ፍራንሲስ ፋልሴቶ ፈረንሳዊው ፍራንሲስ ፋልሴቶ በ1970ዎቹ አጋማሽ አካባቢ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር በመሆን በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፖሪስ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ ይህን ያከናውኑ የነበሩት በአንድ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ድርጅት /NGO/ አማካኝነት ሲሆን የሚቀርቡት ሙዚቃዎች ደግሞ ከመላው ዓለም የተውጣጡ የፍሪ ጃዝ /free jazz/፣ የድምፅ ሙዚቃ / noise music/፣ ኢንዱስትሪያዊና ባህላዊ ሙዚቃዎች ነበሩ፡፡ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የተሟላ ስዕል ሊሰጥ ይችላል የተባለውና በቡዳ ምዩዚክ የተካተተው ተከታታይ የኢትዮጲክስ ሲዲ አዘጋጅና ፈጣሪ ነው፡፡ ፍራንሲስ ፋልሴቶ፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የ1960ዎቹ ማገባደጃና የ1970ዎቹ መግቢያ በጣም ውጤታማና ምርታማ ዘመን ተብሎ የሚጠቀስ ነው፡፡ ኢትዮጲክስ ጥቂት ባህላዊ ሙዚቃዎችንና የደርግ መንግሥት ውድቀት ድረስ የተሰሩ ጥቂት ሙዚቃዎችን ያካተተ ነው፡፡ ፍራንሲስ ፋልሴቶ አቢሲኒ ስዊንግ ኤ ፒክቶሪያል ሂስትሪ ኦፍ ሞደርን ኢትዮጵያን ምዩዚክ /Abyssinie Swing: A Pictorial History of Modern Ethiopian Music/ የተሰኘ በሻማ ቡክስ የታተመ ቆንጆ መፅሐፍ ደራሲ ነው፡፡ “እ.ኤ.አ. በኤፕሪል ወር 1985 ዓ.ም በአንድ የቀን ሁለተኛ አጋማሽ /ከሰዓት በኋላ/ ነበር አዲስ አበባ ወደሚገኘው ታንጎ ሙዚቃ ቤት የሄድኩት፡፡ “መሐሙድ አህመድ ከአይቤክስ ባንድ ጋር” የሚል ርዕስ ካለው የKF 20 ሸክላ የጀርባ ሽፋን ያገኘሁት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የማውቀው ብቸኛ አድራሻ ነው ሙዚቃ ቤቱ፤ ዓሊ በሙዚቃ ቤቱ ውስጥ ነበር፡፡ ማን እንደሆንኩና ወደ ኢትዮጵያ ለምን እንደመጣሁ ወዲያው ነው ያወቀው፤ ድምፃዊ መሐመድ አህመድን ለማግኘትና ድምፃዊው በአውሮጳ የሙዚቃ ዝግጅት እንዲያቀርብ ለመነጋገር 36
መሆኑ ገብቶታል፡፡” በማለት የሚያስታውሰው ፍራንሲስ ፋልሴቶ በመቀጠል “በዕለቱ ዓሊ ወደ መኖሪያ ቤቱ ይዞኝ ሄደ፡፡ ምሽቱን በሙሉ ስናወራ ነጋ፤ ፀሐይ እስክትወጣ፤ ምንም እንቅልፍ አልነበረንም፤ በጣም ትልቅ አጋጣሚ፤ ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ዕድገትና መሻሻል ለመነጋገር በጣም ትልቅ አጋጣሚ ነበር” በማለት ይገልፃል፡፡ ፍራንሲስ ፋልሴቶ እ.ኤ.አ. በ1997 ዓ.ም የኢትዮጲክስ ተከታታይ ሙዚቃ የመጀመሪያ አልበም ባዘጋጀበት ወቅት
Abyssinia Business Nework ልዩ እትም 2012 Special Edition 2020
አብዛኛው የውጪ ዜጋ ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ በቂ እውቀት አልነበረውም፡፡ ለሁለት ተከታታይ አስርት ዓመታት ፋልሴቶ ኢትዮጵያን በዓለም የሙዚቃ ካርታ ላይ የማስቀመጥ ኃላፊነት የተጣለበት ብቸኛ ባለሙያ ነበር፡፡ ፋልሴቶ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ፍቅር የወደቀው እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅ /promoter/ በመሆን በፓይቲየርስ በሚሰራበት አጋጣሚ የመሐሙድ አህመድን “መላ መላ” የሚለውን ዜማ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰማበት ወቅት ነበር፡፡