ድልድይ መጋዚን (Bridge Magazine)

Page 1

BRIDGE MAGAZINE VOLUME 1: ISSUE 2/ DECEMBER 21018


B.F. AUTO SALES

3500 Danforth Ave. Toronto 416-304-1261 / 416-817-6855

We Buy, Sell & Trade Cars Financing available

Volume 1: Issue 2 ድልድይ መጽሔት / December SEPTEMBER 2018 2018

2

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER SEPTEMBER2018 2018Volume 1: Issue 2

33

https:www.tzta.ca


የድልድይ መጽሔት ማውጫ CONTENTS

COVER

Prime Minister Dr Abiy Ahmed has been named among the 100 most influential Africans of 2018 by the New African magazine. The magazine has featured Dr Abiy on its cover page. The Ethiopian Prime Minister has made stunning political reforms in the country since he came to power last April. ...PAGE 20

“ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም” ...ገጽ 12

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

4

https:www.tzta.ca


Thinking of Real Estate? Helen Zeray

Sales Representative

Direct: 647-712-0461

Aziz Mohamed, BA, CCIM, MRICS Broker of Record

Greater Toronto Area: 416.243.2400 Kitchener-Waterloo Region: 519.744.2300

519-744-2300

Direct: 416-930-3512

Call for Free Consultation Canadian Owned & Operated: NO Middleman, NO Franchise Fees, NO Hidden Fees

Sell Direct, Save Direct: MLS Listing $999

Buy Direct, Save Direct: Buyers Get $1000 Cash Back

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

5

https:www.tzta.ca


MARTA FASHION & GIFTS SHOP INC. Fashionable Women Clothing Accessories& Home Decore 35 Church St. Toronto 647-869-2382

ማርታ ፋሽን እና የልብስ መሸጫ መደብር (የሴቶች ልብስ አልባሳት ማሟያዎች እና የቤት ዲኮር) ለማንኛውም በስልክ ቁጥር 647- 869-2382 ማርታ ብላችሁ ደውሉልን በተጨማሪም በአድራሻችን ማለት 35 Church Street East Side, Toronto መጥታችሁ ጎብኙን።

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

6

https:www.tzta.ca


አቶ ዓለማየሁ አስፋው ከትዝታ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ አቶ ዓለማየሁ አስፋው ከትዝታ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ አቶ ዓለማየሁ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ማሕበር በቶሮንቶና አካባቢው ፕሬዚዳንት ናቸው።ለዚህ ቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ በመሆንዎ አመሰግናለሁ። በቀጥታ ወደ ጥያቄ አመራለሁ። አቶ አለማየሁ የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶ ፕሬዘዳንት

1ኛ/ ትዝታ

ስለራስዎ ባጭሩ ቢገልጹልን። እንዴት የኢትዮጵያ ማሕበር ፕሬዚዳንት ሆኑ?

አቶ ዓለማየሁ

በመጀመሪያ የትዝታ ጋዜጣ አዘጋጆች ለሕብረተሰቡ ለምታደርጉት አገልግሎትና እዚህም ለመናገር ለተሰጠኝ ዕድል ላመሰግን እወዳለሁ። ዓለማየሁ አስፋው እባላለሁ። የተወለድኩት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ። አስተዳደጌ ግን ቤተሰቦቼ በየክፍለህገሩ በሥራ ምክንያት ይዘዋወሩ ስለነበረ እኔም አብሬ ተዟዙሬያለሁ። የትምህርት ደረጃዬ ቢኤስ ሲ መካኒካል መሓንዲስ ቀጥሎም ኤምኤስ ሲ ኢሮኖቲክስ። አብዛኛውን እድሜዬን የሠራሁት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን

ከዚያም በኋላ ወደካናዳ መጥቼ ባሁኑ ጊዜ እዚሁ ቶሮንቶ ከተማ እኖራለሁ። ባለትዳርና ሦስት ልጆች አሉኝ፣ ሁለት ሴቶች አንድ ወንድ። እዚህ ከመጣሁበትም ጊዜ አንስቶ የማሕበሩ አባል ሆኜ ቆይቻለሁ። ባለፈው ዓመት በተደረገው የማሕበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የቦርዱ አባል ሆኜ ተመረጥኩ።

3ኛ/ ትዝታ

2ኛ/ ትዝታ

ፕሬዚዳንት ከሆኑ ጀምሮ ያጋጠምዎትን ችግር ቢገልጹልን። የሚያደንቁትም ነገር ካለ?

አቶ ዓለማየሁ

ባሁኑ ጊዜ ማሕበሩ ብዙ ችግሮች አሉት። በመጀመሪያ ምንም ቋሚ ገቢ የለውም። ምንም ሠራተኛም የለውም። ይህም ሆኖ ግን የሕዝባዊ አገልግሎት ሊሰጥ የተዘጋጀ ሆኖ ይታያል። ትልቁ ችግር ይህ ሆኖ ሳለ የሕብረተስቡ ድጋፍ ያለመስጠት ደግሞ

Cell:

ትልቅ ጫና መፍጠሩ አልቀረም። ቦርዱ በተሰጠው ኃላፊነት የተቻለውን ጥረት እያደረገ ይገኛል። ለዚሁም ለማሕበሩ በጎ ፈቃደኞችን በማሰባሰብና ሁኔታዎችን በማመቻቸት በማሕበሩ ውስጥ እንቅስቃሴ ለመፍጠር ያለማቋረጥ ጥረት እየተደረገ ነው።

ሀ) እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ማሕበር የተቋቋመው በካናዳ መንግሥት እርዳታ መሆኑ ይታወቃል። አንዳንድ ሰዎች አስተያየታቸውን ሲሰጡ የኢትዮጵያ ማሕበር ለረጅም ጊዜ አገልግሎቱን ይሰጥ የነበረው ተዳክሟል ወይም የለም ብለው የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ለዚህ ምን ይላሉ? ለ) የኢትዮጵያ ማሕበር መቋቋም በቶሮንቶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ጥቅምና አገልግሎት ቢገልጹልን። ገጽ 8 ይመልከቱ

