጠየቁት ጃንሆይ ፈረንጆ ቹ ለመልሱ ሲቸገሩ ሲያዩ “ግድ የለም እ ንደእናንተም ባይሆን ይቺ አንድ ፍሬ ደ ጃዝማች ከእኛም በላይ ጀብዱ እየሰራ ች እንደሆነ እንሰማለን” ሲሉ መናገራቸ ውን ፓርለሳክ ጽፈዋል። የንጉሱ አቢቹ ን በደጃዝማች ማዕረግ መጥራት ፓርለ ሳክ አስገርሟቸው ነበር። ምክንያቱም ያ ን ጊዜ አቢቹ ምንም ዓይነት ይፋዊ ማዕ ረግ አልነበረውምና ነው። “ልጁ” ማዕረ ግ ባይኖረውም በወታደሩ ልብ ውስጥ ነ ግሶ ነበር። ለዚህም ፓርለሳክ በኮረም ያ ስተዋሉትን መጥቀሱ በቂ ነው። “በኮረም የጦር ሰፈር መሸትሸት ሲል የ ገበሬው ወታደር ማለትም አባቱን፣ ወን ድሙን፣ ጓደኛውን፣ በተንቤኑ የጦር ግ ንባር የመቅበር ዕድል እንኳ ያልገጠመ ው የከፋው፣ ሆድ የባሰው ወታደር፣ እ ሳት አንድዶ እየሞቀ እና የቆላትን ሽንብ ራውን እየቆረጠመ፣ በማሲንቆ እየተደገ ፈች በአንድ የሰላሌ ልጅ የምንትጎራጎረ ውን ሙዚቃ ማዳመጡን ተያይዞታል። አዝማሪው ሳይቀር ስለራሶች ጀግንነት፣ ስለ ንጉሰ ነገስቱ ታላቅነት ማንጎራጎሩን ርግፍ አድርጎ ትቶታል። አንጀት የምት በላዋ የማሲንቆ እንጉርጉሮ ስለ ልጁ አ ቢቹ ነበረች።” አቢቹ ደራ ደራ አቢቹ ደራ ደራ


ሐበሻዊ ቃና

19

ቢዝነስ በጁባ አውት ደንግ በደቡብ ሱዳን ጁባ የጸጉርና ውበ ት ሳሎን ለመክፈት እቅድ ነበራት፡፡ይሁንና ይህ ንን ለማድረግ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ስታጠና ከዓመት ገቢዋም ከእጥፍ በላይ የሚደርስ እጅግ ወድ ሆኖ አገኘችው፡፡ ይህን የአውት ደንግን መሰል ክስተት ለአስር አመታት ያህል የዘለቀው ግጭት የግል ተቋማት እንዳይስፋፉ እንቅፋት በሆነበት በደቡብ ሱዳ ን የተለመደ ነው፡፡ ምንም እንኳን ከ2005 እስ ከ 2007 ባለው ጊዜ የሱዳን ኢኮኖሚ በአማካይ በዘጠኝ በመቶ እድገት ቢያሳይም የንግድ እንቅስ ቃሴውን መደበኛ(ህጋዊ) ማድረግ በደቡብ ሱዳ ን አሁንም ቀላል አይደለም፡፡ በሱዳን 80 በመቶው ሰራተኛ ሀይል መደበኛ(ህ ጋዊ) ባልሆነ የንግድ መስክ የተሰማራ ነው፡፡ ይ ህ ቁጥር በደቡብ ሱዳን ደግሞ ይበልጥ አሻቅቦ ይ ስተዋላል፡፡ ስራ ፈጣሪዎች ለዚህ ሁለት ዋና ም ክንያቶችን ይጠቅሳሉ፡፡ አንደኛዊ ህጋዊ ለማድረ ግ ስለሚያስፈልጉ መስፈርቶች በቂ እውቀት አ ለመኖርን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መደበኛው ን ንግድ ለመጀመር የሚጠይቀው ወጪ ከፍተ ኛ መሆኑ ነው፡፡ በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በ ደቡብ ሱዳን ወደ ህጋዊው ወይም መደበኛ ንግ ድ ለመግባት የሚያስፈልገው ወጪ በሀገሪቱ ከተ ንሰራፋው ህጋዊ ያልሆነ የንግድ እንቅስቃሴ እና አነስተኛ ድርሻ ካለው መደበኛው ንግድ ጋር የተ ቆራኘ ነው፡፡ ምክንያቱም ህጋዊ ንግድ ለመጀመ ር ህጉ ሲከብድ እንዲሁም ለመጀመር የሚያስፈ ልገው ወጪ አልቀመስ ሲል ከንግዱ የሚገኘውን ትርፍ ይቀንሳል፡፡ የስራ ፈጣሪዎችን አያነሳሳም፡ ፡ ለብዙዎችም የስራ እድል እንዳይፈጠር ያደርጋ ል ይላል ጥናቱ፡፡ በጁባ አንድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለ መክፈት 15 ያህል ሂደቶች፤ 15 ቀናት እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ገቢን 250 ነጥብ 2 በመቶው(3ሺህ 77 የአሜሪካን ዶላር) ይጠይቃል፡፡ ከዚህም ባሻ ገር ይህን መሰል ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስፈል ገውን ዝቅተኛ ካፒታል የሚደነግግ ህግ የለም፡፡ ምንም እንኳ በጁባ ያለው ሂደት በካርቱም ካለ ው ቢፈጥንም በወጪ ረገድ ግን ከካርቱም ይልቅ ጁባ ይወደዳል፡፡ በካርቱም መሰል ኩባንያ ለመ ጀመር 36 ቀናት ቢያስፈልግም በገንዘብ ረገድ ግ ን የነፍስ ወከፍን ገቢ 33 በመቶ ያህል ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ የዱይንግ ቢዝነስ 2011 ሪፖርት የንግድ ስራ ለመጀመር ቀላል ሀገሮችን ሲያስቀም ጥ ጁባን ከ183 ሀገራት 123ኛ ደረጃ ላይ አድርጓ ታል፡፡ይህም 125ኛ ደረጃ ላይ ከምትገኘው ኬኒ ያ ሲያስበልጣት 9ኛ ደረጃን ከያዘቸው ሩዋንዳ ደግሞ በኋላ ያደርጋታል፡፡ የንግድ ስራ ለመጀመ ር ብዙ ገንዘብ ከሚያስፈልግባቸው (ውድ) ከተ ሞች ደግሞ ከኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ከጥሎ ጁ ባ ሁለተኛ ናት፡፡ በደቡብ ሱዳን አንድ የንግድ ድ ርጅትን ለማስመዝገብ ብቻ 390 የአሜሪካን ዶላ ር ክፍያን ይጠይቃል፡፡ ለንግድ ፈቃድና ለግብር ምዝገባ ደግሞ በድምሩ 1516 ዶላር ያስፈልጋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 ደቡብና ሰሜን ሱዳን ጠቅላላ ስምምነት ላይ ከደረሱ ወዲህ ለአንድ ዓመት ህ ል የጁባ አስተዳደር በካርቱም መንግስት ለተመዘ ገቡ ኩባንያዎች አውቅና መስጠት አቁሞ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 አዲስ የንግድ ተቋማት መመዝገ ቢያ አቋቁሞ ኩባንያዎችን መመዝገብ ጀምሯል፡ ፡ይንን ተከትሎም 9000 ያህል የንግድ ተቋማት መመዝገብ ችለዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግ ሞ የመንግስት ጨረታዎችን ለመዋዋል የሚፈል ጉ እየበዙ መምጣታቸው በነዳጅ ዋጋ መናር ተቀ ጣጥሎ የተመዝጋቢ ተቋማት ቁጥር እድገት አሳ ይቷል፡፡ ይሁን እንጂ በ2009 እና 2010 የነዳጅ ዋጋ መቀነሱንና የደቡብ ሱዳን እጣ ፋንታ በህዝ በውሳኔ እስኪለይለት በሚል የአዲስ ተመዝጋቢ የንግድ ድርጅቶች ቁጥር ዳግም አሽቆልቁሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በጁባ የንግድ ስራ ለመጀመር ያሰ በ ግለሰብ 11 ያህል ሂደቶችን ማለፍ ይጠበቅበታ

ል፡፡ ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት አ ማካይ ሂደት በሁለት ብልጫ ሲኖረው 2 ሂደቶች ን ብቻ ከምትጠይቀው ሩዋንዳ ግን በብዙ ርቀት ያስቀምጠዋል፡፡ከሚያስፈልጉት 11 ሂደቶች መካ ካል የመጀመሪያ አራቱ ከማመልከቻና ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ሲሆኑ ቀጣዮቹ አምስት ሂደቶች ደ ግሞ ከተለያዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋ ማት ፈቃድ ለማግኘት የሚታለፉ ናቸው፡፡ይሁን ና ግልጽ የሆነ መመሪያና በየደረጃው ባሉ ተቋማ ት መካካል ያለው ቅንጅት የላላ በመሆኑ ከምዝገ ባ በኋላም የሚታለፉ ሂደቶች መኖራቸውን ልብ ይሏል፡፡ እንዲህም ሆኖ በ15 ቀናት ውስጥ በደቡ ብ ሱዳን የንግድ ስራን መጀመር ይቻላል፡፡ ይህ ም ከሰሀራ በታች ባሉት ሀገራት በአማካይ ከሚ ያስፈልገው 45 ቀናት በአንድ ሶስተኛ ያነሰ ነው፡ ፡ የዱይንግ ቢዝነስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ይህ የሆነው የምዝገባ ተቋማት የተደራጁና በኮም ፒውተር የታገዙ በመሆናቸው ነው፡፡ በደቡብ ሱዳን የንግድ እንቅስቃሴ እያደረጉ አለ መግባባት ቢከሰት ለአለመግባባቱ መፍትሄ ለማ ምጣት 111 ቀናትና በአለመግባባቱ ሂደት ይገባኛ ል ብለው ከሚጠይቁት ዋጋ 26 በመቶው ያህል ወጪያስፈልጋል፡፡ ይህም እንደሌሎቹ ሂደቶች 810 ቀናትንና ይገባኛል ከሚሉት 19ነጥብ8 ከመ

ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያብራራም ለተለያዩ የ መንግስት መስሪያቤቶች የሚጠየቀው ክፍያ ከፍ ተኛ መሆኑንና የውሃ መስመር ያላቸው ጥቂት ነ ጋዴዎች ብቻ በመሆናቸው የሚጋጥመውን የው ሃና የመብራት መቆራረጥ በቀዳሚነት ያነሳል፡፡ ምክንያቱም በግንባታው ዘርፍ የሚሰማራ ማንኛ ውም ግለሰብ የራሱን የውሃ ጉድጓድ ማስቆፈርና የሃይል አቅርቦትን በአስተማማኝ መልኩ ለማግኘ ት ወድ ጀኔሬተሮችን መግዛት ይጠበቅበታልና፡፡ ይህም ሆኖ በግንባታው ዘርፍ ለመሰማራት ከሌ ሎች ዘርፎች ጋር ሲነጻጸር ፈጣን ነው ተብሏል፡፡ ደቡብ ሱዳን ለንግድ እንቅስቃሴ ብድር በመፍ ቀድ 176ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ለንግ ድ እንቅስቃሴ ከለላ በመስጠት 173ኛ ደረጃን፤ የ ንግድ ተቋምን በመዝጋት ደግሞ 183ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ይህም በሀገሪቱ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ አለመኖሩን ያሳያል--እንደ ዱይንግ ቢዝነስ ጁባ 2011 ሪፖርት፡፡ የብድር አሰጣጥ ሂደትን ለማሳያነት የሚጠቅሰ ው ሪፖርቱ በ2003 የወጣውና ኩባንያዎችን የ ሚመለከተው ህግ አስተማማኝ ግብይትን በሚ መለከት ያካተታቸው ድንጋጌዎች መጣም ጥቂት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ አካባቢው ምንም አይነት የግልም ሆነ የመንግስ

ማን ምን እየሰራ ነው? አስኮ ጫማ የኡጋንዳ የገበያ ድርሻውን እያሰፋ ነው

ይሆን ሀገሪቱ ያላት ደካማ የመንገድ መሰረተ ል ማትና ከኒሙሌ እስከ ጁባ ያለው በርካታ የፍተ ሻ ጣቢያ እንዲሁም በየአስተዳደሩ ያለው ሂደት ውስብስብ መሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡ ፡ ለምሳሌ የእቃ ማስገቢያ የብድር ደብዳቤ ለማ ግኘት አንድ ነጋዴ መጀመሪያ ከደቡብ ሱዳን ባን ክ ማረጋገጫ ማግኘት ይጠበቅበታል፡፡ ይህም እ ንደ ሪፖርቱ ተጨማሪ 22 ቀናትን ይወስዳል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው የጁባ መንግስት ንግድን በ ቀላሉ መጀመር እንዲቻል የሚያስችሉ ለውጦች ን ለማምጣት ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ለአብነትም እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ የህግ ጉዳዮችና ህገመንግ ስታዊ ልማት ሚንስቴሮች በጋራ በመሆን የንግ ድ እንቅስቃሴ የሚያመቻች ግብረሃይል ማቋቋማ ቸውን ይጠቅሳል፡፡ ከ2010 እስከ 2012 በሚዘልቀው የገሪቱ የእድገ ት ስትራቴጂ ረቂቅ ላይም መንግስት በግሉ ዘርፍ የሚመራ እድገት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እ ንደሚሰራ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ በእርግጥም ለ አስርት ዓመታታ ከዘለቀ ጦርነት እያገገመ ላለ ህ ዝብ የተረጋጋ ስራ ፍጥነቱ የተመጠነ እድገትና የ ንግድ እንቅስቃሴ ዋስትና ከመቼውም በላይ ወ ሳኝ መሆናቸውን የወጣቷ ሀገር መንግስት የተረ ዳ ይመስላል፡፡

