Muhaz vol i issue 12 amharic

Page 1

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ማ ው ጫ

በውስጥ ገፅ 3 30/70 መመሪያን መሰረት ያደረገ ውይይት ተካሔደ

3

የሲቪል ማህበረሰብን አስተዋፅኦ ከማጠናከር አንፃር መንግስት ወሳኝ ሚና እንዳለው እናምናለን

ፒተር ሄንይ

ገፅ 6

ዶርቃስ ኤይድ ኢንተርናሽናል 20 ሠልጣኞችን አስመረቀ

4 የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ሁኔታ በኢትዮጵያ

ብዙወርቅ ከተተ

ከውርስ የመጣ ደግነት

ስኬት

ገፅ 8

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ የ15 ዓመት የተቆርቋሪነት ጉዞ

አቶ ኤፍሬም አላምረው

ተመክሮ ገፅ አቶ ዮናስ ገብሩ |1

14


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

የአዘጋጁ

ማስታወሻ

የአንድ ዓመት ሥራችን ውጤት ሲቃኝ

በአሚከስ ሚዲያ ፕሮሞሽንና ኮሙኒኬሽን አሣታሚ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ቀበሌ 01/03 የቤት ቁጥር 862 ስልክ 011552 67 69/0911228115 ፖስታ 121525 አታሚ ሪላ ማተሚያ ቤት ልደታ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 07/11 የቤት ቁጥር 643 ስልክ 0111520705/0111853232

ማኔጅንግ ኤዲተር ብርሃኔ በርሄ ስልክ 0911 66 35 65 E-mail ezana_7@yahoo.com

ዋና አዘጋጅ ዘለዓለም ወዳጅ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 588 ስልክ 0911 38 28 75 e-mail wzelalem13@yahoo.com

ሥራ አስኪያጅ እንደሻው ኃብተገብርኤል ስልክ 0911 22 8115

ኮምፒዩተር ፅሁፍ እና ሽያጭ ራህመት አብደላ ስልክ 0924 77 87 78

እነሆ ሙሐዝ መፅሔት ለንባብ መብቃት ከጀመረች አንድ ዓመት ሆነን፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የተነሣንበትን ዓላማ ያሳካሉ ብለን ያሰብናቸው ጉዳዮች የያዙ አስራ ሁለት ዕትሞች ለንባብ የበቁ ሲሆን ለሥራችን መቃናት የተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ሰጥተውናል፡፡ በዚህ ረገድ በተለይም የበጎአድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ መረጃዎችን በመስጠትና መጠይቆችን በመመለስ ከዚያም አልፎ የመፅሔቱን ይዘት አስመልክቶ ይሰጡን ለነበረው ገንቢ አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ይህ ግኑኝነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታችን ነው፡፡ በመቀጠል ለመፅሔታችን መረጃዎችንና መጠይቆችን ለሰጣችሁን ተቋማትና ግለሰቦች ያለንን ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ደጋግመን እንደምንገልጸው የመፅሔታችን ዋነኛ ዓላማ የበጎአድራጎት ድርጅቶችንና ማህበራትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት እነዚህ ተቋማት ተጠናክረው በልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሚና በግልፅነትና በተጠያቂነት ስሜት እንዲወጡ ማስቻል እንዲሁም ለዚህ ሥራቸው መቃናት ተገቢው የህግና የአሠራር ስርዓት እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት በዘርፉ ውስጥ ጥሩ ተሞክሮ ያላቸውን ተቋማት በመለየት ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ አድርገናል፣ ዘርፉን በሚመለከቱ የፖሊሲ፣ የህግና የአተገባበር ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሰዎች አስተያየት እንዲሰጡ አድርገናል፤ የተለያዩ ለዘርፉ ጠቀሜታ ያላቸውን መረጃዎች ለማቅረብ ሞክረናል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሥራዎች የተከናወኑት ያለምንም ችግር አልነበረም፡፡ አንዱና ዋነኛው ችግራችን በዘርፉ ውስጥ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች አብዛኛዎቹ ማስጠት በሚቻልበት ሁኔታ መረጃ ሊሰጡን ወይም ሊተባበሩን ፍቃደኛ ያለመሆናቸው ነው፡፡ በትልቅ የፍርሃት ጨለማ ውስጥ ተደብቀው ራሳቸውን ለማውጣት የማይደፍሩ ሆኖም የጨለማ ሐሜት ሥራቸው የሆነ ብዙ “አዋቂ” ሰዎች አሉን፡፡ የድፍረት ብርሃኑ እንዲገለጥላቸው እንመኛለን ፡፡ በራሳችን በኩልም ችግሮች ነበሩብን፡ ፡ የህትመት ጥራትና ጊዜ ያለመጠበቅ፣ በሳል ጽሁፎችን በሚፈለገው መጠን ያለማቅረብ ዋና ዋና ችግሮቻችን ነበሩ፡፡ ሌላው እንደ ድክመት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የሚያነሱብን ስለዘርፉ መልካም አስተዋጽኦ የምታነሱትን ያህል ችግሮቹን በተለይም ችግር ያለበትን ድርጅት ነቅሳችሁ አታወጡም የሚል ይገኝበታል፡፡ ይህ አስተያየት ተገቢነት እንዳለው ብናምንም በነበርንበት ጨቅላ ዕድሜ እንዲህ ዓይነቱን ከባድ ስራ ለመሥራት ቀላል እንደማይሆን ግንዛቤ ሊወሰድልን ይገባል፡ ፡ ቢሆንም በዘርፉ ላይ የሚታዩ አጠቃላይ ችግሮችን አቅማችን በፈቀደው መጠን ያህል ለማንሳት ሞክረናል፡፡ አንዱን ዓመት ጨርሰን ሁለተኛውን ለመጀመር እየታተርን ነው፡፡ ድጋፋችሁና ትብብራችሁ ካልተለየን በአዲስ መንፈስ ተጠናክረን ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡

አ ስ ተ ያ የ ት መፅሔቷ በሲቪል ማህበራትና በኤጀንሲው መካከል ያሉትን የመረጃ ሽግግሮች ለማሳለጥ የተዘጋጀች፤ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረች መሆኗን አይቻለሁ፡፡ የሚቀርቡት ሀሳቦች በጣም ጥሩዎች ናቸው፡፡ ምንያቱም እነኚህ ነገሮች በአንድ መልኩ ሌሎቹ የሲቪክ ማህበራት አንዱ ስለሌላው ግንዛቤ እንዲያገኝ ያስችላሉ፡፡ የመንግሥት አካላት ስራዎቻችንን እንዴትና በምን መንገድ እንደምናካሂድ ማየት የሚችሉበት አጋጣሚም ይፈ ጥርላቸዋል፡፡ ሁለት ገጽ ያለው የማቀባበል ሥራ የመስራት፤ በዚህም ኮሙኒኬሽንን ማዳበር ስለሆነ፣ በኔ በኩል መፅሔቷ በጣም ጥሩ አስተዋጽኦ እንዳላት እገምታለሁ፡፡ እንዲያውም የበለጠ ሰፋ ያለ ተነባቢነት እንዲኖራት ሁኔታዎች ቢመቻቹና የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ብትጠቀሙ ጥሩ ነው የሚል አስተያ የት አለኝ፡፡

ኤፍሬም አላምረው ፎረም ፎር ኢንቫይሮመንት

|2

ዋና ሥራ አስፈፃሚ


30/70 መመሪያን መሰረት ያደረገ ውይይት ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በሲ.ሲ.አር.ዲ.ኤ. መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ ውይይቱን በዋናነት ያዘጋጀው ሲ.ሲ.አር.ዲ.ኤ. ሲሆን በዕለቱም የቅንጅቱ አባል የሆኑ 73 የውጪ ሀገር በጎአድራጎት ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነው ነበር፡፡ የውይይቱ ዋና ዓላማ ከ70/30 መመሪያው ጋር በተያያዘ የበጎአድራጎት ድርጅቶች የስራ ክንውን ምን እንደሚመስል መፈተሸ፣ መመሪያው በተለይ የውጪ ሀገር በጎአድራጎት ድርጅቶች ላይ ያለውን ተጽእኖ መዳሰስ እና ወደ መፍትሔ ሊያደርሱ የሚችሉ ሃሳቦች ላይ መመካከር

ነው፡፡ በዕለቱ ጉዳዩን መሠረት አድርገው የተካሄዱ የተለያዩ ጥናታዊ ስራዎች እና ዳሰሳዎች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ስራዎች ዙሪያ ቤቱ በስፋት ተወያይቶባቸዋል፡፡ ከቀረቡት ጥናቶች አንዱ “የበጎ አድራጎት ደርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ አስተዳደራዊና የዓለማ ማስፈፀሚያ ወጭዎችን አስመልከቶ ያወጣው የ70/30 መመሪያ ሊኖረው የሚችለው እንደምታ” በሚል ርእስ የተካሄደ ነበር፡፡ በጥናቱ መሰረት የመመሪያው አበይት ተግዳሮቶች እና አንድምታዎች ናቸው ተብለው

ከተዘረዘሩት መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፤ 1. የአስተዳደራዊና የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጭዎች ክፍፍል ከበጎ አድራጎት ደርጅቶች የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርዓት እና ከአለም አቀፍ መመዘኛዎች ጋር የሚጣረስ መሆኑ፤ 2. በማንኛውም መርሃግብር የመጀመሪያና የማጠናቀቂያ ወቅቶች የአስተዳደራዊ ወጭዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ - በተለይም ከአንድ የበጀት አመት በላይ በሚወስዱ መርሃግብሮች ሁኔታ፤

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

30/70 መመሪያን መሰረት ያደረገ ውይይት ተካሔደ

በገፅ 18 ይቀጥላል ...

ዶርቃስ ኤይድ ኢንተርናሽናል 20 ሠልጣኞችን አስመረቀ ዶርቃስ ኤይድ ኢንተርናሽናል ለ5ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 20 ሰልጣኞች ጥቅምት 1 ቀን 2005 ዓ.ም. በስልጠና ማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ፡፡ የዕለቱ ተመራቂዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሴቶች ሲሆኑ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡና በራስ አገዝ ቡድን ተደራጅተው የተላኩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ተመራቂዎቹ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ለአንድ ዓመት ሲሆን በሳምንት ሶስት ቀን በድርጅቱ የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል በቂ ስልጠና አግኝተዋል፡፡ የሰለጠኑበትም የሙያ መስክ ኩዊልት፣ የልብስ ቅድና ስፌት፣ የቦርሳ፣ የሽርጥ፣ ለወጥቤት አገልግሎት የሚውሉ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች ወዘተ. የመሣሠሉ ሌሎች ተጓዳኝ የስፌት ስራዎችን በማምረት ሂደት መሆኑን በምርቃቱ ላይ ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል፡፡

የድርጅቱ የአገር ውስጥ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ታረቀኝ ከሰጡት ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ለ4 ጊዜያት የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን የሰጠ ሲሆን ቀደም ሲል በተለያዩ ዙሮች ሰልጥነው ከተመረቁት ሴቶች አብዛኛዎቹ በግል እንዲሁም በቡድን በመደራጀትና በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የተለያዩ ስራዎችን በገፅ 18 ይቀጥላል ...

አ ስ ተ ያ የ ት መፅሔቱ ጥሩ ነው፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ መፅሔት ብቻ አይደለም፡፡ ከሁሉም አቅጣጫ አመለካከቶችን የሚያስተናግድ ነው፡፡ የሲቪል ማህበረሰቡ መኖር ያስገኘውን ጠቀሜታ በሚመለከት ብዙ ጥናቶች (ኬዝ ስተዲ) ማቅረብ ይጠበቅባችኃል፡፡ በእኔ እምነት አሁን ድረስ የሲቪል ማህበረሰቡ እያበረከተ ስላለው አስተዋፅኦ የሚታይና ግልፅ የሆነ የመረጃ እጥረት አለ፡፡ ምንአልባት የሲቪል ማህበረሰቡ የተለያዩ ፕሮግራሞች ያላቸውን ተጠቃሚዎች የበለጠ ማውጣቱ የመረጃ ክፍተቱን ሊሸፍን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ብዙ ጥሩ ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ብዙወርቅ ከተተ ሲኒየር ጋቨርነንስ ፕሮግራም ማኔጀር አይሪሽ ኤይድ ኢትዮጵያ

|3


የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት ተልዕኳቸውን በሚፈፅሙባቸው የተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ በምሑራን የተሠሩ አማራጭ የፖሊሲ ሐሳቦች አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጥናቶችና የምሑራን ትንታኔዎች ይቀርቡበታል፡፡

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

uÑ@ƒ’ƒ UƒŸ< የማህበራዊ ህግ ተመራማሪ

የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ሁኔታ በኢትዮጵያ 1

መግቢያ

የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ድህነትን ለመቀነስ እና የሰዎችን ኑሮ ለማሻሻል እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር ወር 2000 ዓ.ም. በተካሄደው የተ.መ.ድ. የሚሊኒየም ሰሚት በአለም ዙሪያ የሚገኙ አገራት መሪዎች የቀረጹዎቸው ግቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በሁሉም አገራት የሚተገበሩ አለም አቀፍ የልማት ግቦችን የመለየትና የማስቀመጥ ሃሳብ የተጀመረው በሚሊኒየሙ የልማት ግቦች አይደለም፡፡ የተ.መ.ድ. እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ የመጀመሪያው የልማት አስርት አመት ከተከበረበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን አሰራር ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በአገራት ደረጃ የነዚህን ግቦች አተገባበርጀ ለመከታተል የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ሂደትና አሰራር ሲቀመጥ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ በአንፃሩ ከዚህ ቀደም የነበሩት የልማት ግቦች የተጠያቂነት ስርዓታቸው ደካማ እና በተለያያዩ ኮሚሽኖችና አካላት መካከል የተበታተነ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር ወር 2000 ዓ.ም. በኒውዮርክ በተካሄደው የሚሊኒየም ሰሚት 189ኙም የተ.መ.ድ. አባል አገራት የሚሊኒየሙ መግለጫ በመባል የሚታወቀውን እና የተመረጡ ግቦችና ተደራሾችን የያዘውን ሰነድ አጸደቁ፡፡ የሚሊኒየሙ መግለጫ እ.ኤ.አ. ለ2000 ዓ.ም. ታቅደው የነበሩ (ነገር ግን ያልተሳኩ) የልማት ግቦችን ከጊዜው ጋር ያጣጣሙና እ.ኤ.አ. ለ2015 ዓ.ም. ያካተተ ሲሆን በመጀመሪያ በኦ.ኢ.ሲ.ዲ. አባል አገራት የተቀረጸውን ድህነትን በግማሽ የመቀነስ ግብም እውቅና ሰጥቷል፡፡ መግለጫው ስምንት እርስ በርሳቸው የተያያዙ የልማት ግቦችን በማጣመር የጊዜ ሰሌዳ የተቀመጠላቸው ተደራሾችን እና ሊመዘኑ የሚችሉ ጠቋሚዎችን ያካተተ አለም አቀፍ የልማት አጀንዳ አስቀምጧል፡ ፡ እነዚህም ግቦች “የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች” በመባል ይታወቃሉ፡፡ የሚሊኒየሙ ሰሚት መግለጫ ከዚህም ባሻገር ሰብአዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲን ማእከል ያደረገ የአተገባበር ፍኖተ-ካርታም አስቀምጧል፡፡ እነዚህ ስምንት ግቦች በዋነኛነት በድህነት፣ ትምህርት፣ የፆታ እኩልነት እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ በተጨማሪነት ለልማት አመቺ የሆነ ዓለም አቀፍ የንግድና የገንዘብ ስርዓት መዘርጋትን

|4

የሚመለከቱ ተደራሾችንም አካትተዋል፡፡ ለእያንዳንዱ ግብም እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ዓ.ም. ሊሟሉ የሚጠበቁ በቁጥር የተገለጹ ተደራሾች ተቀምጠዋል፡፡ በአጭሩ የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች የአገራት መሪዎች ድህነትን ለመቀነስ እና የሰዎችን ኑሮ ለማሻሻል የተስማሙበትን መአቀፍ ይወክላሉ፡፡ በስምንት ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት የተደረሰባቸውን መሰረታዊ ችግሮች ሰንጠረዥ 1: የሚሉኒየሙ የሌማት ግቦች - ግቦችና ተዯራሾች

