BRIDGE MAGAZINE VOLUME 1: ISSUE 4/ JUNE 2019
President Sahlework Zewde met with PM Justin Trudeau As Sahlework Zewde expresses interest for stronger economic tie with Canada, Justin Trudeau pledged Canada’s continued support to the reform process in Ethiopia
Five things to watch for as Trudeau meets Trump, congressional leaders in Washington... Read more page...16
Ontario Premier Doug Ford shakes up cabinet amid backlash for spending cuts ...Read more page 19
Best moments from Raptors' championship parade ...Read more page 6
እናስተዋውቃችሁ
፣ ደራሲና አቅራቢ የቶሮንቶ ነዋሪ የሆነው አቶ ጴጥሮስ ደጀኔ ...ገጽ 6 ይመልከቱ
ስለ 'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ...ገጽ 10 ይመልከቱ
President Sahlework Zewde having conversation with Canada’s Prime Minister Justin Trudeau. Photo credit : Office of the President, Ethiopia
ከቡርቃ ዝምታ: ወደ ፊንፊኔ ጫጫታ !! ...ገጽ 8 ይመልከቱ
1: Issue 4 ድልድይ መጽሔት / SEPTEMBER June 2019 Volume 2018
2 2
https:www.tzta.ca https:www.tzta.ca
1: Issue 4 ድልድይ መጽሔት / June SEPTEMBER 2019 Volume 2018
3 3
https:www.tzta.ca https:www.tzta.ca
የድልድይ መጽሔት ማውጫ
COVER
ወይ የኢሣት ነገር! ጊዜ ደጉ ስንቱን ያሳያል? ...ገጽ 15 ይመልከቱ
እናስተዋውቃችሁ
፣ ደራሲና አቅራቢ የቶሮንቶ ነዋሪ የሆነው አቶ ጴጥሮስ ደጀኔ ...ገጽ 6 ይመልከቱ
PAGE
Best moments from Raptors' championship parade
Five things to watch for as Trudeau meets Trump, congressional leaders in Washington... Read more page...16
...Read more page 6
President Shellwork Zewde May 28 ,2019 Ethiopian President Sahlework Zewde is traveling to Canada over the weekend, reported state affiliated Fana Broadcasting Corporation (FBC) The purpose of her travel is to attend Women Deliver 2019, a Global conference, which will take place in Vancouver, British Columbia, between June 3 and June 6. The conference is considered as the world’s biggest stage for gender equality. As well, the conference focuses on health, rights, and wellbeing of girls and women.
ከቡርቃ ዝምታ: ወደ ፊንፊኔ ጫጫታ !! ...ገጽ 8 ይመልከቱ
...Read more page 19
ስለ 'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ..ገጽ 10 ይመልከቱ
She is reportedly scheduled to speak during the conference. Prime Minister Justin Trudeau and his wife, Sophie, will be attending the conference, according to information on the organizer’s website. Sahlework has plans to meet with Ethiopians and Ethiopians Canadians in Vancouver area on the sidelines of the conference, as per Fana Broadcasting report.
Ontario Premier Doug Ford shakes up cabinet amid backlash for spending cuts
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር ስርዎመንስዔ፤ ህገመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ ...ገጽ 12 ይመልከቱ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
Justin Trudeau scores basket of treats from Nancy Pelosi after winning NBA Finals bet ...Read page 22
4
https:www.tzta.ca
Thinking of Real Estate? Helen Zeray
Sales Representative
Direct: 647-712-0461
Aziz Mohamed, BA, CCIM, MRICS Broker of Record
Greater Toronto Area: 416.243.2400 Kitchener-Waterloo Region: 519.744.2300
519-744-2300
Direct: 416-930-3512
Call for Free Consultation Canadian Owned & Operated: NO Middleman, NO Franchise Fees, NO Hidden Fees
Sell Direct, Save Direct: MLS Listing $999
Buy Direct, Save Direct: Buyers Get $1000 Cash Back
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
5
https:www.tzta.ca
በዓለም አቀፍ ጉዲፈቻ ዙሪያ የተሰራ (feature) ፊልም የሆኑ ሕጻናት ያሉባት ሃገር -
እነዚህን ሕጻናት ለመንከባከብ የሚያስችል ሃገር በቀል መፍትሄ ባልተዘረጋበት ሁኔታ - የጒዲፈቻ ሂደትን በሙሰና መዘፈቅ ተከትሎ መፍትሄዎችን ከመፍጠር ይልቅ በጅምላ ማገዷ የሕጻናቱን ጥቅም ነው ወይስ የፖለቲካ ገጽታን የሚያስጠብቀው የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።
እናስተዋውቃችሁ፣ ደራሲና አቅራቢ የቶሮንቶ ነዋሪ የሆነው አቶ ጴጥሮስ ደጀኔ ሕጻናት በተፈጥሮ ወላጆቻቸውና በተወለዱበት ባህል ውስጥ ቢያድጉ ለስነልቦናዊም ሆነ አጠቃላይ ጤንነታቸው የተሻለ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢታወቅም በጦርነት፣ በበሽታ፣ በድህነትና በመሳሰሉ ውስብስብ ችግሮች የተነሳ በርካታ ሕጻናት በዓለም አቀፍ ጒዲፈቻ ወደውጪ ሃገር ተልከው ለማደግ ይገደዳሉ። ዓለም አቀፍ ጒዲፈቻን የሚያስፈጽሙት አትራፊ ድርጅቶችና ሶስተኛ አለም ያሉ አትራፊ ወኪሎቻቸው (ደላሎች) በመሆናቸው የተነሳና ሂደቱ በአግባቡ ቁጥጥር ስለማይደረግበት እነዚህ ወኪሎች ወላጆችን በማታለልና ከፍ ሲልም ደግሞ በጉልበት ልጆቻቸውን በመንጠቅ በሕገወጥ መንገድ
ሕጻንትን ወደውጪ የላኩበት ገጠመኞች በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገሮች በርካታ ናቸው። በቁጥር ደረጃ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ ብቻ ጒዲፈቻ ኢትዮጵያ እስከታገደበት ጊዜ ድረስ ከ15 ሺህ በላይ ሕጻናት ወደ አሜሪካ ብቻ መላካቸውን የስቴት ዲፓርትመንት አሃዝ ያሳያል። ይሄንን እና ሌሎች አሃዞችን ታሳቢ በማድረግ ባለፉት 40 ዓመታት ከመቶ ሺህ በላይ ሕጻናት ወደ ውጪ መላካቸውን መገመት ይቻላል። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ በወር ከ20 ሕጻናት በላይ የሚጣሉባትና ከ 4.5 ሚሊዮን በላይ አንድ ወይም ሁለት ወላጅ አልባ
ባጭሩ ግን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሕጻናትን፣ ወላጆችን እና አሳዳጊዎችን የሚንካው ይሄ ሂደት በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊመከርበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ስሜት በመንሳት በቅርቡ '2 መታወቂያ' የተሰኘ በግለሰቦች ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ልብ ወለዳዊ ታሪክ አማካኝነት ጉዳዮን መድረክ የሚሰጥ (feature) ፊልም ተሰርቷል። ይሄ ፊልም ከ4 ወራት በፊት በአዲስ አበባ ብሔራዊ ትያትር ተመርቆ በመላው የአዲስ አበባ ሲኒማዎችና በተወሰኑ የክፍለ -ሃገር ፊልም ቤቶች የታየ ሲሆን ይዞ የተነሳው ለየት ያለ ማህበራዊ ፋይዳ ያለው ጭብጥ በተመልካቹና በሃያስያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶለታል። '2 መታወቂያ' በቶሮንቶ ኦገስት 11 ከሰአቱ 2 (ፒም) ሰዓት ጀምሮ በሮያል ሲኒማ
የሚመረቅ ሲሆን -በታወቀው የቶሮንቶ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይም ለመታየት ማመልከቻ አስገብቷል። የዚህ ፊልም ደራሲና አቅራቢ ቶሮንቶ ነዋሪ የሆነው ጴጥሮስ ደጀኔ ሲሆን - ፊልሙ 25 እጁ በካናዳ 75 እጁ ደግሞ በኢትዮጵያ ነው የተቀረጸው። በፊልሙ ላይ ከ 10 በላይ ካናዳዊ ተዋንያን እና በርካታ ታዋቂና ጥቂት አዳዲስ ኢትዮጵያዊ አርቲስቶች የተሳተፉበት ሲሆን -ሰርቶ ለማጠናቀቅ 2.1 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል። የፊልሙ 'ዣንረ' ልብ አንጠልጣይ ድራማ (suspensedrama) ሲሆን አለፍ አለፍ እያለ ግን በሳቅ ፍንቅል በሚያደርጉ ክስተቶች ተዋዝቷል። ፍጆታው አንድ ሰዓት ከ45 ደቂቃ ሲሆን ታሪኩ የሚያጠነጥነው በሕጻንነቱ ወደ ካናዳ በጉዲፈቻ መጥቶ - ካደገ በኋላ ወላጆቹ በሕይወት እንዳሉ ስላወቀ አንድ ወጣት ዙሪያ ነው። ወላጆቹን ፍለጋ በሚያደርገው ፈታኝ ጉዞ - የሂደቱን ውስብስብ ፈተናዎች በግለሰቦች ታሪክ አማካኝነት ተመልካቹ ይቋደሳል። እያዝናናም እያሳዘንም ትልቅ ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳይን መድረክ የሚሰጠውን ይሄንን ፊልም በሮያል ሲኒማ ኦገስት 11 የቶሮንቶ እና አካባቢው ነዋሪ በመገኘት እንዲከታተል ተጋብዟል።
እናስተዋውቃችሁ፣ ደራሲና አቅራቢ የቶሮንቶ ነዋሪ የሆነው አቶ ጴጥሮስ ደጀኔ “፪ መታወቂያ” በሚል በዓለም አቀፍ ጉደፈቻ ዙሪያ የተሰራ (FEATURE) ፊልም ኦገስት 11 ቀን 2019 ከሰዓት 2:pm ጀምሮ በሮያል ሲኒማ የሚመረቅ ሲህን ሁላችሁም ተጋብዛችዋል።
የፊልሙ ተዋናይ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
6
https:www.tzta.ca
Best moments from Raptors' championship parade
From NBA.com Staff Jun 17, 2019 5:27 PM ET tors dethroned the reigning-champion Golden State Warriors in Game 6 of The Finals last Thursday night. Those good feelings and the championship buzz isn't about to wear off just yet, especially with the Raptors' championship parade making its way through downtown Toronto all day today. Mayor John Tory declared Monday "We The North Day" in Toronto, after the NBA champions' slogan and some 1.5 million are expected to be at the parade.
Kawhi Leonard received the key to Toronto during the Raptors' celebration.
We The North has become We The Champs.
Toronto has been celebrating almost non-stop since the hometown Rap-
Cell:
Here's a quick look at the best moments, sound bites, photos and more from Toronto's title celebration ...