የ“አስኮ” ወታደራዊ እና የስራ ጫማዎች

ብዙዎች “አስኮ” በሚለው የቀድሞ ስሙ ይወቁት እንጂ ትክክለኛ መጠሪያው ጥቁር አባይ ጫማ አክሲዮን ማህበር ነው። አዲ ስ አበባ አስኮ በሚገኘው ቅጽር ግቢው ሁ ለት ፋብሪካዎች አሉት። አንደኛው ለማን ኛውም ሰው የሚሆኑ መጫሚያዎች የሚ መረቱበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የወታደ ራዊ እና የስራ ጫማዎች የሚፈበረኩበት ነ ው። የወታደራዊ ጫማዎቹ ምርት ከሀገር ቤት ተሻግረው በምስራቅ አፍሪካ ተወዳጅ ሆነዋል። ለዚህም የኡጋንዳ ፖሊስ እና ሩ ዋንዳ የሚገኝ የ“ሲኪዩሪቲ” ድርጅት እማ ኞች ናቸው። ካምፓላ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካኝነት ወደ ኡጋንዳ የመጣው ጥቁር አ ባይ ጫማ የመጀመሪያ ደንበኛው ከሆነው የኡጋንዳ ፖሊስ የ35 ሺህ ጫማዎች የስራ ትዕዛዝ የደረሰው እ.ኤ.አ በጁላይ 2009 ነ በር። እ.ኤ.አ በጥር 2010 ላይ የመጀመሪያ ዎቹን ጫማዎች ወደ ኡጋንዳ ላከ። ህዳር ላይ ቀሪ ጫማዎችን ለኡጋንዳ ፖሊስ አስ ረከበ። በዚሁ ዓመት ሩዋንዳ የሚገኝ ኢንተር ሴ ክ የተሰኘ የግል የ“ሴኪዩሪቲ” ድርጅት ጫ ማዎች የሚያቀርቡለት ድርጅቶች በጨረ ታ አወዳደረ። ጥቁር አባይ በጨረታው ተ ሳትፎ አሸነፈ እና ሁለት ሺህ ጫማዎች ለ ማቅረብ ተስማማ። በስምምነቱም መሰረት የሩዋንዳው ድርጅት ጫማዎቹን ባለበት ጊ ዜ አግኝቷል። “አስኮ” በእነዚህ ስኬቶቹ ብ ቻ አልቆመም። የኡጋንዳ ማረሚያ ቤቶች ባወጣው ጨረታ ላይ ተሳትፏል። የ“አስኮ ን” ምርቶች ፖሊሶች ሲጠቀሙ ያዩት የሀገ ሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ሰዎችም ጫማዎ ቹን ወደዋቸዋል።

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ቢዝነስ

ፎቶ-የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

በጁባ አንድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለመክፈት 15 ያህል ሂደቶች፤ 15 ቀናት እንዲሁም 3ሺህ 77 የአሜሪካን ዶላር ይጠይቃል

ቶው ብቻ ከሚያስፈልግባት ካርቱም ጋር ሲነጻጸ ር ጁባን በጊዜ ረገድ ፈጣን በዋጋ በኩል ግን እጅ ግ ውድ ያደርጋታል፡፡ ለዚህም ከደቡብ ሱዳን የ ንግድ እንቅስቃሴ ህጋዊ ያልሆነው ሚዛን መድፋ ቱ በከፊልም ቢሆን በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡ ግብር ለመክፈልም አንድ መካካለኛ የንግድ ተ ቋም በዓመት ውስጥ በአማካይ 218 ሰዓታትን ሲ ያጠፋ ከሚያገኘው ትርፍ ደግሞ 46 በመቶውን ወጪ ያደርጋል፡፡ የዱይንግ ቢዝነስ ሪፖርት ደቡብ ሱዳን በግንባ ታ ፈቃድ አሰጣጥ፤ የንግድ ስራን በማስመዝገብ እንዲሁም ፈቃድ ለመስጠት ባለው ሂደት እንደ የቅደምተከተላቸው 49ኛ፤ 123ኛ እና 124ኛ ላይ ያሰቀምጣታል፡፡ እንደ ሪፖርቱ በእነዚህ ሶስት ሂ ደቶች የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆን ዋና ው እንቅፋት ነው፡፡ በጁባ ጀማሪ ነጋዴ አንድ አዲስ ህንጻን በስሙ ለ ማዞር የንብረቱን 17 በመቶው ያህል ሊያወጣ የ ግድ ነው፡፡ ሁሉንም የግንባታ ፈቃዶች ከእነ አገ ልግሎታቸው ለማግኘት ደግሞ ከጁባ የነፍስ ወከ ፍ ገቢ 5ሺህ936 በመቶውን ይጠየቃል፡፡ ይህን ንም ቢዝነስ ዱይንግ እስከዛሬ ከዳሰስኳቸው ሀገ ሮች ከብዙዎቹ ወድ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል፡፡

ት ብድር ሰጪ ተቋም የለም፡፡ በጁባ ለባለሀብቶች የሚደረግላቸው ጥበቃና ከ ለላም ደካማ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ ም ንም እንኳ የ2003ቱ የኩባንያዎች ህግ ዳሬክተሮ ች የጥቅም ግጭት ሲከሰት ይፋ እንዲያደርጉና ለ ባለድርሻዎችም ቢያንስ የኩባንያውን ካፒታል 10 በመቶ እንዲያጋሩ የሚደነግግ ቢሆንም ይህ ሳይ ሆን ቢቀር የሚከተለውን ቅጣትም ሆነ መሰል የ ህግ እርምጃ በተመለከተ የሚደነግግ የህግ አን ቀፅ የለውም፡፡ ድንበር አቋርጦ በመነገድ በኩል ጁባ ዝቅተኛ አ ፈጻጸም አሳይተዋል ከተባት ከአፍጋኒስታንና መ ካካለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ ብቻ ቀድማ 181ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የኬኒያውን ሞምባሳ ወደ ብ ተጠቅሞ ደረጃውን የጠበቀ አንድ ሙሉ እቃ የጫነ ኮንቴነር ወደ ጁባ ለማስገባት 11 ያህል የተ ለያዩ መረጃዎች፤ 60 ቀናትና 1ሺህ ዶላር የሚጠ ጋ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ይህንኑ ወደብ ተጠቅሞ ተመሳሳይ መጠን ያለው እቃ ወደ ውጪ ለመላ ክ ደግሞ ዘጠኛ የተለያዩ መረጃዎች፤ 52 ቀናትና 5ሺህ ዶላር ይጠይቃል፡፡ ይህም ከአካባቢው ሀ ገራት አማካኝ ጋር ሲነጻጸር ጎታታውና ውዱ ያደ ርገዋል፡፡ ለዚህም ከወደቡ ያለው ርቀት ብቻ ሳ

እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ የንግድ ምዝገባን እንቅስ ቃሴንና ከዘርፉ መውጣትን የተመለከቱ 19 ህጎች አርቅቋል፡፡ ከእነዚህም መካካል በ2008 የወጣ ውን የንግድ ስሞች ምዝገባና በተመሳሳይ ዓመት የወጣውን በጋራ የመስራት እንዲሁም በ2009 የ ወጡትን የግብርና የመሬት አዋጆች ጨምሮ ዘጠ ኙ በደቡብ ሱዳን የህግ አውጭው አካል ጸድቀ ዋል፡፡ የኩባያና ሰራተኛ ደንቦችን ጨምሮ ሌሎ ች ስምንት ህጎች ደግሞ ገና ለህግ አውጭው አካ ል አልቀረቡም፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 ከተቋቋመውና በአምስት ዓመ ታታ ውስጥ 9000 ተቋማትን መመዝገብ ከቻለ ው የንግድ መዝጋቢ በተጨማሪ የንግድ ባንኮች በሀገሪቱ እየተቋቋሙ ነው፡፡ መንገድና ድልድይን የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት አውታሮችንም ጎን ለ ጎን እያስፋፋ ነው፡፡ ይሁንና ተጨማሪ እድገት ለማስመዝገብ አሁንም ብዙ ይቀራል፡፡ እየታየ ያ ለውን ለውጥም ማስጠበቅ ይገባል ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡ ይህ ሁሉ ተደምሮ ታዲያ ፈቃድ ሂደቶችን አሳ ጥሮ ወጪውንም ቀንሶ እነ አውት ደንግን ለመሳ ሰሉ ስራ ፈጣሪዎች ንግድን በጁባ ያቀላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

“ቴዲ ኤር” በደቡብ ሱዳን

የ39ኛ ዓመቱ ጎልማሳ ቴዎድሮስ ሽፈራው ለ13 ዓመት ቻይና ኖሯል። ለኢትዮጵያ ሚ ሊኒየም ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ በ ዓመቱ ሮዜታ የሚባለውን ድርጅቱን ይመ ሰርታል። ሮዜታ በእምነበረድ ማውጣት እ ና መሸጥ፣ በሪል ስቴት እንደዚሁም በአስ መጪ እና ላኪነት የተሰማራ ድርጅት ነው። በዚያው ዓመት በ10 ሚሊዮን ዶላር እንደ ተመሰረተ በተነገረለት እህት ኩባንያው “ቴ ዲ ኤር” አማካኝነትም የበራራ አገልግሎት ይሰጣል። በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መዳረ ሻ ቦታዎችን ለመሸፈን በማሰብ የተቋቋመ ው “ቴዲ ኤር” ስራውን የጀመረው ሴሲና ተብለው በሚጠሩት አነስተኛ አውሮፕላኖ ች አማካኝነት ነው። የአውሮፕላኖቹን ቁጥር አራት ያደረሰው “ቴዲ ኤር” ከሁለት ዓመት በኋላ የበራራ አ ድማሱን ወደ ደቡብ ሱዳን አስፍቷል። ኢ ትዮጵያውያን ችግር በገጠማቸው ጊዜም ፈ ጥኖ ደራሽ አገልግሎቱን ሰጥቷል። በኢትዮ ጵያውያን ይተዳደር በነበረው ኩሽ ሆቴል ላይ ከአራት ወር በፊት በደረሰው የቃጠሎ አደጋ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ወደ አዲስ አበባ ያጓጓዘው “ቴዲ ኤር” ነበር።


ሐበሻዊ ቃና

20

የጉዞ ማስታወሻ

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ቁርጥራጭ ማስታወሻዎች መሀመድ ሰልማን አዲስ ነገር ኦንላይን

ዲግራት ነው ያለሁ ት፡፡ 35 ኪሎ ሜትሮችን ወደ ሰሜን ፈ ቀቅ ብል ኤርትራ ገባሁ ማለት ነው፡፡ ም ክንያቱ በማይገባኝ መልኩ ጥሎብኝ አ ሥመራን እናፍቃታለሁ፡፡ አይቻት ግን አላውቅም፡፡ “የማያውቁት አገር እንዴ ት ይናፍቃል?!” አትበሉኝ፡፡ ተረቱ የማ ይሰራበት ጊዜ ካለስ? ናፍቆቴን በከፊል ለማስታገስ ወደ ድንበር መጠጋት አማረ ኝ፡፡ ወደ ዛላንበሳ፡፡ ያን ከማሳካቴ በፊ ት አዲግራትን ለአጭር ቀናት መቃኘት ይኖርብኛል፡፡ ስለ አዲግራት “አዲግራት ሳንድስቶን” ከሚለው የሰባተኛ ክፍል የኅብረተሰብ ትምህርት የዘለለ እውቀት እንደሌለኝ እ ረዳለሁ፡፡ አሁን ያን አነስተኛ እውቀት ከ ቀሰምኩ ከሁለት አሥርተ ዓመታት በኋ ላ በዚህች ዝምተኛ ከተማ እገኛለሁ፡፡ የ ተለየ ስሜት አላደረብኝም፡፡ አዲግራት ምኗ ያስደምማል? ከጦርነቱ በኋላ አዲግራት ታመመች አ ሉ፣ ልክ ድሬዳዋ ከባቡሩ መቆም በኋላ እንደሆነችው፡፡ ነግቶ እስኪመሽ ታዛጋ ለች፡፡ እንደ ጅማ ፍጹም ባታንቀላፋም፤ እንደ አዋሳ ፍጹም ባትነቃም፤ አዲግራ ት በእኩለቀን እንቅልፍ ሸለብ እያደረገ የሚመልሳት ከተማ ሆነች፡፡ ብዙ የኢት ዮጵያ ከተሞች ቢያንስ ሙዚቃ በስማቸ ው ስለሚዜምላቸው ለጊዜውም ቢሆን ውብ መስለው በሰው አእምሮ የመሳል እድል አግኝተዋል፡፡ በዚህ ረገድ ደሴና ጎንደርን የሚስተካከላቸው የለም፡፡ አዲ ግራት ግን ለዚህም አልታደለችም፡፡ ሟ ቹ እያሱ በርሄ አንድ የማስተዛዘኛ ሙዚ ቃ እንዳዜመላት ሰምቻለሁ፡፡ ከዚያ ው ጭ ስለእርሷ ያዜመ ያለም አይመስለኝ ም፤ ምን ብሎስ ያዜማል? አዲግራት ዜመኞችን አላፈራችም ማለ ት ግን አይደለም፡፡ “የሰሜኑ ቴዲ አፍሮ” እየተባለ የሚሞካሸው ሰለሞን ሃይለ ት ውልዱ አዲግራት ነው፡፡ ከዓመት በፊ ት “ቆሪበለኹ” የተሰኘው አልበሙ በመ ላው ትግራይ ብሔራዊ መዝሙር እስኪ መስል ከጫፍ ጫፍ ተደምጦለታል፡፡ የ አዲስ አበባ ታክሲዎችም በዚህ ሙዚቃ እንደልብ ትርፍ ሰው ጭነዋል፡፡ አዲግ ራት ደግሞ የጆሮ ታምቡሯ እስኪበጠ ስ የልጇን ዜማ ደጋግማ ታስደምጣለች፡ ፡ ልጅ አይጠገብም! በዋና መንገዷ ዳር ቻ የተሰየሙ የሙዚቃና የኤሌክትሮኒክ ስ ሱቆች የላጤ ልብስ ሳጥን የሚያካክል ድምጽ ማጉያዎችን ከደጃቸው አኑረው ይህንኑ የሰለሞን ሀይለን ጥኡም ሙዚቃ ነጋ ጠባ ለከተማዋ ያስተጋባሉ፡፡ በነገራችሁ ላይ በአዲግራት ቆይታዬ የ ቴዲ አፍሮ ፖለቲካዊ መልእክት አላቸ ው የሚባሉ ሙዚቃዎችን እንደልብ ሲ ደመጡ አስተውያለሁ፡፡ ለምሳሌ በከተ ማዋ እምብርት የሚገኘው “ኢትዮ ሙ ዚቃ ቤት” “በ 17 መርፌ በጠቀመው ቁ ምጣ፣ ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲ ወጣ…” የሚለውን ዜማ ከፍ ባለ ድም ፅ ደጋግሞ ሲያስደምጥ ለመስማት ችያለ ሁ፡፡ ከዓመታት በፊት ይመስለኛል ከአ ዲስ አበባ መቀሌ ስጓዝ በአውቶብስ ው ስጥ ይኸው ሙዚቃ በመከፈቱ በተጓዦ ች መሀል ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ በመጨረሻም ሾፌሩ ሙ ዚቃውን እንዲዘጋው ተገዶ አንደነበረ አ ስታውሳለሁ፡፡ አሁን ፖለቲካዊ መቻቻ ል ነግሶ ይሁን የፖለቲካ ግለቱ ተቀዛቀ ዞ ብቻ ቴዲ አፍሮ በአዲግራት እንደልብ ይፈነጫል፡፡ እርሱ መድረክ ላይ ለመዝ ፈን ሳንሱር የሚያደርጋቸው ሙዚቃዎ