ግቦች

ተዯራሾች

ግብ 1 ከፌተኛ ዴህነትና ረገሃብን ማጥፊት

በቀን ከአንዴ የአሜሪካን ድሊር በታች ገቢ ያሊቸውን እና የረሃብ ሰሇባ የሆኑ ሰዎችን ቁጥር በግማሽ መቀነስ

ግብ 2 የመጀመሪያ ዯረጃ ትምህርትን ሇሁለም ማዲረስ

ሁለም ወንድችና ሴቶች ሕፃናት የመጀመሪያ ዯረጃ ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ማረጋገጥ

ግብ 3 የፆታ እኩሌነትን ማረጋገጥና ሴቶችን ማብቃት

የተዛባ የፆታ ምጣኔን በመጀመሪያ ዯረጃ ትምህርት ቢቻሌ እስከ 2005 እና በሁለም ዯረጃዎች እስከ 2015 ማጥፊት

ግብ 4 የሕፃናትን ሞት መቀነስ

ከአምስት አመት በታች የሆኑ ሕፃናት ሞትን በሁሇት ሦስተኛ መቀነስ

ግብ 5 የእናቶችን የጤና ሁኔታ ማሻሻሌ

በወሉዴ ጊዜ የሚሞቱ ሴቶችን ቁጥር በሦሰት አራተኛ መቀነስ

ግብ 6 ኤች.አይ.ቪ. ኤዴስ፣ ወባ እና ላልች በሽታዎችን መዋጋት

የኤች.አይ.ቪ. ኤዴስን ስርጭት፣ የወባና የላልች በሽታዎችን ክስተት ማቆምና መቀሌበስ

ግብ 7 የአካባቢን ዯህንነት ቀጣይነት ባሇው ሁኔታ ማረጋገጥ

በአገራት የሌማት ፖሉሲዎችና መርሃግብሮች ውስጥ ቀጣይነት ያሇው ሌማት መርህን ማካተትና የአካባቢያዊ ሃብትን መመናመን መቀሌበስ እስከ 2015 ባሇው ጊዜ ንጹህ የመጠጥ ውሃ የማያገኙ ሰዎችን ቁጥር በግማሽ መቀነስ እስከ 2020 ባሇው ጊዜ ቢያንስ የ100 ሚሌዮን ዯረጃቸውን ባሌጠበቁ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ህይወት ማሻሻሌ

ግብ 8 ሇሌማት ዓሇም አቀፌ አጋርነትን መፌጠር

ሇመሌካም አስተዲዯር፣ ሇሌማት እና ዴህነት ቅነሳ ከፌተኛ ትኩረት የሚሰጥ ግሌጽ የንግዴ እና የገንዘብ ስርዓትን በብሄራዊና ዓሇም አቀፊዊ ዯረጃዎች ማጠናከር ሇወጣቶች አግባብነት ያሇውና ምርታማ ሥራ መፌጠር

ሇስምንቱ ግቦች አስራ ስምነት ዝርዝር ተዯራሾች የተቀመጡ ሲሆን እነዚህን ሇመከታተሌ

ለመፍታት ማድረግተሇይተዋሌ፡፡ እንደምንፈልግ የሚያሳዩም ዯግሞ 45 ምን ጠቋሚዎች እያንዲንደም አገርናቸው፡፡ በነዚህ ግቦች ሊይ በመነሳት ሉዯረሱ የሚችለ፣ በጊዜ የተወሰኑ እና ተሇኪ ብሔራዊ የሌማት ግቦችን ሲሆን እንዯሚቀርጽ ለስምንቱ ግቦች አስራ ስምነት ዝርዝር ተደራሾች የተቀመጡ እነዚህንይጠበቃሌ፡፡ ለመከታተል እነዚህ 45 ግቦች አነስተኛውን ዯረጃ የሚጠቁሙ ሆነው አገሮች ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ ጠቋሚዎች ተለይተዋል፡፡ እያንዳንዱም አገር በነዚህየየራሳቸውን ግቦች ላይ በመነሳት ሊደረሱ በማገናዘብ በጊዜ ሉያስፊፈዋቸው የሚችሉ፣ የተወሰኑይችሊለ፡፡ እና ተለኪ ብሔራዊ የልማት ግቦችን እንደሚቀርጽ ይጠበቃል፡ ፡ የሚሉኒየም እነዚህ ግቦች አነስተኛውን ደረጃ የሚጠቁሙ አገሮች የየራሳቸውን ነባራዊ ገቢ ሁኔታ የሌማት ግቦች የፌሊጎት ዲሰሳ ጽሁፌ ሆነው (ሚሉኒየም ፕሮጀክት 2004) ዝቅተኛ ያሊቸው አገሮች የሌማት ፖሉሲዎቻቸውንና መርሃግብሮቻቸውን ከሚሉኒየሙ የሌማት ግቦች በማገናዘብ ሊያስፋፉዋቸው ይችላሉ፡፡ የሚሊኒየም የልማት ግቦች የፍላጎት ዳሰሳ ጽሁፍ (ሚሊኒየም ፕሮጀክት 2004) ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች የልማት ፖሊሲዎቻቸውንና መርሃግብሮቻቸውን ከሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ጋር ለማጣጣም የሚሄዱበትን ሂደት በሦስት ደረጃዎች ከፍሎ ያስቀምጠዋል፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ አገራቱ ያሉበትን ሁኔታ ከሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ጋር በማነፃጸር ግቦቹን በ2015 ለመድረስ የሚያስፈልገውን ግብአት ለመወሰን የሚያስችል የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ነው፡፡ ሁለተኛው የእቅድ አዘገጃጀት ደረጃ ደግሞ በሚሊኒየሙ የልማት ግቦች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱን ግኝቶች መሰረት በማድረግ ግቦቹን ለመድረስ የሚያስችል የረጅም ጊዜ የፖሊሲ እቅድ ማዘጋጀት ነው፡፡ የነዚህ ሁለት ደረጃዎች ጥምር ዘገባ ከተዘጋጀ በኋላ የሚመጣውና ሦስተኛው ደረጃ ደግሞ እያንዳንዱ አገር

2

የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 8 ቀን 2000 ዓ.ም. አፅድቃለች፡፡ ነገርግን የልማት ግቦቹን ለማሳካት የሚደረገው ጥረት በግልጽ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ ወር 2003 ዓ.ም. ነበር፡፡ የመጀሪያውን ግዜያዊ የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ሰነድ ኢትዮጵያ


የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች በብሔራዊ የልማት ፖሊሲ መአቀፉ ውስጥ በተሟላ ሁኔታ ለማካተት የተወሰደው የመጀመሪያው ጉልህ እርምጃ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. በመንግስት፣ በተ.መ.ድ. እና በሌሎች የልማት አጋሮች የተካሄደው ‹‹የሚሊኒየም የልማት ግቦች የፍላጎት ዳሰሳ›› ነበር፡፡ ይህ ጥናት የኢትዮጵያ የአስር አመት የሚሊኒየም የልማት ግቦች ጠቋሚ እቅድ እንዲዘጋጅ እና በአገሪቱ ቀጣይ የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ሰነዶች ውስጥ የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች እና የሚያስፈልገው ወጪ በግልጽ እንዲካተት አስችሏል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ በመተግበር ላይ ያሉት የአገሪቱ የመካከለኛ ጊዜ የልማት እቅዶች የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች መሰረት በማድረግ የተቀረጹ ናቸው፡፡ የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች ማሳካት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የአምስት አመት የልማት እቅድ (1998-2002) እና በአሁኑ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ (2003-2007) ውስጥ በግልጽ ተካትቶ ይገኛል፡ ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የአምስት አመት የልማት እቅድ (ፓስዴፕ) የኢትዮጵያ የአስር አመት የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች እቅድ የመጀመሪያው አምስት አመት አካል ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡ ፡ በተመሳሳይ መልኩ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ (ጂቲፒ) የተዘጋጀው እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. የተካሄደውን የሚሊኒየም የልማት ግቦች ዳሰሳ ግኝቶችን መሰረት ያደረገ

ነው፡፡ የሚከተሉት የዚህ ጽሁፍ ክፍሎች በኢትዮጵያ የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች የሚገኙበትን ደረጃ እና ግቦቹን ከማሳካት አኳያ የተገኙ ውጤቶችን ይዳስሳሉ፡፡

2.1

ከፍተኛ ድህነትን ማጥፋት

ኢትዮጵያ እጅግ ድሃ ከሚባሉት አገሮች አንዷ ናት፡፡ እ.ኤ.አ. በ2008 ዓ.ም. በወጣው የሰብአዊ ልማት ዘገባ (ኤች. ዲ. አር.) 44 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ሕዝብ ከብሔራዊ የድህነት ወለል በታች የሚኖር ሲሆን 23 በመቶው በቀን ከአንድ የአሜሪካን ዶላር በታች፣ 78 በመቶው ደግሞ ከሁለት የአሜሪካን ዶላር በታች የቀን ገቢ የሚተዳደር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሰብአዊ ልማት ምጣኔ 0.389 ሲሆን ይህም በአመቱ መረጃ ከነበራቸው 179 አገሮች ውስጥ 169ኛ ደረጃ ያሰጣታል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከብሔራዊ የድህነት ወለል በታች የሚኖረው የአገሪቱ ሕዝብ በመቶኛ እ.ኤ.አ. ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ያለማቋረጥ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በድህነት ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ቁጥር ምጣኔም እ.ኤ.አ. በ1996 ከነበረበት 45.5 በመቶ እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም. 41.9 በመቶ፣ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. ደግሞ 38.7 በመቶ በመድረስ በአጠቃላይ የ ሰባት በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ ከዚያም ወዲህ በድህነት ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ቁጥር ምጣኔ እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም. ወደ 36.6 በመቶ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ወደ 34.6 በመቶ ቀንሷል፡፡ ይህም ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2009/10 ወደ 29.2 በመቶ እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡ ፡ በተመሣሣይ መልኩ የደህንነት ሁኔታን ከማሳየት አኳያ ተመራጭ የሆነው የነፍስ ወከፍ የፍጆታ ወጪ አሃዝም ከፍተኛ የድህነት ቅነሳ ውጤት መገኘቱን ይጠቁማል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ባሉት አስር አመታት የአንድ አዋቂ ሰው አማካይ የነፍስ ወከፍ የፍጆታ

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ያዘጋጀችው እ.ኤ.አ. በኑቬምበር ወር 2002 ዓ.ም. ሲሆን በዚያው ዓመት በጁላይ ወር የመጀመሪያው የተሟላ የድህነት ቅነሳ መርሃግብር ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡ ይህ ኤስ.ዲ.ፒ.አር.ፒ. በመባል የሚታወቀው መርሃግብር እ.ኤ.አ. ከ2002/2003 እስከ 2004/2005 ያሉትን አመታት ይሸፍናል፡፡

ሰንጠረዥ 2: የኢትዮጵያ የሰብአዊ ሌማት ሁኔታ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገሮች ጋር በንፅፅር ሲታይ ጠቋሚዎች

የሰብአዊ ሌማት ምጣኔ

ሌዩነትን የሰብአዊ ሌማት ምጣኔ ጠቅሊሊ የነፌስ ወከፌ ገቢ (ፒፒፒ-2008$) ከገቢ ላሊ የሰብአዊ ሌማት ምጣኔ አማካይ እዴሜ የእናቶች ሞት ምጣኔ አማካይ የትምህርት አመታት

አመት

ኢትዮጵያ

ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገሮች

2000 2005 2009 2010 2010

0.250 0.287 0.324 0.328 0.216

0.315 0.366 0.384 0.389 0.261

ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገሮች/ ኢትዮጵያ 1.26 1.28 1.19 1.19 1.21

2010

992

2050

2.07

2010

0.357

0.436

1.22

2010 2003-2008 2010

56.1 720 8.3

52.7 881 4.5

0.94 1.22 0.54

ምንጭ: የተመዴ የሰብኢ የሰብአዊ ሌማት ሪፖርት (እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም.)

ወጪ ከሰሃራ በ17.4 በመቶ ጨምሯል፤ ይህም በየአመቱ በመቶ በማሳየትም በታች የሚገኙ አገሮች የ1.9ከሰብአዊ ሌማት በ11ኛ አንፃር ከፌተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡የሆነ እ.ኤ.አ. ተግዲሮት ከ2005 እስከ 2010 ጭማሪ ማለት ነው፡፡ የአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ባሉት አመታት የኢትዮጵያ የሰብአዊ ልማት ምጣኔ በሦስት ደረጃዎች ስሇሚያጋጥማቸው የሰብአዊ ሌማት ምጣኔአቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ሰብአዊ እቅድ እንደሚጠቁመው የድህነት መጠን በገቢና በምግብ ፍጆታ ተሻሽሏል፤ አመታዊ ለውጡም እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. ከማሻሻሌ በጊዜ ሂዯት ሇውጥ በማሳየትም ሲለካ ሌማትን በየአመቱ እየቀነሰ መጥቶአንፃር እ.ኤ.አ. ከፌተኛ በ2009/10ውጤት ከነበረበት አስመዝግባሇች፤ በአማካይ 2.73 በመቶ ነበር፡፡ ዯረጃ እ.ኤ.አ. ከ2005 29.2 በ11ኛ በመቶ እና 28.2ሊይ በመቶትገኛሇች፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014/15 22.2. በመቶ እስከ 2010 ባለት አመታት የኢትዮጵያ የሰብአዊ ከታች በሰንጠረዥ ሶስት ላይ እንደሚታየው በኢትዮጵያ ከገቢ አንፃር እና 21.2 በመቶምጣኔ እንደሚደርስ ይቀበላል፡፡ ሌማት በሦስት ዯረጃዎች ተሻሽሎሌ፤ አመታዊ ሇውጡም እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. እስከ ድሃ የሆኑት (የቀን ገቢያቸው ከ$1.25 በታች የሆኑት) ሰዎች ቁጥር 2010 ዓ.ም. በአማካይ 2.73 በመቶ ነበር፡፡ የአጠቃላይ የሕዝቡን 39 በመቶ የሚሆኑት ናቸው፡፡ በአንፃሩ የዘርፈ ብዙ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች ከሰብአዊ ልማት አንፃር ከፍተኛ ድህነት ተጠቂ የሆኑት 90 በመቶ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የሆነ ተግዳሮት ስለሚያጋጥማቸው የሰብአዊ ልማት ምጣኔአቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ልማትን ከማሻሻል በገፅ 10 ይቀጥላል ... አንፃር ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች፤ በጊዜ ሂደት ለውጥ |5


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት የገጠሟቸው ወቅታዊ ስጋቶች እና ተግዳሮቶችን አስመልክቶ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት፣ በጉዳዩ ላይ አግባብነት ያላቸውን ባለሙያዎችና የሲቪል ማኅበረሰቡ ተወካዮች የሚሠጧቸው ቃለ-ምልልሶች የሚተላለፍበት ዓምድ ነው፡፡

የሲቪል ማህበረሰብን አስተዋፅኦ ከማጠናከር አንፃር መንግስት ወሳኝ ሚና እንዳለው እናምናለን

ፒተር ሄንይ ገቨርናንስ ኢንተርን አይ.ኤ.ኢ. (አይሪሽ ኤይድ ኢትዮጵያ)

ብዙወርቅ ከተተ ከፍተኛ የገቨርናንስ ፕሮግራም ማናጀር አይ.ኤ.ኢ. (አይሪሽ ኤይድ ኢትዮጵያ)

ዚህ የሙሐዝ እትም እንግዶቻችን ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ፣ ከፍተኛ የገቨርናንስ ፕሮግራም ማናጀር አይ.ኤ.ኢ. (አይሪሽ ኤይድ ኢትዮጵያ) እና ሚስተር ፒተር ሄንይ ገቨርናንስ