647-988-9173 . Phone 416-298-8200

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

7

https:www.tzta.ca


ከገጽ 7 የዞረ

አቶ ዓለማየሁ

እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ማሕበር ወትሮ እንደነበረው አለመሆኑ ብዙዎች ያውቁ ይመስለኛል። ቀደም ብሎ በነበረው ጊዜ ማሕበሩ ከመንግሥት በቂ የሆነ ባጀትና እርዳታ ያገኝ ስለነበረ ለሕብረተሰቡ በቂ የሆነ አገልግሎት ይሰጥ ነበር። አገልግሎቱን በስደተኛ አገልግሎት፣ በሕዝብ ግንኙነት፣ በሥራ ፍለጋ፣ በቋንቋ ትምህርት፣ በሕጻናት አገልግሎት፣ በአዛውንት ክበብ፣ በሴቶች ማሕበርና በተለያዩ መስኮች አገልግሎቱን ለመስጠት ተሰልፎ በአንድ ዲሬክተር የሚመራ በቂ በሆነ የሠራተኛ ቁጥር እንደነበረው ይታወቃል። ዛሬ ያ ሁኔታ በአንድ ወቅት ላይ መንግሥት ባጀቱን በማቋረጡ ማሕበሩ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ሁሉ ቆሟል። የነበሩት ፕሮግራሞች ሁሉ ተሰርዘዋል። ሆኖም ምስጋና በሚገባቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ትግል ማሕበሩ ብቃት ያለው አገልግሎት ባይሰጥም ኅልውናውን እንዳያጣ ሆኖ ሊቆይ ችሏል። ዛሬም በእርግጠኝነት አለ እንቅስቃሴውንም ይቀጥላል። የማሕበሩ መኖር ለጠቅላላው የኢትዮጵያና ትውልደ ኢትዮጵያ አለኝታ እንደሆነ ሁሉም ሰው ሊረዳው ይገባል። ማሕበሩ በሚያወጣው ፕሮግራሞች ሁሉ በመሳተፍ ሁላችንም በአንድነታችን ጸንተን ለማሕበሩ ድጋፍ መስጠት የገባል። ይሕ ሲሆን እዚህ በምንኖርበት አገር መብታችንን ለማስከበር፣ ተደማጭነታችንን ለማጎልበት፣ ባኅላችንን እንዳይጠፋ ለመጠበቅና ለማሳደግ ብሎም ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የሚተላለፍ እንዲሆን ለማድረግና መብታችንን ለማስከበር ከፍተኛ የሆነ መከታ እንደሚሆን አያጠራጥርም። ተዟዙሬ እንዳየሁትም ይህን ጉዳይ ብዙ ሰዎች የተረዱት ነገር መሆኑን ተረድቻለሁ። ሌሎች ማሕበራት እያደጉ ሲሄዱና ተደማጭነታቸው እየጎላ ሲሄድ የእኛ አንድ አለኝታ ሊሆን የሚገባው ማሕበር ግን የሰዎች ሕብረት በመጥፋቱ ምክንያት ብቻ ወደኋላ እንዲቀር ሆኗል። ዛሬም ሳናመነታ ከተባበርንና ተግተን ከሠራን ግን ሁኔታው በጣም ሊሻሻል እንደሚችል አያጠራጥርም።

4ኛ/ ትዝታ

ሀ) በየዓመቱ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ቀን ይከበራል። ያለፈው ሰፕቴምበር 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቀን እንዴት አለፈ? እስኪ ጠንካራና ደካማ ጎኑን ይግለጹልኝ። ለመጪው ዓመትስ ምን ታስቧል? ለ) ይህ በዓመት አንድ ቀን

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

8

የሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ባኅልና ወግ በካናዳ መንግሥትና ሕብረተሰብ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምን ይሆናል ብለው ይገምታሉ?

አቶ ዓለማየሁ

የዚህ ዓመቱ 2018 በዓል በጥሩ ሁኔታ አልፏል። ብዙዎች እንደተደሰቱ ገልጸውልናል። እኛም በአጠቃላይ ስናየው ተደስተንበታል። እርግጥ እንዲያው ያለምንም ችግር ተለሳልሶ አልፏል ማለት ግን አይቻልም። በአብዛኛው አሁንም ሕብረተሰቡ መተባበር ይጠበቅበታል። ማሕበሩ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት ሥራዎች በጊዜው ካልተጠናቀቁ ችግር መከተሉ የማይቀር ነው።ለምሳሌ ድንኳን የሚከራዩ ድርጅቶች በተወሰነው ጊዜ ገደብ ሳይከራዩ ሲቀሩና በስተመጨረሻው ሽሚያ ላይ ሲገቡ ብዙ ውጣ ውረድና ውዝግብ ክርክር የሚያስነሱ ሁኔታዎች መፈጠራቸው አልቀረም። ለወደፊቱ ይህ ይታረማል ብዬ አምናለሁ። እዚህ ላይ በዓሉን ለማዘጋጀትና በጥሩ ሁኔታ እንዲያልፍ ለደከሙ የቦርድ አባላትና የማሕበሩ ሌሎች አባላት፣ በጣም ለተባበሩንና እርዳታ ለሰጡን የንግድና ሌሎች ድርጅቶችና ግለሰቦች፣ እንዲሁም ጥሪያችንን አክብረው የበዓሉ ተካፋዮች ለመሆን በበዓሉ ቀን እቦታው ለተገኙ የሕብረተሰቡ አካላት ሁሉ በጠቅላላ ከፍተኛ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን። ለወደፊቱም እርዳታቸው እንደማይለየን ተስፋ አለን። ይህ የኢትዮጵያ ቀን የተባለው ባኅላችንን ለቀረው የካናዳ ሕዝብ ሊያስተዋውቅ ስለሚችልና በጉልህ ስለሚያሳይ ተሳታፊ ለነበሩ ሁሉ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ብዬ አምናለሁ።

5ኛ/ ትዝታ

ባለፈው ጊዜ ኢትዮጵያውያንን በማሕበሩ ሥር ለማሰባሰብ ብዙ ውስብስቦች ማለት የፖለቲካ፣ የሃይማኖት የመሳሰሉት ችግሮች እንደነበሩ ለማንም ግልጽ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ረገብ ያለ ይመስላል። ታዲያ የኢትዮጵያ ማሕበር በተለይ ማሕበረተኛውን በአዲስ መንገድ ለማሰባሰብ ምን አቅዷል?

