2024-25
የምዝገባ
መረጃ
በ DPS ውስጥ ትምህርት ቤት መምረጥ Denver Public Schools ለቤተሰቦቻችን
የት/ቤቶች ዓይነቶች በዲስትሪክት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች በ DPS እና በትምህርት ቦርዱ የሚመሩ፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ የሚደረግላቸው። ■
የተወሰኑ በዲስትሪክት የሚተዳደሩ ት/ቤቶች የፈጠራ ት/ ቤቶች ናቸው፣ ለዚህም በ DPS የትምህርት ቦርድ እና በ Colorado የትምህርት ዲስትሪክት እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የተማሪዎችን ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት ይቻል ዘንድ በትምህርት መርሃ-ግብሮች፣ ሰራተኞች፣ የጊዜ ሰሌዳዎች እና በጀቶች ላይ ከፍ ያለ ነፃነት ያላቸው ናቸው።
■
በዲስትሪክት የሚተዳደሩ ት/ቤቶች የተወሰኑ ልዩ የሆኑ/ ስፔሻላይዝድ ት/ቤቶችን ወይም ፕሮግራሞችንም እንዲሁ የሚያካትቱ ሲሆን፣ እነኚህም በተወሰነ የመማር-ማስተማር ዘይቤ ላይ የሚያተኩሩ ወይም ተማሪዎችን በጋራ የፍላጎት መስክ የሚያገለግሉ፣ እንዲሁም ከት/ቤቱ አጎራባች ክልል ውጭ ለሚኖሩ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያቀርቡ የሚችሉ ናቸው። ምሳሌዎች Arts Focus፣ የ Montessori፣ ከፍተኛ ባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ፣ እና ባለሁለት ቋንቋ ትምህርት ቤቶች ወይም ፕሮግራሞችን ያካትታሉ።
በሚያቀርባቸው የት/ቤት አማራጮች ኩራት ይሰማዋል። ለእያንዳንዱ እና ለሁሉም ተማሪ ታላቅ ትምህርት ቤት እንዳለ ከልብ እናምናለን። የት/ቤት ፍለጋዎን ሲጀምሩ ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች ከዚህ በታች ቀርበዋል። መጀመሪያ፣ በአካባቢዎ የሚገኘውን አጎራባች ትምህርት ቤት ቀረብ ብለው ይመልከቱ።
ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 12ኛ ክፍል የሚመጡ ተማሪዎች ሁሉ በአካባቢያቸው አጎራባች ወይም ድንበር - ት/ቤት ውስጥ አንድ ቦታ የማግኘት ዋስትና ይሰጣቸዋል። schoolfinder.dpsk12. org ላይ አድራሻዎን በመፃፍ በአካባቢዎ የሚገኘውን አጎራባች ትምህርት ቤት ለመወሰን ይችላሉ። አሁን እየተማሩበት ካለው ት/ቤት ውጭ በሆነ ሌላ ትምህርት ቤት ለመማር ፍላጎት ካለዎት አማራጮችዎን መፈተሽ የሚችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡ ■
■
ቻርተር ት/ቤቶች በገለልተኛ የዳሬክተሮች ቦርድ የሚተዳደሩ በተናጠል የሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ት/ቤቶች ናቸው። ■
ይህ የምዝገባ መመሪያ በ DPS ውስጥ፣ ፕሮግራሞችን፣ የመገናኛ አድራሻን እና ሌሎችን ጨምሮ እያንዳንዱን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተመለከተ መረጃ ይዟል። ፍለጋዎን ለማቃለል ያግዝዎት ዘንድ፣ ትምህርት ቤቶቹ በአጠቃላይ በከተማዋ አምስት ክፍሎች ይከፈላሉ።
ሁሉም የቻርተር ት/ቤቶች ተጠሪነታቸው ለ DPS የትምህርት ቦርድ እና በዲስትሪክት እንደሚመሩት ት/ቤቶች ለተመሳሳይ የትምህርት አፈጻጸም ደረጃዎች/ስታንዳርዶች ነው።
■
የቻርተር ት/ቤቶች የየራሳቸውን ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን የመንደፍ እና የት/ቤት ፖሊሲዎችን የማውጣት ነፃነት አላቸው።
schoolfinder.dpsk12.org ን ይጎብኙ።
■
ሁሉም የቻርተር ትምህርት ቤቶች በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን በሙሉ በእኩል ሁኔታ ለማገልገል ቁርጠኞች ናቸው። አንዳንድ የቻርተር ትምህርት ቤቶች በታወቀ ቦታ ውስጥ ለሚኖሩ ተማሪዎች ቅድሚያ ይሰጣሉ።
ትምህርት ቤቶችን በአድራሻ፣ በፕሮግራሞች ወይም በፊደል ተራ ቁጥር መፈለግ ይችላሉ።
■
የሚስቡዎትን ትምህርት ቤቶች ያነጋግሩ። ስለ ተማሪዎች ፕሮግራሞች እና ባህል በተመለከተ ከትምህርት ቤት መሪዎች ጋር በቀጥታ ለመመካከር ተተኪ አማራጭ የለም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ት/ቤቶችን በተናጠል ያነጋግሩ።
አንዴ ለ2024-25 የትምህርት ዓመት የተመራጭ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር ከፈጠሩ በኋላ የእኛ ባለ አንድ የጊዜ ገደብ፣ የአንድ የምዝገባ ማመልከቻ በሆነው SchoolChoice ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጁ ይሆናሉ። የ SchoolChoice የዙር 1 የማመልከቻ ጊዜ ከጃንዋሪ 11 እስከ ፌብሩዋሪ 12፣ 2024 ድረስ ነው። ለተጨማሪ መረጃ ገጽ 4 ን ይመልከቱ።
PATHWAYS ት/ቤቶች ■
PATHWAYS ት/ቤቶች በዲስትሪክት-የሚተዳደሩ ወይም
ቻርተር ሊሆኑ ይችላሉ። ጎዳና ቀያሽ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ወደ ዲፕሎማ የሚመሩ እና ከድህረ ሁለተኛ ደረጃ ዕድሎች ጋር የሚያገናኙ ጥልቅ ትምህርታዊ እና ስሜታዊ ድጋፎችን ይሰጣሉ። አብዛኛዎቹ ጎዳና ቀያሽ ት/ቤቶች ከመደበኛ አመዳደቦች ይልቅ በአንድ ዓመት ብዙ ክሬዲቶች የሚገኙበትን እድል ይሰጣሉ።
ምዝገባ እና SCHOOLCHOICE ድረገጽ፥ schoolchoice.dpsk12.org ስልክ ቁጥር፥ 720-423-3493
እንዴት መሳተፍ ይቻላል
Colorado የክፍት ምዝገባ ግዛት ሲሆን DPS የትምህርት ቤቶች የማመልከቻና
ለተማሪዎ ስላሉ
ምዝገባ ሂደትን በተቻለ መጠን ቀላል ለማድረግ ይተጋል። ልጅዎ ትምህርቱን የሚከታተለው
የትምህርት ቤት አማራጮች መረጃ ያግኙ
በመኖሪያ መንደር ወሰን ክልል ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ውስጥም ይሁን Denver ውስጥ የሚገኝ ሌላ ትምህርት ቤት ይምረጥም DPS ሁሉም ተማሪዎች ለመረጧቸው ትምህርት ቤቶች በእኩል ደረጃ ተደራሽ መሆን እንዳለባቸው ያምናል። የሚመጡ ተማሪዎች
■
ለሞባይል-ምቹ የሆነውን የመስመር-ላይ ት/ቤት መፈለጊያ በ schoolfinder.dpsk12.org ላይ ይጠቀሙ።
■
የምዝገባ መመሪያውን ያንብቡ።
■
ትምህርት ቤቶችን በተናጠል ያነጋግሩ።
በአካባቢያቸው ት/ቤት ወይም በምዝገባ ዞናቸው ባለ ት/ቤት የመመዝገብ ዋስትና አላቸው። ይሁን እንጂ፣ በሚቀጥለው ዓመት አዲስ ትምህርት ቤት መማር የሚፈልግ ወይም ያለበት ማንኛውም ተማሪ የእኛ ባለ አንድ የጊዜ ገደብ፣ የአንድ የምዝገባ ማመልከቻ በሆነው በSchoolChoice መሳተፍ ይችላል። ለቅድመ ት/ቤት ተማሪዎች በ DPS ፕሮግራም ለመመዝገብ ዋስትና አይኖርም፣ የቅድመ ት/ቤት ቤተሰቦች በየዓመቱ ማመልከት አለባቸው።
አጎራባች ት/ቤትዎን ያግኙ የ Denver ነዋሪ ከሆኑ፣ ከአካባቢዎ ወሰን ት/ቤት ለመውጣት "ካልወሰኑ" እና ለዘንድሮው የትምህርት ዓመት ልጅዎን ማስመዝገብ ቢፈልጉ፣ አድራሻዎትን በሚያገለግለው አጎራባች ትምህርት ቤት በቀጥታ መመዝገብ ይችላሉ። አጎራባች ትምህርት ቤትዎን ለመወሰን schoolfinder.dpsk12.org ን መጎብኘት ይችላሉ። ለመመዝገብ፣ ለምዝገባ ቀናት እና አስፈላጊ ሰነዶች በቀጥታ የትምህርት ቤቱን ቢሮ ያናግሩ። የተወሰኑ Denver ክፍሎች በመመዝገቢያ ዞኖች ወይም በጂኦግራፊያዊ አካባቢዎች፣ ማለትም በአንድ በተወሰነ ት/ቤት ሳይሆን፣ ተማሪዎች በሚኖሩበት አካባቢ ካሉ በርካታ ት/ቤቶች ውስጥ በአንዱ መመደብ እንዲችሉ ዋስትና በሚያገኙበት አሰራር አገልግሎት የሚያገኙባቸው ናቸው። በቅርቡ የተዛወሩና በ Denver ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እና አሁን በምዝገባ ዞን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም ለአሁኑ የትምህርት ዓመት ከአጎራባችዎ ትምህርት ቤት ውጭ ባለ ት/ቤት ለመከታተል የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ አካውንት በመፍጠር እና በ dpsschoolchoice.my.site.com ላይ በመለያ በመግባት ማመልከቻ ይሙሉ።
የ SchoolChoice ማመልከቻዎን በመስመር ላይ በማስገባት
ያመልክቱ ■
የወላጅ መግቢያ (ፖርታል) የተጠቃሚ ስምዎን እና የይለፍ ቃልዎን በመጠቀም በ dpsschoolchoice.my.site. com ላይ አካውንት ይፍጠሩ።
■
የማመልከቻው ጊዜ ክፍት በሚሆንበት ጊዜ፣ ከጃንዋሪ 11 እስከ ፌብሩዋሪ 12፣ 2024 ድረስ በመለያ ይግቡ እና የት/ቤት ምርጫዎችዎን በደረጃ ያስቀምጡ።