647-988-9173 . Phone 416-298-8200
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
7
https:www.tzta.ca
ከቡርቃ ዝምታ: ወደ ፊንፊኔ ጫጫታ !! (አሥራደው ከፈረንሳ)
ኳኳታ የሃሳብ ድህነት መግለጫ መሆኑን ብናምንም፤ ከአፍ ወለምታው በስተጀርባ ያለውን ትልቅ ስብራት ወጌሻም አይጠግነው !! ማስታወሻ : በዚህ ርዕስ መጣጥፍ ለማቅረብ አስቤ ከጎረምሶችቹ ጋር አብሮ አቧራ ላለማቡነን ስል ትቼው ነበር፤ ሆኖም ጎረምሶቹ የሚያቦኑት አቧራ ዛሬም እያገረሸ በማስቸገሩ፤ ማለት የሚገባኝን ለማለት ወሰንኩ፤ እናም ይኸው:: አገር እበት ወልዳ ጡቶጯን ትል ሲጠባው እያየን ብንታገስ፤ ጭራሹኑ ይባስ ብለው፤ ትዕግስትን እንደ ፍርሃት በመቁጠር፤ አፋቸው ከጥብጣባቸው የሰፋ የኦህዴድ/ ኦነግ "ሁንዱማ ኬኛ" ሁሉም ነገር የኛ! ባይ፤ ባለ ተረኛ ነን ፖለቲከኞች፤ ዛቻና ማስፈራሪያ ፈር እየለቀቀ በመምጣቱ፤ "አህያን በአህያነቷ፤ ተራገጠች ብሎ የሚቀየማት ባይኖርም፤ ዳግም እንዳትራገጥ፤ መጀመርያ በብዕር ልምጭ ለመግራት፤ እምቢ ካለችም ህግ ካለ፤ በህጋዊ ፍልጥ፤ ሃይ እንድትባል ለማመላከት ነው:: ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከደጅ ታሳድራለች " እንዲሉ ሆነና ጠ/ ምኒስትር አብይ አህመድ በእስክንድር ነጋ ላይ ጦርነት እስከማንሳት ያደረጉትን ዛቻ በመጠቀም፤ ዛሬ አቶ አዲሱ አረጋ ቀጤሳ “በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ .............. " በማለት ቀጣዩን የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር የፖለቲካ ዝሙተኖች አጀንዳ ሰፋ አድርገው ነግረውናል :: እኛም አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል እንዲሉ ነውና በሚገባ ከትበናታል :: የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ! እንኳን ከሸውራራውና ሌባው የህወሓት ዘመን፤ ወደ ሸፋፋው የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር የፖለቲካ ወሲበኞች ዘመን፤ በመከራ አደረሰን !! ልብ ተብሎ ይነበብልኝ በደስታ አላልኩም፤ በመከራ እንጂ !! አይምሰላችሁ የኛ መከራ ገና አላለቀም፤ ጠግበው የበሉ የህወሓት ጅቦች ተሰናብተው፤ የተራቡ የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር ጅቦች ናቸው፤ ተጠራርተው፤ አውው !!! እያሉ ያገኙትን ሁሉ ጭዳ ለማድረግና፤ የቀረች የህዝባችንን አንጡራ ሃብትና አጥንት እንደገና ሊግጡ ያሰፈሰፉት :: ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! እያለ ጮሆ የተናገረ ሁሉ ዕውነት ይናገራል፤ ዝም
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
8
ያለ ሁሉ ይዋሻል ያለው ማን ነው ?! ጠቅላይ ምኒስትሩ የዘርና የጎሣ ፖለቲከኞችን ለማሽኮርመም፤ ከነሱ ጋር ሲሆኑ የነሱን ቋንቋ፤ ከእኛ ጋር ሲሆኑ የኢትዮጵያዊነትን ካባ ለብሰው፤ በመልካም ቃላት፤ የአገራዊ አንድነት ፈላጊውን ቡድን የማደንዘዣ መርፌ፤ መውጋቱን ከወዲሁ ቢያቆሙት ይመረጣል:: አብይ አህመድ፤ የወለጋ ባንክ ዘራፊ ወንበዴዎችን፤ የሰላሌ የኦህዴድ/ ኦነግ ነብሰ ገዳዮችን፤ አንዲ ቃላት ትንፍሽ ሳላሉ፤ ብዕርና ወረቀት ብቻ በያዘና ብዙ መስዋዕትነት በከፈለ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ጦርነት ማወጅ ለምን ፈለጉ ? ለምን ፈሩት ? ለመሆኑ ጠ/ ምኒስትሩ ከኡጋንዳው ጉብንታቸው ምን ተምረው ተመለሱ ? በኡጋንዳ በዘርና በጎሣ የተነሳው የህዝብ እልቂት፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ላለው የዘርና የጎሣ ፖለቲካ መፈናቀልና ሞት ትምህርት ሆኗቸው፤ እንደተመለሱ የዘርና የጎሳ ፖለቲካ: ኢትዮጵያን ከመቅበ በፊት እንዲቀበር ያደርጉ ይሆን? ብዬ ነበር :: ምን ያደርጋል ምንም ሳይማሩ ተመለሱ :: የጌዴዎ፤ የንፋስልክ ላፍቶ፤ የአዲስ አበባ ዙሪያ፤ የሱሉልታ፤ የወልቃይት ጠገዴ፤.........ወዘተ. ተፈናቃዮች ወገኖቻችን፤ በጥቅሉ ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ፤ ከተለያዩ የአገራችን ክፍላተ ሃገራት፤ በዘርና በጎሣ ሰበብ እየተፈናቀሉና እየሞቱ፤ ጠ/ ምኒስትሩ የራሷ እያረረ የሌላ ታማስላለች " እንዲሉ በየ ጎረቤት አገሮች የሚያደርጉት የልታይ፤ ልከበር፤ ልደነቅ ጉዞና ሽምግልና፤ በእጅጉ ያሳዝናል: ትዝብት ውስጥም ይከታል :: የአገራዊ አንድነት ካባ ለብሶ: የኦህዴድ/ኦነግ ጥምር አንጃን ማሽኮርመም አደጋው ብዙ ነው................ ክቡር ጠ/ምኒስትር ዕውነቱን ልንገርዎ ! በኢትዮጵያ ጦርነት ለሁል ጊዜ የምናስታውሰው፤ ሠላም ለረጅም ጊዜ የምንረሳው እንዳይሆን ያሰጋል!! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !! እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ ! ሰኔ 15 ወን 2011 ዓ.ም. ( 22/06/2019)
https:www.tzta.ca
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
9
https:www.tzta.ca
ስለ 'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች
ቅዳሜ ዕለት አመሻሽ ላይ ባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ውስጥ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ በአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቤት ውስጥ የተፈጸሙት ጥቃቶች ስላስከተሉት ጉዳት በስፋት ተነግሯል። የባህር ዳሩ ጥቃት የክልሉን ርዕሰ መስተዳደርንና የአማካሪያቸውን ሕይወት መቅጠፉ በይፋ ቢነገርም የተጨማሪ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋበት ለክልሉ አስተዳደር ቅርብ የሆኑ ሰዎች ይናገራሉ። • በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ በአዲስ አበባው ጥቃት ደግሞ በሥራ ላይ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገድለዋል። ባህር ዳር ከተማ በቀዳሚነት በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የጀመረው ተኩስ ቁልፍ ከሚባሉት የክልሉ አመራር ክፍሎች መካከል በሚመደቡት የጸጥታ ጽህፈት ቤት፣ የፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉ ገዢ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደተፈጸመ ተነግሯል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በቴሌቪዥን ቀርበው ባህር ዳር ውስጥ ያጋጠመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ ይፋ ሲያደርጉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ አጭሮ ነበር። አሁንም ድረስ ድርጊቱ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
10
በባለስልጣናት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው? ወይስ እንደተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ? የሚለው ዝርዝር ምላሽ ያላገኘ ዋነኛ ጉዳት እንደሆነ አለ። • ታስሯል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱ ተገለፀ ከዚህ በተጨማሪ ባህር ዳርና አዲስ አበባ ውስጥ ካጋጠመው ክስተት ጋር ተያይዞ በርካታ እያነጋገሩ ያሉና አሁንም ድረስ ግልጽ መልስ ያላገኙ ነገሮች አሉ። ከቅዳሜው ጥቃት ጋር በተያያዘ ያላወቅናቸው ነገሮች የትኞቹ ናቸው? •በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የተፈጸመጥቃት ነው? ወይስ የመንግሥት ግልበጣ? የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ የተገለጸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቃባይ በኩል ሲሆን፤ በርካቶች ክስተቱን የመንግሥት ግልበጣ ብሎ ለመጥራት የሚያበቁ ሁኔታዎች የሉም በሚል ይከራከራሉ። የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሊያስብሉ የሚችሉ ቁልፍ ጉዳዮች በሌሉበትና በሉአላዊ አገር ስር በሚገኝ ግዛት ውስጥ መሆኑ ጥያቄን እያስነሳ ነው። •በጥቃት ፈጻሚዎቹና በክልሉ ባለስልጣናት መካከል እስከ ግድያ የሚያደርስ ቀደም ያለ አለመግባባት ነበር?
ገጽ 11 ይመልከቱ
https:www.tzta.ca
ጤናማ እንጀራ Healthy Choice ከገብስና ጤፍ የተዘጋጀ በጠይርቁን ጊዜ በይትም ሥፍራ ይሁኑ እናቀርባለን። 1764 Keele Street
Tel: 647-347-1764 Cell: 4160835-8082
ከገጽ 10 የዞረ
ቅዳሜ ዕለት ከነበረው ክስተት ቀደም ብሎ የጥቃቱ መሪ እንደሆኑ የተነገረላቸው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ምንም እንኳን በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚያደርጉት ንግግር ከሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት በተለየ አነጋጋሪ ጉዳዮችን አንደሚያነሱ የታወቀ ቢሆንም አለመግባባት እንዳለ በግልጽ የሚያሳዩ ነገሮች አልታዩም ነበር። •ጥቃቱ/የመንግሥት ግልበጣው ምን ውጤት ለማምጣት ያለመ ነበር? ጥቃቱ ወይም የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራው ቢሳካ ምን ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ግልጽ ያለ ነገር የለም። ቢሳካ የፌደራል መንግሥቱ በቦታው እያለ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ክልሉን ተቆጣጥረው አላማቸውን የማሳካት ዕድላቸው በጣም ጠባብ ነው። • የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? •በርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ውስጥ በጥቃቱ ወቅት ምን ተከሰተ? ጥቃቱ የተፈጸመው የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ በሚያደርጉበት ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ ስብሰባ ላይ በነበሩት የክልሉ አመራሮች ላይ ተኩስ ስለመክፈታቸውና ለግድያ ስለመምጣታቸው ከመነገሩ ወጪ የነበሩ ሁኔታዎችና ስለ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። •በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጸሙት ጥቃቶች አላቸው የተባለው ግንኙነትት ግልጽ ያለመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በጄነራሎቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ ባህር ዳር ውስጥ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር የሚያገናኘው ነገር እንዳለ በተደጋጋሚ የተገለጸ ቢሆንም በውጤት ረገድ የሁለቱ ክስተቶች ትስስርን በተመለከተ በግልጽ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