አቶ ዓለማየሁ

የኢትዮጵያ ማሕበር በቶሮንቶና አካባቢው ከመጀመሪያውም ሲቋቋም ከፖለቲካ ነፃ በሆነ መልክ በዘር በሃይማኖት ሳይለይ የተመሠረተ ድርጅት ነው። ላለፉት ብዙ ዓመታትም ይህ ዓላማው አልተለወጠም። ፍላጎት ያለው ገጽ 11 ይመልከቱ

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

9

https:www.tzta.ca


አንዳንድ ጊዜ ሀገር ‘አርብ’ ላይ ትሆናለች!! (ዳንኤል ክብረት)

December 8, 2018 * ሀገርም እንዲህ ትሆናለች፡፡ አርብ ላይ ስትሆን ፀሐይ የጨለመባት ጨረቃም ደም የለበሰችባት ትመስላለች፡፡ መድኃኒት አልባ ተስፋ አልባ ትመስላለች፡፡ ክፉዎች ኃይል አግኝተው ቅኖች የተሸነፉ ይመስላሉ፡ ፡ ወንጀለኞች ደስታ ተጎናጽፈው ንጹሐን መስቀል ሥር ያለቅሳሉ!

አዲሱ አድራሻችን፡ 2704 Danforth Ave. Toronto New Location under the new management

አርብ አዳም እየዳነ ነው፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ እየተገረፈና እየተሰቀለ ነው፤ ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ለብሳለች፤ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ ሐዋርያት ሸሽተዋል፡፡ መጻጉእ በሐሰት መስክሯል፡፡ ጲላጦስ የእውነት ፍርድ ለመፍረድ ተቸግሯል፡፡ በጥብርያዶስ ባሕር ሲበላ ‹ካልነገሥክ› ያለው ሕዝብ ተገልብጦ ‹ካልተሰቀለ› እያለ ነው፡ ፡ ያቺ ቀን የክርስትና የመጨረሻዋ ቀን ትመስል ነበር፡፡ የክርስቶስ ሆኖ የተገኘ ሁሉ ይቀጠቀጣል፡፡ ለዚህም ነበር ወጣቱን ማርቆስን ያባረሩት፡ ፡ ሐናና ቀያፋ ጉልበት አግኝተዋል፡፡ የጭካኔያቸውን ልክ ሁሉ እያወረዱት ነው፡፡ ዮሐንስ ያለቅሳል፣ እመቤታችን በኀዘን ቆማለች፡፡ ሁሉም ነገር ያበቃና የተቆረጠ መስሏል፡፡ በዚህ መካከል ግን የሚነሡ ሙታን ነበሩ፣ የሚቀደድ የጥል መጋረጃ ነበር፣ ፈያታዊ ዘየማን ገነት እየገባ ነበር፤ ዮሐንስ ለእመቤታችን ልጅ ሆኖ እየተሰጠ ነበር፤ የጲላጦስ

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

10

ሚስት ስለ እውነት እየመሰከረች ነበር፡፡ ሮማዊው መቶ አለቃ ስለ ክርስቶስ እውነቱን እየተናገረ ነበር፡ ፡ ግን እነዚህን ጣፋጭ ድምጾች ሌሎች የክፋትና የጨለማ ድምጾች ውጠዋቸው ስለነበር በቂ ሰሚ አላገኙም፡፡ በቂ ሰሚ ያገኙት በኋላ ነው። ሀገርም እንዲህ ትሆናለች፡፡ አርብ ላይ ስትሆን ፀሐይ የጨለመባት ጨረቃም ደም የለበሰችባት ትመስላለች፡፡ መድኃኒት አልባ ተስፋ አልባ ትመስላለች፡፡ ክፉዎች ኃይል አግኝተው ቅኖች የተሸነፉ ይመስላሉ፡፡ ወንጀለኞች ደስታ ተጎናጽፈው ንጹሐን መስቀል ሥር ያለቅሳሉ፡፡ ትናንሽ ጭላንጭሎችን የሚያያቸው፣ ጥቃቅን ብርቱ ድምጾችን የሚሰማቸው ያጣሉ፡ ፡ ሁሉም የዋጠውን ጨለማ እንጂ የተሰቀለውን ብርሃን አያይም፡፡ ግን አርብ ያልፋል፤ ቅዳሜም ይነጋል፡፡ እርሱም በዝምታ ይመሻል፡፡ እሑድም ይደርሳል፡፡ ትንሣኤም ይመጣል፡ ፡ አርብም በእሑድ ትተካለች፡፡ ከአርብ ወደ እሑድ ለመሻገር ግን እንደ እመቤታችንና እንደ ዮሐንስ ያሉ ጽኑዓንን ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ አርብ ላይ ናት፡፡ ግን በቅዳሜ በኩል ተሻግራው እሑድ እንደምትደረስ እናምናለን። ደግ ደጉን እናስብ፣ በጎ በጎውን እንስራ፣ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

https:www.tzta.ca


ከገጽ 8 የዞረ ማንኛውም ሰው ሁሉ መጥቶ ተመዝግቦ የማሕበሩ አባል መሆን ይችላል። አሁን ያለው ቦርድ ባሁኑ ጊዜ ሁሉንም አቀፍ በሆነ መልኩ ጥሪ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ብቻ ለዚህም ቢሆን አብዛኛው ነዋሪ በአንድነቱ አምኖ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። ባሁኑ ጊዜ ደግሞ በአገራችን የተከሠተው ለውጥ አመቺ ሁኔታ በመፍጠሩ ትክክል ነው እዚህም ላለነው ያሁኔታ በመንጸባረቁ ከወትሮው ይልቅ በመካከላችን የነበረውን ያለመግባባት በመጠኑም ቢሆን ያረገበው ይመስለኛል።

6ኛ/ ትዝታ

ራስን ማወቅ ባህልን ማክበር ከሰው ልጅ መብቶች አንዱ ነው። ይህን በማስመልከት የኢትዮጵያን ማሕበር የወደፊት ራዕይ ምን ይሆናል ብለው ያስባሉ?

