Bridge Magazine March 2020

Page 1

BRIDGE MAGAZINE VOLUME 3: ISSUE 1/ DECEMBER 2020

How To Apply For CERB, Canada’s New $2,000 Emergency Response Benefit If you've lost your job because of COVID-19, this is another option alongside EI. Page 20

Emergency Response Benefit...Page 20

ኮሮናቫይረስ፡ ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች...ገጽ 7

እንኳንም ሞት አለ!...ገጽ 10

የኮረና ቫይረስ ባሕሪና መከላከል...ገጽ 15

COVID-19 INFORMATION FOR ETHIOPIANS & ERITREANS IN CANADA • ኮሮናቫይረስ፡ ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች...ገጽ7

• የኮረና ቫይረስ ባሕሪና መከላከል...ገጽ 15

የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ገጽ 14፣ ገጽ 21 እና ገጽ 23 ጠቃሚ ነውና ያንብቡ

World Economic Page 16

Measures to flatten the curve of COVID-19 beginning to work, says Trudeau ...Pge 18 የኮሮናቫይረስ መድሃኒትን ወይም ክትባቱን ለማግኘት ሳይንቲስቶች ምን ያክል ተቃርበዋል? ....ገጽ 12


ድልድይ መጽሔት / SEPTEMBER MARCH 20202018

2

https://www..mytzta.com /https:www.tzta.ca https://www.tzta.ca 2


ድልድይ መጽሔት / MARCH SEPTEMBER 2020 2018

3

3

https://www..mytzta.com /https:www.tzta.ca https://www.tzta.ca


የድልድይ መጽሔት ማውጫ CONTENTS

COVER

Emergency Response Benefit...Page 20

ኮሮናቫይረስ፡ ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች...ገጽ 7

እንኳንም ሞት አለ!...ገጽ 10

የኮረና ቫይረስ ባሕሪና መከላከል...ገጽ 15

የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ገጽ 14፣ ገጽ 21 እና ገጽ 23 ጠቃሚ ነውና ያንብቡ

የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ

Canada Emergency Response Benefit (CERB).

World Economic Page 16

March 25, 2020 - Ottawa, Ontario - Department of Finance Canada

Measures to flatten the curve of COVID-19 beginning to work, says Trudeau ...Pge 18

ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

የኮሮናቫይረስ መድሃኒትን ወይም ክትባቱን ለማግኘት ሳይንቲስቶች ምን ያክል ተቃርበዋል? ....ገጽ 12

4

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

5

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


MARTA FASHION & GIFTS SHOP INC. Fashionable Women Clothing Accessories& Home Decore 35 Church St. Toronto 647-869-2382

ማርታ ፋሽን እና የልብስ መሸጫ መደብር (የሴቶች ልብስ አልባሳት ማሟያዎች እና የቤት ዲኮር) ለማንኛውም በስልክ ቁጥር 647- 869-2382 ማርታ ብላችሁ ደውሉልን በተጨማሪም በአድራሻችን ማለት 35 Church Street East Side, Toronto መጥታችሁ ጎብኙን።

ድልድይ መጽሔት /MARCH 2020

6

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ኮሮናቫይረስ፡ ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች 18 ማርች 2020

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ቫይረሱን ለመካላከል ይጠቅማል; በሽታውን በመከላከል በኩል የፊት ጭንብል የሚኖረውን አስተዋጽኦን በተመለከተ በጣም ውስን መረጃ ብቻ ነው ያለው። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ወረርሽኙን ለመከላከል የግል ንጽህናን በአግባቡ መጠበቅ ወሳኝ ነው። በተለይ ደግሞ እጃችንን ወደ አፋችን፣ አፍንጫችንና ዓይናችን ከማስጠጋታችን በፊት በአግባቡ መታጠብ ከሁሉ የላቀ ውጤታማ መከላከያ ነው። ቫይረሱ ያለበት ሰው እጁ ላይ አስሎ ወይም አስነጥሶ የበር እጀታዎችንና ሌሎች ነገሮችን ከነካ ቫይረሱን ወደ ተነካው እቃ ሊያሸጋግር ይችላል። ስለዚህም በበሽታው ላለመያዝና ስርጭቱን ለመግታት እጅን በመደበኛነት መታጠብ ወሳኙ የመከላከያ መንገድ ነው። የበር እጀታዎች በተለያዩ ሰዎች ስለሚነኩ በሽታውን በማስተላለፍ በኩል አንድ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። ባለሙያዎች

እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በተለያዩ ቁሶች ላይ ለቀናት በህይወት በመቆየት ወደ ሰዎች ሊተላለፍ ይችላል። በሽታው በግብረ ሥጋ ግንኙነት ይተላለፍ እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። በአሁኑ ወቅት ለበሽታው መተላላፊያ ተብለው የሚጠቀሱት ማሳል፣ ማስነጠስና በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን መንካት ናቸው። በእርግጥ እስከአሁን ኮሮናቫይረስ መደሃኒት ወይም ክትባት አልተገኘለትም። ስለሆነም አንዳንድ አባባሎችን መጠንቀቅ አለብን። ለምሳሌ እንደሚከተለው፤ • ነጭ ሽንኩርት ዝናዋ በዓለም የናኘ ነው። የፌስቡክ ገፅ ቢኖራት ኖሮ 6 ቢሊዮን ሕዝብ የሚከተላት ነጭ የደረበች ሽንኩርት. . . ። ነጭ ሽንኩርት ፌስቡክ ለመቆጣጠር ገፅ አላሻትም። የኮሮናቫይረስን መፈወሻ ተበለው ፌስቡክ ላይ ዝናቸው ከናኘ ነገሮች መካከል ነጭ ሽንኩርት አንደኛ ነች። ግን ኮሮናን መከላከልም ሆነ ማዳን ትችል ይሆን? ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ግን እንዲህ ይላል ነጭ ሽንኩርት ብሉ በውስጡ መልካም ነገር አዝሏልና፤ ነገር ግን ከአዲሱ ቫይረስ ሊከላከል እንደሚችል በሳይንስ አልተረጋገጠም።

Cell:

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

እርግጥ የዶ/ር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት እንዳለው ነጭ ሽንኩርት በልኩ መብላት ይመከራል። ከኮሮናቫይረስ ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር የለም። ደቡብ ቻይና ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ይታደገኛል ብለው 1.5 ኪሎ ግራም ነጭ ሽንኩርት ‘ዱቄት’ ያደረጉ አንዲት ሴት ጉሮሯቸው ተቃጥሎ በሕክምና ነው የዳኑት። የዓለም ጤና ድርጅት፤ ፍራፍሬና ጥራጥሬ እንዲሁም አትክልት በልኩ ተመገቡ፤ ውሃም ጠጡ ይላል። ነገር ግን ይላል ድርጅቱ. . . ነገር ግን ኮሮናን ይታደጋል ተበሎ ፈቃድ የወጣለት ምንም ዓይነት ምግብ እስካሁን አልተገኘም። • ተዓምረኛ ንጥረ-ነገሮች፡ ዩቲዩበኛው ጆርዳን ሳዘር በተለያዩ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ብዙ ሺህ ተከታዮች አሉት። ይህ ግለሰብ አንድ ‘ኤምኤም የተሰኘ ተዓምራዊ ንጥረ-ነገር የኮሮናቫይረስን ድራሽ ማጥፋት ይችላል’ እያለ ይሰብካል። ንጥረ ነገሩ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ የተሰኘ አንጭ ኬሚካል አዝሏል። ጆርዳንና መሰሎቹ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ ያለበት ኤምኤም የካንሰር ሴልን ያጠፋል እያሉ ይሰብኩ ነበር። አሁን ደግሞ ለኮሮናቫይረስ ፍቱን መድኃኒት ነው ብለው ብቅ ብለዋል። ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት ገጽ 8 ይመልከቱ

647-988-9173 . Phone 416-298-8200

7

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ከገጽ 7 የዞረ

አስተዳደር ይህንን ኬሚካል መጠጣት ለጤና እጅግ አስጊ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር። መሥሪያ ቤቱ ይህንን ኬሚካል የምትጠጡ ወዮላችሁ፤ ኬሚካሉ በሽታ እንደሚከላከል የሚጠቁም ጥናት የለም ሲል ነው ያስጠነቀቀው። አልፎም ኬሚካሉ ሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽን አሟጦ በመጨረስ ለከፍተኛ የውሃ ጥም ሊያጋልጥ ይችላል።