11
የተቀመጠ ማስረጃ አልተገኘም። • የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ለመዘከር የሃዘን ቀን ታወጀ •ከከፍተኛ ባለስልጣናትና ጄነራሎች ባሻገር ሌሎች የሞቱ ሰዎች ይኖሩ ይሆን? የተለያዩ ምንጮች በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች አምስት ብቻ ሳይሆኑ ቁጥሩ ከዚያ ከፍ እንደሚል እየተናገሩ ቢሆንም ይፋዊ የክልልና የማዕከላዊ መንግሥት ምንጮች ግን ያሉት ነገር የለም። •ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ስለተያዙ ሰዎች ጥቃቱ ተፈጽሞ የመከላከያ ሠራዊት በባህር ዳርና በዙሪያዋ ከተሰማራ በኋላ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው ጥቃት ጋር በተያያዘ በክልሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች የነበሩ ሰዎችና ሌሎችም እንደታሰሩ ይነገራል። ነገር ግን እስካሁን እነማንና ምን ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ የታወቀ ነገር የለም። •የጥቃቱ መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጉዳይ? የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ብርጋዴረ ጄነራል አሳምነው ፅጌ "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው" መሪ እንደሆኑ ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ ተነግሯል። ነገር ግን ጄነራሉ ይህንን ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉት ከነማን ጋር እንደሁነ፣ ክስተቱ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እንዴት እንዳመመለጡ፣ የት እንደሚገኙና አሁን ስላሉበት ሁኔታ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። ሰኞ ከሰዓት በኋላ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ባህር ዳር አቅራቢያ በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው መገደላቸው ታውቋል። ምንጭ፡ ቢቢሲ አማርኛ
https:www.tzta.ca
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር ስርዎ-መንስዔ፤ ህገመንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ (ዶ/ር አበራ ቱጂ) በመሆን ኢትዮጵያን በጎሳ የሚከፋፍለዉን ህገ መንግስትና የጎሳ አከላለል አዉጥተው የአገሪቱ መታዳደሪያ አደረጉ። በዚህም መሰረት ለሃያ ሰባት ዓመታት በአገሪቱ ዉስጥ ጥላቻ ተነዛ።
ዶ/ር አበራ ቱጂ ሚያዚያ 28፤ 2011 ዓ፣ ም ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በኢትዮጵያ የተስፋ ጎህ ቀዶ ነበር። ነግር ግን በጎሳ መካከል የሚፈጠረው ችግር የአገሪቱን ዜጎች በእጂጉ እያሳስበ…
ዶ/ር አበራ ቱጂ ሚያዚያ 28፤ 2011 ዓ፣ ም
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በኢትዮጵያ የተስፋ ጎህ ቀዶ ነበር። ነግር ግን በጎሳ መካከል የሚፈጠረው ችግር የአገሪቱን ዜጎች በእጂጉ እያሳስበ ነዉ። በአገሪቱ በጎሳ ክልል መካከል እየተፈጠረ ያለው ችግር ሁሉንም የአገራችንን ክፍል እያዳራሰ ነው። በኢትዮጵያ ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በአገሩ ውስጥ መፈናቀሉን መንግስት ገልጿል። ህዝቡ በራሱ አገር በኢትዮጵያ ውስጥ ስደተኛ ሆኗል። በዚህ ግጭት ብዙ ኢትዮጵያዊያን በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ብዙዎች የመከራ ኑሮ እየገፋ ነው። ንጹህ ዜጋ በህዝብ ተከቦ በቪድዮ እየተቀረጸ ሲገደልና ተዘቅዝቆ ሲሰቀል እስከማየት ደርሰናል። ለጋ ወጣት ልጅ ተሰልቧል። የዉጭ ዜጎች ሳይቀር ተገድለዉ ከነመኪናቸዉ ተቃጥለዋል። ብዙ ብዙ ተሰምቶ የማታወቅ ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመ ነዉ። ዛሬ ወያኔዎች በስልጣን ላይ ባይሆኑም የተከሉት ከፋፋይና አገር አጥፊ ስርዓት ግን መራራ ፍሬ እያፈራ ነዉ። ባጭሩ የጎሳ ፖለቲካ ንጹህ ዜጎችን እየበላ እያደገ እየተስፋፋና አገር እያፈርሰ ነው። የዚህ የአገራችን ችግር ስረ-መሰረቱ ህውሃትኢህአዴግ በኢትዮጵያ ላይ የፈጠረው፣ ሆን ተብሎ የተተከለ፣ ስርዓታዊና ህገ መንግሥታዊ መሰረት ያለዉ፣ የጎሳ ወይም የዘር መድሎ ፖሊሲ ነው። ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ አዘቅት የምትወጣዉ ይህን የጎሳ ፖለቲካና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ከፋፍይና አድሏዊና አግላይ አከላለል አስወግዳ፣ በምትኩም የዜግነት ፖለቲካና ሁሉንም ዜጎች፣ በየትኛዉም የአገሪቱ ክፍል በዕኩልነት የሚዳኙበት የህግ የበላይነት ስትመሰርትና በተግባር ስታዉል ብቻ ነው። የጎሳ አደረጃጀት በኢትዮጵያ ያመጣዉ ቀዉስ በተግባርና በተጨባጭ ስለታየ መፍትሄው ይህን የችግሩን ምንጭ ማስወገድ ነዉ።
በአለማችን የመጨረሻ ድሃ ከሚባሉት አገሮች መካካል ያለችዉ ኢትዮጵያ፣ በሰላምና በአንድናቷ እንድትኖር፣ ብዙ ጊዜ በማይሰጠዉና ቀስፎ ከያዛት ድህነትና ድንቁርና ላይ ታተኩርና ከመቶ ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎቿን መመገብ ትችል ዘንድ፣ ይህን የጎሳ ፖለቲካና ግጭት ከስር መሰረቱ ማስወገድ ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አስተዳደርና ለኢትዮጵያ ህዝብ የመጀመሪያዉ ዋና ተግባር ሊሆን ይገባል። አገሪቱ በአንድነቷ እንድትቀጠልና የህዝብ ዕርስ በዕርስ ጦርነት እንዳይነሳ፣ በሩዋንዳ ያየነዉ እልቂት በኢትዮጵያ እንዳይደገም፣ ከዚህ የበለጠ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ የለም። በዶ/ር ዐቢይ የሚመራዉ የለዉጥ ሃይልም፣ በቅርብ ጊዜ ታሪክ ባልታየ ደረጃ፣ ከፍተኛ የህዝብ ተቀባይነትና ተወዳጅነት ስላለዉ፣ ይህንም የጎሳ ፖለቲካ ለማስወገድ ግንባር ቀደም ሚና ሊኖረዉ ይገባል። ይህንም ለማድረግ የኢትዮጵያ የህዝብ ድጋፍ ሊሰጠዉ ይገባል። ይህ የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን የመኖር ወይም የሞት ጥያቄ ነው። በአንድ ወቅት የተባይ ማጥፊያ ነዉ፣ ለችግርም መፍትሄ ነው ተብሎ በመንግስት መመሪያ የተረጨ ኬሚካል ምድሩንና አየሩን ከመረዘዉ፣ ዉሃዉን ከበከለው፣ ጠቃሚ ተክሎችን የሚያጠፋ ከሆነ፣ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? መጀመሪያ መደረግ ያለበት፣ ይህን መርዘኛ ኬሚካል በጥቅም ላይ እንዳይዉል በአዋጅ ወይንም በህግ ማገድ ነው። ቀጥሎ መደረግ ያለበት፣ ምንም እንኳ ስራዉ አዳጋች ቢሆንም፣ ጤናማ አገርና ህዝብ እንዲኖር ሲባል፣ የተበከለዉን አካባቢ በተለያዩ በተፈተኑ ዘዴወች ማጽዳትና አካባቢዉን ወደ ጤናማ ይዞታዉ መመለስ ነው። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለም፣ ምክንያቱም ምድራችን አንድ ብቻ ናትና። ኢትዮጵያም አንድ ናት ተለዋጭ አገር የለንም። የአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ በዚህ ይመሰላል። ህዉሃት ወደስልጣን ሲወጣ፣ ከኦነግ ጋር
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
12
በአሜሪካ ፎርቹን 500 ተብለዉ ከሚታውቁት ኢኮኖሚዉን ከሚመሩት ታላላቆቹ ድርጂቶች፣ ወደ ግማሽ የሚጠጉት የተመሰረቱት ከዉጭ በመጡ ሰዎች ወይንም በእነርሱ ልጆች ነው። አገሩ ፈጠራንና ስራን እንጂ ጎሳን ወይንም የመጡበትን አገር ባለማየቱ ነዉ ሃያል ሆኖ የቀጠለዉ። ጎሳን ሳያዩ ከሁልም አገር የመጣን የለማ የሰዉ ሃይል የጠቀማሉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን ዜጎች ከአንድ ክልል ሄደዉ በሌላ ክልል እንዳይሰሩ ተደረገ። ኢትዮጵያዊያን በተሰደዱባቸዉና ወላጆቻቸዉ ባልገነቧቸዉ ምዕራባዊያን አገሮች ለፖለቲካ ስልጣን በሚወዳደሩበት ዘመን፣ የአንድ ጥቁር ኬኒያዊ ልጅ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ሲሆን አይተን፣ ኢትዮጵያዊያን ግን በአገራቸዉ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የመሥራት ተፈጥሯዊ መብታቸው ተነፈገ። ዕዉቀትና ክህሎት በጎሳ ተተካ። ከወሊሶ ሂዶ ወልቂጤ ወይንም ከወልቂጤ ሂዶ ወሊሶ ስራ ማግኘት ጭራሽ የማይታሰብ ሆነ፡፡ ኢትዮጵያ አሳፋሪ ምድር ሆነች። ክፍፍሉ በሁሉም ዘርፍ ሆኖ በቤተሰብ ደረጃ ደረሰ። የባህልን ትሥሥር በማወቅ ከሌላ አካባቢ ከመጡ ወገኖቻቸው ጋር ለመተዋወቅ ሊረዱ የሚገባቸዉ የከፍተኛ ትምርት ቤቶች ሳይቀር የጎሳ ክፍፍል ማሰልጠኛና የጠብና የክክክል ሜዳዎች ሆኑ። የተማሪዎች ማደሪያ አመዳደብና፣ የተማሪዎች ማህበር አደረጃጀት ሳይቅር በጎሳ የተከፋፈለ ሆነ። በሁሉም ነገር ጎሰኝነት ሰረጸ ተስፋፋ። የመንግስት ሰራተኞች በተወለዱበት አካባቢ እንዲወሰኑ ተደረገ፤ ራቅ ካለ ቦታ የመጡት እንዲባረሩ ተደረገ። ይህም የሃሳብ ብዝሃነት እንዳይኖርና፣ አዲስና የተሻለ ሃሳብ በስራ ላይ እንዳይዉል አደረገ። ዜጎች ከሌላዉ የአገሪቱ ክፍል ከመጣዉ ወገናቸዉ ጋር እንዳይተዋወቁ ሆን ተብሎ መጋረጃ ተደረገባቸዉ። የኢሃዲግ መንግስትም ዋናዉ ስራ ህዝብን በጎሳ መለያየትና ማጠር ሆነ። በተጨማሪም ዜጎች የተለየና አማራጭ ሃስብ ማመንጨት እንዳይችሉ የሚያደነዝዝ የህዉሃት ፖለቲካ ሰበካ ተደረገባቸው። ዜጎች ዕውነተኛ መረጃ አያገኙም፣ የተነገራቸውን ብቻ መቀበልና የታዘዙትን መከተል ባህላቸው እንዲሆን ተደረገ። አዲስ በሬ ወለደ ታሪክ በመፍጠር፣ አንዱ በሌላው ላይ ጥላቻና ጥርጣሬ እንዲኖረው ተደረገ። ለዚህ የትግራዩን የመምህር ገበረኪዳን ደስታንና የተስፋየ ገብረአብን ታሪክ ትንተና ማየት ይበቃል። ይህም አሁን ላለንበት ዕርስ በዕርስ መበላላት አደረሰን።