ች በአዲግራት አደባባይ እንደልብ እንደ ሚከፈቱ ቴዲን የምታውቁ ሹክ በሉት፡፡ አዲግራት ሙሉ በሙሉ በተራራ መ ከበቧ፣ ተስማሚ የአየር ንብረት መጎና ፀፏ፣ በበለስና ብርቱካን ምርት መታወ ቋ፣ በክፉ ከመነሳት ያዳኗት ውስን ው በቶች ናቸው፡፡ በተለይ የአዲግራት ጉን ዳጉንዱ ብርቱኳን ጣእሙ ዘላለማዊ ነ ው፡፡ በኢትዮጵያ ትልቁ የመድኀኒት ፋ ብሪካ የሚባለውና “የትእምእት” (ኤፈር ት) እህት ኩባንያ የኾነው “አዲስ መድኀ ኒት ፋብሪካ” ሌላው የአዲግራት ኩራት ነው፡፡ ሻእቢያ በአየር ሊደበድበው ከአ ንዴም ሁለቴ ሞክሮ ስቶታል፡፡ ብዙዎቹ ን የከተማዋን ነዋሪዎች ከሥራ አጥነት የ ታገደው ይኸው ፋብሪካ ነው፡፡

ፎቶ - መሀመድ ሰልማን

አዲግራት “ፒያሳ” እያለች የምትጠራው ሰፈሯ በብዙ ለማኞች፣ በብዙ ሙዚቃ ቤቶችና በጥቂት የአእምሮ ህመምተኞች የተሞላ ነው፡፡

ወልዋሎ ‘ለአዲሳባ “ሸገር” የሚል የዳቦ ስም ከ ሰጠን ለአዲግራት ምን እንላለን?’ የሚ ል የሚኒስትሪ ፈተና ጥያቄ ቢመጣ ስን ት ተማሪ እንደሚመልሰው አላውቅም። “ወልዋሎ” ካሉ መልሱን አግኝተውታ ል፡፡ ይህ ስም በከተማዋ ሁሉም ነገር ላ ይ ተፅፎ ይታያል፡፡ “ወልዋሎ ፀጉር ቤ ት”፣”ወልዋሎ እንዳ-ባኒ” (ዳቦ ቤት ማለ ት ነው)፣ “ወልዋሎ ሙዚቃ ቤት”፣ “ወ ልዋሎ ጥህሎ ቤት”… “ወልዋሎ ከረንቡ ላ”…የወልዋሎ ነገር ማቆምያ የለውም፡ ፡ ከ ወልዋሎ የተረፉት አገልግሎት መ ስጫዎች ደግሞ “አግኣዚ” በሚል ነው የ ሚጠሩት፡፡ “አግአዚ” በአዲግራት ከተ ማ ከትምህርት ቤት እስከ ቡና ቤት ያለ ማንኛውም ድርጅት ሊጠራበት የሚች ል ስም ነው፡፡ አግአዚ ቡቲክ፣አግአዚ ኢ ንተርኔት፣ አግኣዚ ትምህርት ቤት፣አግአ ዚ መሸታ ቤት…ወዘተ በከተማዋ የሚገኘው ቁጥር አንድ የም ሽት ክለብ “ፍሪ -ዞን” ይባላል፡፡ ለመዲ ናችን አዲስ አበባ እንኳ የሚመጥን ዘመ ናዊ ክለብ ነበር፡፡ ሆኖም ክለቡ ከከተማ ዋ በብዙ እርምጃ በመቅደሙ በገበያ እ ጦት ተዘግቷል፡፡ የዛሬን አያድርገውና አ ዲግራት የሞቀች-ያበደች፣ አሸሼ ገዳሜ የሚባልባት ከተማ ነበረች አሉ፡፡ የድን በር ጦርነት ጉሮሮዋን ዘጋው፡፡ ብዙዎቹ ነዋሪዎቿም ተሰደዱ፣ ወደ መቀሌ፣ወደ አዲሳባ፡፡

አዲግራት ንጉራጌ ጉራጌዎችና አዲግራቶች በኢትዮጵያ የ ሰሜንና የደቡብ ዋልታ ጫፍ የሚገኙ ሕ ዝቦች ናቸው፡፡ ሕይወታቸው ግን እንደ መገኛቸው አይራራቅም፡፡ “አንድ ትግሬ እሳት የላሰ ነጋዴ ከሆነ ትውልዱ አዲግ ራት እንደሆነ ትጠረጥራለህ” ሲሉ ነግረ ውኛል። “በአብዛኛው ግምትህ ልክ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡” እሱ እኮ “ወዲ አዲግራት እዩ” ከተባለ በቢዝነስ እየገሰገሰ እንደሆ ነ ይገባኻል፡፡ ወልዋሎዎች “የትግሬ ጉ ራጌዎች” የሚባሉትም ለዚሁ ነው፡፡ አ ዲሳባ “ሃያ ሁለት” በሚባለው ሰፈር ዞ ር ዞር ስትል የሚያፈጡብህ ብዙዎቹ መ ለሎ ሕንፃዎች በትግራይ ተወላጆች የተ ያዙ ናቸው – ከትግራይም በአዲግራቶ ች፡፡ የሳትኮን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ተ ኽላይ የአዲግራትን አፈር ፈጭተው ነ ው ያደጉት፡፡ በቀድሞ ጊዜ ለኤርትራ ንግድ እንቅስቃ ሴ የደም ዝውውር መሆን የቻሉትም አ ዲግራቶች ነበሩ ይባላል፡፡ ኤርትራዎች አዲግራቶችን “አጋመ” ይሏቸዋል፡፡ ስድ ብ መሆኑ ነው አሉ፡፡ አንድን ጉራጌ “ጉ ራጌ” ብሎ እንደመሳደብ፡፡ አንድ አዲግ ራታዊ የ“አጋመ ልጅ ነኝ” ሲልህ ግን በ ታላቅ ኩራት ነው፡፡ በአዲግራት ምድር

ፎቶ-ግራንፓ ኢንተርናሽናል ትያትር ፕሮዳክሽን

“አግአዚ” በአዲግራት ከተማ ከትምህርት ቤት እስከ ቡና ቤት ያለ ማንኛውም ድርጅት ሊጠራበት የሚችል ስም ነው፡፡ አግአዚ ቡቲክ፣አግአዚ ኢንተርኔት፣ አግኣዚ ትምህርት ቤት፣አግአዚ መሸታ ቤት…ወዘተ

ፎቶ-ፍሊከር

የዛሬን አያድርገውና አዲግራት የሞቀች-ያበደች፣ አሸሼ ገዳሜ የሚባልባት ከተማ ነበረች አሉ፡፡ የድንበር ጦርነት ጉሮሮዋን ዘጋው፡፡ ብዙዎቹ ነዋሪዎቿም ተሰደዱ፣ ወደ መቀሌ፣ወደ አዲሳባ፡፡

“አጋመ” የሚለው ቃል የኩራት ምንጭ ነው፡፡ “ጓል አጋሜ” የሚል ጽሑፍ ለጥ ፈው የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን በከተማዋ በብዛት አይቻለሁ፡፡ “የአጋሜ ልጅ! የአ ጋመ ቆንጆ!” እንደማለት ነው፡፡ ጉራጌዎችና አዲግራቶችን የሚያመሳስ ላቸው ጠንካራ የሥራ መንፈስ ብቻ አ ይደለም፡፡ የመስቀል በዓልም የጋራ በዓ ላቸው ነው፡፡አዲግራቶች ልክ እንደ ቤ ተ ጉራጌዎች ከበዓላት ሁሉ ለመስቀል በ ዓል ልዩ ግምት ይሰጣሉ፡፡ አዲግራቶች ዓመቱን ሙሉ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ታች ሲሉ ይከርሙና ልክ የመስቀል በ ዓል ሲደርስ ጓዛቸውን ሸክፈው ወደ አ ገር ቤት-ከአገርቤትም ወደ አዲግራት ያ ተማሉ፡፡ ይህ የማይዛነፍ ዓመታዊ መር ሀ-ግብራቸው ነው፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በሺህ የሚቆጠሩ ትግሬዎች በአዲግራት ደማቅ የመስቀል አከባበር ማድረጋቸው በአገሪቱ ቴሌቪዥን ጭምር ተዘግቧል፡፡

ቸው በመናኸሪያዎች አካባቢ ጥበቃ እን ዲኖር ተደርጎ ነበር፡፡ ቆሸሽ ያለ ልብስ የ ለበሱ ወጣቶች ከጎዳና ታፍሰዋል፡፡ “ሓ ፊሶሞም!” ከደርግ መውደቅ በኋላ ዳግ ም ዝነኛ ቃል ሆነች፡፡ የአዲግራቱ ወዳጄ የዚያን ጊዜ ብዙዎቹ ጓደኞቹ እንዳለቁ ነግሮኛል፤ “የተረፉት ግን አሁን መከላከያ ውስጥ ጥሩ ቦታ ተ ሰጥቷቸዋል፡፡” ይላል፡፡ ይኸው የአዲግ ራት ወዳጄ እንዳወራኝ ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ ለሟች ቤተሰቦች መርዶ ማርዳት ሲጀመር አዲግራትና አጎራባች የገጠር ሰ ፈሮቿ ወደ ትልቅ ድንኳንነት ተቀየሩ፡፡ በእያንዳንዱ የሰፈር ጎዳና የለቅሶ ድንኳ ን መትከል ግድ ነበር፡፡ የድንኳን ተራ ያ ልደረሳቸው ሜዳ ላይ ለቅሶ ለመቀመጥ ተገደዋል፡፡ እስካሁንም ትርጉሙ ላልገባ ን ጦርነት አዲግራትና ዙርያ ገብ የገጠር ቀበሌዎቿ ከሌሎች ከተሞች በበለጠ ብ ዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

የማትስቀው የተስፋዬ ካሳ አገር

ቆንጆዎቹ እናቶች

አዲግራት ከግዙፍ ፖለቲከኞች ባሻገ ር የቀድሞውን ኮሞዲያን ተስፋዬ ካሳን እንዳፈራች ሲነገረኝ ለማመን አንገራገር ኩ፡፡ ተስፋዬ ካሳ አዲግራት ተወልዶ፣ አ ዲግራት አድጎ፣ አዲግራት ጨርቆስ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎ ነው ወደ አዲስ አበ ባ የሄደው፡፡ አዲስ አበባም “ግቢ ገብር ኤል ቤተ ክርስትያን” አገልግሏል፡፡ ይህ ን መረጃ ያገኘሁት ተስፋዬ አብሮ አደጌ ነው ከሚል አንድ የአዲግራት ጎልማሳ ነ ዋሪ ነው፡፡ ይኸው ነዋሪ የነተስፋዬ ካሳ ቤት “ሜዳ አጋሜ” በሚባለው ገበያ /እ ዳጋ/ ወዲያ ማዶ ነው ሲል በጥቆማ አ ሳይቶኛል ፡፡ ከተማዋ ግን የምትስቅ አ ትመስልም፤ በልጇ ተስፋዬ ካሳ ቀልዶ ችም ቢሆን፡፡

እንደ አዲግራት ብዙ የኔ ቢጤዎች ያየ ሁበት ከተማ ትዝ አይለኝም፡፡ ፒያሳ በ ሚባለው የከተማዋ እንብርት “ወልዋሎ ካፌ” በረንዳ ላይ ተሰይሚያለሁ፡፡ ማኪ ያቶ ፉት እያልኩ ለአመል ያክል ያያዝኩ ትን የጉዞ መጽሐፍ እያገላበጥኩ፤ በአን ድ ዐይኔ ከተማዋን እታዘባለሁ። ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል በዚህ ሁኔታ ተቀመ ጥኩ፡፡ በቆይታዬ ምፅዋት የሚጠይቁን ለማኞች ቁጥር በአእምሮዬ ለማስላት ሞ ከርኩ፡፡ ከሰላሳ ይልቃሉ፡፡ ከእነዚህ መ ካከል እጅግ የበዙቱ እድሜያቸው የገፉ የትግራይ እናቶች ናቸው፡፡ “ይርደአኹ ም” የምትለዋን ቁልፍ ቃል ያላወቀ እን ግዳ በአያት የኔ ቢጤዎች ያልተቋረጠ ተ ማፅኖ ስሜቱ ሊረበሽ ይችላል፡፡ መላው ትግራይ እንዲሁ ነው፡፡ በትግራይ ከተሞች በተዘዋወርኩባቸ ው ግዝያት ሁሉ ቅስም የሚሰብር፣ ስሜ ት የሚረብሽ ክስተት የሚገጥመኝ ትግ ራዊ እናቶችን ስመለከት ነው፡፡ በሚሞ ቀው ፈገግታቸው ውስጥ መከራ ይታያ ል፡፡ በቆንጆ ፊታቸው ግንባር ላይ ረዥ ዥም የእድሜ መስመሮች ይጎላሉ፡፡ መ ስመሮቹ የእድሜ መስመር ብቻ አይመ ሰሉም፡፡ ዘርፈ ብዙ የዘመናት ችግራቸ ውን ያሳብቃሉ፡፡ በክልሉ ለዓመታት የ ተካሄዱ ጦርነቶቹ ልጆቻቸውን፣ ሀብታ ቸውን፣ ተስፋቸውን ነጥቀዋቸዋል፡፡ ብ ዙ ጦርነቶች፣ ብዙ የፍትሕ እጦቶች፣ ብ ዙ ረሀቦች፣ ብዙ በደሎች የማያልቁ የሚ መስሉ፣ እስከአሁንም ያላለቁ፡፡ “ወልዋሎ ካፌ” ደጅ ላይ መሰየሜን አ ትርሱ፡፡ ከለማኞቹ ጎን ለጎን ከዋናው አ ስፋልት ላይ ጥቂት የአእምሮ ህመምተኞ ች ይታዩኛል፡፡ እኔ ከተቀመጥኩባት “ወ ልዋሎ ካፌ” ትይዩ የከተማዋ ዝነኛ “እብ ድ” በእንጨት የሰራውን የጦር መሳርያ እያቀባበለ በመተኮሰ ራሱን ያዝናናል፡፡ ስለዚህ “እብድ” ብዙ ማወቅ ፈለኩኝ፡ ፡ ወታደር እንደነበረና በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መካፈሉ ተነገረኝ፡፡ ከዚያ በላይ ስለሱ የሚያውቅ አላገኘሁም፡፡ ወልዋሎ ካፌን ለመልቀቅ ሂሳብ ስከፍል “እብዱ” የእንጨት ጠመንጃውን ወደ እኔ አቀባ ብሎ እየተኮሰ ነበር።