■
ማመልከቻዎን ከ 10 a.m. ጃንዋሪ 11 እስከ 4 p.m. ፌብሩዋሪ 12 ድረስ በማንኛውም ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
SCHOOLCHOICE ለቀጣይ የትምህርት ዓመት ልጅዎን ከአጎራባች ትምህርት ቤትዎ (ወይም አሁን እየተማሩ ካለበት ት/ቤት) ውጪ በሆነ የ DPS ት/ቤት ለማስመዝገብ ከፈለጉ፣ በ SchoolChoice ውስጥ ሊሳተፉ ይችላሉ። በ SchoolChoice ወቅት፣ ቤተሰቦች ለእያንዳንዱ ተማሪ ከፍተኛ የትምህርት ቤት ምርጫቸውን በደረጃ የሚያስቀምጡበት አንድ የተጣመረ ማመልከቻ ያስገባሉ። ከዚያም DPS በነዚህ ምርጫዎች ላይ፣ እንዲሁም ለቅበላ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች እና ሊገኙ የሚችሉ ቦታዎች ላይ በመመርኮዝ ተማሪዎችን ከት/ቤት ያዛምዳል። ስርዓታችን የመጀመሪያ ምርጫቸው የሆነውን ት/ቤት የሚያገኙ ተማሪዎችን ብዛት ለማሳደግ ታስቦ የተቀረጸ ነው። የ 2024-25 የትምህርት ዓመት 1ኛ ዙር SchoolChoice ከጃኑዋሪ 11፣ 2024 ቀን 10 a.m. ሰዓት እስከ ፌብሩዋሪ 12፣ 2024 ቀን 4 p.m. ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። በማመልከቻው ወቅት ላይ በማንኛውም ጊዜ በ dpsschoolchoice.my.site.com ላይ መለያ ፈጥረው ለሚመርጧቸው ትምህርት ቤቶች ማመልከት ይችላሉ።
4
ትምህርት ቤትዎን ለመከታተል እንዲችሉ tይመዝገቡ ■
የት/ቤት ምደባ ውጤቶችን በማርች 2024 መጨረሻ ላይ ይመልከቱ
■
ለ 2024-25 የትምህርት ዓመት ለመመዝገብ ትምህርት ቤቱን ያነጋግሩ
የ SCHOOLCHOICE ቁልፍ ቀናት ጃንዋሪ 11፣ 2024
በ 10 a.m. ሰዓት የ1ኛው ዙር የ SchoolChoice ማመልከቻ ሂደት ይከፈታል። ፌብሩዋሪ 12፣ 2024
የ SchoolChoice የማመልከቻ ጊዜ በ 4 p.m ሰዓት ላይ ያበቃል።
ማርች መጨረሻ፣ 2024
ቤተሰቦች የትምህርት ቤት ምደባዎች ይገለጽላቸዋል ኤፕረል 10፣ 2024
የዙር 2 SchoolChoice 10 a.m ሰዓት ላይ ይከፈታል ኦገስት 31፣ 2024
የዙር 2 SchoolChoice በ 4 p.m. ሰዓት ይዘጋል።
የትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ADVANCEMENT V I A I NDI V I DUAL DETERM I NAT ION (AV I D፣ በግል ቁርጠኝነት መለወጥ/ማደግ) ተማሪዎችን
ጥልቅ አሳቢ እንዲሆኑ፣ ተባባሪ እንዲሆኑ እና ለወደፊታቸው የራሳቸውን ከፍተኛ የሚጠበቁ ሁኔታዎች እንዲወስኑ የሚያስተምር አሳታፊ፣ ጠንካራ እና ተማሪን ያማከለ ከK-12ኛ ክፍል የኮሌጅ ዝግጁነት ፕሮግራም ነው። የዕድል ክፍተቱን ለማጥበብ ቁልፍ ስትራቴጂ እንደመሆኑ፣ የ AVID ተማሪዎች ሙሉ እምቅ ችሎታቸው ላይ ይደርሱ ዘንድ ከአካዳሚያዊ እና ማኅበራዊ ድጋፍ ጋር በከፍተኛ ደረጃዎች እንዲመዘኑ ይደረጋሉ። AVID ለተማሪዎች መሰረታዊ ክህሎቶችን፣ አካዳሚያዊ ልማዶችን እና የኮሌጅ እውቀቶችን በማስታጠቅ ትምህርታቸውን በባለቤትነት ለመምራት አቅም እንዲያገኙ በማድረግ ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ ስኬት ያዘጋጃቸዋል። AVID በአንደኛ ደረጃና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃ በስፋት የጎለበተ ሲሆን በሁለተኛ ትምህርት ቤት ደረጃ ተጨጨማሪ የትምህርት ክፍለ ጊዜ አለው። ADVANCED PL ACEMENT (AP፣ ከፍተኛ ምደባ) ትምህርቶች የሁለተኛ
ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለኮሌጅ ትምህርት በጥብቅ፣ ኮሌጅ-መሰል ተሞክሮ እንዲዘጋጁ ይረዳል። AP በኮሌጅ ቦርዱ የተዘጋጀ እና ከቅድመ-ምረቃ የኮሌጅ ኮርሶች ጋር አቻ ተደርገው የሚወሰዱ ደረጃቸውን የጠበቁ ኮርሶችን የሚሰጥ ሥርዓተ ትምህርት ነው። በብሔራዊ የ AP ፈተና ውጤታቸው የማለፊያ ነጥብን ያገኙ ተማሪዎች በተሳታፊ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ ነጥብን (ክሬዲት) እና ከፍተኛ ምደባን ሊያገኙ የሚችሉ ይሆናሉ። ይህም በኮሌጅ ቆይታቸው ላይ ጊዜን እና ገንዘብን ሁለቱንም የሚቆጥብላቸው ይሆናል። የAP ክፍለ ጊዜዎችን ለሁሉም የሁለተኛ ትምህርት ቤት የክፍል ደረጃዎች፣ ከ9-12ኛ ክፍል ማግኘት ይቻላል። ተማሪዎች የክፍል ደረጃቸውን ሲያልፉ የተመዘነ የGPA ውጤት ይሰጣቸዋል።
ARMY JUNIOR RESERVE OFFICER S’ TR A I NI NG CORPS (JROTC፣ የጦር ሰራዊት ጁኒየር ተጠባባቂ መኮንኖች ስልጠና ሰራዊት)
የባህሪ ትምህርት፣ የተማሪ ውጤት፣ ጤና
እና ደህንነት፣ አመራር እና ብዝሃነትን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያስተምር አስደሳች ፕሮግራም ነው። ዜግነትን ከማሳደግ በተጨማሪ፣ JROTC እንዲሁ ኮሌጅንም ሆነ የሥራ ኃይልን ጨምሮ ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ አማራጮች ተማሪዎችን ያዘጋጃል። በካዴትበሚመሩ ፕሮግራሞች እና በቡድን ውድድሮች አማካኝነት ተማሪዎች እንደ አመራር፣ የቡድን ሥራ፣ የጊዜ አያያዝ፣ ራስን መቆጣጠር መቻል እና ግንኙነትን የመሳሰሉ ጠቃሚ ሙያዊ ክህሎቶችን ይማራሉ። JROTC በ11 የDPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚቀርብ ሲሆን ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው ይህን የማያቀርብ ከሆነ በቅርባቸው ለሚገኘው ፕሮግራም ሊመዘገቡ ይችላሉ። JROTC ለመመረቂያ መስፈርቶች እንደ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ውጤት ተደርጎ ይወሰዳል። የDPS ትምህርት ቤቶች የአርት ፕሮግራሞች ለተማሪዎች ተሳትፎ፣ የግል
ገለጻ እና የመረዳት ችሎታ እድገት የትምህርት አርቶች (የእይታ አርት፣ ቲያትር፣ ዳንስ፣ ሙዚቃ) ጥናትና እድሎችን ይይዛል። ACCELER AT I NG STUDENTS THROUGH CONCURRENT ENROLLMENT (ASCENT፣ በአንድ ላይ ምዝገባ ተማሪዎችን ማፋጠን)
ለDPS ለተሳታፊ ተማሪዎች ለአንድ ሙሉ የኮሌጅ ዓመት (የመኸርና የፀደይ ወቅት መንፈቅ ዓመቶች) የተጨማሪ ትምህርት ክፍያና ክፍያዎቻቸውን እንዲከፍልላቸው የሚፈቅድ የግዛት ፕሮግራም ነው። በ 2009 Concurrent Enrollment program (የአንድ-ላይ ምዝገባ ፕሮግራም ቅጥያ) በመሆን እንደ ሕግ የጸደቀው፣ የ ASCENT ዓላማ ለተማሪዎች ለተባባሪ ዲግሪ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የኢንዱስትሪ የምስክር ወረቀት የኮሌጅ ውጤቶችን የሚያገኙበት የተሳለጠ መስመር መፍጠር ነው። የDPS ተማሪዎች ከመመረቂያ ዓመታቸው በኋላ የፕሮግራሙን የብቁነት መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ በASCENT ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ተማሪዎች ከስምንቱ አሳታፊ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (Arapahoe Community College፣ Community College of Aurora፣
Community College of Denver፣ Front Range Community College፣ Red Rocks Community College፣ Emily Griffith Technical College፣ Pickens Technical College እና Metro State University of Denver) መካከል በአንዱ ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ። የASCENT ተማሪዎች በኮሌጅ የመጀመሪያ ዓመታቸው ውስጥ በሙሉ የትምህርት፣ የማህበራዊ ስነ ልቡና እና የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ ወሳኝ የተጠቃለሉ አገልግሎቶች ይቀርቡላቸዋል። ተማሪዎች ለASCENT ፕሮግራም ብቁ ለመሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳሉ ቢያንስ ዘጠኝ የኮሌጅ ደረጃ ውጤቶች ማምጣት አለባቸው። ከቅድመ ኮሌጅ ወይም የP-TECH ትምህርት ቤት የተመረቁ ተማሪዎች በColorado ግዛት ህግ መሰረት ለASCENT ወይም TREP ብቁ አይሆኑም። ለተጨማሪ መረጃ ወደ
concurrent_enrollment@dpsk12. org ኢሜይል ይላኩ።