በአጭሩ ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት በማለት እንቅስቃሴያቸውን የጀመሩት የስድሳወቹ የተማሪ ፖለቲከኞችና ህዉሃት፣ የአሁኗን ኢትዮጵያ ጎሳዎች በየጉሪያቸው ተከፋፍለው የታሰሩባት ወህኒ ቤት አደረጓት። አሁን በኢትዮጵያ የምናየው የጎሳ ግጭት የዚህ የኢሃዲግ መንግሥት ህገ-መንግስታዊና ሥርዓታዊ (systemic) ከፋፋይ ስራ ውጤት ነዉ። በወያኔና ኦነግ በተደረገዉ የረጂም ጊዜ አዕምሮ አጠባ (brain wash) የተነሳ ወይንም በፍርሃት፣ ብዙዎች ይህን አፍጥጦ የመጣ ሃቅ መረዳት እየቸገራቸዉ ነው። ይህ አስከፊ የዜጎች ዕርስ በዕርስ መገዳደል መቆም አለበት። ብዙ ሰዉ በግልጽ ያልተገነዘበዉ ነገር ቢኖር፣ ህዉሃትና ኦነግ ይህን ስርዓት የፈጠሩት፣ ህዝቡን በጎሳ ከፋፍሎና ደካማ አሻንጉሊት የጎሳ መሪዎችን በማስቀመጥ፣ የአገሪቱን ሃብትና መሬት ለመዝረፍና ለመሸጥ መሆኑን ነው። ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቱ በተጨማሪ፣ በህይወት ለመኖር ስንል፣ ይህ የሚያጫርሰን የጎሳ ክፍፍል አስተዳደርና ፖለቲካ መቅረት አለበት። ለዚህም የሚከተሉት ዝርዝር አሳማኝ ምክንያቶች አሉ። በማናዉቀዉ ፅንሰ-ሃሳብ እየተጋደልን ነው፤ በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ብሔር ብሄረሰቦች ህዝብ የሚለው ፅንሰ-ሃሳብና ትርጉሙ በውል ተለይቶ አይታውቅም፡፡ ፅንሰ-ሃሳቡም ለኢትዮጵያ አግባብ የለውም፡ ፡ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች የሚለው ምን ለማለት እንደሆነ ለብዙው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ህግ አውጭ ነን ብለዉ ፓርላማ ዉስጥ የሚቀመጡት፣ ህግ አስፈጻሚ ነን የሚሉት ባለስልጣናት፣ የቃላቱን ወይንም ጽንሰ ሃሳቦቹን ትርጉም አያውቋቸውም። ስለዚህ ማነው ብሔር፣ ማነው ብሔረሰብ፣ ማነው ህዝብ የሚለው በትክክል አይታወቅም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን ትርጉማቸዉ ባልገባን ባዕድ ቃላት ዕርስ በዕርስ ተከፋፍለን እየተጋደልን ነው። ይህ በብሔር ብሔረሰብ ህዝብ የሚለው ከስታሊን ዘመን ፖለቲከኞች፣ አገራቸዉን በአግባቡ ያላወቁ በአስራ ዘጠኝ ስድሳዎቹ ወጣት የተማሪ ፖለቲከኞች የተኮረጀና ለእኛ አገር ፍፁም አግባብነት የሌለው ባዕድ ነገር ነው እያጋደለን ያለዉ። ያልነበረንና የማይኖርን ወሰን ለመፍጠር ሲባል ህዝብን ማጋደል፤ እነዚህ ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ ተብለው በቋንቋ የተከፋፈሉ ክልሎች መካከል የማያሻማና ግልፅ ወሰንና የመለያ መስመር ለማድረግ የማይቻል ነዉ። የጎሳ የሃሳብ መስመሩ ያለው በወያኔ-ኢሃዲግና ኦነግ ፖለቲከኞች አዕምሮ እንጂ፣ በህዝቡና በመሬት ላይ የለም። ይህን በወያኔዎች የቅዠት ምናብ ያለ የጎሳ የሃሳብ መስመር በህዝቡ ወስጥ ለማስመር ሲባል ህዝብ ወደማይቆም ብጥብጥና ጦርነት እየገባ ነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ክልል አልቆ የጉራጌ
ገጽ 13 ይመልከቱ
https:www.tzta.ca
ከገጽ 12 የዞረ
ዞን የሚጀምረው በትክክል ድንበሩ ወይንም መስመሩ የት ላይ ነው? በመካከል ሁለቱንም ቋንቋ የሚናገሩ የተሳሰሩ ዜጎች የሉም ወይ? በሱማሌና ኦሮሞ፣ በአማራና ትግሬ፣ እንዲሁም በሌሎችም መካካል ህዝቡን የጎሳ ፖለቲከኞች እንደፈለጉት መከፋፈል ባለመቻሉ ግጭቱ ይቅጥላል። የግጭቱ ምክንያት የማይለያይንና የተወሃደን ህዝብ ለመለያየት በሚደረግ ዋጋቢስ ትግል ነው። የትኛዉ ቦታ ወይም መሬት ነው ለማን የሚሰጠው፣ በምንስ መሰረት? በደም ወይም DNA ምርመራ ነው? በሚናገረው ቋንቋ ነው? በህዝብ ብዛት ነዉ? በታሪካዊ ይዞታ ነው? ያስ ከሆነ ወደኋላ እስከመቼ ያለዉን ታሪክ ነዉ የምናየዉ? ቦታዉ በተሰየመበት ቋንቋ ነው? ለምሳሌ አሁን የቅማንት ነዉ፣ የአማራ ነው እየተባሉ ሰዎች የሚሞቱባቸው ቀበሌዎች ጉባይ፣ ሌንጫ፣ መቃ ይባላሉ። በቦታ ስም ካየን ኦሮምኛ ይመስላሉ። የቦታ ስም የተሰየመበትን ቋንቋ ካየን አንዳንድ የኦሮሞ የጎሳ ፖለቲከኞች ቅኝ ገዥ ናቸዉ የሚሏቸዉ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አዲስ አበባን የቆረቆሩት፣ የኦሮሞዉ የራስ ጉግሳ የልጅ ልጅ ልጅ ሲሆኑ፣ ባለቤታቸዉ አጼ ሚኒሊክ ከጣያሊያኖች ጋር ታሪካዊዉን ዉለታ የተፈራረሙበት ቦታ ደግሞ ከጢጣ አልፎ መርሳ ሳንደርስ ዉጫሌ ላይ ነዉ። ትንሽ ኦሮምኛ ለሚችል ሰዉ እንዲህ ያሉ የቦታ ስሞች በተለያዩ በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች መኖራቸዉን ሲሰማ፣ ምንም እንኳ ታሪክ ባያዉቅ፣ እንዴት ነዉ የነመለስን “የመቶ ዓመትን ታሪክ” ተብሎ
የተነገረዉን ተቀብሎ የሚነዳዉ? በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የኦሮም ብቻ ናት ሌላው መጤ ወይም ሰፋሪ ነው የሚሉት ጎሰኖች በ1450 አካባቢ በዚያዉ በአዲስ አበባ አካባቢ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ከተማ እንደነበር ያለዉን የአርኪዮሎጂ መረጃ ማየት አይፈልጉም። የጎሳ ፖለቲከኞች ይህን ትሥሥራችንን የሚያሳየዉን ሃቅ ግን መመርመርና ማጥናት አይፈልጉም። የተነገራቸዉን “የመቶ ዓመት ታሪክ” ይዘዉ ያላዝናሉ እንጂ። ይህንም ጎሰኝነት የእለት እንጀራቸው አድርገዉታል፡፡ ሁሉም የጎሳ ፖለቲከኞች አንድ ትልቁንና የሚያግባባቸዉን ካርታ በመያዝ፣ ታላቋን ኢትዮጵያን የራሳቸዉ በማድረግ ፋንታ፣ የግላቸዉን ትንንሽን የሚያጋጩ ካርታዎችን በኪሳቸዉ ይዘዉ ንግስናቸዉን እየጠበቁ ነው። ግጭቱ በቋንቋ ተለያይቶ ብቻ ሳይሆን በመንደርም እየሆነና መከፋፈሉ የማይቆም ነው። በደቡብ አካባቢ የማይቆም የሚመስል የክልል፣ የወረዳና የራስ አስተዳደር ጥያቄ እየተነሳ ነዉ። ምንድን ነዉ መመዘኛዉ? ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ መሞከሪያ ቤተሙከራ (laboratory) ሆናለች። በድንቁርና ሙከራዉን በሚያካሂዱ “ተመራማሪወች” የቤተ-ሙከራዉ መሳሪያወችና እቃዎች እየተቃጣጠሉ ነው። አሁን የምንፈራዉ አጠቃላይ ቤተ ሙከራው እንዳይቃጠልና እንዳይወድም ነዉ። በዚህ በክልል ድንበር የተነሳ እስከአሁን በአሰቃቂ ሁኔታ ያለቁት ወገኖቻችን፣ የተፈናቀሉት ዜጎች በቂ ትምህርት አይሰጠንሞይ? መቼ ነዉ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
13
የራሳችን ጉዶች የፈጠሩት መከራ የሚበቃን? ኢትዮጵያዊያን ምን አደነዘዘን? ቀኑ እየጨለመብን ይመስላል፡፡ አንድ ክልል ለተወሰኑ የህብረተሰብ አካል ሲሰጥ፣ በሌላ አባባል ሌላው የህብረተሰብ ክፍል የዚያ አካል አይደለም ወይንም ባዕድ ነዉ ማለት ነው። ይህም “የኔ የብቻዬ ነው” ለማለት ነዉ። የአማራ ክልል ለአማራ ነው ማለት፣ በሌላ አባባል፣ የትግሬው አይደለም፣ የኦሮሞው አይደለም፣ የጉራጌው አይደለም ማለት ነዉ። ስለዚህ አከላለሉ፣ የአንተ ነው ተብሎ ለአንድ ጎሳ ሲሰጥ፣ ሌላውን በዚህ ቦታ አያገባህም፣ ይህ አካባቢ የኔ እንጂ የአንተ አይደለም ማለት ሲሆን፣ ህገመንግስታዊ የሆነ ፍፁም አግላይ የሆነ፡ አሰራር ነው። በየትም አለም የራሱን ዜጎቹን እንዲህ የሚያገልና የሚከፋፍልና የሚያጋድል ህግ የለም። ለምሳሌ በህንድ በማንነት ፖለቲካ አደረጃጅት አገር አፍራሽ መሆኑን የተረዳው የህንድ የመጨረሻዉ ፍርድ ቤት፣ የማንነት ፖለቲካ እንቅስቃሴ ህገ ወጥ እንደሆነ በይኗል፣ አግዷል። የጎሳ አከላለል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የዉጭ ጠላት ቢመጣበት እንኳ ተግባብቶና ተባብሮ አገሩን መከላከል እንዳይችልና፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተሸረበ ስልታዊ (strategic) ደባ ነው። ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚመኙ የዉጭ ጠላቶችም እንዳሉን አንዘንጋ፡፡ አንዳንዶች የአረብኛ ቴቪዥን ፕሮግራም ከፍተዉ ለአይዞህ ባዮቻቸው እለታዊ ስራቸዉን በዘገባ ሲያቀርቡ እንደነበረ አይተናል፡፡
የቡድን ጥያቄ የዜጋን መብት በማክበር ይፈታል። የጎሳ ፖለቲካ፣ ግለሰቦች የሃሳብ የበላይነት ማግኘት ሲያቅታቸው፣ ወደ ስልጣን ለመዉጣት የሚጠቀሙበት አቋራጭ መንገድ ነው። የግለሰብ መሰርታዊ መብቱ ከተከበረ፣ ያማይከበር የቡድን መብት የለም። በየትኛዉም የአገሪቱ ክፍሎች፣ በክልል ወይም ጎሳ ሳይወሰን፣ ዜጎች በአፍ መፍቻ በቋንቋቸው መማር፣ በቋንቋቸው መጠቀም፣ መዳኘት፣ የመስራት፣ ሃብት የማፍራት፣ መሪያቸዉን የመመረጥ፣ ሃሳብቸዉን የመግለጽና የመደራጀት መብታቸው ያለምንም ገደብ ሊከበርላቸው ይገባል። ይህን ለማደረግ የግድ የጎሳ አደረጃጀት ወይም የጎሳ ክልል አያስፈልግም። ለአንዱ መብት ለመታገል፣ የዚያ ሰዉ ጎሳ አባል መሆን የግድ አያስፈልግም፣ ዜጋ ወይንም ምክናያታዊ ሰዉ መሆን ብቻ ይበቃል። ጎንደር ዉስጥ ያለ አንድ ኦሮምኛ ተናገሪ፣ የምችለው ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ ነዉ፣ በኦሮምኛ ልዳኝ ይገባኛል ካለ፣ አስተርጓሚ ሊመደብለት ይገባል። ይህን ለማደረግ የግድ የጎሳ ክልል አያስፈልግም። ይህ በየትኛዉም የአገራችን ክፍል የዜጎች ሁሉ መብት ሊሆን ይገባል። በጎሳ ግጭት የማይነካና የማይጎዳ ክልል ወይንም የህበረተሰብ ክፍል አይኖርም። ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ያየነው ይህን ነዉ። የጎሳ ፖለቲካ መሃንዲስ ነን የሚሉት ግለሰቦች፣ ሌላዉ መጤ፣ ሰፋሪ፣
ገጽ 14 ይመልከቱ
https:www.tzta.ca
ከገጽ 14 የዞረ ቤት የለሽ፣ ነዉ እናባርረዋለን፣ የሚሉት ሳይቀሩ ራሳቸዉ ባጠመዱት ወጥመድ እየገቡ ነው። ኦሮሞ ከሶማሊ፣ጉጂ ከጌዶ፣ ቤኒሻንጉ ከኦሮም፣ ኦሮሞ ከአማራ፣ ሲዳማ ከወላይታ፣ አማራ ከቅማንት፣ አማራ ከትግሬ፣ አማራ ከቤኒሻንጉል ብዙ ቦታ ማቆሚያው የማይታወቅ ግጭት ተነስቷል። ይህ ችግር ወደ እኔ አይመጣም ብሎ ተዝናንቶ የሚቀመጥ የህብረተሰብ ክፍል የለም። በዚህ ከቀጠለ የጊዜ ጉዳይ ሆኖ እንጂ እሳቱ ሁሉንም ያዳርሳል። አንድ ቀን ደግሞ ከቁጥጥር ዉጭ ሊወጣ ይችላል። ስለዚህ ይህ ሁኔታ አንዱ ወገን አባራሪ ሆኖ ሌላው ተባራሪ፣ አንዱ የራሱን አገር ሲመሰርት ሌላዉ አገር የሚፈርስበት ክስተት አይደለም፣ የዕርስ በዕርስ መተላላቅ እንጅ። ማንም አይተርፍም። አንዱ ወገን ሲጠቃ ሌላዉም አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ራሱን ያዘጋጃል፣ በምላሹም ጥፋት ያደርሳል። እየገደለ ይሞታል። በነሩዋንዳ፣ የመን፣ ሶሪያ የደረሰው እልቂት በኛ ላይ ካልደረሰ አንማርም ብሎ እልቂትን መጋበዝ ከድንቁርናም አልፎ ደደብነት ነው። በጎሳ ስም ማጥፋትና ማጥቃት እንጂ ተጠያቂ ጎሳ አይኖርም። ጎሳ ሰው አይደለም “አብስትራክት” ሃሳብ እንጂ፡፡ በጎሳ ፖለቲካ መሪወች በጎሳ ስም በግለሰብ ላይ ጥፋት ይፈጸማሉ እንጂ ተጠያቂ የሚሆን ወይንም ሃላፊነት የሚወስድ ጎሳ ወይም ቡድን ግን አይኖርም፣ ሊኖርም አይገባም። የጎሳ ፖለቲካ በህግ አግባብ በማይጠየቅ ቡድን ስም፣ ግለሰቦች ወንጀል የሚፈጽሙበት አሰራር ነዉ። ግለሰቦች በቡድን ስም ያለህጋዊ ዉክልና ሃይል የሚያገኙበት ነገር ግን ጥፋቱን በህግ ወደማይጠየቅ ጎሳ የሚያላክኩበት፣ በጥፋታቸዉም ሲጠየቁም ጎሳችን ወደሚሉት ቡድን ሂደዉ የሚደበቁበት ሀገወጥነትና በጥላቻ የተነሳ ወንጀለኝነት ነዉ። የጎሳ አከላለሉ፣ አሁን እንዳለ እንዲቀጥል ቢደረግ እንኳ፣ አገሪቱን ወደ ኢኮኖሚያዊ አዘቅጠት ከዚያም ወደ ማህበራዊ ቀውስ ይወስዳታል። በየትም አገር ለዕድገት አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ነገሮች አሉ። አንዱና የመጀመሪያው የህግ የበላይነት ነው። ሌላው የንብረት ባለቤትነት መብት ሲሆን፣ ስራን፣ ችሎታን፣ ፈጠራንና፣ ተወዳዳሪነትንና የሚያበረታታ ነጻ ገበያ ነው። ይህም የሰዉን ሃብት በነጻነት ማንቀሳቀስን መሰረት ያደረግ ነዉ። እዲሁም እነዚህን በስርዓትና በህግ የሚያስከበር ህጋዊ ተቋማት ሊኖሩ ይገባል። ማንም አካባቢ ሆነ ግለሰብ በራሱ ብቻ ምሉዕ እይደለም። አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን። ነገር ግን ማንም ቢሆን ያለውን ሀብትና ዕዉቀት አውጥቶ ወይንም ሙያውን ተጠቅሞና ተቀናጅቶ ለመሥራት የህይወትና የንብረት ዋስትና ያስፈልገዋል። በአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሰዎች ህጻናት ሳይቀሩ ካደጉበት አካባቢ በግፍ እየተባረሩና እየተገደሉ፣ ምን አይነት ሰዉ ነው ህይወቱን ለአደጋ እየሰጠ በዘላቂነት አገርን አልምቶ ራሱንም የሚጠቅመው? ከምንም በላይ ከግዚአብሄር ቀጥሎ ሃይል ያለውን የሰው አዕምሮ በትምህርት አልምቶና እንደተፈላጊነቱ