• ጓዳ ሠራሽ ‘ሳኒታይዘር’ ባለሱቅ፤ ሳኒታይዘር አለ?» «ውይ! አንድ ቀርታ ነበር። እሷን ደግሞ ለእኔ . . .»ከመዳፎቻችን ላይ ባክቴሪያ ነሽ ቫይረስ እንዲሁም ቆሻሻ ያስወግዳሉ የሚባልላቸው ‘ሳኒታይዘሮች’ [ተህዋሲያን ማጽጃ ፈሳሽ] ከገበያ እየጠፉ ነው። ጣልያን ውስጥ ነው አሉ። የሳኒታይዘር እጦት የወሬ ሟሟሻ ሆነ። ኮሮናቫይረስ ሰቅዞ የያዛት የጣልያን ነዋሪዎች ታድያ ወደ ኩሽና ገቡ። የተገኘውን ነገር መቀላቀል ጀመሩ። በአገሬው ዘንድ ታዋቂ የሆነ አንድ ኬሚካል ግን ቆዳ እንዲያፀዳ ሳይሆን እምነ-በረድ እንዲያፀዳ የተሰናዳ ነው። በተለይ ደግሞ ውስጣቸው በመቶኛ ከፍ ያለ የአልኮል መጠንን ያዘሉ ፈሳሾች ለመቀየጫነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ደግሞ የምንጠቀማቸው ሳኒታይዘሮች ቢያንስ ከ60-70 በመቶ የአልኮልነት መጠን ቢኖራቸው ሲል ይመክራል። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ኩሽና ውስጥ ቫይረስና ባክቴሪያ የሚገድል ‘ሳኒታይዘር’ ማምረት ከባድ ነው ይላሉ። ቮድካ እንኳ 40 በመቶ ብቻ የአልኮል ይዘት ነው ያለው። • እና ሌሎች. . . ከላይ ከተጠሱት አልፎ የቀለጠ ሲልቨር መጠጣት፣ ውሃ በ15 ደቂቃ ልዩነት መጠጣ [የሞቀ ውሃማ ፍቱን ያሉም አልጠፉም]፣ ሙቀት ማግኘት እና አይስ ክሬም አለመላስ የኮሮናቫይረስን ለመፈወስ ፍቱን ናቸው ተብለው በማኅበራዊ ድር-አምባዎች ማስታወቂያ የተሠራላቸው ናቸው። ሳይንሱ ግን እስካሁን የተረጋገጠ ፈውስ አልተገኘም ይላል። ነገር ግን በሽታውን ለመከላከል ዋናውና ቀላሉ መፍትሔ እጅን በሳሙን በደንብ ፈትጎ መታጠብ፣ የእርስ በርስ ንክኪን መቀነስ፣ ፊትን በእጅ አለመነካካት፣ በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ አለማድረግ. . . ነው። አደራዎትን 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ስልቅጥ አድርገው በጠላ ካወራረዱ በኋላ እንደ ዉሃኗ ነዋሪ ርዕሰ-አንቀፅ እንዳይሆኑ። ሐኪም ያላዘዘውን መጠቀም ጠንቅ ነውና!

ገጽ 11 ይመልከቱ

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

8

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

9

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


እንኳንም ሞት አለ! – በላይነህ አባተ March 28, 2020 |

መጽሔት አስፍረዋል፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo. com) ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኮሮና በሽተኛ የአገሪቱ የህክምና አገልግሎቶች ማስተናገድ ስላልቻሉ የጣሊያን ሐኪሞች የህይውት ዘመናቸው የተገባደደውን እየተው ለመኖር ብዙ እድሜ ለቀራቸው አገልግሎት ለመስጠት እንደተገደዱ ዓለም ተመልክቷል፡፡

አዲሱ አድራሻችን፡ 2704 Danforth Ave. Toronto New Location under the new management

ይኸንን ህሊናን የሚፈታተን ውሳኔ በበለጠገችዋ ጣልያን የተመለከተ በዘራፊዎች በደኸየችውና በዘር የገመድ ጉተታ በተወጠረቺው ኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችለውን ኢፍትሐዊ የኮሮና ሕክምና ሂደት ታሰበው እንኳንም ሞት አለ ሊያሰኘው ይችላል፡፡ ህሊና ያለውና ከሙያ ሥነምግባር እስከመጨረሻው ያልተፋታ ምሁር ቢገኝ ፍትሀዊ የህክምና አገልግልቶትን በተመለከተ መንደርደሪያ የሚሆን ሐሳብ በታማኝነቱና በተነባቢነቱ በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው የኒው ኢንግላድ የሕክምና መጽሔት በዚህ ወር እትሙ አቅርቧል፡፡* ይህ መጽሔት የሰነዘረውን ሐሳብ ቃል በቃል ሳይሆን ለአንባቢያን በሚገባ መልኩ እንደዚህ ቀርቧል፡፡ የቀረበውን ሐሳብ እንደ መንደርደሪያ መንገድ መጠቀም እንጅ የምዕራባውያንን የሥነ ምግባር ጦማር እንደ ጦጣ ቀድቶ እንደ ሶሻሊዝምና ካፒታሊዝም በሕዝባችን ጫንቃ የመጣሉን እውር አኪያሄድ ማስወገድ ይገባል፡፡

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

10

የሕክምና አካላዊና መንፈሳዊ እሴቶች ባጠሩበት በዚህ የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ቅድሚያ አገልግሎት ማግኘት የሚገባው ማን እንደሆነ ለመወሰን የሚከተሉትን መርሆች እንዲመረኮዙ የህክምና ጠበብቶች በኒው ኢንግላንድ የህክምና

የጤና ባለሙያዎች ቅድሚያ አገልግሎት ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው ተሌላው ማህበረ ሰብ የተለዩ ስለሆኑ ሳይሆን ቶሎ አገግመው ይህንን ወረረሽኝ ለመታገል የሚያስፈልጉ ኃይሎች ስለሆኑ ነው፡ ፡ ስለዚህ የጤና ባለሙያዎች እንደ ፊት መሸፈኛ፣ ክትባት፣ የማገገሚያ አልጋዎችና ላቦራቶሪ የመሳስሉ አገልግሎቶች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ለመድሀኒት ወይም ክትባት ምርምር መሞከሪያ በመሆን የሚሳተፉ ሰዎችም ቅድሚያ አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል፡ ፡ በበእነዚህ ሰዎች ላይ የሚደረገው ምርምር ለዓለም ሕዝብ መድህን የሚሆን መድሀኒት ወይም ክትባት ሊፈጥር ስለሚችል የሙከራ ሰዎች ቅድሚያ የህክምና አገልግሎት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይኸንን ማድረጉ ሌሎችም ለመሞከሪያነት በፈቃደኝነት እንዲመዘገቡ ይገፋፋል፡፡ ተቁጥር አንድና ሁለት ውጪ ላሉ በሽተኞች የቅድሚያ አሰጣጡን ጠበብቱ የወሰኑት ጀርሚ ቤንታም የተባለ እንግሊዛዊ ፈላስፋ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በቀመረው ዩቲላተራሊዝም መርህ ተመርኩዘው ይመስላል፡፡ የዩቲላተላዝም ፍልስፍና ከፍተኛ ጥቅም የሚያመጣውን ወይም አብዛኛውን ሰው የሚጠቅመውን ወይም የሚያስደስተውን ተግባር ፈጥም ይላል፡፡ በዚህም መሰረት መጽሔቱ መዳን ለሚችሉ ብዙሐን ወይም ቢተርፉ ብዙ ዓመት ሊኖሩ ለሚችሉ ቅድሚያ ይሰጥ ይላል፡፡ የጣሊያን ሀኪሞች እየተገበሩ ያሉትም ይኸንን ይመስላል፡፡ “እግዜር የመረጠውን ጠርቶ ይውሰድ” በሚባልበት በእኛ አገር ይህ መርህ ዱላ ሊያማዝዝ ይችላል፡፡ ቢተርፉ የመኖር እድላቸው ተመሳሳይ ዘመን ሊሆን የሚችሉ በሽተኞች የህክምና አገልግሎት “ቀድሞ የደረሰ ይውሰድ” በሚል መወሰን እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡ ቀድሞ በደረሰ መሆን የሌለበት ምክንያትም ከጤና ተቋማት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ብቻ ተጠቃሚ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያን

ገጽ 11 ይመልከቱ

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ከገጽ 8 የዞረ አንፃር ሲታይ ቀድሞ የደረሰ ይታከም ከተባለ ተህክምና አገልግሎት እጅግ እርቆ የሚገኘውን 85% የአገሪቱ ሕዝብ ይሙት ብሎ እንደ መወሰን ነው፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር አገልግሎት አሰጣጡ በእጣ ወይም በሎተሪ መልክ ቢሆን የተሻለ ፍትሐዊ ይሆናል ባይ ናቸው፡፡ የህክምና ቅድሚያ አሰጣጡ ሳይንሳዊ ምርምሮችን የተከተለ መሆን ይገባዋል፡ ፡ ለምሳሌ የኮሮና በሽታ ሽማግሌዎቹንና ሥር የሰደደ በሽታ ያለባቸውን የበለጠ እንደሚያጠቃ ሳይንስ አረጋግጧል፡ ፡ ስለዚህ በኮሮና ተመለከፍ በፊት የሚደረጉት እንደ ክትባት ያሉ መከላከያዎች ቅድሚያ ለእነዚህ ሰዎች መሆን ይገባቸዋል፡፡ በኮሮና በጠና ከታመሙ ግን የመትረፍ እድላቸው ስለሚያጠራጥር ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው አልጋዎች ታክመው ሊዲኑ ለሚችሉ በሽተኞች ቢሆን ይመረጣል፡፡ ኮሮናን ለመቆጣጠር የሚደረገው እርብርብ በስኳር፣ በኩላሊት፣ በጉበት፣ በልብና ሌሎችም በሽታዎች የሚሰቃዩትን በሽተኞች እንዳያስረሳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ አንባቢያን እንደተለመደው “ ድካምህ ከንቱ ነው በኢትዮጵያ ተውጪ ዘመናዊ ሕክምና የሚያገኙት ነፍሰገዳይ ባለስልጣናት፤ በአገር ውስጥም የተሻለውን የህክምና አገልግሎት የሚያገኙት ዘርፈው የከበሩ ዲታዎችና ዘመድ ያላቸው” እንደሚሉኝ ይገባኛል፡፡ አንባቢ ባይነግረኝም ዘራፊና ባለስልጣኖች እያንዳንዱን ገበሬ ማህበር ሆስፒታል ማዳረስ የሚችል ገንዘብ በአውሮጳ፣ አሜሪካ፣ ኤስያና ደቡብ አፍሪካ የቁንጣን ቁርጠት ለመታከም እንደሚደፉ እገነዘባለሁ፡፡ የደፋው ቆብ የሚያስገድደውን ግዴታ መወጣት ቀርቶ ትርጉሙን የሚያውቅ ፓትርያሪክና ጳጳስ በላንባዲና ተፈልጎ የማይገኝበት ዘመን የደርስን መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ሼህ፣ ሃጂና ፓስተሮች ተነፈሰ ገዳዮች ሲወባሩና ሲላላሱ የሚውሉበት ወቅት መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ሙያና ሥነምግባር እንደ ተተኮሰ ቀለህና እርሳስ ተለያይተው ምሁራን የነፍሰ ገዳይ ካድሬዎችና ሎሌዎች ሆነው የሚያገለግሉበት ዘመን እደሆነም አውቃለሁ፡፡

