John 14 : 22 - finish 22 Judas, not Iscariot, said unto Him "ጌታ ሆይ፥ /Geta Hoy/Lord, How is it that Thou will manifest Thyself unto us, and not unto the world?" 23 ኢየሱስ/Eeyesus/Jesus answered and said unto him, "If a man loves Me, he will keep My words: and My Father will love him, and We will come unto him, and make Our abode with him. 24 He that loves Me not, keeps not My sayings: and the word which ye hear is not mine, but the Father's which sent me. 25 These things have I spoken unto you, being yet present with you. 26 But the Comforter, which is the መንፈስ ቅዱስ /Menfes Qidus/Holy Spirit, Whom the Father will send in My name, He shall teach you all things, and bring all things to your remembrance, whatever I have told you. 27 Peace I leave with you, my peace I give unto you: not as the world gives, give I unto you. Let not your heart be troubled, neither let it be afraid.
22 የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ። ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው? አለው። 23 ኢየሱስም መለሰ አለውም። የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። 24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። 25 ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤ 26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። 27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።