አዘዋዉሮ መጠቅም ካልተቻለ፣ ከድህነት መዉጣት አይቻልም። አደጉ የሚባሉት የአለማችን አገሮች እዚህ የደረሱት በቆዳ ስፋታቸው አይደለም፣ በተፈጥሮ ሃብታቸዉም አይደለም፣ የሰው ሃብታቸዉን አስተምረዉና አልምተው ይበልጥ ምርታማና ዉጤታማ በሚሆነብት ቦታ አሰማርተዉ፣ ያለዉን የማምረትና የመፍጠር ችሎታ በመጠቀማቸዉ እንጂ። የምጣኔ ሃብት እድገት ምንጩና ቁልፉ የሰዉ ልጅ አዕምሮ ነው። ትርጉም ያለዉ የኢኮኖሚ ለውጥ ያመጣዉ ፈጠራ innovation ነዉ። ለዚህም አሜርካንን፣ ጀርመንን፣ ጃፓንንና ቻይናን የመሳሰሉትን አገሮች ማየት ይበቃል። ጎሰኝነት አሳፋሪ ድንቁርና ነው። አገር አያሳድግም። ዜጎች ለዓመታት ለፍተው ላባቸዉን አንጠፍጥፈው ያፈሩትን ንብረት በሚቀሙበት አገር፣ ንብረታቸው በጎሰኞች በሚቃጠልበት አገር፣ የውጭ አገር ባለሃብት ቀርቶ፣ ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ሀብት ወደ ዉጭ ያሸሹ እንደሁ እንጂ በልማት ላይ አያውሉትም። ምንም እንኳ እንድ አንዶች ቢኖሩም፣ ያገኙትን የተፈጥሮ ሃብት አራቁተውና በክለዉ፣ የኢትዮጵያን ባንኮች ዕዳ ላይ ጥለው፣ ዘርፈው ለመውጣት ካልሆነ፣ በአገሪቱ ሰላም ተማምነው ያላቸዉን ሃብት አፍስሠዉ ዘላቂ ልማት አያመጡም። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሰዉን ልጅ ስራ እየተሻማ ባለበት ዘመን፣ በተራ ጉልበት ስራ ላይ በሚመሰረቱ ጥቂት የቻይና ፋብሪካዎችም ላይ መተማመንም አይቻልም። በቴክኖልጂ (robotics, 3D printing, artificial inteligence) ምርታማነታቸዉን ሲያሳድጉና በጥቂት ሰዎች ብቻ ማምረት ሲችሉ፣ ስራዉን ወደ አገራቸዉ ይመልሱታልና። ወይም የተሻለ ሰላም ወደ አለበት አገር ያዞሩታል። በህዝብ ልማትና ምርታማነት ላይ ያልተመረኮዘ ዕድገት ዘላቂነት የለዉም፡፡ በጎሳ ግጭት የሚንገራገጭ ኢኮኖሚ ዛላቂ እድገት አያመጣም። ወያኔ የፈጠረዉ የጎሳ ሥርዓት፣ ሰው በችሎታውና ዕውቀቱ ወይም የሥራ አፈፃፀሙ የሚለካበት ሳይሆን በጎሳ ፖለቲካ ታማኝነቱ ወይም በገዛዉ ሰርቲፊኬት ነዉ። ይህም ወጣቱን በአቋራጭ ሀገወጥ ሃብት ፈላጊ እንጂ የዕዉቀት ፍላጎት እንዳይኖረው አድርጓል፡፡ በማጭበርበር ላይ የተመረኮዛ ኢኮኖሚ የትም አያደርስም። አንዲት አዋሳ ተወልዳ ያደገች ወጣት የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን አጠናቃ ሥራ እያፈለገች ያጋጠማትን የገለፀችው ልብ የሚነካ ነበር። አንድ አጎቷን ይህን ጠየቀቸው። አጎቴ፣ እኛ ምንድን ነን? አጎቷም ምን ማለትሽ ነው ይላታል፡ እሷም “ዘራችን” ምንድን ነው? አለች፣ አጎቷም በመገረም “ዘሯ” የተቀላቀለ መሆኑንና በቀላሉ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን አብራራላት። እሷ ግን ሥራ ለማግኘት ዘር ይመረጣል። የተወለድኩት እዚህ፡ ነው። ነገር ግን አንቺ የዚህ ክልል ዘር አይደለሽም እያሉ ስራ ሊቀጥሩኝ አልቻሉም ብላ ወጣቷ በሃዘን ተናገረች። ከአገራችን በድህነት ወደኋላ ከመቅረት በተጨማሪ፡ ህውሃቶች ህዝቡን በጎሳ ከፋፍለው በፈጠሩት ስርዓት ሰው የሙያ ችሎተው ሳይሆን ጎሳዉ ታይቶ ሥራ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
14
የሚቀጠርበት ድንቁርና የሚበረታታበት አገር ሁኗል። በዚህ ሁኔታ ያደገ ወጣት ለአገሩ ምን አይነት በጎ አመለካከት ሊኖረዉ ይችላል? አገራችን ያላትን የሰው ሃይል ማልማት እትችልም። ያላትንም የለማ ህዝብ በሚያስፈልግበት ቦታ መጠቀም አልቻለችም። ወደ 105 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላትና 80 በመቶ ወጣት በሆነበት አገር፣ ወጣቱን በአግባቡ አስተምሮ በሥራ ማሰማራት ዋነኛ ጉዳይ መሆን ሲገባው፣ በጎሳ ፖለቲካ ላይ በማተኮረ ሰውን ሠርቶ እንዳይበላ ማድረግ በወገን ላይ የሚፈፀም ከባድ ወንጀል ነው። በአንድ አካባቢ ሰልጥነው የተቀመጡ ሥራ አጥ ወጣቶች ሲኖሩ በሌላ አካባቢ ደግሞ ያሉትን ባለሙያወች በጎሳቸዉ የተነሳ አባርሮ ህዝቡ ባለሙያ አጥቶ በችግር ይሰቃያል። ይህም የጎሳ ፖለቲካ ያመጠው ጣጣ ነው።አገራችን ካለባት አጠቃላይ ድህነት በከፋ የገጠሩ አካባቢ ከፍተኛ የተማረ የሰው ሃይል እጥረትና ችግር አለበት። በከተማዎች አካባቢ የተጠራቀመው የሰው ሃይልና ሃብት ራቅ ወዳለዉ የአገሪቱ ገጠር ክፍል ሄደ እንዳይሠራ፣ እንዳያለማ፣ የሰዉ ህይወት እንዳያድንና፣ አገሩንም እንዳያዉቅ፣ ይህ የጎሳ ክፍፍል መስናክል ሆኗል። በአገሪቱ ገበሬው ያመረተውን ምርት በማዕከላዊ ገበያ መሸጥ ባለመቻሉና የስርጭት ችግር በመኖሩ ነው በአገራችን የምግብ እህል እጥረት የሚፈጠረው ተብሎ፣ የገበያ ልውውጥ ማዕከል (የኢትዮጵያ ምርት ገበያ) ያቋቋመዉ መንግሥት፣ ለዕድገት ፍጹም አስፈላጊ የሆኑትን የተማሩ ወጣቶች ግን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነጻነት ሄደው መሥራት እንዳይችሉ አድርጓል። የጎሳ ፖለቲካና ግጭትና ዘረኛ ቅስቀሳ በህዝብ መካከል የሚይረሳ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል። ይህም ለወደፊት የአገሪቱን አንድነት አደጋ ላይ ይጥላል። የዘሬ ጥፋት የነገ ታሪካዊ ችግር ይሆናል። በአርባጉጉ፣ በደኖ፣ አጣየ፣ ጂጂጋ፣ ቡራዩ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጌድኦ፣ ጋምቤላ፣ አጣየና፣ ጎንደርና ሌሎችም አካባቢ ጎሳ ለይቶ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት በቪደኦና ፎቶግራፍ ተቀርጾ ታሪክ ይመዘግበዋል። መጪዉን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ልንማርበትና ላለመድገም ሁላችንም ሃላፊነት አለብን። ዘመኑ ከአንድ ክፍለ ዓለም ሌላው ክፍለ ዓለም መረጃ በቅፅበት የሚደርሰበት፣ የአገር አለማቀፍ ድንበሮች የሰውን እንቅስቃሴ የማይገድቡበት ዘመን ነው። የተፈጥሮ ሃብትም ቢሆን የልዩነትና የግጭት ምንጭ መሆን የለበትም። እያንዳንዱ አካባቢ የራሱ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት አለው። አንዱ ነዳጅ፡ ሲኖረው ሌላው እብነበረድ ሊኖረው ይችላል፣ አንዱ ደግሞ ለም የእርሻ መሬት ሊኖረው ይችላል፤ ሌላዉ ሲሚንቶን ማምረት የሚያስችል ሃብት ሲኖረዉ፣ ሌላዉ የዉሃ ሃብት ይኖረዋል። ስለዚህ ሁሉም ዋጋ አለው ሁሉም ለአገራችንና ለህዝባችን ያስፈልጋል። ዘመኑ በጎሳ ታጥሮ የምንኖርበት አይደለም። የሚያዋጣዉና ሃይል የሚኖረን የጎሳን አጥር አስወግደን ስንተባበርና ሁላችንም በችሎታችን ስናበረክት ነው።
ኢትዮጵያ የጎሳ መብት የግለሰብን ወይንም የዜጋን መብት ያጠፋባት አገር ሆናልች። ኢትዮጵያ ዜጋ የሌላት የጎሳ ስብስብ ተደርጋለች። በጎሳ ፖለቲካ ማንም በዘላቂነት አያተርፍም። ኢትዮጵያ አሁን ለገባችበት የፖለቲካ ችግር ዋናዉ መንሰዔ የጎሳ ፖለቲካ ነዉ። በየከተማዉ የዚህ ብሄርና የዛ ብሄር እርቅ እያሉ በባለስልጣናት በቴሌቪዥን ለመታየት ሲባል ገንዘብ ማበከኑ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። ችግሩ ከስሩ ይነቀል። ዶ/ር ዐብይ ከጎሳ ፖለቲካ ድርጅት መሪነታቸው ከፍ ብለው የአጣቃላይ ኢትዮጵያ መሪነታቸዉን በተግባር ሊያሳዩን ይገባል። ስለዚህ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግስት ተቀዳሚ ስራ ይህን የችግሩ ምንጭ የሆነዉን የጎሳ አደረጃጀትና ፖለቲካ በህግ ማገድና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያለአድሎ የሚያስተናግድ የዜግነት ፖለቲካን በህግ ማስፈን ነው። ከዚህም በላይ ቅድሚያ የሚያሻ ጉዳይ የለም። ዶ/ር ዐብይ ይህን ካላደረጉና ለዉጡን ካልመሩ ለሚደርሰዉ ጉዳት ከተቀዳሚ ተጠያቂነት አያመልጡም። ይህንም ማድረግ ይቻል ዘንድ ኢትዮጵያዊያን ረጋ ብለንና ምክንያታዊ፣ ገንቢና ሰላማዊ ወይይት በማድረግ፣ ችግሩ ምን አመጣዉ የሚለዉን ከስር መሰረቱ በመመርመር፣ ካለፈዉ ስህተት በመማር፣ የወደፊት አቅጣጫችንን ራሳችን መንደፍ አለብን። ሁሉ ነገር እያለን ሚሊዮኖች በሚራቡባት አገራችን፣ ሰዉ ቅድሚያ ሰጥቶ በጎሳ የተነሳ ሲጋደል ከማየት የበለጠ ለኢትዮጵያዊያን አሳፋሪ ነገር የለም። አገራችን እየፈረሰች ሃላፊነቱን ለተወሰኑ የጎሳ መሪወች መተዉ የለብንም። ሁላችንም እኩል ሃላፊነት አለብን። የኢትዮጵያ ምሁራን ፈረንጆች ከጻፉት የመማሪያ መጽሃፍ ዕዉቀት (textbook knowledge) በዘለለ፣ የአብዛኛዉን የአገራችንን ህዝብ ኑሮና ችግር ከተለያየ የዉቀት ዘርፍ ቀርቦ በማጥናት ለአገራችን ሁኔታ የሚስማማ አገር በቀል የመፍትሄ ሃሳብ ሊያቀርቡ ይገባል። የኢትዮጵያ ህግ አዉጭወች፣ አገሪቱን ወደዚህ ደረጃ ያደረሱትን ከፋፍይና አግላይ ህጎች በማስወገድ፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የትም የአገሪቱ ክፍል በነጻነትና በሰላም የሚኖርበት ህግ ሊያወጡ ይገባል። የሃይማኖት መሪዎች እባካችሁ እዉነቱን ተናገሩ። እንዲዚሁም የኢትዮጵያ ጦር ሃይል፣ የአገሪቱን ዳር ድንበርና የአገር አንድነትና የአገር ዉስጥ ሰላም ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን አዉቆ፣ የተጣለበት አገራዊ ሃላፊነት በንቃት ሊወጣና ኢትዮጵያን ሊጠብቅ ይገባል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ መሪወችና ባለድርሻወች፣የአገሪቱን ስልታዊ (strategic) ጥቅም፣ ለጊዚያዊና የአጭር ጊዜ የፖለቲካ ድል መስዋዕት ሳያደርጉ፣ የጎሳን ፖለቲካ በህግ በማገድ፣ ለዘላቂ ሰላምና ዕድገት መሰረት በሆነው የዜግነት መብትና ፖለቲካ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።__ ማስታወሻ በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ tztafirst@gmail.com ይላኩልን።
https:www.tzta.ca
ወይ የኢሣት ነገር! ጊዜ ደጉ ስንቱን ያሳያል? (ግርማ በላይ)
ግርማ በላይ ግንቦት 26 2011 ዓ.ም.
