3 minute read
ሕብስት ጥሩነህ
የ 13 ዓመት ታዳጊ፣ቀይ፣ አጭር አፍሮ ጸጉር፤በልጅነቷ በቤት ውስጥ የነሂሩት በቀለ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ሀመልማልአባተና የሌሎች ድምጻውያንን ዜማ ታንጎራጉር ነበር፡፡ ህብስት ጥሩነህ፡፡ በውስጧ የነበረውን እምቅ የሙዚቃ ችሎታና ዝንባሌ የተገነዘበው ባህሩ የተባለየወንድሟ ጓደኛ ነው ህብስትን መጀመሪያ ወደ ታንጎ ሙዚቃ ቤት ይዟት የሄደው፡፡
ቀድሞውን ህብስት ምንም እንዳፈራ፤ መክሮና አስጠንቅቆ ነው ወደ ሙዚቃ ቤቱ የወሰዳት፤……ታንጎ ሙዚቃ ቤት በር ላይ የተቀመጠው ድምጽ ማጉያ /loud speaker/ ከፍ ባለ ድምጽ ሙዚቃ ያሰማል፡፡ የህብስት ወንድም ጓደኛ ባህሩ የትንሿን ልጅ እጅ ይዞ ወደ ሙዚቃ ቤቱ ገባ፡ ፡ የሙዚቃ ቤቱ ባለቤትና ሀላፊ አሊ አብደላ ኬይፋ ከሙዚቃ ቤቱ ጥግ በሚገኝ አንድ ከመስታወት የተሰራ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መደርደሪያ አጠገብ ሙሉ ሱፍ ልብሱን ከነከረባቱ ግጥም አድርጎ፤ እጆቹን አጣምሮ ቆሟል፡፡ “አቶ ዓሊ!.. ያቺ ያልኩህ ልጅ ይህች ነች፡ ፡” አለ የህብስት ወንድም ጓደኛ፡፡
Advertisement
“አሁን ይህች ህጻን ልጅ ትዘፍናለች?” አለና ታዳጊዋን ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ ተመለከታት፡፡ ዓሊ ቀጠለናም “እስኪ ዝፈኝልኝ!” አላት፤ በዚህ ጊዜ ታንጎ ሙዚቃ ቤት ካሴት የሚገዙ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ ካሴት የገዙ ሰዎች ደግሞ ከሙዚቃ ቤቱ ሲወጡ ማየት ሌላ ትዕይንት ነበር፤ ግርግሩ ህብስትን ትንሽ ግራ እንዲገባት ማድረጉ አልቀረመ፡፡ ነገር ግን ትንሿ ህብስት የንዋይ ደበበን“የጥቅምት አበባ’’ ዜማ በደንብ አድርጋ ተጫወተች፡ ፡ ዓሊ ደንገጥ አለና “ እስኪ ሌላ ዘፈን ተጫወቺ! ” አላት፤ ህብስትም በመቀጠል የሀመልማል አባተን “የትዳሬ ማገር” የሚለውን ዜማ ተጫወተችለት፡፡ በህብስት ድምጽ ሀይልና ውበት እንዲሁም ድፍረት በጣም የተገረመው ዓሊ “ ይህች ልጅ በጣም ትልቅ ደረጃ መድረስ የምትችል ናት፡፡” ብሎ ደስታውን፡፡
Photo by Daniel Tiruneh
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው እንግዲህ ዓሊ ኬይፋ ከህብስት ጥሩነህ ጋር ተወዳጅ ስራ ለመስራት እንደ አርቲስት አየለ ማሞ ከመሳሰሉት የሚዚቃ ሰዎችና ሮሃ ባንድ ከህብስት ጋር እንዲሰሩ የወሰነው፡፡ “ ጋሽ አየለ ማሞ የሰራልኝ ‘በርቺ በሉኝ’፣ ኦሮምኛና አንድ ሌላ ዘፈኔን ነው፤ ‘’እናቴን አደራ” የሚለውን ዜማ ጨምሮ ሰባቱን ዘፈኖች ዜማና ግጥም የሰሩልኝ ደግሞ ሱራፌል አበበና ተመስገን ተካ ናቸው፡፡”
ህብስት ይህን አልበም ስትሰራ እንደ ጀማሪና ልምድ እንደሌለው ድምጻዊ ለሮሃ ባንድ ሙዚቀኞች አስቸጋሪ አልነበረችም፤ ወዲያው ህብር ፈጥራ የመጀመሪያና ታዋቂ ያደረጋትን አልበም በስኬት ለማጠናቀቅ ችላለች፡፡ የሙዚቃ ጉጉት ከልጅነት ጋር ተደምሮ ገንዘብ ለእርሷ
ብዙ ትርጉም አልነበረውም፤ “እንዴ! ክፍያ? በነጻስ ቢሆን እኔ እኮ ካሴት መስራቴን እንጂ ስለገንዘብ በወቅቱ ምንም አስቤ አላውቅም፡ ፡” ብላለች ህብስት ስለ መጀመሪያ ስራዋ ክፍያ ስትጠየቅ፡፡