BLENDED LE ARNI NG (የተዋሃደ ትምህርት) የኦንላይን ላይ ዲጂታል ሚዲያን
ከተለምዷዊ የክፍል ውስጥ ዘዴዎች ጋር ያዋህዳል።
CAREER AND TECHNICAL EDUCAT ION (CTE፣ የሙያ እና ቴክኒክ ትምህርት) ለተማሪዎች ከሙያ
ጋር ተያያዥነት ባላቸው መንገዶች (የታወቁ የትምህርት አይነቶች ያሏቸው፣ ከሙያ ጋር የተቀናጁ የትምህርት ቤት ፕሮግራሞች) ላይ የሚመዘገቡበት እድል የሚሰጡ የሙያና ኮሌጅ ስኬት ፕሮግራሞች ናቸው። መንገዶቹ የተዘጋጁት ለሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የኢንዱስትሪ የምስክር ወረቀት ወይም የኮሌጅ የምስክር ወረቀት ለመስጠት ታስበው ነው። እውነተኛ ዓለም እና ፕሮጀክት ላይ መሰረት ባደረጉ ፕሮጀክቶች በኩል፣ ተማሪዎች ሙያዊ ክህሎቶችን የሚማሩ ሲሆን መፍትሄዎችን ለማፍለቅም አቅም ይኖራቸዋል። በእያንዳንዱ ት/ቤት ስለሚገኙ የ CTE ፕሮግራሞች እና ቀያሽዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ ይህን ይጎብኙ፥ collegeandcareer.dpsk12. org።
CAREER DEVELOPMENT (የሙያ ልማት) ከK-12ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች
ዝንባሌዎቻቸውና ፍላጎቶቻቸውን ለይተው እንዲያውቁ እና ስለ የወደፊት የሙያ መንገዳቸው በመረጃ የተደፉ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ የሚያስችሏቸው የሙያ አሰሳና ልማት እድሎችን ለማቅረብ ታስቦ የተዘጋጀ የሙያና የኮሌጅ ስኬት ፕሮግራም ነው። DPS ከንግድ ድርጅቶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና እንደ ሙያተኛ ተጋባዥ ተናጋሪዎች፣ የስራ ማዕቀፎች፣ ኢንተርንሺፕ፣ ስልጠና፣ ልምምዶች (የተግባር ልምምድ) እና ሌሎችም የመሳሰሉ ስራን መሰረት የሚያደርጉ ተሞክሮዎችን ከሚያቀርቡ መንግስታዊ ድርጅቶች ጋር በትብብር ይሰራል። ስራ ላይ መሰረት ካደረገ ቀጣይ ፕሮግራም ትግበራ በተጨማሪ፣ የሙያ እድገት ቡድኑ ተማሪዎችን ትርጉም ባላቸው የሙያ ውይይቶች ላይ የሚደግፍ ሲሆን ይህም ተማሪዎች የስራ ግባቸውን የሚደግፉ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉ ነው። በእያንዳንዱ ት/ቤት ስለሚገኙ የሙያ እድገት ፕሮግራሞች እና ቀያሽዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ ይህን ይጎብኙ፥ collegeandcareer.dpsk12.org። COLLEGE LEVEL E X AM I NAT ION PROGR AM (CLEP፣ የኮሌጅ ደረጃ የፈተና ፕሮግራም) የCLEP ተማሪዎችን
በሚያውቋቸው የትምህርት አይነቶች ላይ ለመፈተን የተዘጋጁ የኮሌጅ ቦርድ ፈተናዎች ናቸው። የCLEP ፈተናን የሚያልፉ ተማሪዎች ከኮሌጅ የትምህርት አይነቶች ማለፊያ ጋር ተመሳሳይ ውጤቶች የሚሰጧቸው ሲሆን እነዚህም ተማሪዎቹን የኮሌጅ ዲግሪ ለማግኘት ጊዜና ገንዘባቸውን ለመቆጠብ የCLEP ፈተናዎችን እንዲጠቀሙ ያስችሏቸዋል። DPS 28 የCLEP ፈተናዎችን ለመስጠት የተፈቀደላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉት። የCLEP ፈተና በማንኛውም የተማሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንቅስቃሴ ወቅት ሊወሰድ ይችላል። ለተጨማሪ መረጃ ወደ concurrent_ enrollment@dpsk12.org ኢሜይል ይላኩ። የማህበረሰብ ማዕከሎች ሁሉም ተማሪዎች እኩል የመማርና የመነሳሳት እድል እንዲያገኙ
ለማስቻል የአዋቂና ታዳጊ ህጻናትን የማህበራዊ፣ የስነ ልቡና፣ አካላዊና የትምህርት ፍላጎቶች የሚደግፉ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ። የማህበረሰብ ማእከሎች ለDPS ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አዋቂዎችና ህጻናት ግልጋሎት ይሰጣሉ። COMPETENC Y-BASED LE ARNI NG (በብቃት-ላይ የተመሠረተ ትምህርት) ተማሪዎች ጊዜው፣ ቦታው ወይም
የሚማሩበት ቦታ ምንም ይሁን ምን በትምህርት ይዘቱ ላይ ብቁ መሆናቸውን በማሳየት ወደ ቀጣዩ ደረጃ እንዲያልፉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። CONCURRENT ENROLLMENT (CE፣ የአንድ ላይ ምዝገባ) እና DUAL ENROLLMENT (DE፣ የሁለቲዮሽ ምዝገባ)
ተማሪዎችን ለኮሌጅ የትምህርት አይነቶች በመመዝግ በተመሳሳይ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃና የኮሌጅ ውጤት የሚያገኙበት እድል ይሰጣቸዋል።
ተያያዥ/የአንድ ላይ ምዝገባ የብቁ ተማሪ የትምህርት ወይም ሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት አይነቶችን ጨምሮ በተመሳሳይ ጊዜ በዲስትሪክት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አይነቶች መመዝገብ ተብሎ የሚገለጽ ሲሆን ይህም በአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሚወሰድ ከልምምድ ወይም አፓረንትሺፕ ፕሮግራም ጋር ተያያዥነት ያለው የትምህርት ስራን ሊያጠቃልል ይችላል። ተያያዥ ምዝገባ ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች ያለ ምንም የትምህርት ወጪ መቅረብ አለበት። የትምህርት አይነቶቹ በእድገት ትምህርት ወይም የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ፣ የምስክር ወረቀት ወይም የመግቢያ መንገድ የትምህርት አይነት ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ወይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል የሚዛወሩ መሆን አለባቸው። ተማሪዎች ከ9-12ኛ ክፍል ጀምሮ ለCE ትምህርት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። የሁለቲዮሽ ምዝገባ በተያያዥ ምዝገባ የህግ መስፈርቶች ውስጥ ለማይካተቱ የኮሌጅ የትምህርት አይነቶች መመዝገብ ተብሎ ይገለጻል። የሁለቲዮሽ ምዝገባ ተጨማሪ ክልከላዎች እና/ወይም መስፈርቶች እና ከፍተኛ የምዝገባ ወጪዎች ሊኖሩት ይችላል። ምሳሌዎቹ ከፍተኛ የትምህርት ወጪዎችና የክፍል ደረጃ ክልከላዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ተማሪዎች ከ9-12ኛ ክፍል ጀምሮ ለDE ትምህርት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ የአንድ ላይ ምዝገባ ቡድን (Concurrent Enrollment) በ concurrent_enrollment@ dpsk12.org ኢሜይል ይላኩ። CREDI T RECOVERY (ክሬዲት ማግኛ) ተማሪዎች ለመመረቅ
በትክክለኛው ጎዳና ላይ ይገኙ ዘንድ በበስኬት ላላጠናቀቋቸው ትምህርቶች ነጥብ የማግኛ አማራጭን የሚሰጥ ነው። DPS በሁሉም ዲስትሪክት በሚያስተዳድራቸው ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በብቃት ላይ በተመሰረቱ የመሰመር-ላይ እና የመምህር-ድጋፍ ፕሮግራም መልክ ይሰጣል።
DENVER SCHOL AR SH I P FOUNDAT ION FUTURE CENTER S (የ DENVER ስኮላርሽፕ ፋውንዴሽን የወደፊት ማእከላት) ፣ በበርካታ የ DPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
የሚገኝ ሆኖ፣ ተማሪዎች በአራት-ዓመት፣ በሁለት-ዓመት ወይም በቴክኒክ ትምህርት ቤት ለኮሌጅ ሲዘጋጁ ድጋፍ ይሰጣል። ተማሪዎች
8
ለስኮላርሽፕ እንዲያመለክቱ፣ ዕድሉን እንዲያገኙ እና በኮሌጅ ውስጥ ውጤታማ እንዲሆኑ አማካሪዎች ያግዟቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ denverscholarship.org ን ይጎብኙ። DI SCOVERY L I NK (የግኝት ሊንክ) በዲስትሪክቱ ውስጥ ከ45 በላይ ትምህርት ቤቶች የሚቀርብ በDPS-የሚሰጥ ከትምህርት በፊትና በኋላ ፕሮግራም ነው። የግኝት ሊንክ እንደ ቦታው ላይ ተመስርቶ በክፍያ ላይ የተመሰረተ እና ነጻ ፕሮግራም ያቀርባል። ለተጨማሪ መረጃ equity.dpsk12.org/extendedlearning/discovery-link ን ይጎብኙ። የግኝት ሊንክ በ DPS ትምህርት ቤቶች የሚቀርብ ብቸኛው ከትምህርት በፊትና በኋላ ፕሮግራም አይደለም፤ እባክዎ ስለ ትምህርት ቤቶች ልዩ ፕሮግራሞች የተመለከቱ ዝርዝሮችን ለማግኘት በቀጥታ ትምህርት ቤቶችን ያነጋግሩ። ቅድመ ኮሌጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች በአራት