“ተማምለን ነበር እንዳናንቀላፋ፤ ተኝተሸ ተገኘሽ መተማመን ጠፋ፡፡” ብሎ የገጠመው ጎረምሣ እውነት ብሏል፡፡ በኢሣት ዙሪያ ሰሞኑን የሚወራው ደስ አይልም፡ ፡ በመልካም ጓደኛሞች መካከል መጥፎ መንፈስ የገባ ይመስላል፡፡ በኢሣት መንደር የተነሣው አቧራና ጭስ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ጠቡ አደባባይ እየወጣ ነው፡፡ የጠቡ መንስዔም ኢትዮጵያን በአዲስ መልክ ሰንጎ የያዛት የዘረኝነት አገዛዝና እርሱን እንደግፍ አንደግፍ በሚሉ ኃይሎች መካከል የፈለቀ ቁርቋሶ መሆኑ እየተነገረ ነው፡ ፡ ያም አለ ያም አለ በመጨረሻ እውነት ማሸነፏ አይቀርም፡፡ በጎመን የደለሉት ሆድ ጉልበት ሆኖ አቀበት ሲያወጣ፣ መጣ የተባለው የይስሙላ ዴሞክራሲም ሕዝብን አዋህዶ ሀገር ስትለማ በቅርቡ ልናይ ነው፡፡ የአጋሰሶች ዘመን ሊያልቅ ሲል፣ የከሃዲዎች አበቅቴ ሊጠናቀቅ ዳር ዳር ሲል፤ የሌሊት ወፎች የጨለማ ዘመን ሊያበቃ ጎህ ሲቀድ ምልክቱ ብዙ ነው፡፡ እንዲህ ብዬ መግቢያየን ልጨረስ፡፡ ኢሣት መፍረስ አልነበረበትም፡፡ ያፈረሱት እነማንም ይሁኑ ትንሽ መታገስ ነበረባቸው፡ ፡ ሊያውም ለብዙ አሠርት ዓመታት በሚገባ በሠለጠኑበት ነጭ ውሸት በታጀበ ዲስኩር፡ ፡ ሀፍረትን ሸጠው የበሉ ናቸው፡፡ ከወያኔ የሚያንሱት አራት ኪሎን በግልጽ ባለመያዛቸው ብቻ ነው፡፡ የጅብ ችኩል ነው የሆኑት፡፡ በሀገራችን
የፈጠጠው እውነት አፍራሾቹ እንደሚሉት የሚያዝናና ሳይሆን ከሕወሓት ዘመንም የከፋ ቆፈናም መሆኑን ለመገንዘብ ከአዲሱ አገዛዝ ጋር በጥቅም ትስስርና በድውይ ዓላማ ቁርኝት አለመጠመድን ብቻ ይጠይቃል፡፡ የሁላችንም ትግል አንድን ጎሣ በሌላ ለመተካትና በኮፒ/ፔስት ዘረኝነትን ለማንገሥ ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነበር – ለጊዜው ምኞታችን ሁሉ በነበር ባይቀር፡፡ ይሁን ግዴለም፡፡ “በቅሎ ገመዷን በጠሰች” ቢሉ “ማሰሪያዋን አሳጠረች” እንዲሉ ነው፡፡ እንጂ ምድረ ዘረኛና እስስት ለማንም ቢያጎበድድ ነፃነት እንደራቀች ትቀራለች ማለት አይደለም፡፡ የኢሣት ምርጥ ጋዜጠኞች ከኢሣት መባረራቸው እውነት ከሆነ የሚባረሩበትን ምክንያት ለማወቅ ብዙ ምርምርን አይጠይቅም፡፡ ሊሆን የሚችለው አሽቃባጭነትና አጎብዳጅነት ነው፡፡ ሊሆን የሚችለው ድርጅታዊ ሽርሙጥና ነው፡፡ ለሀገርና ለሕዝብ ሲምሉና ሲገዘቱ የነበሩ አንጋፋ ዜጎችና እንደግል ንብረታቸው የሚቆጣጠሩት ድርጅታቸው ለአዲሶቹ አህዲዳዊ ወያኔዎች ካደሩ ወዲህ ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ናቸው፡ ፡ ሆድና ጥቅም ሰውን ስንትና ስንት ጊዜ እየሠራ እንደሚያበላሸውም በእግረ መንገድ እየተረዳን ነው፡፡ የት ይደርሳሉ ብለን በጉጉት እንጠብቃቸው የነበሩ ምሁራንና ለሀገር ተቆርቋሪ ይመስሉን የነበሩ ዜጎች ምናልባት በትግሉ መራዘም ምክንያት ተስፋ ከመቁረጥና ከመሰላቸት የተነሣ ሊሆን ይችላል ሃሳባቸውን በመቀየር ወደተግማማ አሠራር እየወረዱ ናቸው፡፡ በዚያ ላይ እነዚህ የመርገምት ፍሬዎች እጅግ በቀለኛና ሸፍጠኛ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
15
ናቸው፡፡ የሚጠሉትን ለመበቀል የሚጓዙት ርቀት ከፈጣሪያቸው ከወያኔ ቢብስ እንጂ አያንስም፡ ፡ ይህ የመበቃቀል አዙሪት አንድ ቦታ ላይ ካልተበጠሰ ይሄ ሰሞኑን በኢሣት ጋዜጠኞች ላይ የተፈጸመው ደባና ተንኮል በሌላ ሥፍራና ሁኔታ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ነገረ ሥራችን ከዝንጀሮ ቆንጆ የመምረጥ ሆነና ዐረፈው፡፡ በተቃዋሚውም ሆነ በመንግሥት ጎራዎች የሚታዩት ፊቶች ሁሉ አንድ የመሆናቸው ምሥጢርም የሀገራችን ፖለቲካ መረገሙንና ሊያንሠራራ አለመቻሉን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ክፉኛ ተረግማለች፡፡ ፖለቲከኛ እንዳይወጣላት በተለይ ትልቅ እርግማን አለባት፡፡ የሰው ዐይን መጥፎ ነው፡፡ እነዚያን መሰል ድንቅ ዜጎች የሰው ዐይን ገባቸውና ኦህዲድ ሥር ተነጥፈው ሲርመጠመጡ ማየት አንጀትን የሚበላ የዘመናችን ዘግናኝ አውነት ሊሆን ቻለ፡ ፡ የአንዳንድ ሰው መጨረሻ በርግጥም ያሳዝናል፡ ፡ ይህ በሌላ በኩል የሚያሳየው አነሳሳቸውም ላይ ግርታና ያላወቁት የግል ችግር የነበረባቸው መሆኑን ነው፡፡ ዕድሜ ሰጥቶኝ መጨረሻውን ብቻ ያሳየኝ፡፡ ወይ ሀገር! አገር ሲያረጅ ጃርት ማፍራቱ ለካንስ እውነት ነው፡፡ ወያኔ በአምሳሉ ቀፍቅፎ የተወልን ድርጅቶች የማያሳዩን ተዓምር ላይኖር ነው፡፡ በስመ አብ! አማራ ጠሎቹ እነዚህን መሰል የከንቱ ትውልድ አብነቶች አካሄዳቸው ባጭር ካልተቀጨ በሀገርም ሆነ በንጹሓን ዘጎች ላይ የሚያስከትሉት አደጋ ከፍተኛ ነው፡፡ ተሰሚነታቸውን፣ የሚችሉ ደግሞ ከግል ገንዘባቸውና ከሕዝብ የሚሰበስቡትን ሀብትና ጥሪት፣ በጥቅሉ መላ አቅማቸውን
በመጠቀም የሚያደርሱት ጉዳት አንዳንዴ ሊቀለበስ የማይችል ሊሆን ይችላልና መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ እልከኞች ናቸው፤ የደምና የሥልጣን አራራ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ለመግደልና ለማስገደል ወደኋላ አይሉም፡፡ ዕብሪተኞች ናቸው፡፡ ትምክህተኞችም ናቸው፡፡ በዝቅተኝነት ስሜት የሚሰቃዩ በመሆናቸው ሲንጠራሩ የሰማያትን ግንቦች ሊያፈርሱ ይደርሳሉ፡፡ ብዙዎቹ ሃይማኖት የሚባል ነገር አያውቁም – አላቸው የሚባሉትም ለማስመሰል እንጂ አስተምህሮውን በተግባር አያውሉትም፡፡ የበቀለኝነታቸውና የእልኻቸው መንስዔ ሞራላዊና ባህላዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ዕሤቶች ከውስጣቸው ተንጠፍጥፈው መውጣት ነው፡፡ ከነዚህ ጋር ጦርነት መግጠም ልፋት ነው፤ ከዶንኪሾቶች ጋር ገጥሞ ማን ሊያሸንፍ?ይህንንም ስል አይሸነፉም ለማለት አይደለም፡፡ እነሱን ለማንበርከክ በነሱ መንገድ መጓዝ አይገባም፡፡ ልዩ ዘዴ ያስፈልጋል፡፡ ዋናው ግን ጊዜ ነው፡፡ ጊዜ እንኩቶ ያደርጋቸዋል፤ ይጠራርጋቸዋልም፡፡ ዘረኝነት መጥፎ የአስተሳሰብ ልምሻ ነው፡፡ አንድ ሰው የፈለገውን ያህል ቢማርና ዶክተር ፕሮፌሰር ቢሆን በዚህ በሽታ አእምሮው ከተሽመደመደ ሌት ከቀን የሚያውጠነጥነው ጥፋትን እንጂ ልማትን አይሆንም፡፡ እነ አቶ ፀጋየ አራርሳንና መሰል የዚህ ደዌ ልክፍተኞችን በዋቢነት ማየት በቂ ነው፡፡ እየተሰቃዩ ያሉት በዚህ ደዌ ነው፡፡ የኢሣት ነገርም ከዚሁ ከሚጠነባ የዘረኝነት ሥነ ልቦናዊ በሽታ ጋር የተያያዘ መሆኑ አያጠራጥርም፡ ፡ አማራ ሲባል ከስም አጠራሩ ጀምሮ ደማቸውን
ገጽ 21 ይመልከቱ
https:www.tzta.ca
Five things to watch for as Trudeau meets Trump, congressional leaders in Washington
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
16
Trudeau meets Trump, congressional leaders in Washington the Democrats would ultimately MIKE BLANCHFIELD back the deal, and made a point WASHINGTON to highlight Trudeau’s meetTHE CANADIAN PRESS ing with her after their confab, PUBLISHED JUNE 20, 2019 Prime Minister Justin Trudeau calling it “a terrific thing.” We spent Thursday in Washington, likely won’t know for weeks meeting with U.S. President how successful Trudeau was in Donald Trump at the White persuading Pelosi. One test will House and getting face time be whether the matter moves with the top Democrat on Cap- through Congress before the itol Hill, House of Represen- end of July, when it adjourns tatives Speaker Nancy Pelosi. for the summer. Trudeau sigHere are five things to take nalled at the end of the day that reopening the deal to meet any away from the day: new demands is a non-starter 1. WORKING TOWARDS for the Liberals. CERTAINTY ON CONTINENTAL TRADE UNCER- 2. HELPING TWO CANADIANS IN BIG TROUBLE IN TAINTY Trump foisted an acrimoni- CHINA ous renegotiation of the North Two Canadian men, Michael American Free Trade Agree- Kovrig and Michael Spavor, ment on Canada and Mexico, have been languishing behind and after more than a year of bars in China for more than six hard bargaining, everyone sur- months. Their arrests are widely vived. The leaders of the three viewed as retaliation for Canacountries signed the deal late da’s arrest of Huawei executive last year but final legal ratifica- Meng Wanzhou in Vancouver tion remains a significant hurdle on an American extradition – especially in the United States. warrant. Chinese leaders have Trump has insulted Pelosi, who snubbed Trudeau and his cabessentially holds the cards on inet ministers but Trump has ratification because she con- been playing hardball with the trols the agenda in one house of People’s Republic in an escalatCongress. Still, Trump sounded ing trade war that is rocking the upbeat in a meeting in the Oval global economy. Trade will be Office, figuring that Pelosi and Continued on page 17
https:www.tzta.ca
Continued from page 16 the subject of a meeting Trump has next week with China’s President Xi Jinping at the G20 leaders’ summit in Japan and he promised the prime minister he will raise the detainees. Trudeau said he and Trump had an “extended conversation” in private about the situation Canada finds itself in with China, which includes blocking imports of Canadian canola and pork. But what Trump will say to Xi isn’t clear – all Trudeau would say is that he expects Kovrig and Spavor to be on the agenda for the meeting. 3. WINNING IN THE EYES OF CANADIANS Managing relations with the United States – Canada’s largest trading partner, neighbour, close friend and ally – is arguably one of the most important duties of a prime minister. Trudeau has had a rough time with Trump, to put it mildly. Trump insulted him over Twitter after leav-