አቶ ዓለማየሁ

በበኩሌ እንደማስበው በመጀመሪያ በአሁኑ ጊዜ ያለነው ሰዎች ስለነገ በማሰብ ለልጆቻችን ሊከተሉት የሚገባውን የሞራል ብቃትና በራስ የመተማመን ተባብሮ በመሥራት ኃላፊነት በመውሰድ በእርግጠኝነት በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩና የሚከበሩ እንዲሆኑ በአንክሮ ማስተማር ይኖርብናል ብዬ አምናለሁ። ታማኝነት ያላቸው ብርቱ ዜጎች ለማትረፍ ካሰብንበትና ከተጋን የምንችል ይመስለኛል።

7ኛ/ ትዝታ

በኢትዮጵያ አሁን ለውጥ እየተካሄደ መሆኑ እሙን ነው። ለማሕበሩ ያለውን እንደምታ ቢገልጹልን፧

አቶ ዓለማየሁ

ምንም እንኳን ዶክተርምስንቃወመው ከነበረው ፓርቲ፣ ከኢሓዴግ፣ የመጣ መሆኑን ብንረዳም ቀደም ብለው የነበሩትን ችግሮች ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ የሕዝቡን ፍላጎት በጣም በሚያረካና ለአገሪቱም ጠቃሚ በሆነ መልክ ለውጥ ለማምጣት በመቻሉ ለእኔ እንደሚመስለኝ ሁላችንም ከፍተኛ ድጋፍ መስጠት ያለብን ይመስለኛል። ይህ በአገር ቤት የሚሆነው ሁኔታ እዚህም ላለነው ስለሚንጸባረቅ ወትሮ የነበረውን የመቃቃር ነገር በጣሙን የሚያረግብ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ሁኔታ ለማሕበሩ ሰዎችን ለማሰባሰብ በጎ ጊዜ የሚፈጥር ይመስለኛል።

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

11

8ኛ/ ትዝታ

በተለይ በአሁኑ ጊዜ ለአዲስ ትውልድ ካናድያን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና እንዲሁም ሴቶች በኢትዮጵያ ማሕበር በይበልጥ እንዲሳተፉ የታሰበ ጉዳይ ካለ ቢገልጹልን።

አቶ ዓለማየሁ

አዎን ካናዳ የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ግራ እንዳይጋቡና ውሎ አድሮም የሞራል ችግር እንዳያመጣ ብርቱ ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ይመስለኛል። በመጀመሪያ ልጆች ያሉን ቤተ ሰቦች ኃላፊነት መውሰድ ግዴታችን ይሆናል። ለዚህም በተጭማሪ ጠንካራ የሆነ መሕበር ያለ እንደ ሆነ የተለያዩ ፕሮግራሞች በመፍጠርና ልጆቻችን በሚፈልጉት ዓይነት ቅልጥፍናና ሥልጣኔ እውቀትን የሚያዳብሩ ማሰልጠኛዎች ሁሉ ማድረግ ይቻላል። ባሁኑ ጊዜ ለዚህ ዓይንቱ ጉዳይ በማሰብ የወጣት ባለሞያዎች ስብስብ በማሕበሩ ሥር ተቋቍሟል። ቀስበቀስ ደግሞ ልጆች ባህላቸውንና ቋንቋቸውን እንዲማሩ ማድረግም የሚያዳግት አይመስለኝም። ለሁሉም ግን የሁላችንን መተባበርና ተግቶ መሥራትም ያስፈልገናል።

9ኛ/ ትዝታ

ከላይ ያልጠቀስኩት ለአንባብያን ማለት የሚፈልጉት ካለ!

አቶ ዓለማየሁ

ከላይ ከተባለው ሌላ ላስገነዝብ የምፈልገው ነገር የጥንት አባቶቻችን ጥቃት አይወዱም። በምንም ሁኔታ መደፈር አይቀበሉም። አባቶቻችን የራሳቸው የሆነ ሥልጣኔ፣ የራሳቸው የሆነ ሥራዓት፣ የራሳቸው ባህል፣ የራሳቸው ቋንቃና ጽሑፍ፣ የራሳቸው አለባበስ፣ አበላል፣ አጠጣጥ ሳይቀር የነበራቸውና በጀግንነት ራሳችውን አስከብረው በሞራል በኩራት የኖሩና ለተከታታይ ትውልድ አገራቸውን ጠብቀው አስተላልፈውልናል። ብዙ አገሮች በመጥፎው ቅኝ አገዛዝ ሥር ሲወድቁ እነሱ ተሰውተው ለሚቀጥለው ትውልድ በነፃነት አገር አስረክበውናል። የአገራችንን ክብር መጠበቅ ከእንግዲህ ደግሞ፣ ወደድንም ጠላንም፣ የእኛ ፋንታ ሆኗል። የግል ጥቅማችንን ብቻ እምናስተውል ከሆነ ምንም ጊዜ ሕብረት አይኖረንም። በአገር ደረጃ ማሰብና ሕብረት ፈጥረን ቋሚ ሥራ ሠርተን ልክ እንደአባቶች ራሳችንን ሰውተን ካልሆነ በስተቀረ ለመጪው ትውልድ ትተን የምንሄደው ምንም ነገር አይኖርም። ትልቅ መስዋዕትነት ይጠይቃል።

https:www.tzta.ca


“ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም”

ሊሆን ይችላል ተብሎ ያልታሰበ ግን የሆነ! ዶ/ር አቢይ ምስጋና ይገባሃል

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፖለቲካ አላማቸው ሲሉ ሕዝብን ወደ ራሳቸው ፍላጎት ለማምጣት ሌሎችን በጠላትነት የሚፈርጁ ሕዝበኛ ወይንም ፖፕሊስት አይደሉም ሲል ታዋቂው የትንተና መጽሔት ፎሪን ፖሊሲ ዘገበ። አንዳንድ በስም ኢትዮጵያውያን

