በሌሎች ቋንቋዎች የቤተ መፃህፍቱ አባል ለመሆን የሚያስፈልግ መረጃ ወደ ዌሊንግተን ከተማ ቤተ መፃህፍት እንኳን በደህና መጡ፡ማንኛውም ሰው የዌሊንግተን ከተማ ቤተመጻሕፍት አባል ለመሆን ይችላል! በዌሊንግተን 14 የቤተ መፃህፍት ቅርንጫፎች አሉን በአቅራቢያዎ የሚገኘውን ቅርንጫፍ ያግኙ. እያንዳንዱ ቤተ መፃህፍት ነፃ ኮምፒውተሮች እና Wi-Fi፣ እንዲሁም ነጻ የእንግሊዘኛ ትምህርት ቡድኖችን ጨምሮ ለህፃናት፣ ልጆቸ እና አዋቂዎች ነጻ ኩነቶች አሏቸው።
የዌሊንግተን ከተማ ቤተ መፃህፍት አባል መሆን፡የዌሊንግተን ከተማ ቤተመጻሕፍት አባል ለመሆን ምንም ዓይነት ክፍያ የለውም። እባክዎን እንደ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ ወይም የተማሪ መታወቂያዎ ያሉ መታወቂያዎችን ወደ ቤተመጽሐፍት ይዘው ይምጡ እና የቤተ-መጻህፍት ባለሙያዎቻችን እንዲመዘገቡ ይረዱዎታል።
በቤተ መፃህፍቱ መጽሃፎች፣ መጽሔቶች፣ ሲዲዎች፣ ዲቪዲዎች፣ እና ሌሎች እንደ ኢ-መጽሐፍት ያሉ በውሰት ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እቃዎች አሉ። መጽሐፍትን በተውሶ ለመውሰድ ክፍያ የለውም። ከመመለሻው ቀን አስቀድመው ሲመለሱ፣ ምንም ክፍያ አይጠየቁም። መጽሔቶች፣ ሲዲዎች እና ዲቪዲዎች በውሰት ለመውሰድ ክፍያ አላቸው። ከመመለሻው ቀን ዘግይተው ለሚመልሱ፣ ለተበላሹ/ለተጎዱ ወይም ለጠፉ ዕቃዎች ክፍያ አለው። ያልተከፈለ ዕዳ ወደ ዕዳ ሰብሳቢ ኤጀንሲ ይላካል። እኛ እዚህ የምንገኘው እርሶዎን ለመርዳት ነው፡በዌሊንግተን ከተማ ቤተመጻሕፍት ጥሩ ጊዜ እንድያሳልፉ እንፈልጋለን። ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እባክዎን ይጠይቁን - እኛ እዚህ የምንገኘው እርሶዎን ለመርዳት ነው! የትርጉም አገልግሎት፡የዌሊንግተን ከተማ ቤተ መፃህፍት የትርጉም አገልግሎት ይስጣል፣ ከ60 በላይ ቋንቋዎች ላይ ተአስተርጓሚዎች ይገኛሉ። ቤተ መፃህፍቱን በሚጠቀሙበት ወቅት አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ እባክዎን ለቤተ-መጻህፍት ባለሙያ ይንገሩ እና ባለሙያው በስልክ ከአስተርጓሚ ጋር ውይይት እንዲያድረጉ ያመቻቻሉ።