ሓፊሶሞም የኤርትራ ጦርነት አዲግራትን ያዳከማ ት በንግድ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ልጆ ቿን ቀርጥፎ በልቶባታል፡፡ ይህ የድንበ ር ጦርነት ለአዲግራትና አካባቢዋ የዘው ትር ጭንቅ የዘውትር ጣር ነበር፡፡ ከጦር ነቱ ቀጠና በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ለተ ገኘቸው አዲግራት እያንዳንዱ ምሽት የ ጭንቅ ሌት ሆኖ አልፏል፡፡ መንግሥት በአዲግራትና አካባቢዋ የ ሚገኙ የትግራይ ቀበሌዎችን እያሰሰ፣ ወ ጣት እያደነ ለጦርነት መልምሏል፤ ለዚ ያውም በግዳጅ፡፡ በትግራይ በሚገኙ ሁ ለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገብቶ ሰ ፊ የማሳመን ሥራ ሠርቷል፡፡ በየክፍሉ እየዞረ ተማሪዎችን ለውትድርና መዝግ ቧል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ መልማዮ ች “እናንተ መዋጋት አይጠበቅባችሁም፣ ኮምፒውተር ላይ ቁጭ ብላችሁ ነው የ ምታዋጉት፤ የተማረ ሰው ስላስፈለገን ነ ው የምናስቸግራችሁ” እያሉ ያባብሉ ነ በር አሉ፡፡ በወቅቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የነበረ የአ ዲግራት ወዳጄ እንዳጫወተኝ ከሆነ ይ ህ ማባበል የኋላ ኋላ ብዙም አዋጪ ሆ ኖ ስላልተገኘ ወደ ግዳጅ ምልመላ ተገብ ቷል፡፡ “የአዲሳባ ሕዝብ መጥቶ ሊዋጋላ ችሁ ትጠብቃላችሁ እንዴ?!” እንባል ነ በር ይላል ይኸው ወጣት፡፡ ጦርነቱ እየ ተራዘመ ሲመጣ ከአንድ ቤተሰብ ቢያን ስ አንድ ልጅ መገበር ግዴታ ተደረገ፡፡ ይህን ያላደረጉ ቤተሰቦችም ለእስር ተዳ ርገዋል፡፡ በድንበር ጦርነቱ ወቅት ጥሩ ገ ቢ የነበራቸው ወጣቶች ልጆቻቸውን በ ብዛት ወደ አዲስ አበባ ማሸሽ ችለዋል፡ ፡ የቀበሌ ሹማምንት ሕዝቡ ልጆቹን ወ ደ ከተሞች እያሸሸ እንደሆነ በመረዳታ

ወዲ ገሰሰ ወዲ ገሰሰ አለማያ ዩኒቨርሲቲ አብሮኝ የተማረ ወጣት ነው፡፡ የአራት ዓመት የ ዲግሪ ትምህርቱን ለመጨረስ 7 ዓመት ፈጅቶበት ነበር፡፡ዩኒቨርሲቲ እንደገባ የ አሉላ አባነጋ የቅርብ ዘመድ እንደሆነ በ ማስወራቱ ስሙ በዩኒቨርሲቲው ገነነ፡፡

ከአዲግራት እስከ


ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ሁለተኛ ዓመት ስንደርስ ደግሞ “አፄ ዮ ሃንስ አራተኛ የእናቴ የቅርብ ዘመድ ናቸ ው” ሲል ዘር ቆጥሮ፣ ፍሬሽማን ላይ የወ ሰደውን የኢትዮጵያን ታሪክ አጣቅሶ ተ ሟገተ፡፡ በዚህም የብዙ ተማሪዎች መጠ ቋቆምያ ለመሆን በቃ፡፡ ከተማሪ ዐይን ለ መሰወር ግን ሱስ ውስጥ መደበቅ ነበረበ ት፡፡ወዲ ገሰሰ በከፍተኛ የጫትና የአደገ ኛ እፅ ሱስ ከመጠቃቱ በፊት ይፈጥራቸ ው በነበሩ ቀልዶቹ ይታወቅ ነበር፡፡ በእ ርሱ ስም የተመዘገበች ቀልድ ዛሬም ድረ ስ አትረሳም፡፡ ላካፍላችሁ፡፡ በአለማያ ዩኒቨርሲቲ አብዝተው ስለ አ ሳ ሀብትና ስለ አለማያ ሀይቅ ይጨነቁ የ ነበሩ ዶክተር ነበሩ፡፡ ዶክተር ብሩክ ይ ባላሉ፡፡ ሌሊት ሌሊት እየተነሡ በአለማ ያ ሀይቅ ላይ ምርምር ያደርጉ ነበር፡፡ ዘ ወትር ለአሳ ሀብት እንደተጨነቁ ነው የ ኖሩት፡፡ ወዲ ገሰሰ ታድያ አንድ ወቅት ላይ በአገሩ የአዲግራት ልጆች “ፈተና እ የደረሰ ነው፤ አጥና፤ ኋላ ይቆጭኻል” የ ሚል ምክር ሲለገሰው እንዲህ አለ አሉ፡ ፡ “who cares about the dead fish except Dr. Brook.” ዶክተር ብሩክ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨ ርሲቲ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ምክት ል ዲን ናቸው፡፡ ወዲ ገሰሰ ግን በአዲግ ራት ከተማ ቪዲዮ ቤት ቆሞ ፊልም ይ ተረጉማል፡፡ ዲግሪ ይዘህ እንዴት ይህን ስራ ትሰራለህ አልኩት፡፡ “who cares about the dead fish except Dr. Brook” አለኝ፣ ሲጋራውን ፊቴ ላይ እ ያቦነነ፡፡ ወዲ ገሰሰ ይህንን አባባሉን እስ ከዛሬም አልተወውም ማለት ነው፡፡ ወ ደ “እብደት” ሰፈር እያመራ ለመሆኑ ቅን ጣት ታክል አልተጠራጠርኩም፡፡ who cares about….!

የእነ አርከበ ቤት አዲግራት “ፒያሳ” እያለች የምትጠራ ው ሰፈሯ በብዙ ለማኞች፣ በብዙ ሙ ዚቃ ቤቶችና በጥቂት የአእምሮ ህመም ተኞች የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ሰፈር አንድ ባለአንድ ፎቅ ቀይ ቡኒ ሕንፃ ይታያል፡፡ የቀድሞ የ “አግኣዚ ትምህርት ቤት” ተ ማሪዎች “አልሙናይ ኅብረት ጽ/ቤት” ነ ው፡፡ በቀድሞው ዘመን ትግራይ ውስጥ የትምህርት እድል ለማግኘት ሦስት ቦታ ዎች ብቻ ነበሩ፡፡ አቶ መለስ የተማሩበ ት የአድዋው ንግሥተ ሳባ፣ እያሱ በርሄ የተማረበት የመቀሌው አፄ ዮሃንስ እና የ አዲግራቱ አግኣዚ ናቸው፡፡ የአዲግራቱ “አግኣዚ ትምህርት ቤት” የአሁኖቹን ት ላልቅ ባለስልጣናት አስተምሯል፡፡ አቶ ስዩም መስፍን፣ ጄነራል ሀየሎም አርአ ያ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም /ያልተረጋ ገጠ/፣ አቶ ታደሰ ሀይለ፣ አቶ አርከበ አ ቁባይ ወዘተ የዚሁ ትምህርት ቤት ፍሬ ዎች ናቸው፡፡ የተወዳጁን የቀድሞ የአዲሳባ ከንቲባ የ አርከበ እቁባይን ቤት እናሳይህ ሲሉኝ በ ዙርያው አርከበ ሱቆች አይጠፉም ብዬ ለራሴ ቀለድኩ፡፡ብዙም አልተሳሳትኩ ም፡፡ የነአርከበ ቤት በዋናው የአዲግራ ት መንገድ በስተቀኝ “እስላም መቃብር” ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ 500ካሬ ላይ ያረፈ በድንጋይ ርብራብ የታጠረ የገጠር ቤት ነው፡፡ ዙርያውን ተሸንሽኖ ለሱቆች ተከ ራይቷል፡፡ “ጂኤም ፀጉር ቤት”፣ “ፍሰሀ ክሊኒክ”፣ “ቲዜድ መስታወት ስራ”፣ እና አንድ ስም ያልተሰጠው ፑል ቤት የነአር ከበን ቤት ተከራይተው ይነግዱበታል፡ ፡ የአቶ አርከበ ወንድም እስከ ቅርብ ጊ ዜ ድረስ ቤቱን ይቆጣጠር እንደነበረ ተነ ግሮኛል፡፡ አቶ አርከበ ልምድ የቀሰሙት

ከቤታቸው ኖሯል፡፡ እንደ መቀሌ ሁሉ በአዲግራትም የአ ቶ መለስ ምስል ያለበትን ነገር መመል ከት ቀላል ነው። ብዙ ነዋሪዎች የርሳቸ ው ምስል ያለበትን ቲሸርት ለብሰው ይ ታያሉ፤ ምፅዋት ጠያቂዎችን ጨምሮ፡፡ ባጃጆች ላይ “ረዥም እድሜ ለአቶ መ ለስ” የሚል ጽሑፍ ተመልክቻለሁ፡፡ ፀ ጉር ቤት ውስጥ የፀጉር ቁርጥ አይነቶች ን በሚያሳዩ ፖስተሮች መሀል የአቶ መ ለስ ግርማ ሞገስ ያለው ፎቶ ተሰቅሎ አ ስተውያለሁ፡፡ እነአርከበ ቤት ከፊሉ ለፑል ቤት እን ደተከራየ ነግርያችሁ ነበር፡፡ በዚሁ ፑል ቤት ጎራ ብዬ ከአዲግራት ልጆች ጋር ፑ ል በገጠምኩ ጊዜ ያየሁትም ይህንኑ ነ ው፡፡ በፑል ቤቱ ግድግዳ ዙርያ ብዙ የ ምእራቡ አለም የራፕና የሂፕሆፕ ዜመ ኞች ፎቶ ተለጥፏል፡፡ እነ አር ኬሊ፣ብሪ ትኒ ስፒርስ፣ 50ሴንት፣ ጂ ዩኒት፣ ጃኔት ጃክሰን፣ ጄኔፈር ሎፔዝ፣ ሻኪራ፣ ቢዮን ሴ፣ ጄይዚ ወዘተ ሰውነታቸውን ተገላል ጠው የተነሷቸው ባለቀለም ፎቶዎች ተ ሰቅለዋል፡፡ በእነዚህ መሀል የአቶ መለስ ፎቶ ሰርጎ ገብቷል፡፡ ይህ የአቶ መለስ ፎ ቶ የሚገኘው “ማርያም ጠብቂኝ” የሚ ል የቅድስት ማርያም ፎቶ ስር መሆኑ ነ ገሩን ይበልጥ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ አ ቶ መለስ ካፖርት ለብሰው ሞባይል እያ ናገሩ ይታያሉ፡፡ “እመቤቴ ጠብቂልኝ” የ ሚል ትርጉም እንዲኖረው ተደርጎ የተዘ ጋጀ ነው? የአቶ መለስን ፎቶ ከቅድስት ማርያም ምስል ስር የማስቀመጡን ነገር ኢንተርኔት ለመጠቀም በገባሁባቸው ሁ ለት ካፌዎች ውስጥም ተመልክቻለሁ፡ ፡ የተሰጠኝ ማብራርያ እኔው እንደገመ ትኩት አይነት ነው፡፡ “እመቤቴ እንድት ጠብቅልን ነው” ብላኛለች አንዲት በጽ ሕፈት ሥራ የምትተዳደር ሴት። ነገሩ ሰ ምና ወርቅ ይሁን አይሁን ግን ለማረጋገ ጥ አልችልም።

ሐበሻዊ ቃና

21

የጉዞ ማስታወሻ

ፎቶ - መሀመድ ሰልማን

በጦርነቱ የወደመ በዛላንበሳ የሚገኝ ፋብሪካ

ወደ ዛላንበሳ

ፎቶ - መሀመድ ሰልማን

በግንባታ ላይ የሚገኘው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ

የሃይማኖቶች ፍቅር በኢትዮጵያ በዕድሜ አንጋፋው የካቶ ሊክ ካቴድራል የሚገኘው በአዲግራት ነ ው፡፡ ለከተማዋ ግርማ ሞገስ ሆኗታል፡ ፡ አባ ወልደ ሥላሴ ተስፋዬ ይባላሉ የካ ቴድራሉ አስተዳዳሪ፡፡ በአክብሮት ተቀ ብለው አስተናገዱኝ፡፡ ወደ መቅደስ ይ ዘውኝ ገብተው የሎሬት ሜተር አርቲስ ት አፈወርቅ ተክሌን ድንቅ ስእል አስጎበ ኙኝ፡፡ ስእሉ በመቅደሱ የፊት ለፊት ግ ድግዳ በትልቁ ተዘርግቶ ይታያል፡፡/ፎቶ ውን ይመልከቱ/ አርቲስት አፈወርቅ ይ ህንን ስእል የሰራው በ1967 ሲሆን ግማ ሽ ብር ብቻ ተከፍሎት ቀሪውን በበጎ ፍ ቃደኝነት ነው የሰራው፡፡ አንጋፋው ካቴድራል በ1947 ነው ግን ባታው የተጀመረው፤ የሚገርመው ካቴ ድራሉ በ1960 ሲመረቅ የእስልምናና የ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በግ አርደ ው ደግሰዋል፡፡ ያኔ የተጀመረው የሃይማ ኖቶቹ ወንድማማችነት ዛሬ አድጎና ተመ ንድጎ በሚያስገርም ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ አባ ወልደ ሥላሴ ቢሮ ስት ገቡ በወርቃማ ቀለም የተጻፈ የምስክር ወረቀት ታያላችሁ፡፡ “አላሁ አክበር” የ ሚል ቃል በጉልህ ተጽፎበታል፡፡ ትገረ ማላችሁ፡፡ የአዲግራት ሙስሊሞች አን ዋር መስጊድን ሲገነቡ የካቶሊክ ቤተክር ስቲያን የገንዘብ መዋጮ እና ሌሎች ድጋ ፎችን በማድረጓ የተሰጣት የምስክር ወ ረቀት ነው፡፡ አዲግራት የሚገኘውን የጎልጎታ መድ ኀኔዓለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን

ዛላንበሳ

ጎበኝ ያገኘኃቸው ህንዳዊት መነኩሲት እንደነገሩኝ ከሆነ ማዘር ቴሬሳ ጋር ሆነ ው መንግሥቱ ኀ/ማርያምን ጎብኝተው ታል፡፡ በሕዝቦቹ ላይ በደል እንዳያደር ስ በግልጽ ተማጽነውትም ነበር፡፡ የቅድ ስት ማርያምን ምስልም በስጦታ መልክ ሲያበረክቱለት “ኀይለማርያም የሚለው የስምህ ትርጉም ‘የማርያም ኃይል’ ማለ ት ስለሆነ ነው ይህንን የምሰጥህ” ብለው ት ነበር፡፡ “መንግሥቱም በስጦታው እ ጅግ ተደሰተ” ብለውኛል፡፡ አዲግራት መሞካሸት ካለባት በሃይማ ኖት ተከታዮቿ መልካም የእርስ በርስ ቁ ርኝት መሆን ይኖርበታል፡፡ ሙስሊሞች ቤተክርስቲያን ሲሰራ እገዛ አድርገዋል፡ ፡ ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የማህሌት ቅ ዳሴን ተራ በተራ አንዱ የአንደኛው ቤተ መቅደስ በመሄድ ያካሄዳሉ፡፡ መስጊድ በማሰራት ፍቅራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይህ ንንም በአዲግራት ቆይታዬ እውነት መ ሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ አባ ወልደ ሥላሴን ተሰናብቼ ስወጣ “ኢትዮጵያን ወደፊት የሃይማኖት ግጭ ት ያሰጋታልን?” ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ እ ያቅማሙ “ይመስለኛል!” ካሉ በኋላ በዝ ምታ ተዋጡ፡፡

ፎቶ - መሀመድ ሰልማን

ደቡብ ኤርትራ ከሰሜን የኢትዮጵያ ጫፍ ስትታይ ይህን ትመስላለች

ማን ያሠራው ይመስላችኋል? ከሙስሊ ምና ከካቶሊክ አማኞች የተውጣጣ ኮ ሚቴ፡፡ ይህ በዐይኔ ያየሁት ነገር ነው፡፡ “መድኅን ለድኅነት ሕይወት” የተሰኘ ማ ኅበር በጋራ መሥርተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ አቅም ያጡትን ይደግፋሉ፡፡ ቤተ እምነ ቶችን ያስገነባሉ፡፡ የተቸገሩ ይጦራሉ፡፡ እኔ በጎበኘኋቻው ጊዜ የደርግ ተጎጂ ቤ ተሰቦችን በይቅርታው ጉዳይ በማነጋገር ሥራ ተጠምደው ነበር፡፡ አባ ወልደ ሥ ላሴ ጠረጴዛቸው ላይ አንድ ደብዳቤ አ ንስተው አሳዩኝ፡፡ ያን ቀን ሙስሊሞች ለ ምሳ ግበዣ እርሳቸው እንዲገኙላቸው የ ላኩት ደብዳቤ ነው፡፡ አባ ወልደ ሥላሴ በአዲግራት ካቴድራ ል ከሎሬት አፈወርቅ ስእል ባሻገር በትን ሽ የመስታወት ብልቃጥ የተቀመጠ ነገር አሳዩኝ፡፡ለቤተክርስቲያኑ በረከት ሲባል ከማዘር ቴሬሳ ሰውነት ተወስዶ የተቀመ ጠ የስጋ ቁራጭ ነበር፡፡ /ፎቶውን ይመ ልከቱ/ በብዙ ሀገራት ባሉ ካፌድራሎች ይህ የማዘር ቴሬዛ የስጋ ቡራኬ ይገኛል/

ማዘር ቴራዛ ማዘር ቴሬሳ ሶስት ጊዜ ኢትዮጵያን እን ደጎበኙ ተነግሮኛል፡፡ ከዓመት በፊት የ መቀሌ ደንቦስኮ የካቶሊክ ማእከልን ስ

የአዲግራቱ ወያላ “ዛላንበሳ! ዛላንበሳ! አ ሀደ ሰብ ዛላንበሳ!” እያለ ጮኾ ተጣራ፡፡ ስጠጋው ጊዜ “እተው እተው…ቀልጥፍ” አለኝ፡፡ ተሳፈርኩኝ፡፡ ከአዲግራት ወደ ዛላንበሳ ለመሄድ የ10 ብር ታክሲ መያ ዝ በቂ ነው፡፡ ሚኒባሱ እኔ ከተቀመጥኩ በት የኋላ ወንበር ስር ኩልል ያለ ድምፅ የሚያወጣ ሰፒከር ተገጥሞለታል፡፡ በስ ፒከሩ ኤርትራዊው አብረሃም አፈወርቂ ለብቻው ነግሶበታል፣ ኢሳያስ አፈወርቂ በአሥመራ ብቻቸውን እንደነገሡት አይ ነት፡፡ “ሰማይ፣ ፊቅረይ፣ ፊሺክ በሊ፣ ሚ ስጥር ፊቅሪ፣ ሀደራ፣ ሺኮር ….” የተሰኙ ትን ዜማዎች እያከታተለ ይጫወታል፡፡ የታክሲው መጋረጃ “ይከፈት-አይከፈ ት” በሚለው ክርክር ውስጥ ከጎኔ ከተቀ መጠው ጎልማሳ ሰው ጋር ተግባባሁ፡፡ በ ትግርኛ የተጀመረው ትውውቃችን እኔ ቋንቋው ላይ ባሳየሁት መደነቃቀፍ ወደ አማርኛ ተሸጋገረልኝ፡፡ ጎልማሳው ሰው ጥርት ያለ አማርኛ ይናገራል፡፡ በጥያቄ አጣደፍኩት፡፡ በግራና ቀኝ የምናልፋቸ ውን ተራራዎች እያመለከተ ስምና ውለ ታቸውን ተረከልኝ፡፡ በክፍሉ ታደሰ “ያ ትውልድ” ቅፆች ብቻ አውቀው የነበረ ውን የአሲምባ ተራራን በስተቀኛችን በ ርቀት አመላከተኝ፡፡ የአይጋ ተራራዎችን ም እንዲሁ፡፡ ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ን ውጊያ አነሳሁበት፡፡ “እንደሚባለው ብዙ ሰው ሞቷል እን ዴ?” ፈራ ተባ እያልኩ ጠየኩ። ምላሹን በለበጣ ፈገግታ ብቻ ገለጸል ኝ፡፡ ለተወሰነ ርቀት በዝምታ ከተጓዝን በኋላ አንዲት ኮረብታ አመላከተኝ፡፡ “እ ዚህች ጋ ብቻ አንድ ሻለቃ አልቃለች፡፡” ለወታደራዊ ቋንቋዎች ባእድ ስለሆንኩ አንድ ሻለቃ ስንት ወታደር እንደምትይ ዝ መጠየቅ አሳፍሮኝ ሐዘኔን ጭንቅላቴ ን በመወዝወዝ ገለጽኩለት፡፡ “ያችን ደግሞ አየሃት? ሻእቢያ ብዙ ሕ ይወት ከፍሎባታል፤ ያችን ደግሞ እያት ትንቅንቅ ነበር፤ ፈንጅ ቀብረውብን ነበ ር፡፡ ይችን አየሃት? ‘ፋፂ ከተማ’ ትባላ ለች፡፡ ይህ የምታየው ተራራ ደግሞ ‘አ ምባህይወት’ ይባላል፡፡ ሲተረጎም ‘ታደ ጋቸው’ እንደማለት ነው፡፡ ይህ ተራራ ባይኖር ኖሮ በዚህች ከተማ አንድም ሰ ው አይተርፍም ነበር፡፡ ሻእቢያ በተደጋ ጋሚ በአየር ሲደበድባት ተራራው ከለላ ሆኖ ነው ሕዝቡ የተረፈው፡፡ …ያችን ደ ግሞ..እያት …ወዲያ ማዶ….ይችን ኖ…ኖ ይችኛዋ ኮረብታ…. አየሃት አይደል…እ ዛ በአንድ ሌሊት ያለቀው….ደግሞ….።” ጎልማሳው ሰው ከታክሲው በስተግራ ና በስተቀኝ እንደ ፔንዱለም እየወዘዘወ ዘ ተራሮቹን አስቃኘኝ፡፡ የሁሉም ተራራ ች ገድል ጦርነት ነው፡፡ ሞት ነው፤ እልቂ ት ነው፡፡ አብረሃም አፈወርቂ “ተአዲለ”

የሚለውን ዜማ በሚስረቀረቅ ድምፁ ያ ዜማል፡፡ ድምፁ ይስረቅረቅ እንጂ የሚ ያዜመው ዜማ የጦርነት ነው፡፡ ጎልማሳው ሰው ከፋፂ ከተማ ትንሽ ኪ ሎ ሜትር እንደተጓዝን “እኔ መውረጃ ዬ ደርሷል፣ ደህና ሁን” ብሎ ተሰናበተ ኝ፡፡ ምስጋናዬን ሳልጨርስ ሰውየው በ ሚገርም ቅልጥፍና ከታክሲው ዱብ ብ ሎ ወረደ፡፡ ምድረ በዳ ላይ፡፡ በመስኮ ት አሻግሬ አየሁት፡፡ ጥቂት ወታደሮች በተጠንቀቅ ሰላምታ ሲሰጡት ተመለከ ትኩ…በ..ር…ቀ…ት፡፡

ኦሮማይ! ዛላንበሳ ደርሻለሁ፡፡ ከአንድ ኢትዮጵያ ዊ ቤት ጓሮ ቆሜያለሁ፤ ኤርትራን በቅር ብ ርቀት እያየኋት ነው፡፡ ከድንጋይ ር ብራብ የተሠሩ የኤርትራ ቤቶች ቁልጭ ብለው ይታዩኛል፡፡ አንድ የኤርትራ ቤ ተክርስቲያንም ጉልላቷ ይታየኛል፡፡ እን ደ እረኛ “ስማእንዶ!” እያልኩ ጮኸ ብ ዬ ብጣራ እንኳ አቤት! ሊሉኝ የሚችሉ ኤርትራውያን አይጠፉም፡፡ አሁን በአን ድ ኢትዮጵያዊ ቤት ጓሮ ቆሜ በቅርብ የማያት ሆኖም የማልረግጣት የኤርትራ ደቡባዊ የገጠር ከተማ “አምበስተገለባ” ትባላለች፡፡ እኔ ከቆምኩበት በስተሰሜን በ24 ኪሌ ሜትር ርቀት ደግሞ “ሰንአፌ” ትገኛለች፤ ከእኔ በ140 ኪሌ ሜትር ርቀ ት ደግሞ አሥመራ፡፡ ዛላንበሳ ፈርሳ የተገነባች ከተማ ናት፤ ለ ዚያውም በተባበሩት መንግሥታት ድር ጅት እርዳታ፡፡ በጦርነቱ ሻእቢያ ያፈራ ረሳቸው ቤቶች አሁንም ፍርስራሻቸው ተከምሮ ይታያል፡፡ የተወሰኑ አዳዲስ ቤ ቶች ተገንብተዋል፡፡ ለአንድ የፈረሰ ቤት 60 ሺህ ብርና ከዚያ በታች እርዳታ ተ ደርጎ ነው ከተማዋ ነፍስ የዘራችው፡፡ በ ከተማዋ አንድዬ አስፋልት ላይ ታች ሲ ሉ የሚታዩት የመከላከያ ዩኒፎርም የለበ ሱ ሰዎች ናቸው፡፡ የከተማዋ ውብ መኪ ናዎች ደግሞ የወታደር “ኦራል”ሎች ናቸ ው፡፡ የከተማዋ ሊስትሮዎች የሚጠርጉ ት ረዥሙን የወታደር ከስክስ ጫማ ነ ው፡፡ ከተማዋ አሁንም ከ10 ዓመት በኋ ላ ከጦርነቱ መንፈስ የተላቀቀች አትመ ስልም፡፡ “ኢትዮጵያ ሆቴል” ጎራ አልኩኝ፤ የከ ተማዋ ትልቁ ሆቴል ነው፡፡ ነጭ ጋውን የለበሱ ሙሉ ፀጉራቸው ከለበሱት ነጭ ጋውን ጋር ፍጹም “ማች” የሚያደርግ ሰ ው “ታይ ክእዘዝ” አሉኝ፡፡ የሆቴሉ ባለ ቤት ናቸው፡፡ ተስተናጋጅ ስለሌለ አስተ ናጋጅ መቅጠር አልፈለጉም፡፡ ራሳቸው ታዘው፣ ራሳቸው ሠርተው፣ ራሳቸው ያ መጡታል፡፡ አቶ ጣእመ ለምለም እንደ ሚባሉ ግድግዳ ላይ በስማቸው ከሰቀሉ ት የትግርኛ ጥቅስ ተረዳሁ፡፡ “ሲመክሩ ት እምቢ ያለ መከራ ይመክረዋል” አይ ቶ ጣእመ ለምለም ትላለች ጥቅሷ፡፡ ያዘ ዘኩትን ለመሥራት ተፍ ተፍ እያሉ ወሬ ማውራት ጀመሩ፡፡ እያወሩ መሥራት ይ ችላሉ፡፡ የሚያወሩት ሰው የናፈቁም ይ መስላሉ፡፡ በቤቱ ያለኔ ማንም እየተስተ ናገደ አልነበረም፡፡ “አቦይ! እዚህ ያለ ዲሽ የኤርትራ ቲቪ ን ማየት ይቻላል የሚባለው እውነት ነ ው?” አልኳቸው፡፡ መልስ ሳይሰጡኝ እ ጃቸውን በፎጣ ጠራርገው የቲቪውን የ ርቀት መቆጣጠርያ ነኩት፡፡ የኤርትራ ቲ ቪ አንዳንድ የልማት ዜናዎችን በጭፈራ አጅቦ እያቀረበ ነበር፡፡ “ዙርያውን የም ታየው እኮ ኤርትራ ነው፣ የመጣህበት ታክሲም ኤርትራ የእኔ የምትለውን መ ሬት ረግጦ ነው ያለፈው፤ ወደከተማዋ ለመግባት ስለማይመች ነው የኛ ወታደ ሮች የሚቆጣጠሩት” አሉኝ፡፡ ቆየት ብለው የቲቪውን ድምፅ አጠፉና ከጎኑ የተደቀነውን ሬዲዮ ነካኩት፡፡ የት ግርኛ ዜማዎች መዥጎድጎድ ጀመሩ፡፡ የ ኤርትራ ኤፍ ኤም ነበር፡፡ ከአሥመራ የ ሚተላለፈው “95.00 ኤፍ ኤም አሥመ ራ” ዛላንበሳ ካረፍኩበት ሆቴል ኩልል ባ ለ ድምፅ ይሰማል፡፡