የጠቀሳቸው ጋዜጠኞችና

(Foreign Policy magazine) December 8, 2018 አክቲቪስቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ በወሰዳቸው አብይ አሕመድን ሕዝበኛ ሲሉ ርምጃዎች በሃገራቸው ያገኙትን ቢያነሷቸውም ዶክተር አብይ ሕዝባዊ ድጋፍና በውጭ አለም አሕመድ እንደ አሜሪካው ያላቸውን ተቀባይነት ዘርዝሯል። ትራምፕም ሆነ እንደ ቱርኩ ኤርዶጋን በራሳቸው ዙሪያ ዶክተር አብይ አሕመድ ያገኙትን ሰዎችን ለማሰልፍ ተቀናቃኛቸውን ድጋፍና ተቀባይነት በበጎ በጠላትነት የሚፈርጁ አይደሉም የማይመለከቱና ይልቁንም ይህንን ሲል ምስክርነቱን ሰቷቸዋል። “አብይ ማንያ” ወይንም “የአብይ ልክፍት” በማለት የሚጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከመንግስቱ ሃይለማርያምም ሆነ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ከመለስ ዜናዊ በተለየ ከፍረጃ ጣይብ ኤርዶጋን፣ከሕንዱ ጠቅላይ ፖለቲካ ወተው ሁሉንም ሃይሎች ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና በሃገራቸው ጉዳይ እንዲሳተፉ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ እያደረጉ ናቸው ሲልም በሰፊው ትራምፕ ጋር እንደሚያመሳስሏቸው ዘርዝሯል። ገልጿል። ከ48 አመታት በፊት የተመሰረተውና መቀመጫውን በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ፎሪን ፖሊሲ መጽሔት “አብይ አሕመድ ፖፕሊስት/ወይም ሕዝበኛ አይደለም”በሚል ርዕስ በቶም ጋርድነር በቀረበው ጽሁፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ስልጣን

ሆኖም ዶክተር አብይ አሕመድ እንደተጠቃሶቹ የሃገር መሪዎች ፖፕሊስት ወይንም ሕዝብን በዙሪያቸው ለማሰለፍ ተቀናቃኞቻቸውን በጠላትነት የሚፈርጁ አይደሉም ሲል መጽሔቱ ምስክርነት ሰቷል።

ዶክተር አብይ አሕመድ ሕዝብን በዙሪያቸው ለማሰለፍ ከመድረኩ የተገለሉትን የሕወሃት መሪዎችን እንኳን በጠላትነት ሲፈርጁ ያልታዩ፣ አሸባሪ ተብለው ከሃገራቸው የተገለሉ ሃይሎችን በሃገራቸው ጉዳይ በባለቤትነት እንዲሳተፉ ያደረጉ፣በጥቅል ከፍረጃ ይልቅ መደመር በሚል መርሃቸው ሁሉንም ባለድርሻ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ሲል በጽሁፉ አስፍሯል። ፎሪን ፖሊሲ ላቀረበው መሞገቻ ጽሁፍ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕግ ባለሙያ የሆኑትን አቶ መኮንን ፍሬውን በአስረጅነት ጠቅሷል። አቶ መኮንን ፍሬው እንደገለጹት ዶክተር አብይ አሕመድ እንደ ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ተቀናቃኞቻቸውን ኢምፔሪያሊስቶች፣እንደ አቶ መለስ ዜናዊ ጠባብና ትምክተኛ እያሉ ፍረጃ ውስጥ አይገቡም።

ትናንት ዛሬ አደለም ( በእውቀቱ ስዩም)

December 8, 2018 ይገርማል!! ያገራችን ገበሬ የሚያርስበት በሬና ማረሻ ጥንታዊ ሰው ከአራት ሺህ አመት በፊት ይገለገልበት የነበረውን ነው:: ይሁን እንጂ ቢቀናው ክላሺንኮቭ ይታጠቃል:: ደሞ ገበሬውን ዘመናዊ ጠመንጃ እንጂ ዘመናዊ ማረሻ ለማስታጠቅ የሚያልም አክቲቪስት አይተን አናውቅም::

ዘመናይ የብሄር አክትቪስት ጦርነት በናፈቀ ቁጥር ያባቶቹን ጀብድ ይዘክራል:: ባባቶቹና በሱ መካከል በሰፊው የሚያዛጋ የጊዜ ገደል እንደተዘረጋ አይገባውም:: የድሮ ሰዎች ከማረስ ይልቅ መዋጋት ቢወዱ አይገርምም:: ያኔ ጦርነት ወጭው ትንሽ : ትርፉ ብዙ ነበር:: ጥቂት የተደራጀ ጭፍራ ጥቂት ፈረስና ጦር ይዞ በሺ የሚቆጠር የቀንድ ከብት መማርክ ይቻል ነበር:: ዛሬ አንድ መንደር አርሶ የሚያበላ ትራክተር ባስራ አራት ሺህ ዶላር መግዛት ትችላለህ:: አንድ መንደር አፈር የሚያስበላ ታንክ ለመሸመት ከፈልግህ ግን ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር መክፈል ይጠበቅብሃል:: እና በዚህ ዘመን ተዋግቼ አተርፋለሁ ብሎ ጉራውን የሚነፋ አዲስ የተመረተ ዴዴብ መሆን አለበት!!! ድሮ በሰላምም ሆነ በጦርነት ባጭሩ መቀጨት ያባት የናትህ እዳ ነበር:: በጦርነትም ሆነ በሰላም ጊዜ ከሞት ጋር ያለህ ርቀት ተቀራራቢ ነው:: ይህን የሚያውቁት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በማይጨው ዋዜማ የክተት አዋጃቸው

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

“ቤትህ ቁጭ ብለህ በሳልና በጉንፋን ከመሞት ጠላትን መክተህ ብትሞት ክብር ነው” ብለው ዜጋውን ጀንጅነውታል:: ልክ ነው! በህዳር በሸታ ከመሞት በጦርነት መሞት ስም እና ምርኮ ሊያስገኝ ይችላል::

