Abyssinia Business Network /ABN/ Special Edition 2020

Page 44

ሕብስት ጥሩነህ የ 13 ዓመት ታዳጊ፣ቀይ፣ አጭር አፍሮ ጸጉር፤በልጅነቷ በቤት ውስጥ የነሂሩት በቀለ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ሀመልማልአባተና የሌሎች ድምጻውያንን ዜማ ታንጎራጉር ነበር፡፡ ህብስት ጥሩነህ፡፡ በውስጧ የነበረውን እምቅ የሙዚቃ ችሎታና ዝንባሌ የተገነዘበው ባህሩ የተባለየወንድሟ ጓደኛ ነው ህብስትን መጀመሪያ ወደ ታንጎ ሙዚቃ ቤት ይዟት የሄደው፡፡

ቀድሞውን ህብስት ምንም እንዳፈራ፤ መክሮና አስጠንቅቆ ነው ወደ ሙዚቃ ቤቱ የወሰዳት፤……ታንጎ ሙዚቃ ቤት በር ላይ የተቀመጠው ድምጽ ማጉያ /loud speaker/ ከፍ ባለ ድምጽ ሙዚቃ ያሰማል፡፡ የህብስት ወንድም ጓደኛ ባህሩ የትንሿን ልጅ እጅ ይዞ ወደ ሙዚቃ ቤቱ ገባ፡

፡ የሙዚቃ ቤቱ ባለቤትና ሀላፊ አሊ አብደላ ኬይፋ ከሙዚቃ ቤቱ ጥግ በሚገኝ አንድ ከመስታወት የተሰራ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች መደርደሪያ አጠገብ ሙሉ ሱፍ ልብሱን ከነከረባቱ ግጥም አድርጎ፤ እጆቹን አጣምሮ ቆሟል፡፡ “አቶ ዓሊ!.. ያቺ ያልኩህ ልጅ ይህች ነች፡ ፡” አለ የህብስት ወንድም ጓደኛ፡፡

Photo by Daniel Tiruneh

“አሁን ይህች ህጻን ልጅ ትዘፍናለች?” አለና ታዳጊዋን ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ ተመለከታት፡፡ ዓሊ ቀጠለናም “እስኪ ዝፈኝልኝ!” አላት፤ በዚህ ጊዜ ታንጎ ሙዚቃ ቤት ካሴት የሚገዙ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ ካሴት የገዙ ሰዎች ደግሞ ከሙዚቃ ቤቱ ሲወጡ ማየት ሌላ ትዕይንት ነበር፤ ግርግሩ ህብስትን ትንሽ ግራ እንዲገባት ማድረጉ አልቀረመ፡፡ ነገር ግን ትንሿ ህብስት የንዋይ ደበበን“የጥቅምት አበባ’’ ዜማ በደንብ አድርጋ ተጫወተች፡ ፡ ዓሊ ደንገጥ አለና “ እስኪ ሌላ ዘፈን ተጫወቺ! ” አላት፤ ህብስትም በመቀጠል የሀመልማል አባተን “የትዳሬ ማገር” የሚለውን ዜማ ተጫወተችለት፡፡ በህብስት ድምጽ ሀይልና ውበት እንዲሁም ድፍረት በጣም የተገረመው ዓሊ “ ይህች ልጅ በጣም ትልቅ ደረጃ መድረስ የምትችል ናት፡፡” ብሎ ደስታውን፡፡

42 Abyssinia Business Nework ልዩ እትም 2012 Special Edition 2020

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው እንግዲህ ዓሊ ኬይፋ ከህብስት ጥሩነህ ጋር ተወዳጅ ስራ ለመስራት እንደ አርቲስት አየለ ማሞ ከመሳሰሉት የሚዚቃ ሰዎችና ሮሃ ባንድ ከህብስት ጋር እንዲሰሩ የወሰነው፡፡ “ ጋሽ አየለ ማሞ የሰራልኝ ‘በርቺ በሉኝ’፣ ኦሮምኛና አንድ ሌላ ዘፈኔን ነው፤ ‘’እናቴን አደራ” የሚለውን ዜማ ጨምሮ ሰባቱን ዘፈኖች ዜማና ግጥም የሰሩልኝ ደግሞ ሱራፌል አበበና ተመስገን ተካ ናቸው፡፡” ህብስት ይህን አልበም ስትሰራ እንደ ጀማሪና ልምድ እንደሌለው ድምጻዊ ለሮሃ ባንድ ሙዚቀኞች አስቸጋሪ አልነበረችም፤ ወዲያው ህብር ፈጥራ የመጀመሪያና ታዋቂ ያደረጋትን አልበም በስኬት ለማጠናቀቅ ችላለች፡፡ የሙዚቃ ጉጉት ከልጅነት ጋር ተደምሮ ገንዘብ ለእርሷ


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.