ኢንተርን አይ.ኤ.ኢ. (አይሪሽ ኤይድ ኢትዮጵያ) ናቸው፡፡ የሙሐዝ ዝግጅት ክፍል ከነዚህ የለጋሽ ድርጅት ተወካዮች ጋር በአንድ አገር እድገት ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ሚና፣ በሲቪል ማህበረሰብ፣ በመንግስት እና በልማት አጋሮች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ተፈፃሚ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ስላስከተለው ውጤት አነጋግሯቸዋል፡

|6


አይ.ኤ.ኢ.፡ - በአጠቃላይ የአንድ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋም ሊጫወተው የሚገባው እና የሚችለው ሚና የሚወሰነው በተቋሙ ዓይነት፣ በሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ የእድገት ደረጃ እና ለዘርፉ ከተቀመጠው ምህዳር እንዲሁም በዘርፉ ውስጥ የሚገኘው አመራር ጥራት እንደሆነ እናምናለን፡፡ ይሁን እንጂ አንድ በሳል የሲቪል ማህበረሰብ ተቋም ምህዳሩ የሚፈቅድለት ሲሆን ሊጫወት የሚችለው ሚና የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ - ሊሰፉ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅና መሞከር፣ የዜጎችን የተደራጀ እንቅስቃሴ ማሳለጥ፣ መንግስታዊም ሆነ ሌላ ሃይል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሚፈጽምበት ሁኔታ የክትትል ሚና መጫወት፣ መረጃ ማሰራጨትና ግንዛቤ ማዳበር፣ አቅም ግንባታ፣ በተጨባጭ ጥናትና መረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ትንተና እና አድቮኬሲ፣ ያልተሟላ ፍላጎት ባለበት ሁኔታ የአገልግሎት አቅራቢነት ሚናን መደገፍ እና ሌሎችም፡፡

በቁጥጥር ስርአት ውስጥ የተካተቱት አንዳንዶቹ ድንጋጌዎች መንግስት የክትትል ሚና በሚጫወትበት የራስ በራስ ቁጥጥር ስርአት ማዕቀፍ በተሻለ መልኩ ተፈፃሚ እንዱሆኑ የሚችሉ ናቸው ፡ በአጠቃላይ ይህ የመንግስት ሚና፡ - አወንታዊና ግልጽ ቁጥጥርን ጨምሮ ደጋፊ ምህዳር መፍጠር፣ ትክክለኛ ባህሪ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ መኖሩን ማረጋገጥ፣ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ምክክርን ማሳለጥ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት በክልልና በአካባቢ ደረጃ ከዜጎችና ከአካባቢ አስተዳደር ጋር መስራት እንዲችሉ በቂ ምህዳር ማመቻቸት፣ እና በመንግስት መዋቅርና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ቅንጅት፣ መማማርና የክህሎት ልውውጥን ለማጠናከር የሚያስችል የአቅም ግንባታን ያጠቃልላል፡፡

ሙሐዝ፡ ሙሐዝ፡ - የሲቪል ማህበረሰብን ማህበረሰብ ከማጠናከር አኳያ የመንግስት ይጠበቃል? አይ.ኢ.ኤ.፡ ሚና ምን መሆን አለበት? አይ.ኤ.ኢ.፡ - የሲቪል ማህበረሰብን አስተዋጽኦ ከማጠናከር አንፃር መንግስት ወሳኝ ሚና እንዳለው እናምናለን፡፡ ከዚህም አልፎ መንግስት ከሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እንቅስቃሴዎች ትምህርት ሊወስድ የሚችልባቸው ሁኔታዎችም ይኖራሉ፤ ለአብነት የዜጎችን ተሳትፎ ከማሳደግ እና ከታች ወደላይ የሚካሄድ የልማትና መልካም አስተዳደር አሰራር አማራጮችን በተለይም የመንግስትን ሚና የሚደግፉና የግድ ሰፊና አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ያለበት የመንግስት ሚና ሊደርሳቸው የማይችሉትን የህብተሰብ ክፍሎች የሚደርስ አሰራርን በተመለከተ፡

-

ከሲቪል ዘርፍ ምን

የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ እንቅስቃሴውን ከሚያካሂድበት አግባብ እና ከመንግስት፣ ከለጋሽ ድርጅቶችና ከማህበረሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር ከፍተኛ እመርታን አሳይቷል፡፡ ነገርግን በነዚህ ስኬቶችና ልምዶች ላይ ተነስቶ ወደተሻለ ደረጃ ከመሸጋገር አኳያ ብዙ ይቀረዋል፡ ፡ በኛ እይታ ከሲቪል ማህበረሰብ የሚጠበቀው ነገር ውስጣዊ አስተዳደርን፣ ውጤታማነትን እና አመራርን ጨምሮ የሚከተሉትን ያካትታል - ለመርህ ታማኝ መሆን፣ የአመራር ብቃት እና በአርዓያነት መምራት፣

አወንታዊ መስተጋብር፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ የማያቋርጥ ለውጥ ማለትም ያለማቋረጥ በሚለዋወጥ የፋይናንስና የፖለቲካ መአቀፍ ውስጥ ራስን አጣጥሞ መቀጠል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ዓይነቶች በተሻለ ውጤታማነት አብሮ የመስራትና እርስ በርስ የመማማር ልምድ ማዳበር፣ ከሚወክሉትና ከሚያገለግሉት የማህበረሰብ ክፍል ጋር የተሻለ ግንኙነት መፍጠር፣ ከፖሊሲ አውጭዎችና ተመራጮች እና ከሌሎችም ጋር በተሻለ መልኩ አብሮ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

ሙሐዝ፡ - በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅና አዋጁን ተከትለው በወጡት መመሪያዎች ዙሪያ ያልዎትን አስተያየት ሊሰጡን ይችላሉ? አይ.ኤ.ኢ.፡ - የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅን እና በቀጣይ የወጡትን መመሪያዎች በተመለከተ በአጠቃላይ የምዝገባና ቁጥጥር የፖሊሲ መአቀፍ ማስፈለጉን እንገነዘባለን፡፡ እዚህ ላይ በዋነኝነት ታሳቢ መደረግ ያለበት የአዋጁ ዓላማዎች ናቸው፡፡ በኛ እይታ ቁልፍ ተግዳሮት ሊባሉ የሚችሉት የ90 – 10 መመሪያ እና የሲቪል ማህበረሰብ ከአገር ውስጥ ምንጮች ሃብት የማሰባሰብ አቅም ናቸው፡፡ በተጨማሪም ምንም እንኳ የመቶኛ ስሌቱ በቂ ቢመስልም የ70 – 30 መመሪያም በኛ እይታ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትን ዓይነት፣ ባህሪያትና ስብጥር በበቂ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ አይደለም፡፡ የአስተዳደራዊ እና የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጭዎች አተረጓጎም ችግር አለበት፡፡ በዚህም ዙሪያ ቀጣይ ውይይቶች እየተካሄዱ በገፅ 11 ይቀጥላል ...

|7

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ሙሐዝ፡ - በአገሪቱ በመልካም አስተዳደር እና በአጠቃላይ ልማት ዙሪያ የሲቪል ማህበረሰብ ሚና ምንድነው?


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

በራስ ተነሳሽነት በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ሲቪል ማህበረሰቦች በጎ ሥራ የሚዳሰስበት ዓምድ ነው።

ከውርስ የመጣ አዲስ አበባ አዲሱ ገበያ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ወ/ሮ ዘውዲቱ መሸሻን የማያውቅ የለም፡ ፡ የአካባቢው ሰዎች የተቸገረና መንገድ ላይ የወደቀ ሰው ከተመለከቱ፤ “ወ/ሮ ዘውዲቱጋ ውሰዱት፤ እሳቸው የድሀ እናት ናቸው” በማለት ስለእሳቸው ርህራሄ ምሥክርነታቸውን ይሰጣሉ፡ ፡ እሳቸውም የወደቁትን አንሥተው፣ የተቸገሩትን ረድተው፣ እናት ላጡ እናት ሆነው፣ እቅፍ ድግፍ አድርገው ይይዟቸዋል፡፡ ወ/ሮ ዘውዲቱ ከፊታቸው ፈገግታ፣ ከልቦናቸው ደግነትና ርኅሩኅነት የሚነበብባቸው የወደቁትን አሳዳጊ፤ ያጡትን ሰብሳቢ እናት ናቸው፡፡ ይህም ባህሪያቸው ነው “ወይዘሮ ዘውዲቱ መሸሻ የበጎ አድራጎት ድርጅት”ን የወለደው፡፡

ጅማሬ

ወ/ሮ ዘውዲቱ ወላጆቻቸውን ያጡና ለችግር የተጋለጡ ልጆችን ሰብስበው ማሳደግ የጀመሩት በጥቅምት ወር 1984 ዓ.ም. ይሁን እንጂ ከዚያ አስቀድሞም ልጆችን ሰብስቦ ማሳደግ ከአያቶቻቸው ጀምሮ በቤታቸው የነበረ ነው፡፡ እሳቸውም በበርካታ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ መሆናቸው ለዚህ በጎ አድራጎት ሥራ አስተዋጽኦ እንዳደረገ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘውዲቱ |ለሰው ማዘንና የተቸገረን መርዳት ከአያቶቼ የወረስኩት ነው´ የሚል ብሂል አላቸውÝÝ ወ/ሮ ዘውዲቱ ሕፃናትን እየሰበሰቡ ማሳደግ የጀመሩትአርሲ ሄደው በነበሩበት ወቅት ከተመለከቱት ችግር የተነሣ ነው፡፡ በወቅቱ ያገኟቸው ልጆች አሳዳጊ አጥተውና ተጎሳቁለው ሲመለከቱ ኅሊናቸው ዕረፍት ነሳቸው፡፡ እናም የአቅማቸውን ለማድረግ በማሰብ በጊዜው የነበሩ የቤተክህነት ኃላፊዎችን ሲያማክሩ “እኛም እንረዳሻለን” የሚል ተስፋ በማግኘታቸው አምስት ልጆች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ ይሁን እንጂ እንረዳሻለን ካሏቸው የጠበቁትን ባለማግኘታቸው ያመጧቸውን ልጆች በራሳቸው ማሳደግ ጀመሩ፡፡ ወ/ሮ ዘውዲቱ በወቅቱ ከፍተኛ የጤና ችግር ነበረባቸው፡ ፡ ነገር ግን ከጤናቸው ይልቅ ያመጧቸውን ልጆች ለማሳደግ ቅድሚያ ሰጡ፡፡ ልጆቹን እያስተማሩ ሲያሳድጓቸው ቀስ በቀስ ጤናቸው እየተስተካከለላቸው መጣ፡፡ በዚህ የተነሣ፤ “እግዚአብሔር ጤናዬን ከሰጠኝማ ማሳደጉን አጠንክሬ እቀጥልበታለሁ” በማለት የበጎ አድራጎት ተግባራቸውን አጠናክረው ተያያዙት፡፡ ቀስ በቀስም የልጆቹ ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ሁለት መቶ ሃምሣ በመድረሱ ስራው መስመር ይዞ ሕጋዊ እንዲሆን

|8

ወ/ሮ ዘውዲቱ መሸሻ በማሰብ ቦርድ አቋቋሙ፡፡ ድርጅቱም “ወይዘሮ ዘውዲቱ መሸሻ የበጎአድራጎት ድርጅት” በሚል ስያሜ በ1996 ዓ.ም. ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ በአሁኑ ጊዜ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 20/21 የቤት ቁጥር 1274 ልዩ ስሙ ኮተቤ መሳለሚያ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የበጎ አድራጎት ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ልጆቹን የሚያሰባስቡት ከየት ነው?

ወ/ሮ ዘውዲቱ ገዳማትና አድባራት ሔደው መሳለም የዘወትር ተግባራችው ነው፡፡ በዚያም የተቸገረ አይተው


ደግነት አያልፉም፡፡ “ላስተምራችሁ፤ እኔ የበላሁትን በልታችሁ ታድጋላችሁ” በማለት አሳዳጊ ያጡና የተቸገሩ ሕፃናትን እንዲሁም የችግረኛ ልጆችን ለአጥቢያው ቤተክርስቲያንና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀው በማምጣት ዘመናዊ እና መንፈሳዊ ትምህርት እያስተማሩ በመልካም ሥነ-ምግባር ኮትኩተው ያሳድጋሉ፡፡ ከተለያዩ አካባቢዎች ለችግር የተጋለጡ ልጆችን ሰብስበው ስለሥራ ክቡርነትና ስለሀገር ፍቅር በማስተማር ነገ ከራሳቸው ተርፈው ለወገኖቻቸው እና ለሀገራቸው አለኝታ የሚሆኑ ብቁ ዜጎች ለማፍራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ዘውዲቱ ይህን ሁሉ በጎ ተግባር የሚያከናውኑት የተትረፈረፈ ሀብት ኖሯቸው ሳይሆን ቪላ ቤታቸውን፣ መኪናቸውን እና ሀብት ንብረታቸውን ሸጠው መሆኑን የሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ ይመሰክሩላቸዋል፡፡

ፍሬዎቻቸው

ቀደም ሲል እንደተገለጸው ወ/ሮ ዘውዲቱ በቤት ውስጥ ሰብስበው የሚያሳድጓቸው ልጆች ሁለት መቶ ሃምሳ ናቸው፡፡ ከነዚህ ልጆች ጎንለጎን ሌሎች ሁለት መቶ የሚሆኑ ለችግር የተጋለጡ ልጆች በየቤታቸው እንዲረዱ ያደርጋሉ፡፡ ወ/ሮ ዘውዲቱ ዋና አላማቸው ልጆችን ሰብስቦ መመግብ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ህይወታቸውን ማሻሻልና ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ ማድረግም ጭምር ስለሆነ ልጆቻቸው በእውቀትና በክህሎት ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርሱ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡ ፡ በዚህም ጥረታቸው ወደተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት በዲግሪ ስድስት፣ በዲፕሎማ ሰባት፣ እንዲሁም በሠርተፍኬት ዘጠኝ ልጆች ተመርቀውላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገና በመማር

ያጋጠማቸው ችግር

እንደሚታወቀው በማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ የተለያዩ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ወ/ሮ ዘውዲቱም የገጠሟቸው የተለያዩ ተግዳሮቶች አሉ፡፡ ቀደም ሲል ሁለት መቶ ሃምሣ ልጆችን ያሳድጉበት የነበረው ቤታቸው በቀለበት መንገድ ግንባታ የተነሳ ፈርሶባቸዋል፡ ፡ ደረጃውን የጠበቀ የግለሰብ ቤት ለመከራየት ደግሞ የገንዘብ አቅም ውሱንነት ማነቆ ሆኖባቸዋል፡፡ አሁን ያሉበትን ቤት እስኪያገኙና እስኪረጋጉ ድረስ የሚያሳድጓቸው ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እስከመስተጓጎል ደርሰውባቸው ነበር፡፡ ድርጅቱ አሁን በሚገኝበት ቤትም ቢሆን ከልጆቹ ብዛት አንፃር እንደበፊቱ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን ወ/ሮ ዘውዲቱ ይናገራሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ብዙ ልጆች በአንድ ክፍል ውስጥ ተጨናንቀው እንዲኖሩና በአንድ አልጋ ላይም ሁለት ልጆች እንዲተኙ ማድረግ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ንዋይ ዘርዓ ዮሐንስ፥ ልጆቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ሲያብራሩ “አኗኗራቸው በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ በቆርቆሮ መጋዘንና በአፈር ቤት ውስጥ በአንድ አልጋ ለሁለት እየተኙ በተጨናናቀ ሁኔታ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ላይ ከዕቃ ጋር ተጣበው ነው ያሉት፡፡ ይህ ደግሞ ለጤናቸው ያሰጋል” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት ጉለሌ አካባቢ እያሉ እስከ ሁለት መቶ ልጆች በየቤታቸው እንዲረዱ ያደርጉ ነበር፡ ፡ ይህ በቤት ውስጥ ከሚያሳድጓቸው ልጆቻቸው በተጨማሪ ነው፡፡ ቋሚ የሆነ ገቢም ሆነ ምንም ዓይነት የገንዘብና የቁሳቁስ ዕርዳታ ሳይኖር ለእነዚግ ሁሉ ልጆች ምግብባ አልባሳት አሟልቶ½ ጤንነታቸውን ጠብቆና