ዛሬ ሰላም ወጭ ቆጣቢ ነው:: ሰላም ያለው ብዙ ሀብት ብዙ እድል ብዙ ተስፋና ብዙ እድሜ ይኖረዋል:: ታድያ ለሰላም ሲባል ወደረኞቻችንን ብንለማመጣቸው ብናቆላምጣቸው ብንወያያቸው እንዴት ነውር ይሆናል? ዛሬ መደራደር መወያየት የሚያሳፍርበት : ውረድ እንውረድ የሚያስኮራበት ዘመን አይደለም:: ዛሬም እንደ ጥንቱ በርስት ወይም በማንነት ሰበብ የሚደረግ ጦርነት የሚጎዳው ዜጎችን እንጂ ጌቶችን አይደለም:: ከእምባቦ ከሰገሌ እና ከባድመ ክሽፈት እንዳየነው አገሬው በጦርነት ያልፋል: አገር መሪው ግን ይተርፋል:: በእምባቦ ጦርነት ንጉስ ምኒልክና ንጉስ ተክለሃይማኖት ገጥመው በብዙሺህ የሚቆጠር ባላገር ያአሞራ ቀለብ ሆነ::

12

ሁለቱ ሃያላን ግን ታርቀው ተፋቅረው ረጅም እድሜ ኖሩ:: ሰገሌ ላይ የንጉስ ሚካየል ባላገርና የተፈሪ መኮንን ባላገር ተፈሳፈሰ:: ደሙን ለሁለቱ መሳፍንት የክብር ሲል አፈሰሰ:: ንጉስ ሚካኤልም ሆነ ተፈሪን ግን ከጦርነቱ ማጠናቀቂያ ባንድ ድንኩዋን ውስጥ ተቀምጠው ” አባቴ እንኩዋን አተረፈዎ! ልጄ እንኩዋን አተረፈህ” እየተባባሉ ተቃቀፉ:: በባድመ ጦርነት ያ ሁሉ ወጣት አላማም ሆነ ኢላማም በሌለው ጦርነት ሜዳ ላይ ቀረ:: የጦርነቱ ጠንሳሾች ለሙታን ተገቢውን መታሰቢያ ሳያደርጉ ላደረጉት ይቅርታ ሳይጠይቁ በህይወት ይርመሰመሳሉ :: ነገም ከዚህ የተለየ አይሆንም!! እና እምቢ በል!!! አሻፈረኝ በል!! በቀረርቶ አትወሰድ! በመፈክር አትሸወድ!! ለሚያዋጉ እንጂ ለማይዋጉ ጦርአውርዶች : እንኩዋን ህይወትህን ትኩረትህን ለመስጠት አትሞክር!!

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

13

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

14

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

15

https:www.tzta.ca


Trudeau says government will limit access to handguns, assault weapons

Prime Minister Justin Trudeau

THE CANADIAN PRESS PUBLISHED DECEMBER 6, Prime Minister Justin Trudeau says his government plans to limit access to handguns and assault weapons to confront gun violence in the country. Speaking to Montreal radio station 98.5 FM Thursday on the anniversary of the

1989 Ecole Polytechnique massacre, Trudeau did not rule out a full ban when asked by the host. “We are currently reflecting on how we are going to do better to counter the violence caused by handguns and assault weapons, yes,” Trudeau said. “What’s happening is unacceptable.” The prime minister said

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

the government is looking at different alternatives to address the situation. “But, yes, we want to limit the easy access that criminals unfortunately still have to handguns and assault weapons,” he said. In 2015, Trudeau’s Liberals campaigned on a promise to “get handguns and assault weapons off our streets.” In October, as Ottawa held consultations on a possible ban of the weapons, groups representing survivors and families of victims of Quebec mass shootings questioned the government’s commitment. They said they feared reforms would come too late in the government’s mandate to be passed before the next election, scheduled for October 2019. Trudeau’s comments Thursday came as Montreal marked the 29th anniversary of shootings that killed 14 women at the Ecole Polytechnique engineering school.

16

In a statement, Trudeau noted the victims were targeted because they were women. “We remember the victims of this hateful act of violence and unite against the misogyny at the root of this tragedy,” he said. His statement did not mention firearms, but it called for action against violence and discrimination affecting women. “Survivors and advocates are leading the fight for change, and their example inspires all of us,” he said. In a ceremony Thursday morning, flowers were laid at a Montreal monument honouring the victims: Genevieve Bergeron, Helene Colgan, Nathalie Croteau, Barbara Daigneault, Anne-Marie Edward, Maud Haviernick, Maryse Laganiere, Maryse Leclair, Anne-Marie Lemay, Sonia Pelletier, Michele Richard, Annie St-Arneault, Annie Turcotte and Barbara Klucznik Widajewicz.

https:www.tzta.ca


Minister Bibeau concludes visit to Ethiopia by announcing initiatives to empower women and girls and the empowerment of women and girls is the best way to reduce poverty.

Marie-Claude Bibeau, Minister of International Development November 16, 2018 - Addis Ababa, Ethiopia - Global Affairs Canada Canada recognizes that supporting gender equality

The Honourable MarieClaude Bibeau, Minister of International Development, concluded a three-day visit to Ethiopia by announcing $23 million in funding for two initiatives that will help advance gender equality and the empowerment of women and girls in Ethiopia, including women’s economic empowerment. The first initiative, Innovative Finance for Women Entrepreneurs, will help 25,000 women entrepreneurs better support their families and communities by improving their access to

financial services, new technologies and leadership training. The second initiative, Women’s Voice and Leadership, will support 48 local women’s organizations across four regions of Ethiopia to strengthen their capacity to promote gender equality and the empowerment of women and girls in their communities.

Throughout her visit, the Minister engaged with Ethiopia’s Prime Minister Abiy Ahmed, local government officials, survivors of gender-based violence, local women’s groups and entrepreneurs to discuss how Canada and Ethiopia can continue their strong collaboration to close the gender gap to ensure no

one is left behind.

Quotes “Canada is a staunch champion of gender equality and is proud of its longstanding collaboration with the Government of Ethiopia. Ethiopia’s Prime Minister is undertaking impressive reforms and is showing leadership in promoting gender equality at the highest levels. Today’s announcement will help further these efforts to ensure all Ethiopians, especially women, girls and youth, have equal access to social, political and economic opportunities.” Marie-Claude Bibeau, Minister of International Development

Ethiopia is the largest recipient of Canada’s assistance in Africa.