ing the G7 in Quebec last year and he imposed punishing steel and aluminum tariffs on Canadian exports as a bargaining chip in the NAFTA talks. All of that would seem to be history. Trump gave Trudeau a warm welcome at the White House, calling the prime minister “a friend of mine” and touting how the two have worked together on the new trade pact. Trudeau dismissed the past tiff, saying it was focused on what matters in the relationship between the two countries, such as the flow of goods and people across the border. What may matter more for Trudeau – and Conservative Leader Andrew Scheer – is how Canadians interpret the interaction between Trump and the prime minister when voters go to the polls in October. 4. HUAWEI, OR NOT HUAWEI The Trump administration is clear: the Chinese telecom gi-
ant is a national-security threat and won’t be supplying any of the equipment for America’s next-generation 5G wireless network. The Trump administration doesn’t want Canada or its allies using Huawei products either. The Trudeau government is taking its time deciding. Trudeau and Public Safety Minister Ralph Goodale have repeatedly said they will make an evidence-based decision on the advice of their security experts. That likely won’t come before the October election, however. Trump was expected to push the issue with Trudeau when they talked in private. In public, nothing appeared to change.
bet on the NBA Finals that saw the Toronto Raptors defeat her home-state Golden State Warriors. Pelosi paid up on the bet the two made late in the series by handing over California wine, chocolate and nuts. Trudeau didn’t go empty-handed, giving the U.S. House Speaker some Raptors swag and chocolate made by Peace by Chocolate, a company created by a family of Syrian refugees in Nova Scotia. But there was no slam-dunk about whether the champions will get an invite to the White House, in keeping with what is now an often-controversial tradition. All Trump said is that he would think about it.
5. THAT’S THE WAY THE BASKETBALL BOUNCES In addition to trying to salvage the North American economy, protect jobs and bring certainty back to big-business planning, Trudeau had the opportunity to gloat to Pelosi over winning his
Our Morning Update and Evening Update newsletters are written by Globe editors, giving you a concise summary of the day’s most important headlines. Sign up today.
Tel:- 647-7027528 ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
17
https:www.tzta.ca
Matis coffee
Tel:- 647-3463346
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
Konjet Atlaw Owner
1947 Weston Road, Toronto ON 18
https:www.tzta.ca
Ontario Premier Doug Ford shakes up cabinet amid backlash for spending cuts JEFF GRAY QUEEN'S PARK REPORTER LAURA STONE QUEEN'S PARK REPORTER PUBLISHED JUNE 20, 2019
tive MPs say they have heard concerns about the Premier from voters.
Lisa MacLeod stands next to Ontario Premier Doug Ford after being named Ontario's Minister of Tourism, Culture and Sport at Queen's Park in Toronto on Thursday, June 20, 2019.
TIJANA MARTIN/THE CANADIAN PRESS Ontario Premier Doug Ford has unveiled a cabinet shuffle that moves several prominent ministers out of key roles after he faced fights over spending cuts, sagging poll numbers and loud boos at public events. A year into his term, Mr. Ford demoted his finance minister, Vic Fedeli, two months after he delivered the government’s first budget in April. The budget contained targeted cuts to municipalities and other services that, since the details came to light, have dogged Ontario’s Progressive Conservatives. The changes expand the cabinet table to 28 seats from 21, and make room for several newcomers. They follow complaints in PC circles that the government has had trouble communicating its message, as some recent polls suggest that
under Mr. Ford, the party has suffered as much as a 10-percent decline in support from the 40.5 per cent it won in last June’s election. Opinion: Why Doug Ford’s cabinet shuffle could put more pressure on the Premier himself Doug Ford gives $165,000 appointments to insiders and lacrosse player connected to chief of staff Doug Ford Year One: A recap of Ontario’s tumultuous 12 months Ontario, the country’s most populous province, home of its financial hub and generator of nearly 40 per cent of Canada’s gross domestic product, will be a key battleground for this fall’s federal election. Senior Liberals see Mr. Ford’s performance as a potential liability for Conservative Leader Andrew Scheer, and routinely link them in public statements. Senior Conserva-
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
19
Lisa MacLeod, who clashed with the parents of autistic children over the government’s changes to funding for treatment, was moved from Children and Social Services to Tourism, Culture and Sport. Lisa Thompson, who, as education minister, faced off against school boards over plans to increase class sizes – saying it would make students more resilient – moves to Government and Consumer Services. Only eight of Mr. Ford’s ministers kept their jobs in the changes, which come just days after the Premier was booed at an event to celebrate the Toronto Raptors’ NBA championship win. In May, he was booed at the opening of the Special Olympics in Toronto. After Lieutenant-Governor Elizabeth Dowdeswell swore in the new cabinet, Mr. Ford provided few details on the reasons for the moves. He acknowledged his government has had problems with communication, but said he wanted media coverage to be more “fair and balanced.” Asked if he is to blame for the recent criticism, he replied: “I look at continuous improvement. It starts with me. Every one of our cabinet ministers, I feel they’ve done a good job, they can always do a better job. I can always do a better job as well.” The decision to demote Mr.