ዓመታት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቆይታቸው ውስጥ የሁለተና ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ እና በተጓዳኝ የተባባሪ ዲግሪ፣ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማስረጃ ወይም ቢያንስ 60 የኮሌጅ ውጤቶች እንዲሰጡ ታስበው ተዘጋጅተዋል። የቅድመ ኮሌጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚመረጡት በ Colorado ስቴት የትምህርት ቦርድ ነው።
EDCONNECT የአሁን ተማሪዎቻችን ከነገ አስተማሪነት ጋር ለማገናኘት የሚሞክር ዲስትሪክት አቀፍ የትምህርት መንገድ ነው። የEdConnect ፕሮግራም በአንዳንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚቀርብ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማእከላዊ ደረጃ ይቀርባል። የEdConnect ፕሮግራም የተዘጋጀው ተማሪዎችን ለመምህርነት ዲግሪና ፍቃድ የሚያፋጥኑ የመጀመሪያ የኮሌጅ የትምህርት አይነቶችን እንዲወስዱ ለማድረግ ታስቦ ነው። የEdConnect ልምምዶች ለDPS አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር ስራዎቻቸው ተመድበዋል። ለተጨማሪ መረጃ ወደ concurrent_enrollment@dpsk12.org ኢሜይል ይላኩ። E XPEDI T IONARY LE ARNI NG (የተግባር ተኮር ትምህርት)
በዋና ዋና የትምህርት ዓይነቶቸ በተለመደው ዘዴ የሚሰጡ ትምህርቶችን ከማህበራዊ አገልግሎቶችና ከትክክለኛ ፕሮጀክቶች ጋር በማዋሃድ ተማሪዎች ከመማሪያ ክፍላቸው ውጭ ያለውን የገሃድ ዓለም እንዲመረምሩ የሚያግዝ ነው።
INTERNATIONAL BACCALAUREATE (IB) PROGRAMMES (ዓለም አቀፍ ባካሎሬት (IB) ፕሮግራሞች) ለላቀ ትምህርት
ይበልጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ አቀራረብን ይሰጣሉ። የኢንተርናሽናል ባካሎሬት (IB) የመጀመሪያ ዓመታት፣ የመካከለኛ ዓመታት እና የዲፕሎማ ፕሮግራሞች በዓለም ዙሪያ የማይለዋወጥና ከፍተኛ እውቅና ያለው ፈታኝ ሥርዓተ-ትምህርትን ያቀርባሉ። የ IB ትም/ ቤቶች ተማሪዎቻቸው የየሀገራቸውን ቋንቋ እና ባህል ሙሉ በሙሉ እንዲመረምሩና እንዲያውቁ ድጋፍ በማድረግ የመማር ማስተማር ዓለምአቀፋዊ ገጽታዎች ላይም ትኩረት ያደርጋሉ። የIB ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ የተማሪዎችን ዕውቀት፣ ግላዊ ማንነት፣ ውስጣዊ አስተሳሰብ እና ማህበራዊ ክህሎቶችን በማዳበር በከፍተኛ ፍጥነት በሚለዋወጠው እንደመንደር እየጠበበች ባለች ዓለም
የትምህርት ቤት ፕሮግራሞች የቀጠለ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን እንዲዘጋጁ ያደርጋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ IB ኮርሶችንና ፈተናዎችን የሚወስዱ ተማሪዎች በኮሌጅ ቅበላ ሂደቶች ከሌሎች ልቀው የሚወጡ ሲሆን በአሜሪካ ውስጥ በአብዛኞቹ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ክሬዲቶችን የማግኘት ወይም የላቀ አቋም የማግኘት እድል አላቸው። I NTERNAT IONAL FOCUS SCHOOLS (ዓለም አቀፍተኮር ት/ቤቶች) የክፍል ውስጥ ትምህርትን ከአጠቃላዩ ነባራዊ
ዓለም ጋር የሚያስተሳስር ልዩ ሥርዓተ ትምህርትን ያቀርባሉ። ተማሪዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረች ባለች ዓለም ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያግዟቸውን ክህሎቶች እያዳበሩ ልዩ ልዩ ባህሎች እና ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰቦችን ይመረምራሉ።
MONTESSOR I PROGR AMS (የሞንቴሶሪ ፕሮግራሞች)
በራስ-መር የመማር ከባቢ ውስጥ የሕጻናትን ተፈጥሯዊ እድገት ለመከታተል እና ለማገዝ ይረዳሉ። የDPS ሞንቴሶሪ ፕሮግራሞች ህጻናት የፈጠራ፣ የችግር አፈታት፣ የማህበራዊ ኑሮ እና የጊዜ አጠቃቀም ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ ድጋፍ ማደረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራሉ።
NATIVE AMERICAN CULTURE AND EDUCATION (NACE፣ የአሜሪካ ተወላጆች ባህል እና ትምህርት) እና FOCUS SCHOOLS (ትኩረት ት/ቤቶች) የጋራ ታሪክ እና ባሕል ያላቸውን
ተማሪዎች በአንድ ላይ በማሰባሰብ የድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። የ NACE ሰራተኛ ተማሪዎች በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ ሁሉንም አጋጣሚዎች እና ግብዓቶች ማግኘት የሚችሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ዓላማው የአሜሪካን ኢንዲያን እና የአላስካ ተወላጅ ተማሪዎችን የምረቃ ምጣኔ መጨመር ነው። ለተጨማሪ መረጃ NACE ን በ 720-423-2042 ያነጋግሩ። የግል ትምህርት ተማሪዎችን በጊዜ ሂደት የተሟላ የመማር
ስሜት እና የትምህርት እድገታቸው የባለቤትነት ስሜት እንዲያዳብሩ ለማድረግ የተማሪዎችን የህይወት ዘመን የተማሪነት ማንነቶች ማጎልበት ላይ ትኩረት የሚያደርግ የትምህርት አቀራረብ ነው። PRE-COLLEGI ATE PROGR AMS (የቅድመ-ኮሌጅ ፕሮግራሞች) ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃን ካጠናቀቁ በኋላ
ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በማዘጋጀት ላይ ያተኮሩ ናቸው፤ ይህም በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወቅት የኮሌጅ ክሬዲት ማግኘትን ሊያካትት ይችላል።
PROJECT-BASED LE ARNI NG (በፕሮጀክት ላይ የተመሠረተ የትምህርት ዘዴ) ተማሪዎች ረዘም ላለ ጊዜ
ተጨባጭ፣ አሳታፊ እና ውስብስብ ጥያቄ፣ ችግር ወይም ፈተናን ለመመርመር እና ምላሽ ለመስጠት በመስራት እውቀትን እና ክህሎቶችን የሚቀስሙበት ዘዴ ነው።
P-TECH ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (የቴክኖሎጂ የቅድመ ኮሌጅ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች Pathways) የተዘጋጁት ተማሪዎችን ከፍተኛ ክህሎቶችን ለሚጠይቁ የወደፊት ስራዎች ለማዘጋጀት የመንግስት-ግል ትብብር ለመፍጠር ታስበው ነው። P-TECH ልዩ ትኩረቱን የተለያየ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና የዘር ሁኔታ ያላቸው፣ የመጀመሪያው ትውልድ የኮሌጅ ተማሪዎች፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎች እና አካል ጉዳተኛ ተማሪ የሆኑ ተማሪዎች ምዝገባን ማበረታታት ላይ አድርጎ ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ነው። P-TECH ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚመረጡት በ Colorado ስቴት የትምህርት ቦርድ ነው። የP-TECH ሞዴሎች በትላልቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን ሁሉም በተወሰነ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች በP-TECH ውስጥ መመዝገብ አይጠበቅባቸውም።
ወቅታዊ በግዛት የተዘጋጀ DPS P-TECH፥ Abraham Lincoln ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት SERV ICE LE ARNI NG (የአገልግሎት ትምህርት) እንደ
የበጎ ፈቃደኛ ቅንብር ባለ የማኅበረሰብ ፕሮጀክት ላይ ያለን ሥራ በክፍል ውስጥ ከሚካሄዱ ጥናቶች ጋር ያቀናጃል።
STE AM የተለያዩ ሙያዎች የትምህርት አቀራረብ ሲሆን የተማሪ
መጠይቅ፣ ውይይት፣ ፈጠራና ጥልቅ አሳቢነትን የሚመሩ ነጥቦችን ለማግኘት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ አርቶችና ሂሳብን ይጠቀማል።
TE ACHER RECRUI TMENT EDUCAT ION AND PREPAR AT ION PROGR AM ( TREP፣ የመምህር ምልመላ የትምህርት እና ተሳትፎ) በማስተማር መንገድ
ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ለድህረ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት አይነቶች እንዲመዘገቡ የሚያስችል የግዛት ፕሮግራም (SB21-185) ነው። TREP ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በኋላ በነጻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት በሙሉ ጊዜ እንዲማሩ የሚያስችል አምስተኛ/ስድስተኛ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መርሀ ግብር ነው። ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከተመረቁበት ዓመት ቀጥሎ ባለው የመኸር ወቅት አሳታፊ የTREP የኮሌጅ ትምህርት ይከታተላሉ። TREP ለተማሪዎች እንደ ማስተማሪያ ወይም የማማከር አገልግሎት መንገድ ሊያገለግል ይችላል። ከቅድመ ኮሌጅ ወይም የP-TECH ትምህርት ቤት የተመረቁ ተማሪዎች በColorado ግዛት ህግ መሰረት ለASCENT ወይም TREP ብቁ አይሆኑም። ለተጨማሪ መረጃ ወደ concurrent_enrollment@dpsk12.org ኢሜይል ይላኩ።
9
የ DENVER HEALTH የትምህርት ቤት የጤና ማዕከላት በ 19 የ DPS ካምፓሶች ውስጥ የሚገኙት የ Denver Health የትምህርት ቤት የጤና ማዕከላት፣ ለማንኛውም የ DPS ተማሪ፣ ትምህርት ቤታቸው፣ የኢንሹራንስ ሁኔታ ወይም የመክፈል አቅም ምንም ይሁን ምን፣ ነጻ የጤና እንክብካቤ ይሰጣሉ። በልጅዎ ትምህርት ቤት ውስጥ የማይገኝ ከሆነ፣ ለእርስዎ ይበልጥ የሚቀርበውን ማዕከል ሊጠቀሙ ይችላሉ። እነዚህ ማዕከላት በሚከተሉት ቦታዎች ይገኛሉ፡ ■
■
ABRAHAM LINCOLN
(2285 S. Federal Blvd.) BRUCE RANDOLPH
(3955 Steele St.)
■
EAST (1600 City Park Esplanade)
■
EVIE DENNIS ግቢ
(4800 Telluride St.)
■
FLORENCE CRITTENTON
■
GEORGE WASHINGTON
■
JOHN F. KENNEDY
■
(55 S. Zuni St.)
(655 S. Monaco Parkway) (2855 S. Lamar St.) KEPNER ካምፓስ
(911 S. Hazel Court)
■
KUNSMILLER
■
LAKE ካምፓስ (1820 Lowell Blvd.)
■
MANUAL (1700 E. 28th Ave.)
■
MARTIN LUTHER KING, JR. ኧርሊ ኮሌጅ
■
MONTBELLO ካምፓስ
■
NORTH (2960 Speer Blvd.)
■
NOEL ካምፓስ
■
PLACE BRIDGE አካዳሚ
■
SOUTH (1700 E. Louisiana Ave.)
■
■
(2250 S. Quitman Way)
(19535 E. 46th Ave.) (5000 Crown Blvd.)
(5290 Kittredge St.) (7125 Cherry Creek Drive North) THOMAS JEFFERSON
(3950 S. Holly St.)
WEST ካምፓስ (951 Elati St.)
ለተጨማሪ መረጃ denverhealth.org ን ይጎብኙ።
10
ቅድመ-መደበኛ ትምህርት በ DPS ዕድሜያቸው 3 እና 4 ለሆኑ ልጆች
ድረገጽ፥ earlyeducation.dpsk12.org ሥልክ ቁጥር፥ 720-423-2678
የቅድመ-መደበኛ ሕፃናት ትምህርት ወይም ECE በመባልም የሚታወቀው የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ሕፃናት ልጆች በአስተሳሰብ፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና በስሜት እንዲጎለብቱ ያግዛል። ይህ ጠንካራ መሠረት ወደ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ዓመታት ለመግባት እና የመማር ደስታቸውን በተሳካ ሁኔታ ለመቀጠል ያዘጋጃቸዋል። የDPS ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ከ80 በሚበልጡ የDPS ት/ ቤቶች ጥራት ያለው የግማሽ ቀን እና የሙሉ ቀን ቅድመ-መደበኛ ት/ቤት ፕሮግራም ይሰጣል። የ DPS ቅድመ-መደበኛ ት/ቤት ፕሮግራሞች አካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉንም ተማሪዎች ለማገልግል የተነደፉ ናቸው። በቦታ ውሱንነት የተነሳ ለምዝገባው ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም። የColorado Department of Early Childhood (CDEC፣ ኮሎራዶ የቅድመ ትምህርት መምሪያ) ለUniversal Preschool Colorado፣ በተጨማሪም (UPK) ተብሎ ለሚጠራው በአዲስ የምዝገባ ሂደት የቅድመ ህጻንነት ትምህርቱን እያስፋፋ ነው። የDPS ቤተሰቦች ለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት በUPK አሰራር አማካኝነት በ upk.colorado.gov ማመልከት አለባቸው።
ክፍያ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት በክፍያ ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ነው። ክፍያ የሚወሰነው በቤተሰብ ቁጥር መጠን እና ጠቅላላ ገቢ ላይ በሚሰላ የክፍያ ሚዛን ሲሆን ከነፃ እስከ ከዲስትሪክ ውጭ ክፍያ ሊደርስ ይችላል። UPK እያንዳንዱ ህጻን ለአጸደ ህጻናት ብቁ ከመሆኑ በፊት ባለው አመት ውስጥ ለግማሽ ቀን በግዛት የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግለት፣ በፈቃደኝነት የሚሆን የቅድመ ትምህርት ቤት ብቁ መሆኑን ያረጋግጣል። እድሜያቸው 3-ዓመት የሆኑ ብቁ መሆኛ ምክንያቶችን የሚያሟሉ ልጆች የ UPK Colorado ማመልከቻን ካጠናቀቁ ቢያንስ ለግማሽ ቀን (በሳምንት 10 ሰዓት) የቅድመ ትምህርት ፕሮግራም ብቁ ናቸው። እድሜያቸው 4-ዓመት የሆኑና ብቁ መሆኛ ምክንያቶችን የሚያሟሉ ልጆች ለተጨማሪ ከክፍያ ነጻ የቅድመ ትምህርት ቤት ሰዓታት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። እድሜያቸው 4 ዓመት የሆኑ ተማሪዎችም በDenver የቅድመ ትምህርት ፕሮግራም ለሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት መምሪያን በ earlyeducation@dpsk2.org ያነጋግሩ።
እንዴት መመዝገብ እችላለሁ? በECE-3 ወይም ECE-4 ፕሮግራም ለመመዝገብ የሚያመለክቱ ቤተሰቦች በ1ኛ ዙር የት/ቤት ምርጫ ጊዜ ማመልከቻ እንዲያስገቡ በጥብቅ ይበረታታሉ። በዙር 1 የትምህርት ቤት ምርጫ ጊዜ ማመልከቻ ማስገባት ቤተሰቦች በሚፈልጉት የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ ቦታ የማግኘት የተሻለ እድል ይሰጣቸዋል። 1ኛ ዙር የትምህርት ቤት ምርጫ ጃንዋሪ 11 ቀን በ10 a.m. ይከፈትና ፌብሯሪ 12 ቀን 2024 በ4 p.m. ይዘጋል። ከ1ኛ ዙር በኋላ፣ በUniversal Preschool (UPK) ኮሎራዶ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከቻን ለመሙላት እንዲችሉ ቀጣይ እርምጃዎችን ለማሳወቅ DPS ቤተሰቦችን ያገኛል/ያነጋግራል። ኦክቶበር 1 ላይ ወይም ከዚያ በፊት 3 ዓመት የሚያሞሉ ተማሪዎች ለECE-3 የቅድመ-መደበኛ ት/ቤት ፕሮግራሞች ለማመልከት ብቁ ናቸው። ኦክቶበር 1 ላይ ወይም ከዚያ በፊት 4 ዓመት የሚያሞሉ ተማሪዎች ለECE-4 የቅድመ-መደበኛ ት/ቤት ፕሮግራሞች ለማመልከት ብቁ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ ገጽ 4 ን ይመልከቱ።
11
አጸደ-ሕፃናት በ DPS
ዕድሜያቸው 5 ዓመት ለሆኑ ልጆች
ድረገጽ፥ earlyeducation.dpsk12.org ሥልክ ቁጥር፥ 720-423-2678
DPS በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የትምህርት ስኬታማነት የመሰረታዊ ትምህርት እድገትን የሚያበረታቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የሕፃናትፕሮግራሞችን ያቀርባል። የሙሉ ቀን መዋዕለ ህፃናት በአብዛኛዎቹ የ DPS የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ይገኛል። የ Colorado ስቴት ለሁሉም ተማሪዎች የሙሉ ቀን መዋዕለ ህፃናት ወጪን ይሸፍናል። ስለዚህ በማንኛውም የ DPS የመዋዕለ-ህጻናት ፕሮግራም ለመከታተል ምንም ወጪ የለም።