Tel:- 647-7027528 ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

17

https:www.tzta.ca


Addis Ababa International Movement (AIM) Launch ethnonationalists. Due to this

Addis Ababa International Movement (AIM) Launch Date:12/08/2018 This is a statement of establishment of the Addis Ababa International Movement (AIM). AIM firmly believes that Addis Ababa belongs to all and every citizen of Ethiopia. To that effect, it will work in organizing and supporting movements that will address the social, political, and economic rights of Addis Ababa residents. Addis Ababa has been serving as the political and economic capital of Ethiopia for more than a century. Throughout the century, it has hosted a multitude of identities from all corners and merged those into an overarching unique character with a common destiny creating a melting pot that respects humanity, togetherness, and friendship without the limitations of ethnicity and religion. However, EPRDF’s constitution with its language based Ethnic Federalism, completely ignores the multi-ethnic and cosmopolitan nature of Addis Ababa. It lacks coherent and legitimate ideological underpinning to administer the city and her people. It is a well-known fact that, the ruling party, TPLF/EPRDF has long denied the plular identity of Addis Ababa and reduced her administration to a matter of ethnic political calculus and her fate at the hands of

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

18

constitutional betrayal, Addis Ababa can not decide anything of consequence by herself. Her residents have lost their democratic rights and have been denied ownership of their city. Official appointees are beholden to the party and not to the people. Moreover, ethnonationalists have been waging war by labeling Addis Ababa residents as settlers. This has marginalized them from fully exercising their democratic rights as citizens. The solution to remedy the disenfranchisement is to organize. This is why we have established Addis Ababa International Movement (AIM). Its main objectives are: to work on true representation of the interests of its residents socially, politically and economically; to reaffirm that Addis Ababa belongs to all Ethiopians and not any one specific group; organize intellectuals to research on various fields and make available their works to the public; to provide intellectual and moral backing to groups working on values that align with AIM. Currently, AIM has about 2000 registered members worldwide. We call upon all Ethiopians to register as members and help the movement. For additional information about Addis Ababa International Movement (AIM), please use the following emails depending on the chapters closest to your residence. 1.contactAhunUS@gmail.com 2.contactAhunEU@gmail.com 3.contactAhunETH@gmail. com Addis Ababa International Movement (AIM)

https:www.tzta.ca


TZTA interviews Ato Alemayehu Asfaw, the President of Ethiopian Community Association in the GTA and Surrounding Regions to fulfill my obligation in order to be able to contribute my share within my knowledge and capacity, however small. I also believe that working for the community would broaden someone’s understanding of the society. It also helps to develop the interests of individuals in related areas.

Ato Alemayehu, the President of Ethiopian Community

1) TZTA Tell me about yourself and your organization briefly. Ato Alemayehu First of all, I would like to thank TZTA for the opportunity given to me to speak and also for the services you render to the community for several years. I was born in Addis Ababa and grew up in Ethiopia in various provinces while, at the time, my parents used to move from place to place for work assignments. My back-ground education is basically mechanical engineering with B.Sc. degree and specializing in aeronautics with M.Sc. Most of my work life was with Ethiopian Airlines and had a number of years of service. I came to Canada because of various reasons and I’m now a resident of the GTA. I’m married, have three children, two girls and a boy. During the 2017 annual general meeting of Ethiopian Community Association in the GTA and Surrounding Regions I was elected to the board of directors. I have been a member of the association since I came in 2001. 2) TZTA Why do you need to work as a volunteer in the Ethiopian community? Ato Alemayehu I believe it’s everybody’s obligation and responsibility to serve the community; and, I want

3) TZTA What is the weakness and strength of your organization? Ato Alemayehu Ethiopian Community Association was established in 1981 as a non-profit organization free of any sort of political affiliation. No changes have been made to its policy since its inception. For a long time in its history the Association has had government support from the federal, provincial and municipal entities as well as other donor organizations. Like any organization the Association has had its challenges. It has had various problems and ups and downs. Among those the most important and difficult ones, I must say, are 1. The decision taken by the federal government to cut its entire budget and 2. The lack of or diminished community support from the society as well as the lack of unity within the Ethiopian community. The Association used to be managed by an Executive Director and had a number of employees to run it. It used to give the following services: = Immigration services = Social assistance program = Language training = Seniors club = Women’s association = Employment services = And other services Even though there have been some difficulties, the Association could survive and tried to meet its obligation, although very much reduced, with the help certain devoted individuals who should be praised.

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

4)TZTA a)What can we learn from the past accomplishment of the Ethiopian Day celebration? b)Could you explain the level of preparation for the up coming Ethiopian Day? c)What kind of message can the Ethiopian Day celebration send to Canadians? d)Why do we need to celebrate Ethiopian Day and Ethiopian New Year together? Ato Alemayehu The Ethiopian New Year falls in September, according to the Ethiopian calendar. The Association celebrates the Ethiopian New year every September on a week end, which is close to the New Year and calls that festival Ethiopian Day. The reason behind the festival is to set the day as a remembrance to our country’s traditions, introduce and show our cultures, make a get-together event and celebrate our community. This is a public festival and everybody can join the celebration. All Canadians of different origins can learn and appreciate our cultures and traditions. The 2018 celebration did go very well, although there were some organizational problems such as tent rental issues. Again, people in our community should learn to follow programs and schedules that the Association puts out and perform within set deadlines. When that cannot happen, the situation becomes disrupted and difficult to manage. I hope things of that sort won’t happen next time. In the end, I would like to convey my sincere thanks to the board members and other members of the Association who gave their valuable time to make a successful celebration, all of the Ethiopian community and other organizations who participated, as well as members of the public who came to our festival. 5) TZTA What kind of support and cooperation do you seek