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

11

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሶቅራጥስ በቃላቸው ጸንተው እንደ ኢዮብ መከራን እየተቀበሉ የሚኖሩ ጥቂቶች እንዳሉ እገምታለሁ፡፡ እነዚህ ተፍትህና ተእውነት መቃብር በሚያለቅሱት እንባ የህሊና

ዓይኖቻቸው የቆስሉ ጥቂቶች ያዳምጣሉ ብዬም አስባለሁ፡፡ ሌላውን ገድለው ወይም አስገድለው መኖር ለሚጓጉ፤ ሌላውን አስርበውና አስጠምተው ዲታ ለመሆንና ሽቅብ ለመሽናት ለሚቋምጡት፣ የሌላውን የመታከም እድል ዘግተው እነሱ ተፈውሰው ረጅም እድሜ ለመኖር ለሚሹ የምለው ስምንተኛ ክፍል ሳለሁ በአማርኛ ክፍለ-ጊዜ ሽንጤን ገትሬ የተከራከርኩበትን ርዕስ ነው:- እንኳንም ሞት አለ! ነፍሰ-ገዳይ ዘራፊ ባለስልጣን ሆይ! ተባሩድህ የተረፈውን ሕዝብ በኮሮናና በሌሎችም በሽታዎች አስጨርሰህ አንተ ውጪ አገር ለመታከም ታቀድክ ዛሬ ብታመልጠው ነገ አንቆ ሲው የሚያደርግህ እንኳንም ሞት አለ፡፡ በመስቀልህ የማትገዛው ጳጳስና ፓትርያሪክ ሆይ! ተባሩድ፤ ተቆንጨራና ተታቦት ቃጠሎ ተርፈው አስራት የምትቀበላቸው ምእመናን በኮሮና ሲያልቁ ዝም ታልክ ይኸንን የአስራት ድሎትህን የሚነፍግ እንኳንም ሞት አለ፡፡ መንኩሰ ሞተን ረስተህና ለሥጋህ ሳስተህ በጎችህን እያሳረድክ የምትኖር ህሊና አልባ አለማዊ መነኩሴ እንኳንም ሲው የሚያደርግ ሞት አለ፡፡ ሙያህ የሚጠይቀውን ግብረገብነትና ስትመረቅ የማልከውን መሐላ እንደ ቀበኛ ላም ቦጫጭቀህ ነፍስ አጥፊዎችን በማገልገል ላይ ያለህ ሐኪም፣ ጠበቃ፣ ዳኛ፣ መሀንዲስ፣ የምጣኔ ሐብት በላሙያና ሌላህም በሆድህ ተገዝተህ ሕዝብህ ባለቤት እንደ ሌለው ጫካ ሲጨፈጨፍ ዝምብለህ ስለኖርክ እንኳን ሞት አለልህ፡፡ አሁንም ጅብ ተማሪን ሲያፍንና ኮሮናም ሕዝብን ሲጨረግድ ጪጭ ብለህ ተቀረህ እንኳን ቀን ጠብቆ ና የሚል ሞት አለህ፡፡ ሞት ተፊታችን እንደ ክረምት ጨለማ ተገትሮ ምድር ያልቻለውን ግፍ ተፈጠምን ሞት ባይኖር ህዋም የማይችለው ግፍ እንፈጥም ስለነበር እንኳንም ሞት አለ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ *Who Gets Health Resources in a Covid-19 Pandemic? The New England Journal of Medicine https:// www.nejm.org/doi/full/10.1056/ NEJMsb2005114?query=featured_ coronavirus መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮናቫይረስ መድሃኒትን ወይም ክትባቱን ለማግኘት ሳይንቲስቶች ምን ያክል ተቃርበዋል? 26 ማርች 20

አይዘነጋም። ክትባቱ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ሊታደግ ይችላል?

የኮሮናቫይረስ መድሃኒትን ወይም ክትባቱን ለማግኘት ሳይንቲስቶች የሚያደርጉት ጥረት ምን ይመስላል? ኮሮናቫይረስ በመላው ዓለም እየተስፋፋ ቢሆንም ወረርሽኙን የሚያስቆም ክትባትም ሆነ መድሃኒት እስካሁን አልተገኘም። በመሆኑም ሕይወትን ለመታደግ የሚያስችለውን መድሃኒት ለማግኘት ምን እየተሰራ ነው? የሚለውን ጥያቄ በወረርሽኙ የሚሰቃዩም ጭንቀት የሆነባቸው ሰዎችም ይጠይቃሉ። የቫይረሱን ክትባትና መድሃኒት ለማግኘት ምርምሮች በአይን እርግብግቢት ፍጥነት እየተከናወኑ ነው። 20 የሚደርሱ ክትባቶች በሂደት ላይ ናቸው። አንደኛው ክትባት እስከ ዛሬ ባልተለመደ መልኩ ከእንስሳት ላይ ሳይሞከር በቀጥታ በሰው ላይ ተሞክሯል። ሌሎች ሳይንቲስቶች ደግሞ እንስሳት ላይ እየሞከሩ ሲሆን በዚህ ዓመት መጨረሻ በሰው ላይ ይሞክራሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። በእርግጥ ሳይንቲስቶች ተሳክቶላቸው ክትባቱን በዚህ ዓመት መስራት ቢችሉ እንኳን የተገኘውን ክትባት ለመላው ዓለም በሚበቃ መልኩ አምርቶ የማቅረብ ቀሪ ብዙ ሥራ ይኖርባቸዋል። ይህም ማለት ቢያንስ እስከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ድረስ ክትባቱ ላይደርስ ይችላል ማለት ነው። ሁሉም ነገር ባልተጠበቀ ፍጥነት እየተከናወነ ያለ ተግባር ነው። በዚህ ፍጥነት ደግሞ ምንም እክል እንደማያጋጥም እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በአሁኑ ወቅት በሰው ላይ እየተስፋፉ ያሉት አራት የኮሮናቫይረስ አይነቶች ናቸው። ሁሉም ጉንፋንን ያስከትላሉ። ለዚህ ደግሞ ምንም ክትባት አልተዘጋጀም።

በትልልቅ ሰዎች ላይ የሚኖረው ፈዋሽነት ያን ያክል ላይሆን እንደሚችል ይጠበቃል። ይህ ደግሞ የክትባቱ ችግር ሳይሆን በእድሜያቸው የገፉ ሰዎች ያሏቸው በሽታን የሚከላከሉ ሕዋሳት በፍጥነት በሽታን ለመከላከል መልስ አይሰጡም። ይህ ደግሞ በየዓመቱ በተለያዩ ወረርሽኞች ላይ ተሞክሮ የተረጋገጠ ነው። የጎንዮሽ ጉዳት ይኖረው ይሆን? ሁሉም መድሃኒቶች የህመም ማስታገሻን ጨምሮ የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው። ነገር ግን አንድ በሂደት ላይ የሚገኝ ክትባት ምን ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ማረጋገጥ የሚቻለው በክሊኒካል ሙከራ ነው። ይህ ደግሞ ጥብቅ ክትትል የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ክትባቱን ሊያገኝ የሚችለው ማን ነው? ክትባቱ ከተገኘ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት የክትባቱ ስርጭት የተገደበ ይሆናል። ከዚያም ውጤቱ ከታወቀ በኋላ ለማን ቅድሚያ እንደሚሰጥ ይወሰናል ማለት ነው። ኮቪድ-19ን [ኮሮናቫይረስን] ከፊት ሆነው የሚዋጉት የሕክምና ሞያተኞች የመጀመሪያዎቹ የክትባቱ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። በትልልቅ ሰዎች ላይ ክትባቱ በትክክል የሚሰራ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ አዛውንቶች ቀጣዮቹ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ይሆናል ማለት ነው። ወይም ደግሞ አዛውንቶችን የሚንከባከቡ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ንክኪ ስለሚኖራቸው እነሱም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ወገኖች መካከል ናቸው። የመድሃኒቱ ሁኔታስ? ሐኪሞች የጸረ ቫይረስ መድሃኒት እየቀመሙ ሲሆን ይህም በኮሮናቫይረስ ላይ ይሰራ እንደሆን እየሞከሩ ነው። ይህም ሰዎችን ማዳን የሚችል መሆኑን ለማረጋገጥ ምርምሮች በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰሩ ይገኛሉ። ቫይረሱ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሰባቸው አገራት ላይ በየካቲት ወር ሙከራው ተካሂዶ ነበር። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ብሩስ አይልዋርድ “በአሁኑ ወቅት ውጤታማና በትክክል ይሰራል ብለን የምናስበው አንድ መድሃኒት ብቻ ነው” ማለታቸው