ዓሊኬይፋ በወቅቱ ህብስት ገንዘብ የማስተዳደር አቅም እንደሌላት በመረዳት ለዚህ ለመጀመሪያ ስራዋ 3000 ብር የከፈላት ሲሆን ገንዘቡንም የተቀበሉት አባቷ አቶ ጥሩነህ ነበሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዓሊ ለህብስትና ለቤተሰቦቿ ያስፈልጉ የነበሩ ነገሮችን አድርጓል፡፡ ህብስት ይህን በተመለከተ እንዲህ ብላለች፣ “ በእውነቱ ከሆነ ጋሽ ዓሊ ለእኔና ለቤተሰቦቼ ከጠበቅኩት በላይ ነው በርካታ ነገር ያደረገው፤ ልክ እንደ አባት በመሆን ትልቅ አክብሮትና ድጋፍ ነው ያደረገልኝ፡፡ ”
ድምጻዊ ህብስት ጥሩነህ ከዓሊ ጋር የሰራችው የመጀመሪያዋን አልበም ብቻ ቢሆንም ቀጣይ ስራዋን እንድትሰራ እገዛ አድርጎላታል፡፡ ሁለተኛዋን አልበም ለመስራት በዝግጅት ላይ ሳለች ነበር ዓሊ ከሀገር ለመውጣት በሂደት ላይ የነበረው፡፡ በመሆኑም ዓሊ ህብስት ሁለተኛ አልበሟን እንድታወጣ ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ከአቶ ተሾመ ጋር አገናኛት፡፡ እርሷም ሁለተኛ አልበሟን ሰርታ ለህዝብ አቀረበች፡፡
“ አሁን እኔ እዚህ ደረጃ እንድደርስ የዓሊ ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡” የምትለው ድምጻዊ ህብስት ጥሩነህ ዓሊ ታንጎ የሙዚቃ ማሳተም ስራ ላይ ብቻ አያተኩርም፤ በሙዚቃ ውበት፣ በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችና በድምጻውያን መካከል ስለሚኖረው ውህደትና መግባባት የእራሱ የሆነ እውቀትና ክህሎት ነበረው ትላለች፡፡
ዓሊ አብደላ ኬይፋ የድምጻዊ ህብስት ጥሩነህ የመጀመሪያ አልበም የሙዚቃ ቪዲዮ ዝግጅት በተመለከተ በኢትዮጵያ ያልተለመደ አጋጣሚ እንዲፈጠር በማድረጉ በሀገሪቱ የሙዚቃ ታሪክ ዘላለም ሊታወስ የሚገባ የሙዚቃ አሳታሚ ነው፡፡
እንደዚሁ ቦታ እየቀያየርን ነው የሰራነው፡ ፡ ‘ምን ይሻላል፣ ምን ይበጃል? የሚለው ዘፈን ብቻ ነው እስቲድዮ የተቀረጸው በተረፈ አስሩንም ዘፈኖቼን በአንድ ቀን ነው እንዲቀረጹ ያደረገው፡፡” ብላለች ህብስት ጥሩነህ፡፡
የዓሊ ታንጎን ውለታ የማትረሳው ህብስት “ ዓሊ እኔ እዚህ ደረጃ ለመድረሴ ከፍተኛ ድርሻ አለው፤ ልክ እንደ አባቴ ነው፡ ፡ የመጀመሪያ አልበሜን በምሰራበት ጊዜ እንደ አባት እየተቆጣጠረና እየመከረ ስኬታማ እንድሆን የረዳኝ መሰረቴ ነው፤ ከእርሱ ጋር የስጋ ዝምድና ያለኝ ያህል ነው የሚሰማኝ፡፡” ብላለች፡፡
Abyssinia Business Nework Special Edition 2020 ልዩ እትም 2012 43 ዓሊ በወቅቱ የአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ይገኝ ወደ ነበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሄዶ ከስራ ሀላፊዎች ጋር በመነጋገርና በማሳመን በህብስት የመጀመሪያ አልበም ውስጥ የሚገኙትን አስሩንም ዘፈኖች የሙዚቃ ክሊፕ እንዲሰራላቸው በማድረግ ታሪክ መስራቱን ድምፃዊ ህብስት ጥሩነህ በአግራሞት ታስታውሳለች፡፡ “በጣም የሚገርመኝ ደብረዘይት ሆራ ሀይቅ ሄደን ‘ እምዬን አደራ‘ የሚለውን ዘፈኔን ውሀ ላይ፣ የሆነ ዘፈኔን የአበባ ቦታ፣ የሆነ ዘፈኔ ቤት ውስጥ፣ ሌሎችንም ለረጅም ጊዜ በአካል ለመገናኘት ሳይችሉ ቢቆዩም አሁን ላይ የዓሊ አብደላ ኬይፋ ወዳጅ ዘመዶችና ጓደኞች እርሱ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላበረከተው አስተዋጽኦና ለበርካታ ድምጻውያን መሰረት በመሆኑ ላዘጋጁት የእውቅናና የክብር መርሀ-ግብር ዋዜማ ላይ ሆና “ ዓሊ በጣም እወድሀለሁ! አከብርሀለሁ! እግዚሀብሄር ዕድሜና ጤና ይስጥህ! ” በማለት ለሙያ አባቷ ያላትን ምኞት ገልጻለች፡፡