19

from our readers, community members, other Ethiopians and guests at large? Ato Alemayehu The Association always awaits community members with open arms to register and become members. We would like to create unity and fight for our rights together; because together we’ll win. We need a lot of support. Let’s work hard, let’s sacrifice for the sake of our children and grand children, let’s help each other and make peace amongst ourselves. In this regard, the current board of directors is trying its best to seek cooperation from the community members to participate in whatever capacity whether giving out donation, advice or physical help. It puts a lot of effort to bring back our unity. 6) TZTA What kind of special message do you wish to send to our readers in the community? Ato Alemayehu The message I intend to send may be to call upon all community members to draw their attention to our historic back ground. Our forefathers were martyrs and fighters for their survival and freedom. They had their own history and tradition, their own system, their own culture, their own language and script, and even their own type of dresses and eatery. They diligently worked hard and sacrificed themselves to protect these values and were able to give our generation modern education. That’s why our country Ethiopia was never colonized while many African countries fell into this kind of demonizing rule, which significantly kills people’s moral. The formula was quite simple, unite and stand together. Whether we like it or not today it’s our turn to bear the yoke. Let’s raise our fathers’ principles with big moral intentions for success and respect.

https:www.tzta.ca


Ethiopian Prime Minister among 100 most influential Africans of 2018 Posted by: ecadforum

(FBC) — Prime Minister Dr Abiy Ahmed has been named among the 100 most influential Africans of 2018 by the New African

magazine. The magazine has featured Dr Abiy on its cover page.

litical reforms in the country since he came to power last April.

The Ethiopian Prime Minister has made stunning po-

He released thousands of prisoners, lifted bans imContinued on page 20

Tackling Hate Speech in Ethiopia Criminalizing Speech Won’t Solve Problem

The prime minister and other public figures could also speak out regularly and openly about the dangers of hate speech. Donors, eager to support the reform process, could help support such a strategy. And social media companies should do more, including ensuring they have sufficient resources to respond quickly to reports that speech on their platform may lead to violence.

Felix Horne Senior Researcher, Horn of Africa

@felixhorne1

Internet café in Lalibela, Amhara Region, Ethiopia. © 2010 Hemis.fr/AFP Photo Hate and dangerous speech is a serious and growing problem in Ethiopia, both online and offline. It has contributed to the growing ethnic tensions and conflicts across the country that have created more than 1.4 million new internally displaced people in the first half of 2018 alone. The government says it will pass a new law on hate speech to counter this. But around the world, laws criminalizing hate speech have been often and easily abused – and there are other options. In the past year, speeches by government officials, activists and others in Ethiopia have disseminated quickly through

Ethiopia’s own track record offers reason for alarm. In the past, the Ethiopian government has used vague legal definitions including in its anti-terrorism law, to crack down on peaceful expressions of dissent.

Ethiopians also need new platforms and opportunities to express their grievances and discuss critical issues, beyond social media. The growing list of independent media outlets, as well as universities, civil society organizations, political parties, and others could provide helpful environments for discussion.

What Ethiopia needs is a comprehensive new strategy – one that even a carefully drawn hate speech law should only be one small part of. This could include public education campaigns, programs to improve digital literacy, and efforts to encourage self-regulation within and between communities.

Ethiopia is currently rewriting its civil society law and anti-terrorism law – both of which were used in the past to stifle dissent and limit freedom of expression. It should be careful not to undermine those efforts by drafting a new law that could be used for the same kinds of abuse.

Internet café in Lalibela, Amhara Region, Ethiopia.EXPAND

social media and helped trigger or fuel violent conflicts in the country.

It is encouraging that Ethiopia’s government says hate speech must be addressed. But any law that limits freedom of expression by punishing hate speech must be narrowly drawn and enforced with restraint, so that it only targets speech that is likely to incite imminent violence or discrimination that cannot be prevented through other means. Many governments have tried and failed to strike the right balance, and

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

20

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue 2

21

Contined on page 22

https:www.tzta.ca


Continued from page 20

posed on political parties as well as unblocked websites.

www.abayethiopiandishes.com

At Abay Ethiopian Dishes, our mission is to deliver exceptional Ethiopian dishes to your home, at an affordable price...

The goal of Abay Ethiopian Dishes is to save you time, energy, money and deliver to you a healthy, nutritional and tasty food. How do you save time? Our wots and kulets have onion, garlic, ginger, turmeric, Ethiopian berbere, tomato paste,cooking oil, and several Ethiopian spices.So we help you save time from shopping, peeling (onion, garlic, ginger) cutting, grinding and cooking it 3-5 hours to get that authentic Ethiopian flavour. Then you have to place what you cooked in containers, clean all the utensils you used, clean your stove, kitchen, disinfect and deodorize your home.I wonder what you will do with that extra time in your hand.Spend quality time with your children, socialize with friends,take extra coarse,serve God and man or do overtime at your job that pays you $$$$$ more as suppose to minimum wage? We can even deliver it to your home, already packed and ready to be eaten or you can store and keep it and use it as needed (our canned kulet does not need fridge). Also, now we have vegan wots, key and alicha (misir, shiro, tomato, cabbage and carrot, whole lentlies, split chickpeas and red beets salad). Just go to www.AbayEthiopianDishes.com. Enjoy!

The country has also signed peace deal with neighboring Eritrea and appointed a gender-balanced Cabinet with 50 percent women. Six other Ethiopians, including Group CEO of Ethiopian Tewolde Gebremariam, CEO of Ethio-Telecom Frehiwot Tamiru as well as founder and executive director of soleRebels, Bethlehem Tilahun, appeared in the list. Presidents of Egypt, Rwanda, and South Africa are also included in the list. In terms of countries, entries are led by Nigeria with 18 names followed by Kenya (11) South Africa (10) Egypt (8) and Ethiopia (7).

እንክዋን ለአዲሱ አመትና ገና በአል በሰላም በደስታ አደረሳችሁ። መጪው 2019 ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የምህረት፣ የመደመር፣ የአንድነትና የዲሞክራሲ መስፈን በውድ አገራችን ኢትዮጵያ እንዲሆን እንመኛለን። የመጽሔቱ አዘጋጅ ተሾመ ወልደአማኑኤል

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue

22

https:www.tzta.ca


በኮሚሽን ወንበር እናከራያለን። ደውሉልን!

ድልድይ መጽሔት / DECEMBER 2018 Volume 1: Issue

23

https:www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / DECEMBER Volume 1: Issue 2 2018

24

https:www.tzta.ca


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.