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

12

ይህም መድሃኒት ለኢቦላ ተብሎ የተዘጋጀ ሲሆን በርካታ የቫይረስ አይነቶችን እንደሚገድል ተረጋግጧል። ቢሆንም ግን በኮሮናቫይረስ ላይ የሚኖረው ፈዋሽነት የሙከራ ውጤቱ እየተጠበቀ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ በሽታዎች ሊኖሩባቸው ስለሚችል እነሱ ሆስፒታል ገብተው መታከም ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ክትባቶች ሰውነትን በማይጎዳ መልኩ በአካላችን ውስጥ እንዲገቡ ተደርገው በሽታ ተከላካይ ሕዋሳቶቻችን ባክቴሪያዎችንና ቫይረሶችን እንዲያወቋቸው ያደርጋሉ። ከዚያም ሰውነታችን እውቅና ይኖረውና እነዚህ ቫይረሶች ወይም ባክቴሪያዎችን እንደ ወራሪ ስለሚያያቸው ባጋጠሙት ጊዜ ወዲያውኑ መዋጋት ይጀምራል። ሰውነታችን ከዚያ በፊት ተጠቅቶ ቢሆን እንኳ እንዴት መዋጋት እንዳለባቸው ስለሚያውቁ ወዲያውኑ ሥራቸውን ይጀምራሉ።

በሁለት የኤችአይቪ መድሃኒቶች (ሎፒናቪር እና ሪቶናቪር) ላይ ትልቅ ተስፋ ተጥሎ ነበር፤ የሙከራ ውጤቱ ግን ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው የሆነው። ሰርቷል ለማለት የሚያስደፍር አይደለም። መድሃኒቶቹ ምንም መሻሻል አላሳዩም፤ የኮቪድ-19 በሽታ የበረታባቸውን መፈወስም ሆነ ከሞት መታደግ አልቻለም። በጣም ከበረታባቸው ሰዎች ላይ ሲሞከር መድሃኒቱ ቫይረሱን መዋጋት የሚጀምረው በጣም ዘግይቶ ነው። ምናልባትም ሊሞቱ ሲቃረቡ ማለት ነው። በእርግጥ የወባ በሽታ መድሃኒት (ክሎሮኩን) ላይም የመስራት ሰፊ ፍላጎት አለ። በቤተ ሙከራ በተደረገ ሙከራ መድሃኒቱ በትክክል እንደሚሰራ ቢረጋገጥም ታማሚዎች ላይ ግን ሙከራ ተደርጎ ውጤቱ ገና አልታወቀም። ሙከራዎች በአሜሪካና በሌሎች አገራት ላይም በመደረግ ላይ ናቸው። ታዲያ ክትባት ወይም መድሃኒት እስኪገኝ ምን እናድርግ? አሁን ላይ ያለው የተሻለውና ከኮሮናቫይረስ ሊከላከል የሚችለው ክትባት እጅን በደንብ መታጠብ ብቻ ነው። አንድ ጊዜ በበሽታው ከተያዙ ደግሞ በሽታው ብዙ ሊባል በሚችል ሰው ላይ ስለማይበረታ በቀላሉ ቤትዎ ውስጥ አርፈው ፓራስታሞል እየወሰዱና በርካታ ፈሳሽ ነገሮችን እየተጠቀሙ ራስዎን ማስታመም ይችላሉ።

የኩፍኝና የሌሎች ህመሞች ክትባቶች የተሰሩት በጣም የተዳከሙና ለበሽታ የማይዳረጉ ቫይረሶችን በመጠቀም ሲሆን በየወቅቱ ለሚቀሰቀስ ጉንፋን የሚሰጠው ክትባት ደግሞ አቅማቸውን እንዲያጡ የተደረጉ ቫይረሶችን በማካተት ነው። ለአዲሱ የኮሮናቫይረስ የሚሰራው ግን አዲስ ነው፤ በትንሹ በመሞከር የሚሰራ ነው። “መሞከር እና ውጤቱን ማየት” አይነት የሙከራ አካሄድ ነው ሳይንቲስቶች የሚጠቀሙት። ምክንያቱም የአዲሱ ኮሮናቫይረስ ተፈጥሯዊ መዋቅር ስለሚታወቅ ቫይረሱን ለመስራት አስፈላጊው መረጃ ስላለ ነው። አንዳንድ የክትባት ሳይንቲስቶች የተወሰነ የኮሮናቫይረስን የመራቢያ ኮድ ናሙና በመውሰድ ከሌላው ላይ ሲጨምሩት ቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ ምንም ጉዳት የማያመጣ ይሆናል። ከዚህ በኋላ የሆነን ሰው በዚህ በተገኘው ውጤት እንዲያዝ ቢደረግ በጽንስ ሃሳብ ደረጃ ይህ ሰው የመከላከል አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። ሌሎች ሳይንቲስቶች ደግሞ የዘረ መል ኮድ (ዲኤንኤ ወይም አርኤንኤ) ይወስዱና ወደ ሰውነት ይጨምሩታል። በዚህም የቫይረስ ፕሮቲን ማመንጨት በመጀመር የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ቫይረሱን እንዴት መዋጋት እንዳለባቸው መማር ይጀምራሉ። አበበ ካነበብው የላከልን። ጊዚያዊና ጠቃሚ ስለሆነ አትመንዋል።

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

13

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


COVID-19 INFORMATION FOR ETHIOPIANS & ERITREANS IN CANADA ይህ ጽሁፍ የላከልን ሥዩም ሲሆን ጠቃሚ ሆኖ ስለአገኝነው አውጥተንዋል። ለማንኛውም ጥያቄ ቢኖራችሁ በኢሜል አድራሻ፡ habesha.help@gmail.com ብላችሁ መልእክት ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

MONEY & GOVERNMENT BENEFITS Last Updated: March 25, 2020

የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ Canada Emergency Response Benefit (CERB). March 25, 2020 - Ottawa, Ontario - Department of Finance Canada

የካናዳ መንግሥት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በሚደርሰው የኢኮኖሚ ጉዳት እንዳይጠቁ ለመከላከል ወሣኝ፣ ፈጣንና አመርቂ እርምጃ እየወሰደ ነው። ማንም ለቤተሰቡ አስፈላጊ ነገሮችን ለማቅረብ ጤንነቱን አደጋ ላይ መጣልን እንዳይመርጥ ለቤተሰቡ በሚያቀርበው ምግብ፣ መድኃኒት ለመክፈል፤ ቤተሰቡን ለመንከባከብ እና ከጤንነቱ የትኛውን ልምረጥ በሚል መጨነቅ የለበትም። እንደገናም ሠራተኞችን ለመደገፍ ብሎም ንግድ ቤቶች ሠራተኞቻቸውን እንዳያጡ ለመርዳት የካናዳ መንግሥት የአስቸኳይ ዕርዳታ ጥቅሞችን ደንግጓል። Canada Emergency Response Benefit (CERB) ይህ ጥቅማጥቅም(CERB) በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሥራቸውን ላጡ ሠራተኞች እስከ አራት ወራት በወር $ 2000 ይሠጣል። ይህ አሠራር ከዚህ ቀደም ቃል ከተገቡት ዕርዳታዎች የተሻለና ቀልጣፋ አሠራር ነው። የዚህ ጥቅም(CERB) ተጋሪዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ስራቸውን ያጡ፣ የታመሙ፣ መጠበቂያ ቤት የገቡ፣ ወይንም የታመመ የቤተሰብ አባል የሚንከባከቡ፣ ትምህርት ቤትና የሕፃናት መዋያ በመዘጋቱ ምክንያት ካለክፍያ ልጆቻቸውን

ለመንከባከብ ሥራ አቁመው ቤት ለመዋል የተገደዱ ሠራተኞችን ያካትታል።

ይህ ጥቅም (CERB) የቅጥር ዋስትና ክፍያ (EI) የማይመለከታቸው የወር ደሞዝተኞችን፣ ኮንትራት ሠራተኞችን፣ በግል የሚሠሩ ግለሠቦችን ያካትታል። በተጨማሪም ከሥራ ያልተባረሩ፣ ግን በኮቪድ-19 ምክንያት የታመሙና መስራት ያልቻሉ፣ ክፍያ የማይሠጣቸውም የዚህ ጥቅም ተካፋዮች ናቸው። ይህ የንግድ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን እንዳያጡ ያግዛል። የቅጥር ዋስትና ክፍያ (EI) በከፍተኛ ቁጥር ያለውን ማመልከቻዎች ለማስተናገድ የሚያስችል መዋዕቅር ስለሌለው ሁላችሁም በኮቪድ-19 ምክንያት የተጉላላችሁ ሁሉ በዚህ ጥቅም የምትካተቱ ይሆናል። የቅጥር ዋስትና ክፍያ እየተቀበላችሁ ያላችሁ ለዚህ ጥቅም ማመልከት አይኖርባችሁም። በዛው መቀጠል ይኖርባችኋል። የቅጥር ዋስትና(EI) ክፍያችሁ ከኦክቶበር 3 2020 በፊት የሚያበቃ ከሆነ፣ የቅጥር ዋስትና(EI) ክፍያው እንዳቆመ ለዚህ ጥቅም ማመልከት ትችላላችሁ። ለቅጥር

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

ዋስትና(EI)

14

ክፍያ

ያመለከታችሁና ማመልከቻው በሒደት ላይ የሆነ መልሳችሁ ማመልከት አይኖርባችሁም። የቅጥር ዋስትና ክፍያ ለማግኘት መጠይቁን የምታሟሉ መደበኛ የቅጥር ዋስትናችሁን ማግኘት ትችላላችሁ። ከ16 ሳምንታት በኋላም ሥራ ያልጀመራችሁ እንደሆነ ለዚህ ጥቅም(CERB). ማመልከት ትችላላችሁ።