ተከታትሎ በሚገባ እያስተማሩ በመልካም ሥነ-ምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ ማድረግ በአሁኑ ጊዜ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ በመሆኑም ቀ/ሮ ዘውዲቱ የሚያከናውኑት መልካም ሥራ ሊደነቅ እና ሊበረታታ የሚገባው ነው፡፡” በማለት አቶ ንዋይ ችግሩን ይገልፃሉ፡፡ ድርጅቱ በአሳዳሪነት ሕፃናትና ታዳጊ ወጣቶችን የሚያሳድግ ትምህርት ቤትም በመሆኑ የምግብ½ የአልባሳት½ የሕክምና አገልግሎት½ የትምህርት ቤት ክፍያ ወዘተ. ወጪዎች አሉበት፡፡ቀደም ሲል ለገቢ ማስገኛነት ታቅደው የተጀመሩት የዳቦ ማምረቻ፣ የወፍጮ ቤት፣ የሽመና እና የጧፍ ስራ ድርጅቶችም ትርፋማ ሳይሆኑ በመቅረታቸው በአሁን ሰዓት ድርጅቱ እነዚህን ወጪዎች በዘላቂነት የሚሸፍን ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ የለውም፡፡ ካለው የገንዘብ አቅም ውሱንነት የተነሳም ደረጃውን የጠበቀ ፕሮጀክት ነድፎ ተቋሙን ሊያሳድግ የሚችል ገንዘብ የሚያፈላልግ ባለሙያ ለመቅጠር አልተቻለም፡፡ ይሁን እንጂ ድርጅቱ በዚህ ሁሉ ተግዳሮት ውስጥ ሆኖ የተመሰረተበትን አላማ ለማሳካት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፡፡

የወደፊት ዕቅድ

በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ ያለበት ዋነኛ ችግር ለልጆቹ የሚሆን በቂ መኝታ ሥፍራ እና የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ለማሟላት የሚያስችል ገንዘብ የሚሰጥ ቋሚ ለጋሽ አለመኖሩ ነው፡ ፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቦርዱ ዕቅድ አውጥቶ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመንግስትን ፖሊሲ መሠረት ባደረገና የአካባቢውን ህብረተሰብ ባሳተፈ መልኩ ልጆቹ ለወደፊት ከጠባቂነት ተላቀው ራሳቸውን ችለው የሚኖሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ዕቅድ አዘጋጅቷል፡ ፡ ለዚህም የተለያዩ የሙያ ስልጠና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ልጆቹን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ ---------------------------------------

|9

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ላይ የሚገኙ ልጆች አሏቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ሥራ የያዙና ራሳቸውን በመቻል ቤተሰብ መስርተው ለወግ ለማዕረግ የበቁም አሉ፡፡


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

አገራት ውስጥ ከፍተኛ የሚባለው ነው፡፡

የሚሊኒየሙ

ከገፅ5 የቀጠለ

...

የድህነት ቅነሳ ከከተሞች ይልቅ በገጠር የጎላ ውጤት አሳይቷል፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች የድህነት ተጠቂ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል በቁጥር እ.ኤ.አ. በ1996 ከነበረበት 47.5 በመቶ እ.ኤ.አ. በ2005 ወደ 39.3 በመቶ ወርዷል፡፡ በነዚህ አመታት ለታየው የድህነት ቅነሳ በተለይም በገጠር የፍጆታ ወጪ ከመጨመሩ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ በሌላ በኩል በአጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ የነፍስ ወከፍ ገቢ ጭማሬ የታየ

ሰንጠረዥ 3: የዘርፇ-ብዙ ዴህነት (ኤም.ፒ.አይ.) ሁኔታ በኢትዮጵያ ኤም.ፒ.አይ.

የዘርፇ-ብዙ ዴህነት ሰሇባ የሆነ የህብረተሰብ ክፌሌ

ቢያንስ አንዴ አይነት የዴህነት ተጠቂ የሆነ የህብረተሰብ ክፌሌ በመቶኛ (እ.ኤ.አ. 2000-2008)

ጂኒ ኮፉሸንት

በገቢ መጠን ከዴህነት ወሇሌ በታች የሚኖረው የህብረተሰብ ክፌሌ (እ.ኤ.አ. 2000-2008)

(እ.ኤ.አ. 2000-08)

0.582

ቁጥር (%)

የዴህነት ጥሌቀት (%)

ትምህርት

ጤና

የኑሮ ዯረጃ

90

64.7

83.9

48.2

94.2

29.8

ፒ.ፒ.ፒ. $1.25 በቀን (%)

ብሄራዊ የዴህነት ወሇሌ (%)

39

44.2

ምንጭ: የተመዴ የሰብአዊ የሰብኢ ሌማት ሪፖርት (እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም.)

ከሊይ ከገጠር በሰንጠረዥ ሶስት ይልቅ ሊይ እንዯሚታየው የሆኑት (የቀን በሴቶች የተያዙት በኢትዮጵያ ወንበሮች ቁጥርከገቢ 21 አንፃር ሲሆን ጭማሬው (13.8 በመቶ) የሚሆኑትዴሃ በግል የጤና ተቋማት ተወልደዋል፡ ገቢያቸው ከ$1.25 ሰዎች የአጠቃሊይ የሕዝቡን 39በ2005 በመቶዓ.ም. የሚሆኑት (18.75 በመቶ)ቁጥር ብቻ ነው፡፡ በከተማ (33.5 በመቶ) የጎላ ነበር፡፡ በታች የሆኑት) ፡ እ.ኤ.አ. በተካሄደው የስነናቸው፡፡ በአንፃሩ የዘርፇ ብዙ ዴህነት ተጠቂ የሆኑት 90 በመቶ ህዝብ ሲሆንእናይህም ከሰሃራ በታች መሰረት ጤና ቅኝት (ዲ.ኤች.ኤስ.) 2.4 የሕፃናትን ሞት መቀነስ 2.2 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን የሚባሇው ነው፡፡ ከሚገኙ አገራት ውስጥ ከፌተኛ እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. ከ1998 እስከ 2004 ባሉት አመታት በ2005 ዓ.ም. የጨቅላዎች የሞት የእናቶች ሞት መጠን በህይወት ከተወለዱት ለሁሉም ማዳረስ መጠን 77 የነበረየጎሊ ሲሆን ውጤት ከአምስት አመት የዴህነት ቅነሳ ከከተሞች ይሌቅ በገጠር አሳይቷሌ፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች 100,000 ህፃናት 637 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2009/10 የመጀመሪያ ደረጃ (ከ1ኛ እሰከ በታች ያሉ ህፃናት የሞት መጠን ደግሞ የዴህነት ተጠቂ የሆነው የህብረተሰብ ክፌሌ በቁጥር እ.ኤ.አ. በ1996 ከነበረበት 47.5 በመቶ 8ኛ ክፍል) አጠቃላይ የቅበላ ምጣኔ (ጂ.ኢ.አር.) በህይወት ከሚወለዱት አንድ ሺህ ሕፃናት 2.6 የዴህነት ኤች.አይ.ቪ. ኤድስ፣ ወባ እና እ.ኤ.አ. በ2005 ወዯ 39.3 በመቶ ወርዶሌ፡፡ በነዚህ አመታት ሇታየው ቅነሳ በተሇይም 95.9 በመቶ (93 በመቶ ለሴቶች እና 98.7 በመቶ 123 ነበር፡፡ ይህም በአምስት አመታት በገጠር የፌጆታ ወጪ ከመጨመሩ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ በላሊ በኩሌ በአጠቃሊይ ከፌተኛ የሆነ ለወንዶች) ደርሷል፡፡ በዚሁ አመት (እ.ኤ.አ. ውስጥ የ20.6 በመቶ እና 25.9 በመቶ ሌሎች በሽታዎችን መዋጋት የነፌስ ወከፌ ገቢ ጭማሬ የታየ ሲሆን ጭማሬው ከገጠር (13.8 በመቶ) ይሌቅ በከተማ (33.5 በ2009/10) የተጣራ የቅበላ ምጣኔ (ኤን.ኢ.አር.) ቅናሽ ያሳያል፡፡ በተመሣሣይ መልኩ ኢትዮጵያ በኤች.አይ.ቪ. ኤድስ ወረርሽኝ በመቶ) 89.3 በመቶ (87.9 የጎሊ በመቶ ነበር፡፡ ለወንዶች እና 86.5 የክትባት ሽፋን በሦስት አመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁት አገሮች አንዷ

በመቶ ለሴቶች) ነበር፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ከ52 በመቶ ወደ 69 በመቶ ጨምሯል፡፡ ስትሆን እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. የበሽታው 2.2 የመጀመሪያ ዯረጃ ትምህርትን ሇሁለም ማዲረስ የቅበላ ምጣኔ መረጃ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. በተካሄደው የስነ- ስርጭት 3.5 በመቶ ነበር፡፡ በቅርቡ የተጠናቀሩ ከፍተኛ መሻሻል ነገርግን የመጀመሪያ በክልሎች ህዝብ እና (ከ1ኛ ጤና ቅኝት እ.ኤ.አ.ያሳያል፡፡ በ2009/10 ዯረጃ እሰከ(ዲ.ኤች.ኤስ.) 8ኛ ክፌሌ)የዲ.ኤች.ኤስ. አጠቃሊይ የቅበሊ ምጣኔ እና የወላዶችና ህፃናት ክትትል መካከል ያለው አጠቃላይ የቅበላ ምጣኔ እና መሰረት በድን ሆነው የሚወለዱ ህፃናት (ኤ.ኤን.ሲ.) መረጃዎች (ጂ.ኢ.አር.) 95.9 በመቶ (93 በመቶ ሇሴቶች እና 98.7 በመቶ ሇወንድች) ዯርሷሌ፡፡እንደሚያመለክቱት በዚሁ የተጣራ የቅበላ ምጣኔ ልዩነት ከፍተኛ ነው፡፡ ቁጥር በህይወት ከሚወለዱት አንድ የወረርሽኙ ስርጭት(87.9 ከተፈራው ያነሰ ነበር፤ አመት (እ.ኤ.አ. በ2009/10) የተጣራ የቅበሊ ምጣኔ (ኤን.ኢ.አር.) 89.3 በመቶ በመቶ ሺህ ሕፃናት 37 የነበረ ሲሆን ይህም የስርጭት መጠኑም እ.ኤ.አ. በ2006/7 2.1 ሇወንድች እና ማረጋገጥና 86.5 በመቶ ነበር፡፡ የአንዯኛ ዯረጃ ትምህርት የቅበሊ ምጣኔ መረጃ 2.3 የፆታ እኩልነትን ሴቶችንሇሴቶች) በ2000 ዓ.ም. ከነበረው 52 ጋር ሲነፃጸር በመቶ (በከተማ 7.7 በመቶ እና በገጠር 0.2 ሇወንድችም ሆነ ሇሴቶች ከፌተኛ መሻሻሌ ያሳያሌ፡፡ ነገርግን በክሌልች መካከሌ ያሇው ቅናሽ አሳይቷል፡፡ ሆኖም በኢትዮጵያ በመቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2009/10 የኤች. ማብቃት አጠቃሊይ የቅበሊ ምጣኔ እና የተጣራ የቅበሊ ምጣኔ ሌዩነት ከፌተኛ ነው፡፡ በተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ.) ውስጥ ከሚወለዱ አስራ ሦስት ህፃናት አይ.ቪ. ስርጭቱ 2.4 በመቶ እንደነበረ እና አንዱ የአንድ አመት ልደቱን ሳያከብር ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥርም 1.1 የተቀረጹትን እኩልነት ጋር የተያያዙ የፆታ እኩሌነትን ማረጋገጥና ሴቶችን ማብቃት 2.3ከፆታ የልማት መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ ይሞታል፤ ከስምንት ህፃናት አንዱ ደግሞ ሚሊዮን እንደነበረ ይገመታል፡፡ በተመዴ የሌማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዱ.ፒ.) የተቀረጹትን ከፆታ እኩሌነት ጋር የተያያዙ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. ያገኘችው የአምስት አመት ልደቱ ድረስ በህይወት 2.7 ዓ.ም.የአካባቢን በተጨማሪም እ.ኤ.አ. የጨቅላዎች የሌማት መመዘኛዎች መሰረት በማዴረግ ኢትዮጵያ በ2005 ያገኘችውደህንነት ውጤትቀጣይነት ውጤት 0.393 ሲሆን ይህም የ148ኛ ደረጃ አይቆይም፡፡ ሞት ምጣኔ እና የሕፃናት ምጣኔአገሪቱ ሲሆን ይህም ያሰጣታሌ፡፡ በዚህሞት ስላት እኩሌነት አንፃር ባለው ከፆታ ሁኔታ ማረጋገጥ ያሰጣታል፡፡0.393 በዚህ ስሌት አገሪቱ ከፆታ የ148ኛ እኩልነት ዯረጃ በክልሎች መካከል፣ በገጠር እጅግ ያሌሇሙ አንዶ ነች፡፡ በከተማና በእማወራዎች የሚተዲዯሩ ቤተሰቦች ገቢበየጊዜው አንፃር እጅግ ያልለሙ ከሚባሉትከሚባለት ውስጥ አንዷ ውስጥ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት እንዲሁም በትምህርትና ሃብት መጠን ነች፡፡ በእማወራዎች ቤተሰቦችያነሰ ገቢ ነው፣ በአባወራ የሚተዳደሩ ከሚተዲዯሩት የሴቶች ኤኮኖሚያዊ ተሳትፍ ከወንድች ሲነፃጸር እየጨመረ መጥቶ ጋር እ.ኤ.አ. በ1990 ዓ.ም. ልዩነት ያሳያል፡፡ እ.ኤ.አ. በአባወራ ከሚተዳደሩት ያነሰ ነው፣ የሴቶች ከፍተኛ ከነበረበት 19 በመቶ ተነስቶ እ.ኤ.አ. በ2009/10 ከአምስት አመት በታች ያሉ ኤኮኖሚያዊ ተሳትፎ ከወንዶች ጋር ሲነፃጸር በ2009/10 68.5 በመቶ ደርሷል፡፡ በገጠራማ ዝቅተኛ ነው እንዲሁም ከስራ አጥ ሰዎች ውስጥ ህፃናት የሞት መጠን እና የጨቅላዎች አካባቢዎች የንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት የሴቶች ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ በመጀመሪያና የሞት መጠን ወደ 101/1000 እና እ.ኤ.አ. በ2004/05 ከነበረበት 35 በመቶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሴቶችን ተሳትፎ 45/1000 ቀንሷል፡፡ በ2009/10 65.8 በመቶ ደርሷል፡፡ በዚሁ ስንመለከት በ2005/2006 የተጣራ የቅበላ 2.5 የእናቶችን የጤና ሁኔታ ጊዜ በከተሞች ስሌቱ ከ80 በመቶ ወደ ምጣኔው ለወንዶች ያደላ ከፍተኛ በዛባት 91.5 በመቶ አድጓል፡፡ የመፀዳጃ አገልግሎት ያሳያል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት ስርዓቱ ከፍ ማሻሻል ተደራሽነት ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ እያልን ስንሄድ የፆታ ድርሻው የበለጠ እየተዛባ የፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ. በ2009/10 የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 5 ይሄዳል፡፡ በመጨረሻም በሦስተኛው ፓርላማ መረጃዎች አንደሚያመለክቱት በአገሪቱ ሚሊዮን ሄክታር ነበር፡፡ በሌላ በኩል እ.ኤ.አ. (እ.ኤ.አ.2005-2010) ከነበሩት ወንበሮች የወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ምጣኔ በ2010 ዓ.ም. የተደረገው የሚሊኒየሙ በሴቶች የተያዙት 117 (22 በመቶ) ብቻ መሆኑ እ.ኤ.አ. በ2009/10 55 በመቶ ደርሷል፡፡ የልማት ግቦች ዳሰሳዊ ጥናት እንደሚያሳየው እንደሚያሳየው የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. ከተወለዱ ህጻናት በኢትዮጵያ የብዝሃ ሕይወት የሚገኝበት ዝቅተኛ ነው፡፡ በአሁኑ ፓርላማ የሴቶች ተሳትፎ ውስጥ እጅግ የሚበዙት (94 በመቶ) አደገኛ ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው በመቀመጫ ቁጥር ሲታይ የተወለዱት በቤት ውስጥ ሲሆን አምስት የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ገልፆአል፡፡ ለዚህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር በመቶ የሚሆኑት ብቻ በህዝብ የጤና | 10 ቤት 27.8 በመቶ ደርሷል፤ ተቋማት እንዲሁም ከአንድ በመቶ በታች ››››››በገፅ 16 ይቀጥላል ... በፌደሬሽን ምክር ቤት ግን


ናቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአዋጁ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመለማመድና ለውጦቹን ለመተግበር የተሰጠው የመሸጋገሪያ ጊዜ በጣም አጭር እንደነበረ እናምናለን፡፡ በተጨማሪም በቁጥጥር ስርዓቱ ውስጥ የተካተቱት አንዳንዶቹ ድንጋጌዎች መንግስት የክትትል ሚና በሚጫወትበት የራስ በራስ ቁጥጥር ሥርዓት መአቀፍ በተሻለ መልኩ ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፤ በዚህ ሁኔታ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትን አወንታዊ በሆነ መልኩ መቆጣጠር ይቻል ነበር፡፡ በቁጥጥርና ክትትል ስርዓቱ ውስጥ ከሲቪል ማህበረሰብ ጋር መስተጋብር ያላቸው የተለያዩ የመንግስት አካላትን ስልጣንና ሚና በይበልጥ ግልጽ ማድረግም አስፈላጊ ነው፡፡ እንደኛ አስተያየት ነገሮች እየሰከኑ የመጡ ቢመስልም ሁኔታው ገና በለውጥ ሂደት ላይ ያለ ነው፡ ፡ ማንኛውም የምዝገባ ወይም ቁጥጥር ስርዓት የዘርፉን እድገት እንዳያቀጭጭ የሲቪል ማህበረሰብን አመጣጥ፣ የእድገት ደረጃና እመርታ ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡

ሙሐዝ፡ - አንዳንድ ወገኖች የመመሪያዎቹ በስራ ላይ መዋል በተለይ ከሦስት ዓመት በላይ የመተግበሪያ ጊዜ ያላቸውን መርሃግብሮች በአሉታዊ መልኩ ተፅእኖ አሳድሮባቸዋል ይላሉ፡ ፡ በዚህ ላይ የርስዎ አስተያየት ምንድነው? አይ.ኤ.ኢ.፡ - ተጽእኖ መኖሩ በግልጽ የሚታይና ቀጣይም ነው፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች - በተለይም መያዶች - የልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ግራ የተጋቡበት ሁኔታ ነበር፡፡ ብዙ መያዶች ሰራተኞቻቸውን ለመቀነስ ተገድደዋል፤ ሌሎች ደግሞ ቀውስ ውስጥ የገቡበት ሁኔታ ነበር፡ ፡ በመካሄድ ላይ ከነበሩ መርሃግብሮች አግባብነት ባለው ሁኔታ ለመውጣት ያላቸው አቅም የተገደበ ይመስላል፡ ፡ ከላይ እንደተጠቀሰው አፈፃጸሙ ገና በሂደት ላይ ያለ ነው፡፡ ስለዚህም የአዲሱን የሕግ መአቀፍ ተጽእኖዎች ገና

ከገፅ 7 የቀጠለ

...

ሙሉ በሙሉ አልተመለከትናቸውም፡ ፡ ይህንን ለመገምገም በቀጣይ ወራት ከመንግስት አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡ የአዋጁ አንዱ ግልጽ አሉታዊ ተጽእኖ በሰብአዊ መብቶች እና በአድቮኬሲ ስራዎች ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያውያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የገንዘብ አቅርቦት ላይ የታየው ነው፡፡ አየርላንድ ለተ.መ.ድ የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ለመመረጥ ባደረገችው የተሳካ ዘመቻ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ ለማሻሻል ለመንግስትና ለሲቪል ማህበረሰብ የአቅም ግንባታና የስልጠና ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡ በተጨማሪም የሁሉም ሰብአዊ መብቶች (ማለትም የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የባህል፣ የኤኮኖሚና ማህበራዊ) መከበር ለልማት ወሳኝ እንደሆነ አየርላንድ ታምናለች፡፡ ለኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትም ሆነ ለሕብረቶች ድጋፍ ማድረግ ተግዳሮቶች አሉበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ መያዶች ነገሮችን በድጋሚ እንዲያጤኑ ያስገደደበት ሁኔታ እንዳለ እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ አስተዳደራዊ ወጪዎችንና የሕብረቶችን ሚና መገምገም፣ ከቦርድ እና አጠቃላይ ጉባኤ አደረጃጀት አንፃር ግምገማና ማሻሻያዎችን ማድረግ፣ ወዘተ… ነገርግን እነዚህ አወንታዊ ውጤቶች በሌላ መንገድም ሊገኙ ይችሉ እንደነበር እናምናለን፡፡ ለነዚህ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች ምላሽ ለመስጠት አይ.ኤ.ኢ. ከሌሎች ለጋሽ አጋሮች ጋር በመሆን ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ሰንቆ ለተዘጋጀው የአምስት አመት የሲቪል ማህበረሰብ ድጋፍ መርሃግብር (ሲ.ኤስ.ኤስ.ፒ.) ዋነኛው የልማት አጋር ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለሁለተኛው ዙር የፒ.ቢ.ኤስ. ማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም መአቀፍ ውስጥ መሳተፉን ቀጥሏል፡፡ በምግብ ዋስትና፣ ስነምግብ፣ ጤና እና ላይቭሊሁድ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ጥቂት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንም እንደግፋለን፤

ለአዳፕቴሽን ፋሲሊቲ፣ ቲ.ኢ.ሲ.ኤስ. እና ሌሎች መርሃግብሮችም መጠነኛ ድጋፍ እናደርጋለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከመንግስት አካላት ጋር አወንታዊ መስተጋብር ማካሄድ እና በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ለጋሾችና አጋሮች ጋር በምክክር መድረኮች መሳተፍ ቀጥለናል፡፡ ስለዚህም ከሌሎች ጋር በመሆን የጋራ አላፊነትና ተጠያቂነትን ለማበረታታት የነበረን ቁርጠኝነት ቀጣይነቱ አያጠራጥርም፡፡

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

የሲቪል ማህበረሰብን...

ሙሐዝ፡ - ወደፊት ከልማት አጋሮች የሚጠበቀው የገንዘብ ድጋፍ አዝማሚያው ምን ይመስላል?

አይ.ኤ.ኢ.፡ - በኛ በኩል አይ.ኤ.ኢ. በአለም አቀፍ ደረጃ የሁዋይት ፔፐር ሪቪው እና አዲስ የአፍሪካ ስትራቴጂ ዝግጅት አጠናቋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አገራዊ ስትራቴጂያችን የትግበራ ዘመን በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለቀጣይ ከአምስት እስከ ሰባት አመታት የምንከተለውን አዲስ ስትራቴጂ ዝግጅት ለማጠናቀቅ አንድ ተጨማሪ አመት ይቀረናል፡፡ ምንም እንኳ በቅርቡ የኤኮኖሚ ችግሮች የተከሰቱ ቢሆንም አየርላንድ (በተለይ በነፍስ ወከፍ ስሌት) ለውጭ የልማት ትብብር ከፍተኛ ሃብት ትመድባለች፤ ኢትዮጵያም በልማት ትብብራችን ውስጥ አጋራችን ሆና ትቀጥላለች፡፡

ሙሐዝ፡ - በልማት አጋሮችና በመንግስት መካከል ያለውን የውይይትና ምክክር ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል? አይ.ኤ.ኢ፡ በአይ.ኤ.ኢ. እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው መስተጋብር ለውጥ እያሳየ መጥቷል፡ ፡ ግንኙነቱ ትሁት፣ ሙያዊ፣ አወንታዊና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ እና በማንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችንን አቋም ይዘን ››››››በገፅ 12 ይቀጥላል ...

| 11


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

የሲቪል ማህበረሰብን...

ከገፅ 5 የዞረ ...

የምንቀጥልበት ዓይነት ነው፡፡ ይህ ውይይት የተለያዩ መልኮች ሊኖሩት ይችላሉ፡ ኦፊሴላዊና ኦፊሴላዊ ያልሆነ፣ የሁለትዮሽ ወይም ብዙ ለጋሾችን የሚያሳትፍ፡፡ አይ.ኤ.ኢ. በዋነኞቹ የውይይት መድረኮች ተሳታፊ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ ወርኪንግ ግሩፕ (ሲ.ኤስ. ኤስ.ደብሊው.ጂ.)፣ የፒ.ቢ.ኤስ. ማህበራዊ ተጠያቂነት ሰቲሪንግ ኮሚቴ እና የሃይ ሌቭል ፎረም (ኤች.ኤል.ኤፍ.) ይገኙበታል፡ ፡ ይህን ከመንግስት ጋር ያለንን ግንኙነትና የመወያየት ባህል ከጥንካሬ ወደ ጥንካሬ እንደሚሄድ እርግጠኞች ነን፡፡ ተቀራርቦ መስራትና መሰረታዊ መርሆዎችን ማክበር ከመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ አጋሮቻችን ጋር ለሚኖረን የውይይት መድረክም ሆነ አጋርነት ቁልፍ ስትራቴጂዎቻችን ናቸው፡፡ እነዚህን ግንኙነቶች የሚመሩ የተለያዩ ፖሊሲዎች አሉን፡፡ መልካም እድል ሆኖ የምናደርገው የልማት ድጋፍ ከሌሎች ጉዳዮች ጋር የተሳሰረ አይደለም፤ ይሁን እንጂ በጀቶችን፣ አተገባበርን እና ውጤቶችን የምንገመግምበት አሰራር አለን፤ በደብሊን የሚገኙትም ባለስልጣኖች ከፍተኛ የተጠያቂነት ደረጃ ይጠብቃሉ፡፡

ሙሐዝ፡ በልማት አጋሮችና መንግስታዊ ባልሆኑ ድረጅቶች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት ትመለከቱታላችሁ? አይ.ኤ.ኢ.፡ - ከሲቪል ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ

| 12

እንደ ልማት አጋር በአጠቃላይ ገንዘብ የማሰባሰብ አቅምን ማሳደግ በተመለከተ ከመናገር ያለፈ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ ያልሰራን መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል ለመናገር የምንችለው ስለራሳችን ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳ ዋነኛው አጋራችን የኢትዮጵያ መንግስት ቢሆንም ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር ያለንም ግንኙነትና መስተጋብር በተመሣሣይ መርሆዎችና አሰራሮች ሊመራ እንደሚገባ እናምናለን፡ ፡ አይሪሽ ኤድ የሲቪል ማህበረሰብ ፖሊሲ እና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲ አቅጣጫዎች አሉት፡፡ በራችን ሁልጊዜም ለሲቪል ማህበረሰብ ክፍት ነው፡፡ በግልጽነት እና በዓላማ ላይ በተመሰረተ አጋርነት እናምናለን፤ በተቻለንም መጠን በእኩልነትና በአላፊነት የሚመራ አጋር ለመሆን እንጥራለን፡፡ ከሲቪል ማህበረሰብ ጋር ያለን ግንኙነት የማይለዋወጥና ፍትሃዊ መሆን እንዳለበትም እናምናለን፡፡ የሲቪል ማህበረሰብን ሚና መደገፍ እንጂ መተካት አንፈልግም፡፡ ከምናከናውናቸው መርሃግብሮች አንፃር በሲቪል ማህበረሰብ እና በአይ.ኤ.ኢ. መካከል ብቻ ሳይሆን በሲቪል ማህበረሰብ እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት - በተለይም በመንግስት መካከል ያለውን ግንኙነትና መስተጋብር በመልካምና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ማድረግ አቅምን በማሳደግ ልናግዝ እንደምንችልም እናምናለን፡፡ በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፉን አቅም ለመገንባት እና በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንዲችል ለማድረግ ይህ ሁኔታ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ሙሐዝ፡ - መንግስታዊ ያልሆኑ

ድርጅቶችን ከአገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ አቅም ለማጠናከር ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ? አይ.ኤ.ኢ.፡ - ከአገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ አቅምን መገንባት ከባድ ስራ ነው፡፡ ነገርግን ምንም እንኳ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚለያዩ ቢሆንም ሊሞከሩ የሚችሉ ምሳሌዎች እንደሚኖሩ እናምናለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን የተመለከተውን አዲስ መመሪያ አተገባበርና ተጽእኖ በመገምገም ላይ እንገኛለን፡፡ አንዳንድ ጥናቶች ከመመሪያው ድንጋጌዎች ውስጥ ለአተገባበር አስቸጋሪ የሆኑ እንደሚገኙባቸው ያሳያሉ፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን በአገር ውስጥ በማከናወን ላይ እንደሚገኙም እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ በአግባቡና ግልጽ በሆነ ሁኔታ ጥቅም ላይ እስከዋለና በቂ ክትትል እስከተደረገ ድረስ ከውጭ የሚገኝ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ወሳኝ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ የሲ.ኤስ.ኤስ.ፒ. አንዱ ዋነኛ አካል ይህንን ጉዳይ የሚመለከት ነው፡፡ እዚህ ላይ እንደ ልማት አጋር በአጠቃላይ ገንዘብ የማሰባሰብ አቅምን ማሳደግ በተመለከተ ከመናገር ያለፈ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ ያልሰራን መሆኑን መግለጽ ያስፈልጋል፡ ፡ ምንም እንኳ አንዳንድ ተሞክሮዎች ቢኖሩም የስኬት ደረጃቸው ይለያያል፡ ፡ ለጋሾች ከመንግስት እና ከዘርፉ ጋር በመሆን በዚህ የቀጣይነት ወሳኝ ክፍል ላይ አቅምን፣ አዳዲስ ሃሳቦችንና ውይይትን መደገፍ አለባቸው፡፡

እናመሰግናል፡፡ --------------------------------


በ11ኛው የሙሐዝ መፅሔት እትማችን በትይዩ ዓምድ በእንግዳነት ከጋበዝናቸው የአገር ውስጥና የውጪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎች ያነሷቸውን አብይ ነጥቦች ቀንጭበን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዛሬው የመድረክ ዓምዳችንም የቀሪዎቹን አምስት የትይዩ አምድ እንግዶቻችን ዋና ዋና ሃሳቦች እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

አዲሱ የ30/70 ደንብ እኛን የበለጠ ይጎዳናል፡፡ ገቢያችን በጣም ትንሽ ነው፡ ፡ ይህን በመቶኛ ብናሰላው ከበርካታ ገንዘብ ላይ የሚመጣ 30 በመቶ እና ከትንሽ ገንዘብ ላይ የሚመጣ 30 በመቶ ልዩነት አለው፡፡ ከብዙ ገንዘብ ከሆነ ብዙ ፕሮጀክቶችን በመያዝ አንድ ሠራተኛ ብዙ ሥራን እንዲሰራ ማድረግ ይቻላል፡፡ እኛ ካለችን አነስተኛ ገቢ ላይ 30 በመቶ ብቻ የሚኖረን ከሆነ የበለጠ በጣም ትንሽ ይሆናል፡፡ አስተዳደራዊ ወጪ ተብሎ የገባው የሥራ ዓይነት ደግሞ በጣም ብዙ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ - የአማካሪ ክፍያ፣ የፕሮጀክት ኦፊሰር ደመወዝና ሌሎች በርካታ ወጪዎች አስተዳደራዊ ወጪዎች ናቸው፡፡ በዚህ ላይ መጀመሪያውኑ እንደአስተዳደር ወጪ የሚቆጠሩ የቢሮ ኪራይ፣ የመብራት፣ የውሃ፣ የነዳጅና የመሳሰሉት ጥቃቅን ወጪዎች አስተዳደራዊ ናቸው፡፡ በተለይ ይህን መመሪያ በኢትዮጵያዊ ማኅበራት ላይ ሲያወጡ እንዴት አድርገው እንደተመለከቱት አላውቅም፡፡ የአዲሱ መመሪያ አተገባበር በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ እኛ እንዴት እንቀጥላለን ስለሚለው ነገር የምገምተው ምንም ነገር የለም፡፡ ወ/ሮ ሳባ ገ/መድኅን የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዳይሬክተር

አዋጁን ተከትለው የወጡት ደን ቦችና መመሪያዎች ያመጧቸው ስኬቶች፣ አንደኛ እነዚህ ደንቦችና መመሪያዎች አዋጁ ሲወጣ ጠቅለል ያለ ስለሆነ ዘርዘር ብለው ለአፈጻጸም እንዲመቹ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡ ሁለተኛ እነዚህ መመሪያዎች አዋጁን ተከትለው የወጡ ናቸውና የበጎ አድ ራጎት ድርጅቶችም ሆኑ ማህበራት ከአዋጁ አንጻር አፈፃፀማቸ ውን እና የተቋቋሙበትን ዓላማ ከመተግበር አኳያ እንዴት ነው ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት የሚለውን አቅጣጫ አስይዘዋል፡፡ በእ ነዚህ መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚቋቋሙት ለሦስተኛ ወገን ለመሥራት ነውና ህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚ ያደርጋሉ፤ ትክክለኛ የልማት አጋርም ይሆናሉ፡ ፡ ስኬቱ እንግዲህ ይህንን ለማስፈፀም መቻሉ ላይ ነው፡፡ ሆኖም አፈፃፀማቸው ገና በመሆኑ ያመጡትን ስኬት የመገምገም ደረጃ ላይ ገና አልደረስንም፡፡ አቶ አሰፋ ተስፋዬ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽን የሥራ ሂደት ባለቤት

በሥራ ላይ ያሉ መሠናክሎች ብዙ ናቸው፡፡ አንደኛውና ትልቁ መሰናክል የገንዘብ ሀብት እጥረት ነው፡፡ ለምሣሌ፡ - እኛ የአዳፕቴሽን ሥራ ላይ ብዙዎችን መድረስ እየፈለግን የአቅምና የገንዘብ እጥረት ስለነበረ መድረስ አልቻልንም፡ ፡ ሁለተኛው ችግር ከመንግሥት፣ ከለጋሾችና ከአጋሮች ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ያሉብንን ችግሮች በደንብ እየተነጋገርን መስመር ለማስያዝና ለመፍታት መድረኮች አለመኖራቸው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የራሳችን የሆነ የውስጥ ችግር ነው፡፡ ይኸውም ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ እየተለወጠ ካለው አካባቢያዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ለመቀጠል የጋራ ወደሆነው መገናኛ መድረክ ከመምጣት ይልቅ በራሱ የውስጥ ሥራና ተግባራት የመወጠር ችግር ነው፡ ፡ እነዚህ ጉዳዮች ከችግሮቻችን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሁን በተለይ ለኔ ትወርኮቹ የ30/70ው ጉዳይ ሌላ ችግር ሆኖ መጥቷል፡፡ በተለይ ፕሮግራም ያሏቸው ሥራዎች አስተዳደራዊ ወጪዎች መሆናቸው በተለያዩ መድረኮች ላይ ችግር እንደሆኑባቸው እየተገለፀ ነው፡፡ አቶ እሸቱ በቀለ ፖቨርቲ አክሽን ኔትወርክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር

በአዋጁና በ30/70 መመሪያ መሠረት የበጀት አጠቃቀምን በሚመለከት አስተዳ ደራዊ ተብለው ተቀመጡ ነገርግን በእኛ በአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ ሥራ ውስጥ አስተዳደራዊ ሊሆኑ የማችሉ በርካታ ውስብስብ ወጪዎች አሉ፡፡ ሕጉ እነኚህን ሥራዎች አስተዳደራዊ ነው ብሎ አስቀምጧል፤ በእኛ በኩል ደግሞ ፕሮግራም አካሎች ናቸው፡፡ ሌላው ችግር በአዋጁ አፈፃፀም ላይ የሽግግር ጊዜ እንዲኖር አለመደረጉ ነው፡ ፡ ለምሣሌ፡- ፌሬሬሽኑ በቀጥታ ያስፈፅማቸው የነበሩ ፕረጀክቶችን ለማ ህበራት ለማስተላለፍ አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሮብናል፡፡ እነዚህን ፕሮጀ ክቶች ለማጠናቀቅ የሽግግር ጊዜ ቢኖር ወደፊት የሚቀረጹ ፕሮጀክቶ ችን በአዲሱ አዋጅና መመሪያ መሠረት እያስተካከሉ ለመሄድ ያግዝ ነበር፡፡ ነገርግን ህ ሁኔታ ባለመመቻቸቱ የጀመርናቸው ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ ቀርተዋል፡፡ አቶ ተሾመ ደሬሳ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበራት ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ

ኤጀንሲው ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር ሊኖረው የሚገባው ግንኙነት እጅ እና ጓንት መሆን ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኛ በኤጀንሲው የሚወጣውን መመሪያ የማክበር ግዴታ እንዳለብን ሁሉ ኤጀንሲውም ደግሞ ሁሉንም በአንድ ዓይነት ከመፈረጅ ይልቅ መልካም የሚሰራውን በማበረታታት፤ የሚያጠፋውን በማረም አቻችሎ መሥራት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በመመሪው አተረጓጎም ላይ ልዩነት ሳይኖር እንደ ድርጅቶቹ ሥራዎች ዓይነትና ባህሪይ እየታየ መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች ኤጀንሲው በአግባቡ ሊያስተናግድ ይገባል፡፡ ወ/ሮ ሮማን ደገፉ ፋዌ ኢትዮጵያ

| 13

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

መድረክ


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ተመክሮ

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ የ15 ዓመት የተቆርቋሪነት ጉዞ አቶ ኤፍሬም አላምረው የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የማህበሩ አመሰራረት የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ማህበር የተመሠረተው እ.ኤ.አ. በ1997 ነው፡ ፡ ለመመስረቱም ምክንያት የሆኑት በወቅቱ በአካባቢ ስራ ላይ ይቆረቆሩ የነበሩ የተወሰኑ ግለሰቦች ሲሆኑ እነኛ በጎ ፈቃደኞች አንድ ላይ ተደራጅተው በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ለውጥ እናምጣ በሚል የውስጥ ተነሳሽነት ለማህበሩ መመስረት ፈር ቀዳጅ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ ማህበሩ የተመሰረተው ምንም እንኳን በአገሪቱ ውስጥ በጊዜው የነበረው የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታ በጣም ጎልቶ የወጣ ጉዳይ ባልነበረበት ወቅት ቢሆንም በአካባቢ ጥበቃና በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዙሪያ የህብረተሰቡን በተለይም ደግሞ በተለያየ ደረጃ ያሉትን የውሣኔ ሰጪ አካላት ግንዛቤ ለማሳደግ እና ያለውን መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡

የማህበሩ አላማዎች ማህበሩ ሲመሠረት አላማ ያደረጋቸው ሶስት ጉዳዮች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው አላማ በአካባቢ ጥበቃና በተፈጥሮ ሐብት እንክብካቤ ዙሪያ የህብረተሠቡን ግንዛቤ መጠን ማሳደግ ነው፡፡ ሁለተኛው አላማ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የመንግሥት አካላት በችግሩ ዙሪያ ሊኖራቸው የሚገባውን ግንዛቤ ማሳደግ እና በአካባቢ እንክብካቤ ዙሪያ የተለያየ ተሳትፎ የሚያደርጉትን የህብረተሠብ አካላት ለማበረታታት እና የተጀመሩትን በጎ ጅምሮች ማጠናከር ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ በአገሪቱ በተለያየ ቦታ ላይ የራሳቸውን የአካባቢ ችግር ራሳቸው መናገር የሚችሉ ግሩፖችን ማቋቋም ነው፡፡

| 14

ማህበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራት የማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ኤፍሬም አላምረው እንደገለጹት በመጀመሪያ አካባቢ ማህበሩ ይዞት የተነሳው ጉዳይ በአገራችን ውስጥ እምብዛም የተለመደ ነገር ስላልነበረ ከሁሉም አስቀድሞ ግንዛቤ የመፍጠሩ ጉዳይ በማህበሩ ዋነኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነበር፡፡ ይህንንም ለማድረግ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮች አካሂዶ በጥናት ላይ የተመሰረተ የአድቮኬሲ ሥራ ለመሥራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ ከዚህ ረገድ ማህበሩ ለሀገራችን አስፈላጊ ናቸው በሚባሉ በአካባቢ ጥበቃና በአየር ንብረት ዙሪያ ላይ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮች በስፋት እንዲካሄዱ ጥረት ከማድረጉም በላይ የጥናቱን ውጤት አሳትሞ ለሚመለከተው አካል እና ለጠቅላላው ህብረተሠብ የማዳረስ ሰፊ ተግባር አከናውኗል፤ አሁንም በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከምስረታው ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የተለያዩ ስብሰባዎችንና የመወያያ መድረኮችን በማዘጋጀትና አሉ የተባሉትን የአካባቢ ችግሮች በጋራ መድረክ በመነጋገር መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉትን አማራጮች የማቅረብ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ችግር የተያያዘው ከተፈጥሮ ሀብት ጋር ነው፡፡ በአገራችን አንደኛውና ዋነኛው የተፈጥሮ ሀብት የደን ሀብት በመሆኑ ማህበሩ በግንባር ቀደምነት የደን ጥበቃን (ፎሬስትሪ) ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ ለረጅም ጊዜ እየሠራበት ይገኛል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የማህበሩ የትኩረት አቅጣጫ የሆነው የውሃ ሃብት ሲሆን በዚህም ዙሪያ ከፍተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደርሰው ጫና በአብዛኛው ከኃይልምንጭ


የተገኙ ስኬቶች እንደዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የማህበሩ ስኬቶቹ የአንድ ድርጅት ስኬት ብቻ ናቸው ተብለው ሊወሰዱ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ቀደም ሲል የተዘረዘሩት የማህበሩ አላማዎች በሙሉ አንድ ድርጅት ብቻውን የሚሠራቸው ስራዎች ሳይሆኑ በቅንጅት እና በመተባበር የሚከናወኑ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህ ማህበር ከተመሰረተ ጀምሮ ባከናወናቸው ተግባራት ስኬታማ የሆነባቸው በርካታ ሥራዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ አኳያ ማህበሩ በአገራችን ግንባር ቀደም ድርጅት ከመሆኑ አንፃር እ.ኤ.አ. ከ2005 ጀምሮ በአድቮኬሲና ኮሚኒኬሽን ላይ ስኬታማ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ከዚህም የተነሳ የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ አገራችን ውስጥ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን እንዲያገኝና የህብረተሰቡ መነጋገሪያ እንዲሆን ለማድረግ አስችሏል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ማህበሩ ከተቋቋመበት አላማ አኳያ ሲታይ ትልቅ ስኬት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ማህበሩ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመሆን የሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የህትመት ውጤቶች አሉ፡ ፡ እነዚህ የህትመት ውጤቶች በሙሉ በምርምር ላይ የተመሰረቱ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ብዙዎቹ ህትመቶች ዋና ዋና የአካባቢ ችግሮች የሚባሉትን ነገሮች ማዕከል ያደረጉ ናቸው፡፡ የህትመት ውጤቶቹ መውጣታቸው ብቻ ሳይሆን ደግሞ ስርጭታቸውም ሰፊ ሽፋን ነበረው፡ ፡ ለምሳሌ፡- ማህበሩ “አክርማ” የሚለውን መጽሔት ለረጅም ዓመታት በማዘጋጀትና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ማለትም በ23ቱም ዩኒቨርሲቲዎች እና በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በማሰራጨት በአካባቢ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር አከናውኗል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ማህበሩ የአካባቢን ጉዳይ የሚያወሩ ቡድኖች በ6 ክልሎች ውስጥ 12 ቦታዎች ላይ አቋቁሟል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በማህበሩ ድጋፍ ቢቋቋሙም የተወሰኑት አሁን ራሳቸውን ችለው የራሳቸውን የአካባቢ ችግር በራሳቸው ለመፍታት ጥረት ማድረግ ላይ ደርሰዋል፡ ፡ ከዚህም በተጨማሪ አስራ ሁለቱም ቡድኖች በየክልላቸው ህጋዊ ሰውነት አግኝተው በአሁኑ ጊዜ በፌደራል ደረጃ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ::

ማህበሩ አማራጭ የኃይል ምንጮች ላይ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል እ.ኤ.አ. በ2006 በአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ሽልማት ፕሮግራም፥ ሌላኛው የማህበሩ ስኬት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ለአካባቢ ጥበቃ እውቅና ሰጥቶ ሽልማት የማከናወን መርሀ-ግብር የጀመረው የመጀመሪያ ድርጅት የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ ሲሆን በዚህ እንቅስቃሴም በርካታ አመርቂ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ የአካባቢ ተቆረቋሪዎች መድረክ ህዝቡ ስለአካባቢው ያለው ግንዛቤ እንዲጨምር ከማድረጉና “እኔ የአካባቢዬን ሁኔታ ለመለወጥ እፈልጋለሁ” ብለው የሚንቀሳቀሱ ብዙ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ለማነሳሳት ከመቻሉም ሌላ በዘርፉ መንግሥትን የማትጋት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡ ፡ በተጨማሪ መንግሥት ያወጣቸው ፖሊሲዎች መተግበራቸውን ከራሱ አስፈፃሚ አካላት ብቻ ሳይሆን ከሌላውም ዜጋ ከሚቀርብለት ጭምር እንዲሆን ለማድረግ ህብረተሰቡን የሚያሳትፍበትንና የተለያዩ ሃሳቦችን የሚቀበልበትን መድረክ የሚያመቻች ስኬታማ ተግባር አከናውኗል፤ በማከናወንም ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአካባቢ ተቆረቋሪዎች መድረክ በአገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ካውንስል ውስጥ የሲቪል ማህበረሠቡን ወክሎ ይሳተፋል፡፡ ካውንስሉ ውስጥ ያሉት አባላት በሙሉ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ የአካባቢ ተቆረቋሪዎች መድረክ ሲቪል ማህበረሰቡን በመወከል ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ የማህበሩ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ማህበሩ ያጋጠሙት ዋና ዋና ተግዳሮቶች

አንድ ነገር ሲሰራ አነሰም በዛም የተለያዩ ችግሮች ወይም ተግዳሮቶች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ የመድረኩ ኃላፊዎች እንደሚገልጹት ካለፉት አምስት አመታት ወዲህ እየተሻሻለ መጣ እንጂ ቀደም ባሉት ጊዜያት የማህበሩ ስራ የቅንጦትና ትርፍ ስራ ተደርጎ ይታሰብ ነበር፡፡ ተቋሙ ራሱ ተቀባይነት ያለውና በመንግሥትም ሆነ በሌሎች አካላት ዘንድ አስፈላጊ መሆኑ ያልታመነበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የአካባቢ ጥበቃን ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ አድርጎ ስራውን ለመስራት ለማህበሩ ትልቅ ተግዳሮት ነበር፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ምንም እንኳን አካባቢና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን በተመለከተ አገሪቱ ውስጥ ከአዋጁ ጀምሮ ጥሩ ጥሩ ፖሊሲዎች የወጡ ቢሆንም ለማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ትልቅ ተግዳሮት የነበረው በተለይ እየወረደ በሚሄድበት ጊዜ የፖሊሲ፣ የአዋጅና የደንቦች አፈጻጸም ጉዳይ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው የአብዛኛው ህብረተሰብ የዕለት ተእለት ኑሮ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የተደገፈ ነው፡፡ ስለዚህ የተፈጥሮ ሀብት ላይ ኑሮውን መሠረት ያደረገ ህብረተሰብን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ ሲሰራና በተፈጥሮ ሀብት ላይ ያለውን ጥገኝነት እንዲያቆም ሲጠየቅ በምትኩ ሌላ አማራጭ እንዲከተል ማቅረብ ግድ ይላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት በሚያካሂደው የኢንቨስትመንት ሥራ ምክንያት ደኖች ሊጨፈጨፉ ይችላሉ፡፡ እናም እነኚህን ነገሮች አጣጥሞና ፖሊሲ አውጪዎችን አሳምኖ ሁለቱን አቻችሎ መሄድ ያስፈልጋል የሚለውን ጉዳይ ማስረዳቱ በማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ነበር፡፡ በማህበሩ የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ሌላው ተግዳሮት የነበረው ከተለያዩ የመንግሥት አካላትና መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር ቅንጅት የመፍጠሩ ጉዳይ ነበር፡፡ እንዲሁም ደግሞ ቀደም ሲል የማህበሩ ዓላማ በራሱ በስፋት ተቀባይነት ስላልነበረው በየጊዜው የሚዘጋጁት ፕሮጀክቶች በለጋሾች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ትልቅ ተግዳሮት ነበረበት፡፡ ከዚህም የተነሳ ለስራው አስፈላጊ የሆነ የገንዘብ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የማሟላት ችግር ቀላል አልነበረም፡፡ በመሆኑም በጥቂት ሰው እና በጥቂት ግብአት ብዙ ስራ ለመስራት ግድ ይል ነበር፡፡ የማህበሩ ፕሮግራም ማናጀር የሆኑት አቶ ዮናስ ገብሩ እንደገለጹት ከሀገሪቷ ስፋት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችም አሉ፡፡ አገሪቷ ሰፊ በመሆኗ እና በተለይም ደግሞ ብዙ አግሮ ኢኮሎጂካል ዞኖች ያሉባት በመሆኗ ለሁሉም አካባቢ የሚስማማ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ማስጨበጥም ሆነ