Fedeli, the former mayor of North Bay, Ont., stunned some senior Conservatives, who view him as a steady hand. Mr. Fedeli was the party’s interim leader in early 2018, after Patrick Brown resigned. A source close to Mr. Ford’s inner circle who was granted anonymity because they are not authorized to speak publicly said the Premier believed the budget rollout could have been smoother, and that the spending cuts should have been spelled out clearly from the beginning. Replacing Mr. Fedeli as Finance Minister is Rod Phillips, who as environment minister shepherded the government’s greenhouse gas emissions plan and its easing of protections for endangered species, both criticized by environmentalists. Mr. Phillips, 54, formerly chairman of the Postmedia newspaper chain and president and chief executive officer of the Ontario Lottery and Gaming Corp., has been around PC Party politics for decades, serving as chief of staff to Toronto mayor Mel Lastman in the late 1990s. Caroline Mulroney, who as attorney-general faced protests over budget cuts to Legal Aid Ontario, moves to Transportation, and the current minister, Jeff Yurek, replaces Mr. Phillips at Environment. Taking over from Ms. Mulroney as Attorney-General is Doug Downey, 49, the rookie MPP for Barrie-Springwater-Oro-Medonte and a lawyer and former city councillor in Orillia, Ont.
Continued on page 22
https:www.tzta.ca
ከገጽ 15 የዞረ የሚያንተከትክባቸው ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡ ፡ አማራን ለገንዘብ ማሰባሰቢያነትና ለትግል ማስኬጃ መናጆነት እንጂ ወደ ሀብትና ሥልጣን እንዳይጠጋ ለማድረግ ከገዢዎች ጋር በኅብረት እንደሚሠሩም እናውቃለን፡፡ እንጂ ኦህዲድን በአንቀልባ ለማዘልና ከሕዝብ ጋር ተጣልቶ ኢሣትን ለመበተን የሚያበቃ ሀገራዊ ድባብ በአሁኑ ወቅት ጨርሶውን የለም፡፡ ዶክተር አቢይንም ሆነ ኦነግንና ኦህዲድን በአንቀልባ አዝለው የመዞር መብታቸው በመሠረቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በሀገር ቁስል ግን እንጨት የመስደድ መብት ፈጽሞ የላቸውም፡፡ ይህ ነገር ጊዜ ቢፈጅም ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ሊረዱት ይገባል፡፡ በማፍረስና በመበተን የሚታወቁ ግለሰቦች አደብ ቢገዙ ከተጨማሪ የካርማ ጽልመት ራሳቸውን ሊታደጉ ይችላሉና ዘመድ ወዳጅ ካላቸው ይምከራቸው፡፡ እናጠፋዋለን ብለው የተነሱት አማራ እንደሆነ አይጠፋም – ዕርማቸውን ያውጡ፡፡ የሚጠሉት የሚመስሉት በዓላማና በግብር ግን የሚመሳሰሉት መለስ ዜናዊ ራሱ በመርፌ ማምከንን ጨምሮ ብዙ ቢለፋም አማራን ሊያጠፋ አልተቻለውም – ቀድሞ ራሱ ጠፋ እንጂ እንዲያውም፡፡ ይልቁናስ ለነሱም መዳን ትልቁ ምክንያት የሚሆነው እርሱ ነው – አማራው፡፡ ጊዜው ሲደርስ ነው ታዲያ፡፡ ኢትዮጵያዊነትንና አማራነትን ለመለያየት የሚደረገው የባንዳዎችና የግብረ አበሮቻቸው እልህ አስጨራሽ ትግል ጉልበቱን ጨርሶ ሲከስም ኢትዮጵያዊነት አፈሩን አራግፎ ከተቀበረበት ይነሣል፡፡ ያም ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሠገሠ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ የፀረ-ኢትዮጵያ ኃይላት እንዲህ መንቀዥቀዥና ግምባር መፍጠር ምሥጢሩ ውስጣቸው የዚያን ወርቃማ ዘመን መምጣት እየነገራቸው እንደሆነ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
20
በስድስተኛው ስሜት መገንዘብ ይቻላል፡፡ የኢሣት ዕውቅ ጋዜጠኞች ይህን ነገር አትናደዱበት፡፡ ለበጎ ነው፡፡ ይሁዳ ክርስቶስን በ30 ብር እንደሸጠው አስታውሱ፡፡ ሊያልቅ ሲል ብዙ ነገሮች እንደሚበለሻሹም ተገንዘቡ፡ ፡ ይልቁናም ምንም ሳትበሳጩና እልህ ውስጥ ሳትገቡ ሌላ የሚዲያ አውታር መሥርቱ፡፡ ይቻላል፡፡ ነባሩን ኢሣት የሚያስንቅ ሌላ ጣቢያ መገንባት ይቻላል፡፡ ነባሩን ኢሣት ባለጊዜዎቹ ‹ተንበርካኪዎች› ይፈንጩበት፡፡ ሲፈልጉ ኢቲቪ ቁጥር ሁለት ይበሉት፡፡ ሲሻቸው ኦኤምኤን ቁጥር ሁለት ይበሉት፡፡ ከነሸጣቸውም ኦቢኤን ቁጥር ሁለት ያድርጉት፡፡ እሱ የማንኛችንም ራስ ምታት አይደለም፡፡ ሥራ ግን መሠራት አለበት፡፡ መሸነፍ የለም፡፡ “የኢትዮጵያ ሬዲዮና ሣተላይት ቴሌቪዥን” (ኢርሣት – ERSAT) ብላችሁ ብታቋቁሙ የምትችሉ ይመስለኛል፡፡ ማንኛውንም ነገር ሞክሩ፤ አንዱ ይሳካል፡፡ የፈሰሰ አይታፈስም፡፡ ማፍረስ የለመደም አይመለስም፡፡ “መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል” እንዲሉ ነውና ከመነሻቸው ጀምሮ ሲያፈርሱና ሲበትኑ ከኖሩ ሰዎች ምንም ደግ ነገር እንደማይጠበቅ ተረድታችሁ ራሳችሁን በሌላ መልክ አደራጁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችሁ እንደሚቆም ደግሞ በጭራሽ አትጠራጠሩ፡ ፡ መከዳት ዕጣው የሆነው ይህ የተገፋ ሕዝብ ሁሉንም ምሥጢር ያውቃልና ችግሩን ስለሚረዳ ፊት አይነሳችሁም፡፡ ይቅናችሁ፡፡ ___ ማስታወሻ:በዚህ ጽሁፍ ላይ የተንጸባረቁ ሳሃቦች የጸሃፊውን/የጸሃፊዋን እንጂ የድረገጹን አቋም አያንጸባርቁም። ነጻ አስተያየት ወይንም ሃሳብ በዚህ ድረ ገጽ ለማውጣት ጽሁፍዎትን በ info@ borkena.com ይላኩልን።
https:www.tzta.ca
Water And Drain Work Plumbing Services Sam-Certified Plumber
Tel:-
647-568-0192
437-227-7336
Email:- infowdworkplumbing.com http://www.infowdworkplumbing.com
Repair toilet filvalve
Install Buth Tub
Repair and install drain line under sinks
Kitchen faucet installation
Pex, Wesbro, and copper pipes.
Install shower faucets
Leak Search and fix
Install shower valve
Install and repair shower valve
Install garbrador (garage disposal)under kitchen sink
Install outdoor hose bib faucet
Re piping drain line on any floor
Install main sump pump and backup pump operating with battery
Re piping refrigerator water line. Install refrigerator water line
Install water heater tank
water filteration under kitchen sink
Repair and install or replace outside hose bib faucet
Unclogged main drain line
Install two pieces toilet (toilet bowl and toilet tank)
Install main shut off valve and re piping water pipes in copper or pex pipe.
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
21
https:www.tzta.ca
Continued from page 17
Etobicoke-Centre MPP Kinga Surma, who was a councillor’s aide at Toronto city hall, has been named an associate minister of transportation for the Greater Toronto Area. Ms. Mulroney, a lawyer and daughter of former prime minister Brian Mulroney, ran for the PC Party leadership last year. Transportation is a key portfolio for Mr. Ford, and Ms. Mulroney and Ms. Surma will oversee the takeover of Toronto’s subway system and be in charge of making plans for new subway lines a reality.
Justin Trudeau scores basket of treats from Nancy Pelosi Continued from page 20
after winning NBA Finals bet Kate Sullivan byline By Kate Sullivan, CNN
When asked why he had moved Ms. MacLeod to a less important portfolio, Mr. Ford pointed out that running the tourism ministry puts her in charge of the government’s effort to attract a private-sector partner to redevelop Ontario Place, the defunct amusement park on Toronto’s waterfront. The autism file goes to Todd Smith, who was economic development minister. And just as the government gears up for renewed battles with unions representing teachers, whose contracts expire at the end of August, 32-year-old Toronto-area MPP Stephen Lecce (King-Vaughan), a newcomer to cabinet, takes over as Education Minister. Another former leadership rival, Health Minister Christine Elliott, stays in her current role, and remains deputy premier. But her responsibility for long-term care has been given to Merrilee Fullerton, the former minister of training, colleges and universities. Opposition NDP Leader Andrea Horwath said Mr. Ford was trying to shift blame for his policies: “Doug Ford is throwing his cabinet under the bus for his cuts. ... I am sure that some now-demoted ministers tried to stand up to Mr. Ford. And look what happened to them.” Interim Liberal Leader John Fraser said the changes show the government is rankled by the criticism and is in disarray: “It’s panic. The Premier is panicking.” Our Morning Update and Evening Update newsletters are written by Globe editors, giving you a concise summary of the day’s most important headlines. Sign up today.
(CNN)Canadian Prime Minister Justin Trudeau scored a basket of treats from House Speaker Nancy Pelosi on Thursday after winning a bet that the Toronto Raptors would defeat the Golden State Warriors to win the NBA Championship. Pelosi presented Trudeau with a basket of California wine and chocolate at a joint news conference with the Prime Minister at the US Capitol. "I'm here to settle the wager," the California Democrat said. "As I promised," Pelosi said, handing Trudeau the basket, "products of the great state of California -- starting with chocolate, almonds, walnuts, pistachios and wine." She congratulated Trudeau on the Raptors' historic win: Last week, the team beat the Warriors 114-110 in Game 6 of the NBA Finals to win its first NBA title. Trudeau accepted the gift, saying, "Canadians are gracious in defeat and even more gracious in victory." He then pulled out a gift of his own, telling Pelosi, "I put together a little bit of Raptors swag -- I don't expect you to wear it." Trudeau also presented her with chocolate he said was made by a company called Peace by Chocolate in the Canadian province of Nova Scotia that was started by a family of Syrian refugees. "I really do have to recognize the Warriors' graciousness and their extraordinary sportsmanship
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
22
that they showed," he said. "It was a tremendous battle between the Raptors and the Warriors." Pelosi said she and Trudeau had made the bet shortly after they returned from Normandy in France, where they -- along with President Donald Trump and other world leaders -- commemorated the 75th anniversary of D-Day earlier this month. Trudeau was in Washington on Thursday for a bilateral meeting with Trump at the White House and for meetings with House and Senate leaders at the US Capitol. Trudeau tweeted later Thursday that he had had a good meeting with Pelosi, where they "talked about the recent progress made toward the ratification of the new NAFTA and expanding trade between Canada and the US." Trudeau also tweeted about their exchange of gifts, saying, "Thanks for the basket of California's finest, @SpeakerPelosi. No matter who won our #NBAfinals bet, Canadians don't show up empty-handed. @Peacebychoco is some of Canada's best chocolate, and a heartwarming Syrian refugee success story. Hope you enjoy!" Pelosi also tweeted about the exchange, saying, "It is always a pleasure to visit with you, @JustinTrudeau -- I hope you enjoy your basket of California's finest. Looking forward to continuing to build on the strong friendship between our two countries!" CNN's Paula Newton and Matthew Hoye contributed to this report.
https:www.tzta.ca
ሾላ ገበያ
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
23
https:www.tzta.ca
ድልድይ መጽሔት / June 2019 Volume 1: Issue 4
24
https:www.tzta.ca