የካናዳ መንግሥት ከኪሳችሁ ገንዘብ እንዳይጠፋ እየተጋ ነው። ይህንን ጥቅም ይህ ጥቅም (CERB). በአፕሪል 2020 መጠቀም ይቻላል። የቅጥር ዋስትና(Employment Insurance/EI) ክፍያ ማግኘት የምትችሉ ግን ለ(EI) here, ማመልከት ትችላላችሁ። ይህንን ጥቅም (CERB). ለማግኘት ያመለከቱ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን ማግኘት ይጀምራሉ። ይህ ክፍያ ከማርች 15 2020 እስከ ኦክቶበር 3 2020 ድረስ ይኖራል።

ነገር ግን የቻልነውን ማለት ለ እርስዎ የያዘው ትርጉም ምንድነው? መካካሻ የሚያገኙት እንዴት ነው? የአስቸኳይ ዕርዳታ ጥቅማ ጥቅም እንዴት ሊያገኙ ይችላሉ? ጥቅማ ጥቅሙ ከአፕሪል 2020 ጀምሮ ይሠጣል ካናዳውያን ጥቅማ ጥቅሙን ለማግኘት የብቁነት ማረጋግገጫ ምጠይቆችን ማምሟላት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በየ አሥራ አምስት ቀኑ ብቁነታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ካናዳውያን ጥቅማጥቅሙን ለማግኘት በሚከተሉት ሶስት መንገዶች ማመልከት ይችላሉ። CRA MyAccount secure portal; My Service Canada Account;

ቅጥር ዋስትና = Employment Insurance (EI)

ከክፍያ ነፃ የሆኑ ለዚሁ የተመደቡ ስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም መደወል

የካንዳ ፌዴራል መንግሥት ለካናዳውያን የ27 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ እንደሚያደርግ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶኦ ቢል ሞንሮ አስታወቁ። ሚኒስትሩ " በቻልነው ሁሉ" የሕዝባችንን የፋይናንስ ጤንነት ለመጠበቅ "የቻልነውን ሁሉ" እናደርጋለን ብብለዋል።

Original source: https:// www.canada.ca/en/department-finance/news/2020/03/ in t ro d u ce s - c a n a d a - e m e r gency-response-benefit-to-help-workers-and-businesses.html

ተከታዩን ገጽ 21 ይመልከቱ

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


የኮረና ቫይረስ ባሕሪና መከላከል March 27, 2020

አቅም ሲኖራቸዉ ትኩስ ምግባ ምግቦችም መዉሰድ ተመራጭነት አለዉ ፡፡ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም አይስ ክሬም፣ ቀዝቃዛ ቢራ እና ድራፍት ከመጠጣት እንዲቆጠቡ ይመከራሉ ፡፡ የበሽታዉ ስሜት ካጋጠምዎ አፍዎ እና ጉሮሮዎን ሁል ጊዜ ማራስ እንዳለብዎ እንዳይዘነጉ፡፡ ቢያንስ በየ 15 ደቂቃው አንድ ያልቀዘቀዘ ፈሳሽ እንዲጠጡ ይመከራሉ። ፈሳሽ መዉሰዱ ለምን ይመከራል?

ጠቃሚ መረጃ ኮርና ቫይረስ ከተለመደው ጉንፋን ባሕሪ ጋር ተቀራራቢ አይደለም የቫይረሱ ምልክት አፍንጫን የሚያርስ ወይም ብርዳማ ጉንፋን ወይም ደግሞ አክታ የለበት ሳል የለዉም። የኮርና ቫይረስ ደረቅ እና ሻካራ ሳልን የመፍጠር እና የሚከረክር ምልክት አለዉ፡፡ በመቀጠል ቫይረሱ በተለምዶ መጀመሪያ ላይ የጉረሮ አካባቢ ላይ ህመምና የድርቀት ስሜት ያስከትላል ፡፡ ይህ ምልክት ከ 3 እስከ 4 ቀናት ዉስጥ ሊከሰት ይችላል ፡፡ ቫይረሱ በተለምዶ በአየር መተላለፊያ የጉረሮ ትቦ ውስጥ የሚገኘውን እርጥበት የመጠቀም ባሕሪ አለዉ ፣ ይህንንም የጉረሮ እርጥበት በመጠቀም ወደ ሳንባችን ይወርዳል፣ ሳንባችን ላይ ከተቀመጠ በኋላ በ 5 ወይም በ6 ቀናት ዉስጥ የሳንባ ምች ያስከትላል ፡፡ የሳንባ ምች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ በኋላ ከፍተኛ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር ማሳየት ይጀምራል። አብዛኛዉን ግዜ እንደምናዉቀዉ አይነት የጉንፋንና የብርድ ስሜት ላይሰማን ይችላል። ነገር ግን የኮርና ሻይረስ በጉረሮ ላይ የህመም ስሜት ሊፈጠር ይችላል።

በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የገባ ማንኛዉም ሰዉ በአስቸኳይ ህክምና ማግኘት ግድ ይለዋል፡፡ በቫይረሱ መያዝና አለመያዝን ለማረጋገጥ የጤና አማካሪዎች በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ላይ ይህን ቀላል ሙከራ እንዲከዉኑ ይመክራሉበጥልቀት አየር ወደ ሳንባዎት ያስገቡና ለ 10 ሰከንዶች ያህል ቆይተዉ ያስገቡትን አየር ወደ ዉጭ ያስወጡ ፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም አይነት ደረቅ ሳል ካላጋጠመዎ በበሽታዉ ያለመያዞን በመጠኑ ያዉቃሉ ። ይህ ሙከራ በሳንባችን ዉስጥ የጤና እክል አለመኖሩን የሚያሳይ ቀላል መንገድ ነዉ። ቅድመ መከላከል የኮሮና ቫይረስ ከ 80 ድግሪ ሴንቲግሬድ (27 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ) የሚበልጥ ሙቀት ዉስጥ የመቆየት ወይም የመቋቋም አቅም የለዉም ፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ (Infusions) ፣በስጋ እና በአትክልት የተሠሩ ትኩስ ሾርባ (Broths) መጠጦችን መዉሰድ ወይም ደግሞ በቀላሉ እንደ ሙቅ ውሃ ያሉ ትኩስ ነገርችን በተደጋጋሚ መጠጣት ጠቃሚ ነዉ። ትኩስ ፈሳሽ ነገሮች ቫይረሱን የመግደል

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

15

ቫይረሱ በአፉ ውስጥ ቢገባም እንደ ዉሃና መሠል ፈሳሾችን በምንጠጣበት ግዜ ወደ ሆድ እንዲንሸራተት ስለሚገደድ እንደነ ጋስትሪክ ያሉ የጨጓራ ​​አሲዶች ቫይረሱን የመግደል ብቃት ስላላቸዉ ነዉ፡፡ ነገር ግን በቂ ፈሳሽ ካልተወሰደ ቫይረሱ በጉሮሮ ቱቦ (Trachea) ዘልቆ ወደ ሳንባ ውስጥ ሊገባ ስለሚችል ለበሽታዉ ተጋላጭነታችንን ያጎላዋል። በተጨማሪ የፀሐይ ብርሃን በቂ ሙቀት ቫይረሱን የመግደል ሐይል ስላለዉ የለበስናቸዉን ልብሶች ወደ እቤት ስንገባ ማስጣቱ ጠቃሚ ነ። ፀሐይ መሞቁም እንዲሁ ጠቃሚ ሲሆን ቫይታሚን ሲ ያዘሉ ፍራፍሬዎች እና መድሐኒት መዉሰዱ የመከላከል ሐይል ያዳብራል። ኮሮናቫይረስ (400 ከ ናኖ ሜትሮች እስከ 500 ዲያ ሜትር) መጠን ያለዉ ስለሆነም የፊት ጭንብል (Mask) መጠቀሙ የቫይረሱን መተላለፉን ሊያቆምዉ ይችላል። በበሽታው የተያዘ ሰው በአጠገባችን ቢያስነጥስ ቫይረሱ መሬት ላይ ሰለሚወድቅ ወደ እርሶ እንዳይደርስበዎ ለመከላከል 10 ጫማ ያህል እርቆ መቆሞን ያስታዉሱ።

ፀባይ ስላለዉ እነዚህን ቁሳቁሶች ከነኩ እጆትን በደንብ መታጠብ እና / በአልኮል ወይም በማፅጃ ኬሚካሎች ማፅዳትዎን ይስተዉሉ። በተጨማሪ ቫይረሱ በልብስ ወስጥ ከ 6 እስከ 12 ሰዓታት የመኖር ሐይል አለዉ። ሆኖም የተለመዱ ሳሙናዎች ሊገድሉት ስለሚችሉ ልብሶቾን ማጠብ አይዘንጉ፡፡ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችና ቁስ ነገሮችን ፀሐይላይ በማስጣት ቫይረሱ መከላከል ይችላሉ ፡፡ ወደ እቤቶ ሲገቡ ጫማዎን አዉልቀዉ በረንዳ ላይ ለፀሐይ ማስጣት ይበጃል ጃኬትና ካፖርት የመሳሰሉትንም ማስጣቱ መልካም ነዉ። ቫይረሱ በእጃችን ላይ የሚቆየው ለ 10 ደቂቃዎች ያህል ብቻ ነዉ፡፡ በዚያን ጊዜ ዓይኖን መንካት እንደሌለብዎ ይወቁ፣ አፍንጫን ወይም ከንፈሮችን በመንካት ቫይረሱ በጉሮሮ ውስጥ እንዲገባ ያስችለዋል ፡፡ ጉሮሮ ውስጥ ሊገባ የሚችል የቫይረስ መጠንን የሚቀንሱ ወይም ሊቀንሱ የሚችሉ ፀረ-ህዋስ ማፅጃዎችን መጠቀም አስፈላጊ ነዉ። ለምሳሌ ሊስተሪን ወይም ሃይድሮጂን,እና ፕሮኦክሳይድ ( Listerine or Hydrogen Peroxide) በመጉመጥመጥ እና ጉረሮ ላይ በማንቋረር መጠቀም ቫይረሱን የገድላል። ይህን ማድረግ ቫይረሱን ወደ ጉሮሮ ወደ ሳንባ ውስጥ ከመውረዱ በፊት ያስወግዳል። ሀይድሮጅን ተቀጣጣይነት ባሕሪ ስላለዉ መጠንቀቁ የሚበጅ ሲሆን በተጨማሪ ለእጅ የምንጠቀመዉን የእጅ ማፅጃም (sanitation) የመቀጣጠል ባሕሪ ስላለዉ ወደ ኪችን(ማድ ቤት) ስንገባ እጃችን ማድረቁ ተገቢ ነዉ። ፈጣሪ ይጠብቀን ይጠብቃቹ ፡፡