ወደ ገጽ 23 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

22

ትዝታ

የባንክ “ታዴ”ዎች በኤርሚያስ አማረ- ቤልጅየም

ታደሰ ተብላችሁ ስም የወጣላችሁ እን ዳትቀየሙኝ፡፡ “ታዴ” ከአንድ ደርዘን ዓ መት በፊት አዋሽ ባንክ ውስጥ በጣም የ ምንቀራረብ ጓደኛሞች የምንጠራራበት የቢሮ ሰዓት ኮዳችን ነበር፡፡ ነገሩ እንዲ ህ ነው፡፡ የሥራን ዓለም “ሀ“ ብዬ የተያ ያዝኩት ልክ የሚካኤል ዕለት ነሐሴ 12 ቀን 1990 ዓ.ም አዋሽ ኢንተርናሸናል ባ ንክ ውስጥ ነበር፡፡ ለምረቃ ያሰፋኋትን “ሱት” ቂቅ ብዬባት በተመራቂ ሰልጣኝ ነት (Graduate Trainee) ወደተመደብ ኩበት ስቴዲየም ቅርንጫፍ አመራሁ፡፡ የፍሬሽ ነገር … ገና አንድ ደንበኛ በር ላ ይ ተፈትሾ ወደ ውስጥ ዘው ከማለቱ ከ ሁሉም ቀድሜ የምነሳው እኔ ነበርኩኝ፡፡ አንዲህ እንዲህ እያልኩ አንድ ወር ሞላ ኝ፤ መላመድም መጣ፡፡ ቆየት ካሉት የባ ንኩ ባልደረቦች ጋር ለምሣ እና ለሻይ አ ብሮ መውጣት ተጀመረ፡፡ አዲስ ስለነበ ርኩኝ ወሩ መቼ እንደደረሰ ትዝ አይለኝ ም … አቤት ፍጥነት፡፡ ገነት የተባለች የ ቅርንጫፉ የቁጠባ ሒሳብ ክፍል ኃላፊ ለደመወዝ መቀበያ የሚሆነኝ አካውንት እንድከፍት ስትነግረኝ በሕይወቴ ለመጀ

ቶ አገኘሁት፡፡ 5 ብር አስቀርቼ ሌላውን ጠራርጌ አወጣሁና ምሽቱን ከሁለት የዩ ኒቨርሲቲ ጓደኞቼ ጋር ተዝናናንበት፡፡ እ ንደ አባቴ 20 ብር በዝረራ ባያስወጣንም ወደድ ያሉ የአዱ ገነት የምሽት ክለቦችን ከመዳፈር ግን አላገደንም፡፡ በሁለተኛው ቀን ብሩ አለቀ፡፡ ሁለተኛ ው ደመወዜ የ30 ቀን ሳይሆን የ300 ቀን ያህል ራቀብኝ፡፡ ብጎትተው ብጎትተው ሊደርስ ነው? ጭራሽ ብድር ውስጥ ዘፈ ቀኝ፡፡ መቼም ሳይደግስ አይጣላም አይ ደል … ባንክ የምትሠሩ ታውቁታላችሁ፤ አንድ “ኢመርጀንሲ ሎን” የሚባል ፈተ ና ከባንኮች መንደር አለ፡፡ የሶስት ወይ ም የአራት ወራትን ደመወዝ ለባንኩ ሠ ራተኞች በብድር መልክ የሚያሰጥ እና ከወለድ ነፃ ሆኖ በ24 ወራት ውስጥ የ ሚከፈል ዕዳ ነው፡፡ ልክ ሁለተኛ ወሬን ስጨርስ የ”ኢመር ጀንሲ ሎን” አመልካች ሆንኩኝ፡፡ ሁለት ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት ብር አፈ ስኩኝ፡፡ ማን ይቻለኝ! ለአራት ወራት ኪ ሴ ሳይናጋ በጥሩ ሁኔታ ዘለቅኩኝ፡፡ አም ስተኛው ወር ላይ ግን ለደመወዝ አንድ

ወዲያው ወዲያው ብድር እያደስን መውሰዳችን “ታዴ” የሚለውን ስም አትርፎልን ዞር አለ

መሪያ ጊዜ በምቀበለው ደመወዝ ላይ ሰ ፋፊ ዕቅዶችን መንደፍ ጀመርኩኝ፡፡ የተ ቀጠርኩበት ቋሚ ደመወዝ 715 ብር ሲ ሆን ታክስና የጡረታ መዋጮ ሲነሳበት ግማሽ ሺህ የተጣራ ይደርሰኛል፡፡ ተማሪ ሳለሁ አባቴ ስለ እነርሱ ዘመን የብር የመግዛት አቅም አንድ ዕውነተኛ ገጠመኙን አጫውቶኝ ነበር፡፡ ጊዜው በ1950ዎቹ መጨረሻ ነው፡፡ በትምህር ት ቤት ጥሩ ውጤት ያስመዘገበው አባባ ከአያቴ (አባ መንግሥቱ ይባላሉ) 20 ብ ር ተሸለመ፡፡ ከባለንጀሮቹ ጋር 20 ብሩን ይዘው በሞያሌ ወደ ኬንያ ለማሳበር ሁ ሉ አቅደው ነበር፤ አንዳነጋገሩ፡፡ “የ፩ ብ ር ዳቦ ገዛን፤ አራት ሆነን መጨረስ አቃ ተን፡፡ ከሰፈር ራቅ ብለን ጠላ ተጎነጨን በት፤ ብሩ ፍንክች ሊል ነው! እየዞርን ያ ማረንን እየገዛን ስንበላና ስንጠጣ 20 ብ ሩ ሳያልቅ ቀኑ መሸብን” በማለት የነገረ ኝ ታሪክ አዋሽ ባንክ ገብቼ የመጀመሪያ ደመወዜን እስክቀበል ድረስ እንደ ግነት ነበር የወሰድኩለት፡፡ ልክ ነሐሴ መጨረ ሻ ላይ ገነት ባስከፈተችኝ አካውንት ው ስጥ 400 ብር የሚያክል ግዙፍ ብር ተኝ

ሳምንት ሲቀረኝ ያንጠራራኝና ብርድ ብ ርድ ይለኝ ጀመር፡፡ ትዝ ሲለኝ የአራት ወራት ወርሃዊ ክፍያዬን ፈፅሜያለሁ ለ ካ፡፡ 90 ሲባዛ በ4 እኩል ይሆናል 360፡ ፡ ቀሪውን ዕዳዬን ከየትም ሞላልቼ ከዘ ጋሁ በኋላ አዲስ ብድር ወዲያው ጠየኩ ኝ፤ ነገሩ እዛው በዛው ይባላል፡፡ አዲሱን ብድር ስቀበል የተጣራ 360 አልያም እ ንደከፈልኩት ወርሃዊ ክፍያ መጠን ይደ ርሰኛል፡፡ ባስ ሲልብኝ 3 ወር እየጠበቅ ኩኝ፤ ከቻልኩት ደግሞ ከአምስት ወራ ት በኋላ ብድሩን እያደስኩኝ ሕይወትን ከአዋሽ ባንክ ጋር ለሰላሳ ስድስት ወራት ታግያታለሁ፡፡ ታድያ ወዲያው ወዲያው ብድሩን እያ ደስን መውሰዳችን ታዴ” የሚለውን ስ ም አትርፎልን ዞር አለ፡፡ ጠዋት ስንገና ኝ ኤርሚያስ፣ ብርሃኑ፣ ነብዩ ተረስተው በታዴ (ታደሰ) ስም ሰላምታ መለዋወጥ ጀመርን፡፡ ዛሬ ዛሬ በባንኮች መንደር እ ንዲህ ዓይነት ነገር ይዘወተር ይሆን? እስ ቲ ታደሰዎች አለን በሉን፡፡

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

የእኛ ዘመን አስኳላ በልጅነታችሁ የሰራችሁት ወይ ጓደ ኞቻችሁ ሲሰሩ ያያችሁት የጅል ሥራ የሚመስል የልጅ ሥራ የለም?፡፡ አሁን ስታስቡት ልጅነት ጅልነት እንደሆነ የ ምታዩበት ወይም የአሁኑ ዘመን ልጆች ቢሆኑ አይሰሩትም የምትሉት ነገር ማ ለቴ ነው፡፡ የ3ኛ ወይ የ4ኛ ክፍል ተማ ሪ እያለሁ ያጋጠመኝ አንድ ሁለት ነገ ር ሰሞኑን ትዝ አለኝ፡፡

የደደብ ታቱ! አንድ ሰሞን የክፍላችን ተማሪዎች ግ ንባራቸው ላይ ቁስል እና ጠባሳ ይታ ይባቸው ጀመር፡፡ ከቀን ወደ ቀን ግን ግንባሩ የቆሰለ ተማሪ ቁጥር እየበዛ መ ጣ፡፡ እናም ወሬው እኔ ጋ ደረሰ፡፡ ትን ሽ ሞክሬው ሲያመኝ ትቼው ይሁን ወ ይም የአባቴን ግርፊያ ፈርቼ እያማረኝ ትቼው ይሁን አላስታውስም፡፡ ቢሆን ም ግን የተመከርኩት እና ሁሉም ተማ ሪ የቆሰለበት ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ‹‹በ ጣትህ ግንባርህን ዝምም....! ብለህ ስ ትፈትገው ትምህርት ይገባሃል!››፡፡ ም ክሩ መፈተግ ይላል እንጂ ስንት ጊዜ መፈተግ እንዳለብን ስለማይጠቅስ የነ በረው አማራጭ ሲፈትጉ..ሲፈትጉ..ወ ሎ ሲደማ ወይ ሲያቃጥል በግድ ማቆ ም ነው መሰለኝ፡፡ ትምህርት እንዲገባ ግንባር ማቁሰል፡፡ የጅል ጠባሳ ለጥፎ ወሩን ሙሉ መታየት፡፡ የደደብ ታቱ!

የደብተራ ምክር! የእርሳስ ቅራጭ መብላት የተጀመረበ ትንም ዘመን አስታውሳለሁ፡፡ ለወትሮ ው እርሳስ በመቅረጫ ስንቀርጽ የሚወ ድቀውን ፍቅፋቂ እንጨት እንጥለው ነበር፡፡ አንድ ሰሞን ግን ሁሉም ቅራ ጩን በጥንቃቄ ይሰበስብ ጀመር፡፡ አን ድ ቀንም እንደሚበላ ነገሩኝ፡፡ ለምን? ጭንቅላት ይከፍታል! ጎበዝ ተማሪ ያ ደርጋል! በላሁ እንዳልላችሁ ውሸት ይ ሆንብኛል፡፡ መብላቴንም አለመብላቴ

ይህ ጹሁፍ ከኤርሚያስ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው

በናኦድ ቤተሥላሴ (ሜሪ ላንድ፣ አሜሪካ)

ንም አላስታውስምና፡፡ ፋሽኑ ግን ከነም ክሩ ትዝ ይለኛል፡፡ የደብተራ ምክር ሳይ ሆን አይቀርም! መቼም ጎበዝ ተማሪ ለመሆን የማይመ ኝ የለምና፤ ወደ ጎበዝ ተማሪነት የሚወ ስድ ማንኛውም አቋራጭ፤ ምንም ዓይነ ት የጅል ሥራ ቢሆን ተቀባይነት ማግኘ ቱ ብዙም አያስገርምም፡፡ ቢሆንም ግን ያስገርማል! በምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ! ልጄ አንድ እርሳሱን የሙጥኝ ብሎ ይንከባከባታል፡ ፡ ማይ ላኪ ፔንስል ይላታል! የቤት ሥራ የሚሰራው በእርሷ ነው፡፡ የረሳሁትን የ ልጅነት ታሪክ አስታወሰኝ! እንደ እኔ ልጅነት፤ ልጄም እርሳሱን ል ብላ እንዳይለኝ ብቻ!