እንዴት መመዝገብ እችላለሁ? ኦክቶበር 1 ላይ ወይም ከዚያ በፊት 5 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ለነፃ የሙሉ ቀን መዋዕለ ህፃናት ብቁ ናቸው። የሚገቡ የአጸደ ሕፃናት ተመዝጋቢዎች በአቅራቢያቸው ባለ ትምህርት ቤት የመመዝገብ ዋስትና አላቸው። በአቅራቢያዎ የሚገኘውን ትምህርት ቤት ለማግኘት፣ schoolfinderdpsk12. orgን ይጎብኙ። ከአጎራባች ትምህርት ቤትዎ በተለየ ትምህርት ቤት ለመከታተል፣ በ DPS SchoolChoice ሂደት በኩል ማመልከት አለብዎት። ለተጨማሪ መረጃ ገጽ 4 ን ይመልከቱ።
12
የመጓጓዣ አገልግሎት (ትራንስፖርት) ድረገጽ፥ transportation.dpsk12.org ስልክ ቁጥር፥ 720-423-4600 ኢ-ሜይል፥ transportation@dpsk12.org
የDPS የመጓጓዣ አገልግሎቶች ምርጥ የደንበኛ አገልግሎት ከማቅረብና የDPS የዲስትሪክት ዋና ዋና እሴቶችን ከመከተል ጎን ለጎን ተማሪዎችን በአስተማማኝና ውጤታማ በሆነ መልኩ
የምዝገባ ዞኖች በምዝገባ ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ ተማሪዎች ለዚያ ዞን የተመደበ የትራንስፖርት አገልግሎት ተተቃሚ ይሆናሉ። ■
ያጓጉዛሉ።
የተናጥል ት/ቤቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት የተመለከተ መረጃ በዚህ መመሪያ ውስጥ በየት/ ቤቱ መገለጫ ክፍል ይገኛል።
በእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ውስጥ ወደ እና ከ DPS ት/ ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማቅረብ በ በእሩቅ ሰሜንምስራቅ እና በመካከለኛ አጎራባች መንደሮች በሞላ በተናጠል አጎራባች መንደሮች በሞላ በተናጠል የሚዘዋወሩ የትምህርት ቤት አውቶቡሶች የምልልስ ሥርዓቶች ናቸው። ስለ Success Express ሸትል የበለጠ ለማወቅ እና ሙሉ መርሀ ግብርችን ለማግኘት transportation.dpsk12. org/eligibility-and-routing/success-expressshuttle/ ን ይጎብኙ። ■
■
የምዕራብ የምዝገባ ዞን፥ በ West የመካከለኛ ት/ቤት የምዝገባ ዞን ውስጥ የሚኖሩና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤትን የሚከታተሉ ተማሪዎችን የሚያገለግል የትራንስፖርት ሥርዓት ነው።
■
ሩቅ ደቡብ-ምስራቅ የምዝገባ ዞን፥ በሩቅ ደቡብ-
የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (ከK-5ኛ ክፍል)
በአጎራባች ወይም በአቅራቢያ ት/ቤታቸው የሚማሩ እና ከት/ቤቱ ከ1 ማይል በላይ ርቀው የሚኖሩ ከሆኑ የመደበኛ አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመጠቀም ብቁ ይሆናሉ። ■
■
ምሥራቅ የመጀመሪያ ደረጃ የምዝገባ ዞን ውስጥ የሚኖሩ ተማሪዎችን የሚያገለግል የአውቶብስ ትራንስፖርት ሥርዓት ነው።
የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (ከ6ኛ-8ኛ ክፍል)
በአጎራባች ወይም በአቅራቢያ ት/ቤታቸው የሚማሩ እና ከት/ቤቱ ከ2.5 ማይል በላይ ርቀው የሚኖሩ ከሆኑ የመደበኛ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመጠቀም ብቁ ይሆናሉ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (ከ9ኛ-12ኛ ክፍል)
(ከቅርብ እና ሩቅ ሰሜን-ምስራቅ Success Express የጉዞ መስመሮች ውጪ) በአጎራባች ወይም በአቅራቢያ ት/ ቤታቸው የሚማሩ እና ከት/ቤቱ ከ2.5 ማይል በላይ ርቀው የሚኖሩ ከሆኑ የክልላዊ ትራንስፖርት ዲስትሪክት (RTD) አገልግሎትን ለመጠቀም ብቁ ይሆናሉ። ብቁ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የክልላዊ ትራንስፖርት ዲስትሪክት (RTD) አገልግሎት መጠቀሚያ ይለፍ ከት/ቤታቸው ያለክፍያ ይሰጣቸዋል። ስለ RTD የአውቶቡስ መስመሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት transportation.dpsk12.org ን ይጎብኙ።
ደቡብ-ምዕራብ የምዝገባ ዞን፥ በ Southwest
የመካከለኛ ት/ቤት የምዝገባ ዞን ውስጥ የሚኖሩና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤትን የሚከታተሉ ተማሪዎችን የሚያገለግል የትራንስፖርት ሥርዓት ነው።
ደረጃ/ስታንዳርድ ■
ከመካከለኛ እስከ እሩቅ ሰሜንምስራቅ አገልግሎት የሚሰጡ SUCCESS E XPRESS መጓጓዣዎች፥
■
የታላቋ PARK H I LL /CENTR AL PARK መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የምዝገባ ዞን፥ በ Park Hill/Central Park
አካባቢዎች የሚኖሩ ተማሪዎችን የሚያገለግል የትራንስፖርት አገልግሎት ሥርዓት ነው። ለተጨማሪ መረጃ transportation.dpsk12.org/
eligibility-and-routing/enrollment-zonetransportationን ይጎብኙ።
የማግኔት ት/ቤቶች እንደ ከፍተኛ ባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ ባለ የማግኔት ፕሮግራም የተመዘገቡ የትራንስፖርት አገልግሎት መስፈርቶችን የሚያሟሉ እና በማግኔት ትራንስፖርት አገልግሎት ዞን ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።
13 13
ተጨማሪ መረጃ የልዩ ፍላጎት ትምህርት በ DPS የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራሞች የሚሰጡት የእያንዳንዱን ተማሪ ፍላጎት መሠረት በማድረግ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው የማዕከል-ተኮር ፕሮግራም ተያያዥ አገልግሎት ተደርጎ ነው። ለልዩ ትምህርት ፍላጎት ተማሪዎች የሚቀርበውን የትራንስፖርት አገልግሎት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለተማሪ እኩልነት/ ፍትሃዊነት እና ዕድል ክፍል በ 720-423-3437 ደውለው ወይም ወደ stutrans@dpsk12.org ኢ-ሜይል በመፃፍ መጠየቅ ይችላሉ። በብዙ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርት በአቅራቢያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በብዙ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርት (MLE) አገልግሎቶች በማይሰጡ ጊዜ፣ ተማሪዎች በአካባቢያቸው ውስጥ የ MLE አገልግሎቶችን በሚያቀርብ ትምህርት ቤት ለመሳተፍ - እንዲሁም ወደ ት/ቤቱ የመጓጓዣ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ ይሆናሉ። የ ELA ት/ቤት አድራሻዎችን እና የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያዎችን ለማግኘት mle.dpsk12.orgን ይጎብኙ። የልዩ ሁኔታ ጥያቄ ሂደት ከአጎራባች ት/ቤታቸው ውጭ “የመረጡ” ወይም ለትራንስፖርት አገልግሎት ብቁ ያልሆኑ ነገር ግን የአውቶብስ አገልግሎትን መጠቀም የሚፈልጉ ተማሪዎች ቤተሰቦች የትራንስፖርት ልዩ ሁኔታ ጥያቄ ሊያስገቡ ይችላሉ። ይህ ጥያቄ በወላጅ ፖርታል በመጠቀም በኦንላይን ላይ ይሞላል፤ myportal. dpsk12.org ን ይጎብኙ እና ወደ "ትራንስፖርት" ገጽ ይሂዱ። ስለ ልዩ ሁኔታ ጥያቄ ሂደት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት transportation.dpsk12.org/eligibilityandrouting/exception-request-process ን ይጎብኙ።
14
የአውቶቡስ ግንኙነቶች በት/ቤት አውቶቡስ የሚጓዙ ተማሪዎች ወላጆች በ SchoolMessenger አማካኝነት ስለተማሪያቸው የአውቶቡስ አገልግሎት ቅጽበታዊ እና ወቅታዊ መረጃን ያገኛሉ። በትራፊክ፣ በድንገተኛ ሁኔታ ወይም በአየር ጸባይ ምክንያት አውቶቡሶች ከ 10 ደቂቃ በላይ በሚዘገዩበት ጊዜ የጽሑፍ፣ እና የድምፅ ማሳወቂያዎች ለወላጆች ይላካሉ። ለትራንስፖርት አገልግሎት ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ወላጆች፣ ልጃቸውን ለትምህርት ቤት ሲያስመዘግቡ በሰጡት የስልክ እና የኢሜይል አድራሻ መሰረት SchoolMessenger ለመቀበል በቀጥታ ይመዘገባሉ።
ማስታወሻ፥ በወላጅ ፖርታል ላይ በመግባት የግንኙነት መረጃዎን ማረጋገጥ እና ማሻሻያ ማድረግ ይችላሉ።
የልጅዎን ፍላጎቶች ማሟላት የባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ አገልግሎቶች ድረገጽ፥ studentequity.dpsk12.org/gifted-talented ሥልክ ቁጥር፥ 720-423-2056
የባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ አገልግሎቶች ምንድን ናቸው? DPS ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ተለይተው የታወቁ ባለተሠጥኦ እና ባለችሎታ (GT/HGT) ተማሪዎችን፣ እንዲሁም በመደበኛ የተሰጥኦ ቋት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን ፍላጎቶች የማሟላት ኃላፊነት አለባቸው። ከK-8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች በGT አስተማሪ የሚደገፉ ሲሆን የቻርተር ትምህርት ቤቶች በተመደበ የግንኙነት ባለሙያ ይደገፋሉ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሳይትን መሰረት ባደረገ ቡድን እና በማእከላዊ አስተዳደር ሰራተኞች ይደገፋሉ። በDPS ትምህርት ቤቶች የሚቀርቡ የGT አገልግሎቶች በመደበኛ ትምህርት ክፍል በባለተሰጥዖ ትምህርት መምህር ጋር በጋራ ከሚቀርብ ትምህርት እስከ የስምሪት ፕሮግራሞች፣ የክላስተር ምደባዎች፣ የችሎታ ምደባዎች፣ የስርዓተ ትምህርት ማጠጋጋት፣ የማፋጠኛ ይዘት፣ የማበልጸጊያ እድሎች እና የማግኔት አገልግሎቶች (HGT ወይም ለማግኔት ብቁ ተብለው ለተመደቡ ተማሪዎች) ያካትታሉ። የባለ ችሎታ ትምህርት አስተማሪ በተለያዩ የመመሪያ አሰጣጦች ላይ ከክፍል አስተማሪዎች ጋር በመተባበር የተሻሻለ የትምህርት እቅድ ላላቸው ተማሪዎች ተመራጭ አሰራሮችን ያቀርባሉ። ተጨማሪ አገልግሎቶች እና እድሎች በመደበኛነት ላልተለዩ ሆኖም በተወሰነ የትምህርት ወይም ችሎታ መስክ ፍላጎት ላሳዩ ተማሪዎች የችሎታ ልማት ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ። ስለ የባለተሰጥኦ እና ባለችሎታ ፕሮግራም በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ በትምህርት ቤትዎ የሚገኘውን የGT አስተማሪ ወይም የግንኙነት ባለሙያ ያነጋግሩ ወይም የGT ፕሮግራም እቅዶችን ከድረገጽ ላይ ይመልከቱ። ለአገልግሎቶች ብቁ መሆን
ተማሪዎች ለአገልግሎቶች ብቁ የሚሆኑባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። ሁሉም በአጸደ ሕፃናት፣ ሁለተኛ እና ስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ለ GT ለመለየት በአጠቃላይ/ዩኒቨርሳል ምርመራ ላይ ይሳተፋሉ። በሌላ የክፍል ደረጃዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ለፎል ወይም ጸደይ/ስፕሪንግ የተዘጋጀውን የፈተና ማመልከቻ መሙላት ይችላሉ። ማመልከቻው እና የማመልከቻ ግዜ ገደቦች በGT ድረገጽ ላይ ይገኛሉ። የከፍተኛ ባለተሰጥ እና ባለችሎታ ፕሮግራም (HGT)
የባለተሰጥኦ እና ባለችሎታ ማግኔት ፕሮግራም ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ለሆኑ ለማግኔት ብቁ ወይም ከከፍተኛ ባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ (HGT) ተብለው ለተለዩ ተማሪዎች የትምህርት አማራጭ ያቀርባል። ይህ የትምህርት አማራጭ የሚቀርበው ልዩ የንቃተ ህሊና ችሎታ እና ልዩ የማህበራዊና ስነ ልቡና ፍላጎቶች የሚያሳዩ ተማሪዎች ከፍተኛ ፍላጎቶችን ለመፍታት ነው። አንድ ልጅ ለማግኔት ብቁ ወይም HGT ሆኖ ከተለየ በኋላ ወላጆች Cory፣ Edison፣ Gust፣ Lena Archuleta፣ Polaris በEbert፣ Southmoor፣ እና/ወይም Teller የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችን እና Morey መካከለኛ ት/ቤትን በSchoolChoice ማመልከቻቸው ውስጥ ማካተት ይኖርባቸዋል። ስለ GT ምደባ ወይም የHGT አማራጮች ለተመለከቱ ጥያቄዎች እባክዎ studentequity.dpsk12.org/gifted-talentedን ይጎብኙ ወይም የአሁን የGT አስተማሪዎን ወይም የባለተሰጥዖ እና ባለችሎታ ተማሪዎች መምሪያን ያነጋግሩ።
15
በብዙ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርት (MLE) ድረገጽ፥ mle.dpsk12.org ሥልክ ቁጥር፥ 720-423-2040
የ MLE አገልግሎቶች ምንድን ናቸው? የእያንዳንዱ ተማሪ ቋንቋ ጠቃሚ ነው፤ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋር ሲቀናጅ ደግሞ በት/ቤት እና በሕይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። Multilingual Education (MLE፣ በብዙ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርት) ፕሮግራሞች Multilingual Learners (MLLs፣ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች) እንግሊዝኛንም እየተማሩ በዐበይት የትምህርት ዓይነቶች እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ በሰለጠኑ መምህራን የሚሰጥ ትምህርት እና በትጋት የማያቋርጥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕድገት ድጋፍ ዋነኞቹ መገለጫ ባሕሪዎቻቸው ናቸው።
ብቁ የሚሆነው ማነው? ዋና ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ያልሆነ እና በእንግሊዝኛ ገና ብቁ ያልሆኑ ተማሪዎች ለ MLE አገልግሎቶች ብቁ ይሆናሉ። በምዝገባ ወቅት፣ ሁሉም የአዳዲስ ተማሪዎች ወላጆች Home Language Questionnaire (HLQ፣የቤት ውስጥ ቋንቋ መጠይቅ) የተባለ አንድ ቅጽ ይሞላሉ፤ ይህም በተማሪው እና በቤተሰቦቹ የሚነገረውን/ሩትን ቋንቋ/ዎች ለመለየት የሚያስችል ነው። በ HLQ ከእንግሊዘኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ከገባ፣ ወላጆች የ MLE ፕሮግራም ለልጃቸው መርጠዋል። ልጁ ለ MLE ፕሮግራም አገልግሎቶች ብቁ መሆኑን ለመወሰን ት/ቤቱ የልጁን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃ ይገመግማል እንዲሁም የተማሪውን ብቃት ይመዝናል።
በ DPS ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የ MLE ፕሮግራሞች ■
ባለ ሁለት ቋንቋ TRANSITIONAL NATIVE LANGUAGE INSTRUCTION (TNLI፣ የመሸጋገሪያ የአፍ-መፍቻ ቋንቋ መማርማስተማር) ፕሮግራሞች፣ ባለሁለት ቋንቋ ፕሮግራሞች ተብለው የሚታወቁ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ስፓኒሽኛ ለሆኑ MLLዎች
የሚሰጡ ናቸው። በአንደኛ ደረጃ የTNLI ፕሮግራም ስር ተማሪዎች በመጀመሪያ ደረጃዎች የስፓኒሽ ቋንቋ የመመሪያ አሰጣጥ ይከታተላሉ። ተማሪዎች በፕሮግራሙ እየቀጠሉ ሲሄዱ አራተኛ ክፍል ሲደርሱ የስፓኒሽና እንግሊዘኛ ቋንቋ መመሪያ አሰጣጥ ምጣኔው 50፡50 እስከሚደርስ ድረስ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመሪያ አሰጣጡ እየጨመረ ይሄዳል። በሁለተኛ ደረጃ የTNLI ፕሮግራሞቻችን ስር ተማሪዎች በእያንዳንዱ መንፈቅ አመት ቢያንስ ሁለት ዋና ዋና የትምህርት ይዘቶችን በስፓኒሽ ቋንቋ ይወስዳሉ። የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ፕሮግራሞች ግብ ተማሪዎን የስፓኒሽ ቋንቋ እውቀትና ይዘት ክህሎቶችን በሚማሩበት በተመሳሳይ ጊዜ እንግሊዝኛ እንዲማሩ በማድረግ የሁለቱም ቋንቋዎች ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ መርዳት ነው። የሁለት ቋንቋ ፕሮግራሞች መምህራን ተማሪዎችን ሌሎች የትምህርት አይነቶችን ከመማር ጎን ለጎን እንግሊዘኛ እንዲማሩ ለመርዳት ልዩ ስልጠና የወሰዱ ከመሆኑም በተጨማሪ ብቁ የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪ ናቸው። በTNLI ትምህርት ቤቶች የመመሪያ አሰጣጡ በምርምር ተኮር የቋንቋ ምደባ መመሪያዎች የሚመራ ሲሆን መመሪያዎቹ በእያንዳንዱ ቋንቋ የሚሰጠውን መመሪያ መቶኛ ይወስናሉ። የትኞቹ ትምህርት ቤቶች በክልል ከ ECE እስከ 12ኛ ክፍል የሁለት ቋንቋ የመመሪያ አሰጣጥ እንደሚያቀርቡ ለማወቅ mle.dpsk12.org/programs/bilingual-tnli/ ን ይጎብኙ።
■