ቫይረሱ በጠጣር ነገሮች ላይ እስከ 12 ሰዓታት ያህል የመቆየት ብቃት አለዉ። ስለሆነም እንደ በሮች፣ የበር እጀታዎች፣ በአሻራ የሚከፈቱ ሴንሰሮች፣ ብረት ነክና እንጨት ሰር የሆኑ እና የመሳሰሉት ጠንካራ ገጽታዎች ላይ የመቀመጥ

ኪንግ ኢቲች ይህን መጣጥፍ የላክችልን አልማዝ ስትሆን ለንባብ አብቅተነዋል።

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


World Economic Forum Convenes Global Business for COVID Action Platform

The World Economic Forum on Wednesday announced the creation of the COVID Action Platform The global platform, the first of its kind, aims to convene the business community for collective action, protect people’s livelihoods

March 23, 2020 well as other stakeholders, aiming to integrate and inform joint action For more information, please visit http://wef.ch/ COVIDActionPlatform (Link live at launch) Geneva, Switzerland, 11 March 2020 – The dramatic spread of COVID-19 has disrupted lives, livelihoods, communities and businessand facilitate business cones worldwide. But the sum tinuity, and mobilize supof many individual actions port for the COVID-19 reby stakeholders around the sponse world will not add up to a The platform is created sufficient response. Only with the support of the coordinated action by busiWorld Health Organization ness, combined with globand is open to all businessal, multistakeholder coes and industry groups, as operation can mitigate the risk and impact of this unprecedented global health emergency. In response to this emergency, the World Economic Forum, acting as partner to the World Health Organization (WHO), has launched the COVID Action Platform. The platform is intended to catalyse private-sector support for

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

16

the global public health response to COVID-19, and to do so at the scale and speed required to protect lives and livelihoods, aiming to find ways to help end the global emergency as soon as possible. The COVID Action Platform will focus on three priorities: Galvanize the global business community for collective action Protect people’s livelihoods and facilitate business continuity Mobilize cooperation and business support for the COVID-19 response The COVID Action Platform is open to all global businesses and industry groups, as well as other stakeholders, including governments, that wish to team up with the private sector on their response. The platform will operate a network where CEOs, organizational leaders andContined on page 17

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


Contined from page 16

designated COVID-19 corporate responders can offer their help and team up on specific projects, launch actions and keep each other informed of best practices. “COVID-19 is causing health emergencies and economic disruptions that no single stakeholder can address,” said Klaus Schwab, Founder and Executive Chairman of the World Economic Forum. “Our best and only response to it should be to take concerted action. The COVID Action Platform is at the centre of our mission and we draw upon all our members and partners, communities and capabilities to make it a success.”

“The private sector has an essential role to play in combating this public health crisis through their expertise, innovation and resources,” said Tedros Adhanom Ghebreyesus, Director-General of WHO. “We call on companies and organizations around the world to make full use of this platform in support of the global public health response to COVID-19.” The COVID Action Platform was conceived after a World Economic Forum conference call with over 200 corporate leaders from all over the world. It is supported by WHO and the Wellcome Trust and is the first initiative of its kind,

operating globally. The Forum has established a special team to support the platform’s work. Working with the Pandemic Supply Chain Network, one of the projects which will initially be launched on the Platform aims to strengthen supply chains to ensure that COVID-19 essential health commodities are available, accessible, affordable and of good quality. Other actions will include supporting mechanisms for business donations to the public health response and the development of available and accessible vaccines, diagnostics, treatments and protective equipment, as well as tracking the economic impact of the virus, while pursuing collaboration to

address disruptions. Companies can register for the COVID Action Platform on http://wef.ch/ COVIDActionPlatform Follow World Economic Forum coverage of COVID-19 on https:// www.weforum.org/focus/ coronavirus-covid-19 The World Economic Forum, committed to improving the state of the world, is the International Organization for Public-Private Cooperation. The Forum engages the foremost political, business and other leaders of society to shape global, regional and industry agendas.

Tel:- 647-7027528 ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

17

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


Measures to flatten the curve of COVID-19 beginning to work, says Trudeau In his daily press conference Saturday, the prime minister referenced slowing numbers in British Columbia

Prime Minister Justin Trudeau at a news conference at Rideau Cottage as efforts continue to help slow the spread of coronavirus disease (COVID-19) in Ottawa,March 27, 2020. Blair Gable/Reuters

flatten the curve. Obviously there are sacrifices we are all making, but it is beginning to work.”

He said “promising numbers out of British ColumMarch 28, 2020 bia” showed that the meaOTTAWA — Prime Minis- sures were beginning to ter Justin Trudeau opened work but he added, “We his daily address on an op- need to keep it up.” timistic note when referring to numbers out of British On Friday, Dr. Bonnie HenColumbia that indicated a ry, the provincial health offlattening of the curve. ficer, said it appeared physi-

cal distancing had started to “We need you to continue slow the rate of growth of to stay home,” Trudeau said COVID-19 in the province on Saturday. “We need you to do everything you can to Read more page 19

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

18

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


Continued from page 18 by as much as half. She said it provided a “glimmer of hope” but she was anxious not to “over call it.” The prime minister also mentioned that as of noon Monday, boarding of domestic flights and trains will be denied to people showing any symptoms related to COVID-19. He said all Canadians are being asked to remain home as much as possible in an effort to stop the spread of the novel coronavirus, but in particular those with symptoms of COVID-19 should not go out. Those symptoms include fever and cough. “We are giving further tools to airlines and rail companies to ensure that anyone exhibiting COVID-19 symptoms does not travel,” he said. He said it will be up to the companies to ensure the new rules are followed. Trudeau also addressed the situation of the 248 Canadians stranded on a cruise ship off the coast of Panama, where some passengers have tested positive for COVID-19 and four others have died. The federal government is working with the Panamanian government and Holland America, which operates the Zaandam, in an effort to get the Canadians home. He said the efforts are part of the “herculean task”

Global Affairs Canada is undertaking to repatriate stranded Canadians around the world.

things like that, but it’s really stressful and scary to her, and this definitely rocked her a bit.”

Two passengers on board the MS Zaandam have tested positive for the disease while 53 passengers and 85 crew have flu-like symptoms, Holland America said in a statement.

The crew is preparing to move his mother to the sister ship, the Rotterdam, he said.

There are 1,243 passengers and 586 crew on board, the company said in a statement. The Zaandam is anchored off the coast of Panama and plans are underway to move healthy people to its sister ship nearby, Holland America said. “We continue to engage with the Panamanian government, and are working with Holland America on their plans to get passengers home,” said Global Affairs Canada spokeswoman Angela Savard. Michael Kasprow is terrified for his 81-year-old mother, Julie, who is currently contained to her room with her friend on the Zaandam. She is healthy, he said, and had her vital signs checked yesterday. “My mom’s demeanour certainly changed in the past 24 hours from, ‘This will be OK,’ to hearing news that people on board had passed away,” Kasprow said. “My mom is my superhero and is incredibly circumspect when it comes to

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

19

“From what I understand, they are going to move healthy and asymptomatic passengers over to the Rotterdam to find some place to dock,” Kasprow said. All ports along its route are closed, Holland America said. “While the onward plan for both ships is still being finalized, we continue to work with the Panamanian authorities on approval to transit the Panama Canal for sailing to Fort Lauderdale, Florida,” the company said. Kasprow, from Toronto, said he is dealing with a mixture of emotions with the uncertainty about his mother, who lives in Thornhill, Ont.

An offshore supply vessel is seen next to the cruise ship MS Rotherdam, which brought supplies and Covid-19 test kits to the MS Zaandam, where four passengers died, pictured off the coast of Panama City, Panama March 27, 2020. Erick Marciscano/Reuters

“I just want her home in her stupid chair for 14 days so we have everybody in the same area and I can talk to her from the end of the driveway,” he said. Meanwhile, Canada’s chief public health officer Theresa Tam said the latest data shows about seven per cent of COVID-19 cases in the country have resulted in hospitalization, three per cent have required critical care and about one per cent have been fatal. She noted that about 30 per cent of people hospitalized are aged 40 and under. “We continue to keep a close eye on the severity of the disease, because although there will be day-today fluctuation, a sustained trend of increased severity could point to a higher rate of infection in vulnerable populations or that the health system is being overwhelmed,” Tam told a news conference. But she also noted “signs of hope” from British Columbia, where data indicates the province’s COVID-19 experience will likely resemble South Korea’s rather than brutally hit Italy. Tam noted that B.C. was the first area of Canada to experience community transmission. “It is too early to know for sure, but after weeks of public health interventions, the rate of growth appears to be slowing,” she said.