በ ገፅ 17

ይቀጥላል

| 15

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ፍላጎት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ስለሆነም ማህበሩ አማራጭ የኃይል ምንጮች ላይ የተወሠኑ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2007 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የአየር ንብረት ለውጥ ሌላው የትኩረት አቅጣጫ በመሆን እየተሠራበት ነው፡፡


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ከአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ አስደናቂ መረጃዎች የሚከተለውን ከአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነት ጋር የተያየዙ መረጃዎችን ለማመን ያዳግታል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን በማንበብ ይወቁ፡፡ የአልኮል ሱሰኝነት የአካል ጉድለት ያለባቸው ሕፃናት ለመወለዳቸው ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ • ከመደበኛው እስከ 6.5 እጥፍ የሚሆኑ ወጣቶች በአልኮል ሱስ ምክንያት ይሞታሉ፡፡ • ቁጥር የሚታየው በምግብ ዝግጅትና ኮንስትራክሽን ሰራተኞች መካከል ከሚከሰቱት ችግሮች መካከል በከፍተኛ • • • • • • • • •

አደንዛዥ እጽ መጠቀም ነው፡፡ የማቋረጥ አደንዛዥ እፅ ከሚጠቀም ቤተሰብ የሚገኙ ሕፃናት በአስምና፣ በጆሮ ኢንፌክሽን የመያዝና ትምህርት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ 12.5 ዓመት በአጠቃላይ አደንዛዥ እፅ መጠቀም የሚጀምረው በታዳጊነት እድሜ ሲሆን አማካይ እድሜውም እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 41 በመቶው ስምንተኛ ክፍልን ካጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል 52 በመቶ የሚሆኑት አልኮል ቀምሰው ያውቃሉ፣ ያውቃሉ፡፡ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሲጋራ አጭሰው ያውቃሉ፣ 20 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አደንዛዥ እፅ ሞክረው ደግሞ ከአንድ በመቶው 17 ያውቃሉ፣ ጓደኛ ተጠቃሚ እጽ 28 በመቶ የሚሆኑት ታዳጊዎች ቢያንስ አንድ አደንዛዥ በላይ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ ጓደኛ ያውቃሉ፡፡ ከመጠቀም ጋር በአሜሪካን አገር ከሚከሰተው የሞት መጠን 25 በመቶ የሚሆኑት ከእፅና መድሃኒቶችን ያለአግባብ የሚያያዙ ናቸው፡፡ በአሜሪካን አገር ከሚታየው የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነት ችግር ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ከሄሮይን እና ኮኬይን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአልኮል ተጠቃሚነት የሂስፓኒክ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ መጠን ሲኖረው ነጮች እና ጥቁር አሜሪካውያን ይከተላሉ፡፡ የአንድ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚ የህክምና ወጪ በአማካይ ከአንድ ጤነኛ ሰው ወደ ሁለት እጥፍ ይሆናል፡፡

የሚሊኒየሙ... ከገፅ 10 የቀጠለ

...

ምክንያቶቹ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃን ታሳቢ ያላደረጉ የሰፈራ እና የኢንቬስትመንት እንቅስቃሴዎች፣ የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲና እቅድ ያለመኖሩ እና በየጊዜው እየጨመረ የመጣው የበካይና መርዛማ ንጥረነገሮች ተጠቃሚነት እንደሆኑ ኤጀንሲው ገልፆአል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ. በ2009/10 ከአገሪቱ ሕዝብ 65 በመቶ የሚሆነውን የመኖሪያ ቤት እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ ተንቀሳቅሷል፡ ፡ እስከ 2009/10 ድረስ በቤቶች ልማት መርሃግብር 213,000 አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ተሰርተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቤቶችና አካባቢዎችን በ35 በመቶ ለመቀነስ ታቅዶ እስከ 2009/10 ድረስ በ40 በመቶ መቀነስ ተችሏል፡፡

| 16

------------------

የማጣቀሻ ምንጮች 1.

Civil Society Contributions towards Achieving the MDGs in The Gambia, October 2005

3.

Jacqui Boulle and Debbie Newton, MDG Campaigning Toolkit, CIVICUS: World Alliance for Citizen Participation and Millennium Development Goals Campaign office (not dated)

2.

4. 5. 6. 7. 8. 9.

2. Jacqui Boulle and Debbie Newton, MDG Campaigning Toolkit, CIVICUS: World Alliance for Citizen Participation and Millennium Development Goals Campaign office

Ministry of Finance and Economic Development (MoFED), Ethiopia: The Millennium Development Goals (MDGs) Needs Assessment Synthesis Report, Development Planning and Research Department, Addis Ababa, December 2005 MoFED, Ethiopia: 2010 Millennium Development Goals Report: Trends and Prospects for Meeting MDGs by 2015, September 2010

Neville Gabriel, The Millennium Development Goals: Towards a Civil Society Perspective on Reframing Poverty Reduction Strategies in Southern Africa, Presented at the Southern Africa MDGs Forum, Johannesburg, 2 – 4, July 2003

Roadmap towards the implementation of the United Nations Millennium Declaration: Report of the Secretary General to the General Assembly (A/56/326, September 2001) Roberto Bissio, Civil Society and the MDGs, Development Policy Journal, Volume 3, UNDP, April 2003

Satishkumar Belliethathan (Ph.D), Yitbarek Tibebe and Girum Woldegiorgis, The Impact of Climate Change on Millennium Development Goals (MDGs) and Plan for Accelerated and Sustained Development to End Poverty (PASDEP) implementation in Ethiopia, Poverty Action Network of civil society organizations in Ethiopia (PANE) and DanChurch Aid, Addis Ababa Ethiopia, December 2009


፡ በተመሳሳይ መልኩ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክም የሚያነሳቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ ይህን በተመለከተ አቶ ኤፍሬም የሚከተለውን ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ዮናስ ገብሩ የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች መድረክ ፕሮግራም ማናጀር ለፖሊሲ አፈጻጸም የማትጋት ስራዎችን ለማካሄድ ያስቸግር ነበር፡፡ በተጨማሪም በማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ውስጥ ፖሊሲው መልስ የማይሰጣቸው አንዳንድ አነስተኛ ክፍተቶች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ፡- የመጀመሪያው የአካባቢ ጥበቃ ስትራቴጂ ወይም የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ስትራቴጂ ሲወጣ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነበር፡፡ በሌላ መልኩ የአገሪቷ ስፋትና የስነምህዳሩ ስብጥር በጣም የተለያየ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉንም አይነት የአካባቢ ተሟጋችነት ስራ ወይም የማትጋት ስራ ለመስራት በባለሞያ የተደገፉ ጥናቶች ማካሄድ የግድ ይላል፡ ፡ በመሆኑም እነኝህን ጥናቶች እንዲያካሂዱ የሚፈለጉ ባለሞያዎች የዚያኑ ያህል ይበዛሉ፡ ፡ ባለሙያዎቹን ለመቅጠር ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ገንዘቡ የሚገኘው በአብዛኛው ከለጋሾች በመሆኑም ራሱን የቻለ ችግር ነበረው፡፡ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ማህበሩ ከለጋሾችም ጋር ለመተዋወቅና ጥሩ መስተጋብር እንዲኖር ለማድረግ በተለያዩ አለም አቀፋዊ እና ክልላዊ ቅንጅት ውስጥ ሊኖረው የሚገባው ተሳትፎ ሊገደብ ችሏል፡፡ የማህበሩ ሰራተኞች በብዙ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ነበረባቸው፡፡ አንዱ በአንዱ በኩል ሲሳተፍ ሌላው በሌላው በኩል መሳተፍ እና የአገራችንን የአካባቢ ችግር ማስረዳት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጡ ያስከተላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ማስረዳት ነበረበት፡፡ ነገር ግን በገንዘብ አቅም ውሱንነት የተነሳ ማህበሩ ይህን ማድረግ አልቻለም፡፡ ይህ ሁኔታ የማህበሩ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ ነው የቆየው፡፡

ከ30/70 መመሪያ ጋር በተገናኘ ማህበሩ የገጠመው ችግር በርካታ ድርጅቶች ከ30/70 መመሪያ ጋር በተያያዘ የሚያነሷቸው የተለያዩ ቅሬታዎች አሉ፡

“የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የሚመሩበትን የህግ ማዕቀፍ መንግሥት ሲያወጣ ብዙ ነገሮች በግልጽ የሚታዩና ችግር የሌላቸው ናቸው፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ገደብ የማይደረግባቸው ናቸው በማለት ከተናገሯቸው ሴክተሮች መካከል የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖዎችን ለመቋቋም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ግንባር ቀደሙን ስፍራ የሚይዙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚያመጣው ጉዳት በኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ዘርፍ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡ ፡ ተጽእኖው የውሃ ሀባታችንን፣ የእርሻ እንቅስቃሴያችንን፣ ሌላው ቀርቶ የማዕድን ኢንዱስትሪ ተግባራችንን ጭምር በተለያየ መልኩ ይጎዳል፡፡ ስለዚህ በአዋጁ ዙሪያ በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች የተስማማንበትና ገደብ የማይደረግበት ጉዳይ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የ30/70 መመሪያ በሚወጣበት ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለእንቅስቃሴያችን አግባብነት ያላቸው ነገሮች በአስተዳደራዊና በፕሮግራም ወጪ ሲከፋፈሉ ወይም የአላማ ማስፈጸሚያና የአስተዳደራዊ ወጪ ተብለው ሲቀመጡ መዛባቶች ተፈጥረዋል፡፡ “በእርግጥ አስተዳደራዊ ወጪዎች ለልማት የተባለውን ወጪ መብላት የለባቸውም፤ ይሄ የታወቀ ነው፡፡ ከዛሬ 20 ዓመት በፊት የ30/70 መመሪያ እንደ ጽንስ ሃሳብ ከመምጣቱ አስቀድሞ ይህ አስተሳሰብ ነበረ፡፡ ያን ጊዜ ግን አስተዳደራዊና የፕሮግራም ወጪ የምንላቸውን በምንከፋፍልበት ጊዜ ግልጽ የሆነና የሚታይ ሁኔታ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ሰው ችግኝ አፍልቶ ዛፍ ተክሎ ደን ለማልማት ቢፈልግ ለችግኙ የጫካ አፈር ያቀርባል፤ አሸዋ ካለበት ፈልጎ ያመጣል፤ ብዙ መቶ ኪሎ ሜትር ሊሄድ ይችላል፤ ለችግኙ የሚሆን ሰንበሌጥ ከሩቅ ቦታ ፈልጎ ለማምጣት ይገደዳል፡ ፡ መኪናዎች ይጠቀማል፤ ለመኪናዎቹ ነዳጅ ያስፈልገዋል፤

ከገፅ 15 የቀጠለ

...

አፈሩን ለማስጫን የሰው ኃይል ይጠይቃል፡ ፡ እንደገና ደግሞ ገበሬዎችንና በገጠር ውስጥ የሚሰማሩ የልማት ሰራተኞችን በመቅጠር ማሰልጠን ይኖርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ነገር የፕሮግራም ወይም የአላማ ማስፈጸሚያ ወጪ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ አንድ አካባቢ የሚተከሉ ዛፎች አግባብነት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ነገር ለመመርመር የሙከራ ስራ የሚሠሩ ባለሙያች ተቀጥረው በየስፍራው ሙከራ ያካሂዳሉ፤ ለነሱ የሚከፈለው ደመወዝም የፕሮግራም ወጪ ነው፡፡ ነገርግን አሁን ያለውን ሁኔታ በምናይበት ጊዜ ግን ይህ ሁሉ ነገር አስተዳደራዊ ወጪ ሆኗል፡፡ ለባለሙያው መጓጓዣ የምትጠቀምበት መኪና የተከራየኸውም ቢሆን የራስህ የነዳጅ እና የኪራይ ወጪው አስተዳደራዊ ወጪ ነው፤ ችግኝ ለማጓጓዝ የሚደረገው ክፍያም አስተዳደራዊ ወጪ ሆኗል፡፡ በመሆኑም እነኚህ ዓይነት ነገሮች የስራ ማነቆዎች ናቸው፡፡ “በተመሳሳይ መልኩ ከአካባቢ የአየር ንብረት መለወጥ ጋራ በተያያዘ የአየር ንብረት ለውጡን ለመላመድ ገበሬዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ በምናደርግበት ጊዜ የጥናት ደረጃ አለው፤ እንደገና ከጥናቱ በኋላ የሰርቶ ማሳያ ደረጃ አለው፤ ከሠርቶ ማሳያ ቀጥሎ ደግሞ ሰዎቹን የማብቃት ስራ አለ፤ አይተውት አምነውበት እንሰራዋለን ሲሉ ደግሞ ማሰልጠን ያስፈልጋል፡ ፡ እንዲህ አይነት ነገር ሲደረግ በአካባቢ ያሉ የመንግስት ተቋሞችም ቢሆኑ እያንዳንዱን ነገር ላያውቁት ስለሚችሉ የነሱን አቅም መገንባት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ በተጨማሪም በየገጠሩ ያሉ ሠራተኞቻችንን እና የሥራ ኃላፊዎች ለማሰልጠን እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስለፕሮግራሙ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ወርክሾፕ በማዘጋጀት ሀሳብ የምንለዋወጥበት ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ቢሆንም ይህንን ማድረግ አንችልም፡፡ ምክንያቱም እነኛ ወጪዎች በአዲሱ መመሪያ መሠረት አስተዳደራዊ ወጪዎች ናቸው፡፡ አንድ ድርጅት የሚሠራቸውን ስራዎች ካላስተዋወቀ፣ በቅርበት እየተከታተለ በመስክ ደረጃ ያለውን እንቅስቃሴ መረጃ ሰብስቦ ካላሰራጨ፣ እንደገና ደግሞ ምርምር ፣ ግምገማና ምዘና ካላካሄደ፣ ስልጠና ካልሰጠ፣ አቅም ካልገነባ ውጤታማ የሆኑ የልማት ስራዎችን ይሠራል ብሎ ለማመን ያስቸግራል፡፡ የ30/70 መመሪያ አግባብነቱ እንዳለ ሆኖ የትኛዎቹ የወጪ አርዕስቶች ላይ ነው አግባብነት ያለው? የትኛው ጋር ነው አግባብነት የሚጎለው? ብለን ማሰብ አለብን፡፡ በተለይ ደግሞ ለዚህ ሰለባ የሚሆኑት በአብዛኛው የአካባቢ ጥበቃና

በ ገፅ 19

ይቀጥላል

| 17

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች...


30/70 መመሪያን...

...