DUAL L ANGUAGE (ባለ ሁለት ቋንቋ) ሁለት ቋንቋ ተናጋሪነትን፣ በሁለት ቋንቋዎች ማንበብና መጻፍን እና የባህል አድናቆትን የማሳደግ ግብ ያለው በሁለት ቋንቋዎች ትምህርት የሚሰጥ የረጅም ጊዜ ፕሮግራም ነው። በ DPS ውስጥ፣ ሁሉም በወረዳ የሚመራ የባለ ሁለት ቋንቋ ፕሮግራም መመሪያው የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ቢያንስ 50 በመቶ መመሪያ ስፓኒሽ፣ እስከ አምስተኛ ክፍል፣ እና በሁለተኛ ደረጃ ላይ የስፓኒሽ ቋንቋ ስነ ጥበባት፣ እንድ አንድ የይዘት አካባቢ በስፓኒሽ ማስተማር ያጠቃልላል። ፕሮግራሙ የትኛውም ቢሆን ሁሉም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች እንግሊዝኛን እንዲናገሩ እና እንዲጽፉ መሠረታዊ ክህሎቶችን (ዘዴዎችን) ለማስጨበጥ የታለመ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕድገት (ELD) ትምህርት በየቀኑ ይሰጣቸዋል።
■
ENGL I SH AS A SECOND L ANGUAGE I NSTRUCT ION (ESL፣ እንግሊዘኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ፣ EL A-E በመባልም ይታወቃል) ማንኛውንም ቋንቋ ለሚናገሩ MLLዎች ነው። በELA-E ፕሮግራሞች ስር የይዘት ትምህርት እንደ አስፈላጊነቱ ከአፍ መፍቻ
ቋንቋ ድጋፍ ጋር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ካላቸው የእድሜ እኩዮች ጋር በእንግሊዘኛ ይሰጣል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ያሉ መምህራን ተማሪዎች እንደ ንባብ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ያሉ ሌሎች ትምህርቶችን ሲማሩ እንግሊዝኛ እንዲማሩ ለማገዝ ልዩ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ትምህርት ቤቶች በተጨማሪም በአፍ መፍቻ ቋንቋ መምህር ወይም የ ELA-S ምንጭ መምህር አማካኝነት በቤት ውስጥ ቋንቋዎ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያደርግልዎ ይችላል። ■
16
የ DPS SE AL OF BI L I TER AC Y (ባለ ሁለት ቋንቋ ችሎታ ማረጋገጫ ማኅተም) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው በሚመረቁበት ወቅት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቋንቋዎችን በብቃት ላጠናቀቁ ተማሪዎች የሚሰጥ ሽልማት ነው። ማኅተሙ በተመራቂ ተማሪው የትምህርት ማስረጃና ዲፕሎማ ላይ እንዲሁም ለወደፊት ቀጣሪዎችና የኮሌጅ ቅበላዎች በሚሰጠው የስኬታማ ማጠናቀቂያ መግለጫ ላይ ይመታል። ለተጨማሪ መረጃ mle.dpsk12.org/seal-of-biliteracy/ ን ይጎብኙ።
■
የአዲስ ገቢዎች ማእከላት ለአሜሪካ አዲስ ለሆኑ፣ ትምህርታቸውን አቋርጠው ለነበረ፣ የ 1.0-2.4 ACCESS ደረጃዎች ያላቸው እና
ከአዲስ የትምህርት ስርዓት ጋር ለመስተካከል ተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው። የአዲስ ገቢዎች ማዕከላት የሚገኙት በ Place Bridge አካዳሚ (K-8)፣ Merrill የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ Abraham Lincoln ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣እና በ South ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።
ስለ MLE አቅርቦቶች የበለጠ ለማወቅ ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ። በትምህርት ቤት የተለየ የ MLE ፕሮግራሞች ዝርዝር በ mle.dpsk12.
org ላይ ይገኛል። ለበለጠ መረጃ በ 720-423-2040 ይደውሉ።
17
የልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ድረ ገጽ ፥ studentequity.dpsk12.org ስል ክ ቁ ጥ ር፥ 720-423-2400 ኢ- ሜ ይል ፥ ess@dpsk12.org
የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶች ምንድን ናቸው? የልዩ ፍላጎት ትምህርት በትምህርት ክትትል ላይ እክል በሚፈጥር የአካል ጉዳት ምክንያት በልዩ ሁኔታ የተነደፈ ትምህርት ለማግኘት ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች በፌደራል የታዘዘ ፕሮግራም ነው። የ DPS ት/ቤቶች በ Individuals with Disabilities Education Act (IDEA፣ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች የትምህርት ህግ) ስር ብቁ የሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ፍላጎቶችን ለማሟላት ትምህርታዊ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ። አንድ ተማሪ ብቁ ከሆነ/ች፣ ለተማሪው/ዋ በልዩ ሁኔታ የተነደፈ የትምህርት አሰጣጥን ለማቅረብ የግለሰባዊ የትምህርት ፕሮግራም (IEP) ይዘጋጃል። ተማሪዎች በተጨማሪ እንደ ነርሶች፣ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች፣ የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኞች፣ ከንግግር ቋንቋ ፓቶሎጂስቶች፣ ከአውድዮሎጂስቶች፣ ከትምህርታዊ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች፣ ብሬይሊስቶች፣ የዝንባሌ እና እንቅስቃሴ ልዩ ባለሙያዎች፣ መስማት ለተሳናቸው እና የመስማት ችግር ላለባቸው መምህራን፣ ማየት ለተሳናቸው ወይም የማየት ችግር ላለባቸው መምህራን፣ የቅድመ ልጅነት የልዩ መምህራን፣ የስራ ቴራፒስቶች እና የአካል ቴራፒስቶች ካሉ ተዛማጅ አገልግሎት ሰጪዎች ድጋፍ ሊያገኙ ይችላሉ።
ብቁ የሚሆነው ማነው? የትኛውም በIDEA ስር ብቁ የሆነ ተማሪ በIDEA በተለዩ በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ምድቦች ስር የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቁ ነው። ወላጆች/አሳዳጊዎች በግምገማና ብቁነት ሂደት ላይ እንዲሁም በግል ትምህርት እቅድ (IEP) ዝግጅት ላይ ይሳተፋሉ። “አካል ጉዳተኛ ህጻን” ማለት፥ በIDEA ግምገማ መሰረት የንቃተ ህሊና አካል ጉዳቶች፣ መስማት አለመቻልን ጨምሮ የመስማት ችግር ያለበት፣ የንግግር ወይም ቋንቋ እክል ያለበት፣ ማየት አለመቻልን ጨምሮ የማየት ችግር ያለበት፣ ከባድ የስነ ልቡና መረበሽ ያለበት (በIDEA aእንደ የስነ ልቡና መረበሽ የተለየ)፣ የአጥንት እክል፣ ኦቲዝም፣ ከባድ የአንጎል ጉዳት፣ ሌላ የጤና እክል ያለበት፣ ልዩ የመማር ችግር ያለበት፣ መስማት-ማየት የማይችል፣ ወይም የተለያዩ አካል ጉዳቶች ያሉበት እና በዚህም ምክንያት የልዩ ትምህርትና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚያስፈልጉት ተብሎ የተለየ ተማሪ ነው።
የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶች የት ይገኛሉ? የቻርተር ት/ቤቶችን ጨምሮ ሁሉም የ DPS ት/ቤቶች አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሊኖሯቸው የሚችሉ ከቀላል እስከ መካከለኛ ክብደት ያላቸውን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟሉ የሚችሉ የተለያዩ የአገልግሎቶች ዓይነቶችን ያቀርባሉ። ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመጠነኛ እስከ መካከለኛ ፕሮግራም ያቀርባሉ። አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለአንዳንድ ተማሪዎች እንደ መስማት የተሳናቸውና የመስማት ችግር ወይም ኦቲዝም ያለባቸው የመሳሰሉ የበለጠ ልዩ ፍላጎቶች የሚሆኑ ልዩ ፕሮግራሞች አሏቸው። የእያንዳንዱ ልጅ የ IEP ቡድን ተማሪዎቹ በዚህ ደረጃ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች እንደሚያስፈልጋቸው ይወስናል።
የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እችላለሁ? ተማሪዎች ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶች በቀጥታ አይመዘገቡም። አንዴ ልጅዎ በትምህርት ቤት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ አገልግሎቶች በአግባቡ የሚጀምሩ መሆኑን ለማረጋገጥ እባክዎ በቀጥታ ትምህርት ቤቱን ያነጋግሩ።
18
19