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


How To Apply For CERB, Canada’s New $2,000 Emergency Response Benefit If you've lost your job because of COVID-19, this is another option alongside EI. By Melanie Woods

COVID-19, as well as working parents who must stay home without pay to care for children because of school or daycare closures. It also applies to anyone who was laid off and qualifies for EI. But unlike EI, it also applies to people who don’t, such as freelancers, contractors and people still technically employed but no longer receiving income due to the pandemic.

SEAN KILPATRICK/THE CANADIAN PRESS Prime Minister Justin Trudeau addresses media from Rideau Cottage in Ottawa on March 24, 2020. If you lost your job or cannot What is the Canada Emergency work because of the COVID-19 Response Benefit (CERB)? pandemic, more help is on the The government previously way. announced two benefits in response to the pandemic. One On Wednesday, the federal was for those directly impactgovernment passed a $107-bil- ed by COVID-19 or caring for lion emergency package, which someone impacted by it, and included the new Canada one for people who lost their Emergency Response Benefit job as a result of the pandemic, (CERB) designed to support but did not qualify for EI. people economically impacted by the ongoing COVID-19 pan- The Canada Emergency Redemic. sponse Benefit announced Wednesday is an amalgamation “The hard truth is people are of those two benefits. out of work because of this crisis and worried about what The benefit is $2,000 a month comes next. So I want you to for up to four months, directly know that we’ll be there to help paid to Canadians impacted by you. Our government is doing COVID-19, whether you are everything we can to be there not working because you are for you,” Prime Minister Justin sick, or you’ve been laid off or Trudeau said. lost work hours because of the pandemic. The new benefit allows people to claim $2,000 a month for up Who qualifies? to four months in emergency The CERB covers Canadians support. But how does it work? who have lost their job, are And do you qualify? sick, quarantined, or taking care of someone who is sick with

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

20

To qualify, applicants must have had $5,000 in employment income, self-employment income, or maternity or parental leave benefits for 2019 or in the 12-month period preceding the day they make the application. So basically, it’s designed to fill any gaps left by existing income support programs when it comes to people who’ve lost work because of COVID-19. What makes this different than employment insurance (EI)? The EI system couldn’t handle the huge influx it experienced last week. Trudeau noted during his daily address Wednesday that nearly a million Canadians applied for EI in the past week, more than 10 times the previous one-week high. “The EI system was not designed to process the unprecedented high volume of applications received in the past week. Given this situation, all Canadians who have ceased working due to COVID-19, whether they are EI-eligible or not, would be able to receive the CERB to ensure they have timely access to the income support they need,” said the government in a news

release. If you are already receiving EI regular and sickness benefits, you will continue to receive your benefits and should not apply to the CERB. If your EI benefits end before October 3, 2020, you can apply for the CERB after your benefits end. Canadians who are eligible for EI regular and sickness benefits would still be able to access their normal EI benefits, if still unemployed, after the 16-week period covered by the CERB. For a refresher on how to apply for EI if you lost your job because of coronavirus, click here. How do you apply? Trudeau said Thursday that the application process will open through the Canada Revenue Agency “as soon as possible.” You’ll be able to apply through the CRA MyAccount secure portal, your secure My Service Canada Account or over the phone. If you’ve already applied for EI and your application hasn’t been processed yet, you’ll automatically be applied for the CERB instead. When can you expect your first payment? Trudeau said Thursday that the first payment will come within 10 days of applying for the CERB. The CERB will be paid out in a $2,000 lump sum every four weeks, for up to 16 weeks.

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ከገጽ 14 የዞረ COVID-19 ለታክሲ፣ ለኡበር ሾፌሮችና ለሌሎች በግል ሥራ ለሚተዳደሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ጥያቄ፡ እኔ የታክሲ/የኡበር/የሊፍት ሾፌር ወይንም በ፤ግል ሥራ የምተዳደር ነኝ በኮቪድ ምክንያት መሥራት አልቻልኩም። ለቅጥር ዋስትና ክፍል (EI ) ክፍያ ለመጠየቅ ማመልከት አልችልም ለሌላ መንግሥታዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለማመልከት ብቁ ነኝ? መልስ ፦ አዎ በኮቪድ-19 ምክንያት ምንም ገቢ የሌላቸው፣ ወይንም ገቢ የቀነሰባቸው ሆኖም ግን ከሥራ ያልተሰናበቱ ለአዲሱ የካናዳ አስቸኳይ እገዛ ፕሮግራም (CERB) ተካተዋል። ይህም ማለት የኮንትራት ሠራተኞች፣ ምትክ ሠራተኞች፣ እና በግል ሥራ የሚተዳደሩ (ታክሲ/ኡበር/ሊፍት ሾፌሮችን) ጭምር በዚህ ፕሮግራም ይጠቃለላሉ። ጥያቄ፡ ታክሲ/ኡበር/ሊፍት ሾፌሮች እና በግል ስራ ተዳዳሪዎች ለአስቸኳይ እገዛ ፕሮግራሙ CERB?) ወዲያውኑ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ? መልስ፡ የለም ሁሉም ተጠቃሚ አይደሉም። በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን አመልካቾች በ2019 ወይንም ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ $ 5000 ገቢ የነበራቸው ሊሆኑ ይገባል። ይህ ገቢ የቅጥር ገቢ፣ የግል መተዳደሪያ ሥራ ገቢ፣ ወይንም የወሊድ ዕረፍት ገቢ፣ ወይንም የወላጅ ከሥራ በማረፍ የሚገኝ ጥቅማ ጥቅምም ሊሆን ይችላል። ጥያቄ: የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እንዴት ማመልከት እችላለሁ? መልስ፡ የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) ማመልከቻ ቅፅ በኦንላይን April 6, 2020. ታገኛላችሁ። ድረገፁ ገና አልተገለፀም ድረገፁ በተገለፀ ጊዜ በኛ ድረገፅ https://ethioerisupport.webnode.com/ ላይ መረጃውን እናወጣለን። ጥያቄ ፡ ከካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ምን ያህል ገንዘብ አገኛለሁ? መቼ ነው የማገኘው? መልስ፡ የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) የሚከፍለው ከማርች 15 ጀምሮ ለአራት ወራት የሚከፈል በወር $2,000 ይሆናል። ማመልከቻውን ባሥገቡ በ10

ቀናት ውስጥ ክፍያውን ያገኛሉ። ይህም ማለት ቀጥታ ወደ ባንክ የሚዘዋወር ከሆነ በአፕሪል 16 2020 በፖስታ የሚላክ ቼክ ከሆነ ደግሞ ምናልባት ጥቂት ቀን ሊዘገይ ይችላል። ጥያቄ ፡ ለቅጥር ዋስትና (EI) አመልክቼ ከሆነስ? እንደገና ለካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) ማመልከት ይኖርብኛል? መልስ፡፡ የለም ለቅጥር ዋስትና ክፍል (EI) , አመልክተው ከሆነ ማመልከቻዎ ቀጥታ ወደዛ ስለሚዘዋወርና ለ16 ሳምንታት በዛው ማመልከቻ ስለሚከፈልዎት የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) ማመልከት አይኖርብዎትም።

ጥያቄ፡ እስካሁን ድረስ ለቅጥር ዋስትና ክፍል (EI) ያላመለከትኩ ከሆነ ለቅጥር ዋስትና ክፍል(EI) ላመልክት ወይንስ የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ማመልከቻን ልጠብቅ? መልስ፡ ይህ ጥያቄ መልሱ እስካሁን ግልፅ አይደለም። ለጥንቃቄ ሲባል ምናልባት ለቅጥር ዋስትና ክፍል ማመልከት ይችሉ ይሆናል። አለበለዛ ግን እስከl April 6 ጠብቀው የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) ማመልከት ይችላሉ። ማሳሰቢያ: አፕሪል 6 ማመልከቻው ሲለቀቅ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ በተመሳሳይ ጊዜ ስለሚጠቀሙበት የቴክኒክ ችግር ሊያጋጥም ስለሚችል ከወዲሁ ይዘጋጁ ጥያቄ : የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB) ተጠቅሜ ከጨረስኩ በኋላ ሕመም ላይ ብሆን፣ ወይንም ሥራ አጥ ብሆንስ? መልስr: በቂ የቅጥር ዋስትና ክፍል ክፍያ ያለዎት ከሆነ ከአራት ወራት በኋላ የካናዳ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ (CERB). ሲያበቃ የቅጥር ዋስትና ክፍል ክፍያዎን መውሰድ ይችላሉ። Original source for most information: https://cupe.ca/canada-emergency-response-benefit-qa k

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

21

Last Updated: March 25, 2020 ለኮቪድ-19 ከኦንታሪዮ መንግሥት ቢሮ የተሰጠ ምላሽ

ፕሪሚይር ፎርድ እና ሚኒስትር ፊሊፕ የጤና እክብካቤንና ድጋፍን ለነዋሪው ለመስጠት የሚክከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር

ሰዎችና ስራዎች በኮቪድ-19 ምክንያት የትምሕርት ቤቶችና የሕፃናት መዋያዎች መዘጋት ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል እስከ አሥራ ሁለት ዓመት ላለ ልጅ በልጅ $200 ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ላሉ፣ ልዩ ዕገዛ ለሚፈልጉ ልጆች እና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ጨምሮ $250፣ የአመታዊ የአስተማማኝ ገቢን (GAINS) ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዕጥፍ ማድረግ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያን ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለእርሻዎች፣ ለአነስተኛ ንግድ ተቅቋማት፣ ለ45 ቀናት ድጋፍ ለማድረግ ዝቅተኛ ተመን ብቻ ማስከፈል፣ ለሕክምና ባለሞያዎች፣ ለፖሊስ ኃይሎች፣ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች፣ እና ለማረሚያ ቤቶች ዖፊሰሮች የሕፃናት መዋያ ማመቻቸት ለስድስት ወራት የሚቆይ የኦንታሪዮ ተማሪዎች ዕገዛ ፕሮግራም ብድርንና ወለድን ፋታ በመስጠት ነዋሪዎች ከኪሳቸው ገንዘብ እንዳያጡ መርዳት ------------------------የቶሮንቶ ከተማ ነዋሪዎች ቤት ተከራይ ለሆኑ የተዘጋጀ https://www.toronto.ca/home/me-

dia-room/news-releases-media-advisories/?nrkey=4548F3F23C148BE28525853500559827 March 24, 2020 ዛሬ ከንቲባ ጆን ቶሪ የቶሮንቶን ነዋሪ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ተፅዕኖ ላሳደረባቸው ለመርዳት የሚከተለውን ዕርዳታ እንደሚያገኙ መግለጫ ሰጥተዋል። በኮቪድ ሳቢያ ስራ ላቆሙት ለተከራዮች እስከ 90 ከመቶ ድረስ የቤት ኪራይ ክፍያቸውን በገቢያቸው ልክ እንዲተመንና -----------------------ለአከራዮች https://www.toronto.ca/home/ covid-19/economic-support-recovery/economic-support-recovery-for-individuals-families/ የኦንታሪዮ ፍርድ ቤት ከቤት ለማፈናቀል፣ ኪራይን እንዲከፍሉ ለማስገደድ፣ ችሎት አይቀመጥም። ምንም እንኳን አከራይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢፅፍም ተከራይ ቤቱን ለቆ ለመውጣት አይገደድም። Original source: https://news. o n t a r i o. c a / m o f / e n / 2 0 2 0 / 0 3 / ontarios-action-plan-responding-to-covid-19.html

CHILDREN'S EDUCATION AND RESOURCES ቤተ ሰባችሁ በጣም ፈታኝ በሆኑት

ማርች 25 2020 ውድ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች የ ኮቪድ19ን መስፋፋት ለመገድብ የሚደረጉት ጥረቶች በሁላችንም በኩል ቀጥለው ባሉበት ወቅት እናንተና

ሁኔታዎችም በደህና ሁኔታ ወስጥ እንደምትገኙ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ መራራቅ ተጽእኖ እንዳስከትለና ከወትሮ ተግባሮች ተቆጥቦ ሁሉንም ነገር እንደነበር አድርጎ ለማስቀጠል የምታደርጓቸው ጥረቶች በብዙዎቻችሁ ላይ እየተደራረቡባችሁ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡ ፡ ከዚህ ቀደም ተከስቶ በማያውቀው በዚህ ኩነት ወቅትም የልጆቻችሁን

ተከታዩን ገጽ 23 ይመልከቱ

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ከገጽ 23 የዞረ ትምህርት በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ይኖሯችኋል፡፡ ሁሉንም ጥያቄዎቻችሁን በዚህ ጊዜ መመለስ ባልችልም፥ ብዙዎቹን ለመዳሰስ ግንዛቤ ላስጨብጣችሁ እወዳለሁ፡፡ በቅድሚያ፥ ፕሬሚየር ደግ ፎርድ ከጅምሩ አሳውቀውት በነበረበው መሠረት ትምህርት ቤቶች በተያዘው የጊዜ ዕቅድ ማለትም በ April 6, 2020 ተመልሰው የማይከፈቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህን በተመለከተ ያገኘነው ምንም ተጭማሪ መረጃ ባይኖረንም፥ ተጨማሪ መረጃ እንደ ደረሰን ለወላጆችና ጋርዲያኖች እናሳውቃለን፡ ፡ ሆኖም በዚህ አጋጣሚ፥ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበውን “በቤት ተማሩ” (Learn at Home) የተሰኘውንና በቶሮንቶ ትምህርት ቤቶች ቦርድ ተዘጋጅቶ የተሰጠውን “የተማሪ መማርያ” (Student Learning Resources) የተሰኘውን ጠቀሜታ ያላቸውን የትምህርት መገልገያዎች መጠቀም እንድትቀጥሉ እንጠይቃለን፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ሊራዘም ለሚችል የትምህርት ቤቶች የመዘጊያ ወቅት ሊያገለግል የሚችል ሥርዓተ ትምህርት መሰናዶ የሚሆን ዕቅድ የማደራጃ ጊዜ አድርገው የሚቀጥሉትን ሁለት ሳምንታት እንዲጠቀሙባችው ለትምህርት ቤቶች ቦርዶች ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ክትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን፥ በመላው ትምህርት ቤቶች ደረጃ ተማሪዎችን እንዲሁም በተጓዳኝነትና በአማራጭነትም ወላጆቻቸውንና ጋርዲያኖችን ከመምህራን ጋር ማገናኘት የሚያስችልና መምህር መራሽ የሆነ ትምህርትን በሚቻለን ሁሉ ከቦታው ለመመለስ ዕቅድ በማውጣት ላይ እንገኛለን፡፡ ይህን ዕቅድ ለመቅረጽም በርካታ ወሳኝነት ያላቸውን ኩነቶችን ከግምት ውስጥ ከተናል፡፡ · መገልገያ መሣሪያዎችና (devices) ኢንተርኔት ለተማሪዎች ለማቅረብ የሚቻልባቸውን መንገዶችን መፈለግ · ለየት ያለ የመማሪያ ዘዴዎች ለሚያስፈልጋቸው፥ የተለየ የትምህርት አሰጣጥ ለሚሹና ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ሁኔታዎችን ማመቻቸት · ለጎልማሳ (adult) ትምህርት ተማሪዎችና ትምህርታቸውን ለሚቀጥሉ ዕቅድ ለማውጣት · ተማሪዎችና ቤተሰቦች በኦንላይን

ተደራሽ የሚያደርጉ መገልገያዎችን ማቅረብን ጨምሮ ለተማሪዎች የአእምሮ ጤንነትና ደኅንነት ድጋፍ ማበርከት እንደምትገነዘቡት፣ ትምህርት ቤቶች ዝግ በሆኑበት ሰዓት ለ247 000 ተማሪዎች የሚሆን ዕቅድ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ አሰናድቶ ማቅረብ ተግዳሮት እንደሆነ ቢያንስ ለማለት ይቻላል፡፡ ግባችን የወቅቱን ሁኔታዎች ከግምት ያስገባ፥ ተማሪዎች በሙሉ የዓመቱን ትምህርት እንዲያጠቃልሉ አድርጎ ማስተማርና ወደ ተከታዩ የትምህርት ዘመን እንዲያልፉና እንዲመረቁ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ነው፡ ፡ ይህንንም ጠቀሜታ ያለውን ዕቅድ በተቻለ መጠን በቅርቡ ለወላጆችና ለጋርዲያንስ ይፋ እናደርጋለን፡፡ የሕዝብን መሰባሰብ ለመገደብና የኮቪድ19ን ስርጭት ለመቀነስ፥ የቶሮንቶ የጤና ጥበቃ ቢሮ የከተማው ንብረት የሆኑ የመጫወቻ መስኮች፥ የስፖርት ሜዳዎች፥ የቅርጫት ኳስና የቴኒስ ዐውዶችን ጨምሮ በርካታ የሕዝብ መገልገያዎችን ዝግ ማድረጉን ገልጿል፡፡ በቶሮንቶ ከተማ ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ይህንን እንዲያደርጉ ታዘዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የቶሮንቶ ትምህርት ቤቶች ቦርድ፥ ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ፥ የስፖርት ሜዳዎችን፥ የቅርጫት ኳስና የቴኒስ ዐውዶችን ጨምሮ የመጫወቻ መስኮችንና ሌሎች መገልገያዎችን በሙሉ ዝግ ያደርጋል፡ ፡ አዘውትራችሁ እንደምታደርጉት፥ ከሕዝብ ጤና ጥበቃና ከመንግሥት ባለ ሥልጣናት ይህን በማስመልከት የሚሰጡ ዘገባዎችን መከታትል እንድትቀጥሉ አበረታታለሁ፡፡ የቶሮንቶ የሕዝብ ጤንነት ቢሮ የእርስዎንና የቤተሰብዎን ደኅንነትና ጤንነት በተመለከተ ወቅቱን የጠበቀ ምክርና በርካታ ጠቃሚ መረጃዎን ይሰጣል፡፡ ምንም እንኳን ከፊታችን የተደቀኑ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፥ በአንድነት አልፈናቸው የምንሄድበት መንገድ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ፡ ፡ ሰለ ትእግስትዎና ሰለሚገነዘቡን ላመሰግንዎት እፈልጋለሁ፡፡ በቅርቡ ተጨማሪ መግለጫ እሰጣለሁ፡፡ ከትሕትና ጋር ጆን ማሎይ የትምህርት ዳይሬክተር

ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

22

ይህ ጽሁፍ የላከልን ሥዩም ሲሆን ጠቃሚ ሆኖ ስለአገኝነው አውጥተንዋል። ለማንኛውም ጥያቄ ቢኖራችሁ በኢሜል አድራሻ፡ habesha.help@gmail.com ብላችሁ መልእክት ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

23

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


ድልድይ መጽሔት / MARCH 2020

24

https://www..mytzta.com / https://www.tzta.ca


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.