ቲቸር ኃይለኛ ናቸው በእኛ ዘመን አስተማሪ የሚከበረው በ ኃይለኛነቱም ነበር፡፡ ኃይለኛ ማለቴ በ ጭካኔ ግርፊያቸው ማለቴ ነው፡፡ መቼ ም በየትምህርትቤቱ ያለ የአሰተማሪ ግ ርፊያ አይነት ቴያትር እንጂ እውነት የተ ደረገ አይመስልም ነበር፡፡ የቲቸር ተስፋ ዬንም ግርፊያ ስታይል ሳስታውስ የሚሰ ማኝ ይኸው ነው፡፡ ቲቸር ተስፋዬ የስድስተኛ ክፍል የሳይን ስ አስተማሪ ነው፡፡ ግማሹን ክፍለጊዜ የ ሚያሳልፈው በክፍላችን ካሉት ተማሪዎ ች መካከል በመልክ ቁንጅና ከተመሰከ ረላት፤ በሃብታም ልጅነቷ እና በእድሜ ዋም ታላቃችን ከሆነችው ከወይንእሸት ዴስክ ላይ ተቀምጦ ነው፡፡ አስተማሪ ነ ውና ደብተር ማስደገፊያዋ ዴስክ ላይ ይ ቀመጥና ቁልቁል እያየ ይነዘንዛታል!፡፡ ቲቸር! ስለሆነ ማንም ምንም አይለው፡ ፡ እርሱ ከወይንእሸት ጋር ሲያወራ ድን ገት አንዱ ተማሪ ድምጽ ያሰማ እንደሆነ ያ ተማሪ ጉዱ ፈላ፡፡ ልጁ ይጠራና ከተማሪ ፊት ይንበረከካ

እስካሁን

ል (ወይንእሸት የምትቀመጠው ፊት ወ ንበር ላይ ነው)፡፡ ከዚያ ተማሪው የእጆ ቹን መዳፎች መሬት ላይ እንዲያደርግ ይታዘዛል፤ ከዚያ ቲቸር ተስፋዬ ዳስተር ያነሳና እጁ ላይ ያስቀምጣል፤ ከዚያ በሸ ፋፋ ጫማው ተረከዝ ዳስተሩን ዘሎ ይረ ግጠዋል፡፡ ልጁን አያድርገኝ.. ሌላም አስተማሪ ደግሞ አለች! ቲቸር ፈለቀች፡፡ የእርሷ ስታይል ደግሞ በጣቶ ች መካከል እስኪሪቢቶ አስገብቶ የተማ ሪውን ጣቶች ባለ በሌለ ኃይሏ ጨፍል ቃ ማፍተልተል ነው፡፡ ቢክ እስኪሪቢቶ ቀፎው ክብ አይደለም፤ ባለ ብዙ ማዕዘን ነው፡፡ ለዚህ ቅጣት ተመራጭ መሳሪያ ዋ ነበር፡፡ እስከአሁን ሳስበው ያመኛል.. ቲቸር አክሊሉ ደግሞ ጥፋት አጠፋ የ ተባለውን ልጅ የሚቀጣው በተማሪዎች እርዳታ ነው፡፡ መጀመርያ የልጁን እጆ ች ተማሪዎች እንዲይዙት ያደርጋል፡፡ ተ ማሪዎች ልጁን ወደ ዴስካቸው ሲወጥ ሩት፤ ቲቸር አክሊሉ የልጁን ቂጥ መለ ጥለጥ ነው፡፡ ቲቸር ተሰማ ቢላት (ዳሪክተሩ) በበግ

እና

ታናሽ ወንድሜ የፊልም ሱሰኛ ብቻ ሳይሆን አቃቂረኛም ነ ው፡፡ አቃቂሩ ግን መደዴ አይደለም ሙያዊ ነው፡፡ አልፎ አል ፎ ወደ ቤቱ ስሄድ የማገኘው ፊልም ሲያይ ነው፡፡ እኔን ሲያየ ኝ ታዲያ ‹‹Ramboን ላምጣልህ ወይስ Titanicን ይለኛል›› እ ውነቱን ነው ታዲያ፡፡ እኔም እውነቴን አንዱን እመርጣለሁ፤ ለአስራ ምናምነኛ ጊዜ በተመስጦ አያቸዋለሁ፡፡ የፊልም ዓለ ሜ በራምቦ እና ታይታኒክ ዘመን ላይ እንዳለቀ እርግጠኛ ነኝ፡ ፡ ምክንያቱም አሜሪካ ከመጣሁ እንኳን እኒህን ፊልሞች በአ ሳፋሪ ቁጥር ደጋግሜ አይቻቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎ የምወዳቸው አይነት ፊልሞች ብቅ ብለው አይቻለሁ ግን ማ ን እንደ ራምቦ! ሌላው መዞር ያቆመው ዓለሜ የዘፈን ዓለሜ ነው፡፡ የኔ የዘፈን ዓለም የሚያቆመው ኤፍሬም ታምሩ ላይ ነው፡፡ ‹‹ልመደው ል መደው ሆዴ›› የሚውን ካሴት ሙሉውን ዘፈን በቃሌ የማውቀ ው ይመስለኛል፡፡ ከዚያ ወዲያ ከአንድ ሳምንት በላይ የወደድ

አለንጋ ይጋረፋል፤ ቲቸር መልካ በው ሃ ጎማ፤ ቲቸር አበባ በማስመሪያ፤ ቲ ቸር በለጡ ጆሮ በመቆንጠጥ….ሁሉም ብቻ የራሱ ስታይል አለው፡፡ ከሁሉ ግን የሚገርመው የትምህርት ቤቱ ዘበኛ የሃምሳ አለቃ ግርፊያ ነው፡ ፡ ሃምሳ አለቃ የትምህርትቤቱ ገራፊ ና ቸው፡፡ ቀንደኛ ረባሾች ለሃምሳለቃ ተ ላልፈው ይሰጣሉ፡፡ ሃምሳ አለቃ፤ ቦር ጫም፤ ሁልጊዜ የጣሊያን ኮፍያ የሚ ያደርጉ፤ የንጉሡ ዘመን ቅሪት ያለባ ቸው የክቡር ዘበኛ ወታደር ነገር ናቸ ው፡፡ ከደባሪ የዘበኝነት ሥራቸው የሚ ገላገሉት ተማሪ ለመግረፍ ሲጠሩ ብ ቻ ነበር፡፡ ሃምሳ አለቃ መቀስም ያዥ ናቸው፡ ፡ ጠዋት ጠዋት ሰልፍ ላይ ጸጉር ሲ ፈተሸ፤ ቅጫም የተወረረ ጸጉር መገኘ ቱ አይቀርም፡፡ የሃምሳ አለቃም መቀስ የሚሰራው ያኔ ነው፡፡ ያንን ጸጉር እን ዳይሆን አድርጎ መሸክሸክ የሃምሳ አለ ቃ ስራ ነው፡፡ ከአስተማሪዎች እና ከሃምሳ አለቃ የ ተረፈ ግርፊያ ደግሞ የሚከናወነው በ ክፍል አለቆች ነው፡፡ የክፍል አለቃ እ ንደ ንጉስ ያደርገዋል፡፡ እኔም ይሄ እድ ል ገጥሞኝ የነገስኩበት ክፍል ነበር፡፡ ...እና አንድ ቀን አስተማሪዋ አንድ ሁ ለት ተማሪዎችን ‹‹ግረፋቸው›. ብላ ወ ረወረልኝ፡፡ አንደኛዋ ተገራፊ በእድሜ ም በቁመት ከእኔ እጥፍ ናት፡፡ ስለዚህ የእጇን መዳፎች አነጣጥሬ መምታት አልቻልኩም፡፡ እናም ባለ በሌለ ኃይ ሌ ተንጠራርቼ የሰነዘርኩት አለንጋ የክ ንዷ መታጠፊያ ላይ አረፈ…ከዛ ክፍሉ ን ቀውጢ አደረገችው..ከዛ ወዲህ ተ ማሪ ገርፌ አላውቅም፡፡ ይሄን ሁሉ ትዝታ ያመጣብኝ በእኛ ስቴት አንድ የሬስሊንግ ስፖርት አስተ ማሪ በተማሪው ጥያቄ የተማሪውን ፀ ጉር በመቁረጡ ከሥራ ተባረረ የሚል ዜና ሰምቼ ነው፡፡ ሃምሳ አለቃ አሜሪ ካ ቢኖሩ ኖሮ ስንት ጊዜ ይባረሩ ነበር?

ላይ ነኝ ኩት ዘፈን የለም፡፡ ለዘመኑ ዘፈኖችማ የሞትኩ ብቻ ሳልሆን፤ አጽምም ነኝ፡፡ እንደምንም ሞራሌን አነሳስቼ ቴዲ አፍሮን ልወ ድ ሞክሬ ነበር ግን ከንቱ ድካም ሆነብኝ፡፡ ማን እንደ ኤፍሬም! በእኔ ወጣትነት ዘመን የታተሙ መጽሐፎችን ሁሉ አንብቤአ ለሁ ብዬ ብናገር ብዙም አላጋንንም፡፡ ከሲሳይ ንጉሱ መጽሐፎ ች በኋላ ግን የመጽሐፍ ዓለሜ መዞሩን አቁሟል፡፡ ኮኮብ መጽ ሐፎቼ ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› እና ‹‹ከሰመመን›› ሊሆኑ ይችላ ሉ፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎ የትርጉም መጽሐፎችን አንብቤአ ለሁ ግን ወደድኳቸው ማለት አይደለም፤ ማን እንደ ሰመመን! በሕይወታችን ብዙ ዓለሞች አሉን፡፡ ዓለሞች አንድ አንድ እያ ሉ ማቆም ሲጀምሩ እርጅና ጀመረ ይባላል፡፡ ሁሉም ሲያቆሙ ግን ሞት ይባላል መሰለኝ፡፡ ሁለቱም ጽሁፎች የተወሰዱት ከናኦድ ጡመራ ናኦድ ላይቭ ብሎግ ስፖት ዶት ኮም ሲሆን ለአምዱ እንዲስማማ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

ሐበሻዊ ቃና በ habeshawi kana ብላችሁ ፈልጉን “ላይክ” () የሚለውን ምልክት ተጫኑ

ወቅታዊ ዘገባዎች፣ “ሊንኮች”ን እና ፎቶዎች ያገኛሉ


ሐበሻዊ ቃና

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ከአዲግራት እስከ ... ከገጽ 14 የዞረ “38th Parallel” የዛላንበሳ ዋናው አስፋልቱ ሳያልቅ ኢት ዮጵያ ታልቃለች፡፡ ሁለት ወታደሮች በ መሀላቸው ቀጭን ሽቦ ዘርግተው በሽቦ ው ዳርና ዳር ቁጭ ብለው የኢትዮጵያ ን ሰሜናዊ ድንበር መጨረሻ ያውጃሉ፡፡ ቀጭኗን ሽቦ የኢትዮጵያ 38th Parallel ብለን ልንጠራት እንችላለን፡፡ አንድ ሕ ዝቦች የነበሩትን ሰሜንና የደቡብ ኮሪያ ን ይህች ቀጭን መስመር ለያይታቸዋለ ች፡፡ አንድ ሕዝቦች የነበሩትን ኤርትራን ና ኢትዮጵያን ይህች ቀጭን ሽቦ ሁለት እንደሆኑ ታውጃለች፡፡ ማዶ ለማዶ የሚተያዩት የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ሕዝቦቻቸው መስ መሯን እንዳያልፉ ይከላከላሉ፡፡ ርቀታ ቸው በሜትሮች የሚለካ ነው፡፡ ዘወትር ምሽት የኤርትራ ወታደሮች በክራር ሲያ ዜሙ ይሰማል፡፡ ክራሩ ብቻ አይደለም የሚሰማው፡፡ ምሽት አልፎ አልፎ የተ ኩስ ለውውጥም ይካሄዳል፡፡ ለክፉ የማ ያደርስ የተኩስ ልውውጥ፣ ሚዲያዎች የማይዘግቡት የተኩስ ልውውጥ፡፡ ወዳ ጃዊ የተኩስ ልውውጥ፡፡

ነጯ መኪና ኤርትራዊያን ቀጭኗን የሽቦ መስመር ለማለፍ ጨለማን ተገን አድርገው አብ ዝተው ይተጋሉ፡፡ ብዙዎቹ ይሳካላቸዋ ል፡፡ ጥቂቶቹ ይረሸናሉ፡፡ እድለኛ ከሆኑ ደግሞ ወደማጎሪያ ይላካሉ፡፡ የኤርትራ ውያኑን ጥረት ለመደገፍ የኢትዮጵያ ወ ታደሮች የሽፋን ተኩስ ያደርጋሉ፡፡ ጉቦ የተቀበሉ የኤርትራ ወታደሮችም የውሸ ት ተኩስ ይከፍታሉ ይባላል፤ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ፡፡ ልክ ጎህ ሲቀድ በኢት ዮጵያ መሬት ጥቂት ኤርትራውያን “በቅ ለው” ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ቀጭኗን መስመ ር ለማለፍ የተሳካላቸው ብቻ ናቸው፡፡ በአጭር የሚቀሩም ሬሳቸው ይለቀማ ል፤ ጠዋት ጠዋት፡፡ በሕይወት የኢትዮ ጵያን አፈር የረገጡትን የኤርትራ ልጆች የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰብስበው ያስቀ

ምጧቿል፤ “ሐርድ ቶፕ” የምትባለው ነ ጯ መኪና እስክትመጣ፡፡

ዛላንበሳ በመልሶ ግንባታ ላይ ነጯን መኪና በዛላንበሳ የማያውቃት የ ለም፡፡ የእጅ ሰዓት ለማያስሩ ነዋሪዎች የ ሰአት መቁጠርያ ሆና ታገለግላለች፡፡ የተ ባበሩት መንግስታት ድርጅትን ታርጋ የ ለጠፈችው ይህች ነጭ መኪና ዘወትር ማለዳ ወደ ቀጭኗ ሽቦ ተጠግታ ወደ ኢ ትዮጵያ የተሻገሩ ኤርትራዊያንን ታጭቃ ለች፡፡ እየከነፈች መጥታ እየከነፈች ትሄ ዳለች፤ ወደ ሽመልባ እና ሌሎች የስደተ ኛ ካምፖች፡፡ የዛላንበሳ ነዋሪዎች እንደነ ገሩኝ ነጯ መኪና እረፍት የላትም፡፡ በየ እለቱ ያለማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ የሚያ ቋርጡ የስደተኞችን ብዛት ለሚያይ ኤር ትራ ከኢሳያስ በስተቀር ሰው የቀረ አይ መስለውም፡፡