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ከገፅ 3 የቀጠለ

3. በመመሪያው ላይ ከተዘረዘሩት ስብስቦች በአንዱ ብቻ የማይወሰኑ ወይም ከአንድ በላይ ስብስብ ስር የሚወድቁ ተግባራትን የሚያከናውኑ መያዶች መኖራቸው፤

ግንባታ እና በእውቀት ሽግግር ላይ ትኩረት መቀነስ፤

4. ትንንሽ እና ጀማሪ መያዶች አስተዳደራዊ ወጭዎቻቸውን ለመሸፈን የሚያስችሉ ብዙ መርሃግብሮች የማይኖራቸው በመሆኑ የሚፈጠርባቸው ጫና፤

11. ኦዲተሮች የገንዘብ እና የደንብ አከባበር ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ ስልጣን የተሰጣቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ የኦዲት ወጪ፤

5. አስተዳደራዊ ወጭዎችን ለመቀነስ ሲባል ዝቅተኛ ብቃትና ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች የመቅጠር አዝማሚያ ሊፈጠር የሚችል መሆኑ፤ 6. የኢትዮጵያውያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በቂ ገቢ ለማሰባሰብ ሲሉ ብቻ ወደ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለመቀየር የሚገደዱ መሆኑ፤ 7. የድርጅቶቹን ዋና ጽ/ቤቶች እና የኢትዮጵያ ጽ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት ከ70/30 መመሪያ አንፃር ማጣጣም፤ 8. አስተዳደራዊ ወጭዎችን ለመቀነስ ሲባል ራቅ ባሉ ወይም በቂ አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች የሚከናወኑ መርሃግብሮች የሚቀንሱበት ሁኔታ መኖሩ፤ 9.

በጥናትና

| 18

ምርምር፣

በአቅም

10. ሕብረቶች አስተዳደራዊ ወጪ ብቻ የሚኖራቸው በመሆኑ ለሌሎች ተግባራቶቻቸው እውቅና አለመሰጠቱ፤

12. የኦዲት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በኤጀንሲው የሚሰየሙ መሆኑ ውድድርን ከመቀነስ በተጨማሪ በተወሰኑ ድርጅቶች ላይ ከሚፈጠረው የሥራ ጫና አኳያ የስራ ክንውን እና የኦዲት ሪፖርቶች መዘግየት፡፡ ሁለተኛውና በውይይቱ ላይ የቀረበው ሌላው

“የዓለም አቀፍ መያዶች እንቅስቃሴና የ70/30 መመሪያ እንደምታዎች፡ - መመሪያውን በማስፈጸም ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ መልካም እድሎችና ተግዳሮቶች” የሚል ሲሆን መመሪያው

ስብስቦች ዝርዝር አንደገና መከለስ - በተለይም የአለም አቀፍ መያዶች ተግባራትን ዘርፈ ብዙ እና ሁሉን አቀፍ ባህሪ ታሳቢ በማድረግ፤ 2.

የ30 በመቶ የአስተዳደራዊ ወጭዎችን ዝርዝር ከአለም አቀፍ አሰራር እና ከመርሃግብር ኡደት መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንደገና መለከስ፡ ፡ በተለይም የሚከተሉት የዓለማ ማስፈጸሚያ ወጭዎች ተደርገው የሚታዩበት ሁኔታ ቢታሰብ፡ -

የመርሃግብር አስተባባሪ/ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር፣

ክትትልና ግምገማ፣

ለመርሃግብር አቀራረጽ አማካሪዎች፣

የመርሃግብር ተሸከርካሪዎች፤

3.

ከስታትስቲክስና ከቁጥር ባሻገር እርስ በርስ መተማመንና የአጋርነትን መንፈስ ማዳበር፡፡ የመርሃግብሩን ወይም የድርጅቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባ አተረጓጎምና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ አረዳድ ለወደፊት ትብብር ተመራች አካሄድ ይሆናል፡፡

ጥናት

ምንም እንኳን አስፈላጊ መሆኑ ባይካድም ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር አስቸጋሪነት እንዳለው በዝርዝር ለማሳየት ሞክሯል፡ ፡ በተጨማሪም ለወደፊቱ ምን ማድረግ ይገባል በሚል ሃሳብ ዙሪያ የሚከተሉትን ሀሳቦች በአማራጭነት አስቀምጧል፤ 1.

በመመሪያው

ላይ

የተቀመጡትን

ማስፈጸሚያ

በመጨረሻም መመሪያው በበጎአድራጎት ድርጅቶች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ እና አንድምታ በድጋሚ ያጤነው ዘንድ ለበጎአድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲው አማራጭ ሀሳቦችን በመሰንዘር ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡


በመስራት የራሳቸውን ገቢ ከችግር ለመላቀቅ ችለዋል፡፡

ለማዳበርና

የቦሌ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ሴቶችን በልማት ተጠቃሚና ተሳታፊ ማድረግ የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አጀሉሽ ተፈራ ለተመራቂዎች በዕለቱ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “መንግሥት የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት እያደረገ ባለው ከፍተኛ የጥረት እንቅስቃሴ ውስጥ ዶርቃስ ኤይድ ኢንተርናሽናል እያከናወነ ያለው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም” በማለት ድርጅቱ እያከናወነ ያለውን ተግባር አመስግነዋል፡፡ በተጨማሪም “አሁን ባገኛችሁት ሙያዊ ስልጠና በመታገዝ የራሳችሁን ገቢ ከመፍጠርም በዘለለ ቤተሠቦቻችሁን ብሎም አገራችሁን የምትጠቅሙና ሰፊ ራዕይ ያላችሁ ዜጎች እንድትሆኑ አደራ እላለሁ” በማለት ለተመራቂዎች አደራ አስተላልፈዋል፡፡

ከገፅ 3 የቀጠለ

...

“ይህ ድርጅት ከወደቅንበትና ከተረሳንበት ስፍራ ተነስተን ይህን የመሠለ ስልጠና እንድናገኝና የራሳችን ገቢ እንዲኖረን መንገድ የከፈተልን ከመሆኑም በላይ የወደፊት ሰፊ ራዕይና ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን አድርጎናል፡፡” በማለት የገለፁት የሠልጣኞቹ ተወካይ ወ/ሮ ሂሩት አክለው እንዳብራሩት ዶርቃስ ኤይድ ኢንተርናሽናል ለሰልጣኞቹ የሙያ ስልጠና ብቻ ሳይሆን በስልጠና በቆዩበት አንድ አመት ውስጥ የትራንስፖርት አበል ይሰጣቸው እንደነበር ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የድርጅቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፍቅሩ በበኩላቸው ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ከሰልጣኞቹ መካከል አንዷ አካል ጉዳተኛ እንደሆነች ጠቁመው በቀጣይነት ድርጅቱ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ጋር በጥምረት ለመስራት ማቀዱን ገልፀው አክለውም በዘንድሮው ዓመት ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ 25 ችግረኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ድርጅቱ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡ “የዚህን ዓመት ስልጠና ወር ውስጥ በቂ ክህሎት ሰልጣኞች ከተመረቁ በኋላ የመንግሥት አካላት ጋር

በሳምንት ለ5 ተከታታይ ቀናት በማድረግ በስድስት በማስጨበጥ ለማስመረቅ ታቅዷል” ያሉት አቶ ፍቃዱ የገበያ ችግር እንዳይኖርባቸው ድርጅቱ ከሚመለከታቸው በቀጣይነት እንደሚሠራ አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም የዕለቱ ሰልጣኞች ሰርተፍኬትና ልዩ ልዩ ሽልማት ከክብር እንግዳዋ ከተቀበሉ በኋላ ያመረቷቸውን የስፌት ውጤቶች ለተሳታፊዎች በማሳየትና በመሸጥ የዕለቱን ዝግጅት አጠናቀዋል፡፡

ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

ዶርቃስ ኤይድ..

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች... ከገፅ 17 የዞረ

...

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የሚደረጉ ትግሎች ናቸው፡፡ “ውጤታማ የሆነ የአካባቢ ተሟጋችነት ስራ የሚሠራው በተለያዩ አለምዓቀፍ መድረኮች ላይ መገናኘት እና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ፊልሞችን መቅረጽና ማዘጋጀት ሲቻል ነው፡፡ በአሁኑ መመሪያ እነኚህ ሁሉ አስተዳደራዊ ወጪዎች ሆነው ተመድበዋል፡፡ የተለያዩ አለምዓቀፍ መድረኮች ላይ ለመሳተፍ ቢያስፈልግ እዛ ቦታ ለሚቆይ ሰው የሚያስፈልጉት ወጪዎች ሁሉ አስተዳደራዊ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ የ30/70 መመሪያ በመርህ ደረጃ አግባብነት ያለው ቢሆንም እነዚህን ሁኔታዎች አለማገናዘቡ እና የወጪ ክፍፍሉ በቂ ምርምር ሳይደረግበት መካሄዱ ችግር ፈጥሯል፡፡ ማንኛውም ለልማት የተባለ ገንዘብ በአስተዳደራዊ ወጪነት መጥፋት እንደሌለበት የሚያጠያይቅ ባይሆንም ከዛ ባለፈ ግን ባለሞያዎችን እንዳይንቀሳቀሱ እና ከሙያ ጋር የተያያዙ የተለያዩ የቴክኒክ ዕቃዎች እንዳይኖራቸው ስናደርጋቸው እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡ ፡ ለምሳሌ፡- አንድ የደን ባለሞያ ጫካ ውስጥ እየዞረ ቅኝት ለማድረግ ኮምፓስ ያስፈልገዋል፡፡ ነገርግን በአዲሱ መመሪያ መሠረት መሳሪያውን ለመግዛት ዕቃው የድርጅቱ ንብረት ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ወጪ የሚደረገው ገንዘብ አስተዳደራዊ ወጪ ነው የሚሆነው፡፡ እንደ እኔ እምነት ግን ህብረተሠቡ ጋር የሚሄድ ነገር ብቻ ሳይሆን ስራውን በአግባቡ ለመስራት የሚያስፈልጉ ወጪዎችም ጭምር ከፕሮግራሙ ወይም ከፕሮጀክቱ ወጪ ጋር መካተት ይኖርባቸዋል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡” በተመሳሳይ መልኩ የመመሪያውን ተጽእኖ በተመለከተ አቶ ዮናስ የሚከተለውን ሀሳብ

ሰንዝረዋል፤ “የኛን ድርጅት በተናጠል ስንመለከተው የአድቮኬሲና የኮሙኒኬሽን ድርጅት ነው፡ ፡ ከዚህ በፊት እኛ እንደ ፕሮግራም ብለን የያዝናቸው ነገሮች በ30/70ው መመሪያ ሙሉ በሙሉ አስተዳደር ስር ገብተዋል፡ ፡ ለምሳሌ፡- ብዙ ስራዎች ‘አውትሶርስ' ተደርገው ይሠራሉ፡፡ አብዛኛውን ስራ በውጪ አማካሪዎች እናሰራለን፤ ስብሰባ እናካሂዳለን፤ ምርምሮች ይዘጋጃሉ፤ ይህ ሁሉ የሚሰራው እዚህ ባለው የሰው ሀይል ብቻ አይደለም፡፡ እንደ እኛ ላለ የአድቮኬሲ ድርጅት የማማከር ስራ መደበኛ ስራ ነው፡፡ እነኚህን የመሳሰሉና ሌሎችም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ስር የነበሩ ክንውኖች አሁን አስተዳደራዊ ወጪ ተብለዋል፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የሚደረጉ የስብሰባ ወጪዎች በሙሉ ለኛ የፕሮግራም ወጪዎች ነበሩ፡ ፡ አሁን ባለው አሠራር ግን ተሳታፊው ማህበረሰቡ ካልሆነ ወጪው አስተዳደራዊ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የደመወዝ ጉዳይ አለ፡፡ ለምሳሌ፡- አንዳንድ ጊዜ በአዲሱ መመሪያ የፕሮጀክት ሠዎች ደመወዝ ራሱ ወደ አስተዳደር የሚታሰብበት ሁኔታም አለ፡፡ በእኔ አስተያየት በመመሪያው ሥር ይኼ የፕሮግራም ሌላው ደግሞ የአስተዳደር ነው ተብሎ የተደረገው ክፍፍል በተጨባጭ በአድቮኬሲ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት አይደለም፡፡

የማህበሩ እቅድ የማህበሩ የስራ ኃላፊዎች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ አዲስ ከወጣው የህግ ማዕቀፍ ጋር በተጣጣመ መልኩ ማህበሩ የአሠራር ለውጦች እንዲያደርግ የግድ ይላል፡፡ በመሆኑም ማህበሩ በአዲስ መልኩ ስትራቴጂክ ፕላን ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡ ከዚሁ ጋር አንዳንድ ድርጅቱን የማጠናከር ስራዎች ለምሳሌ፡ - የአስተዳደር መመሪያዎችን፣ የፋይናንስ

መመሪያዎችን እና የመሣሰሉትን ነገሮች ሁሉ ለመቀየር እና ድርጅታዊ መዋቅሩን ለማስተካከል ዝግጅት እያካሄደ ነው፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን መጠናቸው ገዘፍ ያሉ በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ የፕሮግራም ቀረፃዎችን ለማካሄድ ታስቧል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በየቦታዎቹ ሄዶ ማጥናትና ዳሰሣዎችን ማድረግ ስለሚያስፈልግ በዚህ አቅጣጫ ሰፊ ስራ ለመስራት ታቅዷል፡፡ በተጨማሪም ዶክመንቶች በተለያዩ ድርጅቶች ፎርማቶች መሠረት ማዘጋጀት እና ፕሮፖዛሎችንም ለጋሾች በሚፈልጉት አይነት መቀረጽ ስላለባቸው ስራዎቹ ተጣጥመው በስፋት ይሰራሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ በአጠቃላይ የማህበሩን የወደፊት እቅድ በተመለከተ አቶ ኤፍሬም የሚከተለውን ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡ የሳቸውን ሀሳብ በቀጥታ በማቅረብ ጽሁፋችንን እንቋጫለን፤ “ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ተግባር ካላቸው ድርጅቶች ጋር በመሆን ከኤጀንሲው ጋር የጀመርነው ውይይት ውጤታማ ከሆነ በተከታዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሰፋ ያሉ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተን ብዙ አካባቢዎችን ለመድረስ የሚያስችል ስራ እንሰራለን፡ ፡ አሁን የያዝናቸው የአካባቢ ተሟጋችነት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች የሚያስከትሉትን ጉዳት የህዝቡን ድምጽ ሆነን ለዓለም የማሰማት ስራዎች ይቀጥላሉ፡ ፡ እኛ አሁንም አድቮኬሲን አልተውንም፤ አድቮኬሲ እንዳለ አስተዳደራዊ ወጪም እንኳን ቢሆን አንተወውም፡፡ በተጨማሪም ያንን ሊያጣጥሙ የሚችሉ የፕሮግራም ስራዎችን መንግሥት ያወጣቸውን ደንቦችና መመሪያዎች በሚቀበሏቸው መልኩ እየሠራን የተሟጋችነታችንን እና መድረኮችን የማዘጋጀት ሚናችንን እንቀጥላለን፡፡” ----------------------------------

| 19


ቅፅ1 ቁጥር 12 ህዳር 2005

RESURRECTION ORPHANS AND WIDOWS SERVICE REVEAL YOUR LOVE IN ACTION ORGANIZATIONAL OVERVIEW

Resurrection Orphans and Widows Service (ROWS) is a non–governmental, non- political and not-for profit organization established in Addis Ababa, Ethiopia in 2008 G.C. ROWS is aimed at particularly reaching children and widows in impoverished and disadvantaged communities throughout the cities of Ethiopia by providing services and performing activities free of charge.

MISSION STATEMENT

Releasing children from their economic, social, physical and spiritual poverty and enable them to become responsible and fulfilled adults.

SPECIFIC OBJECTIVES • Provide educational support to OVC on a home base sponsorship including provision of school materials, school fee, tutorial class fee, uniform, shoes and stationery. • Provide food supply for needy OVC each month. • Cover medical expenses of OVCs in the program. • Create income-generating activities for needy widows through skill training and provision of seed money. • Provide self-reliance and family planning awareness for families of the sponsored children.

HOW YOU CAN HELP

| 20

• ROWS Child Sponsorship Program (CSP) asks donors for a commitment of $30 a month for a minimum of one year. 100% of your pledge goes to your sponsor child. • ROWS Widows Program requests for a one time donation of $300 to cover provision of initial seed money for starting income generating activity for one trained widow. • Let people know about the needs of ROWS. Contact Address info@rowsinternational.org www.rowsinternational.org +251-911-518004, +251-911-821200, +251-11-8960231 For direct deposit, use the following details below; Bank of Abyssinia - Filwuha Branch Swift Code: ABYFETAA C/A 1538, Addis Ababa, Ethiopia


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.