ድንበር አልባው ቡና የዛላንበሳ አባወራዎች የኤርትራ ሴቶች ለሚስትነት መልካም ናቸው በሚል ከ ብዙዎች ጋር ተጋብተው ወልደው ከብ ደዋል፡፡ ማዶ የሚገኙት የአምበሰተገለባ የኤርትራ ቀበሌ ነዋሪዎች ደግሞ የዛላን በሳ ሴቶች ብርቱ ናቸው በሚል ከኢት ዮጵያውያን ጋር ተጋብተው ወልደው ከ ብደዋል፡፡ ድንገት ጦርነት የሁለት አገር ሰዎች አደረጋቸው፡፡ አሁን ለቡና መጠ ራራት አይችሉም፡፡ ነገር ግን ቡና አፍል ተው ከወታደሮች ጋር ጥሩ ተግባቦት ባ ላቸው እረኞች በኩል ኤርትራ ላሉ ዘመ ዶቻቸው ይልካሉ፡፡ ለአማቾቻቸው ጥ ህሎና ቡና ያሾልካሉ፡፡ ወታደሮቹን ተለ ማምጠው ገብተው ቶናና በረካ ጠጥተ ው የሚወጡም አሉ፡፡ ቡናና ጌሾ በእረ ኞች በኩል ለኤርትራ ዘመዶች መላክ የ ተለመደ ነው ብለውኛል፡፡ ኩርፊያ፣ ጦርነት፣ ድንበር፣ ቂም የማ ይገባቸው ከብቶች ድንበር እየተሻገሩ ያ ስቸግራሉ፡፡ ወታደሮች ሰብሰብ አድርገ ው ድንበር አካባቢ ያቆዩዋቸውና ባለቤ ቶቻቸው ሲመጡ ይመልሱላቸዋል፡፡ ይ ህ ሰላማዊ ድንበር ዘለል የከብቶች ልው ውጥ ግን ሁልጊዜ ሰላማዊ እንዳልሆነ ተ መልክቻለሁ፡፡ ዛላንበሳ ከመግባቴ ከቀና

ት በፊት የሆነውን ላውጋችሁ፡፡ ጥቂት ኢትዮጵያዊ ከብቶች የኤርትራን ድንበር ተሻግረው ይሄዳሉ፡፡ ሆኖም ኤ ርትራዊያኑ ከብቶቹን ለመመለስ አልፈ ቀዱም፡፡ ዐይናቸውን በጨው አጥበው አላየንም አሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቁጥ ራቸው ላቅ ያሉ ኤርትራዊ ከብቶች ወደ ኢትዮጵያ ሲሻገሩ ኢትዮጵያውያን ይዘ ው “የእኛን ካልመለሳችሁ የእናንተን አን መልስም” የሚል አቋም ይይዛሉ፡፡ በዚ ህ አቋማቸውም ለመጽናት ይወስናሉ፡፡ ሁኔታው ያሳሰባቸው የአጎራባቿ አምበ ሰተገለባ ቀበሌ ነዋሪዎች ሽማግሌዎችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ድርድር ይጀም ራሉ፡፡ ድርድሩ ፍሬ አፍርቶ ኤርትራው ያኑ አላየንም ያሏቸውን ከብቶች በሙሉ ለመመለስ ፍቃደኛ ሆነው የእነርሱን ከ ብቶች እየነዱ መሄድ ችለዋል፡፡ አልጀር ስ የማያስኬድ ድርድር፤ አብዱልአዚዝ ቡቶፍሊካ የማያውቁት ስምምነት፤ የመ ለስና ኢሳይያስ ፊርማ የማያስፈልገው ስ ምምነት፡፡ ባሳለፍነው መስቀል ደግሞ እንዲህ ሆ ነ፡፡ በዚህች ደቡባዊ የኤርትራ ቀበሌ አ ቅራቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኢ ትዮጵያዊት ልጃቸው እና ጥቂት ቤተሰ ቦቻቸው ለመስቀል በዓል ሊጠይቋቸ ው ከአዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡ አገር አ ማን ባሉበት ድንገት የኤርትራ ወታደሮ ች አምስት የቤተሰቦቻቸውን አባላት አ ፍነው ይወስዳሉ፡፡ እናት ክፉኛ በሐዝ ን ተዋጡ፡፡ ምንም ማድረግ አልተቻለ ም፡፡ በስንተኛው ቀን በኤርትራ ቲቪ ታ ዩ ተባለ፡፡ ከኢትዮጵያ ጠፍተን መጥተን ነው…እያስባሉ ያናዝዟቸዋል፡፡ ከዚህ ክ ስተት በኋላ ድንበሩ አካባቢ በፀጉረ ል ውጦች ላይ ጠበቅ ያለ ክትትል ይካሄድ ጀምሯል፡፡ ኢትዮ-ኤርትራዊው የትራክተሩ ሾፌር ይህ ታሪክ የተፈጸመው በ2000 ዓ.ም ነ ው፡፡ ጥቂት የውጭ ሚዲያዎችም ዘግበ ውታል፡፡ የኤርትራ መንግሥት አንድ ት ራክተር ከነሾፌሩ ድንበር አካባቢ ያለው ን ጋሻ መሬት እንዲያርስ ይልከዋል፡፡ ሾ ፌሩ ባጋጣሚ ወደ ኤርትራ ከመሰደዱ በፊት የአዲግራት ልጅ ነበር፤ ካቻማሊ፡

23

፡ በአዲግራት ቤተሰብ አፍርቷል፡፡ ድን በር አካባቢ መሬቱን እያረሰ ሳለ ኢትዮ ጵያዊ ቤተሰቦቹ ናፈቁት፡፡ ትራክተሯን ቀስ እያለ ወደ ፊት ነዳት፤ ድንበር የሚያ ርስ መስሎ ማርሽ ቀየረ፡፡ እያከነፈ ወደ ኢትዮጵያ መሬት ገባ፡፡ የኤርትራ ወታደ ሮች በተኩስ እሩምታ አጣደፉት፡፡ የት ራክተሩን ግዙፍ ጎማ እንጂ ሾፌሩን አላ ገኙትም፡፡ ሾፌሩ ኢትዮጵያ ገባ፡፡ የኢት ዮጵያ ወታደሮች ደግሞ የሽፋን ተኩስ ሰ ጡት፡፡ ሾፌሩ ኢትዮጵያ ቢገባም የተኩ ስ ልውውጡ ግን ሊበርድ አልቻለም፡፡ የትራክተሩ ድራማ 37 የኤርትራ ወታደ ሮችና ሁለት የኢትዮጵያ ወታደሮችን ሕ ይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆነ፡፡

የአሥመራ ናፍቆት የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም፤ ከአሥ መራ በቀር፡፡ ይህችን ሕልም የመሰለች ከተማ ሳስብ ክፉኛ የእኔነት ስሜት ይወ ረኛል፡፡ ሁሌም እንደማውቃት እንጂ እ ንደማላውቃት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ የእኔ እንጂ “የእነርሱ” ሆና አይሰማኝም፡ ፡ ደግሞም የእኔ ነበረች፣ የእኔም ትሆን ይሆናል፤ ማን ያውቃል? ሃምሳ ዓመት… መቶ ዓመት…150 ዓመታት? የ“ኦሮማዩ” ጸጋዬ “የባህር እንቁ” የሚ ላትን ከባህር ጠለል በላይ በ7500 ጫ ማ ከፍታ የምትገኘዋን አሥመራን አው ቃታለሁ፤ የዘንባባ ጫካዎቿን፣ እንደ “ገ ዛ ባንዳ”፣ “ሰንበል ጉዳይፍ”፣ “ገጀራት ማይ ወላጮ”፣ “እዳጋ ሐሙስ”፣ “ማይ ተመናይ”…ያሉ ውብ ሰፈሮቿን በበዓሉ ግርማ ጽሑፍ አሳምሬ አውቃቸዋለሁ፡፡ ጸጋዬ አሥመራ ውስጥ ያልወሰደኝ ቡና ቤት አለ እንዴ? አሥመራን አታውቃት ም አትበሉኝ፡፡ ለካንስ ወደ ድንበር መሄድ ናፍቆት ያ ፋፍማል እንጂ አያበርድም፡፡ ከድንበር አንጋጥቼ ያየሁሽ ናይ ሰሜናዊ ፅብቅቲ አሥመሪና! ኻብ አንቲ ንግሥቲ ይበልጽ መልክኪ… ዛላንበሳ ጠረፍ ላይ ሆኜ የበዓሉ ግርማ ፍቅር- ፊያሜታ ስትስቅብኝ ተሰማኝ፡ ፡ “አባቴ ይሙት ደደብ ነህ!” እያለች፡፡

ልፎ ... ከገጽ 14 የዞረ ም፣ አንስቅ። የመለያያ ግብዣችን ሳቁ ቀ ጭን ነበር። የበጋ ወፍራም ደመና ይሄ ባ ለነጎድጓዱ በመስኮት ዋኝቶ የገባብን ይ መስላል። በምንቀባበለው ንግግር መሃል እንደጨለማ የጠቆረ ባዶነት አለ። እና ቴ ከተቀመጠችበት እጆቿን ሰዳ ሁሉመ ናዬን ትዳብስና ሰዎች ወሬ የያዙ ሲመ ስላት፣ አኔ እንደማያዩአት ሁሉ፣ እጆቿ ን ቡና ባሞቃቸው ከንፈሮቿ ትስማለች። “ተውኝ እናንተ ደግሞ” ትላለች በማ ፈር። ከጥፍራም ጣቶቿ ሀዘን፣ እና ሁሉን በ መረዳት የተጎነጎኑ ሳቆች ከጥርሶቿ ወደ ወለሉ ይወድቃሉ። ሆዴ እንደ ቅቤ ይ ቀልጣል። መፈንዳትም መሸንቆርም እ ፈልጋለሁ። አይኖቼ ውስጥ እንባ ይተኛ ል። ይቆጠቁጠኛል። ወደ ውጭ እወጣ ና መነጽሬን አንስቼ በአይበሉባዬ እጠር ጋለሁ። መቅደስ ተከትላኝ ትወጣለች። ከጀርባዬ ታቅፈኛለች። የምለያትን አዲ ስአባ ያች ያላትን ያጠባችኝ፣ የቆሰሉ ጡ ቶቿን የመገመግሁ፣ በሰርኔ አየርዋን የሳ ብኩ፣ ጎመንዋን ያኘኩ….ጭር ባለ ማታ ይሄን ሁሉ አያለሁ….ስለመከዳትም አፍ ራለሁ። “ከዚህ ሀገር የማይሻል የለም” ይላሉ ወ ይዘሮ አስካለ የወርቅ ሃብላቸውን እየዳ በሱ። “የት አዩ አንቱ ደሞ” “ምን መሰላችሁ…” ቤተሰቦቼን እና እንግዶች የሚሉት ባይ ሰማኝም ጉምጉምታ አዳምጣለሁ…. የመቅደስ ሽቶ በትከሻዬ በኩል ይወጣ ና የሻምፑ…የአበባና የዲኦዶራነት ሰን

ሐበሻዊ

ደል ያለው….ገና አገር ሳለቅ…ዘለስ ካለ ው ጡቶቿ ስር የሚሰነፍጠው ላቧ ናፈ ቀኝ…እዚህ ቤቴ ፊት ለፊትም በመስመ ር የበቀሉ ጥቂት ዛፎች ነበሩ…ሚስጢራ ዊ ሆያ ሆዬ አላቸው አብረውኝ ነሐሴን ሲጨፍሩ….ምን ያህል ደስታ ነበር? እጄ መሃል ያረፈችው አስር ሳንቲም ስንዝር በደስታ ስታሳድገኝ….ምን ያህል ደስታ ነ በረው የእንቁጣጣሽን የአበባዬ ሆይ ቀ ጭን ድምጽ ተከትለን እነ ዝናሽን እያባረ ርን አንግጫቸውን ቀምተን….እወዲያ አ ስፓልት አሻግረን በየቤቱ ገብተው ሙ ጥኝ ሲሉ…እንዴት ሳቅን? ከድህነቴ ያገ ኘሁት ነጻነት እነዚያ የመስከረም እርጥ ብ ቄጤማዎች…… መቅደስ ጉንጮቼ ላይ ሳመችኝ። ብዙ ዎች እንደ ትልቅ ዕጣ የሚቆጥሩትን ወደ ባዕድ አገር የመሄድ ነገር፣ ችግር መሃል ቆሜ ለምን እጠራጠረዋለሁ? አልፈርድ ባቸውም። እንዲፈርዱብኝም አልሻም። ወፍራምነቷን አቀፍኩት። የሆነች ነገር ልናገር እፈልጋለሁ። የሆነ ች ትንሽ ነገር። ግን ዝም ብዬ በኃይል አ ቀፍኳት። ተራኪው ከመቅደስ ጋር ተጋብቶ ወደ ሆላንድ ይጓዛል። በእዚያ ያጋጠመው የሆነውን፣ ኖሮ በአውሮፓ ምን እንደሚመስል የተረከበትን በቀጣዩ እትም ይጠብቁ። * ልፎ ማለት ወንዶች ሲገረዙ ከብል ታቸው ተቆርጦ የሚቀበረው (የሚጣለ ው) ቁራጭ ነው። ይህ አጭር ልቦለድ የተወሰደው አዳም ረታ በቅርቡ ካሳተመው አምሰተኛ መጽሀፉ “ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ” ነው

ቃና

በየ 15 ቀኑ

ምጥን ማስታወቂያዎች ሱፐር የመኪና እጥበት ሙሉ የመኪና እጥበት n መኪኖችን ሰርቪስ ማድረግ n

ስልክ

0702 329127 አድራሻ፦ ካባላጋላ፣ ካፒታል ፐብ ጀርባ

ናፍቆት ኢንተርኔት ካፌ

Technical Management Solutions Ltd

- ፈጣን ኮኔክሽን - ፎቶ ኮፒ - የሕትመት አገልግሎት - ስካኒንግ

q General plumbing

ከምርጥ የኢትዮጵያ ቡና እና ማኪያቶ ጋር አድራሻ፦ ካሳንጋ/ ጋባ መንገድ ከጆን ሱፐር ማርኬት አጠገብ

እንኳን ደስ ያላችሁ

q Carpentry q Electrical work q Painting Innovation and Excellence

CALL NOW

+256 777 202833, +256 701 202833

የልደት፣ የሰርግ፣ የመልካም ምኞት መልዕክቶችን በምጥን ማስታወቂያ ማውጣት ከፈለጉ በ+256-778-693669

ይደውሉልን

ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁት ሰብለ አሰፋ እና ደረጀ ብዙአየሁ መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ። ቹፒ እና ቴስ


ሐበሻዊ ቃና

24

ከሰኔ 18- ሐምሌ 1 ቀን 2003 (June 25-July 8, 2011)

ፎቶ- አዲስ ፎርቹን (www.addisfortune.com)

አስቴር አወቀ


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.